HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው @hamernoah Channel on Telegram

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

@hamernoah


እግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ ( ፩ ተሰሎ ፭÷ ፳፭ ) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ትክክለኛ አድራሻዎቼ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
ቴሌግራም 👉 -https://t.me/hamernoah
My -email ☞[email protected]
መካነ ድር፡https:hamernoah.wordpress.comሁላችሁም ተሳታፊ ሁኑ

HamerNoah (Amharic)

ሔረኖኤስና ሾሩእሞም የሕዮትንና ምክርታችንን ለሕዝበ ክርስቲያቸው በግብራታቸው እና ትምህርታቸው የሚያግዙት ቴሌ ግራሜ ነው። እናቴሌ እንዲሁም በሌሊቴንቶሰችና የሴቲም ፊልምን የፀሓይ መረጃዎች መነሻ ብቻ እና ሃቃታችን ይደርገናል። የእግዚአበሔር ቃል፣ ምንጭ፣ ቅዱስ መላእክት እና መድኃኒቶች በሚገኙ የሕዝበ ፅሁፎች ላይ ለክርስቲያቸው መሸሸጊዎችን እና መስለዎችን አገኘሁበት። ስለእኛ ስንጸልይ በሌሊቴንቶሰች ለማወቅ የዚህ ቴሌ እና ስለ ክርስቲያቸው መልስ ይምረጡና። በበለስተ መስቀለ እና እኩልነታ ፕረሚዝ ለማክሰኞ ቅድመ ድንግል ታምሩና እኛ ከሰክሣሪ እስከ ግልሙ ዘመን ላይ ያረጋግጡን።

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

24 Nov, 11:21


https://hamernoah.wordpress.com/2024/11/24/%e1%88%b0%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%88%98%e1%8c%a3%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88/
"ሰንበት ትምህርት ቤትን ከመጣንበት መንገድ ይልቅ በተሻለ መንገድ ልናደራጀውና ልንጠቀምበት ይገባል በማለት መመሪያ አስተላለፉ" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

23 Nov, 19:02


የጾመ ነቢያት መግቢያ እና መከራከሪያ ነጥቦች ከኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ጋር

ጾመ ነቢያት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲሆን ከልደት አስቀድሞ  በ3ቱ ወንጌላውያን 44 በዘመነ ዮሐንስ 43 ቀናት የሚጾም ነው፡፡
ይህ ጾም በተለያየ ስያሜዎች ይጠራል፡፡
1.ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡
ነቢያት በየዘመኑ እየተነሡ 40 መዓልት 40 ሌሊት ጾመዋል፡፡ ለአብነት ያህል ለማንሣት ሙሴ 40 መዓልት 40 ሌሊት ጾሞ የኦሪትን ሕግ ተቀብሏል፡፡ ኩፋ 1፡1-6  ኤልያስ እንዲሁ ጾሞ ወደ ሰማያት ተነጥቋል፡፡ 1ነገ 19፡1-21 ዕዝራም እንዲሁ ጾሞ በምርኮ ጠፍተው የነበሩ የነቢያት መጻሕፍት ተገልጠውለት ጽፏቸዋል፡፡ ወዘተ
318 ሊቃውንት አባቶቻችን ትንሣኤን ጾመ ኢየሱስን ጾመን እንደምናከብረው በዚህ ወቅት የጌታችንን ልደት ለማክበር ልደቱንና አዳኝነቱን ሲሹ የፍየል ሌጦ ለብሰው በየተራራውና በየፍርኩታው የዞሩለት፣ ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት፣ ሱባዔ የቆጠሩለት ነቢያትን እናስታውሳቸው ዘንድ ሠርተውልናልና፡፡
2. ጾመ ማርያም ይባላል፡፡
እመቤታችን ሰማይና ምድርን የፈጠረ ጌታን ስወልድ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ? ብላ ጾማዋለችና፡፡
3. ጾመ ሐዋርያት ይባላል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ትንሣኤን ጾመ ኢየሱስን ጾመን እናከብራለን፤ ልደትን ስናከብር ምን ሠርተን እናከብራለን? ብለው ጾመውታልና፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
ከዚህም ሌላ የገና ጾም፣ ጾመ ልደት እየተባለ ሊጠራ ይችላል፡፡

የጾሙ መግቢያ
የጾሙ መግቢያ ሁልጊዜ (በአራቱም ወንጌላውያን) ኅዳር 15 ቀን ይገባል፡፡ ይህን አስመልክቶ የሕጉ መጽሐፍ  "ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ኅዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት" መጀመሪያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካውም የልደት በዓል ነው ይላል (አን 15) እኩሌታ የሚለውን ይዘው የኅዳር እኩሌታ 16 ነው የሚሉ አሉ፡፡ ለዚህ ምላሽ የሚሆነን!
1.15+15=30 ይሆናል እንጅ 15+16=30 አይሆንም፡፡
2.ስንክሳሩ ወበዛቲ ዕለት አመ ፲ወ፭ ጥንተ ባዓለ ጌና በኅዳር 15 ቀን የገና ጾም መጀመሪያ ነው ይላል፡፡ (ስንክሳር ዘኅዳር 15)
3. የመልክአ ማርያም ደራሲ የ20 እኩሌታ 10 መሆኑን ሲገልጥ ማርያም ጽዮን  ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቀ እሥራ ይላል ስለዚህ የ30 እኩሌታ 15 ነው፡፡
4.ፍትሐ ነገሥቱ የኅዳር እኩሌታ ብሎ በማለቱ
5. ቅዱስ ሲኖዶስ በ1983 ጾሙ በአራቱም ወንጌላውያን በኅዳር 15 ብቻ እንዲገባ ወስኗል፡፡ (እሥራ ምዕት ተመልከት) ከዚህ ሁሉ ምስክር ወጥቶ የሰፈር ጎረምሳ ባወራው መነዳት የእንቢተኝነት ጥግ ነው፡፡
ሌላኛው በኅዳር 19 ይገባል የሚለው የብሂለ ተቀብዐ ወገኖች ሐሳብ ነው ስንክሳራችን ግን በዚህችም ዕለት የሮም፣ የአፍርንጊ፣ የሶርያ፣ የአርማንያ ክርስቲያኖች ከግብጽ፣ከኢትዮጵያና ከኖባ በቀር የገናን ጾም የሚጀምሩበት ነው ይላል  (ስንክሳር ዘኅዳር 19) ስለዚህ የ19 መግቢያ የኛ ባሕል አይደለም፡፡ ታዲያ ነቢያት የጾሙ 40 ነው ለምን 44 ቀን እንጾማለን? ከተባለ ጌታችን የጾመ 40 መዓልት 40 ሌሊት ነው ለምን 55 ቀን እንጾማለን? ሐዋርያት የሰኔን ጾም የጾሙት 40 ቀን ነው ለምን ከፍና ዝቅ እያደረግን እንጾማለን? ፍለልሰታነን የጾሙ 16 ቀን ነው ለምን 14 ቀን እንጾማለን? አየይ! የቀኖናን ጠባይ አለመረዳትኮ ነው በሉ በክፍል ሁለት ጠብቁኝ፡፡

@ከሊቀ ማዕምራን መ/ር ተርቢኖስ ቶለሳ

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

23 Nov, 01:30


✍️ በአማን ተስፋ ሕይወት !✍️

"ማንኛውንም ነገር ለመውደድም ኾነ ለመጥላት :ነገሩን አስቀድሞ ከሥሩ ከመሠረቱ ማወቅ ያስፈልጋል እንዲሁ #መጥላት :እንዲሁም #መውደድ ተገቢ አይደለም ደህና አድርጎ ቀምሶ ጣዕሙንም ዐውቆ መቅረብም ኾነ መራቅም የዐዋቂዎች ፋንታ ነው"ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ
#የተስፋ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት የልደት በዓል አከባበር ገና በዋዜማው እንዲህ ደምቋል ።(ሮሜ 8፥28) በአማን ተስፋ ሕይወት የሚያሰኝ ነው። የሚወጣ እንጀራ ከምጣዱ እንደተባለው አይነት ናቸው።
"ቅዱስ ጳውሎስ ... #ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናል፤ ይልቁንም ፈጥኜ እንድመለስላችሁ ይህን ታደርጉ ዘንድ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።" እንዳለ አገልግሎታችን የተሳካ እንዲሆን ለእኛም ጸልዩልን (ዕብ.፲፫፥፲፰)

መ/ር ተመስገን ዘገዬ

ከ____ሀ/ስብከት ከደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን !
ኀዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲ ፯ ዓ.ም
ተጨማሪ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ ።መረጃውን መጠቀም ይቻላል፥ #ምንጭ ግን ይጥቀሱ
E-mail [email protected]
telegeram https://t.me/+U-n_2um5SI7skWIk
Instagram temesgen.zegeye4
YouTube - www.youtube.com/@hamernoah208
Website -hamernoah.wordpress.com
Facebook https://www.facebook.com/temesgen.zegeye.7

