ስለ ጤና @siletenawot Channel on Telegram

ስለ ጤና

@siletenawot


ታማኝ የሆነ የህክምና መረጃ እና ምክር አገልገሎት!
ጥያቄ ወይም አስተያየት ካሎት በሚከተሉት አድራሻ ፃፉልን ይደርሱናል!
💯% በነፃ!!!
@Dr_Temesgen or [email protected]

ስለ ጤና (Amharic)

ስለ ጤና ማለት በሚሆን መልእክት የሚጠቀሙ ያገልግሎታዎችን እና መረጃዎችን ከተጠቃሚ ጅምማኑን ጋር ሰባት ደረጃዎች ይሰጡልን። ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለበት አድራሻ ፃፉልን እንደገመፃሽያሽ ማስተላለፊያ የሚሆነውን በግዳች ለማድረግ እናውቃለን። ባለመጠቀም %100 በነፃ። ለተጨማሪ እኔዎቼ ከባለድርሻሽ ተመለስላል። @Dr_Temesgen ወይም [email protected] የሚገኙ መረጃዎችን ለመጠቀም እናውቃለን።

ስለ ጤና

09 Feb, 04:22


@Dr_Temesgen_Dejene

ስለ ጤና

05 Feb, 13:27


📣እንክብል የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ጥቅሞች እና ጉዳቶች💬
በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ

🟠
ጥቅሞች
⬇️
🔸ታማኝ እና እየተጠቀሙት እርግዝና 🔸የመፈጠር እድሉ ዝቅተኛ ነው
🔸የእንቁላል ማቀፊያ ካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
🔸የማህጸን ግርግዳ ካንሰር ተጋላጭነት ይቀንሳል
🔸ከማህጸን ዉጪ የሚከሰትን እርግዝና ይቀንሳል
🔸የወር አበባ ዉህደት ወቅቱን ጠብቆ እንዱኖር ያደርጋል
🔸ከወር አበባ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ህመምን ይቀንሳል
🔸ብጉር ያስተካክላል
🔸የማህጸን ኢንፌክሽን የመያዝ እድልን ይቀንሳል

🔴ጉዳቶች
⬇️
🔺ቀን በቀን ተከታትለን መዉሰው ይጠበቅቦታል
🔺የአባላዘር በሽታን አይከልከልም
ማቅለሽለሽ
🔺ግፊትን ተያይዞ ሊያስከትል ይችላል
🔺የደም መርጋትን ይጨምራል

🔵ይህንን የእርግዝና መከላከያ መጠቀም የሌለባቸው ማናቸው?

🔷በፍጸም መጠቀም የሊለባቸው
⬇️

🔹ከዚህ በፊት ወይም አሁን ላይ

🔹የስትሮክ በሽታ ተጠቂ የሆነች
🔹የጉበት በሽታ ካለባት
🔹የልብ ድካም ህመም ያለባት
🔹እድሜዋ ከ35 በላይ ሆኖ ሲጋር ምታጨስ

◾️በሃኪም ትዛዝ ብቻ መጠቀም ያለባቸው
⬇️
▪️ወፍራም ሴት
▪️ሚግሬን ያለባት
▪️ግፊት ታካሚ
▪️የድብርት በሽታ ያለባት
▪️ምታጠባ እናት
▪️ምታጨስ ሴት
▪️እድሜዋ ከ 35 በላይ የሆነ


ማንኛዉንም የእርግዝና መከላከያ ከመጠቀሞት በፊት ስለ ጥቅሙ እና ጉዳቱ ባለ ሙያ ማማከሮን አይርሱ!!!
ይህ መረጃ ለወዳጅ ዘሞዶ እንዲደርስ ሼር ማድረግን አይርሱ
@Dr_Temesgen_Dejene

ስለ ጤና

15 Dec, 19:06


#ምርጥ #ባህሪ

🔺️ ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ፡፡

🔺️ አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር፡፡

🔺️ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ፡፡

🔺️ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን፡፡

🔺️ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት፡፡

🔺️ ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን ከመፍጠር ተቆጠብ፡፡

🔺️ ፀዳ በል፡፡ በደንብ ልበስ ፣ ፏ በል!

🔺️ ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን፡፡

🔺️አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ፡፡

🔺️በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን፡፡

🔺️ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ ብቻ መዝናቸዉ፡፡

🔺️ የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ ሁሉ አትናገር፡፡

🔺️ ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ፡፡

🔺️ ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ፡፡

🔺️ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ፡፡

🔺️ የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ፡፡

🔺️ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል፡፡

ለአንቺም በተመሳሳይ እህቴ፡፡

ስለ ጤና

15 Dec, 18:54


@Dr_Temesgen_Dejene

ስለ ጤና

19 Nov, 09:45


#ከመጠን_ያለፈ_ላብ/Hyperhidrosis

ይህ እክል በአብዛኛው በወጣቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን የተወሰነ ቦታ ላይ ወይም ሙሉ ሰውነት ላይ ሊሆን ይችላል እክሉ ለሂወት አስጊ ባይሆንም ከሰው ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ተጽኖ ያሳድራል ከዛም አልፎ ድብርት ለሚባለውን በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል። ከመጠን ያለፈ ላብ በእጅ መዳፍ፤እግር፤ብብብት እና በዳሌ አካባቢ ላይ በብዛት ይከሰታል ይህም የሆነበት ምክንያት በነዚህ አካባቢ ላብን የሚያመነጩ ህዋሶች በብዛት ስለሚገኙ ነው።
አምጪ ምክንያቶች
🔷 Idiopathic/ምክንያቱ አይታወቅም
🔷 ዉፍረት
🔷 ሪህ
🔷 ማረጥ/menopause
🔷እጢ/Hodgkin disease
🔷ስኳር
🔷እንቅርት
የተለያዩ ኢንፈሽኖች/ቲቢ፤ወባ..
🔷 መድሃኒቶች/ለድብርት የሚወሰዱ

🔶ህክምናው
አንዳንድ የቀን ተቀን ኑሮዋችን ማስተካከል ቀላል የማይባል ለዉጥ ያመጣል
ለምሳሌ፤-🔶ላብን መከላከያ የሚነፉ ግባቶሽን መጠቀም/ዶድራንት ላብን አይቀንስም/

🔶በብብት ስር የሚቀመጡ ላብ መጣጭ ጨርቆችን መጠቀም

🔶በኒለን የሚሰሩ ልብሶችን አለመልበስ

🔶ሲንቴቲክ የሆኑ ጫማዎችን አለማድረግ

🔶በነዚህ ማይስተካከል ከሆነ ከሚዋጡ መድሃኒቶች ጀምሮ እስከ ሰርጀሪ ህክምና አለው
#Share ለጓደኛዋ እና ቤተሰቦ ሼር ያድርጉ
@Dr_Temesgen_Dejene

ስለ ጤና

03 Nov, 18:01


ለፀጉራችን ምን ዓይነት እንክብካቤ ማድረግ እንችላለን?

1. ፀጉራችንን በየሳምንቱ የመታጠብ ልምድ ማዳበር ይኖርብናል፤ ይህን የማድረግ ጥቅሙ በፀጉራችን ላይ የተጠራቀመውን የፀጉር ቅባቶችን ከላብ ጋር አንድ ላይ በመሆን ፀጉራችንን እንዳያቆሽሹ እና ለፎሮፎር እንዳንጋለጥ ይረዳናል፡፡

2. ኮንዲሽነር (conditioner) መጠቀም፡- የዚም ጥቅም የሚሆነው ፀጉራችንን ካለምንም ችግር ማበጠር እንድንችል ያደርገናል በተጨማሪም ለፀጉራችን ልስላሴ ይሠጠዋል፡፡ ኮንዲሽነር ስንጠቀም በፀጉራችን ጫፍ ላይ በመጀመር ወደሌላው ማዳረስ ይቻላል፡፡

3. ፀጉራችንን ከድርቀት ለመከላከል እንዲሁም የፀጉርን ወዝና ልስላሴ ለመጠበቅ የተለያዩ ገበያ ላይ ያሉ ትሪትመንት ቅባቶችን በወር ከአንድ እስከ ሁለት ጊዜ መጠቀም ጥቅሙ የበዛ ነው፡፡

4. ፀጉር ቤት ወይም ቤት ሆነ ፀጉራችንን በእሳት/ፔስትራ ከመሰራታችን በፊት heat protector products መጠቀም ፀጉራችንን ከጉዳት ይከላከለዋል፡፡

5. ፀጉራችንን ራሳችን ቤት ውስጥ የምንሠራ ከሆነ (ተኩስ) ፀጉራችንን በሳምንት ከአንድ ጊዜ በላይ ለእሳት/ፔስትራ ማጋለጥ የለብንም፡፡

6. ሹሩባ በምንሠራበትም ጊዜ ፀጉራችን መጥበቅ የለበትም፡፡ ፀጉራችን በሚጠብቅበት ጊዜ ፀጉር ስለሚጎዳ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡

@Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

31 Oct, 11:40


ውሃ ለጤንነት!!

ሰውነታችን ውሃ  ሊተካ የማይችል ጠቀሜታ እናዳለው ይታወቃል፤ በቂ ውሃ መጠጣት ለጤና እና ደህንነት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን ባለማወቅም ይሁን በቸልተኝነት ሰውነታችን የሚፈላገውን ያህል በቂ ውሃ አንጠጣም፡፡ በትክክል ለመስራት ሴሎቻችን በቂ ውሃ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የሰውታችን 60% የሚሆነውን ውሃ ይይዛል፤ የደማችን 90% ውሃ ነው፡፡ 70% የሚሆነው አለማችን ክፍል በውሃ  ተሸፍኗል፡፡
 
ከዚህ በታች ውሃ መጠጣት የሚያስገኝልንን ጥቅሞች እንዘረዝራለን፤
1.      የመገጣጠሚያችን ፈሳሽ 80% ውሃ ነው  
3.      ኦክስጂንን በሰውነታችን ውስጥ እንደ ልብ ለማንቀሳቀስ
4.      የቆዳን ጤንነትን እና ውበትን ለመጠበቅ
5.      ዋና ዋና የሚባሉትን የሰውነት ክግሎቻችንን እንደ አእምሮ፣ ህብለሰረሰር፣ እና ሌሎችን ከአደጋ ለመጠበቅ
6.      የሰውነትን ሙቀት ለማስተካከል
7.      ስነ- ልመትን ለማቀላጠፍ
8.      ከሰውነታችን ቆሻሻ በቀላሉ ለማስወገድ
9.      የደም ግፊትን ለማስተካከል
10.  የአተነፋፈስ ስርዓትን ለማስተካከል
11.  በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ቫይታሚን እና ሚነራሎችን ተደራሽ ለማድረግ
12.  ኩላሊትን ከጉዳት ለመከላከል
13.  በአካዊ እንቅስቃሴ ወቅት አቅምን ለማጎልበት
14.  ክብደት ለመቀነስ
15.   ከስካር ለመላቀቅ ይረዳል፡፡
 
ጤናማ ማሕበረሰብን እንፍጠር!!
@Dr_Temesgen_dejene

ስለ ጤና

30 Oct, 14:13


የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?

የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች
· የፍሰት መጠን መብዛት
· የፍሰት መጠን ማነስ
· መቅረት
· የቀኑ መዛባት
· ቶሎ ቶሎ መምጣት

2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች
የፍሰት መጠን መብዛት- ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡

መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።

የፍሰት መጠን ማነስ፡- ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)

መቅረት፡- ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤ መንስኤዎቸሁም
· እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት
· ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቀኑን ማዛባት፡- ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
መንስኤዎች፡- የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር

ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡- ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ።

መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል።

(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
@Dr_Temesgen_dejene

ስለ ጤና

28 Oct, 15:32


ልጅ ሳለን ከንፈራችን ሲቆስል "ስጋ በልቼ ወይም ቅባት ያለው ምግብ በልቼ በፀሃይ ወጥቼ ነበር" ያላለ ማን አለ? ተጎ ቅጠል እና ዳማከሴ ያልተጠቀመ?
.
የምች በሽታ ምንድን ነዉ?
.
ምች (cold sore) በተለምዶ ከሚከሰቱ የቇዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛዉ ሲሆን በተለይም የላይኛዉ ወይም የታችኛዉ የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቇዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ ውሃ የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች ይታወቃል።
.
የምች በሽታ ምክንያት ?
.
በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores ) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን ነው።
.
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስቤተሰቦች በዉስጡም ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያዎች ሲኖሩ 8ቱ በሰዉ ልጅ ላይ በሽታ ያስከትላሉ ። ከነዚህም መካከል የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 ይገኙበታል ።
.
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች ቆዳን ጨምሮ በኣይን፣በመራብያ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ኢንፌክሽኖች ያስከስታሉ።
.
የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) እንዲሁም ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2)
.
ከጨቅላ ህፃናት እስከ የእድሜ ባለፅጋ የእድሜ ክልል ኢንፌክሽን መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ኤች .ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) በምች አምጪ ባህሪዉ ይታወቃል። ኤች.ኤስ.ቪ -1(HSV-1) ከሰዉ ወደሰዉ በቆዳ-ቆዳ እና በቆዳ -የሚውከስ ሽፋን(የአፍ ዉስጥ ለስላሳ ሸፍን መሰል) ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2) ደግሞ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንዲሁም ከመራቢያ አካላት-ፊት በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል።
.
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ዝርያዎች በነጭ የደም ሴሎቻችን ተጠግተዉ ከሰዉታችን ሙሉ በሙሉ በመወገድ ፈንታ በሰዉነታችን የነርቭ አካላት ዉስጥ በመሸሸግ የሰዉነታችን ዉስጣዊ ሁኔታዎች ምቹ እስኪሆኑ በመጠባበቅ ከተሽሽጉበት በመዉጣት በድጋሜ የምቸ በሽታን ያስከትላሉ ።
የምች በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ??
.
የምች በሽታ ተህዋስያን ለመጀመርያ ጊዜ በሰዉነታችን ኢንፌክሽን ስያስከስቱ በአብዛኛዉ ምንም ምልክት አይኖራቸዉም ነገር ግን በሚከተሉት ጊዜያት ሲከሰቱ የሚከተሉትን የመሳሰሉ ምልክቶች ልያሳዩ ዪችላሉ።
.
የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ ፣ የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ዪችላል ከዚህም ከ24 ሰአታት በኋላ ከስራቸው ቀልተዉ ዉሃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ይፈጠራል። በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከተፈጠሩበኋላ በቀላሉ በመፈንዳት ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ዪሸፈናሉ
.
ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጓዳኝ የራስ ምታት ፣ ትኩሳት ፣ የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ዉስጥ የሚገጙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ እጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል። ቁስለቶቹም በተለምዶከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ።
.
የምች በሽታን በተደጋጋ የሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸዉ ?
.
ለሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም የመዉረድ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች (የኤች.አይ.ቪ ፣ የካንሰር ህመሞች) በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ ሆርሞናዊ ለውጦች
በተለምዶ በቫይረስ በሚመጡ 1እንደ ጉንፋን ያሉ ኢንፌክሽንዎች መጠቃት
ጭንቀት እና የአእምሮ ዉጥረት ወዘተ
.
በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቤታችን ምን ማድረግ እንችላለን ?
.
የህመም ማስታገሻ በምች በሽታ ሚመጡ ቁስለቶች በተያያዘ የሚሰማዎትን ህመም ለመቀነስ ያለ ሃኪም ትዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን (Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን (Paracetamol) በፋርማሲ ባለሙያው ትዛዝ መሰረት መጠቀም ይቻላል ።
.
ቅዝቃዜ
ከምች በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን በቁስላቶቹ ዙርያ የሚከሰት የቆዳ መቅላት እና መቆጣትን ለመቀነስ በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዘያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ እንደሚረዳ የቆዳ ሃኪምዎች ዪናገራሉ።
.
እራስን ከጭንቀት ነጻ ማድረግ
የአእምሮ ዉጥረትን መቅነስ የሰዉነትን በሽታ መከላከል አቅም እንደሚጨምር በጥናትዎች ተረጋግጥዋል። ስለዚህም የሚያዝናኑን ነገሮችን በመፈለግ እና የአካል ብቃት አንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከዚህም በዘለለ የባለሙያ ምክር በማግኘት ልንከላከለዉ ይገባ
.
ለምች በሽታ የባህል ህክምናን መጠቀም ተገቢ ነዉ?
.
የባህል ህክምናየአንድ አካባቢ ተወላጆች ለዘመናት ያካበትዋቸዉ እንስሳን እና እጸዋት ነክ እዉቀቶችን አንዲሁም ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን መሰረት ያደረገ የህክምና ዘርፍ ነዉ። ጆርናል ኦፍ እስያ-ፓሲፊክ ባዮዲቨርሲቲ (Journal of Asia-Pacific Biodiversity) በወጣዉ ጥናት መሰረት የአለማችን 64% የሚሆነዉ ማህበረሰብ ለሚገጥሙት የጤና እክሎች የባህል ህክምናን እንደ መጀመርያ አማራጩ ይጠቀማል። በአገራችን ኢትዮጺያ ደገሞ ከ80% በላይ የሚሆነዉ ማህበረሰብ የባህል ህክምና ተጠቃሚ እንደሆነ የተለያዩ አገር በቀል ጥናቶች ያመለክታሉ።
.
የምእራባዉያን ባህል ህክምና በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ ፣ ብርቱካን ፣ ኪዊ እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን እንድንጠቀም ዪመክራል። የአገራችን የባህል ህክምና ደግሞ ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ሃገር በቀል ተክል ቅጠሎች ጭማቂ በመጠጣት ወይም ቅጠሎቹን አንድ ላይ በመጨፍለቅ ቁስለቶቹ ላይ በማድረግ እንድንጠቀም ይመክራል።
.
በዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) ጠቅላላ አጠቃቀም እንዲሁም ስለጸረ ምች አምጪ ትህዋስያን ባህሪያቱ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ስለ አጠቃላይ ጸረ-ህዋስ እና ጸረ-የሰዉነትመቆጣት (Anti-inflammatory) ባህሪያቱ የሚያወሱ አንዳንድ የሃገር በቀል ጥናቶች ብቅ ብቅ ብለዋል።
.
ለምች በሽታ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነዉ?
.
በምች በሽታ የሚመጡ ቁስለቶች በአብዛኛዉ ጊዜ በራሳቸዉ የሚድኑ በመሆናቸዉ የሃኪም ምክር መሻት ላያስፈል ይችላል። ነገር ግን ከታች የተዘረዘሩትሁኔታዎች በሚከሰቱበት ጊዜ የሃኪም መክር ማግኘት የግድ ይላል።
.
የኤች.ኣይ.ቪ ወይም የካንሰር ተጠቂ ከሆንን
የምች በሽታ ቁስለቶች አይናችን አካባቢ ከተከሰቱ
ከ2 ሳምንታት በላይ ሳይድኑ የሚቆዩ ቁስለቶች
የአቶፒክ ደርማታይቲስ (Atopic dermatitis) ታማሚ ከሆንን : በተደጋጋሚ ቁስለቶቹ የሚ ያጋጥሙ ከሆነ ሃኪም ማማከር ግድ ይላል።
.
#በህክምና ምን ሊረዱ ይችላሉ ?
ሃኪምዎ ቁስለቶቹን አጢኖ ከተመለከተ/ች በኋላ አሳይክሎቪር (Acyclovir) እና ቫልሳይክሎቪር (Valcyclovir) የመሳሰሉ ጸረ ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎችን እንዲሁም የትለያዩ የህመም ማስታገሸ መድሃኒትዎችን ልያዝሎ ይችላል። ጸረ- ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎቹ በቆዳ ላይ የሚቀቡ ወይም በኣፍ የሚዋጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
.ዉድ አንባብያን ፣ የምች አምጪ ተህዋሲያን እጅግ ተላላፊ በመሆናቸዉ የምች በሽታ በሚከሰትብን ጊዜ የፊታችንን እና የእጃችንን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ ያስፈልገናል። ቁስለቶቹ ባጋጠሙን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን የከንፈር ቀለሞች እና ቅባቶች ሌሎች እንዳይጠቀሙ በአግባቡ ማስወገድ ወይም ለይቶ ማስቀመጥ ብልሃት ነዉ።
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ በቀናነት ሼር ያድርጉት
@Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

