Mulualem’s View @mulualemsview Channel on Telegram

Mulualem’s View

@mulualemsview


በውሳኔ አሰጣጥ፣ በስትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና በክርስትና ሃይማኖት ዙሪያ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሠረተ እምነት ላይ በመመሥረት) ሃሳቦችን አጋራለሁ።

Mulualem’s View (Amharic)

መለምያም ዕፃዎች! እናመሰግናለን ከ’ሙሉአልም ብላላ’ አሰጣጥ የቴሌግራም እና የሞባል አፈቃቂ የኮምኒካል። እንቅስቃሴው በደብረ ምስራቅ አገለግላቸው እና በታችኛው ተወዳጅ እንቅስቃሴ እንዴት እንዴት መሆን አለብሻለሁ ታበራራልክ? መለምያም፣ አስገራሚያዎችና ፍንጭ አዲስ ዓለም በማኅበረሰብ መምሪያ ቦታ ታያለህ። ያህዌ ራእይቶችን አጋራለሁ።

Mulualem’s View

22 Nov, 15:11


ልክ እንደ ራሳችን ሁሉም ሰው የየራሱ የሕይወት ትግል ውስጥ ነው ያለው። በሰዎች ጫማ ውስጥ ራስን ዘወትር እየከተቱ ማየት ከእኔነት ሩቅ ሀገር ይመልሰናል። እኔ እኔ የሚለው መንፈስ ከሰዎች ብቻ አይደለም የሚያርቀን ከሕይወት እውነትም ጭምር እንጂ። ሌላው ሰውም የራሱ ግን ከኛ ጋር በሰውነት የሚጋራው ትግል ውስጥ እንዳለ ማሰብ ከፍተኛ የመረዳት አቅምን ይሰጣል። አንድን ነገር ካልተረዳነው ደግሞ መፍትሔ መስጠት ራሱ አንችልም።

Mulualem’s View

19 Nov, 05:00


በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ትልቁ ስህተት አንድን ሰው በሁሉ ነገር (ጉዳይ) ማመን ነው። እኔ ስለ ሮኬት ምንም እውቀት የለኝም። ስለ ፖለቲካ ግን በቂ እውቀት አለኝ። ተምሬዋለሁ። በሆነ ወቅት መተዳደሪያዬ አድርጌዋለሁ። ከዛ ደግሞ የሕግ እውቀት ጨምሬበታለሁ። ስለዚህ ስለፖለቲካ ግንዛቤዬ ጥሩ ነው። ስለፖለቲካ ስለማውቅ ግን ስለ ሮኬት ስናገር መደመጥ የለብኝም። ወይም ስለ ልጆች አስተዳደግ ወይም ስለ መድኃኒት። አንድን ሰው በሆነ የትምህርት ዘርፍ ወይም የሀብት መጠን ስለበለጣችሁ ፥ እናንተ በተሻለ ልታውቁ በምትችሉት ጉዳይ ላይ ልምከራችሁ ወይም ሀሳቤን አድምጡኝ ካለ፤ ያ ትልቁ ስህተት ነው። በሕይወት ውስጥ ይሄን ጉዳይ ማስተር ካደረግን እጅግ ብዙ ከሆኑ ጥፋቶች እንጠበቃለን።

Mulualem’s View

17 Nov, 20:45


https://www.mulualemblogs.com/post/እርግጠኝነት

Mulualem’s View

10 Nov, 17:38


C.S. Lewis on the value of starting where you are:
“You can't go back and change the beginning, but you can start where you are and change the ending.”

Mulualem’s View

10 Nov, 09:15


https://www.mulualemblogs.com/post/ሪፍሌክሽን

Mulualem’s View

08 Nov, 16:29


“የምታምነውን አትንገረኝ። ባልጀራህን እንዴት እንደምትወደው አሳየኝ። ከዛ ምን እንደምታምን እኔ ነግርሃለው።”

Mulualem’s View

08 Nov, 03:57


ወደድንም ጠላንም በዚህ ዓለም ላይ እንደ ሥራችን የኛ መገለጫ የለም። የሰው ልጅ ሥራው ብቻ ላይሆን ይችላል ማንነቱ። ነገር ግን ሥራውን (ፕሮፌሽኑን) የሚያህል መገለጫ የለውም። ለዚህ ነው በፕሮፌሽኑ ከፍጽምና በታች ምንም ላያረካው መጣር ያለበት።
መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር ሰውን በፕሮፌሽኑ ነበር የሚጠራው። ቀራጩ፣ አሳ አጥማጁ፣ መቶ አለቃው፣ ነቢዩ፣ አናጺው፣ ካህኑ እና መሰል የፕሮፌሽኑ መጠሪያዎች ነበር ሰው መሆኑን ወክለው የሚቀርቡት። በፕሮፌሽኑ የሚያሾፍ፣ በፕሮፌሽኑ ፍጹም ለመሆን የማይሰራ፣ በሥራው ምርጥ አይደለም የማይተካ ለመሆን የማይተጋ ሰው ራሱን እየሰደበ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ሰውነቱን ነው ያዋረደው። ለዚህ ነው ለሙያችን ያለን ደረጃ (ስታንዳርድ) እጅግ ከፍ ማለት ያለበት።

Mulualem’s View

07 Nov, 14:45


Be careful of having an opinion unless you have to. The easiest thing to do is to have an opinion. The hardest thing is not to have one.

Mulualem’s View

06 Nov, 14:13


If there is a single lesson we learn from Trump’s victory, that's - don't give up. But fight. Always fight.

Mulualem’s View

04 Nov, 16:07


የሚቆጨኝ ነገር ስላለፈው በመጸጸት ያሳለፍኩት ጊዜ ነው። ምክንያቱም ካለፈው ትምህርት እንጂ ጸጸት ምንም ሲጠቅመኝ አላየውም። በጣም ግን የሚቆጨኝ ነገር አለ። ስለመጪው የገመትኩበት እና የፈራውበት ጊዜዎች። ምክንያቱም 99 ፐርሰንት የፈራውት እና የገመትኩት ፈጽሞ አልደረሰም።

Mulualem’s View

03 Nov, 17:49


አንድ ሰው ትዕቢተኛ ነህ (arrogant ነህ) ስትሉት አይደለውም ካለ፤ ለመሆኑ ከዛ በላይ ማረጋገጫ የለም። "እስቲ ለምን እንደዛ እንዳልከኝ ንገረኝ" የሚል ሰው ፥ ብልህ ነው። "አመሰግናለሁ! ልክ ልትሆን ትችላለህ ግን እስቲ በደንብ አሳየኝ" የሚል ሰው ግን ብልህ ብቻ አይደለም ትሁትም ነው።

Mulualem’s View

03 Nov, 13:06


https://www.mulualemblogs.com/post/እጥረት-እንሁን

Mulualem’s View

31 Oct, 21:16


ምርጫ ነው። ሁሉም ምርጫ ግን ሕመም አለው። ዛሬ ትንሽ መቸገር ወይስ ነገ ብዙ መቸገር። ሁለቱም ችግር ናቸው። መቼ እና በምን ያህል መጠን ነው ጥያቄው። ዛሬ ከእንቅልፍህ ነቅተህ ስፖርት መስራት ወይስ ነገ በበሽታ ምክንያት ብዙ አለመተኛት? ዛሬ የሚያምረንን መብላት ወይስ ነገ በሚያማርረን መያዝ? ምርጫ ነው። ደስታን የማዘግየት፣ የሰው ወሬን ዛሬ የመቻል ነገን ግን በረዥሙ መርካት።

Mulualem’s View

30 Oct, 03:42


አንድን ሥራ በፍላጎት እንሰራዋለን ማለት አያስለፋንም ማለት አይደለም። ካልደከምንበት የፈለግነው ከስንፍናችን አንጻር ነው ማለት ነው። በፍላጎት እንሰራዋለን ማለት ቢደክመንም ደስ ይለናል ማለት ነው። ለሌሎች አሰልቺ እና አበሳጭ የሆነው ድካም ለኛ ግን የርካታ ምንጭ ነው። ያ ነው የምንሰራውን ነገር መውደድ ማለት። ላብ አለበት፣ ድካም አለበት፣ ጭንቀት እና መውደቅ አለበት፣ ብዙ ጊዜ መሳሳት አለበት። ግን ርካታ እና ትርጉም ተለይተውት አያውቁም።

Mulualem’s View

28 Oct, 13:54


ሰውን በችግሩ ጊዜ የምንረዳው ያን ችግር ከኛ እርዳታ ውጪ ማለፍ ስለማይችል አይደለም።

Mulualem’s View

27 Oct, 15:39


https://www.mulualemblogs.com/post/ረጅሙ-እና-ከፍ-ያለው-ዙፋን

Mulualem’s View

26 Oct, 09:06


አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ንግግር የሞገተበት መጣጥፍ አለው። "ለሀገሬ ምን አደረኩላት ሳይሆን ሀገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ብዬ ነው መጠየቅ ያለብኝ" የሚል። ፕሬዝዳንት ኬኔዲ "ሀገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን ፥ ለሀገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ" ብሎ ነበር። ቤተመዛግብቱ ሙሉጌታ ግን ይሄን ሀሳብ ሞገተ። ይመስለኛል ተሰዶ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ሀገሩ ልታደርግለት ከምትችለው መቶ እጥፍ በላይ አሜሪካ አድርጋለት ሲያይ፣ ሀገር እንድትሆን ደሙን ያፈሰሰላት ኢትዮጵያ እንደሰው ሳትቆጥረው ፥ አሜሪካ ግን "ክቡር ሰው ነህ" ስትለው የተሰማው ስሜት ይሆናል።

"ኢምፔሪያሊዝም ይውደም፣ ምዕራባውያን ሴጣን ናቸው" ያሉ ሁሉ ፍጻሜያቸው አሜሪካ አሳይለም መጠየቅ ነበር። በተለይ የስልሳዎቹ ትውልዶች። ምክንያቱም ልባቸው እውነቱን ያውቃልና። ቻይናን፣ ራሺያን ወይም ኩባን ለፖለቲካ ይደግፉ ይሆናል። ልጆቻቸውን ግን የሚልኩት፣ መጦሪያ ቤታቸውን ግን የሚገዙት ይውደም ያሉት ሀገር ላይ ነው።

እነዚህን ሰዎች ሳስብ አንድ ስሙን የረሳውት ፈላስፋ ት ዝ ይለኛል። ይሄ ፈላስፋ ከአንድ መናጢ ደሃ ጎን ቁጭ ብሎ ለቁራሽ ዳቦ የሚሆን ገንዘብ ይለምናል። ሰው ሁሉ ግን እርሱን እያለፈ ለመናጢ ደሃው ይሰጣል። በዚህ ጊዜ ደሃው "አየህ አይደል ሰው ለእኔ እንጂ ለአንተ አያዝንም" አለው። ፈላስፋው ለማኝም መልሶ "አዝነውልህ እኮ አይደለም። ነገ ሁሉም እንዳንተ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለሚያውቁ ነው የሚሰጡህ። እንደ እኔ ግን እንደማይሆኑ ያውቁታል። ምክንያቱም የማሰብ አቅማቸው እኔ ጋር እንደማይደርስ ይረዳሉና" አለው። እኔ ምዕራባውያንን የሚያወግዙ ግን ሲሰደዱ እዚህ የሚመጡ እንደ አንዳርጋቸው ያሉ ሰዎችን ሳይ ይሄ ፈላስፋ ነው ትዝ የሚለኝ። ለሁሉ የምትሆን ሀገር፣ የነጻነት ሀገር የመገንባት አቅም እንደሌላቸው ያውቃሉ። እንደ ቻይና እና ራሺያ ግን መሆን እንችላለን ብለው የሚያስቡ ይመስለኛ። መመሳሰል ነው መውደድን የሚጭረው።

ግን የምንሰደድበት ሀገር ሲሆን ፍላጎታችንን እናያለን። ቻይና ሄደን መማር እንችል ይሆናል፤ መቼም ግን ቻይና ሀገራችን እንደማይሆን፣ ልጆቻችንም እዚህ ቢወለዱ ሀገራቸው እንደማይሆ ከልብ እናውቃለን። ሁልጊዜ ባዳ ነን። በዓለም ላይ ከየትም መጥተን ከሀገራችን በላይ የምንሆንባት ሀገር አሜሪካ ብቻ ትመስለኛለች።

ጄኔቫ ስኖር ከአንዲት እዛ ሀገር ከተወለደች ሊባኖሳዊ ጋር ግንኙነት ጀምረን ነበር። እዛ ተወልዳ እዛ አድጋ፣ ፈረንሳይኛ እየተናገረች ዜጋ ግን አላደረጓትም። ገና መሆን አትችልም ነበር። ካናዳ መሰደድ ታስብ ነበር። አሜሪካ ሀገር ግን አንድ ሰው ሲፈልግ የግል ነጻነቱን አስጠብቆ፣ ሲፈልግ ትንሿ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ እያለ መንገድ አሰይሞ፣ ታቦት አምጥቶ፣ ገዳም ተክሎ የጋርዮሽ ኑሮ ይኖራል። ከነጭ እኩል አልሆንኩም ብሎ ያስፈራራል። በዚህ ዓለም ከዚህ ሀገር ውጪ እንደዚህ የምንሆንበት የትም ያለ አይመስለኝም። ይሄን ሲያይ ይመስለኛል ሙሉጌታ ሉሌ "ሀገሬ ግን ለእኔ ምን አደረገችልኝ?" ያለው።

ለምሳሌ በዛሬው ቀን በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራዊ በመሆኑ ብቻ መንግስት አስሮት የነበረ፣ በኋላም ከሀገር አምልጦ የመጣ ደንበኛችን ነበር። ልጆቹን ጥሎ ስለመጣ የአሳይለም ኬዙ እንዲፋጠንለት (expedite እንዲደረግ) ጠየቅን። ሀገሩ በዘሩ ምክንያት አሰረችው። አሜሪካ ግን ከልጆችህ መነጠል የለብህም ብላ፤ የመሳካት ዕድሉ በጣም ጠባብ በሆነው የማፈጠን ሂደት ጥያቄያችንን ተቀብለው አስተናገዱልን። ሰውኛ ሥራዓት ማለት ይሄ ነው። ይሄ የሚሰጠው ደስታ ነው፤ በክፍያ በአስር እጅ ከዚህ ከሚበልጠው የኮሜርሻል ሊቲጌሽን ወደ ኢምግሬሽን ያመጣኝ። ምክንያቱም ይሄ ሀገር ለእኔ የሰጠውን መብት ሌሎች እንዲያገኙ መስራት ትልቅ ርካታ አለው።

በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን ሕግ አክባሪ ነን። ለቤተሰቦቻችን የምናስብ፣ የራሳችንን ስኬት ብቻ የማናይ፣ ወገባችን ጎብጦ ዘመዶቻችንን ለመርዳት የምንጥር ነን። ሙያዬን ይሄን ለማገዝ መጠቀም፣ ኢትዮጵያኖችን ከፍተኛ ፕሮፎሽናሊዝም በተሞላበት መልኩ መርዳት እና ህልማቸውን እውን ማድረግ መቻል ከምንም በላይ አስደሳች ሥራ ነው። ረፍት የለንም ርካታ ግን አለን። ቅዳሜ እሁድ አናውቅም ግን ሌሎች በኛ ላይ ሀሳባቸውን መጣል የሚችሉብን ፥ አምነውን መተኛት እና ማረፍ የሚችሉ ሙያተኞች ነን። ምክንያቱም ከልባችን በአሜሪካ ሕልም እናምናለን። የሕግ ሀገር እንደሆነ እናውቃለን። ሰዎች ከሠሩ የሚለወጡበት እንደሆነ እናያለን።

ግን ሁላችንም ይሄ ሀገር የምር ውለታ እንዳደረገልን ማየት አለብን። ለዚህ ደግሞ የሀገሩን ሕግ፣ ባህል፣ ንጽህና፣ ታላቅነት የማስጠበቅ ሞራላዊ ግዴታ እንዳለብን አንዘንጋ። ምክንያቱም ለብዙዎቻችን ሰው ማለት ምን እንደሆነ፣ ምን ዓይነት ክብር እንዳለው ያሰየችን አሜሪካ ናት። "አሜሪካ ምን አደረገችልኝ?" ብለን የመሞገት ድፍረት የለንም። በሃይማኖት የምትቀርበን ራሺያ ሳይሆን ካሊፎርኒያ በርሃ ውስጥ ነው ገዳም የተከልነው። ፍጹም ነጻነት ስንፈልግም መጥተን ያገኘው እዚው ሀገር ነው። ለዚህ ነው ሙሉጌታ ሉሌ ታማኝነቴ ላደረገችልኝ ሀገር ነው የሚል የመሰለኝ።

Mulualem’s View

24 Oct, 13:15


በሕይወት በጣም ቀላል ኑሮ ለመኖር በጣም ከባድ ነገርን መምረጥ ያስፈልጋል። ከምንም ነገር በላይ ሕይወት ወለፈንዲ ነው። ማለትም ሕይወት ኮውንተር ኢንቲዩቲቭ (counter intuitive) ነው።

ለምሳሌ ደስተኛ ለመሆን ደስታን አለመፈለግ ነው። ልክ እንቅልፍን ሆን ብላችሁ ልተኛ ስትሉ እንደሚርቃችሁ፥ ደስታ ላይ ስናተኩር ደስታ ይርቀናል። የራሳችሁ ደስታ ላይ ማዕከል ያላደረገ ነገሮችን ስትሰሩ ደስተኛ የመሆን አጭሩ መንገድ ያ ነው። በሕይወት ትርጉም የሚፈልግ ሰውም ራሱን ፍጹም ከባድ ለሆነ ነገር ያጋልጥ (expose yourself to greater challenges)።

Mulualem’s View

22 Oct, 17:58


በሕይወቴ ከስካመሮች ያመለጥኩበት ሚዛኔ የልዑል ራስ ካሳ ለቀደማዊ ኃይለሥላሴ ምክር ነው።
“በጣም ጥሩ ነውና ውሸት ነው።”

አንድ ነገር በጣም ጥሩ ከሆነ የኔን ራዳር አያልፍም።

Mulualem’s View

21 Oct, 14:56


ፍላጎት ደካማ ያደርጋል፤ ፍላጎትን መቆጣጠር ደግሞ ፍላጎትን የማርኪያ አጭሩ መንገድ ነው።