Ethio Fm 107.8 @ethiofm107dot8 Channel on Telegram

Ethio Fm 107.8

@ethiofm107dot8


በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ethio Fm 107.8 (Amharic)

ኢትዮ Fm 107.8 ብንግስት እና ትምህርት እናደጋለው ። ከዚህ በፊት አገር ከኢትዮጵያ ነፃ ውይይቷ በነካ በጾበኞች እና ፋንች ላይ ውስጥ የቆመውን መረጃ እንዲያካፈል ያሰራገን እኛ ዊንፓልያዊ ከተማ ነን ። በሚቀጥለው በፍቅር ላይ ማሳየት ይቻላል ለማለት በተመለከተ የተቀናጀ የሳይንስ እቃዎች እንረዳለን ። ከዚህ እጅግ በርክቶ የተሻለ ተስፋፊ አለበለን ።

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 13:13


የቼልሲው ጄምስ አዲስ ጉዳት አጋጥሞታል

ሪስ ጄምስ ባጋጠመው ቀለል ያለ ጉዳት ምክንያት ከሌስተርሲቲው ጨዋታ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ አረጋግጠዋል ።

የቼልሲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በጉዳት ላይ፡ "አንድ የተጎዳ ተጫዋች ብቻ ነው ያለን እሱም ሬስ ጄምስ ትንሽ ነገር ተሰምቶት ነበር እናም ምንም አይነት ስጋት ልንወስድ አንፈልግም።
"በእርግጠኝነት የተጎዳው እሱ ብቻ ነው። የተቀሩት፣ አንዳንዶቹ የተሻሉ ናቸው፣ አንዳንዶቹ አሁንም ጥርጣሬዎች ናቸው፣ ማየት አለብን።

"የጡንቻ ችግር ነው እና ምንም አይነት አደጋ መውሰድ አንፈልግም።" ማሬስካ ለአጭር ጊዜ የሚደርስ ጉዳት መሆኑን ገልጿል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 13:06


የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖች በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንደሚያወግዝ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰጡ በተባለው መግለጫ ላይ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የሚወገዝ ድርጊት ነው ብለዋል።

የሸኔ አሸባሪ ቡድንና ጽንፈኛው ቡድን የተለያየ ቋንቋ ይናገሩ እንጂ ድርጊታቸው ተመሳሳይ ነው በማለት ገልጸው÷ ቡድኖቹ በህዝቡ መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር አስነዋሪ ድርጊቶች እየፈጸሙ መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪ የሸኔ ቡድን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጽመው ድርጊት የህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅና ልማት እንዲደናቀፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ራሱን ፋኖ እያለ የሚጠራው ጽንፈኛው ቡድን የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል ።

የክልሉ መንግስት በቡድኖቹ የሚፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊትን በማውገዝ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የህግ ማስከበር እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መጠቆማቸው የዘገበው ኢዜአ ነው።

በአሸባሪው ሸኔ ላይም ተከታታይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሰላም መንገድ የመረጡት የቡድኑ አባላት እጃቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል።

ህዝቡ አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖችን ለማስወገድ በጋራ እንዲቆምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 12:43


የአለም አቀፉ የወንጀኞች ፍርድ ቤት በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል፡፡

የአይሲሲ ፍርድ ቤት ኔታንያሁ እና ጋላንት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ጥፋተኛ አድርጓቸዋል፡፡

ይህም ረሃብን እንደ የጦር መሳሪያ መጠቀም ፣ ግድያ፣ ስደት እና ኢሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸምን ይጨምራል።

ቢቢሲ በሰበር ዜናው እንዳለው ይህ ማለት ኔታንያሁ እና ጋላንት የሮም ስምምነት ፈራሚ የሆኑትን 120 ሀገራት መጎብኘት አይችሉም ።


ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 11:21


ኢትዮጵያዊው ማርሻል አርት ተወዳዳሪ ሳቦም ኤልያስ 3 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሸናፊ ሆነ

በ ሀገረ አሜሪካ በተደረገ የ አለም አቀፍ ማርሻል አርት ፌስቲቫል ኢንተርናሽናል ውድድር ኢንስትራክተር ሳቦም ኤልያስ ኩመል አሸናፊ ሆኗል።

በሀገረ አሜሪካ ፍሎሪዳ ከተማ በአለም አቀፍ ማርሻል አርት ፌስቲቫል ውድድር 17 ሀገራት የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል።

ከ ኢትዮጵያ ብቸኛ ተወዳዳሪ የሆነው ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም ኤልያስ ኩመል በሦስት ውድድሮች በመሳተፍ አንድ ወርቅና ሁለት የብር ሜዳሊያ በማግኘት የኢትዮጲያን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲታይ አድርጓል።

ኢንተርናሽናል ኢንስትራክር ሳቦም ኤልያስ ኩመል በመጀመሪያ ደረጃ የፖተርን ውድድር የወርቅ ሜዳልያ፣ በነፃ ፍልሚያ ውድድር የብር ሜዳልያ፣ በሁለተኛ ደረጃ የፖተርን ውድድር የብር ሜዳልያ አግኝቷል።

ኢንስትራክተር ሳቦም ከዚህ ቀደም ለ 3 ተከታታይ አመታት (2022-2024) በአሜሪካን ሀገር በተደረገ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ውድድር አሸናፊ ነው።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 09:12


የዛሬ የህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 09:09


የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 08:58


የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ዛሬ ተጀምሯል

የመጀመሪያው ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝድ በማድረግ ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ በመቐለ ከተማ ነው በይፋ የተጀመረው፡፡

በመጀመሪያ ዙር በክልሉ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናና የማቋቋምያ ገንዘብ በመስጠት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀል ስራ ይሰራል።

በአሁን ሰዓት ታጣቂዎች የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች እና ሚድያዎች ፊት የታጠቁትን ቀላል መሳሪያ እያስረከቡ ነው።

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 07:55


ዩክሬን በብሪታንያና ፈረንሳይ ስቶርም ሻዶ ሚሳኤል ሩሲያን መደብደብ ጀመረች

አሜሪካ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን አሳልፋ መስጠቷን ተከትሎ ሁለቱ አገራት ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ዩክሬን ስቶርም ሻዶ በተሰኙ ሚሳኤሎች ሩሲያን ማጥቃት ጀምራለች ተብሏል፡፡

ሩሲያም የእጃችሁን ታገኛላችሁ ስትል እየዛተች ነዉ፡፡

የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በሰጡት ምላሽ አገራቸው ዩክሬን ለምትጠቀማቸው ለእነዚህ ሚሳኤሎች ተገቢውን ወታደራዊ ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።

ለዩክሬን ተሰጠ የተባለው ‘ዘ ስቶርም ሻዶ’ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ከዚህ በፊት የለንደንና እና የፓሪስ አየር ኃይሎች በባሕረ ሰላጤው አካባቢ በኢራቅ እና በሊቢያ ውስጥ ጥቅም ላይ አውለውታል።

የጦር አውድማ ላይ ሩሲያ የበላይነቷን እያሳየች ትገኛለች። የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ግዛቶች እየተቆጣጠሩ ወደፊት በመገስገስ ላይ ናቸው።

አባቱ መረቀ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

21 Nov, 07:52


በትግራይ ክልል ያለው ማህበራዊ ቀውስ ከጊዜ ጊዜ ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ተባለ

ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ በትግራይ ያለው ማህበራዊ ቀውስ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ከጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ሲሉ ትዴፓ ገልጿል።

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ገብረ ጊዮርጊስ ግደይ፣ በክልሉ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር የተራዘመ የማህበራዊ ቀውስ ችግር እንዲኖር አድርጓል ብለዋል።

በተለይም በክልሉ የሚገኙ የጊዜያዊ አስተዳደሩም ይሁን የህውሀት እና ትጥቅ ያልፈቱ አካላት በማህበረሰቡ ላይ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ ብለዋል።

የክልሉ ነዋሪ በኑሮ ውድነት ተፈትኗል ስደትን የመጨረሻ አማራጭ አርጎ እየተሰደደ እንደሚገኝ ያነሱት አቶ ገብረጊዮርጊስ በክልሉ ወጥቶ ሰርቶ መግባት ቅንጦት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት "ሁሉንም ያማከለ አካታች ውይይት ሊኖር ይገባል" ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ መልኩ ከጣቢያች ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ ከክልሉ ነዋሪ የተለያዩ ቅሬታዎች እንደሚደርሴቸው ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ሂደት በመንግስት መስሪያ ቤት የሚገኙ ሀላፊዎ እንቅፋት እንደሆኑም አንስተዋል ።

ለአለም አሰፋ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም