የስብዕና መታወክ የሚጀምረው ስብዕናችን እያደገ ሲመጣ ወይም አዕምሯችን በሚበስልበት በጉርምስና ዕድሜ ላይ መሆኑ ይነገራል፡፡
እንዲሁም የተለመደ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የስነ ልቦና ችግር መሆኑ ይጠቀሳል፡፡
የሰው ልጅ ማንነት በአስተሳሰብ እና በድርጊቶች ላይ ተጽእኖ በሚያሳድሩ ልዩ ባህሪያት የተሰራ እደሆነ ይነሳል፡፡
የስብዕና መታወክ ያለባቸው ሰዎች ለመሥራት እና ከሌሎች ጋር አወንታዊ ግንኙነት ለመመሥረት ሊከብዳቸው ይችላል፡፡
በአለማችን ላይ 7.8 በመቶ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎቸ የዚህ ችግር ሰለባ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የስብዕና መታወክ ምን ማለት ነው?
የተዛባ አመለካከት፣ የተዛባ ድርጊት፣ የተዛባ አስተሳሳብ እና ባህሪ አንድ ላይ ሲደመሩ የሚመጣ ነው፡፡ የተዛባ ስንል ደግሞ ቀን በቀን ባለው ህይወታችን ውስጥ ወጣ ያለ ባህሪያት ስናሳይ ነው፡፡
መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
- በቤተሰብ ይህ ችግር ካለ
- ያደግንበት አካባቢ
- ተፅዕኖ የመቋቋም አቅማችን ተጠቃሽ ናቸው።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- ተጣራጣሪ መሆን (ሰዎችን አለማመን)
- ሰዎችን ለመቅረብ አለመፈለግ
- ነገሮችን እንደ አዲስ ለመሞከር መፍራት
- አንዳንዴ ከሌላው ሰው የተሻልን ነን ብሎ ማሰብ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ነገር ግን ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እነዚህን ነገሮች ስለማያስተውሏቸው እንደዚህ አይነት የስነ ልቦና ችግር እንዳለባቸው ላይገነዘቡ ይችላሉ፡፡
የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
- የተጠራጣሪነት ስሜት ስላላቸው ከሰዎች ጋር ለመቀላቀል መቸገር
- ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ እንዲፈጠርባቸው ማድረግ
- ከማህበራዊ ህይወት መገለል ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
የስነ ልቦና ባለሙያን በማግኘት የስነ ልቦና ህክምና ማድረግ ዋነኛው ነው፡፡
በመጨረሻም ችግሩን ለመከላከል ልጆችን በምናሳድግበት ሰዓት በጥሩ መልኩ ማሳደግ የተሻለ ማንነት ይዘው እንዲወጡ ለማድረግ እንደሚረዳ እና ይህ የስነ ልቦና ችግር በቀላሉ ከተደረሰበት ወዲያው መቅረፍ የምንችለው ስለሆነ በጊዜ ባለሙያዎችን ማማከር ይገባል፡፡
አቶ ልዑል አብርሀም (የስነልቦና ባለሙያ)
@melkam_enaseb