አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

@oneamhara2


======================

አዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
Telegram:
https://t.me/oneamhara2

Twitter:
One__amhara

Email: [email protected]

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

22 Oct, 16:54


በዘመቻ በሃይሉ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር በአገዛዙ ሰራዊቶና አመራሮች ላይ በወሰደው ድንገተኛ ደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና ጦር አዛዥ እና በናደው ክፍለጦር ዋና ጦር አዛዥ ቀኝ አዝማች ይታገስ በተመራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙ አሽከር የሆኑት የመርሃቤቴ ወረዳ የብልፅግና አመራሮች በባህርዳር ስብሰባ ሰንብተው እና በአገዛዙ ሰራዊት ታጅበው ከለሚ ወደ መርሃቤቴ አለም ከተማ ለመቀባበል እንዲሁም በዚህ ሳምንት ከአለም ከተማ ያገቷቸውን ባለሃብቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ወጣቶች  እና የነቁ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ሸዋሮቢት ለመውሰድ ጉዞ እያደረገ ባለበት ሁኔታ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር መቅደላ ብርጌድ ሶስተኛ ሻለቃ ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:20 ሰዓት ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ  በአናብስቶቹ የናደው ክፍለጦር አባላት ከጀማ ድልድዩ አቅራቢያ ልዩ ስሙ አጥበርበር በተባለ አካባቢ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘሩ ሲሆን  ጠላት የአማራን ህዝብ ለመፍጀት ሲጠቀምበት የነበረ አንድ ዙ23 ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸዉን ለንሥር ብሮድካስት ገልፀዋል።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ የወራሪው ብልፅግና ሰራዊት እስረኞቹን ተቀብሎ ወደ ለሚ እየወጣ ባለበት ሰአት ከ9:00 ጀምሮ እስከ 9:40 በቀጠለው ውጊያ በሮቃ መገንጠያ አካባቢ ላይ አይበገሬወቹ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር የራስ አበበ አራጋይ ብርጌድ አንድ ሻለቃ እና የናደው ክፍለጦር ተወርዋሪ ሰራዊት  በጠላት ላይ በወሰዱት ፈጣን ምት ሀለት ሲኖትረክ እና ሁለት ኤፍኤሳር የጭነት አይሱዙ ላይ የነበረ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ንሥር ሚዲያ ለማወቅ ችሏል።

በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በየመንገዱ ላይ ያገኘውን የአርሶ የደረሰ ሰብል ሲያቃጥልና በከባድ መሳሪያ አካባቢውን ሲያሸብር እንደዋለ ለንሥር የደረሰዉ መረጃ ያመላክታል።

                     
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር
ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

22 Oct, 15:03


🔥#የግፍ_ግድያ‼️

ጥቅምት 5/2/2017 ዓም ላስታ ላሊበላ አንድ የ12 ዓመት ልጃገረድ ወደ ወራሪው ካንፕ ተወስዳ በጅምላ
#ከተደፈረች በኋላ #አንገቷን_ቆርጠው ገድለው ጥለዋት መገኘቷን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።



#በከንቱ_ከመሞት_ከፋኖ_ጋር_እንሰለፍ‼️

#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

12/2/17 ዓ.ም

@hageremedianews

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

21 Oct, 17:12


የወሎና የጎንደር ጀብዱ

በወሎና በጎንደር ቀጠና በተካሄዱ ውጊያዎች ፋኖ በአገዛዙ ጦር ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ

በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ በወሎ በትላንትናው እለት ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት በተደረገ አውደ ውጊያ በባለ ሽርጡ ክ/ጦር ዋና አዛዥ እንድሪስ ጉደሌ እየተመራ
ጊራና ከተማ ፣ፋፍም፣ ጊዶ በር፣ ጉቤ ፣ ውረኔ በተባሉ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ፈፅሟል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ገልጿል።

በዚህ በጊራና በነበረው ውጊያ በሻለቃ ደምሌ እና በፋኖ ሰለሞን ሞላ እየተመራ የልጅ እያሱ ክ/ር ጦርም ተሳትፎ ማድረጉ ታውቋል፡፡

የብልጽግናን ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከተማውን ተቆጣጥረን በዚህ ሰዓት አሰሳ በማድረግ ላይ እንገኛለን ያለው ድርጅቱ በተጨማሪም ከሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ የአገዛዙ ቁልፍ ቦታዎች መሀል አምባ፣ሊብሶና ውርጌሳንም በመቆጣጠር እያስጨነቅነው እንገኛለን ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገዛዙ ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለማስገባት  በምድር ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታርን እንዲሁም በሠማይ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጉዞን ሢያደርግ መዋሉን የአማራ ፋኖ በጎንደር አሳውቋል።

በተመሣሣይ ከባሕር ዳር የተነሳውን ጦር ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር  የአገዛዙ ጦር በከባድ መሣሪያ ታግዞ ዘምቷል።

ሆኖም ድልን እሥትንፋሳቸው ያደረጉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት የአገዛዙን ጦር የተለያዬ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለውበታል።

በደፈጣ የታጨደው የአገዛዙ ጦር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ካለ በኋላ ራሱን አደራጅቶ ተመልሷል። ድንጋጤን መለያው ያደረገው የአቢይ ጦር በምድር ውጊያ እንደተሸነፈ ሢያረጋግጥ በሠማይ በሄሊኮፍተር ታግዞ ከእንደገና ውጊያን አድርጓል።

ነገር ግን አሸናፊነት ከአባቶቻቸው የወረሱት፣ ሥነ ልቦናቸው በዕውነት የጸናው፣ ትግላቸው ሕልውናን ማሥቀጠል እንደሆነ ያመኑት የአሥቻለው ደሤ ቀኝ እጆች፣ የውባንተ አባተ ልጆችና የናሁሰናይ ወንድሞች በአገዛዙ የጦር ጋጋታ አልተረበሹም።

የአማራ ፋኖ በአለም በር ላይ የልብ ትጥቅን በደምብ ታጥቆ በውሥን ጦር አገዛዙን ሢለበልብ ውሏል። አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በነበረው ውጊያ የአገዛዙ አመራሮችም ጭምር ሢደመሰሱ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በዚህ ሠዓት በአገዛዙ ቁሥለኞች ተሞልቷል። የአገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሪም እንደቆሰለና ታቦር ሆሥፒታል እንደገባ አረጋግጠናል ብሏል በአርበኛ ባዬ ቀናው የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

21 Oct, 16:19


ሰበር ዜና
፨፨፨፨፨፨

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የስናን አባ ጅሜ እና የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ ጠላት እንደ ቅጠል ሲረግፍ ውሏል።ገና በጠዋቱ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡ ገበያ ስንቅ ለማቀበል ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ የፋኖ አባላት በደፈጣ አስደንብረውት ይወጣሉ።

በዚህ የተደናበረው እና በፍራቻ የተዋጠው ፈርጣጭ የአብይ አህመድ ወንበዴ ቡድን እንደገና ሐይሉን አጠናክሮ ከደብረ ማርቆስ ባለ ጎማውን መድፍ፣ዙ23 እና ሞርታር ብሎም ድሽቃውን ጠምዶ ከደብረ ማርቆስ አስፍቶ ወደ ረቡ ገበያ ወጣ።

ረቡ ገበያ ላይ መሽጎ ስንቅ መቀበል አልችል ብሎ ራብ የሚያነጉደውና ህዝቡን እያስገደደ የእለት ጉርሱን የሚደፍነው የጠላት ኃይል ደግሞ ሞርታሩንና ድሽቃውን ጠምዶ ከከተማው ወጥቶ ስንቁን ለመቀበል ጉዞ ጀመረ።

ይህን ሁሉ ግሳንግስ የሚስበው በጠዎቱ አንድ ቲም የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ በተተኮሰበት ጥይት ተደናብሮ በልመታ ነው ፍራቻ ነው።ዳሩ ግን በነበልባሉ ሺ አለቃ ባለው ጊዜ ወንዴ የሚመራው የስናን አባ ጅሜ ብሮጌድ የፋኖ አባላት ሁለቱን ሻለቃ ግራና ቀኝ ደፈጣ አስይዞ ይጠብቀው ኖሯል።

ያልታሰበ ዱብዳ እንራታ ላይ ጠላት አለ ብሎ ሲጠብቅ የነበረ የአብይ ሽፍታ ቡድን ከረቡ ገበያ በቅርብ እርቀት ሁለቱ ስንቅ ተቀባይና አቀባይ ሳይገናኙ መንገድ ላይ ያላሰበው ዱብዳ ወረደበት።

የፋኖ_ጥይት እንደ ዶፍ_ዝናብ ይወርድበት ጀመር።የአብይ ፈርጣጭ ቡድን በየቀኑ ከተወሸቀበት ከተማ ወይም አስፓልት በወጣ ቁጥር ሬሳ እየጫነ መፈርጠጥ ልማዱ ነውና ዛሬም እንደ ትናንቱ ቁጥር ስፍር የሌለው ሬሳና ቁስለኛውን ሬሽን ጭኖበት በመጣው መኪና ጭኖ ተመልሷል።

ይህን ሁሉ ጀብዱ የሚፈፅሙት ሲጥሉ እንጅ ሲዋጉ ለአይን ጥቅሻ የማይታዩት የስናን አባ ጅሜ ብርጌድ የነበልባልና የፋሲካው ሻለቃ የፋኖ አባላት ናቸው።
ከጠዋቱ አራት ሰዓት የጀመረው የደፈጣ ውጊያ ወደ መደበኛ ውጊያ ተሸጋግሮ እስከ እኩለ ቀን ሰባት ሰዓት ድረስ ጠላትን ሲያደባዩት መዋላቸውን የብርጌዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መለሰ ለክፍለ ጦራችን ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ (ሸርብ) ገልጿል።ድል ቁርሱ የሆነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም በብርጌዶቹ የእለት ተእለት ተጋድሎ ታሪክ በአምዱ እያስመዘገበ ይገኛል።


  ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

21 Oct, 08:58


ደፈጣ

ጥቅምት 11/2017ዓም
     ሸበል በርንታ

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ሽፈርው ገርበው ብርጌድ በትላትነው እለት ጥቅምት 10/2017ዓም የጠላት ሀይል ከሸበል በርንታ ወደ እነማይ ወርዳ ባንጃ ሸርር ቀበሌ በጉዞ ላይ እያለ  በሸበል በርንታ ወርዳ ወርጎ ቀበሌ የጡጭ ጎጥ ላይ በደፈጣ ተመቶል።በዚህ የደፈጣ ውጊያ በጠላት ሀይል ላይ ከባድ ኪሳራ ገጥሞት ጠላት ወደ ነበርበት ቦታ ተመልሶል።

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

21 Oct, 08:57


ሰበር መረጃ
፨፨፨፨፨፨፨

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የጎንደር ከተማ ጃንተከል ብርጌድ በትናንትናው እለት ፈንጠር ላይ ባደረገው የደፈጣ ጥቃት የልዩ ሀይል አዛዥ ኮማንደር እያቸውና የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር እይልኝ ከስምንት የግል ጠባቂዎቻቸው ጋረ በተወሰደ እርምጃ እንደተደመሰሱ ታዉቋል።

  በዛሬው እለት አስክሬናቸው ከጎንደር በመነሳት ወደ ትውልድ አገራቸውና  ቤተሰቦቻቸው በአውሬው መንግስት የመከላከያ ልዩ ሀይልና ፖሊስ አባላት ሽኝት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም በደፈጣ ውጊያው ስድስት ቆስለው አራት ተማርከዋል።የጃንተከል ብርጌድ ዋና አዛዥ (አሞራው) እርምጃው በሌሎች አመራሮች ላይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ጠላትን ከገባበት ገብተው እንደሚቀጡት አስታውቀዋል።

©የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ

  ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

21 Oct, 08:37


መረጃ ጎንደር❗️

ጎንደር አዘዞ ተስፋ ከቆረጠው ሰሜን ምዕራብ ዕዝ አጠገብ የሚገኘው 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ  ትናንት ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ በተጠመደ ፈንጅ  ቁጥሩ ያልታወቀ ሚሊሻ፣ አድማብተና እንዲሁም ፖሊስ ሙትና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ።

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

19 Oct, 15:48


ሰበር መረጃ
፨፨፨፨፨፨፨

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት ከአዲስ ዘመንና ከእብናት ኃይሉን አግተልትሎ በአንቦ ሜዳና አካባቢው ወረራ ለመፈፀም በሌሊት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴ ቢያደርግም በጀግናው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ተመክቶ መመለሱን የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ  ገልጿል።

ከአዲስ ዘመን አቅጣጫ የተነሳው የጠላት ሀይል በተለያየ አቅጣጫ በማስፋት ከበባ ሊፈፅም  ቢሞክርም ብራ በተባለው አካባቢ ደፈጣ ይዞ የቆየው የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር የአንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ነበልባል ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ወደመጣበት አስፈርጥጦ ልኮታል ሲል ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለጣቢያችን ገልጿል።

የጠላት ሀይል ከላይ የጀት ሀይል በማንሳፈፍ በምድር ዲሽቃና ሞርተር አግተልትሎ ቢገባም በአናብስቶቹ የሊቦ ፋኖ ተመትቶ የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለ 251አክሎ ገልጿል።


  ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

18 Oct, 21:45


★የድል ዜና

ከላይ ድሮን ከታች ታንክና ዲሽቃ ይዞ ወደ ዉጊያ ያመራው የአብይ አህመድ ሰራዊት አስከሬኑን ታቅፎ ተመለሰ።

      (ወሲል የወንዶች ወኪል)
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በድሮን፣በታንክ፣በሞርተር እና ዲሽቃ በመታጀብ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ወሲል ቀበሌ በሚገኙ የፋኖ አባላት ላይ የተደራጀ ጥቃት ለመፈፀም ከቦታው የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል።

የጠላትን ሴራ አክሽፎ የመለሰው በዋሴ ተገነ የሚመራው የተስፋ ብርጌድ ሻለቃ አራት የፋኖ አባላት የጠላትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ በወታደራዊ ቋንቋ አገላለፅ ገዥ ቦታ ቀድሞ በመያዝ እስካፍንጫው ታጥቆ የመጣን የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ መልሶታል።

ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ አርሶአደሩ ሰብሉን እንዳይሰበስብ እንቅፋት እንሆናለን ሰብሉንም በከባድ መሳሪያ እናቃጥላለን በሚል ሰይጣናዊ ተልዕኮ አማራን ለማጥፋት የሚጋጋጠው ቡድን በተስፋገብረስላሴ  ብርጌድ የፋኖ አባላት እየተደመሰሰ ሲሆን ለበረኸት ወረዳ ማህበረሰብ የእናቶች አገልግሎት መዋል ያለባቸው አምቡላንሶች የጠላትን ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛ ማመላለሱን ቀጥለውበታል።

    ድል ለአማራ ህዝብ!
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

18 Oct, 14:59


ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

★የድል ዜና

ከላይ ድሮን ከታች ታንክና ዲሽቃ ይዞ ወደ ዉጊያ ያመራው የአብይ አህመድ ሰራዊት አስከሬኑን ታቅፎ ተመለሰ።

     
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በድሮን፣በታንክ፣በሞርተር እና ዲሽቃ በመታጀብ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ወሲል ቀበሌ በሚገኙ የፋኖ አባላት ላይ የተደራጀ ጥቃት ለመፈፀም ከቦታው የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል።

የጠላትን ሴራ አክሽፎ የመለሰው በዋሴ ተገነ የሚመራው የተስፋ ብርጌድ ሻለቃ አራት የፋኖ አባላት የጠላትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ በወታደራዊ ቋንቋ አገላለፅ ገዥ ቦታ ቀድሞ በመያዝ እስካፍንጫው ታጥቆ የመጣን የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ መልሶታል።

ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ አርሶአደሩ ሰብሉን እንዳይሰበስብ እንቅፋት እንሆናለን ሰብሉንም በከባድ መሳሪያ እናቃጥላለን በሚል ሰይጣናዊ ተልዕኮ አማራን ለማጥፋት የሚጋጋጠው ቡድን በተስፋገብረስላሴ  ብርጌድ የፋኖ አባላት እየተደመሰሰ ሲሆን ለበረኸት ወረዳ ማህበረሰብ የእናቶች አገልግሎት መዋል ያለባቸው አምቡላንሶች የጠላትን ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛ ማመላለሱን ቀጥለውበታል።

    ድል ለአማራ ህዝብ!
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
    

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

18 Oct, 13:24


በጦርነት ላይ ትንታኔ የሚሰራው አለም አቀፉ ተቋም “ፋኖ የሰለጠኑ ተዋጊዎች ያሉት ሃይል ነው” ሲል ገለጸ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አለም አቀፉ የጦርነት እንቅስቃሴዎችን አጥኚ ተቋም “Institute for the study of war” /ISW/ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በአማራ ፋኖ እና በልጽግናው አገዛዝ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በሚመለከት ትንታኔያዊ ሪፖርት አቅርቧል፡፡በሪፖርቱም የፋኖ ሃይሎች ከሃምሌ ወር ጀምሮ ባደረጉት አዲስ የማጥቃት ዘመቻ በርካታ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ገልጿል፡፡

በአለማችን ላይ የሚካሄዱ ጦርነቶችን እየተከታተለ በባለሞያዎች የሚያስተነትነው ይህ ተቋም የፋኖ ሃይሎች በተበታተነ ሁኔታ ያሉና የየራሳቸው አመራር ያላቸው ቢሆኑም ሁሉም በሚገባ የሰለጠኑና ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ናቸው ብሏል፡፡ከቀድሞ የክልል ልዩ ሃይልና የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ጭምር የተካተቱባቸው እንደሆኑ ያመለከተው ሪፖርቱ በክልሉ ህዝብም ድጋፍ እንዳላቸው አስረድቷል፡፡


እንደሪፖርቱ ከሆነ ከ2015 ሰኔ ወር ጀምሮ እስከ 2016 መጋቢት ወር ድረስ በየወሩ የፋኖ ሃይሎች በአማካኝ በወር 25 ጥቃቶችን ፈጽመዋል፡፡ይህ አሃዝ ባለፉት ጥቂት ወራት ግን በሶስት እጥፍ ማደጉን ገልጿል፡፡ በቻርት ፣ በካርታና በግራፍ ተደግፎ

የቀረበው ሪፖርቱ በርካታ ጉዳዮችን በስፋት ዳሷል፡፡በመሆኑምእስከዛሬ ፋኖን እና እንቅስቃሴውንበሚመለከት ከቀረቡ አለም አቀፍ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች የተሻለና የተብራራ እንዲሁም መረጃዎችን ያካተተ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ይህ ተቋም በአለማችን ላይ ያሉ ትላልቅ ጦርነቶችን በመተንተን እና የዳሰሳ ጥናት በመስራት የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የሚሰራቸውን ትንታኔዎች አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደምንጭነት ሲጠቅሱት ይሰማል፡፡

 ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

16 Oct, 06:06


የድሮን ጥቃት!

ዛሬ በጠዋቱ በረኸት ወረዳ 04 ቀበሌ ላይ የብልፅግና አገዛዝ ድሮን ተጠቅሞ የንፁሀን ቤት ላይ ጥቃት አድርሷል።

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

15 Oct, 18:28


5/2/17 ዓ.ም

🔥ወሎ ቤተ-አምሃራ የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው ተጋድሎ‼️

ጥቅምት 4 እና 5 ዞብል አምባ ክፍለጦር ታጠቅ ልዩ ዘመቻና ዲቢና ወርቄ ባለ ሽርጡ ብርጌድ ከሙጃ አቦሆይ ጋሪያና በቅሎ ማነቂያ በኩል የመጣዉን ጠላት ተኩለሽና አካባቢው ላይ እንዲገባ በማድረግ ከበባ ዉስጥ አስገብተው እየቀጠቀጡት ይገኛሉ:: ከወልድያ ዙሪያ ቃሊምና ሮቢት አካባቢ በአዋስ በኩል ዉጊያ የጀመረው ጠላት የወልድያ ዙሪያው ዉጊያ ተበላሽቶበት ግራ ተጋብቶ የሚገኝ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ዉጊያ የጀመረዉና በአቦሆይ ጋሪያና በበቅሎ ማነቂያ ወደ ተኩለሽ የወረደው ጠላት ከበባ ዉስጥ ይገኛል::

በዚህ ዉጊያ ዞብል አምባ ክፍለጦር ሰፊ ቀጠና ሸፍና የአምበሳዉን ድርሻ ወስዳ ተጋድሎ እያደረገች ያለች ሲሆን ዲቢና ወርቄ ባለሽርጡ ብርጌድ ታጠቅና ልዩ ዘመቻም የገባዉን ጠላት ከበባ ፈፅመዉ ተጨማሪ ስንቅና ጥትቅ እንዳይደርሰው አድርገዉ ዘግተዉ ይገኛሉ::

በሌላኛው ቀጠና ሃውጃኖ ክፍለጦር ከራያ ቆቦ በዋ ሚካኤል እስከ ራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ ድረስ ሰፊ ቀጠና በመሸፈን ተጋድሎ እያደረገች ትገኛለች:: ጮቢ በር ተራራ ላይ ያለው የጠላት ሃይል ከሃውጃኖ ክፍለጦር መካናይዝድ በኩል የሚወረወርበትን ሞርታር መቁዋቁዋም አቅቶት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው:: ከዚህ በተጨማሪም ሃውጃኖ ክፍለጦር በተኩለሽና በአቦሆይ ጋሪያ አካባቢ ተከቦ ያለው ጠላት ከራያ ቆቦ ከተማና ከራያ አላማጣ አካባቢ ተጨማሪ ሃይል እንዳይደርስለት ቀጠናዉን ዘግታ ትገኛለች::

በዚሁ በወሎ ቤተ-አምሃራ አማራ ሳይንት
ከ10 በላይ የጥምር ጦር አባላት ሲደመሰሱ ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛም ተጫነ!
ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ መቅደላ ወረዳ ውስጥ ኮሬብ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ የረንዛ የሚባል ስፍራ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ በወሎ አምሓራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ፋኖዎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ጉርቦ ለጉርቦ ሲተናነቁ የዋሉ ሲሆን በድምሩ ከ10 በላይ ጠላት ሲደመሰስ በውጊያው የቆሰሉትም ወደ ሆስፒታል ሲጋዙ ውለዋል::
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ በለጠ ምትክ በመራው በዛሬው ኦፕሬሽን ጠላት ላይ የከፋ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል::

አሳምነው ክፍለጦር የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማና አካባቢው ላይ ባለፉት ሶስት ቀናቶች ታላቅ ተጋድሎዎችን በማድረግ በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈች ሲሆን በክፍለጦሩ መካናይዝድ በኩል የሞርተር ጥቃት በመፈፀምም ወልድያ ከተማ መድፍ ማቃጠላቸዉና ማውደማቸው የሚታወቅ ነው::

በዚሁ በወሎ ቤተ-አምሃራ የአማራ ፋኖ በወሎ  እያደረገው ባለው ከፍተኛ ተጋድሎ አገዛዙ ሽንፈቱንና የቁልቁለት ጉዞዉን የተያያዘው ሲሆን የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትም በአውደ ዉጊያ እየደረሰበት ያለዉን ሽንፈት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ በመጨፍጨፍ እየተበቀለ ይገኛል:: ምንም እንኩዋን የኦነግ ብልፅግና ቡድን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ዘር ማጥፋት እየፈፀመበት ያለ ቢሆንም በሰሞኑ ዉጊያ ከወልድያ ስታዲየም በሚወነጨፍ መድፍ ቃሊምና አካባቢው ላይ የንፁሃንን ህይወት ቀጥፎዋል:: ቆቦ ከተማ ሆርማትና ጠዘጠዛ የሚወነጨፍ መድፍ በዋ ሚካኤል እና አካባቢው ላይ በተመሳሳይ የንፁሃን ህይወት ተቀጥፎዋል:: ባለፉት ጊዜያት በርካታ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ንፁሃኖች በአገዛዙ ጭፍጨፋ እንደተፈፀመባቸው የሚታወቅ ነው::


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

15 Oct, 16:09


ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም


#ደጋዳሞት !

# በደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ የድሮ ጥቃት ተፈፅሟል። የድሮን ጥቃቱ በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ የተፈፀመ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መውደሙን የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዮሀንስ ዓለማየሁ ተናግሯል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 6፡15 ላይ አገዛዙ  ደጋዳሞት ወረዳ  ፈረስቤት ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በዚህ ጥቃት በካባቢው የነበረ አንድ ህጻን የተጎዳ ሲሆን ወረዳ ጽህፈት ቤቱም ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በዚህ ሰዓትም ተጨማሪ ድሮን አሰሳ እያደረገች ነው፡፡

የአማራን ህዝብ ለማጥፋ* ት  እና  ወደ ኋላ ለማስቀረት የሚታትረው አገዛዙ፡ ተቋማትን እና የህዝብ መገልገያ ቁሳቁሶችን በድሮን እና ከባድ መሳሪያ እያወደመ ቀጥሏል፡፡  በመውደቅ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ  አገዛዝ  መሰል ዘግናኝ ጸረ_ህዝብ ጥቃት ይፈጽም እንጂ፡  ከመውደቅ ወይም ከመገርሰስ የሚታደገው አንዳች ሀይል አይኖርም!

ድል ለፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

15 Oct, 11:15


5/2/17 ዓ.ም


🔥#ኮሬብ_ወሎ‼️

የአማራፋኖ በወሎ አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ትናንት ጀምሮ እያደረገ ባለው እልህ አሥጨራሽ ትግል የብልጽግና ሚኒሻና አድማ ብተና
#በኮሬብ ከተማ የረንዛ በተባለ ቦታ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል  የሸህ ሁሴን ልጆች ግንባርን ለይተው በመምታት የሚታወቁት ጀግኖቹ የህዝብ ልጆች እየለበለቡት ይገኛሉ።
ይህ ብርጌድ በበለጠ ምትክ (ድሮን)እየተመራ አሥደማሚ ቀዶጥገና ሠርቶ የአገዛዙን አሽከር ከአፈር ደባልቆታል ከአሥር በላይ የተደመሠሠ ሲሆን ከዚሁቁጥር ያላነሠ ሆስፒታልእደገቡ አረጋግጠናል። በቀጣይ ጠላትን ሙሉ በሙሉ ከወረዳው ለማሥለቀቅ አሥፈላጊውን ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል ሲል መቅደላ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ለንስር አማራ ገልፀዎል‼️


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

15 Oct, 09:46


5/2/17 ዓ.ም


🔥#የቦንቦ_ጥቃት ‼️

አመራሩ በቦንብ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ
በደሴ ከተማ የፍርድቤት ሰብሳቢ የነበሩት ባንዳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል‼️

አቶ ሙሉጌታ ከበደ የደሴ ከተማ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኛ ከመኪናቸው ውስጥ በፈነዳ ቦሞብ ህይወታቸው ማለፉን የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዎል።
ዛሬ አመሻሽ (2:25) ከሹፌራቸው ጋር እየተጓዙ ባለበት ነው ቦምቡ ከመኪናው ውስጥ ፈንድቶ ህይወታቸው ያለፈው ሲሉ የፀጥታ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል።


#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

14 Oct, 19:47


🔥#የቦንብ_ጥቃት‼️

የደሴ ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በሆነው ሳሙኤል ሞላልኝ መኖሪያ ቤት አካባቢ 2 የቦንብ ጥቃት ተፈፅሟል💪
3/2/17 ዓ.ም



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

14 Oct, 14:36


4/2/17 ዓ.ም

#ወልድያ

የሰሜን ወሎ ዞን መናገሻ በሆነችው ወልድያ ከተማ ዙሪያ አፍሪኬር፣ ጥቁር ውሃ፣ ጦጣ ማደሪያ እና ጉቦ በተባሉ አከባቢዎች ትናንት ምሽት ከባድ ውጊያ ተካሂዷል።

በከተማዋ ዙሪያ በተለይ ከጎንደር በር ኬላ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ምሽቱን ሁለት ጊዜ ከባድ ውጊያ እንደተደረገበት የመረብ ሚዲያ የወሎ ቅርንጫፍ ማሰራጫ ጣቢያ ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።

ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ምሽት 01 ሰዓት እና ምሽት 04 ሰዓት ላይ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የተደረገ ሲሆን በዚህም በርካታ የመከላከያ ሰራዊትና የአድማ ብተና አባላት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል።

ጎንደር በር የሚገኘው የወልድያ ከተማ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሁለተኛ ጊዜ ትናንት ምሽት ጥቃት እንደተፈመበት የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

400 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበት በተሰራው በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየም ማዘዣ ጣቢያውን ያደረገው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በትናንት ምሽቱ ውጊያ እንዴት ሆኖ ወደ አፋር እንደሸሸ መረብ ሚዲያ ዘግቧል፡፡



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

13 Oct, 17:43


3/2/17 ዓ.ም


🔥#ቤተ_አማራ_ወልድያ አሁን | ምድር አንቀጥቅጥ ውጊያ‼️

በሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ፍንዳታ እየተሰማ ሲሆን ወደ ቃሊም አቅጣጫ ነው የመከላከያ ሜካናይዝድ አባላት መድፍ አዙረው የሚተኩሱት:: ከሼሁ ስታዲየም የሚተኮሰው መድፍ በቃሊም ግንባር የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለ ጦር የቆረጠውን የመከላከያ ሰራዊት ቅሪት ለማስወጣት ነው:: አሳምነው ክፍለ ጦር ግን  አልሰማም አላስወጣም ብሎ ይዞት ምድር ቀውጢ ሆናለች በተየያዘ
#ወልድያ ቆንጆዎች ገብተዎል።

የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ጽጌ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በዛሬው ዕለት የ801ኛ ኮር ሰራዊትን ጥሰው ወልዲያ ከተማ ገብተዋል:: ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ትንቅንቅ ላይ ናቸው:: የከባድ መሳሪያ ተኩስ አሁንም አልቆመም! መከላከያ በጨበጣ ሲያቅተው በርቀት መድፍ እየተኮሰ ሲሆን ቅንቡላው የሚያርፍበት አልታወቀም:: ንፁሀንን የመፍጀት ውሳኔ ነው:: የወልዲያ ህዝብ ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን!   ወልድያ አካባቢ ያላቹህ መረጃ በዉስጥ መስመር እንድታደርሱንም እንጠይቃለን።



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

አንድ አማራ ሰበር ዜናዎች

13 Oct, 13:20


3/2/17 ዓ.ም

🔥#ነጎድጓድ_ክፈለ_ጦር💪

የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ተከማችቶ በነበረ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል ላይ በምሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ‼️

ከሰሞኑ የአማራን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ በሚል ፉከራ ያለ የሌለ ሀይሉን አግተልትሎ  ወደ አማራ ክልል የገባው የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ቅጥረኛ አራዊት ሰራዊት ባሰበው ልክ ሳይሆን በግልባጩ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።
በትናንትናው አመሻ እለትም የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል  ደብረብርሃን ከተማን ለመጠበቅ በሚል ከደብረብርሃን ከ5ኪሎሜትር በላይ በማትርቀው ወሻውሽኝ ቀበሌ መሽጎ ህዝብን ለማሰቃየት በተቀመጠ ባንዳ አድማ ብተናና ቅጥረኛ ሚሊሻ  በአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ በካምፑ ላይ በተወሰደ በሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ብትንትኑ ወጥቶ ወደ መሀል ደብረብርሃን ፈርጥጧል።
በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽ ሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ ምኒልክ ሻለቃ መሪ ፊትአውሪሪ ደሳለኝ ሽፈራ በተመራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ሀይል ሰብዐዊ እና ቁሳዊ ሀብቱን አጥቶ ወደመጣበት የፈረጠጠ ሲሆን የወገን ሀይልም ግዳጁን በሰላም አጠናቆ ወደ መጣበት በሰላም ተመልሷል።
       "ድላችን በክንዳችን"

©የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል



#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