ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ @hymnsofmes Channel on Telegram

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

@hymnsofmes


Thank you for your interest to join
Our Telegram channel.
▫️The primary function of this channel is :
☞To proclaim our savior JESUS CHRIST through a lifestyle of praise and worship.

መዝሙረ ዳዊት 96
2፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ (Amharic)

ስለ ወደዚህ ታሪኩ ይደሰቱ፦ውጤእ መዝሙር ዳዊት! ናት አየር መድኃኔዓ ምስክርአት አለ። በትክክለኛ መብት ያሳያል፦ ፡፡ ለጸናጽ የእሱ መርሓ እና ምስሎች በመንፈሳዊ ቅኝ እና ቸሩ እንዲፈቀድ በማዳኑ ከፎቶ ይህን አዝናኝ መረጃ ማግኘት እና ምስክር በመጠቀም እንዲሆኑ እንጠቀምላት። ፡፡ ማዳኑን አውሩ ዝናም ነው፦ ጄስራስ ክሪስት በስተቀር፣ ቅኝ እና እንስሳ እናመሰግናለን። ወደ ሴቲንግስ ፡፡ 96 ፡፡ 2 ፡።

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

20 Nov, 08:44


#ዛሬ_የአምልኮና የቃል ጊዜ

🗓 እሮብ ህዳር 11/2017

ከምሽቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ

⛪️ ዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

18 Nov, 06:01


⭐️በ ማቴ 17 : 1-8 ኢየሱስ 3 የፀሎት ጓደኞች ነበሩት ። እነርሱም ዮሐንስ ፣ ዼጥሮስ እና ያዕቆብ ነበሩ።

⭐️በትንቢተ ዳንኤል 2:17-19 ስናይ ደግሞ ዳንኤል 3 የፀሎት ጓደኞች (ሲድራቅ ፣ ሚሳቅና አብድናጎ ) እንደ ነበሩት እናያለን።

⭐️የፀሎት ጓደኝነት ታላቅ ውጤት አለው። ሲፀልዩ የተቋጠረ እንቆቅልሽ ተፈቷል (ዳን 2:19 )። ከዚህ የምንማረው ዳንኤል የፀሎት ጓደኝነትን የያዘው በቅድስና ጉዳይ ከእርሱ ጋር አንድ አቋም ከነበራቸው ጓደኞቹ ጋር ነበር (ዳን 1:8)።

#የፀሎት_ጓደኝነት
- ተመሳሳይ ሸክም ያላቸው ሰዎች።
- ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ሰዎች።
- የመንፈስ እና የልብ አንድነት ያላቸው ሰዎች።
- ተመሳሳይ የፀሎት ትጋት ያላቸው ሰዎችን ያካትታል።

⭐️የፀሎት ጓደኞች ፀሎታቸው በጣም ውጤታማ ከመሆኑም በላይ ፈጣን የሆነ የፀሎት ምላሽ ያስገኛሉ። በፀሎታቸው ሰዓት የእግዚአብሔር መንፈስ በነፃነትና በሙላት ይሰራል።


🔔የፀሎት ጓደኛ አለህ / ሽ?


@hymnsofmes
@hymnsofmes

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

12 Nov, 12:49


ወደ ፊልጵስዩስ 1
6፤ በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤

🌟 Bishoftu Mehal Ketema Full Gosple Church
, Ethiopia Sunday Service Recap 🌟

November 10, 2024
#ማዳኑንአውሩ
@hymnsofmes

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

11 Nov, 08:54


የዕለቱ ቃል
⭐️ጳውሎስ በተከታታይ በተያያዙ አጫጭር ትእዛዛት በክርስቶስ ያለንን ሕይወት መግለጹን ቀጥሏል። በዚህ ቁጥር ውስጥ ያሉት ሦስቱ ትእዛዛት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ ደህንነት ቁልፍ ነገሮች ናቸው።
#በተስፋ_ደስ_መሰኝት።
#በመከራ_ታጋሽ_መሆን።
#በፀሎት_መፅናት።

⭐️ ተስፋ ወደፊት የሚያዝ ቢሆንም ዛሬን ያስይዛል። ይህም ማለት፣ ተስፋ ነገን እያስናፈቀ ለዛሬ የሚሆን ስንቅና አቅም ነው። ስለዚህም፣ "በተስፋ ደስተኞች ሁኑ" (ሮሜ 12፥12) ተብሎ ተጽፏል። ደስታው ደግሞ ነገን ብሩህ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን ዛሬንም የሚያፈካ ነው፤ ደስ የሚላቸው ብርሃን የበዛላቸው፣ ጉልበት የሚጨምሩም ናቸው። ተያይዞም፣ "በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ" ተብሏል።

⭐️መከራ ምሬትን በመውለድ ፈንታ ትዕግሥትን ሊያበዛ ይገባል። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች መካከል (መከራ) ደግሞ በጸሎት መጽናት የማይተካ መፍትሄ ነው። የመከራ ብዛት በጽኑ ጸሎት ይሳሳል፤ ይታለፋልም። ጊዜው ደስታ ባያመነጭም እንኳን፣ በእግዚአብሔር የተያዘ ተስፋ ዛሬን በደስታ ይሞላል።

⭐️ሕይወት ደስ የማይል ሊሆን ይችላል ፣ እና ሁሉም ጊዜዎች ደስተኛ ጊዜዎች አይደሉም። ሆኖም ጳውሎስ በምድር ላይ ያለው የህይወት ትግል ከሚመጣው ክብር ጋር ሲወዳደር ዋጋ እንደሌለው ጠቁሟል (ሮሜ 8፡18)።


ፀሎት🙏🏾

አባቴ ሆይ ስለጨመርክልኝ ቀን አመሰግንሀለው ፥ ወደ ጥሪዬ ግብ ስጓዝ በተስፋ እንድደሰት፣ በመከራ እንድጸና እና በጸሎት እንድጸና እርዳኝ። በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ ፤ አሜን 🙏🏾

⭐️ በመልዕክቱ ከተጠቀማችሁ ለ 1 ሰው #share አድርጉት።
@hymnsofmes
@hymnsofmes

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

06 Nov, 03:15


⭐️ ሐዋሪያው ጳውሎስ በኋላ ከሚጠቀምባቸው ቁጣ እና ማስጠንቀቂያ የተሞላባቸው የእርምት ቃላት አኴያ ስንመለከት ይህ መክፈቻ ይበልጥ አስደናቂ ነው።

⭐️በመካከላቸው ለሰማቸው የተሳሳቱ ባህሪዎች እና አመለካከቶች ምላሽ ለመስጠት የፃፈው ደብዳቤም ነው።

⭐️ጸጋን በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ ይቀበላሉ፤ ያለ ልዩነት ይሰጣልና። ጳውሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን የሚነቅፍባቸው ብዙ ነገር ቢኖርም፣ በጌታ ለሆኑትና ላገኙት ሁሉ ግን እውቅና ይሰጣል፤ "በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር ስለ እናንተ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ" (1፥4)።

⭐️ ይህ ጸጋ ማንነት ላይ የሚመሠረት ስላልሆነ የሰዎችን መንፈሳዊነት አይለካም። ተቀባዮቹ ሲጠቀሙበት ግን ጸጋው መንፈሳዊ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

⭐️ የጸጋ መብዛት ደግሞ ተቀባዮቹ እንዲታረሙ፣ እንዲያድጉና እንዲጸኑ ስለሚያደርግ እግዚአብሔርን ያስከብራል። ይህ ጸጋም በክርስቶስ የተሰጠ ብቻ ሳይሆን፣ በክርስቶስም የሚጠበቅ ነው።

🙏🏾ፀሎት!

እግዚአብሔር ሆይ ስለማይቋረጠው የ ጸጋ ስጦታህ ዘወትር ላመሰግንህ እወዳለው! ይህንን የጸጋ ስጦታ የሰጠህኝ ፥ የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ እየጠበኩኝ ፥ ደግሞ እስከ መጨረሻ ጸንቼ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድሆን ነውና ዕለት ዕለት አንተን እንድመስልህ በመንፈስህ ሙላኝ። በኢየሱስ ስም አሜን!!
———————————————————
#ማዳኑንአውሩ
@hymnsofmes

ማዳኑን አውሩ | ᴘʀᴏᴄʟᴀɪᴍ ʜɪꜱ ꜱᴀʟᴠᴀᴛɪᴏɴ

06 Nov, 03:02


“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ”
— ራእይ 21፥5 —

🌟 Yougo City Church
Addis Ababa, Ethiopia Sunday Service Recap 🌟

November 3, 2024
#ማዳኑንአውሩ
@hymnsofmes