EOTC ቤተ መጻሕፍት @eotclibilery Channel on Telegram

EOTC ቤተ መጻሕፍት

@eotclibilery


ይህ Channel የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ስብከትች እንዲሁም የተለያዩ ለአብነት ትምህርት የሚሆኑ በድምፅ ፤ይሁን በጹሁፍ እንዲሁም በ Video ሚለቀቅበት Channl new
ተጨማሪ ወይም ሚፈልጉትን መፃህፍት

ብለው ይጠይቁን
ማስታወቂያም እንሰራለን በውስጥ መስመር ይጠይቁን
የሰማነዉን እንናገራለን!
ያየነዉን እንመሰክራለን!

EOTC ቤተ መጻሕፍት (Amharic)

ኢዶቤተ መጻሕፍት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ስብከትች እንዲሁም የተለያዩ ለአብነት ትምህርት የሚሆኑ በድምፅ ፣ ይሁን በጹሁፍ እንዲሁም በ Video ሚለቀቅበት Channel ያየነዉንን ሚፈልጉትን መፃህፍት። ብለው ይጠይቁን፣ ማስታወቂያም እንሰራለን በውስጥ መስመር ይጠይቁን፣ የሰማነዉን እንናገራለን! ያየነዉን እንመሰክራለን!

EOTC ቤተ መጻሕፍት

21 Nov, 06:58


https://www.youtube.com/live/ohCsTilZipU?si=oRJwRBmFtAch_-xO

EOTC ቤተ መጻሕፍት

20 Nov, 16:29


😭 .ሥድስቱ.መክነው የነበሩ  ሴቶች ። .................

.........  ሐና   እና   ሐና...................
ሁለቱ በልጅ የከበሩ እናቶች ናቸው። ቀዳማዊት ሐና እመ ሳሙኤል እና ደኅራዊት ሐና እመ  ማርያም ናቸው ።

ቀድማዊት ሐና መክና ኑራ፤ መውለድ ተስኗት ተነቅፋ ተዘልፋ ፥ተገፍታ ተንከራታ የወለደች እናት ናት። የባሏ ሚስት  ፍናና ትባላለች። ባለ መውለዷ  ንቃት አቃላት ነበር። ፦የቤተ መቅደሱ  ሊቀ ካህን ኤሊም ስታለቅስ አይቶ፥ አንች ሴት ስካርሽ መቼ ነው የሚለቅሽ?"
   ብሎ የነቀፋት  እናት ናት።

ጸሎቷ  እንባዋ ሰካራም አስመስሏት፤ልጅ በማጣት የተናቀች ስትሆን ፤ የነገሩትን የማይረሳ ። የለማኑትን የማይነሳ ጌታ !! ታላቅ ልጅ ሰጣት።እርሱም አንድ ሲሆን ስለ ሰባት የሚቆጠር።ፍጹም የሆነ ልጅ ነው። ሳሙኤል ይባላል። ንጉሥ ዳዊትን ቀብቶ ያነገሠ እርሱ ነው፤ እስመመካን ወለደት ሰብዓተ ወወላድሰ ስዕነት ወሊደ የተባለው ነው።  መካን ሰባት ወለደች። ወላድ ግን መውለድን ተሳነች" ተብላለች። ሁለተኛዋ ሐና ፦ ከነገደ ይሁዳ የተወለደው የደጉ ሰው የኢያቄም ሚስት ሐና ናት ።

ሐናም መካን ነበረች። ቢወልዷት እንጅ የማትወልድ ፤ በቅሎ እያሉ ጎረቤቶቿ የሰደቧት ነበረች። ሐናም ከባለቤቷ ኢያቄም ጋራ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ትገሰግስ ነበር። ነገር ግን ሐና እና ኢያቄም መካን ናቸውና የቤተ መቅደሱ ካህንም፦ የወለዱ ሰዎች የሚመገቡት ተረፈ መሥዋዕት ነበረና  ።ያንን ይከለክላቸዋል። እናንተ ብዙ ተባዙ ብሎ ጌታ ለአዳም የሰጠውን ቃል የነሳችሁ ፤ ክፉ ብትሆኑ አይደለምን?"  ብሎ ይከለክላቸው ነበር።

ሐና እና ኢያቄምም  እያለቀሱ ይመለሱ ነበር። አርጋብን(ርግቦችን )  አይታ ሐና ታለቅስ ነበር። ርግቦች ሲዋለዱ ሲራቡ እኔ ምንድን ነኝ?"እያለች።

እጸውን (ዛፎችን) ታያለች ለምልመው አብበው አፍርተው ትመለከት እና ዛፎች ሲያፈሩ ፦ ወፎች እና ርግቦች ሲራቡ እኔ የማልወልደው ምን ሁኘ ነው?የሆነውስ ሁኖ  የኔ   የሐና  ተፈጥሮየ   ከድንጋይ ወገን ይሆንን? ብላ ምርር ብላ ታለቅሳለች
በመጨረሻም ሁለቱም ራእይ አዩ። ከሰባቱ ሰማያት ይልቅ የምታባራ፤ የምትበልጥ አዲስ ሰማይ፤ አዲስ ምድር ድንግል ማርያምን ወለዱ።የአምላክ እናት ከመካኗ ከሐና ተወለደች። ወገኖቼ !! ለካ አንዳንድ ጊዜ መከራ ሲቀድምም ጥሩ ነው። እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ ያለ መከራ ጸጋ ክብር አይገኝም መባሉ ለካ እንዲህ እሙን ነውን ? ይገርመኛል።

የሣራ   መምከን የታዘዦች አብነት የሆነውን ይስሐቅን አመጣልን።ዘፍ  21፥3
የራሄል መምከን  ዮሴፍን አመጣልን። ዘፍ29 ፥31
የ....ምክነት ሶምሶንን አመጣልን። መሳ 13 ፥22
የሐና መምከን ነቢዩ ሳሙኤልን አመጣልን።1ሳሙ 1፥2
የኤልሳቤጥ መምከን  መጥምቁ ዮሐንስን አመጣልን።ሉቃ 1፥13 
የኋለኛዋ ሐና መምከን ድንግል ማርያምን አመጣልን። ነገረ ማርያም፤
የድንግል ማርያም   ድንግልና     ኢየሱስ ክርስቶስን አመጣልን።ኢካ 7፦14
ምክነት የቀደመው ልደት እንደምን ይደንቃል?
በሕይወታችሁ፦ኅዘን፡ይቅደምላችሁ።ማጣትም ይቅደምላችሁ።ታናሽነትም ይቅደምላችሁ።መናቅ መዋረድ፥ መተቸት መነቀፍ  ይቅደምላችሁ። የነዚህ ሁሉ ተከታይ  ክብር መሆኑን ግን ልንገራችሁ።

ግድ የላችሁም  አሁን እየተገፋችሁ ፤  እየተገረፋችሁ እየተሳደደዳችሁ ይሆናል። ነገ ግን ይህ ሁሉ  በእናንተ ላይ  የለም።ከነገ በኋላ ደግሞ ፈጽሞ የለም። መምከን ይስሐቅን ለመውለድ ከሆነ ለምን ሰባት ጊዜ አይመከንም። ሳሙኤልን ለመውለድ ከሆነማ፥ መጥመቁ ዮሐንስን ለመውለድ ከሆነስ ምኑ ይነቀፋል?ምእመናን !! በሥጋ  መምከናችሁ፤  በምድር በምድራዊ ልጅ  ባይካስም  እንኳን በብዙ ነገር  ግን ይካሳል። ብዙ የምንወልዳቸው ልጆች ይኖሩናል። ብቻ አእምሯችሁ አይምከን። ሕይወታችሁ አይምከን እንጅ።  የጻድቅ ሰው መካን የለውም። ክፉ ሰው ኅጢአትን ጸንሶ እንዲወልዳት ደግ ሰውም ጽድቅን ጸንሶ ይወልዳታል። እናቶቼ!!መምከን አንገታችሁን ያስደፋችሁ ፤ ባለ መውለዳችሁ ያለቀሳችሁ፤ ያዘናችሁ ሐናዎች፥ ኤልሳቤጦች ፤ራሔሎች ትኖሩ ይሆን?? አይዟችሁ ያለምክንያት እንዲህ አልሆናችሁም። ወይ ሰውን በሥጋ ትወዳላችሁ ።ይሄም ካልሆነ ሰውን በምጽዋት ፤ በእውቀት፥ በፍቅር ትወልዳላችሁ። በሥጋ የወለዳችሁት ልጅ ባይኖራችሁም የጽድቅ  ፤ የፍቅር።፤ የንጽሕና እናቷ መሆን፡ትችላላችሁ።የእናቶቻችን፡በረከታቸው  አይለየን። የቅድስት ሐና እና የቅዱስ ኢያቄም አማላጅነት ለሁላችን ትድረስ።ኢያቄም እና  ሐና ሰማይን ወለዱ።ሰማያቸው ደግሞ ክርስቶስን ወለደች።

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

19 Nov, 09:40


አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፬. ሸኖ ጎልባ ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሚካኤል ደብር፤ (በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ሰኖ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ሸኖ፡፡
፭. መላሃይዘንጊ ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ8ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፮. ላስታ ላሊበላ ቤተ ሚካኤል፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ የታነፀ፥ ከ11ዱ የላስታ ላሊበላ ፍልፍል ሕንጻዎች አንዱ)
አድራሻው፤ ላስታ ሀገረ ስብከት፥ ላሊበላ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ፡፡
፯. ገርዓልታ ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል፤
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ገርዓልታ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ገርዓልታ፡፡
፰. ሚካኤል ዓምባ፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ውቅሮ፥ (በመቀለና በአዲግራት መሃል)፥ አጽቢ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ውቅሮ → አጽቢ፤
፱. ባሕር ዳር ሽምብጥ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ13ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፥ ቀበሌ 13
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር ከተማ → ሆስፒታል በሚል ታክሲ (ዲፖ ጋር)፡፡
፲. እስቴ አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ፤ (በአፄ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በልጃቸው በአቡነ ፊልሞና የተሠራ ታሪካዊ ጠበል ያለበት)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ እስቴ ወረዳ፥ ደስኳ አጋማች ቀበሌ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እስቴ፡፡
፲፩. በሮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል፤ በ16ኛው መ/ክ/ዘመን መጨረሻ የተመሠረተ
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ሳይንት ወረዳ
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → አማራ ሳይንት፡፡
ወይም፤ ከጎጃም በመርጠሉ ማርያም → አማራ ሳይንት
፲፪. ጎንደር ፊት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት ተመሠረተ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፲፫. ጎንደር አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፲፬. ተንታ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ (ንጉሥ ሚካኤል በሚያስደንቅ ሁኔታ ያሠሩት)
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል፥ ተንታ ወረዳ፥ ጠዓት ቀበሌ፥ እሜገኝ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ፡፡
፲፭. አጃና ቅዱስ ሚካኤል፤ (በቀስተ ደመና ጠበል አጥማቂው)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለት፥ አጃና፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ → አጃና፡፡
፲፮. ቦንብ አርግፍ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት፤ የጁ ወልዲያ)
፲፯. ቦረዳ ቅዱስ ሚካኤል
፲፰. ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ኢቲሳ)
፲፱. አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት)
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፵፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
1.. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ ሚካኤል
ጎሚስታው ሚካኤል (ትግራይ)
እንዳ ቅዱስ ሚካኤል (ትግራይ)
መቀለ ቅዱስ ሚካኤል
5. ጾረና ቅዱስ ሚካኤል (ኤርትራ)
ዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ደብረ ዘይት /ቢሾፍቱ/ ደብረ አሚን ቅዱስ ሚካኤል
ዱከም ቅዱስ ሚካኤል
ናዝሬት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
10. ድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል
ጭሮ አሰበ ተፈሪ ቅዱስ ሚካኤል (ድሬዳዋ፥ አሰበ ተፈሪ)
ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል
አርባ ምንጭ ላከ ኢየሱስና ሚካኤል
ዲላ ቅዱስ ሚካኤል
15. አሰላ ደብረ ሰላም ቅድስ ሚካኤል
ጂጂጋ ቅዱስ ሚካኤል
ሚዛን ቴፒ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ቦንጋ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል
ኢሉባቦር ሌንቃ ቅዱስ ሚካኤል
20. እነሞርና ኤነር ወረዳ ቅዱስ ሚካኤል (ጉራጌ ሀ/ስብከት)
አሰቦት ደብረ ወገግ ቅዱስ ሚካኤል (ምሥ. ሀረርጌ ሀ/ስብከት)
ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል
ኩክ የለሽ ዛሪያ ቅዱስ ሚካኤል
ጅሩ ሞቶሎኒ ቅዱስ ሚካኤል (ጅሩ አርሴማ ውስጥ)
25. መንዝ ይገም ቅዱስ ሚካኤል
መሐል ሜዳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
የሲጠር ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል (መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ)
ወንጪት ቅዱስ ሚካኤል (በነብር የሚጠበቅ)
ሸዋሮቢት ጫሬ ቅዱስ ሚካኤል
30. ወልዲያ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ኮምቦልቻ ቅዱስ ሚካኤል
ደሴ ጢጣ ደብረ ሲና ቅዱስ ሚካኤል
ራያ ቆቦ ቅዱስ ሚካኤል
ደብረ ማርቆስ ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል
35. ደብረ ማርቆስ አጠገብ ብዕርና ቅዱስ ሚካኤል
ደምበጫ ቅዱስ ሚካኤል

መርዓዊ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ባሕር ዳር ድባንቄ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
አዘዞ አይራ ቅዱስ ሚካኤል
40. ዛራ ቅዱስ ሚካኤል (ባሕር ዳር አጠገብ ሐሙሲት)
ጉመር ደብረ ኅሩያን ቅዱስ ሚካኤል
ካምባ ቅዱስ ሚካኤል
ሳንቃ ወይራ ቅዱስ ሚካኤል
ዳስ ዓምባ ቅዱስ ሚካኤል
45. ላሐ ቅዱስ ሚካኤል
46. ጊራራ ቅዱስ ሚካኤል
47. መለኮዛ ቅዱስ ሚካኤል
48. ዋይሎ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል

EOTC ቤተ መጻሕፍት

19 Nov, 09:39


አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 10 ከጉራራ ከፍ ብሎ፤
ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ → ጉራራ፡፡
፲፮. ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሩዋንዳ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ (ቦሌ) → ወረገኑ፡፡
፲፯. ቃሊቲ ሰፈረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ሰፈረ ገነት፡፡
፲፰. ንቡ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሃራብሳ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉ ዲምቱ → ንቡ ሚካኤል፡፡
፲፱. ጀሞ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሜክሲኮ) → ጀሞ፡፡
#እንዲሁም_በአንድነት_በተሠሩ_በሚከተሉት_አብያተ_ክርስቲያናት_ይከበራል፤
፳. ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ጎላ (ኢምግሬሽን ጀርባ)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል (ኢምግሬሽን)፡፡
፳፩. ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ዮሴፍ፥ ደጃዝማች መርዕድ መንገድ፥ ቀለበት መንገድ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ከላጋር (ከፒያሣ) (ከ4 ኪሎ) (ከቦሌ)(ከመገናኛ) → ቃሊቲ መናኸሪያ /በቀለበት መንገድ/
ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/
፳፪. ጀሞ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሜክሲኮ) → ጀሞ፡፡
፳፫. ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያምና ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ሰፈረ ገነት፡፡
፳፬. ኮተቤ ማኅደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሎቄ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሎቄ፡፡
፳፭. ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ለቡ፥ ፉሪ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ለቡ፡፡
፳፮. ቂሊንጦ መካነ ፍስሐ ቅዱስ ሚካኤልና በዓታ ለማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ቂሊንጦ አደባባይ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉዲምቱ፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቂሊንጦ፡፡
፳፯. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ አቃቂ ኬላ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉዲምቱ፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቱሉዲምቱ፡፡
#እንዲሁም_በድርብነት_በሚከተሉት_አብያተ_ክርስቲያናት_ይከበራል፤
፳፰. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ ዐደባባይ፤
ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ → 6 ኪሎ (ማርቆስ)፡፡
፳፱. ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቦሌ በሚል ታክሲ → መስቀል ዐደባባይ፡፡
፴. ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ልደታ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጦር ኃይሎች በሚለው ታክሲ → ልደታ፡፡
፴፩. ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አረዳ ክፍለ ከተማ፥ ሰባራ ባቡር፥ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ (አርበኞች መንገድ)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → በዊንጌት አስኮ /ሩፋኤል ፊንሐስ/ ታክሲ →  ዮሐንስ፡፡
፴፪. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ፥ አራት መንታ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት፡፡
፴፫. ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ልኳንዳ፥ ፈጥኖ ደራሽ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ አጣና ተራ → ልኳንዳ → (በስተግራ ባለው አስፓልት በእግር 5 ደቂቃ ፈጥኖ ደራሽ ማሰልጠኛ)፡፡
፴፬. ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተ ማርያም ወቅድስት ልደታ ወቅድስት አርሴማ ገዳም፤
አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አስኮ፥ ካኦ ጄጄ ዱቄት ፋብሪካ፥ ቃሌ ተራራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → አስኮ፤
፴፭. ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ የሺ ደበሌ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → የሺ ደበሌ፡፡
፴፮. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ፡፡
፴፯. ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና አቡነ ሀብተ ማርያም ቤ/ክ፤

አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ኮተቤ፥ ካራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ኮተቤ (ካራ)
፴፰. ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ቆሬ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → አለም ባንክ → ካራቆሬ (ረጲ)፡፡
፴፱. ፉሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጋራ ኦዳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጋራ ኦዳ፡፡
፵. ሐመረ ወርቅ ማርያምና አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ወርቁ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ወርቁ ሰፈር፡፡
፵፩. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → ሰፈረ ገነት፡፡
፵፪. ቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባና ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቡልቡላ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ሳሪስ አቦ → ቡልቡላ መድኀኔ ዓለም (ኮንዶሚኒየም)→ ወደ ላይ በአስፓልቱ የ5 ደቂቃ የእግር መንግድ፡፡
ወይም፤ ከቦሌ መድኃኔ ዓለም → ቡልቡላ (በአዲሱ መንገድ)
፵፫. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ አቃቂ፥ ጋራው መድኃኔዓለም፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → አቃቂ፡፡
፵፬. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሣሎ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ሣሎ፡፡


ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን #፲፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡

፩. #እየላ_ቅዱስ_ሚካኤል፤ (#የ3 #ሺህ_ዓመታት_ባለታሪክ፤ ከታቦተ ጽዮን ጋራ በ980 ከክ.ል.በ. ታቦቱ የመጣ፤ መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ፤ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መጥቶ የባረከው)
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ግዳን (እየላ)፡፡
፪. ሰሜን ትግራይ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል፤ (መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ)
አድራሻው፤ ሰሜን ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ሰሜን ትግራይ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፫. ጎሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተሠራ)

EOTC ቤተ መጻሕፍት

19 Nov, 09:38


ኅዳር 12 ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ)

በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ በእለተ እሁድ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ሲሆን እርሱም የነገደ ኃይላት አለቃቸው ነው በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የአጋእዝትን ነገድም በአለቅነት ደርቦ የያዘ ሲኾን፡፡ ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት አለቃቸውም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (በዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ 13 (የአእላድ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ምሕረትን የሚለምንበት ነው፡፡
በዚህ ቀን የሚከበረው እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እያመራቸው ማውጣቱን ለማዘከር ነው፡፡
ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ በ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ በ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ ፈርኦን በግብፅ ነገሠ፡፡  እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩ በኋላ ከእብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ እንዲያሳርፉዋት ጠየቀች ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ  አሉዋት፡፡ ከመሐጸኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፡፡ ራሔልም አለቀሰች ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባ የሕዝበ እስራኤል ሁሉ ጩኸት እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) በማድርግ ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ 
ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ ጠላታቸውን የመታላቸውን እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መና ከሰማይ እያወረደላቸው ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ቀኑን በደመና ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጉዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓን ገብተዋል፡፡ /ዘጸ 15/
ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ በረከት ይክፈለን፡፡ 
                            

#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_ #፵፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡

፩. የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (በኦሪት ዘመን መሥዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት የነበረ፥ ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ በ4ኛው ክ/ዘመን በአብሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሾላ መገናኛ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሾላ መገናኛ፤
፪. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ራስ ካሳ ሚካኤል) (ጭቁኑ)፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ራስ ካሳ
ታክሲ፤ ከ4ኪሎ(ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ፡፡
፫. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (አዲሱ ሚካኤል)
አድራሻ፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ አውቶቡስ ተራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4ኪሎ) → አውቶቡስ ተራ፡፡
፬. አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ወህኒ ቤት) (ከርቸሌ)
አድራሻ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፥ ቡልጋርያ (ከርቸሌ) (አፍሪካ ኅብረት)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ቄራ፡፡
፭. ኮተቤ (ሲኤምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲኤምሲ)
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሲኤምሲ፡፡
፮. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ፡፡
፯. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡
፰. ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤተል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → አየር ጤና፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → አለም ባንክ/ኤር ጤና/፡፡
፱. ኤረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ (ፒያሳ) → ጎሮ፡፡
፲. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት አርሴማ ገዳም፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ)(ከአዲሱ ገበያ) → ቀጨኔ፡፡
፲፩. አያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት)
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፥ ጎሮ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ጎሮ፡፡
፲፪. ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል፥ 24ቱ ካህናተ ሰማይና ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ
፲፫. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቦሌ ሚካኤል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቦሌ ሚካኤል፡፡
፲፬. የካ አባዶ ገ/አ/ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ
፲፭. ምሥራቀ ፀሐይ ዳንሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤

EOTC ቤተ መጻሕፍት

18 Nov, 08:14


ወፍም ቤትን አገኘች
                         
Size 16.1MB
Length 46:08

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery

EOTC ቤተ መጻሕፍት

15 Nov, 10:00


🌟

⬇️ይህንን የቤተክርስትያን ቻናል ያውቁታል ?
⬇️ይህ ቻናል ለምን ተመሠረተ?
⬇️ምን ምን ጥቅም አለው?


ይህ ቻናል ለማታውቁት ስሙ ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ይባላል። ይህ ቻናል የተከፈተው ለቤተክርስትያን አስተምህሮ እንዲሁም ለዝማሬ ከዛም በተጨማሪ ለቤተክርስትያን አገልግሎት ለማገዝ ተብሎ የተከፈተ ቻናል ነው። ጥቅሞቹ :-

➡️ የቤተክርስቲያን ጥቅስ
➡️ የቤተክርስትያን ፕሮፋይል
➡️ መዝሙር
➡️ አስተምህሮት ያገኛሉ


ቻናሉን ለመቀላቀል Join❤️‍🔥 ሚለውን ይጫኑ ❗️

EOTC ቤተ መጻሕፍት

15 Nov, 07:51


https://www.youtube.com/live/7lsqNeFUkuM?si=TL9FYOs2TltZRCqC

EOTC ቤተ መጻሕፍት

14 Nov, 16:20


፪. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም_፤
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎጃም (በመርጡለ ማርያም) → መካነ ሰላም ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. ቦሌ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐ ቤቴ ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፡፡

፫. #አምባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም፤
አድራሻው፤ ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ሰቆጣ (ዋግኽምራ)፡፡

፬. #ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ቸቸላ (ሆስፒታል አጠገብ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → ሆስፒታል → ቊስቋም፤

፭. #ደሴ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፡፡

#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፩ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ግብፅ_ቊስቋም _ማርያም_ገዳም_፤
(#እስከ_ቅርብ_ዘመናት_በግብፅ_የኢትዮጵያ_ርስት_የነበረ_)
አድራሻው፤ ግብፅ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብፅ → ገዳመ ቊስቋም፤

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

13 Nov, 13:34


ታላላቅ ሥራን አድርጎልኛልና 
                                                  
Size:- 102MB
Length:-1:33:17
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

11 Nov, 18:24


የወይን ባለቤት 
                                                  
Size:- 72MB
Length:-1:18:41
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

08 Nov, 19:37


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

EOTC ቤተ መጻሕፍት

08 Nov, 19:12


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

EOTC ቤተ መጻሕፍት

08 Nov, 14:54


ስህተቱ በግዴለሽነት መቅረቡ ነው!

በዘመነ ሐዋርያት በጣም አስቸጋሪና ፈታኝ ከነበሩት ነገሮች መካከል በቋንቋ፤ በባህል፣ በአመጋገብና በአኗኗር እንዲሁም በሥርዓት የማይገናኙ ቤተ አይሁድንና ቤተ አሕዛብን አንድ አድርጎና አጣጥሞ ለመኖር መቸገር ነበር ይህም በሌላው አማኝ ብቻ ሳይሆን በአገልጋዮች ሐዋርያት መካከል ሳይቀር ውዝግብና መለያየት እስከመፍጠር ደርሶ እንደነበረ ታሪክ ያስረዳል ከዚህም አልፎ አንድ ሲኖዶሳዊ ስብሰባ አስፈልጎት በስብሰባ ውሳኔ አግኚቷል
ዛሬም የይሁዲነት ጽንፍ የያዙ የሚመስሉ ሁሉን ካልተጸየፍንና ካላወገዝን የሚሉና ሁሉን ካላደረግን የሚሉ ለአሕዛብነት ጽንፍ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ብቅ ብቅ እያሉ ነው

የሐዋ 10:11,ላይ እንደተጻፈው ለቅዱስ ጴጥሮስ ባየው ራእይ ልዩ ልዩ እንስሳትና አራዊት በተዘረጋ ሸማ ወርደው ታዩትና አርደህ ብላ ሲባል የሚያረክስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም በማለት መልስ ሲሰጥ እግዚአብሔር የቀደሰውን አታርክስ የሚል መልስ ተሰጥቶታል ምሥጢሩ አራዊታዊ ና እንስሳዊ ግብር ሳይቀር የበረታባቸውን አሕዛብን ሁሉ ወደ ክርስትና ለመጥራት የሚገልጽ ቢሆንም ፍጥረታቱ የረከሱ አለመሆናቸውንና እንዳልተከለከሉ ግን ያስረዳል
ነገር ግን ደግሞ ጴጥሮስ አለመብላቱ አእምሯችን ያልፈቀደነውን ነገር የግድ መብላትም እንደሌለብን ያሳያል
ከዚህም አልፈው እንኳን እንደ አሕዛብ መብላት ይቅርና ከአሕዛብ ጋር አብሮ መመገብ ሳይቀር እንደ መርከስ የሚቆጥሩ ስለነበሩ ቅዱስ ጴጥሮስ አይሁድ አዩኝ አላዩኝ ብሎ አብሯቸው ለመብላት ይቸገር ነበርና ቅዱስ ጳውሎስ በአደባባይ እንደወቀሰው በመልእክቱ ሳይቀር ገልጾታል ገላ 2:11 ይህንንም በአመጋገባቸው አሕዛብን መንቀፍ ግብዝነት ተብሎ ተጠርቷል

በኋላ ግን በኢየሩሳሌም በመጀመሪያው የሲኖዶስ ውሳኔ መፍትሔ ስለተሰጠበት አልፎ አልፎ ቢታይም የማኅበር ፈተና መሆኑ ግን ቀንሷል
በመጀመሪያው የሲኖዶስ ጉባኤ ከተወሰኑት ነገሮች መካከል በአመጋገብ ዙሪያ ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የመጡ ክርስቲያኖች ከጣዖት ከተሠዋ ምግብ እንዲርቁ የሞተና ደም አንቆት የሞተን እንስሳ እንዳይበሉ እንጂ ስለ ሌላ የምግብ ክልከላ መመሪያ አልተጻፈም ከቤተ አይሁድ የመጡት ግን በአመጋገብ ዙሪያ በኖሩበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል እንጂ እንደ አህዛብ እንዲበሉ አልተገደዱም የሐዋ 15:28
ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊት እናት እንደመሆንዋ መጠን የምንመገበውን መንፈሳዊ ምግብ ትመርጥልናለች እንጂ ሥጋዊ ምግቡንማ ለጸሎትና ለጾም ከምንተጋበት ሰዓት ውጪ ደስ ያለንንና አእምሯችን የተቀበለውን የሚጠቅመንንና ጉዳትም የማያስከትለውን ሁሉ እንድንበላ ፈቅዳልናለች

ብዙ ቤተ አሕዛብና ቤተ አይሁድ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል እንደ ሮሜና እንደ ቆሮንቶስ ላሉ ከተሞች ቅዱስ ጳውሎስ በአመጋገብ ጉዳይ ሁለቱን ለማስማማት እጅግ በጥንቃቄ ጽፎላቸዋል ሮሜ 14:17-23፣ 1ቆሮ 6:12፣ 10:23፣ ቲቶ 1:15 ገላ 2:11 ስለ አመጋገብ ሁሉ እንደተፈቀደልን ይገልጽና ነገር ግን ስለ ሁለት ነገር ደግሞ መከልከል እንዳለብን ያስረዳል
የመጀመሪያው ከአእምሮ የተነሣ ለአእምሯችን የሚመች መስሎ ካልታየን መተው እንደሚገባንና አለመብላት እንደሚሻል
ሁለተኛው በእኛ ምክንያት ሰዎች የሚሰናከሉ ከሆነ ደግሞ መተው እንዳለብን ይጠቅሳል

🤔,በሚበሉ እንስሳት መካከልም ሰሞኑን በእግረኛው ሚዲያ የቀረበው ጉዳይ ንግግሩ ምንም ስህተት ሳይኖርበት የአቀራረብ ስህተትና ግዴለሽነት ግን አለበት
ሁላችንም እንደምናውቀው የመጀመሪያ የጉባኤ ቤትም ሆነ የኮሌጅ ክርክሮቻችን ከሚባሉት ነገሮች አንዱ ይህ የምግብ ጉዳይ ሲሆን ታላላቅ መምህራን ግን ጥንቃቄና ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መልስ ይሰጡበት ነበር
ዛሬ ይሄንን እረስተው ሊቀ ጳጳሱን ጀግና እያሉ የሚያሞጋግሱ ኃላፊነት የሌለበት መልስ መሆኑን የዘነጉና ሌሎች ደግሞ እንደ ትልቅ ክህደት ቆጥረው ሊቀ ጳጳሱ ላይ የትችት ውርጅብኝ የሚያቀርቡ አሉ
ቤተ ክርስቲያን አኃቲ ናት ማለት ሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት ናቸው ማለት አመጋገባቸው ሁሉ እንደ እኛ ሆኖ ይመስለናል እንዴ?
ቻይናዊው ጃፓናዊው አሜሪካዊው አውሮፓዊው አረቡ አፍሪካዊው ወደ ኦርቶዶክስ ገባ ሲባል አመጋገቡን ሁሉ ቀይሮ ይመስለናል እንዴ? አይደለም እኮ
ነገር ግን እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን ልክ እንደ አይሁድ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ቀጥታ ስለተሸጋገርን ልክ እንደ አይሁድ የአመጋገብ ሥርዓታችንም ከተፈጥሮ ሕግ ጋር የተስማማ ነውና ከባህል ከማንነት ከትላንት ታሪክ አንጻር ብዙዎችን አንመገብም የማንመገበው የረከሱ ናቸው ብለን ሳይሆን በባህልም በሥርዓትም ሳንመገባቸው ስለኖርን አእምሯችን ስለማይቀበላቸውም ነው

እንደ እኔ እንደ እኔ እዚህ ሚዲያ ላይም ጠያቂውም ሆነ መላሹ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለምዕመኑ እንዴት ይረዳዋል የሚል ኃላፊነትን ያልተላበሰ ጥያቄና መልስ ነው የተካሄደው
ጥያቄው የሕዝብ ነው ወይ?
ምን ምን እንብላ ብሎ የጠየቀ አለ ወይ?
ተፈቅዷል መባልስ ለምን ጉዳይ ነው? የሚሉትን ሳያካትት ቀጥታ ደረቅ ጥያቄና መልስ ስለሆነ እንጂ ፕሮግራሙ ጥፋት የለበትም
እኛ ኢትዮጵያውያን በባህላችን በሥርዓታችን ያልተለመደ ነገር መብላት የሌለብን እርኩስ ስለሆነና ኃጢያትም ስለሆነ ሳይሆን በሥርዓት እጅግ ያሸበረቅን ልክ እንደ አይሁድ የኦሪት መሠረት ያለን ባህላችንም የማይፈቅደው አእምሯችንም የማይቀበለው ስለሆነ ያልተለመዱትን ብንበላ
አንደኛ ለሌሎች እንቅፋት እንሆናለን
ሁለተኛ ለሌላ የግዴለሽነት ኃጢያት እንገፋፋለን
ሦስተኛ አእምሯችን የማይቀበለው ነገር ስለሆነ አእምሯችን የማይቀበለውን ነገር በማድረጋችን የመበደልና የመርከስ ስሜት ስለሚፈጠር ከዚህም የተነሣ እንዳንበላ ይመከራል እንጂ ብዙ በሀገራችን የማንበላቸው ነገሮች የማይበሉት ሕገ ወንጌል ከልክሎና ቤተ ክርስቲያንም አትብሉ ብላን አይደለም ይህም ሊታወቅ ከኦርቶዶክሳውያን ውጪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ አልፎ አልፎ የተወሰኑትን ካልሆነ በስተቀር ይህንን ሲያደርጉት አይታይምና
ሊቀ ጳጳሱም ሆነ ጠያቂው እንደ እውቀት ትክክል ቢሆኑም እንደ ኃላፊነት ግን አጀንዳ እየፈጠሩ ለሌሎች ነገሮች በር ከመክፈት ይልቅ በቁዔት ያለውና ኃላፊነት የሚሰማው ንግግር አላደረጉምና ቢያስወቅስ እንጂ የሚያስመሰግን ሥራ አይመስለኝም
በመሠረቱ የልጁ ጥያቄ መንገድ የሚያስት ቢሆንም ሊቀ ጳጳሱ በተረጋጋ ስሜትና በአባታዊ ጥበብ መልስ እየሰጡ ነበር የእንስሳትን ዝርዝር እየጠራ ሲናገር እርሳቸውም በቁጥብነት እንዴት እንደመለሱ በጣም ገርሞኛል ከዚያ በተረፈ ሊቀ ጳጳሱ ላይ ሌላ ቅሬታ ካለን በሌላ ነገር መውቀስ እንጂ እዚህ ላይ ግን ከክርስትናው አስተምህሮ የተንሸራተቱበትም ሆነ ያጠፉት ጥፋት አይታየኝም ጥያቄውን በተጻፈው የመጽሐፍ ቃል ልክ መልሰውታል እንደ ሚዲያ ግን ለሕዝብ መገለጽና መተንተን ባለበት ልክ የተተነተነና የቀረበ አይመስለኝም ይህ ደግሞ አጠቃላይ የኦርቶዶክሳውያን ባለ ሚዲያዎች ሁሉ የሚመስል ችግር ነው አጀንዳ መምዘዝና ብዙ ሰው ፕሮግራሙን እንዲያደምጠው ለማድረግ ከማሰብ የዘለለ ብዙ ሰው ይማርበታል ወይ የሚል የኃላፊነት ስሜት ብዙም አይታይባቸውም።
ወቀሳውም ቢሆን ያን ያህል አጀንዳ ለመሆንም አያበቃምና ነገሩን ከልኩ በላይ አናስጩኸው እላለሁ።

መ/ር ዘላለም

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

04 Nov, 20:19


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

EOTC ቤተ መጻሕፍት

04 Nov, 20:12


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

EOTC ቤተ መጻሕፍት

04 Nov, 17:47


ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥቅምት ፳፯
በዓለ መድኀኔዓለም ወመብዓ ጽዮን

ልዩ አዋጅ ዘጥቅምት መድኀኔዓለም

የጥቅምት መድኀኔዓለም የማኅሌቱ ሥርዐት ‹‹የመልክአ መድኀኔዓለምን›› እና ‹‹የመልክአ መስቀልን›› የሚከተል ነው፡፡

‹‹የመልክአ መድኀኔዓለም››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘአዲስ አበባ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የሚለውን እንዲከተሉ፤

‹‹የመልክአ መስቀል››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም›› የሚለውን እንዲከተሉ እናሳስባለን፡፡

✤ መልካም በዓል ✤
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

01 Nov, 05:13


የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን
አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
2. በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
4. የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆነ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ
ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
6. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ
ያሳስባል፡፡
7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኀበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery

EOTC ቤተ መጻሕፍት

01 Nov, 05:12


#ቅዱስሲኖዶስ

" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ 

ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "


(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)

/ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል /

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

29 Oct, 16:54


💰ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ

አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
                 👇👇

EOTC ቤተ መጻሕፍት

29 Oct, 16:35


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

EOTC ቤተ መጻሕፍት

29 Oct, 16:18


ታርቀን እናስታጉለው!

በአንድ ትልቅ ደብር ላይ የእርስ በርስ የካህናት ቅራኔ ይፈጠርና ጠቡ እየሰፋ ሄዶ ብዙዎቹ ይኮራረፋሉ
ይህን የተረዱት የደብሩ አስተዳዳሪም ካህናቱን በሙሉ ሰብስበው ለማስታረቅ ስብሰባ ያደርጋሉ
የተጣሉበት ነገር ሲነሣ ነገሩ ነገር እየወለደ ለእርቅ የተጠራው ስብሰባ የጠብ እስኪመስል ድረስ ሁሉም ተበደልሁ የሚል ስለሆነ አጀንዳው እየሰፋ ሄዶ የቅዳሴ ሰዓት ይደርሳል

በዚህ ሰዓት የደብሩ ቄሰ ገበዝ ይነሣና አሁን የቅዳሴ ሰዓት ስለደረሰ ምዕመናኑም ወደ ቤተ መቅደስ እየገቡ ስለሆነ የእርቁን ስብሰባ ለሌላ ቀን እናድርገውና አሁን ወደ ቅዳሴው እንግባ የሚል ሐሳብ ያቀርባል

አብዛኞቹም እሺ እንደሱ ይሻላል በማለት ሐሳቡን ደገፉት
አስተዳዳሪው ግን እውነተኛ አስተዋይ አስተዳዳሪ ነበሩና
አይ ሊቃውንት በፍጹም ይህንን የእርቅ ስብሰባ አቋርጠን ቅዳሴ አንገባም እንዲህ ተጣልተን ከምንቀድስ እኛ ታርቀን ቅዳሴውን እናስታጉለው
እኛ ተስማምተንና ተፋቅረን ቅዳሴው ይቅር ምዕመናን ለምን ቅዳሴ ታጎለ ብለው ከጠየቁን ታርቀን ነው በሏቸው ብለው ለእርቅ ያላቸውን የጸና አቋም አቀረቡ

😍ይህ ንግግር የሁሉንም ኅሊና ነካቸውና ያዙኝ ልቀቁኝ ተበድያለሁ የሚል ካህን ሁሉ እየተነሣ አስቀየመኝ ባለው ካህን ፊት እየወደቀ ማረኝ መባባል ጀመረ
5 ሰዓት የፈጀው የእርቅ ጭቅጭቅ በ5 ደቂቃ ብቻ ፍጻሜውን አገኘ ይባላል

አስተዳዳሪው እውነታቸውን ነው ተኮራርፈን ከምንሰብክ ተቀያይመን ከምንፈምር የጎሪጥ እየተያየን ከምንጸልይ እየተፎካከርን ከምንጸነጽል ታርቀን ብናስታጉለው ይሻል ነበር

ቤተ ክርስቲያኗን የፍቅር አውድማ መሆኗ እስኪያጠራጥር ድረስ በመለያየት የተለከፍነው ሁሉ ምነው እንደነዚያ አስተዳዳሪ ሁሉን ከእርቅ ብንጀምረው ምናችን ይጎዳል!

ይቅር በሉን ብንባባል ምን ይቀነስብናል!

የትኛውንም አገልግሎት በእርቅ ካልጀመርነው መሪ እቅድ ተዘረጋ፣ ማኅበር ተቋቋመ፣ የተማረ ሰው ተሾመ፣ በቋንቋ ተሰበከ፣ ወዘተ መዳረሻው ወደ ላይ ሳይሆን ወደ ታች ነው።

ወደ አባቶች የምክር ጠጠር መወርወር ድፍረት ቢሆንብኝም የቅዱስ ሲኖዶስ እቅዶችና አጀንዳዎች ሁሉ በመስማማት አሸናፊና ተሸናፊ ሳይኖር በፍቅርና በመተራረም ካልሆነ በስተቀር ያው ተኮራርፎ መቀደስን እንደመምረጥ ነው የሚሆነውና ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ በዚህ ጉዳይ ላንለያይና ላንወቃቀስ ስህተቱንና ክፍተቱን ተረድተን ተዋደንና ተስማምተን በፍቅር ቋጭተነዋል የሚል የምሥራች ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ ነው።

ይመስለኛል የሁሉም አማኝና አገልጋይ ምኞት ሲኖዶሳዊ ውሳኔዎችን ከመስማት ሁሉ በላይ የአባቶች አንድነትና ፍቅር ነው የሚያስጨንቀው
ፍቅርና አንድነት፣ ትህትናና መከባበር ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ ናቸውና እግዚአብሔር የአንድነትና የፍቅር ዘመንን ያሳየን

እኛም ምዕመናንና አገልጋዮች ሁላችንም አባቶቻችን የሁላችንም እኩል አባት ናቸውና የየትኛውም አባት ክብር የእኛ ክብር ነው የማንም አባት መነቀፍና መዘለፍ የእኛ ውርደት ስለሆነ በአባቶች መካከል አንዱን ከመውቀስና ሌላውን ከማንገሥ በአንዱ ከመፍረድና በሌላው ከመደሰት ተቆጥበን አንድነታቸውን እየናፈቅንና እየተመኘን ስለ አንድነታቸውና ስለ ፍቅራቸው እንጸልይ።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

28 Oct, 18:02


📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE

EOTC ቤተ መጻሕፍት

25 Oct, 20:15


ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???

EOTC ቤተ መጻሕፍት

25 Oct, 19:50


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

EOTC ቤተ መጻሕፍት

25 Oct, 15:53


ዘጥቅምት ፲፯፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፩ኛ ዙር ዓመት፤  ፬ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲፯)
በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት፤ ወቅዱስ ፊልጶስ ሰማዕት፤ ወዕረፍቱ ለአቡነ ዲዮስቆሮስ ካልዕ፤ ወልደታ ለቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል፤ ወዕረፍቱ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ እኁኁ ለቅዱስ ባስልዮስ።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

25 Oct, 12:15


በትግራይ ክልል የሚገኙ የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ !


ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከትን ሲመመሩ የነበሩት የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ" የተባለው ሕገወጡ "ቤተ ክህነት" ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታውቋል።


በትግራይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እና ገዳማትን በሕገወጥ መልኩ ተቆጣጥሮ የሚገኘው ይኸው ቡድን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከባድ "የቀኖና" እርምጃ እወስዳለሁ ሲል መዛቱንም ከተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ታውቋል።


የትግራይን ሕዝብ ለፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ይህ ቡድን አሁንም በጥፋት ሥራዎቹ የቀጠለ ሲሆን በ"ሕገ ቤተ ክርስቲያን" ስም አንድ ሰነድ ማጽደቁ ነው የተገለጸው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እስከ አሁን የተባለ ነገር ባይኖርም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር።

ዘገባውን ለማሰናዳት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ተጠቅመናል።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

22 Oct, 14:17


ስለጠባይና ስለቅንነቱ እጅግ አድርጐ ወደደው፡፡ ከዚያም አስኬማው ወይም ቆቡ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ አመነኰሰው፤ ስሙንም ዘሚካኤል ብሎ ጠራው፤ በዚህ ጊዜ እድሜው 14 ዓመት ነበር፡፡
አባ ዘሚካኤል አስኬማ ካደረገ በኋላም በታላቅ ትጋቱ በጸሎቱና በጾሙ አባ ጳኵሚስ ተደነቀ፡፡ ስለሱም ዝናው በየሀገሩ ሁሉ እስከ አባቱ አገር ሮም ድረስ ተሰማ፡፡ አባ ዘሚካኤል ገና በሕፃንነቱ የምንኵስና ማዕረግ መቀበሉን ከሰሙ በኋላ ወደ እሱም 8 ቅዱሳን የመጡ ነበሩ፡፡ እነሱም፦ አባ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ፣ አባ ይምዓታ ከሀገረ ቁስያ፣ አባ ገሪማ ከሮም፣ ከአንፆኪያ አባ ድሕማ፣ ከቂልቅያ አባ ጉባ፣ ከእስያ አባ አፍጼ፣ ከሮሚያ አባ ጴንጠሌዎን፣ ከቂሳርያ አባ አሌፍ ነበሩ፡፡ እነሱም አባ ጳኵሚስ የምንኵስናውን አፅፍ አጐናፀፏቸውና አመነኮሷቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸውም ስማቸውን ሰየሟቸው፡፡ እኒህም አባቶች ስለትዕግስት፣ አርምሞ፣ ትህትና፣ ስለሥርዐተ ማኀበር አመሠራረት ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ ተማሩ፡፡
    ከዚህ በኋላ በዚያ ገዳም ለብዙ ዓመታት በፍቅር በአንድነት ከአባ ቴዎድሮስ ጋር ተቀመጡ፡፡ በዚህን ጊዜ ግን አባ ጳኩሚስ አርፈው አባ ቴዎድሮስ ተተክተው ነበር፡፡ እነዚህም አባቶች ወደየሃገራቸው ሄደው ማስተማርና ሃይማኖትን ማስፋፋት እንዳለባቸው ተስማምተው ወደየሀገራቸው ተመለሡ፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን በዚያው ቆየ፡፡ እሱ ልቡን የነካችዉ ዜናዋንም የሰማላት ሃገር ነበረችና፡፡ ይህቺውም ሃገራችን ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ እሱም ማንም ሰው ሳያውቅና ሳያየው ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መጥተው ጐብኝተዋታል፡፡ ያለመምህራንና ያለአስተማሪ ያመነች የዚህችን ሀገረ እምነቷንና ሥነስርዐቷን ተመልክቶ ተደነቀ፡፡ እነዚያን 8 መነኰሳትም ከያሉበት ስለሃገሪቷ እየነገረ ጠራቸው የሚገርመው ግን እነሱም ስለዚህች ሀገር እንደሰሙ ያለምንም ማመንታት መጥተዋል፡፡ እነሱም ሕዝቡን እንደሰሙት አገኙት፡፡ አባ ዘሚካኤል አቡነ አረጋዊ የሚለውን ስያሜ ያገኙት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ትህትናቸውና ታዛዥነታቸው እሳቸው ሲመነኩሱ ገና ሕፃን ነበሩ ስራቸው ግን የአረጋውያን ነበርና አንተስ ሐፃን አይደለህም የልጅ አዋቂ ነህ ሲሉ አረጋዊ አሏቸው፡፡
አቡነ አረጋዊ በኢትዮጵያ ሲኖሩ በሄዱበት ስፍራ ብቻቸውን የሚፀልዩበትን ቦታ ሁል ጊዜ ይፈልጉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም በመንገድ እየሄዱ ሳሉ ትልቅ ተራራን (ደብረ ዳሞን) ተመለከቱ፤ ከሦስተኛው ቀን በኃላም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ‹‹አንተ እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቀሃል›› አለው፡፡ አባታችንም አቡነ አረጋዊም ‹‹ከዚህች ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጥያቴ እናዘዝና እለማመን ስለበደሌም ይቅርታን እጠይቅ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም እንዲፀልይና ታላቅ ዘንዶም ወደርሱ እንደሚላክለት ነገረው፡፡ በሦስት ሰዓትም ዘንዶው መጣ፤ አባታችንም የዘንዶውን ጅራት ይዘው ወደላይ ወጡ ብቻቸውን አልነበሩም፡፡ ዘንዶው እንዳያስደነግጣቸውና እንዳይጐዳቸው ሰይፍን ይዞ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቃቸው ነበር እንጂ፡፡
አባታችን አቡነ አረጋዊም የእርጅና ዘመናቸው በደረሠ ጊዜ እግዚአብሔር ወደእርሱ በመንፈቀሌሊት ተገልጾ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይኸውም ‹‹መታሰቢያህን ያደርግ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ቧለሟልነትን እሰጠዋለሁ፤ በእውነተኛ ሀይማኖት ሁሉ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፤ ያጻፈ፤ የተረጐመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፤ ይህ ሁሉ ላደረገም እስከ 14 ትውልድ ድረስ እምርልሀለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አልሞተም በዓመቱ "ሞትን የማይቀምሱ አሉ፡፡" ብሎ እንደተናገረው /ማቴ 16 ፥ 28/ ጥቅምት 14 ቀን 558 ዓ/ም ተሠውረዋል፡፡ ከጻድቁ አባት በረከት ይክፈለን፤ በቃልኪዳናቸው ይጠብቀን፤ አሜን፡፡

**#ቅዱስ_ሙሴ_ብእሴ_እግዚአብሔር_በዓለ_ዕረፍታቸው_፡፡
ታሪኩ ከሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስና ከቅዱስ ቶማስ ዘቶርማቅ ጋር ተመሳሳይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለ የቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

EOTC ቤተ መጻሕፍት

22 Oct, 14:16


#ጥቅምት_14፤ ** #ቅዱስ_ገብረክርሰቶስ_(#አብደል_መሲህ_) #በዓለ_እረፍቱ_፤

በጎ ሥራን ከሚሠሩ፤ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ  ከቊስጥንጥንያው ንጉሥ ቴዎዶስዮስና ከመርኬዛ ልጅ የላቸውም ነበርና ኢየሩሳሌም ድረስ ሂደው በስዕለት ያገኙት ታላቅ አባት ነው፡፡ ስሙንም ቤተሰቡ አብደል መሲህ ብለው ሰየሙት፤ (አብደል ማለት አገልጋይ ማለት ሲሆን መሲህ ማለት ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜውም ገብረ ክርስቶስ (የክርስቶስ ሥራ) ማለት ነው፡፡
      እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስቲያንንና ሥጋዊ ትምህርትን አስተማሩት፤ አድጎም በጎለመሰ ጊዜ የሮሜውን ንጉስ ልጅ አጭተው እንደሥርዓቱ አጋቡት። እሱ ግን በምድራዊ ሕይወት ከመደሰት ይልቅ በሰማይ ስለሚያገኘው ነገር አብዝቶ ይናፍቅ ነበርና በጋብቻ ከመኖር ይልቅ ምንኵስናን ይወድ ነበርና በሰርጉ ዕለትም እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ  ሙሽራው ገብረክርስቶስ ተነስቶ ወደ ሙሽራይቱ ሔዶ እጇንም ይዞ ከእርሷ ጋር ቃልኪዳን አደረገ፤ ከዚያም የሃይማኖት ጸሎትን አድርሶ ለእርሷም ምን አይነት ሕይወት መኖር እንደሚፈልግ አስረድቷት የተሞሸረበትን ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለብሶ ለመሄድ ተነሳ፡፡ ሙሽራይቱም ‹‹እኔን ለማን ትተወኛለህ?›› ብላ አልቅሳ ጠየቀችው፡፡ እርሱም ‹‹በእግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ፤ እኔም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ፤ የአባቴ መንግስት ኃላፊ ነውና፡፡ አንቺም መሀላሽን አስቢ፡፡›› አላት፡፡ ያን ጊዜ መሃላዋን አስባ ዝም አለች።
      ከቤቱ ተነስቶ ወጣ፤ በመርከብ ከሚጓዙ መንገደኞች ጋር ያመት መንገድም ወደሚሆን አርመንያም ተጓዘ።
     በነጋም ሰዓት አባትና እናቱ ሙሽራው ልጃቸውን ለማግኘት ወደ ሰርጉ አዳራሽ ገቡ፤ እንዳሰቡት ግን ሙሽራው ልጃቸውን አላገኙትም፤ ይልቁንም ሙሽሪቷን እያለቀሰች አገኟት እንጂ፡፡ እነሱም አጥብቀው በጠየቋት ሰዓት መሐላን አስምሏት በሌሊት እንደሄደ ነገረቻቸው፤ ታላቅ ለቅሶን አለቀሱ። ይፈልጉት ዘንድም ንጉሥ አባቱ አምስት መቶ አገልጋዮችን ላከ፡፡ ለድሆችና ለምስኪኖችም ምጽዋት ያደርጉ ዘንድ ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው ገብረክርስቶስ ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራች አርመንያ ሀገር በምትገኝ በአንዲት ቤተክርስቲያን ደጅ መኖር ጀምሮ ነበር፡፡      
አባቱ የላካቸው ሁለቱ አገልጋዮችም ከዚያ ደርሰው ስለርሱ መርምረው ነበር፤ ወሬውን ግን ማግኘት ተሳናቸው፡፡ ለድሆችም ምጽዋትን ተቀብሏል ግን እንደማንኛውም የኔቢጤ ስለመሰላቸው ማወቅ ተስኗቸው ነበር፡፡ በዚህችም ቦታ ማንም እሱ የንጉሥ ልጅ፤ ቅዱስ መሆኑን ሳያውቅ 15 ዓመት ኖረ፡፡                           
      እመቤታችን ለአንድ ቄስ ተገልጻ ገብረ ክርስቶስን ወደ ቤ/ን ያስገባው ዘንድ አዘዘች፤ ገብረክ ርስቶስም ይህን ባወቀ ጊዜ በሌሊት ተነስቶ በእመቤታችን ስዕል ፊት ‹‹እመቤቴ ሆይ የተሰወረ ሥራዬን አንቺ ለምን ገለጥሽ አሁንም ወደ ሚሻለኝ ምሪኝ›› ብሎ ስዕሏን ተሳልሞ በሌሊት ወጥቶ ወደ ባህሩ ወደብ ደረሰ፡፡
    ወደሌላ ሃገርም ሊሄድ ወዶ በመርከብ ተሳፈረ ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ከአባቱ አገር ደረሰ እሱም እናትና አባቴ ለኔ የፈለጉትን እየሰጡኝ ለነሱ ምጽዋት ይሆንላቸው ዘንድ በደጃቸው ልኑር ብሎ በፈቃዱ ወደ እነርሱ ሄደ፡፡ የእነርሱን መዳን ሽቷልና ፊቱ በጣም ተለውጧልና ከቤተሰቦቹም ይሁን ከገረዶቻቸው መሃል ማንም ያወቀው አልነበረም ከውሾቹ በቀር፡፡ ለአባቱም እኔ መጻተኛ ነኝና በቤተ መንገሥትህ ደጅ ፊት ለፊት እንዳትረሳኝ ጎጆ ሥራልኝና ልኑር አለው፤ አባቱም የልጁን ኹኔታ አስቦ እኔም ልጄ እንዲሁ አይደል ብሎ ፈቀደለትና መኖር ጀመረ፡፡ የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎችና እንዲንከባከቡት የታዘዙት ሠራተኞች ግን ሲገቡና ሲወጡ ሽታው እንዳያስጨንቀን ይህን ምስኪን አስውግዱልን እያሉ ወጭትና ድስትም እያጠቡ በላዩ ይደፉበት ነበር፡፡ ውሾችም እንዲናከሱበትና እንዲበሉት የሥጋ ትርፍራፊ ይጥሉበት ነበር፡፡ ውሾች ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር፡፡
ቅዱስ አባ ገብረ ክርስቶስም ጊዜ እየረዘመ በሄደ ጊዜ የባሮቹ በደል እየበዛ ሲመጣ (መቋቋም ስላቃተው ሳይሆን ለእነሱ በደል እንዳይሆንባቸው ሲል) ወደ እግዚአብሔር ይወስደው ዘንድ ለመነ፡፡ ከዚያም ታሪኩን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻው ጽፎ በእጁ ይዟት አረፈ፤ የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ፈጣሪም እንደፈለገ ነፍሱን ከሥጋው ለየለት፡፡ ለሱም ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ የዕረፍት ቀኑም እሑድ ነበርና ሕዝቡ ሁሉና ካህናቱ ከሊቀጳጳሳቱ ጋር በቅዳሴ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሳሉ ‹የእግዚአብሔርን ሰው በንጉሡ በቴዎዶስዮስ ቤት ፈልጉት› የሚል ቃል ከሰማይ ሰሙ በዚያን ጊዜ ሂደው በአረፈበት ቦታ አገኙት፡፡ በእጁም ውስጥ የተጨበጠ ክርታስን አዩ፡፡ ሊወስዷትም ሽተው መውሰድ ተሳናቸው በአንድነትም በጸለዩ ጊዜ እጁ ተፈትታ ወስደው አነበቧት፡፡ አባትና እናቱም ልጃቸው እንደሆነ አወቁ ታላቅ ጩኸትም ሆነ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ አክብረውም በጥምቀት 14 በእረፍቱ ቀን ቀበሩት መቃብሩም በሽተኞችን ሁሉ በመፈወስ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተዓምራቶችን የሚያደርግ ሆነ ከጻድቁ ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡

፠*፠ #አቡነ_አረጋዊ ፠*፠ (#ዘሚካኤል)#ወቅዱስ_ሙሴ_ብእሴ_እግዚአብሔር
#አቡነ_አረጋዊ (#ዘሚካኤል)

ትውልዳቸው ሮም ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከአባታቸው ይስሐቅና ከእናቸው እድና  የተገኙ የቅዱሳን ፍሬ ናቸው፤ ወንድሞቹም ቴዎድሮስ እና ገብረ አምላክ ይባላሉ፡፡ የቀድሞው ስማቸው ዘሚካኤል ነበር፡፡ “አረጋዊ” የተባሉት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ነው፡፡ በእድሜ ልጅ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና ሥራቸው አዋቂ ስለነበሩ አረጋዊ ብለዋቸዋል፡፡
ወላጆቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፤ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እየጸናና እየበረታ ሄደ፡፡ ዕለት ዕለት ጧትና ማታም ወደቤተክርስቲያን እየሄደ ጸሎት ከመጸለይ አያቋርጥም ነበር፡፡
እድሜውም ለጋብቻ ሲደርስ አባትና አናቱ ያገባ ዘንድ ሚስት አጩለት፡፡ እሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ እየተቃኘ የምንኵስና ሕይወትን ለመኖር ፈልጓልና፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የምንኵንስና ሕይወትን ለመኖር ወደ አባ ጳኩሚስ ዘንድ ሄደ፤ ወደ ገዳሙም በገባ ጊዜ አንድ መነኵሴ አገኙትና ‹‹ልጄ ሆይ ከወዴት መጥተሃል እነሆ አንተ ሕፃን እንደሆንክ እመለከታለሁና›› አሉት፡፡ እሱም አመጣጡ ከሮም እንደሆነና ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ የሚፈልገው ነገር እንዳለ ነገራቸው፡፡ እሳቸውም ነገሩን ከሰሙ በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ዘንድ ወሰዱት፡፡
አባ ጳኩሚስም በአየው ጊዜ ከመንበሩ ተነስቶ  በፍፁም ፍቅር አቅፎ ሳመው የእግዚአብሔር ጸጋ በእሱ ላይ አድሯልና፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ስለምን ጉዳይ ወደ እሱ እንደመጣ ጠየቀው፡፡ አባ ዘሚካኤልም ‹‹እንደአንተ እንደ አባቴ መነኵሴ እሆን ዘንድ መጥቻለሁ›› አለው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደመሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኵሰህ ለመኖር እንደምን ይቻልሃል?›› ሲል መለሰለት፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን የምድር መንግሥት ኀላፊ ጠፊ እንደሆነ ያውቃልና ከዓለም ንግሥና ይልቅ ዘለዓለማዊ መንግሥትን ይወርስ ዘንድ እንደሚሻ ያመነኵሰውም ዘንድ አጥብቆ ጠየቀው፡፡ አባ ጳኩሚስም ፈተናን ፈትኖት መቋቋም የሚችል ከሆነ እንደሚያስገባው ነግሮ የተለያዩ ፈተናዎችን ፈትነው፡፡ አባ ዘሚካኤልም የተባለውን የታዘዘውን ሁሉ በትጋት ፈጸመ፡፡ አባ ጳኵሚስም ስለሃይማኖቱ ጽናት

EOTC ቤተ መጻሕፍት

22 Oct, 12:31


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰየመ።

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስአበባ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጥቅምት 2017 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰይሟል።

ምልዓተ ጉባኤው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመክፈቻ መልዕክት ዛሬ ጠዋት መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ከቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት በኋላም የመወያያ አጀንዳ ቀርጸው የሚያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን ነው የሰየመው።

በዚህም መሰረት

1.ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
4.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ (ዘስያትል)
5.ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
6.ብፁዕ አቡነ  ኤጲፋንዮስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ የተመረጡ ሲሆን አጀንዳ የማርቀቅ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚያቀርቡትን ረቂቅ አጀንዳ ከመረመረና ማስተካከያ ካደረገበት በኋላ የጸደቀውን አጀንዳ መሰረት በማድረግ በቅደም ተከተል እየተወያየ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

40,724

subscribers

1,832

photos

79

videos