አንሶ ሚያደገድግ ትን ሲል እኔን ባይ
ሲወድቁ ሚነጠፍ ሲያስነጥሱ አባባይ
ከስር የማይጠፋ ልክ እንደራስ ጥላ
ጠገብኩኝ እያሉ በግድ የሚያበላ
ሰውማ መች ጠፋ…
ብኩርናውን ክዶ የሚሆን አገልጋይ
ንጉስ የሚያደርግህ ፈቅዶ በራሱ ላይ
ሳይበርድ የሚደርብ ሳይጠማ ሚያጠጣ
ዘራፍ ያሉ እንደሆን አብሮ የሚወጣ
ሰውማ መች ጠፋ…
በመራኸው ሚሄድ እንደከብት መንጋ
ይጠብቃል እንጂ…
የኪስህ ደጃፉ በብር እስኪዘጋ
🖌 ነጋ ገዙ
☆LIKE☆COMMENT☆SHARE☆
👉@hasabnbegtm🥀💚
👉@hasabnbegtm🥀💛
👉@hasabnbegtm🥀❤️