ደቡባዊ ፋኖ ተመሰረተ‼️
"የኢትዮጵያ ፋኖ በደቡብ (ኢትዮ ፋኖ)" በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተመሠረተ።
ድርጅቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል አደረጃጀት መመስረታቸውን እና ሕዝባዊ መሠረት መያዙን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።
ድርጅቱን የመሠረቱ አመራሮች ከኤቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የኦሮሙማ አገዛዝ በያዘው የግዛት ማስፋፋት እና ሰልቃጭ አካሄድ የሕልውና አደጋ ደቅኖብናል ብለዋል።
በየጊዜው በአገዛዙ የሚፈፀም አፈና እና የወጣቶች ስወራ በስፋት እየተከናወነ አድራሻቸው የጠፋ የደቡብ ወጣቶች መኖራቸውን አንስተዋል።
የያዝነው ትግል የፀረ-ጭቆና ነው ሲሉ አስተባባሪዎቹ አርበኛ ናደው ዘለቀ እና አርበኛ ደመቀ በቀለ ተናግረዋል።
የደቡብ ሕዝብ ከፍተኛ አፈና ውስጥ ነው ያሉት አስተባባሪዎቹ አሁን በዚህ አገዛዝ ስር አንመራም የሚል ብሶት ተቀጣጥሏል ብለዋል።
የደቡብ ወጣት ከምንግዜውም በላይ "የኢትዮጵያ ፋኖ በደቡብ" አደረጃጀትን በመቀላቀል ላይ ይገኛል ብለዋል።
በቀጣይም በደቡብ ክልል የተለያዩ ቀጠናዎች የተጀመረውን አደረጃጀት በማጠናከር ፀረ-አገዛዝ ትግሉን እንደሚያቀጣጥሉ ተናግረዋል።
የአማራ ፋኖ ትግል ለደቡብ ወጣቶች ትግል ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት አስተባባሪዎቹ በትጥቅና በአደረጃጀት እየተጠናከርን እንቀጥላለን ብለዋል።
ABC TV ከአስተባባሪዎች ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ በዛሬው እለት እንደሚያስተላልፍ ይገልፃል።
ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
#ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418
20/05/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
አዲስ አበባ
https://t.me/Moamediamoresh
https://t.me/Moamediamoresh