Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት @ethphi Channel on Telegram

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

@ethphi


EPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center.

For any information and help call 8335 or send us a message through [email protected]

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (English)

The Ethiopian Public Health Institute (EPHI) is one of the oldest and most well-known public health institutes in Africa. It plays a crucial role in safeguarding the health of the Ethiopian population through various public health programs and services.

Operating 24/7, EPHI's Emergency Operation Center is dedicated to managing public health emergencies and ensuring a quick and effective response to any health crises. With a team of experienced professionals and state-of-the-art facilities, EPHI is at the forefront of promoting public health in Ethiopia.

Whether you need information, assistance, or have a health-related emergency, you can contact EPHI by calling 8335 or sending a message to [email protected]. Stay informed and connected with EPHI to ensure the well-being of yourself and your community.

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

21 Nov, 12:40


WB and ECSA-HC Delegates Visited EPHI
---------------------------
Delegates from the World Bank (WB) and East, Central and Southern Africa Health Community (ECSA-HC) visited the Ethiopian Public Health Institute (EPHI) on November 20, 2024. The purpose of the visit was to share experience on the Human Papiloma Virus (HPV) testing services currently being provided in Ethiopia.
Dr. Mesay Hailu, Director General of EPHI, along with the Director of Laboratory Capacity Building Directorate and laboratory technical experts of EPHI welcomed the delegates. The Director General outlined the roles of EPHI in strengthening the national health security through several key initiatives like spearheading and coordinating public health emergency management efforts, ensuring that response strategies are both comprehensive and effective; conducting essential health researches and synthesizing scientific evidence to inform public health policies, strategies, intervention programs and practices; building sustainable and resilient laboratory systems for the provision of  high-quality laboratory services, and advancing digital health data science and analytics towards improving the country's health information systems to effectively support public health decision-making in real time.  
A senior laboratory expert of the Institute delivered a presentation on Ethiopia's laboratory system, focusing on its organizational structure, successes, challenges, future perspectives and opportunities. The presentation has also touched upon the country's Strategic Plan for the advancement of the National Health Laboratory System and services. Furthermore, the presentation has provided progress updates on overall lab activities including Ethiopia's strategy and implementation mechanisms for the provision of quality human papilloma virus (HPV) diagnostic services. Finally, the delegates visited the EPHI’s` molecular laboratory where referral HPV testing service is also provided.
www.ephi.gov.et/news

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

21 Nov, 11:32


በሀገራችን እየተከሰተ ስላለው ጉንፋን መሰል በሽታ የተሰጠ ማብራሪያ
---------------------------
የጉንፋን በሽታ በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጉሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ። በርካታ ቫይረሶች ለጉንፋን መከሰት ምክንያት ቢሆኑም በጣም የተለመዱት ግን ሪኖ ቫይረስ ፣ኮሮና ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ሲሆኑ ሪኖ ቫይረስ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል። ደረቅና ነፋሻማ የአየር ፀባይ (ወቅት) ቫይረሶች በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራጭ ስለሚያግዝ እና የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን (ሙከስ መምብሬን) ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍተኛ ድካም፣ ብርድ ብርድ ማለት፣የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ።
ይህ የጉንፋን መሰል በሽታ ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ እና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች (droplets) ጋር በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ፣ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ወይም እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ሊተላለፍ ይችላል። ስለሆነም የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግ፣ የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁሶችን ንጽሕና በመጠበቅ፣ የቤት እና የብዙሃን መጓጓዣ ትራንስፖርት መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታውን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ህጻናት፣ አረጋውያን፣ ተጓዳኝ የጤና ዕክል (አስም፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ የልብ ህመም፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ) በሽታዎች ያሉባቸው እና ነፍሰጡሮች ይበልጥ ተጠቂ ስለሚሆኑ በበሽታው ከተያዙ አስፈላጊው ክትትልና የህክምና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል፡፡
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ክፍል በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የጤና ተቋማት የቅኝት ስራውን በመደበኛነት ላለፉት 15 አመታት እየሰራ ይገኛል። ከአሁን በፊት በተሰራው የቅኝት መረጃ መሰረት ይህ ጉንፋን (ጉንፋን መሰል) በሽታ በሀገራችን አመቱን ሙሉ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ከመስከረም እስከ ታህሳስ ድረስ የስርጭት መጠኑ ከፍ ይላል፡፡በዚህም መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት (መስከረምና ጥቅምት 2017ዓ/ም) ከሁሉም የቅኝት ጣቢያዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎች መካከል 35% አር ኤስ ቪ፣ 6.2% ኢንፍሉዌንዛ፣ እንዲሁም 2% የኮረና ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸው ተረጋግጧል። የአር ኤስ ቪ (RSV) ቫይረስ ተጠቂዎች ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ወቅት ከሚከሰተው መጠን ከፍ ያለ ሲሆን ቫይረሱ ከተገኘባቸው ህሙማን መካከል 88.5% የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡ ለሚቀጥሉት 2 ወራት የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡
በቂ እረፍት ማድረግ፣ ፈሳሽ መውሰድ፣ በልጆች የአፍንጫ መታፈን ከገጠመ ለብ ባለ ውሀ ላይ ትንሽ ጨው በመጨመር በአፍንጫ ጠብ ማድረግ፣ በእንፋሎት(ስቲም) መታጠን እንዲሁም ህመም ማስታገሻ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከላይ በተዘረዘሩት በቤት ውስጥ በሚደረጉ ክትትሎች ለውጥ ከላሳየ እና የህመም ምልክቶቹ እየተባባሱ ከሄዱ (በተለይም በህጻናት ላይ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ማቃሰት፣ እና ሌሎችም ምልክቶች ከታዩ) ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማገኘት ያስፈልጋል፡፡

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

18 Nov, 16:27


በአገር አቀፍ ደረጃ የወባ በሽታን አሁናዊ ሁኔታንአስመልክቶ ሳምንታዊው የውይይት 
ስብሰባ ተካሄደ
-----------------
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በተገኙበት በአገር አቀፍ ደረጃ  የወባ 
በሽታ አሁናዊ ሁኔታን አስመልክቶ  ዛሬ ህዳር  9/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የስልጠና  ማዕከል በበይነ መረብ ሳምንታዊ  የውይይት ስብሰባ ተካሄደ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝን  በተመለከተ የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ የክልል ጤና  ቢሮዎች እንዲሁም ክላስተሮች ወረርሽኙን  ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶች እና የቀጣይ  እርምጃዎችን በዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን  ለወባ ትንኝ መራቢያ የሆኑ ቦታዎችን የማጽዳት፣ የተለያዩ የውሃ መጠራቀሚያ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን፣ የአጎበር ስርጭት እና የኬሚካል ርጭትን በተመለከተ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን፤ ለዚህም በተሰሩ በርካታ የመከላከል ስራዎች ምክንያት የወባ በሽታ ወረርሽኝን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉንና በቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑን እና በቀጣይም እንደሃገር የተጣለውን ግብ ከዳር ለማድረስ የተለያዩ የመከላከያና የመቆጣጠሪያ መንገዶችን በመጠቀም ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩም ሲቀርቡ ከነበሩ ሪፖርቶች መረዳት ተችሏል፡፡ 
 ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የውይይቱን ማጠቃለያ በሰጡበት በወቅት እንደገለጹት በአገር አቀፍ ደረጃ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ግልጽ የሆነ አሰራር በመዘርጋትና ሁሉን ያማከለ እቅድ በማውጣት በተደረገው ቅንጅታዊ ስራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ከተጣለው አገር አቀፍ ግብ አንጻር በቀጣይ ምን ያህል ውጤቶች እንደሚቀሩ በመፈተሽ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የቅኝት ስራዎችን በመስራት እና ለውሳኔ በማቅረብ በቀበሌና በጤና ተቋማት በኩል የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎችን በቅንጅት መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው እየተሰሩ ያሉ በርካታ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች በሚገባ ሕብረተሰቡ ዘንድ ደርሰው ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን፣ በቀጣይም ቤት ለቤት የሚደረጉ ጉብኝቶች፣ የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን የማጽዳት የንቅናቄ ዘመቻዎችን፣ የግንዛቤ ትምህርቶችን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራዎችን በማጠናከርና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በቅንጅት መሰራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ የወባ በሽታ ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ የልማት ቀጠናዎች ላይ በርካታ ሰዎች የሚሰባሰቡ ከመሆናቸውም በላይ በሌሊትም ጭምር ስራዎችን የሚሰሩ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት የግንዛቤ ስራዎች መሰራት እንደሚገባ የጠቆሙ ሲሆን የሚሰራጩ የተለያዩ የመከላከያ ግብዓቶችንም በአግባቡ መጠቀም ተገቢ መሆኑን ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

