ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል @ethiopialightoftheworld Channel on Telegram

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

@ethiopialightoftheworld


ይህ ቻናል የተለያዩ በዓለም ላይ የተከሰቱ ክስተቶችን ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ጋር የሚያነፃፅር ነው። ይህ የዋናው የራዕይ ዮሐንስ 20 ግሩፕ ቅርንጫፍ ቻናል ነው።

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል (Amharic)

የኢትዮጵያን ከዓለም አየር ብቻ ኮደናዎችን ከአየር አገልግሎት መልዕክት ጋር ቻናል ለመኖር ተጠቅሰው። በተጨማሪም የራዕይ ዮሐንስ 20 አመት ግን ባለማንሳት አልባ ከቆይ ከሌሎች ሊሰጥልን እርስዎ ነው። ይህ የዋናው የራዕይ ዮሐንስ 20 ግሩፕ ቅርንጫፍ ቻናል ነው። ይህ በአባይ በጣቂያው ዜና የተያዙ የያርፍ ቻናሎችን እና ተይዞ የሚታወቁ የቻናለችን ወሬዎችን አንተጋጠቡ።

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

02 Dec, 10:24


አሁን ምሽት 5:04 ከጎሮ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው መንገድ በቅርብ ርቀት የእሳት አደጋ ማጋጠሙን የደረሰኝ ጥቆማ ያመለክታል።ምንጮቼ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለውኛል።

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

01 Dec, 05:19


Newyork

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:52


የወንድማችን ገብረ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት።
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
21/03/2017 ዓ.ም

👉 እንግዲህ ከጠረጋው ቁጣ ማን ይተርፋል? ማንስ ወደትንሣኤው ዘመን ይሻገራል? ግልጽ ነው ደግሜ እላለሁ ለአውሬው ያልሰገደ ምልክቱንም ያልወሰደ ያላመለከ ተሻጋሪ ነው። ኃብትንም እውቀትንም ጉልበትንም ማምለክ ሌላው የአውሬው አምልኮትም እንደሆነ እንወቅ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:51


የእህታችን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
21/3/2017

👉 ከዚህ  ደብዳቤ  ጋር  በልዑል  ፊት  ከከበሩት  ዋና  ዋና  ሊቃነ  መላእክቶች  ---  ሊቀ  መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል፣ ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ገብርኤል፣  ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ሩፋኤል  ትእዛዙንና  ውሳኔውን  ለመፈጸም  በኃያል ሙላት ተነቃንቀዋል።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ተጻፈ በ7/5/2012 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:50


የእህታችን ምፅላለ መድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስ አበባ
21/3/2017

👉 ሰባቱም መላእክት የቁጣውን ፅዋ ሁሉ ሊያፈሱት በፍጥነት ወደ ምድራችን ገሰገሱ። እንግዲህ ወዴት መሸሸግ ይቻልሃል? የመከርነው የዘከርነው የጮህነው ከዚህ እቶን ላይ ወድቀህ ከነዘር ማንዘርህ እንዳትጠፋ ነበር፤ አልሆነም! እኔም ምናምንቴው በፊቱ የታመንሁ የሥላሴ ባሪያ ለ15 ዓመታት ጮኬ ለፍልፌ አቅሜን ሁሉ ጨረስኩ ዛሬ የምነግርህ የሥላሴ ብርቱ ትእዛዝ ሆኖብኝ እንጂ ዳግም ወደእናንተ መድረስ አልሞክረውም ነበር። ስለ አባቴ ፍቅር ስለአባታዊ ትእዛዙ ስል ስለእናቴ ድንግል ስል መርዶህን እነግርሃለሁ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:49


የወንድማችን ሰይፈ ሚካኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስ አበባ
21/3/2017

👉 ወገኖቼ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! አዎን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች! እንዲሁም ይህን መልእክትም ሆነ የቀደሙትን ሰባት መልእክታት ለመስማት ዕድሉ የገጠማችሁ፥ ይህን ታላቅ ምሥጢር የእግዚአብሔርን እውነት ለመገንዘብ የሚያስችል ልቡና ይስጣችሁ! መቼም እግዚአብሔር ልቡናችሁን ካላበራው የቀደመው እባብ ሐሰተኛው ነቢይ ዘንዶው ያላደነቆረው፣ ወደራሱም ያላካተተው የአዳም ዘር የለምና! ጥቂቶቹ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ የተመረጣችሁ የከበራችሁ ታላቁን መከራ የታገሳችሁ ልትፅናኑ ይገባችኋል። ዛሬ ቀናችሁ ሊሆን ነውና! ብርሃናችሁ ሊበራ ድካማችሁ ሊታይ ሸክማችሁ ሊራገፍ መድኃኔዓለም ሊክሳችሁ ነውና! አመስግኑ!

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 9 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:48


የወንድማችን ገብረ ሥላሴ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ናዝሬት
21/3/2017
ክፍል ፪

👉 በዚህም  መሰረት  ለወዳጆቻቸው በየግንባራቸው  ላይ  ምልክት  ተደርጓል  ፡፡  ይህንን  የሚያዩት  ለቁጣው  ጠረጋ  እሳት  ለብሰው  እሳት  ጎርሰው  ምድርን እያንቀጠቀጡ  የሚመጡት  ቀሳፊ  መላእክት  መቅሰፍትን  ያዘሉ  ፍርድና  ትእዛዝ  ፈፃሚዎች  ተግባር  ላይ  ሆነው  ያለ  ምሕረት ምልክት  አልባ  የሆኑትን  እንደተፈረደባቸው  እንደተወሰነባቸው  እንደታዘዘባቸው  የአፈፃፀም  እርምጃ  ሲያከናውኑ  ሲያዩ  ብቻ ነው  ፡፡  በጊዜውና  በሰአቱ  የታዘዙበትን  ሲፈፅሙ  ብትጮህ  ብትለምን  እንባህን  እንደጎርፍ  ብታፈስ  ደምም  ብታነባ  እሚሰማህ የለም  ቀሳፊዎቹ  የመጡት  የአምላካቸውን  ትእዛዝ  ለመፈፀም  ተግባራዊ  ለማድረግ  እንጂ  ሊማለዱ  ሊያማልዱ  አይደለም  ፡፡

👉 ከኢትዮጵያ  የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት በአብርሃሙ ሥላሴ ፈቃድ የወጣ                                                መልእክት አስር ገጽ 30 የተወሰደ
ተጻፈ 7/5/2015 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:47


የወንድማችን ገብረ ሥላሴ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ናዝሬት
21/3/2017
ክፍል ፩

👉 ጊዜ  የለም  አብቅቷል  መሽቶባችኋል።  አሁን  ከፊታችሁ  ሁሉም  ነገር  ተጭኖ  መጥቷል።  መግቢያ  የለም። መደበቂያ በፍጹም የለም አበቃ!!

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 47የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:46


ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

🥢 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ የትዕቢተኛዎችንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ትንቢተ ኢሳያስ 13፡11

በ 21/3/2017 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

30 Nov, 04:42


በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዘጠኝ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ‼️
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሐሙስ ዕለት ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎችን ከቤታቸው በመውሰድ መግደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች  ተናገሩ።
ግድያው የተፈጸመው ሐሙስ ኅዳር 19/ 2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6፡00 አካባቢ መሆኑን ቤተሰቦች ገልጸው፤ ታጣቂዎቹ ዘጠኝ ወንዶችን ከቤታቸው ከወሰዱ በኋላ ወንዝ አካባቢ እንደገደሏቸው ገልጸዋል።

ቤተሰቦች እንሚሉት ግድያው የተፈጸመው በአካባቢው በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ይፈጽማል ባሉት “በሸኔ ታጣቂዎች” መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳው ሶሌ ፈረንቀሳ በተባለ ቀበሌ ተፈጽሟል የተባለው ግድያ “ሃይማኖት ተኮር” እንደሆነ ነዋሪዎች እና ቤተሰቦች ገልጸዋል።

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

29 Nov, 09:30


#NewsAlert

በኦሮሚያ ክልል ፣ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ፣ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነና ከ60 ሔክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ የለማ ሸንኮራ አገዳ ሙሉ ለሙሉ በእሳት መውደሙን ዋዜማ ከፋብሪካው ሠራተኞች ሰምታለች።

ሸንኮራ አገዳው በሦስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የለማ መሆኑን የጠቀሱት ሰራተኞቹ፣ አደጋው የተከሰተው ትላንት ኅዳር 19/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሸንኮራ አገዳው በተጨማሪ ንብረትነቱ የስኳር ፋብሪካው የሆነ ዋጋው እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚገመት ማሽን በእሳቱ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጪ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ከስድስት ሰዓታት በላይ እንደፈጀና ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ማጥፋት መቻላቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሸንኮራ ልማቱ ላይ በተደጋጋሚ የእሳት ጥቃት ፈፅመው ያውቃሉ። የአሁኑ አደጋ መንስኤ እስካሁን በይፋ አልታወቀም። [ዋዜማ]

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

29 Nov, 08:07


https://vm.tiktok.com/ZMhwcga3b/

ራዕይ ዮሐንስ 20 የንፅፅር ቻናል

27 Nov, 12:23


ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር ላይ የተዘራ የደረሰ ሰብልን አወደመ

በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል።

አርሶ አደሮቹም በአካባቢው ባሕል መሰረት ሰብላቸውን በደቦ ለመሰብሰብ ነገ ዛሬ በሚሉበት ወቅት ድንገት የጣለው በረዶ ሰብላቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመባቸው ተናግረዋል።

አቶ ራራ ደሴ የተባሉ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አርሶ አደር በደረሰው ጉዳት በማዘንና በመደናገጥ በርካታ አርሶ አደሮች ለከፋ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

"ጉዳቱ ያልተጠበቀ ነው፤ እንኳን እኛ እንስሳቱ ራሱ የሚበሉት ድርቆሽ ሳር አልተረፈም" ሲሉ አርሶ አደሩ ማሬ ታረቀኝ ለአሚኮ ተናግረዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያው ጥላሁን ዓለም ለአሚኮ እንደገለጹት ከ600 በላይ አርሶ አደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል።