Maleda Sport ማለዳ ስፖርት @yemaledasport Channel on Telegram

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

@yemaledasport


ዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ክስተቶችን በተለየ መልኩ ወደ እርስዎ የምናደርስበት ለእግር ኳስ መረጃዎች ትክክለኛው ቻናል👍👌

ጥልቅ እይታና ሚዛናዊ አቀራረብ መለያችን ነው!


Amazing channel on telegram 👏🙌


👇Admin👇
👉 @alrightmama 👉 @Hello_CJ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት (Amharic)

ማለዳ ስፖርት በተለየ መልኩ ወደ እርስዎ የምናደርስበት ለእግር ኳስ መረጃዎች ትክክለኛው ቻናል። ዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ክስተቶችን የባህል ሳምኖች እና ማንኛውም ኳስ መረጃዎችን በማህበረሰብ የምንሰራበት ጥናት። በMaleda Sport ማለዳ ስፖርት በአዝናኝ ማህበረሰብ እና የመሣሪያ ችሎታ በእግር ኳስ ውስጥ ዜና ህብረተሰብን ማቅረብ ያደረጉት ወቅታዊ ውሳኔ ይቀላቀሉ። ስነምግባር፣ በደቡብ በኩል መንገድ ዩኒቨርሲቲ እና የባለአዳዲስ የስፖርት ህብረተሰብ አውታር ተመልከቱ። እባኮትም በቻናሌችን ወይም በ@alrightmama ወይም @Hello_CJ አዲስ አዝናኝ ስፖርት በትክክለኛው ደረጃ ያግኙ። ይህን፣ ማህበረሰብና ህብረተሰብ መርህ እንዴት ሊሆን እንችላለን? እና መሰረትን ስጡ።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

07 Dec, 17:08


🔵 የባለ ብዙ ሀሳቡ ፔፕ አሁንም በደካማው የውጤት ጉዞ ውስጥ ቀጥለዋል።

ማንቸስተር ሲቲ በሴልኸረስት ፓርክ ከፓላስ ጋር 2-2 እኩል ተለያይቷል።

ፔፕ እና ሀሳባቸው በማንቸስተር ሲቲ ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ስድስት ተሸንፈው ፣ በሁለት አቻ ፣ በአንድ ደግሞ ድል አድርገዋል።

21 ጎሎችን ለማስተናገድ የተገደዱት ፔፕ ጋርዲዮላ በደቡብ ለንደን ከሰሞነኛ የኋሊት አዙሪት ጉዟቸው ለመውጣት በቂ ሀይል አልነበራቸውም።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

07 Dec, 16:28


🔵 በዘጠኝ ጨዋታዎች 21 ጎሎችን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ በሴልኸረስት ፓርክ በፓላስ 2-1 እየተመራ ይገኛል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

05 Dec, 17:18


እግር ኳሱ እንዲያድግ በፊልም እና መሰል ባለሙያዎች መዋቀር ወይም መመራት አለበት ?!

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመታዊ የአርቲስት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

ጉባኤው ኢንጅነር ሀይለእየሱስ ፍስሀን ፕሬዘዳትነት አድርጎ ሲመርጥ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን ም/ፕሬዘዳትነት እና አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ አቃቤ ነዋይ ሆነው ተመርጠዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

04 Dec, 21:32


🔴 ጋብሪኤል ባይኖርም አርሰናል ከቆመ ኳስ ጎል ከማስቆጠር ባህሉ አልቆመም።

ዩሪዬን ቲምበር ከዴክላ ራይስ የተሻገረለትን ኳስ በግንባር በመግጨት ኳስና መረብን በማገናኘት አርሰናል በኤምሬት ማንቸስተር ዩናይትድን 1-0 መምራት ችሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

04 Dec, 19:13


🔴 ማርከስ ራሽፎርድ እና አማድ ዲያሎ በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል በቋሚነት አልጀመሩም።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 21:41


🔴 የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነገ ጥዋት የስንብት ደብዳቤ ይደርስሃል ...

🔵 ፔፕ ጋርዲዮላ ጣቶቹን በመቀሰር ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሳክቻለሁ ...

የአንፊልድ ስቴዲየም አብይ ሁነት።

ሊቨርፑል ማንቸስተር ሲቲን 2-0 በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥቦች ሊጉን በበላይነት መምራት ችሏል።

ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በ 11 ነጥቦች ዝቅ ብሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 21:41


🔴 ግብጻዊው ንጉሥ ሞ ሳላ በ 20 ጨዋታዎች 24 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ፍጹም የተለዬ ብቃቱን በከፍታ ማማ አስቆጥሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 21:41


🔵 የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም።

19 ጎሎችን አስተናግዶ ፍጹም የከፋውን የውጤት እጦት እያስመዘገበ በኋሊት አዙሪት ውስጥ ተቀምጧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 21:41


🔵 ማንቸስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች 19 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 18:06


🔵 ማንቸስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች 19 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 16:25


🔴 የፕሪሚየር ሊጉ አሁናዊ ምርጥ ተጫዋች !

ግብጻዊው ኮከብ ሞ ሳላ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 16:19


🔴 ኮዲ ጋክፖ ሊቨርፑል በአንፊልድ ማንቸስተር ሲቲን 1-0 እንዲመራ አስችሏል።

ሊቨርፑል 1-0 ማንቸስተር ሲቲ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 15:23


🔴 በሩበን አሞሪም ስር የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን በኦልድትራፎርድ ከኤቨርተን ጋር ያደረገው ማንቸስተር ዩናይትድ በአስደናቂ ብቃት 4-0 ድል አድርጓል።

ኤቨርተንን በኦልድትራፎርድ በማስተናገድ በአዲሱ አሰልጣኙ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን ያከናወነው ማንቸስተር ዩናይትድ 4-0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ ግሩም ድል አስመዝግቧል።

ማርከስ ራሽፎርድ እና ጆሽዋ ዘርክዚ በተናጥል ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ኮከብ በሆኑበት ጨዋታ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና አማድ ዲያሎ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት አሲስት አስመዝግበዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ ከወራት በኋላ እጅግ አስደናቂ ብቃት ባሳየበት የከሰዓት ጨዋታው በኤቨርተን ላይ በሁሉም ረገድ ብልጫ ወሶዶ 4-0 ሲያሸንፍ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ትልቁን የስኬት ትሩፋት በድል ጀምረዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 15:02


🔴 ማንቸስተር ዩናይትድ 4-0 ኤቨርተን

ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ አስደናቂ ብቃት እያሳየ ይገኛል።

ኤቨርተንን 4-0 እየመራ ሲገኝ ራሽፎርድ እና ዘርክዚ ሁለት ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና አማድ ዲያሎ በተናጥል ሁለት አሲስት አስመዝግበዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 14:46


🔴 በሁለት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎች

ማርከስ ራሽፎርድ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 14:27


🔴 ብሩኖ ፈርናንዴዝ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት አሲስት በማስመዝገብ ዩናይትድ ኤቨርተንን 2-0 እንዲመራ የላቀ ሚና ተጫውቷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Dec, 14:26


የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤቶች

🔴 ማንቸስተር ዩናይትድ 2-0 ኤቨርተን
🔵 ቼልሲ 2-0 አስቶን ቪላ
⚪️ ቶትንሀም 0-0 ፉልሃም

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

30 Nov, 19:30


🔴 በለንደን ደርቢ አርሰናል ዌስት ሀምን 5-2 በሆነ ጣፋጭ ውጤት ድል በማድረግ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ያለበትን ውብ የለንደን ምሽት አሳልፏል።

በለንደን ስቴዲየም አርሰናል ዌስት ሀምን 5-2 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ያለበትን ግሩም ድል ሲያስመዘግብ በሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች 13 ጎሎችን ከመረብ አገናኝቷል።

ቡካዮ ሳካ ዳግም ድንቅ ብቃት ባሳየበት ጨዋታ በውድድር አመቱ 10 ኛ አሲስት በማስመዝገብ በአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች በቀዳሚነት መቀመጥ ችሏል።

በ 18 ጨዋታዎች በ 18 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገው ኮከብ ለአርሰናል የውጤት ማማ የጎላ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

25 Nov, 18:31


🔴 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ኮከብ በተሰኘበት ጨዋታ አል ናስር የካታሩን አል ሃራፋ 3-1 በማሸነፍ ግሩም ድል አስመዝግቧል።

ኮከብ ዳግም የተለየ ድንቅ ምሽት ባሳለፈበት የእስያ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ከመረብ አገናኝቶ 913 ኛ የልቀት ፕሮፌሽናል ጎሉቹ ላይ መድረስ ችሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

25 Nov, 18:22


🔴 ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ጎሎችን ከመረብ በማገናኘት ድንቅ ምሽት አሳልፏል።

በ 2024 40 ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

913 የፕሮፌሽናል ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

25 Nov, 17:18


🔴 ክርስቲያኖ ሮናልዶ 912 ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Nov, 18:28


🔴 በሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ተለያይቷል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም መሪነት የመጀመሪያ ጨዋታው ከኢፕስዊች ጋር ያደረገው ማንቸስተር ዩናይትድ 1-1 አቻ ተለያይቷል።

በ 81 ኛው ሰከንድ ማርከስ ራሽፎርድ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ ሆኖ የነበረው ዩናይትድ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ውስን ደቂቃዎች ሲቀሩት ጎል አስተናግዶ በአዲሱ አሰልጣኝ ያከናወነውን የመጀመሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Nov, 18:20


ኪሊያን ኧምባፔ ኳስና መረብን አገናኝቶ ሪያል ማድሪድ ሌጋኔስን እየመራ ይገኛል።

ቪኒሲዬስ ጁኒዬር ለኪሊያን ኧምባፔ ጎል አሲስት ማድረግ ችሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Nov, 17:02


🔴 ድንቅ አጀማመር ድንቅ የደስታ አገላለጽ!

ማንቸስተር ዩናይትድ በሩበን አሞሪም መሪነት የመጀመሪያ ጎሉን በ 81 ሰከንድ ውስጥ አግኝቷል።

የአማድ ዲያሎ ግሩም ሩጫ የማርከስ ራሽፎርድ ድንቅ ጨራሽነት ለአዲሱ አሰልጣኝ የተሳካ ጅማሮ መልካም ሁነትን ፈጥሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Nov, 16:08


🔴 አምስት ጎሎች በተስተናገዱበት ጨዋታ ሊቨርፑል ሳውዛምፕተንን 3-2 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Nov, 16:08


🔴 ግብጻዊው ኮከብ ሞ ሳላ ዳግም ድንቅ ብቃት ባሳየበት ጨዋታ ለሊቨርፑል የድል ጎል አስቆጥሮ ቀዮቹ መሪነታቸውን በስምንት ነጥቦች ከፍ እንዲያደርጉ የላቀ ሚና ተጫውቷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

23 Nov, 19:30


ጄምስ ማዲሰን በልደት ቀኑ ኮከብ በሆነበት የኤቲሃድ ምሽት ቶትንሀም ማንቸስተር ሲቲን 4-0 ድል ሲያደርግ ፔፕ ጋርዲዮላ አምስተኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ቶትንሀም በኤቲሃድ ማንቸስተር ሲቲን 4-0 ድል ሲያደርግ የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን በተከታታይ ጨዋታዎች አስከፊ ሽንፈት ማስተናገዱን ቀጥሏል።

ጄምስ ማዲሰን በልደት ቀኑ ሁለት ጎሎችን ከመረብ በማገናኘት በኤቲሃድ ፍጹም የተለየ ድርብ የደስታ ምሽት ሲያሳልፍ ፔድሮ ፖሮ እና ብንሪያን ጆንሰን ተጨማሪ ጎሎችን ለስፐርሶቹ አስቆጥረዋል።

የፔፕ ጋርዲዮላ ልጆች ከተከታታይ አስከፊ ሽንፈት የሚወጡት መንገድ ዝግ በሆነበት ምሽት ሌላ መሪር ሽንፈት በማስተናገድ የውጤት እጦት ላይ ለመቀጠል ተገደዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

23 Nov, 17:03


🔴 መድፈኞቹ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3-0 ድል በማድረግ ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል።

በኤምሬትስ ኖቲንግሃም ፎረስትን ያስተናገደው አርሰናል 3-0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ ድንቅ ውጤት አስመዝግቧል።

ቡካዮ ሳካ ፣ ቶማስ ፓርቴ እና ንዋነሪ የመድፈኞቹን የድል ጎሎች በስማቸው አስመዝግበዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

23 Nov, 15:52


🔴 ኮከቡ ቡካዮ ሳካ በ 11 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በ 11 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

23 Nov, 14:33


🔵 ኢንዞ ፈርናንዴዝ በሰማያዎቹ መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ጎል አስቆጥሮ አሲስት ባስመዘገበበት የኪንግ ፓወር ጨዋታ ቼልሲ ሌስተርን 2-1 ድል አድርጓል።

በኪንግ ፓወር ሌስተርን የገጠመው ቼልሲ 2-1 በማሸነፍ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ያለበትን ድንቅ ውጤት አስመዝግቧል።

ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም በተመለሰበት ቀዳሚ ጨዋታ በኪንግ ፓወር ሰማያዎቹ ቀበሮዎቹን 2-1 ድል በማድረግ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ያሉበትን መልካም እንቅስቃሴ አድርገዋል።

ኒኮላ ጃክሰን እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ የቼልሲን ድል ጎሎች ከመረብ ሲያገናኙ ጆርዳን አዩ ለሌስተር ሲቲ በፍጹም ቅጣት ምት የማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

23 Nov, 13:06


🔵 ኒኮላ ጃክሰን ሰባተኛ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን በማስቆጠር እምርታውን አስቆጥሏል።

ኒኮላ ጃክሰን በውድድር አመቱ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችን አስቆጥሮ ሶስት አሲስት አስመዝግቧል።

በ 10 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገው አፍሪካዊ ሰማያዎቹን በግሩም ጎል የማስቆጠር ብቃት ለድል እየመራ ይገኛል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

16 Nov, 03:21


🔴 ሁለት ግሩም ጎሎችን በማስቆጠር ድንቅ ምሽት ያሳለፈው ኮከቡ በደማቅ ክብረወሰን ከፍ ብሎ አምሽቷል።

የ 39 አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖላንድ ላይ ግሩም የባይስክሊክ ጎል በድንቅ ብቃት በማስቆጠር ልዩ ምሽት አሳልፏል።

በፓኒካ ምት ድንቅ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ከመረብ ያገናኘው የአለም እግር ኳስ ኮከብ በምሽቱ የፖርቹጋል ድል ሁለት ውብ ጎሎችን በማስቆጠር ከፍታውን ዳግም በልቀት አስቆጥሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ 910 ጎሎችን ከመረብ ያገናኘ ሲሆን ለ 1000 ታሪካዊ ጎሎች 90 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል።

እጅጉን የላቁ ክብረወሰኖችን በመሰባበር ሪከርዶች የሚከተሉት ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአለም አቀፍ ጨዋታዎች 132 ድሎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው ባለታሪክ ተጫዋች ሆኗል።

ሁለት ውብ ጎሎችን አስቆጥሮ አንድ አሲስት ያስመዘገበው የጨዋታው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ 39 አመት ለብሄራዊ ቡድን በአንድ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች የሆነበትን ፍጹም ድንቅ ስኬት አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

09 Nov, 14:59


⚪️ ቪኒሲዬስ ጁኒዬር ሀትርክ በሰራበት የቤርናቢዩ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከተከታታይ ሽንፈት ማግስት ኦሳሱናን 4-0 አሸንፏል።

ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒሲዬስ ጁኒዬር ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ኮከብ በሆነበት ጨዋታ ጁድ ቤልንግሀም በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ጎሉን በማስቆጠር ከጎል ጋር መታረቅ ችሏል።

በኤል ካላሲኮ ደርቢ 4-0 ተሸንፎ በቻምፒየንስ ሊጉ ደግሞ በሚላን 4-1 የተሸነፈው ሪያል ማድሪድ ኦሳሱናን 4-0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

09 Nov, 13:54


⚪️ ጁድ ቤልንግሀም በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ጎል አስቆጥሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

05 Nov, 12:54


🔴 ሞዛርቱ ወደ ልምምድ ተመልሷል።

የመድፈኞቹ መሃል ሜዳ ክፍል ዘዋሪ ማርቲን ኦዲጋርድ ከጉዳት መልስ ወደ ልምምድ ተመልሷል።

ያለ ሞዛርቱ ከድል ጋር ለመቀራረብ የተቸገረው አርሰናል አምበሉን ከኢንተሩ ወሳኝ ጨዋታ አስቀድሞ አግኝቷል።

መድፈኞቹ ያለ ማርቲን ኦዲጋርድ በአደረጓቸው ጨዋታዎች ሁለት ሽንፈት ሲያስተንግዱ በሶስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ለመለያየት ተገደዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

03 Nov, 15:58


⚪️ ዶሚኒክ ሶላንኬ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ኮከብ በሆነበት የሰሜን ለንደኑ ጨዋታ ቶትንሀም አስቶን ቪላን 4-1 በሆነ ውጤት ድል አድርጓል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

03 Nov, 12:53


በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ባለመሸነፍ የተጓዙ ክለቦች

አርሰናል 2003/04 ላይ በ 49 ጨዋታዎች
ሊቨርፑል 2019/20 ላይ በ 44 ጨዋታዎች
ቼልሲ 2004/05 ላይ በ 40 ጨዋታዎች
ማንቸስተር ሲቲ 2023/24 ላይ በ 32 ጨዋታዎች

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 17:17


🔵 ማንቸስተር ሲቲ በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸንፏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 17:00


🔵 ወደ ቫይታሊቲ ስቴዲየም ያቀናው ማንቸስተር ሲቲ በበርንማውዝ 2-1 ተሸንፏል።

ማንቸስተር ሲቲ ደካማ እንቅስቃሴ ባደረገበት የቫይታሊቲ ምሽት የ 2-1 መሪር ሽንፈት ሲያስተናግድ የሊጉን መሪነት ለሊቨርፑል አስረክቧል።

በሊጉ የውድድር አመት አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ የተጓዘው የፔፕ ጋርዲዮላው ክለብ ለበርንማውዝ እጅ ለመስጠት የተገደደ ሲሆን ወደ ሁለተኛ ደረጃ የተንሸራተተበትን ደካማ ውጤት አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 17:00


🔴 የአርነ ስሎት አስደናቂ የውጤት ጉዞ በቀጠለበት የአንፊልድ ምሽት ሊቨርፑል ከመመራት ተነስቶ ብራይተንን 2-1 ድል በማድረግ መሪነቱን ተረክቧል።

ኮዲ ጋክፖ እና ሞ ሳላ የቀዮቹን የድል ጎሎች ከመረብ ሲያገናኙ ግብጻዊው ኮከብ በፕሪሚየር ሊጉ የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ስምንተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠበትን ድንቅ ምሽት በአንፊልድ አሳልፏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 16:33


🔴 ቀዮቹ በአንፊልድ ስቴዲየም ከመመራት ተነስተው በኮዲ ጋክፖ እና ሞ ሳላ ጎሎች ሳቢሳዎቹን 2-1 መምራት ችለዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 16:26


🔵 በርንማውዝ 2-0 ማንቸስተር ሲቲ በቫይታሊቲ ስቴዲየም

🔴 ሊቨርፑል 0-1 ብራይተን በአንፊልድ ስቴዲየም

🔴 ኒካስትል ዩናይትድ 1-0 አርሰናል በሴይንት ጄምስ ፓርክ (የተጠናቀቀ)

ለመሪዎቹ ፍጹም አስቸጋሪ ቅዳሜ!

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Nov, 14:27


🔴 በሴንት ጄምስ ፓርክ የምሳ ሰዓት ጨዋታ ኒካስትል ዩናይትድ አርሰናልን 1-0 ድል አድርጓል።

በፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ ወደ ሴይንት ጄምስ ያቀናው አርሰናል በኒካስትል ዩናይትድ 1-0 ተሸንፏል።

አሌክሳንደር ኢዛቅ የኒካስትል ዩናይትድን የድል ጎል ከመረብ በማገናኘት የሰሜን እንግሊዙ ተወካይ ከአምስት ጨዋታዎች ያለ ድል ጉዞ ማግስት አርሰናልን በማሸነፍ የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Nov, 17:58


የነሀሴ ወር ምርጥ ተጫዋች ራፊኛ
የመስከረም ወር ምርጥ ተጫዋች ያማል
የጥቅምት ወር ምርጥ ተጫዋች ሌቫንዶቭስኪ

የባርሰሎና ፊት መስመር ኮከቦች በተከታታይ የላሊጋው የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን የግላቸው አድርገዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Nov, 15:19


🔴 በመጋቢት ወር 2020 ላይ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ በአውሮፓ 10 ትልልቅ ሊጎች ውስጥ በሚገኙ አሰልጣኞች ትልቁን የማሸነፍ ፐርሰንት ይዟል።

77% ድል አድርጓል

ስፖርቲንግ ሊዝበን በሩበን አሞሪምስር ከ 156 ጨዋታዎች 120 ድል አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

29 Oct, 16:44


🔴 ማንቸስተር ዩናይትድ ሩበን አሞሪምን አዲሱ አሰልጣኝ ለማድረግ በስፖርቲንግ ሊዝበን ያላቸውን የ £8.3 ሚሊዮን የውል ማፍረሻ ለመክፈል መዘጋጀቱን በርከት ያሉ የአውሮፓ ጋዜጦች በፊት ለፊት አምዳቸው አስነብበዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

29 Oct, 12:59


🔵በብዙ የተንደላቀቀ ህይወት ምርጫው እንዳልሆነ በብዙ የሚወሳለት ኮከቡ በማህበራዊ በጎ አድራጎት በመሳተፍ አንቱታን አትርፏል።

የባሎን ዶር አሸናፊው ሮድሪ።

ሽልማቱ ይገበዋል የሚለውን ለጊዜው ትተን ኮከቡ ግን በቅርቡ ከተመለከትናቸው የተከላካይ አማካኝ ኮከቦች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

ከሰርጂዮ ቡስኬት በመቀጠል ድንቅ ኮከብ እንደሆነ በድፍረት መናገርም ይቻላል።

በተለይ አሁን ላይ እግር ኳስን ከሚጫወቱ የተከላካይ አማካኝ ተጫዋቾች የሚስተካከለው የለም ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል።

The best CDM after all

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 22:04


🔵 ሮድሪ በባሎን ዶር ክብር ነግሷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 22:01


በባሎንዶር ሽልማት ከ 1-3 የወጡ ኮከቦች

ሮድሪ
ቪኒሲዬስ
ቤሊንግሃም

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:58


ዣቪ ፣ ኢኔስታ ፣ ቡስኬት ፣ ቪያ ያላሳኩትን የባሎን ዶር ሽልማት ሮድሪ በማሳካት ስፔን ከ 64 አመታት በኋላ በትልቁ ሽልማት ልጅ አግኝታለች።

ሮድሪ ባሎን ዶርን ያሸነፈ የመጀመሪያው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ሲሆን ከ 64 አመታት በኋላ ደግሞ የመጀመሪያው ስፔናዊ ተጫዋች ሆኗል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:58


🔵 ሮድሪ የ 2024 የባሎን ዶር አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።

ታላቁ የእግር ኳስ የኮከቦች ሽልማት በፓሪስ ይፋ ሲሆን ስፔናዊው የማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ አማካኝ ትልቁን ክብር በልቀት አሸንፏል።

የዩሮ ዋንጫ እና የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ከሌሎች ክብሮች ጋር ያሳካው ሮድሪ ባሎን ዶርን ያሸነፈ የመጀመሪያው የተከላካይ አማካኝ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብር አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:26


🔵 ከሌላኛዋ ንግስት አሌክሲያ ፑቴያስ በኋላ በአለም እግር ኳስ እስከወዲያኛው የነገሰች ድንቅ ኮከብ አይታና ቦንማቲ።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:21


ስፔናዊቷ የባርሰሎና ኮከብ አይታና ቦንማቲ በተከታታይ አመት ለሁለተኛ ጊዜ የባሎን ዶር ክብርን በማሸነፍ በእግር ኳሱ የንግስት ዙፋን ደፋታለች።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:14


ባሎን ዶር ሪያል ማድሪድ የአመቱ ምርጥ ቡድን መሰኘቱን ተከትሎ ቪኒሲዬስ ጁኒዬር በሌለበት የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች ምስል አድርጎ ለማድሪዱ ክለብ እንኳን ደስ አለህ ብሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 21:14


⚪️ ስኬታማው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የባሎን ዶር የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ክብር አሸናፊ ሆነዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:50


🔵 ኤሚ ማርትኔዝ በባሎን ዶር ሽልማት የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

የአለም ሻምፒዮኑ በሁለት ተከታታይ አመት ውስጥ የላቀውን ሽልማት የግሉ አድርጓል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:42


🔴 ቀጣይ ባሎን ዶር 👑

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:28


🔴 ሀሪ ኬን እና ኪሊያን ኧምባፔ በ 2024 ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የገርድ ሙለር ክብር አሸናፊዎች ሆነዋል።

በሽልማቱ ላይ ሀሪ ኬን ብቻ ነው የተገኘው።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:21


🔴 ቶኒ ክሩስ በኢንስትግራም ገጹ ቪኒ ጁኒዬርን ምርጥ ሲል አሞካሽቶታል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:17


⚪️ አንድም ተወካይ በፓሪስ ያላከው ሪያል ማድሪድ የአመቱ ምርጥ ቡድን ሽልማትን አሸንፏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:15


🔴 ይሄንን ትልቅ ክብር በማሸነፌ የድል ኩራት ተሰምቶኛል።

ሽልማቱ ለእናቴ ፣ ለአያቴ ፣ ለቡድን ተጫዋቾቼ ፣ ለአሰልጣኙ እና እኔን ለደገፉኝ በሙሉ ይሁንልኝ።

ላሚን ያማል

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

28 Oct, 20:06


🔴 የ 2024 ኮፓ ትሮፊ ክብር አሸናፊ ላሚን ያማል

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Oct, 20:27


🔴 ጆዜ ሞሪኖ በቀይ ካርድ ተሰናብተዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Oct, 20:12


🔴 በሽርፍራፊ ሰከንዶች ልዩነት ከሁለት ግሩም ጎል የማዳን ብቃት በኋላ ጆዜ ሞሪኖ ለአንድሬ ኦናና አድናቆትን ችሮታል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

24 Oct, 14:03


⚪️ ቪኒሲዬስ ጁኒዬር ራፊኛን በማሸነፍ የቻምፒየንስ ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተሰኝቷል።

በቻምፒየንስ ሊጉ ሀትሪክ የሰሩት ቪኒሲዬስ ጁኒዬር እና ራፊኛ ሀትሪክ መስራት የቻሉ ሲሆን የሪያል ማድሪዱ ኮከብ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል።

በሳምንቱ በኤል ክላሲኮ ደርቢ የሚገናኙት ሁለቱ ኮከቦች ተፎካካሪ በሆኑበት የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ቪኒሲዬስ ጁኒዬር አሸናፊ ሆኗል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

20 Oct, 17:35


🔴 በአንፊልድ ሰማያዎቹን ያስተናገዱት ቀዮቹ 2-1 ድል በማድረግ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

በሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ አንፊልድ ስቴዲየም ላይ ቼልሲን ያስተናገደው ሊቨርፑል 2-1 በማሸነፍ በአርነ ስሎት ስር ድንቅ ብቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ሞ ሳላ እና ከርትስ ጆንስ ሊቨርፑልን ባለድል ያደረጉ ጎሎች ከመረብ ሲያገናኙ ኒኮ ጃክሰን ቼልሲን ከሽንፈት ያልታደገች ጎል በስሙ አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

20 Oct, 16:18


🔴 ኮከቡ 162 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን በማስቆጠር ከምንግዜውም የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ዘጠነኛ ላይ የተቀመጠበትን ድንቅ ሁነት ፈጥሯል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

20 Oct, 16:04


🔴 የቀድሞ ክለቡ ላይ ስምንተኛ ጎሉን ያስቆጠረው ሞ ሳላ በአንፊልድ ሊቨርፑልን መሪ ያደረገ ኳስ ከመረብ አገናኝቷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

20 Oct, 15:02


🔵 ጆን ስቶንስ በጭማሪው ደቂቃ የመጨረሻ ሽርፍራፊ ሰከንድ ላይ ጎል አስቆጥሮ ማንቸስተር ሲቲን ባለድል አድርጓል።

ማንቸስተር ሲቲ በጭማሪው ደቂቃ በአስቆጠረው ጎል የ 2-1 ጣፋጭ ድል ተቀዳጅቷል።

በሞሊኒክስ ወልቭስን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ በሁለቱ ተከላካዮች ባስቆጠሯቸው ጎሎች ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል።

ጆስኮ ግቫርዲዮል እና ጆን ስቶንስ ለማንቸስተር ሲቲ የድል ጎሎችን ከመረብ አገናኝተዋል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

20 Oct, 13:30


🔴 ወልቭስ በሞሊኒክስ ማንቸስተር ሲቲን 1-0 እየመራ ይገኛል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

19 Oct, 16:04


🔴 በኦልድትራፎርድ ብሬንትፎርድን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ በአሊያንድሮ ጋርናቾ እና ራስመስ ሆይለንድ ጎሎች 2-1 ድል አድርጓል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

17 Oct, 11:54


🔴 ከብሄራዊ ቡድኑ የውጤት እጦት በላይ ፍጹም አመንክዮ የሌለው ሀላፊነት ያለመውሰድ ደግሞ ውሃ የማያነሳ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ አስተያየት ከአነጋጋሪም በላይ ነው።

በእርግጥ አሰልጣኙ በሁለት ተከታታይ አመታት በተለያዩ ሁለት ክለቦች የሊጉ አሸናፊ በመሆን ግሩም የግል ማህደር አላቸው።

ነገርግን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ውጤት ማምጣት እንኳን ይቅርና ቡድኑ ጭላንጭል ተስፋ እንኳን ያልታየበት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተመልክተናል።

እና ፍጹም አመንክዮ የሌለው አስተያየት በመስጠት እራስን ለመከላከል መሞከር ደግሞ ሁነቱን ይበልጥ አስከፊ አድርጎታል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

16 Oct, 02:19


🔵 ኮከቡ ቦሊቪያ ላይ ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሀትሪክ የሰራ ሲሆን ሁለት ተጨማሪ ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የተለየ ብቃቱን ዳግም አስቀጥሏል።

የአለም እግር ኳስ ልሂቃኑ ሊዮኒዬል ሜሲ ቦሊቪያ ላይ ሀትሪክ ሰርቷል ፣ ሁለት ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ፍጹም ድንቅ ብቃት አድርጓል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

15 Oct, 20:09


🔴 የ 39 አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አክሮባቲክ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

15 Oct, 19:37


ምን ጉድ ነው?!

ኢትዮጵያ 0-3 ጊኒ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

15 Oct, 18:01


🔴 ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሶስቱ አናብስትን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ተስማምቷል።

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱከል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን ከስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።

የቀድሞው የቼልሲ እና ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ቶማስ ቱከል ሶስቱ አናብስትን በአሰልጣኝነት ሀላፊነት ለመረከብ በሁሉም ረገድ ከስምምነት ላይ ደርሷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

14 Oct, 13:44


🔴 የአለማችን ወጣቱ ኮከብ ላሚን ያማል በአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች 38 ጥፋቶች የተሰራበት ሲሆን ብዙ ጥፋት የተሰራበት ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

12 Oct, 16:57


🔴 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

እረፍት

ጊኒ 3-0 ኢትዮጵያ

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

10 Oct, 19:48


🔵 ክሪስቶፈር ንኩንኩ ለፈረንሣይ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል።

የሰማያያዎቹ አጥቂ በፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረበትን ድንቅ ምሽት ሲያሳልፍ በውድድር አመቱ በክለብ እና አገሩ በስድስት ጨዋታዎች ሰባተኛ ጎሉን ከመረብ አገናኝቷል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

07 Oct, 04:31


🔴 ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶችን በማዳን ድንቅ ብቃት ያሳየው ዴቪድ ዳህያ ክለቡን ባለድል አድርጓል።

ሁለት ፍጸም ቅጣት ሞቶችን በማዳን የተለመደ ድንቅ ምሽት ያሳለፈው ዴቪድ ዳህያ ፊዮረንቲና ሚላንን ድል እንዲያደረግ አስችሏል።

የቲዮ ሄርናንዴዝ እና ታሚ ኤብራሃም ፍጹም ቅጣት በግሩም ብቃት በማዳን ልዩ ምሽት ያሳለፈው ዴቪድ ዳህያ ፊዮሬንቲና ሚላንን 2-1 ድል እንዲያደርግ አስችሏል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

05 Oct, 13:26


🔴 በሴልኸረስት ፓርክ የደቡብ ለንደኑን ክርስቲያል ፓላስ የገጠመው ሊቨርፑል በዲዮጎ ዦታ ጎል 1-0 በማሸነፍ በሊጉ መሪ ሆኖ የቆየበትን ድንቅ ውጤት አስመዝግቧል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

02 Oct, 11:18


🔴 ትናንት ምሽት በቻምፒየንስ ሊጉ ኤምሬትስ ላይ ቡካዮ ሳካ ወደ ሜዳ ይዞት የገባው የራሂም ስተርሊንግ የ7 አመት ልጅ ነው።

የራሂም ስተርሊንግ የ 7 አመት ልጅ ቲያጎ ስተርሊንግ ይሰኛል።

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

01 Oct, 20:26


🔵 ኧርሊንግ ሀላንድ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አስገራሚ ቁጥር አስመዝግቧል።

41 ጨዋታዎች
42 ጎሎች