Harari Mass Media Agency @hararimassmediaagency Channel on Telegram

Harari Mass Media Agency

@hararimassmediaagency


Harari Mass Media Agency is a public media operating in Harar, Ethiopia.
ገፃችንን በመከተል ትኩስ ዜና እና መረጃዎችን ያገኛሉ።

Harari Mass Media Agency (Amharic)

Harari Mass Media Agency ከጃበለ ሂደት ያለው የመለስ ዜና ድርጅት ነው ፡፡ በኢትዮጵያ ሀረር አድማስ በሚል ስብከቶች ላይ በመተከል ያለው አካባቢ ነው ፡፡ ሰላም፣ የመረጃ እና የባህል ዜናዎችን በተግባር ያስተምሩ።

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 20:01


ቆይታ ከሀረሪ ክልል ም/ፕሬዝዳንት እና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ከወ/ሮ ሮዛ ኡመር ጋር በሀረሪ ቴለቭዥን ሐሙስ ከቀኑ 10፡45 ላይ ይጠብቁን‼️

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:43


ኢትዮጵያ በማዕድን ሃብት የበለጸገች ሀገር ናት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**
መንግስት ይህን ጸጋ ወደ ልማት ለመለወጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። የግሉ ሴክተር በማዕድን ዘርፍ ላይ እንዲሳተፍም ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:37


በሀረሪ ክልል በመጀመሪያው ሩብ አመት 707 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ ።
****
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት የክልሉን ገቢዎች ቢሮ የሩብ አመት አፈፃፀም ገምግመዋል ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት የክልሉን ገቢዎች ቢሮ የሩብ አመት አፈፃፀም ገምግመዋል ።

የቢሮው ማኔጅመንት አባላት እና ሀላፊዎች በክልሉ ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በወ/ሮ ፈቲያ ሳኒ ለተመራው ሉዑክ የስራ አፈፃፀም አቅርበዋል ።

በተለይም በገቢ ዘርፍ በተከናወነው የሪፎርም ስራዎች የተቋሙን ሁለተናዊ አቅም መገባቱን ጠቁመዋል ።

በተለይም በቢሮው ይታዩ የነበሩ የባለሙያዎች የክህሎት ማነስ፣ ለብልሹ አሰራር መጋለጥ ፣ ግብር ከፋዩን በተገቢው አለማስተናገድ ፣ የፋይሎች መጥፋትና የባለሙያ መዋቅር አለመኖር ግብር ከፋዩን ያንገላቱ የነበሩ አሰራሮችን በመቀየር አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል ። በዋናነትም ከ12ሺ በላይ የተገልጋይ ፋይሎችን ወደ ዲጂታል በመቀየር ከሰው ንክኪ የፀዳ ማድረግ ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ህብረተሰቡን ከእንግልት ያሳረፈ የሪፎርሙ ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።

ይህን ተከትሎ በበጀት አመቱ 1ኛ ሩብ አመት 779 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 91 በመቶ አፈፃፀም በማሳየት 707 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 62በመቶ እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል ።

የክልሉ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት በቀረበላቸው ሪፖርት ላይ ተንተርሰው ሀሳብና አስተያየታቸውን ሰተዋል ።

ቢሮው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሄደበት ርቀት ጥሩ ቢሆንም አሁንም የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ግብር ከፋዩ በዜጎች ቻርተር በወጣው የሰአት ደረጃ መሰረት መገልገል እንዳለበት ጠቁመዋል ። ከገንዘብ ማስልያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት ፣ በሆቴሎች ላይ የሚታዩ የደረሰኝ አለመቁረጥ ጉዳይን ቢሮው በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በክልሉ ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ሳኒ ባስቀመጡት አቅጣጫም የተገልጋይ ፋይሎችን ወደ ዲጂታል በመቀየር ከሰው ንክኪ የፀዳ ማድረግ እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለህብረተስቡ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንፃር የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል ።

እየታዩ ያሉ የሲስተም መቆራረጥ ችግርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ዘለቄታዊ እልባት መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ለግብር ከፋዩ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንደሚገባ አንስተው ተገልጋዩን በስርአትና በማያንገላታ መልኩ አገልግሎት መስጠት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ሳኒ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

ዘጋቢ :- ገዛኸኝ አራጌ
ቀን 11 / 03 / 17

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:36


የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ውጤታማ ለማድረግ ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የሀረር ክልል ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
*****
ኤጀንሲው በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ምልከታ አድርገዋል፡፡

በሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ሀላፊ ወይዘሮ ነቢላ መሀዲ የተመራ ልኡካን ቡድን በክልሉ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ውስጥ በሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅና በወሊፍ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ የስልጠና አሰጣጥ ሁኔታ ጎብኝተዋል፡፡

በተቋማት ላይ በየግዜው ክትትል መደረጉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን የኤጀንሲው ሀላፊ ወይዘሮ ነቢላ መሀዲ ገልፀዋል፡፡

የክትትል ስራው ያለውን ስኬት ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማሟላት ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ሀላፊዋ ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሌጆች ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት አስፈላጊው ግብዓት ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ወይዘሮ ነቢላ አስፈላጊውን መስፈርት የማያሟሉ ተቋማት ላይ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ተቋማቱ ከራሳቸው ትርፍ አስበልጠው ለሀገር ጉዳይና ትውልድ መቅረጽ ላይ ትኩረት ሰተው ሊሰሩ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ :- ሙህየዲን ሙክታር
11 / 03 / 17

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:35


19ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የሀረሪ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ከወጣት አደራጀቶች ጋር ፓናል ውይይት አካሄደ፡፡
******
በፓናል ውይይቱ በህገ መንግስቱና ፌደራሊዝም ላይ ያተኮሩ ፁሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

በመድረኩ በፌደራሊዝምና ህገ መንግስቱ ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ፡፡ የውይይት ፅሁፉን ያቀረቡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ የህግ ጉዳይ አማካሪ አቶ ሀምዲ መሀመድ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህገመንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው ለዚህም በየ ዓመቱ ይከበራል ።

በዚህም ሁሉም ዜጋ ለህገ መንግስቱ ተገዢ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የህገመንግስቱ አስፈላጊነት ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ፣ ዲሞክራሲና የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በሀገራዊ ጉዳይ አንድ አቋም ያለው ህዝብ ለመፍጠር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የህግ የበላይነት ከሌለ የመንግስት ቅቡልነት አይኖርም ያሉት አቶ ሀምዲ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው በህገመንግስቱ ዙሪያ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው በክልሉ የሚካሄዱ የሰላምና የልማት ስራዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት የሚሳተፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የማጠቃለያ ሀሳብ ያቀረቡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ የህግ ጉዳይ አማካሪ አቶ ሀምዲ መሀመድ ህገ መንግስታችን ሁሉም ህዝቦች በቋንቋቸው እንዲናገሩ ባህላቸው እንዲተዋወቅ እድል የሰጠ ስለሆነ እለቱን በደማቅ ሁኔታ እናከብራለን ብለዋል፡፡

ወጣቶች በአንድነት በተሰማሩበት ዘርፎች ስኬት ለማስመዝገብ ሊሰሩ ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ :- ቱራ አያና
11 / 03 / 17

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:34


ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካን መረቁ።
******

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡

ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

11 03 2017

Harari Mass Media Agency

20 Nov, 15:33


በ2025 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ 6ኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብልክን 2ለ1 አሸነፈች።
***

ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ ኬንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን ዋሊያዎቹ በበረከት ደስታና መሐመድኑር ናስር ግቦች 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ባትችልም የመጨረሻውን የምድብ የማጣርያ ጨዋታዋን በድል ማጠናቀቅ ችላለች።

10/3/2017

Harari Mass Media Agency

19 Nov, 16:26


በሀረሪ ክልል የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል
*****
በሐረሪ ክልል የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ከነገ ረቡዕ ህዳር 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ በክልሉ የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አስታወቀ።

በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መሰረት በማድረግ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ከነገ ረብዕ ህዳር 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ወር እንደሚቆይ ከክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት ለምዝገባ ተከታዮቹ ሰነዶችና ሁኔታዎች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል:-

1) በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሰነድ፣

2) የአከራይና ተከራይ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት፣ የጥብቅና ፍቃድ፣ የሠራተኞች ጡረታ መታወቂያ፣ የዩንቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ተማሪ የታደሰ መታወቂያ ወይም የሙያ ሥራ ፍቃድ ኦርጅናልና ኮፒ፣

3) የመኖርያ ቤት ኪራይ ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆን ሕጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናልና ኮፒ፣

4) አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ ማለትም:-

ሀ) የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም

ለ) ሰነድ አልባ ይዞታዎች መሆኑን ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ወይም

ሐ) በፍርድ አፈጻጸም የተሸጠ ንብረት ሰነድ ወይም

መ) የተከራየው ቤት በውርስ የተገኘ ሆኖ ስም ዝውውር ካልተፈፀመ የወራሽነት ማረጋገጫ

ኦርጂናልና ኮፒ ይዘው በአካል መቅረብ ያለባቸው መሆኑንና ምዝገባው በየወረዳው በሥራ ሰዓት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምዝገባ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያላከናወኑ አከራይ እና ተከራዮች በቅጣት ወደ ውል ሥርዓቱ እንዲገቡ የሚደረግ መሆኑ ተጠቁሟል።

10 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

19 Nov, 15:41


ለበጋ መስኖ ልማት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መግባቱም ተገልጿል
****
ሀረሪ ክልል ባሳለፍነው ነው አመት በበጋ መስኖ ልማት ትልቅ ውጤት የተመዘገበ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮም በበጋ መስኖ ልማት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን የሀረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ አስታውቋል ።

በክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ የግብርና ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ሬድዋን በበጋ መስኖ ውጤታማ ስራ ለመስራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መካሄዱን ተናግረዋል ።

በየደረጃው ላሉ የግብርና ባለሙያዎች አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱን በመጠቆም ለዚህም በቂ የግብአት አቅርቦት ለወረዳዎች መከፋፈሉን ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ ከባለፈው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው 4500 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ በበቂ ሁኔታ የጣለው ዝናብ ለበጋ መስኖ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ገልፀው አርሶ አደሩም ይህን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይባል ብለዋል፡፡

ከባለፈው አመት በተሻለ መልኩ ተሞክሮ በመውሰድ ያሉትን ክፍተቶች ለማሻሻል የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የወባ ስርጭት ባለበት አካባቢ በሙሉ ያለው መሬት ሊለማ ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ ለዚህም ትኩረት ተሰቶበት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ስራዎች ሕብረተሰቡን በምግብ ዋስትናው ማረጋገጥ እና የኢኮኖሚ አቅሙን ለማሳደግ ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረው ህብረተሰቡም በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና ምርቶች እንዲያኙ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለስራው ውጤታማነት ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ አመራሮች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ ፡- ዲኔ መሀመድ
10 / 03 / 17

Harari Mass Media Agency

12 Nov, 17:30


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ጋር በመሆን የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መስህቦችን ጎበኙ።
**
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜና ሌሎችን አመራሮች ጋር በመሆን የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎችና የቱሪዝም መስህቦችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በከተማው የተካሄዱና በመካሄድ ላይ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክን፣ የኑር ፕላዛ መዝናኛን እና የሀረር የጀጎል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ተመልክተዋል።

በከተማው የተካሄዱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ታሪካዊ ዕሴትን በጠበቀና ለነዋሪው የተሻለ ምቾት መስጠት በሚያስችል መልኩ መካሄዳቸውን እንደተመለከቱ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል።

በኮሪደር ልማቱ የሐረር ከተማ መንገዶች ለትራንስፖርት ፍሰት መሳለጥ ብሎም ለእግረኞች እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ስራዎቹን ጥራትና ፍጥነትን አስጠብቆ ከማጠናቀቅ አንፃር የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ገልፀዋል።

ዘጋቢ ዳኛቸው ደምሴ
03 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

12 Nov, 17:28


የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክን ጎበኙ።
******
የኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ከሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክን እና የጅብ ማብላት ትርኢትን ተመልክተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭና በክልሉ መንግስት ድጋፍ በተገነባው የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ ነው አመራሮቹ የጅብ ማብላት ትርኢቱን የተመለከቱት።

የሀረር ከተማ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከማሳደግ አንፃር ፓርኩ ለትርኢቱ የፈጠረው ምቹ ሁኔታም የሚደነቅ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር አክሲዎን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ዑማ (ኢ/ር) ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች በሀረር ከተማ በነገው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ1ኛ ሩብ ዓመት ጉባኤ ላይ ከፍተኛ የፌዴራል እና ክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ዳኛቸው ደምሴ
03 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

12 Nov, 14:11


ኢፌድሪ ትራንስፖርት ዋ ሎጀስቲክስ ወዚር ዶክተር አለሙ ስሜ ድሬዳዋ ኣሲማ ቦኡ
*******
ኢፌድሪ ትራንስፖርት ዋ ሎጀስቲክስ ወዚር ዶክተር አለሙ ስሜ ዋ ሚኒስትር ሚሕራ ጋርዞ ጢርሃን ተእሲሳች መስኡላች ድሬዳዋ ቦኡ።

ወዚርዞ ዶክተር አለሙ ስሜ ዋ ዪትጠረሁ ተእሲሳች መስኡላች ድሬደዋ ኤርፖርት ዚዲጁሳ ሐረሪ ሑስኒ ሳዪ ፓርቲ መ/ጋር መስኡል ጌስሲ ጌቱ ወዬሳ ዋ አላያች ኤመሮታችቤ ዱጉስ ተቄበሎት ኣሹሉዩ።

ዶክተር አለሙ ስሜ ዋ ዪትጠረሁ ተእሲሳች መስኡላች ድሬደዋ አሲማ ዚቦኦ ጊሽ ሞይ ባድ ሑቁፍ ደረጀቤ ዪትሜሐርዛል ትራንስፖርት ዋ ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር 1ታኝ ሩቡእ አመት ሶሰም ለአይቤ መትሳአድሌ ኢንታ።

ሚኒስቴር ሚሕራ ጋርዞ የሚሕራዛል አሐድታኝ ሩቡእ አመት ሶሰም ለአይቤ ላቂ ፌዴራል ዋ ሑስኒ ላቂ ኤመሮታች ዪትሳአዳሉ ባይቲቤ ዪቴቀባል።

03 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

12 Nov, 14:10


Ministeerri Geejjibaa fi Loojistikii Federaalaa Dr. Alamuu Simee magaalaa Dirree Dawaa seenan.
***
Ministeerri Ministeerri Geejjibaa fi Loojistikii Federaalaa Doktar Alamuu Simee fi hoggantoonni dhaabbilee itti Waamamaa waajjira ministeeraa Magaalaa Dirree dawaa seenaniiru.

Ministeerri Dooktar Alamuu Seemee fi qondaaltonni dhaabbilee buufata xiyyaaraa idile addunyaa Dirree Dawaa yeroo gahan itti gaafatamaan waajjira Paartii Badhaadhina Naannoo Hararii Obbo Geetuu Wayyeessaa fi hoggantoonni birootiin simannaa ho'aa taasifameera.

Dr. Alamu Simee fi hoggantoonni dhaabbilee itti waamamaa waajjira ministeerichaa Dirree Dawaa kan galan Yaa'ii Idilee kurmaana 1ffaa Ministeera Geejjibaa fi Loojistikii boru sadarkaa biyyaatti gaggeeffamu irratti hirmaachuuf akka tahe ibsameera.

yaa'ii Idilee kurmaana jalqabaa ministeerichi gaggeeffamu irratti hoggantoonni olaanoo federaalaa fi naannoo ni hirmaatu jedhamee eeggama.

03 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

12 Nov, 13:30


የኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ድሬደዋ ከተማ ገቡ
***
የኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜና የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ድሬዳዋ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳና ሌሎች አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ዶክተር አለሙ ስሜና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ድሬደዋ ከተማ የገቡት በነገው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ1ኛ ሩብ ዓመት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ሲል የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያካሂደው የአንደኛ ሩብ ዓመት ጉባኤ ላይ ከፍተኛ የፌዴራል እና ክልል ከፍተኛ አመራሮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

03 / 03 / 2017

Harari Mass Media Agency

05 Nov, 05:50


የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት በአለማች ሊያሳድረው ስለሚችል ተፅኖ።
**********

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለአሜሪካ ህዝብ ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም።

አሜሪካ «የአለም ልዕለ ሀያል» እንደመሆንዋ እና ተፅኖዋ ከግዛቷ የሚሻገር እንደመሆኑ የአለም ሀገራት የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት በጥብቅ ይከታተላሉ።

ይህ የአሜሪካ ምርጫ በብዙ ሺ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ባሉት ዩክሬን፣ አፍሪካ እንዲሁም መካከለኛ ምስራቅ የመሰሉ ሀገራት እጣፋንታን ሊወስን እደሚችል ይታመናል።

እየተጠበቀ የሚገኘው የአሜሪለካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማን ሊያሸንፍ ይችላል የሚለውን ውጤት ከወዲሁ ለመገመት አዳጋች ነው ተብሎለታል።

ሁለቱ ተፎካካሪ እጩ ፕሬዝዳንቶች አጣብቂኝ የሆነ ፊክክር እንደሚገጥማቸው ይገመታል፣ ፉክክሩም ብርቱ ሚያስብለው ተጨባጭ ምክንያቶች አሉት ።

ይህም የ78 አመቱ ቱጃሩ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም በመገኘታቸው ነው።

የቢቢሲ ጋዜጠኛው አንቶኒ ኡርቸር ዶናልድ ትራምፕ «ብረት ለበስ ፓለቲከኛ ናቸው » ይላቸዋል።

ምክንያቱም ሰውየው አበቃላቸው፣ የገዛ ባልደረቦቻቸው ክደዋጨዋል፤ ሊታሰሩ ነው ፣ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው ሲባሉ ከርመዋል።

ታዲያ አሁን አፈር ልሰው ፣ ለሁለተኛ እድል ነብስ ዘርተዋል ተነስተዋል ።

በተለይ በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያ በሆነ ታሪካዊ ክስተት ከዚህ በፊት ፕሬዝዳንት ሆኖ ተሸንፎ እንደገና ለሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንት ለመሆን ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የደፈረ ፕሬዝዳንት የለም ከዶናል ትራምፕ በስተቀረወ።

በሌላ በኩል ደግሞ የዲማክራቷ ካማላ ሀሪስ በታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን ብርቱ ተፎካካሪ ሆነው በመቅረባቸው ምርጫውን አጣብቂኝ ያረገዋል።

ሁለቱም እጩዎች ሰሞኑን በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የምረጡኝ ቅሰሳ ያካሄዱ የነበሩ ሲሆን በተለይ በአሜሪካ ወሳኝ ድምፅ ያላቸው ክልልሎች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ካሊፎሪኒያ፣ ፔንሲልቬኒያ፣ ፍሎሪዳ፣ ኒዎርክ እና ሚቺጋን ዋንኛ መፋለሚያ ሜዳ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት ላይ አሜሪካ በአዲሷ ፕሬዝዳንቷ ምን አይነት ፓሊሲ ልትተገብር ትችላለች፣ የፍልስጤማዊያ ሰቆቃስ መፍትሄ ያገኝ ይሆን?

አሜሪካ ከምርጫው ውጤት በሗላ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ምን አይነት ግንኙነት ይኖራት ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዋች የአሜሪካ ህዝብ በድምፁ ውሳኔ ሚሰጥባቸው ጉዳዬች እንደሆኑ የማያጠያይቅ ቢሆንም እያንዳንዳቸው ጉዳዩችን በዝርዝር መመልከቱ ጠቀሜታ ይኖረዋል፨

ወደ ሀጉራችን አፍሪካ በቅድሚያ ስንመለከት ምንም እንካነኳን እጩዋቹ አፍሪካን የተመለከተ እቅዳቸው እስካሁን በግልፅ ይፋ ባያደርጉም የቀድሞ የፓርቲው አመራሮቻቸው እና መንግስታቸው የተገበሯቸውን ፓሊሲዎች መቃኘቱ ወሳኝ ይሆናል፨
በሪፐብሊካኑ ትራምፕ የቀድሞ አስተዳደር ዘመን አሜሪካ አፍሪካን ያልጠቀሙ ውሳኔዎች ማስተላለፏ ይታወሳል ፣ ለአብነት ለመጥቀስ ያህል አሜሪካ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ (UNFPA) የምታደርገው ድጋፍ በመቋረጡ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ በ150 የአለም ታዳጊ ሀገራት የእናቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ መዳኒት አቅርቦት ላይ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖ እንደነበር መጥቀስ ይቻላል።

ይህ የትራምፕ አስተዳደር እንደገና ከምንም በላይ በ2020 አፍሪካን አንዲሁም ታዳጊ ሀገራትን ይጠቅማል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ከነበረው የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት በትራምፕ ውድቅ መደረጉ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን አለምን አጣብቂኝ ውስጥ የከተታት ታሪካዊ እና አሳፋሪ ውሳኔ እንደነበር ይታወሳል።

አፍሪካ እና አሜሪካ በኢኰኖሚ ያስተሳስር የነበፈው የአገዋ ስምምነት ቀጣይነት ማረጋገጥ እና ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ስለ ማካተቱም እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም።

ወደ መካከለኛው ምስራቅ ስንመለስ ደግሞ ሌላው ዲሞክራቶች እና ሪፐብሊካን ሚከፋፍለው ጉዳይ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ሲሆን እስካሁን ግልፅ ተደርጐ የተጠቀሰ ነገር ባይኖርም ትረምፕ ሚመረጡ ከሆነ የእስራኤል ፍልስጤም ጦርነት እንደሚያስቆሙ ከወዲሁ ቃል ገብተዋል፨

ፕራምፕ ይህን ማለታቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሙስሊም ኮሚኒቲዎች እና የአረብ አሜሪካዊያን ቀልብ ስበዋል ገና ከወዲሁም ድጋፍ እንዲሰጧቸው ምክንያት ሆንዋል።

ትፕራም የሚታወቁበት ሙስሊም- ጠል ፓሊሲያቸው አሁን በተገላቢጦሽ ሆነ እንዴ እንዲባልመ አስችሏል።

የካማላ ሀሪስ ፓርቲ የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት ለማስቆም ባለመቻሉ በበርካታ ሰላም ወዳድ አሜሪካዊያን እና ሙስሊሞ አሜሪካዊያን እንዲተች እና ድጋፍ እንዲያጣ አድርጐታል።

ለዚህ ዋንኛ ምክንያት ደግሞ እስራኤል በፍለስጤሞች በምትወስደው "የዘር ፍጅት" የዲሞክራቶች እጅ አለበት ይህ ማለት ደግሞ ዲሞክራቶችን መምረጥ ማለት "የዘር ማጥፋቱን" መደገፍ ማለት ነው የሚል እምነት እዲፈጠር ምክንያት ሆንዋል በበርካታ የአሜሪካ የፓለቲካ አንቂዎች ዘንድ።

በተመሳሳይ ሁኔታ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እየተባባሰ መምጣቱ የአረብ ሀገራት በተለይ በፍልስጤማዊያን ዘንድ የሰላም ተስፋ እንዲመናመን አድርጐታል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ምርጫ በሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ላይም ቀጥታ ተፅኖ የሚኖረው ይሆናል።

ለምሳሌ ትራምፕ እንዳሉት «ዳግም እኔ ምመረጥ ከሆነ የዩክሬንን ጦርነት አስቆማለሁኝ» ማለታቸው ለዩክሬናዊያም ድል የመጐናፀፍ ተስፋቸውን መና ያስቀረ ንግግር ሆኖባቸዋል።

ትራምፕ ከተመረጡ አሜሪካ ለዩክሬን ምታደርገው ወታደራዊ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታቋርጥ የምትችልበት እድል ሰፊ ነው።

አሊያም ሩሲያ በሀይል የያዘቻቸው ግዛቶች ጠቅልላ እንድትወስድ ትራምፕ ለሩሲያ ይፈቅዳሉ በእዚህም ሰላም ለማስፈን ሊሞክሩ ይችላሉ የሚለው ሀሳብ የበርካታ የፓለቲካ ልሂቃን ግምት ነው።

ይህ ባይሆን ደግሞ የአብዛኛው ዪክሬናዊያን ፅኑ ምኞት ነው ።

የዩክሬናዊያን ብርቱ ምኞት ዲሞክራቷ ካማላ ሀሪሲ ተመርጠው በአሜሪካ ድጋፍ ሩሲያን ሽንፈት ማቅመስ ነው።

ትራምፕ መጤ ጠል፣ በተለይ ከጐረቤታቸው ሜክሲኮ ጋር የገቡት ሰጣ ገባ፣ ከአረብ እና ከሙስሊም ሀገራት አንዲሁም አፍሪካን የተመለከቱ አላስፈላጊ ድንበር ያለፉ ንግግሮቻቸው በርካታ አፍሪካዊያንን ያስከፋ ጉዳዪ የአፍሪካ ህብረት ቅር ያሰኛ እንደነበር አይዘነጋም።

አሁንም ትራምፕ በእዚሁ አቋማቸው የሚገኙ ይሆን? ብረት ለበሱ ፓለቲከኛ ከስህታተቸው ተምረው መልካም ወዳጅነትስ ይፈጥሩ ይሆን።

የአፍሪካ እና የህንድ የዘር-ግንድ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ከማላ ሀሪስ ከአፍሪካ ሀገራት መልካም ወዳጅነት ለመፍጠር አስበውስ ይሆን?

በበሀር ጠንክር

ምንጮች: - አልጀዚራ እና ቢቢሲ

ትንታኔ ዜና

26 07 17

Harari Mass Media Agency

03 Nov, 14:57


በክልሉ የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት " በሚል ርዕስ አራተኛ ዙር ስልጠና ዝግጅትን በሚመለከት ውይይት ተካሄደ።
**
የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት " በሚል ርዕስ አራተኛ ዙር ስልጠና ዝግጅትን በሚመለከት ውይይት ተካሄደ።

ዛሬ በተካሄደው የፓርቲ አመራሮች ውይይት ላይ የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ ዕድገት በሚል ርዕስ ለሶስት ተከታታይ ዙሮች የተሰጠውን ስልጠና መነሻ በማድረግ በቀጣይ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና አባላት ለመስጠት የሚያስችል የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር አወያይቶዋል።

በዚህ ከጥቅምት 27/2017 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ለመስጠት የታቀደው የስልጠና መድረክ ላይ የሚሳተፉ አባላት የመለየት፣ በስልጠናው በአካሄድና በአጠቃላይ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት በመፍጠር የዕለቱን ውይይት አጠናቀዋል።

24/2/2017

Harari Mass Media Agency

03 Nov, 14:57


በሀረሪ ክልል ባለፉት ሦስት ወራት ከ707 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
*****
በሀረሪ ክልል ባለፉት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከ707 ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ272 ሚሊየን ብር ጭማሪ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

የሀረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር እንደተናገሩት በክልሉ በ2017 ዓ.ም በሦስት ወራት ውስጥ 707 ሚሊየን 413 ሺህ 881 ብር መሰብሰቡንና ከታቀደው እቅድ አንፃርም 91 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ 382,357,580.67 ብር ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ 207,894,499.85 ብር ፣ ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች 8,015,209.03 ብር እንዲሁም 109,146.561.64 ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ272 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው የጠቆሙት ወ/ሮ ኢክራም ይህም የ62.83 በመቶ እድገት ማሳየቱን ነው የተናገሩት፡፡

በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤን ለማጎልበት በትኩረት መሰራቱ፤ ከደረሰኝ አቆራረጥ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግና የህግ ማስከበር ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ በመሠራቱ እንዲሁም በተቋሙ የአገልጋይነት ስሜት እንዲጎለብት አሰራር ስርአቶችን በማሻሻልና የማዘመም ስራ መሰራቱ በገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማሳደር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የገቢ አሰባሰብ ሥራው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸሻለ ቢመጣም አሁንም የግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ህግ አለማክበር፣ ሸማቹ ለገዛው ዕቅ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህል አለመዳበር ለገቢ አሰባሰብ ስርአቱ ተግዳሮት መሆናቸውን አስረድተዋል።

በቀጣይም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በማጠናከር በበጀት አመቱ ለመሰብሰብ የታቀደው 3 ነጥብ 1 ቢልየን ብር ገቢ ለማሳካት ይሰራል ብለዋል ሲል የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

በክልሉ በአሁኑ ወቅት 32 ሺ ግብር ከፋዮች እንደሚገኙ ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

24 / 02 / 2017

Harari Mass Media Agency

03 Nov, 14:56


በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት በክልሉ የተቋቋመው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
****

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በሀረሪ ክልል ተቋቁሞ የነበረው የዳቦና ዱቄት ማምረቻ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ መልኩ እየሰራ መሆኑ ተገልፃል፡፡

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሊ አብደሩሂም ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 400 ኩንታል ዱቄት እና 300 ሺ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው መሆኑን ገልፀው ምርቱን ከሀረር አልፎ ወደ ጎረቤት ክልሎች ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፋብሪካው ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን የስራ እድል ተጠቃሚ ያደረጋቸው ወጣቶች ሰርተው ኑሮአቸውን የተሻለ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፋብሪካው ምርት ተረካቢዎች በበኩላቸው ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን ገልፀዋል።

ፋብሪካው ከዚህ በላይ የማምረት አቅሙን በማሳደግ ሕብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ በትኩረት የሚሰራ መሆኑ ተገልፃል፡፡

ዘጋቢ ፡- ሚሒየዲን ሙኽታር
24 02 17

Harari Mass Media Agency

03 Nov, 14:55


ለአቅመ ደካሞች የሚደረግ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሀረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
****
ጽሕፈት ቤቱ በ350 ሺህ ብር ያደሰውን የአቅመ ደካማ ቤት አስረክቧል፡፡

የሀረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት በ350 ሺ ብር ያደሰውን የአቅመ ደካማ ቤት ለባለቤቶቹ አስረክቧል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጽሕፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ የታደሰው ቤት ቀደም ሲል ጠባብ እና ለኑሮ ምቹ ያልነበረ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ ለኑሮ ምቹ በሆነ ሁኔታ የታደሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፅህፈት ቤቱ በቀጣይም ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ቤቱ የታደሰላቸው ቤተሰቦች በበኩላቸው ቀደም ሲል ቤቱ የፈረሰ የነበረ መሆኑን ገልፀው ክረምት በዝናብና በብርድ ሲሰቃዩ የነበረ መሆኑን ገልፀው ቤቱ ስለታደሰላቸው በጣም መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

መሰል ሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ ፡- አብዲ ኡስማን
24/02/17

Harari Mass Media Agency

03 Nov, 14:54


በክልሉ በ3 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የአርቴፊሺያል ሳር የእግር ኳስ ሜዳ 65 በመቶ መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ።
*****
ሜዳው ለአገልግሎት ክፍት ሲሆንም የወጣቱን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርገውም ተገልጿል

በሀረሪ ክልል በተለምዶ ራስ መኮንን ሜዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እየተሰራ የሚገኘው  የሰው ሰራሽ የሳር የማልበስ ስራ በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል ።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘከሪያ አብዱላዚዝ እንደገለፁት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ በክልሉ በ3 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የአርቴፊሺያል ሳር የእግር ኳስ ሜዳ  65 በመቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል ።

የእግር ኳስ ሜዳ ግንባታ በመገባደድ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ሀላፊው  ግንባታው ሲጠናቀቅም የወጣቱን ስፖርታዊ ማዘውተሪያ ስፍራ ፍላጎት ይበልጥ ተደራሽ ያደርገዋልም ብለዋል።

በተለይ ሸንኮር አካባቢ ለሚገኙና ብሎም በክልሉ ለሚገኙ ወጣቶች ስፖርታዊ አገልግሎት የሚሰጠው የእግርኳስ ሜዳው ከራስ መኮንን ትምህርት ቤት ባሻገር ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም በተወሰነላቸው የሰአት ኪራይ ክፍያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል ።

ከአጎራባች ክልሎች በተወሰደ ልምድ በከፍተኛ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የአርቴፊሺያል ሳር የእግር ኳስ ሜዳ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል ።

ዘጋቢ - ፍቃዱ በላይ
24/01/17

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 19:13


ከኢማም አህመድ ስታዲየም እስከ ግብርና ማዞሪያ የኮሪደር ልማት ስራ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ለትውልድ በሚሻገር መልኩ እየተሰራ ነው‼️

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:58


የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀሮማያ ዩንቨርስቲ አስታወቀ፡፡
*****
ዩንቨርስቲው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋና ኩርፋጨሌ ወረዳዎች በምርመር እያባዛ ያለውን የስንዴ እና ሌሎች ሰብሎችን የምርጥ ዘር ምርምር ስራን ጎብኝተዋል።

ሀሮማያ ዩንቨርስቲ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ እና ግራዋ ወረዳዎች የስንዴ እና ሌሎች የእህል ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

በዩንቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢሳቅ ዩሱፍ በወረዳዎቹ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስራዎቹን ለማጠናከር ና አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የግብርና ቴክኖሎጂን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ባለሙያዎች ና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የግረዋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጃፋር አብዶሽ ዩንቨርስቲው የአርሶአደሩን ኑሮ እንዲሻሻል እያደረገ ያለው ድጋፍ አበረታች ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ድጋፉ ምርትና ምርታማነት እንዲሻሻል እያገዘ መሆኑን ገልፀው ወረዳውም አስፈላጊውን ትብብር የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኩርፋ ጨሌና ግረዋ ወረዳዎች ከአካባቢው አየር ንብረት ጋር የሚጣጣሙ የስንዴ ፣ገብስ ፣ምስር፣ባቄላ፣ ጤፍ ና የተለያዩ የእህል ዘሮች እየለሙ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ :- ትግስት በለጠ
22 / 02 /17

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:58


ለባለ ሶስት እግር ኮድ 1 tvs ባጃጅ የተከለከለ መንገድን የተከፈተ መሆኑን የሐረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን አስተዉቋል።
***

በሐረር ከተማ ለትራፊክ ፍሰቱ ጤናማነት ሲባል አሰራሮች እሰኪስተካከሉ ድረስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስከ ራስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ድረስ ለኮድ አንድ tvs ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ የተከለከለ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ ተለዋጭ ሁኔታ እስኪገለፅ ድረስ ለግዜው የተከፈተ እና ማሽከርከር እንደሚቻል የሀረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን አስተወቀ።

ከሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን
22/2/2017

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:57


በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል።
***
በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ወቅታዊ የግብርና መረጃዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ በመኸር እርሻው 20 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በአነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች መልማቱን አስታውሰው፤ በሰፋፊ እርሻም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥም እስካሁን 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ ምርት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሰብል ስብሰባ መጀመሩን ጠቁመው፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ምርቱን እንዳያበላሽ በርብርብ መሰብሰብ እንዳለበት ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን መታቀዱን ጠቁመዋል።

እስካሁን በበጋ የመስኖ ሥራ 850 ሺህ ሄክታር የመሬት ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው፤ 505 ሺህ ሄክታር የሚሆነው በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የ24 ሚሊየን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ሂደት መጀመሩን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ለኢትዮጵያ አፈር ተስማሚ የሆኑ ማዳበሪያ ለማቅረብ ሂደቶች ተጀምረዋል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት 2 ሚሊየን ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ መታቀዱንም አመልክተዋል።

ከሌማት ትሩፋት አኳያም ዘንድሮ 150 ሚሊየን ጫጩቶችን ለማሠራጨት ዕቅድ ተይዞ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም እንዲሁ።

12 ቢሊየን ሊትር የወተት ምርት ለማግኘት መታቀዱንም አንስተዋል።

በዓመቱ 8 ቢሊየን የዶሮ እንቁላል፣ 218 ሺህ ቶን ሥጋ እንዲሁም 297 ሺህ ቶን የማር ምርት ለማምረት የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

22 02 17

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:55


ፓርቲያችን ብልፅግና ድህነትን በማቃለል ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል :- አቶ አብዱልሀኪም ኡመር
*****

ብልፅግና ፓርቲ ድህነትን በማቃለል ዘላቂ የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ተናገሩ

በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ንቅናቄ አካል የሆነው ቴክኒካል ኮሚቴ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል።

በምክክር መድረኩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ተናገሩ።

በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ምግብ ዋስትናችንን በማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም በግብርናና በግብርና ውጪ ባሉት የልማት ስራዎች በማስፋት ከተረጂነት ወደ ምርታማነትን ማሸጋገር እንደሚገባ አንስተዋል።

በተለይም በውሃ ፣ በጤና ፣ በግብርናና በስራ እድል ፈጠራ በሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ዜጋ ተኮር ስራዎችን ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ደህነትን በማቃለል በዘላቂነት የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ በማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ሽግግር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችና የሚተገበሩ እቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ መቀመጡን ከቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

22/2/2017

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:54


የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውጤታማ ተግባራትን ማስፋት እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን የ2017 በጀት አመት የስራ እንቅስቃሴን ምልከታ አድርገዋል።

የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኒ ረመዳን በዚሁ ወቅት እንዳብራሩት ባለስልጣኑ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን ለማሻሻል ባከናወናቸው ተግባራት በአይን የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል።

የክልሉ ነዋሪዎችን የውሃ ችግር ለማቃለል ከፍተኛ የምርት ማሻሻያ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ዲኒ ከውሃ አገሎግሎት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ከህዝብ ክንፍ ጋር በቅርበት እየተሰራ ስለመሆኑም አመልክተዋል።

ተቋሙ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን ለማዘመንም ደንበኞች የውሃ ክፍያቸውን ባሉበት ሆነው በባንኮችና በቴሌብር በኩል እንዲከፍሉ የሚያስችል የክፍያ አማራጭ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

የክልሉን የውሃ ምርት አቅርቦትን በማሻሻል የደንበኞች እርካታን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የገለፁት ስራ አስኪያጁ በተቋሙ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠርና አገልግሎትን ለማሳለጥ የሚያስችል ዘመናዊ ህንፃ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግረዋል።

በቀረበው ማብራሪያ ላይ በመንተራስ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በዚሁም ባለስልጣኑ የውሃ ምርትንና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን በማሻሻል የደንበኞችን እርካታን ለማሳደግ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የለውጥ ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ብለዋል።

በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በክልሉ በየወረዳው ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ የህዝብ መፀዳጃና የገላ መታጠቢያዎችን ስራ ማስጀመር እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈም የውሃ አገልግሎት ቆጣሪ ንባብ ትክክለኛነት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማስተካከል እንደሚገባም አመልክተዋል።

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኒ ረመዳን ከቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የተነሱትን ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በግብአትነት በመውሰድ ክፍተቶችን ለማሻሻልና ውጤታማ ተግባራትን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በክልሉ ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ሳኒ በባለስልጣኑ እየተካሄዱ ያሉ ተጨባጭ የማሻሻያ ስራዎችን በበጀት አመቱ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

የፍሳሽ አወጋገድ ስርአትን ማሻሻል እንደሚገባ የገለፁት ወ/ሮ ፈቲያ የውሃ ስርጭትና ፍትአዊ ተደራሽነትን ለማስፋት እየተካሄደ ያለውን ተግባር ማጎልበት እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘጋቢ ፦ሄኖክ ግርማ
22/02/17

Harari Mass Media Agency

01 Nov, 17:51


በሀረር ከተማ ከኢማም አህመድ ስታዲየም እስከ አራተኛ ግብርና ማዞሪያ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 70 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ።
***

በሀረሪ ክልል በኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወኑ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ 1.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና ከኢማም አህመድ ስታዲየም እስከ አራተኛ ግብርና ማዞሪያ የሚዘልቀው ፕሮጀክት አንዱ ነው።

ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 3 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ዋና ዋና የሚባሉ ስራዎቹ እንደተጠናቀቁና አሁን ላይ አጠቃላይ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ተቋራጭ ኢኮ ሴፍ ኢንጂነሪንግ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሐመድ ሙሄ ነግረውናል።

ምንም እንኳ እየጣለ ያለው ዝናብ በኮሪደር ልማት ስራዉ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም ቀን-ከሌት ርብርብ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ስራዉ በጥራት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

የፕሮጀክቱ ሙሉ ስራ ሲጠናቀቅ ለሀረር ከተማ ተጨማሪ መልካም ገፅታን በማላበስ ለኗሪዎቿ ምቹና ለጎብኚዎችም ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ውስጥ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በተጠቀሰው ስፍራ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት 15 ሜትር ስፋት ያለው የተሽከርካሪ መንገድ፣ በቀኝና በግራ በኩል 5ሜትር ተኩል ስፋት ያላቸው የእግረኛ መንገዶች፣ የአረንጓዴ ልማት ስፍራዎችና የመንገድ ዳር መብራቶችን አካቷል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 100 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ፣ የአካባቢው የስራ ባህል የቀየረና የሙያና ክህሎት ሽግግርም የተፈጠረበት ስለመሆኑ ኢንጂነር መሀመድ ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማት ስራው እውን እንዲሆን ህ/ሰቡ የግል ይዞታውንና የንግድ ቦታውን ጭምር በመልቀቅና በማፍረስ ለልማቱ ግንባር ቀደም አጋር በመሆን በቀናነት እያሳየ ላለው ትብብር ኢንጂነር መሀመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በፕሮጀክቱ የተቋማት ቅንጅት ጎልቶ የታየበትና የክልሉ መንግስት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገበት በጥሩ አፈፃፀም ላይ የሚገኝ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡ በኮሪደር ልማት ስራው እያሳየ ያለውን የሚደነቅ ትብብርና ድጋፍ በሌሎች የልማት ዘርፎችም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል።

ዘጋቢ፦ ሔኖክ ዘነበ
22/02/17