Tirita 97.6 FM Radio @tiritaradio Channel on Telegram

Tirita 97.6 FM Radio

@tiritaradio


ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ''

ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።

Tirita 97.6 FM Radio (Amharic)

ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ከልብዎ የቀረበ ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ፣ "Tirita 97.6 FM Radio" ከልብዎ የቀረበ። ይህ የአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የሚዲያ ነው። ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም በየንግድ ያግኙበታል፣ የትርታ ሚዲያ ትንተና ጋር ከፈለጉን በኋላ ሕዝብ ተመሳሳይ መዋሥያ እና ድምፅ እናስታዋለን። "Tirita 97.6 FM Radio" ትርታ ድምፅ ቆይታችን፣ ለማወቅ እና ስለመገኘት እናመሰግናለን። በጣም ከዚህ በኋላ በምን እርዳታ እና ችግሮች እንደማያከናውነው፣ ለማግኘት መልኩን እናጠብቅማለን። በትክክለኛው ምሳሌ ለመከታተል ከሚጠበቀው ይመልከቱ።

Tirita 97.6 FM Radio

19 Nov, 18:30


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን አሸነፉ!
***
በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ኬንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን÷ ዋሊያዎቹ በበረከት ደስታና መሐመድኑር ናስር  ግቦች 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

19 Nov, 10:24


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
***

የአዲስ አበባ
ከተማ ምክር ቤት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን ተሿሚዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።

በዚህም መሰረት:-

1. አቶ ወንድሙ ሴታ - በም/ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ

2. አቶ ተንኩዌይ ጆክ ሮም - የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኃላፊ

3. አቶ ይመር ከበደ ይማም - የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር

4. አቶ ግዛቸው አይካ - በአዲስ አበባ ምክርቤት የመሰረተ ልማትና መዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

የቦታ ለውጥ ያደረጉ

1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ

2. አቶ ቢንያም ምክሩ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

3. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ በማፅደቅ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማጠናቀቁን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

18 Nov, 13:54


አየር መንገዱ የዓለም አራት ኮኮብ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አገኘ
*
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ ፓሴንጀር ቾይስ አዋርድ 2025 (APEX Passenger Choice Awards 2025) የዓለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አገኘ።

ይህ የዓለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች በረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽኑ ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ  ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እውቅናውን አስመልክተው “ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የአገልግሎት ደረጃዎችን ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው። ጥረታችን እውቅና በማግኘቱ በጣም ደስተኞች ነን፣ ይህም ለበለጠ ስኬት እንድንጥር ያነሳሳናል” ብለዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

15 Nov, 18:03


የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል
***
በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

14 Nov, 12:26


ከአንድ ሺ በላይ ጥንዶች አንድ ላይ ይሞሸራሉ!
***
በዘንድሮ የ"የሺ ጋብቻ" መርሀ ግብር ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 250 ተጋቢዎችን ጨምሮ ከአንድ ሺ በላይ ጥንዶች ይሞሸራሉ ተብሏል።

"ቤተሰብን መመስረት ሀገርን መገንባት ነዉ" በሚል መርህ በ2005 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹን ተጋቢዎች የዳረዉ ያሜንት ኃ/የተ/የግል ማህበር፣ ሶስተኛዉን ዙር የብዙዎች ጋብቻ መድረክን በያዝነዉ ዓመት እንደሚከዉን ዛሬ በሀርመኒ ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታዉቋል።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ በሚካሄደዉ የየሺ ጋብቻ መርሀ ግብር ላይም፤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች 250 ጥንዶችን ጨምሮ በኢትዮጲያ ካሉት ተጋቢዎች ጋር በድምሩ 1ሺህ 250 ጥንዶች ይዳራሉ ተብሏል።

በሚኒሊየም አዳራሽ በሚካሄደዉ የዘንድሮዉ የየሺ ጋብቻ መርሀ ግብር ላይም 2017 ኪ.ግ የሚመዝን ድፎ ዳቦ፣12 ሺህ የሚደርሱ የቡና ሲኒዎች ያሉት የቡና እንጠጣ ፕሮግራምን እንደሚኖርም ተመላክቷል።

