ወዳጄ! ሁል ጊዜ ለራስህ የታመንክ ሁን። አንተ ብቻ እውነት የሆነውን ፈጽም እንጂ ሰዎች ስለሚያስቡትና ስለሚያደርጉት አትጨነቅ። ወዳጄ! የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ነጻነት የሚያጣውና በብዙ ሰንሰለት ታስሮ የሚኖረው ይሉኝታ ስለሚይዘውና ሰው ምን ይለኛል የሚለውን ሀሳብ በልቡ በማግዘፉ ነው።
❤ ወዳጄ! በዚህ ዘመን እውነትን የሚኖር፣ ብልግናን የሚጠየፍ፣ ክፋትን የሚሸሽ፣ ሌብነት ዝርፊያና ኃጥያትን የሚንቅ ሰው አታገኝም። ደግሞም የልብህን የሚረዳ፣ እውነትህ የሚገባውና አንተ እያለፍክበት ያለውን መንገድ የሚያውቅ የለም። ሁሉም በመሰለውና በገመተው የሚፈርድ ነው።
❤ ወዳጄ! ሰውን እቃ አድርጎ የሚኖረው ዲያቢሎስ ነው። አንደበቱ እጅ እግር አይን ጆሮው የመንፍስ ቅዱስ የሆነ ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ነው። አሁን በምድር ያለን ሰዎች ያለ ሃይማኖት ምግባር ስርዓትና ህግ እንደ እንስሶቹ የምንኖር ነን። ስለዚህ ሰው ሰውን ቢወቅሰው ከእግዚአብሔር ህግ በመውጣቱና ነፍሱን የሚጎዳ ነገርን በማድረጉ አይደለም። ይልቁኑ እውነትን በመያዙ፣ እግዚአብሔርን በመውደዱ፣ ሃይማኖቱን በማጥበቁ፣ በመጾም በመጸለዩና ከአለም ጋር አንድ ባለመሆኑ ሰው በሰዎች ይከሰሳል ይነቀፋል ይጠላል ይሰደዳል ይበደላል ይሰቃያል ይሰደባል የሱ የሆነው ይነጠቃል።
❤ እናት አባት እንኳን በቤት ውስጥ ፈራ እግዚአብሔር ያለው ልጃቸው ላይ መከራና ፈተናውን ያበዛሉ። ወዳጄ! በጥፋት መንገድህ እንጂ በመልካምና በስኬት መንገድህ የሚደግፍህ የሚያጽናናህና የሚረዳህ የለምና ከሰው ሁሉ ሚስጥርህን ስራህን ኑሮህን ገንዘብህን አላማ ሀሳብህን ሁሉ ደብቅ። ብቻ በተግባር ከፈጸምክ በኋላ ይወቁ።
❤ ወዳጄ! አንተ ራስህን ከወደድክና ለእግዚአብሔር ከታመንክ ማንም ቢወድህ ቢጠላህ፣ ቢያቀርብ ቢያሸሽህ፣ ቢያከብር ቢያዋርድህ፣ ቢያደንቅ ቢያጥላላህ የሚሰማህ የደስታም ሆነ የሀዘን ስሜት የለም። ሰዎች ሁሌም ከእነሱ ጥቅም አንጻር እንጂ በእውነት መነጽር አይመለከቱም። ስለዚህ አንተ የሰውን አትንካ፣ ክፋትን አትፈጽም፣ እንዲህ ካሉ ሁሉ ጋር አንድነት አታድርግ እንጂ እነሱ ምንም ቢያደርጉህ ከታገስክ ለአንተ ሀብት ነው።
❤ ወዳጄ ራስን መውደድ ማለት ዘወትር በጾም በጸሎት በስግደት በንሰሀ እየቆረቡ የነፍስ ስራን መስራት ነው። ስለ ስራ ራስን ማስቀደም፣ ስለጥቅምና ሽልማት ወዳጅን ማስቀደም ነው። ይህን ያደረገ ሰው ለራሱ፣ አጠገቡ ላሉ ሰዎች፣ ለሀገሩና ለእግዚአብሔር ብዙ ይጠቅማል። ራስን መውደድ ለመብላት መጠጣት ለመልበስ ለቁስና ለስስት ከሆነ ግን አሁን እንደምንኖረው የሙታን ህይወት ሆኖ ይፈጸማል ዘመናችን🙏
✞ @orthodox_tewahdo_nen ✞
✞ @orthodox_tewahdo_nen ✞