እንማር @enmare1988 Channel on Telegram

እንማር

@enmare1988


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
   ለ Promo - @Kiya988

https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q

Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

እንማር (Amharic)

እንማር (Enmare) የተለያዩ መፅሀፎችን ወይም የተከታታይ ልቦለድን እና ግጥምን በማዋቀር እንዲለያቸው መፅሐፍት መሳሪያ ከገበያ ያወጣል። በዚህ Channel ከግጥም እና ፍልስፍና እንዲለያቸው የተለያዩ PDF መፅሐፍት እና ፍላጎቶችን በነፃነት ይዝናኑ። በዚህ Channel ላይ አስተያየትና promotion በማድረግ @Kiya988 ይቀርብላል። የተለያዩ መፅሐፍትን ለመከታተል ይረዱ፣ ምንጭ በመኖሩ፣ እና መረጃዎቹን የጀመረውን የ Youtube ቻናሎች በዚህ አድራሻ ላይ ተጠቃሚ መረጃዎች ለመልኩ ይህንን ሂደት በሚረዳ ይከናወንላችሁ።

እንማር

23 Nov, 04:24


ሁሌም ጠዋት ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ እያንዳንዱ ቀን አዲስ የምስጋና'ና ሌላ እድል እንደሆነ ራሴን አስታውሳለሁ።

ይህ አስተሳሰብ የእኔን አመለካከት ይለውጣል... በተለመደው ውስጥ ያለውን ውበት እንድመለከት ያስችለኛል። የፀሐይ ሙቀት፣ የወዳጅነት ፈገግታ፣ ወይም ዝምታ...የጸጥታ ጊዜ፣ እነዚህ ትንንሽ ነገሮች ሕይወት በብዙ በዕድሎች የበለጸገች መሆኑን የሚያስታውሱ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ቀን አዲስ ጅምር አለው፣

ይህም ለሕይወቴ አስፈላጊ በሆኑት ላይ እንዳተኩር እና መድረሻውን ብቻ ሳይሆን ጉዞውን እንዳደንቅ ያበረታታኛል። በዙሪያዬ ላለው አለምም አወንታዊ አስተዋፅዖ እንዳደርግ ሃይል ይሰጠኛል ...

Happy ቅዳሜ💥

እንማር

23 Nov, 04:23


#።"Advertising

🔷ዛሬየወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ🔷
አስቸኳይ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♀🏃‍♀
🗓ቀን:-  13_21/03/2017🗓

🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️1 የስራው አይነት:-ኮካ ኮላ ፋብሪካ                                 ላይ  ሽያጭ
       
የት/ደረጃ:- 10 -ዲግሪ
ደሙዝ:- 8,000-20,000
ፆታ:-  ሴት/ወንድ
ልምድ:-  0 አመት
ብዛት:- 13
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️2 የስራው አይነት:-መረጃና ምዝገባ
                             ክፍል ሀላፊ
የት/ደረጃ:-  ዲግሪ
  ደሙዝ:-   12,000-15,000
   ፆታ:-  ሴት/ወንድ
   ልምድ:-   ከ 0አመት ጀምሮ
  ብዛት:-     5
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
  ↘️3 የስራው አይት:- መምህርነት
            በሁሉም የት/ አይነት

የት/ደረጃ:-በማንኛውም ዲግሪ/ዲፕ
ደሙዝ:-    15,000-23,000+ሰርቪስ
ፆታ:-     አይለይም
ልምድ:-  ከ0 አመት ጀምሮ
ብዛት:-   13
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️4   የስራው አይነት:-ስልክ ኦፕሬተር 
                 ለኤጀንሲ/ለራይድ
የት/ደረጃ:-   10/12ኛክፍል
ደሙዝ:-    10,000 እና ከዚያ በላይ
ፆታ:-     አይለይም
ልምድ:-   አይጠይቅም
ብዛት:-   7
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️5   የስራውአይነት:ጉዳይ አስፈፃሚ
                /ፖስተኛ
የት/ደረጃ:-   10/12ኛ ክፍል
ደሙዝ:-  13,000+ትራንስፖርት
ፆታ:-    አይለይም /  ቀልጣፋ
ልምድ:-   አይጠይቅም
ብዛት:-8
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️6. የስራው አይነት:-   ለNGO 
                    በሁሉም ዘርፍ
የት/ደረጃ:-   10-ዲግሪ
ደሙዝ:-  26,000_32,000
ፆታ:-   ሴት/ወንድ
ልምድ:-   አይጠይቅም
ብዛት:-    20
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️7   የስራው አይነት:-  ሹፍርና ህ2/የድሮ 4ተኛ
የት/ ደረጃ:-   10
ደሙዝ:-   12,000- 18,000
ልምድ:- ከ0- 2አመት
ፆታ:- ወንድ
ብዛት:-   10
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️8   የስራው አይነት:- ሒሳብ ሰራተኛ    
                        
የት/ደረጃ:-  ዲፕሎማ/አካውንታት
ልምድ:-   ያላት ቢሆን ይመረጣል
ደሙዝ:-15,000
ፆታ:-   ሴት
ብዛት:-    7

🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️9 የስራው አይነት:-ሞተረኛ
             
የት/ደረጃ:-  10ኛ ክፍል
ደሙዝ:-  6000+ ኮሚሽን
ልምድ:- ከ0-3 አመት
ፆታ:-  ወንድ
ብዛት:-   8
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️10  የስራው አይነት:- ደንበኞች አገልግሎት
                      
የት/ደረጃ:- 12 - ዲግሪ
ደሙዝ:-    15,000+
ልምድ:- አይጠይቅም
ፆታ:-  አይለይም
ብዛት:-  12
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️11 የስራው አይነት:-  Any 
                             Engineering
የት/ደረጃ:- ዲግሪ
ደሙዝ:-25,000
ልምድ:- ከ0አመት ጀምሮ
ፆታ:-  ሴት/ወንድ      
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️12 የስራው አይነት:-  እንግዳ ተቀባይ
የት/ደረጃ:- 10 -ዲግሪ
ደሙዝ:-  10,000
ፆታ:- ሴት
ልምድ:- 0 አመት
ብዛት:- 4
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
↘️13የስራው አይነት:-  አሲስታንስ
የት/ደረጃ:-  ዲግሪ
ደሙዝ:- 20,000
ልምድ:- ከ0 አመት ጀምሮ
ብዛት:- 8
🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛🔛
🔹አመልካቾች በአካል ወይም በተወካይ ቢሮአችን በመምጣት ዶክመንታቹን አሟልታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ🔹
        
            🔹አድራሻችን🔹
🔷🔷22 ማዞሪያ ደብረዳሞ ሆቴል ፊት ለፊት ዜድ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ  203
                እንገኛለን🔷🔷

          ለተጨማሪ መረጃ
     ☎️   09 70 15 61 28
     ☎️  07 14 16 86 96

እንማር

22 Nov, 19:49


እንዲህ ነው የሆነው "ሰላም ስጠኝ" ላልኩት አንተን ሰላሜን ሰጠኝ...."ፍቅር ስጠኝ" ላልኩት አንተን ሸለመኝ...."መኖር አስመኘኝ" ብዬው ነበረ...አንተ መጣህ....አንተ ስትኖር ያለመደበትን መኖር ማጓጓት ጀመረ...እንደ አዲስ አፍቃሪ ሆንኩኝ...በስልክህ ሳወራህ ራሱ እንደምታየኝ ነገር መሽኮርመም....ሳታየኝ መቅለስለስ ጀመርኩ....አቅሌን አሳትከኝ አንተዬ።

አሁን ቀልድ አልፈጅም ብልህስ....እንጨት እንጨት በሚል ቀልድ ስንፈራፈር ላየኝ ጤንነቴ ያጠራጥራል....ውስጤ ካስገባሁህ ጀምሮ እንዲሁ ሳቅ ሳቅ ይለኛል...ነጭ ልብሴ ላይ ቡና በሚከለብስብኝ አስተናጋጅ እራሱ አልበሳጭም....ያለመደብኝን "ያጋጥማል አትጨነቅ" ብዬው ቲፕ ሰጥቼ እወጣለሁ....የደሀ ብሬን በቲፕ ጨረስኩልህ አንተዬ።


አሁን የኮሊደር ልማት የሚሉት ነገር አይጎረብጠኝም....እንደ ድሮው "አይ ይቺ ሀገር...አይ ይሄ መንግስት" ስል አልውልም....እንደውም መንግስት ቤትህን ለልማት አፍርሶ ከእኔ ጋር ቢያዳብልህ ብዬ ሳልፀልይ እቀራለሁ ብለህ ነው....መቼም አያልቅብህም ይሄንንም አስመኘኃኝ አንተዬ።

የምትመጣበትን ሰአት መቁጠር የዘወትር ተግባሬ ሆነ....እንደድሮው ሰአቴን ጠብቄ መብላት ብዙም አላስታውስም...ብዪ ስባል "መልኬ በቃኝ" ማለት ጀምሬያለሁ....በረሀብ ልሞትልህ ነው አንተዬ።

እንደ እብድ ተቆጠርኩልህ....የሰፈሬን ሰው በቀን ሰባቴ እንደምን ዋላችሁ  እላለሁ....ጥርሳቸው ላለቀው የሰፈራችን አዛውንት የጥርስ ቡሩሽ ከነሳሙናው ገዝቼ እንኩ ብላቸው እርግማን ተከናነብኩ...ለመላጣው የእድሩ ሊቀመንበር ሚዶ ሰጥቼ እናቴን ከእድሩ አሰናበትኳት....ቀባሪ አሳጣኧኝ አንተዬ።


ሁለት ቦታ ጎኖጉኜው የሚከርመው ፀጉሬ ፈተና በዛበት....ፀጉር እንደምትወድ ስትነግረኝ ሲደብረኝ የቆረጥኩት እና ደንግጦ የቀረው ፀጉሬን አሳድግልኝ ብዬ ጥላ ተሳልኩ....እግዜሩም ታዘበኝ አንተዬ።



ብቻ እንኳን መጣህ❤️



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

እንማር

22 Nov, 18:50


''...የሚያምር አንገቷን በእጇ ደግፋ እንደ ክራር ደምፅ በለሰለሱ ቃላቶቿ መናገር ጀመረች።

ከድምጿ ውበት የበለጠ ትህትናዋ አስደመመኝ ❤️

እንማር

22 Nov, 17:16


ህልም እልም

"በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ"
"ምነው?" ሚስት መብራት አበራች
"ሰው ገደልኩ"

"መቼ?"

"አሁን በህልሜ…አንቺን ሲነኩብኝ አልወድ፣ ምን እንደፈረደበት እንጃ ይሄ ጎረቤታችን ጎሹ ሲስምሽ የደረስኩኝ ይመስለኛል።

ከራስጌ ቆንጨራዬን መዘዝ ሳደርግ ያ ዲብ ሰውነቱ'ኳ ሳይከብደው ፈትለክ ይላል። ሲበር፣ ሳባርር…ሲበር ሳባርር ጎሹ እንዴት እንደሆነ እንጃ እየራቀኝ ይሄዳል።

ቆንጨራውን እንደቅዝምዝም ሃይ ብዬ ስወረውረው ጀርባው ላይ ስክት ሲል ብንን አልኩ። በስመ አብ ወወ…"
"ህልም አይደለም!"
"እ"

"አዎ እውነት ነው። ትናንት ጎሹ መሳም ስሞኛል፣ ግን አላባረርከውም፣ ዝም ብለህ ነው ያየኸው?"
"ነው እንዴ? ነፍስ ከማጥፋት እግዜር አወጣህ በይኛ"


,,,ውልብታ,,,

#ዓለማየሁ_ገላጋይ

እንማር

22 Nov, 17:02


ሰውየው በፈረስ በሚሳበው ጋሪው አሸዋ በማመላለስ ላይ ሳለ ሀይለኛ ንፋስና ወጀብ የቀላቀለ ዝናብ መዝነብ ጀመረ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ከዝናቡ ሽሽት ሩጫ ሆነ ባለመኪናዎችም መስኮታቸውን ዘጋግተው መሸጉ ባለጋሪው ግን ፍንክች አላለም ፈረሱን ጥብቅ አድርጎ በማቀፍ ዝናቡ እስከሚያባራ ለሰዓታት አብሮት ቆመ::

ከዚያም ዝናቡ አባርቶ ከእቅፉ ቀና ሲል በዙሪያ የነበሩ ዝናቡን የተጠለሉና መኪናቸው ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ዓይኖች በፍቅር በማዘንና በፈገግታም ጭምር ወደሱ እንዳተኮሩ ተመለከተ።

ከዛ እሱም ፈገግ በማለት "እሱ (ፈረሱ) በምፈልገው ጊዜ ጥሎኝኮ አልሔደም ታዲያ እኔስ በዚህ ወቅት እንዴት ብቻውን ጥዬው ልሔድ ይቻለኛል።!? በማለት በለሆሳስ ተናገረ።

በንፋሱ በወጀቡ ጊዜ አብረውህ የነበሩትን ፀሀይ ወጣ ብራ ሆነ ብለህ ጥለኻቸው አትህድ

እንማር

21 Nov, 16:07


📔ጊዜ የማይሽረው ጥበብ ፤ በተግባር የታገዘ እና ደረጃ በደረጃ የሚሰጥ የብልፅግና ፕሮግራም ተሻጋሪ መፅሐፍ)

🟢ደራሲ- ዋላስ ዲ. ዋትልስ

📖📔ተርጓሚ- ኢዮብ ካሣ

ከመፅሐፉ ውስጥ የተወሰዱ

*የእውነት መበልፀግ ማለት በትንሹ መርካት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን የበለጠ መጠቀምና ማጣጣም እየቻለ፣ በትንሹ መርካት የለበትም፡፡ ምን አለፋችሁ --- በትንሹ መርካት ሃጢያት ነው! የተፈጥሮ ዓላማ፣ የሀይወት እድገትና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለህይወት አቅምን፣ ሞገስን፣ ውበትንና መትረፍረፍን ለማጎናፀፍ የሚያግዙ ነገሮች ሁሉ ሊኖሩት ይገባል፡፡ ለምን ቢሉ --- ሁሉም የመበልፀግ መብት አለውና፡፡

*ተፈጥሮ የተሰራችው ህይወትን ለማሳደግ ነው፡፡ የሚያነሳሳት ዓላማም ህይወትን የማሳደግ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለህይወት ምቾት የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተትረፍርፎ ይቀርባል፡፡ ፈጣሪ ራሱን መቃረንና የራሱን ሥራዎች ማውደም ካልፈለገ በቀር፣ የምንም ነገር ችግር ወይም እጥረት አይፈጠርም፡፡

*እናንተ ስለድህነት አታውሩ፤ ስለድህነት አትመራመሩ፤ ስለድህነት አትጨነቁ፡፡ የድህነት መንስኤ አያሳስባችሁ፡፡ ድህነትን ጉዳያችሁ አታድርጉት፡፡ እናንተን አይመለከታችሁም፡፡ እናንተን የሚመለከታችሁ መፍትሄው ነው - መድሃኒቱ! በርትታችሁ ሃብታም ሁኑ! ድሃውን ለመርዳት የተሻለው መንገድ ራስን ማበልፀግ ብቻ ነው::

*ህልማችሁን እውን ለማድረግ የሚስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ በውስጣችሁ አለ፡፡ ተነግሮ የማያልቅ፤ የትየለሌ አቅም አላችሁ፡፡ የፈጠራ አቅም የለንም ብትሉም ፤ ቀደም ሲል ሳይሳካላችሁ ቢቀርም፤ ሁሉንም ሞክራችሁ ምንም የቀራችሁ እንደሌለ ብታስቡም እንኳን —— ለዚህ መፅሃፍ አዕምሮአችሁን ከፈቱ፡፡


@Enmare1988
@Enmare1988

እንማር

21 Nov, 15:43


ከመፅሐፉ ውስጥ የተወሰዱ

*የእውነት መበልፀግ ማለት በትንሹ መርካት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን የበለጠ መጠቀምና ማጣጣም እየቻለ፣ በትንሹ መርካት የለበትም፡፡ ምን አለፋችሁ --- በትንሹ መርካት ሃጢያት ነው! የተፈጥሮ ዓላማ፣ የሀይወት እድገትና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለህይወት አቅምን፣ ሞገስን፣ ውበትንና መትረፍረፍን ለማጎናፀፍ የሚያግዙ ነገሮች ሁሉ ሊኖሩት ይገባል፡፡ ለምን ቢሉ --- ሁሉም የመበልፀግ መብት አለውና፡፡

*ተፈጥሮ የተሰራችው ህይወትን ለማሳደግ ነው፡፡ የሚያነሳሳት ዓላማም ህይወትን የማሳደግ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለህይወት ምቾት የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተትረፍርፎ ይቀርባል፡፡ ፈጣሪ ራሱን መቃረንና የራሱን ሥራዎች ማውደም ካልፈለገ በቀር፣ የምንም ነገር ችግር ወይም እጥረት አይፈጠርም፡፡

*እናንተ ስለድህነት አታውሩ፤ ስለድህነት አትመራመሩ፤ ስለድህነት አትጨነቁ፡፡ የድህነት መንስኤ አያሳስባችሁ፡፡ ድህነትን ጉዳያችሁ አታድርጉት፡፡ እናንተን አይመለከታችሁም፡፡ እናንተን የሚመለከታችሁ መፍትሄው ነው - መድሃኒቱ! በርትታችሁ ሃብታም ሁኑ! ድሃውን ለመርዳት የተሻለው መንገድ ራስን ማበልፀግ ብቻ ነው::

*ህልማችሁን እውን ለማድረግ የሚስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ በውስጣችሁ አለ፡፡ ተነግሮ የማያልቅ፤ የትየለሌ አቅም አላችሁ፡፡ የፈጠራ አቅም የለንም ብትሉም ፤ ቀደም ሲል ሳይሳካላችሁ ቢቀርም፤ ሁሉንም ሞክራችሁ ምንም የቀራችሁ እንደሌለ ብታስቡም እንኳን —— ለዚህ መፅሃፍ አዕምሮአችሁን ከፈቱ፡፡

እንማር

21 Nov, 07:26


አትሳሳት ጓደኛዬ........


ዝቅ የሚሉት ለህሊናቸው ያልተገዙ ሰዎች ብቻ ናቸው..ዝቅ የሚሉት ክብር ባለሌለው ቦታ ላይ የተገኙ ሰዎች ብቻ ናቸው......ዝቅ የሚሉት አይምሯቸውን ከልባቸው ጋር  ያላዋዱ ሰዎች ናቸው...

ታዲያ ለምንድን ነው እኔ ማፍረው?

ለምንድን ነው ዝቅ የምለው?

ለምንድን ነው ራሴን የምከሰው?


መጀመሪያ ራስህን አፅዳ.....ውስጥህ ያሉትን መጥፎ ልማዶች ሁሉ በደምብ አፅዳ.....መሲሑንም ይቅር በለኝ በለው.....ቀን-ከሌት ራስህን በመገንባት አሳልፍ.....መቼም ቢሆን ራስህን ከመግዛት ወደኃላ እንዳትል...ክብር ባሌለውም ቦታ ላይ አትገኝ....ከዛ ሁሉም ሰው አንተን የማያከብርበት መንገድ ያጣል.....ይሄ ነው ቀና ብሎ መሄድ ማለት...ይሄ ነው ሰላማዊ ሰው ማለት...❤️

እንማር

21 Nov, 07:24


🎙ለዮቱበሮች ና ለቲክታከሮች ለቪዲዮዋቹ ጥርት ያለ ድምፅ የምትቀዱበት 🎙#K9 ዋይርለስ ማይክ በ 1 ካርቶን 2 ማይኮች የያዘ  #20_ሜትር_ ርቀት_ድረስ_የሚሰራ   ጫጫታ ቦታ ውስጥ ቮይስ ብትቀዱም  የናንተን ድምፅ ብቻ በጥራት ለይቶ የሚቀዳ ከስልክ ቮይስ የበለጠ ጥራት ያለው  ማይክ ለገብያ  አቅርበንላቹሀል ይደውሉልን 📞 0777403952
      0941546755  

👇በውስጥ መስመር
@Laday_33

እንማር

20 Nov, 20:42


"ንፋስ አልወድም"....አለቺኝ ካዘነበለችበት ሳትነቀል....

"ለምን"....ጠየቅኩ....

"ስለማይረጋ...ባንድ አቅጣጫ ስለማይነፍስ...ወዲህ ብቻ ገፍቶ ስለማይተው...ወዲህም ወዲያም ስለሚያደርግ...አቋም ስለሚያሳጣ....አንዴ ሽው ካለበት ስለማያድር...."....በረጅሙ ተነፈሰችና ቀጠለች....

"ገፍቶ ከጣለህ በኃላ ደግፎ ሊያነሳህ ስለማይመጣ....ከመጣም ደግሞ ደጋግሞ ሊያፈርስህ ስለሚመጣ....ታውቃለህ ንፋስ ደካሞች ላይ እንደሚበረታ....ብቻ ምን አለፋህ የወደቀ ላይ ምሳር ለማብዛት ስለሚመጣ ያስፈራኛል...."

"አትፍሪ እኔ አለሁልሽ...."....አልኳት በልበ ሙሉነት....

"ከግዑዝ ነገር ፀብ የለኝም...ስለ ንፋስ ሳወራ ራስህን ታያለህ ብዬ ጠብቄ ነበር...."

"ማለት...."

"ከግዑዙ ንፋስ እዚ ፊቴ ያለኧው ንፋስ ታስፈራኛለህ...."

"ማለት...."

"ንፋስ ነህ እያልኩህ ነው...."

"አይደለሁም...."

"ነህ...አንተ ግን እያባበልክ አለሁ እያልክ ነው የምትጥለው...ግዑዙ ንፋስ አያባብልም...ሁሌም የቻለውን ሊያፈርስ እንደሚመጣ አውቃለሁ....የሰው ንፋስ ከጣለ መነሳት ቅዠት ነው...እና እሱን ንፋስ ነህ"....


በረጅሙ ተንፍሳ አቆመች....እኔም ደግሜ አልጠየቅኳትም....



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

እንማር

20 Nov, 17:58


ልፈልግም ስትለኝ እምባዬ እንዳይመጣ ታግዬ ፈገግ አልኩኝ ። ለእምባዬ ፊት መስጠት አልፈለኩም ። የሄደን ሰው እምባ አይመልሰውም ብዬ ነው መሰለኝ !

ግን ከፋኝ ፦

ተደግፌባት ነበር ። አደጋገፌ በጥርጣሬ አልነበረም ። ከኔ እሷን አምናት ነበር ፣ እንዳልጎዳት ስጣጣር ነበር ። እንዳላሳዝናት ሁኔታዬን ሁሌ አየው ነበር !

አልፈልግህም ስትለኝ ....

ጭር አለብኝ በግርግር ውስጥ ጭርታ ስሜት እንዴት ይወለዳል ? ጭርታው አስፈራኝ ጭርታው ድብርት ወለደ ። ስታብራራ መልስ መስጠት አልፈለኩም ። እንዲ ስለው እንዲ ይላል ብላ ምላሽ ተሸክማ እንደመጣች ገብቶኛል ።

ምላሽ ካጠና ሰው ጋር ውይይት ትርፍ የለውም ። ማን ለማን ብሎ ከማን ጋ ይሆናል ? ይሄ መስቀል ሳላጉረመርም የምሸከመው ነው !!

ግን ይሄን ሁሉ ሲሰማኝ ፈገግ ብዬ ነበር ።

እሷም አልፈልግህም ስለው ፈገግ ብሎ ነበር ትል ይሆናል ።
©Adhanom Mitiku

እንማር

20 Nov, 16:39


'' አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ ። አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም _ ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ ።

አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም _ የባከኑ መሥዋትነቶች ይባላሉ። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ

አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል _ ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን አንቀጥላለን። አንዳንድ ሕዝቦች በውል ተረስተዋል _ ለመታሰቢያነት የቀረላቸው ምንም የለም።

አንዳንድ ኮቴዎች በመረሳት ተጠቅተዋል አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል። ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሦስት መሃላ ተክደዋል። ....''

እንማር

19 Nov, 18:46


...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።

የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።

"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ

መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''

ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።

ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።

ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።

አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም

በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።

አለመኖር 📚

እንማር

19 Nov, 18:11


''የአንዲት ሴት ዓይኖች ቅፅበታዊ ዕይታ የዓለማችን ደስተኛ ሰው ሊያደርግህ ይችላል...

እንማር

18 Nov, 18:19


አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች...

ቤቴን አጽድቼ ካስተካከልኩ በኋላ ወንድሜ ደወለ...ከባለቤቴ ጋር ልንጠይቅሽ እንመጣለን ኣለኝ። ኩሽና ገባሁ ለእንግዶቸ ያለኝ ላዘጋጅ።

ለመስተንግዶ ምንም አላገኘሁም! አንድ ነገር ላቀርብላቸው ብፈልግ፡ ምንም ማግኘት ኣልቻልኩም ጥቂት ብርቱካን ብቻ አገኘሁ… እናም ወዲያውኑ ሁለት ብርጭቆ ቀዝቃዛ ጭማቂ አዘጋጀሁ።

ወንድሜ እና ሚስቱ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኘችን ያለው የወንድሜ ሚስት እናት ከሳቸው ጋር ነበረች።

ሁለት ብርጭቆ ለሚስቱና እናትዋ ኣቀረብኩላቸው። ኣንድ ብርጭቆ ውሃ ደግሞ ለወንድሜ። 7up እንደምትወድ ኣቃለሁ ኣልኩት።

ትንሽ ጠጣና ውሃ መሆኑን ኣወቀ። እናትየዋ እኔ 7up ነው የምፈልግ ለሆዴ ይመቸኛል እና ስጡኝ.. ትላለች። ግራ ገባኝ ደነገጥኩ …

ወንድሜ እንዲህ ሲል አዳነኝ: - አዲስ ብርጭቆ ከኩሽና ኣመጣለሁ ብሎ ብርጭቆውን ይዞት ሄደ። ከዚያም የጠርሙሱ መሰበር ድምፅ ሰማን፡

እናም ተመልሶ መጥቶ አማቱን እንዲህ አላት... የሚያሳዝነው ከኔ ወድቆ ብርጭቆውን ተሰበረ.. ግን ምንም አይደለም ሌላ ላመጣሽ ወደ ግሮሰሪ እሄዳለሁ... ኣላት።
አማቹ አያስፈልግም አለች...

ሲወጡ ወንድሜ ሲሰናበተኝ፡ አቅፎ በእጄ ገንዘብ አስጨበጠኝና እና እንዲህ አለኝ: ​​-ከኩሽናው 7up ማጽዳት እንዳትረሺ፡ ጉንዳኖችን እንዳያመጣ! ብሎ በፈገግታ እና በፍቅር ተሰናበተኝ..።
ራስሺን ተንከባከቢ ኣለኝ።
በዚህ መንገድ... ወንድሜ ጭንቀቴንና ጉድለቴን ሸፈነልኝ.. ስሜቴን ጠበቀልኝ..

ወንድማማችነት እንዲህ መሆን ኣለበት...Happ

እንማር

18 Nov, 17:22


''ቀድሞ የተዘጋጀ ማንነት ይዛችሁ አልተወለዳችሁም። በግንባራችሁ ወይ በመዳፎቻችሁ መስመር ላይ የሆነ ነገር ተፅፎባችሁ አልተፈጠራችሁም።

ወደዚህ አለም ስትመጡ ምንም እንዳልተፃፈበት ባዶ መፅሀፍ ሆናችሁ ነው። ዕድላችሁን የምትፅፉት፣ ዕጣ ፈንታችሁን የምትፅፉት ራሳችሁ ናችሁ ፤ ስለዚህም ራሳችሁን መሆን አለበችሁ...

እንማር

17 Nov, 18:13


⭐️ ከኮንዶም እና ሲጋራ ውጪ ገዝቶኝ አያቅም!!እኔ ደሞ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ገና ሲመጣ እራሱ ሰውነቴን ውርር እስኪያደርገኝ ያስጠላኛል።ሌላ ቦታ አይገዛም?? ደሞ በዚ ድህነቱ ላይ ሲጋራ ኮንዶም...ምናለ ቀንስራ ለላጠው እጁ ባዝሊን ቢገዛ??ምናለ ፀጉሩን ቢቆረጥ?? ምናለ ዳቦ ቢገዛበት??ሞጋጋ.....(ብስጭት እያልኩ ጓደኛዬ ላይ እነጫነጫለሁ
እኔ ምለው ረዱ ምን አገባሽ ቆይ ሽቀላሽ አደል እንዴ??


አረ የሱ 10 ብር በአፊንጫዬ ይውጣ!!
እንደው ቆይ ይሄንን ጉድሽን ባየሁልሽ...ሆ..ሰው እንዴት ከመሬት ተነስቶ ሰው ይጠላል...?
ዳኑ በግርምት እያወራችኝ ሰፈራችን የሚመረቀው አዲሱ ስላሴ ቤተክርስትያን በር ላይ ደርሰን
ተሳልመን ገባን።

መቼስ የምእመናኑ ብዛት ጠጠር አያስጥልም።ሰፊው የስላሴ ግቢ ውስጥ ነጭ ኩታ የተነጠፈ እስኪመስል በአሉ ድምቅ ብሎ ታቦታቱ ወጥተው ዝማሬው ጫፍ እስከጫፍ ያስተጋባል።ዳኑ ደሞ በማህበር የሚዘምሩትን ወጣቶች ስለምትወድ ተከታትለን ወደ
ዘማርያኑ እንደቀረብን ነበር ቀና ስል ከዛ ሰይጣን ጨብራራ ሱሰኛ ልጅ ጋ አይን ለአይን የተጋጠምነው...

በስመአብ አረ ይኼንን ሰይጣን ማላይበት የት ልሂድ!!?? (በስጭት ስል ድምፄን መሠሠት የሚያቅተኝ ነገርስ? አንባረቅኳ!!
አረ ቀስ በይ ረዱ..ማነው?ምንድነው??
ያ ሲጋራ የሚገዛው ልጅ ነዋ...እዚህም አየሁት። ደሞ አለማፈሩ...!! (አልኳት ንዴቴ ብሶ ድምፄን ለመቀነስ እየታገልኩ

የታለ በናትሽ አረ አሳዪኝ...
ዳኑ ተሰብስቦ በሚዘምረው ምእመን መሀል በጥፍሯ ቆማ አንገቷን አስግጋ ስታማትር ቆይታ ድንገት ዘጭ ብላ ቆማ ደርቃ ስትቀር ነገሯ አስደንግጦኝ እኔ ፈዝዤ አየኋት..
አንቺ ምን ሆነሻል???ምንድነው
ሚያፈዝሽ??....አትናገሪም እንዴ???አንቺ ዳኑ??

(ትከሻዋን እየነቀነቅኩ ብዙ ከጠሯኋት በኋላ በቆምኩበት ጥላኝ ወደኋላ ዞራ ስትራመድ ተከታትለን ሄዴን አንድ ጥግ ቁጭ አለን
ምንድነው ዳኑ???ይሄ ምን አይነት የተረገመ ሰይጣን ነው???ቆይ አንቺም ታቂዋለሽ ማለት ነው!!??

እረፊ ረዱ ሰይጣን አትበይው!! እረፊ ክፉ አትናገሪ!! በረከት እኮ ነው ረዱዬ በረከ....(ነጠላዋን አይኗ ላይ ሸፍና ተንሰቀሰቀች
ማነው በረከት??ምንድነው???የት ታቂዋለሽ??

በረከት ነዋ.....አንድ ጊዜ ስለሱ ነግሬሽ አልነበር? በረከት ዲያቆኑ...ማለቴ እኔና እሱ...(ዳኑ ፀጥ ስትል ከሆነ አመት በፊት የተፈጠረው ክስተት ትዝ ብሎኝ በቆምኩበት ቁልቁል ተዘረፈጥኩ
አላምንሽም ዳኑ!!!

⭐️አዎ ተቀይሯል!!እሱን አይመስልም!!ግን እኔ መልኩ አይጠፋኝም!!ይሄ ሁሉ የኔ ስህተት ነው።ታውቂ የለ ያፈቅረኝ ነበር... ይወደኝ ነበር...የመጀመርያውም የመጨረሻውም እኔ እንደሆንኩ ነበር የሚያምነው።ግን እኔ አልረባም... እስካሁን ከሱጋ የተገናኘንበትን ቀን እረግማታለሁ!!!እሱን አፈቅርሀለው ብዬ የዋሸሁበትን ቀን እረግማታለሁ!!!

ለሊት ከሌላ ወንድ ጋ አድሬ ነጠላውን ተከናንቦ ከማህሌት ሲመጣ የተገናኘንባትን ቀን ረግማታለሁ....ከዛች ቀን
ወዲህ ነው ዲያቆኑ ትሁቱ አገልጋዩ በረከት የጠፋው፤ሱስ የጀመረው፤መስከር የለመደው...ይቅር በለኝ እለዋለሁ
እያልኩ ስፈልገው ኖሬያለሁ ግን ከአባቱ ጋ ሰፈሩን ለቆ እንደወጣ ከሰማሁ ወዲህ...
ዳኑ እንባዋ እንደ ጅረት ከአይኖቿ ሲወርድ የበረከትን ሁኔታ አሰላሰልኩት ከዚህች ቤተክርስትያን በር አይጠፋም።

አንዳንዴ ሲያልፍ ከዛ ሲወጣ አይቼው አውቃለሁ። ብዙ ጊዜ እዛው ቆሞ ሲጃራ ለኩሺልኝ እያለ ላይተር በሚይዝባት እጆቹ ዳኑ ብሎ ክንዱ ላይ የተነቀሰው ትዝ ብሎኝ አንገቴን አቀርቅሬ...
ዳኑዬ ይገባኛል ግን ደሞ አንዴ ሆኗል... በረከት ከቤተመቅደሱ አገልግሎት ይራቅ እንጂ ከክርስቶስ ልጅነት አራቀም።

እኔም በረከትን ማውቀው እዚህ የስላሴ ህንፃ ሲሰራ ለቀንስራ ከመጣ ወዲህ ነው።ታውቂያለሽ....አንዳንዴ ህይወታችን እና ስራችን ይለዋወጥብናል።እግዚአብሔር ተጠቦ አክብሮ አስውቦ የፈጠረውን ታላቅ ቤተመቅደስ በውጪ አፍርሰን በሌላ በኩል ደሞ በገንዘባችን የተዋበ ቤተመቅደስ ሰርተን እልል ብለን እንመርቃለን።

⭐️ ወደኋላ ግን ስናስበው አፍራሾቹም ሰሪዎቹም እኛው ሆነን እንገኛለን።አየሽ ቤተመቅደስ የሚገነባው ለምእመናን አይን ማረፊያ፤ፎቶ መነሻ፤ሳይሆን የልባቸው ማረፊያ እና መሸሸጊያ እንዲሆናቸው ነው....ምንም ህንፃውን ብናስውበው የኛ ህይወት በእግዚአብሔር አባትነት ካልተዋበ ትርጉም የለውም።''እግዚአብሔር እየፈረሰ ቤቱን የሚያንፅ ሳይሆን.እየታነፀ ቤቱን የሚሰራ ትውልድ ነው ሚፈልገው"

⭐️ በረከት በዲቁናው ሰወችን ባያንፅ ሰወች የሚታነፁበትን ዛሬ የቆምንበትን መቅደስ ግን በላቡ በጉልበቱ ከማነፅ አልሰነፈም ፈጣሪ ደሞ በጎቹን ጥሎ አይጥልም አንዴ ቃሉን በልቡ የዘራ ከነቆሻሻውም ቢሆን ይመላለሳል እንጂ አይቀርም።ሁሌ አዲስ ቤተክርስትያን እንገንባ እነጂ እኛ ለክርስቶስ ነዘላለም አዳዲስ ህንፃወቹ ነን...አታልቅሺ በቃ በማርያም(እጇን ከአይኗ ላይ አንስቼ ላቅፋት ስል... ሂጄ አገኘዋለሁ ረዱዬ ....(ከተቀመጠችበት ፍንጥር ብላ ተነስታ ወደሚዘምሩ ምእመናንን እየገፋች ስታልፍ ተከተልኳት "በረከት ግን
ቆሞ በነበረበት ቦታ ላይ አልነበረም በረከት
ሄዳል....

✍️
ቻቻ