AHADU RADIO FM 94.3 @ahaduradio Channel on Telegram

AHADU RADIO FM 94.3

@ahaduradio


አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

AHADU RADIO FM 94.3 (Amharic)

አሐዱ ራድዮ 94.3
በእርሱ አትቀመጡ፦ 'AHADU RADIO FM 94.3' የቴሌግራምና የቴሌቧል ኢትዮጵያ መረጃዎች እና ምንም እንደሆነ ከአንድ እስር ቤተሰብ የሚገኝበት ሕይወት ሲሆን ኢትዮጵያዊን እና ለዓለም ሳሆማ ወቅቶችን ለመጫወት በመቀየት እንጠናቅቃለን። ከአንዱን እስር እስከ ሌሎችን መረጃዎች ዘገቦች በዚህ ቤተሰብ በዓል አድርገን የእንቆማ የቅድመ-ምርምር እና ፕሮግራሞችን ልክቶለን። ከሌሎች ቦታዎች ውስጥ በጣም ካሉት መጽሐፍ እንጠብቃለን እና ማጠናቀቅን ስለሚችል ከዚህ የሚቆይ አንዱን ስኬት አስተናግዶ ቀበሌ፣ እጠቀማለን።

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 18:31


#አሐዱ_ወንዞች

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/xhpwUL9w2zI?si=7kgJ-Todxf4DjOWB

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 18:02


መንግሥት የሠራተኞችን የመጠቀም ዕድል እስካላመቻቸ ድረስ የሚሰሩበትን የሥራ ሰዓት ቢጨምር ውጤታማ አይሆንም ተባለ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌደራሉ መንግሥት የሠራተኞችን የመጠቀም ዕድል ቅድሚያ ሰጥቶ እስካላሻሻለ ድረስ፤ የሰዓት ጭማሪ ብቻውን በሕግ ቢያጸድቅ፤ ውጤታማ ሊያደርደገው አይችልም ሲሉ አሐዱ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

አሐዱ ከሰሞኑ የመንግሥት ሠራተኞች ከዚህ ቀደም በሳምንት ሲሰሩ የነበረውን የ39 ሰዓት ወደ 48 ሰዓት ከፍ አድርገዉ እንዲሰሩ የሚያስገድደዉን ረቂቅ አዋጅ መሰረት በማድረግ፤ “በሠራተኞቹ ላይም ሆነ በመንግሥት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አያሳድርም ወይ? እንዲሁም ከአለም ዓቀፍ ሕግጋት አንጻር እንዴት ይታያል” ሲል ጠይቋል፡፡

የሕግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ በሰጡት ምላሽ፤ "አንድ ሰው በአለም ዓቀፍ ሕግ በቀን መስራት ያለበት 8 ሰዓት ነው" ብለዋል፡፡

ከዚህ በላይ ከሆነ ግን እንደ ድርጅቱ እና ሠራተኛው ፍቃደኝነት የሚወሰን መሆን እንዳለበት አስረድተዋል።

የውሳኔውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት መልኩ እንደሚመለከቱት የገለጹት የሕግ ባለሙያው፤ በአንድ በኩል መንግሥት በሠራተኞች ላይ የሰዓት ጭማሪ ሲያደርግ የደሞዝ ጭማሪም ማድረግ እንዳለበት ጠቁመው፤ "በሌላ መልኩ ደግሞ በመንግሥት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደልም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የሕግ ባለሙያ አቶ ወንድሙ ኢብሳ በበኩላቸው፤ "በምንም አይነት መልኩ በሠራተኛ ላይ አንድ ተቋም ሥራ ሲጨምር ሆነ የሥራ ሰዓት ሲያራዝም በዛው ልክ የሠራተኛውን ደሞዝ ማሻሻል አለበት" ባይ ናቸው፡፡

"ነገር ግን ይህን ማድረግ ካልተቻለ አመርቂ ውጤት ማምጣት አይቻልም" ብለዋል፡፡

"ሠራተኞችን ሳያስፈቅዱ አስገድዶ ለማስራት መሞከር ሀገርን ለይበልጥ ኪሳራ ማጋለጥ እንጂ ግብ የሚያመጣ ለውጥ ማምጣት አይቻልም" ሲሉም የሕግ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሳምንቱ መጀመሪያ ሕዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባከናወነው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቁ ይታወሳል።

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 17:25


#UPDATE
በአለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

👉 በ40 ሰዎች ላይ ከባድና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሷል


ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መከሰቱን በስፍራው ካሉ ነዋሪዎች ሰምቶ አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውንና የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ነዋሪዎቹ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፋን እንዲሁም፤ በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

በአደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 15:05


ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ከመከላከል አኳያ የሕግ ክፍተት መኖሩ ተገለጸ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጾታን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች ላይ እየተደረገ ያለ ቅደመ መከላከል ሥራ ቢኖርም እንደ ሀገር የሕግ ክፍተት መኖሩን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

ከችግሩ ጋር ተያይዞ የጥቃቱ ፈፃሚ አካላት በሕግ ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ የሚበይነው ውሳኔ አስተማሪ አለመሆኑ ተነስቷል፡፡

በተለይም የተቀመጠው ሕግ በሥራ ቦታ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ብቻ እርምጃ የሚወሰድባቸው በመሆኑ፤ በሥራ ባልደረባ አማካኝነት ከሥራ ገበታ ውጭ  የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል የሕግ ክፍተቶች መኖራቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስቴር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲን ተናግረዋል፡፡

የሕግ ክፍተቶች በመኖራቸው ሳቢያ በስፋት እየተስተዋለ የመጣዉን የአስገድዶ መድፈር፣ ግድያ እና ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል አስቻይ አለማድረጉን ሚኒስቴር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ቀድመዉ የወጡ ነገር ግን በጊዜያቸው ትክክል የነበሩ ውሳኔዎች፤ አሁን ላይ 'አስተማሪ አይደሉም' ተብሎ የተለዩ ሕጎች ተለይተው እንዲሻሻሉ ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ጠቁመዋል።

በቀጣይ በየደረጃቸው ካሉ በሚመለከታቸው ተወካዮች ምክር ቤት አና ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት በመወያየት የተለዩ ሕጎች ማሻሻያ እንዲደረግ እና ድርጊቱን ፈፃሚዎችን አስተማሪ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወልደሐዋሪያት ዘነበ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 13:41


"የማሳልፋቸውን ውሳኔዎች እና እቅዴን ለመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ለንግዱ ማህበረሰብ የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም" ብሔራዊ ባንክ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት የማሳልፋቸውን ውሳኔዎች እና እቅዴን ለመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ለንግዱ ማህበረሰብ የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም ሲል ገልጿል።

ባንኩ ይህንን ያለው ከንግዱ ማሕበረሰብና የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ተደጋግሞ ለሚነሳበት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ነው።

ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ያሳለፋቸው ገንዘብ ነክ ፖሊሲዎች ከማዕከላዊው መንግሥት አስተዳደር የታቀዱ መሆናቸውን ለአሐዱ የተናገሩት፤ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱራፌ ናቸው።

ምክትል ዳይሬክተሩ ባንኩ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ኢኮኖሚው እንዲሻሻልና የአገር ገቢ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ማዕከላዊ ባንኩ እስካሁን የገንዘብ ስርዓቱን ለዘብተኛ በሆነ መንገድ እየመራው እንዳለም ጠቅሰው፤ አጠቃላይ ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን ይፋ ማድረግ እንደማይጠበቅበት ገልጸዋል።

አክለውም የውጭ ምንዛሪን ስርዓቱን ገበያ መር እንዲሆን ማስቻልን ጨምሮ፤ ለባንኮች እንዲተገብሩት የተላለፈው ከ14 በመቶ በላይ የብድር ጣርያ ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ንግድ ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበት ስርዓት መዘርጋቱ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገባውና አንዳንዶቹ አዲስ ያስተዋወቃቸው የገንዘብ ገበያ ስርዓቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በዚህ መሰረት ሁሉንም የመንግሥት ውሳኔዎች እወቁልን እያሉ በየጊዜው ማስተዋወቁን ብሔራዊ ባንክ አስፈላጊ ብሎ እንደሚያምንበት፤ የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ስርዓት ምክትል ዳይሬክተሩ አበባየሁ ዱራፌ ሲናገሩ ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተደጋጋሚ የሚደረገውን የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ፤ "ገበያውን ከመጠበቅ አንፃር ጥንቃቄ የጎደላቸው ሕጎች እያወጣ ነው" በሚል ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ የሚታወቅ ነው።

ይሁንና ባንኩ "የተሳኩ ውሳኔዎች አሳልፌያለሁ" የሚል እምነት እንዳለው ከዳይሬክተሩ መረዳት ተችሏል።

በሌላ በኩል አጠቃላይ የገንዘብ አስተዳደር ስርዓቱ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በተለይም ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ያከናወናቸው ሥራዎች የተሳለጡና የተሳኩ እንደነበሩም ገልጸዋል።

አሁን ላይ ባንኩ በፍራንኮ ቫሉታ የወሰደውን እርምጃ ሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ በፍጥነት የሚገታ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን ተነግሯል።

የገንዘብ ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን መስርያ ቤቶች ውሳኔውን ተፈፃሚ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ለመተግበር የሚያስችሉ ስርዓቶች በመዘርጋት ረገድ እየተሰራበት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።

የባንኩ ውሳኔዎችም መለካት ያለባቸው በምጣኔ ሐብቱ በመጡት ተጨባጭ ውጤቶች መሆን እንደሚኖርበትም አቶ አበባየሁ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአማኑዔል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 11:48


#አሐዱ_አብይ_ጉዳይ

ጥንቅሩን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://youtu.be/I657y-_k_YI?si=5BJAQbP9cRmWDbzg

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 09:36


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ60 በላይ መምህራኖች መታሰራቸውን ተገለጸ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ፤ 66 የሚደርሱ መምህራኖች "ደመወዝ ይከፈለን" የሚል በመጠየቃቸው ታስረዋል ሲል የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር አስታውቋል፡፡

የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑቱ አቶ ሽመልስ አበበ፤ "መምህራኖቹ ደመወዝ ይከፈለን ብለው ስለጠየቁ ብቻ ለእስር ታዳርገዋል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በየትኛውም መልክ ደመወዝ መጠየቅ ለእስር ሊዳርግ አይችልም" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ "ይህ አይነት ስርዓት አልበኝነት አካሄድ የትምህርት ስርዓቱን ለማደከም የታለም ነው" ሲሉ አውግዘዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መምህራንን ማሰር የጀመረው ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ መሆኑን ያስታወሱም ሲሆን፤ "ይህ አይነት መምህራንን የማሸማቀቅ አካሄድ ሊቆም ይገባል" በማለት አሳስበዋል፡፡

መምህራኖቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በወረዳው ፖሊሶች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ደርሶባቸው ለአካል ጉዳት የተዳጉም ሳይኖሩ እንዳልቀር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በውል የማይታወቁ መምህራን አሁንም የሕክምና እርዳታ የሚፈልጉ ቢሆንም፤ እርዳታ እንዲያገኙ በጸጥታ ሃይሎች ክልከላ እንደተደረገባቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አክለውም፤ "ስልጣንም ያልፋል፣ ሁሉም ነገር ባለበት አይቀጥልም፣ ነገር ግን በተለይ ተደጋጋሚ የመምህራን ጥያቄ ማፈን ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በታሪክም የሚያስወቅስ ነው" ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

መምህራኖቹ ተቃውሞ ያነሱት፤ በክልሉ መንግሥት ይሁንታ የ25 በመቶ የደመወዝ ቅነሳው ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ላይ መደረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በወረዳው 683 መምህራኖች እንዳሉ የተገመተ ቢሆንም፤ 66 የሚደርሱት መታሰራቸው ተገልጿል፡፡

በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 08:47


በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መከሰቱ ተሰማ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን አሐዱ የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡

አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለእረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አደጋው ያደረሰውን ጉዳት መጠን አስመልክቶ፤ አሐዱ ዝርዝር መረጃ ባገኘበት ሰዓት ወደእናንተ ያደርሳል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

AHADU RADIO FM 94.3

23 Nov, 07:03


"ተሃድሶ የሚወስዱት የቀድሞ ታጣቂዎች ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኃላ ያሉት ብቻ ናቸው" ብርጋዴር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ

ሕዳር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞ ታዋጊዎች ሲባል ግርታ ውስጥ የመግባት ነገር መፈጠሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነርና የመከላከያ ሠራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

"ታጣቂዎችን የመለየቱ ሥራ በምን አግባብ ነው እየተሰራ ያለው?" የሚለው ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን የገለጹት ጄነራሉ፤ የተለያዩ ማረጋገጫዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም "የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደ ክልል ያለውን የተዋጊ ብዛት አሳውቋል" ያሉ ሲሆን፤ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴርም ባለቤት በመሆኑ እንደ ሀገር ያለውን የታጠቀ አካላትን በመለየት ተከታትሎ ማስረጃ ማቅረቡን አስረድተዋል፡፡

ይህ ቁጥጥር የሚረጋገጠው ግን ተመዝግቦ ይፋ ሲደረግና መስፈርቶችን ሲያሟላ ብቻ መሆኑን የተገለጹ ሲሆን፤ "በስምምነቱ መሰረት ትጥቁን ያሰረከበ መሆን አለበት" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ቦታ አሁንም የትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን ያነሱት ጀኔራል ደርቤ፤ ይህንን በሚመለከት ሌላ ኮሚሽን ሳያስፈልግ ባለው ኮሚሽን ተጠቅመው ወደ ትጥቅ መፍታት እንዲመጡ ጠይቀዋል፡፡

በዚህም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል፣ ትግራይ እና አፋር አካባቢ ላሉ ታጣቂዎች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፋር ክልል ከሰሞኑ ትጥቅ የማሰፈታት ሂደቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የጀመረው ትጥቅ የመፍታትና ወደ ማህበረሰብ የመቀላቀል ሥራ በትግራይ ክልል መቀሌ የተጀመረ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር 320 ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል መግባታቸው ተገልጿል፡፡

በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

19,791

subscribers

4,466

photos

157

videos