ጌታዬ ሁለመናዬ! @yarieddessale Channel on Telegram

ጌታዬ ሁለመናዬ!

@yarieddessale


ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ስለመላዕክት፣ ስለቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ተዓምራት፤ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን ወቅታዊ ትምህርቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞችን ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ጌታዬ ሁለመናዬ! (Amharic)

ጌታዬ ሁለመናዬ! ይህ አንዲስ ቅድስት ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን እና እንዲሁም ቅድስት ድንግል ማርያም ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ ማህበረሰብን እንከብራለን፡፡ በአስቀድሞቹ ተናጋሪ ትምህርቶች፣ መንፈሳዊ ፊልሞች እና ታሪኩዎች ከቀላሉ እንዲያገኙ እንጠቀማለን፡፡ ይህ በድምጽና በጥምጣም ከሚመካከሩበት ጽሑፍ መማመር እንደሚችሉ ጌታዬ ሁለመናዬ ለእግዚአብሔር የሚሰላለውን ምሕረት አስቀድመህ ይባላል፡፡

ጌታዬ ሁለመናዬ!

09 Nov, 03:29


"በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤
ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።"
(ዮሐ 16: 33)

https://t.me/YariedDessale

ጌታዬ ሁለመናዬ!

07 Nov, 15:09


"እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው።" (ናሆ 1:3)

ጌታዬ ሁለመናዬ!

06 Nov, 14:19


👑ሹመተ ጵጵስና👑

ዛሬ ከቫቲካን በተገኘ መረጃ፡
የማኅበረ ኮንቦኒ የዓለም አለቃ የሆኑት ክቡር አባ ተስፋዬ ታደሰ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ ሆነው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተመርጠዋል። እንኳን ደስ አለን!
https://press.vatican.va/content/salastampa/en/bollettino/pubblico/2024/11/06/241106b.html

Via ወንድም ሰናይ መስፍን


#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6802

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

05 Nov, 08:44


“ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።”
— መዝሙር 113፥2

ጌታዬ ሁለመናዬ!

01 Nov, 15:40


“…ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤
ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤”
(ምሳ 23፥17 )

ጌታዬ ሁለመናዬ!

01 Nov, 03:00


" አብሮ መጸለይ ስጦታ ነው።"
    
   (ፓፓ )

https://t.me/YariedDessale/6798

ጌታዬ ሁለመናዬ!

30 Oct, 12:08


I need You, Lord Jesus Christ.


https://t.me/YariedDessale/6797

ጌታዬ ሁለመናዬ!

30 Oct, 02:52


“የክርስቲያን ተስፋ ዘላቂ መሆን ያስፈልጋል።”

( ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ )

ጌታዬ ሁለመናዬ!

28 Oct, 13:45


“…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።”
(መዝ. 113፥3 )

https://t.me/YariedDessale/6795

ጌታዬ ሁለመናዬ!

27 Oct, 05:59


#ፀጋ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው
#ጸጋ ማለት በሌላ አገላለጽ ከእግዚአብሔር ሕይወት መሳተፍ ማለት ነው፡፡/ቁ.1997/፡፡

🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

የጸጋ ሙላት/ጸጋን ተሞላሽ/ሉቃ. 1፡ 28/

🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#በቅዱስ_መጽሐፋችንና እንደ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ፥

#ፀጋ ማለት በጌታ ፊት የተሰጠን ሞገስ፤ የእግዚአብሔር ነጻና የማይገባ ስጦታና እርዳታ ለተጠራንበት ጥሪ ምላሽ መስጠት የሚያስችለን ማለትም የእርሱ ልጆች ለመሆን፤ የመለኮታዊ ሕይወትና ዘላለማዊ ሕይወት ለመውረስ የተጠራነውን ጥሪ  ተካፋዮች ለመሆን የሚያስችለን ነው፡፡/ት.ክ.ቁ 1996/

#ፀጋ ማለት በሌላ አገላለጽ ከእግዚአብሔር ሕይወት መሳተፍ ማለት ነው፡፡/ቁ.1997/፡፡

እንግዲህ ፀጋ የይገባኛል ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ መሆኑን በታላቅ ትህትና ታስተምራለች፡፡ የእግዚአብሐየር ስጦታ ነው ስንል በተሰጠን ፀጋ ማትረፍ ደግሞ የኛ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡

#ቅዱሳን በምድራዊ ሕይወታቸው በተሰጣቸው ፀጋ በማትረፍ ሰማያዊ አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡ ብዙዎች ፀጋን ተቀብለው ሕይወትን አግኝተዋል፡፡ "በዚህ ፀጋ ጸንታችሁ ቁሙ'1 ጴጥ. 5፡12/፤
👑

"ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ፀጋ እንዳይጎድልበት…'ዕብ.12፡15 የሚል መመሪያን ተቀብለናል፡፡ "ፀጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን 72 ጢሞ. 1፡9/ እንዲሁም በቃሉ እንደምናገኘው የፀጋ ሙላት #ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡/ዮሐ. 1፡16/ ከዚህ የፀጋ ሙላት ነው እኛ በፀጋ ላይ ፀጋ የተቀበልነው፡፡

#የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የፀጋ ሕይወት ስንመለከት ፀጋን መቀበል ብቻ ሳይሆን "አንቺ ፀጋ የተሞላሽ'/ሉቃ. 1፡28/ የሚል ድንቅ ሰላምታ ነው የቀረበላተ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል እንደምናገኘው የፀጋ ሙላት እራሱ ልጇ በፀጋ ሞላት፤ ለፀጋ ባለቤት ማደሪያ ትሆን ዘንድ፡፡ ይህ የፀጋ ሙላት ቅዱሳን እንደተቀበሉት ብቻ አይደለም ምክንያቱም የእርሷ በፀጋ መሞላት እጅጉን ልዩ ነው፡፡ ያ የተሞላችው ፀጋ የጌታ እናት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ስለዚህም የጌታ እናት የሚያደርጋት ፀጋ ስለኛ ትማልድ ዘንድ ሞገስ ሆኗታል፡፡ 


#እንደማጠቃለያ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምልጃዋ የሚመነጨው ከቅድስት ሥላሴ፤ የጌታ እናት ከመሆኗ እና በተሞላችው ፀጋ ነው፡፡ 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

(አስተምህሮ:- በክቡር አባ ዓብዮት ክብረት)

አዘጋጅና አቅራቢ: ያሬድ ደሳለ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6793

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

25 Oct, 11:36


Immaculate Heart of Mary,
Pray for us and the whole world. Amen!!


https://t.me/YariedDessale

ጌታዬ ሁለመናዬ!

24 Oct, 14:22


"የጌታዬ እናት" (ሉቃ. 1፡43)
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#የአምላክ_እናት /Theotokos/    

🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾
        
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ሆና በመገኘቷ እግዚአብሔር እራሱ ወልድን ትወልድ ዘንድ መረጣት፤ #ድንግል_ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች የተባለው ትንቢት ቃል ይፈጸም ዘንድ ሰዓቱ በደረሰ ጊዜ አምላክን ጸንሳ ወለደች፡፡ #ኤልሳቤጥም በታላቅ መንፈስ ተሞልታ "የጌታዬ እናት'/ሉቃ. 1፡43/ ብላ የጌታ እናት መሆኗን አወጀች፡፡

ለሰው ልጆች ሁሉ ከተሰጠ ስጦታ ሁሉ ለማርያም የተሰጠው ስጦታ ድንቅ ሆኖ ተገኘ፡፡ "ታላቅ ነገር አድርጎልኛል'/ሉቃ. 1፡ 49/ በእርሷ የተከናወነው የእግዚአብሔር ስራ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይላት ዘንድ መደላድል ሆነ፡፡

🌹👑🌹🌱🌻🌱🌱🌹🌱

ከፍጥረተ አዳም እስከ ልደተ ክርስቶስ የአምላክ እናት ለመሆንና የአለም ሁሉ ቤዛ የሆነውን አማኑኤልን ለመታቀፍ የበቃ #ከእመቤታችን ድንግል ማርያም #በስተቀር ማንም አልተገኘም፡፡

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱


እዚህ ጋር #ስለአማላጅነቷ ስናወራ ከዚያ የበለጠውን ስጦታ ማለትም የጌታ፤ የአምላክ እናት መሆኗን መዘንጋት ተገቢ አይደለም፡፡ የጌታዬ እናት ከመባልና ከመሆን የበለጠ አንዳች ነገር የለም፡፡ በቃና ሰርግ ላይ ወይን እኮ አልቋቸዋል ብላ ብቻ አላቆመችም ወደ ሰርገኞቹ ሄዳ አድራጊ ፈጣሪነቱን፤ የታምራት ባለቤትነቱንና ክብሩን በሚገልጽ መልኩ እርሱ የሚላችሁን አድርጉ አለቻቸው፡፡

የእናትችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በልጇ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላት ጥልቅ እምነት ማሳያ ነው፡፡ 

የእናታችን አማላጅነት ከሁላችንም ጋር ይሁን

. . . . ይቀጥላል።

( #አስተምህሮ:- በክቡር አባ ዓብዮት ክብረት)

#አዘጋጅና_አቅራቢ: ያሬድ ደሳለ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6791

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

23 Oct, 18:44


“ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።”
  — ምሳሌ 13፥14

https://t.me/YariedDessale

ጌታዬ ሁለመናዬ!

23 Oct, 17:45


“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።”
— ያዕቆብ 4፥8

ጌታዬ ሁለመናዬ!

22 Oct, 11:15


"እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የታደልሽ ነሽ" (ሉቃ. 1፡ 45)
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#ቅድስት_ሥላሴ  #በማርያም ሕይወት

🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

በቅዱስ መጽሐፍ ከዘፍጥረት አንስተን እስከ ዮሐንስ ራዕይ ስንመለከት ቅድስት ሥላሴን በሙላት የተቀበለና ማደሪያ የሆነ የተገኘ እንደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡

#በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ አባታችን አብርሃም የተቀበላቸውን ሦስቱን ሽማግሌዎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ማሳያ አድርገው አስተምረው አልፈዋል፡፡ "የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰዎች መካከል ነው'/ራእይ 21፡3/ ይላል ቃሉ። እመቤታችን በሰዎች መካከል የሚያድረው በስጋዋ አደረ፡፡ የታላቁ የቅድሰድት ስላሴ ማደሪያ ሆና በፍጥረት መካከል ተገኘች፡፡ "የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ' መዝ. 26፡ 8 


#በሉቃስ ወንጌል በአንደኛው ምዕራፍ ላይ እንደምናገኘው ሊቀ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ የምስራቹን ቃል ሊያበስራት ወደ እርሷ በመጣ ጊዜ በመላእኩ ቃል ውስጥ ቅድስት ሥላሴ እንዴት በማርያም ሕይወት ውስጥ እንደታየ መረዳት ልበ ደንዳና ካልሆኑ በስተቀር ለማንም አይከብድም፡፡ የማርያም ቅድስት ሥላሴን በምን መልኩ እንደተቀበለች ቃል በቃል ከወንጌል ወስደን እናስቀምጠው፡፡

🌱👑
1) እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፡፡/ሉቃ. 1፡28. 

ለብዙ ቅዱሳንና ለእስራኤል እራሱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነኝ ብሎ ሲናገር አብሯቸውም ሲሆን አይተናል፡፡ የእመቤታችን ለየት የሚያደርገው ከዚህ ቀደም በመላእክቱ፤ በነብያቱና በቅዱሳን ለሌሎች በተናገረው መለኩ ሳይሆነ እጅጉን ረቂቅና ልዩ በሆነ አሰራሩ ነው፡፡ ይህም የወልደ እግዚአብሔር ማረፊያ ናትና፤ ወልደ አምላክን ትወለዳለችና፤ አማኑኤልን ትወልዳለችና እግዚአብሔር ለማዳኑ ስራ ከእርስዋ ጋር ሆነ፡፡ ሊያዘጋጃትና ተልዕኮውን ሊፈጽምባት፡፡ እግዚአብሔር በእውነትም ከእርስዋ ጋር ነው፡፡  


🌱👑
2)  መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል/ሉቃ. 1፡ 35/

እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን በእያንዳንዳችን ላይ ያሳርፋል፤ እኛ እንደቃሉ መሰረት የቅዱሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ መቅደስ ነው/1 ቆሮ. 6፡ 19/ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ…ኤፌ. 2፡ 22/፡፡ ሰው ሕይወቱን በቅድስና ሲመራ አምላኩን ደስ የሚያሰኝ ለራሱም ቅድስና ለሌሎችም ደህንነትን የሚያስገኝ ሕይወት ሲኖር መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ፍሬ ያፈራል፡፡/ገላ. 5፡ 22/ ይህም የመንፈስ ፍሬ ከሰው ጋር በፍቅር፤ በሰላም፤ በትዕግስት፤ በበጎጎት፤ በቸርነትና በገርነት እንዲኖር ለአምላኩ ታማኝ እራሱን የሚገዛ እንዲሆን ኃይል ይሰጠዋል፡፡ ይህ አንዱ መንፈስ በእመቤታችን ሕይወት ላይ ያፈራው በማህጸኗ ያደረው ፍሬ፤ ሕይወት የሚሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱሰ ስራ በእርሷ ሕይወት እጅጉን ልዩና በማንም ላይ የማይደገም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሆነ ነው፡፡       


🌱👑
3) …ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ/ሉቃ. 1፡ 31-33/ 

ታላቁ የአምላክ ስጦታ ሰውን ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ከሰማያዊ ዙፋኑ ወርዶ በታላቅ ትህትና የሰው ስጋን ለበሰ፡፡ ከትውልድ ሁሉ የተለችውና የተመረጠችው ለልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡    
እግዚአብሔር አስቀድሞ የሚወስን አምላክ ነውና ወስኗት ከሴቶች ሁሉ እጅጉን ብርክት ሆና በመገኘቷ ጊዜው በደረሰ ጊዜ በፊቱ #ሞገስን አግኝታለችና ጠራት፡፡

#የእርሷ_መጠራት ጌታ ለቅዱሳኑ ለአብርሃምና ለዳዊት የገባውን ኪዳን ይፈጽም ዘንድ አብ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ሆኖ፤ ወልደ እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በማህጸኗ እንዲጸነስ በማድረግ አከበራት፡፡

#በአብ ዘንድ ሞገስን ያገኘች፤ ወልድን ጸንሳ የወለደች፤ መንፈስ ቅዱስን በሙላት የተቀበለች፤ ማዕደረ ሥላሴ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአማላጅነቷ ምንጭ እራሱ በእርሷ ላይ ያለው ቅድሰት ሥላሴ ነው፡፡ 

#የልጇን_አስተምህሮ ቀድማ የኖረች/እኔ የዋህና ትሁት ነኝ ከእኔ ተማሩ…/ማቴ. 11፡ 29/ ይኼ ሁሉ ድንቅ ነገር በሕይወቷ ሲከናወን "እግዚአብሔር #እኔን_ዝቅተኛይቱን_አገልጋይ ተመልክቷልና…'//ሉቃ. 1፡ 48/ በማለት መልካም መአዛ እንዳለው ሽቱ አምላኳን በትህትናዋ ማረከች፡፡ ቅድስናዋንና ጽድቋን በተግባር አሳየች፡፡ የተላበሰችው ጽድቅ ኢየሱስን እስክትወልድ ብቻ አይደለም ይልቁንስ የሕይወቷ አካል ነው፡፡ ጽድቅ ደግሞ በጌታ ፊት ሞገስ ታሰጣለች፡፡ በጻድቃን ይደሰታልና፡፡ ስለዚህም "የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው'/ያዕ. 5፡ 16/፤ "የጻድቃንን ጸሎት ይሰማል'/ምሳሌ 15፡ 29/፡፡

#የእመቤታችን_ምለጃ የሕይወቷ ሁሉ ድምር ውጤት ነው፡፡ ቃሉን በማመንና በመቀበል የተመሰገነች፤ "እንደቃልህ ይሁንልኝ'/ሉቃ. 1፡ 38/ ያለች፤ ሳታመነታ የማይቻለው እንደሚቻል/ሉቃ. 1፡37/ የማይሆነው እነደሚሆን አመነች "እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የታደልሽ ነሽ'/ሉቃ. 1፡ 45/፡፡

#ጽድቋን በሕይወቷ በተግባር በማሳየት የጽድቅ አክሊልን የደፋች እናት፡፡ ምልጃዋ ከጽድቅ ሕይወቷ የሚመነጭ መንፈሳዊ ምንጭ ነው፡፡ #በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝታለች፡፡ ይህ ሞገስ ሞገስ የእመቤታችን ምልጃ ነው፡፡ 

#ቅዱስን_መላእክት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ናቸው፤ ቅዱሳን ደግሞ በፊቱ ሊያቆማቸው የሚችለውን የጽድቅ ስራ ለመስራት ይታገላሉ፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን መላእክት የሚሰግዱለትን ቅዱሳን የሚያመልኩትን ቅድስት ሥላሴን ተቀበለች፡፡ ሞገስና አግኝታለችና፡፡ ስለዚህም ከምልጃ በላይ የሆነ ስጦታ የተቀበለች እመቤታችን ለቅድስት ስላሴ ማረፊያ ሆናለች፡፡

#እንኳንስ_ማማለድ ይቅርና የሥላሴ ማደሪያ ሆናለች፡፡  በአመክንዮ እንኳን ብንረዳው ቅድስት ስላሴን በተግባር በስጋዋና በሕይወቷ ያስተናገደች እናት ምልጃዋ በዚህ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡
. . . . ይቀጥላል።

(አስተምህሮ:- በክቡር አባ ዓብዮት ክብረት)

አዘጋጅና አቅራቢ: ያሬድ ደሳለ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6788

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

21 Oct, 12:15


May Almighty God have mercy on us, forgive us our sins, and bring us to everlasting life.

Amen

ጌታዬ ሁለመናዬ!

21 Oct, 12:13


"May all the powerful Angels and Saints of God keep you safe from evil and eternal destruction." Amen🙏

ጌታዬ ሁለመናዬ!

20 Oct, 07:41


Father, may your will be done on earth and in my life.

Amen

ጌታዬ ሁለመናዬ!

18 Oct, 13:25


ከተወዳጁ አገልጋይ #ከዘማሪ #አሸናፊ_ደበላ የተላለፈ:


ሁላችሁንም ሰላም ብያለሁ። እንኳን እግዚአብሔር በሰላም አገናኘን። እንደ ቃሉ አብረን እየሠራን እንታነጻለን።
ከሚዲያው፥ በተሳትፎ ድራሼ ከመጥፋቱ አንጻር (በበቂ ምክንያት ቢሆንም) 'አፖሳሰት'... crazy ሆኖብኛል ... ታገሱኝ። ቀስ በቀስ ..። እስኪ ለማንኛውም አዲስ የ YouTube ቻናል በዚህ ሁለት ሦስት ቀን ውስጥ ከፍቻለሁ። ቻናሉን በዚህ ሊንክ እየገባችሁ Subscribe አድርጉት (በአክብሮት) አመሰግናለሁ። ተባረኩ!!

👇👇👇👇

https://youtu.be/Q7GeWtPOEtA?si=2ADPhAE2524XX2OV


👆👆👆👆👆👆

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6783

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

16 Oct, 18:25


የእርሷ ዘር የአንተን እራስ ይቀጠቅጣል'/ዘፍ. 3፡ 15/

🌹🌱🕊🌱🌾🕊🌹🌹🌱🕊🌱

 የፍጥረታት ሁሉ ገዢ፤ ጌታ፤ ፈጣሪና ባለቤት የሆነው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ፍጥረታትን በድንቅ አሰራሩ ሲፈጥር በሰማይ በራሪ አህዋፍ፤ በባህር ተምዘግዛጊ የውሃ ላይ ፍጥረታት እንዲሁም በምድር ተራማጅ ሆነው በተሰጣቸው የኑሮ ስጦታ ይኖሩ ዘንድ በቃሉ ተፈሩ፡፤ እግዚአብሔር የፈጠራቸው እነዚህ ሁሉ ፍጥረታት የእግዚአብሔርን ክብር የሚያውጁ የእርሱ የክብሩ ነጸብራቅና መገለጫ ናቸው፡፡ ፍጥረታትን አይተን ስሙን አሰራሩን እናከበራለንና፡፡ ”ፍጥረታት ይናገሩ“ ብለን በዝማሬ ስሙን እንደምንወድስ ሁሉ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ከፍ አድርጎ የሰውን ልጅ የፍጥረታት ሁሉ የበላይ ይሆን ዘንድ መርጦ ሾሞታል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ በአፈጣጠሩ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሕይወትና ክብር ተካፋይ ይሆን ዘንድ በአሰራሩም በአፈጣጠሩም ልዩ እንዲሆን ፈቀደ፡፡ 


የሰው ልጅ ገና ከጅማሬው መለኮታዊነቱንና በውስጡ ፈጣሪ ያኖረውን መለኮታዊ ክብርንና ሕይወትን የመካፈል ጥሪ ወደ ጎን በመተው ከአፈር ተሰርቷልና አፈርነትን ወደደ፡፡ መለኮትን በተሰራበት አፈር፤ ክበሩን በውርደት፤ ፈጣሪን በፍጡር፤ ሕይወትን በሞት፤ መታዘዝን በትዕቢት፤ ቅድስናን በኃጢአት፤ ገነትን በገሃነም ለወጠ፡፡

ዋጋውም ሞት ሆነ/ሮሜ. 6፡23/፤ ደስታው ወደ ሃዘን፤ መለኮታዊ አልባሱ በቅጠል፤ ክብሩ በነውር ይቀየር ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ ታላቅ ቡራኬን ከተቀበለበት የፈጣሪ አንደበት/ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሉ፤ በፍጥረት ላይ ሁሉ ሥልጣን ይኑራችሁ፡፡ ዘፍ. 1፡ 28/ እርግማንን ተቀበለ/ዘፍ. 3፡ 16-19/ የሰው ልጅ የሞት፤ ኃጢአትና የመከራ ጉዞ ከዚህ ሲጀምር ምህረቱ እጅግ ወሰን የሌለው የእግዚአብሔር የማዳን ጉዞ ከዚሁ ይጀምራል፡፡ የሰው ልጅ ጠፍቶ ወይም ሞቶ እግዚአብሔር አይሻምና፡፡/ሉቃ. 15፡ 24/ ለክብሩ ፈጥሮታልና አዳም ወደ ቀድሞ ክብሩ ይመለስ ዘንድ የደህንነት ጉዞ ይጀምራል፡፡ በእባብ ለተመሰለው ሰይጣን እግዚአብሔር "የእርሷ ዘር የአንተን እራስ ይቀጠቅጣል'/ዘፍ. 3፡ 15/አለው፡፡ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች/ ኢሳ. 7፡ 14/ እንዲሁም የዚህ ቃል ሙላት በአዲስ ኪዳን በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ገላ. 4፡ 4 ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን/የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን… ልጁን ላከ/፡፡ በሰው ልጅ የደህንነት ታሪክ ጉዞ ውስጥ በእግዚአብሔር ምርጫና ፈቃድ የእመቤታችንን መጠራትና ስፍራዋን እናስተውል ዘንድ አስፈላጊ ነው። 

ይቀጥላል....


#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6783

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

16 Oct, 04:48


“ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ።”

— መዝሙር 35፥18

ጌታዬ ሁለመናዬ!

13 Oct, 04:22


"⁴⁶ #ማርያምም እንዲህ አለች፦
⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤" (ሉቃስ 1)

ጌታዬ ሁለመናዬ!

10 Oct, 16:30


“ #ኢየሱስም፦
ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”

ዮሐንስ 11፥25

ጌታዬ ሁለመናዬ!

09 Oct, 07:51


"  ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?"
(1 ዮሐ 4: 20)

https://t.me/YariedDessale

ጌታዬ ሁለመናዬ!

09 Oct, 04:33


🌹👑 #የመጽሐፍ_ምረቃ_ጥሪ 👑🌹

ለረዥም ጊዜ ስናዘጋጀው የነበረው "የሉቃስ ወንጌል ማብራሪያና አስተንትኖ" በእግዚአብሔር ፈቃድ አሁን ስለተጠናቀቀ ለምርቃቱ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

- ቀን፦ እሑድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8:30

- ቦታ፦ ለገሐር በሚገኘው የመድኃኔዓለም ካቶሊካዊት ቤ/ክ ግቢ በሚገኘው አዳራሽ ይሆናል።

በዕለቱ በፊሶን ዘማርያን የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ዝማሬዎችና መነባነብ ይቀርባሉ።

ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርት ተምራችሁ እንዲሁም በዝማሬዎች መንፈሳችሁ አንጻችሁ ትመለሳላችሁ።

እሑድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ላይ ለገሐር መድኃኔዓለም ግቢ እንገናኝ።

ይህንን ሥራ ለማጠናቀቅ ብዙ ዓመታት ፈጅቶአል። በዚህ ሒደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የረዳችሁኝ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ እላለሁኝ።
የተባረከና የተቀደሰ ጊዜ ይሁንልን፤ አሜን።

ክቡር አባ ምስራቅ ጥዩ (ዶ/ር)


#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6778

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

08 Oct, 21:50


🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#የጋብቻ_ሕይወትና የማይቀየረው እውነታ።

(በክቡር አባ ምሥራቅ ጥዩ (ዶ/ር))
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

     የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፤ እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ የተወገዘ ነው(ዘፍ 19)፤ ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች በሥጋቸው ቅጣት ይቀበላሉ(ሮሜ 1፡27)፤ የእግዚአብሔር መንግሥት አይወርሱም(1ቆሮ 6፡9-10)። 
    

ሌላው ደግሞ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለቤተሰብ ሕይወት ትልቅ ክብር አላት፤ ቤተሰብ ደግሞ በቅድስት ቤተሰብ ማለትም በኢየሱስ፣ በማርያምና በዮሴፍ የተመሰለ ነው። በተጨማሪም የቤተሰብ ሕይወት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን ጥምረትና አንድነት የተመሰለ ነው(ኤፌ 5፡23-31)። ይህ ክቡርና ቅዱስ ምሥጢር ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር ነው፤ ማንም ስላራገበው ወይም ብዙ የሜዲያ ግርግር ስለፈጠረ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ቤተ ክርስቲያን እውነትን ይዛ ጉዞዋን ትቀጥላለች።

     #ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል የቃል ኪዳን ሕይወት ነው። የወንድና ሴት ቃል ኪዳን የሚደረገውም ከእግዚአብሔር ጋር ነው። እግዚአብሔር የወንድና የሴት ጥምረት (የትዳር ሕይወት) ገና ከፍጥረት ታሪክ ጀምሮ ባርኮታል(ዘፍ 1፡27)፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ገሊላ ውስጥ ቃና በተባለው መንደር ተገኝቶ ጋብቻን ባርኮታል(ዮሐ 2)። በተጋቡት ወንድና ሴት አማካይነት የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ይንጸባረቃል፤ ጥንዶቹም የፍቅር ማደሪያ ሆነው ይመሰክራሉ። 

      ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቅዱስ ቃል ታስተምረዋለች፤ ትኖረዋለች። በተጨማሪም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስና በሕገ ቀኖና ውስጥ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ አርቅቃ አስፍራዋለች። ስለዚህ የሚቀየር እውነታ የለም፤ ፈጽሞ አይኖርም። ቤተ ክርስቲያን ይህንን እውነታ ይዛ ጉዞዋን እስከ የክርስቶስ ወደዚህች ዓለም ዳግመኛ ተመልሶ መምጣት ድረስ ትቀጥላለች። ሐዋርያው ጳውሎስ “እውነትን በፍቅር እየተናገርን ራስ የሆነውን ክርስቶስ ለመምሰል በሁሉ ነገር እናድጋለን” እንዳለው ሁሉ(ኤፌ 4፡15) ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም እውነትን በፍቅር እያስተማረች ጉዞዋን ትቀጥላለች።

   #በአጠቃላይ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚለወጥ እውነታ የለም፤ ከክርስቶስ የተቀበለችውን እውነታ ትኖረዋለች፤ ለቀጣዩ ትውልድ ምንም ሳይሸራረፍ ታስተላልፈዋለች፤ ሰዎች ይህንን እውነታ መረዳት እንዲችሉ በየጊዜው በተለያየ መንገድ ታስተምራለች። 


#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6774

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

08 Oct, 01:22


My Catholic Faith

"Through him, and with him, and in him, O God, almighty Father, in the unity of the Holy Spirit, all glory and honour is yours, for ever and ever. Amen. "

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6773

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

06 Oct, 22:32


🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#ተመሳሳይ_ፆታ #ጋብቻና የማይቀየረው እውነታ።

(በክቡር አባ ምሥራቅ ጥዩ (ዶ/ር))
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾


          በቅርብ ጊዜያት በብዙዎች ዘንድ ከሚናፈሱት የተዛቡ ወሬዎች መካከል አንዱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን እንዲደረግ ልትፈቅድ ነው፤ ተመሳሳይ ፆታ ሆነው የተጋቡት በጉዲፈቻ መልክ ልጅ እንዲያሳድጉ የሚፈቅድላቸውን ሕግ ልትቀበል ነው የሚሉትና ተመሳሳይነት ያላቸው አስተያየቶች በማኅበራዊ ሜዲያ በኩል ሲነገርና ሲራገብ እየሰማን ነው። አንዳንድ ዜና ማሰራጫዎች ደግሞ የሕዝቡን ትኩረት ለመሳብና ብዙ ተመልካች ለማፍራት በማለት ይህንን አጀንዳ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለውይይት እንደቀረበ አድርገው ሲነዙት ነበር።

       በእርግጥ የዚህ ወሬ ሁሉ አንዱ ምክንያት የሆነው እ.አ.አ. በ2023 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮ ተፈርሞ የወጣው “Fiducia supplicans” የሚለው ሐዋርያው መልእክት ነው፡፡ መልእክቱም የተመሳሳይ ፆታ ጥምረት ሕይወት ውስጥ ያሉ ጥንዶች ወደ ካህናት ዘንድ ቀርበው “አባቴ ሆይ! ይባርኩኝ (ይባርኩን)” በማለት ቢጠይቁ ካህናት እንዲባርኩአቸው የሚፈቅድ ወይም የሚያበረታታ ወይም የሚመክር መልእክት ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሐዋርያዊ መልእክት ብዙ አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሎአል፤ ብዙ አገራትም በግልጽ ተቃውመውታል፤ ነቅፈውታል፤ ተችተውታል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የአፍሪካ ጳጳሳት ጠንከር ባለ መልኩ ምላሽና አስተያየት ሰጥተውበታል፤ ከሰጡትም አስተያየትና ትችት መካከል የተወሰኑትን እንዲህ ይጠቀሳሉ፡፡

በፊት ከአረማዊነት (ከአሕዛብነት) ሕይወት ወደ ክርስትና ጉዞ ይደረግ ነበር፤ አሁን ግን ይህ መልእክት እንደሚያሳየው ከሆነ ከክርስትና ወደ አረማዊነት (አሕዛብነት) እንደመጓዝ ነው፡፡
ምዕራባውያንን ታሳቢ በማድረግ ይህ መልእክት ከተነገረ ጥሩ ነው፤ ግን ደግሞ አፍሪካውያንን ታስቦ ደግሞ ከአንድ ሚስት በላይ የሚፈቅደውን ሕግ ይጽደቅልንና ለሕዝባችን እናስተምር፡፡
ይህ ሐዋርያዊ መልእክት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአብሮነት ጉዞ (ሲኖዳሊቲን) አያበረታታም፤ እንዲያውም ኅብረትና አንድነትን የሚቃወም ነው፡፡
  
  በእርግጥ ይህ ሐዋርያዊ መልእክት ስለ ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ አይናገርም፤ ተክሊል ፈጽሙላቸው አይልም፤ ወይም ጋብቻ በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚፈጸመውን ቅዱስ ተግባር መሆኑን የሚሸረሽር አሳብ የለውም፡፡ ሆኖም ግን የብዙ አገራት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታን በመጥቀስ እየሞገቱት ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮ በተለያየ ጊዜ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተገድደዋል።   
       ሐዋርያዊ መልእክቱ ስለ ቡራኬ በሚያወራበት ደረጃ እንኳ ይህን ያክል ሙግትና ተቃውም ከተነሣ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቢወራ በቤተ ክርስቲያን ላይ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መረዳቱ አያዳግትም፡፡ ሆኖም ግን ሰዎች ይህንን መነሻ በማድረግ በተዛባ መልኩ ስለ ተመሳይ ፆታ ጋብቻ ስለመፈቀዱ በተሳሳተ መልኩ ያወራሉ፡፡ 

        በእርግጥ ሰዎች የሚያወሩትና ይህንን ወሬ በተለያየ መንገድ በመጀመሪያ ስለ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ የቆመችበትና የታነጸችበት መሠረትና የያዘችውን እውነታ ያልተረዱ ናቸው። አንዳንዶች ደግሞ ይህ ነገር የራሳቸውን ምኞትና ፍላጎት ስለሆነ ምኞታቸውን እንዲፈጸም በማለት ብዙዎችን እየቀሰቀሱ የሚያስወሩት ከንቱ ወሬ ነው። ሌሎች ደግሞ ሆን ብለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ስምና ክብር ዝቅ ለማድረግና ለማዋረድ የሚሠሩት የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው።
. .  .   ይቀጥላል።

ዋና ዓላማችን፦ ክርስትናን ክርስቶስን እንወቅ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6772

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

06 Oct, 05:42


“አምላካችንስ የደኅንነት አምላክ ነው፤
ከሞት መውጣትም ከእግዚአብሔር ነው።”
— መዝሙር 68፥20

ጌታዬ ሁለመናዬ!

05 Oct, 16:58


🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#ሰው_ሠራሽ የወሊድ #መቆጣጠሪያና የማይቀየረው እውነታ።

(በክቡር አባ ምሥራቅ ጥዩ (ዶ/ር))
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾


      እ.አ.አ. በሐምሌ 1968 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ስለ ሰው ሠራሽ የወሊድ መቆጣጠሪያና ተያያዥነት ስላላቸው የሥነ ምግባር ሕይወት በተመለከተ አንድ ትልቅ የክፍለ ዘመኑ ሐዋርያዊ መልእክት አስተላልፈዋል። የዚህ ሐዋርያዊ መልእክት ሰነድ መጠሪያ ስሙ “Humanae Vitae” ትርጓሜውም “ስለ የሰው ልጅ ሕይወት” ወይም “ለሰው ልጅ ሕይወት” የሚል ነው። 
     ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ይህንን ሐዋርያው መልእክት ወይም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሲያዘጋጁት ብዙ ክርክርና አስተያየት ከሕዝቡ፣ ከተለያዩ ሊቃውንትና ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኩል ቀርቦ ነበር። አስተያየቱም “ይህ ሐዋርያዊ መልእክት ከታወጀ ብዙ ምእመናን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ትተው ወደ ሌላ እምነት ይሄዳሉ፤ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ መንጋ ታጣለች” የሚል ነበር። ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ለዚህ አስተያየት ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል፤ “እውነት አትለወጥም፤ በምንም መልኩ አትቀየረም፤ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልኩት እውነታ ሳይሸራረፍ ለመጪው ትውልድ አስተላልፈዋለሁ፤ በዚህ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የሚርቅ ካለ የራሱ ውሳኔ ነው፤ እኔ ግን “ሕዝቡ ወደ ሌላ እምነት ሊሄድ ነው” በማለት እውነታውን አልሸራርፍም፤ አልቀይርም፤ እውነት ሁሌም እውነት ሆኖ ይኖራል”። 
       ሐዋርያዊ መልእክቱ (ስለ የሰው ልጅ ክቡር ሕይወት) ብዙ መልእክት የያዘ ነበር፤ ነገር ግን ብዙዎች ሲነጋገሩበት የነበረው “ሰው ሠራሽ የወሊድ መቆጣጠሪያ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ መሆኑን” በሚገልጸው ላይ ነበር። ሐዋርያዊ መልእክቱ የሰው ልጅ ሕይወት እንዲቀጥልና እንዲቋረጥ የማድረግ መብት ያለው አምላክ ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም ሰው ሕይወት እንዲቀጥል ከአምላክ ጋር መተባበር አለበት እንጂ የአምላክን ክቡርና ድንቅ ሥራ በተለያየ መድኃኒትም ሆነ መንገድ ማሰናከል አይችልም፤ ይህም እውነታ ከመጀመሪያው የነበረና ወደፊትም የሚኖር መሆኑን ሰነዱ ይገልጻል። 
     ዘግይቶ በተደረገው ጥናት ግን ምእመናን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ትተው ይሄዳሉ እንደተባለው ሳይሆን ይልቅስ ይህንን ሐዋርያዊ መልእክት በሚገባ የተረዱት የሌላ እምነት ተከታዮችም ጭምር ትምህርቱን እንደተቀበሉትና እንደደገፉት ታውቋል። እውነት ሁሌም ያሸንፋል፤ ብዙዎችንም ይማርካል። ይህ እውነታ ዛሬም አልተቀየረም። 

. .  .   ይቀጥላል።


ዓላማችን፦ ክርስትናን ክርስቶስን እንወቅ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6770

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.

ጌታዬ ሁለመናዬ!

04 Oct, 07:44


🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

#የማይቀየረው እውነታና #ቅዱስ_ቁርባን።

(በክቡር አባ ምሥራቅ ጥዩ (ዶ/ር))
🌱🕊🌾🥀🌱🌱🌴🌱🌱🌱🌱🌾

     ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ በዙሪያው በተሰበሰበ ጊዜ “ከሰማይ የወረደው ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል” በማለት አስተማራቸው(ዮሐ 6፡51)። በተጨማሪም “ሥጋዬን የሚበላና ደሜንም የሚጠጣ ሁሉ ለዘላለም ሕይወት አለው፤ ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ” አላቸው(ዮሐ 6፡53-56)። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ማጉረምረም ጀመረ፤ “ይህ ሰው ሥጋውን እንድንበላ እንዴት ሊሰጠን ይችላል?(ዮሐ 6፡52)፤ ይህ ነገር ማን ሊቀበለው ይችላል?” በማለት ብዙዎች ትተውት ሄዱ(ዮሐ 6፡60)። ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ብዙዎቹ ወደ ኋላ አፈገፈጉ(ዮሐ 6፡66)። ሆኖም ግን ኢየሱስ ሲሸሽ ወይም ሲኰበልል ለነበረው ሕዝብም ሆነ ለደቀ መዛሙርቱ “ኑ ተመለሱ፤ አሳቤን ቀይሬአለሁ፤ ኑ አትሂዱ የተናገርሁትን አሻሽለዋለሁ” አላላቸውም፤ ይልቅስ ለቀሩትና አጠገቡ ለነበሩት ደቀ መዛሙርት “እናንተም መሄድ ትፈልጋላችሁን?” በማለት ጠየቃቸው(ዮሐ 6፡66)። 

      በእርግጥም እውነት አይለወጥም፤ ሰዎች ቢሄዱም እውነት በምንም ዓይነት መልኩ አይቀየርም። የሰዎች መሄድ መምጣት እውነትን ሊያናውጠውና ሊያናጋው አይችልም። ያኔ ኢየሱስ በትንሽዋ መንደር የመሠረተውና በዙሪያው ለነበሩት ጥቂቶች የሰጠውን ቅዱስ ቁርባን በዓለም በአራቱም አቅጣጫ በቢሊዮን በሚቆጠሩ ሕዝቦች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ አግኝቶ ይኖራል፤ መኖርም ከጀመረ እነሆ ሁለት ሺህ ዓመታት ተቆጥረዋል፤ ብዙዎችም ይህንን ምሥጢር ተካፍለው ዘላለማዊውን ሕይወት ተካፋይ ሆነዋል። 
      
#ቅዱስ_ቁርባን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ሥጋውና ደሙ ነው። ይህን ሕያው እንጀራ የሚበላና ደሙንም የሚጠጣ ለዘላለም ይኖራል(ዮሐ 6፡51)። በሥልጣኔ የሰከሩ አውሮፓውያን “ቅዱስ ቁርባን ባንቀበል ምን እንሆናለን? ምንስ ሊቀርብን ይችላል?” ብለው ሲጠይቁ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ዐሥራ ስድስተኛው እንዲህ ብለው መልሰውላቸዋል፤ “ቅዱስ ቁርባን ባትቀበሉ ምንም ነገር አይቀርባችሁም፤ ሊቀርባችሁ የሚችለው አንድና አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እርሱም የዘላለም ሕይወት ማጣትን ነው”። በእርግጥ የዘላለም ሕይወት ያጣ ሰው ሁሉንም አጥቶአል፤ ያጣውም ለሚሊየን ወይም ለቢሊየን ዓመታት ሳይሆን ለዘላለሙ ነው። ይህ ደግሞ በምንም የማይመለስና የማይካስ ኪሳራ ነው፡፡
 
የማይቀየረው እውነታና ሰው ሠራሽ የወሊድ መቆጣጠሪያ፦  እ.አ.አ. በሐምሌ 1968 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ.. . . .

ይቀጥላል።


ዋና ዓላማችን፦ ክርስትናን ክርስቶስን እንወቅ


#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇

https://t.me/YariedDessale/6769

☝️#ኑ ☝️#እንማማር 

The Universal Catholic Church Teaching Channel.