ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች) ሆነዋል፤ ፍርሃት ከውስጣቸው ተወግዶ መንፈሳዊ ድፍረት አግኝተዋል፤ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ከዕብራይስጥ ቋንቋ በተጨማሪ ፸፪ ቋንቋዎች ተገልጸውላቸው ምሥጢራትን ተርጉመዋል፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!
http://www.eotcmk.org