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

22 Nov, 13:23


በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ጎርጎራ ከተማ የምትገኘው ምዕራፈ ቅዱሳን ደብረሲና ጽዮን ማርያም አንድነት ገዳም

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

22 Nov, 12:36


https://hamernoah.wordpress.com/2024/11/22/7-%e1%88%9d%e1%8a%a5%e1%88%98%e1%8a%93%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%89%bb-%e1%8b%ab%e1%88%89%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a4%e1%88%ae-%e1%89%85%e1%8b%b1%e1%88%b5-%e1%88%9a%e1%8a%ab%e1%8a%a4/
7 ምእመናን ብቻ ያሉት የአርቤሮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

20 Nov, 17:40


የትም ይዋሉ የት ✍️

የቅዱስ ሚካኤል ዋዜማን በአንጋፋው ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን የነበረን ሣምንታዊ ጉባኤ ምእመናን
ተረጋግተው ሲማሩ ስመለከት ብዙ መምህራን እንደደከሙበት በቂ ምሥክሮች ናቸው።
የጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ምእመናን የትም ይዋሉ የት ለሣምንታዊ ጉባኤው ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ ።
#ሁሉም ነገር ህልውናውን ያጣው ከዚህ የሠርክ ጉባኤ አገልግሎት መራቅ ሲመጣ ነው። ስለዚህ ሠርክ ጉባኤ በሃይማኖት ዐይን ለተመለከተው ክርስቲያኖች ሆይ ሕይወት ነው።
ክርስቲያኖች ሆይ በሠርክ ጉባኤ እንዳትቀልዱ።ነገ የምትቅሙ ዛሬ የዘራችሁትን ነው። የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በዘራነው የሠርክ ጉባኤ ዘር ትወሰናለች።
የዛሬ መሠረት የሆነው የትናንቱ አባቶች የዘሩት ዘር ነው።የነገም ዘር የሚሆነው የዛሬው ሥራችን ነው። የሠርክ ጉባኤ ትምህርታችን የትናንት ማያ፣ የነገ ማስያ፣ የዛሬም መዋያ ነው። በራሳችን ዐይን ወደ ኋላ ማየት እና ለነገም መተንበይ የሚቻለው በጉባኤያት ትጋት ነውና።
በዝማሬ ፦ዘማሪት መሠረት

#መ/ር ተመስገን ዘገዬ
ከጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን
ኀዳር ፲፩ ቀን ፳፻፲ ፯ ዓ.ም

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

20 Nov, 05:07


https://hamernoah.wordpress.com/2024/11/20/%e1%8b%a8%e1%8b%98%e1%88%98%e1%8a%93%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%a4%e1%89%b0-%e1%8a%ad%e1%88%ad%e1%88%b5%e1%89%b2%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b3%e1%88%aa%e1%8a%ad-%e1%89%a3%e1%88%88/
"የዘመናችን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ባለአደራዎች እናንተ በመሆናችሁ የተሰጣችሁን ታሪካዊ አደራ በትጋት በመወጣት ቤተ ክርስቲያንን ልትታደጓት ይገባል" ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ!

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

19 Nov, 11:41


https://hamernoah.wordpress.com/2024/11/19/%e1%8b%a9%e1%8a%92%e1%89%a8%e1%88%ad%e1%88%b2%e1%89%b2%e1%8b%8d-%e1%88%83%e1%8b%ad%e1%88%9b%e1%8a%96%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8a%90%e1%8c%bb%e1%8a%90%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%8b%a8/
ዩኒቨርሲቲው  ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገለጹ፡፡

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

19 Nov, 09:33


ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ በሁሉም የአዲስ አበባ የማኅበሩ ሱቆች ሥርጭት ላይ ናት ።በማሠራጨት ትምህርተ ወንጌል ለሁሉም እንዲደርስ ጥረት እናድርግ

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

18 Nov, 13:31


https://hamernoah.wordpress.com/2024/11/18/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%89%a1%e1%8a%90-%e1%8c%8e%e1%88%ad%e1%8c%8e%e1%88%ad%e1%8b%ae%e1%88%b5-%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%88%a5%e1%88%8d%e1%8c%a0%e1%8a%93-%e1%88%9b/
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርትና ሥልጠና ማእከል የዜማ መሣሪያ ሠልጣኞች ተመረቁ፡፡

1,370

subscribers

3,344

photos

51

videos