(በትባረክ ኢሳያስ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

13 Nov, 16:53


ከነገ ጀምሮ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ - ብሔራዊ ባንክ

****

ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለአካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።

የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት፣ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።

በወቅቱ አሰራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ብለዋል።

ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

12 Nov, 15:14


ልቀት ኮሌጅ ነፃ የትምህርት እድል ሰጠ
***
ልቀት የኪነጥበብ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የተመሰረተበትን ሰባተኛ  ዓመት ምክንያት በማድረግ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለ200 ተማሪዎች የአንድ ሴሚስተር  ከወርሃዊ ክፍያ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ኮሌጁ ህዳር 2 ቀን 2010 ዓ.ም በአራት ወጣት ባለሞያዎች ተመስርቶ በሀገሪቱ ትምህርትን በከፍተኛ ጥራት እና ልዩነት እያስተማረ ቆይቷል።

ኮሌጁ በልዩነት በሚታወቅበት የፊልም ትምህርትን በአዲስ አበባ በብቸኝነት በዲፕሎማ ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ በግል ኮሌጆች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የፊልም ጥበብ ትምህርትን በመጀመሪያ ዲግሪ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ልቀት ኮሌጅ በየዓመቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በከፍተኛ ቅናሽ በማስተማር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም የተመሰረተበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ  የመጀመሪያውን ሴሚስተር ወርሃዊ ክፍያ በነጻ  የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ነፃ የትምህርት እድል የተሰጠባቸውም የትምህርት መስኮች:-ቪዲዮ ካሜራና ኤዲቲንግ፣
አካውንቲንግ፣ ማርኬቲንግ፣
የሰው ኃብት አስተዳደር እና
የቴአትር ጥበባት ሲሆኑ ምዝገባ ከህዳር 2 - 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን የተቋሙ ዲን መሉጌታ ሙሃመድ ገልፀዋል።
ተመዝጋቢዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ዋናውን እና ኮፒ ፣ በተጨማሪም ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው በአካል ቀርበው መመዝገብ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
ዕድሉ መጠቀም የሚፈልግ ሁሉ  አራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚገኘው የኮሌጁ ቢሮ በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ በ09 84 71 71 44/09 40 08 99 99 መደወል እንደሚቻልም አሳውቋል

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

11 Nov, 09:08


የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ ወጣ
***
በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ሲኾን፣ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ መውጣቱም ተገልጿል።

ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡

ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል የሚደረግ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል መባሉን ትርታ ከአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሰምቷል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

Tirita 97.6 FM Radio

09 Nov, 16:11


የራይድ መንደር ግንባታ ሊጀመር ነው!
***
በሜትር ታክሲ አገልግሎት ፈር ቀዳጅ የሆነው የሀይብሪድ ዲዛይንስ ምልክት ራይድ እና ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ከኦቪድ ሪል ስቴት በገቡት ውል መሰረት የራይድ መንደር ግንባታ ሊጀመር ነው።

በዛሬው እለትም የራይድ ዘመናዊ መንደር በሚገነባበት በገላን ጉራ አካባቢ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

ራይድ ትራንስፖርት ለአሽከርካሪዎች፣ ለደንበኞቹ፣ ለሰዋሰው መልቲሚዲያ እና በስሩ ለሚገኙ ድርጅቶች ሰራተኞች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የያዘው ፕሮጀክት ወሳኝ ምዕራፍ የተጀመረበት መሆኑ ተገልጿል።

ራይድ አምስት ሺ ቤቶችን ከስድስት ወር እስከ አንድ አመት ባለው ግዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ማቀዱን የሃይብሪድ ዲዛይንስ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳምራዊት ፍቅሩ አስታውቀዋል።

በዛሬው መርሀ ግበር ላይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ አመራሮች ጨምሮ፤ ከራይድ ትራንስፖርት፣ ከሰዋሰው መልቲሚዲያ እና ከኦቪድ ሪል እስቴት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ200 በላይ የራይድ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች እና የስራ ባልደረቦች ተገኝተዋል።

(በአህመዲን ሸረፋ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