የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ/ም
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙን የልህቀት ደረጃ በሚያሳድግና የሃገሪቱን ክብር በሚመጥን አግባብ እያሳየ የሚገኘው ፈጣን የለውጥ ግስጋሴ መላው ሠራዊታችንን የሚያኮራ እንደሆነ የመከላከያ ጀኔራል መኮንኖች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን በጎበኙበት እለት አረጋግጠዋል ።
የዩኒቨርሲቲውን ሁሉን አቀፍ የለውጥ ግስጋሴ ተዘዋውረው የተመለከቱት ጀኔራል መኮንኖቹ ከአካባቢያዊ የውበት ገፅታው ጀምሮ በትምህርት ፣ በምርምር ፣በልማት ስራዎች በጠንካራ ሪፎርም ታግዞ ያመጣው ተጨባጭ ለውጥ ለሌላውም በአራዓያ ሊወሰድ የሚገባ እንደሆነም የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ገልፀዋል ።
የተቋሙ ቀልጣፋ የለውጥ ሂደት የሚያመላክተው የአመራሩን በሳል የአመራር ሰጭነት ቁርጠኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ያሉት ጀኔራል መኮንኖቹ ዩኒቨርሲቲው ከባለድርሻዎች ጋር ያለው ስኬታማ ትስስርና ቅንጅት የለውጡ ማሳያ መሆኑንም በትኩረት ተገንዝበዋል ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የያዘውን ሁለንተናዊ ለውጥ አጠናክሮ በመቀጠል ወደ ፊት የሰራዊታችንን የልህቀት ደረጃ በተለያዩ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልፀዋል ።
ዘጋቢ በላይነህ ፈንቴ
📌telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenseUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን !