ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏 @mahibereestifanos111 Channel on Telegram

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

@mahibereestifanos111


በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል

Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏 (Amharic)

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏 የእስራኤል ልጆችን እና ኢምሬዶን መሳኮችን በተመሳሳይ ስብሰባዎች ለመተግበር የሚያዳግም መጽሀፍ ድረገፅ የሚስቡት ተደራሽ ታሪኩን እያየኩ ነው። በመንፈሳዊ ትምህርቶች, ግጥሞች, ያሬዳዊ ዜማዎች, ምስባክ, መዝሙሮች በአውዲዮና በቪዲዮ እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል። እያዳግማቸው የመዝሙር አማካኝን መታወቅ ቀላል እንዲሆኑ እናመሰግናለን። አይከናወንም ከፈለግ እናስፋለን! ከአውዲዮ እጁን ውስጥ ሊታየን ክፋል እስከዚህ ጉዳይ ውስጥ ያለናል።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Feb, 19:02


📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
                   👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Feb, 18:48


🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው ●✥

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

17 Feb, 17:07


ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል። 

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

15 Feb, 17:26


አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️

1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ   50  ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ   25  ብር ካርድ

➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

15 Feb, 17:23


🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው ●✥

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

14 Feb, 11:52


[ ✔️ Minte Boy WAVE ✔️ ]

መመዝገብ የምትፈልጉ ማሟላት ያለባቹ መስፈርት .....!

➛| ግዴታ ከ 20K በላይ መሆን አለበት ቻናላቹ !
➛|የኦርቶዶክስ ቻናል ቢሆን ይመረጣል !
➛| ከ 20K በታች አትምጡ 🙏

👆 ይሄንን ያሟላ በ
@Minte_boy በኩል ያናግረኝ!

𝐅𝐨𝐥𝐝𝐞𝐫 𝐋𝐢𝐧𝐤 👇
https://t.me/addlist/bV7vKqmFYXU3NmVk

Ⓜ️

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

14 Feb, 04:11


👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏


ሥላሴን አመስግኑ ሥላሴን አመስግኑ
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

ሰናይ አርብ 🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

12 Feb, 21:02


#ኢየሱስ_ትወዱታላችሁ ?
ብጹ አቡነ ሺኖዳ ብዙ ሺህ ህዝብ በተገኙበት ጉባኤ እያስተማሩ እያሉ ከግብፅ

ገጠራማ ቦታ የመጣ አንድ ዲያቆን ጥያቄ በወረቀት ጽፎ ላከ፡፡በአካባቢያቸው በአክራሪዎች
ብዙ ክርስቲያኖች እንደሚገደሉ እና መፍትሔ እንዲሠጣቸው ነበር የጠየቀው፡፡

ሺኖዳም ከአስር ሺህ ለማያንሱ ተማሪዎቻቸው
እንዲህ ሲሉ ጠየቁ

# ኢየሱስ ክርስቶስን ትወዱታላችሁ ?
ህዝቡም ለ3 ደቂቃ ያህል በእልልታ አጨበጨበ፡፡
ምን ጥያቄ አለው ብለው መመለሳቸው ነበር፡፡
ጳጳሱም ሌላ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

# አብራችሁት ትሞታላችሁ ?
በዚህን ጊዜ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሱ፡፡ለረዥም
ደቂቃዎች አጨበጨቡ፡፡
# ያመኑት ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለመሞት እንደሆነ አረጋገጡ፡፡
# ይህ ነው ጥሪያችን !
#ይህ ነው ክርስትና! ትንሣኤ ያለ ሞት የታለ?

••••••ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ
የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንድንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን?ሮሜ 6÷3።

ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ
በረከታቸው ይደርብን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

12 Feb, 15:21


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

12 Feb, 14:55


📕✞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት የሰርግ ደግሶ የነበረው  ማን ነበር ?
     

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

08 Feb, 04:13


“አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።”
— መዝሙር 142(143)፥8


🙏ምህረት የምንሰማበት ማለዳ ይሁንልን🙏

🥰 ሰናይ ቀዳሚት ሰንበት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

07 Feb, 04:52


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ
ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር 29 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡- ‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠን
ቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

• የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !

እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣ አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤

እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤

ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፎቶ መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Feb, 19:07


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Feb, 19:00


♥️🌹ጋብቻ ምን ማለት ነው⁉️🌹
ጋብቻ እና የዘር ሐረግ ምን ያገናኛቸዋል⁉️
ጋብቻ የሚፈቀደው ከስንት ዓመት ጀምሮ ነው⁉️
ሴት ሙሽራ ከወንድ ሙሽራ ቀኝ ለምን ትሆናለች⁉️
🌹ሙሽሮች በጫጉላ ጊዜያቸው ለምን አይጾሙም⁉️
ያገባሁት ሰው ካልተመቸኝ ብፈታው ምን ችግር አለው⁉️
እንደምንጋባ እርግጠኛ ከሆንን ግብረስጋ ግንኙነት ብንፈጽም ምን ችግር አለው⁉️

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Feb, 18:50


😢😢😢😢😢😢😢😢😢

የኔን ስራ ተወው ምግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


ሰናይ ምሽት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Feb, 23:36


ዛሬ በዚህ ቦታ እንደተሰበሰባችሁ ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ🥰🥰🥰🥰


መልካም እለተ ሰንበት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Jan, 20:27


አበው ስለ #እመቤታችን_ዕረፍት እንዲህ አሉ፦

"ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች "ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ።"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

"ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው። በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ

"የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ

(በ Deacon Henok Haile የተሰበሰበ)

#credit ፀሐየ ጽድቅ #channel

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Jan, 14:57


አስተርእዮ ማርያም “

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል

ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ

ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።

ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።
የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።
ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።
ሰአሊ ለነ ቅድስት
የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን

ምንጭ። MK


https://t.me/mahibereestifanos111

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

29 Jan, 09:58


🌕 "ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፡ 🌷
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና።"

👑◈ እንኳን ለክብርት እመቤታችን በዓለ ዕረፍት አደረሰን። ◈👑

መልካም በዓል 🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

28 Jan, 18:12


🥰🥰🥰🥰🥰
🥰83 ዓመት🥰
🥰🥰🥰🥰🥰

❤️የልደት በዓል❤️
እድሜ ከጤና ይስጦት
በረከቶት ትድረሰን🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

28 Jan, 18:00


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

28 Jan, 04:54


#እግዚአብሔርን_መፍራት

ከፍርሃታችን የሚመጡትን ጥቅሞች ታያላችሁ? ፍርሃት ባይጠቅም ኖሮ አባቶች ለልጆቻቸው ሞግዚቶችን አይቀጥሩም፤ ሕግ አውጪዎችም በከተሞች ላይ ዳኞችን አይሾሙም ነበር። ከገሃነም የበለጠ የሚያስፈራስ ምን አለ? እናም ገሃነምን ከመፍራት የበለጠ የሚጠቅም ነገር የለም:: ገሃነምን መፍራት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይመራናልና፡፡ ይህ ፍርሃት ባለበት ምቀኝነት ቦታ የለውም፤ ይህ ፍርሃት ባለበት የገንዘብ ፍቅር ቦታ የለውም፤ ቁጣ ይጠፋል፣ ክፉ ምኞቶች ይወገዳሉ፡፡

አንድ ዘብ ሁልጊዜ ነቅቶ በሚጠብቅበት ቤት ውስጥ ሌባ፣ ዘራፊ ወይም ክፉ አድራጊ ሊመጣ እንደማይችል ኹሉ ፍርሃት አዕምሯችንን ሲይዝ፣ ልቅ ምኞቶች በቀላሉ አያጠቁንም፡፡ ይልቁንም ሸሽተው በየአቅጣጫው፣ በፍርሀት ምክንያት ይባረራሉ፡፡

ነገር ግን ፍርሃት ማባረር ብቻ አይደለም ጥቅሙ፤ ክፉ ፍላጎቶቻችንን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን በጎነት ወደ ነፍሳችን ለማምጣትም ይጠቅማል፡፡ ፍርሃት ባለበት ለጋስ መሆን አለ፤ የጸሎት ብርታት፣ ትኩስ የሚደጋገም እንባ እና ለንስሃ የነቃች ነፍስ አለች። ኃጢአትን የሚሸፍን በጎነትን የሚያብበው በማያቋርጥ የፍርሃት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ነው:: ስለዚህ በፍርሃት የማይኖር ሰው ልቡ ደንድኖ የሰይጣን ባርያ እንደሚሆን ኹሉ፣ በፍርሃት የሚኖር ሰው በማያውቀው ጎዳና እንደማይጓዝ ኹሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት በትክክለኛው የጥበብ መንገድ ይወስደናል፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ ገጽ 20 #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Jan, 19:23


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


"ይቅር ማለት ለሌሎች ያንተ ስጦታ ነው፤
መርሳት ደግሞ ለራስህ ያንተ ስጦታ ነው።"

  
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ሰናይ ሌሊት ይሁንላችሁ🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

24 Jan, 19:11


#ጌታችን_ለምን_በሌሊት_ተጠመቀ?
በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ_ለምን_ጌታ_ከውኃ_ከወጣ_በኋላ_ወረደ?
ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡
ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡
ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ይሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

     ወስብሐት ለእግዚአብሔር

#ይቀላቀሉን!!

@credit - tsehaye tsidk channel

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

23 Jan, 17:27


#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ.  3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)



ይቀጥላል....

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

23 Jan, 04:36


እነሆ የ 2017 ጥምቀት አለፈ
🥰🥰🥰 ተመስገን 🥰🥰🥰

በጥምቀት ዙሪያ በብዙሀን ዘንድ ጥያቄ የሚፈጥሩ.....

👉ጌታችን ለምን ተጠመቀ?

👉ጌታችን መች ተጠመቀ?*

👉ስለምን በ 30 ዓመት ተጠመቀ?

👉 ጌታ ለምን በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ?

👉 ቅዱስ ዮሐንስ በማን ስም ጌታን አጠመቀው?

👉 ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቅ ለምን እጁን አልጫነበት?

👉 ጌታችን ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው?

👉 ለምን በውሐ ተጠመቀ?

👉 ለምን በሌሊት ተጠመቀ?

👉 መንፈስ ቅዱስ ለምን ጌታ ከውሐ ከወጣ በኋላ ወረደ?



🥰❗️እነዚህን ጥያቄዎች ዛሬ ማታ ሙሉ መልስ እንሰጥበታለን 🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

23 Jan, 03:58


♥️🌹ጋብቻ ምን ማለት ነው⁉️🌹
ጋብቻ እና የዘር ሐረግ ምን ያገናኛቸዋል⁉️
ጋብቻ የሚፈቀደው ከስንት ዓመት ጀምሮ ነው⁉️
ሴት ሙሽራ ከወንድ ሙሽራ ቀኝ ለምን ትሆናለች⁉️
🌹ሙሽሮች በጫጉላ ጊዜያቸው ለምን አይጾሙም⁉️
ያገባሁት ሰው ካልተመቸኝ ብፈታው ምን ችግር አለው⁉️
እንደምንጋባ እርግጠኛ ከሆንን ግብረስጋ ግንኙነት ብንፈጽም ምን ችግር አለው⁉️

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

22 Jan, 19:07


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

22 Jan, 18:46


💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
               ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Jan, 17:26


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Jan, 17:10


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Jan, 09:00


መቼ ላግባ?

እንኳን ለቃና ዘገሊላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

19 Jan, 08:48


🙏🙏🙏❤️❤️❤️

እንዳንድ ፎቶዎች ከቃላት በላይ ናችው::

* እምነት
* ፅናት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

19 Jan, 06:42


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
"ማናቸውን አስቤ አደንቃለሁ #ከሱራፌል ዘንድ እንደ ባህር ማዕበል የሚቀርብልህን ምሥጋና ነውን? ወይስ በዮርዳኖስ #በትህትና መቆምህን"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

             #ቅዱስ_አትናቴዎስ
      
                   ❤️❤️❤️
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በደህና አደረሰን።
                         ❤️❤️❤️
 

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

18 Jan, 18:31


ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል....❤️

#ይቀላቀሉን!!
@Tsehaye_Tsidk
@Tsehaye_Tsidk

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

18 Jan, 05:46


እንኳን አደረሳችሁ



🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ከተራ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

17 Jan, 19:49


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

17 Jan, 16:41


💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧



እንኳን ለብርሐነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ


የበዓለ ጥምቀትን መዝሙሮች እዚህ ያግኙ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/ortho_mezmur
https://t.me/ortho_mezmur
https://t.me/ortho_mezmur

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

14 Jan, 11:45


🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

ዛሬና ነገ ይመረቃል (ጥር 6 እና 7)

ጥንታዊው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳቱ ተጠናቆ ለምርቃት ደርሷል

🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🔥🔥🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

12 Jan, 18:37


ልደተ እግዚእነ - የመጨረሻው ክፍል

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው


በዓሉን አፍአዊ በኾነ መልኩ ለማክበር ከብዙ ጊዜ በፊት አዲስ ልብስና አዲስ ጫማ ትገዛላችሁ፡፡ ብዙ መብልና ብዙ መጠጥ ታዘጋጃላችሁ፡፡ ሌላ ለዕለቱ የሚያስፈልጋችሁ ነገርም አስቀድማችሁ ታሰናዳላችሁ፡፡ ገላችሁን ትታጠባላችሁ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ስለ ነፍሳችሁ ምንም ደንታ የሌላችሁ፣ በርኵሰት የቆሸሻችሁ፣ ቃለ እግዚአብሔርን የተራባችሁና የተጠማችሁ ኾናችሁ ማየት በእውነት ያለ ሐሰት እጅግ የሚያበሳጭ ነው፡፡

ለምንድን ነው እንደዚህ የምታደርጉት? ለምንድን ነው ነፍሳችሁ ዕራቆቷ ሳለች፥ አፍአዊ ሰውነታችሁን ብቻ ንጹህ ልብስን የምታለብሱት? ለምንድን ነው ባልንጀራችሁ ለሚያየው ልብስ እጅግ የምትጨነቁ ኾናችሁ ሳለ፥ እግዚአብሔር ለሚያየው ልብስ ግን ግድየለሾች የምትኾኑት?