28 Oct, 08:54


1. በመነጽር ሊስተካከል የሚችል የእይታ ችግር ( Refractive error)
2. የዓይን ሞራ (cataract)
3. በተለያየ ምክንያት የሚከሰት የዓይነ መስታወት ጠባሳ ( በተለይም የቪታሚን ኤ እጥረት፤ ኩፍኝ፤ የዓይነ መስታውት ቁጣ/ምርቀዛ…ወዘተ)
4. የዓይን ግፊት ህመም (Glaucoma)
5. የእይታ ነርቭ ችግር (Optic atrophy)
6. የእይታ አንጎል ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች (Cerebral visual impairment)
7. ያለ ጊዜው ቀድመው በሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ላይ ረቲና ውስጥ የሚፈጠር ችግር [Retinopathy of Prematurity (ROP)]
8. ከውልደት ጀምሮ የሚፈጠሩ የዓይን በሽታዎች (congenital. malformations)

በህጻናት ላይ የዓይን ችግሮችን እንዴት መለየት እንችላለን?

• በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትሉ በሽታዎችን መከላከል ወይም በህክምና ማስወገድ የምንችላቸው ናቸው፡፡
• ይኸውም አስቀድሞ በጊዜው ( በተለይም ህጻናት የዓይንና አንጎል እድገት ላይ ባለበት ከ8 ዓመት በፊት) ችግሩን በመለየትና አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ነው፡፡
• ነገር ግን የአብዛኛዎቹ ህጻናት ዓይን ችግር የሚታወቀው ትምህርት ሲጀምሩ በትምህርት ቤት ውስጥ በሚያሳዩት የዕይታ ችግር በመምህራኖቻቸው ሲሆን ይህም ዉጤታማ ህክምና ለማድረግ በጣም የዘገየ ሊሆን ይችላል፡፡

• ስለሆነም ወላጆች/አሳዳጊዎች አስቀድመው፤
1. የህጻናትን ዓይን በማየትና
2. በሚያሳዩት ባህርይ የዓይን ችግር መኖሩን መለየት ይችላሉ፡፡

በህጻናት ዓይን ላይ ችግር ስለመኖሩ ጠቋሚ ምልክቶች፡-

1. በዓይን ዉሰጥ መሃል ላይ ነጭ ነገር/ነጥብ መታየት
2. መጫወቻ አሻንጉሊት/ብርሃን ወይም የሰውን ፊት አተኩሮ አለማየት እና የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በዐይናቸው አለመከተል ( በጨቅላ ህጻናት ላይ የእይታ መቀነስ ምልክት ነው)
3. አንዱ ወይም ሁለቱም ዓይኖች መጠን ከመደበኛ በታች ትንሽ ወይም ትልቅ መሆን
4. ሸውራራ ዓይን
5. የዓይን ቅላት
6. የዓይን ውስጥ እብጠት /ቁጣ/ምርቀዛ
7. አብዝቶ በተደጋጋሚ እንባ መፍሰስ
8. ዓይነ መጎልጎል (Proptosis)

ህጻናት የሚያሳዩትን የባህርይ ለዉጥ በማጥናት የዓይን ችግር መኖሩን መለየት:-

1. ጨቅላ ህጻናት 3 ወር እድሜ ሲሞላቸው የሰው ፊት ላይ ካላተኮሩና ፈገግታ ካላሳዩ
2. ህጻናት አተኩረው ሲያዩ አንድ ዓይናቸውን የሚሸፍኑ ከሆነ
3. ሲያነቡ ወይም የሚያዩትን ነገሮች ወደ ፊታቸው የሚያቀርቡ ከሆነ ወይም ወደ
ቴሌቪዥን፤ ኮምፒዩተር፤ ሰሌዳ በጣም ቀርበው ብቻ የሚያዩ ከሆነ
4. አተኩረው ሲመለከቱ ፊታቸውን ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያዞሩ ወይም
ጭንቅላታቸውን የሚያገድሉ ከሆነ
5. እድሜያቸው ከፍ ያሉ ህጻናት ደግሞ የሚያዩት ነገር ደብዛዛ ነው ወይም ለማየት
ተቸግሬለሁ ብለው ከተናገሩ
6. በትኩረት ሲመለከቱ ወይም ከሩቅ በሚያዩበት ጊዜ የዓይን ቆብ አጥብበው የሚያዩ ከሆነ
7. የሚያዩት ነገር ደርቦ / ሁለት ሁለት ሆኖ መታየት
8. ዓይነ ዥዋዥዌ (ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የዓይን እንቅስቃሴ)
9. በተደጋጋሚ ዓይናቸውን ማሸት/ማሳከክ ሲኖር

ወላጆች/አሳዳጊዎች የህጻናትን ዓይን ጤና ለመጠበቅ ምን ማድረግ አለበቸው?

• የህጻናትን የእጅና የፊት ንጽህና መጠበቅ
• ክትባት በወቅቱ ማስከተብ (በተለይም የኩፍኝ ክትባት)
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ (በተለይም አትክልትና ፍራፍሬ በቪታሚን ኤ የበለጸጉ
ምግቦችን እንደ ካሮት፤ ማንጎ፤ አቮካዶ፤ አረንጓዴና ሰፋፊ ቅጠላ ቅጠል ያላቸውን)
🥕 🥑 🥦
• የህጻናት ዓይን ላይ ችግር መኖሩን ከጠረጠሩና ጠቋሚ ምልክቶችን ካዩ ሳይዘገዩ
ወዲየውኑ ወደ ዓይን ሕክምና ተቋም በመውሰድ ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡

በህክምና ተቋም የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

- የእይታ ልኬት ይደረጋል
- የመነጽር ልኬት (ህጻናት ሲሆኑ የዓይን ጠብታ በመጨመር የሚደረግ ምርመራ)
- የዓይን ዉጪና ውስጥ ምርመራ
- እንደችግሩ ዓይነት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ምርመራዎች (ለምሳሌ፡ አልትራሳውንድ፤ CT scan/MRI) ማድረግ ሊያስፈልግ ይቻላል፡፡
- ሙሉ ምርመራ ለማድረግ የማይተባበሩ ህጻናት ከሆኑ ደግሞ የሰመመን (ማደንዘዣ) መድኃኒት በመስጠት የሚደረግ ምርመራ
• የህጻናትን ሕክምና መዘገየትን ማስወገድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
• የሐኪም ምክር በተገቢው መፈጸም ወሳኝ ነው፡፡
• መደበኛ ክትትል ሳያቋርጡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሕክምናው

እንደ ችግሩ ዓይነትና ደረጃ የተለያየ ሲሆን፡-
• የመድኃኒት ሕክምና
• የመነጽር ሕክምና
• አንድ ዓይን ለተወሰነ ጊዜ በመሸፈን ስንፈተ ዕይታን ማስተካከልና
• የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊሆን ይችላል።

ጤነኛ ህጻናትን መቼ መቼ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል?

• በወቅቱና በጊዜው መታከም ያለባቸው አስቀድመው ያልታወቁ የዓይን ችግሮች/በሽታዎች የህጻናት ዓይነ ስውርነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
• በመሆኑም አስቀድሞ በወቅቱ ችግሮችን በማወቅና በመለየት መቅረፍና ዓይነ ስውርነትን መከላክል ይቻላል፡፡
• ይኸውም መደበኛ የዓይን ምርመራ በማድረግ ነው፡፡

የመጀመሪያ የዓይን ምርመራ መቼ መደረግ አለበት?

• አንድ አመት እድሜ ላይ ፤ ከዚያ መዋለ ህጻናት(KG) ከመግባታችው በፊት።

በአጠቃላይ፡-
• ከልደት - 2 ዓመት ዕደሜ ፤መጀመሪያ ምርመራ በ 6 - 12 ወር ዕድሜ ላይ
• ከ 3 - 5 ዓመት ዕድሜ ፤ ቢያንስ አንድ ጊዜ ማስመርመር
• ከ6 – 17 ዓመት ዕደሜ፤ አስቀድሞ 1ኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፤ ከዚያ በዓመቱ
ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡
@Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

28 Oct, 07:54


1. በመነጽር ሊስተካከል የሚችል የእይታ ችግር ( Refractive error)
2. የዓይን ሞራ (cataract)
3. በተለያየ ምክንያት የሚከሰት የዓይነ መስታወት ጠባሳ ( በተለይም የቪታሚን ኤ እጥረት፤ ኩፍኝ፤ የዓይነ መስታውት ቁጣ/ምርቀዛ…ወዘተ)
4. የዓይን ግፊት ህመም (Glaucoma)
5. የእይታ ነርቭ ችግር (Optic atrophy)
6. የእይታ አንጎል ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች (Cerebral visual impairment)
7. ያለ ጊዜው ቀድመው በሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ላይ ረቲና ውስጥ የሚፈጠር ችግር [Retinopathy of Prematurity (ROP)]
8. ከውልደት ጀምሮ የሚፈጠሩ የዓይን በሽታዎች (congenital. malformations)

በህጻናት ላይ የዓይን ችግሮችን እንዴት መለየት እንችላለን?

• በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትሉ በሽታዎችን መከላከል ወይም በህክምና ማስወገድ የምንችላቸው ናቸው፡፡
• ይኸውም አስቀድሞ በጊዜው ( በተለይም ህጻናት የዓይንና አንጎል እድገት ላይ ባለበት ከ8 ዓመት በፊት) ችግሩን በመለየትና አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ነው፡፡
• ነገር ግን የአብዛኛዎቹ ህጻናት ዓይን ችግር የሚታወቀው ትምህርት ሲጀምሩ በትምህርት ቤት ውስጥ በሚያሳዩት የዕይታ ችግር በመምህራኖቻቸው ሲሆን ይህም ዉጤታማ ህክምና ለማድረግ በጣም የዘገየ ሊሆን ይችላል፡፡

• ስለሆነም ወላጆች/አሳዳጊዎች አስቀድመው፤
1. የህጻናትን ዓይን በማየትና
2. በሚያሳዩት ባህርይ የዓይን ችግር መኖሩን መለየት ይችላሉ፡፡

በህጻናት ዓይን ላይ ችግር ስለመኖሩ ጠቋሚ ምልክቶች፡-

1. በዓይን ዉሰጥ መሃል ላይ ነጭ ነገር/ነጥብ መታየት
2. መጫወቻ አሻንጉሊት/ብርሃን ወይም የሰውን ፊት አተኩሮ አለማየት እና የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በዐይናቸው አለመከተል ( በጨቅላ ህጻናት ላይ የእይታ መቀነስ ምልክት ነው)
3. አንዱ ወይም ሁለቱም ዓይኖች መጠን ከመደበኛ በታች ትንሽ ወይም ትልቅ መሆን
4. ሸውራራ ዓይን
5. የዓይን ቅላት
6. የዓይን ውስጥ እብጠት /ቁጣ/ምርቀዛ
7. አብዝቶ በተደጋጋሚ እንባ መፍሰስ
8. ዓይነ መጎልጎል (Proptosis)

ህጻናት የሚያሳዩትን የባህርይ ለዉጥ በማጥናት የዓይን ችግር መኖሩን መለየት:-

1. ጨቅላ ህጻናት 3 ወር እድሜ ሲሞላቸው የሰው ፊት ላይ ካላተኮሩና ፈገግታ ካላሳዩ
2. ህጻናት አተኩረው ሲያዩ አንድ ዓይናቸውን የሚሸፍኑ ከሆነ
3. ሲያነቡ ወይም የሚያዩትን ነገሮች ወደ ፊታቸው የሚያቀርቡ ከሆነ ወይም ወደ
ቴሌቪዥን፤ ኮምፒዩተር፤ ሰሌዳ በጣም ቀርበው ብቻ የሚያዩ ከሆነ
4. አተኩረው ሲመለከቱ ፊታቸውን ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያዞሩ ወይም
ጭንቅላታቸውን የሚያገድሉ ከሆነ
5. እድሜያቸው ከፍ ያሉ ህጻናት ደግሞ የሚያዩት ነገር ደብዛዛ ነው ወይም ለማየት
ተቸግሬለሁ ብለው ከተናገሩ
6. በትኩረት ሲመለከቱ ወይም ከሩቅ በሚያዩበት ጊዜ የዓይን ቆብ አጥብበው የሚያዩ ከሆነ
7. የሚያዩት ነገር ደርቦ / ሁለት ሁለት ሆኖ መታየት
8. ዓይነ ዥዋዥዌ (ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የዓይን እንቅስቃሴ)
9. በተደጋጋሚ ዓይናቸውን ማሸት/ማሳከክ ሲኖር

ወላጆች/አሳዳጊዎች የህጻናትን ዓይን ጤና ለመጠበቅ ምን ማድረግ አለበቸው?

• የህጻናትን የእጅና የፊት ንጽህና መጠበቅ
• ክትባት በወቅቱ ማስከተብ (በተለይም የኩፍኝ ክትባት)
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ (በተለይም አትክልትና ፍራፍሬ በቪታሚን ኤ የበለጸጉ
ምግቦችን እንደ ካሮት፤ ማንጎ፤ አቮካዶ፤ አረንጓዴና ሰፋፊ ቅጠላ ቅጠል ያላቸውን)
🥕 🥑 🥦
• የህጻናት ዓይን ላይ ችግር መኖሩን ከጠረጠሩና ጠቋሚ ምልክቶችን ካዩ ሳይዘገዩ
ወዲየውኑ ወደ ዓይን ሕክምና ተቋም በመውሰድ ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡

በህክምና ተቋም የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

- የእይታ ልኬት ይደረጋል
- የመነጽር ልኬት (ህጻናት ሲሆኑ የዓይን ጠብታ በመጨመር የሚደረግ ምርመራ)
- የዓይን ዉጪና ውስጥ ምርመራ
- እንደችግሩ ዓይነት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ምርመራዎች (ለምሳሌ፡ አልትራሳውንድ፤ CT scan/MRI) ማድረግ ሊያስፈልግ ይቻላል፡፡
- ሙሉ ምርመራ ለማድረግ የማይተባበሩ ህጻናት ከሆኑ ደግሞ የሰመመን (ማደንዘዣ) መድኃኒት በመስጠት የሚደረግ ምርመራ
• የህጻናትን ሕክምና መዘገየትን ማስወገድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
• የሐኪም ምክር በተገቢው መፈጸም ወሳኝ ነው፡፡
• መደበኛ ክትትል ሳያቋርጡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሕክምናው

እንደ ችግሩ ዓይነትና ደረጃ የተለያየ ሲሆን፡-
• የመድኃኒት ሕክምና
• የመነጽር ሕክምና
• አንድ ዓይን ለተወሰነ ጊዜ በመሸፈን ስንፈተ ዕይታን ማስተካከልና
• የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊሆን ይችላል።

ጤነኛ ህጻናትን መቼ መቼ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል?

• በወቅቱና በጊዜው መታከም ያለባቸው አስቀድመው ያልታወቁ የዓይን ችግሮች/በሽታዎች የህጻናት ዓይነ ስውርነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
• በመሆኑም አስቀድሞ በወቅቱ ችግሮችን በማወቅና በመለየት መቅረፍና ዓይነ ስውርነትን መከላክል ይቻላል፡፡
• ይኸውም መደበኛ የዓይን ምርመራ በማድረግ ነው፡፡

የመጀመሪያ የዓይን ምርመራ መቼ መደረግ አለበት?

• አንድ አመት እድሜ ላይ ፤ ከዚያ መዋለ ህጻናት(KG) ከመግባታችው በፊት።

በአጠቃላይ፡-
• ከልደት - 2 ዓመት ዕደሜ ፤መጀመሪያ ምርመራ በ 6 - 12 ወር ዕድሜ ላይ
• ከ 3 - 5 ዓመት ዕድሜ ፤ ቢያንስ አንድ ጊዜ ማስመርመር
• ከ6 – 17 ዓመት ዕደሜ፤ አስቀድሞ 1ኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፤ ከዚያ በዓመቱ
ማስመርመር ያስፈልጋል፡፡
@Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

28 Oct, 06:37


Join my channel
t.me/Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

28 Oct, 06:27


የእናት ጡት ወተት ጥቅሞች
📌 በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተሞች አካባቢ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸዉን የሚያጠቡት ከራሳቸው የጡት ወተት ይልቅ የጣሳ ወተትን ስመርጡ ይስተዋላሉ::

📌 በእርግጥ ሁሉም እናቶች የራሳቸው ምክንያት አላቸው::

📌ሆኖም ግን እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናትን ወተት የሚተካ ሌላ አይነት ወተት ወይም ምግብ እስካሁን አልተገኘም ‼️

📌የእናት ጡት ወተት ጥቅሙ ልጇ ብቻ ሳይሆን ለእናትም ለቤተሰብም ለማህበረሰብም ከፍ ሲልም ለሀገር ነው:: እስኪ በዝርዝር እንየዉ፦

1. ጡት ማጥባት ለእናት ያለው ትቅም ፦

✍️ ከ ወሊድ በዋላ ማህፀን ቶሎ እንዲኮማተር እና ወደ ቦታ እንዲመለስ ያረጋል ይሄም የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል
✍️ ከወሊድ በዋላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
✍️ የጡት እና የእንቁላል ማኩረቻ ካንሰርን ይከላከላል
✍️ በ እድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ ስኳር ደም ግፊት እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
✍️ በ እናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
✍️ በተፈጥሮ ስለሚገኝ ወጪ ቆጣቢ ነው
✍️ ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል

2. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ያለው ጥቅም:

👉 ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ይረዳል
👉 የብሩህ አይምሮ(Higher IQ) ባለቤት ያረጋቸዋል
👉 የተለያዩ የህፃናት ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል ለምሳሌ የ ጆሮ፣የሳምባ፣ የአንጀት ፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
👉 የልጆች አለርጂን ይከላከላል
👉 ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል
👉 የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታ(Type 1 Diabetus Mellitus) ይከላከላል
👉 ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይከላከላል

3. የእናት ጡት ወተት ማጥ ባት ለቤተሰብ እና
ለ ማህበረሰብ ያለው ጥቅም

📌 የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የ ጤና ወጪ ይቀንሳል
📌 ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::

እባክዎን ካነበቡ በኋላ ሼር ያድርጉት !

ዶክተር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም
@Dr_temesgen_dejene

ስለ ጤና

18 Oct, 07:41


በእርግዝና ወቅት ሊስተዋሉ የሚገቡ አድገኛ ምልክቶች


👉ከባድ የሆነ እራስ ምታት
👉ከፍተኛ ትኩሳት/ብርድ ብድር ማለት/ማንቀጥቀጥ
👉ብዥ ማለት
👉ራስን ስቶ መውደቅ
👉ከማህጸን ደም መፍሰስ
👉የጽንስ እክንቅስቃሴ መቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ መቆም
👉ፊት ወይም እጅ ማበጥዝ
👉ከፍተኛ የሆነ ሆድ ህመም
👉ከአልጋ ለመነሳት መክበድ
👉ለመተንፈስ መቸገር
እንዚህን ምልክቶች በራሶ ላይ ወይም በእርጉዝ እናት ላይ ካስተዋሉ ወደ ጤና ተቋም ያድርሱዋቸው
ዶ/ር ተመስገን ደጀኔI
ጠቅላላ ሃኪም
@siletenawot

ስለ ጤና

12 Oct, 03:51


የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ከመውሰዶ በፊት
ጥቅሙን እና ጉዳቱን ያውቃሉ?

የወሊድ መከላከያ እንክብሎች

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ከሚጠቅሙን አማራጮች ውስጥ አንዱ በአፍ የሚወሰድ ወይም ኪኒን ተብሎ የሚጠራው የመከላከያ አይነት ነው፡፡
የተወሰኑ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች ኢስትሮጂንና ፕሮጀስትሮን /Estrogen and progesterone/ የተባሉ ሁለት ዓይነት ሆርሞኖችን ይይዛሉ፡፡ እነዚህ እንክብሎች ቅልቅል /Combination/ እንክብሎች ሲባሉ ሌሎች ደግሞ ከፕሮጀስትሮን (Progesterone) ብቻ የተሰሩ እንክብሎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ወሳጅ ሴቶች ቅልቅል እንክብሎችን ይወስዳሉ፡፡
ጥቅሙ
- ወቅቱን የጠበቀ የወር አበባ መታየት
- ለመውሰድ ቀላል ነው
- ዘጠና በመቶ (90%) ያህል አስተማማኝና ተስማሚ ነው፡፡
- የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ችግር አለመፍጠር
- እርግዝናን አለማዘግየት
- ከሌሎቹ የእርግዝና መከላከያ አይነቶች ጋር ሲነፃፀር በአንፃራዊ መልኩ ትንሽ የሚባል የደም መፍሰስ መኖር
- ቅልቅል እንክብሎች (Combination)ተጨማሪ ጥቅሞች ይሰጣሉ
ብጉርን፣ የአጥንት መሳሳትን፣ ካንሰር ያልሆነ የጡት ማደግ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝናን፣ የማህፀን ካንሰርንና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ከብረት ማዕድን ማነስ የሚመጣ የደም ማነስን በመከላከል በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡
ጉዳት
- በየቀኑ ግንኙነት ባይደረግ እንኳን እንክብሉን መውሰድ
- ማቅለሽለሽና ማስታወክ ፣ የጡት ህመም
- ሆድ መንፋት፣ የባህሪ መለዋወጥ በ2-3 ወራት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል
- ከ2-3 ወር የሚቆይ የወር አበባ መዛባትና መጠን መቀነስ (አንዳንዴ ጠብታ ብቻ መታየት) ፡፡ የወሊድ መከላከያ እንክብልዎን መርሳትም ይህን ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡

 እነዚህ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች መወሰድ የሚኖርባቸው የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ከአምስተኛው ቀን ጀምሮ በየእለቱ ያለማቋረጥ ለሀያ አንድ ቀን ነው፡፡

የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መውሰድ ሲጀምሩ ሰውነትዎ እስኪለማመድ ድረስ መድሀኒቶቹ ለመስራት 7ቀናት ይፈልጋል/ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጀመሪያዎቹ 7ቀናት ተጨማሪ /ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል (ለምሳሌ ኮንዶም)፡፡

በመድሀኒቶቹ ምክንያት የሚከሰትን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስና እርግዝናን ለመከላከል እንክብሎቹ መወሰድ ያለባቸው 24 ሰዓታት ባልበለጠ ልዩነት መሆን አለበት፡፡
@siletenawot

ስለ ጤና

10 Oct, 16:19


8ቱ ደም የመለገስ የጤና ጥቅሞች

1. አዲስ የደም ሴል ምርትን ያነቃቃል
2. የልብ ድካምን እና የደም ቧንቧ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳል
3. የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
4. የደም ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል ፤ እንዲሁም ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
5. ጤናማ ጉበት እንዲኖረን ይረዳል
6. የደም ውስጥ የ iron መጠንን በመቆጣጠር Hemochromatosisን(ጤናማ ያልሆነ የ iron ክምችትን) ይከላከላል
7. ነፃ የጤና ምርመራ ያገኛሉ
8. Psychologically speaking, የለገሱት ደም የሌሎችን ህይወት ለማዳን እንደሚውል ባሰቡ ጊዜ በራስ የመተማመን ስሜትዎን ይጨምራል ፡፡

የሰውን ሕይወት ለማዳን ግዴታ የጤና ባለሙያ መሆን የለብዎትም!

470 ሚ.ሊ(ml) ደም መለገስ የ 3 ሰዎችን ህይወት ሊያድን ይችላል!

አሁኑኑ ደም ይለግሱ ፤ ሕይወትን ያድኑ!

Dr. Eyob Dagnew

@siletenawot

ስለ ጤና

16 Sep, 18:35


ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት በራሳችን ልናደርግ የምንችላቸዉ፡፡
👇
ማድረግ የሚገባ
--------------------
#ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ
#ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ (አእምሮአችን መደበኛ የሆነ የእንቅልፍ ፕሮግራም እንዲይዝ ያደርጋሉ ፡፡)
#የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ (ጠዋት ጠዋት ቢሆን ይመረጣል )
#እራት በጊዜ መመገብ ( ከመተኛት ሶስት-አራት ሰዓት ቀደም ብሎ )
#መኝታ ክፍልን ብርሀን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ

ማድረግ የሌለብን
👇
#አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማወራት፤ ቻት ማደረግ
#አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ ማየት፣ ሬዲዮ ማዳመጥ
#አነቃቂ ነገሮች አመሻሽ ላይ መጠቀም
#አልኮል መዉሰድ (ለአጭር ጊዜ የሚረዳ ቢመስልም ከጊዜ በኃላ የተቆራረጠ እንቅልፍ ያስከትላል ፡፡)

ከላይ የተዘረዘሩት ቀላል ዘዴዎች ስለሆኑ የማይሰሩ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ያለ መድኃኒት ጥሩ እንቅልፍ እንድተኙ ረድተዋል፡፡

ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ
👇
-ከላይ የተጠቀሱትን አድርገን አሁንም በቂ እንቅልፍ የማናገኝ ከሆነ
- ተያያዞ የድብርት ስሜት የሚሰማ ከሆነ
-ተያይዞ ጭንቀት ካለ
-በአጠቃላይ የእንቅልፍ ችግሩ በሥራችን ወይም በማህበራዊ ህይወታችንን ላይ ተፅኖ ካሳደረ።
አንድ ሶስተኛ ስንንከባከብ ሁለት ሶስተኛው ላይ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንችላለ

ለምን የሙከራ ስራውን ዛሬ አንጀምርም።መልካም አዳር

@siletenawot @siletenawot

4,560

subscribers

810

photos

8

videos