Thoughts @justhoughtsss Channel on Telegram

Thoughts

@justhoughtsss


ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም?

comment for the writer : @nhymn

discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1


Since: Dec-10-2022

Thoughts (Amharic)

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም? እናመሰግናለን! ቸል በዚህ ቤት እንዴት ቸል እያጠናቀን አልቻሉም? ማንም ያልታዩ እና ዝናብዎችን የምንፈጸመው አይመሰግንም። ይህ ቤት በዓለም ላይ የተባለው አገልግሎት ነው ። የቸል ቤት፦ @justhoughtsss

ሓየት ለማረጋገጥ፣ @nhymn

ለምለም ወይም አማርኛ ዘዴ በዓለም ለማንጽልን የጋቢት ቤት፦ https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

የየኛ ቴዎድሮች ፦ https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1


ከዚህ ባለፈው ቀን፦ ሴፕቴምበር-10-2022

Thoughts

20 Nov, 21:30


Thoughts pinned «For paid promotion @nhymn»

Thoughts

20 Nov, 21:30


For paid promotion
@nhymn

Thoughts

20 Nov, 20:16


#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)

አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …

እንደ አሞራ ዙሬሽአንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ፣ ‘ዋይ ፣ ዋይ …’

አጃኢብ ነው መቼም!

ስትሄጅ ተራመድሁ... ስትቆሚ ቆሜ 
ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራበእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀንልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞስብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 
ቃላት ድል ነስተውሽበኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜለታ 
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋትዝታሽ ተረታ።

(እንቢ በይኝ ዳግም
እልህን ላጣጥም ። )

Thoughts

20 Nov, 17:01


https://t.me/+TIgGH_hEYiUzegbN

Thoughts

19 Nov, 21:02


...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።

የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።

"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ

መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''

ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።

ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።

ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።

አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም

በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።

አለመኖር 📚

Thoughts

19 Nov, 05:25


ሕይወት ቀላል ነበረች።

ቀላልም ትሆን ነበር።

ሞታችንን እንደሞታችን እንጂ እንደሞታቸው ላንሞት፣

ሕይወትን እንደሕይወታችን ከመኖር ይልቅ እንደ ሕይወታቸው ለመኖር መረጥን።

ለምን?

Thoughts

18 Nov, 02:19


እንኳን ደህና ቀሩ
[Red-8]

ዘጠና ዘጠኙን፡ አልጋዬ ስር ትቼ
አንዳንድ የምናፍቅ፡ ከጠፉት ሉኮቼ
ሥጭር ላቆሰሉኝ፡ ሙቼ ለፃፍኳቸው
አንድ ቀን አግኝቼ፡ ዳግም ላነባቸው፡
ወደ ወደቁበት ፡ ሀገርና ቅዬ
ያተጫነብኝን፡ ብዕሬን ፈንቅዬ፡
መጣለሁ ያልኩኝ፡ ከሞት ተነስቼ
እኔም ክርስቶስ ነኝ፡ ለጠፉት ግጥሞቼ።

ቢሆንም ቢሆንም፡

አዳማ ፍራንኮ፡ ከእርጎ ቤቱ በቀኝ
ይመጣል እያለች፡ የምትጠብቀኝ
ያቺ ወረቀት ግን ፡ ግጥም የፃፍኩባት
እንኳን ጠፍታኝ ቀረች፡ እንኳን ቀረሁባት።

ያቺ ኮብላይ ግጥሜ፡
መነሀሪያ አጠገብ፡ ቅጥቅጡ እስኪሞላ
ፍቅሩን በመጠበቅ፡ ለፈረሰ ገላ
ለማይረካ ናፍቆት፡ ለማይቆረጥ ጥም
ሻንጣዬን አዝዬ፡ በውሃ ጥም ዝዬ፡ የደረስኳት ግጥም
ሲበቃኝ ከኪሴ፡ አጥፌ ያኖርኳት
እንኳን የወደቀች፡ እንኳንም የጣልኳት።

አንዴ በፃፈው ልክ፡ እየተሰፈረ፡
ላንዴ ባፈለቀው፡ ጥቅስ እየታሰረ
ስንቱ ፈጣሪ ነው፡ ባለበት የቀረ?
ፍጡር ተነቦ ነው ፡ አምላኩ ሚከበር ፡
ፍጡር ተነቦ ነው፡ አምላኩ ሚቀበር
እንኳንም ወደቀች...
ብትኖር እሷን ብዬ፡ እዚያው እቀር ነበር።

አፈር ልሆን ሄድኩኝ፡ እሷን ከአፈር ጥዬ
በዝናብ ርሳ፡ በጣይ ተቃጥዬ
ያስተዋወቀንን፡ መልካችንን ትተን
ተላልፈን ይሆናል፡ ይሄኔ ተያይተን።

በተፃፃፍንበት፡ በነበር መች ቆየን?
በየደረስንበት፡ እንዳዲስ ተቃኘን
እሷ በሷ ሆዬ፡ እኔ በትዝታ
ከንግዲህ በኋላ፡ ባገኛትም እንኳ ፡ ከጣልኩበት ቦታ
አትሆነኝም ሎሌ ፡ አልሆናትም ጌታ።

እሷም ብቻ አይደለች፡ ያኮራችኝ ጠፍታ...

ከሶስት ቁጥር ቶታል ፡ በታቦት ማደሪያ
ለፀሀይ ዩኒፎርም ፡ ጋርደን ሰደርያ
ሲመሽ ከገብርኤል፡ እስከ አቦ ማዞሪያ
መንገዳችን እንጂ፡ ወሬያችን ሳይበቃን
መካኒሳን አልፈን ፡ ሳርቤት በቫቲካን
ለሚያረማምዱኝ፡ ለወክ አጣጮቼ
የታጠፈች ግጥሜን፡ ከኬሴ አውጥቼ
ቆም ሄድ እያልን፡ የመንገድ ባውዛው፡ በየደመቀበት
ያነበብኩላቸው ፡ የላመች ወረቀት...
ያቺ የዋህ ግጥም፡ «አንድም ሰው እንዳይሞት!» የሚል መዝጊያ ያላት
እንኳን የትም ጠፋች፡ እንኳን የትም ጣልኳት!

« አንድም ሰው እንዳይሞት? »
አረ ባክሽ?... እውነት?
የልጅነት ግጥሜ፡ ስሚኝ ተረት ተረት...

ዮኒፎርም አውልቀው፡ ከአብሮ አደግ ርቀው
በዓለም ስቃይ ልክ፡ ልብን አተልቀው
ከምኞት ደመና፡ በግፍ ወንጭፍ ወርደው
በወክ ካካለሉት ፡ካደጉበት ሰፈር፡ ተነቅለው ተሰደው
ተቃጥለው ከፃፉት ፡ በሀቅ በፍትሕ ጥም
«አንድም ሰው እንዳይተርፍ!» ይማፀናል ግጥም።

እንኳን ጠፋታ ቀረች፡ ግጥሜ እንደልጅነት
ዓለሙን ሳታውቀው ፡ የተፃፈች ጀነት
በምኞት ቡርሿ፡ ሲዖል ለማቆንጀት
ስትጣጣር ያኔ፡ እንኳን ነቃሁባት፡
እንኳን የትም ጣልኳት፡ ይቺ ተረት ተረት...
የወተት ግጥሞቼ፡ እየተነቀሉ፡ ሲበቅል የስጋው
ለነከሰኝ ሁሉ፡ ሰው ብዬ ስጠጋው
እንኳንስ ልታገል፡ ስለት እንዳይወጋው...
ሞት አንሷል ብዬ ነው፡ አሁን የምሰጋው።

ምን ያቺ ብቻ...?

እየደረሳቸው፡ የመሰወር እጣ
ከሀይስኩል መድረክ፡ ፑሽኪን እስክመጣ
ከአዳማ ክበብ፡ ከግቢ እስክወጣ
ከጦቢያ በጃዝ ፡ከፒክኒክ በረንዳ
ጆሮ እየጠመድኩኝ፡ በስንኝ ልነዳ
ከኪሴ እየሳብኩኝ፡ መመለስ ዘንግቼ
የትም የጣልኳቸው ፡ ባይተዋር ግጥሞቼ

ያጡትን ለማግኘት፡ ጠፍቶ ከመመኘት
ተነፋፍቆ ኖሮ፡ ተጣባብቆ መቅረት
ከሚባል መንትያ ፡ቀንበር ነፃ ይውጡ
ከእንግዲህ ግጥሞቼ ፡ ወደኔ እንዳይመጡ...

'ጠፍተን ያልተገኘን፡ ልጆችም ነን' ቢሉ
እንድውጣጣባቸው፡ ለተደለደሉ
ሆኜ ለተውኳቸው፡ ሆኜ ላለፍኳቸው፡ አልቀው ለተጣሉ
ላለፉት እኔዎች፡ መቃብሮች ናቸው፡ የፃፍኳቸው ሁሉ።

Thoughts

16 Nov, 18:03


‹‹ነጭ ሽንኩርት አይወድም››

(የታሪክ ሃሳብ- የAllison Symes “ok” አጭር ታሪክ)


---———————————
‹‹ምንም አልል ፍኖትዬ፡፡ ይልቅ መደወልሽ ገርሞኛል››
‹‹የእኔ ቆንጆ…ከናሆም ጋር መለያየታችሁን ሰምቼ…››
‹‹አዎ…ብቻዬን ሁለት ልጅ ማሳደግ ይከብደኛል ብዬ ባልፈራ ኖሮ ከአመታት በፊት ነበር የምፈታው››
‹‹ታዲያ አሁን ልትፈቺው እንዴት ወሰንሽ…?ልጆቹ አሁንም ትንንሽ አይደሉ?››
‹‹ወፈርሽ ብሎ ሲያንቋሽሸኝና ሲያሸማቅቀኝ ራሴን እያስራብኩ አስራ ሶስት ኪሎ ከቀነስኩ በኋላ ‹ታውቂያለሽ…ስትወፍሪ ነበር የምታምሪው…የሚታቀፍ ነገር ሲኖርሽ…አሁንማ ሙግግ አልሽ› አላለኝም? ….ለማንኛውም ፍኖቲና፣ ናሆም ምንም ምግብ ላይ ነጭ ሽንኩርት ሲገባ አይወድም እሺ?››
‹‹ም…..ን?››
‹‹ሰምተሻል…ይልቅ የሚገርመው አትሰማም ብለሽ ማሰብሽ ነው…እስከዚህ ጅል ናት ብለሽ ነበር የምታስቢው..? ምንስ ቢሆን አስር አመት ጓደኛዬ አልነበርሽ…?.ለማንኛውም….እኔን ያደረገኝን እስኪያደርግሽ ወጡን ያለ ነጭ ሽንኩርት ቀቅይለት…ሲሰለቸው ጥሏቸው የሚሄዳቸው ልጆችን ውለጂለት…››


ስልኩ ተዘጋ፡፡

Thoughts

16 Nov, 18:02


‹‹ፎቶ የላትም››
÷÷÷÷÷÷÷÷




እናታችን የሞተችው በድንገት ስለነበር ጀርመን ሃገር የሚኖረው ወንድሜ ለቀብሯ መድረስ አልቻለም ነበር፡፡





ያ ደግሞ በሃዘን የተቆራመደ አንጀቱን ቅርጥፍ አድርጎ በላው፡፡


ተንገበገበ፡፡


ሳላያት፣ ሳልሰናበታት፣ ቆሜ ሳልቀብራት፣ እርሜን ሳላወጣ እያለ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ፡፡



በዚያ ሰሞን ያለ ልክ ሲብከነከን ቢቸግረን፣ 

‹‹እስቲ እናንተን ይሰማ እንደሆን ተው በሉት›› ብለን የተማፀንናቸው አዛውንቶች ፣

‹‹  የሚወዱትን ሰው አፈር ማልበስ እንዴት አድርጎ አንጀት እንደሚቆርጥና ቁርጥን ለማወቅ፣ ሃዘንን ለመወጣት እንደሚያግዝ የደረሰበት ያውቀዋል..ተዉት ያልቅስ..እንዲህም ሆኖ በወጣለት!›› ይሉ ነበር፡፡



ይሄን የሰማው ወንድማችን፣

‹‹እውነታቸውን ነው! ተዉኝ …ከወጣልኝ ላልቅስ….ምስኪኗ እናቴ እኮ ይሄ አይገባትም ነበር፡፡ አምስት አመት ሙሉ አይንህን ልየው፣ ናፈቅከኝ እያለች ስትለምነኝ፣ ስታለቅስብኝ አሻፈረኝ ብዬ ይሄው ቁርጥ ሲሆን መጣሁላት…ግን ምን ዋጋ አለው…! በእኔ ጉዳይ እህህ እንዳለች ሄዳ አፈር እንኳን አላለበስኳት›› እያለ ...
ቀን ከሌት ያነባ ነበር ፡፡


