Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/ @deacongetabalewamare Channel on Telegram

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

@deacongetabalewamare


#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እና እኔ #ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን

http://youtube.com/channel/UCDHaGNE2Sx_FkqdTi8E_Tfg

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/ (Amharic)

ሰዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እና እኔ ሰዐሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ የቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን፣ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ነው። ይህ በዚህ በርካታ የሰውየውን የሌሎች ያለ አስረናዉን አዝናኝ አድርጓል። የሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እና እኔ ሰዐሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ የቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን፣ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ነው። እባኮት ለም-ሳምንት በጋራ የምግብ ጠብታዊና ምንጭ የሚለው ስለ ሁኔታ እንዲሆን አድርጉ። ስለ ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እና እኔ ስለ ሰዐሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ መሆን እንዲያመለክት እባኮታለን።

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

28 Jan, 20:46


🌹+ + አስተርእዮ + +🌹
#ሞት_ለሚሞት_ይገባል
#የማርያም_ሞት_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል "

"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"

እንኳን ለ 2017ዓ.ም
የ #አስተርእዮ ማርያም በዓል አደረሳችሁ!!!

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

28 Jan, 20:44


🌹+ + አስተርእዮ + +🌹
#ሞት_ለሚሞት_ይገባል
#የማርያም_ሞት_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል "

"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"

እንኳን ለ 2016 ዓ.ም #አስተርእዮ ማርያም በዓል አደረሳችሁ!!!

#እመቤታችን_ለምን_ሞተች?

🍂 #ጥር_21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ይታሰባል፡፡

ሞት በአዳም በደል ምክንያት የመጣ ዕዳ ነው፤ባህርያዊ ሳይሆን ባህርያዊ መስሎ ከባህርያችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር ፍዳ ነበር፡፡ ሞት ጌታችን ሳይገድለው/ሳይሽረው በፊት ወደ ሲኦል መውረጃ መንገድ ነበር፤
ለአጋንንት እግር እርግጫ፤ ለመንጸፈ ደይን ተመቻቻተን የምንሰጥበት ሂደት፤ሥጋ በመቃብር የሚፈርስበት፤ነፍስ በሲኦል የምትሰቃይበት ክስተት ነበር፡፡

🍂ክርስቶስ ሲመጣ ግን ይህ ሞት የሚለው ንባብ ሳይቀየር ትርጉሙና ምሥጢሩ ተቀየረ፤መጠጫው ጽዋው ሳይቀየር መጠጡን እንደመቀየር ነው፤መሞት በሐዲስ ኪዳን መሻገር ነው፤ወደ ዘለዓለም ሕይወት መጠራት፤መቃብርም ለትንሣኤ ዘጉባኤ መቆያ ስፍራ ነው፡፡

🍂 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን ሞተች? ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት ከሆነ እመቤታችንም የሞተችው ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ፤

አነዚህ ሰዎች በሐዲስ ኪዳን ሞት ምን እንደሆነ ያለመረዳታቸውና እንዲሁም የእመቤታችን ሞት ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን ባለማወቃቸው ምክንያት የሚናገሩት ነው፡፡

🍂 ሞት ጥንተ አብሶ ያለበት ብቻ ነው የሚሞተው ከተባለ ጌታችን ራሱ መሞቱ ጥንተ አብሶ ስላለበት ነው ያሰኛል፤ ይህ ደግሞ እርሱ ንጹሕ ሆኖ ሳለ ስለእኛ ሞተ የምንለውን የድኅነት ፅንሰ ሀሳብ ከንቱ ያደርግብናል፤ስለዚህ ሞት ከክርስቶስ በኋላ የመብቀል ሂደታችን መሆኑን እንመርምር፡፡

🍂 ይህን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይነግረናል:—
"አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም"፤ይላል 1ኛ ቆሮ 15፡36፡፡ ሰለዚህ ሞት በሐዲስ ኪዳን ሕያው ለመሆን የምናልፍበት ሂደት (process) ነው፡፡

ራሱ ጌታችንም ሲያስተምረን:—

"እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም"፤ዮሐ 5፡24፡፡

ዳግመኛም ፦ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አያይም" ብሏል፤ዮሐ 8፡51፡፡

ይህም ማለት ነፍስ ከሥጋ አትለይም ማለት አይደለም፤እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ነፍስ በገነት እንደምትኖር፤ ከዚያም በትንሣኤ ዘጉባኤ ጊዜ ነፍሳችን ከሥጋችን ጋር ተዋሕዳ ተነሥተን ከመላእክት ጋር እያመሰገንን የምንኖረውን ዘላለማዊ ሕይወት ለመግለጽ እንጂ፡፡

🍂 እመቤታችን ቃሉን በመስማትና በማመን በመጠበቅ የመጀመሪያዋና ተወዳዳሪም የሌላት ናት፤ ማንም ሊሰማው የማይችለውን "ቃል ሥጋ ኮነ" ን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማች መስማት ብቻ ሳይሆን ያመነች ናት፤ቅድስት ኤልሳቤጥ "ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃል ዘነገሩኪ እምኀበ እግዚአብሔር ፤
(ከእግዚአብሔር የተነገረሽ ቃል እንደሚፈጸም ያመንሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ) ብላ እንዳመሰገነቻት (ሉቃ 1፡45) "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" ብላ ስታምን ነበር ሞትን ያለፈችው፤ትንሣኤ ልቡናን ቀድማ የተነሣችው፤ ይህ ምሥጢር የተከናወነባት ናት፤እያንዳንዱን የጌታን ቃል በልብዋ ትጠብቀውና ታስበው እንደነበር ተጽፏል፤ሉቃ 2፡51፡፡

🍂 እንዲህ ከሆነ ሕይወት የሆነውን ጌታ ፀንሳ፤ወልዳ የድንግልና ጡት ያጠባች ሆና እንዴት ትሞታለች?
ሕይወትን የዳሰሱ እጆች፤ሕይወትን የተመለከቱ ዓይኖች፤ሕይወትን ያቀፉ ጉልበቶች እንዴት ለሞት ይሰጣሉ? ብለን ስንጠይቅ የሚከተሉት ምላሾች ይኖሩናል፡፡

➊ ከተገፋችበት ፤ከተንከራተተችበትና የኀዘንና የመከራ ሰይፍን ካስታናገደችበት ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ወደመንግሥተ ሰማያት መጠራቷን፤የማያልፈውን ዋጋ እንደተቀበለች ለማሳየት እንጂ የሞት ሞት የሚባለውን መፍረስና መበስበስን፤ወደ ሲኦል መውረድን የሚያሳይ እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ይህንንም ቅዱስ ያሬድ "ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘ ይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ዳዊት አቡሃ በመሰንቆሁ እንዘ የኀሊ፤የሰው እጅ ያልሰራት ድንኳን ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረላት እመቤታችን አባቷ ዳዊት በመሰንቆው እያመሰገናት ከሚያረጀው ዓለም ወደማያረጀው/ወደማያልፈው ሄደች"
በማለት እነደነገረን ነው፡፡

➋ ከሰማይ የወረደች (ኃይል አርያማዊት) ናት የሚሉ አሉና ሰው እንደሆነች እና ከምድር እንደተገኘች፤ሙሉ የሰውነት ማንነት ያላት መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤ እመቤታችንን ሞት ባያገኛት ካልዕ ፍጥረት (ልዩ ፍጥረት) ስለሆነች ነው ብለው ብዙዎች በተከራከሩ ነበር፤ይህም ደግሞ ክርስቶስ የነሣውን ሥጋና ነፍስ (ምሥጢረ ተዋሕዶን) ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተው ነበርና በዚህ ምክንያት በሕገ ሰብእ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ስለተገኘች በሕገ ሰብእ ሞት ተጠርታለች፤ ይህ ሞቷ እሷን ሌላ ፍጥረት የጌታን ተዋሕዶ ምትሐት ከማለት የሚታደግ መድኃኒትም ጭምር ነው፡፡

➌ ፍትሑ ርቱዕ (ፍርዱ ቅን የሆነ) እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ ያጠይቃል፤ እመቤታችን እንደማንኛውም ሰው ሞትን ባታይና ባትቀምስ ፍርዱ ትክክል አይደለም፤ አንዱን በሞት ይወስዳል ሌላውን ይተዋል፤ወዲህም ልጅዋ አምላክ ነውና ሞትን ያልቀመሰችው በልጅዋ ምክንያት እንጂ እርሷ የተለየ ቅድስና ስላላት አይደለም በተባለ ነበርና ሞትን እንድትቀምስ ፈቅዷል፤ሞትን መቅመሷ በክብር ላይ ክብር ቢጨምርላት እንጂ ቅንጣት ታህል ክብር አይቀንስባትምና፡፡

ይህንንም ደራሲው፦

"ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤
#ክርስቶስ_ሥጋውን_ለነሳበት_አካል_በሞት_አላዳላም" በማለት ተናግሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድም ፦

"እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኩሉ
አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ"

(በፍርድ እንደማያዳላ ስለዚህ ነገር ዕወቁ፤የእርሱ እናት፤የሁሉ እናት እመቤታችን ሞትን ትቀምስ ዘንድ ወልድ በማይሻር ቃሉ አዘዘ) በማለት አስረግጦ ተናግሯል። (የዕለቱ ዚቅ)፡፡

➍ #በነገረ_ማርያም ላይ እንደተጻፈው እመቤታችን የዕረፍት ጊዜዋ መድረሱን ጌታችን ሲነግራት እንዴት እኔ የአንተ እናት ሆኜ ሞት ያገኘኛል? በማለት ጠይቃለች፤ቅዱስ ያሬድ እንደገለጸው "እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ ከመ ኩሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤እንደማንኛውም ሰው ሞት በጎበኛት ጊዜ የአምላክ እናት እንደምን አለቀሰች?" (የዕለቱ ዚቅ)፡፡
ጌታችንም አንቺ ስትሞቺ ባንቺ ሞት ምክንያት ከሲኦል የሚወጡ ነፍሳት አሉ በማለት ነገራት፤

🍂#እመቤታችንም ርኅርኅት ናትና በኔ ሞት ምክንያት ነጻ የሚወጡ ነፍሳት ካሉ አንድ ጊዜ አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት ብላ መልሳለታለች፤ይህም ማለት ሁሉም ነፍሳት በእመቤታችን ሞት ምክንያት ከገነት ይወጣሉ ማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ባወቀ የእናቱ ሞት ቤዛ እንዲሆናቸው የመረጣቸው ነፍሳት መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

• በብሉይ ኪዳን ጥንተ አብሶ ያለባቸው ሰዎች ሲሞቱ መልአከ ሞት ይታያቸው ነበር ለእመቤታችን ግን ልጅዋ ራሱ ክርስቶስ ነው የተገለጠላት፤

• በብሉይ ኪዳን የሞቱ ሰዎች ወደ ሲኦል ነበር የሚወርዱት እመቤታችን ግን ሥጋዋ በገነት ነፍሷ በልጅዋ እጅ ነበር፤

• ከአዳም ልጆች ወገን የመጨረሻውን ትንሣኤ የተነሣ የለም፤እመቤታችን ግን እንደ ልጅዋ ተነሥታለች ዐርጋለች፤መዝ 131፤8፡፡

🌹 #ሰለዚህ_የእመቤታችን_ሞት_ይደንቃል፤

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

28 Jan, 20:44


ሁላችን ከሞታችን በፊት የሰራነው ብዙ ኃጢአት አለ፤ እመቤታችን ግን ንጽሕት ናት
ሞቷም በሲኦል ስላሉ ውስን ነፍሳት በልጅዋ ፈቃድ ቤዛ ሆኖ የተሰጠ፤የተከፈለ ነው፡፡

#ሞት_ለሟች_ይገባል
👏 #የድንግል_ሞቷ_ግን_ለሁሉ_ይደንቃል !!! 👏

/👉ምንጭ #ከመጋቤ_ሐዲስ_ነቅዐ_ጥበብ_ከፍያለው/

🙏🏾 የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🏾
ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን ያሳድርብን!!!

የልጅዋ የወዳጅዋ ቸርነት አይለየን

#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እና እኔ #ሠዓሊ_ዲን_ጌታባለው_አማረ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን
በዚህም ገጽ የቅዱሳንን መንፈሳዊ ሕይወት ከተጋድሏቸው ጋር ፤ የቅዱሳን መላዕክትን ተራዳኢነት እንዲሁም ገድላት ድርሳናትን ከቅዱሳት ስዕላት ጋር ተስማምተው ያገኙበታል ።

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

25 Jan, 19:29


🍂 በ England uk ለሚድልስቦሮ ደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከሠራናቸው ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የሰማእቱ የ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥዕል

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264

t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

25 Jan, 19:28


ደ ብ ረ ፡ ይ ድ ራ ስ : ተ ራ ራ : ወ ስ ደ ው :
አ ፅ ሙ ን : በ ተ ኑ ት

#ጥር_18 ቀን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በብዙ ተጋድሎ ውስጥ ሆኖ « እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው » በማለት የተመዘዘ ሰይፍ የነደደ እሳትን የከሀዲውን የዲድያኖስ ቁጣ ሳይፈራ መከራን ታግሷል የጌታውን የአምላኩን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የመሰከረበት ዕለት ሲሆን ።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በማይመረምረው ጥበበ እግዚአብሔር በመታመኑ ብዙ መከራ ደረሰበት በጉድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አብስለው አቃጥለው አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ በዚህ ጥር 18 ቀን ደብረ ይድራስ ወደ ተባለ ረጅም ተራራ ወስደው አፅሙን በተኑት ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት አንድ አካል ሆኖ ወደ ቀድሞ መልኩ ዳግም ተመልሶ አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በመሄድ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ።

ለቁጥር የበዙ አሕዛብ አይተው አደነቁ ከንጉሥ ሠራዊትም ከአሕዛብም ብዙዎችን በጌታችንም አመኑ በማመናቸውም ምክንያት በከሀዲው በንጉሥ ዲድያኖስ ሰማዕትነትን ተቀበሉ ።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በታላቅ ድምቀት ይህንን ቀን ታሳቢ በማድረግ በዓልን ሰርታ ታከብረዋለች ።

✎﹏ዳዊት ተስፋዬ Daweit Tesfay ✍️
ጥር 18 2017 ዓ.ም

የታላቁ ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ
ረድኤት ረድኤት በረከቱ አይለየን
በአማላጅነቱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏🏽

🍂 በ England uk ለሚድልስቦሮ ደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከሠራናቸው ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የሰማእቱ የ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥዕል

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

23 Jan, 11:13


ከተለዩ የተለየች የተባልች የተባለች #የኪዳን_ጽላት_ያለብሽ
የተሠወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ ፤ ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ። ( የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም )

✍️ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት 🎨
@seali_kesis_amare_kibret 🖌️

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት #ሠዐሊ

+251913684351
+251923075264

t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

17 Jan, 19:08


+ + ያን ጊዜ #ኢየሱስ_በዮሐንስ ሊጠመቅ + + ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።

#ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል
አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።

#ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤
እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።
ያን ጊዜ ፈቀደለት።

ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤
እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ
እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤

እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦
#በእርሱ_ደስ_የሚለኝ_የምወደው_ልጄ_ይህ_ነው_አለ።

( ማቴ 3 ፥ 13 -17 )

🙏🏽 እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ 🙏🏽

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
@seali_kesis_amare_kibret

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

12 Jan, 06:51


ከ ሐ ዋ ር ያ ት ፡ ጋ ር ፡ ሸ ሽ ቶ : ያ ላ መ ለ ጠ : ቅ ዱ ስ : ዮ ሐ ን ስ

#ጥር_አራት ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የዕርገቱ መታሰቢያ ቀን ነው ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ሄኖክና እንደነ ኤልያስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገ ፍቁረ እግዚእ የተባለ ቸር አባት። #ቅዱስ_ዮሐንስ_እኮ

ሰማያዊ ሰው ፥ ንሥረ ክርስቶስ
ምድራዊ መልአክ ፤ ከጌታ ደረት የተጠጋ
የቃና ዘገሊላ ታዳሚ ፤ የፍጥሞ ደሴት ግዞተኛ
ድንግልን በቤቱ ያስጠጋ ፤ የኤፌሶን ሰው አጥማጅ
የክርስቶስ ፍቅር ምርኮኛ ፤ የጥብርያዶስ ዓሣ አጥማጅ
ከመስቀሉ የማይነቃነቅ ታጋሽ ፥ ዖፈ መድኅን ፤ ነባቤ መለኮት
በቀራንዮ የጌታውን መዋረድ ያየ ፤ ምጽአትን አልፎ የሚያይ ደኃራዊ
ሰማይ የሚያደርስ የብርሃን ዐምድ ፤ በቀራንዮ መስቀሉ ሥር የታመመ
በብዕሩ ሙሴን የቀደመ ቀዳማዊ ፤ በደብረ ታቦር የጌታውን ክብር ያየ
በጌታ ቀን በመንፈስ የዋለ ተስፈኛ ፤ ወደ መቃብሩ ግን የሚሮጥ ችኩል
ጌታ ይወደው የነበረ ሐዋርያ ፥ ፍቅርን በመስቀል አይቶ ተፋቀሩ ሲል የኖረ
መላእክት ከእርሱ ሊማሩ ሚችሉት ምሥጢር የተገለጠለትነባቤ መለኮት
በሕማሙቀን ፊቱየጠቆረ ኀዘንተኛ፤በራእዩ ከእግሩሥር ወድቆ የተደመመ

ለ ነ ባ ቤ : መ ለ ኮ ት : ለ ቅ ዱ ስ : ዮ ሐ ን ስ
የ ሚ በ ቃ : ቃ ል : ይ ኖ ር : ይ ሆ ን

ፍቁረ : እግዚእ : የተባለ : ቅዱስ : ዮሐንስ : ወንጌላዊ : በረከት
ረድኤቱ : ከሁላችንም : ጋር : አድሮ : ለዘላለም : ይኑር : አሜን

✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ጥር 3 2017 ዓ.ም

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
       0923075264
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

11 Jan, 18:21


+  በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ +
🍂 እሳቱ ላላቃጠለህ +
+  መለኮት ለሳመህ  +🍂 
+  ድንግል ላቀፈችህ  ላንተ
🍂#ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባሃል  +

             
+   ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ   
+  ዮሐንስ ታኦሎጎስ
          
            🙏🏾

+  ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ       
+  ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
         
           🙏🏾

+   ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ          
+    ዮሐንስ ድንግል 

            🙏🏾

ከብዙ ጸጋህ . . . ለእኛ ለባሮችህ
ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን
እንማጸንሃለን 🙏

👉 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
       0923075264
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

11 Jan, 18:20


🍂🌹 ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 🌹🍂
#ጥር_4 ሞትን ሳያይ  እንደተሰወረ፤ የፍልሰቱ መታሰቢያ

+  በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ እሳቱ ላላቃጠለህ
+  መለኮት ለሳመህ  ድንግል ላቀፈችህ  +
+  ድንግል ላቀፈችህ  ላንተ #ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባሃል  +

+   ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ   ዮሐንስ ታኦሎጎስ
+  ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ        ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
+   ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ           ዮሐንስ ድንግል 

አባቱ 🍂 ዘብዴዎስ ሲባል
እናቱ 🍂 ማርያም ባውፍልያ ትባላለች።

. #ቅዱስ_ዮሐንስ የጌታችን ደቀመዝሙር ከመሆኑ አስቀድሞ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር ገና በወጣትነቱም የመሲሁን የክርስቶስን መምጣት ከመምህሩ ከመጥምቀ መለኮት ስለተረዳ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፤
ዕድገቱም በገሊላ ነበር።

ሐዋርያነቱንም በደስታ እና በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስ ሳይለይ በመከራውም ሰዓት አስከ መስቀሉ ድረስ አብሮት ነበር አልተለየውምም። ፍቁረ እግዚእ መባሉም ከጌታችን ባለመለየቱ ጌታችንም ይወደው ስለነበር ነው።

በክርስቶስ መስቀል አጠገብ ከእመቤታችን ጋር በሀዘን እና በልቅሶ ቢገኝ ጌታችን እነኋት እናት ብሎ በእርሱ አንጻር ለእኛ እናታችን ትሆነን ዘንድ ሰጥቶናል፤ እንዲሁም ለእናቱ እነሆ ልጅሽ ብሎ በእርሱ አንጻር ለእርሷ ልጇቻ እንሆን ዘንድ ሰጥቶናል

#ቅዱስ_ዮሐንስም የጸጋ እናቱን ወደ ቤቱ ከወሰደ በኋላ እመቤታችን ከዮሐንስ ጋር 15 ዓመት ኖራለች። ጸጋን የተመላች እመቤታችን የተቀበለው ቅዱስ ዮሐንስ ምስጢር ተገልጾለት ምስጢረ መለኮትን እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ ብሎ “ በመጀመሪያ ቃል ነበር ...” ብሎ ድርሰቱን ጀምሯል።

ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ
     🍂  የዮሐንስ ወንጌል
    🍂   3 መልእክታት
     🍂 የዮሐንስ ራዕይ
እነዚህን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጽፏቸዋል።

ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ከሆነው ከደቀመዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር የሐዋርያነት ተጋድሎውን የፈጸመው፤ ያስተማራው በቀደመችው ኤፌሶን በአሁኗ ቱርክ ነው።

#የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያሰበ ፣ እያዘነ እያለቀሰ 70 ዘመን ቁጽረ ገጽ ሆኖ ኖሯል።
በቅድሥት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንሥር ነዉ፡፡ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡

. #ንሥር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ፤
ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡

ንሥር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡

ንሥር አይኑ ንጹህ ነዉ ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡

🍂 በዚህም #ዮሐንስ_ዘንሥር ተብሏል፡፡

ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡
ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ

“ #ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? “ ( ዮሐ 21፡20 )
ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡
በማቴ 16፡18 ላይ “ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ “
ያለዉ ቃል ለ#ቅዱስ_ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡

🙏🏾  #የቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ
በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏🏾
ወርኃዊ መታሰቢያ በዓሉም በ4 ነው

ከብዙ ጸጋህ ለእኛ ለባሮችህ
ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን
እንማጸንሃለን 🙏🏽

👉 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
+251913684351

      ዲ/ን ጌታባለው አማረ
     የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

11 Jan, 05:45


አንተ ከኔ ጋር ነህ... አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ......... አማኑኤል
ድል አርገህልኛል.... አማኑኤል
የጭንቄን ተራራ...... አማኑኤል
በጉባኤ መኃል....... አማኑኤል
አፌ አንተን አወጀ.... አማኑኤል
የከበረ ደምህ....... አማኑኤል
ነፍሴን ስለዋጀ...... አማኑኤል

ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
📞 +251923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

29 Dec, 09:07


ከመ ለቢወነ ብከ ናእርፍ በማኅደረ ሕይወት ፤
ፈጥረህ የምትገዛ የባሕርይ አምላክ ሆይ ! አንተን አውቀን ከገቡ መውጣት ካገኙ ማጣት በሌለባት መንግሥተ ሰማያት እንኖር ዘንድ

እንዘ ንገብር ፈቃደከ : ሀበነ ንሑር በትአእዛዝከ ፤
ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪትን ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ጠብቀን እንኖር ዘንድ እውቀቱን ስጠን

( ጸሎተ ኪዳን )

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
ቅዱሣት ሥዕላት ሠዐሊ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

25 Dec, 19:44


ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት
#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ

Created by; @qagnewcreatives

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

24 Dec, 10:59


🎨 ሕብረታችን ✍️🖌️

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት #ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ

📞251923075264

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

20 Dec, 11:03


#ቅድስት_ሃና

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Created by ; @qagnewcreatives

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

18 Dec, 09:48


ታምራትን እያደረገ ሁለት መቶ አርባ ሺ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣ፡፡

ያባታችን የረፍት ጊዜ በደረሰ ሰዓት ጌታችን ለአባታችን
ቃልኪዳን መታሰቢያህን ያደረገ ዝክርህን የዘከሩ
የገድልህን መጽሐፍ የጻፉ ያጻፉ ቤተ ክርስቲያንህን የሠሩ
ያሠሩ የሠሩትን ኃጢአት ይቅር እላቸዋለሁ።

ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ገድልህን የጻፈውን ያጻፈውን
ያነበበውን የተረጎመውን ጽፎም በቤቱ ያስቀመጠውን ሰው የተለያዩ በሽታ የሚያመጡ ሰውን የሚፈትኑ ርኩሳን
አጋንንት አይቀርቡትም ተላላፊ በሽታ ወይም ተስቦ
ተቅማጥ ርኃብ ቸነፈር የውኃ መታጣት የልብስ መራቆት
መዥገር አይደርሱበትም ሌጌዎን የተባለ ክፉ ጋኔንም
ፈጽሞ አይቀርብም። ፋኑኤልና ሩፋኤል እስከ ዘለዓለሙ
ይጠብቁታል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ
የሰማይ መላእክት በተድላ በደስታ ወደ ሰማይ ያሳርጉታል።
እንዲሁም ጌታችን በርካታ ቃልኪዳኖች ላባታችን
ተሰቷቸዋል ገድላቸውን ገዝተን እናንብበው በቤታችን
እናስቀምጠው ።

አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
በሚያዚያ 9 ቀን አርፉ ::

የአባታች የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
ረድኤት እና በረከት አይለየን 🙏🏽



ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /

📞 +251923075264

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

18 Dec, 09:47


🍂 ጻድቁ አባታችን #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
ታህሳስ 9 በዓለ ልደታቸው

አባታቸው መልዓከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም
ይባላሉ፡፡የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር
ዳውንት ይባላል፡፡

ጻድቁ አባታችን በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ
ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ
ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው
በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን
በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡

ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን
የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን
የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ
እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡

🍂 ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ጆሮውን ወደ
ልመናቸው አዘነበለ እንዳለ መዝ 33፤29 እግዚአብሔር
አምላክ በዓይነ ምህረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም
ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ቀን
ተጸንሶ #ታህሳስ_9 ቀን ተወለደ፡፡በተወለደ እለትም ተነስቶ
በእግሩ ቆሞ 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ ጣዕም ባለው አንደበቱ
ተናገረ፡፡ 9 ጊዜም ህጻናትን ለሚያናግሩ ገዥ ለሚሆኑ
ለአጋይዝተ አለም ስላሴና ለእመቤታችን ለመስቀሉም
ሰገደ፡፡እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ብዙ ሰዎች ከህጻኑ
አንደበት የስላሴን ምስጋና ሰምተው ፈጽመው አደነቁ
ዳግመኛም በዚህ ህጻን ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ
አድሮበታል ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ሀገራቸው ገቡ፡፡

አባቱና እናቱም መጀመሪያ ስለመወለዱ ዳግመኛም
የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ምስጋና በማቅረቡ ደስ
አላቸውና እግዚአብሔር ይህን ህፃን ሰጠን እኛ በአብ
በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስዕል ፊትና ለፍጥረት ሁሉ
ለምትራራ ከሁሉ በላይ በሆነች አምላክን በወለደች
በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ቁመን እንደለመንን
ልመናችንን ሰምታ የተመረጠ ልጅ ሰጠችን ብለው
አመሰገኑ፡፡የመንጻት ወራት በተፈጸመ ጊዜ በ40 ቀን
አባትና እናቱ በጸራ ወርቅና ብር ንጉስ ይኩኖ አምላክ ወደ
አሰራው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ወስደው አዳም
በ40 ቀኑ ወደ ገነት እንደገባ በቤተክርስቲያን ስርዓት
ተጠመቀ፡፡

አዳም በአርባ ሄዋን በሰማንያ ቀን ወደ ገነት
እንደገቡ ኩፋሌ 4፤9 ካህናትም መንፈስ ቅዱስ
እንዳናገራቸው ስሙን እስትንፋሰ ክርስቶስ ብለው ሰየሙት ስጋ ወደሙን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ የስሙም ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቀው አደገ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቦናውን ብሩህ አድርጎለት በ5 ዓመቱ የቅዱሳን መጽሐፍትን፣ ቃላትን ፣ብሉያትንና
፣ሐዲሳትንም፣ድርሳናትንም አወቀ፡፡ ከመምህር ኪራኮስ
የመፅሐፍትን ትምህርት ከነትርጓሜው በ7 ዓመቱ ጨረሰ፡፡

🍂 በማስተዋል ሲመለከት አባቱንና እናቱን ዘመዶቹን የተወ ቃሌን ይጠብቃል መንግስተ ሰማያትን ይወርሳል ይህን ያላደረገ ሊያገለግለኝ አይችልም የሚለውን አገኘ ማቴ
10፡37 ይህንንም ቃል በልቦናው ይዞ የምነናውን ስርዓት
ይጠብቅ ነበር፡፡ 7 ጊዜ በመዓልት 7 ጊዜ በሌሊት
በየዕለቱ 150 መዝሙረ ዳዊትን ሲያደርስ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊቱን በትምህርተ መስቀል አማትቦ
ጸሎት በጀመረ ጊዜ እጆቹን ሲዘረጋ ወጥመዳቸውን
ያጠመዱ አጋንንት በነፋስ ፊት እንዳለ ጢስ ተነው ይጠፋሉ

እየተሯሯጡም ፈጥነው ይሸሻሉ፡፡ ከዚህ በኃላ ስሙ
ማርቆስ ከሚባል ጳጳስ ድቁናን ተቀበለ፡፡ ልጄ
ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ
ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ እንዳለ ሲራክ 2፤1 ይህንን
አለም ናቀ፡፡ ልዩ ክብር የሚሆን የምንኩስናን ልብስ
ይቀበል ዘንድ በተወለደ በ 14 ዓመቱ ወደ ደብረ ሐይቅ
ገዳም ሄደ ከባህር ዳር ቆሞ የሙሴን ጸሎት ወደ
እግዚአብሔር ጸለየ ያለመርከብ ባህሩን ተሻግሮ ወደ
ቤተክርስቲያን ገባ፡፡የኢየሱስ ሞዐ ልጅ የሚሆን አበምኔቱ
በመነኮሳት መጽሐፍ እንደተፃፈ 3 ዓመት ፈተነው፡፡ በኃይቅገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት ያገለግል ነበር፡፡ከአባ ህንጻ ደብረ ድባ ከሚባል ቦታ የቅስና ስልጣን ተቀበለ፡፡

🍂 አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ለማስተማር ወደ
አባቶቹ ሀገር ወደ አባቱ መቃብር በገባ ጊዜ እዚያው ደርሶ
ቤተክርስቲያን ሰራ እለቱን ስንዴ ዘርቶ፣ወይን
ተክሎ፣ጽድንም ወይራን ግራርን ተክሎ በአንዲት ቀን
ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እለቱን አድርሷል፤ስንዴውን
ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሷል፡፡
ከእለታት በአንድ ቀን አባታችን በጸሎት ላይ ሳለ መልአኩ
ቅዱስ ሚካኤል ከብሩህ ደመና ጋር ወደ እርሱ መጥቶ
በደመና ጭኖ ከፈጣሪው ዘንድ አደረሰው፡፡ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱሳኖቹ እንዲባረክ
ካደረገ በኃላ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘው ወደ
ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ አድርሰህ አሳየው
አለው፡፡መላዕኩም እንደታዘዘው አደረገ፡፡መልሶም ወደ
ኢትዮጵያ ምድር ደብረ ዛብሒል ወደ ምትባል ቦታ
አደረሰው፡፡ ከዚያም ደርሶ ድንቅ ታምራትን አደረገ ውሃም
ከአለት ላይ እያመነጨ ህሙማንን ፈወሳቸው፡፡

በባህር ውስጥ ጠልቆ ዘወትር በሄደበት ሀገር ሀሉ
ሲጸልይየሚያርፍበትን ቦታና ስጋዬ የሚቀበርበትን ቦታ ግለጽልኝብሎ በጸለየጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተልኮ መጥቶ የአባትህ አባት ከሸዋ ሀገር መጥቶ ታቦተ እግዚአብሔር አብን ወደ አስተከለበት ወደ አባ ሙሴ ደብር ወደ አባትህና እናትህ ቦታ ዳውንት ምትባል ሀገር ሂድ ብሎ የእረፍት ቦታውን ነገረው፡፡ከዚያም ወደ ብዙ ገዳማት በመሄድ ቡራኬን ተቀበለ፡፡ ከአራት ዓመት በኃላ አረጋውያን መነኮሳትንተሰናበታቸው መርቀውት ተለያዩ፡፡

🍂 የኢትዮጵያን ገዳማትተዘዋውሮ እየጎበኘ ጎዣም ደረሰ ፤በዚያ እያስተማረ፣ እያጠመቀ የታመሙትን
እየፈወሰ፣የእውራንን አይን እያበራና ሙታንን እያስነሳ በዚያ ተቀመጠ፡፡ በባህር ውስጥም ገብቶ 9 ዓመት ለኢትዮጵያ ጸለየ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኃላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ይህችን ሀገር እና የኢትዮጵያን ህዝቦች ምሬልሃለሁ ከዚህች ባህር
ውጣ አለው፡፡ አባታችንም ከባህር ውስጥ ወጥቶ ተንበርክኮ ለጌታችን ሰገደ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማረፊያህ ቦታ ምስራቅ ወደ ምትሆን ወደ ዳውንት ሂድ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ አባታችንም በአስራሰባት ዓመቱ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄድበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ደረሰች፡፡ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸለየ አለቀሰ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ አላት ጸሐይም ወደ ኃላ ተመልሳ በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃል ቆመች ደብረ አሰጋጅ እንደገባ ጸሐይም አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ
እገባ ዘንድ ፍታኝ አለችው እግዚአብሔር ይፍታሽ ባላት
ጊዜ ገባች፡፡

🍂 እድሜው ሰላሳ ሦስት በሆነ ጊዜ ወደ ደብረ ድባው
አበምኔት መጥቶ ሚያዝያ ዘጠኝ ቀን ምንኩስናን ተቀበለ፡፡በዚያ ደንጋይ ፈልፍሎ ዋሻ አዘጋጀ፡፡ ሉቃስ የሳላት ከግብፅ የመጣች የድንግል ማርያምን ስዕል አስገብቶ የዋሻውን በር ዘጋ፡፡ ያለ ደቀመዝሙሩ ልብሰ ክርስቶስ
በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር አይገናኝም፡፡በዚህ ድንቅ ድንቅ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

15 Dec, 11:58


አምላከ #ቅድስት_አርሴማ
ከመከራ ሥጋ ከመከራነፍስ ይጠብቀን🙏🏻

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ ክብረት
📞 +251923075264

#ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopia #orthodox #viral #viralvideos #viralreels #viralpost #viralvideo #copy #ተዋህዶ #ethiopianorthodox #eritrea #eriterianorthodox #facebook #insta #instagram #instagramvideo #art #artgallery #artist #church #icon #iconic #image #photo #photography #photographer #iconographer #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

14 Dec, 18:13


የሰማዕቷ : ቅድስት : አርሴማ : ረድኤት : ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የቅድስት : አርሴማ : ቃልኪዳኗ : ሀገራችንን : ኢትዮጵያን : ከክፉ : ይሰውርል ።


ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
📞 +251913684351

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

14 Dec, 18:12


#በታኅሳስ_ወር_በ6ኛው_ቀን የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያኗ ቅዳሴ ቤቷ በአርማንያ ሀገር ፣ በኪልቂያ ፣ በሶርያ ፣ በአንጾኪያና በግብጽ አውራጃዎች ሁሉ ሆኗል።

« ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ » እንዳለ እግዚአብሔር አምላክ ለእናታችን ቅድስት አርሴማ ስለ አምላኳ ስትል ከብዙ ጽናትና ተጋድሎ በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ኪዳን ገባላት

« በእኔ ስም አምነሽ የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ ፤ በዓልሽን ያከበረ ፤ ዝክርሽን የዘከረ ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ » ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል ፡፡

በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ በገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው ፡፡

የሰማዕቷ : ቅድስት : አርሴማ : ረድኤት : ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የቅድስት : አርሴማ : ቃልኪዳኗ : ሀገራችንን : ኢትዮጵያን : ከክፉ : ይሰውርል ።

© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ ✍🏽 Daweit Tesfay
ታኅሳስ 6 20 17 ዓ.ም

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንደሳሉት
📞 +251913684351

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

11 Dec, 17:34


መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤ በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ።


ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

11 Dec, 17:32


መ ቅ ደ ሲ ቱ ን ፡ በ መ ቅ ደ ስ ፡ አ ስ ቀ መ ጧ ት

#ታኅሣስ_3_ቀን እመቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ የጀመረችበት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ የታየበት ለካህናቱና ለሕዝቡ ያስረዳበት ዕለት ናት ይህም እንዲት ነው ቢሉ

ሐና ከነገደ ይሁዳ የተወለደ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው አግብታ ስትኖር እንደ አያቶቿ መካን ሆነች በዚህ እያዘኑ ሳለ ሐና ቤተ እግዚአብሔር እጅ ነሥታ ስትመለስ ርግቦች ከዛፍ ሥር ልጆቻቸው ጋራ ሲጫወቱ አየች ።

« አቤቱ ፈጣሪዬ ሁሉን ሁለት ሁለት አድርገህ ፈጥረህዋል ለመሆኑ ባሪያህ እኔን ምን ብለህ ፈጥረሃታል ? ደንጊያ ብለህ ፈጥረሃታል ? ለእንስሳቱ ለአዕዋፉ ያልነሣህውን ዘር ለእኔ ለምን ነሣህኝ » ብላ ምርር ብላ አለቀሰች ከዚህም በውኋላ ሐናና ኢያቄም ሱባዔ ያዙ ስእለትም እንዲህ ብለው ተሳሉ።

« አቤቱ አምላካችን ሆይ ስድባችንን ብታርቅልን ልጅም ብትሰጠን ወንድ ልጅ ከሆነ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ያብላን ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መብራት አብሪ መሥዋዕት አቅራቢ እንዲሆን ለአንተ እንሰጣለን ።

ሴት ብንወልድ ውኃ ቀድታ እንጨት ሰብራ እንጀራ ጋግራ ትርዳን ትጡረን አንልም መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ እንድትኖር ለአንተ እንሰጣለን ብለው ብፅዐት ገቡ ። » የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸሩ አምላክ ልመናቸውን ሰምቶ ከስቶታ ሁሉ በላይ የሆነች ስጦታ እመቤታችንን ሰጣቸው ።

እመቤታችን የስእለት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋት ሄዱ ፡፡

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ ባለ ጊዜ ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ ፡፡

ዘካርያስ ለርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ መልአኩ ወደላይ ራቀበት የርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ ራቀበት ፡፡

ካህናቱና ሕዝቡም በሙሉ ተራ በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት ትታት እልፍ አለች ፡፡

ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት ፡፡

© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
Daweit Tesfay
ታኅሳስ 3 20 17 ዓ.ም

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /

📞 +251923075264

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

09 Dec, 18:27


“ነቢይ ዘከመ እሳት ⇨ እሳታዊ ነቢይ”
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥

"ወተንስአ ኤልያስ ነቢይ ዘከመ እሳት ወቃሉኒ ከመ ነድ ያውኢ ⇨ እሳታዊው ነቢይ ኤልያስ ተነሣ ቃሉም እንደ እሳት ያቃጥል ነበር" 【ሲራ. ፵፰፥፩】

መነሻችን የሚሆነው ጥያቄ ነው?
☞ [መኑ ውእቱ] ዘዐርገ በነደ እሳት በሰረገላት ወበአፍራስ ዘእሳት ?
በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረስ ወደሰማይ የወጣ ማነው?
ይህን ጥያቄ የሚያነሳው ሲራክ ብለን የምንጠራው ኢያሱ ወልደ ሲራክ ወይም ኢያሱ ወልደ አልዓዛር በመጽሐፉ ፵፰ኛ ምዕራፍ ቁጥር ፱ ላይ ነው።

በመጽሐፈ ሲራክ መቅድም ሊቃውንቱ ይኽን ነግረውናል
ሲራክ፦ ፀሐፊ ማለት ነው፤ ፀሐፊው ኢያሱ ወልደ አልዓዛር ወልደ ሲራክ ይባላል።
፶፩ ምዕራፎች ፦ በአቀራረቡ ከሰሎሞን መጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይነት አለው።
ይዘት ፦ ለመንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወታችን ጥበብና ምክር የሚሰጥ ነው።

ሲራክ ስለእሳታዊ ነቢይ ይጠይቃል፤
ማነው? በእሳት ተጠቅልሎ የተወለደ ፣ በእግዚአብሔር ቃል ሦስት ጊዜ ከሰማይ እሳት ያወረደ ፣ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ተጭኖ ወደሰማይ የነጎደ ማነው?
በዘይቤ መንፈሳዊ ትምህርትነትና ምክር በስፋት የያዘው ይኽ መጽሐፈ ሲራክ የእሳትን አስተማሪ ምሳሌነ አጉልቶ በብዙ መንገድ ይነግረናል ለአብነት
☞ ወርቅን ወርቅ ለመሆኑ የሚፈትኑት በእሳት እንደሆነው ሁሉ ጻድቅም ችግር በሚያመጣ መከራ ተፈትኖ የሚያልፍ ነው 【፪፥፭】
☞ የሚነድ’ እሳት የሚጠፋው በውኃ እንደሆነው ኃጢዓት የሚሰረየው በምጽዋት ነው 【፫፥፳፰】
☞ ከተናጋሪ ሰው ጋር መከራከር በእሳት ላይ እንጨት እንደመከመር ነው 【፰፥፫】
☞ መልከ መልካምና ደምግባት ያላት ሴት ፍቅር የሚነድ’ እሳት ነው 【፱፥፰】
☞ በነጻ ፈቃድ እንዲመርጥ ለሰው እግዚአብሔር ያቀረበው የጽድቅና የኃጢዓት መንገድ እንደ እሳትና ውኃ ነው 【፲፭፥፲፮】
☞ ሰው በልቡ ሐሳብ መፈተኑ ሸክላ በእሳት እንደሚፈተነው ነው 【፳፯፥፭】
☞ የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣው እሳት ነው 【፳፰፥፳፪】…

እሳት በጠባዩ ይቡስ (ደረቅ) ፣ ውዑይ (የሚያቃጥል) እና ብሩህ (የሚበራ) ነው። በፍጥረትነቱም ከዐራቱ አሥራው ፍጥረታትና ባሕርያት አንዱ ሆኖ በሁሉ የሚገኝ በይብስቱ ከነፋስ በውዕየቱ ከመሬት በብርሃኑ ከውሃ የሚስማማ ፍጥረት ነው።

ሲራክ ምዕራፉን የሚጀምረው የነቢዩን ማንነት እንዲህ ሲል ነግሮን ነው! "ወተንስአ ኤልያስ ነቢይ ዘከመ እሳት ወቃሉኒ ከመ ነድ ያውኢ ⇨ እሳታዊው ነቢይ ኤልያስ ተነሣ ቃሉም እንደ እሳት ያቃጥል ነበር" 【ሲራ. ፵፰፥፩】

አልያስ ማለት ቀናዒ
መደንግጸ አብዳን፡ ሕገ መነኮሳት ሠራዒ
ኤልያስ ማለት ድንግል
ብእሴ ሰላም ፡ መምህረ እስራኤል
ኤልያስ ማለት ቅብዓ ፍሥሐ
ለቤተክርስቲያን ፡ አንቀጸ ጽርሐ
ኤልያስ ማለት ካህነ ኦሪት
ምዑዘ ምግባር ፡ መዝገበ ሃይማኖት
ኤልያስ ማለት ጸዋሚ
ለእግዚአብሔር ቊልኤሁ ፡ ዝጉሐዊ ተሐራሚ

ኤልያስ ማለት…

ኤልያስ ቴስብያዊ ፣ ኤልያስ ቀርሜሎሳዊ ፣ ኤልያስ ታቦራዊ ፣ ኤልያስ ዘሰራጵታ፣ ኤልያስ ነቢየ ፋፃ … በኩረ ሐዋርያት ፣ ቢጸ ነቢያት ፣ ነቢየ ክርስቶስ ፣ ነቢየ ልዑል ባለብዙ ግብር ባለብዙ ስም …

የዚኽ እሳታዊ ነቢይ ስሙ እንዲህ የበዛው ሥራው ስለበዛ ነው "በአምጣነ ዕፁ ለእሳት የዐቢ ነዱ ⇨ በእንጨቱ ብዛት የእሳቱ ነዲዱ ይበዛል" እንዲል【ሲራ. ፳፰፥፲】

ወሬዛ በኃይሉ አረጋዊ በመዋዕሉ ተብሎ የተገለጠ ጸሐፌ ትዕዛዝ ቅዱስ ኤልያስ ጥር ፮ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ተጭኖ ወደሰማይ ያረገበት ቀን ፣ ታኅሳስ ፩ በአክአብ ፊት በኃይል ለዘለፋ የተገለጠበት(የናቡቴ ዕረፍት) ፣ «ነሐሴ ፳፬ ቀን ደግሞ ልደቱ» ነው፤ በእነዚኽ ቀናት ልንዘክረውና ልናከብረው ይገባል!

እንኳን እሳት ያወረደውን ቀርቶ የወረደውን እሳት ማክበር ተገቢ ነው ፤ አበው እንዴት መያዝ እንደሚገባው ሲነግሩን «እሳትን በገል ውሃን በቅል» ብለዋል።
ሙሴ አንደበቱ ትብ የሆነው እሳት በልቶ ፣ መጻጉዕ እጁ የተኮማተረው እሳት ጸፍቶ መሆኑን እናውቃለን።

ሊቁ እንዲህ ተቀኝቷል
"መጻጉዕ ሕፃን ኢያእመረ ነፍሰ ዓዲ
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

【 መጻጉዕ ሕጻን ነው ነፍስ ማወቅ መች ጀመረ ?
ቢበስልማ ኖሮ ወደሚነደው እሳት እጁን ባልጨመረ 】

ኤልያስ ማለት በእብራይስጡ (ኤል אֵל) እና (ያስ/ ያህ יָהּ)ከሚሉ ሁለት የፈጣሪያችን ስሞች የተገኘ ጥምረት ሆኖ "እግዚአብሔር ጌታዬ ነው" የሚለውን ፍቺ ይሠጣል። በቅዱሱ መጽሐፍም ከታላቁ ነቢይ ውጪ ሌሎች ሁለት እስራኤላውያን በዚህ የከበረ ታላቅ ስም ተጠርተዋል።

በግሪኩ ደግሞ ኤሊያ ἐλαία (አላህያህ) ማለት ወይራ ማለት ነው። ይህን ያዞ ጌታችን የወይራ ዛፍ በበዛበት ተራራ በደብረ ዘይት ሲጸልይበት የነበረውን ዋሻ የኤልዮን ዋሻ እያለ ይጠራዋል

“ወመዐልትሰ ይሜህር በምኵራብ ወሌሊተ ይወፅእ ወይበይት ውስተ ደብር ዘስሙ ኤሌዎን ⇛ዕለት ዕለትም በመቅደስ (በምኩራብ) ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን [ኤሌዎን በሚባል] ደብረ ዘይት ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር ” 【ሉቃስ ፳፩፥፴፯】

መጽሐፍም ኤልያስ ማለት ወይራ ማለት ነው የሚለውን ልሳነ ጽርእ ይዞ የወይራን ተክል ፍሬና ዘይትን ኤልያስ እያለ ይገልጣል (The tree , the fruit or the oil ☞ ዕፀ ዘይት ፣ ፍሬ ዘይት ፣ ቅብዐ ዘይት)

【ኩፋ ፲፯፥፲】 "ወነሥአቶ እሙ ወሐራዊ ወገደፈቶ ታሕተ አሐቲ ኤልያስ ወሖረት ወነበረት አንጻሮ መጠነ አሐቲ ምንጻፍ እስመ ትቤ ኢይርአይ ሞት ለሕጻንየ ወነቢራ በከየት ⇨እናቱ አነሳችውና ሔዳ በአንዲት የወይራ/ዘይት እንጨት ሥር አኖረችው የልጁን ሞት አላይም ብላለችና በዚያ ተቀምጣ አለቀሰች" (13፥31)

【ሔኖ ፫፥፳፬】 "ወአሕቲ መስፈርተ ኤልያስ ትገብር ዐሠርተ ምክያደ ዘይት ⇨አንዲቱም መስፈሪያ ዘይት አስር የዘይት አውድማንበትመላለች "

የእኛ ሊቃውንት ስሙን በዘይቤና በምሥጢር እያራቀቁ «ዕፀ ዘይት ማኅቶት በቅድመ እግዚአብሔር ፣ ሥዩም ላዕለ ምድር ወሥሉጥ ላዕለ ሰማይ ወላዕለ ማይ » በማለት ገልጠውልናል። በ«መልኩ» መነሻ ላይም
ሰላም ለትርጓሜ ስምከ ዘተብህለ ዘይተ
… በጸውኦ ስምከ ኤልሳዕ ዮርዳኖስ አዕተተ" ይላል

የቅዱስ ዮሐንስ ራእይ ቃልም ለእርሱ መነገሩን በምሥጢር አስማምተው ይተረጉማሉ።

"ዕፀ ዘይት ወመኃትው በቅድመ እግዚአብሔር "【ራዕ ፲፩፥፬】
አቡቀለምሲስ በዚህ የራእዩ ክፍል በአምላካቸው ፊት ወይራና መቅረዝ እያለ አክብሮ የጠራው ሔኖክና ኤልያስን ነው።
✧ ወክልኤ ዕፀ ዘይት እለ ቅድመ እግዚአብሔር
(በእግዚአብሔር ፊት ያሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የሚሆኑ ሁለቱ የወይራ ዛፎች) መባላቸው
☞ ሄኖክ ማለት ተሐድሶ(አዲስ መሆን) ማለት ነው።
ተሐድሶ በዘይት ነውና
☞ ኤልያስም ማለት ከላይ እንዳየነው ዘይት ማለት ነው።

ወክልኤ መኃትው እለ ቅድመ እግዚአብሔር
(በእግዚአብሔር ፊት ያሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የሚሆኑ ሁለቱ መብራቶች) መባላቸው
☞ በትምህርታቸው የሰውን ልቡና ብሩህ ያደርጋሉና

ነገረ ዘይት/ ወይራ ዛፍ (About Olive Tree)

ከዕለተ ሠሉስ ዕፀው መካከል ዕፀ ዘይት (የወይራ ዛፍ) አንዱ ነው! ቅባት የሚሰጥ ለመብልነት ለመብራትም የሚውል የወይራ ወገን ነው::

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

09 Dec, 18:27


* በሕገ ልቡና በሰብአ ትካት ለጥፋት ውኃ መወገድ በሰላም አብሣሪዋ ርግብ የመጣ ምልክት ይኼ ወይራ ነው! "ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ።" 【ዘፍ ፰፥፲፩】

* በሕገ ኦሪት ከምድረ ርስት ከነአን ገጸ በረከት አንዱ ይኼ ወይራ ነው! "ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥..." 【ዘዳ. ፰፥፰ በቤተ መቅደሱ ያሉ ሁለቱ ኪሩቤል የተቀረጸው : የመቅደሱ መግቢያ መቃን እና የቅድስተ ቅዱሳኑ ደጃፍ አምድ የተሰራው ከዚሁ ከወይራ ነው! 【፩ ነገሥ. ፮፥፳፫-፴፬】

* በሕገ ወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው ሌሊት ሌሊቱን ጌታችን የመረጣት የጸሎት ሥፍራ ምጽአቱን ያስተማረባትና ዕርገቱን የፈጸመባት ደብር የወይራ ዛፍ የበዛባትን ሥፍራ "ደብረ ዘይትን" ነው! 【ሉቃ. ፳፩፥፴፯】 ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።

በነገረ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ምሳሌነቱ

የወይራ ዛፍ የቤተ እግዚአብሔር መብራት ምንጭ ነው! የፈጣሪን ገጸ ምህረት ተወካፌ ጸሎትነት ያሳያል "አንተም መብራቱን ሁል ጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።" 【ዘጸ· ፳፯፥፳】
የወይራ ዛፍ ክር የሚነድበት ዘይት መገኛ ነው! ለእግራችን መብራት ለመንገዳችን ብርሃን የሆነ ህጉን ለሚያስተምሩ ምግባር ለሚያሰሩ አበው ምሳሌ ነው! "ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።" 【መዝ. ፻፲፰፥፻፭】
የወይራ ዛፍ በቤተ እግዚአብሔር ያማረ የተወደደ እንደሆነ እንዲሁ በሥላሴ ፊት ባለሟልነት በምዕመናን ዘንድ መወደድ በአጋንንት ዘንድ መፈራት ያላቸውን አበውን የመስላል! "ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ... ውበቱም እንደ ወይራ ይሆናል" 【ሆሴ. ፻፬፥፮】
የወይራ ዛፍ ብዙ ፍሬ እንዲያፈራ ባለ ብዙ ጸጋና ክብር የሆኑትን አበውን ይመስላል! " ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።" 【መዝ. ፻፳፯፥፫】
የወይራ ዛፍ ቀን ከአእዋፍ ሌሊት ከአራዊት በአጥር በቅጥር ተጠብቆ እንዲኖር በረድኤቱ በቤቱ ጥላ ተጠብቀው የሚኖሩ አበውን ይመስላል! "እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤" 【መዝ· ፶፩፥፰】

ለዚህ ነው የኢያሴንዩና የቶና ልጅ ኤልያስን ባለራእዩ ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፈ ቀለምሲስ «ዕፀ ዘይት ወመኃትው በቅድመ እግዚአብሔር » እያለ የሚጠራው። እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው። ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል። እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው። በረከታቸው በሁላችን ይደር !

🍁 [ኦ ኤልያስ] ; ብፁዓን ፡ እለ ፡ ያአምሩከ ፤ ወእለ ፡ ስርግዋን ፡ በፍቅርከ ፤ ወንሕነሂ ፡ ሕይወተ ፡ ነሐዩ ፡ (በእንቲአከ) ።

🍁 [ኤልያስ ሆይ] ; የሚያውቁህና በፍቅርህ ያጌጡ ሰዎች ብፁዓን ናቸው፣ እኛም ስለአንተ በሕይወት እንኖራለን።

🍁 [Oh Elijah] ; Blessed are they that saw thee, and slept in love; for we shall surely live.
【ሲራ ፵፰፥፲፩, Sirach 48:11】

መጽሐፍ እጅግ ማግነናችንን ከአምላክ ማስተካከላችን እንዳልሆነ ሲነግረን እንዲህ ይላል ⇨ አኮ ዘናስተአርዮ ምስለ ፈጣሪሁ አላ ናስተማስሎ በኵሉ ግብር ምስለ አምላኩ። ⇨ ከፈጣሪው ጋር የምናስተካክለው አይደለም በሥራዎቹ ሁሉ ከአምላኩ ጋር እናመሳስለዋለን እንጂ ⇨ We do not equate Him with the Creator, but we view him as an example of God in all his works.
አልያስ ፍጥረቱ እንደኛው መሆኑን “ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥” 【ያዕ፭፥፲፯】 ነገር ግን ከመጠን ይልቅ ማክበራችን ታዘንና ተለምነን መሆኑን ልብ ይሏል “ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። ”【፩ኛ ተሰ ፭፥፲፪】

አንድ #ማስተካከያ በማመልከት መልእክታችንን እንቋጫለን።

ኤልያስ የተወለደው በምን ቀን ነው?
መጽሐፈ ስንክሳራችን ታኅሳስ ፩ ቀን "የተገለጠበት ቀን” የሚለውን ይዘው ናቡቴ ባረፈበት ቀን ተወልዷል የሚሉ መምህራንና አድባራት ጭምር ይታያሉ፤ መገለጡ በጾመ ነቢያት በነቢይነቱ በ’ነ አክአብ ፊት ፣ በሐሳውያን ነቢያትና በካህናተ ጣኦት ዘንድ፣ በእስራኤላውያን መካከል… መሆኑን ለመግለጥ እንጂ መወለዱን የሚገልጥ እንዳልሆነ መጽሐፍ ያብራራል።
ታዲያ ልደቱ መቼ ነው ያሉ እንደሆነ «መልኩ» በዚሕ መልክ አስቀምጦታል

"…ኤልያስ እምከ ካልዕተ ሣራ ጠባብ
ልደትከ አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ
እንዘ ኩለንታከ በእሳት ግልቡብ …"

ከዚህ ውሥጥ «ልደትከ አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ»
አብ የተባለው ወርኅ የቱ ነው ብለን የአይሁድን ዜና መዝገብ ብንፈትሽ ታሪክ ጸሐፊው ዮሴፍ (Flavius Josephus ⇝Yoseph Ben Mattithyahu) እንዲህ በማለት የወሩን ቁጥር ጭምር ያመለክትልናል
"ወርኃ ኃምስ ወውእቱ ወርኅ ወርኃ አብ ⇨ አምስተኛው ወር እርሱም አብ የሚባለው ወር ነው"【መጽሐፈ ዮሴፍ ኮርዮን ፶፫፥፭】

ይህ በዕብራውያኑ አብ የተባለው ለሚያዝያ ፭ኛው ወር በእኛ ደግሞ ወርኃ ነሐሴ ነው፤ ስለዚህ የኤልያስ ልደቱ "አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ" ባለው መነሻ ነሐሴ ፳፬ ይውላል ማለት ነው።

“እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።”【ሚል ፬፥፭ 】

#የቅዱስ_ኤልያስ_በረከቱን
#አምላካችን_ለሁላችን_ይላክልን 🙏

✍️ ከቴዎድሮስ በለጠ ታኅሳስ ፩/፳፻፲፮ ዓ.ም. ( Edited & Яερ๑šтεd ƒr๑๓ ጥር ግዝረት ፳፻፲፭ ከእንጦጦ ርእሰ አድባራት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አልያስ ወኤልሳዕ)

መጋቤ ሐዲስ Tewodros Belete Mengistu
የታላቁ ነቢይ የቅዱስ ኤልያስ ረድኤተ አይለይዎ
በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማልን 🙏🏾🙏🏾🙏🏾

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንዲህ ወብ አድርገው ሥለውታል

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

06 Dec, 17:18


🍂 #ቅዱስ_አማኑኤል 🌹
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ

አቤቱ ቸርነትህ ፈጥና በላያችን ትደረግ
የፊትህም ብርሃን በሰውነታችን ይገለጽልን

🍂
የሚያድነን ይቅርታህ በቸርነትህ ይምጣ ይደረግልን
ደስ የሚያሰኘን ቸርነትህም ይገለጽ
አቤቱ ከከፉ ነገር ከስህተትም ጠብቀን
ተመለሱ እመለስላችኋለው ብለህ በረድኤት ተቀበለን

🍂
በእኛና በአንተ መካከል ያለውን ፍቅር አንድነትን ይቅርታህን አድርግልን ፤
የበደለውን ሰው በንስሐ ወደአንተ መመለስ ይቻልኻልና
ሥፍር ቁጥር በሌለው በቦታህ ሁሉ እንሰግድልሀልን

🍂
ጩኸን አሰምተን በለምንን ወደ አንተ በለመንን ጊዜ
አንተ ትሰማናለህና
የሰውነታችንንም ድካም ትሸከምልናለህ ፤ ታቀልልናለህ
ኃጢአታችንንም ትታገሠናለህ

አቤቱ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር
መሐሪ ይቅር ባይ ነህ ፤ 🙏🏽

+_+_+_+_+_+_+_+_+_

/ ሊጦን ዘረቡዕ /

…………………
መዓትህ የራቀ
…………………..
ምህረትህ የበዛ
…………………………………………..
አምላካችን ቅዱስ አማኑኤል ሆይ
…………………………………………………
እንደ በደላችን ሳይሆን እንደቸርነትህ

ማረን
ራራልን
ይቅርም በለን
🙏🏾
…………………………………..

#ሥዕለ_ቅዱስ_አማኑኤል
#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሣሉት
@seali_kesis_amare_kibret

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /
+ 251923075264

@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

05 Dec, 18:59


+ + አቤቱ ጌታዬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ + +
ከቤተ ያዕቆብ የወጣ የዘይት ዛፍ
ከዕሴይ ሥር የወጣ የሃይማኖት በትር፤
ከዳዊት ግንድ የበቀለችም አበባ ነኽ (ኢሳ ፲፩፥፩)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በቅዱሳን አንደበት አንተ የሚጣፍጥ ስም ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በእውነት ለሚጠሩኽ አንተ የሚጣፍጥ ዕሳቤ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
አንተ መንፈሰ ኮከባቸው ለደበዘዘባቸው መመኪያ የኾንኽ የአጥቢያ ኮከብ ነኽ (ዘኊ ፳፬፥፲፯፤ ራእ ፳፪፥፲፮)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቅዱሳን ገጽ ላይ ዘወትር የሚያበራ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ (ሚል ፬፥፪)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከቊጣው የተነሣ የጨለማ አበጋዞች የደነገጡለት፤ ከማግሣቱም የተነሣ የምድር ተራሮች የተንቀጠቀጡለት ከይሁዳ ነገድ የተገኘ አሸናፊ አንበሳ ነኽ (ራእ ፭፥፭)

___
+ #አቤቱ_ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ከሕፃንነቴ ዠምረኽ ተስፋዬ አንተ ነኽ፤

+ በማሕፀንኽ አንተ ሰወርኸኝ በኹሉም ጊዜ አንተ ዕሳቤዬ ነኽ ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የመድኀኒቴ ቀንድ አንተ ነኽ

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የራሴ አክሊል አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለአፌ ጣፋጭ የኾንኽ የሕይወት እንጀራ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለጒረሮዬ
መልካም የኾንኽ የመድኀኒት ጽዋዕ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ያልተሸመነም ያልተፈተለም ልብስ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ዕጥፍ የኾንኽ ወርቅ የተገኘኽም ዕንቊ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
የበዛ ምናን የተረፈም መክሊት አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ አዳምና ስለ ልጆቹ ስትል መከራን የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በሔዋንና በልጆቿ ስሕተት ምክንያት የመስቀልን ሕማማት የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ሰው ልጆች በደል ስትል የመስቀልን ችንካሮች የተቀበልኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ አንተ በኹሉም ላይ ጌታ ነኽ፤
ሥልጣንኽም በኹሉም ላይ ነው፤
ታላቅነትኽም ከኹሉም በላይ ነው፤
የኹሉም ጌታ ተባልኽ፤
በኹሉም ዘንድ ተጠራኽ፤

__
+ አንተ #ሊቀ_ካህናት ነኽ፤
+ አንተ ንጉሠ ነገሥት ነኽ፤
+ አንተ ታላቅ መምህር ነኽ፤
+ አንተ የእረኞች አለቃ ነኽ፤
+ አንተ የምትናገር በግ ነኽ፤ አንተ ፍሪዳ ላም ነኽ፤
+ አንተ የአንበሳ ልጅ አንበሳ ነኽ፤
+ አንተ የሕይወት ውሃ ምንጭ ነኽ፤
+ አንተ #የመድኀኒት_ቀንድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅና የሕይወት መንገድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ፤
+ አንተ የብርሃን ኮከብ ነኽ፤
+ አንተ #የሕይወት_እንጀራ ነኽ፤
+ አንተ የመድኀኒት ጽዋ ነኽ፤
+ አንተ የሰው ልጅና የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ፤
___
ይኽነን ኹሉ ስለ እኛ ፍቅር ስትል ተጠራኽበት) በማለት አምላኩ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰገነው ምስጋና እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲነበብ፣ ሲተረጐም፣ ሲመሰጠር ይኖራል፡፡

ዮሐንስ በራዕዩ ላይ በኲረ ሙታን (ራእ ፩፥፭)፤
የምድር ነገሥታት ገዢ (ራእ ፩፥፭)፤
የታመነው ምስክር (ራእ ፩፥፭)፤
የይሁዳ አንበሳ (ራእ ፭፥፭)፤
የታረደው በግ (ራእ ፭፥፲፪)፤
የታመነና እውነተኛ (ራእ ፲፱፥፲፩)፤
የእግዚአብሔር ቃል (ራእ ፲፱፥፲፫)፤
ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ (ራእ ፲፱፥፲፮)፤
አልፋና ኦሜጋ (ራእ ፳፪፥፲፫) ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የዳዊት ሥርና ዘር (ራእ ፳፪፥፲፮)፤
የሚያበራ የንጋት ኮከብ (ራእ ፳፪፥፲፮)
-------------------------------------------
/ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /

#ጌታችን_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ዘወትር እናመሰግንህ ዘንድ
ውሳጣዊ አዕምሯችንን ብሩህ አድርግልን ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

04 Dec, 08:35


🍂 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕት
ህዳር 25 በዓለ ዕረፍቱ

✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ የነበረበት ዘመን በሶስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ንጉስ ዳክዮስ የሮም ገዥ ሆኖ የነገሰበት ዘመን እንደመሆኑ በዘመኑ የተከበረ የተባለ የውትድርናን ትምህርት ተምሮ ለንጉሱ አገልጋይ ሁኖ ነበር ።

✝️ አባቱ በአደን ላይ ሳለ ሊበሉት ከመጡ ገጸ ከለባት እግዚአብሔር ስላዳነውና እንዲያውም አገልጋዮች ስላደረጋቸው በዚህ ተአምር መነሻነት ቤተሰቡ ሁሉ በክርስትና ሐይማኖት አምነው ተጠምቀዋል ።

ከጥምቀት በኋላ
አባቱ ✝️ ኖኅ
እናቱ ✝️ ታቦት
ተብለው ተሰይመዋል

✝️ቅዱሱም ፕሉፓዴር ከሚባል ከቅድሞ ስሙ መርቆሬዎስ ተብሏል። ትርጓሜውም የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው።

🍂 ባርባርያን በሮም ላይ በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ የጦር አዛዥ ነበርና የእግዚአብሔር መልአክ በሰጠው ሰይፍ በመዋጋት ድልን ተቀዳጅቷል። የባርባርያንን ንጉሥም ገድሎታል።

🍂 ንጉስ ዳኬዎስ ግን “ ድልን የሰጡን ጣዖታቴ ናቸው። “ በማለት ለጣዖታቱ በዓል አደረገ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ይህንን ድርጊት በአደባባይ ተቃወመ በንጉሱም ፊት ትጥቁንና ልብሱን ማዕረጉንም አውልቆ ወረወረው።

🍂 በዚህ የተቆጣው ንጉሡም በወታደሮች አስይዞ መከራን ያደርሱበት ዘንድ ወደ ቂሳሪያ ( ቀጰዶቅያ ) ላከው ።በዚያም የሰማዕትነት ስቃይን ከተቀበለ በኋላ ፦

✝️ በኅዳር 25 ቀን አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ ።

✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከዕረፍቱ በኋላ ጸሊም (ጥቁር) የሆነ ፈረሱ ለሰባት ዓመታት በየሀገሩ እየዞረ ስለ ክርስቶስ መስክሯል።

✝️ በንጉሡ በዑልያኖስ ዘመን ክርስቲያኖች መከራና ስቃይ በበዛባቸው ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በቅዱስ መርቆሬዎስ #ሥዕል ፊት ሲጸልዩ ሳለ
“ #አድነነ_ሥዕል_ከመ_ዘይብል_ኦሆ “
/ #ስዕሉም_እንደሚታዘዝ_ዘንበል_አለ።/

🍂በስእሉ ላይ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሀዲውን ንጉስ ዑልያኖስን ሲገድለው ከጦሩም ጫፍ ትኩስ ደም ሲንጠባጠብ ታየ።
ባስልዮስና ጎርጎርዮስም ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እጅግ ተደሰቱ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሐዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን ስላጠፋላቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ ።

🙏🏽የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን
ከመከራ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏🏽

👉🏻#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እንደሣሉት


ዲያቅን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

01 Dec, 07:59


መልካም ልደት ለእኔ ህዳር ጽዮን

አአኵተከ ፡ እግዚኦ ፡ አምላኪየ ፡
ዘልፈ ፡ ዘወሀብከኒ ፡ ኃይለ ፡ ወጥበበ ፡
እስመ ፡ ናሁ ፡ ዘይሁብ ፡ እምረተ ፡ ለልቡባን ፡
ጥበበ ፡ ለጠቢባን ፡ እምብዕለ ፡ ፀጋሁ ።

"ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች የሰጠ ፤ የሚሰጥ ዛሬም ጥበብና ኃይልን. . . . . የሰጠኸኝ የአባቶቼ አምላክ አመሰግንሀለው ።"
( ት.ዳን 3÷ 21-24 )

"እገኒ ለከ እግዚኦ እስመ ግሩመ ተሰባሕከ መንክር ግብርከ ወነፍስየ ትጤይቆ ጥቀ......"
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥርያለኹና አመሰግንሃለው

ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ታውቀዋለች
እኔ በስውር በተሰራኹ ጊዜ አካሌም ከምድር ታች
በተሰራ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም

#ያልተሰራ_አካሌን_ዐይኖችህ_አዩኝ
#የተፈጠሩ_ቀኖቼ_ኹሉ
#አንድ_እንኳን_ሳይኖር_በመጽሐፍህ_ተጻፉ

አቤቱ ዐሳቦችህ በእኔ ዘንድ
እንደ ምን እጅግ የከበሩ ናቸው
( መዝ 138፥14-17 )
~~~~~~~~
🍂
እንድንከባት፣ እንድናቅፋት፣ በዙሪያዋ ተሰብስበን እንድንመካባት፣ በብርታቶቿ ተማምነን ልባችንን እንድናሳርፍባት፣ ጽዮን አንባችንን፣ ጽዮን መታመኛችንን፣ ጽዮን መመኪያችንን የሰጠን አምላክ ይክበር ይመስገን!!!

🙏🏽......ለአመቱ በሰላም በጤና ያድርሰን ....🙏🏽

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

ህዳር ጽዮን ( 21 )
November 30

📸 💎LEGACY IMPRESSION ®
☎️+251984187946☎️
📸BOOK NOW📸
@Legacy Impression

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

25 Nov, 18:14


#የቀዳሜ_ሰማእት_የቅዱስ_እሥጢፋኖስ ረድኤት በረከት አይለየን።
በአማላጅነቱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን
🙏🏾 🙏🏾 🙏🏾


ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalew
0923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

24 Nov, 07:36


“ሰላም ለሚናስ ኅሩይ ዘክርስቶስ ሐራይ
ጽድቀ ዘአብደረ እምነ ንዋይ፤
አምሳለ ወርኅ ወከመ ፀሓይ ብሩህ”፡፡

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

24 Nov, 07:35


በምልጃው ፈጥኖ በመድረስ የሚታወቀው
#ቅዱስ_ሚናስ ኅዳር 15 በዓለ ዕረፍቱ

#ቅዱስ_ሚናስ በመላው ዓለም በተለይ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእጅጉ የሚወደድና ተአምር አድራጊ ሲጠራ ፈጥኖ የሚደርስ "ገባሬ ተአምር ወመንክር" (wonder-worker) በመባል የሚታወቅ ሰማዕት ነው። በተማፀኑት ጊዜ በምልጃው ፈጥኖ ነው የሚደርሰው፡፡

ይኸውም ከደጋግ ቤተሰቦች የተገኘ ሲኾን አባቱ ኢዩዶክሲዮስ፤ እናቱ ኢዩፎሚያ ትባላለች። ልጅ ስላልወለደች በእመቤታችን በዓል ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላት በሥዕለ ማርያም ተማፀነቻት፤ ያን ጊዜ ከእመቤታችን ሥዕል አሜን የሚል ቃል ተሰማ፡፡

ከዚያም ይኽነን ለባሏ ነገረችው፤ ከዚያም እግዚአብሔር የተባረከውን ልጅ በ285 ዓ.ም ላይ ሰጣት፤ ስሙንም ከእመቤታችን ሥዕል “አሜን” የሚል ቃል ስለተሰማ ርሱንም ሚናስ ብለው ሠይመውታል፡፡

ዜና ገድሉ Mina was his original name, according to the story his mother called him "Mēna" because she heard voice saying amēn. Minas [Μηνας] is how he is known in Greek, while in Armenian and Arabic he is known as "Mīna" [مينا].
ይላል፤ እነርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በስፋት አስተማሩት፤ በዐሥራ ኹለት ዓመቱ አባቱ ሲያርፍ ከሦስት ዓመት በኋላ እናቱ ዐርፋ ቅዱስ ሚናስ ብቻውን ቀርቷል፤ ከዚያም መኳንንቱም አባቱን ይወድዱት ስለነበር በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት፡፡

ዲዮቅልጥያኖስ ክርስቶስን በካደ ጊዜ ቅዱስ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገብቶ ተጋድሎን ዠመረ፤ ከዕለታት ባንዳቸው ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊልን ሲቀዳጁ ተመለከተ ከዚኽ በኋላ ወደ ከተማ ተመልሶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ መኰንኑ ቅዱስ ሚናስ በወገን የከበረ መኾኑን ያውቃልና ብዙ የሹመት ቃል ኪዳን ቢገባለትም ከክርስቶስ ፍቅር ሊለይ እንደማይችል ነገረው፨

ያን ጊዜ ብዙዎች ሥቃያት አድርሶበት ስለሰለቸው ራሱን በሰይፍ እንዲቈርጡት አዝዞ ከክርስቶስ ቃል ኪዳን ተቀብሎ ኅዳር ዐሥራ ዐምስት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ፤ በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ለሚጠሩት በምልጃው እጅግ ፈጥኖ ይደርስላቸዋል።

የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጅ ከሰማይ “ሚናስ ንኡድ ክቡር ነኽ፤ ከልጅነትኽ ዠምሮ የቅድስናን ሕይወት በመምረጥ ሦስት አክሊላትን ሰጥቼኻለኊ፤ አንደኛው ስለቅድስናኽ፣ ኹለተኛው ስለ ብቸኝነትኽ፤ ሦስተኛው ስለ ሰማዕትነትኽ” የሚል ድምፅን ከጌታችን ሰምቷል፡፡

ከዚያም መኰንኑ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ወደ እሳት እንዲጣል ቢያስደርግም እሳት ለ3 ቀናት ፈጽሞ ሥጋውን ሊነካ አልቻለም፤ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ባማሩ ልብሶች ገንዘው አኖሩት፤ የመርዩጥ አገር ሰዎች ሰራዊትን ሊአከማቹ ስለወደዱ ምልጃው ይረዳቸው ዘንድ የቅዱስ ሚናስን ሰውነት ወሰዱ፤ እነርሱም በባሕር በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያሉ አውሬዎች ከባሕር ወጥተው አንገታቸውን ወደ ሚናስ ሥጋ በዘረጉ ጊዜ ከሰውነቱ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጥላቸዋለች፤ ሰዎቹም ይኽነን አይተው በእጅጉ ተደንቀዋል፡፡

ወደ እስክንድርያ ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከርሳቸው ጋር ሊወስዱ ወድደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ኾነ፤ ኹለተኛም ሌላ ገመል ቢጭኑ ርሱም የማይነሣ ኾነ፤ ስለዚኽ ዛሬ ድረስ የቅዱስ ሚናስ ሥዕል ሲሳል እነዚኽ ገመሎች አብረው ይሳላሉ፤ እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት ቦታ መኾኑን ዐውቀው የከበረ ሥጋውን በዚያው አኖሩት፤ ከዚያም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለት ሠኔ 15 ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተፈጽሞ ብዙዎች ድንቆች ተደርገዋል።

ብዙዎች ሕሙማን የከበረ ሥጋውን እየዳሰሱ ሲፈወሱ በቦታው ሳለኊ በዐይኖቼ ተመልክቼያለኊ፤ ዛሬም የከበረ ዐፅሙ በግብጽ ይገኛል፤ እኔም ለሐዋርያዊ አገልግሎት ግብጽ በኼድኩበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ በወርቃማ መጎናጸፊያ የተቀመጠ የቅዱስ ሚናስን የከበረ ሰውነቱን ለመዳሰስና ለመጸለይና ሻማ ለማብራት ችያለኊ፡፡

ቦታው እጅግ የከበረ መኾኑ ሊታወቅ እመቤታችን በጸሎት ለሚማፀኗት ከቅዱስ ሚናስ ጋር በመገለጽ እንደምትባርካቸው ይነገራል።

በግብጽ ያሉ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ቅዱስ ሚናስ ከጌታችን በተቀበለው ቃል ኪዳን በተማፀኑት ጊዜ ፈጥኖ ስለሚደርስላቸው በእጅጉ ይወዱታል፤ በተለይ ከአቡነ ሺኖዳ በፊት ለነበሩት በቅድስና ሕይወታቸው ይታወቁ ለነበሩት ለአቡነ ቄርሎስ ቅዱስ ሚናስ ተገልጦላቸው እንደባረካቸው ይነገራል፨

ከጥቂቶች በቀር በዚኽ ዘመን ያለን ብዙዎቻችን ስለዚኽ ሰማዕት ታሪክ ስላላወቅን በቃል ኪዳኑ መጠቀም አቅቶናል፤ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን ኢትዮጵያ ከባሕር ዳር 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከአቡነ ሐራ ድንግል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ እንዳለ ሰምቼያለሁ፤ ይኽም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፨

ቅዱስ ያሬድ በድጓው

“ብፁዕ አንተ ሚናስ ዘመነንከ ክብረ ዘበምድር ወኀረይከ ዘበሰማይ ወኮንከ ሐራሁ ለክርስቶስ”
(የምድር የኾነ ክብርን ንቀኽ የሰማይ ክብርን የመረጥኽ የክርስቶስ ጭፍራው የኾንኽ ሚናስ አንተ ንኡድ ክቡር ነኽ)፡፡

“ሚናስ ኅሩይ በታዕካ ሰማይ ገጹኒ ብሩህ ከመ ፀሓይ በብዙኅ ሰላም አዕበዮ እግዚአብሔር”
(በሰማይ አዳራሽ የተመረጠው ሚናስ፤ ፊቱም እንደ ፀሓይ ብሩህ ነው፤ ብዙ በኾነ ሰላም እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው) ይለዋል (ድጓ ዘሚናስ)

ሊቁ ዐርከ ሥሉስ
ይኽነን የቅዱስ ሚናስን ተጋድሎውን፦

“ሰላም ለከ ሐራዊ መስፍን
ሰማዕተ መድኅን
ዘሰመየተከ ሚናስ ዘጾረተከ ማሕፀን
አመ ጸለየት ጸሎተ እንዘ ይእቲ መካን
እምሥዕለ ማርያም ሰሚዐ ዘይቤ አሜን”

(መካን ሳለች ጸሎትን እየጸለየች ሳለች ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል አሜን የሚልን ቃልን ሰምታ የተሸከመችኽ ማሕፀን ሚናስ ብላ የሰየመችኽ የመድኅን ክርስቶስ ምስክር፤ የጦር መኰንን ለኾንኽ ላንተ ሰላምታ ይገባል) በማለት ቅዱስ ሚናስን አወድሶታል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-

“ሰላም ለሚናስ ኅሩይ ዘክርስቶስ ሐራይ
ጽድቀ ዘአብደረ እምነ ንዋይ፤
አምሳለ ወርኅ ወከመ ፀሓይ ብሩህ”፡፡

(የክርስቶስ ምርጥ ጭፍራ ከገንዘብ ይልቅ ጽድቅን የመረጠ እንደ ምሳሌው እንደጨረቃ ለደመቀና እንደ ፀሓይም ብሩህ ለኾነ ለሚናስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፡፡

የቅዱስ ሚናስ ረድኤት በረከት ይደርብን 🙏🏽

ምንጭ : መጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዶስ ታዳሰ

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
📞 0923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

19 Nov, 17:56


ተፈጸመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ
ተፈጸመ ሐና በወለትኪ።

" ሰለም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ።
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ።

#ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ።
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ።
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ"።


👉🏻 #ሠዐሊ_ቀሲስ አማረ_ክብረት እንደሳሉት 📞 0913684351

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

19 Nov, 17:52


🍂 አምላክን ለወለደች ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም እናት የሆነች የተመሰገነች #የቅድስት_ሐና የዕረፍቷ በዓል ነው ህዳር 11

#ቅድስት_ሐና ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት።

ለማጣትም ሦስት ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት። ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥ ወለደቻት።

ይችንም #ቅድስት_ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ #ኢያቆም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

ቅድስት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን #የተባረከችና #የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ቅድስት ሐናና ቅዱስ ኢያቄም ስእለታቸውን የሚሰጡበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ ሳይሰስቱ ለእግዚአብሔር ቤት እንድታገለግል ሰጧት፤ ቅድስት ሐናም ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በኋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለአምስት ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት ትስማትም ነበር።

🍂 #እመቤታችን ስምንት ዓመት በሞላት ጊዜ ግን
የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ #ቅድስት_ሐና ደረሰ።
ከክርስቶስ ልደት ስምንት ዓመታት አስቀድማ
ብፅዕት እናት ቅድስት ሐና በኅዳር ፲፩ ቀን ዐረፈች።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት
የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባል። 🙏🏽

“ #ሰለም_ለኪ_ለጸሎተ_ኵሉ_ምዕራጋ።
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ።
#ሐና_ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ።
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ።
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ”።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን 🙏🏽
በቅድስት ሐና በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም 🙏🏽
ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። 🙏🏽

👉🏻 #ሠዐሊ_ቀሲስ አማረ_ክብረት_እንደሳሉት
📞 0913684351

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

19 Nov, 11:28


የቅድስት ሃና ሥዕል
ህዳር 11 በዓለ ዕረፍቷ

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
0923075264

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

17 Nov, 07:34


✣ #_አርባዕቱ_እንስሳ  ✢ #ህዳር_8 በዓላቸው
      መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ
               አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ
 
🍂አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን🍂
                      ሰዐሉ በእንቲአነ
      ( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )  

                    #_ኪሩቤል
                          🔥 ገጸ ሰብዕ
                          🔥  ገጸ አንበሳ
     #_ሱራፌል
          💥 ገጸ ላህም
          💥  ገጸ ንስር

👉 ገጸ ሰብዕ ፦ ስለ ሰው ልጆች ይለምናል
      ገጸ አንበሳ ፦ ስለ አራዊት ይለምናል
      ገጸ ላህም ፦ ስለ እንስሳት ይለምናል
      ገጸ ንሥር ፦ ስለ አዕዋፍ ይለምናል
( ሥንክሳር ኅዳር 8 ፥ ቁጥር 17 )

🔥 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
     አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

     ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
         ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
        ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
        ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔥  አርባዕቱ አንስሳት
                 የጳጳሳት
                 የቀሳውስት
                 የዲያቆናት
                የምዕመናን
   ( የቤተ ክርስቲያን አምድ እኚህ ናቸውና )

   🔥 የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።

            ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
                  ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
                   ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
                    ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔥አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።
    
🔥 “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።”
   ( ራእይ 4፥8 )

  🔥 #አርባዕቱ_እንስሳት
     #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ።
   እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤  ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።  

ወርኃዊ መታሰቢያ በዓላቸው  በ 8 ነው።

🙏🏽 በረከት ረድኤታቸው አይለየን 🙏🏽

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

16 Nov, 10:16


✍️🎨ቃልሽን ሰምቶ ጽንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነውሬ ተወገደ
የጌታዬ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይኸው ባረከችኝ

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

#ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopia #orthodox #viral #viralvideos #viralreels #viralpost #viralvideo #copy #ethiopianorthodox #eritrea #eriterianorthodox #facebook #insta #instagram #instagramvideo #art #artgallery #artist #church #icon #iconic #image #photo #photography #photographer #iconographer

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

01 Nov, 16:44


የ #ቅዱስ_ኡራኤል መማመጸኛ ሥዕል

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
0923075264

Created by ; @qagnewcreatives

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

31 Oct, 06:07


🌹 እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ንዒ #ማርያም ልጅሽን ታቅፈሽ እመቤቴ ሆይ ነይ #ማርያም

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
0913684351

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

29 Oct, 07:01


ቅዱስ ገብርኤል
ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
0923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

28 Oct, 17:16


#ገብርኤል #ገብርኤል መልአከ ራማ ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እናስማ

+ ጸሎት ልመናችንን +
🍂 ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል ተቀብሎ
ለሁላችን ፍቅር አንድነትን ያድለን

ከመከራ ሥጋ ከመራ ነፍስ
በክንፈ ረድኤቱ ይጠብቀን
🙏🏽 #አሜን 🙏🏽

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞 +251923075264
t.me/deacongetabalewamare

Created by ; @qagnewcreatives

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

26 Oct, 18:32


🍂 + #ከሽፍቶቹም_አንዱ ጌታችንን በራሱ ተሸክሞ እንደሸኛቸው እንዲሁም ጌታችን የተሰበረ ሰይፉን እንደቀድሞ እንዳደረገለት የሚናገር ተአምር

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

26 Oct, 18:32


🍂 + #ከሽፍቶቹም_አንዱ ጌታችንን በራሱ ተሸክሞ እንደሸኛቸው እንዲሁም ጌታችን የተሰበረ ሰይፉን እንደቀድሞ እንዳደረገለት የሚናገር ተአምር

በጐዳና ሲሄዱ ሁለት ወንበዴዎች አገኙዋቸውና አስፈራሯቸው #አንደኛው_ወንበዴ_ግን_ልቡ_ራራና_ሕፃኑን_ከእናቱ_ክንድ_ወስዶ_ዓይኖቹን_ጐንጮቹን_እጅ_ነሣቸው።

🍂ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ሲጓዝ ወንበዴው በፊት ለፊት እየሄደ መንገድ ይመራቸው ነበር። በዚህም ያ ጊዜ ያ ወንበዴ በእንቅፋት ሲሰነካከል ሰይፉ ከድንጋይ ላይ ወደቀና ከሦስት ቦታ ላይ ተቆራረጠ ።

🍂ሕፃኑም #ጥጦስ ሆይ ፤ የሰይፍህን ስብርባሪ ሰብስበህ አምጣ አለውና መንበዴው ጥጦስም ስብርባሪውን ሰብስቦ ሰጠው። በዚህም ጊዜ ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስ ከርስቶስ ስብርባሪውን አገጣጠመና እንደቀድሞ አድርጐ ሰጠው።

🍂+ወንበዴውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰበረውን ሰይፍ ቀድሞ እንደነበረ አድርጎ ስለ ሰጠውና አስቀድሞ የማያውቀውን ስሙን አውቆ በስሙ #ጥጦስ ብሎ ስለጠራው ፈጽሞ አደነቀ ። አመስግኖም ሰገደለት ።

🍂+ዮሴፍም ወንበዴውን እየሸኘው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እጅ ይዞ በወንበዴው እራስ ላይ ጫነው ። ወንበዴውም ተጐንብሶ አቤቱ ጌታየ ሆይ በኔ ላይ ቸርነትህን አሳድረህ ባርከኝ አለው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ አዳምን ቀድመኸው ወደ ገነት እንድትገባ ዕውነት እልሃለሁ ቁልፉም ከአብ ዘንድ ይሰጥሃል አለው።

🍂 ከወንበዴዎቹ አንዱም ይህን አነጋገር ሰምቶ ሳቀበት ተቀጸጸበበትም ፤ይህን ባለ ዘመኑ ሁሉ የሰው ደም ሲያፈስ የኖረ ወንበዴ ከአዳም ቀድሞ በገነት ይገባል ። መክፈቻውም ይሰጠዋል ማለቱ በዕውነት ከደቂቀ ነቢያት ወገን ቢሆን ነውን ብሎ ዘበተበት ።

🍂+
የተማረ የሆነ የወንበዴዎች አለቃም መልሶ #በዕውነት_የዓለም_መድኃኒት_ክርስቶስ_የተባለ_ይህ_ሕፃን_ነው ። እናቱም ይህቺ ድንግል ናት አለው ። ከዚህም በኋላ ተለያይተው ወደየበዓታቸው ሄዱ ። ዮሴፍ ግን ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ናዝሬት ሄደ ። የሰማይና የምድር አምላክ በመጣ ጊዜ ናዝራዊ ይባላል ሲል ነቢዩ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ አለውና።

🍂+
ግብጻዊው ነቢይም እግዚአብሔር በኋለኛው ዘመን በናዝሬት በተገለጸ ጊዜ መንግሥትን ፤ ክህነትን ትንቢትንም ከእሥራኤል ልጆች ወስዶ ገንዘብ ያደርጋል ፤ እነሱን ግን በዓለም ላይ ይበትናቸዋል ። ከዚያም ተመልሰው በቀደመ ሥርዓታቸው ጸንተው ሊኖሩ አይችሉም ብሏልና።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ናዝሬት ገብተው በተቀመጡበት ጊዜ ታላላቅ ተአምራትን ማድረግ ጀመረ ። / ተአምረ ኢየሱስ /


ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ፦ አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ ሰደበው።

#ሁለተኛው_ግን መልሶ፦ አንተ እንደዚህ ባለ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን?

ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

ኢየሱስንም፦
#ጌታ_ሆይ_በመንግሥትህ_በመጣህ_ጊዜ_አስበኝ_አለው።

ኢየሱስም፦
#እውነት_እልሃለሁ_ዛሬ_ከእኔ_ጋር_በገነት_ትሆናለህ_አለው።

( ሉቃ 23 ፥ 39 - 43 )

🍂 ይቅርታው ቸርነቱ ለዘላለሙ በዕውነት 🍂
🙏 ለሁላችን ይደረግልን ። 🙏

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንደሚገባ አድርገው እንዲህ ሥለውታል :

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

24 Oct, 14:54


🍂 #ዲያቆን_ፊልጶስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያው #ቅዱስ_ፊልጶስ ነው በዚህ በጥቅምት 14 ቀን ዓመታዊ በዓለ እረፍቱ የሚታሰብበት ወቅት ነው

🍂 በሐዋርያት አሳሳቢነት ማኅበረ ምእመናንን እንዲያገለግሉ ከተመረጡት ሰባት ዲያቆናት አንዱ ነው ። ( ሐዋ፦ 6 ፥ 5 ) መኖሪያው በቂሣርያ ሲሆን ባለትዳርና የአራት ሴቶች ልጆች አባት ነው ፡፡

🍂 ወደ ሰማርያ ወርዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሷል ( የሐዋ፦ 21 ፥ 8 ) የሀገራችንን ጃንደረባ ( ባኮስን ) አስተምሮ ያጠመቀው ይህው ዲያቆን ፊልጶስ ነው ብዙ መከራ እየተቀበለ ለብዙዎች የመዳን ምክንያት ሆኗል ።

🍂 ለእግዚአብሔር : ምስጋና : ይሁን :
እኛንም : በቅዱስ : ሐዋርያ : ጸሎት ይማረን :
በረከቱም : ከእኛ : ጋር : ለዘላለም : ትኑር : አሜን 🙏🏽

👉🏻 ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
+251913684351

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

#ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopia #orthodox #viral #viralvideos #viralreels #viralpost #viralvideo #copy #ethiopianorthodox #eritrea #eriterianorthodox #facebook #insta #instagram #instagramvideo #art #artgallery #artist

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

24 Oct, 11:58


“እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።”
( ሉቃስ 10:19 )

ከሰው ወገን አማልክት ይባሉ ዘንድ በመንፈስ የጠላትን ኃይል ሁሉ እንረገጥ ዘንድ የሰጠኸን የማይፈታውን እንፈታ ዘንድ ከአባትህ ዘንድ ፍቅርን አደረግህልን. . . ( መጽሐፈ ኪዳን )

እንዲህ ተብሎ የሰጣቸውን ቃል በእውነት ካየንባቸው  በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች መሃል.... ፃድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ አንዱ ናቸው

🍂ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታችን በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾላቸው ምድራዊ መንግስትን ትተህ ስላገለገልኝ ህልፈት ሽረት የሌለባትን ሰማያዊ መንግስቴን አወርስሀለው ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።

🍂በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሀለው አንተም ከሞት ኃይል ትሰወረላህ ብሏቸዋል። እነደ ተነገራቸውም አንደ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል።

🙏 የጻድቁ አባታን አቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከት አይለየን 🙏

👉🏻 ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

Created by ; @qagnewcreatives @semahegndemeke

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

21 Oct, 06:36


ያሬድ ፈልፈለ ማኅሌት ወቅኔያት ወባሕረ ጥበባት እስመ ኮንከ መርሀ ይዜምሩ ለኢትዮዽያ ያሬድ ካህን ጥዑመ ልሳን

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

20 Oct, 14:43


🌺ክበበ ጌራ ወርቅ አክሊለ ጸጌ #ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ

#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
📞 +251923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

18 Oct, 12:18


ወሐለወት አሐቲ ድንግል ፤ መዓዛ አፉሀ ከመ ኮል

🌹 “መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።”
( ሉቃስ 1፥28 )

#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ 🖌️🎨
📞 +251923075264

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

15 Oct, 11:32


በቃልና በኑሮ ሆነሀል ምስክር
እንደፀሀይ ያበራል በእግዚአብሔር ሀገር
ሰማያዊ ነህ እንጂ አይደለህም ምድራዊ
#ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ርእሰ ባህታዊ

👉🏻 አባቴ #ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት በ 1996 ዓ/ም
የሣለው የጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሥዕል

#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
+251923075264

Created by ; @qagnew01 @semahegndemeke

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

08 Oct, 18:43


🌹 #ቅድስት_አርሴማ 🌹

የንጉሥ ድርጣድስ የመከራ ጽዋ ሳያስፈራት ምድራዊ ሀብትን እና ሹመትን በመናቅ በሐይማኖቷ ጸንታ በመስከረም 29 ቀን አንገቷን ተሰይፋ የሰማዕትነት አክሊልን የመቀዳጀቷን በዓል እናከብራለን ። 🙏🏽

ከእርሷም ጋር በሐይማኖት በገድል ጸንተው የሚኖሩ ሃያ ሰባቱ ቅዱሳን አብረዋት ሰማዕት ሆነዋል።

🌹 #ሰላም_ለጸዓተ_ነፍስኪ 🌹

ወደ አዘነበለ አንገትሽ በሚያልፍ ሰይፍ ጊዜ
ለነፍስሽ መውጣት ሰላምታ ይገባል።
አርሴማ ሆይ መሥዋዕትን በሚቀበል ጌታሽ ዘንድ
የተረፈ ረድኤትሽ በእኔ ላይ ይወርድ ዘንድ
በአንደበቴ እለምንሻለሁ ።
የተቆጠሩ ሞትሽ ይህን አሳይቶኛልና

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ
ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን
ቃልኪዳኗ ሀገራችን ኢትዮጵያን
ከክፉ ይሰውርልን
🙏🏽🙏🏽🙏🏽

👉🏻 ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

05 Oct, 17:18


🌹🌸“አንቺ #ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ ።”መኃልየ. 7፥1 🌸🌹

“ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦

ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥
ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥
እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።

እርሱም ተነሥቶ
ሕፃኑንና እናቱን
በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ። “

/ ማቴ 2 ፥ 13-15 /
————————

🌹 #እመቤቴ_ማርያም ሆይ በእውቀት የተሸለምሽ
በትዕግስትም የተሞላሽ ነሽ ።

ኃጢአት ሞትን እንዳነገሠችው ሁሉ
ያንቺም ጸጋ ጽድቅን አነገሠው

🌹 የአጥቢያ ኮከብ ጨለማን እንደሚያርቅ
እንደዚህም ሁሉ ልጅሽን የማመን ብርሃንም
የበደልን ጨለማ አስወገደ ።
#ፍቅርሽን_የሚሻ_ምእመን_ብጹእ_ነው።

ከበረከትሽ ይጠግብ ዘንድ
በቤትሽ ደጃፍ ተረከዙን የሚያመላልስ
የሚገሰግስም ሰውም ብጹእ ነው ።

/ እንዚራ ስብሐት ቁ.35 /
————————————-

👉🏻 የእመቤታችን የወላዲተ አምላክን ከልጇ ጋር የመሰደዷን የስደቷን መታሠቢያ በምናደርግበት በዚህ ወቅት የሚታሠቡ የሚወሱ ትምህርቶችን ፣ ታሪኮችን በስዕል አስማምተን እንዘክራለን ። 🙏🏽እግዚአብሔር በሰላም ያስፈጽመን 🙏🏽

🎨 #ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት ✍️ እና እኔ
🎨 #ሠዓሊ_ዲን_ጌታባለው_አማረ ✍️ ልጃቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን ሠዓልያን

@deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

03 Oct, 18:02


🍂 + #አቡነ_ጎርጎርዮስ_ዘላዕላይ_ግብፅ፡ በትሩፋት በገድል በጾም በጸሎት በሰጊድ በትኃርምት ሕይወት የከበሩ ፤ የላዕላይ ግብፁ ታላቁ ተአምረኛው አባት መስከረም 24 በዓለ ዕረፍታቸው

🍂 #አቡነ_ጎርጎርዮስ_ዘላዕላይ_ግብፅ፡- ደገኛ የሆኑ ወላጆቻቸው እጅግ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ልጃቸውንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረው በሃይማኖትና በምግባር ኮትጉተው አሳደጓቸው፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስም ሲያድጉ ወደ ኤጲስ ቆጶሳቱ ዘንድ ወስደዋቸው አናጉስጢስነት ተሾሙ፡፡

🍂 ከዚህም በኋላ ወላጆቻቸው በሥርዓት ሚስት ሊያጋቧቸው ሲሉ #ጻድቁ ግን ይህንን አልወደዱምና ፈጽሞ እምቢ አሉ፡፡ሁለተኛም ወደ ጳጳሱ ዘንድ ወስደዋቸው ዲቁና ተሾሙ፡፡

#አቡነ_ጎርጎርዮስ ወደ ታላቁ አባት #አባ_ጳኩሚስ አዘውትረው እየሄዱ ይማሩ ነበር፡፡ እጅግ ባለጸጎች ከሆኑት ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ከፍለው በመውሰድ ለአባ ጳኩሚስ በመስጠት ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤትና ሌላም በጎ ሥራዎችን ሠሩ፡፡ከዚህ በኋላ አቡነ ጎርጎርዮስ ዓለምን ፍጹም ንቀው ተጠቃለው ወደ ገዳሙ በመግባት በአባ ጳኩሚስ እጅ መንኩሰው በታላቅ ተጋድሎ ለ፲፫ ዓመታት ኖሩ፡፡

🍂 የቅድስና ሕይወታቸውን አርአያነታቸውንና ምሳሌነታቸውን ያዩ ብዙ አምንዝራዎች የክፋት ሥራቸውን እየተው #ንስሃ እየገቡ ንጹሐን እስኪሆኑ ድረስ የሚጋደሉ ሆኑ፡፡አቡነ ጎርጎርዮስ በአባ ጳኩሚስ ዘንድ ለ፲፫ ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ ታላቁ አባ #መቃርስ ወደ አባ #ጳኩሚስ መጥተው አብረው አገለገሉ፡፡

አባ መቃርስም ወደ ገዳማቸው አስቄጥስ ለመመለስ በፈለጉ ጊዜ አባ ጳኩሚስ አቡነ ጎርጎርዮስን አብረው እንዲሄዱ አዘዟቸውና ጻድቁ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄዱ፡፡ከአባ መቃርስ ዘንድም ብዙ ዘመን በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡

🍂 ከዚህም በኋላ አቡነ ጎርጎርዮስ ብቻቸውን በዋሻ ውስጥ እየተጋደሉ ይኖሩ ዘንድ አባታቸውን እንዲያሰናብቷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባ መቃርስ ፈቅደውላቸው መርቀው ሸኟቸውና አቡነ ጎርጎርዮስ ተጋድሎአቸውን በዋሻ ውስጥ ለመፈጸም ወጡ፡፡በተራራ ላይ ቆፍረው ባዘጋጇት አንዲት ዋሻ ውስጥም ለ፯ ዓመት ሲጋደሉ ኖሩ፡፡

🍂 #አባ_መቃርስም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ብቻ በልደትና በትንሣኤ ቀን እየመጡ ይጎበኟቸው ነበር፡፡ ሥጋ ወደሙንን አብረው ተቀብለው አባ መቃርስ ወደ ገዳማቸው ይመለሳሉ፡፡

አባታችን ከ፳፪ ዓመት ተጋድሎአቸው በኋላ
🍂 #ጌታችን መልአኩን ልኮ ከ፫ ቀን በኋላ ጊዜ ዕረፍታቸው እንደሆነ ነገራቸው፡፡ መልአኩም መጥቶ ‹‹ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወጥተህ ወደ ዘላለም ሕይወት ትገባ ዘንድ አለህ›› አላቸው፡፡

አባታችንም በአስቄጥስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳትን ጠርተዋቸው ከተሰናበቷቸውና ከተመራረቁ በኋላ መስከረም ፳፬ ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ጎርጎርዮስ 🙏🏽
ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣. 🙏🏽
በጸሎታቸው ይማረን፡፡. 🙏🏽

👉🏻 ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

02 Oct, 11:15


🍂 ሰላም ፡ለዑራኤል ፡ለኢትዮጵያ ፡ማኅቶታ ። በከዊኖቱ ፡ ብርሃነ ፡ ዘአሰሰለ ፡ ጽልመታ
ዑራኤል ፡ መልአክ ፡ ለሀገርነ ፡ ጥንተ ፡ ሕይወታ ።
ከመ ፡ ለዕዝራ ፡ አርአዮ ፡ ፍኖተ ፡ ብዙኅ ፡ ሐተታ
አርእየነ ፡ ለነ ፡ በምስጢር ፡ ፍኖታ ።

ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆናት ለኡራኤል ሰላም እላለሁ
በብርሃናዊነቱ ጨለማዋን አርቋልና
ከጥንት ጀምሮ ለሀገራችን ህይዎቷ የሆንከው መልአኩ ኡራኤል
ለነቢዩ ዕዝራ በብዙ መንገድ ጥበብ እንደመራኸው
ለእኛም መንገዷን በምስጢር አሳየን

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

30 Sep, 18:10


👉🏻 ይህችንም የእመቤታችንን ሥዕል

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት ✍️🎨

እንዲህ ውብ አድርገው
አሳምረው ስለዋታል

📞 251913684351

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

30 Sep, 18:10


🌹   #ብዙኃን_ማርያም   🌹 መስከረም  21 በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡

    በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤

#የመጀመሪያው በቤተክርስቲያን ታሪክ በ፫፻፳፭ ዓ/ም  ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት  ከሩቅም ከቅርብም በኒቂያ የተሰባበሰቡት ቀን፤

#ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል / ግማደ መስቀሉ / በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡

+   +   +    #ጉባዔ_ኒቅያ    +   +   +

🍂  በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡

🍂  ጊዜው ታላቁ ንጉሥ #ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

🍂 በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ /  #ሁለት_ሺሕ_ሦስት_መቶ_ዐርባ_ስምንት / ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡

🍂 ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በ #እለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን “ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ” ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው

“ #ዘዕሩይ_ምስለ_አብ_በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው” ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡

🍂  ንጉሡም “ #ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን”
ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው
  /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት

“ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን” የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡

🍂  ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት #መስከረም_፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት “#ብዙኃን_ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

+    +   +    #ዕፀ_መስቀል    +   +  +

🍂 በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡

🍂   +     +     +   🍂

  የእመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት 🙏🏽

የቅዱስ መስቀሉ ረድኤት ጥበቃ አይለየን 🙏🏽

በዓሉም የሰላም የበረከት የረድኤት በዓል ይሁንልን🙏🏽
     


👉🏻 ይህችንም የአእመቤታችንን ሥዕል
#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት ✍️🎨
እንዲህ ውብ አድርገው አሳምረው ስለዋታል
📞 251913684351

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

29 Sep, 09:12


የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሣሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና

#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ 🖌️🎨

📞 +251923075264

#ቅዱሳት_ሥዕላት #ጸሎት #ጸሎት_ቤት
#ethiopianorthodox #holy #icon #iconic #orthodox #ተዋህዶ_ለዘላለም_ትኑር

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

28 Sep, 07:43


አያቴ አባቴና እኔ

በአምላኩ ደም የተቀደሰ፣ ከፈጣሪው ጎን በወጣ ውኃም የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ዕፅ ነው! ለገነት ዛፎች አክሊል፣
ለገዳም ዛፎችም ክብር የሆናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

ለአሸናፊ የእግዚአብሔር በግ መሠዊያ የሆነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ለእሥራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የሆነ ዕፅ አንዴት ያለ ነው!
የጎልጎታዊው የምሥጢር ወይን መፍለቂያ የሆነ ዕፅ አንዴት ያለ ነው!

ከእርሱ ምእመናንን ለማተም የሚሆን የሕግና የሥርዓት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዓይነት ነው!
ብሩካን በጎቸን ለማጠቢያ የሚሆን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዓይነት ነው!

ምድርን የቀደሳት ፣ ሰማይንም ያማተበበት፣
ዓለምንም ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ
ዕፅ አንዴት ያለ ነው!

ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
አዳምን ከስሕተት ያዳነው፣ ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

ስለ እርሱ (አስቀድሞ) በኦሪትና በነቢያት የተነገረ፣
በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
የተከሉትን የበተናቸው፣ ያመኑትንም የሰበሰባቸው ዕፅ አንዴት ያለ ነው!

ቤተ ከርስቲያንን በኢየሱስ ከርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ አንደምን ያለ ነው!

አልጫውን ያጣፈጠ፣ ርኩሱንም ያነጻ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ድኻውን ከፍ ከፍ ያደረገ፣ በደለኛውንም ያጸደቀ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ደካማን ያበረታ፣ ሕመምተኛውንም ያዳነ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ጥቂቱን ያበዛ፣ ሰነፉንም ጥበበኛ ያደረገ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
መካኗን ወላድ ያደረገ፣ ጨለማውንም ያበራ ዕፅ አንደምን ያለ ነው:

የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነ ዕፅ አንደምን ያለ ነው!

—————————
መስከረም 16/ 2017
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

27 Sep, 17:17


በመስቀልከ ጽልመተ አብራህከ በመስቀልከ ሙታነ አንሣእከ
ወዘተኀጉለ ረዳእከ በመስቀልከ

በመስቀልህ ጨለማን አበራህ
በመስቀልህ ሙታንንአስነሣህ
የጠፋውንም ረዳህ

DN ARCHITECT @semahegndemeke

መስከረም 16/ 2017
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

27 Sep, 10:07


መስቀሉሰ ለክርስቶስ ብርሃን እለ ነአምን
ትብል ቤተ ክርስቲያን ዛኅኑ ለባሕር ወመርሶ ለአሕማር
#ዝንቱ_ውእቱ_መስቀል


ቤተ ክርስቲያን “ የክርስቶስ መስቀል “
ለእኛ ለምናምን ብርሃን ነው ትላለች ፤
የባሕር ጸጥታ የመርከቦችም ወደብ ይህ መስቀል ነው

DN ARCHTECT Bini G-wold

መስከረም 16/ 2017
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/

26 Sep, 18:28


ኃይልነ ወፀወንነ ወሞገስነ
ዝንቱ ውእቱ #መስቀል


እኔ እና አባቴ
ሠዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
መስከረም 16 / 2017 ዓ/ም