Event Addis Media @eventaddis1 Channel on Telegram

Event Addis Media

@eventaddis1


Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye

Website:https://eventaddis.com/

Event Addis Media (English)

Are you a lover of art and culture? Do you enjoy attending exhibitions, music events, and workshops? If so, Event Addis Media is the perfect Telegram channel for you to stay connected with Addis Ababa's artistic community! Keep up to date with all the latest happenings in the local arts scene, from upcoming art exhibitions to music performances and cultural experiences. Event Addis Media provides a platform for you to discover new talents, explore various art forms, and connect with like-minded individuals who share your passion for creativity. Whether you're an artist looking to showcase your work or simply someone who appreciates the arts, this channel is the place to be. By joining Event Addis Media, you will have access to exclusive updates on upcoming events, behind-the-scenes looks at art installations, and opportunities to participate in workshops and discussions with artists and cultural influencers. Don't miss out on the chance to immerse yourself in the vibrant and diverse artistic community of Addis Ababa. Connect with us on Telegram at @eventaddis1 and become a part of our growing community of art enthusiasts. Stay informed, inspired, and engaged with Event Addis Media!

Event Addis Media

13 Jan, 19:47


📌የአስቻለው ፈጠነ አዲስ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "አሞራው ካሞራ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃው ሥራውን ነገ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል።

ሙዚቃው ለአፄ ቴዎድሮስ የልደት መታሰቢያ የተሰራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።

በተጨማሪም ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር በለቀቀው "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

13 Jan, 17:08


📌የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዕጩ ተሿሚ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ ምትክ ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) እንዲሾሙ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጩነት ያቀረቧቸው ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኮሚኒኬሽን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ በዩንቨርስቲው የማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር መሆናቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው በላኩት ደብዳቤ ፣"የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ዶ/ር ሳምሶን መኮንን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ እንዲሾሙ እጠይቃለሁ" ብለዋል።

በደብዳቤው ላይ የተጠቀሰው አዋጅ ድንጋጌ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በባለስልጣኑ ቦርዱ ተመልምሎ በመንግሥት አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሰየም የሚገልጽ ነው።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ነፃ መሆን እንዳለበት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 17 ስር ተደንግጓል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ በነገው ዕለት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

የባለስልጣኑ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር በቅርቡ በአቶ ብናልፍ አንዷለም ምትክ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Jan, 18:45


📌የአንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ የስንብት የሙዚቃ ኮንሰርት እንዴት ነበር?


የጋሽ ማሕሙድ የምስጋና ምሽት በአብዛኛው ጥሩ ዝግጅት የተደረገበትና በርካታ ሞያተኞችም የተሳተፉበት ለሌሎች አንጋፋ ሞያተኞችም ክብርና እውቅና የመስጠትን ልምምድ አስፈላጊነት ያሳሰበ ዝግጅት ነበር ።


የፕሮግራሙ ትልቅ ችግር ሰዓቱ ነበር።ለጋሽ ማሕሙድ ፍቅርና ክብራቸውን ለመግለጽ ኮንሰርቱን የታደሙትን ዕድሜያቸው 60ዎቹና ሰባዎቹን የተሻገሩ ትልልቅ ሰዎችን እስከ ሌሊት ስምንት ሰዓት ማስጠበቅ በፍጹም ትክክል አይደለም።ይህ አይነቱ የክብር መግለጫ ስነስርዓት ቀደም ብሎ ተጀምሮ የሚደረጉ ንግግሮችና ሌሎች ፕሮግራሞችም ቀልጠፍ ብለው ማለቅ ነበረባቸው።


ጋሽ ማሕሙድ ጉንፋን ይዞት ያሰባቸውን ሙዚቃዎች መጫወት ባይችልም ጥቂት ስራዎቹን በትግል ዘፍኗል።አክብረው ለመጡ አድናቂዎቹ ሲል አንድ ዘፈን ከተጫወተ በቂ ነበር ። የቀረው ፐርፎርማንስ ግን ለእርሱም ለአድማጩም አሳቃቂ ኾኖ ተሰምቶኛል ።


ከምሽት ሶስት ሰዓት ጀምሮ በአዳራሽ ለተገኘው ታዳሚ ከሌሊቱ ዘጠኝ ተኩል ሊዘፍን የወጣውን ኤፍሬምን ጨምሮ እዚያ የተገኙ ድምጻውያን ከራሳቸው ዘፈኖች ይልቅ የጋሽ ማሕሙድን ስራዎች በራሳቸው ቃና በመጫወት ቢያከብሩት ምሽቱ የእርሱ መኾኑን አስረግጠው ማሳየት ይችሉ ነበር ። የውጪ ሀገር ልምድ ይህን ያሳያል ። የትላንቱ የነርሱ ተሳትፎ የማሕሙድን መብራት መሻማት መስሏል ። እርግጥ ስጦታዎችን በመስጠት ክብራቸውን ገልጸዋል ። በጎው ነገር ያ ነው ።


ይህን መሰሉ ዝግጅት ዋና ፊታውራሪ መኾን የነበረበት መንግስት የኋላ ወንበር መያዙ አስተዛዛቢ ነው ። የድሬደዋ አስተዳደር የምስጋና ሰርተፍኬት ልኳል ።


የነጻነት መድረክ መሪነት ፍጹም ዝግጅት ያልተደረገበትና የተዝረከረከ ነበር ። ለቴሌቪዥን ዝግጅቱ ከሚያደርገው ዝግጅትና የአቅራቢነት ለዛ ጥቂቱን እንኳ አላየኹም ።


ከነእንከኖቹም ቢኾን ይህን መሰሎቹ የምስጋና መድረኮች መለመድ ይኖርባቸዋል ። ይህን ዝግጅት ያሰናዱት ኹሉ ምስጋና ይገባቸዋል ።

በዮሴፍ ጥሩነህ የተጻፈ

@EventAddis1

Event Addis Media

11 Jan, 06:05


📌"የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል

በደራሲ አህመድ ሁስ የተዘጋጀው "የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" የተሰኘ  የልቦለድ መጽሐፍ ነገ እሁድ ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

11 Jan, 05:58


📌የገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ገጣሚና ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ የበኩር ስራው የኾነውን "የምድር ዘላለም" ከፃፈ በኋላ ዘለግ ላሉ አመታት "ሰው እስካለ ድረስ" የተሰኘውን የግጥም መድበል ሲያሰናዳ ቆይቷል።

"ሰው እስካለ ድረስ" ከበርካታ ግጥሞቹ መካከል በዚህ ኮረብታ ኮረኮንች በሆነው የሕይወት ጎዳና በማይረብሽ መልኩ ለግጥም አፍቃሪያንና ተደራሲያን ይሆኑ ዘንድ ተመርጠው የታተሙ ናቸው።

ግጥም የሕያው ስሜቶች ምስክሮች ናቸው እንዳለው ባለቅኔው፣ የዲበኩሉ ግጥሞች ምስክሮች ናቸው።

በተለያዩ ጊዜያት የተፃፉ ልዩ ልዩ ጭብጥ ያላቸው ግጥሞችን ያካተተው መድበሉ፤ በ126 ገጾች ተቀንብቦ በ297 ብር ለአገር ውስጥ፣ በ20 ዶላር ለውጭ አገር ገበያ ቀርቧል፡፡"ሰው እስካለ ድረስ" በሁሉም መጻሕፍት መደብር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

11 Jan, 05:58


📌አዲስ አድማስ ጋዜጣ 25 ዓመት ሞላው!

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ የመጀመሪያው ዕትም ለንባብ የበቃው ታህሳስ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ነው፡፡ ጋዜጣው ባሳለፍነው ማክሰኞ ታህሳስ 29 2017 ዓ.ም 25ኛ ዓመት ሞላው፡፡

ይህንንም ምክንያት በማድረግ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም የ25ኛ ዓመት ልዩ ዕትም ለንባብ በቅቷል።

ጋዜጣው በእርግጥም ልዩ ዕትም ነው፡፡ በተባ ብዕራቸው የሚታወቁ የአገሪቱ አንጋፋ ደራስያንና ጸሃፍት በሳል ጽሁፎቻቸውን ያቀርቡበታል፡፡

የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ጥበባዊ ርዕሰ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡ ከአዲስ አድማስ ጋር የተያያዙ ማራኪ ትዝታዎችና ገጠመኞች ይነበቡበታል፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት በአዲስ አድማስ ላይ ከወጡ ጽሁፎች የተመረጡ በዚህ ልዩ ዕትም ተካተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

10 Jan, 16:45


📌"ደህና ይግጠምሽ" ሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ

የድምጻዊ መሳይ ተፈራ "ደህና ይግጠምሽ" የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ጥር 2 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች አድርሷል።

የሙዚቃው ግጥም በናትናኤል ግርማቸው፣ዜማ ደግሞ በመሳይ ተፈራ ካሣ ተሰርቷል።ታምሩ አማረ በሙዚቃ ቅንብር የተሳተፈ ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮውን ሱራፌል መዝገበ ዳይሬክተር አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

10 Jan, 16:09


📌ኤም  ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት ኩባንያ የፊልም ስክሪፕት ግዢ ስምምነት ተፈራረመ። 

ስምምነቱ ኩባንያው እየሰራ ከሚገኘው የፊልም ማርኬቲንግ ሥራ በተጨማሪ በፊልሙ ኢዱስትሪውን ውስጥ ለመፍጠር ላልመው በጎ ተፅዕኖ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑን በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አስታውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ቢሮውን ከመክፈቱ አስቀድሞ ከፓራ ማውንት፣ ሶኒ ፒክቸርስ እና ሌሎች የፊልም ኩባንያዎች ጋር ሥራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን በኢትዮጵያ ቢሮውን በከፈተ ማግስት በተለያዩ በጎ ተግባራትን ሲፈፅም እንደቆየም ሰምተናል።

የኩባኛውን በኢትዮጵያ ሥራ መጀመር በማስመልከት በመጀመሪያ የወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከ6 ወር በኋላ ደግሞ ለንሕምያ የኦቲዝም ሴንተር የተለያዩ የንፅሕና እና መማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ ችሏል።

በዛሬው ዕለት የተደረገው የፊርማ ሥነሥርዓት የፊልም ሀሳብ ያላቸው ደራሲያን ስክሪፕታቸውን ሸጠው በሌሎች አካላት ሥም ለዕይታ ይበቃ የነበረበትን ልማድ በማስቀረት ደራሲያን በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለማሳየት የተደረገ እንደሆነም ከመድረኩ ለማወቅ ችለናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

10 Jan, 16:09


በ3.5 ሚሊዮን ብር የታተመው የአርቲስት መሀሙድ አህመድ የህይወት ታሪክ መጻሕፍ ተመረቀ

የአርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወት ገጽታዎች ያካተተውና በደራሲ ወሰን ደበበ ማንደፍሮ የተዘጋጀው
መጻሕፍ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ተመረቋል።

አርቲስት መሀሙድ አህመድ ላለፉት 63 ዓመታት በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶች ፣ የቤተሰብ የኋላ ታሪክና የወዳጅ ጓደኞቹን እንዲሁም የሙያ ባልደረባዎቹን ምስክርነት አካቶ የያዘው የሕይወት ታሪክ መጻሕፍ ለማዠጋጀት አስር ዓመታት እንደፈጀ በምርቃት ዝግጅት ላይ ተገልጿል።

ንብ ባንክ በ3.5 ሚሊዮን ብር ህትመቱን ስፖንሰር ማደርጉ
በዕለቱ ተገልጿል። መጻሕፉ ለምረቃ በበቃበት ዕለት በልዩ
ሁኔታ የታተመውንና አምስት ሺህ ብር ዋጋ የተቆረጠለት መጻሕፍ ለሽያጭ ቀርቦ በማሪዮት ሆቴል የተገኙ እንግዶች ገዝተዋል።

በልዩነት ግን ኢንጂነር ቢጃናይ እና ዶ/ር ሐውለት አሕመድ 500 መጻሕፍትን በ2.5 ሚሊዮን ብር የገዙ ሲሆን የሰን ሻይን ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በ500 ሺ ብር 100 መጻሕፍት ገዝተዋል።

ዘገባው የባላገሩ ቴሌቪዥን ነው።

Event Addis Media

09 Jan, 19:12


📌"KITFO film festival" ነገ ይካሄዳል!

(መግቢያው በነፃ ነው)

ፕሪስቲጅ አዲስ የኢትዮጵያን የጥበብ ኢንዱስትሪ ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን ከ2012 ዓም ጀምሮ ወጣትና አንጋፋ ለሆኑ የፊልም ባለሙያዎች ተሞክሯቸውን ለወጣቶች ሚያጋሩበት አስተማሪ የሆነ መድረክን ገንብቷል።

ይህንን ተግባሩን ያጠናክር ዘንድ "KITFO film festival" የተሰኘ  የፊልም ፌስቲቫልመቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው "KITFO TV" ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል ።

ዝግጅቱም ነገ አርብ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን የባህል ማዕከል የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ፌስቲቫል ስድስት ሀገርኛ እንዲሁም ኢንተርናሽናል ፊልሞች ይቀርባሉ።ነፃ ምግብና መጠጦችም ይኖራል።መግቢያውም ሙሉ በሙሉ በነፃ ነው።

ይህንን የፊልም ፌስቲቫል ነገ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ መታደም ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

09 Jan, 13:59


📌"ጀቢና"ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

በደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር የተዘጋጀውና "ጀቢና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ለእይታ ይበቃል። "ጀቢና" በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ ፊልም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁን ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በለታሪክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ነው።

በፊልሙ ላይ ቤተልሔም ሸረፈዲን፣እታፈራሁ መብራቱ፣ ካሣሁን ፍስሃ(ማንዴላ)፣ ናትናኤል መኮንን፣አስራት ታደስ እና ሌሎችም ተውነውበታል።

ይህ ፊልም ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

09 Jan, 13:59


📌የድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) አልበም

የድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) "አልጣሽ" ሲል የሰየመውን የመጀመሪያ አልበሙን በዚህ ወር ለአድማጮች እንደሚያደርስ ተገልጿል።

በዚህ አልበም ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በግጥም ይልማ ገብረዓብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ ተስፋ ብርሀን በዜማው አበበ ብርሀኔ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ አህመድ ተሾመ(ዲንቢ)) በቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ አብዛኛውን ያቀናበረ ሲሆን ቀሪውን ከአቤል ጳውሎስ በጋራ ሰርተውታል፡፡

ይህ የድምጻዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) አዲስ አልበም ጥር 16 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል፡፡

ድምጻዊው "ደሴ ላይ" ፣ "ልቤ አቃተው" እና ሌሎችም ነጠላ ሙዚቃዎች ከዚህ ቀደም ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Jan, 11:56


📌የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት እታፈራሁ መብራቱ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Jan, 11:56


📌"ቃልና ሙዚቃ" የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል። ይህ ልዩ ውይይት ነገ ጥር 1 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ የሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ ዳሰሳ ታቀርባለች ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

04 Jan, 08:53


📌ሀገራችን ኢትዮጵያ በሉሰበርግ ልትመሰገን ነው

‎የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአውሮፓ ጉብኝትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት በሉክሰምበርግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  የማስታወሻና የምስጋና ዝግጅት የፊታችን ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ይካሄዳል።

‎በዕለቱ የኢትዮጵያና የሉክሰምበርግ ሠዓሊያን  ወቅቱን የሚያስታውስና ነጻ የፈጠራ ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የሥዕል ትርዒት ይከፈታል ተብሏል።

‎በመርሃግብሩ ላይ አስር የሀገራችን ሠዓሊዎች ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሠዐሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ ሀገሩን ወክሎ ንግግር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

‎የንጉሱ የሉከሰምቦርግ ጉብኝትለየት  የሚያደርገው በወቅቱ በነበረው የአንደኛው  የዓለም ጦርነት ጉዳት ምክንያት የገንዘብ  ልግስና ማድረጋቸው ሲሆን ፣በዚህ ዝግጅት  ላይም የከተማዋ ከንቲባና ንጉሳዊያን ቤተሰቦችንጨምሮ  ታላላቅ  እንግዶች  በመገኘትንግግር  እንደሚያደርጉ፣ ኢትዮጵያንም እንደሚያመሰግኑ ይጠበቃል ።

‎ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከዚህ የአውሮፓ ጉብኝት  በኋላ መከፈቱን ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

04 Jan, 04:56


📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" አምስተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት አራት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ አምስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም አብዬ መንግስቱ ለማ  ይዘከራሉ፤ አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ ደግሞ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

04 Jan, 04:56


📌"ያልተወጋ ፍቅር "መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል።

በመምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ የተዘጋጀው "ያልተወጋ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል።

በዕለቱም አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ደራሲ የዝና ወርቁ፣ደራሲ አበራ ለማ፣ገጣሚ ፍሬሕይወት መላኩ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ይገኙበታል።

መምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ ለ4 ዓመታት በመምህርነት፣ ለ12 ዓመታት በምክትል ር/መምህርነት ሠርታለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

03 Jan, 11:44


📌አራተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ

የቤት ሻጮችና ገዢዎች፣ እንዲሁም ገንቢዎች የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር ዕድል ይሰጣል የተባለለት አራተኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

ከዛሬ ታህሳስ 25 እስከ ታህሳስ 27/2017 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ስላለው ቤት ግንባታዉ ያለበት ደረጃ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።

ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በመሆኑ የኤክስፖውን ሳይጎበኙ ቤት እንዳይገዙ በሚል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ልዩ የገና በዓል ቅናሽ መኖሩም ተገልገልፃል።

አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይሄ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያሉበት ለተረጋጋና ምክንያታዊ የቤት ግዥ ዉሳኔ ምቹና ዓይነተኛ አጋጣሚ እንደሚፈጥር የዝግጅት ክፍሉ ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ቤት ገዥ እና አልሚ ይህ ዕድል ሳያመልጠዉ ኤክስፖዉን እንዲሳተፍ ጥሪ አቅረቧል፡፡

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

02 Jan, 19:18


📌"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

የገጣሚ ዘውዴ አለልኝ  ‹‹ጊዜን መሸከም›› የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፍ 54 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን  በ162 ገጽ የተቀነበበ ነው።የመጽሐፉ ቅርጽ በዋሽንት አውታረ ቅኝት የተሠራ ሆኖ በጥቁር፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ እና ነጭ ቀለማት የተከፋፈለ ነው። 

ቀለማቱ ከኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች  ዋሽንት፣ ክራር፣ ነጋሪት እና ሞረሽ ከምትባል ወፍ ጋር የተቀነባበረ ነው ተብሏል።

እያንዳዱ ክፍል ቀለማዊ እና ሙዚቃዊ ፍካሬ መግቢያ አለው። እንዲሁም ግላዊ መግቢያ እና ድኅረ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ ተካቷል።

መጽሐፉን ለመግዛት የምትፈልጉ በኦንላይን online ማዘዝ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

የመግዣ ዋጋው በኢትዮጵያ ብር 350 ሲሆን፣ በውጭ ሀገር መገበያያ $20  ዶላር ተተምኗል።

አካውንት ቁጥር...
አቢሲኒያ ባንክ ( bank of abyssinia) 200869327  ዘውዱ አለልኝ አራገው ( zewdu alelgn aragaw)

ዳሽን ባንክ (Dashen bank)  5472769396011 ዘውዱ አለልኝ  አራጋው ( zewdu alelgn aragaw)

ንግድ ባንክ (CBE ) 1000298476936 (Daniel abreha) ዳንኤል አብርሃ

ቴሌ ብር / tellebirr፦ 0913240885 zewdu alelgn

ክፍያ የፈጸሙን የባንክ ደረሰኝ Screenshot  አድርገው፣ ወይም ፎቶ አንስተው በዚህ የቴሌግራም ሊንክ ይላኩልን @Gizienmeshekem2424 ይላኩልን ተብላችኋል።

Event Addis Media

02 Jan, 19:18


📌በድምጻዊት ዲባን በኢሮብ አካባቢ በሚነገረው ሳሆ ቋንቋ የተሰራ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ ።

ድምጻዊት ዲባን በሳሆ ቋንቋ የሰራችው "Kokam liyo" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በDIBAAN የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

እዚህ አልበም ውስጥ ከተካተቱ 11 የሙዚቃ ስራዎች አስሩ ላይ በሙዚቃ ቅንብር የተሳተፈው ሙሳ ማቲ ነው።

የሙዚቃ አልበሙን በዚህ ቻናል በኩል https://youtube.com/playlist?list=PLQZbkiZabnHwu_BSzbOYPMtNm7dcs6iNl&si=a41zArVDFNDA1ybg ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ድምጻዊት ዲባን ወደ ጥበቡ አለም የተሳበችው ገና በልጅነቷ ነው በተለይ ለሞዴልንግ እና ሙዚቃ ልዩ ፍቅር አላት። ተሰጦዋን በትምህር ለማሳደግም የሞዴልንግ ትምህርት ተምራለች። ዲባን አሁን ላይ ወደ ሙዚቃው እያደላች ቢመስልም የሞዴሊንግ ስራንም እየሰራች ትገኛለች። ከዚህ ቀደም "ይባንድራ" የተሰኘ ነጠላ ዜማ ለአድማጮች ያደረሰች ሲሆን በመቀጠልም በ" ጋሆ"(GAHO) የተሰኘ የሙዚቃ ስራዋን ደረጃውን ከጠበቀ ቪዲዮ ጋ አዋዳ ዳግም ለአድማጮች ተመልካቾች አቅርባለች።

ኢሮብ በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ስቶን በሰሜን ከኤርትራ በምሥራቅ ከአፋር ክልል ትዋሰናለች።  የብሔረሰቡ ቋንቋ ሳሆ በመባል ይታወቃል፡፡

ማኅበረሰቡ የሚገለገልባቸው የትንፋሽ፣ የክርና የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች በአብነት ከሚጠቀሱት ናቸው፡፡ ሙዚቃ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው ቦታም ከፍተኛ የሚባል ነው፡፡ ውድድር በሚደረግባቸው ባህላዊ የሙዚቃ ሥርዓቶች ማሸነፍ፣ በኅብረተሰቡ መካከል የሚሰጠውን ዋጋ ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

02 Jan, 11:23


📌 ኃይሌ ሪዞርት ጅማ ሥራ ጀመረ

ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ አሥረኛውን መዳረሻ እና ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል በጅማ ከተማ  አገልግሎት አስጀምሯል።

ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራ የጀመረው ኃይሌ ሪዞርት ጅማ 105 የእንግዶች ማረፊያ ክፍሎች፣የምግብ አዳራሾች፣የተለያዩ ባሮች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ስፓ፣ ጂምናዚየም፣ ከ30 እስከ 500 ሰዎችን የሚይዙ 5 የስብሰባ አዳራሾች፣ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

የመሰብሰቢያና የምግብ አዳራሾች በአካባቢያው በሚነገሩ ታሪካዊ ስያሜዎች እንደተሰየመም ተገልጿል።

ኃይሌ ሪዞርት ጅማ ከ210 በላይ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ በሙሉ አቅም ሥራ ሲጀምር 400 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ከፍተኛ ጥራት ባለው የአገልግሎት ባህል ህብረተሰቡን ለማገልገል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አቶ ተስፋዬ አስራት አስረድተዋል።

በሐዋሳ ከተማ አንድ ተብሎ የተጀመረው የኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ ዘንድሮ አስራ አምስት ሆኖታል።

ሐይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በቀጣይ የሻሸመኔውን እና የደብረብርሃን ከተማ መዳረሻውን በቅርቡ ለማስመረቅና ስራ ለማስጀመር ቀን ከሌት እየሰራ መሆኑን የሐይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ  ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ ተናግረዋል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

01 Jan, 19:05


📌"አሲና ገናዬ" የተሰኘ ሙዚቃ ተለቀቀ

ድምጻዊት ረቂቅ አስግደው በአጃቢ ድምጻዊነት የተሳተፈችበትና በካሶፒያ የተዘጋጀው "አሲና ገናዬ" የተሰኘ ሙዚቃ ለአድማጮች ደርሷል።

የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በዮሐንስ ዘካሪያስ የተጻፈ እና ከሕዝብ የተወሰደ ነው ተብሏል።

ሙዚቃውን በ https://youtu.be/ZJZ2mm6VANw?si=oFGfbwA2cLDFQ7-V መስማት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

Event Addis Media

30 Dec, 10:20


📌የንባብ ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ

10ኛው ዙር ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ሳምንት የፊታችን ሀሙስ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ፌስቲቫል በመጽሀፍት ማምረትና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ አካላት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ያደርጋልም።

በዚህ የንባብ ባህል ፌስቲቫል በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ ቤተ መጽሀፍት ቤቶች ደረጃቸው እና ያሉበት የጥራት ደረጃ ለህዝቡ ይስተዋወቅበታል ተብሏል።

በተጨማሪም የተለያዩ የህትመት ውጤቶች እንደሚተዋወቁም ነው የተነገረው።በቤተ መጽሀፍቶችና በአታሚዎች መካከል ድልድይ በመሆን የህትመት ውጤቶችን በቀላሉ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ እንዲደርሱ ያግዛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

28 Dec, 22:39


📌የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች

• የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር - Elatick

• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ

• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ

• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት - ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi

• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት - ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ

• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮንቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ

• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ

• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ - ጃዝሚን/jazmin_hope1/

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት - ኤላ Review

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ - Baes

• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ

• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ

• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu

• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ -ባዚ

• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ /Elatick/

• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ - I did it በዘነዘና

• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ - አቤል ብርሃኑ

• የዓመቱ ምርጥ ኢንፎርማቲቭ ኮንቴንት አዋርድ - ሙሴ ሰለሞን

• የዓመቱ ምርጥ ኢመርጂንግ ኮንቴንት አዋርድ - ስኬት

• ቤስት ሾርት ሙቪ ቪዲዮ አዋርድ - ቤንጂ

• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በወንድ አሸናፊ - ከርተንኮል

• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በሴት አሸናፊ - ማህሌት ይብራለም

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

28 Dec, 15:45


📌"ኢትዮ ኮሊውድ" የተሰኘ ግዙፍ የፊልም መንደር በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው።

ልክ "ሆሊዩድ፣ፖሊዩድ እና ኖሊዩድ" የፊልም መንደሮች ያለ ግዙፍ የሆነ "ኮሊውድ ኢትዮጵያ "የተሰኘ የፊልም እና ኢኮ ቱሪዝም መንደር  በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በኮንታ ዞን ኤላ አንቻኖ ወረዳ  በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከሪበላ ሀይቅ ዙሪያ ሊገባ እንደሆነ ተሰምቷል።

መንደሩ 43,000 ሺ ካሬ ካርታ በመረከብ አስገራሚ  በሆነው የዘንባ ጫካን ለዚህ አገልግሎት ለማዋል ስራ መጀመሩን አርቲስት  ወንድዬ ኮንታ ይፋ አድርጓል።

ይህ የፊልም መንደር እና የኢኮ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ መንደር በውስጡ ፣የአርቲስቶች መኖሪያ መንደር፣ታላላቅ የፊልም አክተሮች እና የዘርፉ ሙያተኞች የሚገለገሉበት ሎጅ እና ማረፊያ ገስቶች ሀውሶች፣ አርት ስኩል የሙያ ኮሌጅ ፊልድ ሆስፒታል እና የባህላዊ ህክምና መስጫ ዞን፣ የሀይቅ ላይ የጀልባ መዝናኛ፣ የቱሪስት ካምፒንግ ሳይት እና መናፈሻ፣ የክሮማ ፣ የኤዲቲንግ፣ የሳውንድ ትራክ መቅረጫ እና ማቀነባበሪያ ስቱዲዮዎች የሲኒማ አዳራሾች፣ብሮድካስት የቴሌብዥን እና የሬድዮ ጣቢያ ፣ የሰርከስ ፣ የስዕል ጋለሪ እና የቅርፃቅርፅ  ፣ የመጻሕፍት ገበያ ማዕከል፣የባህላዊ አልባሳት ማምረቻዎች፣የዲዛይነሮች የጥበብ ውጤቶች፣የገበያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎችም ዘርፈ ብዙ  አገልግሎት መስጫን ያካተተ ነው ተብሏል።

አርቲስቱ የሚቆጠር ገንዘብ ሳይኖረው ትውልድን በሚያንፅ ሀገርን በሚያሻግር ድንግል ሀሳቡ የተማረኩ በገንዘብ የሚያግዙትን ባለሀብቶች ፣ ወዳጅ ጓደኞች ፣ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ከጀርባው በማሰለፍ   ግዙፉ ካምፓኒው በሁለት እግሩ እንዲቆም አስፈላጊውን ሁሉ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

አርቲስት ወንድዬ ኮንታ ይህ ትልቅ ሀሳብ እንዲሳካ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ያሉ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስተርን እና የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፐብሊክ ሰርቪስን ጨምሮ ሁሉንም ከልብ አመስግኗል።

ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚል ስያሜ የኢንቨስትመንት ሰርተፊኬት በማግኘት እና ሰፊ ይዞታ በመያዝ  ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል።

ይህ ፕሮጀክት የኮንታ አከባቢን እንደብራዚሉ አማዞን ጫካ ከፍተኛ የዶላር ምንዛሪን እንዲያመጣና ዓለምአቀፍ የፊልም እና የቱሪዝም የገበያ ውድድር ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር  የታሰብ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1

Event Addis Media

27 Dec, 07:59


📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 ዋዋጎ

ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍የሕይወት ታሪክ

ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

26 Dec, 04:30


📌6ኛው የወር ወንበር ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል

በዕለቱ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ይኩኖአምላክ መዝገቡ “ኪን እና ስየማ፡ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ በለቀማ” በሚል ርእስ ሃሳባቸውን ያቀርባሉ። ከታዳሚዎች ጋርም ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

በዝግጅቱ እንትትሳተፉ ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል።


📌 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ

ከ10፡00-12፡00

📝በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ በመሙላት ይመዝገቡ
https://bit.ly/3BFVvGS

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

26 Dec, 04:30


📌አዲስ የቪዲዮ ሥነጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል።

ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአዲስ ዓለም አቀፍ የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ስነ-ጥበብ ማዕከል በምሽቱ 12:00 ጀምሮ  ይከፈታል።

ፌስቲቫሉም ለ 5ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ይህ አምስተኛው  ፌስቲቫልም በቅርቡም ህይወቱ ላለፈው ሠዓሊና የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ሙያተኛ ሙሉጌታ ገ/ኪዳን መታሰቢያ እንዲሆን ተሰይሟል ተብሏል።

የዘንድሮው መሪ ቃልም "የማንሰራሪያ ተረኮች" ወይንን"Re(Cover) Story" ሆኗል።

ለዚህ ፌስቲቫል 350 ሠዓሊያን ከ 84 ሀገራት ያመለከቱ ሲሆን የመጨረሻወቹ 12 ስራዎች ተመርጠዋል ተብሏል።

በዚህ ፌስቲቫል እነዚህ የተመረጡ ስራዎችና የተጋበዙ 4 ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ፕሮግራሞች ለእይታ ይቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

24 Dec, 10:06


📌በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" ለንባብ በቃ

መጽሐፉ 57 ወጎች እና ሽሙጦች የተካተቱበት ሲሆን በ207 ገፆች ተቀንብቧል። ደራሲው ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ቁምነገር አዘል አዝናኝ ጽሑፎች ይታወቃል።

የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ  ጉዳዮችን የሚዳስሱ ወጎች በተካተቱበት መፅሐፍ ጀርባ ላይ አቶ ሙሼ ሰሙ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እና ዶክተር መስፍን ፈቃዴ አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

መጽሐፉ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

24 Dec, 10:06


📌የድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" ሙዚቃ ተለቀቀ

የወጣቷ ድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ሙዚቃ በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ደርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Dec, 11:07


📌የሀዲንቆ የማሲንቆ አልበም ነገ ይለቀቃል

በመስንቆው ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ ሀዲስ አለማየሁ በመድረክ ስሙ (ሀዲንቆ) የተዘጋጀው የመስንቆ አልበም ነገ ታህሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የሙዚቃ አልበሙ "Streets of haddis" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።

ተጨማሪውን ያንብቡ:http://surl.li/jsqasd

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Dec, 11:07


"የለውጥ ሰበዞች" የፎቶግራፍ አውደርዕይ ተከፈተ

የአምስት ፎቶ ባለሞያዎች የፎቶግራፍ ስራዎች የሚቀርብበት "የለውጥ ሰበዞች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የፎቶግራፍ አውደርዕይ ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ውስጥ ተከፍቷል።

ዝርዝሩን በድረገጻችን ያንብቡ: http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Dec, 11:07


📌"ብስክሌት በአዲስ" ፌስቲቫል

"ብስክሌት አዲስ" የተሰኘ የብስክሌት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ:http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

21 Dec, 05:52


📌በአርቲስት ዘነበች ታደሰ"ጭራ ቀረሽ" ህይወትና ሥራ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል።

በሀገራችን በቴያትርና ሙዚቃ ዘርፍ በሁለገብ ሙያተኛነት ደምቀው ሲያበሩ ከነበሩ ከያኒያኒን መካከል አንዷ የነበረችው አርቲስት ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) ሕይወትና ስራዎች ላይ የሚያጠንጥን መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

በዶ/ር ጌታቸው ተድላ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ አርቲስት ዘነበች ታደሰ ማን ነች? ለምንስ ጭራ ቀረሽ የሚል ስያሜ ተሰጣት? ለጥበብ ምን አበረከተች? የሚሉ ጥያቄዎችን ሊመልስ የሚችል በፅሁፍና በምስል የተደራጀ መፅሐፍ  እንደሆነ ተገልጿል።

አርቲስት ዘነበች ታደሰ  'ሎሚ ብወረውር' በሚለው ዘፈኗና በመድረክ ላይ ውዝዋዜዋ ይበልጡን በህዝብ ልብ ውስጥ የምትታወስ ትሁን እንጂ ጥቂት በማይባሉ የመድረክ ቴያትሮችና የቴሌቪዥን ድራማ ብሎም ፊልም ላይ  በመሳተፍ አቅሟን አሳይታለች።

ለአብነት ያህል (Shaft in Africa) ላይ ከታዋቂው የሆሊዉድ ተዋናይ ሪቻርድ ራውንድትሪ ጋር የመተወን እድል ሲገጥማት በጥሩ ብቃት የተሰጣትን ሚና ለመወጣት የቻለች ብቁ ሙያተኛ ነበረች።

'ጭራ ቀረሽ' የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መፅሀፍ  ዛሬ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመርቆ ለንባብ ይበቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

21 Dec, 05:51


📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ ነገ ይካሄዳል

52ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዮናስ ታረቀኝ " ፍራንስ ካፋካንና ሥራዎቹን በጨረፍታ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ታህሣሥ 13 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

20 Dec, 04:48


📌የሜላት ቀለመወርቅ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል

የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዜሮ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በራሷ ዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ይደርሳል።

ድምጻዊት ሜላት በማህበራዊ ትስስር ገጿ"አዲሱን የሙዚቃ ቪድዮ  ስራዬን በራሴ ዩትዩብ ቻናል ወደናንተ አደርሳለው። ሁሌም በስራዎቼ ስለምታበረታቱኝ በጣም አመሰግናለው" ብላለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

20 Dec, 04:48


📌የድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ባለውለታዬ" የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል

የቀደሞ ድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ የሙዚቃ ስራዎችን በድጋሚ የተጫወተውና "ዘንድሮ" በሚል ርዕስ በአልበም መልክ ለአድማጮች ያደረሰው ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ባለውለታዬ" የሙዚቃ ቪዲዮውን ዛሬ ታህሥሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

20 Dec, 04:48


📌"የቀለም ጨዋታ" ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በብርሃኑ መብሬ ተደርሶ በኪሩቤል ስዩም የተዘጋጀው "የቀለም ጨዋታ" የተሰኘ አዲስ ፊልም ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

"የቀለም ጨዋታ" ፊልም አንድ ዓመት ከ4 ወር በላይ ጊዜን የወሰደ ሲሆን  ደረጄ ሀይሌ፣ሙሉዓለም ጌታቸዉ፣ሱራፌል ብስራት፣አለምፀሀይ እሸቱ፣ተመስገን ሚካኤል፣ ሳባ ታደሰን ጨምሮ ከ85 ተዋናኒያን እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው "የቀለም ጨዋታ" ፊልም ታህሳስ 11፣12 ፣13 እና 18፣19፣20 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

19 Dec, 12:30


📌የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ምርቃት ተሰረዘ

ጃዋር መሐመድ 'አልጸጸትም' በሚል ርዕስ ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በናይሮቢ ሊያስመርቀው የነበረው መጽሐፍ ከተለያዩ አካላት በደረሱ ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ረቡዕ፣ ታህሳስ 9/ 2017 ዓ.ም ይፋዊ የሆነ ዛቻ/ተቃውሞ ከኢትዮጵያ መንግሥት መድረሱን እኚሁ ምንጭ ገልጸዋል።

ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ዛሬ ሐሙስ ታሕሳስ 10 2017 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረው የመፅሐፍ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታውቋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ነው የዘገበው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

19 Dec, 12:30


📌"ቅደመ ጥምረት ለመገናኘት መዘጋጀት"የተሰኘ ልዩ የፍቅር ግንኙነት ስልጠና ቅዳሜ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

- በልባችሁ የፃፋችሁት የፍቅር ታሪክ ምንድነው?

- የህይወት መንገዳችሁ በትዳር እንዲሆን ከወሰናችሁ በኋላ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ስታስቡ  "ትክክለኛው" ሰው ብላችሁ በልባችሁ ያሰባችሁት ሰው ለምን የለም?

- ያለፈው ያልተሳካው  የፍቅር ግንኙነት ለምን አልተሳካም? በልባችን ምንስ ጥሎ  አለፈ?

- የፍቅር ግንኙነት ከመጀመር በፊት እራሴ ጋር ምን ልጨርስ?

-በትክክል የምፈልገው ምንድነው?

ካነበብናቸው መፅሐፍት፣ከሰማናቸው ታሪኮች፣ሙዚቃዎች፣ካደግንበት ማህበረሰብ፣ከኖርነው ኑሮ፣ካልተሳኩ የፍቅር ግንኙነት/ቶች ተነስተን በልባችን የፃፍነው የፍቅር ታሪክ አለን።

-በፍቅር ግንኙነት መንገድ ላይ ከሚመጣው ሰው ጋር ይህን በልባችን የሰራነውን የፍቅር ታሪክ እንኖረዋለን።

እነዚህን ጉዳዮች እንመክርባቸው ዘንድ ቅድመ ጥምረት የተሰኘ  አስደሳች፣ መስተጋብራዊ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም አዘጋጆተናል።

ስልጠናው የግንኙነት አቅምን ለማወቅ እና ለጤናማ፣ አስደሳች እና ዘላቂ አጋርነት የሚያስፈልጎትን  ክህሎቶች ለመማር የሚረዳ  የስልጠና ፕሮግራም ነው።
 
ካልተሳካ የፍቅር አዙሪት ለመላቀቅ ፣ እዉነተኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እና ለዘላቂ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ለመገንባት አሁኑኑ ይደውሉ ...0946-444445
ቀን :-ቅዳሜ፣ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም
ሠዓት:ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ቦታ :- ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ :-300 ብር ብቻ

       ኑ ና ለፍቅር ተዘጋጁ!!
ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር ማዕከል
https://t.me/+ESVZ5qsyls9lODJk

📌Ads

Event Addis Media

19 Dec, 04:45


📌የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ "HIN GAABBU" ወይንም "አልፀፀትም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ዛሬ ሐሙስ በፈረንጆች  December 19,2024 በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ታህሳስ 10 2017 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ ይመረቃል ተብሏል።

መጽሐፉ ከኬንያ ናይሮቢ በተጨማሪም በተለያዩ ሀገራት እንደሚመረቅም ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

19 Dec, 04:45


📌ዋዋጎ ትውፊታዊ ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው

በታረቀኝ ብርሃኑ ተደርሶ በጥላሁን ዘውገ የተዘጋጀው "ዋዋጎ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ትውፊታዊ ተውኔት ለመድረክ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ትውፊታዊ ተውኔት ላይ  ተስፋዬ ይማም፣በፍቃዱ ከበደ፣ ጥላሁን ዘውገ ፣ወይንሸት አበጀ እና ሌሎችም እንደሚተውኑበት ተገልጿል።ተውኔቱም አርብ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ለመድረክ እንደሚበቃ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

18 Dec, 19:26


📌የኢሳት ቲቪ ዜና አንባቢ ከስራ ታገደች

ሰሞኑን የኢሳት ቴሌቪዥን የዜና አንባቢ ትዕግሥት ተስፋዬ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቆሴ ወረዳ የተመለከተ ዜና ስታነብ ቆሴ የሚለውን ስም ለመጥራት ሲያስቸግራት ያለውን ቪዲዮ በቲክቶክ ገጿ ላይ በመለጠፍ የተለያዩ ትችቶችን ስታስተናግድ ነበር።

ኢሳት ቴሌቪዥን ይህን ተመልክቶ ዜና አንባቢዋን እና የተቆረጠውን ቪዲዮ አሳልፎ የሰጣትን ባልደረባ ከስራ ማገዱ ተሰምቷል።

ዜና አንባቢዋ በማህበራዊ ትስስር ገጿ ይቅርታ መጠይቋ ይታወቃል።

📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

18 Dec, 13:00


📌በደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" መጽሐፍ ላይ የፊታችን ቅዳሜ ዳሰሳና ውይይት ይካሄዳል

ልዩ መርሐግብር:- የመፅሐፍ ዳሰሳ እና ውይይት

የመፅሐፉ ደራሲ :- ሕይወት ተፈራ

ዳሰሳ አቅራቢዎች :
1.በድሉ ዋቅጅራ /ዶክተር ደራሲ ገጣሚ /
2.ይኩኖአምለክ መዝገቡ / ወመዘክር ዳይሬክተር/
3.ተስፋዬ እሸቱ /ተባባሪ ኘሮፌሰር/
4.ሀብቱ ግርማ /ጋዜጠኛ/
5. ኤፍሬም ስዩም (ገጣሚ እና ደራሲ)

የፕሮግራም አወያይ :- መሰረት አበጀ /መምህር/

ለውይይት የተመረጠው መጽሐፍ:- ተድባብ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት

ቦታ:- አራት ኪሎ ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ውስጥ

ቀን:- ቅዳሜ: ታህሳስ 12 2017 ዓ. ም : ጠዋት ከ4:00 እስከ 6:30 ድረስ::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

17 Dec, 13:07


📌የፎቶግራፍ አውደርዕይ በሳይንስ አካዳሚ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ከአዲስ አበባ ፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል፡፡

በዚህ አውደርዕይ ታዋቂ ባለሙያዎች አንቶኒዮ ፍዮሬንቴ፣ ሙሉጌታ አየነ፣ ማኅደር ኃይለሥላሴ፣ ናሆም ተስፋዬና ሚካኤል ጸጋዬ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