------


ከሳምንት በኋላ ማንንም ሳያማክር ቤት ውስጥ በየአልበሙ ውስጥ ያለውን ፎቶ ማተራመስ ያዘ፡፡



‹‹ምን ፈልገህ ነው?›› አልኩት፡፡
‹‹እማ ያለችበትን የቤተሰብ ፎቶ አፋልጊኝ››  አለኝ፡፡




ሶሰት በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰባችን ፎቶዎችን የያዙ ባለ ብዙ ገፅ፣ ረጅምና ሰፋፊ አልበሞችን አሰስን፡፡ በእነዚህ አልበሞች ውስጥ የአስርት አመታት የቤተሰባችን ታሪክ በፎቶ ተቀምጧል፡፡



እማዬን ግን በእነዚህ ፎቶዎች ውስጥ ልናገኛት አልቻልንም፡፡




ልጆቿ በሙሉ፣



‹‹እንዴት ለብዙ አይነት መታወቂያዎች ከተነሳቻቸው ጉርድ ፎቶዎች በስተቀር ከቤተሰብ ጋር አንድ ደህና ፎቶ አይኖራትም?…ይሄን ሁሉ ዓመት፣ ይሄንን ሁሉ ፎቶ ስንቀጨቀጭ የት ነበረች?..እንዴትስ ይሄንን አሳዛኝ እውነት እስከዛሬ ድረስ አላስተዋልነውም?›› በሚል ጥያቄ ተጠመድን፡፡




ከዚያ…የቤተሰባችንን ወሳኝ ፎቶዎች ባየሁ ቁጥር እማዬ የት ሄዳ አብራን እንዳልተነሳች ማሰላሰልና ማስታወስ ጀመርኩ፡፡




ወንድሜ ጀርመን ሲሄድ እጅብ ብለን ልንሸኘው ሄደን፣ በመጨረሻው የመለያያ ሰአታችን ቦሌ ኤርፖርት የተነሳነው የቤተሰብ ፎቶ ውስጥ ያልገባችው ስታለቅስ አድራና ውላ አይኖቿ ክፉኛ ስላበጡ


‹‹እንዲህ መስዬ ፎቶ አላበላሽም››  ብላ ነው፡፡





የታናሽ ወንድሜ ምርቃት ቀን ተሰብስበን ፎቶ ስንነሳ ‹‹ነይ ግቢ››  ስንላት ያልተነሳችው ገና ከኩሽና ወጥታ ሳትለባብስ ስለነበር፣  ‹‹እንዲህ ሆኜማ አልነሳም- ባይሆን በኋላ የሃገር ባህል ልብሴን ለብሼ ታነሱኛላችሁ›› ብላ ነው፡፡ (ያ በኋላ ግን አልመጣም)




የታላቅ እህቴ የመጀመሪያ ልጅ ክርስትና ዕለት ሰብሰብና ፈገግ ብለን ፎቶ ስንነሳ፣ እዚህኛውም ፎቶ ላይ ያልገባችው ከቤተክርስትያን መልስ የህጻኗን ሽንት ጨርቅ ልትቀይር ጓዳ ገብታ ነው፡፡




የእኔ ሰርግ እለት ደህና ፎቶ የሌላት፣ ‹‹ እነዚህን ሰዎች ሳልወድ በግድ፣ እኔ ልወጣው እያልኳችሁ በውድ ዋጋ ቀጥራችሁ እንዳያዋርዱኝ›› ብላ የምግብና መጠጥ አቅራቢዎቹን እግር በእግር ስትከታተል ፋታ አጥታ ነው፡፡





ሙሉ ቤተሰቡ ተሰብስቦ ላንጋኖ ሲሄድ በስንት ልመና እሺ ብላ ብትመጣም ሁላችንም ሃይቁ ዳር ሄደን የተነሳነው ፎቶ ላይ የሌለችው በየቦታው የጣልናቸውን ቦርሳዎችና ሌሎች ንብረቶቻችንን እያየች፣
‹‹ሁላችንም ከሄድን ይሄን ሁሉ ኮተታችሁን ማን ሊጠብቅላችሁ ነው›› ብላ ቀርታ ነው፡፡





እናታችን የትም መቼም እኛን ማገልገል እንጂ ከእኛ እኩል መታየትን፣ ለፎቶ ተዘጋጅቶ ፈገግ ማለትን እንስፍስፍ አንጀቷ ስለማይፈቅድላት፣  የቤተሰቡ ዋልታና ማገር ሆና ሳለ፣ በቤተሰብ ፎቶ ላይ ግን አትታይም፡፡



አንዱም የጋራ ፎቶ ላይ አትገኝም፡፡

እርግጥ ነው፤ ምትክ የሌላት እናታችን ሞት ዘወትር ይጠዘጥዘን ነበር፡፡



በየትኛውም የጋራ ፎቶ አብራን መኖሯ አለመመዝገቡን በጣም ከመሸ፣ እጅግ ከዘገየ በኋላ ባስተዋልን ጊዜ ግን ዳግም ቁስላችን አመረቀዘ፣ ሃዘናችን ልክ አጣ፡፡

Thoughts

16 Nov, 13:02


ለራሴ አዝዤ አላውቅም።

እሷ ስትበላ ራሱ ማየት ሀሴት ይሰጠኛል። እነገናኛለን ብዙ ምግብ አዝላታለሁ

መጀመሪያ ፀጥ ብላ እየተሻማች ቀጥሎ የምግቡን እያንዳንዱን ቅመም ለማዳመጥ በሚመስል አኳኋን አይኗን ጨፍና ስትመሰጥ ትቆይና

መጥገብ ስትጀምር ስለ ምግብ አስደሳች ተፈጥሮ lecture እያረገቺኝ በልታ ስትጨርስ ትንሽ አውርተን እንለያያለን።

ሁሉም ነገር በምግብ ካልተመሰለ ግር ይላታል።

አንድ ቀን እኮ ነው እንዲሁ ተገናኝተን እየበላች "ስሚማ" አልኳት "እ" አለቺኝ ቀና ሳትል

"ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?" አልኳት እንደአንተ አይነት እንድትል ነበር

"እንደ ፈንዲሻ..." አላስጨረስኳትም ቱግ አልኩ
"የጠየኩሽ እኮ ስለ እኔ..." አመለጠኝ

"ማለቴ ስለ ወንድ ምርጫሽ ነው እንጂ ስለ ምግብ ምርጫሽ አይደለም።

"አስኪ አስጨርሰኝ ስለ ወንድ ምርጫዬ በምግብ አድርጌ እያስረዳውህ እኮ ነው" አለቺኝ"

የሆዳም ነገር እያልኩ"በሆዴ "ይሁን ቀጥዪ የሚል ፊት አሳየኋት
" እንደ ፈንዲሻ በደስታዬ ጊዜ ብቻ የሚኖር እንደ ንፍሮም በሀዘኔ ጊዜ ብቻ የማገኘው ሳይሆን
እንደ እንጀራ ሁሌ የሚያስፈልገኝ ስፈልገው የማላጣው እንዲሆን ነው" ብላኝ መብላቷን ቀጠለች።

"ወይ አንቺ ጉደኛ እንጀራ የሆነ ባል ይሰጠኝ እያልሽ ነው" እያልኳት እሷ ስተስቅ እኔ ስገረም አበቃን።

©nani


https://t.me/justhoughtsss
https://t.me/justhoughtsss
https://t.me/justhoughtsss

Thoughts

16 Nov, 12:58


How poets are born? 😂

ፍቅረኛህ ከተቀጣጠራችሁበት ሰአት ዘግይታ ስልክ ስትደውል አላነሳም ስትል የሚላክ ቴክስት:-

ኖርማል ሰዎች:-ማርፈድሽ ሳያንስ ደግሞ ስልክ አታነሽም በይ ሲመችሽ ደውይ ከእነ ከቤጋ ምሳ ልበላ ሄጃለሁ ቻው።

ገጣሚዎች:-
እመጣለሁ ብለሽ ጠብቄሽ ነበረ
ዳሩ ግን ችላ አልሽኝ ስልክ ማንሳት ቀረ?
እመጣለሁ ያልሽኝ መምጣት እንዴት ነበር
በመጠበቅ ብዛት አንገቴ ሲሰበር
ሲያዝንልኝ ነበረ የተቀመጥኩበት የሲባጎው ወንበር ።

እጠብቅሻለሁ እጠብቅሻለሁ የመጣው ቢመጣ
ሰማይ ቢያስገመግም መትረየስ ቢንጣጣ

እጠብቅሻለሁ እንደ ወፏ ጫጩት እንዳለች ከጎጆ
እስኪመጣ ድረስ ድጋሚ አባ ሳንጆ

በመቅረትሽ ምክንያት አይቀንስም ፍቅሬ
ግድም አይሰጠኝም የመንደሩ ወሬ
እጠብቅሻለሁ
እጠብቅሻለሁ

ሁለት ቀን ስልኳ ከተዘጋ ደግሞ አንድ የግጥም መድብል መፅሐፍ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጀባ😂😂

Koan ad
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery

Thoughts

15 Nov, 17:08


"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው" አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ"
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?' አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

ይልቅ እንጠጣ እስኪ

Thoughts

14 Nov, 14:28


I see myself in you all...

Some, try to find joy while being alone,
Some, need people to feel whole,
I, seek one who'll embrace,
The loneliness of my soul.

Some, cry to cover their dignity,
Some, avoid sincerity,
I, seek to live with,
Who'll free me from my insanity.

They, encountered joy when needed,
They, lived on an immature world,
What a needy coward.

But then, who am I to judge....!




Benon/Me

Thoughts

13 Nov, 12:45


እፈራለሁ
[ ]

ቆይ፥
መንፈስ ብትሆኚስ?
ለእኔ ብቻ የሚታይ ፥ ከህልም የተሰራ፥
'ዴልዩዥን' ብትሆኚስ?
የምኞት መዶሻ ፥ ጠራርቦ ያቆመሽ ፥ የልቤ ፈጠራ፤

ከጨዋታ መሐል ፥ ድንገት ብትጠፊብኝ፤
'የታለች?' ስላቸው፥
'ማን ናት ደሞ?' ብለው ፥ ሰዎች ቢስቁብኝ፤

ህልም ብትሆኚስ?
ስነቃ ብትቀሪስ?
ቆይ አሁን፥
ጭራሹን ባትኖሪስ?

ሞልተሽኝ በእቅፌ፥
እጆቼን ቀንፌ፥
ደስታዬ እንደድመት ፥ ልቤን እየላሰው፥
ሳቅ ሆዴን ሲያምሰው፥
ባዶዬን ቢሆንስ፥
ብቻዬን እንደእብድ ፥ የምታየው ለሰው?
እንደንፋስ ነክቶኝ ፥ ሲያልፍ ሰቀቀኔ፥
ከተዳከምሁበት ፥ ከውብ ሰመመኔ፥
'ቢሆንስ?' እያልሁኝ፥
ድንገት እየባነንሁ ፥ እፈራለሁ እኔ፥

መቼም፥
ነፍሱን መርጦ አጥቦ ፥ ውድ አካል ቢያለብሰው፥
ምን ያህል ቢወደድ ፥ ፍቅር ቢያንተርሰው፥
እንዲህ ሁሉ አምሮለት
በስጋና በደም ፥ አይገለጥም ሰው።

©ሚካኤል ሚናስ

@wegochi

Thoughts

12 Nov, 04:42


እንኳን በሕይወት ነቃችሁ‼️

በሰላም ስላደራችሁ ደስ ይበላችሁ!

በዓለም ላይ በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ አይሮፕላኖች እየተነሱ በሰላም ያሰቡበት በመድረስ ያርፋሉ፡፡ ከእነዚህ በረራዎች መካከል ግን የአንዱም እንኳን በሰላም መግባት በዜናዎች ላይ ሲነገር አንሰማም፡፡ ሆኖም፣ አንድ በረራ ላይ አደጋ ከደረሰ ግን ትኩረት ይስባል፣ ዜናውን ይሞላዋል፣ ወሬው ይሸጣል፡፡  

የአንድ ጤናማ ሰው ልብም ቢሆን በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ ይመታል፡፡ ይህንን ያህል ጠንክሮ የሚሰራው አካላችን ግን በቀን ውስጥ ትዝም አይለን፡፡ የምናስታውሰው መምታት ለማቆም ሲዳዳውና የምቱ ድግግሞሽ ሲለይብን ነው፡፡ ለምን? መልካሙ ነገር ተለምዷል፡፡ የምስራች የሆነው ነገር ትዝም አይለን፡፡ 

ዛሬ መልካም መልካሙን ላስታውሳችሁ፡፡ ዛሬ የምስራቹ ትዝ ይበላችሁ፡፡ በሰላም የመንቃታችሁ ጉዳይ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ እናንተ ላይ ያለመድረሱ ጉዳይ፣ የደረሰባችሁ ነገር ከዚህ የከፋ ያለመሆኑ ጉዳይ . . . ትዝ ይበላችሁ፡፡

ከደረሰብን ክፉ ነገር የሆነልን መልካም ነገር ይበዛልና ደስ ይበላችሁ፡፡

ፈጣሪን አመስግኑ! ቤተሰቦቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና በሕይወታችሁ ላይ መልካም ተጽእኖ ያደረጉ ሰዎችን አድንቁ!

መልካም ቀን!

Thoughts

11 Nov, 12:32


የእለት ‹‹ነገራችንን›› አትንሳን!
(አሌክስ አብርሃም)

እያንዳንዱ ብሔርና ብሔረሰብ "ኢትዮጵያ አገሬ ባህሌን፣ ወጌን ፣ትውፊቴን ታክብር አለበለዚያ ...." ቢልስ? ለምሳሌ ብዙ ጊዜ የሰወችን "አክሰንት" ወይም ሌላ አካላዊ ገፅታ፣ ባህልና አምልኮ በመስማትና በመመልከት ? በጨዋነት ብሔራቸውን ትገምታላችሁ። እና አክሰንታቸው እንደፈለገ ይወለጋገድ ፣ ገፅታቸውም ይሁን አለባበስና ባህላቸው ምንም ይሁን እምነታቸውን አትመኑበት ቢያንስ ፊት ለፊት መጥፎ ነገር አትናገሩም። ብሔር ናታ! እሳት ናታ! ኡፉ ናታ! እንደውም "ኢትስ ኦኬ" ልትኮራበት ነው የሚገባው ብላችሁ ለመመሳሰል ዘጭ እንቦጭ ምናምንን ነው የምትሉት። ኋላ ቀር ጎጅ ምናምን ማለትማ አይታሰብም።

ቦርጫም ወንድ ስታዮ ግን፣ ስፖርት ስሩ፣ ኮሌስትሮል .... ምናምን የምትሉት ለምንድነው? ለቅፅበት እንኳን ፊታችሁ የቆመው ጓድ የቦዲ ማህበረሰብ ያፈራው ኢትዮጵያዊ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ለምን አታስቡም? ከተማ ብገባም ወግና ባህሌን ማንነቴን አልጥልም እምቢኝ ያለ ቦዲያዊ የለም ያለው ማነው?! በቅድም አያቴ በምንጅላቴ ቦዲ ነኝ ቢልስ? እንደውም "ቦርጭን ለማጥፋት" የሚል ንግግር የአንድን ብሔር ወግና ባህል ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ በህግ ሊታገድ ይገባል ቢልስ? በብሔራዊ ቴሌቪዢናችን ሳይቀር ባለሙያ ጋብዛችሁ "እንዴት ቦርጭ ማጥፋት እንደሚቻል" ትሰብካላችሁ። ምንዓይነት ሕዝብን መናቅ ነው ይሔ ወገኖቸ?! የጥላቻ ንግግር ልንለው እንችላለንኮ።

የሆነ ሆኖ የቦዲ ማህበረሰብ ግን በሞጋሳ / ጉዲፈቻ ወዘተ የብሔራቸው አባል የሚያደርጉበት ስርዓት ይኖራቸው ይሆን? ባንዴ በኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ነበር የሚሆኑት። ወይ ደህና መካሪ ማጣት!ከተሜው በሙሉ ቦርጭ የታደለው ነውኮ የሚመስለው። ደግሞ ጅም ሂዱ ማለት ምንድነው የአንድ ብሔረሰብን መገለጫ ለማጥፋት ይሄ ሁሉ ርብርብ ለምን? እንደውም ከለጠጥነው ዘር ማጥፋት ጭምር ነው! ቦርጭ ከሌለ ሚስት የለም! ሚስት ከሌለ ዘር ከየት ይተካል? ዘር ማጥፋት ወይ የተወለደውን መጨፍጨፍ አልያም እንዳይወለድ ማድረግ አይደለምን? ይችንም ብሔር ጋር ካላያያዝናት ማንም እየተነሳ ሊዘልፈን አይደል? በዚህ አጋጣሚ የሐመር ሴቶች ኢቲቪ ፣ፋና ተቀጥረው በባህላዊ አልባሳታቸው ተውበው ዜና ያንብቡ ፕሮግራም ይምሩ ፣ ፖርላማ ይሰየሙ ብየ የጠየኩት ነገር ከምን ደረሰ? ኧረ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ እየሰጣችሁ ጓዶች!

እስኪ ሰላም ያውለን!

@ዳና

Thoughts

10 Nov, 15:23


እንዲያድግ የሚፈልጉትን አበባ ውሀ አለማጠጣት በእርግጥ ማስተባበያ የሚሰጥበት ነገር ነው? አዎ ልክ እንደሱ ለሁለት ሰው ጥምረት ያኛው ሰው ብቻ ጥረት ያድርግ ብሎ መጠበቅ ልክ ይሆናልን?!

እሺ ይሁን...አበባውን ውሀ አለማጠጣት ማስጠየቁ እንዳለ ሆኖ እየተንከባከቡት አላድግ ያለ አበባ አውጥቶ እስኪጥሉት የትዕግስት መጠኑ ስንት ይሆን?! ለፍቶ ለፍቶ ለውጥ ሲያጡ ለመተው፥ ላለመኮነን ስንት ይሆን የሚፈጀው?!


ናኒ



https://t.me/justhoughtsss

Thoughts

10 Nov, 14:25


የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ስላለኝ ፥ ተራራውን አንቀሳቅሳለሁ። ተራራውን ግን ገፍቼው አላውቅም። የማውቀው ተራራውን ወደ እኔ ማቅረብ ነው። የኔ ችሎታ... መከራን ከደመና ውስጥ መጥራት፣ ከአለት ውስጥ ፈልፍሎ ማውጣት፣ እንዲሁም ከጥልቅ ጉድጓድ ስቦ ማውጣት ነው። ግን ይህም ተዓምር ነውና።

Thoughts

09 Nov, 06:50


  ምን እየጎዳን እንደሆነ ታውቃለህ?!
ግማሽ እውቀት...

    በዘመናችን እንደዚህ ወቅት የተራራቅንበትን ጊዜ አላውቅም "ያ አብሮ አደግሽ እንዴት ነው ደህና ነው ግን?" ተብላ ስትጠየቅ "አውርተን አናውቅም ግን online አየዋለው ያው ደህና ቢሆን ነው" ትላለች

     እሱም ቢጠየቅ "የሆነ ነገር ገጥሟት ቢሆንስ የጠፋችው ወይ ደውልላት ወይ አግኛት እንጂ" ሲባል "ኧረ ምንም አላጋጠማትም story ስታደርግ አያለው ያው ደህና ብትሆን አይደል?!" ይላል

     ምን ማለት ነው?! ይሄ ቁንፅል መረጃ እውነት የደህንነት ማረጋገጫ ይሆናል?! ወይስ ህመማቸውን እና ችግራቸውን post እንዲያደርጉ ነው የምንጠብቀው?!

     ሰው ከsocial media ሲጠፋ personal time ፈልጎ ነው ወይ ጠግቦ ነው ከማለት ውጪ ምን ያህሎቻችን ነን concerned ሆነን የእውነት ደህንነታቸውን ለማወቅ የምንፈልገው

     ስንደውልላቸው ተፍገምግመው "ደህና ነኝ" የሚሉን ሰዎችስ ስናገኛቸው ተጎሳቁለው አስደንግጠውን አያውቁም?! ስለዚህ ይሄ የተቀነጨበ መረጃ ስለወዳጆቻችን እውነተኛ ሁኔታ እንድንደመደም እንዳያደርገን

    scroll ማድረጊያ ጊዜ አለን አይደል እስኪ ለመገናኘት እናድርገው እሱን ጊዜ አይመስላችሁም?!


ናኒ


https://t.me/justhoughtsss