ጥበብ እና ፍልስፍና @ethiosecret Channel on Telegram

ጥበብ እና ፍልስፍና

@ethiosecret


_ ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ወደ ጥበብ እና ፍልስፍና ሀገራዊ ቻናል በደህና መጣችሁ እያልኩኝ በዚህ ቻናል ውስጥ በይበልጥ
+ፍልስፍ
+ ሀገራዊ ጉዳዮች
+ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች
+ መንፈሳዊ ጉዳዮች
+ ታሪካዊ ጉዳዮች
+ እንዲሁም የተለያዩ አሳታፊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል ሲሆን እናንተም የቻናላችን ቤተሰብ በመሆን ለሌሎችም በማጋራት ኢትዮጵያዊነትን እናስፋፋ እላለሁ አመሰግናለሁ

ጥበብ እና ፍልስፍና (Amharic)

ጥበብ እና ፍልስፍና ለሁሉም ኢትዮጵያዊነት እና አስቲንግ ጉዳዮችን በቀላሉት እንነጋገሩ። ይህ ቻናል ከገላት ጋር የተለያዩ ፍልስፍናዎችን ሲጠቀሱ፣ ለሁሉም አዋጅ የተለያዩ ሀገራችንን እና እንዲሁም መንፈሳዊና ታሪካዊ ጉዳዮችን ለመረጃት እንችላለን። ethiosecret ቻናል ሊጠቀሙ ለብርቱካንና ብርሀን ያሉት ሰሞኑን ዌብ ለማበርካት እናስፋፋ ላይ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በተጨናነበት ጥበብ እና ፍልስፍና እናንተን መሆናቸውን እናስፈላለን።

ጥበብ እና ፍልስፍና

13 Nov, 18:21


አለምን አትርፈህ፤ነፍስህን አታጉድል።        
          ጥበብ ከብርና ከወርቅ ይልቃልና።

                       
             ፦Bob marley

ጥበብ እና ፍልስፍና

11 Nov, 17:47


#Movies🎥 🎥

ጥበብ እና ፍልስፍና

08 Nov, 18:21


What is love?

ጥበብ እና ፍልስፍና

07 Nov, 18:21


ብዙ ጊዜ በግሌ በዘመናችን ቅዱሳን የሉም እንዴ የሚል ጥያቄ ያጭርብኝ ነበር የበርሃው ምሥጢር የሚል  የእማሆይ እህተ ማርያምን  መጽሐፍ ሳነብ ግን እንደከዋክብት የበዙ ቅዱሳን ከባለ ስልጣን እስከ ሽፍታ ፣ በውሃ ውስጥ ከሚጸልዩ  እድሜ ዘመናቸውን ቆመ እስከሚጸልዩልን ቅዱሳን ታሪክ አንብቤ ውስጤ ረክቷል። የሀገራችን የትልቅነቷ የቅድስናዋ ምንጭ  እነዚህ ቅዱሳን ናቸው ...በየዓመቱ ከጳጉሜን 1 እስከ መስከረም 2 መላው ኢትዮጵያን መባረካቸውን ሳነብ ደሞ ሐሴት አደረኩ።
መጽሐፉ ሁለት ክፍል አለው። በመጀመሪያው ክፍል የዘመናችን የኢትዮጵያውያን የቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን ሲያወሳ በሁለተኛው ክፍል የዘመናችንን የምንኩስና ሥርአት ከገዳም እስከከተማ ያስዳስሰናል።

ይሄን መጽሐፍ ያነበበ በርግጠኝነት ብዙ ያተርፍበታል።

ጥበብ እና ፍልስፍና

03 Nov, 18:21


ሐ ሽ ማ ል

በማዕበል ፈጠነ

ጥበብ እና ፍልስፍና

29 Oct, 15:04


ጥበብ እና ፍልስፍና pinned «በፍም እሳት መቃመስ -በያዕቆብ ብርሀኑ ተፈጥሮ ህብሯ፣ መገለጫ መልኳ (manifestation) እልፍ ነው፡፡ ውሉን ካገኘኸው፣ ከውሻ ጩኸት፣ ከውኃ እናት እንቅስቃሴ ትማራለህ፡፡ ከቴሌስኮፕና ማይክሮስኮፕ በላይ ደመነፍስህን ታምነዋለህ፡፡ የተፈጥሮን ውል ካገኘኸው ስለሁሉም ነገር ለመማር ዓይኖችህን መጨፈን ብቻ እንደሚበቃህ ይገባሃል፡፡ ዝም ረቂቅ ጸሎት፣ ዝም በመንፈስ መገናኘት እንደሆነ ይገለጥልሃል፡፡…»

ጥበብ እና ፍልስፍና

26 Oct, 20:19


Don't let loneliness lead you back to toxic people.

ጥበብ እና ፍልስፍና

24 Oct, 18:21


Asral projection የእናንተ የመንፈስ፣ የንቃተ ህሊና ወይም የ"asral body" ተግባር ነው። በምትተኙበት ጊዜ ወይም በጥልቅ የሰመመን ሁኔታ ውስጥ አካላዊ ሰውነታችሁ ትቶ ይሄዳል። Asral plane & Asral projection  የተለያዩ የአለም ክፍሎች ይዳስሳል እና ከአካላዊ ገደብ የመውጣት ወደ አስራል ግዛቶች የማረፍ። አልፎ ተርፎም የተለያዩ planes ወይም የህልውና መጠኖች ውስጥ ዘልቀን የምንገባበት መሳርያ ነው።

እንደስያሜውም Asral projection & asral travel.. out-of-body experience ወይም projection of consciousness እና ሌሎች ከሥጋዊ አካል ውጭ የሚከሰትን ተግባራትን ለመግለጽ ምሁራን የሚገለገሉበት ቃላቶች ናቸው።

እራሳችሁን ከሰውነታችሁ ውጭ ተመልክታችሁ ታውቃላችሁ። እንደ "Lucid dream" ብሩህ ህልም ዓይነት ከሆነ ቦታ የመውደቅ ወይም የመብረር ስሜት ያላቸው ህልሞች አይታችሁ ታውቃላችሁ። በጣም እውነተኛ ህልሞች ስሜታችሁ እና ግልጽነታችሁ ከፍ ያሉበት ክስተቶች። ያኔ በasral projection ውስጥ አልፋችሁ ይሆናል።
----------------------------------------
አንዳንዶቹ በዚህ ችሎታ የተወለዱ ናቸው፤ ሌሎች ደግሞ የሞት አፋፍ ላይ እንደመድረስ ያለህ ክስተትን ተጠቅመው ይከፍቱታል። ሆኖም ማንም ሰው ይህንን ቴክኒክ በተመስጦ እና በተግባራዊ ድግግሞ በንቃት ማዳበር ይችላል።

ሁሉም የሰው ልጆች ለሊት ለሊት ያልማሉ እና ብዙ ሰዎች የተገደበ መንገድ ይኖራቸዋል። ሁሉም ሰው በእንቅልፍ ወቅት ከሰውነት ውጭ የሆኑ ልምዶችን እንደሚያሳልፍ ይገመታል። ነገር ግን የማስታወስ እድላቸው የደበዘዘ ነው ወይም የአዕምሮ የትውሰታ ማህደር ያጠራቀመውን የምስል ቆይታን እየገረበ ይገድበኋል!።

አዕምሮ በተፈጥሮው ነገሮችን የማመሳሰል ባህሪ አለበት። ለAsral projection ሙከራ መዘጋጀት ጥልቅ የሰውነት መዝናናትን ይጠይቃል። ይሄም እንቅልፍ ሊወስደን በማንቀላፋት ሂደት ውስጥ ሳለን እና ከእንቅልፋችን በነቃን ከ10-15 ደቂቃ መሐከል ላይ ያለ Alpha state ነው።

ስለዚህም በሙከራችን ውስጥ እንቅፋት የሚሆንብን አዕምሮአችን ነው፤ ከአካላችን ተለይተን እንዳንወጣ ታስረን እንድንቀር የሚያደርገን ያለፈው ጊዜ "ትውስታ" የመጪው ጊዜ "ምናባዊ" አሳብ ነው። በዚህ ሰንሰለት የተለያዩ ቅዠቶችን እየፈጠረ ሰምጠን እንድንቀር ይታገላል፤ ምክንያቱም አዕምሮ ለማያውቀው ነገር ጠላት ነው።


በእንደዚህ አይነት የቲዎሪ አሳብ በተግባራዊነት ስንቆም አዳዲስ ነገሮች ይፈጠራሉ። መንፈስ ከአካል የመገንጠሏ ተግባር ቁስልን እንደማከክ ያለ ስሜት እርካታው ገደብ የለሽ ነው።

ስጋችን ጥልቅ መዝናናት ውስጥ ሲገባ መንፈስ በመሐከል ተለይታ ትንሳፈፋለች፤ የራሳችን አካል ተኝቶ እንመለከተዋለን፤ የመጀመርያ ጊዜ Out-body ያለ ስጋ የተንሳፈፈው መንፈሳችንን አንድ እርምጃ ለማራመድ ምንአልባት ሰዓታት ይፈጃል፤ ከዚህ በፊት አይተናቸው የማናውቃቸው ጥቃቅን ነፍሳተና ቫይረሶችን እናስተውላለን፤ ሌሎች መንፈሶችንም በዙሪያችን እንዳሉ እንመለከታለን፤ የመጀመርያችን ሲሆን አጋንት የሚባሉ እርኩስ መንፈሶች እኛን ለማስደንገጥና ለማስፈራራት ጥርሳቸውን እያንቀጨቀጩ የመሳለቅ አባዜ አለባቸው፤ ራምፓ እዚህ ጋር "ፍርሃት ትልቁ break ነው!" ይለናል። ምክንያቱም ከማስፈራራት ውጭ የተለየ እርምጃ የላቸውም። ያን የፍርሃት መስመር ጥሰን Fearless መሆን ስንጀምር እነዚህ የአየር ላይ አጋንቶች የተለያዩ ምናብ ገጽታዎች ይሰጡናል። ልክ የምንወደውን ሰው በመምሰል አልያም በሞት የተለየን ሰው ተመስለው የተለያዩ የሚያምሩ ህልሞች ያቀብሉናል። በነዚህ አሳቦች ተታለን በሚሰጡት ቅዠቶች እየተዝናናን ከሆነ እስከመጨረሻው አጥምደው ያስቀሩናል!።

            ይቀጥላል......

@ethiosecret

ጥበብ እና ፍልስፍና

22 Oct, 18:21


..... የቀጠለ

ማንኛውም አሳሽ የሆነ ፈላጊነቱም ጥልቅ የመፈለግ ስሜት ያለው፤ ለማወቅ በሚደረግ ተነሳሽነት ህልሞችን የመረዳት መንገድ ላይ የሄደ፤ ወደ ግልፅ ህልም ውስጥ ይገባል እሱም self hypnosis ጋር የተስማማ እራስን ለመረዳት ጥሩ መሳሪያ ነው።

በምንሰራው ውስጥ ዋነኛው ይህ ነው በlucid dream  ወደ ብሩህ ህልም ማቃለል ይቻላል፤ በlucid dream ኢንዳክሽን ሂፕኖሲስን ለመጠቀም እና ህልም አላሚው በእውነታው ላይ ያለውን ክስተቶች አሰሳውን ለማከናወን በህልም ውስጥ መንቃት አለበት። አሁን ባለው ጥናት ስለ posthypnotic አንድ ሰው የተወሰነ ተግባር በመፈጸም ማለትም ውስን የሆነ አንድ ወጥ አሳብ ላይ ትኩረት ወስዶ እውነታውን ማረጋገጥ ይችላል። ይህ Hypnotic trans ካለቀ በኋላ Deep dreams of hypnosis ዘልቀን እንገባለን።

Deep dreams of hypnotized በመነሳት በህልም መነጠል ታላቅ ተጋድሎን ይጠይቃል። ይህም "ህልም" በምንለው ምስለ አሳብ ውስጥ ብዙ የመሄድ ምን አልባትም ዓመታትን የመቆየት ሂደት ነው። ስለዚህ በስፋት የሚያብራራው "inception theory" ነው።  Dreams of hypnosis በሌላ ሰው ተጽእኖ ስር መሆናችንን የሚጠቁም እንደሆነ እና ምናልባትም መቆጣጠርን መፍራትን ያመለክታል። ይሄም ስለሌላ ሰው ያለን አሳብ በታላቅ ኃይል ወይም ከኛነታችን በበለጠ በአንድ ሰው ህልውና አዕምሮአችን ከተገዛ የታሰበው ቦታ ለመድረስ እንቅፋት ይሆንብናል። ለዛም ስለሌሎች ያለንን አሳባዊ ይዘት ማጥራት አለብን። በሂፕኖሲስ ውስጥ ሆነን ህልም ከተመለከትን እና የሚያበረታቱ መላምቶችን እየተቀበልን ብሎም እየተረዳን ከሆነ ታላቅ አቅም ላይ የመድረስ ችሎታችንን እያሳደግን ነው።

ከራሳችን ጋር ነን መላ ህይወታችን ስለራሳችን ባወቅን መጠን ለራሳችን የምንሆነው ትልቅ ጥቅም ማስታወስና  ዘና ባለ መንገድ ተፈጥሮአዊ የደስታ ሁኔታችን በዙሪያችን ማጠንከር ነው። በግሌ ህልማችን ሁል ጊዜ ወደዚያ ቦታ ሊመራን እንደሚሞክር አምናለሁ። ያም በራሳችን ውስጣዊ ቤት የመዝለቅ በረከት ነው።

እውነት እውነት እላችኋለው ይህ ህልም ነው፤ እኔንና እናንተን መላው ዩኒቨርስ በእርሱ ውስጥ ይሽከረከራል፤ ይህ አዙሪት የምንረግጠው መሬት ላይ ነፍስ ዘርቶ ይንቀሳቀሳል፤ ህልም ያለፈውን ሁናቴ ጥርት ባለ መልኩ የምናስታውስበት እና የወደፊቱ ክስተቶችን የምንተነብይበት ብሎም የዛሬ ህይወታችንን በጥልቅ የምንረዳበት Great time travel ነው!።

   @ethiosecret