የተዋሕዶ ፍሬዎች @yetewahedofera Channel on Telegram

የተዋሕዶ ፍሬዎች

@yetewahedofera


Buy ads : here
https://telega.io/c/yetewah
🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
👉 መዝሙር
👉ብሒለ አበው
👉ስብከት
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
🎯የሚለቀቅበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ

የተዋህዶ ፍሬዎች መንፈሳዊ ቻናል
ለአስተያየት 👉 @Teyaka_Lemtykebot
ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ @fikreabe ላይ ያናግሩን

የተዋሕዶ ፍሬዎች (Amharic)

የተዋሕዶ ፍሬዎች በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን የሚለቀቅበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ። የተዋሕዶ ፍሬዎች ይህም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ማሳደጉን እና ለሙሉ ብሒለ አበውን ይዘግዛል። ለማስታወቂያ እና ማስባሪያ ለመረጋጋ ከባድ ትምህርት እስከ @Teyaka_Lemtykebot ዋጋችሁ በማቅረብ የዚህ ቻናልን ተከተሉ። አሁንም እንዲያቀርበን ከ @fikreabe ዳይሬክተገቢ በቀላሉ እናዝናል።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 13:53


+ ንስሐ ግቡ +

የጌታቻን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ አሰቀድሞ በዮሐንስ ለሀጥያት ስርየት ማጥመቅ መንገድ ጠራጊነት የተጀመረ ነው እርሱም እኔስ ለጠጅ ፡ ቢረሌን ፡ ለልብስ ፡ ገላን ፡ እንዲያጥቡለት ፡ ለሱ ፡ ጥምቀት በሚያበቃ ጥምቀት አጠምቃቹሀለው ይል ነበር እንዲሁም እርሱ የሚያጠምቀው ጥምቀት ክርስቶስ ከሚያጠምቀው ጥምቀት ልዩ መሆኑን ሲገልፅ "በመንፈስ : ቅዱስ : እሳትነት" ክፍውን : ሕሊና : ከበጎው : ሕሊና የሚለይበት ስልጣነ ክህነት ገንዘቡ የሚሆንለት በማለት ይገልፃል ። ዮሐንስ ትንቢት የተነገረለት ያለነቀፌታ ይኖሩ ከነበሩ በእግዚአብሔር ፈት ጻድቃን ከነበሩ ከካህኑ ዘካርያስ እና ከኤልሳቤጥ የተወለደ ነው ። በሉቃ 8-11"

***
በእግዚአብሔር ፈት በቤተ መቅደስ ገብቶ የማጠን ተራ በመዓት አንድ ጊዜ የደረሰበት ካህኑ ዘካርያስ በመሰዊያው ቀኝ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ታየው ። ይህም በዓመት አንዴ ሳይሆን አንድ ጊዜ በፈሰሰ ደሙ አለምን የሚያድን አምላክ ሊወለድ መሆኑን ሲነግረው ነው አንድም ካለመታዘዝ ወደ መታዘዝ የሚመልስ ከጣኦት አምላኪነት ወደ እግዚአብሔር አምላኪነት የሚመልስ ልጅ ትወልዳለህ ሲለው ነው በተጨመሪም በቀኝ እጁ አምላክን የሚያጠምቅ ልጅ ትወልዳለህ እያለ መንገሩ ነው ("ጸያሔ ፍኖት" ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ) ።

ለዚህም ነበር በሰፈው ፈት ፃድቃን መስለው ይታዩ ለነበሩት በእግዚአብሔር ፈት ፅድቃቸው ከተመሰከረላቸው ቤተሰብ የተገኘው ዮሐንስ እርሱ በጌታ ፈት ታላቅ የሆነ ሉቃ 1፡15 በህሊና የተሰወረውን ክፍ ግብራቸውን ሳይፈራ እግዚአብሔር ገልጦለት ይገስፃቸው ነበር ፈሪሳውያንን "መልካም ፍሬ የማያፈራ ይጣላል " ማቴ 3-10 እያለ የነብያት ልጆች መሆናቸው ብቻ ንስሃ ካለመግባታቸው የሚመጣባቸውን ቅጣት እንደማያስመልጣቸው ክቡዳነ አእምሮ ለሆኑት ለእነርሱ "ንስሀ ግቡ" እያለ ያስተምራቸው ነበር ። ምንመካባቸው ብዙ የተከማቹ ሀብት ይዘን ሊሆን ይቻላል በዘመንድ ብዛት የእከሌ ዘመድ የእከሌ ዘር እያልን ምንመፃደቅባቸው በሰው ፈት ከሁሉ የተሻልን ለመምሰል የምናቀርባቸው ቁሶች ከመቃብር አይሻገሩም ያለን ግዙፍ ቤት በሁሉ ፈት ለመመካት ይዘነው አንዞርም አንድ ቦታ እንደተተከለ ይቀራል የሰማይ መንግስት እንወርስ ዘንድ ዮሐንስ ዛሬም "እንግዲህ ለንስሐ የሚያበቃቹሁን በጎ ስራ ስሩ" ይለናል " ማቴ 3-8 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል " ጸጋስ ይሉሃል የኃጥያት ስርያት ማግኘት "

እንኳን አደረሳቹሁ ። !!!

(ዲያቆን ፍፁም ከበደ)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:48


አንተኑ ብለው ነው

እንዲወጡ በአዋጅ ፥ ሳይነገራቸው
እንዲህ አድርጉ የሚል ፥ አዛዥ ሳይኖራቸው
በደመራ ዙሪያ ፥ ጧፉን እያበሩ
የመስቀልህን ነገር ፥ በደስታ የሚያከብሩ
አንተኑ ብለው ነው !
ለክብርህ መግለጫ ፥ ለሚወጣው ታቦት
መንገዱን አፅድተው ፥ ፀሐይ ያስመሰሉት
አስፋልቱን በኦሞ ፥ እንደ ልብስ ያጠቡት
አንተኑ ብለው ነው !
የካህናትህ እግር ፥  መሬት እንዳይነካው
በየአደባባዩ ፥ ምንጣፍ ተሸክመው
ሲያነጥፉ የዋሉት ፥ ከፊት ከፊት ቀድመው
አንተኑ ብለው ነው !
በቤተ ክርስቲያን ፥ ስፍራ ባይኖራቸው
የአገልግሎት ድርሻ ፥ ማንም ባይሰጣቸው
ጎዳናውን ሁሉ ፥ እንደ መቅደስ ቆጥረው
ሊያከብሩህ የተነሱ ፥ ጎናቸውን አስረው
ምንም ብንንቃቸው ፥ ባንሰጣቸው ስፍራ
ክደውህ ያልጠፉት ፥ ነፍሳቸው ተማራ
አንተኑ ብለው ነው !

ስለ ቤትህ ሰዎች ፥ ክፉ እየሰሙ
በመናፍቃን ፊት ፥ በእፍረት እየደሙ
ጠብና ግርግር ፥ ሳያሸብራቸው
ፀንተው የተገኙት ፥ እውቀት ሳይኖራቸው
አንተኑ ብለው ነው !
በመናፍቃኑ እየተሰደቡ 
በቅዱሳኑ ስም የተሰበሰቡ
ጽዋ ተሸክመው ፥ በየአደባባዩ
ነቀፋዉን ችለው ፥  በሰው ፊት የታዩ
አንተኑ ብለው ነው !
ሽቱ እንደ ውሃ እያርከፈከፉ
በመቅደስህ አንጻር ፥ በፍቅር የሚደፉ
የቤትህን አፈር ፥ ትቢያ እየላሱ
ዛሬም የትናንቷን ፥ ሃይማኖት ያልረሱ
አንተኑ ብለው ነው !
ማህሌቱን ሳያውቁ ፥ ስርዓቱን ሳይረዱ
በሚያስፈራው ሌሊት ፥ በውርጩ በብርዱ
በገላጣ ሜዳ ፥ ታቦትህን ከበው
በፍቅር የሚያድሩት ፥ ጋቢ ተከናንበው
አንተኑ ብለው ነው !
እረኛ አጣን ብለው ፥ ሮሮ ሳያሰሙ
በበረትህ ያሉትን ፥ ቤትህን ሳያሙ
ማንን እንይ ብለው ሳያጉረመርሙ
ዛሬም በትህትና ፥ መስቀል የሚስሙ
አንተኑ ብለው ነው !

ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ
ሼር ሼር ሼር ይደረግ
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:44


Drshaye Akele:
👉 በዓለ ጥምቀት👈



    👉ጥምቀት_ምንድን_ነው?

          ተወዳጆች የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገረ ጥምቀቱን እንዲህ መናገር እንጀምራለን

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል።

ጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍቺውም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዘፈቅ፣ በተገብሮ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው።

በሌላ አገላለጽ ጥምቀት ማለት በተጸለየበት ወይም በተለየና በከበረ ውኃ (ማየ ገቦ ወይም ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር መጥለቅ፣ መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው። በመሆኑም የምንጠመቅበት ውኃ ተራ ውኃ አይደለም።

ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው።

   💎የጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው

   💎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል።

   💎በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: 📗ማቴ. 3:1📗

ታሪካዊ የጥምቀት በዓል አከባበር በኢትዮጲያ

💧ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን የቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን፣ የሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።

💧በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል።

💧በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

💧ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና እንክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል።

💧የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ።

💧ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ።

💧ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebration በዐዋጅ አስነግረው ነበር።

💧ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ካወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።

💧ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል።

💧በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮

💎ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል። የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል። የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።

💎ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው።

ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው።

እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው።

ኢያሱ የጌታ፣

እስራኤል የምእመናን፣

ዮርዳኖስ የጥምቀት፣

ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው።

ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣

ታቦቱ የጌታችን፣

ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣

ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።

ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል።

‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው።

👉ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ።››።

💎ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው። ከወንዝ ዳር ያለ መጠለ

ያ መዋልና ማደር አይቻልም። በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር። በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ።

💎እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ፈጣሪያችን በዓሉን የበረክት የረድኤት ያድርግልን፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
   ምንጭ ፦ ሥርዓተ ተዋህዶ ርትዕት
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


አዲስ ዝማሬ "ተጠመቀ ኢየሱስ" ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ሞገስ እና ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


#በፍስሐ_ወበሰላም

በፍስሐ ወበሰላም
ወረደ ወልድ ውስተ ምጥማቃት/፪/
#ትርጉም
በደስታና በሰላም እግዚአብሔር ወልድ
ወደ መጠመቂያ ወረደ

#ሥጋ_ሰብእ

ሥጋ ሰብእ መዋቴ(፪)
ወገብረ መንጦላዕተ(፬)
#ትርጉም:-
የሚሞተውን የሰውን ሥጋ
መሠወሪያው አደረገ(ተዋሐደ)

#አስተርአየ_ገሐደ

አስተርአየ ገሐደ አስተርአየ እንዘ ሕፃን
እንዘ ሕፃን ልህቀ(፪)በዮርዳኖስ ተጠምቀ (፪)እንዘ ሕፃን(፪)
#ትርጉም:-
በግልጥ ታየ እንደ ህፃናት ቀስ በቀስ አደገ በዮርዳኖስ ተጠመቀ

#አንሶሰወ

አንሶሰወ/፪/ወአስተርአየ/፪/
በዮርዳኖስ ኧኸ ተጠምቀ በዮሐንስ/፬/
#ትርጉም:-
ተመላላሰ ታየ በዩርዳኖስ ወንዝ
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ


#ነድ_ለማየ_ባሕር

ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ/፪/
ማየ ባሕር ኀበ የሐውር ፀበቦ/፬/
#ትርጉም:-
እሳት የባሕሩን ውሃ ከበበው
ባሕሩም የሚሄድበት ጨነቀው

#ልደቶ_ጥምቀቶ
ልደቶ ጥምቀቶ አስተርእዮቶ ለመድኃኒነ (፪)
እለ ቀደሙነ(፭)መሃሩነ እለ ቀደሙነ(፪)
#ትርጉም፡-
የቀደሙ አባቶቻችን የጌታችንን ልደቱን
ጥምቀቱን መታየቱን/መገለጡን/ አስተማሩን

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


ኦ ክርስቶስ (የጥምቀት መዝሙር) Ethiopian Orthodox Mezmur(ማኅተብ ቲዩብ)

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


✞ጥምቀተ ባሕር✞

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ(፪)
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ(፪)

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዞች ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ
አዝ = = = = =
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
አዝ = = = = =
ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምስጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ
አዝ = = = = =
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የፅድቅ መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

"ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ …"
ማቴ ፫፥፲፬-፲፯

● መዝሙር ●
♡ በ/ሰ/ት/ቤት ♡

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


#በየቀኑ_መዝሙር_በግጥምና_በዜማ_ከፈለጉ_frowarded_በመንካት_ቤተሰብ_ይሁኑ
አብረን በድምፅ እንዘምር የምትችሉት ሁሉ ዘምሩ🙏

ሥላሴ ትትረመም

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር (፪)

ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ
አዝ
ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል
አዝ
በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት
አዝ
በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ(፪)
አዝ
ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ  
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ

ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ

ተጨማሪ መዝሙሮች ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
 
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


በዮርዳኖስ የተጠመቀው | Be Yordanos Yetetemkaw | በማህበር ፊልጶስ | የጥምቀት መዝሙር | የመዝሙር ግጥሞች | ethiopian ortodox
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
  
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


ሀሌ ሀሌ ሀሌ ሉያ የህብረት ዝማሬ[ new ye timket mezmur

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


የኛ ነው ዋሻው እምነቱ ዘማሪ አሸናፊ አበበ Yegna New Ashenafi Abebe for more vedios please Subscribe

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


"እልል እልል ደስ ይበለን ይዘን መጥተናል ታቦታቱን እልል ብላችሁ ተቀበሉን" |Timket Mezmur Collection | የጥምቀት በዓል መዝሙሮች ስብስብ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


በእደ ዮሀንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ||የጥምቀት መዝሙር

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


የጥምቀት ዝማሬ |እዩት ሎሌው ሲያበራ | Ethiopian Orthodox Timket mezmur collection
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


Ethiopia ortodox mezemur....የሰላሙ መሪ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Jan, 06:42


ደስ ይበለን በጣም ድስ ይበለን የጥምቀት በዓል መዝሙሮች Timiket ጥምቀት መዝሙር
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የተዋሕዶ ፍሬዎች

11 Jan, 17:05


♦️
ቅዱስ ገብርኤል ያለ መዋለጃ ዘር የሚሆን ፅንሷን፤ ያለሩካቤም የሚሆን መውለዷን ይነግራት ዘንድ ወደ ማርያም ተላከ ገብርኤል ሳያበስራት በሥጋ ይወለድ ዘንድ እግዚአብሔር ቢወድ ኖሮ በቻለ ባደረገም ነበር። ነገር ግን በየጥቂቱ ሲያድግ ስለፅንሷ በልቧ ይህ ከጽኑ ደዌ የመጣ ነውን ወይስ የሰውን ልጅ ከሚተነኳኰሉት ከመናፍስት ብላ #እንዳትደነግጥ_ለእናቱ_አሰበላት፤

♦️
ስለዚህም ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ያለሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ይላት ዘንድ ብርሃናዊ መልአኩን ወደርሷ ሰደደ፡ ማርያምም ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆንልኛል አለች፣ መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል ካንቺም የሚወለደው ቅዱስ ነው የልዑል ልጅ ይባላል አላት።

♦️#ብርቱ_ከብርቱ_ካልሆነ_በቀር_አይወለድምና ስለዚህ የልጁ እናት ለመሆን ያጸናት ዘንድ የልዑል ኃይል ጋረዳት የፍጡራን አካል ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ አይቀደስምና። ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ለመለኮት ማደሪያነት ያከብራት ዘንድ ወደ እርሷ ለመምጣት ቀደመ፤ እንደምትለኝ ይሁንልኝ ባለች ጊዜ እንዳበሰራት ሆነላት ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሆነ፤

♦️
ሰውነቱ ከመለኮት የተለየ ነውን እንዳንል መለኮቱስ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ከአብ ተወለደ ሰውነቱ ግን ከእርሷ ካልሆነ በቀር ከዚያ ጊዜ አስቀድሞ አልተወለደም። መልአኩ የምስራቹን ቃል መደምደሚያ ከአንቺም የሚወለደው ቅዱስ ነው የልዑል ልጅም ይባላል እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ብሎ በመናገር ደመደመ።
ሉቃ. 1፥26-35

📍መጽሐፈ ምስጢር 14÷12-13


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

11 Jan, 09:26


አዲስአበባ ያላችሁ በመርሀግብሩ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ ሼር ይደረግ
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

10 Jan, 14:59


💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
               ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት

የተዋሕዶ ፍሬዎች

10 Jan, 05:02


#ጾሙስ_አበቃ.....?

ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!

የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!

✍🏽#በአባ_ገብረ_ኪዳን


@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Jan, 16:47


እኔም ላወድስሽ ተናገረ የማርያምን ክብር ዳዊት በዝማሬ ተናገረ ሳታውቀው አለፈ ዳዊት በዝማሬ
በዳዊት በገና በያሬድ ዝማሬ
እኔም ላወድስሽ ቃላትን ደርድሬ
የጌታዬ እናት ስምሽ ይጣፍጣል
ባህዛብ መካከል አፌ አንችን ይጠራል
ማርያም ማርያም ስልሽ ጠላት ይሸበራል
አሁንም ጠራሁሽ አውሬው እርር ይበል
አምላኬ ስጥራሽ ሰምቻለሁ በፍቅር
እናቴ ለክብርሽ አልሻም ምስክር
ምልጃና ፀሎትሽ ምርኩዜ ሆኖኝ
አሰፈሪውን ለሊት ስንቱን አለፈኩኝ
ልቤ አይከፈትም ዝግ ነው ለጠላቴ
ዘውትር አይለየኝም ስእልሽ ከደረቴ ሞትስ ለሟች ይገባ ነበረ የአንች ሞት ግን ለሁሉ ያስደንቅ ነበረ የአንቺስ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር
ስጋሽ በምድር ላይ የት አለ እንደ ፍጡር
አርጓል ወደ ስማይ ከክርስቶስ መንበር።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Jan, 11:57


እንኳን ተወለድክ መምህር!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዛሬ ልደቱ ነው ።


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Jan, 11:55


​​#አንቲ ዘበአማን

አንቲ ዘበአማን አንቲ ዘ በአማን
ረከብኪ ጸጋ ግብረ ድንግል
የዓቢ ክብራ ለማርያም/፪/


/አዝማች/

በግሽን ተራራ------------------ዘበአማን
በክብር ተቀምጠሻል---------ዘበአማን
ታላቁን በረከት------------------ዘበአማን
በእጅሽ ጨብጠሻል-----------ዘበአማን
እንሰግድልሻለን-----------------ዘበአማን
የጸጋ ስግደት--------------------ዘበአማን
እመቤቴ ማርያም---------------ዘበአማን
የጌታዬ እናት---------------------ዘበአማን


/አዝማች/

ልሂድ ወደ አንባሰል-----------ዘበአማን
ወደ ግሸን ዓንባ----------------ዘበአማን
አድርጊኝ እንደ ሕጻን-----------ዘበአማን
ወደ ቤትሽ ልግባ---------------ዘበአማን
ልረፍ በመስቀሉ----------------ዘበአማን
ከደጅሽ መጥቼ-----------------ዘበአማን
የዓለምን ጫጫታ--------------ዘበአማን
ሁሉንም ረስቼ-------------------ዘበአማን


/አዝማች/

ሩቅ ነው መንገዴ---------------ዘበአማን
ብርቱ ነው ዳገቱ----------------ዘበአማን
ንገሪው ለልጅሽ-----------------ዘበአማን
እርሱ ነው ጉልበቱ--------------ዘበአማን
ሳልረግፍ እንደ አበባ-----------ዘበአማን
ሳልመጣ በአልጋዬ-------------ዘበአማን
ሕይወቴን አደራ-----------------ዘበአማን
ነፍስ እና ሥጋዬ-----------------ዘበአማን


/አዝማች/

ያመሰግኑሻል-----------------------ዘበአማን
ዓለም ዘለዓለም--------------------ዘበአማን
ሥምሽ ይጣፍጣል----------------ዘበአማን
ድንግል ማርያም-------------------ዘበአማን
በተሰጠሽ ጸጋ-----------------ለማርያም። 
በአማን በአንቺ አማላጅነት-----------------ዘበአማን
ለልጆችሽ ይብዛ-------------------ዘበአማን
ዕድሜ እና በረከት----------------ዘበአማን


/አዝማች/

ያመሰግኑሻል---------------------ዘበአማን
ዓለም ዘለዓለም------------------ዘበአማን
ሥምሽ ይጣፍጣል--------------ዘበአማን
ድንግል ማርያም-----------------ዘበአማን
በተሰጠሽ ጸጋ---------------------ዘበአማን
በአንቺ አማላጅነት----------------ዘበአማን
ለልጆችሽ ይብዛ------------------ዘበአማን
ዕድሜ እና በረከት---------------ዘበአማን


/አዝማች/

ረከብኪ ጸጋ ክብረ ድንግል
የዓቢ ክብራ ለማርያም
ረከብኪ ጸጋ ክብረ ድንግል
የዓቢ ክብራ ለማርያም።

@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

07 Jan, 06:05


🎆እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት፡ እርሱም ክርስቶስ፡ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።🚩🚩🚩💖

                          (ሉቃ. 2፡10)

🎆 🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆እንኳን ለብርሃነ ልደቱ 🎆🎆
🚩 በሰላም በጤና አደረሳችሁ🚩🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆
🍬🍬🚩🚩🚩🚩
🎆የተዋህዶ ፍሬዎች 🌐 🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🎆 ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና 🚩

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 16:02


🕊                       


[     ይህቺ  ምሽት !      ]


💖   እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ  💖

ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ  !
🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆
------------------------------------------❤️🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🌹
" ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው [ አምላክ ] የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡  ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን ! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ !
🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን !
🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት !
💖💖💖💖💖💖💖💖
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት ! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት !  የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት !
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው !
💡💡💡💡💡💡💡💡
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡

ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ 🎁 የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ !
🫴🫴🌹
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት ! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!"
🍬🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆
[   ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ    ]
🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆
         †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 05:39


[ጥንተ አብሶ] "እመቤታችን ላይ ለሚነሱ የመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ" | መምህር ኢዮብ ይመኑ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 05:39


[ጥንተ አብሶ] "እመቤታችን ላይ ለሚነሱ የመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ" | መምህር ኢዮብ ይመኑ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 04:51


#ገና_ገሀድ_አለው
#የገና በዓልና ጾመ ገሀድ

➻#የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን እና መሰል የሕዝቡን የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኞቹ ጉዳዮች አበው ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።
#ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?
📚➻ፍትሐ ነገሥት፡ ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/
➻#የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/
#የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?
📚➻ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/
➻#ልደት ጋድ አለው?
📚➻ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/
    ✥➻ ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡
                 ➻  40 ጾመ ነቢያት
                   ➻ 3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ
                   ➻ 1 ጋድ
               ድምር = 44 ቀናት ይሆናል።
✤➻ የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 565/ ነገር ግን አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲሁ ነው፡፡
✢➻ ይህንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?
➻#መልስ፡ በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፣ ለማይቆርቡ፣ ንስሐ ለማይገቡ፣ ለማያስቀድሱ፣ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ ሥርዓት የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው #ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም የገናን ጾም ክርስቲያን ሁሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል፡፡ ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/፡፡ ይህም ከገና ጾም ተሸርፎ የሚጾም ነገር እንደሌለው ያሳያል፡፡
መልካም በዓል ይሁንልን!!! 
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው ፣ መጽሐፈ አቡሻኽር...ሌሎችም!!!
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 03:58


++ ሥነጽሑፍ - የልደት ግጥም !

( ርዕስ - ታላቅ ነው ልደቱ )

በጉዞ ላይ ነበር ጌታችን ሲወለድ
ሊፈፅም ሲመጣ የአባቱን ፈቃድ
በቤቴሌሒም ዋሻ በዛች በግርግም
ከሠው ልጅ ተገኘ መድሀኒአለም
የጌታን መወለድ መላዕክትም አይተው
እረኞች በሌሊት በስራ ላይ ሳሉ
በጌታ ብርሃን ዙሪያቸውን ተሞሉ
መላዕክት ከሰው ጋር በአንደ ላይ ዘመሩ
የጌታን መወለድ ለእረኞች ሲያበስሩ
ምስጋና ለእግዚአብሔር በላይ በአርያም
ለሠው ልጅ ይሁን በምድርም ሠላም
ብለው ተቀኙለት ለሠራዊት ጌታ
ስጋ ለብሶልና ሰይጣንን ሊረታ
ይህ ታላቁ ቀን ከመሆኑ በፊት
ተገልፆ ነበር የክርስቶስ ልደት
ለሠበዐ ሠገል እርሱን ላከበሩት
የጌታን መወለድ ባይናቸው ለማየት
እጅ መንሻ ይዘው ሠጡት በእጃቸው
የልባቸውን ፍቅር ለመግለፅ ፈልገው
እውነተኛ ካህን አንተ ብቻ ነህ
ከሀያላን ሁሉ አቻ የሌለህ
ለማየት ፈልገው ለአምላካቸው
ንፁህ ባህሪ ነህ እንከን የሌለብህ
ሠዎችን አንፅተህ የአንተ ለአረግህ
ብለው ለመናገር ለሀያላን ጌታ
ወርቅ አቀረቡለት ለክብሩ ስጦታ
ኢሳያስ በትንቢት ከሩቅ ተመልክቶ
መከራውን  ፃፈ ላምላኩ ራርቶ
የጌታውን እመም ያየውን አበሳ
በአንባ እየተራጨ በትንቢቱ አበሳ
ሠባ ሠገልም ይህንን ተረድተው
የጌታ ስቃዩን ለመግለፅ ቢያሻቸው
በበረት ተኝተው የነበሩ እንስሳት
ፈክተው ተነሡ በእኩለ ሌሊት
እነሱም ሊያከብሩ የአማኑኤል ልደት
እንስሳቱም አውቀው  የእነርሱን ጌታ
እስትንፋስ ገበሩ ለዋለው ውለታ
የጌታን መወለድ መገኘት በበረት
በምድር ፈጠረ ታላላቅ ታምራት
ድንቅ ድንቅ ነገራት ሆኑ በዕለቱ
እውነቱም የጌታ ታላቅ ነው ልደቱ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወመስቀሉ ክቡር ይቆየን !!
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 03:58


(መምህር ኢዮብ ይመኑ)
-እጠብቅሀለሁ-
እጠብቅሀለሁ በመጠቂያዬ፤
ትመጣለህና ሳትረሳ ጌታዬ።
ቀናት ቢያሰለቹ፥ ቢቆጠር ዘመናት፤
አምንሀለሁ ነፍሴን፥ እንደማትተዋት።
በምንም በየትም። በሁሉም ሁኔታ፤ 
እጠብቅሀለሁ፥ በእድሜ ጀምበር ማታ።

አማርሬህ፥ አኩርፌህም፥ አምቼህም፥ እኔ አውቃለሁ፤
ትግስትህን ሳልታገስ፥ ብዙ ነገር ብዬሀለሁ፤
ለዘመኔ እሾህ ሆኜ፥ ከቤትህም ጠፍቻለሁ፤
አትድረስብኝ አልደርስም፥ ብዬ በስምህ ምዬ አውቃለሁ።
ማታ እግሮቼን አጥበህ፥ በትህትና ለመከርከኝ፤
አላውቀውም፥ ማነው እሱ፥ ብዬ ባፌ መሰከርኩኝ።
ስታበራ ብቻ ሳይሆን፥ ጌቴሴማኒ ፀዳል ስትሆን፤
ቀያፋም ቤት መጥቻለሁ፥ ስትገረፍ ጅራፍ ልሆን።

ለካ እኔ ፈጠንኩ እንጂ፥ አንተ እኮ አልዘገየህም፤
በሰዓትህ ትመጣለህ፥ ቆየህ ምነው? አልልህም። 
እንደ ዕንባቆም እጮሀለሁ፥ አምላኬ ሆይ እልሀለሁ፤
ስትሰጠኝ ብቻ ሳይሆን፥ ብትከለክለኝም እጠብቅሀለሁ።
ፀጋህን ከኔ ውሰድልኝ፥ እኔ አንተን ከማጣህ፤
እንደዘኪዎስ ከዛፍ ልውጣ፥ ቤቴ ግባ አይቼህ።
በዝምታ ልቤን ክፈት፥ ግባ ማነው? ሳልልህ፤
አንተ ብቻ ናልኝ እንጂ፥ ከቤቴ ጋር ላምልክህ።


ደሞ እንዲህም ብዬሀለሁ፥ መቼ ጠይቄው መች መለሰ፤
ምነው ልቦናን ነሳኝ፥ እኔን ከሰው አሳነሰ።
ለምንድነው ያዋረደኝ፥ ዝም የሚለው እንዲህ ስሆን፤
ለካ አንተ የምትመጣው፥ እንደ አልዓዛር አፈር ስሆን፤
ለካ ህመም አይደለም፥ ሞትም አይደል የሚያቆምህ፤
በአራት ቀኔ ሳትፀየፍ፥ መቃብሬን ትከፍታለህ።
ለካ መሽቶም ትመጣለህ፥ እድሜ ዘመን አይገታህም፤
የጠበቀህ እርፍ ይላል፥ ላንተ ምንም አይሳንህም።
:
እንደ ዮሴፍ ብጠላ፥ በወንድሞቼ ብከዳ፤
በሰላሳ ዲናር ብሸጥ፥ ብንከራተት ምድረበዳ።
የአባቴ አይንም ቢፈስ፥ ቢናፍቀው የልጅ መልኬን፤ 
የሀሰት ፍርድ ቢፈርዱብኝ፥ ብወረወር እድሜ ልኬን።
ፍርድ አጣመው ቢያንገላቱ፥ ፍርዱም ቢሆን እድሜ ይፍታ፤
ማንም ዳግም አያስረኝም፥ አንተ መተህ ስትፈታ።
አንተ ምን ይሳንሀል፥ በወህኒው በኩል በር አለህ።
በጲጢፋራ መንበር፥ ልታነግሰኝ ትመጣለህ

ታማኝ ነህ  ለጠበቀህ፥ ማህጸንን ትፈታለህ፤
ሲስቁብኝ ልትባርከኝ፥ በመቅደስህ ትመጣለህ።
መካን ብባል የተጣለች፥ ስሜም እንኳ በቅሎ ቢሆን፤
መቶ ፍሬ ይገኝብኝ፥ አብዛኝና ለዘር ልሁን።
የሀናን ለቅሶ የሰማህ፥ የኤልሳቤትን እንባ ያበስክ፤
ልጅ የጠየቀችህን፥ በልጆች የምትባርክ፤
ዛሬ አለሁ ያንተ ሀና፥ ዛሬም አለሁ ያንተ ኤልሳቤት፤
እንደ ዮሀንስ ባርከህ ስጠኝ፥ ባንተ ጊዜ በለኝ አቤት።
:
መሮኛል ስልህ ወደላይ፥ የበታቼን ሳላየው፤ 
አንተ ባልቆረጥከው ቀን፥ የራሴን ሞት የተመኘው።
ምነው መታገስ ከበደኝ፥ ነገን ዛሬ ደመደምኩት፤
ምነው ተስፋ ቆረጥኩ፥ ዛሬን አሁን ቀበርኩት።
እንደ ሙሴ በእድሜ ማታ፥ ከከንዓን ሩቅ ብሆን፤
የልፋቴን ሳልቀበል፥ ዕጣ ፈንታ ሞትን ቢሆን፤
በታቦርም ትመጣለህ፥ ቃልኪዳንህ አይታጠፍም
ካንተ ይሰጠዋል እንጂ፥ ሰው በራሱ አያተርፍም
:
ከእሳት በፊት ትደርሳለህ፤
ወይስ ነዶ ትመጣለህ፤
ስወገር ትደርሳለህ፤
ወይስ ፍርዱን ትሽራለህ፤
ስትታመም ትመጣለህ፤
ወይስ ስሞት ታስነሳለህ።
አልወተውትህም እታገስሀለሁ፤
በሁሉም ሁኔታ እጠብቅሀለሁ።
++++
የተናቀን የተረሳን፥ አንተ ስታስታውሰው፤
የጠሉኝ ቢሰበሰቡ፥ ቢሉኝ እንዳንተ እናንግሰው።
ቋጠሮዬን ስትፈታ፥ ከቀበሮ ደስታ ጠብቀኝ፤
ጽድቅህን እኔ እሻለሁ፥ መንግስትን አትንፈገኝ።
+++
( መምህር ኢዮብ ይመኑ)

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 03:38


+  የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ +

ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል::

እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ  የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል::  ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ  ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል::

ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት ስም : ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሠጠን ስም : ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል::

       ኢየሱስ ✍🏽

አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ?

ጌታችን በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል::

ክርስቶስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12)

እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ::

ወዳጄ ክርስቶስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው::

"ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ"
ሉቃ 10:20

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Jan, 03:38


ነቢዩ ኢሳይያስ ‘ስሙም ድንቅ!’ ብሎ እንደተናገረው የታተመችው ደብዳቤ ድንግል ማርያም የታቀፈችው ማድነቅ እንጂ ማወቅ የማይቻል ሕፃንን ነበር፡፡

እኛ የሰው ልጆች የጠበቅነው ፈራጅና ተበቃይ ፣ በእጆቹ ሰይፍን የያዘ ንጉሥን ነበር፡፡ እርሱ ግን የመጣው ሕፃን ሆኖ ነበር፡፡ እንደ ኃያል ገዢ ስንጠብቀው ‘ከእናቱ ጡት ወተትን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ’

የሰው ልጆች ራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር በማስተካከል ለሠራነው በደል ቅጣትን ልንሰማ ለተጠያቂነት ዝግጁ ሆነን ጠበቅነው፡፡ እርሱ ግን ፍቅራችንንና እንክብካቤያችንን ፣ ደግነታችንን የሚጠይቅ ፣ መታቀፍን የሚሻ ሕፃን ሆኖ እጆቹን ወደ እኛ ዘረጋ፡፡

እኛ መቼም በእግዚአብሔር ላይ ኖሮን የማያውቀውን እምነት እግዚአብሔር በእኛ ላይ አሳየ፡፡ የእኛ ኩራትና ትዕቢት ሳያግደው ራሱን ዝቅ በማድረግ ወደ እኛ ወረደ፡፡

በዚህ ሕፃን ዓለም ሁሉ ተደነቀ ፤ ሁሉም ከጠበቀው በላይ የሆነ ነገርን አገኘ፡፡

መካኒቱ ኤልሳቤጥ ወለደች ፣

ዲዳው ዘካርያስ ትንቢት ተናገረ ፣

ድንግሊቱ እናት ሆነች ፤

እረኞች ከመላእክት ጋር ቆመው ወግ አወጉ ፤

የከብቶች በረት ቤተ መንግሥት ሆነ ፣

እንስሳት የወለደችን እናት ከብርድ ለመከለል ከበቧት ፣

ከዋክብት መንገድ መሪ ሆኑ ፣

ነገሥታት በድሆች ቤት እጅ መንሻ አቀረቡ ፤

አረጋዊው ስምዖን ሞትን መፍራት አቆመ ፤

ኃያሉ ንጉሥ ሔሮድስ ሁለት ዓመት ያላለፉ ጨቅላ ሕፃናትን እንደ ኃያላን ወታደሮች ፈራቸው፡፡

ይህ ሕፃን ያላመጣው ድንቅ ነገር አልነበረም!


ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Jan, 19:34


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Jan, 18:32


መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇

የተዋሕዶ ፍሬዎች

03 Jan, 14:00


አትገላለጪ!!
ውበት ያንቺ አይደለም መልክሽ የእግዚአብሔር ነው
አትመፃደቂ አንቺ እንደፈጠርሽው ልክ እንዳመጣሽው
ገላሽን ደብቂ ልብሱን ወርውረሽው እርቃን አትሁኚ
ቆንጆ አርጎ ለሰራሽ ለሰራዊት ጌታ በደስታ አመስግኚ
ጠጉርሽ ተጠቅልሎ እርዝመቱ ቢገዝፍ
የዳሌሽን መስፋት አይቶ ወንዱ ቢከንፍ
አጉል ብዙ አትኩሪ አትመፃደቂ ከአምላክ አትራቂ
ሴት መባልን ሳይሆን ሴትነት እወቂ
ክብርሽ በለበሽው በዥንጉርጉር ልብስሽ
በተቀባባሽው በተለቀለቅሽው ሁሉን ነገር ባረግሽ
አይታይም እኮ እንደውም ይረክሳል ብን ብሎ ይጠፋል
ብዙ ሳታግጪ በስብሶ ይፈርሳል በእሳት ይበላል
ስለዚ እናቱ አትገላለጪ ልብሱን አታማሪው
እየቀዳደድሽው ልብስ እንዳጣ ለማኝ አርገሽ አትልበሽው
አምላክን ፍሪና ልባሟን ሴት ሁኚ ግራ አትጋቢ
ሁሉም ፈራሽ በስባሽ ሲዖል እንዳትገቢ
ሴት ማለት ብልኽ ናት የሚለውንም ቃል አገናዝበሽ ስሚ
አትገላለጪ እርቃን አትሁኚ አሁንስ ታረሚ
ወንዱም የሚወድሽ ከልቡ ሚመርጥሽ
ስለተገላለጥሽ ፍፁም እንዳይመስልሽ
ክብርሽን ጠብቀሽ ስትከናነቢ ስትሸፏፈኚ
ሁሉን ታገኛለሽ ከደጅሽ ይመጣል በአምላክ ተማመኚ
ወንዱም ልንገርካ ለሴት ብቻ አይደለም
ሁሉን ነገር ስማ እስኪ ተግብር አንተም
ማታ ሊክ ሲመሽ መጠጥ ቤት አትሩጥ
ሊኪዳኑም ቢሆን ስልክክ ለይ አታፍጥ
ተነስና እሩጥ ደጁ ተመላለስ ጠዋትና ማታ
ሂድ እኔ ልነገር  አንተ የሀገር ወጣት ታገኛለ እፎይታ🥰🥰
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

02 Jan, 18:57


ድንግል ማርያም ተልኮ “ትፀንሻለሽ፣ ትወልጃለሽ” በማለት መድኃኒታችንን
ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትፀነስና እንደምትወልድ ነገራት። ይህም መጥምቁ
ዮሐንስ ከተፀነሰበት ጊዜ ፳፱ ቀን) አንሥቶ ሲቆጠር መጋቢት 29 ቀን ይሆናል።
መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት “መካን ትባል ለነበረችው (ለኤልሳቤጥ) ይህ
ስድስተኛ ወር ነው” ሲል የተናገረው የፅንሰትዋን ጊዜ የሚያመለክት አይደለምን?
ሉቃ 1፥36-38። ስለዚህ መጋቢት 29 ቀን ቃል ሥጋ የሆነበትና በድንግል
ማኅፀን የተፀነሰበት ዕለት ነው ማለት ነው። ከዚህ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ
ወንድ ልጅ በእናቱ ማኅፀን የሚቆይባቸውን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት (275
ቀናት) ስንቆጥር ጳጉሜን ጨምሮ ዕለተ ልደቱ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ላይ ይውላል።

ስለዚህም መጋቢት 29 ቀን የተፀነሰው ጌታችን ከኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ
ሁሉ ፈጽሟልና ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእናቱ ማኅፀን ቆይቶ ታኅሣሥ 29 ቀን
በቤተልሔም ዘይሁዳ ተወለደ። ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት
ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የታሪክና የትውፊት ማስረጃዎችን መሠረት
አድርጋ የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 29ቀን በታላቅ
ምስጋና ታከብራለች።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስርስትያን እና ሌሎችም ቤተ ክርስቲያናት በዓለ ልደትን ታኅሣሥ ፳፱ ቀን የሚያከብሩት በተረዳና በታወቀ ማስረጃና መሠረት ላይ ተመሥርተው ነው እንጂ እንዲሁ አይደም።

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ የምዕራባውያን የልደት በዓል ለምን December 25 ሆነ?

ይቀጥላል……

ሼር በማድረግ ለሁሉም እናድርስ
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


አዲስ የገና መዝሙር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ Faarfanna Dhaloota Gioftaa EOTC
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Ethiopia :- የምስራች ደስ ይበለን | የገና(የልደት) መዝሙር | yemisirach des yibelen | ye gena mezmur | ዮናስ ቲዩብ yonas

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Zemari Artist Yigerem Dejene /በኤፍራታ/ የገና መዝሙር

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Ethiopia :- የምስራች ደስ ይበለን | የገና(የልደት) መዝሙር | yemisirach des yibelen | ye gena mezmur | ዮናስ ቲዩብ yonas

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Zemari Artist Yigerem Dejene /በኤፍራታ/ የገና መዝሙር

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


#ገና ደስታችን ገና ደስታችን ገና ደስታችን / #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የገና መዝሙር

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


"በኤፍራታ ምድር" | ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


"ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ | ግጥም- በዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


እሰይ እሰይ ተወለደ // አዲስ የልደት መዝሙር በዘማሪ በሱፈቃድ አንዳርጋቸው // mezmur by Besufekad Andargachew

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


"ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ | ግጥም- በዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Ethiopia: እሰይ እሰይ ተወለደ - ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ (Esey Esey Tewelde - Z. Fantu Welde)
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


Ethiopia: እሰይ እሰይ ተወለደ - ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ (Esey Esey Tewelde - Z. Fantu Welde)

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

01 Jan, 08:46


እሰይ እሰይ ተወለደ // አዲስ የልደት መዝሙር በዘማሪ በሱፈቃድ አንዳርጋቸው // mezmur by Besufekad Andargachew

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

31 Dec, 17:01


ካህናተ ሰማይ ስንት ናቸዉ?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

29 Dec, 03:21


#ቅዱስ_ቁርባን ለምን ያሰፈልጋል ?

#ወንድማችን አክሊል

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Dec, 04:25


✝️እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል: ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝️

✍️በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)

አምላከ ቅዱሳን በመልአኩ ረድኤት ጠብቆ ለጻድቃኑ በረከት ያብቃን::

#ቻናሉን_ይቀላቀሉ

Telegram:
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Dec, 04:24


ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ:
‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)
#ቅዱስ_ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለርዳታ የሚደርስ፣ በጨለማ እና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ‹‹ይወርዳል ይወለዳል›› በማለት በየወገናቸው እና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት ያስፈጸመና የምሥራችን ቃል የተናገር፣ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል ከእፉኝት መርዝ የከፋ በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩ

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና  የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡
#ቅዱስ_ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ (አክሲማሮስ. ገጽ.፴፭) በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡
#ቅዱስ_ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡
#ቅዱስ_ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)
#ቅዱስ_ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)
ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)
ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)
#ቅዱስ_ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው››  ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)
#ቅዱስ_ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው #ቅዱስ_ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-
ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ
ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ
ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ
አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ
ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ
ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡
በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)

ቅዱስ ገብርኤል እና ተራዳኢነቱ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Dec, 04:24


#ቅዱስ_ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ በስደት ሲሰደድም ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)
#ቅዱስ_ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ›› እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን  ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፱)
#ቅዱስ_ገብርኤል  ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤  ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት፤ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል››እንዲል (መዝ.፺፩፥፲፩)፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል››(መዝ.፴፬፥፩)፤ ‹‹በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡››(ዘጸ.፳፫፥፳)

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብረ በዓሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎት እና በምስጋና ታከብራለች፡፡ በተለይም ታኅሣሥ ፲፱ ቀን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በዓል የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አግብርተ እግዚአብሔር አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከእቶነ እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በግእዝ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ትማልም አሲረነ ሠለስተ እደወ ወደይነ ውስተ እቶነ እሳት  ዮምሰ እሬኢ አርባዕተ እደወ እንዘ ያንሶሰዉ ማዕከለ እሳት ፍቱሐኒሆሙ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል››፤ ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤ ዛሬ ግን ዐራት ሆነው ከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ፤ ዐራተኛውም የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል፤ በማለት ይገልጸዋ፡፡ (ወዲያውም ከእቶኑ ሂዶ‹‹ አንትሙ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብድናጎ አግብርተ እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ ኑ ውጡ›› አላቸው ብር ብር እያሉ ከእሳቱ ውስጥ ወጥተዋል፤ በልብሳቸው ላይም ጥላሸት እንኳን አልተገኘም፤ ናቡከደነጾርም ይህን አይቶ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፤ ንጉሡም አዋጁን በአዋጅ መልሶ ለሕጻናቱ በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይ ክብር ጨምሮላቸዋል)፡፡
የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር፤ አሜን፡፡

#ማህበረ_ቅዱሳን
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Dec, 04:07


ሃጢአት በመስራት ሰው ድኅነቱን አያጣውም የሚለውን የፕሮቴስታንት አስተምህሮ በእግዚአብሔር ቃል ስናፈራርሰው መቋቋም ያቃታቸው አንዳንድ ልጆች “አይ እኛም እኮ እንደ እናንተ ነው ምናምነው” ብለው ሲመጡ ሳይ ትንሽ ፈገግ ያደርገኛል..

ፕሮቴስታንቶች ያው ድብልቅልቁ የወጣ አስተሳሰብ ነው ያላቸው ድኅነት ላይ.. አንዱ በሃጢአት ድኅነት ይታጣል ሲልህ ሌላኛው አይታጣም ይልሃል.. አንዱ እምነት ብቻ ስል ጥምቀትንም አግልዬ ነው ሲል ሌላኛው ይመጣና አንተ እውር ጥምቀትን ማግለል አይቻልም ይለዋል ሎል.. አንዱ ዳግም ውልደት(በ irresistible grace) ከእምነት ይቀድማል ሲል ሌላው ደግሞ በእምነት ነው ምንወለደው ይላል..

በፕሮቴስታንቱ መልካም ሥራ ለመዳናችን እንደ ማረጋገጫ(evidence) ይሆናል እንጂ ከዘላለም ሕይወት ጋር ግን ግንኙነት የለውም ነው ተብሎ የሚታመነው..

ምናልባት ግን የዘላለም ሕየወታችንን እንዳናጣም መልካም ሥራ መስራት አለብን የተባለት የእምነት መግለጫ ካላችሁ እዚሁ ኮመንት ላይ አስቀምጡና እንየው😁😁
ከ አክሊል
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

26 Dec, 20:03


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

የተዋሕዶ ፍሬዎች

26 Dec, 19:48


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️

         

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Dec, 20:39


ጥንተ አብሶ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Dec, 20:30


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Dec, 13:23


<<እመቦ ዘወድቀ በኃጢኣት ኢይርሳዕ እስመ ዘኢይትረሳዕ>>

<<በኃጢኣት የወደቀ ሰው ቢኖር አይርሳ የማይረሳ ነውና>>


ቅዳሴ እግዚእ
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Dec, 13:23


ጾም እንዴት ነው ?.....❤️

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ ነፍስ አባቱ ይኼድና ሰላም ካላቸው በኋላ "ልጄ መንፈሳዊ ሕይወት እንዴት ነው?" አሉት ወጣቱም መልሶ "በጣም ጥሩ ነው!" ይላቸዋል። እሳቸውም ደስ ብሏቸው "ጎሽ ልጄ በርታ! እና ጾሙስ እንዴት ይዞኻል?" ሲሉት ወጣቱም "አይ አባቴ ጾም እንኳን እየጾምኩ አይደለም።" አላቸው።

"ለምን ልጄ ምን ነካኽ?"  "አይ አባቴ ጾም ከገባ በኋላ ፍሪጅ ውስጥ የነበረ ሥጋ ወጥ ረስቼው በላኹት። ከዛም ያው አንዴ ሽሬያለኹ ብዬ አልጾምም።" አለ።

የነፍስ አባቱም በጣም አዘኑና  "ልጄ አንድ ጥያቄ ልጠይቅኽ?" ወጣቱም "እሺ ይጠይቁኝ!" አለ። እርሳቸውም "እሳት አየሞክ እያለኽ ሳታስበው በድንገት እግርኽን ወደ እሳቱ ቢገባና እግርኽ ቢቃጠል አንዴ ተቃጥያለኹ ብለኽ ሳታወጣው ዝም ትላለኽ? ወይስ ታወጣዋለኽ?" አሉት።

እሱም በድንጋጤ "እንዴ አባቴ! ለምን ዝም እላለኹ? ቶሎ ብዬ አውጥቼ በፍጥነት ወደ ህክምና ኼጄ እታከመዋለኹ።" በማለት መለሰ።

"ጥሩ ብለኻል ልጄ! በጾምም አንዴ በልቻለኹ ብሎ መብላት ተገቢ አይደለም። ኃጢኣትም ነው ልጄ! ልክ ከእሳቱ እግርኽን ቶሎ ብለኽ አውጥተኽ ወደ ህክምና እንደ ኼድክ ነፍስም ከቁስሏ ቶሎ ብለኽ ከስሕተት ተመልሰኽ በጾም በጸሎት ማከም ይገባኻል። በስህተት የሻርከውን ንስሐ ይሰጥኽና የቀረውን መጾም ነው የሚገባኽ! ልጄ በስሕተት ላይ ስሕተት እየጨመርክ መንፈሳዊ ሕይወትኽን ማጥፋት የለብኽም!" በማለት ቀኖና ሰጥተው ጾሙን እንዲጾም ነግረው አሰናበቱት።

ያሰተማረን የመከረን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን 🙏❤️

               ✥••●◉ ✞ ◉●••✥
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

24 Dec, 12:09


የክርስቶስ ልደት ታህሳስ 29 ወይስ ዴሴምበር 25?

የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ 29 ቀን ታከብራለች?
ምዕራባውያንስ የልደትን በዓል ለምን December 25 ያከብራሉ?
የጌታችን በዓለ ልደት መቼ ተጀመረ?
መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን?
የልደት በዓል የሚከበርበትስ ቀን በምዕራባውያንና በእኛ ቤተ ክርስቲያን ለምን
ተለያየ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ
በቀጥታ ካለመገለጹ የተነሣ ትክክለኛውን ቀን ለማግኘት ታሪክን ተከትለው ብዙ
የደከሙ አሉ። ከዚሁም የተነሣ ዕለተ ልደቱን በተመለከተ የቀናት ልዩነቶች
ተከሥተዋል።

ሆኖም ግን ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ቀኑን ይህ ነው ብሎ
በግለጽ ባይናገርም አመልካቺ የሆነ ፍንጭ ሳይሰጥ ግን አልቀረም። ይህንን
ለመረዳት በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ አንድ ከቁጥር 8-14 የተጻፈውን
መመልከት ያስፈልጋል።

“በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ
ካህን ነበረ። ሚስቱም ከአሮን ልጆች ወገን ነበረች። ስምዋም ኤልሳቤጥ
ነበር። . . . እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል ወደ ቤተ
መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ
ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ ፍርሃትም ወደቀበት። መልአኩም እንዲህ
አለው፦ ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፣ ሚስትህ ኤልሳቤጥ
ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፣ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ተድላና ደስታም
ይሆንልሃል፣ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።” /ሉቃ፩፥፭፣ ፰፥፲፬/

በዚህ ክፍለ ምንባብ በጣም አስፈላጊ የሆነ አመልካቺ (ጠቋሚ) ነገር ተመልክቶ
እናገኛለን። ሆኖም ይህን አሳብ ፈልፍሎ ለማግኘት ከቅዱሳት መጻሕፍት ቃልና
አሳብ ጋር ተዛምዶ ሊብራራና ሊተረጎም ያስፈልገዋልና ነገሩን በጥንቃቄና
በማስተዋል መከታተልን ይጠይቃል። ዋናው አመልካቺ ፍሬ ነገር መልአኩ ቅዱስ
ገብርኤል ለዘካርያስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ያበሠረበት ቀን
በዕብራውያን ዘንድ “በዓለ ሥርየት” ተብሎ ይከበር የነበረው ቀን መሆኑ ነው።
በዓለ ሥርየት የሚባለው በዓል በዕብራውያን አቆጣጠር በሰባተኛው ወር
ማለትም በታስሪን (ጥቅምት) አሥረኛ ቀን የሚውል ታላቅ በዓል ነበር። ይኸውም
በዓል በኦሪት ሕግ “በሰባተኛው ወር፣ በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ
ትነጻላችሁ። ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል . . .” ተብሎ የታዘዘበት ታላቅ በዓል
ነበር። /ዘሌ ፲፮፥፳፱–፴፤ ፳፫፥፳፯፤ ዘኁ ፳፱፥፯-፲፩/

በዚህ በዓል ቀን ሊቀ ካህናቱ የተቀደሰ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ወደ መቅደስ
ይገባል። በእግዚአብሔር ፊት ባለው መሠዊያ የእሳት ፍህም አምጥቶ ጥናውን
ይሞላል። እንዳይሞት የጢሱ ደመና በምስክሩ ላይ ያለው መክደኛ
(ማስተሥረያ) ይሸፍን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ
ያደርጋል።እንዲሁም ካህኑ ለማስተሥረይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ
መጀመሪያ ለራሱ፣ ከዚያም ለሕዝቡ ሁሉ አስተሥርዮ እስኪወጣ ድረስ
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሌላ ማንም ሰው አይኖርም ነበር። ዘሌዋ ፲፮፥፲፯።
እንግዲህ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ እነዚህ ድርጊቶች መፈጸማቸውን
ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ገልጾአቸዋል። “እርሱም (ዘካርያስ) በክፍሉ ተራ
በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ
ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።” ይላል።
ስለዚህ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ቀን የተጠቀሰው ሥነ ሥርዓት
በሚፈጸምበት በበዓለ ሥርየት ቀን ሲሆን ይህም በዕብራውያን አቆጣጠር
በጥቅምት አሥረኛ ቀን ነው።
ስለዚህ ቅዱስ ሉቃስ ይህን ቀን በተለየ ሁኔታ
ጌታችን ለተወለደበት ቀን ታሪካዊ የአኀዝ መነሻና የመሠረት ድንጋይ መሆኑን
ጠቁሞ አመልክቶአል ማለት ነው።
ይህ ዘካርያስ የተበሰረበት ቀን የአይሁድ በዓለ ሥርየት የዋለበት በዕብራውያን
የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት አሥረኛ ቀን መሆኑን ብዙ ጥንታውያን የቤተ
ክርስቲያን አባቶች መተርጉማን ገልጸው እናገኛለን።
ለምሳሌም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ማር ዮሐንስ ወንጌለ ሉቃስ ምዕራፍ
አንድን ሲተረጉሙ ሰፋ ባለ ሐተታ ገልጸውት እናገኛለን። የኢትዮጵያ
መተርጉማንም በተወራረሰ የሊቃውንት ትርጓሜ “ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ
ገባ” ከሚለው ላይ በታሪክ ሲያትቱ “የጥቅምት ጨረቃ ሠረቅ ባደረገች በአሥር
ቀን ነው፤ ዕለቱም ዕለተ ዮሴፍ (በዓለ ሥርየት) ነው፤. . . ተሰብስበው ይጸልያሉ፣
ወበይእቲ ዕለት አሕምምዋ ለነፍስክሙ (በዚያች ዕለት ራሳችሁን ታዋርዳላችሁ)
እንዲል” ብለው አስረድተዋል። (ትርጓሜ ወንጌል፣ ገጽ 324)

እስከዚህ ድረስ ዘካርያስ ዮሐንስን እስከሚወልድ የተበሠረበት ቀን በዓለ ሥርየት
በሚባል በዕብራውያን አቆጣጠር ታስሪን (ጥቅምት) አሥር ቀን ለመሆኑ
የተገናዘበበትን ትምህርታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ አይተናል። አሁን ደግሞ
ይህን አቆጣጠር ከኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት
እንደሆነና መቼ እንደሚያርፍ እንመልከት።
በዕብራውያን አቆጣጠር በዓለ ሥርየት የዋለው በጨረቃ አቆጣጠር ጥቅምት
አሥር ቀን ስለነበር ይህንን ወደ ኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር መልሶ ዕለቱን ለማግኘት ወደ ዘመን አቆጣጠር መግባት ግድ ይሆናል። ነገር ግን ወደዚህ የቀን
አቆጣጠር ዝርዝር ብንገባ የያዝነውን ጉዳይ እንዳያወሳስበው ዝርዝር ሐተታውን
ትተን እንዲሁ ዕለቱ የሚውልበትን ብቻ እንመልከት። በዕብራውያን አቆጣጠር
ወርኀ ታስሪን (ጥቅምት) አሥር ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር የዋለው መስከረም
27 ቀን ነበር። ይኸውም የጨረቃ የቀን አቆጣጠር ሲለወጥ የሚገኝ ነው።
ይህም ማለት በጨረቃ አቆጣጠር 10 ቀን የነበረው በዓለ ሠርቅ በፀሐይ የቀን
አቆጣጠር መስከረም 27 ቀን ነበር ማለት ነው።
ስለዚህ ዘካርያስ የተበሠረው መስከረም 27 ቀን ሆኖ እናገኘዋለን። በዓሉ
ወዲያው እንዳበቃ ዘካርያስ ወደ ቤቱ ገባ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ተፀነሠ።
ቅዱስ ወንጌል “የማገልገሉ ጊዜ ሲፈጸም ወደ ቤቱ ገባ። ሚስቱ ኤልሳቤጥም
ፀነሠች” ሲል ያስረዳል። ቅዱስ ያሬድ ይህን መሠረት በማድረግ “ወእምድኅረ
ክልዔ መዋዕል ፀንሠት ኤልሳቤጥ ብእሲቱ ከሁለት ቀንም በኋላ ፀነሠች” ብሏል።
ስለዚህ ዮሐንስ መጥምቅ የተፀነሠው መስከረም 29 ቀን ነው ማለት ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊና በፊቱ የሚሄድ
መልእክተኛ መሆኑ በነቢያት ትንቢት ተነግሮ ቆይቷል። ኢሳ ፵፥፫-፭፤ ሚል ፫፥፩።
እንደ ትንቢቱም ቃል ሁሉ ዮሐንስ ከፅንሠቱ ዕለት ጀምሮ በተፈለገው መንገድ
ለጌታችን ጎዳናውን እያቀና የሚሄድ የፊቱ መልእክተኛ ሆኖ ተገኝቶአል። ሉቃ
፩፥፸፮-፸፱። መጥምቁ ዮሐንስ የተፀነሠበትና ለተወለደበት ቀን ከዚህ በላይ
እንደተመለከትነው መነሻ አብነት ሆኖ ይገኛል ማለት ነው።
እንግዲህ በዚህ ታሪካዊ ቁርጠኝነትና ትስስር መሠረት ኤልሳቤጥ በፀነሰች
በስድስተኛ ወሯ ለዘካርያስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅድስት

የተዋሕዶ ፍሬዎች

24 Dec, 12:09


ድንግል ማርያም ተልኮ “ትፀንሻለሽ፣ ትወልጃለሽ” በማለት መድኃኒታችንን
ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትፀነስና እንደምትወልድ ነገራት። ይህም መጥምቁ
ዮሐንስ ከተፀነሰበት ጊዜ ፳፱ ቀን) አንሥቶ ሲቆጠር መጋቢት 29 ቀን ይሆናል።
መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት “መካን ትባል ለነበረችው (ለኤልሳቤጥ) ይህ
ስድስተኛ ወር ነው” ሲል የተናገረው የፅንሰትዋን ጊዜ የሚያመለክት አይደለምን?
ሉቃ 1፥36-38። ስለዚህ መጋቢት 29 ቀን ቃል ሥጋ የሆነበትና በድንግል
ማኅፀን የተፀነሰበት ዕለት ነው ማለት ነው። ከዚህ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ
ወንድ ልጅ በእናቱ ማኅፀን የሚቆይባቸውን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት (275
ቀናት) ስንቆጥር ጳጉሜን ጨምሮ ዕለተ ልደቱ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ላይ ይውላል።

ስለዚህም መጋቢት 29 ቀን የተፀነሰው ጌታችን ከኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ
ሁሉ ፈጽሟልና ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእናቱ ማኅፀን ቆይቶ ታኅሣሥ 29 ቀን
በቤተልሔም ዘይሁዳ ተወለደ። ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት
ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የታሪክና የትውፊት ማስረጃዎችን መሠረት
አድርጋ የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 29ቀን በታላቅ
ምስጋና ታከብራለች።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስርስትያን እና ሌሎችም ቤተ ክርስቲያናት በዓለ ልደትን ታኅሣሥ ፳፱ ቀን የሚያከብሩት በተረዳና በታወቀ ማስረጃና መሠረት ላይ ተመሥርተው ነው እንጂ እንዲሁ አይደም።

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ የምዕራባውያን የልደት በዓል ለምን December 25 ሆነ?

ይቀጥላል……

ሼር በማድረግ ለሁሉም እናድርስ
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Dec, 16:43


በዐብይ አሕመድ አሊ ዘመነ መንግሥት፦

፩   ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል ነው ከዚህ የተነሳ በሃገሪቷ ያሉ ምዕመናን ያለ ማንም ከልካይነት ይገደላሉ፣ሃብት ንብረታቸውን ይቀማሉ፣ቤታቸው ይፈርሳል ፣በግፍ ይሰደደሉ።

፪ ) ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ ሃገር እንዲመራ፣ሥልጣን እንዲይዝ ፣በመንግሥትና በግል መሥርያቤቶች እንዲቀጠር አይፈቀድለት።

፫)ፖለቲካ ፓርቲ እንዲመሠርት፣እንዲታጠቅና ከክፉዎች ራሱን እንዲጠብቅ አይፈቀድለትም።

፬) እርሰበርሱ እንዲጨራረስ የማይረባ አጀንዳ ይሰጠዋል።

፭) ልጅ መዉለድ እንዳይችል ቁጥሩም እንዲቀንስ  ይደረጋል(በክትባት፣በወሊድ መከላከያ)

፮  ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል መንቀሳቀስ ነውር ነው።ከተፈቀደልህ ዉጭ መኖር አትችልም።

፯  የጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ልዕልናዋን ማውራትም ሆነ ማስተማር የድሮ ሥርዐት ናፋቂ፣ነፍጠኛ፣አሓዳዊ፣ጨፍላቂ ፣አንድ እምነት ባይ፣ደንቆሮ፣ኋላ ቀር፣ጽንፈኛ  የሚል ታርጋ ያስለጥፋል ከዚህም አልፎ ለእሥርና ለሞት ይዳርጋል።በአንጻሩ ደግሞ ስለ" አዲሲቷ ኢትዮጵያ" የሚሰብኩ ይሸለማሉ ፣ሥልጣን ይመጸወትላቸዋል፣የለውጡ ደጋፊዎች  ተብለውም ይሞካሻሉ።


፰ አንድ ሰው ከብሔሩ ዉጭ  ትዳር መመሥረት አይችልም።

፱ ራሱ መንግሥት ከመሠረተልህ እምነት እና ሲኖዶስ ውጭ ሌላ መከተል አይቻልም።

፲ ኦርቶዶክሳዊነትን ማዋረድ እንደ ጀግንነት ይቆጠራል።

        ኢዮሳፍጥ ጌታቸው
ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Dec, 16:16


1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Dec, 16:08


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Dec, 05:40


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «ተወዳጆች። ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር) #በኢንቴክስ-ፉድ-ኤይድ-ፕላስ በሰላም ዘርፍ ዕጩ ሁነዋል። ሁላችንም በመምረጥ እኛኑ ለምነው ተጨንቀው ለጉባኤ ቤት ከሚደክሙት ባሻገር በዚህም ተሳትፈን ለዓላማቸው መሳካት መንፈሳዊ ድርሻችንን መወጣት አለብን። ካሸነፉ #10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ። 9355 ላይ BIW08 ን በመላክ መምረጥ ይቻላል። 🗓 ድምጽ መስጠቱ  እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17 ቀን…»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Dec, 05:40


ተወዳጆች።

ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር)
#በኢንቴክስ-ፉድ-ኤይድ-ፕላስ በሰላም ዘርፍ ዕጩ ሁነዋል።

ሁላችንም በመምረጥ እኛኑ ለምነው ተጨንቀው ለጉባኤ ቤት ከሚደክሙት ባሻገር በዚህም ተሳትፈን ለዓላማቸው መሳካት መንፈሳዊ ድርሻችንን መወጣት አለብን።

ካሸነፉ #10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ።

9355 ላይ BIW08 ን በመላክ መምረጥ ይቻላል።


🗓 ድምጽ መስጠቱ  እስከ ሐሙስ
ታህሳስ 17 ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Dec, 16:02


Live stream finished (5 minutes)

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Dec, 15:56


Live stream started

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Dec, 12:28


+ በብዙ ቋንቋዎች የተሰጠ ሃይማኖት አለን +


የክርስትና ሊቃውንት እንደሚሉት የእስልምና መጽሐፍ (በተለይ በቀድሞ ዘመናት ) በአንድ ቋንቋ ዘውግ በመወሰኑ መልእክቱ ከአሣሱ ለዐረቦች እንጂ ለሁሉም የሰው ዘር እንዲዳረስ የታሰበ አለመሆኑን እንደሚያመለክት ይጠቁማል ። "ከቆጵሮስ ሰዎች የተላከ ደብዳቤ" በሚል ርዕስ በሚታወቀው የ14ኛው መ/ክ/ዘመን የክርስትና ጥብቅና ደብዳቤ ሙስሊሙ የቆጵሮስን ሰዎች ለምን እስልምናን እንዳልተቀበሉ ሲጠይቃቸው ቁርዓን በዐረብኛ ብቻ መጻፍ እና ይህ ጉዳይ በራሱ በቁርዓን ትኩረት ተሰጥቶት የተደነገገ በመሆኑ እስልምና ሃይማኖት ለሌላቸው እና ብዙ ጣዖታትን ለሚያመልኩ ዐረቦች እንጂ ለእኛ ለክርስቲያኖች አይደለም እኛ በብዙ ቋንቋዎች የተሰጠ ሃይማኖት አለን እንዳሉት ተዘግቧል ። ( የልቦና ችሎት በረከት አዝማራው ገጽ-85)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Dec, 13:52


✞በዕፀ መስቀሉ✞

በዕፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ
የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ
ከፍቅርም በላይ ሆነና መሠጠኝ
ከመስቀል ሥር ሁኜ ፊቱን እያየሁኝ

ዓለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ
የጸብን ማዕበል በፍቅሩ የገታ
ሕይወቴን ጸጥ አድርጎ ይምራት በምልሐቱ
እኔ ምን አለፍኝ አልደክምም በከንቱ
አዝ= = = = =
ደሙ ከወዙ ጋር ተዋሕዶ ሲወርድ
በእኔ በደል ጌታዬ ቀረብልኝ ለፍርድ
ሀጥያቴን በጫንቃዉ ተሸክሞልኛል
በደሌን ደምሥሶ ንፁሕ አድርጎኛል
አዝ= = = = =
የቀራንዮ ግፍ በአንተ ላይ የሆነዉ
ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣዉ
እሾሕ አሜኬላዉ ተደምስሶልናል
የንጹሕ በግ ደም አዳምን ታድጓል
አዝ= = = = =
ይኽንን ሥጋዬን ብሉ ይላችሁዋል
ይኽንን ደሜንም ጠጡ ይላችሁዋል
ከመስቀል ሥር ሆነን ደሙን እንቀበል
ሥጋዉን እንብላ ሠዉ ሆይ ችላ አንበል

መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሀይሉ
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Dec, 06:18


ቁ ፩
share
@behle_abew
@behle_abew
@behle_abew

የተዋሕዶ ፍሬዎች

15 Dec, 03:54


#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Dec, 19:17


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት በቂምልሽ ተሰቶበታ ይቱብላይ ታገኙታላቹ።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Dec, 18:56


🌎አንዴ ብቻ ይንኩት አለማትን የፈጠረውን ጌታ በሕይወት ያመስግኑ ፣ ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቦታ በጣም ይጠቅማቹሀል !
                 👇👇👇

.            ✦              ‍ ‍ ‍ ‍                  ,    

.             .   ゚     .         🌑            .           .            

 ˚                     ゚     .               .      🌎 ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ,                * .                    .           ✦           ˚              *                      .  

.             .   ゚     .             .

      ,       .                               ☀️                                *         .           .             .                                                               ✦      ,         *   🚀        ,    ‍ ‍ ‍ ‍               .            .                                   ˚          ,                              .                 

         

             *          ✦                                .                  .        .        .     🌑            .           .            

 ˚                     ゚     .               .

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Dec, 05:41


ዘመኔን ሙሉ የጠበቀኝ አባት
የህፃንነት መናኝ
የበረሀው መናኝ
የሰማዕት ልጅ ሰማዕት
የካህን ልጅ ካህን



🥰 🥰 ዮሐንስ 🥰🥰

እንኳን አደረሳቹ ቤተሰብ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

07 Dec, 19:34


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

የተዋሕዶ ፍሬዎች

07 Dec, 18:16


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Dec, 19:45


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Dec, 19:15


ቅድስት ሥላሴ በአካል ስንት ናቸው?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

03 Dec, 19:47


❗️❗️❗️❗️❗️❗️

የተዋሕዶ ፍሬዎች

03 Dec, 15:03


የሰዎች ሃሳብ መማሪያችን እንጅ መደገፊያችን አይሁን

አንዱ ሰውዬ ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ ያለቅሳል።ይህንን የተመለከተ አንድ🙎‍♂ ሰው ወደ እርሱ ይመጣና"ለምንድነው የምታለቅሰው?" በማለት ይጠይቀዋል።ሰውዬውም " አንድ ማንኪያ ሙሉ ስኳር እዚህ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ የወንዙን ውሃ ብቀምሰው ምንም አይጣፍጥም" በማለት ይነግረዋል ፤ሌላኛው ሰውዬ በሳቅ  ፍርስ ይላል፡፡ ሰውዬው ግራ ተጋብቶ እንዴ"ምን ሆነህ ነው የምትስቀው?"በማለት ይጠይቀዋል።ሌላኛው ሰውየም በሳቁ መሃል አንተ ጅል! መጀመሪያ አታማስለውም ነበር! በማለት ይመልስለታል😃

አንዳንድ ሰዎችም እንደዚህ ናቸው ከአእናንተ የባሰ ስህተት ውስጥ እያሉ የተሻሉ እየመሰላቸው በትንሿ ስህተታችሁ ይስቁባችኋል፤ይሳለቁባችኋል፣ያጣጥሏችኋል።አንዳንድ ሰወች ሀሳብና አስተያየት ሲሰጡን ትክክለኝነቱ ሀሳባቸውን በነፃነት መግለፃቸው ብቻ የሚሆንበት ጊዜ አለ።የሚያውቁትን ስለነገሩን ብቻ ለእኛ ይጠቅመናል ወይም ከእኛ የተሻለ አውቀዋል ማለት አይደለምና የተነገረንን ሁሉ ለመተግበር እና ለመቀበል ከመቸኮል ባለፈ ቆም ብለን ማሰብና መመርመር አለብን።ምክንያቱም የአንዳንድ ሰዎች ምክር እና አስተያየት ከእኛ የባሰ ስህተት ውስጥ መሆናቸውን እንድናውቅ ያደርገናልና ከስህተታቸው እንድንማር ይረዳናል እንጅ ለችግራችን መፍትሄ ላይሆን ይችላል።

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

03 Dec, 04:27


“የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡”

አባ እንጦንስ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

02 Dec, 14:00


ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

የተዋሕዶ ፍሬዎች

29 Nov, 17:34


እመቤቴ የአምላክ እናት

እመቤቴ የአምላክ እናት
ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት
ለልጅሽም ክብር ውዳሴ
ታቀርባለች ዘውትር ነፍሴ(2)

ልቤ ተነሳሳ ተቀኘ ለክብርሽ
በፍጹም ልቦና ሊያመሰግንሽ
ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሀም ድንኳን
የታጠረች ተክል እመ ብዙሀን

አዝ

የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት
የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት
የሰማይ የምድር ንግስ ናትና
ክብር ይገባታል ዘውትር ጠዋት ማታ

አዝ

አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት
በምልጃሽ አስቢኝ ሗላ ስራቆት
ያንን የሳት ባህር አሻግሪኝ ድንግል ሆይ
እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@Yemezmur_Gitimoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
 

የተዋሕዶ ፍሬዎች

29 Nov, 17:28


የፅድቅ በር ነሽ

የፅድቅ በር ነሽ የሙሴ ፅላት
አክሊለ ሰማእታት መራከ ፀሎት
የጌታዬ እናት ንፁ አክሊላችን
አመልማለ ሲና እመቤታችን 2



እመቤታችን  ለኛ  ምርኩዝ ነሽ
እመቤታችን  ከለላም ነሽ
እመቤታችን  የእሳት ሙዳይ
እመቤታችን  እሳት ታቀፍሽ
እመቤታችን በብርሀን ተከበሽ
እመቤታችን ወርቅ ለብሰሽ
እመቤታችን ከሴቶች ሁሉ
እመቤታችን አንቺን መረጠሽ

አዝ

እመቤታችን ድንግል ሆይ ልጆችሽ
እመቤታችን ጥሪ ይጠሩሻል
እመቤታችን ስምሽን ለልጀ ልጅ
እመቤታችን ያሳስቡልሻል
እመቤታችን በተሰጠሽ ፀጋ
እመቤታችን በኣማላጅነትሽ
እመቤታችን ምህረትን አሰጪኝ
እመቤታችን ከመሀሪው ልጅሽ
 
አዝ

እመቤታችን ያለታረሰች እርሻ
እመቤታችን ዘር  የልተዘራባት
እመቤታችን የህይወትን ፍሬ
እመቤታችን ሰጠችኝ የኛ እናት
እመቤታችን የተሰዋው መሲ
እመቤታችን እናቱን ወደዳት
እመቤታችን በቀኙ ቆማለች
እመቤታችን ድንግል እመቤት ናት

አዝ

እመቤታችን የእውነት ደመና
እመቤታችን ዝናብ የታየባት
እመቤታችን ወዳናለች ድንግል
እመቤታችን የታተመች ገነት
እመቤታችን ትምህርት የሆነችው
እመቤታችን እንዘምርላት
እመቤታችን ደስ  ይበልሽ  እንበል
እመቤታችን የብርሃን እናት

join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

29 Nov, 17:27


#ሰባቱ_መንጦላእት

ሰባቱ መንጦላእት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
   
           አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
           ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍፁም ሠላምታ
            ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
            መለኮት እንዴት ነው የተዋሀደው
               
      ይሄን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
      ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጻል

                /አዝ=====

ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ከዓለም ስጋ ሆነ
ስፋትና ጥበት ሰማይና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሬ እና ግብር
           
      ይሄን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
      ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጻል

                /አዝ=====


         እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
         ትላንትና ዛሬን ያገናኘብሽ
         ምልኧትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
         ባንቺ ተዋሀዱ ፈጣሪ እና ፍጥረት
           
      ይሄን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
      ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጻል


                /አዝ=====

ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ህሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነግርግን አይችልም ምንም ቢገሰግስ
ከመሠወሪያው ዘንድ ከልጅሽ እንዲደርስ

    ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
    መልክአ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል


   join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Nov, 05:02


#ልጄ_ሆይ፦

ሕይወት አጭር ናት!
የሁሉም ሰው ትርፍ ትዝታ መሆን ነው።

ስለዚህ፦

👉ቅናትን
👉ምቀኝነትን
👉ተንኮልን
👉ኩራትን
👉ንቀትን እና
👉ከሰዎች መቆራረጥን

አስወግድ!!

የተዋሕዶ ፍሬዎች

26 Nov, 19:07


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare

የተዋሕዶ ፍሬዎች

26 Nov, 19:03


የመጥምቁ ዩሐንስ አባት ስም ማን ይባላል?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Nov, 14:24


ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመለሰ

+ 70 ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ +

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ማዕተብ በኩል 70 ወጣቶች ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በልጅነት ጥምቀትና በቄደር ጥምቀት ተመለሱ::

ጃን ማዕተብ ሥራ ከጀመረ ጊዜ አንሥቶ በአንድ ለአንድ (የገፅ ለገፅ) የትምህርት መንገድ የተማሩት እነዚህ ንዑሰ ክርስቲያን ከእስልምና ከፕሮቴስታንት ከካቶሊክ እና እምነት የለሽነት የተመለሱ መሆናቸውን የጃን ማዕተብ የንዑሰ ክርስቲያን ክትትል አስተባባሪ ዶ/ር ቤተልሔም ገልጻለች::

"በወላጆቻቸው ፣ በትዳር አጋሮቻቸውና በወዳጆቻቸው ጥቆማ ወደ እኛ የሚመጡትን ወጣቶች በመጀመሪያ ያሉበትን የግንዛቤ ደረጃ የመመዘኛ ቃለ መጠይቅ ካደረግንላቸው በኋላ በየርእሰ ጉዳዩ በጠነቀቁ (specialize ባደረጉ) መምህራን አንድ ለአንድ እንዲማሩ በማድረግ መምህረ ንስሓ በማገናኘት እስከጥምቀት ድረስ የማብቃትና የመከታተል ሥራዎችን ስንሠራ ቆይተናል" ያሉት የጃን ማዕተብ ሰብሳቢ ዲ/ን እርሱባለው ኩምሳ "ከተጠመቁት መካከል በሚገባ ተምረው በንዑሰ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ከእኛ ጋር ማገልገል የጀመሩም አሉ" በማለት ገልጸዋል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር የተቀላቀሉት ወጣቶች መካከል በሔዱባቸው ቦታዎች እስከ ሰባኪነት የደረሱና አንዳንዶቹም "የተሐድሶ" ሥልጠና ሠጪዎች የነበሩም እንዳሉበትና ለወራት በአንድ ለአንድ ትምህርትና ሱባኤ ጉባኤ በመማር ላይ እንደሚገኙ ተገልጾአል:: ከእነዚህም መካከል አስቀድሞ በዘማሪነት ሲያገለግል የነበረውና ወደ ተሐድሶ ተወስዶ የነበረው ዘማሪ ሐዋዝም ላለፉት ስምንት ወራት በጃን ማዕተብ ሲማር ቆይቶ በይፋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቄደር ጥምቀት ተመልሶ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይፋዊ የይቅርታ ደብዳቤውን አቅርቦአል::

ጃን ማዕተብ በብዙ ድካም የሠራውን የፕሮጀክት ምክረ ሃሳብ በመተግበርም በቀጣይ ጉዳይ ተኮር የሆኑ የዕቅበተ እምነት ጉባኤያትና ዐውደ ጥናቶችን በማዘጋጀት ሒደት ላይ መሆኑን የገለጸው ዲ/ን እርሱባለው "ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት" ላይ ማተኮርና የንዑሰ ክርስቲያን የመግቢያ ትምህርት ዶክመንት የማዘጋጀት ሥራዎችም እየተሠሩ መሆኑን ገልጾአል::

በጃን ማዕተብ የተሰናዳው "ወደ ኦርቶዶክስ (ወደ ቀናችው ሃይማኖት) መመለስ" የተሰኘ ዕቅበተ እምነታዊ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ማታ በጃንደረባው ሚድያ ቻናል ይለቀቃል::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#በፍጹም_ልብህ_ብታምን_ተፈቅዶአል

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

24 Nov, 03:26


"የኔ ፍቅር እስቲ ዛሬ ስጋ ጋብዘኝ"የሚል ድምጿ ነበር ከሀሳቤ ብንን ያደረገኝ፡፡ገና ከተዋወቅን'ኳ ሁለት ሳምንታችን እኮ ነው፡፡ሳያት.. ወጪ አታስወጣም፤ መጠጥ አጠጣም፤ ጨዋ ናት ብዬ ነበር የቀረብኳት፡፡ምክንያቱም እኔ ቁርስ ዘልዬ ምሳ አማካኝ ሰአት በልቼ እራቴን በማሰብ ብቻ የማሳልፍ መናጢ ደሀ ነኝ፡፡እሷን ቁርጥ ጋበዝኩ ማለት የወር ደሞዜን ለአንድ ወፍራም የስጋ ቤት ባለቤት በነፃ ገበርኩ ማለት ነው....

በዛላይ ወይን መጠጣት እንዴት እንዳማረኝ .....(ስትል ጭራሽ በተቀመጥኩበት ፌንት ልበላ!!!ሰይጣን ጎኔ የተቀመጠ ያህል አማትቤ እሷ መሆኗን ለማረጋገጥም ቃጣኝ፡፡ "እቺማ እሷ አደለችም'' እያለም ልቤ ይሞግተኝ ገባ።እሷ ግን እራሷ ፍሬዬ ናት...

እ....እሺ ችግር የለውም፡፡ማለቴ ትንሽ መሸት ቢል አይሻልም??(አልኳት ተበድሬ ያልመለስኩላቸውን ሰወች ቆጥሬ ስጨርስ ሌላ ምበደረውን ሰው እያሰላሰልኩ

እን..ዴ ፍቅር ቀን ነው እንጂ ሚጀመረው፡፡ ማታማ ታውቅ የለ....(ተሸኮረመመች፡፡ለካ የአልጋም አለብኝ!!!ነገሩ ይበለኝ....በዚ ኑሮ ውድነት እኔን የመሠለ መናጢ ሴት ጋ ምን ይሰራል?!ምንም፡፡እኮ ይበለኛ!!!

ፍሬ ከወትሮዋ ለየት ብላ ስትቅበጠበጥ ነገሯ አላማረኝም፡፡ከኑሮዬ ጋ ትመጥናለች ታረጋጋኛለች ለትዳር ትሆናለች ብዬ ብቀርባት ገና በቀናት ውስጥ ኑሮዬ ልትገለባብጠው የመጣች መቅሰፍ ሆና ታየቺኝ፡፡ምናልባት ደሞ የምትመርጠው ቤት ትልቅ ከሆነስ??.....(እንባ እንባ እያለኝ ተከተልኳት

የኔ ፍቅር እዚ ይሻለናል አደል...?(መስቀያው ላይ ነጭ ነገር ያንጠለጠለ ስጋ ቤት እያሳየቺኝ...ደነገጥኩ፡፡ስጋ ቀይ አልነበር እንዴ???መልኩን ቀይሮ ነው?

አይ እዚህማ ግርግሩ ጫጫታው እያልኩ ዘላብጄ ረከስ ያለውን ቤት ፍለጋ አይኔን ሳማትር ፍሬ እጄን እንደያዘች ከፊታችን ወዳለ ቤተክርስትያን አመራች....

የት ነው ምትሄጂው ፍቅር??(አልኳት መተንፈሻ ጊዜ ስላገኘሁ ልቤ ጮቤ እየረገጠ

ስጋ ቤት(አለች ፈገግ ብላ እያየቺኝ

እሱማ አዎ.. ታድያ እዚህ..

እኮ ስጋ ቤቱኮ እዚህ ነው፡፡(ነጠላዋን ከቦርሳዋ አውጥታ አንዱን ሰጥታኝ አንዱን እራሷ እያጣፋች

አልገባኝም!!

የኔ ፍቅር ለዘመናት እያየን ባላየን እየሰማን ባልሰማ ያለፍነው ምርጡ ስጋ ቤት ይኼ ነው!!

አየህ ፆም መያዣ ሲባል ሁሉም የሚመጣለት የበሬው ስጋ እና የሚጠጣው አለማዊ ወይን ነው፡፡እዚህ ቤት ግን እለት እለት ያለማቋረጥ የክርስቶስ ስጋው ይቆረሳል፡፡ደሙ ይፈሳል፡፡ያውም ደሞ በነፃ...ግን ሁላችንም የበሬው ስጋ ሰልፍ ላይ ሆነን አንድም ቀን አስተውለነው አናውቅም፡፡

አሹዬ..ቅድም ስጋ ጋብዘኝ ስልህ ምን ያህል እንደተጨነቅክ እያየውህ ነበር... ምናልባት አንድ ትልቅ ሚባል ቤት ብንገባ አድሮ ቢውል የሚበላሸውን ስጋ ብዙ ሺወች እናወጣበት ይሆናል፡፡እዚህ ደሞ ማንም የማይጋፋበት፤አንዴ ቢበሉት የማያስርብ፤አንዴ ቢጠጡት የማያስጠማ የክርስቶስ ስጋ እና ደም በነፃ እየታደለ ማንም ሰው በልቶት አያቅም፡፡እንዲያውም የማያስርበውን ምግብ ትተን የሚያስርበው ጊዜያዊውን ምግብ መቃረም ልማድ አድርገነዋል፤ስራችንም ሁሉ የፈሪ ፉከራ ሆኗል....አስተውለካል??ፈሪ ሁሌ ከሚጣላው ሰው ጋ ሳይገጥም በፊት እንዲሁ በፉከራ ይደክማል ልክ ግጥሚያ ሲጀመር ግን እሱ ሮጦ ከጠፋ ቀይቷል..

እኛም ልክ እንደዛው ነን፡፡ፆሙ ሳይገባ ክራችንን አስረን በየሆቴሉ ስንጎፈላ፤ ስንፎክር፤ እዩኝ እዩኝ ስንል አምሽተን ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ እዛው ስጋ ቤት ነን!!

ታድያ አይበቃም??እስከመቼ ፈርተን??እስከመቼ ለስጋ ወደሙ ራሳችንን ሰስተን?የኔ ፍቅር ስጋ ቤቱ ይኸውና ወይኑም (ደሙም)በነፃ እዚህ አለ፡፡ክርስትያን ፆም የሚይዘው ጭፈራ ቤት ሳይሆን እዚህ ነው!!ና አሁን ወደ ተከበረው ሥጋ ቤት እንግባ....
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

23 Nov, 18:46


🛑የወሲብ ቪዲዮ የምታዩ ተጠንቀቁ፣ እነዚህን ጉዳቶች እወቁ! የወሲብ ቪዲዮ የመመልከት 31 አደገኛ ጉዳቶች!

ለሁሉም ክርስቲያን እንዲደርስ
👉
#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉
@enatachinmaryam

የተዋሕዶ ፍሬዎች

23 Nov, 01:50


የጌታችን በዐለ ልደት መቼ? ለምን?

መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን? የልደት በዐል የሚከበርበት ቀንስ በምዕራባውያንና በእኛ ቤተክርስቲያን ለምን ተለያየ?
የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ ፳፱ ታከብራለች? ምዕራባውያንስ የልደትን በዐል ለምን December 25 ያከብራሉ?

በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Nov, 07:31


"የሠረቀሽ ሰው ካለ ለምን አትናገሪም'' ይሏታል ታክሲ ውስጥ ያሉ ሰወች በየተራ፡፡እሷ እቴ...ከገባች አንስቶ ዝም ብላ ትነፋረቃለች፡፡አታወራም፡፡እኛም የሆነችውን ከመገመት በቀር ግራ ገብቶን አስሬ እያየናት

እሺ ቆይ የት ነው ምትሔጂው (አልኳት፡፡ እንድታወራ እንጂ አለባበሷ እና የያዘችው የድባብ ጥላ እና ጧፍ ያስታውቃል

ሚካኤል አለች (ድምጿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ

በቃ እቺማ ተጠማቂ ናት፡፡ሚካኤል በእለተ ቀኑ ሊያሰናብትላት ነው...( አሉ ነጠላ ለብሰው ከኋላችን የተቀመጡት እናት፡፡ዞሬ ከማየት በቀር መልስ ሳልሰጣቸው መልሼ ምታለቅሰውን ሴት እያየኋት

እና ለምን ታለቅሻለሽ እሺ?? ለምን አትረጋጊም?? (ሁኔታዋ ግራ የገባው ነው፡፡ቸግሯት ነው እንዳልል አንገቷ ላይ ያለው የወርቅ ሀብሏ ይጣራል፤ሀበሻ ቀሚሷ እና የእጅ አንባሯ ከማማሩ የተነሳ አይን ያጥበረብራል።በዛላይ ቦርሳዋ ውስጥ ያለው ስልክ ያለማቋረጥ ይጮሀል..ታድያ ምን ሁና ነው??

እሺ ስልኩን አንሺው እባክሽ...አረ በበአሉ አታልቅሺ..

አለቅሳለሁ!! ነግሬው ነበር..ማህፀኔን ክፈት ታረቀኝ ቅረበኝ ብዬው ነበር ሚካኤል ጨከነ እንጂ፡፡ይኸው ተስፋ አድርጌው ስጠብቀው ዛሬም ልጅ ከለከለኝ!!ምነው እሱ... እኔን አይሰማም?እኔን አያይም??ደጅ መጥናቴን እንባዬን አይቆጥርም??ምነ እሱ..(የምላት ጠፋኝ።ለካ የከበደ ሸክሟን ላለመተንፈስ ኖሯል ዝም ያለችው

በቃ አይዞሽ የእግዚአብሔር ቀንኮ..

ቀኑ መቼ ነው??ይኸው ያልደረሰ ስለቴን ሳገባ 5አመቴ!! ተስዬ አታሳፍረኝም..ታሳካዋለህ..ዛሬ ባይሆን ነገ እያልኩ..ፀሎቷ እንደሰመረ፤ ልጇን እንደታቀፈች፤ እልል እያልኩ ስንቴ ታቦቱን ሸኘሁ??ስንቴ ለመንኩት??እና ቀኑ መቼ ነው??መልስልኛ??ቀኑን ታቃለህ??

(ቁጣዋ እየበረታ ሲመጣ ጭንቅ ያዘኝ፡፡ምነው ሚካኤል" አልኩ እኔም በልቤ፡፡እናቴ ተስላ ለምናው እንደማይዘገይ አውቃለኋ...ምነው ታድያ ልጇን ቢያስታቅፋት??እያልኩ በውስጤ እያብሰለሰልኩ

መጨረሻ!!(አለና ረዳቱ ከሀሳቤ ብንን አደረገኝ፡፡ከዛች ሴት መለየቱ ቢከብደኝም እንባዋን ለመጨረሻ ጊዜ እያየሁ

እናት አይዞሽ እግዚአብሔር አለ..ግን ስልክሽ አሁንም አላረፈም ምናልባትኮ...

ኤጭ!!!( እያለች ቦርሳዋን በርብራ አውጥታ "ሔለው'' አለች እሷም ንዝነዛው የሰለቻት ትመስላለች.....ከታክሲ ወርደን ጎኗ ቆሜ እያየኋት ከትንሽ ዝምታ በኋላ ምታለቅሰው ሴት ጥላዋን እንደታቀፈች ከመቅፅበት እልልታዋን አቀለጠችው...የማያቋርጥ፤ ጩኸት የቀላቀለ፤ ለዘመናት የታፈነ ረጅም እልልታ....

ዞሬ አጠገቤን ኋላዬን ፊቴን ቃኘሁ ምን መጣ?? ምን ተፈጠረ ???ምን ሆንሽ???

ዶክተር ደወለልኝ...የሠማሽው ውጤት ያንቺ አደለም ፀንሰሻል አለኝ፡፡ከቅድም ጀምሮ ሲደውል የነበረው እሱ ነው፡፡ሚካኤል ማህፀኔን ከፈተው....ሚካኤል ደረሰልኝ...አባቴ ታረቀኝ.....ልጅ ሰጠኝ....ሀያሉ ሰማኝ(ጥላዋን እንደታቀፈች እንባዋ የቀላ ጉንጯ ላይ እየዘነበ ፊቷን አዙራ ወደ ሚካኤል ቤተክርስትያን እሮጠች.....የሚካኤል ታቦት ወደ አውደ ምህረቱ ሲወጣ ደወሉ ሲደወል እኔም ከምእመናን ጋ ዝቅ አልኩኝ፡፡ቀኑ ዛሬ !!

"ቀኑ ያልደረሰ እንጂ ያልሠመረ ስለት የለም"
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Nov, 05:51


https://www.youtube.com/live/r5BHPvaR56s?si=zl3gyoiJEZ8lEzcf

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Nov, 19:33


✞ ይለይብኛል ሚካኤል ✞


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

አዝ====
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

አዝ====
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ===
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Nov, 18:11


ኅዳር 12

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል  ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

   ( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ!!


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Nov, 06:36


🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Nov, 15:23


https://www.youtube.com/live/aC9FUtVHFqs?si=wBUNYf59d2i_cuD4

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Nov, 03:29


Anyone online 👀? Check this👇👇

የተዋሕዶ ፍሬዎች

15 Nov, 07:41


ደብረ ቁስቋም

ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብጽ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

በስደቱም ጣዖታተ ግብጽ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፤ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቡና አውጥቶ አሳደደ፡፡

እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)

ጌታችን ኢየሱስ  በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቁርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮  የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም (ትርጉም ፳፻፫ ዓ.ም)
              ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

14 Nov, 13:33


ኦርቶዶክሳዊ ቻናል/ግሩፕ ያላችሁ ከ7k በላይ Promotion ውስጥ መግባት የምትፈልጉ ሳያመልጣችሁ


    👇👇👇
@Maryamn_27

የተዋሕዶ ፍሬዎች

14 Nov, 12:59


💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
💒                                          💒
💒      #የተዋህዶ_ፍሬዎች        💒
💒◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈💒
💒       ከ፩ኛ ዓመት ጀምሮ         💒
💒 መንፈሳዊ ኮርሶችን መማር     💒
💒          ለምትፈልጉ፦              💒
💒       እሄን ጹህፍ ነክተው         💒
💒    ወደ እግዚአብሔር ቤት       💒
💒        መግባት ይችላሉ           💒
💒  💠መልካም ትምህርት💠    💒
💒◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈💒
💒                                          💒
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒

የተዋሕዶ ፍሬዎች

13 Nov, 19:24


+ በመንፈስ ታድሳችሁ ስትነሱ መሰናክል ለሚሆኗችሁ እንዲህ በሉ +

አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ:: ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች

እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት::

ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው:: በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ ማንነትን ይለብሳሉ:: ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው:: ፈጣሪ "ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም:: "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም::

ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው:: ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር:: ከመመረጡ ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ:: ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም:: እርሱም በትሕትና  "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም : "ጭንጋፍ" ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም የማያንስ ሐዋርያ ነበረ:: እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም"  እርሱ መኖር አቁሞ በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ::

አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም::  በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ:: ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ::

ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር:: በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው:: አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው:: ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ::
ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ: "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን ተመካከሩ::
ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :-
አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር:: እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል:: (ዘፍ 50:15-21) ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ:: ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው::

እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም:: አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል:: "እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው" ነበር ያለው:: ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት ዮሴፍ አይደለም:: "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

ታሪኮቹን እየደጋገምን የምናቀርበው አስተማሪ ስለሆኑ ነው። 🙏🙏
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

10 Nov, 12:18


ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

10 Nov, 05:42


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Nov, 20:49


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Nov, 20:47


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

የተዋሕዶ ፍሬዎች

09 Nov, 17:12


ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ🌹🌹🌹

ንግሥተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል፤
(ኅብረ ሐመልሚል ቀይህ ወፀዓድዒድ)
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ፡፡
(የብር ዝንጕርጕር፣ የነጭና የቀይ ድብልቅ መልክ ያለው
ንጹሕ ተዓምርሽ በወርቅ አምሳል የተዘጋጀ ነው፤ ሊቁ አባ
ጽጌ ድንግል /ጽጌ ብርሃን/ የደረሰው እነሆ ያማረ የተወደደ
ማኅሌተ ጽጌ የተባለ ምሥጋና መላ፥ ተፈጸመ፤ የሰማይና
የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወዳጅሽ በእቅፍሽ
ውስጥ እንዳለ ይህንንም የማኅሌተ ጽጌ ምሥጋናን
ተቀበዪ፥ ወደ ሰማይ አሳርጊ፡፡)
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

07 Nov, 08:04


"ላለማመን እንጂ ለማመን በዙሪያችን ብዙ ምስክሮች አሉልን!"
         (ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ )

  | ዐይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርን መኖር የሚክዱ ተመራማሪዎች የራሳቸውን እውቀት መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔርን አለመኖር ከነገሩት በኋላ <እስኪ አንተ እግዚአብሔር መኖሩን በተጨባጭ አስረዳን?> ሲሉ ጠየቁት።

ቅዱስ ዲዲሞስ ተመራማሪዎቹ ጭልጥ ብለው መሳሳታቸውን ቢያውቅም በጥሞና ያዳምጣቸው ነበር እንጂ አልተበሳጨም።

ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "ምሽት ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው።

እነርሱም የቀጠሮአቸውን ሰዓት አክብረው ምሽት ተመልሰው መጡ።

ቅዱስ ዲዲሞስም "እስኪ ወደላይ አንጋጣችሁ የሰማዩን ገጽታ ተመልከቱ" አላቸው።

እነርሱም እንዳላቸው ሰማዩን ተመለከቱ።

እርሱም "በሰማይ ላይ ምን ምን ይታያችኋል?" አለ።

እነርሱም "ከዋክብት" ብለው መለሱለት።

እርሱም "በስጋዊ አይናችሁ የማየት ችሎታ እነዚህን ክዋክብት በቀን ማየት ትችላላችሁን?" አላቸው።

እነርሱም "አንችልም" አሉት።

እርሱም "ለምን ማየት ያቅታችኋል?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ደገመላቸው።

እነርሱም "ምክንያቱም ከዋክብትን ለማየት የግድ መምሸት አለበት" አሉት።

እርሱም "በእርግጥ ትክክል ናችሁ የመለሳችሁት ምላሽ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እንደምናውቀው የተሰወረውን ነገር ለማግኘት ብርሃን ያስፈልጋል። እነዚህን የምታዩአቸው ከዋክብት ለማየት ግን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ሊኖር የግድ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርንም ለማየት ቁሳዊ ነገርን ማየት በሚቻልበት በሳይንስ መሳሪያና ፍልስፍና ሳይሆን በእምነት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ልነግራችሁ እወዳለሁ።" በማለት አስረዳቸው።