አውደርዕዩ ቅዳሜ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም 10፡00 ላይ በአካዳሚው ሙዚየም በይፋ ይከፈታል፡፡ እርስዎም በአክብሮት እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡

የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል፡፡
ከፒያሳ ወደ ውንጌት መስመር በሚወስደው ጎዳና - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ -
በተለምዶ ወረዳ ስምንት ተብሎ በሚጠራው ቀጭን መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ወይንም ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል
https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://t.me/+VZQIhKm-NoAwYjM0

ለተጨማሪ መረጃ በ0911838281 ይደውሉ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

14 Dec, 10:42


📌የየሺህ ጋብቻ ብራንድ አምባሳደሮች

አርቲስት ተስፋዓለም ታምራትና ቃልኪዳን አበራ እንዲሁም አርቲስት ይገረም ደጀኔ እና ፅዮን ዮሴፍ የዘንድሮው የ"የሺህ ጋብቻ" የጋብቻ ፌስቲቫል ብራንድ አምባሳደር በመሆን ተሹመዋል።

በያሜንት ኤቨንትስ የሚዘጋጀው "የሺህ ጋብቻ" የዘንድሮው የጋብቻ ሥነሥርዓት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ 1ሺህ ጥንዶችን እንዲሁም 250 የሚደርሱ ጥንዶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በማካተት በአጠቃላይ ከ1250 በላይ ጥንዶች የፊታችን ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጋብቻቸውን ይፈፀማሉ።

በዚህ ግዙፍ የጋብቻ ሥነሥርዓት በተለየ መልኩ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ከ25 ሺህ በላይ የቡና ሲኒ እንዲሁም 2017 ኪ.ግ የሚመዝን ባህላዊ ዳቦ ለታዳሚዎች  ይቀርባል ተብሏል።

ሁነቱንም በዓለም ድቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲስፍር ለማድረግ የሚሠራበት ታላቅ ዝግጅት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሺህ ጋብቻ ትልቅ ዓላማ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት አዲስ አበባን የሃኒሙን ማዕከል ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጿል።

አጠቃላይ ለዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው በጀት 68,997,500 ብር እንደሆነ ተነግሯል።

"የሺህ ጋብቻ"  ከዚህ ቀደም በ2005 እና በ2016 ዓ.ም ስኬታማ የብዙኃን  ጋብቻዎችን አከናውኗል።

የጋብቻ ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

07 Dec, 08:06


📌8ኛው ኦዳ አዋርድ ተካሄደ

በ2010 ዓ.ም  የተለያዩ የኦሮሞኛ ቋንቋ ሙዚቀኞችን እና አርቲስቶችን በመሸለም የተጀመረው ኦዳ አዋርድ ለ8ኛ ጊዜ ሽልማቱን አከናውኗል። በዘንድሮው ሽልማቱም ከሀገር አልፎ የአፍሪካ ሀገራት አርቲስቶችን አካትቶ ሽልሟል።

በጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማርያም የተጀመረው ኦዳ አዋርድ በበሻቱ መልቲሚዲያ እና በሌሎች አጋር አካላት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ሲሸልም ቆይቶ 8ኛውን ሽልማት ከኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመኾን የ2017 መድረኩን አካሂዷል።

ዩጋንዳዊውን ኤዲ ኬንዞ እና የኤርትራዋ ሚለንን ጨምሮ ከስምንት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት 18 አርቲስቶች በሽልማቱ ተካትተዋል።

የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ እና የምርጥ መጽሐፍ ሽልማቶች የተሰጡ ሲኾን በ2016 ዓ.ም ተስፋ የተጣለባት ድምጻዊት አሳንቲ አስቹ ተሸላሚ ኾናለች።

የዓመቱ ምርጥ ሴት ድምጻዊት ለምለም ኃይለ ሚካኤል ዋሊኒ በተሰኘው ሙዚቃ አሸናፊ መኾን ችላለች።

የ2016 ዓ.ም ምርጥ የዘመናዊ ሙዚቃ አሸናፊ  ሲቦይ አጃም ኾኗል።

የ2016 ዓ.ም ምርጥ የጥንድ ሙዚቃ አደም መሐመድ እና ጫልቱ ቡልቶ አሸንፈዋል።

የ2016 ዓ.ም የሕይዎት ዘመን ተሸላሚ የጉራጊኛ ድምጻዊ ደምሴ ተካ ኾኗል።

ሌላኛው በሕይዎት ዘመን ተሸላሚ ደግሞ ክቡር ዶክተር ኪሮስ ዓለማየሁ የተሸለሙ ሲኾን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ምርጥ የምሥራቅ አፍሪካ አርቲስት ሽልማትን ድምጻዊት ሚለን አሸንፋለች።

የዩጋንዳው ኤዲ ኬንዞ፣ የሩዋንዳው ብሩሲ ሜሎዲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሌሎች አርቲስቶችም በልዩ ልዩ ዘርፎች አሸንፈዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

07 Dec, 08:06


📌የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል 

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በመጪው  ታህሣሥ ወር በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ይካሄዳል።

ፌስቲቫሉ  የጎፍ ኢንተርቴይመንት ከኢፌዴሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ከኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ጋር በጋራ መተባበር ያዘጋጁት ነው።

ይህ የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ከታህሣሥ 11 እስከ ታህሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት  በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

ዝግጅቱም የብሪክስ ሀገራት የፊልምና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል ማስጀመሪያ ልዩ መርሐግብር ነው።

በፌስቲቫሉ ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው"ሂሩት አባቷ ማነው ?" ጨምሮ በሁለቱም ሀገራት የተመራረጡ ታላላቅ ፊልሞች የሚታዩ ሲሆን ፣ የፓናል ውይይቶች ፣ወርክሾፖች ፣እና የትውውቅ መድረኮች የሚፈጥረ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዘርፍ መልካም አጋጣሚን የሚፈጠር ትልቅ መድረክ ነው ተብሏል።

በዚህ ታላቅ ፌስቲቫል የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ከቻይና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የፊልም ባለሞያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኙበታል።

ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆየው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ስድስት ኪሎ በሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

06 Dec, 05:09


📌የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት

ዓመታዊው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በግዮን ሆቴል ለ4ኛ ጊዜ ዛሬ አርብ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ይከፈታል።

ይህ 100 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ዓመታዊ ዝግጅት ከህዳር 27 እስከ እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

100 ድርጅቶች ስራቸውን በሚያስተዋውቁበት በዚህ ዓውደርዕይ ላይ በመገኘት ስለተቋማቱ ስራ መረጃ አግኙ አዲስ ትስስሮችን ፍጠሩ ተብላችኋል።

የዝግጅቱ መግቢያ በነጻ ነው።

ማስፈንጠሪያውን ተጭነው ይመዝገቡ https://forms.gle/RKZ2moy9G6SUgNK7A

Event Addis Media

05 Dec, 16:25


📌አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ አካሂዷል።

ኢ/ር ሃይለእየሱስ ፍስሀ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው ሲመረጡ፤ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።

ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጊዮን ሆቴል ሲያካሂድ ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩትን ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚዎችንም መርጧል።

አንጋፋዋ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ፣አቶ ሲሳይ ዳኜ ፣ደ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ፣አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ፣አቶ ሸሀመለ በቀለ፣አቶ በለጠ ወልዴ፣ ወ/ሮ አሰፋሽን ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ተካተዋል።

ፌዴሬሽኑ አለብኝ የሚለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ አርቲስቶችን ወደ ስራ አስፈፃሚ በማምጣት የማርኬቲንግ ስራዎችን ለመስራት እንዳሰበ ለማወቅ ተችሏል።

ቀደም ተብሎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ላይ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ግብዣ ቀርቦለት ሳይቀበለው እንደቀረም ከታማኝ ምንጭ ለመረዳት ተችሏል።

በቀጣይ ተመራጮችን በባላገሩ ሜዳ ፕሮግራም ላይ ይዘን እንቀርባለን።

Via:- ባላገሩ ስፖርት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

05 Dec, 08:31


📌ደራሲና ገጣሚ ደበበ ሰይፉ  ያነባቸው የነበሩት 650 የግል መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተመፅሀፍት ሊበረከቱ ነው፡፡

ህይወቱ ካለፈ 24 ዓመት  ያለፈው የገጣሚ ፣ተመራማሪና የዩኒቨርሲቲ መምህር ደበበ ሰይፉ    የግል መፅሀፎች ለአብርኾት ቤተመፅሀፍት ሊበረከቱ እንደሆነ ተሰማ።

በጥልቅ አንባቢነቱ የተመሰከረለት ደበበ ሰይፉ ከ650 በላይ የመጻህፍት ዐይነቶች ነበሩት ህዳር 27 2017 ዓ.ም መፅሀፎቹ ለአብርሆት ይበረከታሉ ተብሏል፡፡

ገጣሚ ደበበ ሰይፉ ከ 1960ዎቹ ጀምሮ በቴአትር እና በሥነ ፅሁፍ መምህርነት ያገለገለ ሲሆን የህይወት ታሪኩም በተወዳጅ ሚድያ  በሲዲ በድምፅ ዶክመንተሪ ተሠርቶ መመረቁ ይታወቃል። "የብርሀን ፍቅር" እና "ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ" የተሰኙ የግጥም መድበሎንችም  ያስነበበን የኪነ ጥበብ ሰው ነበር።

ይህንኑ የመፅሀፍ ርክክብ ምክንያት በማድረግ የደበበ ሰይፉ ቤተሰቦች ከተወዳጅ ሚድያ ጋር  የጀመሩት የማህበራዊ ሚድያ የንባብ ዘመቻ እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

05 Dec, 08:31


📌"ነገን አብረን እንሳል" አውደርዕይ ነገ ይከፈታል

በስልሳ ተጽዕኖ ፈጣሪ አካልጉዳተኛ ሠዓሊያን የተዘጋጀው  የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ህዳር 27 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይከፈታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

03 Dec, 12:15


📌የወር ወንበር" ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል!

"የወር ወንበር" ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በየወሩ የሚዘጋጅው "የወር ወንበር" መሰናዶ በዚህ ወር "ሐተታ ፀንሰ ሐሳባዊነት" በሚል ርዕስ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ውይይት ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ ሠዓሊና ቀራጲ በቀለ መኮንን የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

03 Dec, 12:15


📌የኹለተኛው ቤተ-መቅደስ ዳሰሳ" እሁድ ይመረቃል

"የኹለተኛው ቤተ-መቅደስ ዳሰሳ"የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ይመረቃል ተብሏል።

በቢንያም ታደሰ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከ9:30 ጀምሮ ሳር ቤት በሚገኘው በኢቫንጀሊካል ቴኦሎጂካል ኮሌጅ(ETC) ይመረቃል።በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕ/ር አባ ዳንኤል አሰፋን ጨምሮ የተለያዩ ኃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

03 Dec, 12:15


📌ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ

በኢትዮጵያ ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ኢኒሼቲቭ የተባለ ተቋም የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ ስራ እንደጀመረ በዛሬው ዕለት በይፋ አስታውቋል።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ቴክኖ ሰርቭ ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን አብረው እንደሚሰሩም ገለጸዋል።

በይፋዊ የስራ ማጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ እንደተገለፀው ጥምረቱ የስንዴ ዱቄት አምራች እና የምግብ ዘይት ፋብሪካዎችን በቫይታሚን በማበልፀግ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ተግልጿል።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለ140 ፋብሪካዎች የቴክኒካል ድጋፍ እና ለተጨማሪ 40 ፋብሪካዎች ደግሞ ስልጠና መስጠቱንም ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ  አሁንም አሳሳቢ የሆኑ የአመጋገብ ችግሮች እያጋጠሟት መሆኑ ተነግሯል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሠረት ከአምስት ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት 22 በመቶ ከክብደታቸው በታች መሆኑም ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

02 Dec, 09:10


📌ለሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ህክምና የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ ቀን አውደርዕይና ጨረታ ተዘጋጀ

የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "ነፃነት" የተሰኘና ለአንድ ቀን  ብቻ የሚቆየ የሥዕል አውደርዕይና ጨረታ የፊታችን ህዳር 26 ቀን 2017 ይካሄዳል ተብሏል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ በስዊድን ለሚያደርገው ህክምና ወጪን ለመሸፈን ነጻነት የተሰኘ የስዕል ኤግዚብሽን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በመጪው ሃሙስ ሕዳር 26 ቀን በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ በሚካሄደው የሥዕል አውደርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ሰዎችና ሠአሊዎች ይገኛሉ ተብሏል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ እንደገለፀው ከዚህ የሥዕል አውደርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በቅርቡ ስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የእግር ህክምና ወጪው 3 ሚልየን ብር እንደሆነ ተናግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

02 Dec, 07:43


📌ተወዳጇ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ በሲትኮም ድራማ እየመጣች ነው

በተለያዩ የቴሌቪዥንና ሬድዮ ድራማዎች እንዲሁም ፊልሞችና ተውኔቶች ላይ የምናውቃትና ከቴሌቪዥን ድራማዎች ጠፍታ የቆየችው አንጋፋው አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ በአዲስ የቴሌቪዥን ሲትኮም ድራማ እየመጣች እንደሆነ ተሰምቷል።

አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የምትሳተፍበት ሲትኮም ድራማ "ዞሮ መውጫዬ"የተሰኘ ርዕስ ያለው እንደሆነም ተገልጿል።

ይህ ሲትኮም ድራማ አርቲስት ሙሉዓለም ታደስ እና አርቲስት ሚካኤል ታምሬ የተጣምሩበት እንደሆነም ተነግሯል። ድራማው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍም ተሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

02 Dec, 07:43


📌"የዱር አበባ" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

የገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ "የዱር አበባ" የተሰኘ አዲስ የግጥም መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 28 ከቀኑ 11:00 ጀምሮ መገናኛ(24) በሚገኘው ሞሰብ የሙዚቃ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በድምቀት ይመረቃል ።

በዕለቱም በዝግጅቱ ላይ ረድኤት ተረፈ፣ግሩም ተበጀ፣አልዳ ግዛቸው ፣ሰለሃዲን አሊ፣ምግባር ሲራጅ፣ፍቃዱ አየለኝ፣ሰይፉ ወርቁ ፣መዘክር ግርማ፣አንተነህ አክሊሉ፣አንዱ ጌታቸው፣እልፋገድ እምሻው ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Dec, 15:59


📌የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ ሆኗል

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ በመሆን ልዩ ዋንጫ፣ አንድ ሚሊዮን ብር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ነፃ የትምህርት እድል አሸናፊ ሆኗል።

2ኛ ሚኪያስ ጌቱ

3ኛ ማቲያስ አንበርብር

4ኛ ብዙአየሁ ሰለሞን

ውጤቱ የ2 ዙር የዳኞች ውጤት እና ተመልካቾች በ8600 በፅሁፍ መልእክት የሰጡት ድምፅ ተደምሮ ነው አሸናፊው የተለየው ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

30 Nov, 08:22


📌የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍጻሜ ውድድር

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍጻሜ ውድድር ነገ እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል።

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ አይዶል ዝነኞች ከአዳዲሶቹ ምርጦች ጋር እሁድ በዓመቱ ኮከብ ልዩ ፕሮግራም ላይ ይገናኛሉ ተብሏል።

ዳግማዊት ፀሀዬ፣ ዳዊት አለማየሁ፣ ተመስገን ታፈሰ፣ አዝመራው ሙሉሠውና ሌሎች የአይዶል ፈርጦች አዳዲሶቹን ኮከቦች ያገኟቸዋል።

እሁድ ህዳር 22 በሚካሄደው የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ኘሮግራም ላይ አርቲስቶቹ ልዩ ቆይታ ይኖራቸዋል።

1 ሚሊየን ብር በሚያሸልመው የዓመቱ የፍፃሜ ውድድር በሙዚቃ ድግስ ደምቆ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁሉም ቻናሎች በመላው ዓለም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በቀጥታ ይተላለፋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

30 Nov, 08:22


📌የ"ቅኔ ሰርከስ"የሰርከስ ድግስ ዛሬ ይካሄዳል

የቅኔ ሰርከስ የሰርከስ ደግስ ልዩ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ጎሮ አካባቢ በሚገኘው በቅኔ ሰርከስ ማዕከል ይካሄዳል።

ይህ የሰርከስ ዝግጅት መግቢያው ለአዋቂ 400 ብር ሲሆን ለህፃናት 200 ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

29 Nov, 08:28


📌ደራሲና ተዋናይ ደሞዝ ጎሽሜ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት እሁድ ይካሄዳል።

ደራሲና ተዋናይ ደሞዝ ጎሽሜ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 79ተኛ መድረክ "ኢትዮጵያዊ ጥበብ" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ እሁድ ሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

29 Nov, 08:28


📌"መሀል ከተማ" ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በኤርሚያስ ታደሰ የተዘጋጀውና "መሀል ከተማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የአማርኛ ፊልም ዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

ይህ ፊልም ሕዳር 20፣ 21፣ 22 በይፋ ይመረቃልም ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

28 Nov, 13:13


📌"አሚን አሚንዬ" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

የገጣሚ መሐመድ እድሪስ ካሣ"አሚን አሚንዬ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ላይ ሀሴን ከድር ፣ቴዎድሮስ ካሣ፣ረድኤት አሰፋ፣እሱባለው አበራ፣ሚካኤል ምናሴ፣መስፍን ወንድወሰን ፣ዮሴፍ ይድነቃቸው ፣ያስሚን ሰፋ፣ፈይሰል አሚን፣ሐብታሙ ሀደራ የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ሙኒራ አብዱራህማን መድረኩን ትመራዋለች።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

27 Nov, 11:15


📌"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ "ጠይም ጤዛ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።በዕለቱም አንጋፋው እና ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን እንደሚያገሩ ተገልጿል።

"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ሐምሳ የግጥም ስራዎችን በውስጥ የያዘ ሲሆን 94 ገፆች ተቀንብቦ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።ጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም በሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት ላይ የዓመቱ ምርጥ የግጥም መደብል አሸናፊ የሆነበት "ኮብላይ ዘመን" መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል።

በተጨማሪም በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ)አወዳዳሪነት ከተለያዩ ደራሲዎች ጋር በጋራ በተሰናዳው "ሠላሳዎቹ" የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ውስጥም ስራው ታትሞለታል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Nov, 14:52


📌"መንግሥቱ ኃይለማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"መጽሐፍ ሁለተኛ እትም ለንባብ በቃ

በደራሲ ይታገሱ ጌትነት የተዘጋጀው "መንግሥቱ ኃይለማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"መጽሐፍ ሁለተኛ ህትመት ለንባብ በቅቷል።

የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያው እትም በሀገር ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሽጦ ከገበያ ጠፍቶ ነበር። ዳግም ህትመቱ ከዛሬ አንስቶ በዋልያ አሳታሚ አማካኝነት በሁሉም የመጽሐፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል።

በውጭ ሀገር መጽሐፉን ለማግኘት አማዞን ላይ በ https://a.co/d/6V7LBpt መጠቀም ይችላሉ።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Nov, 14:51


📌ይህ "Event Addis Media" ነው 💥

የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይወዳጁ+ያጋሩ!

ቴሌግራም:https://t.me/EventAddis1

ቲክቶክ:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rgsgcVSeW7&_r=1

Website:https://eventaddis.com/

Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851

አስተያየትዎን ይጻፉልን: @Tmanaye

Event Addis Media

25 Nov, 11:12


📌ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በአሜሪካ ኤምባሲ

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ፕሮግራሙ በተወዳጅ የፍቅር ዘፈኖቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥር እና በአዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ደግሞ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ድምፃዊ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ሚካኤል በላይነህን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች "ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ ማክሰኞ ሕዳር 17 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል በላይነህ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ነገ ማክሰኞ ሕዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Nov, 17:30


📌"የፍቅር ካቴና" ተውኔት በልዩ ዝግጅት ነገ ይቀርባል

ድርሰት እና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንት ፅጌ የሆነው "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ነገ እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በልዩ ዝግጅት በዓለም ሲኒማ ይታያል።

በተውኔቱ ላይ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ሚኪ ተስፋዬ ፣ወይንሸት አበጀ፣ አሸናፊ ማህሌት ይተውኑበታል።

የቴአትር ወዳጆች ዓለም ሲኒማ መጥታችሁ  የእረፍት ቀናችሁን በፍቅር ካቴና ቲያትር እየተዝናናችሁ ጥሩ ጊዜን እንድታሳልፉ ተጋብዛችኋል ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Nov, 05:30


የጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ "የነፍስያ ድምጾች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ አንጋፋ እና ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Nov, 05:23


📌የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ ይበቃል

የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ ዋልያ መጻሕፍት እንደሆነ ተገልጿል።

ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Nov, 05:23


📌"የዕድገት ጉዟችን በዘመናት መካከል"

የዕድገት ጉዟችንን በዘመናት መሐል የሚቃኝ ፓናል ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 14 2017  ዓ.ም ይደረጋል፡፡

በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና  ቤተ-መጽሀፍት  አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ በሚደረገው በዚህ መርሐግብር ታላላቅ ሰዎች ይታደማሉ፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ የአርካይቭ ማዕከል ምረቃ ስነስርአት ላይ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ- መንግስት የተመዘገቡ እድገቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች በውይይት አቅራቢዎች ይዳሰሳሉ፡፡

በፓናሉ ላይ ንግግር ከሚያደርጉት መካከል በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከፕላን እና በጀት ጋር ከፍተኛ ኃላፊነት የነበራቸው አቶ በቀለ እንደሻው እና አቶ ተድላ ተሾመ ይገኙበታል፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት  የአርካይቭ ማዕከሉን በሚያስመርቅበት ዕለት  የድርጅቱ መሥራቾች እንዲሁም ደጋፊዎች የሚታደሙ ሲሆን  በዕለቱም በፊልም ባለሙያው የማነ ደምሴ የተዘጋጀ 20 ደቂቃ የጊዜ ፍጆታ ያለው ዘጋቢ ፊልምም ይቀርባል፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት በ2014 የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን  የተለያዩ መታሰቢያዎችን  የማቋቋምና የማስተዳደር ብሎም የማሻሻል ሥራዎችን የሚሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም ታሪክ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ጠቃሚ ተግባራትን የሚያከናውን ሲሆን  ነጻ የትምህርት እድሎችንም  ይሰጣል፡፡

የዚህ መርሀ ግብር ሁነት አዘጋጅ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ሲሆን መድረኩን በመምራት ደግሞ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ  ድርሻውን እንደሚወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Nov, 18:44


📌 የሮፍናን ኮንሰርት በአዳማ  ተሰርዘ

ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቅዳሜ ህዳር  14 2017 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ ይዞለት የነበረው "የኔ ትውልድ" ኮንሰርት ሙሉበሙሉ እንደተሰርዘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMh7w27h3/

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Nov, 10:36


📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

50ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ተመስገን ዋና " ሳይንስ እና ኃይማኖት:በተዋሥኦ መካከል" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Nov, 10:36


📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ ዶክተር ዳዊት አሰፋ እና ዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ መጻሕፍት ደግሞ "የሁሉ" እና "ኦቲዝምና አንዳንድ ከያንያን ስለሚያጠቃቸው የአዕምሮ ሕመም" ናቸው።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Nov, 10:36


📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Nov, 09:36


📌አለማየሁ ሄርጶ አዲስ አልበም ሊያወጣ ነው

ተወዳጁ ድምፃዊ አለማየሁ ሄርጶ አዲስ አልበም ሊያወጣ መሆኑን የሙዚቃ ባለሙያው አለማየሁ ደመቀ ለሁሉ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ተናግሯል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMh74T5gA/

Credit: ሁሉአዲስ የሬድዮ ፕሮግራም።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Event Addis Media

22 Nov, 08:12


📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ


📍 "የሕይወት ታሪክ"

ድርሰት: ነብዩ ባዬ እና ቢኒያም ወርቁ
አዘጋጅ: ነብዩ ባዬ እና ቢኒያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

18 Nov, 10:28


📌ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ወደ መድረክ ልትመለስ ነው

ለረጅም ጊዜ ከመድረክ እርቃ የቆየችው ሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ በሚካሄድ አንድ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ስራዎቿን እንደምታቀርብ ተሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhtvQybR/

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

18 Nov, 09:54


📌 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ከ34 ዓመታት በኃላ ለዕይታ ቀርቧል።

እነሆ ዝርዝሩን በድምጻችን ይስሙ: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

18 Nov, 08:53


📌የዝነኛው የቴአትር መምህር መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የ"በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" "የአና ማስታወሻ"ን ጨምሮ በርካታ ተውኔቶችን ያዘጋጁትና  በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ት/ክፍል ውስጥ ተፈሪና ተወዳጅ የሆኑት ዶ/ር ተሻለ አሰፋ ያዘጋጁት "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊን " መጽሐፍ ሊመረቅ እንደሆነ ተሰምቷል።

እነሆ ዝርዝሩን: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/

Event Addis Media

17 Nov, 18:34


📌ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ !

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ ስርጭቱን ጀመረ

ከዚህ ቀደም በድረገፅ፣ በቴሌግራም እና በፌስቡክ አማራጮች ብቻ ዕለታዊ ተመራጭና አማራጭ የኪነጥበብ እና ሁነት መረጃዎችን ሲያቀረብ የቆየው ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ የማኀበራዊ ትስስር ገፅ ከዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መረጃዎችን ማቅረብ ጀምሯል።

ሊንክ: tiktok.com/@eventaddis1

በተጨማሪም በቅርቡ በሌሎችም የማህበራዊ ትስስር ገፅ አማራጮች እንመጣለን።እናመሰግናለን ።

ቴሌግራም: https://t.me/EventAddis1

ድረገፅ: https://eventaddis.com/

Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851

Event Addis Media

16 Nov, 11:48


📌የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

16 Nov, 11:47


📌 "ለዝና" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ

የወጣቱ ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ "ለዝና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃ ትላንትና ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ቀርቧል።

የዚህ ነጠላ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ በድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር እና ሚክስ ማስተር ሮቤል ዳኜ ተሳትፎበታል።

ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ ከዚህ ቀደም "ነይ " "አይናለም" "አይከረም" የተሰኙ ነጠላ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

15 Nov, 07:05


📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

15 Nov, 07:02


📌"ታላላቆችን እናክብር" በተሰኘ ልዩ መርሐግብር 13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅና ሊበረከትላቸው ነው

በተወዳጅ ሚዲያ የተዘጋጀውና በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች የሚመሰገኑበት ልዩ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ ህዳር 7 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል።

በዚህ ልዩ የምስጋና ዝግጅት ላይ 13 የቀድሞ  ጋዜጠኞች ዕውቅና ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ ተብለው የሚጠበቁት ተመስጋኝ ጋዜጠኞች አቶ አስፋው ኢዶሳ፣ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ፣አቶ ሀዲስ እንግዳ፣አቶ ዋጋዬ በቀለ፣ወይዘሮ ሚሊየን ተረፈ፣አቶ ሀይሉ ወልደፃድቅ፣አቶ ተሾመ ብርሀኑ ከማል፣አቶ ተክሉ ታቦር፣ አቶ ይንበርበሩ ምትኬ፣ አቶ ታዬ በላቸው፣አቶ ግርማይ ገብረፃድቅና አቶ ኢሳያስ ሆርዶፋ ናቸው።

ዝግጅቱ ላይ እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸው ያለፈው የሚድያ ሰው ሙለጌታ ወልደሚካኤልም በልጆቻቸው አማካይነት ዕውቅናው ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

እነዚህ ዕውቅና የሚቸራቸው አንጋፋ የሚድያ ሰዎች ከዚህ ቀደም ተገቢውን ዕውቅና ሳያገኙ የቀሩና በሌሎች የሽልማት መርሀግብሮች ያልተካተቱ ነበሩ።

በሁሉም ተመስጋኞች የህይወት ታሪክ ላይ በቂ ጥናት እና ምርምር መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።

በዕለቱ የቀድሞ ጋዜጠኞችን የቆየ ድምፅና ቪድዮ የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ መሰናዶ የሚኖር ሲሆን የሙያ ማህበራት፣የሚድያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህራን እና ሌሎችም ታላላቅ እንግዶች ይታደማሉ፡፡

የመርሀግብሩ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆን ከዚህ ቀደም የ45 ሰዎችን  ታሪክ  በሲዲ የ20  ሰዎችን ታሪክ  ደግሞ  በመፅሐፍ ያሳተመ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

14 Nov, 11:51


📌በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ለዕይታ ሊቀርብ ነው

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ባለ ቀለም ፊልም ወደ ዲጂታል አስቀይሮ ሊያስመርቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽን አማካኝነት ሀገራዊ ዘዉግ ላይ ተንተርሶ የተሰራውና "አስቴር" የተሠኘው አትዮጵያዊ ፊልም የአጻጻፍ ደረጃው ከፍ ያለና ከድርሰት እስከ ፕሮዳክሽን ሙሉ በሙሉ በሀገር ባለሞያዎች የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"አስቴር" የተሰኘው የመጀመሪያው ፊልም የዛሬውን የፊልም ኢንዱስትሪና የፈጠራ ክህሎትን ለማሳደግ መነሻ መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ፤ ቢሮው በቴክኖሎጂ ምክንያት ለዕይታ ሳይበቁ የቆዩ የቀደምት የፊልም ሥራዎችን ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በማፈላለግ ዲጂታላይዝድ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

የፊታችን ህዳር 8 ቀን 2017 ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የፊልሙ ባለቤቶች፣ ተዋናይናዮችና የኪነ ጥበብ አፍቃሪያን በታደሙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

14 Nov, 11:51


📌የዘንድሮው "የሺህ ጋብቻ" ጥር 18 ይካሄዳል

በያሜንት ኤቨንትስ የሚዘጋጀው "የሺህ ጋብቻ" የዘንድሮው የጋብቻ ሥነሥርዓት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

"የሺህ ጋብቻ"  ከዚህ ቀደም በ2005 እና በ2016 ዓ.ም ስኬታማ የብዙኃን  ጋብቻዎችን አከናውኗል።

ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ 1ሺህ ጥንዶችን እንዲሁም 250 የሚደርሱ ጥንዶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በማካተት በአጠቃላይ ከ1250 በላይ ጥንዶችን የፊታችን ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለመዳር አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አዘጋጆቹ ዛሬ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህ ግዙፍ የጋብቻ ሥነሥርዓት በተለየ መልኩ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ከ25 ሺህ በላይ የቡና ሲኒ እንዲሁም 2017 ኪ.ግ የሚመዝን ባህላዊ ዳቦ ለታዳሚዎች  ይቀርባል ተብሏል።

ሁነቱንም በዓለም ድቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲስፍር ለማድረግ የሚሠራበት ታላቅ ዝግጅት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሺህ ጋብቻ ትልቅ ዓላማ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት አዲስ አበባን የሃኒሙን ማዕከል ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጿል።

አጠቃላይ ለዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው በጀት 68,997,500 ብር እንደሆነ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

14 Nov, 11:51


📌ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት እሁድ ይካሄዳል።

ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 78ተኛ መድረክ "የኮሜዲው ዓለም ከሳቅ ባሻገር" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ እሁድ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

13 Nov, 13:58


📌"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የገጣሚ ደጀኔ ተስፋዬ "የመንገዴ መንገድ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ትላንት ማክሰኞ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል።

"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ114 ገፆች ተቀንብቦ በ320 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፉን በፒያሳ ኤዞፕ በሜክሲኮ ጃዕፋር እና በአራት ኪሎው ኢትዮ ፋጎስ (Ethio Fagos) የመጽሐፍ ማከፋፈያዎች ውስጥ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

13 Nov, 13:58


📌ድምጻዊት ራሔል ጌቱ ከዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ጋር "ውዴ" በተሰኘ ሙዚቃ ድጋሚ ተጣምሩ

ከዚህ ቀደም "ኢትዮጵያዊዬ" የተሰኘ ርዕስ በተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮ አብረው የሰሩት ድምጻዊት ራሔል ጌቱ እና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ውዴ" በተሰኘ አዲስ ሙዚቃ በድጋሚ እንደተጣመሩ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

የድምጻዊት ራሔል ጌቱ"ውዴ" ሙዚቃ ነገ አርብ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

13 Nov, 13:57


📌የሥዕል አውደርዕይ

የሠዓሊ እስጢፋኖስ ሰለሞን "Oppressed passion" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።ይሄ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሕዳር 29 ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

13 Nov, 13:57


📌የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ

የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚሆን የቢዝነስ፣ የሥራ ፈጠራ፣ ትምህርት፣ የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ልዩ ዝግጅት ፊታችን ቅዳሜና እሁድ ኅዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም  ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 17:03


📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 17:02


📌ለአርባምንጭ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባሰቢያ ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ ነው።

በአርባምንጭ ከተማ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባቢያ በማስመልከት ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ እንደሆነ አዘጋጆች አስታውቀዋል።

ዛሬ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ከእሺ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት አድረገዋል። እሺ ሚዲያ ለዚህ ስታዲየም ግንባታ ቁልፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እቅዶቹን ይፋ ያደረገ ሲሆን ዝግጅቱን በሀገር ውስጥ ሬዲዮ፣ ቲቪ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች በስፋት እንዲሰራጭ በማድረግ ማህበረሰቡን በማሳወቅ ይጀመራል ተብሏል።

ዲጂታል ዘመቻዎች፣ አምባሳደሮች ታዋቂ/ተፀእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በአምባሳደርነት በመሰየም ፕሮጀክቱን እንደያስተዋውቁ ማድረግ፣ በቀጥታ ስርጭት የሚከናወን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ ስፖንሰርሺፕ፣ የሩጫ ውድድር፣ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ ኮንሰርት፣ ቶምቦላ ሎተሪ፣ በመዋጮና በልገሳዎች ገቢ ማሰባሰብ እንደታሰበ ተነግሯል።

የአፍሪካ ዋንጫ እና የአለም አቀፍ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስቴዲየም 30ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል።  እንዲሁም የመሮጫ ትራክ ስላለው የአትሌቲክስ ውድድሮችን ማስተናገድ ይችላል።

የካፍ ስታንዳርድ የሚያሟላ ካታጎሪ ሶስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እስከ 30ሺ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ስቴዲየም መሆኑ ተገልጿል።

አጠቃላይ የስቴዲየሙ ግንባታ ወጪ 3 ቢሊዮን ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ስራ 6 ወር እና ቀጣይ ሁለተኛ ዙር ምዕራፍ በ6 ወር በአጠቃላይ በአንድ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 17:02


📌የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት አካሄዱ

የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር "ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጥበብ ለሁለንተናዊ ልማትና ለሃገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል አካሄደዋል።

የባህልና ስፖርት ሚንስቴር - ሚንስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ እና ሚንስትር ዲኤታዋ ክብርት ነፊሳ አልማሃዲ በመሩት መድረክ ላይ፣ መንግሥት እና ሚንስቴር መስርያ ቤታቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ  ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ገልፀዋል።

የጥበብ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው ያሉባቸውን ችግሮች አስረድተዋል። ከተሳታፊ  ባለሙያዎቹም  መካከል ተግዳሮቶችን ብቻ ሳይቆጥሩ በተቻለ መጠን ለሃገርና ለህዝብ ጥቅም መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሚንስቴር መሥርያ ቤቱ ይህንን መድረክ አዘጋጅቶ <<ኑ - እንማከር>> ማለቱ ከባለሙያዎቹ ልዩ ምሥጋና ተችሮታል። ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በሃገር ግንባታው ረገድ መልካም ውጤት እንደሚያስገኝ ታምኖበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 12:22


📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ አርብ ይመረቃል

የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ ከገጣሚነቷ ባሻገር በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በጋዜጠኝነት እየሰራች ትገኛለች።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 12:06


📌"እንዴት ልሁን" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

በቅድስት ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በኤልያና ኢንተርቴይመንት የቀረበው "እንዴት ልሁን" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ፊልም ከሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የ"እንዴት ልሁን" ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቸሩ (ጆሲ) ነው።በፊልሙ ላይ እንግዳሰው ሀብቴ፣ሳምሶን ግርማ፣ህይወት ጌታሁን፣ቴዎድሮስ ወዳጆ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

12 Nov, 11:56


📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ይካሄዳል

ተወዳጇ አርቲስት ህሊና ሲሳይ የክብር እንግዳ የሆነችበት"መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሐሙስ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ተወዳጇ አርቲስት ህሊና ሲሳይ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

09 Nov, 07:35


📌የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አልበም ዛሬ ይመረቃል

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" አልበም ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን  2017 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ድግስ ሌሎችም የሙዚቃ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገጹ" ወዳጆቼ አዲሱን ‘አንድ ቃል’ አልበሜን ቅዳሜ ጥቅምት 30 በማርዮት ሆቴል እንደማስመርቅ ስነግራችሁ በልዩ ደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

09 Nov, 07:35


📌"የእግዜር ጣት" ተውኔት ነገ ለእይታ ይበቃል

በአንጋፋው ከያኒ ጌትነት እንየው ተደርሶ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው "የእግዜር ጣት" የተሰኘ ተውኔት ነገ እሁድ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከ10:00 ጀምሮ ፒያሳ አራዳ ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በክቡር ዶ/ር ተስፋዬ አበበ(ፋዘር ) የኪነ-ጥበባት ማዕከል ውስጥ በእይታ ይበቃል።

በተውኔቱ ላይ አላዶር ሽፈራው፣ዳግማዊ የኔዓለም፣ልዑል አስፋው፣ሔኖክ ጥላሁን፣ሰላማዊት ታሪኩ ተውነውበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

09 Nov, 07:21


📌"የእድሜ ልክ" የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል።

"የእድሜ ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው። የሠዓሊ ሚኪያስ አሰፋ "የእድሜ ልክ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነጥበብ ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይሄም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Nov, 12:18


📌"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ "ጠይም ጤዛ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ሐምሳ የግጥም ስራዎችን በውስጥ የያዘ ሲሆን 94 ገፆች ተቀንብቦ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ተሾመ ብርሃኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "እንሆ ጠይም ጤዛ ቤቷ ገብታለች። ዛሬ ከማተሚያ ቤት መደበኛ ህትመቶችን ተረክበናል። ልዩ ህትመቶን ቀድማችሁ የገዛችሁ በጣም በቅርቡ ባላችሁበት ከምስጋና ጋር እናደርሳለን።ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30 አራት ኪሎ ዋልያ መጻሕፍት ከቀን 7 ሰዓት ከ30 ጀምሮ መገኘት ለምትችሉ ከሌሎች ዕውቅ ደራሲያን ጋር እንጠብቃችኋለን። የጥበብ ውጤቶን እያጣጣማችሁ ጠይም ጤዛን በአካል ትወስዳላችሁ" ብሏል።

ጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም በሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት ላይ የዓመቱ ምርጥ የግጥም መደብል አሸናፊ የሆነበት "ኮብላይ ዘመን" መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል።

በተጨማሪም በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ)አወዳዳሪነት ከተለያዩ ደራሲዎች ጋር በጋራ በተሰናዳው "ሠላሳዎቹ" የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ውስጥም ስራው ታትሞለታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Nov, 12:18


📌10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት!

በአፍሪካ ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ አውደርዕይ የሆነው "10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት" ከዛሬ አርብ ጥቅምት 29 እስከ ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

በ10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት የመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር እንዲሁም የጀርመን ሁነት አዘጋጆችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በዝግጅቱ ላይ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚያገናኝ አውደርዕይም እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አውደርዕይ ከ30 አገራት በላይ የተውጣጡ  ከ2 መቶ50 በላይ የፋሽን ፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል።

በተጨማሪም ከ60 አገራት በላይ የሚመጡ ከ7ሺህ በላይ የንግድ አቀላጣፊዎች ይገኛሉም ተብሏል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃጨርቅ ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ የፋሽን መድረክ ሆኖ እንደቆየ ተገልጿል።

10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን ለአምስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል የሚቆይ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Nov, 08:49


📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

49ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ኤደን አባተ "እውነቻ እና የድኅረ ዘመናዊነት ውጥን"" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ታቀርባለች።ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Nov, 08:49


📌ወደ ቦሌ ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ!!

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርጥ የተፈጥሮ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ባሌና አካባቢው ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ።

Dinsho Park አዳር (Wild life)
ሐቤራ ፏፏቴ(Natural Attraction)
ጌሴ grassland
ጎባ ከተማ
ሳነቴ አምባ(wild life and the biggest plateau in Africa)
ቱሉ ዲምቱ (The second Highest point in Ethiopia)
ሪራ ቪሌጅ
ሀረና ጫካ አዳር(የዱር እንስሳት እና ከ1000 km Square በላይ የሚሸፍን Virgin Forest).....እና ሌሎች በርካታ ዉብ ስፍራዎች 😍

4 ቀን 3 ምሽት

ውስን ሰዎች ስለሚጓዙበት ምርጥዬ ሰዎች ቀድማችሁ ቦታ ይያዙ።

የስልክ አድራሻ:

+251984717207

+251933931106

Ads:

Event Addis Media

08 Nov, 04:31


📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ  ጓድ ፋሲካ ሲደልል፣ እና ኮሎኔል መርሻ ወዳጆ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የታኅሣሥ ግርግር(1953 ዓ.ም) እና የግንቦቱ መፈንቅለ መንግስት(1981 ዓ.ም) " ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

08 Nov, 04:30


📌"በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ ልዩ ዝግጅት

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ የማስፈረም፣ የጨዋታና ኪናዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡበት ልዩ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ልዩ መርሐግብር መጽሐፍ መግዛት ለማይችሉ 200 መጻሕፍት በሽልማት መልክ የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ገጣሚያኑ መሐመድ እድሪስ፣መንበረማርያም ኃይሉ፣ ቴዎድሮስ ካሣ፣አበባ የሺጥላ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ተሾመ ብርሃኑ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ደሳለኝ ቢተውና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

07 Nov, 15:33


📌የመጽሐፍ ዳሰሳና የኪነጥበብ ዝግጅት

በፍቅረ ተክለማርያም (አብየ በርሶማ) "ዘሔርሙ" እና "ሰባራ ጥላ" መጻሕፍት ላይ ዳሰሳ እንዲሁም የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመኮለት መዋዕል፣ ሰርፀ ፍሬስብሃት፣አርቲስት ሐረግወይን አሰፋ እና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

07 Nov, 15:33


📌የኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቡድን በአምስት የአውሮፓ ሀገራት ትርዒቱን ሊያቀርብ ነው፡፡

ሠላሳ አምስት አባላት ያሉትና ሙሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ የሚሳተፉበት ከተለያዩ የሰርከስ ማዕከላት አርቲስቶችን፣ የውዝዋዜ፣ ታዋቂ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችና ታዋቂ ድምጻውያንን ያካተተ ልዩ ቡድን በማዘጋጀት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኝው በታዋቂው በሰርክ ፊኔክስ “ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች” በሚል ርዕሰ ትርዒቱን ፓሪስ በፊኔክስ መድረክ፣ እንዲሁም በቤልጅዬም፣ በሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ በስዊዘርላንና በአንዶራ የሀገራችን ኢትዮጵያን ባህል፣አለባበስ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ያካተተ ሙሉ የሰርከስ ትርኢት የያዘ ቡድን ከህዳር 04 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ፈረንሳይ ሊጓዝ መሆኑን አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ/ም በቱሊፕ ኢን ኦሎምፒያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

አዘጋጆቹ ይህ ትርዒት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚሆን የሰርከስ፣ የዉዝዋዜና የሙዚቃ ባለሙያ የሚሳተፉበት ትልቅ ትርዒት መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል፡፡

አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ በተለያዩ አለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ አርቲስቶችን በማሳተፍ የወርቅ የብር የነሃስ እና ስፔሻል ፕራይዝ ተሸላሚዎች እንዲሆኑ እና  የሀገርን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረግ መልካም ገፅታዋን በመገንባት ሰርከስ የሃገር የባህል አምባሳደር እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ  በማበርከት በተደጋጋሚ የወርልድ ጊኒየስ ሪከርድ በማስመዝገብ እና ለዓለም አቀፍ  የሠርከስ ካምፓኒዎች  በማቅረብ ለብዙ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያን የስራ እድል ማመቻቸት ችሏል፡፡ 

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

07 Nov, 15:33


📌"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በገጣሚ ፋሲካው ጌታቸው የተዘጋጀው "ሎሚ ተራ ተራ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም መጽሐፍ ሲሆን በ152 ገፆች ተቀንብቦ በ350 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።

አዲስ አበባ ውስጥ ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት እነዚህን የስልክ መስመሮች 0944233603 ፣0989894675፣0909441907 ተጠቀሙ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

06 Nov, 11:10


📌የዶ/ር ተሻለ አሰፋ "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

06 Nov, 10:19


📌ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከልን በነበረበት ስፍራ መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ

ከከተማው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተገናኘ የፈረሰው የፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማእከል በነበረበት ስፍራ ዳግም እንዲገነባ ከተማ አስተዳደሩ መፍቀዱ ይታወሳል።

ማዕከሉ የሀገርን ባህልና ጥበብ ለማስተዋወቅ ካደረገው ጥረት አንጻር መንግስት በነበረበት ስፍራ የከተማውን ደረጃ የሚመጥን ግንባታ እንዲከናወን ፈቅዷል ሲሉ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ በላይ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ ግንባታውን ለማከናወን በግል አቅም ስለማይቻል ከተለያዩ ሀገራት ካሉ ኢትዮጵያውያን ገቢ ለማሰባሰብ መታቀዱን  ገልጸዋል። እንደ አዲስ ተገንብቶ መቅረቡ የበለጠ ማዕከሉ ደረጃውን እንዲጠብቅ ከማድረግ አንጻር የራሱ ላቅ ያለ ሚና ቢኖረውም ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከፍተኛ ርብርብና አቅም ይፈልጋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ግንባታው መቼ እንደሚጀመር አቶ መላኩ በውል ባይገልጹም መንግስት ባስቀመጠው ህግና ደንብ መሰረት ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንደሚሞከር ተናግረዋል። ባህል ማዕከሉ እስከዚያው ድረስ በሌላ የከተማው ስፍራ መደበኛ ስራውን እንደሚቀጥልና አሁን ላይ የተሻለ ቦታ በማማረጥ ላይ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡

እንዲህ አይነት ሀገርንና ባህልን የሚያስተዋውቁ ስፍራዎችን መንግስት ጠብቆና ህጋዊ እውቅና ሰጥቶ ማቆየቱ ከፍ ያለ ሀገራዊ ጥቅም እንዳለው ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

📍መረጃው የመናኸሪያ ሬድዮ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

06 Nov, 10:18


📌የብሔራዊ ቴአትር አዲሱ ህንፃ ተቋራጩ ከገባበት ኮንትራት ውጭ የዋጋ ጭማሪ በመኖሩ ግንባታው ተጓቷል ተባለ

ከአምሥት ዓመታት በፊት የተጀመረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ ግንባታ በዋጋ ልዩነቶች ምክንያት ተቋራጩ ከመንግስት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አራዳ ኤፍ ኤም ከምንጮቹ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን የግንባታው ተቋራጭ የነበረ ሲሆን አሁን ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።

ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ እየሰራ ቢሆንም የግንባታ ግብዓት የዋጋ ለውጥ ስላመጣ ከመንግስት እና ከደንበኛው ጋር በመነጋገር መልስ ለመስጠት እየሞከረ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በዋናነት ይህ የሆነበት ምክንያት የዋጋ ልዩነቶች በመምጣታቸው ሲሆን፥ ችግሩን ለመቅረፍ ድርድር ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።

ኦቪድ መጀመሪያ ከገባበት ውል ነገሮችን አስተካክሎ ለማምጣት በሙከራ ላይ ነውም ተብሏል።

አዲሱ የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ 19 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፥ በ7 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍና 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለግንባታው የተቆረጠ ወጪ አለው መባሉ ይታወሳል።

አምሥት ዓመታት የህንፃው ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ሰሌዳ የነበረ ቢሆንም እስከ አሁን በግንባታ መጓተት ምክንያት ሊጠናቀቅ አልቻለም።

📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

05 Nov, 11:48


📌የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳትና ቁሳቁስ ለዕይታ ሊቀርብ ነው

የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳት እና ቁሳቁስ ትውልድ እንዲያየው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተቋም ጥቅምት 29 ቀን 2017 በክብር ይቀመጣል ተባለ፡፡

በዕለቱም የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶች  እንደሚገኙ የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ታሪካዊ የሆኑ እና በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ኅያው ሆነው እንዲኖሩ ከድምጻዊያው ቤተሰቦች የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁሶችንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ ለዕይታ እንዲበቃ በባለቤትነት ይረከባል ተብሏል፡፡

ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠን የሚያስታውስ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ እና ሥራች በዕለቱ ለታዳሚያን እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

📌 መረጃው የፋና ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

04 Nov, 05:31


📌"የሕይወት ታሪክ" ተውኔት ዛሬ ይመረቃል

ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ዝግጅት ተመርቆ ዘወትር አርብ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።

በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን ለሁለት ይተውናሉ።

ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

04 Nov, 05:31


📌የዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" ነጠላ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ነገ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በራሱ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ይለቀቃል ተብሏል።

በዚህ የነጠላ ሙዚቃ ስራ ላይ ድምጻዊ አብዱ ኪያር በግጥምና ዜማ ተሳትፏል። አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የሙዚቃ ቅንብሩን ሰርቷል።

ድምጻዊ ዳዊት ፅጌም ስለዚህ የሙዚቃ ስራው በማህበራዊ ትስስር ገፁ" እጅግ በምወደውና በማከብረው ታላቅ ወንድሜና የሙያ አጋሬ አብዱ ኪያር (ABD) ግጥምና ዜማ ደራሲነት ”ዳር  ዳር “ የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዘፈን የሰራሁ ሲሆን፤ በአሜሪካ በነበረን ቆይታ በ "የኔ ዜማ" ባንድ አጃቢነት የተጫወትነውንና አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ያቀናበረውን ይህን ዜማ ማክሰኞ ጥቅምት 26 2017 11:00 ላይ በ Dawittsige official youtube channel ላይ እንደሚለቀቅ ስገልፅ በታላቅ ደስታ ነው"ብሏል።

በተያያዘ መረጃም የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርቱ የፊታችን ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

02 Nov, 11:24


📌የፊልም ባለሞያው በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።

"ምን ልታዘዝ ?" ተከታታይ ድራማ፣"በእናት መንገድ" ፊልምን ጨምሮ በርካታ ፊልሞች ላይ በድርሰትና ዝግጅት ምናውቀው የፊልም ባለሞያ በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 77ተኛ መድረክ "ጥበብ እና ዘመን" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 14:40


📌በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል

የአዲስ እበባ ዩንቨርስቲ የቴአትር ትምህርት ክፍል መምህር በሆነው በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ እንደሚበቃ አሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ  አስታውቋል::

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

መጽሐፉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለንባብ እንደሚበቃም ተገልፆል::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 08:55


📌የአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ  የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 እንደሚካሄድ ተሰማ

"የትዝታው ንጉሥ" የሚል ቅጽል ስም የወጣለት አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የስንበት ሙዚቃ ዝግጅት በአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መጽሐፍ እንደሚመረቅም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው  የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለማሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል በጆርካ ኢቨንት አዘጋጅነት ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም ለማስቀመጥ መታሰቡን ሰምተናል፡፡

በዚህም ጥቅምት 22 ቀን  ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የድምጻዊው የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 08:54


📌ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላና ድምጻዊ ስለሺ ታምራት ድጋሚ የተጣመሩበት "ሞገድ" ገሚስ አልበም ተለቀቀ

"ጣዲቄ" በተሰኘው ሙዚቃው የምናውቀው ድምጻዊ ስለሺ ታምራት ከሁለገቡ ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ጋር የተጣምሩበት "ሞገድ" ገሚስ አልበም ትላንት ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በያምሉ ሞላ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

በዚህ ገሚስ የሙዚቃ አልበም ውስጥ "እንዲህ እንዲያ" ፣"አንገቶዋ"፣ "ኧረ ጉዴ" ፣"እንዳንቺማ" የተሰኙ ርዕስ የተሰጣቸው የሙዚቃ ስራዎች እንደተካተቱበት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 07:35


📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" ሶስተኛው የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 23 ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል።

ባለፉት ሁለት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ሶስተኛውም መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን  ይዘከራሉ፤ አንጋፋው ከያኒ አያልነህ ሙላት ደግሞ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 07:07


📌ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ  የ2024  የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFAA ) ተሸላሚ ሆነ

ላለፉት 25 ዓመታት ከፋሽን ሰዎች ታዋቂዎችን እነ ቺኒዋ አቼቤ፣ አለን ፔተን፣ የሚ አላዴ፣ ብሬንዳ ፋሴ እና ከሰዓሊያን እነ ቼሪ ሳምባ፣ አብዱላሂ ኮንቴ እና  ኢብራሂም አል ሳላሂ በተለያዩ ዓመታት የሸለመው የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFRICAN FASHION & ART AWARD -AFAA ) ዘንድሮው  ከሚሸልማቸው 100 አፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሰዎች  ውስጥ  ብቸኛው ኢትዮጵያዊ  ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ኾኗል።

ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ለሽልማቱ ቀጥታ ተመራጭ እንዲሆን ያበቃው፤ በአፍሪካ ስልጣኔ፣ ባህል እና ፓን አፍሪካኒዝም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስልጣኔ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ በሠራቸው የስዕል ሥራዎች እና በተለያዩ ዓለማት በተሳተፈባቸው ዐውደ ርዕዮች ባገኛቸው እውቅናና ሽልማቶች ነው።

ሠዓሊ እና የታሪክ ባለሙያ ወንድወሰን፤  በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሥነ-ጥበብ አማካሪ፣ በኢቲ - ሜትሮፖሊታን ጋለሪ ዳይሬክተር እና ኩሬተር፣ የሀገር አማን እና ሆርን ሪቪው መጽሔቶች ካርቱኒስት እና አምደኛ፣ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሕክምና ማኅበር አምባሳደር በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

የዘንድሮውን የአፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሽልማት ከNovember 6th - 8th /2024 በዋና ጽሕፈት ቤቱ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያካሂድ አፋ (AFAA) ባወጣው መግለጫ አሳውቋል ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 07:07


📌የቀድሞ ድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ አልበም በድጋሚ ተሰርቶ ለአድማጭ ሊደርስ ነው

በ1980 ዎቹ ከተዜሙ የድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ አልበሞች የተውጣጡ ሙዚቃዎች በድጋሚ ተሰርተው ለአድማጭ ሊደርሱ ነው ተባለ ።

በተለያዩ ነጠላ ዜማዎቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ዘንድሮ'' በተሰኘ የሙዚቃ አልበም መጠሪያ የተሰጠውን የድምጻዊ ተፈራ  ነጋሽ ስራ ይዞ መምጣቱን አስታውቋል።

"ዘንድሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠው አልበም ከሰላሳ ዓመታት በፊት በተዜሙ ዜማዎች በልዩ ጥንቃቄ ለዚህ ዘመን በሚስማማ መልኩ እንደገና የተሰሩ ሙዚቃዎች ናቸው ተብሏል ፡፡

በድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ በተለያዩ አልበሞች ላይ የተቀነቀኑ ሙዚቃዎችን ድምጻዊው በሙዚቃ ፈጠራ ስራዎቹ ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎችን እና የቤተሰቦችን መብት እና ጥቅም ባከበረ ሁኔታ እንዲሁም በማስፈቀድ የሙዚቃው የቀድሞ ለዛ እና ቃናቸውን በጠበቀ መልኩ ስራውንም በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ የድምፅ መሳሪያዎች በመታገዝ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት እንደተሰራ ገልጿል።

"ዘንድሮ” አልበም በትዝታ ፤ በፍቅር ፤ በውለታ የሚዳስሱ ደረጃቸውን የጠበቁ ስራዎች ናቸው ተብሏል።

አልበሙንም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታት እና ከፍተኛ በጀት ማውጣቱን ድምጻዊው አስታውቋል።

ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ ከዚህ ቀደም በሰራቸው ተዛዘብን ፤ ሲያዴ ፤ እንቅልፌን ደርበህ ፤ ላይ ላዩን ፤ አብሮ አደጌ(ተፈራ ነጋሽ) እና ምነው ቀዘቀዘ በተሰኙት ስራዎቹ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 06:56


📌ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመቱን ሊያከብር ነው

ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር ሰላሰኛ አመት የምስረታ በዓሉን ለተከታታይ አስር ቀናቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።

ከጥቅምት 25 አስከ ህዳር  5 2017 ዓ.ም ሠላሰኛ ዓመቱን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብረው ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ይህ ጊዜ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምንከፍትበት ይሆናል ብሏል።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ምህረት ንጉሴ
በዓሉ የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ፣ ለመብታቸው ለመሟገት እና አካታችነትን ለመፍጠር ምን ያህል እንደተጋን እንድንገመግም ያስችለናል ብለዋል።

በሶስት አሰርት ዓመታት ውስጥ በጤና ፣ በትምህርት፣በማህበራዊ ጥበቃ እድሎችን ከማሳደግ፣ዜጎችን በራስ በመደገፍ እና ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ አመርቂ ውጤት ማምጣታችን ግን እሙን ነው " ብለዋል።

ስኬታችንን ስናከብር ብዙ የሚቀሩን ስራዎች እንዳሉብንም እንገነዘባለን ሲሉም ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።

የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክበረ በዓሉ ለሁሉም ጎብኝዎች ክፍት በሆነው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ/ም በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚዘጋጅ ኤግዚቢሽንና የመዝናኛ ፕሮግራም ተጀምሮ ህዳር 05 ቀን 2017ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይጠናቀቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

01 Nov, 06:56


📌በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተምን ጨምሮ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያ አስታወቀ

ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የላቀ ለማድረግ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ  ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።

ከአስር አመት በፊት በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ የተመሠረተው ኤስ አር ኢ የተሰኘ መሠረቱን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና እውቀት ላይ አድርጎ የሰው ልጆችን ህይወት ለመቀየር በማሰብ የተመሰረተ ተቋም ሲሆን በቀጣይ አለምን በሳይንስ ቴክኖሎጂ ለመቀየር ዓላማን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራች አቶ ሳመኤል ከፈለኝ ገልጸዋል።

ተቋሙ ከሰራቸው አበይት የፈጠራ ስራዎች መካከል በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተም ፣ ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች ፣ ከ10 በላይ ኮሌጆች፣ ከአስራ ስድስት በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍ ላይን ዲጂታል ላይብረሪ ማሽን ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ  ለጎርፍ አደጋና ለመሬት መንቀጥቀጥ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ቴከኖሎጂ፣ የግለሰቦችን ማንነት እራሱ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ሰው ሰራሽ አስተውሎት ( አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ) ቴከኖሎጂ እንዲሁም ከ15 በላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማበርከቱን ተቋሙ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ተቋሙ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር በኩል ጉልህ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚታገዝና የሚመራ የትራፊክ መብራቶችን ፣ ባዩሜትሪክ ፣ ለቱሪስቶች መረጃ የሚሰጥ የመረጃ ማዕከል ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን ሰርቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

31 Oct, 05:35


📌የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ በድምቀት ተመረቀ።

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ  ርዕስ የተሰጠው አዲስ  የግጥም መጽሐፍ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም  አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።

በዕለቱም ግጥሞና ወጎች ተነበዋል፣ ሥነጽሑፋዊ ዳሰሳዎችና የሙዚቃ ዝግጅት ቀርቧል።

ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

31 Oct, 04:36


📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

31 Oct, 04:32


📌"የጣዕም ልኬት" ዝግጅት ወደ አየር ሊመለስ ነው

ሙዚቃና ሙዚቃዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰው "የጣዕም ልኬት" የሬድዮ ፕሮግራም በቅርቡ ወደ አየር እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሬድዮ ፕሮግራሙ የሬድዮ ጣቢያውን ከሸገር 102.1 ወደ አንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ቀይሮ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6:00 እስከ 8:00 ይተላለፋል ተብሏል።

"የጣዕም ልኬት" አዘጋጆች የሙዚቃ ባለሞያዎቹ ሰርፀ ፍሬስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌ ናቸው።

የፕሮግራሙ አዘጋጅና የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት ማኀበራዊ ትስስር ገፁ" ምንም ብንዘገይ፣ በመጨረሻ አድርገነዋል። ለበርካታ ዓመታት ከጆሯችሁ ርቃ የቆየችው "የጣዕም ልኬት" ተመልሳ ዐየር ላይ ልትውል ነው።በFM ዐዲስ 97.1 ሬዲዮ ሠርክ ቅዳሜ ከ6:00- 8:00።አዘጋጆች፥ ምዕራፍ ተክሌ እና ሠርፀ ፍሬስብሐ። "በሙዚቃዎቻችን የጣዕም መሠረቶች" ላይ ትኩረቷን ያደረገችው የጣዕም ልኬት ተመልሳለችበቅርብ ቀን" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

29 Oct, 13:53


📌የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ

የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት ተወዳጅ መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀረበዋል።

በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉትና ከገበያ ጠፍተው የነበሩ የበዕውቀቱ ስዩም "መግባት እና መውጣት" ፣"ስብስብ ግጥሞች" እና "ከአሜን ባሻገር የተሰኙ ሶስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል::

ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም  በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይህን መልዕክት አስፍሯል"ውድ የመጽሀፍ ወዳጆች! ከገበያ ጠፍተው የነበሩት የበእውቀቱ ስዩም መጻሀፍት መካከል ፥ መግባት እና መውጣት፥ ስብስብ ግጥሞች እና ከአሜን ባሻገር ' በድጋሜ ታትመው ለገበያ ቀርበዋል፤ መግዛት ወይም መሸጥ የምትፈልጉ ፥ ለገሐር አመልድ ህንጻ፥ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አይንአለም መጽሀፍ መደብር ጎራ በሉ፤ ስልክ  0911814536"።

መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

29 Oct, 13:49


📌"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት በይፋ ተመረቀ !

በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመርቋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥነ-ጥበብና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በቴአትሩ የአንድ ዓመት ጉዞ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሞያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።

@EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 15:04


📌የፍሬዘር ቀናው "ጀሚላዋ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊ ፍሬዘር ቀናው (ባቢ) " ጀሚላዋ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአድማስ ሙዚቃ ዩቲዩብ ቻናል ተለቋል።

"ጀሚላዋ" ሙዚቃ ግጥም በጥላሁን ሠማው ዜማ በአቡዲ ሙዚቃ ቅንብርና ሚክሲንግ በታምሩ አማረ ተሰርቷል። የሙዚቃው ቪዲዮ ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን ነው።

ድምጻዊ ፍሬዘር ቀናው ከዚህ ቀደም "ውሎ መጀን" ፣ "ሙሐባ" ፣ "ናፍቀሽኛል" እኔ ሌሎችም ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 15:04


📌ድምጻዊት ሌሊ ሌንሳም "ሳድግ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊት ሌሊ ሌንሳሞ "ሳድግ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃዋ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቂቃዎች በፊት በራሷ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

"ሳድግ" ሙዚቃ ግጥምና ዜማው በራሷ በሌሊ ሌንሳሞ የተሰራ ሲሆን ሚክስንግና ማስተሪጉን ዳጊ ሙዚየክ ሰርቷል።የሙዚቃው ቪዲዮው ላይ ሮብ ፕሮዳክሽን ተሳትፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 05:21


📌የጠረፍ ካሣሁን አዲስ ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል

የድምጻዊት ጠርፈ ካሣሁን(ኪያ) "ለምን ብዬ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል።

በሙዚቃው ላይ በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ በዜማ ብስራት ሱራፌል፣ በቅንብር ናኦል ኤቤሳ ተሳትፈውበታል።

ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን ከወራት በፊት "ጥሉ ከማን ነው?" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ለአድማጮች ማድረሷ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 05:21


📌"አይዞን" ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል 

ድምጻዊ አብዱ ኪያር እና ናትናኤል አያሌው (ናቲ ማን) የተጣመሩበት "አይዞን" የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
   
በዚህ ኮንሰርት አብዱ ኪያር የተለያዩ ተወዳጅ ስራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን እንዲሁም ናቲ ማን ከረጅም ዓመታት በኋላ ስራዎቹን ያቀርባል።

የመግቢያ ዋጋ ፦ ለመደበኛ 600 ብር፣ በር ላይ  800 ብር፣ ለቪአይፒ ደግሞ 2000 ብር ሲሆን ትኬቶችን በሚሊንየም አዳራሽ፣ ቦሌ ፍሬንድሺፕ በሚገኘው ቻካ ኮፊ፣ 22 በሚገኘው ቻካ ኮፊ፣ ፊሊ ኮፊ ሜክሲኮ፣ አትላስ ቸሩ መድሀኒአለም፣ ይማና ክትፎ እንዲሁም ቴሌ ብር ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 04:50


📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ


📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: አርብ (በልዩ ዝግጅት )
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

25 Oct, 04:34


📌"ክንፋም ከዋክብት" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

50 ገጣሚያን የተሰባሰቡበት "ክንፋም ከዋክብት" ቅጽ አንድ የግጥም መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም የተመረጡ ግጥሞች በገጣሚያን፣አጭር ሂሳዊ ዳሰሳ፣አኩስቲክ ሙዚቃ ጨዋታን ጨምር ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ይከናወናሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

24 Oct, 19:34


📌EVENT ADDIS MEDIA

በቅርብ ይጠብቁን!!

Event Addis Media

24 Oct, 19:29


Channel photo updated

Event Addis Media

24 Oct, 19:28


Channel name was changed to «Event Addis Media»

Event Addis Media

24 Oct, 05:26


📌ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ አሸንፏል

ሁለተኛውን የኢጋድ የ2024 የሚዲያ አዋርድ ኢትዮጵያዊው ወጣት ጋዜጠኛ ምስክር አወል አሸናፊ ሆኗል።

ጋዜጠኛ ምስክር "Narratives of Hope: Inspiring Peaceful, Secure, and Inclusive Future." በሚል ሃሳብ ላይ ተወዳድሮ ነው ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋዜጠኞች ቀዳሚ መሆንና ማሸነፍ የቻለው።
ሽልማቱንም በኬንያ እየተካሄደ ባለው የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ ስነ ስርዓት ላይ ተቀብሏል።

ጋዜጠኛ ምስክር ቀደም ሲል በሸገር ራዲዮ የሰራ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢቢሲ የብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያው ባልደረባ ነው።

መረጃው: የ https://t.me/AhunawiMereja ነው።

ለትኩስ መረጃዎች "አሁናዊ" ቴሌግራም ይቀላቀሉ።

Event Addis Media

24 Oct, 05:26


📌 "ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ሊመረቅ ነው

በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።

በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።

የተውኔቱ የምርቃ ሥነሥርዓትም የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል። እንዳትቀሩ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Oct, 13:09


📌"የቅርብ ሩቅ" ተውኔት ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በእሸቱ ዱብ ተደርሶ በተስፋዬ ገብረማርያም የተዘጋጀው "የቅርብ ሩቅ" ተውኔት ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለመድረክ ይበቃል።በተውኔቱ ላይ ሉሌ አሻጋሪ፣ሔኖክ በሪሁን፣ቅድስት ብሩክ፣ናትናኤል መኮንን፣ብሩክታዊት እሸቱና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Oct, 13:09


📌የወር ወንበር" ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል!

"የወር ወንበር" ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በየወሩ የሚዘጋጅው "የወር ወንበር" መሰናዶ በዚህ ወር "ሳይንስ እና መኸዘብ" በሚል ርዕስ የፊታችን  ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ውይይት ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ ኤምሬትስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Oct, 13:08


📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል!

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት በዓመቱ የመጀመሪያው መሰናዶ የቦታ ለወጥ አድርጎ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 16 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ በዓመቱ የመጀመሪያ መሰናዶ ላይ ደራሲ ተስፋዬ ማሞ እና ደራሲ ይታገሱ ጌትነት ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ መጻሕፍት ደግሞ "ከማዕበል ማዶ" እና "መንግስቱ ኃ/ማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች" ናቸው።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

23 Oct, 13:08


📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

48ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር በርናባስ ሽፈራው "የማርክሳዊነት የገደል ማሚቶች " በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥቅምት 17 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Oct, 17:56


📌"የሕይወት ታሪክ" የተሰኘ አዲስ ተውኔት ለመድረክ የሚበቃበት ቀን ይፋ ሆነ።

ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ከጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአንጋፋው ብሔራዊ ቴአትር መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።

በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን  ለሁለት ይተውናሉ።

ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Oct, 17:56


አርቲስት ናርዶስ አዳነ የሎዛ የሥነምግብ ማማከር ህክምና ተቋም ብራንድ አንባሳደር በመሆን ተሾመች።

አርቲስት ናርዶስ አዳነ የሎዛ የሥነምግብ ማማከር ህክምና ተቋም ብራንድ አንባሳደር በመሆን ለሁለት ዓመታት ስምምነት ፈፅማለች።

የጋራ ስምምነቱ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኤልሶል ሆቴል ውስጥ ተካሄዷል።

ሎዛ የስነ ምግብ ማማከር ህክምና ተቋም ተላላፊ ያልሆኑ የጤና ችግሮችን በምግብ በማከም እንደ ስኳር እና ደም ብዛት ላሉ በሽታዎች ለተጠቁ ታካሚዎች ዘለቄታዊ መፍትሄ በመስጠት እያገለገለ ያለ ተቋም እንደሆነ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Oct, 14:43


የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ ረቡዕ ይመረቃል።

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ  ርዕስ የተሰጠው አዲስ  የግጥም መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ከ11:00 ጀምሮ  አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Event Addis Media

22 Oct, 14:43


📌ዌብሳይት የመስራት ችሎት ላላቸው ዳጎስ ያለ ብር የሚያሸልም ውድድር ሊካሄድ ነው።

የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅረብ በአጭር ጊዜ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እየሆነ የመጣው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ከብልህ ማርኬቲንግ ጋር በመሆን ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየውን የቴክኖሎጂ ውጤት ከ500 በላይ አበልፃጊዎችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበርታታት ፕሮጀክት ቀርጾ መንቀሳቀስ መጀመሩን ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ዋና መስሪያቤቱ ይፋ አደርጓል።

በዚህ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ዌብሳይት የመስራት ችሎት ላላቸው ዳጎስ ያለ ብር የሚያሸልም ውድድር ማዘጋጀቱንም ተቋሙ አስታውቋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ "ይህንን የፈጠራ ውድድር በዘጠና ቀን ዘመቻ ወደስራ ስናስገባ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን የቴክሎጂ እድገት ካለበት ደረጃ በአጭር ጊዜ የከፍታ ማማ ላይ ለማድረስ አልመን ነው የምንሰራው " ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የዌብ ዘርፎች ኢኮሜርስ፣ ቱሪዝም፣ ሆስፒታሊቲ፣ የሄልዝ ኬር፣ የተማሪዎች ሰርቪስ፣የማህበረሰባዊ ትስስር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ማወቅ ተችሏል።

ይህም ፕሮጀክት ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር፤ ለአገር ዉስጥ የምጣኔ ሀብት እድገትና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችል እና አዳዲስ የኢኖቬሽን ስራዎች በማካተት ለዌብ ዲዛይኑ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያላቸዉ ተብሌኖችና ዲዛይኖች እንዲፈጠሩ ለማየት እንደሚያስችል ተገልጿል።

ፎቶ: ተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1