ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . @samuel_dereje Channel on Telegram

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

@samuel_dereje


ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት

ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች

😊 - @Samvocado




https://linktr.ee/samueldereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . (Amharic)

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . እናቴን፣ ሙዚቃን እና ትየሻን የሆኑ ተረኮችን ለእኛና ለምንም ሰው ገላገሉ። ይህ በሁሉም በተለያዩ ኒዘ ሜዳ ጊዜ የሚገኝ ተረኮ ነገር ነው። እናንተም በማያነሱ ጥቆማዎች ሁሉ ጥሩ እንደሆኑ እንደምጉፑ ሁሉ የእለቱና የክንዱ ተረኮችን ለግራም አልቅሱን በሽራ ሊነኩ ነው። በሜዳ ፖሊሶችና በትሩ ምግባሮች ከተነበብን ይችላሉ። ጥቃት በተግባር መመላለሻ ተደራሽነትን አስከብረዋል።

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

19 Jan, 06:42


ነግሬሽ ነበር?

ደመና ቀን እንደማልወድ? ካፊያ እንደሚጨንቀኝ ፣ ዝናብ ድብርቴ እንደነበር? ደሞም ተራ ሁነት – ተጠልዬ ፣ ኮት ደርቤ የማሳልፈዉ።  

ይግረምህ ሲል ጥላ ጨብጠሽ ፥  ዝናብ ላይ አጊጠሽ ካየሁ ወዲህ ክረምት ናፋቂ ሆኛለሁ። 

ተስፋ አይሰንፍ .  .  . ሃምሌ መሃል ወለም ላለኝ ልብ — ይኀዉ ጥር መሃል እታሻለሁ።


.

@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Dec, 18:59


“Believe me, I know what it's like to feel all alone... the worst kind of loneliness in the world is isolation that comes from being misunderstood, it can make people lose their grasp on reality." ― Dan Brown, Inferno

And I wish you also knew this state of isolation. Sadly you don't. Or maybe that's good? But you won't ever be able to get too close. You'll always be on the periphery. I wish I could share more today.

I wish I could tell you more. Why I'm the way I'm. Why I say the things I say. And above all where all the anger & resentment comes from. I wish I could spell it out for you. The damages of the past became the builders of tomorrow's misery.

Someone else did the harm and someone else has to pay for it. How is that even fair you asked me? And I obviously had no answer. The silence between us is not due to lack of conversation. This silence has my screams in every fold.

I wish you could hear that. I wish you knew. My reality has now become your misery.

I'm now your inferno.

I'm extremely sorry.

Because I have a lot of unfulfilled wishes.

And Sorry about that...

Photo: Sosina Mengistu

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

18 Dec, 07:25


ደስታ! ከረሜላ ብቻ አይደለም።



"ልጅ ሆኜ የሆነ ቀን ደስታ ከርሜላ ገዛሁ።  እንደልጅነቴ የኔ በሆነዉ ከረሜላ ያለቅጥ ደስ ብሎኝ ነበር . . ."

ሳዉቃት ልጅ ሆኜ ነዉ። አብሮ አድጌ ነበረች።  ቤቴ ቤቷ አጠገብ ፥ እናቴ የእናቷ ወዳጅ ነበሩ። አብሮ የተሰፋ ልጅነት አለን። ብዙ የሱዚ ገመዶች ቀምቼያት አልቅሳለች ፥ ብዙ  የዉሸት "መታኝ"ኞች ለእናቴ አቃጥራ ተገርፊያለሁ። 

ሰኞ ፥ ማክሰኞ ስትዘል የተደበቀ ፥ ጠጠር ስትለቅም ያልታየኝ ፥ አኩኩሉ ስትል ያልጎላ  ጡት አጎጥጉጣ  አይን ስትገባ  በለስ እንደበላ አዳም ዉበቷ ለአይኔ ተገለጠ።  ( ለእኔ ብቻ አይደለም - ለሃገሩም)

እንደሌላ ቁንጅናዋን ፥ ሴትነቷን ብቻ ሳይሆን ሳቋን ፥ እንባዋን እንዳየ። ሥሥ ጎኗን እንደፈተሸ ( በልጅ ልብም ቢሆን)።  ልጅ ሳለን በልፊያ ከፍም ካልን በጥልቅ ወሬ  ልብ ምቷን እንደመዘነ ፥ ቀድሞ ከንፈሮቿን እንደቀመሰ ፥ በሄደችበት እንዳጀበ  (በዚህ በእኩዮቼ ቢቀለድብኝም) ፥ ከእናት ከአባቷ በፊት ተጠሪዋ እንደሚባል አንድ ሰዉ ፤ ልመስክር። አመሏ ከመልኳ ይረቃል ። ከገጿ እኩል ግብሯ ያምራል። 

ላይወዷት ትከብዳለች!

፪ 

" ከረሜላዬ በእጄ እንዳለች ልጣጯን ብዙ ጊዜ ፈትቼ ብዙ ጊዜ አስሬያታለሁ። ልበላት አልቸኮልኩም! የኔ አይደለች?" 

"የምኞት አስኳል አለመጨበጡ ነዉ ፤ ሰዉ ለያዘዉ አይጓጓዋም?" ይሉት ፍልስፍና አለ።*  እዉነት ይመስላል። ግን አንዳንዴ የጨበጡትም ያጓጓል። አንዳንዴ!

እናም ባደግን ቁጥር መላመዳችን ጎላ! ሳቋ የቀን ማጀብያዬ ሆነ። እቅፏን ብቻ ሳይሆን ኩርፊያዋን እናፍቅ ነበር። አብረን ዉለን ሲመሽ መግቢያችን ያባባናል። እልፍ ጊዜ ቻዉ እያለች ዳግም ከንፈሮቿ ወይ በወሬ ወይ በእኔ ከንፈር ይጠመዳሉ። ሰባ ጊዜ ቻዉ ብላኝ በሰባኛዉ ትሄዳለች። እያመናታች። የሸኘኋትን ልጅ እያናፈኩ ቤቴ እገባለሁ።  

የሆነ የሆነ ቀን የምናወራዉ የለንም። ጋደም ባልችበት ወደ ደረቷ እጠጋና ልብ ምቷን እሰማለሁ። የረጋ ፥ ጊዜ የጠበቀ ነዉ። ወደ ከንፈሯ ስጠጋ ግን ይፈጥናል። ስስማት ከልጅ ልቧ እኩል ትንፋሿ ይፈጥናል። ረግረግ ነበረች። የሆነ እድሜዬ ስሯ ሰርጓል። 

በዚህ ሁሉ ግለታችን ዉስጥ ጭኗን ከፍቼ አላውቅም። የሆነ የሆነ ቀን በእጄ የታፋዎቿን ግለት ለክቻለሁ። አልክድም! ግለቱ ይጋባ ነበር። ግን ቃሏ ይቆይ ስለነበር መሻቷን አልገፋሁም። ገና ዘመናት አብረን አይደለን?።

"የኔ ናት!" ፥ እንደዛ ብዬ ነበር።



"ጉጉቴ ሥሥቴን ሲያሸንፍ  የከረሜላዬን ልጣጭ በእርጋታ ገፍፌ ወደ አፌ ልከት ሳስጠጋ  ከእጄ ወድቃ እግሬ ስር  ያለ አፍር ላይ ወደቀች።  ላነሳት ያየኝ መኖሩን ልቃኝ ቀና ስል ከእናቴ ጋር ተያየን።
 " በል አንሳና ጣል"  ትዛዝ ነበር።


 ከነሥሥቴ ሳላጣጥማት ሄደች - ከረሜላዬ! " 

እድል ፍትህ የላትም። ተስፋ ከጤዛ ያጥራል። ሰዉ ስለፈልገ ብቻ አያገኝም። ሰዉ ስላልጠየቀም አያጣም። ይጠማል ፥ ሲለዉ ሳይደግስም ይጣላል።

እንዲህ ሆነ . . . አደገች ፥ አደኩ። ለዉጥ አሻች። እንደትናንት  በመሳም ልቧ አይመታ ፥  ከሆዷ መሳቅ ተወች።  ሁሉ ቀልድ ለዘዘባት ፥ ወሬችን ወደ ቅጽበቶች አጠረ።  መጣበቃችን ላላ። እኔ እና እሷ እንዳልነበርን። በወራት እኔ እሷን እና ብዙ ወንዶች ሆንን። 

በጊዜ እንደሸረሪቷ ቀስ በቀስ ሸረተት እያልን ከእኔ እጅ እሷ ፥ ከእሷ ልብ እኔ ሾለክን።

የሆነ እለት ምን ጆሮ ለባልቤቱ ባዳ ነዉ ቢሉ ከርሞም ቢሆን ሰማሁት። "ይቆይን ለሌላ እንዳላለች። ብዙ አንዳቀፈች ፥ ብዙ እንዳላበች። ዝግ ጭኗ ፥ ዛሬ መንገድ እንደሆነ።" እና ሌላም ያመመኝ ብዙ ነገር . . 

 ግን ምስክር ነኝ።  ሰናይ እንደነበረች። ጸደይ ነፍስ እንደነበራት!

ከእሷ ወዲህ "መልክ ይረግፋል። አመል እንጂ ዉበት አላፊ ነዉ" ሲባል ሳቅ ያፍነኛል። የቱ ፈላስፋ ነዉ የአመልን ዘላለማዊነት የሰበከን?  የቱ አዋቂ ይሆን ጸባይን ከመልክ በላይ ያነገሰዉ? መልክም ፥ ጸባይም አላፊ ነዉ።  ጊዜ አይለዉጠዉ የለም። 

"ትወደኝ ነበር!"  ነበር እንኳ ይለወጣል።


.

@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

13 Dec, 18:46


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

05 Dec, 18:00


ከዝቅ ይልቅ ፣ ከፍ ያድጣል። ማጣት ከወሰደዉ ምቾት የነጠቀዉ ይበልጣል።  

ሃገሬዉ " ችግር ነዉ ጌትነት ካላወቁበት" እንዲል!


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

03 Dec, 19:00


ቀይዋ ወፍ ፥ ቀይዋ ወፍ . . .

መልከኛ አይደለችም። ወይ ዉብ የሚሉት አይነት። በልክ ግን አይን ትገባለች። ሰዉ ቀን ቢሆን ለበዓል ብታንስ ቆንጆ ቅዳሜ ይወጣታል። ረዥም ናት። ከፊቷ እኩል የጎሉ ጥርሶች ፣ የሚያስቅ ደሞም የሚያጓጓ የከንፈር ቅርጽ አላት።  ቀይ ናት። ጸጉሯ የሆነ ማንነቷን ያሳብቃል። ችኩል አትባልም። እንደዛዉ የረጋች አይደለችም። በአንዴ ሁለቱንም ያልሆነች አይነት. . . 

ሳገኛት ቦሌ መጨላለሙ ነበር። ተቀምጣ ከጠበቀችኝ ካፌ ፍሪዝ ባረገችዉ ጸጉር ጎልታለች። 

 ተነስተን አንድ ቅያስ አልፎ የነበር ባር ገባን።  እንደተቀመጥን "የመጀመሪያ ወንድ ነህ። በስልክ አዉርቼ ያገኘሁት" አለች። ያወራሁትን ሁሉ አላገኝም ልትል። ድምጿ አዘቦት አይነት ነዉ። ዞር ብል የምረሳዉ።

"ልዩ ነኝ ኣ!"

" አይደል" ፈገግ አለች። ስላቅም ፥ ጨዋታም  ያለዉ አይነት። 

 እናወራለን ፥  ስለምን እንደምናወራ ግድ አላለንም። ስለምንም ብናወራ ወሬው አይጠነክርም ፥ አይሳሳምም። አይደብርም ፥ አይደንቅምም። ትንሽ ትስቃለች ፥ ትንሽ እስቃለሁ። ትንሽ ትቀልዳለች ፥ ትንሽ እቀልዳለሁ።

 በመሃል ዝም ይዉጠናል። በደበዘዘዉ ብርሃን አይኗን ፍልጌ አያለሁ። አትረበሽም።  በሃሳቧ ትጠፋለች ፥ እኔ ደግሞ በአይኗ።  እንደወሬያችን ዝምታችንም ያዉ ነዉ። አይቀዘቅዝ አብዝቶ አይሞቅ። ለብ ያለ።

ድንገት ድንገት የሆነ የጠጠረ ጥያቄ ትወረዉራለች። ቀልድ ይመስል። መልሰን በጥያቄዋ ወደ ለዘብተኛ ወሬያችን እንገባለን።  
ሳናዉቀዉ ( ወይ እኔ ብቻ ) ተላመድን። እጆቿ እጄ ላይ ከረሙ። አካሏ ሲቀላት ፥ ሳቋ ነጻ ሲወጣ። 

በመስኮቴ ገባች. . .

የሳምኳት ቅጽበት እንደልጅ የሃሴት እለት ያለ ነዉ። ዛሬ ድረስ ትዝ የሚል . . .

 ሥስማት አይኗን የከደነችበት ዝግታ ፈጥኖ  ፥  ከንፈሬ ከንፈሯ ደጅ እስኪደርስ የዘላለም ያህል ራቀብኝ። ሩቅ ሆኖ.  . . ሲደርስ የጠበኩት እረፍት አለዉ። የሆነ አይነት መመረጥ። 

ከዛ ወዲህ የዝምታ ልዋጭ አገኘን።  መሳም የሚሉት ምትሃት . . .

ከአካሏ ተላመድኩ። በህይወት በብዙ ምርጫ ግራ ፥ ቀኝ ማትሪያለሁ። እሱን ያቀፍኩ ቀን " የምፈልገዉ ይህ ነዉ አልኩ"

በመስኮቴ ወጣች

የሆነ ቀን ድንገት ጠፋች።  እንዲያ ለምጄ። ብደዉል ብደዉል ምላሽ ጠፋ።  ጠብኩ አልደወለችም።  ደገምኩ ፥ ሰለስኩ። አይነሳም። ተዉኩት። 

ረሳኋት። ወይ እንደረስኋት አሰብኩና ህይወት ቀጠለ . . .

ከቀናት ወዲያ እለት እለት ይባስ አስታዉሳት ጀመር። እንዴት? እንጃ! ግን ዘመን አብሬ የከረምኳቸዉን በሳምንት እንዳልረሳሁ በአንድ ጣት ቢቆጠር የማያልቅ ቀን ያገኘኋት እሷ እንዲ ልቤን መርገጫ አሳጣች። 

አላስቻለኝም። መልዕክት ላኩ "ምነዉ" የሚል። የሆነም ቀን እንዲ ጠፍታ መመለሷ ትዝ ሲለኝ። ረጅም ምክንያት ያልሆነ ምክንያት አወራችኝ። " ባንተ አይደለም ፥ ያልፈታሁት ነገር አለ አይነት"  ቃል በቃልም ባይሆን እንደዛ። ልቤ አመነ ፥ ቀልቤ በሞኝ ልቤ ሳቀ . . . 

ደወልኩ። አነሳች።  ረጅም ወሬ ሳወራት መሸ። እንደድሮ ሞቅም ያለለ ፥ ያለዘዘም። ልቤ ዳጋም ተስፋ ጣለ. . .

ዉይ በራ ሄደች! . . .

ከዛ .  . .  ከዛማ ዳግም ጠፈች። ዳግም ደወልኩ ፥  አይነሳም። አሁን ገባኝ ፥ ተዉኩትም። 

ለምን ቀረች? ጥያቄ አይደለም። ምክንያቱ አይገድም መቅረቷ እንጂ  .  . .

ሳስብ ብዙ ሰዉ ገብቶ በሚወጣበት ህይወታችን ጥቂት ናቸዉ  እንዲ ልብን አከዉ የሚያልፉት። ቀናት መተዉ ፥ ወራት የሚናፈቁት።  ስለተለዩ  ፥ ስላማሩ ፥ ወይ ስላወቁበት ሳይሆን እንዲዉ እድል ፥ ምርጫ ሆኖ . . . 

ብቻ ዛሬ ሲገባኝ ያ ቀን ሸረተት ብያለሁ። ከወደ ልቤ . . .


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

22 Nov, 08:47


ዘመኑ ከብዶናል። ኑሮዉ ብቻ ሳይሆን ከጊዜዉ ጋር መግባባቱም።  

ለአንዳንዶች ዘመን ኋላ ቀርታለች። ሃገሩም ፥ ባህሉም አልፎበታል።  ሊጎትቱት ይታገላሉ ፥ እነሱን እንዲመስል። ኋላ ቀር ወይ ያልነቃ እያሉት። አፍ አዉጥተዉም ባይሆን . . . በመብት ወይ በመሰልጠን ስም።

አንዳንዶች ነፍሳችው ገና ነች። ወጉንም ፥ ስርአቱንም እናጥብቅ ባይ ናቸዉ። ቸኩሏል ይላሉ — ትዉልዱ። ሰይጥኗል ፥ ዘምኖ ሞቷል አይነት። ከፊሉ እምነቱን ሙጥኝ ብሎ ፥ ሌላዉ መጪዉ ባህል እሱን አልመስል ሲለዉ። 

ገሚሱ ግራ ገብቶታል። ቢዘምን ቢዘገይ ግድ ያለዉ አይመስልም። ወይ ይሄን ለማሰብ ኑሮዉ ቀና አላረገዉም። የሚከንፍ ባቡር መንጠላጠል ሆኖበት ሰርክ ሊሳፈር ያደገድጋል። አጀንዳዉ እንደ ንፋስ ነዉ። አንዱን አንስቶ ሳያመነዥግ ደግሞ ሌላዉ ያፉጫል። ሃሳብ ይሰጠዋል እንዲያስበዉ ግን ጊዜ የለዉም። 

ደሞም ቅንጦት አይደል? ደህንነት ፣ መጥገብ ይጠይቃል — ስለሚሰማን ለማሰብ።  

ተመሰገን ነዉ! እንዲህ ምን እንደሚሰማን  ለማሰብ ጊዜም ፥ ህይወትም ቅንጦት ለሰጠን። እልፉ ቢጤያችን ያንን አልታደለምና።

.

.

Like Dave says in his special Stick and Stones " I did something most people didn't have the time or the luxury to do, I think about how I feel"


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

21 Nov, 15:54


በማለዳ ወይራ እንደለኮሱበት ጎጆ  ጭስ ያፈነዉ ከተማ ሳይ . . .

እንደሁሉ ያገሬዉ ሰዉ ደጁን ጠርጎ ጥራጊዉን በእሳት እንደሚያነድ ፤ ትዝታሽን ብርታት ኖሮኝ ከሳሎኔ ገፍቼ በራፌ ላይ ባነደዉ ፥

ስማቅቅ "ምን መሆኑ ነዉ" ያለኝ መንደር
ባንቺ ፍቅር መታፈንን ያየዉ ነበር ....


#ህዳርሲታጠን

@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

14 Nov, 07:34


በምልክት ለማያምን ትዉልድ ተአምር አይረጋም።                                       

ተአምሩ ሲጀምር . . . 

 ተራምዳ ከጎኔ ስትቆም በቸኮለም ፣ በሰለቸም ቀልብ ምድር ላይ ሆኜ ከ10ኛ ፎቅ የሚወርደዉን አሳንሰር ስጠብቅ ነበር። 

 ቀይ ናት። ሰአሊ ከሙሉ የሸራዉ ቅብ እልፍ ጊዜ እንደተመላለሰባት አንዲት መስመር  ማርያም የሳመቻት ጠብታ ምልክት ጫፍ ግንባሯ ላይ ብትኖር እሷን አጉልቶ የሚያሳብቅ ቅላት ያላት። 

ቆንጆም ናት። ጥንቅቅ ያላ አፍንጫ ፣  ልቅም ያለ አይን ፣ ሌላ ጥንቅቅ ያለ ከንፈር አላት። ሰልካካ ፥ ብርሃናማ ፥ እንጆሪ ወዘተ እያሉ የማያቃሉት ፥ ማስረዳትን መዘላበድ የሚያረግ ገጽ — ትሁት የሆነ ማማር ። ዛሬ ዛሬ ቁንጅና ላይ ትሁት ዉቃቢ ማንበብ በቀትር ጤዛ እንደማየት አይነት ግራ ገብ ሁነት አለዉ። እፍኝ መልክ  እንስራ ሙሉ አለመርጋት ይጠራል። 

ተአምሩ ሲቀጥል .  .  .
 
 ቀሰስተኛዉ ሊፍት በዝግታ ሲከፈት ቀድማ እንድትገባ ዘገየሁ። ግብዣዬ ገብቷት ቀደመች። ተከትልኩ። 

እፍኝ ካሬ በሆነ አሳንሰር እኔና እሷ ወደላይ ማረግ ጀመርን። ቀና ስትል አይኗ ከአይኔ ገጠመ። ፈገግ አልኩ ፣ ፈገግ አለች። ልቤ ተስፋ ስተፋ ሶስተኛ ላይ እንዲቆም የተጫንኩት አሳንሰር መዉረጃዬ ላይ ደርሶ ተበረገደ። 

[.  . . አዉቃለሁ ያሁሉ ፈላስፋ ልክ ነበር። ህይወት ትርጉም አልባ ናት] 



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

03 Nov, 10:05


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

24 Oct, 11:59


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

05 Oct, 08:12


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Sep, 11:39


ፍቅር ለእዉነት ቦታ የላትም። መወደድ ምናብ ይጠይቃል። የሚደንሱ ልቦች ፣ የሚጠለቁ ጭንብሎች ይፈልጋል። 

ፍቅር ከራስ ጋር የሚደረግ ሽንገላ ነዉ። በአፈቀርከዉ አይን ዉስጥ የምታየዉ የምትሻዉን ፥ የምትወደዉ የጎደለህን ነዉ። መዉደድ ከእዉን ለህልም ይዛመዳል።

"Love is a mutual misunderstanding" እንዲል Oscar Wilde!



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

18 Sep, 19:30


ከጊዜ በላይ መድሃኒት የለም ቢሉ ሰዉ የሌለበት ጊዜ ከምን ያድነኝ ነበር? ከዋግምት ይልቅ ሰዉ ህመም ይነቅላል። ከኮሶ የልብ ወግ ሆድ ያጥባል። የልጅነትን ምች ከዳማከሴ ይልቅ በወዳጅ ፍቅር ይታሻል። 

ቂሜን እንደክረምት አፈር ፥ ጨዋታ ሸርሽሮታል። ሳላዉቀዉ ጓደኞቼ ያጠቡት ህመም ነበር ። ሃዘኔን እንደቅርፊት አብሮ መሳቅ ልጦልኛል።  

ወዳጅ ትልቅ ጸበል ነዉ። ላመነ — የማያባረዉ ጋኔል ፥ የማያስወጣዉ ዛር የለም።

.

.


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

15 Sep, 12:44


ከለት እለት አንድ የአዲስ ትዉስታ ይፋቃል። አዲስ አበባን አዲስ ያረጓትን ህብር ማንነቶች የሰሩ ዉህድ ልጆቿ ፤ በልማት እጅ እንደጥሬ እየታፈሱ የትም ይበተናሉ። መሃል ለእነሱ ክልክል ሆኗል። በገንዘብ ሳይሆን በመደጋገፍ ካሳም የቆሙ እልፍ ረዳት አልባዎቿ ከጃጁበት ደጃፍ፥ ከቆረቡበት ደብር በአንድ ሌሊት ወና የከተማ ዳር ላይ ይተዋሉ። በዳር ከተማ — በዳሁበት ሰፍር ችምችም ዉስጥ እንደመቆም ቀላል አይደለም።

ስለትናንት ዛሬን በእግዜር ማለት ቅንጦት ነው። ለዉጥ አይቀሬ ነዉ። ግን እንደእህል የትም ለሚበተኑ የዘመናት የልጆቿ ትስስር ላፍታ የሚያስብ ቢኖር እወድ ነበር።

ክረምቶቿን በትቦዎቿ የተንቦራጨቁ ፣ አፈሮቿን ለብይ ጉድጓድ የቆፈሩ ፣ ቡሄዋን ፣ አበባዮሿዋን በየበሮቿ የጨፈሩ  ልጆቿ ቢመሯት እወድ ነበር።

...ሌላም ብዙ አዲስ "ሀ" አስብላኝ ሳዉቃት የወዳድኳትን  "ኢትዮጵያን" እናፍቅ ነበር።

ግን - በማንነት በላቆጠ ፖለቲካ ቅርቃር  ዉስጥ በነጋ ቁጥር ህይወት የሚጠልቅባትን ሃገር እያየሁ - ነገ መኖራችንንም እጠራጠራለሁ።


.


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

11 Sep, 18:00


በዓልና ማንነት የሆነ አይነት አንድ መመሳሰል አላቸዉ። እኛን እኛ የሚያደርገን ትዉስታቸን ብቻ አይደለም። ትናንቱን የረሳ አንድ ህመምተኛ ሌላ ሰዉ ሆኗል አንልም። የሆነ መንፈሱን ግን ያጣል። ጎደሎነት አለዉ። ሰዉየዉ ራሱን ሆኖም።

ካምፓስ እያለሁ አንድ ሁለት በዓል አሳልፊያለሁ። ያለ ቤተሰብ በዓል ያ ስሜት አለዉ። አዘቦትነት።

አዲስ አመት በምስርም ለዛ ይጠጋጋል። በዓል ነዉ ግን መንፈሱ የለዉም። የሆነ የጾም ቀን እሁድ . . .


እና መስከረም አንድ ነገ ነዉ :)

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

08 Sep, 09:11


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

07 Sep, 13:49


.

የሆነ እለት ሳቃቸዉ ለእናንተ ብቻ እንዳልሆነ ይገባችኋል። ለሌላ ስቀዉ  ወይ በሌላ ታቅፈዉ አይታችሁ ሳይሆን የሆነ ቅጽበት እንደመገለጥ የምትረዱት ሃቅ ነዉ። በምክንያት ሳይሆን "አሃ" ብለዉ ልቤ ነገረኝ የሚሉት።

የሚሰጧችሁ ሙቀት ዉስጥ የሆነ አይነት አዘቦትነት አለ። መሳማቸዉ ክት አይደለም። እቅፋቸዉ መቁነጥነጥ አለዉ። ይሄ ነዉ የማይሉት ግን ልብ አዉቆ "ቅር" የሚለዉ።  ዉሸት ስለሆነ ሳይሆን ጥልቅ ስላልሆነ።  

እንዲህ ናቸዉ። ቀስበቀስ ይቀርቡና እናንተን እያረጉ ፣ እያሰመጡ እነሱ ግን አይጠልቁም።  ሲሄዱም እንደዛ ነዉ ።
ድንገት — እንደተንሳፈፉ . . .


.

@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

06 Sep, 08:24


.

እንዲ ጷግሜ ሲሆን . . .
ዝናብ ያጨቀየዉ የጸበል መንገድ ትዝ ይለኛል። ጷግሜ በገባ ቁጥር የምንመላለስበት እያንዳንዱ ሁነት — ዛሬ ይመስል።

ሁሉን አስታዉሳለሁ ... ሳቅሽን ፣ ጸጉርሽን ፣ በጸበል የራሰ ነጠላሽን ፥ ፊትሽ ላይ የቀሩትን ነጠብጣብ የጸበል ዘለላዎች በጠዋት ጸሃይ ለመድረቅ ሳይረቱ
ሊተዉሽ ያመነቱትን። በብርድ የሚርበተበቱ ጥርሶችሽን ፣ ጥዬሽ እንዳልሮጥ ልመናሽን!

እንዲ ጷግሜ ሲሆን . . . አንቺን ፣ ጷግሜያችንን አስታዉሳለሁ። የወራት ሃጥ በቅንጣቢ ቀናት ልናጥብ የኖራንቸዉን ስፍር ቀናት ።

ዛሬ እንደትናንት አብረን ዘመን አንቋጭም። እንዲህ በልብ እንናፍቃለን እንጂ ልንኖረዉ አልታደልንም።


.

@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

01 Sep, 16:53


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

30 Aug, 16:29


.

በፍሎረንስ ትርታ መሃል በሚያስገርም ውበቱ ፣ ቴክኒካል ብቃቱ እና በጥልቅ ተምሳሌታዊነቱ  ወደር የሌለዉ ግዙፍ የእምነበረድ ሃዉልት ቆሟል - የማይክልአንጀሎ ዳዊት። ይህ የእምነበረድ ጥበብ ብቻ አይደለም። ሰዉ የመሆን የምናብ ጥግ ፤ በጥበብና በጥበበኛ ፥ በአካልና በአለት ፥ በማመንና በፍርሃት መሃል የነበረ ንግግር እንጂ።

ማይክልአንጀሎ ከዛ ቀደም ዳዊትን የሳሉ ወይ የቀረጹ ጥበበኖች እንዳደረጉት ጎልያድን ድል ካደረገ በኋላ በጀግንነቱ ሊስል አልመረጠም። ይልቅ ዳዊትን ጎሊያድን ከመግጠሙ በፊት ከነሰዋዊ መሸበሩ መቅረጽን መረጠ እንጂ። ድልን ብቻ ሳይሆን ከድል በፊት ያለን ፍርሃት ሊያሳየን።

የ26 አመቱ ማይክልአንጀሎ 4 አመት የፈጀ ዳዊት እዉን ለመሆን ተዓምራዊ ማመን የሚጠይቅ ነበር። በሌሎች ቀራጺዎች ተደጋግሞ ተሞክሮ ተስፋ የተቆረጠበትን ግዙፍ እብነበረድ ብሎክ የፍሎሬንቲን ሪፐብሊክን ጥንካሬ እና ነፃነትን ወደ ሚያመለክት የጥበብ ስራ መቀየር መቻል።  

ቅርጹ የዳዊት ጡንቻዎች ፈርጥመዉ ፣ ደምስሮቹ ተወጥረዉ ፣ ዓይኖቹ ወደ ጠላቱ አተኩሮ ያሳያል። በሚያስደንቅ 5.17 ሜትር ቁመት ላይ የቆመው ዳዊት የአናቶሚካል ፍጹምነት ታይቶበታል።  የሃዉልቱ ምጣኔ ፥ የጡንቻዎቹ ዉጥረት ፥ ያተኮረ እይታዉ የእያንዳንዱ ጥርብ ዝርዝር የሰዉን ልጅ ጥበባዊ ጣሪያ ማሳያ ፥ ሰዉ የመሆን ምልክት ነዉ። የማይክለንጀሎ ዳዊት የሰዉ ልጅ መንፈስ ልዕልና ምስክር ነዉ። 


It stands not just as a masterpiece of Renaissance sculpture, but as one of the greatest artistic achievements in human history.

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

29 Aug, 09:19


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Aug, 07:21


.



@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

23 Aug, 08:17


.


የስንቶቻችን ህሊና ከበቀል ፍትህ ተጠማ? የምን ያህላችን ልብ ከቂም ምህረት ናፈቀ? እዉነት ሁላችን ሰላም ናፈቅን ወይስ "የእኛ" ያልናቸዉ የማይሞቱበት ጦርነት?

እያየን ምልክቶቻችን በጥላቻ ጭቃ ላቆጡ። አርያዎቻችን ከአትሮኖስ መርዝ ወረወሩ ። የደንባራ እረኞቻችን ሰይፍ የእልፍ መንጋ አንገት ቀላ።

ስለነጻዉጪዎቻችን ስንጮህ ስለራሳችን ማንባት ዘነጋን። ለሁላችን የመጣን ሞት መላክ "እንደእኛነት" ከመጋፈጥ ምሮ እንዲያልፈን የቤታችንን በር ዘር መቀባት ወደድን።

በልባችን ካለዉ እባብ የምንፈራዉ ጠላት ማን ነበር? ኩሸት ከሚተፋ ምላሳችን በላይ መጥፊያችን ከየት መጣ?

. . . እኛ የእኛዉ ጠላት ፥ እኛ የእኛዉ ባዳ።


@samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

21 Aug, 11:18


.

Speak a little softer. Maybe much softer. Turn more pages, highlight more lines. Quit doubting (if I start). Start writing (if I stop). Savor moments (if I forget). Compliment that stranger on her smile and turn her into more than a stranger. Write stories for her, so she can share them with my daughter. Face my fears, take them out for coffee, and have tales to share my son. Plant dreams in the quiet corners of my mind. Leave my mark on the world, evidence that I lived, here, and here, and here.

Inhale. Exhale. Carry on. Carry on.


Inspiration and Form - @Spokensincerly - Five year plan



@Samuel_dereje

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

18 Aug, 09:15


በክኒኑ ፈንታ ቀለም እና ቃላት ፥ ሐኪሞች ሲያድሉ
ሕመሙን ማስጌጥ ነው ፣ የሰው ልጅ ዕድሉ::
- በዕዉቀቱ ሥዩም


ቋጠሮዎች ነን - የሰዉ ልጆች። ብዙ ድርብርብ ፍላጎት ፥ ስሜት ፥ ማንነት አሉን። ደሞም ወጥ አይደለንም። በኖርን ቁጥር እንደቅርፊት የሆነ የምንተወዉ ማንነት አለ። ለዉጥ አይቀር እንዲሉ። እንደዛዉ በብዙ ተለወጥን ፣ ኖርን እንበል እንጂ ከጉያችን የማይጠፋ እንኛነትም አለ። ልጅ ሆነን የነበረ።

የዚህ ተከታታይ የሃሳብ ቅኝት ግብ ያ ነዉ። ሕመሙን ማስጌጥ ብቻ ሳይሆን ዉስብስቡን የማንነት ድሪቶ በቀለም እና ቃላት ለመፍታት መሞከር።

በዚህ ቅኝት አንዳንዴ ጥሬ መሳይ ደረቅ ሃሳቦች ይገጥመን ይሆናል። ለምን ከዓመታት በፊት ስለሞቱ ፈላስፎች ይገደናል? ልትሉ ትችላላቹ። የኔ መልስ የምንቆምባቸዉ ትከሻዎች ስለሆኑ ነዉ።

መቼም በሰብአዊ መብት ታምናለህ? ሰዉ ልጅ ክብር ይገባዋል ብለህ? ምን ሃይማኖተኛ እንኳን ባትሆን? አትርሳ የካንት እዳ አለብህ። የሃይማኖተኛ ሃገር ሆኖ መገዳደሉ ገርሞህ ያዉቃል? የሚያደርጉት ግራ ገብቶህ እዉነት እነዚህ በአምላክ ያምናሉ ብለህ? ኒቼ ሊያወራህ ይፈልጋል። ሰዎች የማይረዱህ ይመስልሃል? ወይ ለሆንካቸዉ ነገሮች ወላጆችህን ፣ አስተዳደግህን ኮንነህ? ፍሮይድ ህመምህ ይገባዋል። ድንገት ከዉስጥህ የሚወጡ ማንነቶች አይተህ ታዉቃለህ? ስትናደድ ወይ ሲከፋህ? ማን ነዉ ደሞ ይሄ ሰዉ ብለህ? ዮንግ ለምን የሚለዉን ያስረዳሃል። ያለህ ምንም ሳይመስልህ ሌሎች የያዙት አጓግቶህ ያዉቃል? ለምን በእኩዮችህስ እንደምትቀና? ሬኒ ዤራርድ መልስ አለዉ።

በዚህ ቅኝት የትናንት ሃሳቦችን ከህይወታችን ፥ ከልማዳችን ጋር እያስተያየን አሃ እንላለን። Join me, The Journey is worth it!



ቅኝት የምናደርግበትን አዲሱን ቻናሉን ለመቀልላቀል @samvocado1 ላይ መቀላቀል እፈልጋለሁ ብላቹ ላኩልኝ።

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

14 Aug, 15:39


.


ሰለሞን “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዛብሄርን መፍራት ነዉ’’ እንዲል ሶቅራጥስ ደግሞ “የጥበብ ሁሉ መጨረሻ ራስን ማወቅ ነዉ” ያላል!


ሳድግ ፣ ትንሽ ሳዉቅ የገባኝ አንድ እዉነት ሁሉም ሰዉ ልቡ መሃል ባዶነት ይዞ መዞሩን ነዉ። ያን ባዶነት አንዳንዱ በትዳር ፣ አንዳንዱ በስራ ፣ አንዱ በሃብት ፣ አንዱ በጥበብ ፣ አንዱ በልጅ . . . ሊሞላዉ ያሳዳል።

 ያን ባዶነት ከቀልቡ ሆኖ ላዳመጠዉ እልፍ ጥያቄዎች ይወልዳል። ሰዎች ጥያቄ የሞላን ፍጥረቶች ነን። ብዙ ያልጠየቅናቸዉ ፣ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉን።

እኛ ማን ነን? ስንት አይነት ማንነት አለን? ለምን ያጣነዉ እንሻለን? ለምንስ እንጓጓለን? ለምንስ ምኞታችን አይሞላም? እንዴት ብዙዎቻችን ባዶነት ልባችን መሃል ተሸክመን? ለምን ፍቅር እንሻለን? ምን ይሆን እንዲ መወደድ መድነቅ የሚያስርበን?. . እልፍ ቀላል መሳይ ዉስብስብ ጥያቄዎች።

ትልቁ ጸጋዉ ሰዉ ያወቀዉን ማቆየቱ ነዉ። መጻፍ መቻሉ። ጽፎ ለልጁ ያቆያል። ልጁ ከአዲስ አይጀምርም አባቱ ካቆመበት እንጂ — ሃሳብ ቅብብሎሽ ነዉ። እኔም እነዚህ ጥያቄዎች መልስ አገኝ ዘንድ ፍልስፍናን ፣ ስነልቦናን ፣ ስነ-ጽሁፍን ማገር አድርጌ ለመቃኘት እሞክራለሁ።

በዚህም ቅኝት ኢማኑኤል ካንት ፥ ኒቼ ፥ ካርል ዮንግ ፥ ዥክ ላኮን ፥ ሬኒ ዤራርድን ብሎም ከተለያዩ ልቦለዶች ገጸባህሪያትና ሃሳቦች እየተዋስን መልስ እናስሳለን።

የካንት ተሻጋሪ ማንነት ( Transcendental Self ) ሃሳብና የሞራል ፍልስፍናዉን ተጠቅመን። ስለ ሰዉነት ፥ ስለነጻነት ፥ ራስን ስለመግዛትና ስለ ህሊና ህግ እንቃኛለን። በሌላ ጽንፍ ደግሞ በኔቼን Übermensch ወይም ልዕለሰብ ሃሳብ ታግዘን  ስለፈጠራ (creativity) ፣ ስለሃያልነት ፣ ስለፈጣሪና ምግባር ብሎም ጀርመናዊዉ ፈልስፋ ለማህበርሰብ ህግ መገዛት ራስን በፍቃድ ማሰር ነዉ ሲለን ምን ሊነገርን ነዉ የሚለዉን እናያለን።

ስንት አይነት ማንነት አለን? ራስን መሆን ምን ማለት ነዉ? እንዴትስ መሆን እንችላለን? የሚሉትን ጥይቄዎች በካርል ዮንግና ሌሎች ሳይኮአናሊስቶች ታግዘን ለመመልስ እንሞክራለን።

ለምን እንጓጓለን? ለምን ያጣነዉን እንሻለን? ከእኩዮቻችን ምን ያፎካክረናል? ሰዉ ያገኘዉን ለምን ይንቃል? ያጣዉንስ በምን ምክንያት ነዉ የሚያከብረዉ? ወዘተ የሚሉትን ደግሞ በሬኒ ዤራርድና ላኮን ሃሳቦች እንፈትሻለን።

ነገር ግን ህይወት ፍልስፍናዊ ብቻ አይደለም። ስሜትም የሚመራን ነን። ሰዉ አይደለን። ለዛ ይመስለኛል በእዉቀቱ “በሞቷ ፊትለፊት" የሚለዉ ግጥሙ ላይ . . .

በሞቷ ፊትለፊት፥ ሀሳብ ሁሉ መና
ምከር ሁሉ ኦና
አንባን አይገድብም፥ የስው ፍልስፍና
” ያለዉ።

እዉነት አለዉ። ለዚህም ረዘም ያሉ ተረኮችን እንጽፋለን። ስሜቶችን እንካፈላለን። ከዛም አልፎ በዉብ ቃላትና ጥልቅ ገጸባህሪያት የተጻፉ የተላያዩ ደራሲያን መጽሃፍትን እንቃኛለን። በመጽሃፍቱ ታሪክ ፣ በገጸባህሪያቱ ህይወት ሃዘንን ፣ እንባን ፣ ፍቅርን ፣ ማጣትን ፣ ማመንን ሁሉ እንቃኛለን።

ሃሳብ እንባን አያቆምም። ነገር ግን የዛፍ ስር አፈሩን ከጎርፍ እንደሚያስጥል በሃዘን ፥ በመከዳት በብቸኝነት የሚመጣ ትርጉም ማጣት ይዞን እንዳይጠፋ አጥብቆ ይይዘናል። ምክንያቱም ጽንሰ-ሃሳባዊ መሰረት ፥ የራሳችን እሴትና የህሊና ህግ እንዲኖረን ይረዳናል። ግለሰባዊ ሰላም ራስን ከማወቅ የሚገኝ ነዉና።

ኒቼ ራስን አለመሆን, “የመንጋ አሳቢ” መሆን ነዉ ይላል። Herd mentality የሚለዉ።  ማወቅ ሂደት ነዉ። ብዙ ስራና ብዙ ጉዞ የሚጠይቅ ነዉ። የማንኛዉም ጉዞ መጀመሪያ የሚሄዱበትን ማወቅ ነዉ። ያን ነዉ በዚህ ቻናል የምንቃኘዉ። ሃሳብ ፣ ስነጽሁፍን እንደሰረገላ ተጠቅመን ራስን መሆን ላይ ለመድረስ።


አብራቹኝ ለመጓዝ ፍላጎታችሁ ከሆነ ወራዊ Subscription ያለዉ የቴሌግራም ቻናል ጀምሪያለሁ። ያዉ በእኛ ሃገር Substack , Patreon የመሳሰሉ Creativity monetization መንገዶች ስለሌሉ Improvised Substack በሉት። ቻናሉን ለመቀላልቀል Subscription'ኑ በወር 100 ብር ነዉ። ቻናሉና ፍላጎቴ እኔ ከማጋራቸዉ ጹፍና ሃስቦች ዉጪ Live audio ዉይይቶች ፥ ክርክሮች የምናደርግበት ጥሩ ተዋስዖ ያለዉ one vibrant community መገንባት ነዉ። እንደምትቀላቀሉ ተስፋ አለኝ።

እንዴት የሚለዉን ለማወቅ ከታች ያለዉን መንገድ ተከተሉ!

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

11 Aug, 11:07


 "The True Paradise is the Paradise We Lost" ይላል ፕሩስት። ዉብ አለም ያጣነዉ ብቻ ነዉ እንደማለት። 

ሁሌም ሰዎች ይሸጡልን የሚፈልጉት የምኞት አለም አለ። ድሮ ድሮ "የላብ አደሩ አብዮት የሚወልደዉ እኩልነት" ነበር። " ከበርቴዉ ፣ ፊዉዳሉ" ጠላት ሆኖ መንገድ የዘጋበት። ታገሉ ፣ ገደሉ —  አላዋጣም። ባህል ፣ ሃገር ፣ ዘር ፣ ሰፈር ቀያይረዉ በአለም ባለ እልፍ ቦታ ሞከሩት። ሞት እንጂ የመጣ ዉብ አለም አጡ። 

ዛሬም ሌላ ዉብ አለም ይሸጣሉ። በምኞት ብቻ ያለ። የትናንት አለማቸዉ ልጅ። የዛሬዉ ጠላት በትናንቱ ጠላት እንድንረታ  መሰረት ነበር አሉ።  ሃይማኖት  ፣ ወግ ማጥበቅ ፣ ግብታዊ ለዉጥ እምቢተኝነት ፣ አባታዊ ስርአት ፥ ትዳር ፣ እናትነት ወዘተ። 

ሁሉም ነገር የማህበራሰብ ሽመና ዉጤት ( social constract ) ነዉ። አስተዳደግ እንጂ ተፈጥሮ ምን ይረባን"ን ሰበኩ።

ያ እንዲሆን " ያደግንበት መናድ አለበት። እዉነት ይትብሃል የለም።  እዉነትም ፣ እዉቀትም ፣ ማንነትም አንጻራዊ ነዉ። ባሻቹ ናኙ ። ባፈረስነዉ ላይ ሁሉ እኩል የሚከበርበት ፣ እኩል ሃብት ያለበት ፣ ባሪያ መሳ የሚቀመጥበት የምናብ ሃገር እንገነባለን። " ብለዉ ተመኙ።

አይሆንም! 

"The object of desire is not something that is there; it is something that is missing" ይላል Jacques Lacan. 
ምኞት የማይሞላ መሻት ነዉ ሊለን።  

ለግል የምናልመዉ ይሁን ፥ ማህበረስብ እንዲሆን የምንሻዉ ፤  ሁላችንም በልባችን ገነት አለን — ቢሆንልን የምንለዉ።እንዳለመታደል ጊዜ ፣ ታሪክም እንዳሳየን ብቸኛዉ ደስታ ጉጉት ብቻ ነዉ። ስናገኘዉ ፣ ስንጨብጠዉ ሁሉ ቀሊል ይሆናል።  ደስታዉን ፥ ክብሩን ያጣል። 
 Object cause desire የሚለው ላኮን። 

ሰዉ መሻቱን የሚሻ ፍጥረት ነዉ። ማግኘትን አይደለም።

ምን ወጣትነት ለተበዳይ መራራት ፥ ለአመጽ ቋፍ ላይ መሆን ቢሆን ከታሪክ ግን እናያለን። ግልብ ለዉጥ ያለንንም ያሳጣናል። ዉብ የምናብ አለም በእጃችን ላይ ያለችዉን ለዘመናት የገራናትን የረጋች አለምን ይነጥቀናል። 

" Evil is precisely when you think you are fighting for the absolute good."  - Hagel



@samuel_dereje