ከዚያም እርሱ በተራው "በሰማያት ገጽታ ላይ ከዋክብት እንደሚታዩ ነግራችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ አይነ ሥውር ስለሆንኩ በምን ታረጋግጥሉኛላችሁ?" ሲል አዲስ የጥያቄ ርእስ ከፈተላቸዉ።

እነርሱም ግራ ተጋብተው ምላሽ አጡ እና ከመናገር ይልቅ ዝምታን መረጡ።

እርሱ ግን የእኔ አይነ ስውርነት የከዋክብቱን አለመኖር አያረጋግጥም፤ እኔ አየሁም አላየሁም ከዋክብቱ ዘወትር አሉ። እኔም ምንም ዐይነ ሥውር ብሆንም እንኳን ከዋክብቱን ሳልመለከት እናንተ አይታችሁ በነገራችሁኝ ምስክርነት ብቻ የከዋክብቱን መኖር አምኜ ተቀብየዋለሁ አላቸው። እኔ አንዳች ከዋክብት ሳልመለከት የከዋክብቱን መኖር እንዳመንኩ እናንተም በሥጋዊ አይናችሁ ባትመለከቱም እንኳን በእምነት እግዚአብሔር መኖሩን አታምኑምን? ብታምኑ መልካም ነው።" ሲል በትሕትና ጠየቃቸው።

እነርሱም በጥያቄ መልክ ያቀረበላቸውን አስተሳሰቡን እና ምስክርነቱንም ተቀብለው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት አረጋገጥን አሉት።

በዚህ የክርክርና የውይይት ሁኔታ ዐይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ (በትሕትናውና በድክመቱ) የተናገሩትን አድምጦ የእነርሱን ዕውቀታቸውንና አስተሳሰባቸውን ተጠቅሞ ክብራቸውን ሳይጋፋ የእግዚአብሔርን መኖር በማሳመን ረታቸው።

ክርክራቸውም በዚህ ተደመደመ።

ምንጭ ፦
በአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ በእንግሊዝኛ "CALMNESS" በሚል ተጽፎ በመምሕር ሰለሞን በቀለ "የሕይወት መንገድ" በሚል በአማርኛ ከተተረጎመ መጽሐፍ የተወሰደ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

07 Nov, 05:38


👉እንዴት በሀይማኖቴ ተደስቼ ልኑር?
1) ምስጋና
ባለህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግን።
ምንም ባይኖርህ እንኳን ወደ በጎው ሁሉ እንዲመራህ እየጸለይክ አመስግን ። ያንተን ያህል  ጤና ያንተን ያህል ከጎንህ የሚሆኑ ቤተሰቦች ፣ ስራ ካለህ ያንተን ያህል ስራ የሌላቸው ብዙዎች ናቸው፣
እግዚአብሔር ያደረገልህን ውለታ (ተዓምር ሊሆን ይችላል) አስታውስ በርሱ ደስ ይበልህ አመስግነውም።እግዚአብሔር ከመፈጠራችን ጀምሮ እስከ እድገታችን እኛ ባናስተውለውም ያደረገልን ተዓምር ብዙ ነው።
• ለምሳሌ እኛ እኮ የተወለድነው በየቦታው እንደአሁኑ ክሊኒክም ሆነ  የጨቅላ ህፃናት ህክምና ባልነበረበት ዘመን ነው።
• ብዙዎቻችን ክትባት ባንከተብም ከተለያዩ የልጅነት በሽታዎች ተርፈን አድገናል።
•  ብዙዎቻችን የውሀ እጦት ቢያሰቃየንም ከትራኮማ አምልጠናል
• ብዙዎቻችን ስንት ጊዜ ነው ከመኪና አደጋ የተረፍነው
•  ብዙዎቻችን በየሀገሩ ከነበሩ አለመረጋጋቶች ከጥይትና ከቦንብ ፍንዳታ አምልጠናል።
እንዲህም አመስግነው መድሀኒታችን  ሆይ ምን ውለታ  መመለስ ይቻለኛል? ላንተ እዘምራለሁ እንጅ


2) ሰዎችን አትውቀስ
ሰዎች ሁሌም በሁሉም መልኩ ፍፁም አይደሉም ጥሩ ነገር እንዳላቸው ሁሉ አንተ ክፉ የምትለው(ለእነርሱ እንደ ጥሩ የሆነ) ባህሪም ሊኖራቸው ይችላል
ሰዎች መልካም እንደሆኑ አስብ ዓሉታዊነትን አስወግድ

3) መልካም መልካሙን ማሰብ
ስለራስህም ሆነ ሌሎች በአዕምሮህ መልካም ነገር አስብ
የስበት ህግ በሁሉም ቦታ ይሰራል አንተ ስለራስህ የምታስበውን ነው የምትሆነው በራስህ ደስተኛ መሆን አለብህ። እኔ መልካም አይደለሁም ከሚለው ሐሳብ ይልቅ እራስክን መልካም ለማድረግ መጣር ላይ አተኩር።ጥሩ አርአያ ይኑርህ የእነርሱን ለመከተል ወስነህ ተጓዝ ነገር ግን ለምን እርሱን አልሆንኩም ብለህ ራስክን አትውቀስ አታወዳድርም። አርአያህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ሆነ አስተውል እርሱ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ እንዳለን።

4) መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያ
መዝሙር ያሬዳዊ የሆኑ ዜማውችን ማዳመጥ ልብን ይመስጣል እግዚአብሔርን አመስጋኝ ያደርጋሉ።
የመዝሙር መሣሪያን መለማመድም ሆነ መተግበር በሀይማኖትህ ከምትደሰትበት አንዱ ነው።

5) ግዕዝን ማወቅ
የኢኦተቤ ከግዕዝ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት ግዕዝን ማወቅ እጅግ ደስታን ይሰጣል ቅዳሴዋ ውዳሴዋ ቅኔዋ  አብዛኛው በግዕዝ ነው ግዕዝን ለመማር ባትችል እንኳን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ መጽሀፍት በሶፍት ኮፒም ይሁን በሀርድ ይገኛሉ። እነሱን በመጠቀም በቤክ ውስጥ ሲዘመር ሲቀደስ ማህሌት ሲቆም ላለመደናገር ቀደም ብሎ ሊዘመሩና ሊቀደሱ የሚችሉ ዜማዎችን እስከ ትርጉሙ አውቆ እየገቡ መሳተፍ፤ እነግርሃለሁ ከዚህ ዓለም ውጪ የሆነ ነገር ነው የሚሰማህ ደስታ።

6) ጸሎት
ከልጅነትህ ጀምሮ እየተንከባከበ ካሳደገህ ከሚሳሳልህ ከስጋ አባትህ ጋር ስታወራ ደስ ይልሃል።
ጸሎት ደግሞ ከሰማዩ አባትህ ጋር በኑሮህ ሁሉ ከሚረዳህ ሰላምን ከሚሰጥህ፣ ቸርነትን ከሚያደርግልህ ምንም ስትሆን አባ አባት ብለህ እንድትጠራው የልጅነትን መንፈስ ከሰጠህ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ስትነጋገር እንዴት ደስ አይልህ። በጸሎት ከጻድቃን ቅዱሳን ማህበር ከመላአክት ጋር ስትነጋገር እንዴት ደስ አይልህ።
በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴህ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ፀሎት አድርግ እንደሚረዳህም እየተገነዘብክ ደስ ይበልህ
በጸሎት አንተ የምትፈልገውን አስበህ መጠየቅ ነው ሚጠበቅብህ ሐሳብህን እግዚአብሔር ላይ ተማምነህ መጣል ነው ስራህን እግዚአብሔር ያከናውንልሀል ደስ አይልም።

7) መጽሐፍትን አንበብ
ቅዱሳን መጽሐፍት የነፍስ ምግብ ናቸው ያረጋጋሉ፣ ተስፋ ይሰጣሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ፣ ወደ ንስሀ ይመራሉ።
8) ከሀጢአት መራቅ ንሰሀ መግባት
ብዙ ማብራሪያ መስጠት ይቻላል ባጭሩ ግን ሰውነትህ ቆሽሾ ሻወር ወስደህ ለስጋህ ምን እንደሚሰማህ አስበው የነፍስህንም ሀጢአት ሲወገድላት ስጋህ ይደሰታል ነፍስህ ሐሴት ታደርጋለች
9)  ተሰፋ
ከዚህ ሁሉ በላይ በተስፋ ደስ ይበልህ ተስፋችን መንግስተ ሰማያት ናት። በዚህ ዓለም ምንም መከራ ቢፈራረቅብን ኃላፊ ነው የዚህ ዓለም ደስታም እንደዚሁ አንተ ደግሞ በጠበቧ መንገድ ስለምትጓዝ በብዙ ፈተና መካከል እንኳን ደስ ይበልህ። በሚመጣው አለም የዘላለም ህይወት እንዳለህ እያሰብክ በክርስቶስ ደስ ይበልህ። እግዚአብሔር ለቅዱሳን በሰጠው ቃል ኪዳን ደስ ይበልህ። በሐሳብህ የመላአክትን ማህበር የጻድቃንን ማህበር እያየህ ደስ ይበልህ።
10) ስጋወ ደሙን መቀበል
የደስታ መጨረሻ ከክርስቶስ ጋር ህብረት መፍጠር ነው። ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ወደዚህ ማማ መድረሻዎች ናቸው እውነተኛ የደስታ ምንጭ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
እነዚህና ሌሎች በሐይማኖት ተደስተን እንድንኖር ያስችለናል። ከዚህ በተጨማሪ አንተ ራስህ ምን እንደሚያስደስትህ በማሰብና በመመርመር ማግኘት ይቻላል።

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ
   
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera
   

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Nov, 14:46


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
       በእንተ ዕለተ ስቅለት
          እንጉርጉሮ
  በዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና



❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Nov, 14:44


#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Nov, 06:31


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የተዋሕዶ ፍሬዎች

06 Nov, 04:18


ውድ የተዋህዶ ልጆች 🥰 ይህን አዲስ እና ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻናል join እያልን ነፍሳችንን በቃለ እግዚአብሔር እናረስርስ🙏

ቻናሉን ሲቀላቀሉ  የሚያገኙት ነገሮች

✞የኢ/ኦ/ቤ/ን ስርዓቷን እና ዶግማዋን የጠበቁ ትምህርቶች
✞መንፈስን የሚያድሱ መዝሙራቶችን
✞አስተማሪ ታሪኮችን
✞የሰ/ት/ቤቱን ሁኔታ
✞እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኙበታል

👇#join ለማለት ይሄንን ይጫኑ👇
     👉 @fretewahdo24 👈
👉 @fretewahdo24 👈
    👉 @fretewahdo24 👈

የተዋሕዶ ፍሬዎች

05 Nov, 19:45


ጥምቀት ምንድነው?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

05 Nov, 19:40


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
https://t.me/addlist/d4ZokvPlExwzOWZk

የተዋሕዶ ፍሬዎች

05 Nov, 01:43


የኖትኮይን መስራች የሆነው #ሳሻ እና #የብሉም ምክትል Ceo ቭላድሚር ይሄ አዲሱን Paws ኤርድሮፕ ከጀመሩ ታዋቂ ሰዎች መካከል ይገኙበታል 😮‍💨🔥

Paws በብሉም በኦፊሺያል የትዊተር ገፅም በተደጋጋሚ የተተዋወቀ ሲሆን በWeb 3 የትዊተር ገፅም አዲሱ ዶግስ ይሆናል ሲሉ Paws ን ለብዙዎች አስተዋውቀዋል

Paws ላይ ያስገረሙኝ ነገሮች

1. ከቴሌግራም ድጋፍ ያለው መሆኑ
2. ከቴሌግራም ካልተደገፈ ቴሌግራም አካውንታችን የተጠቀምንበትን ቀን ማወቅ አስቸጋሪ ነው
2. ኖትኮይን የሰጠንን ቶክን ማወቁ
3. ዶግስ የሰጠንን ቶክን ማወቁ

እነዚህ ማሳያዎች የ Paws መስራቾች የሚታወቁ እና
#ከዶግስ #ከኖትኮይን እና #ብሉም በተጨማሪም #ከዱሮቭ ቴሌግራም ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን በቂ ማሳያ ነው

መጀመር ለምትፈልጉ ጊዜው ሳይሄድ በትጀምሩት አሪፍ ይመስለኛል 🫡

Link 👉


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=7Mj9rR5L

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Nov, 20:19


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

የተዋሕዶ ፍሬዎች

04 Nov, 20:12


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

የተዋሕዶ ፍሬዎች

02 Nov, 16:43


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የተዋሕዶ ፍሬዎች

02 Nov, 06:00


ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ሰው አንድ ታላቅ አባትን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ "አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነበንብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደእነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፤ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ የአፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?"

እርሳቸውም፦ "ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም በአፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው። አጋንንትን ለማባረርም ጥቅም ነውና። ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ትደርሰልሃለች፤ ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡" ሲሉ መለሱለት።

(ምንጭ፦ ፍኖተ አእምሮ)
ለመቀላቀል 👉 
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

31 Oct, 19:34


"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

31 Oct, 06:53


የዕለቱ ስንቅ

“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም

ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡

            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሠናይ ዕለተ ኀሙስ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

31 Oct, 02:11


የኖትኮይን መስራች የሆነው #ሳሻ እና #የብሉም ምክትል Ceo ቭላድሚር ይሄ አዲሱን Paws ኤርድሮፕ ከጀመሩ ታዋቂ ሰዎች መካከል ይገኙበታል 😮‍💨🔥

Paws በብሉም በኦፊሺያል የትዊተር ገፅም በተደጋጋሚ የተተዋወቀ ሲሆን በWeb 3 የትዊተር ገፅም አዲሱ ዶግስ ይሆናል ሲሉ Paws ን ለብዙዎች አስተዋውቀዋል

Paws ላይ ያስገረሙኝ ነገሮች

1. ከቴሌግራም ድጋፍ ያለው መሆኑ
2. ከቴሌግራም ካልተደገፈ ቴሌግራም አካውንታችን የተጠቀምንበትን ቀን ማወቅ አስቸጋሪ ነው
2. ኖትኮይን የሰጠንን ቶክን ማወቁ
3. ዶግስ የሰጠንን ቶክን ማወቁ

እነዚህ ማሳያዎች የ Paws መስራቾች የሚታወቁ እና
#ከዶግስ #ከኖትኮይን እና #ብሉም በተጨማሪም #ከዱሮቭ ቴሌግራም ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን በቂ ማሳያ ነው

መጀመር ለምትፈልጉ ጊዜው ሳይሄድ በትጀምሩት አሪፍ ይመስለኛል 🫡

Link
start https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=z6IVSdAp


@EBS_CRYPTO
@EBS_CRYPTO

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 19:35


በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴን ሲወቃ የእግዚአብሔር መልአክ ያገኘው ሰው ማነው ?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 19:29


አሁን የምንፆመው ፆም ምን ይባላል?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 14:03


#ከመናገር_ማሰብ_ይቅደም

"በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡
1️⃣ አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣
2️⃣ አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣
3️⃣ አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡

ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቦና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡ ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት...፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረክረክ ጀመረ አልቻለም ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና

«መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።

✳️የትምህርቱ አላማ ከመናገር ማሰብ ይቅደም እንዲሁ ከመናገር እናገናዝብ ሶስት ጊዜ አንድ ጊዜ ቁርጥ እንዳሉት አባቶች

🌷መልካም ቀን!!!
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 12:58


+++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++

ማልዶ ቤተክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!"

በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው?

ሼር  ያድርጉ
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 12:13


አንድ ደቂቃ ወስደው ያንብቡት ድንቅ ምክር ነው
(ለሌሎች ያጋሩት)

በሠርጉ ዋዜማ እናት ወንድ ልጇን ምን አለችው?

የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ!

አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት አንተ የማትረባ ስለው በጣም ተሸማቀቀ ወደ እኔ እየተመለከተ እንዴት እንደሱ ትያለሽ ? ሲለኝ ቀበል አድርጌ አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር።

ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ!

ካቋረጥኩበት ልቀጥል...... ልክ ብቻየን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ .. ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት እርሱም ተቀበለኝ .. ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ።

አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን። በደንብ አድምጣት ጋሻና መከታ ሁናት በጭንቅ ግዜ ከጎኗሁን ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሓሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር።

ልጄ.. . አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዟቸው ነበር አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ጨው አልጨመርኩም ነበር በጣም አፈርኩኝ አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍላጎቱ ጨምረው ተመገቡ።

እንግዶችም በሄዱ ግዜ ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ስለዋሸው ይቅር በለኝ አለ።

ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት።

ልጄ.. . ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ.. .ወሲብ ጥሩ ነገር ነው።ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል እኔ ግን እስከዚህ እሆናለው... አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት።

አስቸጋሪ ግዜያት ይመጣል አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር  ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ክፍል ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ግን አልተቃወምኩም ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት ምን ሆነሻል? አለኝ ምንም አልኩት ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነት ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት።

ልጄ.. .ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ብልህ ሁን።

እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ፀልዩበት ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር ።

በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው አንተ ምርጥ ልጄ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ሁሌም የእርሱን እርዳታ እሻ!!!

#Anani Moti
Like, Comment, Share.Lot's of thanks.
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 11:55


🤗እግዚአብሔር ላስደስት ብሎ ያስከፋው ጸሎተኛ ሰው ታሪክ!

ከቤተሰቦቹ ስር መሠረት ጀምሮ እግዚአብሔርን አክባሪና አምላኪ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘ አንድ በጣም ጸሎተኛ ሰው ነበረ
- ሁል ጊዜ ይጾማል
- ሁል ጊዜ ይሰግዳል
- ሁል ጊዜ ያስቀድሳል
- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን ይሄዳል
- ሁል ጊዜ እንግዳ ይቀበላል (በሃይማኖት የሚመስሉትን)

ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን አንድ ሽማግሌ ከበሩ ላይ ቆሞ ከመንገድ ላይ እንደመሸበት እና ማደርያ እንዳጣ እናም ሰዎች እርሱ ያሳድርኻል ደግ ሰው ነው ብለው ወደርሱ ቤት እንደ ጠቆሙት ያስረዳዋል።

ይሄ ሃይማኖተኛ ሰውም እውነት ነው ቤት የእግዚአብሔር ነው እኔም እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መጠን መልካም ሥራ እሰራለሁ ነገርግን የተወሰነ ጥያቄ እጠይቅሃለሁ አለው ።

መንገደኛውም ደክሞት ስለነበረ ላቡን በክንዱ ግንባሩን እየጠረገ ይችላሉ ጌታዬ ይጠይቁ እነሆ እመልሳለሁ በማለት ጎንበስ አለ።

ቀጥሎም ጸሎተኛው ሰው ሃይማኖትህ ምነው አለው...
መንገደኛው ሰውም እንግዳ ስሜት ተሰምቶት እእ... ሃይማኖት የለኝም አለ

ሃይማኖተኛው ሰውም ጠይቄውን ቀጥሎ ዕድሜህ ስንት ነው ሲለው 58 ዓመቴ ነው አለው ጸሎተኛው ሰውም አሰብ አድርጎ...

ይቅርታ በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ወደ ቤቴ አይገባም ብሎ መለሰውና

ወደቤቱ ገብቶ ጸሎት ሲጀምር ጌታ ሆይ ዛሬ በቤቴ ለማደር አንድ ሃይማኖት አልባ ሰው ከቤቴ ደጃፍ መጥቶ እንዳሳድረው ቢጠይቀኝ አባረርኩት አንተን ከማያምን ሰው ጋር ከምተኛ ሞቴን እመርጣለሁ አለ።


እግዚአብሔርም
ይህ ሰው ዕድሜው ስንት ነው በማለት ለጸሎተኛው ሰው ጥያቄ አቀረበለት...

ሃይማኖተኛው ሰውም 58 ዕድሜው ነው እግዚአብሔር ሆይ ሲል ተናገረ እግዚአብሔርም መለሰ...

እኔ 58 ዓመት ሙሉ ሃይማኖት ሳይኖረው ያሻውን ሲከውን ሲበድል ሲያጠፋ እያየሁ በምህረት ይህን ሁሉ እድሜ ተሸክሜው ከኖርኩኝ አንተ እንደምን በጣም ጥቂት ለሆነች ሰዓት ያህል የእግዚአብሔርን እንግዳ "ከቤቴ ሂድ" በማለት አባረርህ ?!

በል አሁን በከተማው ከእንዲህ አይነት ዛፍ ስር ተኝቶ ታገኘዋለህና ሄደህ ከቤትህ አምጥተህ እግሩን አጥበህ ምግብ ሰጥተህ በክብር አሳድረህ ጠዋት ላይ ወደ ሚሄድበት ቦታ ሸኘው አለው።

ጸሎተኛው ሰውም እግዚአብሔርን አስደስታለሁ ብዬ አስከፋሁ እያለ በራሱ እያዘነ ፈጣሪ ያዘዘውን ከወነ እግዚአብሔርም ይቅርታን አደረገለት ።

መንገደኛውም በተደረገለት ነገር በጣም ተደንቆ ቅድም እንድሄድ ነግረኸኝ አሁን ግን ካለሁበት ፈልገኸኝ መጥተህ ስለምን እንዲህ ባለ እንክብካቤ አሳደርኸኝ ብሎ ቢጠይቀው የተደረገውን በሙሉ ሲነግረው ልቡ ተነክቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቆ በክርስትና መኖር ጀመረ።


ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ኢየሱስ ክርስቶስ የተራበን አብሉ ሲል ሌላ መስፈርት አላስቀመጠም

በእኔ ያመኑትን አብሉ
በእኔ ያመኑትን አጠጡ
በእኔ ያመኑትን የታሰሩትን ጠይቁ
በእኔ ያመኑትን የታረዙትን አልብሱ
በእኔ ያመኑትን የታመሙትን ጠይቁ
በእኔ ያመኑትን እንግዶች ተቀበሉ አላለም በአጠቃላይ በአምሳሌ የፈጠርኩትን ትእዛዜን ፈጽሙላቸው አለ እንጂ እኛም የምናደርገውን መልካም ስራ በዘር በእምነት ሳንለይ እናድርግ የዛኔ አሕዛቡ በአምላካችን ትእዛዝ ልቡ ተሰብሮ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ይመለሳልና መልካሙን ነገር ከሰው ሰው ለይተን አንተግብር።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

      ✍🏾 ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

30 Oct, 11:52


#ቡናንና #ምግብን #በተመለከተ
ቡና በእለተ ሠሉስ ከተፈጠሩ እፅዋት አንዱ ነው። በገነት ዕፀ ሕይወት፣ ዕፀ በለስና ሌሎች ዕፅዋት ነበሩ። ለአዳም ከዕፀ በለስ በስተቀር ሌላው ተፈቅዶለታል። በኋላ በኦሪት በደብረ ሲና ፈጣሪ ለሙሴ የሚበሉና የማይበሉ አዕዋፋትና እንስሳትን ለይቶ ነግሮታል። በዚህ ሥርዐት እስከ ክርስቶስ መምጣት እስራኤላውያን ተመርተውበታል።[ኦሪት ዘሌዋውያንን በሰፊው ተመልከት]።

በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን ሂዱ ሰውን ሁሉ እያስተማራችሁ እያጠመቃችሁ ደቀመዝሙሬ አድርጉት ብሎ ይልካቸዋል።ማቴ.27፣18። ሲልካቸው ከአይሁድነት ወደ ክርስትና የተመለሱ አሉ። [ከዚህ ላይ አንድ ማለት የምፈልገው የኦሪት አስፈላጊነት ወደ ወንጌል መምራት ነው። ዮሐንስ አፈወርቅ ኦሪትሰ መርሐ ኮነተነ እንዲል። ገና በኦሪት ለእስራኤላውያን አዲስ ሕግ እሠራላችኋለሁ። አማኑኤል ይወለዳል እያለ ትንቢት ሲያናግር ቆይቷል። በኋላም አማኑኤል ተወልዶ አዲስ ሕግ ሐዲስ ኪዳንን ሠርቶልናል። ስለዚህ ማንኛውም አይሁዳዊ ክርስትናን እንዲቀበል ራሱ አዲስ ሕግ እሠራለሁ ስላለ መቀበል የውዴታ ግዴታው ነው። አለበለዚያ ኦሪትን የማይቀበል አይሁዳዊ ቁጥሩ ከአረማውያን ይሆናል]።ሐዋርያት አይሁድን አስተምረው ወደ ክርስትና እንደመለሱ ሁሉ አረማውያንን አሕዛብንም አጥምቀው አስተምረው ወደ ክርስትና መልሰዋል።

ይህ ሲሆን በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሊሰብክ ሲሄድ ከአይሁድነት የተመለሱ ክርስቲያኖችና ከአሕዛብነት የተመለሱ ክርስቲያኖች እርስ በእርስ መናናቅ መጣላት ይጀምራሉ። ከአይሁድ የተመለሱት እኛማ ቀድሞም የእግዚአብሔር ሕዝብ ስንባል የኖርን ነን፣ ነቢያትንም እያስነሳ ሲያስተምረን ኖሯል። በኋላም ወደዚህ ምድር በሥጋ ሲወለድ ከእኛ ነው የተወለደ እያሉ የዘረኝነት ሐሳብ ያነሳሉ። ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱት ደግሞ እንዲህ ብለው ይመልሱላቸዋል "ሕዝበ እግዚአብሔር እንባላለን ትላላችሁ እንጂ ጣዖት አምልካችሁ አሮን አሮን ግበር ለነ አማልክተ እለ የሐውሩ ቅድሜነ ወእለ ይጸብኡ ጸረነ እያላችሁ ሙሴ ከደብረ ሲና ሲመጣ ጣዖት ስታመልኩ አላገኛችሁምን!? ነቢያትን ከእኛ አስነሳልን ትላላችሁ እንጂ ነቢያትንማ ኤርምያስን በድንጋይ ወግራችሁ ገደላችሁት፣ ኢሳይያስን በመጋዝ ተርትራችሁ ገደላችሁት እንጂ መች ተጠቀማችሁባቸው፣ ክርስቶስ ከእኛ ተወለደ ትላላችሁ እንጂ ከእኛ ከአሕዛብ ወገን የሚሆነው ጲላጦስ ሊያድነው ቢወድ ስቀለው ስቀለው ብላችሁ የሰቀላችሁት እናንተ አይደላችሁምን እያሉ መከራከር ይጀምራሉ። በምግብ ዙሪያም ከአይሁድነት የተመለሱት እንደ ኦሪቱ ሥር ዐት ሲሄዱ ከአሕዛብነት የተመለሱት ግን እሪያውንም ምኑንም እየበሉ ቀጠሉ።

ከዚያ ቅዱስ ጳውሎስ "ጥሬ ሥጋን፣ ሞቶ ያደረን እንስሳ፣ ታንቆ የሞተን እንስሳ፣ ለጣዖት የታረደን" እኒህን አትብሉ። በሌላው ግን የሚበላው የማይበላውን አይንቀፈው። የማይበላውም የሚበላውን አይንቀፈው ብሎ መልእክት ይልካል። በሐዲስ ኪዳን የተከለከሉ ምግቦች እኒህ ናቸው። ጥሬ ሥጋ አትብሉ መባሉ እስመ ነፍስ ተኀድር በደም ስለሚል ነው። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 23 ስለ ምግብ ይናገራል። በዚህም መርዝነት ያላቸውን እንስሳት፣ አዕዋፋት፣ እፅዋት እንዳንበላ ታዟል። ይኽውም ስለ ብዙ ምክንያት ነው። አንደኛው ለምሳሌ መርዝ ያለውን ነገር ብንበላው መርዙ ይገድለናል። ይህን ጊዜ ራስን መግደል ስለሆነ ከ10ሩ ሕግጋት ኢትቅትል (አትግደል) ያለውን ሕግ አስሽሮ በነፍስ ስለሚያስፈርድ ነው። አካላዊ ጉዳት፣ ስነልቡናዊ ጉዳት፣ የሚያመጡ ምግቦችን እንዳንበላ ታዘናል። ይኽውም አካላችን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለሆነ (አንትሙ ውእቱ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር) እንዲል አክብረን መያዝ አለብን። አካላችን ከእግዚአብሔር የተሰጠን የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና።

ከዚህ በተረፈ ግን ማንኛውም ሰው የሚመቸውን ቢበላ እና ቢጠጣ ነውር የለበትም። ቡና ይጠጣል። ቤተክርስቲያን ቡና አይጠጣም ብላ ሕግ አልሠራችም። ምናልባት አንዳንድ ገድላት ላይ እና ድርሳናት ላይ አግኝተነዋል የሚል ካለም። በሊቃውንት ጉባኤ ሳይታረሙ በግለሰብ ወይም በአንድ ደብር ብቻ የታተሙ ገድላት እና ድርሳናት ስላሉ እነርሱን ምስክር አድርጎ ማቅረብ አይቻልም። ገድላት እና ድርሳናት አዋልድ ናቸው። አዋልድ ማለትም የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ማለት ነው። ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረተ ሐሳብ ውጭ በተቃራኒ የተጻፉ ካሉ ይታረማሉ። የሊቃውንት ጉባኤ የተመሠረተውም ለዚህ ነው። አዋልድ መጻሕፍት በዋናነት በ81ዱ ከዚያም በ7ቱ መጻሕፍተ ሊቃውንት እና በመጽሐፈ መነኮሳት ሚዛንነት ይመዘናሉ። ከዚያ በተቃራኒ ካሉ ግን የሚታረመው ታርሞ ከሌሎች ቅጅዎች ጋር ተመሳክሮ ይታተማል።

ለምሳሌ ገድለ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዲ ላይ አጼ ዘርዐ ያዕቆብን እንደ ዳግማዊ ዲዮቅልጥያኖስ አድርጎ ያቀርበዋል። ተአምረ ማርያም ላይ ደግሞ እንደ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ አድርጎ ያቀርበዋል። ስለዚህ አንዳንድ ገድላት እርስ በእርስ የመቃረን ምልክት ሲያሳዩ ምክንያቱ ብዙ ነው። አንዳንዱን አላዋቂ እንደ ሥርዋጽ እያስገባ ስለጻፈው ነው። አንዳንዱን ደግሞ ሚሲዮናውያን ስለበረዙት ነው። ብቻ ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ቡናን የሰይጣን ሽንት ነው ያሉ ሰዎችንም ሰምቻለሁ። ይሄ ካለማወቅ የመነጨ ነው። ሰይጣን መንፈስ ነው ስለዚህ እንኳን ሽንት መሽኛ የለውም። ስለዚህ ቡና መጠጣት የምትወዱም ጠጡ። የማትወዱም ካላችሁ ደግሞ ግድ ጠጡ አንልም። ነገር ግን የሚጠጣውን አትንቀፉ። ትልቁ በደል በዚህ ምክንያት ቡና የሚጠጣውን መንቀፍ ነውና። በተረፈ ቡና አይጠጣም እያሉ እየዞሩ የሚያስተምሩ ሰዎችን የጎንደር ግምጃ ቤት ማርያም መምህር የነበሩት መጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት "የቡና ሐዋርያት" ይሏቸው ነበር። የቡናን ሐዋርያት አትስሟቸው። አሁን ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች አሉብን። እንደ ቤተክርስቲያን አሳሳቢ የሆኑ ብዙ ጉዳዮችም አሉ። እንደ ሃይማኖተኛ ከእኛ ምን ይጠበቃል! እንደ ሀገርስ የሚሉትን ጉዳዮች ግን በሰፊው የምመጣበት ይሆናል።ስለዚህ በቡና እና በምግብ ጉዳይ ደግሜ አልጽፍም። ያው በዚህ ጉዳይ ጻፍልን ያላችሁኝ ስለነበራችሁ አንድም ለመታዘዝ ነው።ሌላው አንዳንድ እንደየ ገዳሙ የገዳም ልዩ ሥርዐቶች ይኖራሉ። ለምሳሌ ጠላ ተጠጥቶ በዚያው ቀን የማይገባባቸው ገዳማት አሉ። ከዚያ ገዳም ጠላ ጠጥቶ መግባት አይቻልም። ከዚያ ገዳም ጠላ መጠጣትም አይቻልም። ይህ ማለት ግን እንደ ክርስትና ጠላ አይጠጣም የሚል ድምዳሜ አያስይዝም። የዚያ የገዳሙ የተለየ ሥርዐት ነው። አንዳንድ ገዳማት ደግሞ ሴት የማይገባባቸው አሉ። ከዚያ ገዳም ምሳሌ ክብራን ገብርኤል ሴት አይገባም። ይህ ማለት ግን ሴት ልጅ ገዳም እንድትገባ አይፈቀድም የሚል ድምዳሜን አያስይዝም። ወንዶች የማይገቡባቸው የሴቶች ገዳማትም አሉ። ለምሳሌ ጣና እንጦንስ ገዳም ይህ ማለት ወንድ ልጅ ገዳም አይገባም የሚል እይታን አይሰጥም። ለተጠቃሹ ቦታ ብቻ የሚያገለግል ሥርዐት አለና። እንደ ጠቅላላው ግን ጠላም ይጠጣል። ሴትም ወንድም ገዳም መግባት ይችላል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
https://t.me/yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Oct, 20:06


ቤተክርስቲያን አንዲት ነው። በእርሷ ሁላችንም በክርስቶስ አንድ ነው። የዘረኝነትን እሳቤ ከአእምሮ ውስጥ ነቃቅሎ መጣል ያስፈልጋል። ክፋትን በእኩልነት ማውገዝ፣ መልካም ነገርንም በእኩልነት መቀበል ይገባል። በብሔሩ ምክንያት ጻድቁን ኃጥእ፣ ኃጥኡን ጻድቅ ማለት አይገባም። ክርስትና እውነትን እውነት፣ ሐሰትን ሐሰት ማለት ነው።

ዘረኛ ሰው ክርስቲያን ነኝ አይበል። ክርስቲያን ከሆነ የክርስቶስ ነው። የክርስቶስ የሆነ ደግሞ ሰውን በሰውነቱ በግል ማንነቱ ይለካዋል እንጂ በጅምላ አይናገርም። ከጅምላ ፍረጃ፣ ከዘረኝነት መላቀቅ ያስፈልጋል።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

28 Oct, 11:40


💔  ክፉ ቀን 💔  
✍️  ይህቺ  ልጅ ዳግማዊት ሰለሞን በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሀይማኖት ቤ/ን ሰ/ት/ቤት ውስጥ የምታገለግል የ 18 አመት ብላቴና ናት። ገና ሮጣ ሳትጠግብ የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ነው እንደ ቀላል የታየው የእግሯ ህመም አልጋ ላይ የጣላት። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሀኪሞች ቦርድ ህመሟ "የአጥንት መቅኔ" እንደሚባልና ህክምናውንም በውጭ ሀገር መከታተል እንደሚገባት ቀጥሎም ገንዘቡም 4 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር እንደሚያስፈልጋት ይነገራታል።
  ✍️  አባቷ መቶ አለቃ ሰለሞን አስፋው በውትድርና ከመቆየታቸውም በላይ ለእናት ሀገራቸው አንድ እግራቸውን ሰተው በክራንች የሚሔዱ በጡረታ ደሞዝ የሚተዳደሩ አባት ናቸው። ወሩ ደርሶ ከአስቤዛ ለማይተርፋቸው ሌሎች ማህበራዊውን ህይወት በችግር ለሚመራ ቤተሰብ 4 ሚሊየን እንደ ከባድ መቅሰፍት ነው።
✍️  " እኔ አንዴ አይደለም ለምን አስር ጊዜ አልሞትም ምንም አይመስለኝም። ብዙ ነገር አይቻለሁ። ልጄ ግን መማር ትፈልጋለች እንደ እኩዮቿ ማገልገል ትፈልጋለች መኖር  ትፈልጋለች😭 ቆማ መራመድ ትፈልጋለች ምን አለበት የሷን ለእኔ ባረገው"   አባቷ መቶ አለቃ ሰለሞን በእንባ የሚናገሩት ንግግር ነው።
✍️  ልጄን ከእግዚአብሔር በታች አድኑልኝ የሚለውን የበረከት ጥሪ ሁላችንም በደስታ ተቀብለን አነሰም በዛም ሳንል ለተወሰነ ቀናት በሚቆየው ቻሌንጅ ብንረባረብ ተሰፍሮ ከማያልቀው በረከት ተካፍለን ለእህታችንም እንደርስላታለን።  ይሔ  1000372941549  የአባቷ መቶ ሰለሞን አስፋው አካውንት ነው። የምታስገቡ እህት ወንድሞች ለማስተማርያነትና ለቁጥጥር ያመቸን ዘንድ አስገብታችሁ ስሊፑን በውስጥ መስመር ላኩልን።  ሁላችንም በምንችለው እንሳተፍ። የማንችል ደግሞ ሌሎች ወንድሞች እንዲመለከቱት ሼር በማድረግ እህታችንን ለመርዳት እንተባበር።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 12:01


ቅዱስ እስጢፋኖስ 🌷
================
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስትያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕት አንዱ ነው ... ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ እየወገሩት "እንደ ሀጢአት አትቁጠርባቸው" እያለ ለክፉ ወጋሪ ደብዳቢዎቹ ምህረትን የለመነ ሰማእት ነው: :

የዲያቆናት አለቃ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሁሌም ለሐዋርያት ይታዘዝና ያገለግላቸው የነበረ ሲሆን ብዙዎችን ወደ ሀይማኖት የመለሰ ወንጌላዊ ሰማእት ነው : :

ዛሬ የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ነው : : የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ረድኤት በረከቱ አይለየን 🙏

ጥቅምት 17

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 04:04


መስቀል ማለት ምን ማለት ነው ?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 02:14


*©ማርያም ጎየይኪ*
ጥራዝ 4. ቁ. 97

ማርያም ጎየይኪ እምገጸ ሄሮድስ/፪/
ለአርእዮ/፬/ ተአምረ ግፍዕኪ/፪/

ትርጉም፡- ማርያም ሆይ የግፍሽን ተአምር ለማሳየት
ከሄሮድስ ፊት ሸሸሽ ፡፡

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 02:14


*©አክሊለ ጽጌ*
 
  ጥራዝ 3.ቁ. 92
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀፀላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ክበበ ጌራ ወርቅ/፪/ አክሊለ ጽጌ/፪/

ትርጉም:- በአበባ የተሸለመ አክሊልን የወርቅ ዘውድንም የምታቀዳጂ ማርያም ሆይ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ አክሊል/የነገሠብሽ አክሊል/ ነሽ።

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 02:14


© *ምዕረ በዘባንኪ*
ጥራዝ 2.ቁ. 34

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ/፪/
በሀዚለ ሕፃን/፬/እፎ ደከምኪ/፪/

አንድ ጊዜ በጀርባሽ አንድ ጊዜ በጎንሽ
ሕፃን በመሸከምሽ /፬/ደከምሽ /፪/

  የሚዘመርበት ወቅት  መስከረም 26  እና ኅዳር 6

የተዋሕዶ ፍሬዎች

27 Oct, 02:14


*©የስደት ዘመንሽ*

መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ

በጠላት ፈተና ከሀገር ተሰደሽ
 ስትንከራተቺ አምላክን ታቅፈሽ
 ከገሊላ አንስቶ እስከ ግብፅ በረሃ
የሚያዝንልሽ አጣሽ የሚሰጥሽ ዉኃ
   አዝ
ሰሎሜ ትመስክር ያየሽውን ጭንቀት
 ዮሴፍም ይናገር የሀዘንሽን ብዛት
 እመቤቴ ማርያም ከአንድ ልጅሽ ጋራ
 በግብፅ በረሃ ያየሽዉ መከራ
    አዝ
  ውርጭና ፀሓዩ ሲፈራረቅብሽ
  ረሀብና ጥሙ እንዲያ ሲያንገላታሽ     
  በለጋነት ዕድሜ በሄሮድስ ቅናት
  ከልጅሽ ጋር አየሽ መከራ ስደት
         አዝ
   ልጅሽ አንዲምረን ስለእኛ እንዲራራ         
   ለበረከት ሆነ ያየሽው መከራ    
   መልካም ፍሬ አፈራ ያነባሽው ዕንባ
   ምክንያት ለኛ ሆነ ገነት እንድንገባ
       አዝ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Oct, 20:15


ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Oct, 19:49


የዘንድሮው freshman ተማሪዎች ከታች ባለው ሊንክ ያለውን ቻናል ተቀላቀሉ
@ze_campus_tips
@ze_campus_tips

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Oct, 14:32


"ስስታም ሰው... ኹሉንም እንደ እሳት የሚበላ፣ ኹሉንም ስልቅጥ አድርጎ የሚውጥ፣ የሰው ዘርን ኹሉ የሚጠላ ነው። ኹሉም ነገር የራሱ ይኾን ዘንድ ሽቶ አንድ ሰውስ እንኳን በሕይወት እንዲኖር አይወድም። በዚህ ላይም አያበቃም::

"ገንዘባቸውን ይወስድ ዘንድ ባለጸጎች እንዲኖሩ አይወድም፤ ይሰጣቸው ዘንድ ስለማይሻም ጦም አዳሪዎችን ይጸየፋቸዋል። ኹሉም የእርሱ ይኾን ዘንድ ሰዎች ኹሉ እንዲጠፉ ይፈልጋል፡፡ ምድርም ኹለመናዋ ወርቅ እንድትኾንለት ይወዳል እንጂ እንዲሁ ምድር ብቻ እንድትኾን አይፈልግም። ምድር ብቻ ሳትኾን ኮረብቶችም፤ ዕንጨቶችም፣ ምንጮችም፤ በአጭሩ ኹሉም ነገር ወርቅ ይኾን ዘንድ ይፈልጋል። [ሰማይም ወርቅ ብታዘንብለት አይጠላም።]"

~ የማቴዎስ ወንጌል፥ ቅጽ 2፣ ድርሳን 28፥5


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Oct, 14:08


"የምንጸልየው እግዚአብሔርን ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።"

        ቅዱስ አውግስጢኖስ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

25 Oct, 06:03


የትግራይን ቤተክርሲቲያን ገነጠልን "ሲኖዶስ" አቋቋምን እያሉን ነው!!


የእግዚአብሔር መንግሥት በእልህ እና ዘረኝነት አይወረስም ። ድርጊቱ ኢ ቀኖናዊ በመሆኑ ክህነት የሌለው ሲኖዶስ የሽማግሌዎች ስብስብ እንጅ ሲኖዶስ ሊሆን አይችልም ። ብድግ ተብሎ ሲኖዶስ መመሥረት ቢቻል ኖሮ ኢትዮጵያ ከ1600 ዓመት በላይ ደጅ ባልጠናች ነበር።

የትግራይ አካባቢ በክርስትናው ወርቃማ ታሪክ ያለው ነበር። ምን ያደርጋል አባት ነን ብለው ሕዝቡን ሸወዱት ክርስቶስን እና የክርስቶስ መንጋ በዘር ከፍለው በስልጣን እና ቂም የተያዙ ጳጳሳት ነን የሚሉ ሽማግሌዎች ጥቁር ታሪክ እየሠሩ ኑው። ፖለቲካን እና ሃይማኖትን እየለየን !!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 

የተዋሕዶ ፍሬዎች

24 Oct, 18:23


ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ኦርቶዶክሳዊያን እንደምን አመሻችሁ  ………?
ዲን ፍቅረአብ ወ/ሀና
ተመልሻለሁ እንዴት ናችሁ
የእግዚአብሔር ሰላምታ አይከለክልም እስኪ እግዚአብሔር ይመስገን በሉ 🙏

የተዋሕዶ ፍሬዎች

24 Oct, 07:55


👑ለራስ የሚመልሱት ጥያቄ

💍ወደ ትዳር የሚሄዱ ለራሳቸው የሚመልሱት ጥያቄ

    Bini Girmachew

የወደፊት ባል የምትሆነው ወንድም

   1)ሚስትህን በእውነት ትወዳታለህ?በሚገጥማት  ችግር የራስህን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለህም ቢሆን ለመርዳት ፈቃደኛ ነህ?

2)ምርጫዋንና መልካም ስብእናዋን ለማድነቅ ፍቃደኛ ነህ?

3) ከተወሰነ ዓመት  በኋላ ቢያንስ ከ40ዓመት በኋላ ሚስትህ ይህን ዓለም ስለምትንቅ መንፋሳዊ ፍላጎቷን ተከብርላታለህ?

4)ስሜቷ ስስ ስለሆን ብሶቷን ስትነርግህ ያለ ነቀፋ ታዳምጣታለህ?

5) ፈጣሪ የሚያስተምርህን እውነት አስበህ ታስተምራታለህ?

6)ነገ ከፍተኛ ሹመት ላይ ብትደርስ በከፍተኛ ትምህርት ብትመረቅ የእኔ ብለህ ትቀበለዋለህ?

7)በልጆቿ እና በሠራተኞቿ ፊት ላትነቅፋት ቃል ትገባለህ?

8)ምንም ብስጭት ቢገጥምህ ዱላን ላለመሰንዘር ቃል ትገባለህ?

9)ትዳርህ አንድ መንፈሳዊ አማካሪ በጋራ የምታከብሩት አንድ አዋቂ ወዳጅ አንዲኖረው አስበኀል?

10)አካላዊ ንፅሕናን የአፍ ንፅሕናን ያለማቋረጥ መጠበቅ ተዘጋጅተሀል?ይህ ለራስህ ያለህን ክብር ማያሳያ ነው።

11)ሱስንና ደጅ ማምሸትን ለመተው ዛሬ ወስነሀል?ልጅህ ምን አይነት ሰው እንዲሆን ትፈልጋለህ?ጻፈውና አንተ በሙሉነት ኑረው።ያን ጊዜ ልጅህ አንተ ይሆናል።

12)ያለህን ሀብትና ደሞዝህን ለማሳወቅ ፍቃደኛ ነህ?

13)ልጅ ባትወልዱ ከአሥር ልጅ ሚስትህ እንደምትበልጥ ታምናለህ?

14)በልጆቻችሁ ላይ  የጋራ አቋም እንዲኖራችሁ ትመካከራላችሁ?

15)ቤተሰቦቿ ባይወዱህም ለመውደድ ፍቃደኛ ነህ?

16)ወደ ትዳር ስትገቡ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷና ወዳጆቿ  ጋር ያላትን ኅብረት ታከብርላታለህ?

17)ሚስትህ እኩያህ እንጂ ተማሪህ አይደለችምና በእያንዳንዱ ነገር ልታርማት ትፈልጋለህ?አንዳንዱን ለማለፍ ዝግጁ ነህ?

18)የጋራ ጸሎታና ማዕድ እንዲኖራችሁ አስበህበታል?

19)ስጦታን መስጠት የሕይውትህ ሥርዓት ልተደርገው ትፈቅዳለህ?

   ፈጣሪ የሌለበት ኅብረት በድን ነውና እባክህ ፈጣሪህን ያዝ።

የወደፊት ሚስት የምትሆኚ እህት

1)ባልሽን በልብሽ ታከብሪዋለሽ?የቤቱ ራስ እንደሆነ ትቀበያለሽ?

2)ለልጆችሽ ባልሽ ክቡር መሆኑን ለመንገር ፍቃደኛ ነሽ?

3)ውበትሽ ፀጥታና ዝግታ መሆኑን አውቀሽ ራስሽን በእውቀትና በማስተዋል እየገነባሽ ነው ወይ?

4)የቤቱ ኃላፊነት በይበልጥ ያንቺ መሆኑን ተረድተሽ የራስሽንና  የቤትሽን ንጽሕና ለመጠበቅ ንቁ ነሽ?

5)የትኛውም ውጥረት ቢኖርብሽ ቤትሽ ቀድመሽ በመግባት ባልሽን መቀበል እንዳለብሽ ታውቂያለሽ?

6)ጣፋጭ ምግብ ሰርተሽ ለባልሽ ለማቅረብ ሙያ አለሽ ወይ? ምግቡን ሠራተኛ ቢሠራው ማቅረቡ ግን ያንቺ መሆን እንዳለበት ትገነዘቢያለች? አብዛኛው ወንድ ልጅ በሠራተኛው እጅ ምግብ ሲቀርብለት የራሱ ቤት አይመስለውም።

7)ከወደፊት ባልሽ ጋር ምንም የስጋ ዝምድና እንደሌላቸው አረጋግጠሻል?ከእህትሽ ወይም ከጓደኛሽ ጋር ጓደኝነት ያልጀመረ መሆኑን አረጋግጠሻል?

8)በትምህርትም በገንዘብም ራስሽን መቻል እንዳለብሽ ትገነዘቢያለሽ?ሁለታችሁ ከተስማማችሁ ችግር የለውም።ግን እንዳትቀሪ አስቢ። ደጁን ከረሳሽ ለባልሽም ማዘን አትችይም።

9)የባልሽ ቤተሰቦች አንዳንዴ ሊጠሉሽ ይችላሉ።አንድ ወንድን  ብዙ ሰው ሲወደው ይህ ይከሰታልና በደስታና በማስተውል ተቀበይው።

10) የልጆችሽ ኃላፊነት ይበልጥ ባንቺ ላይ እንዳለ ተረድተሽ ልጆችሽን በፈሪሃ እግዚአብሔር ለማሳደግ ቁርጥ ውሳኔ አድርጊ።

11)ልጅ መውለድ ያንቺ ችሎታ ሳይሆን የፈጣሪ ስጦታ መሆኑን ተረድተሽ ቢከለክልሽ እንኳ ደስተኛ ነሽ ውይ?ምናልባትም በሽታ ልጅ እንደ ይሁዳም ጌታውን የሚሸጥ እንዲወለድ አስበሻል ወይ?እንኪ ብሎ ቢሰጥሽ እንጂ ያውልሽ ብሎ ሲሰጥሽ ከባድ ነው።

12)የባልሽን ቤተሰቦች እንደ ራስሽ ቤተሰቦች ይቅርታ ታደርጊላቸዋለሽ?ካለሽ ላይስ ታካፊያቸዋለሽ?

13)ባልሽ ከደጅ ሲገባ ምንም ቢከፋሽ በብሩህ ፊት ትቀበይዋለሽ ወይ?ያንቺ ብሩህ ፊት ከሌለ ቤቱን ይጠላል።

14)የባልሽን እንግዶች በደስታ ታስተናግጃለሽ? ወንድ ልጅ በቤቱ እንግዶችን መጋበዝ ይፈልጋል።አንቺ ደስተኛ ካልሆንሽ ግን ሆቴል ይጋብዛል።

15)ወደ ትዳር ብትገቢ ብትወልጂም አንደ ድሮ ራስሽን ለመጠበቅ ጎበዝ ሴት ነሽ?

16)እስከ ጋብቻ ድረስ ክብርሽን ጠብቀሽ ለመቆየት ወስነሻል።ቆራጥ ሴትን አንበሳም እንደማይደፍራት ተገንዝበሻል?

17)ዘመናዊነት ሴት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊት ሚስጥ ለመሆን ፈቃደኛ ነሽ?

18)በቅንዓት እየፈጠርሽ ባልሽን መጠራጠር ባልሽን ስርቆት ማስተማር መሆኑን ተገንዝበሻል? ቤትን የሚሠራ ፈጣሪ ነውና በጸሎት ትጊ! ፈጣሪ ያማረውን ቤት ይስራልሽ!!!

✍🏾ተጻፈ የረጅም ዓመት ልምድ ባለው
የስነልቦና አማካሪ BINI GIRMACHEW

🧠ይህን አእምሮ የሰጠውን ፈጣሪ ሳላመሰግን አላልፍም 🙏🏾

የተዋሕዶ ፍሬዎች

23 Oct, 17:07


🌺በድንግል አማረ ህይወቴ🌺

በድንግል አመረ ህይወቴ
በማርያም አማረ ህይወቴ
ስጠራት ገብታልኝ ከቤቴ

በድንግል አማረ ከሞት መሀል ነጥቀሽ
በድንግል አማረ ነፍስን ዘራሺብኝ
በድንግል አማረ ሀጢያተኛ ሳለሁ
በድንግል አማረ ሰው አድርገሽ አ
ቆምሺኝ
በድንግል አማረ ሀዘን መከራዬ
በድንግል አማረ ታሪክ ሆኖ ቀረ
በድንግል አማረ ህይወቴም በአንቺ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
              አዝ====

በድንግል አማረ ሀጢያትን አብዝቼ
በድንግል አማረ ለምፅ ቢያጠቃኝም
በድንግል አማረ አንቺ እያነፃሽኝ
በድንግል አማረ ዳግም ብጨቀይም
በድንግል አማረ እሩሩ ነሽና
በድንግል አማረ ምልጃሽ አይዘገይም
በድንግል አማረ ስምሽን ስጠራ
በድንግል አማረ አታሳፍሪኝም(×፪)
               አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
                   አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በቃጥላ አማረ
በግሸን  አማረ
share 🌐 🌐 🌐 🌐 🌐 🌐 🌐
@Yemezmur_Gitimoche
@Yemezmur_Gitimoche

የተዋሕዶ ፍሬዎች

23 Oct, 02:51


የ ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ 3ኛ አመት የAccounting ተማሪ
የሆነችው እህታችን ሀይማኖት ደግፌ ባደረባት ህመም ምክንያት ትምህርቷን መከታተል አልቻለችም ህመሟም የጡንቻካንሰር አይነት ሲሆን በህክምና አጠራሩ Rhabdomiosarcoma ሲሆን ለዚህም በሰርጅሪ ህክምና ተድርጎላት አሁን የ chemotherapy ህክምና እየወሰደች ትገኛለች ቀጥሎም የ Radiotherapy ህክምና ያስፈልግታል ለዚህም ደግሞ የሚያስፈልገው ገንዘብ ሲሰላ ከ 100,000 ብር በላይ ድረስ ያስፈልጋታል ለዚህም እሷም ሆነ ቤታሰቦቹዋ የማሳከም አቅም ስለሌላቸው እናንተ
ወገኖቻችን ወገናዊ እጃችሁን እንድትዘረጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
እባካችሁ እህታችንን በአቅማችን በመርዳት ወደ ቀድሞ ጤንነቷ ተመልሳ ትምህርቷን እንድትከታተል እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።


Haymanot Degife Bosen 1000191370922

በስልክም ማነጋገር ለምትፈልጉ 0986252118


"እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፡ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።" ሐዋ 20:35
join share
🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐 🌐

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 19:11


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 19:01


የመጥምቁ ዩሐንስ አባት ስም ማን ይባላል?

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 16:52


" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው


ድምፀ ተዋሕዶ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

22 Oct, 11:32


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 12:10


#ሼር
#የካህኑን_ልጅ_እንድረስላት

በዓለም ዙርያ የምትኖሩ ልጅ የምትወዱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ በምስሉ የምናያት ህጻን ስርጉት ጥዑመ ልሳን ትባላለች።

ገና የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን ስትሆን ዕድሏ ሆኖ መናገርም መንቀሳቀስም በሰላም መተንፈስም መቦረቅም አልቻለችም ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ በህመም ላይ ነችና።

ወላጆቿ ምንም ገቢ ስለሌላቸው የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። ዛሬ ላይ #ወገን_ቢያግዘን_የተሻለ_ህክምና ብንሞክርላት ብለው ፊታችን ቆመዋልና ደጋግ ወገኖቻችን ከቻላችሁ በገንዘብ ካልቻላችሁ በሀሳብ፣ በጸሎትና ለሌሎች ረጂዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድታግዟቸው እንማጸናችኋለን።

ቄስ ጥዑመ ልሳን ገደፋው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000561662014

ለበለጠ መረጃ
ቄስ ጥዑመ ልሳን ➛ +251967438386

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 11:12


በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ ያደርጋል!

መጽሐፍም እንዲህ ይላል “ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።” መዝሙር 18፥25-26

አብራችሁ የምትውሏቸው ሰዎች በእናተ ሕይወት ላይ በጎም ክፉም ተጽኖ አላቸው። ማንነታችሁ የሚወሰነው አብራችሁ በምትውሏቸው ሰዎች ነውና አብሯችሁ የሚውሉ ሰዎችን ምረጡ ። መልካም ነገር እንኳን ቢኖራችሁ “አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33 እና ተጠንቀቁ
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

21 Oct, 04:45


የተዋሕዶ ፍሬዎች pinned «»

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 17:46


አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

⛪️⛪️⛪️⛪️

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

⛪️⛪️⛪️⛪️

"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።
⛪️⛪️⛪️⛪️

“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ

⛪️⛪️⛪️⛪️

"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን

★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

ምንጭ: Orthodox Notes (ON)
ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 06:13


share ይደረግ
🌐 @Ortodoxawit_wallpaper 🔂
🌐 @Ortodoxawit_wallpaper 🔂

የተዋሕዶ ፍሬዎች

20 Oct, 06:13


🌺በድንግል አማረ ህይወቴ🌺

በድንግል አመረ ህይወቴ
በማርያም አማረ ህይወቴ
ስጠራት ገብታልኝ ከቤቴ

በድንግል አማረ ከሞት መሀል ነጥቀሽ
በድንግል አማረ ነፍስን ዘራሺብኝ
በድንግል አማረ ሀጢያተኛ ሳለሁ
በድንግል አማረ ሰው አድርገሽ አ
ቆምሺኝ
በድንግል አማረ ሀዘን መከራዬ
በድንግል አማረ ታሪክ ሆኖ ቀረ
በድንግል አማረ ህይወቴም በአንቺ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
              አዝ====

በድንግል አማረ ሀጢያትን አብዝቼ
በድንግል አማረ ለምፅ ቢያጠቃኝም
በድንግል አማረ አንቺ እያነፃሽኝ
በድንግል አማረ ዳግም ብጨቀይም
በድንግል አማረ እሩሩ ነሽና
በድንግል አማረ ምልጃሽ አይዘገይም
በድንግል አማረ ስምሽን ስጠራ
በድንግል አማረ አታሳፍሪኝም(×፪)
               አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
                   አዝ====

በድንግል አማረ ሀዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድመኝ
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሺልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ በቃጥላ አማረ
በግሸን  አማረ
share
@yetewahedofera
@yetewahedofera

የተዋሕዶ ፍሬዎች

19 Oct, 05:35


ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን🌸

የተዋሕዶ ፍሬዎች

18 Oct, 06:46


“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።”
— ማቴዎስ 7፥1-2

“አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።”
— ሉቃስ 6፥37

“በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።”
— ሮሜ 14፥1


አትፍረዱ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

18 Oct, 04:59


እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የተዋሕዶ ፍሬዎች

15 Oct, 18:33


ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው። ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)