18 Nov, 11:50


የአለም ፀረ-ተህዋስያን የመቋቋም ግንዛቤ ሳምንት ህዳር 9-15/2017.
World Antimicrobial Awareness Week(WAAW) November 18-24/2024.
--------------------------
World Antimicrobial Resistance Awareness Week (WAAW) is held from 18–24 November every year. The global campaign aims to raise awareness and understanding of antimicrobial resistance (AMR) and promote best practices among One Health stakeholders to reduce the development and spread of drug-resistant infections. The theme of this year’s WAAW is “Educate. Advocate. Act now.

Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

14 Nov, 03:48


Ethiopia hosts a Global EOC Simulation Exercise
In an effort to improve public health emergency preparedness, Ethiopia is hosting the 2024 Global Emergency Operations Center (EOC) Simulation Exercise (GOCEX-2024).
At the event's opening, H.E. Dr. Mekdes Daba, Federal Democratic Republic of Ethiopia, Minister of Health, stated that the country has made significant investments in health emergency preparedness and regularly assesses risks at the national, sub-national, and district levels, and develops comprehensive Emergency Preparedness and Response plans using a One Health approach. The Minister asserts that these steps will ensure the nation is well-prepared to quickly and successfully address new health threats.
"The Ethiopia Public Health Institute plays a significant role in strengthening public health systems and ensuring preparedness for and response to public health emergencies," stated Dr. Mesay Hailu, Director General of the Ethiopia Public Health Institute. The Director General added that these simulation exercises will enable us to assess the capacity and capability of our national and sub-national public health Emergency Operations Centers. Additionally, this exercise will provide us with an opportunity to learn from one another and build alliances that strengthen our ability to tackle future health challenges.
The Ethiopia Public Health Institute's national public health emergency center has been the cornerstone for the response to public health emergencies, guaranteeing coordination and readiness at every level, according to Dr. Melkamu Abite, Deputy Director general of the institute. Additionally, public health emergency operation centers have made significant progress in developing their operational mode over the years, and the Deputy Director General confirmed that the center will keep aiming for excellence in all of its endeavors.
Dr. Michel Yao, Director of Strategic Health Operations within WHO Health Emergencies Programme. "The GEOCX 2024 simulation provides a unique opportunity for Member States to strengthen their emergency preparedness and response systems, enhancing coordination mechanisms to ensure that PHEOCs are equipped to deliver rapid, life-saving actions during crises. Dr. Nonhlanhla Dlamini, Deputy, WHO country representative for Ethiopia, stated that Ethiopia is joining the international community in demonstrating its dedication to global health security initiatives in addressing public health crises, irrespective of their origin or magnitude, by hosting this Global Emergency Operations Center simulation exercise. The US CDC, European CDC, Africa CDC and UKSA also participated in the simulation exercise, which included over 300 participants from 73 countries.
The WHO EOC-NET secretariat coordinated the worldwide emergency operational center simulation exercise, which was co-hosted by the WHO Ethiopia country office and the Ethiopian Public Health Institute.