እስኪ ንገሩኝ! ይህ ምሥጢር መንፈሳዊ እሳት እንደ ኾነ አታውቁምን? ምንጭ፥ ውኆች በኃይል ከምድር ፈልቀው እንዲጎርፉ እንደሚያደርግ፥ ይህ ምሥጢርስ መለኮታዊ እሳት እንደ ኾነ አታውቁምን? ስለዚህ እማልዳችኋለሁ! ገለባ፣ ወይም ዕንጨት ወይም ደረቅ ሣር ከተሸከማችሁ ወደዚህ ምሥጢር አትቅረቡ - ኃጢአታችሁ ሳይኾን እናንተ ራሳችሁ ትቃጠላላችሁና፡፡

ዕንቊ፣ ወርቅና ነሐስ የተሸከማችሁ ከኾነ ቅረቡ፡፡ እነዚህ እንደ ገለባው፣ ወይም እንደ ዕንጨቱ፣ ወይም እንደ ደረቅ ሣሩ የሚቃጠሉ ሳይኾኑ ይበልጥ ጽሩያን፣ ንጹሃን የሚኾኑ ናቸውና፡፡ ስለዚህ ዕጥፍ ድርብ በቁዔትን ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሱ ዘንድ ዕንቊንና ወርቅን ነሐስንም የያዛችሁ እንደ ኾነ ወደ ምሥጢር ቅረቡ፡፡

ጥቂትም ቢኾን ክፉ ነገር አግኝቷችሁ ከኾነ ግን አስቀድማችሁ ይህን ከእናንተ አርቁት - አዎን ይህን ከነፍሳችሁ አስወግዱት፡፡ የተጣላችሁት ሰው ካለ ታረቁ፡፡ የተበደላችሁ ካላችሁ የበደላችሁን ሰው ይቅር በሉት፡፡ ቂም በቀላችሁን አስወግዱት፡፡ በውስጣችሁ የተፈጠረውን በጎ ያልኾነውንና ያበጠውን አሳብ በይቅርታ ምላጭ በጥታችሁ ሻሩት፡፡ ምንም ዓይነት ሁከት በልቡናችሁ አይኑር፡፡

እንደዚህ ብዬ የምነግራችሁም በዚህ ምሥጢር የምትቀበሉት፥ ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስን ስለኾነ ነው፡፡ ንጉሥ ደግሞ ሰላም የሰፈነበት፣ ፀጥታ የተሞላበትና የተረጋጋ ሊያድር ይገባዋል፡፡ ስለዚህ ንጉሥ ክርስቶስን የሚቀበለው ኹለንተናችሁ እንደዚህ ይኹን፡፡

አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! በራስህ ላይ ብዙ ጉዳትን የምታከማቸው ለምንድን ነው? አንድ ሰው የቱንም ያህል ጉዳት ቢያደርስብህም እንኳን፥ አንተ በራስህ ላይ የምታደርሰውን ጉዳት ያህል እርሱ በአንተ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ አታውቅምን? "እንዴት?"  ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፦ "ጉዳት ካደረሰብህ ሰው ጋር ባለመታረቅህ ሕገ እግዚአብሔርን ከእግርህ በታች ረግጠሃልና፡፡"

ጠላትህ ሰደበህን? ታዲያ እስኪ ንገረኝ! እግዚአብሔርን የምትሰድበው በዚህ ምክንያት ነውን? ከጠላትህ ጋር አለመታረቅ ማለት ጠላትህን መበቀል ማለት ሳይኾን ታረቁ ብሎ ሕግን የሰጠ እግዚአብሔርን መስደብ ነዋ!

ስለዚህ በዚህ አመካኝተህ ባልንጀራህን አትናቀው፤ ያደረሰብህን በደልንም አግንነህ አትመልከተው፡፡ ከዚህ ይልቅ በሕሊናህ እግዚአብሔርንና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ስታስብ የሚከተለውን ነገር ልብ በለው፡፡ የትኛውን? ስፍር ቊጥር የሌለው በደል ደርሶብህ ሊኾን ይችላል፡፡ ውስጥህ ብዙ ተጎድቶ ሊኾን ይችላል፡፡ አንተ ግን ራስህን ጨክነህ ከዚህ አውጣው፡፡ አውጣውና ጎዳኝ ከምትለው ሰው ጋር ታረቅ፡፡ ይህን ስታደርግም ይህ እንዲደረግ ባዘዘው በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ የኾነ ባለሟልነትን ታገኛለህ፡፡ ታላቅ የኾነ ክብር ትጎናጸፋለህ፡፡ አንተ ትእዛዙን በመተግበር እግዚአብሔርን በዚህ በምድር አክብረኸዋልና፥ እርሱም በሰማያት በታላቅ ክብር ይቀበልሃል፡፡ አንተ አሁን ላሳያሃት ጥቂቷን እርሱም በሰማያት እልፍ ዕጥፍ አድርጎ ይከፍልሃል፡፡ ስለዚህ ይህን ከማድረግ ቸል አትበል፡፡

እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና፥ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በክብር፣ በጌትነት፣ በሥልጣንና በምልክና አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ርስቱን መንግሥቱን እንድንወርስ ይርዳን፡፡ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

                    መልካም ግዜ ❤️‍🩹

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

10 Jan, 21:48


ልደተ እግዚእነ - ፫

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው


“ፍርድቤቶች፥ ምክር ቤቶችም ሆይ! ደኅና ሰንብቱ፡፡ የዕለት ለዕለት ሥራዬ ሆይ! ከእነ ውጣ ውረድህ ደኅና ሰንብት፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ነፍሴን ላድናት ቆርጫለሁና፡፡ ‘ሰው ዓለሙን ኹሉ ቢያተርፍ፥ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋልና?’ (ማቴ.16፡26)፡፡” አዎን! ለሚቀጥሉት ቀናት እንዲህ እናድርግ!

ሰብአ ሰገል ከፋርስ አገር መጡ፡፡ እኛም ከዚህ ዓለም ጫጫታ ወጥተን ወደ ንጉሥ ክርስቶስ እንምጣ! እኛ ከፈቀድን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ሩቅ አይደለምና፡፡ እንዴት? ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ባሕር ማቋረጥ አያሻንምና፤ ወደ አምላካችን ለመምጣት ወደ ተራሮች አፋፍ መውጣት አያስፈልገንምና፡፡

ታዲያ ምንድን ነው የሚያስፈልገን? ቤታችንን እንዝጋ፤ በደላችንን አስበን እናንባ - አብዝተንም እናልቅስ፡፡ ያን ጊዜ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የቆመው ግድግዳ ይደረማመሳል፡፡ ያን ጊዜ ወደ አምላካችን እንዳንቀርብ የከለከለን ዕንቅፋቱ ይወገዳል፡፡ አዎን ያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ሩቅ ኾኖብን የነበረው መንገድ ቅርብ ይኾናል፡፡ “አምላክ ቅሩብ አነ እግዚአብሔር ወኢኮንኩ አምላከ ርኁቀ - [ስንለምንህ ባትሰማን ብትርቀን ነው ትሉኝ እንደኾነ] እኔስ በእውነት [ለለመነኝ ሰው] ቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና እግዚአብሔር (ኤር.23፡23)፡፡ ዳግመኛም ክቡር ዳዊት እንዲህ ብሏልና፡- “ቅሩብ እግዚአብሔር ለኵሎሙ እለ ይጼውዕዎ - እግዚአብሔር ለሚለምኑት ኹሉ ቅርብ ነው” (መዝ.145፡18)፡፡

ብዙ ሰዎች ግን ምንም እንኳን እጅግ በዕውቀት ሕፃናትና ደንታቢሶች፣ ስፍር ቊጥር በሌለው ክፋትም የተሞሉ ቢኾኑም ቅሉ፥ ምንም ሳይዘጋጁ መቅረባቸው እንደ ምን ያለ ዕዳ - እንደ ምን ያለ በደልም እንደሚኾንባቸው አያስተውሉም፡፡ ይህን ሳያስተውሉም እንዲሁ እንደ ተራ ኅብስትና መጠጥ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይጣደፋሉ፡፡ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል የሚያስፈልገው ንጹህ ልብስ ሳይኾን ንጹህና የተዋረደ ልብ መኾኑን ሳያውቁ ይቀርባሉ፡፡

ንጹህና በሕሊናው ርኵስ አሳብ የሌለበት ሰው በየዕለቱ ከምሥጢሩ መሳተፍ ይችላል፡፡ በኃጢአት የተተበተበ ሰው ግን አስቀድሞ ንስሐ ሳይገባ ከዚህ ምሥጢር ሊሳተፍ አይገባውም፡፡ ደሙ “ስቴ ዘመኰንን - የሚፈርድ መጠጥ” ነውና፥ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ፥ ይህቺውንም በንስሐ ሳይታጠብና ሳይገባ’ው ወደዚህ መቅረቡ በበደል ላይ ሌላ በደል ከመጨመር ውጭ ምንም የሚያስገኝለት በቁዔት የለም፡፡

ለዚህም ነው፥ እንዲሁ ደንታቢሶችና አፍአዊ ዝግጅት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጋችሁ ወደዚህ መለኮታዊ ምሥጢር እንዳትቀርቡ የምለምናችሁ! አዎን ለዚህ ነው፥ ከዚህ ቅዱስ ምሥጢር መሳተፍ ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ንስሐ እንድትገቡ፣ ስንፍናችሁን ላለመድገምና እንደ ውሻ ወደ ትፋታችሁ እንዳትመለሱ በንስሐና በጸሎት ምጽዋትን በመስጠትና በመንፈሳዊ ተግባራት ኹሉ በመትጋት ለብዙ ቀናት ራሳችሁን እንድታዘጋጁ የምማጠናችሁ! (ምሳ.26፡11)፡፡

ይቀጥላል...

(ትርጉም በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

10 Jan, 20:14


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

10 Jan, 20:05


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️

         

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

10 Jan, 04:41


ልደተ እግዚእነ - ክፍል ፪

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው


በእርግጥ በዚህ በመሠዊያው ላይ ያለው የጌታችን ሥጋ እንደ ቀድሞ በጨርቅ የተጠቀለለ አይደለም፤ ፍጹም በመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ፡፡ እንደዚህ ብዬ ስናገር ምን ማለቴ እንደ ኾነም በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኙት ይረዱታል፡፡ ሰብአ ሰገል ወደ ጌታችን መጥተው ሰገዱለት፤ እናንተ ሕሊናችሁን ንጹህ አድርጋችሁ ከመጣችሁ ግን እርሱን እንድትበሉትና ይዛችሁትም ወደ ቤታችሁ ትኼዱ ዘንድ እንፈቅድላችኋለን፡፡ ስለዚህ መባችሁን ይዛችሁ ቅረቡ - ነገር ግን ሰብአ ሰገል ይዘዉት እንደ መጡት መባ አይደለም፤ ከእነዚህ ይልቅ ልዑልና ቅዱስ የኾነ መባን ነው እንጂ፡፡ ሰብአ ሰገል ወርቅ ይዘው መጡ፤ እናንተ ግን በወርቅ ፈንታ በመጠን መኖርንና ንጹህ ምግባርን ይዛችሁ ኑ! ሰብአ ሰገል ዕጣን ይዘው መጡ፤ እናንተ ግን ነውር የሌለበት ንጹህ ጸሎትን ከመንፈሳዊ ዕጣን ጋር ይዛችሁ ኑ! ሰብአ ሰገል ከርቤ ይዘው መጡ፤ እናንተ ግን ትሕትናንና የተዋረደ ልብን ፍቅርንም ይዛችሁ ኑ! እነዚህን መባዎች ይዛችሁ ከመጣችሁ ከዚህ ቅዱስ ማዕድ (ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ) ያለ ዕዳ መሳተፍ ይቻላችኋል፡፡

እንደዚህ ብዬ የምነግራችሁም በዚያች ሌሊት ብዙዎቻችሁ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ ለመሳተፍ እንደምትመጡ ስለማውቅ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እንደዚህ ብዬ መናገሬ ለድኅነት ያይደለ ለዕዳ ለፍዳ እንዳይኾንብን ነው፡፡ አዎን እንደዚህ ብዬ የምነግራችሁ - የምማጠናችሁ ወደ ቅዱስ ቁርባን ስትቀርቡ አስቀድማችሁ ልቡናችሁን ከርኵስ አሳብ ኹሉ ንጹህ እንድታደርጉ ስለምሻ ነው፡፡      
  
እማልዳችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንድ ሰውስ እንኳ “እኔ በደሌን ሳስበው ያሳፍረኛል፤ ሕሊናዬ በብዙ ኃጢአት የተሞላ ነው፡፡ ከባድ ሸክምም አለብኝ” አይበለኝ፡፡ እናንተ ፈቃደኞች ከኾናችሁ ከአሁኗ ሰዓት ጀምራችሁ [ንስሐ ብትገቡና] ራሳችሁን ብትገዙ፣ ብትጸልዩ፣ ትግሃ ሌሊትንም ብታበዙ የሚቀጥሉት አምስት ቀናት የኃጢአት ቡትቶአችሁን አሽቀንጥራችሁ ለመጣል በቂ ናቸው፡፡ የጊዜው ማጠር አትመልከቱ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስቡ እንጂ፡፡ አታስታውሱምን? የነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔር ቊጣ እንዲመለስ ያደረጉት በሦስት ቀናት ውስጥ ነበር፡፡ የጊዜው ማጠር ይህን ለማድረግ ዕንቅፋት አልኾነባቸውም፡፡ የልቡናቸው መመለስ እግዚአብሔርም ሊያደርግባቸው ከተናገረው ክፉ ነገር እንዲጸጸት አድርገውታል እንጂ (ዮና.3)፡፡

ዘማይቱ ሴትም በሽርፍራፊ ጊዜ ውስጥ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥታ በደሏ ኹሉ ተሠርዮላታል (ሉቃ.7)፡፡ በዚህ ጊዜ አይሁድ፥ ሴቷ ማን እንደ ኾነች ቢያውቅ ኖሮ እንድትዳስሰው ባላደረገ ነበር ብለው አምተውታል፡፡ ጌታችን ግን ዘማይቱ ወደ እርሱ እንድትቀርብ በማድረግ እነርሱን ዝም አሰኝቷቸዋል፤ የሴቲቱንም ትጋት አመስግኖ ኃጢአቷን ኹሉ ይቅር ብሎ ሰዷታል፡፡

የዚህ መልእክቱስ ምንድን ነው? ሴቲቱ የመጣችው ትጉህ ሕሊናን ይዛ ነው፤ የመጣችው ሥርየተ ኃጢአትን ሽቶ በሚንበለበል ልብ ነው፤ አዎን ሴቲቱ ወደ ጌታችን የቀረበችው በደሏን ይቅር እንደሚላት ጽኑዕ እምነትን ገንዘብ አድርጋ ነው፡፡ ያን ጊዜ የተቀደሰ እግሩን ዳሰሰች፡፡ አለቀሰች፡፡ እንባዋን አፈሰሰች፡፡ እግሩን አራሰች፡፡ በራስ ፀጉሯም እግሩን አበሰች፡፡ እግሩን ሳመችው፡፡ ሽቱም ቀባችው፡፡   
      
ወንዶችን ለዝሙት ትማርክበት የነበረው መንገድ የንስሐ መድኃኒትን አዘጋጀችበት፡፡ ለሴሰኝነት ታይበት የነበረው ዓይኗ አሁን የንስሐ እንባ ያፈስሱ ዘንድ ተጠቀመችበት፡፡ ብዙዎችን በበደል ዓዘቅት ይወድቁ ዘንድ ያጠመደችበት ፀጉሯ አሁን የጌታችንን እግር አበሰችበት፡፡ ዘማውያንን የማረከችበት ሽቶ አሁን የጌታችንን እግር ቀባችበት፡፡ 

እናንተም እንደዚህ አድርጉ፡፡ አዎ! እናንተም እግዚአብሔርን ያሳዘናችሁበት መንገድ መቅረቢያችሁ አድርጉት፡፡ በስርቆት እግዚአብሔርን አሳዝናችሁታልን? ያለ አግባብ የወሰዳችሁትን ገንዘብ ለባለቤቱ መልሱ፡፡ ጨምራችሁም ስጡ፡፡ ከዘኪዎስ ጋር ኾናችሁም፡- “ሰርቄ እንደ ኾነ አራት ዕጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ” በሉ (ሉቃ.19፡8)፡፡ በአንደበታችሁ ብዙ ሰዎችን በማንጓጠጥና በመስደብ ፈጣሪያችሁን አሳዝናችሁታልን? ንጹህ ጸሎትን በመጸለይ፣ የሚረግሙአችሁን በመመረቅ፣ የሚበድሉአችሁንም በማመስገን በዚሁ አንደበታችሁ ተማፀኑት፡፡

እነዚህን ለማድረግም ብዙ ቀናትን አይሹም፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማከናወን ብዙ ዓመታትን አይጠይቁም፡፡  እነዚህን ለማድረግ ከእናንተ የሚፈለገው በጎ ፈቃደኝነታችሁ ብቻ ነው፤ እንደዚህ ከኾነም በአንድ ቀን ውስጥ እነዚህን ማከናወን ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ ከክፋት ራቁ፡፡ በጎ ምግባርን ያዙ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እነዚህን ኃጢአቶች ላለማድረግ ወስኑ፡፡ ይህን ካደረጋችሁም ወደ ምሥጢር መቅረብ ትችላላችሁ፡፡ ዕዳ በደልም አይኾንባችሁም፡፡ ከቀድሞ ክፉ መንገዳችን ብንመለስ፣ መልሰን ወደዚያ ኃጢአት ላለመውደቅም ብንወስን፥ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ከእኛ ምንም ነገር እንደማይሻ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ፡፡ ይህንንም የምለው አምላካችን መሐሪና ቸር ስለ ኾነ ነው፡፡ እርጉዝ ሴት ለመውለድ እንድምትቸኩል ኹሉ እግዚአብሔርም ሰውን ለመማር ይቸኩላልና - ይህ እንዳይኾን የሚከለክለው ኃጢአታችን ነውና፡፡

ስለዚህ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ኾኖ እንዳንተያይ የከለከለንን የበደላችንን አጥር እናፍርስ፡፡ በእነዚህ አምስት ቀናት ውስጥም ይህን ኹሉ በመተውና ሱባኤ በመያዝ ገና ከአሁኑ በዓሉን ማክበር እንጀምር፡፡  

ይቀጥላል …

(ትርጉም በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Jan, 19:14


#ሰብአ_ሰገል_ወርቅ_ዕጣንና_ከርቤ_የመገበራቸው_ምስጢር፡-

የጌታችንን ልደት በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው የመገበራቸው (አምሐ አድርገው የመስጠታቸው) ምስጢር እንደምንድን ነው ቢሉ፡-

#ወርቅ፡-
ወርቅ መገበራቸው ይኸን የምንገብርላቸው ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ነህ፤ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወርቅ ጽሩይ ነው፤ ጽሩየ ባሕርይ ነህ ሲሉ፤ እንዲሁም በአንተ ያመኑ ምዕመናንም ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ወርቅ የሃይማኖት ምሳሌ ነው። የሃይማኖት ጽሩይነቱና ግብዝነቱ የሚታወቅ መከራ ሲቀበሉበት ነውና።

#ዕጣን፡-
ዕጣን መገበራቸው ይህንን የምናጥናቸው ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ። አንድም ዕጣን ምዑዝ ነው፤ አንተም በባሕርይ ምዑዝ ነህ ሲሉ እንዲሁ ደግሞ በአንተም የሚያምኑ ምእመናንን ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ዕጣን የተስፋ ምሳሌ ነው። ዕጣን ከሩቅ እንዲሸት ተስፋ ያልያዙትን እንደያዙት ያላዩትን እንዳዩት ታደርጋለችና።

#ከርቤ፡-
ከርቤ መገበራቸው ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ በኋላም የማታልፍ ብትሆንም በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀበላለህ ሲሉ፤ አንድም ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለየውን አንድ ያደርጋል። አንተም ከማኅበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ ሲሉ። አንድም በዕለተ ዓርብ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት። ከርቤ የምዕመናን ምሳሌ ነው። በፍቅር አንድ ይሆናሉና። ከርቤ የፍቅር ምሳሌ ነው። ከርቤ አንድ እንዲያደርግ ፤ ፍቅርም አንድ ታደርጋለችና።

በአጠቃላይ ሰብአ ሰገል ወርቅ፣ እጣን ከርቤ የገበሩለት ሃይማኖት፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ገንዘቦችህ ናቸው ሲሉ ነው። በሌላ መልኩ ወርቅ ለመንግሥቱ፣ ዕጣን ለመለኮቱ፣ ከርቤ ለሞቱ ምሳሌ ናቸው........

ይቀጥላል

ምንጭ : ፀሐየ ጽድቅ ቻናል

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

07 Jan, 02:12


"#ወርቅ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግርም ተኛ፤
#አይሁድ ጨርቁን አይተው፣ አልፈው እና ተራምደው ሔዱ፤ 
#ሰብአ_ሰገል ግን፣ ጨርቁን ገልጠው ወርቁን አጌጡበት"

  ❤️  .... ፍቅር ተወለደ......


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Jan, 20:16


1⃣GB ስንት MB ነው?

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Jan, 20:01


🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው ●✥

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Jan, 18:30


ፎቶ ፦  የ2017 ዓ/ም የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባና ድሬዳዋ እየተከናወነ ይገኛል።

በአዲስ አበባ መርሐግብር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ የልደት በዓል ዋዜማን በዝማሬ እንዲሁም በምስጋና እያከበረ ይገኛል።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Jan, 06:44


ከግርግሙ ማን ይቀራል?

የምድር ነገሥታት ሰማያዊውን ንጉሥ ለማምለክ ሊመጡ ይገባል። ወታደሮችም ሠራዊትን ሁሉ በአፉ እስትንፋስ ያጸናውን ጌታ ለማገልገል ሊቀርቡ ያስፈልጋል። ሴቶችም ኀዘናቸውን ወደ ደስታ ይለውጥ ዘንድ ከሴት የተወለደውን ያዩ ዘንድ ሊመጡ ይገባል። ሕፃናትም ከሚጠቡ እና ከሕፃናት አፍ ምስጋናን ያዘጋጅ ዘንድ ሕፃን የሆነውን ይመለከቱ ዘንድ ሊመጡ ያስፈልጋል። እረኞችም ነፍሱን ስለ በጎቹ የሚያኖር መልካሙን እረኛ ለማየት ይመጡ ዘንድ ይገባል። ባሮችም የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ በነጻነት ያከብራቸው ዘንድ የባሪያውን መልክ የነሣውን ሕፃን ያዩ ዘንድ መምጣት ይገባቸዋል። ዓሣ አጥማጆቹም የቃሉን መረብ አስይዞ ሰው አጥማጅ የሚያደርጋቸውን ወንድ ልጅ ለማየት ይቀርቡ ዘንድ ይገባቸዋል። ቀረጥ ሰብሳቢዎችም ከቀራጮች መካከል ወንጌላዊ አድርጎ የሚመርጠውን ጌታ ለማየት ሊመጡ ይገባቸዋል። ዘማውያን ቅዱሳት እግሮቹን በዘማውያን እንባ እንዲታጠብ የሚሰጠውን የፍቅር አምላክ ለማየት ይቀርቡ ዘንድ ይገባል። ኃጥአን ሁሉ የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔር በግ ለማየት ሊመጡ ይገባል።

ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ!

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Jan, 04:41


🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

'' እንደ ያሬድ በምስጋና የጌታን ልደት እናክብር''

🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

አምና በድምቀትና በብዙ ክርስቲያኖች የተካሄደው የአእላፋት ዝማሬ ዘንድሮም በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል

ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል
ሁላችሁም በቦታው ተገኝታችሁ እንድትባረኩ ተጋብዛችኋል

'' ጃንደረባው ሚዲያ

🥰''እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ማነው?? 🥰

የዚያ ሰው ይበለን..................

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

03 Jan, 17:10


አትርሳ !

አንድ ሰው ወደ ቤተ መንግሥት አንዲት ሴተኛ አዳሪ ይዞ መጥቶ በንጉሡ ፊትም ሩካቤ ቢፈጸም፣ ወይም ቢሰክር፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ተግባር ቢፈጽም የቅጣት ቅጣት ይደርስበታል።

አሁን ራሳችንን ጥያቄ እንጠይቅ። እግዚአብሔር የሰማይም የምድርም ንጉሥ ነው ወይስ አይደለም? ነው! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል ወይስ አይመለከትም? ኧረ ይመለከታል! ታድያ በምድራዊ ንጉሥ ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍሮ የፈጸመ ሰው ጽኑ ቅጣት የሚቀጣ ከሆነ፥ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በእግዚአብሔር ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድነው? ምድራዊው ንጉሥ ቢቀጣ ምድራዊ ቅጣትን ነው። ሰማያዊው ንጉሥ ሲቀጣ ግን ሰማያዊ ቅጣት እንደ ኾነ አናውቅምን?....

ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህን የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ።

         #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


ታያለህና ማረን🙏🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Dec, 18:20


" የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ይህንን የገለጸው አዘጋጁ የኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት ማኅበር ነው።

የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ የዝማሬ መርሐግብር በበዓሉ ዋዜማ ታኅሣሥ 28/ 2017 ዓ/ም ይካሄዳል።

በአዲስ አበባ ከተማ የዝማሬ መርሐግብሩ አምና በተካሄደበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) እንደሚካሄድ ነው አዘጋጆቹ ያሳወቁት።

" የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት በዝማሬ እናክብር " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የልደት በዓልን ዋዜማ በቤተክርስቲያን ተገኝተው በዝማሬ እንዲያከብሩ ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ካዘጋጁት " የአእላፋት ዝማሬ  / The Melody of Myriads " መርሐግብር ውጭ ሌላ እንዳላዘጋጁ እንዲሁም ለዚህ መርሐግብር ተብሎ የሚደረግ ምዝገባም እንደሌለና ምዕመኑ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ  ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በተካሄደው " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የልደት ዋዜማን በዝማሬና በፀሎት ተቀብሎ ነበር።

መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁአን አባቶች ተገኝተው እንደነበር አይዘነጋም።

ከመርሐግብሩ ቀደም ብሎ ምዕመናን በተለይም ወጣቶች የተዘጋጁ መዝሙሮችን አጥንተው እንዲመጡ መዝሙሮቹ በኦንላይን ሲሰራጩ ነበር።

ዘንድሮም በተመሳሳይ ለመርሃግብሩ የተዘጋጁ መዝሙሮች በማኅበሩ  የማህበራዊ ሚዲያዎች (Janderbaw Media Youtube) ተጭነው ምዕመኑ ጋር እንዲዳረሱ እየተደረገ ነው።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Dec, 18:03


አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️

1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ   50  ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ   25  ብር ካርድ

➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Dec, 17:49


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

29 Dec, 06:16


🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

🥹የዓመት ሰው ይበለን🥹

🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

#ቁልቢ & #ሀዋሳ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

28 Dec, 11:03


#photo_ቁልቢ_ገብርኤል

የሰላሜ ቦታ 🥰🥰🥰

እንኳን አደረሳችሁ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Dec, 20:06


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Dec, 19:49


📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Dec, 19:12


🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ሥርዓተ ማኅሌት ዘታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመትትሐየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ። ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አድኅነነ እግዚኦ አምላክነ፤ ረዳኤ ኲነነ ወኢትግድፈነ፤ ወኢትትሐየየነ በዕለተ ምንዳቤነ፤ ርድአነ በኃይለ መላእክቲከ፤ ከመ ኢንትሐፈር በቅድሜከ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሚካኤል ዘትቀውም በየማና ለማርያም ድንግል፤ ወበጸጋማ ገብርኤል አብሣሬ ትስብእቱ ለቃል፤ ዕቀቡነ ዘልፈ ለለመዋዕል፤ እንዘ ትሰፍሑ አክናፊክሙ ዘነበልባል፤ ወረድኤትክሙ አድኅኖ ዘይክል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለከ ገብርኤል ላዕክ፤ ትስብእተ ፈጣሪ ዘትሰብክ፤ ኀበ ማርያም ልደተ አምላክ፤ ለዳንኤል ዘገሠሥኮ ጊዜ መሥዋዕተ ሠርክ፤ ምስዋዒነ ለለሳዑ ባርክ ባርክ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት፤ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፤ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን።
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጎም ምስጢር፤ ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ኪሩብ ፀዋሬ ዓቢይ መንበር፤ ሕዝቅኤል ዘነጸረከ በአምሳለ ብእሲ ክቡር፤ ምስለ ገጸ ላህም ወአንበሳ ወቀሊል ንስር።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ፤ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ፤ ሥጋዌ ቃል ለድንግል ይሰብክ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ/፪/
እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአዕዛኒከ ኆኃተ ቃለ አብ ሕያው፤ ወለመላትሒከ ሰላም አምሳላተ ጽጌ ዘበድው፤ ኦ ገብርኤል መልአከ አድኅኖ ፍንው፤ አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው፤ አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ፫ቱ ዕደው።
@EOTCmahlet

ወረብ
አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ ሊቀ መላእክት አድኅነኒ ሊቀ መላእክት ዘአድኃንኮሙ/፪/
፫ቱ ዕደው አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ዘአድኃንኮሙ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዘአድኃኖሙ እምዕቶነ እሳት፤ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል፤ ከማሆሙ ያድኅነነ፤ እምኲሉ ዘይትቃረነነ።

ወረብ
እምዕቶነ እሳት 'ዘአድኃኖሙ'/፪/ ገብርኤል ሊቀ መላእክት/፪/
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ዘአድኃኖሙ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአቊያጺከ ወለአብራኪከ ገሃደ፤ እለ ያቄርባ ወትረ ለአምላከ ሰማይ ሰጊደ፤ እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ዘኢትፈቅድ ዕበደ፤ ጥበብ ሐነጸት በወርኅከ ውስተ ልበ አብዳን ማኅፈደ፤ ወአቀመት ላቲ ፯ተ አዕማደ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
እግዚአ አእምሮ ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ፤ ዘኮነ ሥውረ ውስተ ማዕምቀ ጽልመት፤ ወሀቤ ቃለ ትፍሥሕት ለእለ ይሰብኩ ዕበየ ኃይልከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ/፪/
ዘኮነ ዘኮነ ሥውረ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
አልቦ እምሰብእ ዘከማየ ዘይቴክዝ ነግሃ ወሠርከ፤ ወአልቦ እመላእክት ናዛዜ ኅዙናን ዘከማከ፤ ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ፤ ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ዝንቱ ዘአቅረብኩ ለከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ/፪/
ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ አርእየኒ ገጸከ አርእየኒ ገጸከ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ነፍስየ ጥቀ ኃሠሠት ኪያከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ገጸከ አርእየኒ/፪/
ወአስምዓኒ ቃለከ ሊቀ መላእክት/፪/
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ፈትለ ወርቅ ወፈትለ ሜላት አመ በአጽባዕትኪ ተባየጹ፤ አምሳለ መለኮት ወትስብዕት እንዘ ኢየሐፁ፤ ተአምረ ብርሃን ማርያም ለፀሐየ ጽድቅ አንቀጹ፤ ጸገይኪዮ እንበለ አብ በሰሚዓ ቃሉ ወድምፁ፤ ለገብርኤል መልአክኪ ዘፍሡሕ ገጹ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል፤ መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤ ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል፤ ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል።

አመላለስ፦
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል፤
መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤

@EOTCmahlet
ወረብ
ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል/፪/
ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤ ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ ወትቤሎ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
ወትቤሎ ይኩነኒ/፪/
በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
'ወእንዘ ትፈትል'/፪/ ወርቀ ወሜላተ/፪/
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ ወረብ
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤
ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤
@EOTCmahlet
ወቦ ዘይቤ፦
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ፤
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም ፤
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

ቅንዋት፦
ሰበክዎ በአፈ ኵሎሙ ነቢያት፤ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት፤ሰበክዎ ነቢያት፤ከመ ይመጽአ ወልድ በስብሐት፣ ሰበክዎ ነቢያት፤ ነቢያት ቀደሙ አእምሮ ሐዋርያት ተለዉ ዓሠሮ፣ሰበክዎ ነቢያት፤ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ፣ዕሌኒ ንግስት ኀሠሠት መስቀሎ፣ሰበክዎ ነቢያት፤ሚካኤል መልአክ ዘልብሱ መብረቅ፣ወገብርኤል ሐመልማለ ወርቅ፤ሰበክዎ ነቢያት፤ውእቱሰ ተመሰለ ከመ ሰብእ፣ወአንሶስወ ውስተ ዓለም፣ማ-ሰበክዎ ነቢያት፤ዘዕሩይ ምክሩ ምስለ አብ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Dec, 06:22


#የንግስ በዓል
እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ

የገናናውን የቅዱስ ገብርኤልን በአል ከአዲስ አበባ 450 km አከባቢ ርቆ በሚገኘው በኢንጂባራ ዘንገና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

የመልአኩ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Dec, 06:16


🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷
ስርዓተ ዋዜማ አቋቋም ዘታህሳስ ገብርኤል
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

ዋዜማው ከመባሉ በፊት መኃትው የሚባለው ስርዓት ይደረሳል

መኃትው በ2

ሃሌ ሃሌ ሉያ ወአንተሰ ለእመ ትፈቅድ ታእምር ኅድግ ሕሊና ዘበምድር፤ወዕድዎሙ ለከዋክብት፤ስነ ሥርዓቶሙ ወኑባሬሆሙ፤እምዝንቱ ኵሉ ተልዒለከ፤በልቡናከ ሐሊ አሐደ ሥሉሰ ዘኢይሰደቅ፤ወአንተሰ ለእመ ትፈቅድ ታእምር ጽርሐ ቅድሳት፤ቀዋሚት ዘመልዕልተ ሰማያት፤እምዝንቱ ኵሉ ተልዒለከ፤በልቡናከ ሐሊ አሐደ ሥሉሰ ዘኢይሰደቅ፤እስመ ኵሎሙ ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት፤ኢይክሉ አእምሮ ህላዌሁ ለወልድ፤እምዝንቱ ኵሉ ተልዒለከ፤በልቡናከ ሐሊ አሐደ ሥሉሰ ዘኢይሰደቅ፤ስብሐት ዘኢየኃልቅ ወስን ዘያንጸበርቅ፤እስመ ወረደ ወልድ ናዛዚ ተዓዛዚ፤ዓራቂ ለኀበ አቡሁ በእንተ ፍቅረ ውሉደ ሰብእ።

መኃትው እንደተደረሰ ይ.ካ : ቅዱስ

ሁሉም በዜማ: እግዚአብሔር ቅዱስ ሐያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት ዘተወልደ...

አንድ ሰው ዋዜማውን ይቃኛል :

አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።

ሁሉም ቅኝቱን ይቀበላሉ :
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።

መሪ፦ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሉያ
መሪ፦ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሉያ
መሪ፦ሃሌ ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሃሌ ሉያ
መሪ፦ሃሌ ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሃሌ ሉያ
መሪ፦አብሠራ ገብርኤል ለማርያም
ተመሪ፦አብሠራ ገብርኤል ለማርያም
መሪ፦ወይቤላ ትወልዲ ወልደ
ተመሪ፦ወይቤላ ትወልዲ ወልደ

ሁሉም በዝማሜ፦

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

መሪ፦ሚካኤል መልአክ
ተመሪ፦ሚካኤል መልአክ
መሪ፦በክነፍ ፆራ
ተመሪ፦በክነፍ ፆራ
መሪ፦መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
ተመሪ፦መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
መሪ፦ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተመሪ፦ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና
መሪ፦ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ተመሪ፦ወልድ ተወልደ እምኔሃ
መሪ፦ወልድ
ተመሪ፦ወልድ

ሁሉም በዝማሜ ፦ ተወልደ እምኔሃ
@EOTCmahlet
አንድ ሠው ምልጣኑን ያዜማል፦

ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ

ሁሉም በዝማሜ ፦ ተወልደ እምኔሃ

ሌላ 2ኛ ሰው ምልጣኑን በዜማ ይላል፦

ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

ሁሉም ማንሻውን በዝማሜ ይላሉ ፦ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

ከዝማሜ በኃላ በቁም 👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

በመረግድ👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

በቁም👉 ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።


በመረግድ👉
ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

በቁም 👉
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።


በመረግድ👉
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም፤አብሠራ ገብርኤል ለማርያም፤ ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ፣ወልድ

ሁሉም  በጽፋት 👉ተወልደ እምኔሃ

በጽፋት👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

ማስቆርቆር👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ማስመታት👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ማስቆርቆር👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ
ማስመታት👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ

አመላለስ እዚህ ጋር ይገባል

አመላለስ፦
ወልድ ተወልደ እምኔሃ/2ጊዜ/
ወልድ ተወልደ እምኔሃ ወልድ ተወልደ እምኔሃ/2ጊዜ/

በ ጽፋት👉ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ወልድ ተወልደ እምኔሃ

ማስቆርቆር👉ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ
ማስመታት👉ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ
ማስቆርቆር👉መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
ማስመታት👉መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
ማስቆርቆር👉ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ማስመታት👉ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና

በጽፋት👉ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ወልድ ተወልደ እምኔሃ

ረጋ ባለ ጽፋት የከበሮ አመታት👉
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።

ማስቆርቆር👉ሃሌ ሉያ
ማስመታት👉ሃሌ ሉያ
ማስቆርቆር👉ሃሌ ሉያ
ማስመታት👉ሃሌ ሉያ
ማስቆርቆር👉ሃሌ ሃሌ ሉያ
ማስመታት👉ሃሌ ሃሌ ሉያ
ማስቆርቆር👉ሃሌ ሃሌ ሉያ
ማስመታት👉ሃሌ ሃሌ ሉያ
ማስቆርቆር👉አብሠራ ገብርኤል ለማርያም
ማስመታት👉አብሠራ ገብርኤል ለማርያም
ማስቆርቆር👉ወይቤላ ትወልዲ ወልደ
ማስመታት👉ወይቤላ ትወልዲ ወልደ
ማስቆርቆር👉ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ
ማስመታት👉ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ
ማስቆርቆር👉መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
ማስመታት👉መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
ማስቆርቆር👉ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ማስመታት👉ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ማስቆርቆር👉ወልድ
ማስመታት👉ወልድ

ሁሉም  በጽፋት 👉ተወልደ እምኔሃ

በጭብጨባ እና ዝግ ባለ ጽፋት
👉ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።

እዚህ ጋር ካህን ወካዕበ በዜማ ካደረሰ በኃላ ለእግዚአብሔር ምድር ብሎ ከተመራሩ በኃላ ዋዜማ ቅኔ በየመሐሉ ይገባል ቅኔ ከተባለ በኃላ መጨረሻ ላይ ሰላም ይጸፋል

ሰላም በጽፋት የከበሮ አመታት

👉አመ ፲ሩ ወ፱ቱ ለወርሀ  ታኅሣሥ አመ ይትጋብዑ መላእክት፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ገብርኤል ይስእል ምሕረተ፤ ለእንስሳ ሣዕረ ለሰብእ ተግባረ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ሚካኤል በየማነ ምሥዋዕ ይቀውም ዓውዶ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ።
@EOTCmahlet

አመላለስ፦
መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል/2/
መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ/4/

https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Dec, 13:35


እነሆ የገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ሆይ ታህሳስ 19 ሊደርስ 2 ቀናት ብቻ ይቀሩናል🥰🥰🥰

❗️ በየአከባቢያችሁ የሚገኙ የቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ስምና ቦታ እንዲሁም ፎቶ በdiscussion ግሩፕ ላይ ላኩልን እናም መምጣት የሚችሉ ሰዎች በቦታው ላይ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ እንለቃለን

❗️ዛሬ ማታ የበዓሉን ስርዓተ ዋይዜማና ስርዓተ ማህሌት የምንለቅ ይሆናል

በሰላም ያድርሰን 🙏🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

21 Dec, 05:39


ሁሌ ብጠራው የማይሰለቸኝ ስም


ሚካኤል❤️
ሚካኤል ❤️
ሚካኤል ❤️

የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Dec, 11:32


+++ የማያሳፍር ተስፋ +++

ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው “የተስፋ አምላክ” ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? “ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ” ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16)

"ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ"

"ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!"

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

15 Dec, 14:08


#ታህሳስ_6

  ዝ     ክ     ረ   -   ቅ     ዱ     ሳ      ን
  
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለድንግልና ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
           አሐዱ አምላክ አሜን!


   ✞ ቅድስት አርሴማ ድንግል ✞

እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል።
✟ ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት።
✟ ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
✟ ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት።
✟ ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት።
✟ ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት።
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-
1. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት።
2. ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት።
3. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት።

ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት። መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር።

ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ 127 ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ።

በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ።

በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው።

ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው።

አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት።

ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።

የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት።

ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው።

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት። በዋናው ገዳሟ (ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና።

ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ። የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን። አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና።"

በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር። ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች።

ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።

--------------------------------------
"እውነት እላቹሃለሁ። የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል። የሚሳናችሁም ነገር የለም።" (ማቴ. 17:20)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

        #ስንክሳር_ዘወርሃ_ታህሳስ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

14 Dec, 18:41


https://youtu.be/z4Qhi17v6y8?si=GnH0iHWqzA-Qhhxz

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

11 Dec, 18:34


አባ መቃሪ በአንድ ወቅት ስለ ትሕትና ሲያስተምር ‹አንድ ባለጠጋ የነበረ ንጉሥ ያለውን ሀብት በአደራ መልክ ከአንድ ደሃ ዘንድ ቢያኖር ፤ ያ ደሃ በእነዚያ ብሮች እና ወርቆች ሊመካ ይችላልን? እንደ ራሱ ንብረትስ በመቁጠር የባለቤትነት ስሜት ሊሰማው ይገባል?› ሲል ይጠይቃል፡፡ በዚህ ቅዱስ አባት ምሳሌ መሠረት ያ ባለጠጋ ንጉሥ እግዚአብሔር ነው፡፡ አደራ ተቀባዩ ነዳይ ደግሞ እኛ ነን፡፡ አደራውም በእጃችን ያሉ በጎ ነገሮች ሁሉ ናቸው፡፡ ያሉንን መልካም ነገሮች እንደ ራስ ንብረት መቁጠርና በሌላው ላይ መኩራራት አደራ ተቀባይነትን እንደ መርሳት ነው፡፡ ሰው ባልፈጠረው በጎነት እንዴት ይኩራራል?


ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Dec, 21:23


ፎቶ ፦ ትላንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቻይና ምድር የመጀመሪያዋን ደብር በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ አከናውናለች።

ለሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና እንደሚገኙት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያዋን ቤተ ክርስቲያን ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን አቁርበዋል።

በቻይና የመጀመሪያው አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆንም  ሾመዋል።

ከቻይና ክፍላተ ግዛቶች የተሰባሰቡ ምዕመናን ፣ ቻይናውያንና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ተሳትፈዋል።

ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም !

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Dec, 18:42


አለማቀፏ ቤተክርስቲያን🥰🥰🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Dec, 06:49


ሰገነት አይመቸኝ

ካባዬም ክብር አይሆነኝ

ሁሉንም ንቄዋለሁ

ያንተን ቤት መርጫለሁ


መድኃኔዓለም 🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Dec, 19:14


https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Dec, 19:00


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Dec, 18:11


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት በቂምልሽ ተሰቶበታ ይቱብላይ ታገኙታላቹ።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Dec, 18:01


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Dec, 17:21


🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

የደቂቀ እስጢፋኖስ ቻናል ቤተሰቦች ስለሆናችሁ #እናመሰግናለን


#10ሺ

🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Dec, 14:29


ሰው ቢጠላችሁ፣ ሰው ቢሸሻችሁ፣ ስታጡ ጓደኛም ቢከዳችሁ፣ ምንም ብትሆኑ፣ ማለዳም ተነስታችሁ ገንዘብ ብታጡ፣ ስራም ብታጡ ቢቸግራችሁ፣ ዳኛም ባይፈርድላችሁ፤ ዝም ብላችሁ አንድ ቃል በሉ "#እግዚአብሔር_ከእኔ_ጋር_ነው!"

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Dec, 11:27


ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Dec, 18:33


https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=0Go7sSnRgmJ6VFe7

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Dec, 07:51


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

❗️ድንቅ ጽሁፍና በጣም ጠቃሚ ነው ሁላችሁም አንብቡት

መምህራችንን እድሜ ከጤና ይስጣቸው 🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Nov, 18:36


+ ታቦትን ከጣዖት ጋር አታስቀምጡ +

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው ፦ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም››(ዘጸ. 20፡4)

ይህንን ትእዛዝ በእሳት ቀለም የጻፈበት ድንጋይ ሳይደርቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ሌላ ትእዛዝ አዘዘው ፦ ‘ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ’ (ዘጸ. 25፡18) እግዚአብሔር ለሙሴ ምን እያለው ነው? ‘የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ’ ካለው መልሶ የሁለት ኪሩቤል ‘የተቀረጸ ምስል ማሠራቱ ለምንድን ነው?’ መርቅያን የተባለው ጸረ ብሉይ ኪዳን የነበረ ውጉዝ ይህንን ተቃርኖ በመጥቀስ የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔርን ክብር ይግባውና ‘በሃሳቡ እንደሚወላውል’ አድርጎ ሐሰትን ተናግሯል፡፡ እውን እግዚአብሔር ‘የተቀረጸ ምስል አታድርግ’ ያለውን የራሱን ቃል ‘ታቦት ሥራ ፣ ኪሩቤልን ቅረጽ’ ሲል እየጣሰው ይሆን?

ታሪኩ በዚህ አላበቃም ፤ እስራኤላውያን ‘የወርቅ ጥጃ ምስል’ ሰርተው ሲያመልኩ እግዚአብሔር አይቶ ቁጣው ነደደ ፤ ቀሠፋቸውም፡፡ (ዘጸ. 32፡4) ቆይቶ ደግሞ ‘እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው’ (ዘኁ. 21፡8) ነገሩ እንዴት ነው? ከወርቅ ጥጃ መሥራት ጥፋት ከሆነ ከነሐስ እባብ መሥራት እንዴት ልክ ሊሆን ይችላል?

ሳዊሮስ ዘገብሎን የእባቡን ምስል አስመልክቶ ሙሴን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ‘የተረገመ ሥዕል በመከራ ለተናወጠ ሕዝብ እንዴት ድኅነትን ሊያመጣ ይችላል? የተነደፋችሁ ሁላችሁ አንጋጥጣችሁ ወደ ሰማይ ወደ እግዝዚአብሔር ተመልከቱ ወይም ወደ መገናኛው ድንኳን ተመልከቱና ትድናላችሁ’ ቢል አይሻለውም ነበር? ከምድርም ፣ ከሰማይም የተቀረጸ ምስል አታድርግ ያለ ሙሴ ስለምን ይህንን አደረገ? እጅግ የታመንከው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ሆይ የከለከልከውን ነገር ራስህ እየሠራህ ነውን? ‘የተቀረጸ ነገር አታድርግ’ ያልህ አንተ ፣ የጥጃ ምስል የሰባበርህ አንተ የናስ እባብን እንዴት ሠራህ? ያውም በምሥጢር ሳይሆን በገሐድ ነበረ!’ (Severian Bishop of Gabala , Homily on the Serpent pg 56)

ነገሩ ወዲህ ነው ፤ በመጀመሪያ ወደ ማብራሪያው ሳንሔድ ‘የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ’ የሚለው ትእዛዝ ራሱ የተጻፈው በተቀረጸ ምስል ላይ መሆኑን በማስተዋል እንጀምር፡፡ ትእዛዛቱ የተጻፉት ከድንጋይ በተቀረጸ ጽላት ላይ ሲሆን የሚቀመጡት ደግሞ ከግራር እንጨት ተሠርቶ በወርቅ በተለበጠና ከወርቅ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ኪሩቤል ያሉበት ታቦት ውስጥ ነበር፡፡ ስለዚህ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ የሚለውን ቃል እያነበብን ያለነው ከተቀረጸ ምስል ውስጥ ባገኘው በተቀረጸ ሰሌዳ ላይ የመሆኑን ምፀት (irony) እንደ ዋዛ አናልፈውም፡፡ ቃሉ የተጻፈበት ፊደልም ቢሆን ሌላው በጣት የተቀረጸ ነገር መሆኑም የሚዘነጋ ነገር አይደለም፡፡

እግዚአብሔር ‘የተቀረጽ ምስል ለአንተ አታድርግ’ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ግን ብዙዎች ከምስሉ ጀምረው አነበቡት እንጂ ቃሉ የሚጀምረው ‘ከእኔ በቀር ሌላ አማልክት አይሁኑልህ’ በሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ‘ሌላ አምላክ አለ ብለህ አትመን ፤ ይህንን አምነህም የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ ፣ አትስገድላቸው አታምልካቸውም’ ብሎ ከጣዖት አምልኮ እንድንርቅ ያዘዘው ትእዛዝ ነው፡፡ በራሱ ፈቃድ እንዲሠሩ ያዘዛቸው ሁለቱ ኪሩቤልም ‘በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ’ (ይሣሉ ብሎ ያሣላቸው) ሲሆኑ አምላክ ናቸው ተብለው ሊመለኩ አይደለምና የላይኛው ትእዛዝ እነርሱን አይመለከትም፡፡ የናሱን እባብም ኃይሉን ሊገልጥበት ወድዶ አሠራው እንጂ ይመለክ ብሎ አላሠራውም፡፡ በኋላ ዘመን የናሱን እባብ እንደ አምላክ ቆጥረው ከሐውልቶች መካከል አቁመው ያመለኩትን ደግሞ ራሱ እንዲሰባበርባቸው አድርጓል፡፡ (2 ነገሥ. 18፡4)

ይህ ሁሉ የሚያሳየን የተቀረጸ ምስል ሁሉ ጣዖት እንዳልሆነ ፤ በተመሳሳይ እንጨት ፣ በተመሳሳይ ወርቅ ቢሠራ እንኳን የተሠራበት ዓላማ እንደሚለየው ፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሠራ ታቦት እግዚአብሔርን ለመተካት ከተሠራ ጣዖት ጋር ልዩነት እንዳለው ነው፡፡

የታቦትንና የጣዖትን ልዩነት በተመለከተ የፍልስጤም ሰዎችን ያህል ግን እውቀት ያለው ያለ አይመስልም፡፡ ፍዳቸውን አይተው ታቦትን ከጣዖት የለዩ እነሱ ናቸው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ፦

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ብዙዎች በግንባራቸው ተደፍተው ስለመስገዳቸውተጽፎአል:: መስፍኑ ኢያሱ በእግዚአብሔር ታቦት ፊትሰግዶአል:: የእስራኤል ሽማግሌዎችም ሙሉ ቀን በታቦቱፊት ወድቀው ምሕረት ለምነዋል:: (ኢያ. 7:6) በታቦት ፊት ከሰገዱ ሁሉ ግን እጅግ በጣም የሚያስደንቀውከፍልስጤማውያን ዘንድ የታየው ሰጋጅ ብቻ ነው::

ዳጎን ይባላል:: ዳጎን ሰው አይደለም:: ደህና አናጢ እጅ የገባ የፍልስጤማውያን ዛፍ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ከእንጨት ጠርበው ያቆሙት ሰው ሠራሽ አምላክ ነው::አይሰማም አይለማም:: አይበላም አይጠጣም::። ለክብሩ መቅደስ ተሠርቶለት ሰዎች በስሙ እየተሰየሙለት (አብደናጎ ገብረ ዳጎን ማለት ነው እንዲል) ይኖራል::

ዳጎን ተንቀሳቅሶ ባያውቅም ታቦተ ጽዮን ተማርካ አጠገቡ ስትመጣ ግን ተንቀሳቀሰ:: ፍልስጤማውያን ዳጎንን ከታቦተ ጽዮን ጋር እኩል አድርገው አስቀመጡት::በማግሥቱ ሲመጡ ግን ሌላ ነገር ጠበቃቸው:: ‘እነሆም፥ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር ፤ ዳጎንንም አንሥተው ወደ ስፍራው መለሱት" 1ኛ ሳሙ.5:3

አይሰሜ አይለሜው ዳጎን በታሪኩ ቁምነገር ሠርቶ አያውቅም ነበር:: በታቦተ ጽዮን ፊት ሰግዶ ማደሩ ግን ብቸኛው ቁምነገሩ ነው:: ታቦትን ከጣዖት እኩል አድርገው ለሚያስቡ እና ጎን ለጎን ላስቀመጡት የአዛጦን ሰዎች"የእግዚአብሔር ታቦት ይኼ ነው እኔ ግን ጣዖት ነኝ" ብሎበተግባር አሳያቸው:: ለእርሱ ሲሰግዱ ለነበሩት ሰዎች ስግደት የሚገባው በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንደሆነ ሰግዶ አሳያቸው:: በእውነት ዓይን እያለው የማያየው ፣ ጆሮ እያለውየማይሰማው ጣዖት እንኩዋን የገባው እውነት ከብዙዎች ተሰውሮ ታቦትን ጣዖት ሲሉ ማየት ያሳዝናል::

"ታቦትን ጣዖት ስትሉ እኛ እንደሰማን ፍልስጤማውያን እንዳይሰሙ፣ ዳጎን እንዳይሰማችሁ” ያሰኛል:: የአዛጦን መቅደስ ታቦት ገብቶበት እንኳን አልተቀደሰም:: የእግዚአብሔር ታቦት ደግሞ ጣዖት ቤት ገብቶ አልረከሰም:: ታቦት ቢማረክ ቢሸጥ ቢለወጥ ታቦትነቱን አያስቀረውም:: እግዚአብሔርም ኃይል የለውም አይባልም:: ልብ አድርጉ ይህ ሁሉ ታሪክ የሚሆነው የእንስሳ ደም ይረጭበት በነበረው በኦሪት ታቦት ላይ ነው::የክርስቶስ ደም የሚፈስስበት ሥጋው የሚፈተትበት አልፋና ኦሜጋ የሚል ስሙ የሚጻፍበት የሐዲስ ኪዳኑ የመሠዊያ ታቦትማ ምንኛ እጥፍ ክብር ይገባው ይሆን? ዳጎን ለዚያኛው ታቦት ከወደቀ ለዚህኛው የቁርባን ጠረጴዛ እንዴት ይሰባበር ይሆን?

ታቦትን ከጣዖት አጠገብ የማስቀመጥ “ፍልስጤማዊ አባዜ” ያለበት ሰው ግን ይህን ለመረዳት ይቸገራል:: "ዳጎንም እንጨት ታቦተ ጽዮንም እንጨት" ይልሃል:: ሁለቱም እንጨት ነው ነገር ግን ታቦተ ጽዮን እግዚአብሔር ያደረባት ስትሆን ዳጎን ሰይጣን የሰፈረበት ነው:: "የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና" መዝ. 96:5

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

30 Nov, 18:36


ሙሴ የያዘውን በትር የግብፅ ጠንቋዮች ይዘውት ነበር::ሁለቱም እባብ ሆነ ልዩነቱን ግን የሙሴ በትር የአስማተኞቹን ዕባብ ውጣ አሳየች:: "ያም በትር ነው ይሄም በትር ነው" ካልከኝ ፈርዖን ይታዘብሃል:: ጌታ የለበሰውም ቀሚስ ነው ፤ ሕዝቡ የለበሱትም ቀሚስ ነው:: በሕዝብ መካከል እንደ እባብ እየተሳበች በብዙ ቀሚሶች እየተዳሰሰች መጥታ የመሲሑን ቀሚስ ስትነካ ደምዋ ቀጥ ላለላት ሴት "ቀሚስ ቀሚስ ነው" በላትና ትመልስልህ::

አዎ ዳጎንም ታቦተ ጽዮንም የተቀረጸ ምስል ናቸው:: ነገር ግን ታቦት የእግዚአብሔር ዙፋን ሲሆን ጣዖት ግን በእሳታዊ ዙፋኑ ፊት እንድ ማገዶ የሚሰባበር እንጨት ነው፡፡ ታቦትን ከጣዖት ጋር ከመመደብ ይሠውረን:: አንድም ታቦት ሰውነታችንን ከዳጎን ኃጢአት ጋር ከማስቀመጥ ይሠውረን::

‘ብርሃን ከጨለማ ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው’ 2ቆሮ. 6፡14-16

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Nov, 22:09


✞ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እግዚአብሔር አስቡ #ለእርሱ_ያላችሁ_ፍቅር_ምልክቱም_እርሱን ሁል ጊዜ በአሳባችሁ ውስጥ መያዛችሁ ነው። ነቢዩ ዳዊትን አስታውሱት!  እርሱ ንጉሥ እና መሪ እንደ መሆኑ በብዙ ሥራዎች ቢጠመድም "አቤቱ ፦ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ!  ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታየ ነው።" [መዝ 118*97] በማለት ተናግሯል። 

       #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

21 Nov, 16:06


አባቴ🥰🥰🥰

እንደኔ ውለታው ያለበችሁ የሚካኤል ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Nov, 19:23


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ስርአተ  ማህሌተ ሚካኤል ህዳር ፲፪
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎  
የየትኛውም ማህሌት መጀመርያ                                        
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

@EOTCmahlet  @EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ፤ ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።
@EOTCmahlet

ዚቅ
አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ ኢዜነዎ ለሰማይ፤ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ ወተከለ ፫ተ ዕፀ ህይወት በዲበ ምድር።
@EOTCmahlet

ነግሥ
ጎሣዐ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤ አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ ወአንተኑ ለ፳ኤል ዘአውረድከ መና።

@EOTCmahlet
ወረብ
አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ/፪/
ወአንተኑ ለ፳ኤል መና ዘአውረድከ/፪/
@EOTCmahlet

ዚቅ
አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ወርእየቱ ከመ ተቅጻ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤ አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ ዘትረ ኮክሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ።

@EOTCmahlet
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤ ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ።

@EOTCmahlet
ወረብ
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን/፪/
በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ/፪/

@EOTCmahlet
ዚቅ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ፤ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሠፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ

ወረብ፦
@EOTCmahlet
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር/፪/
ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/

@EOTCmahlet
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ፤ በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ፤ ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ፤ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።
@EOTCmahlet

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ/፪/

@EOTCmahlet
ዚቅ
ረሰዮ እግዚኦ ለውእቱ ሚካኤል፤ እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን።

@EOTCmahlet
ወረብ
እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል/፪/
እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ/፪/

@EOTCmahlet
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕንብርትከ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤ ነግኃ ነግኅ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤ በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤ ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ።

@EOTCmahlet
ወረብ
"በገዳም"/፫/ ዘሴሰይኮሙ/፪/
ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ/፪/

@EOTCmahlet
ዚቅ
ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤ ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤ በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርባዐ ዓመተ፤ ወሴሰዮሙ መና ኅብስተ፤ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መስፈርተ።
@EOTCmahlet

ወረብ
ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር/፪/
በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ ለ፳ኤል አርብዐ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/

@EOTCmahlet
መልክአ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤ ለለ፩ ፩ ዘበበክፍሉ፤ ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።
@EOTCmahlet

ዚቅ
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤ ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ።

@EOTCmahlet
ወረብ
ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ/፪/
ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት/፪/

@EOTCmahlet
ምልጣን
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ፤ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ

አመላለስ፦
ሰፊሆ ክነፊሁ/2/
ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ/4/

@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር

ሰላም
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Nov, 14:58


https://www.youtube.com/live/cmU6yLCPvvk?si=uyd4iLUGnaXKbbPf

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Nov, 05:41


https://www.youtube.com/live/gb4-l-BuOss?si=eHJufqwRMgx-PKav

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Nov, 02:12


🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ስርአተ ዋዜማ ዘህዳር ሚካኤል
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
መርሆሙ መዓልት በደመና፤ ወኩሉ ሌሊት በብርዐነ እሳት ፤ ወአውጽኦሙ ለህዝቡ በትፍስዕት፤ ፈነወ መልዐኮ ፣ ወአድዐኖሙ፤ማ፦ እንዘ ሚካኤል የሐውር፤ ቅድመ ትይንቶሙ ለእስራኤል።
  

አመላለስ፦
እንዘ ሚካኤል የሐውር/2/
ቅድመ ትይንቶሙ ለእስራኤል እንዘ ሚካኤል የሐውር/2/

ለእግዚአብሔር ምድር፦
ሀ,
በዕደ መልዐኩ ይቀበነ ወይከሠት አዕይንተ አልባቢነ በዕደ መልዐኩ ይቀበነ


እግዚአብሔር ነግሰ፦
ሚካኤል መልአክ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ወበእንተ ነፍሰ ኩልነ መልአኪየ ይቤሎ መልአክት ሠምሮ መልአከ ኪዳኑ ለክርስቶስ አኮኑ


ይት፦
ነዋ ሚካኤል መልአክክሙ ይስዕል ለክሙ ኃበ እግዚአብሔር ልዑል ዘይሰርር ለመድሀኒተ ኩሉ ዓለም በክልዔ ክንፍ


ሰላም፦
በ፪ ዳንኤልኒ ይቤ ነዋ ሚካኤል አሐዱ እመላእክት፤ እምቅዱሳን ቀደምት መጽአ ይርድአኒ፤ አጽንዓኒ ወይቤለኒ፤ ኢትፍራህ ብእሲ ፍትወት አንተ፤ ሰላም ለከ ጽናዕ ወተአገሥ፤ ወእንዘ ይትናገረኒ ጸናዕኩ ወይቤሎ፤ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ፤ ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ፤ ሚካኤል መልአክክሙ።



አመላለስ፦
ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ ወይቤለኒ፤[፪]
ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ ሚካኤል መልአክክሙ[፬]



https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

18 Nov, 17:25


🥰🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🥰


ሕዳር ሚካኤል ሥርዓተ ዋይዜማና ሥርዓተ ማኅሌት


loading................

👉.........👍..........

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

17 Nov, 10:07


#ምክር_ወተግሳፅ

ልጄ ሆይ ለአፍህ መሐላ አታልምደው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ፡፡ ልጄ ሆይ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም፡፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡

አንተስ??  ነገ የሚከተልህ የሰበሰብከዉ ገንዘብ ፥ያፈራሀቸዉ ጎደኞችህ እንዲሁም ሀብትህ አይደሉም በጎ ስራህ እንጂ፥ትዕዛዛትን ፈፅም፥በዉሎህ ቃሉን አስብ፥ ለመፈፀምም ትጋ፥ ያለ ሀጢያቱ ስለ ፍፁም ፍቅሩ የሆነልህን አስብ በዚያን ጊዜ በዋጋ እንደተገዛህ ታስተዉላለህ ጊዜህንም በከንቱ በመኖር አታጠፋዉም።

ክብር ይግባዉና ጌታችን እንዲህ አለ "ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ"

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

15 Nov, 17:21


#ህዳር_6 (፮)

   ዝ     ክ     ረ   -   ቅ     ዱ     ሳ     ን       

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች እንኳን ክብርት ለምትሆን ለበዓለ ደብረ ቁስቋም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

       ✟ በዓለ ደብረ ቁስቋም ✟

የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች። በወንጌል ላይ (ማቴ ፪፥፩-፲፰) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በሁለት ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤውን ገበሩ፤ አገቡለት።

ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሄሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች።
ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በላበትና በእንባ ተጉዛ ምድረ ግብፅ ገብታለች።

የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታች።

ለእኛ የሕይወት እንጀራ ተሸክማ እርሷ ተራበች።

የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች።

የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች።

የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች።

እመ አምላክ

ተራበች፣

ተጠማች፣

ታረዘች፣

ደከመች፣

አዘነች፣

አለቀሰች፣

እግሯ ደማ፣

ተንገላታች።

ለሚገባው ይህ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድህነት ነው። በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው። አራዊት፣ ዕፅዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአምላክ እናት ክብር ይሰጣሉ።
አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል።
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና።
"መድኃኔዓለም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ አደረገ?"

፩. ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ። በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና።
(ኢሳ ፲፱፥፩ ፣ ዕን ፫፣፯)

፪. ምሳሌውን ለመፈጸም። የሥጋ አባቶች እነ አብርሃም፣ ያዕቆብ (እሥራኤል)፣ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና።

፫. ከግብጽ ጣኦት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ።
(ኢሳ. ፲፱፥፩)

፬. የግብጽና የኢትዮጵያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ።

፭. ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ። (ሰው ባይሆን ኖሮ አይሰደድም ነበር። ሄሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም። ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ አርብ ደሙ አይፈስምና።)

፮. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት እና

፯. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው። እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር (ለአርባ ሁለት ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ። ድንግል ማርያም ከርጉም ሄሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሄደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ድንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው። በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሄሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች። በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች።

"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል።
(እሴብሕ ጸጋኪ)

ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው።) ዐረፈች። ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሞ፣ አክሱም፣ ደብረ ዓባይ፣ ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች። በጣና ገዳማትም በተለይ በጣና ቂርቆስ ለመቶ ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጎጃም ወደ ሸዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች።
ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች። በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች።

ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች።
ሄሮድስ መሞቱን መልአከ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል። እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በአምስት ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል።
ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት አራት መቶ አመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቋም ታንጻ ተቀድሳለች። የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች።

ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በ፫፻፺ዎቹ አከባቢ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃንንና ሰማዕታትን አስከትሎ ወረደ። የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንፀው ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሆኗል።

ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-

"እመ ኅሎኩ በጎይዮቱ ውእተ መዋዕለ
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኅበ ተተክለ
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ።" እንዳሉ።
(ሰቆቃወ ድንግል)

እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል።
ይህ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ።
የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና። ስደቷን አስበን ካዘንን፣ መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና።

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ።" ልንልም ይገባል።


--------------------------------------------
ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።
(የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፪፥፬-፮)

   <<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>

#ስንክሳር_ዘወርሃ_ህዳር

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

14 Nov, 17:53


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ስረዓተ ማኅሌት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ነግስ/ለልሳንከ/
@EOTCmahlet
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ/2/
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
@EOTCmahlet
በስመ እግዚአብሔር
@EOTCmahlet
በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤
ሰቆቃወ ድንግል እጽህፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤
ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤
ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤
ርእዮ ለይብኪ አይነ ልብ ዘቦ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ከማሃ ኃዘን ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን/2/
ሶበ በኲለሄ ረከቦ ከማሃ ኃዘን/2/
@EOTCmahlet
ዚቅ
አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ ምንዳቤ ወኃዘነ ወኲሎ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ/2/
ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል/2/
@EOTCmahlet
ምዕረ በዘባንኪ
@EOTCmahlet
ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።
@EOTCmahlet
ወረብ
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ/2/
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ/2/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስዕን ሕፃንኪ ያንቀዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ እስከ ትፀውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ።
@EOTCmahlet
አብርሂ አብርሂ
@EOTCmahlet
አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ፤
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ፤
ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤
ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤
ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ አብርሂ ጽዮን በጽሐ ብርሃንኪ ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል በሰላም ቦአ ኀቤኪ።
@EOTCmahlet
ወረብ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም/2/
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም (ደብረ ... እከሌ)/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ምልጣን
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤ እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤ አማን፤ ወበምድር ሰላም።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም፦
ይቤ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፤ ሶበ ዕኩ ውስተ ዝ ንቱ ቤት፤ አዕረፈት ነፍስየ እምፃማ ዘረከበኒ በፍኖ ት፤ ኀበ ኀደረት ቅድስት ድንግል፤ ምስለ ፍቁር ወ ልዳ ኢየሱስ ክርስቶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም ዓዲ (ወይም)፦
መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም፤ ወልደ ቅ ድስት ማርያም፤ ኃሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉ ሥ ዘለዓለም፤ ግሩም እምግሩማን፤ ብርሃነ ሕይ ወት ዘኢይጸልም ኃደረ ደብረ ቍስቋም፤ ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

11 Nov, 17:49


በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ:-

"ከሞትክ በኋላ ሰዎች በምን ያክል ፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ መላ ዘመንህን እግዚአብሔርን ለማስደሰት ትኖር ነበር።"

❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
ለማን ነው የምንኖረው ⁉️..........
መልሱን ለናንተው ተውኩት🤲
መልካም ምሽትን ተመኘሁላችሁ
🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

10 Nov, 11:25


ተፈጸመ 🥰..........

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Nov, 17:22


ማኅሌት ለምትሄዱ ሁላችሁ

መልካም የበረከትና የምስጋና ሌሊት ይሁንላችሁ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Nov, 17:21


🥰ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ🥰

🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲
የመጨረሻው የማህሌተ ጽጌ እሁድ
🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲

እንኳን አደረሳችሁ......


❗️ ማንም ቢቻለው በቤቱ አይደር የእመቤታችንን በረከት በአቅራቢያችሁ በሚገኙ አድባራት ሄዳችሁ ተካፈሉ ደስ የሚል አገልግሎትና የምስጋና ምሽት ነው🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

በሰው ሀገር ያላችሁ የስዱዳን እናት እመብርሃን በሰላም ለሀገራችሁ ታብቃችሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Nov, 17:15


ተፈጸመ ዘመነ(ወርሀ ጽጌ)🌹


🌹የአዳምን ስደት ተሰደድሽ
🌹የሔዋንን መከራ ተካፈልሽ
🌹የአዳምን ህመም ታመምሽ
🌹የሔዋንን ረሀብ ተራብሽ
🌹የአዳምን ጥም ተጠማሽ
🌹 የሔዋንን መጠላት ተጠላሽ
🌹አዳም ከርስቱ ገነት እንደወጣ አንቺም ከዘመዶችሽ ሀገር ወጣሽ
እንግዲህ ስደቱ ይብቃሽ ተመለሽ

ድንግል ሆይ ለታቀፍሽ ልጅሽ ብቻ አይደለም ስደትሽ በነፍስም በስጋም ለጎሰቆልነው ለእኛ እንጂ🌹

🥀ስለዚህ መድሀኒታችን ሆይ እንወድሻለን🌹☀️🙏

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

09 Nov, 09:10


🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ዘሳድስ ሣምንት ጽጌ በዓለ ልደታ ወራጉኤል ሊቀ መላእክት ስርዓተ ማህሌት
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ለማንኛውም ወርኃዊ እና አመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አሠርገወ ገዳማት ስን በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኩሉ ክብሩ ከመ አሎን ጽጌያት ኢቀደምት ወኢያኃርት :ዓራዛተ ሰርጎ ነሢኦሙ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊሃ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)፦
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
እምሥርወ ዕሤይ ሠሪፃ ዘእምዘርዓ ዳዊት ተወሊዳ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ከመ ፍህሶ ቀይህ ከናፍሪሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወከመ ሮማን መላትሒሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ኅብስተ ሕይወት በየማና ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወጽዋዓ ወይን በጸጋማ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ጸሎታ ወበረከታ ይኩነነ ወልታ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ ፍኖተ ነፈርዓፅ/፪/
ማዕከለ ማኅበር እዜምር ማዕከለ ማኅበር/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን።
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ፦
ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ፤ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ  ጽሩይ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ 
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ :ጌራ ባሕሪይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል በብስራትክሙ መሐይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀሰመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ፦
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ
ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ
ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት
ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።
@EOTCmahlet

መዝሙር ፦
በ፮ ሃሌታ-
ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/፪/
ከመ አሐዱ እምእሉ/፬/

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

07 Nov, 18:01


🥰መድኃኔዓለም ክርስቶስ በአበው አንደበት
🥰
"በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል በቀኖት ተቸነከሩ ወዮ።"
  
             #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››

          #ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

"ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል።
        
ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል።
ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ። አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ።
       
እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በ ሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ። ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ።

እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ።
       
እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር።
      
እርሱ የተሰቀለ ነበር፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር።"

     #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ

🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

07 Nov, 16:51


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel


👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

06 Nov, 11:37


#ጥቅምት_27


  ዝ     ክ    ረ    -    ቅ    ዱ    ሳ     ን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
         አሐዱ አምላክ አሜን።

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለአባታችንና ለአምላካችን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺


✞ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም -  ክ ር ስ ቶ ስ ✞


ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈፀመው የማዳን ስራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት።

ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፤ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።

ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት።

ራሱንም በዘንግ መቱት።

እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ። በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ገረፉት።

ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ታአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ።

በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አስራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍጹም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ። ፈጣሪያችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት ፳፯ የሚውለው ዓብይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓብይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው።

ምንም እንኳ በቅርብ ጊዜ በዓብይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ስርዓት አላቆዩልንም። ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም። በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት ፳፯ ሲመጣ፤ የመጋቢት ፭ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት ፭፤ የመጋቢት ፲ መስቀል ወደ መስከረም ፲፯ መጥቶ እንዲከበር ሆኗል።

አባታችን መድኃኔዓለም ሀገራችን ከገባችበት መከራና መዓት በምህረትና በቸርነቱ ይታደገን።


-------------------------------------------
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ። ሕማማችንንም ተሸክሟል። እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ። ስለ በደላችንም ደቀቀ። የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ። በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።"  (ኢሳ ፶፫፥፬-፭)

     <<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>

         #ስንክሳር_ዘወርሃ_ጥቅምት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

05 Nov, 18:47


🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
አመ ፳ወ፯ ለጥቅምት መድኃኔዓለም ስረዓተ ማህሌት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
@EOTCmahlet
ስረዓተ ነግሥ
@EOTCmahlet
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet

መልክዓ ሥላሴ
@EOTCmahlet
ለኲልያቲክሙ
@EOTCmahlet
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።
ዘጣዕሙ
@EOTCmahlet
ለዝክረ ስምኪ
@EOTCmahlet
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ልዑል ረሰዮ ለመሰረትኪ፤ ዓረፋትኪ ዘመረግድ፤ ደቂቅኪ ምሁራን በኀበ እግዚአብሔር፤ ቆዓ ትጼኑ ቆዓ ጽጌ ወይን፤ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ ጽዮን ቅድስት ቤተ ከርስቲያን፤ ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት።
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማዕዜኑ
@EOTCmahlet
እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፤
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤
ለወልድኪ ህፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ፤
እምግብፅ ይፄውዖ አቡሁ ራማዊ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ለወልድኪ ህፃን ዘስሙ ናዝራዊ(፪) ህፃን፤
እምግብፅ(፪)ይፄውዖ አቡሁ ራማዊ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አንቀጸ ክብሮሙ ለቅዱሳን ሰአሊ ለነ ማርያም እሙ ለመድኅን።
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
@EOTCmahlet
አድኅንኒ በተአምርኪ

አድኅንኒ በተአምርኪ ዳግመ ኢያስቆቁ፤
ሰቆቃወ ዚአኪ ድንግል ይበቊአኒ በሕቁ፤
እስመ አንቲ ወትረ መድኃኒተ አዳም ወደቂቁ፤
ኃልዩ ኀጥአነ እስከ አደኀነ በጽድቁ፤
ከመ በጽጌኪ ንጉሥ ተሰቅለ ዕራቁ።
@EOTCmahlet
ወረብ
አድኅንኒ ኢያስቆቁ በተአምርኪ በተአምርኪ ወላዲተ ቃል፤
እስመ አንቲ ወትረ መድኃኒተ አዳም ወደቂቁ በተአምርኪ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዓዳ እስመ በእንቲአሃ ወበእንተ አዝማዲሃ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ ይቤ አዳምሃ አቤልሃ አብርሐምሃ ይስሐቅሃ ወያዕቆብሃ ወባዕዳነ ነቢያት እለ ከማሆሙ ዓቀቡ ህግየ ከመ በላዕሌሆሙ እሰብሕ እስከ ለዓለመ ዓለም።
@EOTCmahlet
መልክአ መድኃኔዓለም
@EOTCmahlet
ለዝክረ ስምከ
@EOTCmahlet
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሚተ፤
መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤
መድኃኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤
ዘሰተይከ በእንቲአነ ከርቤ ወሐሞተ፤
በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዘሰማዕኮ ጸሎቶ ወስዕለቶ ለመባዓ ጽዮን፤ ተወከፍ ጸሎተነ ፤ሰላመከ ሀበነ፤ እማዕከሌነ ኢትርኃቅ።
@EOTCmahlet
ለመታክፍቲከ
@EOTCmahlet
ሰላም ለመታክፍቲከ እለ ዖራ መስቀለ፤
ወለዘባንከ ክቡር እምዘባነ ኪሩብ ዘተልዕለ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ዘኢተአምር በቀለ፤
ተማኅጸንኩ በጻድቃኒከ እስመ ወሀብኮሙ ቃለ፤
ዘጸውአ ስመክሙ አምህር ብሂለ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሉያ(፫)፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ ዘተሰቀልከ በእንተ ኀጥአን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ ከመ ትቤዙ ነፍሰ ጻድቃን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ በአማን ቃልከ አዳም።
@EOTCmahlet
ወረብ
ሃሌ ሉያ በአማን(፪)ቃልከ አዳም፤
በእንተ ኃጥአን ዘተሰቀልከ መድኃኔዓለም።
@EOTCmahlet
ለመልክዕከ
@EOTCmahlet
ሰላም ለመልክዕከ ዘተጠምቀ በደሙ፤ለጻድቃን አኮ ለቤዛ ኃጥአን ዳዕሙ፤ መድኃኔዓለም ኀቤከ እገይሥ ለለጌሠሙ፤ እስመ ሰማዕኩ ኂሩተከ በከመ ትቤ ቀዲሙ፤ በላዕለ መስቀል አባ ሥረይ ሎሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
እስመ ለነ ለኃጥአን ለእመ መሐርከነ ውእተ አሚረ ትሰመይ መሐሪ፤ ወለጻድቃንሰ እምግባሮሙ ትሜሕሮሙ፤ ወትዔሥዮሙ በከመ ጽድቆሙ።
@EOTCmahlet
ዓዲ
ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት፤ ወበዝኁ ውሉደ ጥምቀት፤ ትእምርተ መድኃኒትነ፤ ቆመ ማዕከለ አሕዛብ፤ እስመ ቤዘወነ ክርስቶስ በዕፀ መስቀሉ፤ ወተሣየጠነ በክዕወተ ደሙ፤ ገብረ ሕይወት ማዕከሌነ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት ወበዝኁ ውሉደ ጥምቀት፤
ማዕከለ አሕዛብ ቆመ መድኃኔዓለም።
@EOTCmahlet
ምልጣን
@EOTCmahlet
እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ፤ አዕበዮሙ ለአበዊነ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
በመስቀሉ ወበቃሉ፤
አዕበዮሙ ለአበዊነ።
@EOTCmahlet
ወረብ
እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን፤
አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን በመስቀሉ ወበቃሉ አሠርገዋ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት፤ምድር ሠናይት ወአኮ ከመ ምድረ ግብፅ፤ምድር ሠናይት እንተ ዘልፈ ይሔውጻ፤እግዚአብሔር እም አመት፤እስከ ርዕሰ ዓውደ አመት፤ምድር ሠናይት ወአኮ ከመ ምድረ ግብፅ፤ያዕቆብኒ ይቤ ርኢኩ ሰዋስወ ዘሰማይ፤ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር፤ሐነጸ መቅደሶ በአርያም፤ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም፤ዝየ አኃድር እስመ ሐረይክዋ፤ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ ሥርጉት፤ዓረፋቲሃ ለቤተ ክርስቲያን በዕንቊ ሰንፔር ወበጳዝዮን ሥርጉት፤ወበከርከዴን ወበመረግድ ሥርጉት፤በአስማተ ፲ቱ ወ፭ቱ ነብያት ሥርጉት፤በአሰማተ ፲ቱ ወ፪ቱ ሐዋርያት ሥርጉት፤ሐፁር የዓውዳ ወጽጌ ሬዳ ብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ንጉሠ ፳ኤል፤አልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ንጉሠ ፳ኤል፤ህየ ማኅደሩ ለልዑል፤ንጉሠ ፳ኤል፤መድኃኔ ዓለም እግዚአብሔር ኀደረ፤ላዕሌሃ ኪያሃ ዘሰምረ ሀገረ።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Nov, 20:19


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

04 Nov, 20:12


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

03 Nov, 06:59


#Paws
በተጀመረ በ 3 ቀን ውስጥ verify የተደረገ የሚገርም airdrop ነው ካለፈ በኋላ እንዳይጸጽታችሁ አሁኑኑ start በሉት

ምንም አይነት tap tap የለውም እንደ #Dogs አንዴ claim ማድረግና task መስራት ብቻ ነው

👇👇👇👇
Start
Start
Start
Start

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

02 Nov, 15:28


⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
ማህሌተ ጽጌ ዘሐምሳይ ሣምንት በዓለ ተክለሃይማኖት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ስርዓተ ነግሥ፦
ለማንኛውም ወርኃዊ እና አመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ገባሬ ኩሉ-
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።
@EOTCmahlet
ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)
@EOTCmahlet
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃን  ቅዱሳን።
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ፦
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ
@EOTCmahlet
ወረብ-
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።
@EOTCmahlet
ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ
@EOTCmahlet

መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ።
@EOTCmahlet

አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፬/
@EOTCmahlet

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Nov, 19:54


💰ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ

አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
                 👇👇

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Nov, 19:30


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Nov, 18:50


#Paws
በተጀመረ በ 3 ቀን ውስጥ verify የተደረገ የሚገርም airdrop ነው ካለፈ በኋላ እንዳይጸጽታችሁ አሁኑኑ start በሉት

ምንም አይነት tap tap የለውም እንደ #Dogs አንዴ claim ማድረግና task መስራት ብቻ ነው

👇👇👇👇
Start
Start
Start
Start

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

01 Nov, 06:57


#Paws
በተጀመረ በ 3 ቀን ውስጥ verify የተደረገ የሚገርም airdrop ነው ካለፈ በኋላ እንዳይጸጽታችሁ አሁኑኑ start በሉት

ምንም አይነት tap tap የለውም እንደ #Dogs አንዴ claim ማድረግና task መስራት ብቻ ነው

👇👇👇👇
Start
Start
Start
Start

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

28 Oct, 18:42


ሁሌም ለጸሎት ስንቆም ይህንን ማለት አንዘንጋ
"
እመቤቴ ሆይ ልጅሽ ሲታገሰኝ ፤ ልቤ የደነደነብኝ እኔን በምልጃሽ አስቢኝ።"

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

27 Oct, 10:22


አባቴ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

26 Oct, 20:01


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ማህሌተ ጽጌ ዘራብዕ ሣምንት በዓለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

@EOTCmahlet
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ እግዚአ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት፤ወሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናግሮ በዓምደ ደመና እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ  ማርያም  ቀጸላ  መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት ።
@EOTCmahlet
ማሕሌተ ጽጌ
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም ይገብር መንክረ፤እንዘ ጻእረ ሞት ያረስዕ ወያሰተጥዕም መሪረ፤በመአዛ ጽጌኪሰ ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ፤ውግረተ አዕባን ይመስሎ ኀሠረ፤እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ውግረተ አዕባን ውግረተ አዕባን ኀሠረ ይመስሎ ይመስሎ ኀሠረ/፪/
ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ በመአዛ ጽጌኪ እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ/፪/
ዚቅ
ሐሙ ርኀቡ ጸምዑ ወተመንደቡ፤ ዘኢይደልዎ ለዓለም ረከቡ፤ ቦ እለ በእሳት ወቦ እለ በኵናት፤ ቦ እለ በውግረተ ዕብን ወቦ እለ በመጥባሕት ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አስበ ፃማሆሙ ነሥኡ ሰማዕት ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ፅጌ፦
ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቋወ ድንግል
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ  ምስካዮሙ ለግፉዓን፤እግዚአብሔር ማኅደር  ዘአልቦ  ከመ  ነዳያን፤ ኢየሱስ ነግድ  ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤ወልደ አብ ፍቁር  ዘበኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ  ብካይ ኮነኒ ዘእሙ  ኃዘን።
@EOTCmahlet
ወረብ
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን/፪/
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አንተ ውእቱ ምርጕዞሙ ለጻድቃን፤ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፤ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መዝሙር
በ፭
ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት፤ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተክርስቲያን፤እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት፤ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ፤ እግዚኣ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት፤ወሠራዕኮ ሰንበተ ለሰብአ ዕረፍተ፤ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ፤ሊቅ ነአምን ብከ ።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Oct, 17:23


ጊዜ ከፋ
ዘመን ጠፋ
ያላንቺማ እናቴ
ማንስ አለኝ ተስፋ

ላፍታ ለደቂቃ
ባክሽ አትራቂኝ
ኪዳነምህረት እናቴ
አለሁልህ በይኝ🤲🤲🤲

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Oct, 17:15


📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
                   👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Oct, 16:58


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

25 Oct, 10:42


ማነው የሕጻኑ ወዳጅ 🥰🥰🥰

ሕጻን ወእሙ
ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

24 Oct, 11:21


#ጥቅምት_14

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
        አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን።

  ዝ     ክ     ረ   -   ቅ     ዱ     ሳ      ን

    ✟ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ✟

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለታላቁ ጻድቅ ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ። የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው።

ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል። በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ።

በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል።

"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ።

በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል።

ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል። በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት። የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል።

እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል። በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች። ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል።

ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ-የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል።

ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ። በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሐረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች።

ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል። ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።

አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን። በረከታቸውንም ያብዛልን።

-------------------------------------------
"ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል። ጻድቅን በጻድቅስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።" (ማቴ. 10:41)

<<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን>>>

      #ስንክሳር_ዘወርሃ_ጥቅምት

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

24 Oct, 03:50


"መጥፎ ቀን እና ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም። ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።"


       
#ቅዱስ_ቄርሎስ_ሣድሳዊ


🥰ሰናይ ሐሙስ ይሁንላችሁ🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

22 Oct, 05:04


ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔጋር ነው(2)

የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

21 Oct, 16:34


የተዋህዶ ልጅ ሆይ ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህ የዳኑባት ጠባቧ የድህነት መንገድ ይህች ናትና እባክህ እንዲሁ ከላይ ሳይሆን ከልብ በሆነ ማስተዋል ጥልቅ በሆነ ተመስጦ አንብበህ ራስህን ትገዛበት ዘንድ ከልብህ ጻፈው!!

እ ን ዲ ህ   በ ላ ት   ነ ፍ ስ ህ ን.....

              ነፍሴ ሆይ!!

ለአምላክ መጸለይን ትሰንፊያለሽ? ለኩራትሽ በተለየ ሽቱ ሰውነትሽን ማንጻት እስከ መቼ ድረስ ጠቃሚ ነገር አድርገሽ ትወጅዋለሽ። ነፍስ ሆይ ከአንቺ የተነሣ ወዮልኝ። ተጋድሎና ቸርነት የለሽምና አንቺ አስቸጋሪ ነፍስ ሆይ ቀንሽ አስቀድሞ ሳያልፍ ዛሬ ንቂ። ከቸርነቱ ጣዕም የተነሣ ይቅርታን ተቀበይና በቅን ልቡና እና በለቅሶ ወደ ንሐሰ ፈጥነሽ ተመለሺ። ዛሬውኑ ተመለሺና እግዚአብሔርን ፍሪው። 

አንቺ መሬት ነሽና ወደ መሬትም ትመለሻለሽ የቤትሽን እወቂ። ብርሃንን ከማየት የተነሣ ዓይኖችሽ እንዲዘጉ እወቂ። ጆሮችሽም እንደሚደነቁሩና እንደማይሰሙ አስቢ። ምላስሽ እንደሚቆለፉ ጉሮሮሽ እንደሚዘጋ ዓይንሽ እንደማይገለጥ እወቂ። እጆችሽ እንደሚቆረጡ እንደሚነሱሽና እንደማይሰጡሽ (እንደማያቀብሉሽ) አስቢ። ለዘለአለም እግሮችሽ እንደሚደክሙና እንደማይሄዱ አስቢ። 

ወደ ንሰሐ ፈጥነሽ አትሮጪምን አንቺ ጎስቋላ ነፍሴ ሆይ ወዮልኝ። በከንቱ ሥራ ሁሉ የደከምሽ እና የተጨነቅሽ አስቸጋሪ ነፍስ ሆይ በበደልና በኃጢአት የሰበሰብሽብው ገንዘብ ወዴት አለ። የጣፈጠው ምግብና የወይን ጠጅሽ ወዴት አለ። ከልጅና ከዘመድ ጋር ጨዋታው እና ደስታው ወዴት አለ። በመታጠብ መንጻት የሚያስደስቱት ሽቶዎች ወዴት አሉ። በወርቅና በብር በዕንቍ ቤትን ማሳመር ወዴት አለ። በተክል ቦታ መደሰትና በሚጠፋ ክብር መጫን ወዴት አለ። 

ነፍሴ ሆይ የዘመንሽ ቅሬታ ትንሽ ስለሆነ ፈጥነሽ ወደ ንሰሐ እሩጭና ይህ ቀን ሳለ የይቅርታ ልብስሽን ልበሺ። 


                #ዜና_አበው

    ደስ የሚል ምሽት ተመኘሁላችሁ🥰🥰

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

20 Oct, 13:41


“ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”

               #አባ_እንጦንስ

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

18 Oct, 17:19


🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet 
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/2/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቋወ ድንግል(ሌላ)
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ
@EOTCmahlet
መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ  በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
@EOTCmahlet
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/

https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

16 Oct, 18:16


😭ደሴ አድባሯን አጣች 😭

ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

በ1921 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ተጉለት ወርቅጉር አካባቢ የተወለዱት አባ መፍቀሬ ሰብዕ በ96 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።

አባቴ ነፍሶት በሰላም ትረፍ 🙏🙏🙏

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

12 Oct, 20:47


🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ስርዓተ ማህሌት ዘካልዕ ጽጌ በዓለ በዓታ ለማርያም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡
@EOTCmahlet

ማኅሌተ ፅጌ፦
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወቦ ዘይቤ ዚቅ
ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ

መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111

12,652

subscribers

377

photos

3

videos