የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ ዜጎችን ሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና አለመኖሩን” አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ “ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች እየተሰራጩ ነው” ሲል አሳስቧል።
ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሲልም አስጠንቅቋል።
“ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራሁ ነው” ሲል ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።
“የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም ሊሆን ይገባዋል” ሲልም አሳስቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm