Mohammed Ahmed Official @abuafnanmoh Channel on Telegram

Mohammed Ahmed Official

@abuafnanmoh


ለጥያቄ እና አስተያየት 👉 @afhasmen

youtube.com/@gharuhira

Mohammed Ahmed Official (Amharic)

ሁሉም ሕጋችሁን ስትናገሩ እናመሰከር! ሰላምም! ወደ Mohammed Ahmed Official ቴሌግራም እንኳንሰሂ! ትእዛዙን በጠቅላላ በሰአት እንስፃለን! ከሰላም ጋር እንቅስቃሽን ፈጥነው የቴሌግራም ቦታዎችን በፕሮፌሰንን ይጋልባል! ሞሃመድ አህመድ የሚያስብ ከወይም በአማርኛ መዝገበህልዎች ተጠቃሚው አንደኛ ህገመንግስት ነው የቴሌግራም እና ሁኔታ ነካሽም! ለሞሃመድ አህመድ የምመስለኝ እና ለቴሌግራም አስተዳደሩ! ከሚካኤል ደስታ ናለው የቴሌግራም ጥያቄ እና አስተያየት @afhasmen ተናጋሪ ነው በግራፌ ሃኪሞሁል! በጠቅላላው ከሚኖረው አስተዳዱ ስለ ቴሌግራም እንቅስፍ አልተቻለም ። መልኩ ሲሞታትትና በቀጥታ ሲበላኝም እንላላለን! ስለውበትም ጠቅላላ አጫጭር በማከማዝ አንደኛው ህዝብ ነው ተመካከረ ።

Mohammed Ahmed Official

09 Feb, 13:17


የናንተ ውጤት - 2

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02JjB8vh5t74ivdxB4KrTHdLwRtdcZo2UcvBRZru7JYcjv94DU48UW2ZZV7ysMCmSal&id=100000439887599&mibextid=Nif5oz

Mohammed Ahmed Official

07 Feb, 16:11


የናንተ ውጤት - 1

https://vm.tiktok.com/ZMkpYkGge/

Mohammed Ahmed Official

24 Jan, 06:24


ባለፈው እንደነገርኳችሁ ጓድ ዓሊ አሚን የቀረበለትን የዳኒያ ሐላዋ እንደ ባቲ የሰደቃ ፍትፍት ወዲያው ካሷረፈው በኋላ ሆዱን በመዳፉ አሸት አሸት እያደረገ «ማሜ ልሄድ ነው» አለኝ። «ወዴት ነው የምትሄደው ዓሊዋ ?» ስለው «ሙኣዚን መሆኔን አታውቅም እንዴ ?» አለኝ። «አረ እኔ ቁባም የለኝ !» አልኩት - በወሎ የአነጋገር ዘዬ።

በአቅራቢያችን ካለ መስጂድ አቅንቶ አዛኑን ሲለቀው በመስጂደል ሓራም ቅጽር ውስጥ ያለሁ መሰለኝ። ዕድሜ ለጣፋጩ የዳኒያ ሐላዋ ይግባና የዓሊ አሚንን ድምጽ ስቱዲዮ ውስጥ የተቀረጸው ነሺዳ ይመስል ይበልጥ አስረቀረቀው።

አሁን ደግሞ በወንድ ልጅ መባረኩን የፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንደለጠፈ ያላሉኝን መርቅኜ በአስተያዬት መስጫ ሳጥኑ ላይ ለልጁ የዐቂቃ ማውጫ 1 ኪ.ግ የዳኒያ ሐላዋ በጀባታ መልክ እንዲወስድ ቃል ገብቼለት ነበር።

እንግዲህ ዓሊ አሚን ቤቱም ቤቴል አካባቢ ሥለሆነ "በቡራቅ" ፍጥነት አፕል ፕላዛ ጋር ደርሶ ሐላዋውን አፈፍ አድርጎ መወሰዱ አይቀርም። ቡራቅ ስል የራሱ የዓሊ አሚን «ቡራቅ ትራቭል» ትዝ አለኝ። የዳኒያን ሐላዋ ሸክፋችሁ በቡራቅ ትራቭል 7 ቀን መካ 3 ቀን መዲና ደርሳችሁ መመለስ ትችላላችሁ።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

24 Jan, 05:36


የክፍለ አገር ነዋሪዎች የዳኒያን ሐላዋ እየቀመሱ «አቤት ሲጥም !» ከሚል ካፕሺን ጋር በፌስቡክ ግድግዳዎቻቸው ላይ የሚያጋሯቸውን ልጥፎች በትዕግስት እና በቁጭት ከመመልከት ውጭ አማራጭ ላልነበራቸው "አንዳንድ" የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይኸው ዛሬ ከተማቸውን በሁለት እግራችን ረግጠን ከጣፋጩ የዳኒያ ሐላዋ ጋር ቤቴል ላይ ተከስተናል።

በቪዲዬው ላይ እንደሚታየው ከተቅዋ መሰጂድ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የቤቴል አደባባይ አለፍ እንዳሉ በቀኝ በኩል ከሚገኘው ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት ካለው የአፕል ፕላዛ ህንጻ ግራወንድ ላይ NK Burger ጎን Sweet Chocolate ውሰጥ እንዲህ ተደርድረን ቁጭ ብለናል። መደርደሪያው ላይ የተቀመጡትን የዳኒያ ሐላዋ ከቋጥኝ ድንጋይ ላይ በንፋሰ እንደተነሳ አቧራ በመጥረግ አዲሰ ሪከርድ እንደምትሰብሩ ተስፋ አድርገን በሩ ላይ በጉጉት እንጠብቃችኋለን 😋😋

የዳኒያን ሐላዋ ሌሎች ቀምሰው የሚያጣጥሙበት መንገድ አስጎምዥቷችሁ እንደ VAR መላልሳችሁ ስትመለከቱ የነበራችሁ እና «ኧረ እባክህ አዲስ አበባ መቼ ነው የምትመጣው ?» በሚል ጥያቄ ፋታ ያሳጣችሁኝ :- ይኸው መጣሁኝ !!

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

19 Jan, 08:32


https://t.me/goldenstar_communications

Mohammed Ahmed Official

18 Jan, 16:46


ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ፋጢማ ኢድሪስ ዓሊ ትባላለች። ትውልድ እና እድገቷ ቃሉ ወረዳ ቀበሌ 18 ልዩ ሥሙ ወረበቾ የሚባል አካባቢ ነው። እንደ ኢትዮጵያ የዘመን ቀመር በ 1991 ዓ.ል ኑሮን ለማሸነፍ የአንድ ዓመት ህጻን ልጇን ለወላጆቿ አስረክባ ከእህቷ ሐዋ ኢድሪስ ዓሊ ጋር ለሥራ ወደ አፋር ክልል ሎጊያ ከተማ አቀናች። ሁለቱም እህትማማቾች በሎጊያ ከተማ የተለያየ ሰፈር ቢኖሩም እስከ 1993 ዓ.ል አጋማሽ ድረስ በተደጋጋሚ የመገናኘት ዕድል ነበራቸው። ከዚያ በኋላ ፋጢማ ኢድሪስ ዓሊ የውኃ ሽታ ሆነች። «እዚህ ቦታ አይተናታል» የሚል አንድም ሰው ጠፋ።

ወላጅ እናቷ አሚናት አሕመድ ሰዒድ ፣ አባቷ ደግሞ ኢድሪስ ዓሊ ቡሽራ ይባላሉ። አባቷ የመጥፋቷን ወሬ ከሰሙ በኋላ ከአሁን አሁን ትመጣለች በሚል ደጅ ላይ ለሁለት ዓመታት «የኔ ፋጦ ፣ ፋጦዬ» እያሉ ሲብከነከኑ ቆይተው ጠረኗን እየናፈቁ ዱንያን ተሰናበቱ።

አሁን ደግሞ በህይወት ያሉት እናቷ «ፋጦዋ የበኩር ልጄ ፣ እግሬን እሾህ ሲወጋኝ የሚነቅልልኝ አጥቼ የወላድ መሃን ሆኛለሁና እባክሽ ካለሽበት ቦታ ብቅ በይ» እያሉ ፊታቸው በየቀኑ በለቅሶ ይወረዛል። ለአንድ ዓመት ብቻ ከእናቷ እቅፍ ውሰጥ የመቆየት ዕድል ያገኘችው የዛሬዋ የ26 ዓመት ወጣት ልጇ ጀማነሽ ዓሊ ሙሐመድም የማታውቃት እናቷን በጉጉት ለማዬት ትናፍቃለች።

ፋጢማ ኢድሪስ ዓሊ ያለችበትን የምታውቁ ሁሉ በሚከተሉት ሥልክ ቁጥሮች ደውላችሁ ልታሳውቁን ትችላላችሁ

ሙሐመድ ኢድሪሰ ዓሊ (ኢትዮጵያ)
+251910083340

ሐዋ ኢድሪስ ዓሊ (ሳዑዲ)
+966578522456

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

05 Jan, 15:43


አንዳንድ ሰዎች ያለፉባቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች ከልብ አዳምጦ የሚፈጥረውን ስሜት ለሌሎች በጽሁፍ ወይም በድምጽ ማስተላለፍና ማጋባት የማይቻልበት ሁኔታ ያጋጥማል። በዚህ የሥሜት እርከን ላይ ሲሆኑ ብዕርም ያዘለውን ቀለም ከመትፋት ይለግማል። ጫፉን ይዘው ቢስቡት መቋጫ የሌለውና በፈተናዎች የተሞላ አድካሚ ረጅም የህይወት ገመድ በርቀት ተዘርግቶ ይታያል። ለመሰል ሙከራዎች የታጩ ሰዎች ትከሻዎቻቸው ሸክሞቹን እንዴት ችለው እንዳለፉት ትንግርት በሆኑ የታሪክ እጥፋቶች የተሞላ መሆኑን የህይወት ምዕራፎቻቸው ይነግሩናል።

ለመስማት የከበደኝን ሁሉ ለናንተ መናገር የማልችልበት ሥሜት ውስጥ የገባሁ በመሆኔ ጆሮዬ የሰማውን እና አይኔ የተመለከተውን በውስጤ ቋጥሬ ወደ ጉዳዩ በቀጥታ መግባትን መርጫለሁ። እናንተም ዝርዝሩን በመተው የተለመደ የድጋፍ እጆቻችሁን ለመዘርጋት እንደምትተባበሩኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

በሥራው የማይታማ ትጉህ ወጣት ሲሆን የሦስት ልጆች አባት ነው። የትኛውን ሥራ ሰርቷል ከማለት ያልሞከረው ሥራ የለም ማለት ይቀላል። ያልወጣውና ያልወረደው ፈተና የለም። ትላንት ቤተሰቡን ቀጥ አድርጎ ሲያስተዳድር የነበረው ብርቱ ወጣት ዛሬ ላይ ከአቅሙ በላይ በሆነ የፈተና ቀለበት ውስጥ ወድቋል። ሰርቶ የሚያበላ ሙያ እያለው በእጆቹ የነበሩትን ንብረቶች በሙሉ አጥቷል። የወጣቱ ረጂም የህይወት ምዕራፉ ሲቀነበብ እንዲህ ነው።

ወጣቱን ወደተካነበት ሙያ በአጭር ጊዜያት የመመለስ ህልም ስላለኝ ለፊኒሺንግ ሥራዎች እና ለቤት ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ወደ 83,000 ብር አካባቢ ዋጋ የሚያወጡ የሚከተሉትን መሳሪያዎች በመግዛት እየተንቀጠቀጠ ቋፍ ላይ ያለውን የአንድ ትልቅ ቤተሰብ ህይወት በማረጋጋት አላህ ከመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ እንዲታደገን ጥቂት የድጋፍ ጠጠሮችን በጋራ እንወርውር የሚል ግብዣዬን አቀርባለሁ። ይህን ወጣት በመደገፍ ለመበታተን ጫፍ ላይ የደረሰውን ቤተሰብ ጎጆውን የማቃናት ፍላጎት ያላችሁ ደጋግ እህት ወንድሞች ሁሉ ፣ በውስጥ መስመር ብታናግሩኝ ሙሉ አድራሻውን ላቀብላችሁ እችላለሁ።

👉 የቦርድና የፍሬም ማምረቻዎች
👉 የቀለም መቀቢያ ማሽኖች
👉 መሰላል
👉 ሳይለንት ኤር ኮምፕረሰር
👉 የግድግዳ እና የወለል ማለስለሻዎች



http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

05 Jan, 13:40


Channel photo updated

Mohammed Ahmed Official

31 Dec, 13:17


ከጠበቅነው ድጋፍ እጥፍ (138,000 ብር) በማግኘታችን የድጋፍ እንቅስቃሴውን በዚሁ ቋጭተናል።

በውስጥ መስመር መጥታችሁ የልጅቱን ሙሉ አድራሻ ያቀበልኳችሁ እና ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባችሁ ቀሪ ወንድም እህቶች ፣ በላኩላችሁ አድራሻ መሰረት ቃላችሁን እንድትሞሉ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

Mohammed Ahmed Official

31 Dec, 13:17


የተዘበራረቁ ጉዳዮቻችሁን ሳይዛነፉ በክር ውስጥ እንደተደረደሩ ስንድዶች አስተካክሎ ህልማችሁን እውን ያድርገው። ድካምን በቃ ብሏችሁ በመዲና እና በመካ መንደሮች ከወዳጆቻችህ ጋር ዘወትር የምትመላለሱበትን ተምኪን ይወፍቃችሁ። ደጆቻችሁ በሲሳይ ተትረፍርፈው የድሆች ዓይን ማረፊያ ያድርጋችሁ። ለችግረኞች ከለላ ፣ ለሚስኪኖች ጥላ ፣ ለተገፉ ሰዎች ደራሽ ፣ ለድሆች እንባ አባሽ ያድርጋችሁ። በልቦቻችሁ ጓዳ ስክነት እና መረጋጋትን አስፍኖ በደስታ የታጀበ ሕይወት ይወፍቃችሁ። ቤቶቻችሁ በፍቅር እና በልጆች ሳቅ ይድመቁ። በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ከሰመረላቸው ደጋግ ባሮቹ ተርታ ያሰልፋችሁ። በረካ ከደጃችሁ አይጥፋ። የሐላል ማዕድ በዙሪያችሁ ይንሰራፋ። የሲሳዩ ካዝና ከነ ቁልፉ በእጃችሁ ይግባ። ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ፣ ለተራቡ አጉራሽ፣ ለታረዙ አልባሽ ፣ ለተበዳዮች እንባ አባሽ ያድርጋችሁ። ከህመም ስሜት ይራቅችሁ። የፈተናን ሸክም መቋቋም የምትችሉበትን ትከሻ ይስጣችሁ። ዘለግ ያለ ዕድሜ ያጎናፅፋችሁ። ወደ አላህ መቃረቢያ በሮችን በሰፊው ይክፈትላችሁ። በማይቀረው ዕለተ ትንሳኤ ከነብዩ ሙሐመድ ﷺ ፣ ከባልደረቦቻቸውና ፈለጋቸውን ከተከተሉ የአላህ ባለሟሎች ጋር በጀነተል ፊርደውስ ጉርብትናውን ይወፍቃችሁ።

አሚን

Mohammed Ahmed Official

30 Dec, 16:26


የዙህር አዛን ከመሰማቱ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በማላውቀው ቁጥር አንዲት እህት ስልክ ደወለችልኝ። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ልትነግረኝ ያሰበችውን ጉዳይ መግለጽ አቀበት የመውጣት ያህል ከበዳት። ቃላት አዋቅራ ለመናገር ብትሞክርም አንደበቷ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ስንዝር መራመድ አልቻለችም። «በቃ፣ ሃሳቤን በጽሁፍ መላክ ይቀለኛል» ብላ ስልኩን ዘጋችው። የላከችውን አጭር የጽሁፍ መልዕክት ካነበብኩ በኋላ ወዲያው ደውዬ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ከኔ ሱቅ እንድትመጣ ነገርኳት። በቀጠሯችን መሰረት ተገናኘን።

ልጅቷ አባቷን የአራት ዓመት ህጻን እያለች በህይወት ያጣች የቲም ናት። አሁን ላይ የ11ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ስትሆን በትምህርት ቤቱ አመርቂ ውጤት አስመዝገበው የተለየ ክፍል እንዲማሩ ከተመረጡት ልዩ ተማሪዎች ምድብ ውስጥ የተካተተች ናት። ከጎኗ የሚቆም አንድም ሰው ባለመኖሩ የህይወትን ፈተና መቋቋም አቅቷት ያለላትን ሲሳይ ለመፈለግ ትምህርቷን ማቋረጥ እንዳለባት የውሳኔ ጫፍ ላይ መድረሷን ተረዳሁ። እኔም እናንተን በመተማመን «ወዳጆቼ እያሉ ይህ በፍጹም ሊሆን አይችልም» በማለት ፎቶ እንድትነሳ እና አዲስ የባንክ ሒሳብ ቁጥር እንዲከፈትላት አመቻቸሁ።

ለቀጣይ አንድ አመት ከግማሽ መንፈቅ የሚያስፈልጋት

👉 የቀለብ ወጪ = 18 X 3,500 = 63,000 ብር
👉 የንህፅና መጠበቅያ = 6,000 ብር

አጠቃላይ = 69,000 ብር ነው

ይህች ጎበዝ ተማሪ ከኑሮ ጣጣ አረፍ ብላ ትምህርቷ ላይ ትኩረት በማድረግ የነገ ህልሟ እንዳይጨናገፍ ከጎኗ በመቆም መሰረታዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ እህት ወንድሞች ሁሉ፣ በውስጥ መስመር ብታናግሩኝ ሙሉ አድራሻዋን ላቀብላችሁ እችላለሁ።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

21 Dec, 07:06


ለክፉ ተልዕኮ ታጭቶ በፍቅር ፍላጻ የተወጋው ሐሳን ኢብኑ ሳቢት !

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

04 Dec, 18:18


ዛሬ ጠዋት ስልኬ ጠራ። ወዲያው አነሳሁት።

እነሱ :- «አሰላሙዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ ፣ ወንድም ሙሐመድ አሕመድ ነህ ?»

እኔ :- «ወዐለይኩሙሰላም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ ፣ አዎ ነኝ»

እነሱ - «ዳኒያ ሐላዋንም አንተንም ፈልገን መጥተን ነበር»

እኔ :- « እሺ መርሐባ ፣ ከየት ነው ?»

እነሱ :- « የመጣነው ከሰንበቴ ጂሌ ጡሙጋ ወረዳ ነው። አሁን ለመመለስ አስበን ነበር። ነገር ግን የዳኒያ ሐላዋ በር ላይ አንተን እየጠበቅን ቆመናል»

እኔ :- «እሺ እመጣለሁ። ትንሽ ደቂቃ ትጠብቁኛላችሁ ?»

እነሱ :- «እሺ እንጠብቅሃለን»

ወደ ሥራ ቦታ ስሄድ ወጣቶቹ የዳኒያ ሐላዋ መሸጫ በር አጠገብ ቆመው ከቅርብ ርቀት ላይ ታዩኝ። አንዳቸውንም አላውቃቸውም። አስፓልቱን ተሻግሬ እየቀረብኩ ስመጣ «አናስገባም ሰርገኛ እደጅ ይተኛ» በሚመስል ሁኔታ በህብረት እንዲህ እያቀነቀኑ ጠበቁኝ። የተወሰነው ቢያመልጠኝም የቀረውን በካሜራዬ አስቀርቼዋለሁ። የዳኒያ ሓላዋንም ቀምሰው ተሰነባብተናል።

Mohammed Ahmed Official

04 Dec, 03:39


በምድር ላይ የሰው ልጅ ቢያጣም እንዲያገኝ የሚመኙና የሚደግፉ ደጋጎች እስካሉ ድረስ ህይወት በጣም ደስ ትላለች። 11,800 ብር የሚያስፈልገው እና ወደ ሥራ ለመግባት የሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣ አንድ ወጣት እንዳለ በጠቆምኳችሁ መሰረት ደጋጎች ባደረጉት ርብርብ በድምሩ 45,000 ብር ወደ አካውንቱ ገቢ አድርገውለታል።

ጃዛኩሙላሁ ኸይራ


ቃል የገባችሁ ወዳጆቼ ቃላችሁን ፈጽሙ
!!!

Mohammed Ahmed Official

03 Dec, 17:45


የሰው ልጅ አይጣ
🍀🍀🍁🍁🍀🍀
ሀተታ አላበዛባችሁም። እንባዬን መቆጣጠር ተስኖኝ ነው ቀጥታ ወደናንተ የመጣሁት። ያየሁትን ማዬት ብትችሉ ኖሮ አብራችሁ ታላቁሱኝ ነበር። የዛሬው ባለ ጉዳዬ ከወደ አዳማ ነው። ወደኔ መልዕክት መላክ የጀመረው ከ3 ወር በፊት ሲሆን ቢያንስ በየሳምንቱ ይደውላል አሊያም አጭር የጽሁፍ መልዕክት ይልክልኛል። በውስጡ ያመቀውን የሃሳብ ጓዝ የተሸከመበት ትዕግስት ይገርመኛል። ዛሬ ግን የቆመበት መሬት የከዳው ያህል ስሜቱ ተሰብሯል። አዳማ የሚኖር ጓደኛዬን እንዲያገኘው ካደረኩ በኋላ ፊቱን በቪዲዮ ስመለከት ቪዲዮውን ዘግቼ ቀጥታ ወደናንተ መጣሁ። አሁን ላይ ወንድማችን ሥራ ለመጀመር እጁ ላይ ከታች የምትመለከቱት የሳንቡሳ እና የቆቀር መስሪያ ማሽን አለው። ከናንተ የምፈልገው ጥቂት ገንዘብ ብቻ ነው። ተከተሉኝ :-

50 ኪ.ግ ዱቄት = 4,100 ብር
20 ሊትር ዘይት = 4,200 ብር እና
የቤት ኪራይ = 3,500 ብር

አጠቃላይ 11,800 ብር ብቻ

እኔ እሸፍነዋለሁ የሚል ደግ ሰው በውስጥ መስመር ያናግረኝና ከህሊና ክስ ያሳርፈኝ።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

03 Dec, 14:23


ለነፍሰጡሮች ልዩ ትኩረት መስጠታችንን የታዘቡ አራሶች «እኛን ማን ያስታውሰን !» የሚል ቅሬታ በማቅረባቸው እስከዛሬ ያላመረትነውንና በአይነቱ አዲስ የሆነ የሐላዋ ዘር ይዘን ብቅ ብለናል። አሁን እያሳሰበን ያለው ትልቁ ጉዳይ ጥያቄው በቡድን ደረጃ መነሳቱ ሲሆን በቀጣይ ለላጤዎች (Abas) ፣ ለሙሽሮች (አብዱራህማን የሰልዋ ወንድም ሀራ) ወዘተ በሚል እየሰፋ በፓርቲ ደረጃ ወደማከፋፈል እንዳንደርስ ነው። በነገራችን ላይ ለዑምራ ተጓዦችም የሚሆን የሐላዋ ፓኬጅ እንደምናቀርብ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን 🤣 ይደውሉ ፣ ይዘዙ 👉 0921555158

Aya Travel Agency አያ የጉዞ ወኪል وكالة سفريات آية
Link Travel Agent
Ustaz Nuru Turki/ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ
Asmamaw Ahmed
Adugnaw Muche
Sofia Juhar
Mubarek Adem
አቡሐኒፋ - ሙሀመድ ሰዒድ
Istanbuladdis Tour and Travel PLC


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

03 Dec, 07:58


በጠዋቱ ቁርሴን ተመግቤ ገና እንደጨረስኩ አንዷ እህት ከአዲስ አበባ ደወለችልኝ።

እሷ 👉 « ወንድሜ፣ የዳኒያን ሐላዋ አዲስ አበባ የት ነው ማግኘት የምችለው ?»
እኔ 👉 « እህቴ ፣ በጣም ይቅርታ ለጊዜው አዲስ አበባ አልጀመርንም። በቅርቡ ኢንሻላህ ብቅ ማለታችን አይቀርም»
እሷ 👉 « እሺ ፣ ከኮምቦልቻ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ ሰው ስላለኝ እባክህ አሁን መላክ ትችላለህ ?
እኔ 👉 «እንዴታ!»
እሷ 👉 «ቀላቅለህ ደህና አድርገህ ላክልኝ»
እኔ 👉 « አብሽሪ ፣ ምንም አያሳስብሽ»
እሷ 👉 «ነፍሰጡር ነኝ አፍጥነው» 🤣

«ለነፍሰጡሮች ስንል የማንወጣው ዳገት ፣ የማንወርደው ቁልቁለት ፣ የማንራመደው ቆንጥር እሾህ የለም» በሚለው አቋማችን ይኸው አሁን የነፍሰ ጡሮችን ፍላጎት በልዩ ሁኔታ የሚያረካውን 2 ኪ.ግ የዳኒያ ሐላዋ ሸክፌ ወደ ባቲ መናኸሪያ በማቅናት ሐላዋውን ወደ ኮምቦልቻ ለሚሄድ ሾፌር ለማስረከብ አይኔ እየተቅበዘበዘ ነው።

ገንዘብ የምንቀበለው ሐላዋው በደንበኞቻችን እጅ ሲገባ ብቻ ነው። ይህን ደግሞ ሐላዋውን የተረከቡ ሁሉ ምስክርነት መስጠት ይችላሉ።

የዳኒያን ሐላዋ ለማዘዝ 👉
+251921555158

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

02 Dec, 03:14


የትኛውን ዘመን እንደተሻገረ ባለውቅም ሥሙን ዘመን ተሻጋሪው ብሎ የሰየመው ሰውዬ ዛሬም ባቲን ከመሻገሩ በፊት ከዳኒያ ሐላዋ መሸጫ ሱቅ ድንገት ተከስቶ አስር ወጠምሻዎች የሚሰፍሩበትን የሐላዋ ማህበራዊ ድቅቅ አድርጎ ከፈጨ በኋላ አፉን በሰፊ መዳፉ እየጠራረገ «በቃ ማሜዋ ሥመለስ ለቤተሰብ የምወስደው 1 ኪ.ግ ከሽነህ ከሁሉም አይነት አስቀምጥልኝ» ብሎኝ ቁልቁል ወደ አፋር ክልል ወርዷል። ደግነቱ የዳኒያ ሐላዋ በቅርቡ ወደ አፋር ክልል መግባቱ አይቀርም እንጂ የሰውዬውን አያያዝ ስመለከተው «ሸሃዳ ኻቲማው» የዳኒያ ሐላዋ እያሉ መሰንበት ይመስላል 🤣🤣

ለማዘዝ 👉 +251921555158

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

02 Dec, 03:12


ለምሳሌ ይህ ዘመን ተሻጋሪው የተባለ ሰውዬ ከበረሃ ወደ ባቲ ገና ከመግባቱ የታክሲ ወረፋ ሆቢ እንደሆነበት የአዲስ አበባ ነዋሪ የዳኒያ ሐላዋ መሸጫ በር ላይ እንደ አክሱም ሐውልት ተገትሮ ሲጠብቀኝ ነበር። በሩ ላይ ቆሞ ሲያቁነጠንጠው ለተመለከተ ሰው "ነጋዴ እንኳ ሱቁን ለመክፈት በዚያ ልክ አይንሰፈሰፍም" የሚል ትዝብት ይወስድ ነበር። ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ ወደ ሥራ ስገባ ስኳር እንዳየ ጉንዳን የስራ ባልደረቦቹን ከኋላው አስከትሎ የሥራ ቦታዬን ወሮታል። አንድ በአንድ ወደ ውስጥ ገቡ። እንደ ልኳንዳ ቤት ሰራተኛ የሐላዋውን ሻኛ በሰንጢ እየቆረጥኩ በየአይነቱ አቀረብኩላቸው። እሱ ግን ዩዜን ቦልትን በሚያስንቅ ፍጥነት ፎቶው ላይ በምትመለከቱት ሁኔታ ሐላዋውን በተመስጦ ይወቃው ገባ። እንኳን የሸመተ ያረሰም በማይችለው አመጋገብ ሐላዋውን ጠራርጎ ባዶውን ሳህን አስረከበኝ። «በልጅ አማሃኝቶ ይበላል አንጉቶ» እንዲል ብሂሉ «እስኪ ለዐይኔ ማሪፊያ ለልጄም ቋጥርልኝ» ብሎ በቴክአወይ ስም ሸክፎ ከአይኔ ተሰውሯል።

ፎቶውን ያነሳሁት የዳኒያን ሐላዋ እየቀመሰ በደስታ መንኮራኩር ኮንታ በደረሰበት ቅጽበት ነው 🤣

ለማዘዝ 👉 +251921555158


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

30 Nov, 17:06


ከናንተ የመጣ ስጦታ
🍁🍁 🍀🍀 🍁🍁

በኑሮ ሸክም አከርካሪው የተሰበረን ህዝብ በበርካታ ጉዳዮች ማሰልቸት ምን ያህል አስጨናቂ እንደሆነ ለሁላችንም የማይደበቅ ሃቅ ነው። ህዝቡ የራሱን የውስጥ ጩኸት በተመስጦ እያዳመጠ የውጩን ጩኸት ለመስማት የሚችልበት አቅሙ ተሰልቧል።
እንዲህም ሆኖ የናተን ድጋፍ ስንጠይቅ ለበጎ መልዕክታችን ትኩረት ሰጥታችሁ ያለ ስስት ጣታችሁን በማዋስ ፍላጎታችንን እውን በማድረጋችሁ የላቀ ምስጋና ይገባችኋል።

ትላንት በዚህ ሰዓት የለጠፍነውን የCYBERTECH ማስታወቂያ ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆን ባደረጋችሁት ሰፊ ርብርብ በድምሩ 45,000 ብር ለማግኘት ችለናል። በገባነው ቃል መሰረትም ገንዘቡን የCYBERTECH ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀደም ብሎ ይህንን ቪዲዮ ሰርቼለት ለነበረው ወንድማችን ካሚል ሙሐመድ ይማም (https://t.ly/suJ88) በአካውንት ቁጥሩ ገቢ እንዲያደርጉለት በመጠየቄ የተባሉትን ፈጽመዋል።

የወንድማችን ካሚል ሙሐመድን የቤት ግንባታ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው። የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ዋጋ መናርን ተከትሎ መጀመሪያ ከተሰበሰበለት ብር ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ስለጠየቀው በCYBERTECH ማስታወቂያ የሚገኘውን ገቢ ለእሱ እንዲውል አድርጊያለሁ። በቅርቡ የቤቱ ግንባታ ተጠናቆ ልጆቹ በደስታ ሲቦርቁ በጋራ ለማዬት ያብቃን - ኢንሻአላህ።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

30 Nov, 06:17


https://www.facebook.com/share/v/1HChPZHnNx/

Mohammed Ahmed Official

29 Nov, 19:21


👆👆👆

በዚህ ልጥፍ ከሚገኝ ገቢ ወደ ኪሴ የሚገባ ስባሪ ሳንቲም የለም። ነገር ግን እናንተ ከረዳችሁኝ ሙሉ ገቢውን የጋራ ደስታ በሚፈጥርልን የበጎ ተግባር ላይ እንደማውለው ቃል እገባለሁ። ገቢው ምን ላይ እንደሚውልም በማስረጃ ከተደገፈ ደረሰኝ ጋር እዚሁ እለጥፍላችኋለሁ። ሥለዚህ ይህን ፖስት በሼር 20 ብር ፣ በላይክ 15 ብር ፣ በኮሜንት 10 ብር የምናገኝበት ትልቅ ጉርሻ በመሆኑ እየተረባረባችሁ እንደ ሰደድ እሳት እንድታቀጣጥሉልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ።

Mohammed Ahmed Official

29 Nov, 19:20


https://www.facebook.com/share/v/1HChPZHnNx/

Mohammed Ahmed Official

28 Nov, 17:37


አንዳንድ ነገሮች ትኩረት ካልሰጠናቸው ከመለመዳቸው ብዛት ምንም ላይመስሉን ይችላሉ። አሁን በታላቁ የባቲ ጃሚዕ መስጂድ የዒሻን ሶላት በጀመዓ ሰግደን እየወጣን እያለ ወደ ቀኝ ሳማትር ዓይኖቼ ከዚህ ስብስብ ላይ አረፉ። አንድ የሚያስገርማችሁን ጉዳይ ልንገራችሁ። ይህ ጀመዓ ከ1999 ዓ.ል ጀምሮ ለአንድ ቀን እንኳ ከዚህ ተግባር ተነጥሎ አያውቅም። በየዕለቱ ቁርኣን በጋራ ይቀራሉ፤ ኪታብ በተራ እያነበቡ ይደማመጣሉ። ከመሃላቸው በዚህ ተግባር ላይ ለዓመታት ጸንተው ወጣትነታቸው የሸሻቸው ሪጃሎች አሉ። ስብስቡ ሥክነት የሰፈነበት ፣ አላህ በእዝነቱ ያካበበው እና በመላዕክት አጀብ የታጠረ ነው።

የምር እቀናባቸዋለሁ 😭

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

28 Nov, 15:51


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

27 Nov, 07:57


አንድ ግለሰብ በራሱ ተነሳሽነት መዋዕለ ነዋዩን እያፈሰሰ ለበርካቶች ምሳሌ በሚሆን እና ማህበረሰብን ሊጠቅም በሚችል የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ሲሰማራ መመልከት ልብን በደስታ ያሞቃል። ወንድማችን ዑመር ሐሰን ኑር በቅርቡ «ባቡል ጀነህ የአረጋዊያን መረዳጃ ፋውንዴሽን» የተሰኘ ድርጅት በመመስረት በባቲ ከተማ ተንከባካቢ ለሚያስፈልጋቸው 84 አረጋዊያን መጦሪያ የሚሆን ግራውንድ + 2 ፎቅ ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ግንባታው የሚያርፍበትን ቦታ ለመግዛትም ከኪሱ ከፍተኛ ወጪ አድርጓል።

ወንድማችን ዑመር ያሰበው የፋውንዴሽን ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለአረጋዊያኑ በየወሩ የዕለት ምግብ በማቅረብ ላይ ይገኛል። እኔም በቦታው ላይ በመገኘት ለሁለተኛ ዙር የተከናወነውን የድጋፍ እንቅስቃሴ ከመመልከት ባሻገር የሚከተለውን ንግግር የማቅረብ ዕድል አግኝቼ ነበር።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

24 Nov, 07:42


ገና በማለዳ ዓይኔ መልካም ነገር ተመለከተ። ጆሮዬ ለዛ ያለው ነገር ሰማ። ቀልቤም ለቀሪው የቀን ውሎዬ የሚሆን የደስታ ማጣፈጫ ቅመም አገኘ። በአሜሪካን አገር የምትኖር አንዲት እህት ወደ መጪው ዓለም ላቀናችው እናቷ የማይቋረጥ ስንቅ ለማቀበል ለአስክሬን ማጠቢያ የሚሆን የውኃ ታንከር መስቀያ ረጂም ማማ በባቲ ጃሚዕ መስጂድ ቅጽር ውስጥ እንዳስገነባላት በጠየቀችኝ መሰረት ግንባታው በመጠናቀቁ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዬት በባቲ ጃሚዕ መስጂድ ውስጥ ተገኝቼ ነበር። በዚህ መሃል ከሴቶቹ መስጂድ ግድዳ አጠገብ በመደዳ ተቀምጠው በማለዳ ቁርኣን የሚቀሩ ህጻናት ተመለከትኩ። ድባቡ የልጅነት ዘመንን አስደናቂ ትዝታ መልሶ የሚያሳይ ትዕይንት ይመስላል። ከሁሉም በላይ ትኩረቴን የሳበው ነገር በተንቀሳቃሽ ምስሉ የምትታየው እናት በመስጂዱ ውስጥ እያለፈች እያለ ህጻናቱ ቁርኣን ሲቀሩ ስትሰማ በመመሰጧ ከሱቅ ለእያንዳንዳቸው ብስኩት በመግዛት በዚህ መልኩ ሰርፕራይዝ ያደረገችበት ሁኔታ ነው።

ለሰጪው ቀላል የሚመስሉ ነገሮች በተቀባዩም ሆነ በአላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አላቸው !!

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

23 Nov, 14:59


በርካታ ነፍሰጡሮች «የዳንያ ሐላዋ ሽታ ከሩቁ እያወደን ሥለሆነ የወሊድ ቀናችን ከመድረሱ በፊት እባካችሁ ላኩልን» እያሉ ትዕዛዝ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። የሸክላ አፈር ሽታ ናፈቀን ይሉ የነበሩ ነፍሰጡሮች የዳንያ ሐላዋ ከቤታችን ይምጣልን ወደማለት በመሸጋገራቸው ድርጅታችን ይህን እንደ ትልቅ ስኬት ይቆጥረዋል። በዚህ አያያዝ በቅርቡ የነፍሰጡሮች ፓኬጅ መጀመራችን አልቀረም 🤣



http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

22 Nov, 13:39


ዛሬ በባቲ ጃሚዕ መስጂድ የጁሙዓ ኹጥባ ከመደረጉ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በምክትል ኢማማችን ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን አንደበት የሰማነውን ሁለት አስደናቂ ክስተቶች ላካፍላችሁ ወደድኩ።

የባቲ ወረዳ ነዋሪዎች የዒድ ሶላት የሚሰግዱበት ቦታ ብርሃናማው ተራራ (جبل النور) ይሰኛል። ቦታው አባጣ ጎርባጣ ከመሆኑ የተነሳ ለመስገጃነት እምብዛም ምቹ  አይደለም። የዒድ በዓላት በመጡ ቁጥር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጉልበቱን በማስተባበር የመደልደል እና የማስተካከል ሥራ ለበርካታ ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። ይህን ጉዳይ የሚከታተለው የባቲ ጃሚዕ መስጂድ ንዑሥ ኮሚቴ ወደፊት ቦታውን ለመስጂድ ግንባታ በሚመች መልኩ ለማዘጋጀት ዕቅድ እንዳለው የሰሙ ጋሽ ሙሐመድ ዐብደላህ ጠሃ የተሰኙ በጎ አድራጊ አባት ለመደልደል እና ለማስተካከል ከ450 ሰዓታት በላይ የሚፈጀውን ቦታ «መሬቱ ለግንባታ ዝግጁ እስከሚሆን ድረስ ሙሉውን የመደልደል ሥራ በግሌ እሸፍናለሁ» በማለት ሁለት ዶዘር መኪናዎቻቸውን በነጻ እንዲሰሩ ፈቀዱ። እስካሁን የ200 ሰዓታት ሥራ ሰርተዋል። በቀጣይ ሌላ ተጨማሪ ማሽን በማስገባት ቀሪውን 200 ሰዓታት ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ በገንዘብ ቢተመን ከአንድ ሚሊዬን ብር በላይ የሚጠይቀውን ሥራ በቢላሽ ድጋፍ አድርገዋል።
 
ሁለተኛውና የሚያስገርመው ደግሞ ባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ በባቲ ከተማ ሂኔሳ በሚባል ሰፈር ለአንድ መስጂድ ግንባታ የሚውል መሬት ለመግዛት በአንድ ሰዓት ውስጥ ከ800,000 ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰብ ችለን ነበር። ለባለ መሬቱ የጎደለውን 210,000 ብር አንዲት እናት ሸፈነች። ይህችው እናት ዛሬ ላይ የመደልደል ሥራ እየተደረገለት ለሚገኘው የጀበለኑር ቦታ «ወደፊት የመስጂድ ግንባታ ስታከናውኑ አጠቃላይ 431,600 ብር ድጋፍ ማድረግ እፈልጋለሁ» በማለት ለባቲ ጃሚዕ መስጂድ ኮሚቴዎች እና ኢማሞች እጇ ላይ የነበረውን ሙሉ ገንዘብ ከአስር ቀናት በፊት አስረክባለች። ነገር ግን ከሁለት ቀናት በፊት ወደ አኼራ ተጉዛለች !!

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

18 Nov, 18:03


ባባቲ መስኮት ሾልኮ የስዊዘርላንድን ሰማይ በምናብ ያጠነው የዳኒያ ሐላዋ ሽታ ከወንድም ኢልያስ አፍንጫ ከምኔው እንደረሰ ባለውቅም በረጂሙ ወደ ውሰጥ አየር ከሳበ በኋላ «ለሁሉም የባቲ አቢዘር መድረሳ መመህራን የዳኒያን ሐላዋ አቅምስልኝ» ባለኝ መሰረት በድምሩ 13 ኪ.ግ ሐላዋ ለሁሉም መምህራን አከፋፍለናል።

ዳኒያ ድንበር ተሻጋሪ ቃና ያለው ሐላዋ

ለማዘዝ 👉
+251921555158

Mohammed Ahmed Official

18 Nov, 10:14


የዳኒያ ሐላዋ መሸጫ ሱቅ በተከፈተ በሁለተኛው ቀን ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለመመልከት ወደ ቦታው ሳቀና «ሙሐመድ ፣ የወንድሜ ልጅ !» የሚል ድምጽ ከቅርብ ርቀት ወደ ጆሮዬ ገባ። ዘወር ስል ምድር ላይ 106 ዓመታትን የቆዩት የዕድሜ ባለጸጋው ጋሽ ሙሐመድ ኣደም የባቲ ጃሚዕ መስጂድ በር ላይ ከነ ግርማቸው ይታያሉ። «ጋሼ ፣ እንዴት ከርቀት እኔ መሆኔን ማወቅ ቻሉ?» ብዬ ጠየኳቸው። «እንዲህ በቅርብ ርቀት ሆነህ ይቅርና ሸህ ዐብዱ ሙሐመድ ሱቅ አጠገብ እያለህ አንተ መሆንህን መለየት አይከብደኝም» አሉኝ። ሸህ አብዱ ማለት የጋሽ ሙሐመድ ኣደም አማች ናቸው ። ከመስጂዱ በር እስከ ሸህ ዐብዱ ሱቅ ያለው ርቀት በግምት 70ሜ ይሆናል።

ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ምድር ላይ ቆይተው ጆሯቸው የነብርን ኮሽታ እንደምትሰማ ሚዳቋ በዙሪያቸው ያለውን ድምጽ የሚያንኳልል ፣ ግዳይ ተመልክቶ ከሰማይ ቁልቁል እየተመዘገዘገ በሹል ምንቃሩ ካሰበበት ቦታ እንደሚያርፍ ንስር ዓሞራ ዓይናቸው የበራ ፣ በግዛቱ ተደላድሎ የሌሎች እንስሳት ንጉስ የሚል ማዕረግ እንደተቸረው አንበሳ ጉልበታቸው የበረታው እኝህ አባት ምን እየተመገቡ ይሆን ይህን ሁሉ ጤና ያደላቸው ??

በዘመናቸው ሐላዋ ይጠቀሙ ይሆን ? 😂

በሉ እናንተም ጣፋጩን የዳኒያ ሐላዋ እያዘዛችሁ ብርታቱን ይለግሳችሁ።

+251921555158

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

17 Nov, 17:17


ይህኛው የዳኒያ ሐላዋ ደግሞ በዘመን ጥግ ላይ በተሸነሸነ የተፈጥሮ ቀለም አሸብርቆ እንደተፈጠረ Sedimentary rock የታጠቀው መቀነት አይንን ያማልላል። ጠዋት ቁርሴን ተመግቤ ስመለከተው «ጀርባውን ለሁለት ከፍለህ ግመጠው ግመጠው» የሚል ክጃሎት የፈጠረው ድምጽ ከውስጤ ሲያስተጋባ ተሰማኝ። በህብረ ቀለማት ያሸበረቀውን የዳኒያ ሐላዋ የቀመሰ በሐላዋ ሱስ ከመያዝ አይተርፍም።

ለማዘዝ 👉
+251921555158

Mohammed Ahmed Official

17 Nov, 16:26


ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ እና የከተማ ነዋሪዎችን አቅም ከግንዛቤ ያስገባ የዳኒያ ሐላዋ ምርት ዛሬ ለመጀመሪያው አከፋፋያችን ማስረከብ ችለናል። በባቲ ከተማ የምትገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከነገ ሰኞ ህዳር 7/2017 ዓ.ል ጀምሮ የዳንያን ሐላዋ መቅመስ እንደምትችሉ ከወዲሁ ለማበሰር እንወዳለን። ይህንኑ ተመሳሳይ የሐላዋ ምርት የህብረተሰቡን አቅም ባማከለ ሁኔታ በሱቃችን የምንሸጥ መሆኑን ለከተማው ነዋሪ ማሳወቅ እንወዳለን።

የዳኒያ ሐላዋ ጥራት እና ጣዕም በተገልጋዮች አንደበት ምስክርነት እየተቸረው ነው

ለማዘዝ 👉
+251921555158

Mohammed Ahmed Official

17 Nov, 10:29


ነዋሪነታቸውን በሀገረ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ያደረጉ ወላጆች (ወንድም ሙሐመድ ያሲን ሰዒድ እና እህት ዳሩሰላም ሰዒድ ኸሊፋ) ልጃቸው ኡበይዳ ሙሐመደ ያሲን 30 ጁዝእ ቁርኣን እዚያው ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በመሃፈዙ አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸው የደስታው ተካፋይ እንዲሆኑ ጣፋጩን የዳኒያ ሐላዋ 20 ኪ.ግ እንድናደርስላቸው በጠየቁን መሰረት ኸሚሴ እና ባቲ ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸው አድርሰናል። ጣዕሙን የቀመሱት ቤተሰቦቻቸውም በምርታችን ጥራት እና ጣዕም በመገረም ደስታቸውን ገልጸውልናል።

ስዊዘርላንድ የሚገኘው ሌላኛው ወንድማችን ሐሰን ኢብራሒም ባቲ እና አዲስ አበባ ለሚገኙት ቤተሰቦቹ 10 ኪ.ግ የዳኒያ ሐላዋ እንዲደርሳቸው በጠየቀን መሰረት ከደጃፋቸው ቆመን አደራውን አድርሰናል። ከተጠቃሚዎች የሚደርሰን አስተያዬት ልብ ያሞቃል።

የዳኒያ ሐላዋን የቀመሰ ህጻን ወላጆቹ ከዳኒያ ሐላዋ መሸጫ ሱቅ በር ላይ በየቀኑ እንዲመላለሱ የሚያደርግ አንዳች ምትሃት አለው።

እናተ እዘዙን እንጂ እኛ ለመተዛዝ ግጁ ነን
+251921555158

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

15 Nov, 08:21


ጁሙዓችሁ እንዲህ አይንን እንደሚያማልለው የዳኒያ ሐላዋ ፍክት ያለ ይሁን !

ዳኒያ የሐላዋ መሸጫ ሱቅ
ለማዘዝ ሲፈልጉ
+251921555158

Mohammed Ahmed Official

15 Nov, 05:37


ዛሬ ዕለተ ሀሙሥ ኅዳር 5/ 2017 ዓ.ል ዳኒያ የሐላዋ መሸጫ ሱቅን በባቲ ከተማ ለመክፈት ችለናል። በርካታ ዓይነት ጣዕም ያላቸው እና በጥንቃቄ እና በጥራት ተከሽነው የተሰሩ ጣፋጭ ሐላዋዎችን በከተማችን እያመረትን ለተጠቃሚዎች ያቀረብን ስለሆነ በታላቁ ባቲ ጃሚዕ መስጂድ የገበያ ማዕከል ኮርነር ላይ ከሚገኘው ሱቃችን ጎራ ቢሉ ለዓመታት የቆየ አምሮትዎን ያወጣሉ። የከተምንበት ቦታ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘረጋውና የባቲ ከተማን ለሁለት ከፍሎ ወደ አፋር ክልል ቁልቁል በሚወርደው አስፋልት ዳር ላይ በመሆናችን በጉዞ ላይ ላሉ ተሳፋሪዎች በቀላሉ ወርደው አገልግሎቱን ለማግኘት ምቾት የሚሰጥ ነው።

ለሰርግ ፣ ለትምህርት ምረቃ ፣ ለቁርኣን ኺትማ፣ ለበዓላት ፣ ለመስተንግዶ ፣ ለቡና ቁርስ ፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች በትዕዛዝ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው። ይህን አፍንጫ የሚያውድ እና የምራቅ አመንጪ እጢዎችን የሚያቅለበልብ ሐላዋ ቤተሰቦቻችሁ እና ወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንዲቋደሱ የምትሹ ባህር ማዶ ያላችሁ ወገኖቻችን ፣ ከናንተ የሚጠበቀው ከታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥራችን ማዘዝ ብቻ ሲሆን እኛ ደግሞ የእናንተን ፍላጎት በዴሊቨሪ እውን እናደርጋለን።

በቅርቡ ወደ ሎጊያ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ደሴ እና ኸሚሴ የምናከፋፍል መሆኑን በአክብሮት እየገለጽን የገርባ እና ደጋን ነዋሪዎች የሐለዋው ሽታ በባቲ መስኮት ከሾለከ ከናንተ ጎረቤቶቻችን አፍንጫ በቀላሉ መድረሱ የማይቀር በመሆኑ ወደ ባቲ በባጃጅ አሊያም ወክ እያደረጋችሁ ብቅ ብላችሁ የጣዕምን ልክ እንድታጣጥሙ እንጋብዛችኋለን።

ለማዘዝ 👉 ሞባይል +251921555158

Mohammed Ahmed Official

06 Nov, 17:01


ከሦስቱ አንዱን
🍁🍁🍁🍁🍁

እህታችሁ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ዕድሜዋ በፈታኝ የህይወት አዙሪት የተሞላ ነው። አካሏ ሳይጠነክር ወደ ትዳር ዓለም ገባች። በትዳር ጎጆ ውስጥ ብዙም ሳትቆይ ባለቤቷ በካንሰር በሽታ ተያዘ። ለ6 ዓመታት ያህል የትዳር አጋሯን አስታመመች። በመጨረሻም አይኗ እያየ በሞት ተለያት። ሁለተኛ የበሽታ ፈተና የአይን ማረፊያዋ በሆነችው ልጇ ብቅ አለ። የልጇን ህይወት ለማትረፍ በሆስፒታል ውስጥ እየተንከራተተች ወራት አሳለፈች። እንደመታደል ሆኖ ልጇ ተረፈች። ያች ልጅ ዛሬ ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ሆናለች።

ሶስተኛው የመከራ ተራ ወደራሷ እህታችን ተሸጋገረ። በስኳር እና በሌሎች ተጨማሪ በሽታዎች ተጠቃች። የሚያሳዝነው ለስኳር በሽታዋ ህክምና የሚያገለግለውን ኢንሱሊን የምታስቀምጥበት ፍሪጅ አጥታ የተጠቀለለ ኬሻ ላይ ውኃ እያፈሰሰች ማኖር ከያዘች ሰነበተች።

እህታችን በእንስሳት ጤና ዲፕሎማ ፣ በአካውንቲንግ ዲግሪ እና በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ማስተርስ ያላት ብርቱ ልጅ ናት። ነገር ግን በዲፕሎማ በተመረቀችበት የእንስሳት ጤና እየሰራች ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቅ አስቤዛ መግዣ የማይበቃ ደመዎዝ በመቀበል ፈታኙን የህይወት ዳገት በእንፉቅቅ እየወጣች ትገኛለች።

ውዶቼ ፣ ከናንተ ሦስት ነገሮችን እፈልጋለሁ

1) ለእህታችን ለስኳር በሽታ የምትጠቀመውን የኢንሱሊን መድሃኒት የምታስቀምጥበት ትንሿን ፍሪጅ ግዙልኝ ወይም

2) የተሻለ የስራ እድል አመቻቹላት

3) ሶስተኛው መፍትሄ ከህጻን ልጇ ጋር የሚገናኝ እና በአደባባይ የሚነገር ችግር ባለመሆኑ ከእኔ ጋር በውስጥ መስመር አሊያም ከእህታችን ጋር በስልክ በመነጋገር ልትረዷት ትችላላችሁ።

እህታችንን ማግኘት እና መደገፍ የምትፈልጉ አድራሻዋን እንዳቀብላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

25 Oct, 11:24


እሺ ማን ብቅ ይበል ??
🍁🍁🍁🍀🍀🍁🍁

የመስጅዱን ቅጽር አልፋችሁ ወደ ውስጥ ስትገቡ ለተከበረው የአላህ ቤት ድምቀት የሆኑና ከቦታው የማይጠፉ ተናፋቂ ሰዎች አጋጥመዋችሁ አያውቁምን ?? መስጂዱን ስታስቡ በአይምሯችሁ ጓዳ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ጎልተው የሚታዩ ደጋጎች ትዝ አይሏችሁምን ?? አንዳንዴ በመስጂዱ ውስጥ እነሱን ማጣት የማታስቡት ቢሆንም ድንገት ካጣችኋቸው «ምን አጋጥሟቸው ይሆን?» ብላችሁ የምትጨነቁላቸው መልካሞች የሉምን ???

ለመስጂዱ ውበት የነበረ አንድ ወንድም ላላፉት ሦስት ቀናት ከተባረከው ቦታ ጠፍቶ የውኃ ሽታ የመሆኑ ነገር ግራ ቢገባኝም ምስጢሩ ግን ዛሬ ገባኝ። ሰሞኑን ከአካባቢው ራቅ ወዳለ መስጂድ እየሄደ ከሰገደ በኋላ ምሽት ወደ ቤቱ ይገባል። ምሳውን እየዘለለ ቁርስ እና እራቱን እንደምንም ቀምሶ ያድራል። ለቤተሰቡ የዕለት ጉርስ ለመፈለግ እየኳተነ ሳገኘው የፊቱ ገጽታ በውስጡ መሸከም የከበደው የህይወት ጓዝ እንዳለ ያሳብቃል። የውስጡን እንዲተነፍስ ሳባብለው ከንግግሩ በፊት እንባው ቀደመው። ድህነት ዓይኑ ይጥፋ !

ወንድማችን ለወራት የተቆለለበትን የቤት ኪራይ መክፈል ቢሳነውም ምስጋና ታጋሽ ለሆኑት አከራዮቹ ይግባና እስከዛሬ በትዕግስት ጠበቁት። አሁን ግን አልቻሉም። እነሱም ኑሮን እየተንገዳገዱ የሚገፉት ከቤት ኪራይ በሚያገኟት ሽራፊ ገንዘብ ሆነና ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በምትኩ ሌላ ተከራይ ማስገባት ሆነ። ወንድማችንም ቤተሰቡን የት እንደሚጥል ግራ ገብቶት አየር ላይ በነፋሰ እንደሚገፋ ፌስታል አቅጣጫ ጠፍቶት እየዋለለ ነው። እንግዲህ ወንደማችን ያለበትን የቤት ኪራይ እና የተወሰነች የቤት አስቤዛ ለመሸፈን 40,000 ብር ማግኘት ከቻልኩ ደስ ይለኛል።

«ከገባሁበት የህይወት አጣብቂኝ አላህ መንጭቆ እንዲያወጣኝ ፣ ወንድሜ ከገባባት የህይወት ቅርቃር ለማውጣት ሰበብ መሆን እፈልጋለሁ» የምትሉ ወንድሞች እና እህቶች የወንድማችንን አድራሻ በውስጥ መስመር ላቀብላችሁ ዝግጁ በመሆኔ ብቅ እያላችሁ ጠይቁኝ። እሺ ዛሬስ ማን ብቅ ይበል ?

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

25 Oct, 07:32


ዓለም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ እሳት በሚነድባት የምድራችን ክፍል ውስጥ ለብቻቸው አጥሮ የተዋቸው አይሰበሬ ትውልዶች እህቶቻቸውን ተሸክመው በባዶ እግራቸው ረጂም ርቀት መጓዝ አይከብዳቸውም። ቃሉ ተፈጻሚ መሆኑ ላይቀር እንግልታቸው አንገላታን እንጂ ለነሱ የተቆረጠው ቀን እንደ ዓይን እና አፍንጫችን ያህል ሩቅ አይደለም።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

23 Oct, 06:00


ውድ የቴሌግራም ተከታዮቼ

በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወይም እሱን የሚመስል ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ የሚያስመጣና የሚሸጥ የምታውቁት ድርጅት ካለ ብትጠቁሙኝ በጣም ደስ ይለኛል።

ለትብብራችሁ አመሰግናለሁ

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

19 Oct, 16:43


220,000
የስስትን ግብዓተ መሬት አፋጥነው ለጋሽ እጆቻቸውን ለመዘርጋት የሚሽቀዳደሙ ጀግኖች ሰልፍ ይዘው ወደ ቤቴ ብቅ ሲሉ ማዬት በዱንያ ውስጥ ከሚያስደስቱኝ ነገሮች ዋነኛው ነው። እናንተ ወዳጆቼ ለጥርዬ ምላሽ መስጠት ያብቃችሁ እንጂ እኔ ደግሞ የገባሁትን ቃል በተጨባጭ ለመፈጸም የአገር ሉዓላዊ ድንበር እንደሚጠብቅ ወታደር በተጠንቀቅ ቆሜያለሁ።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

18 Oct, 17:22


ሰዎቹ ... ቀበቶ አልባ ሱሪ ለብሰው ... ሰንደል ጫማ ተጫምተው ... እዚህ ግባ የማይባል መናኛ ሰዓት እጆቻቸው ላይ አስረው ... ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ግፈኛ ዓለም ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል አድርገው ... በአላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያህል ዋጋ በሌላት ዱንያ ወስጥ "በሳቅ" ኖረው ... በወስጧ የነበራቸውን ቆይታ ሲያገባድዱ የትግሉን ዓርማ ለተተኪው ትወልድ በማስረከብ ጀርባቸውን ለዱንያ ሰጥተው ተሰናብተውናል ...


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

18 Oct, 09:33


በበርካታ ወህኒ ቤቶች ካሳለፋቸው የ22 ዓመታት አስከፊ የእስር ቆይታ በኋላ የደከመ ሰውነቱን ይዞ እትብቱ ወደተቀበረባት የኻን ዩኒስ መንደር የተቀላቀለው ጀግና ዳግም ሰውነቱን ያዘጋጀው በበስመቲ ሩዝ ለማደለብ ሳይሆን መሳሪያውን አንግቦ ለዚያ ቅዱስ ሥፍራ ክብር ሲል ለመዋደቅ ነበር። «ወንድ ሆኖ እንሶስላ እየሞቀ የሚሞት» እንዳለ ሁሉ ጠላቱን ከአንድ አይሉ ሁለት ጊዜ የሞት ጽዋ አግቶ የሚሰዋ ጀግናም አለ።

የሕያ ሆይ ፣ ሥራህም እንደ ሥምህ ህያው ሆኗል !!!

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

15 Oct, 16:40


«በመላው ዓለም የሚገኙ የባቲ ልጆችና ወዳጆች» የሚል ሥም በተሰጠው የቴሌግራም ግሩፕ ላይ የማይታክቱ ወንድሞች እና እህቶች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ 828,221 ብር ፣ በአፋር ወገኖቻችን በኩል ሌት ተቀን በማይደክሙ ወንድሞች እና እህቶች በተደረገ ብርቱ ጥረት 414,350 ብር ፣ እንዲሁም እህታችን Fetehya Hassen ያለችበት የጤንነት ሁኔታ አሳስቧቸው በዱዓም ሆነ በገንዘብ የአቅማችውን ድጋፍ ያደረጉ ወገኖች ተደምረው ለእህታችን ህክምና ወጪ የሚሆን አጠቃላይ 1,242,571 ብር ሊገኝ ችሏል።

«ሰው እያስፈለገኝ ሰው በበዛበት የብቸኝነት ዓለም ውስጥ ሳለሁ ምርኩዝ ሆናችሁ ከጎኔ በመቆም ካለሁበት ክፍል ነገን በተስፋ እንድመለከት የበኩላችሁን ጠጠር የጣላችሁ ወገኖቼ ሁሉ ! ሥማችሁን በነፍስ ወከፍ እየጠራሁ የምስጋና ቃል ብደረድር ምን ያህል ደስታ እንደሚሰማኝ የምናውቀው የፈጠረኝ አላህ እና እኔ ብቻ ነን። የማደርገው ህክምና እንዲሳካ እና ከናንተ ከምወዳችሁ ወገኖቼ ጋር ዳግም በመልካም ጤንነት እንድመለስ በዱዓችሁ አስታውሱኝ» ብላለች።

የድጋፍ እንቅስቃሴውም በዚሁ እንዲቋጭ ተብሏል።


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

07 Oct, 17:30


ለእህታችን ፈትሒያ ሐሰን እየተደረገ ያለው የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ ይገኛል። አሁን ግን ቀደም ብሎ በቴሌግራም በተከፈተ ግሩፕ ሌት ተቀን እየተንቀሳቀሱ ያሉ ወንድሞች እና እህቶች አንድ አደራ ጣሉብኝ። «ባንተ በኩል ለእህታችን ፈትሒያ መታከሚያ የሚሆን ቢያንስ 70,000 ብር ወደ አካውንቷ ገቢ ማድረግ አለብህ» ብለው ኃላፊነት ሰጥተውኛል። "የምትወዱኝ እና የምወዳችሁ ወዳጆቼን የምለየው" አሁን በመሆኑ በሚከተሉት አካውንቶች የምትችሉትን ገንዘብ ገቢ አድርጉና ደረሰኙን በውስጥ መስመር ላኩልኝ። እባካችሁ ደስ እንዲለኝ ጥረት አድርጉ።

Tesfaye Temesgen & Awol Ali
CBE 1000651278205
Mobile
+251911242907

Huseen Abudu Mohammed
CBE 1000650699107


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

07 Oct, 14:44


በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው ርዕደ መሬት ሞገዱ 230 ኪ.ሜ አሳብሮ አዲስ አበባን ለአፍታ ያህል በንዝረት ሲንጣት ባለቤቱ ከፈለገ የምንኖርባትን ምድር ከእጅ ላይ አፈትልኮ እንደወደቀ እንቁላል በሴኮንዶች ልዩነት መከስከስ የሚችል መሆኑን ከዚህ በላይ ጥቆማ የሚሰጥ ማንቂያ ደወል ባለመኖሩ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለመፈተሽ የመጣ የመጨረሻ ዕደል አድርገን እንቁጠረው። ያልታሰበ ቦታ ተገኝተን ባልታሰበ አሟሟት ወደ አላህ ከመጓዝ ይጠብቀን !!


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

06 Oct, 19:15


በፍርግርግ የታጠረውን መስኮት እንዲህ እየከፈትን የብዙዎች ናፍቆት የሆነውን ወርቃማ ጉልላት በቅርብ ርቀት እያየን ንጹህ የሰላም አየር የምንስብበት ጊዜ ሩቅ አይደለም !

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

04 Oct, 16:23


«ሰው ኑሮውን ነው የሚመስለው» የሚለው አባባል በዚህ ፍልስጤማዊ ወጣት ላይ በግልጽ ተንጸባርቋል።

በሰው አልባ አውሮፕላን በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ በአላህ ተዓምር ከሞት በተረፈበት ቅጽበት ከአንደበቱ በተደጋጋሚ ሲወጣ የነበረው ቃል «እኔ በህይወት አለሁ ፣ ውዱእ አድርጌ የመግሪብን ሶላት መስገድ እፈልጋለሁ። የአሱር ሶላት አለፈኝ ፤ የመግሪብ ሶላትም ሊያልፈኝ ነውን ? እባካችሁ ሶላቴን ልስገድ» የሚል ነበር።

ይህ አይበገሬ ህዝብ በወሬ ሳይሆን በተግባር ከአላህ ጋር ያለው ጠንካራ ትስስር አስገራሚ ነው።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

27 Sep, 07:25


የዱንያ ሸክም ትከሻችንን የሚፈትንበት ጥንካሬ በልባችን ውስጥ ለዱንያ በሰጠነው የቦታ መጠን ይወሰናል። ዱንያ በውስጣችን ድንበሯን እያሰፋች በሄደች ቁጥር ወደ አላህ የመቅረብ ዕድላችን ወሰኑ ይጠባል። ከአላህ ግዛት የራቀ ልብ ደግሞ ዕጣው የታፈነ ህይወት መምራት ይሆናል። በታፈነ ህይወት ወስጥ የዱንያን መከራ እና ድሎት እንደ አመጣጡ ለመሸከም የምንችልበት ትከሻችንም ሚዛን ያጣል።

http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

23 Sep, 16:56


ከአፍህ በወጣ ክፉ ቃል ምክኒያት አንዴ የተሰበረን የወዳጅ ልብ ለመጠገን ከምታወጣው ጉልበት ይልቅ ወጪ ቆጣቢ በሆነ ጨዋ አንደበት ተናግረህ የወዳጆችህን ልብ ከነ ውበቱ መጠበቅ አትራፊ ያደርግሃል።


http://t.me/abuafnanmoh

Mohammed Ahmed Official

22 Sep, 17:27


ልብ ጠጋኞቹ
🍀🍀🍀🍀
በቨርጂኒያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለትምህርት ቤታቸው የፅዳት ሰራተኛ ከዚህ ቀደም አስቦ በማያውቀው የልደት ስጦታ ሰርፕራይዝ ለማድረግ በመወሰን ህልማቸውን አሳክተዋል።

ተማሪዎቹ የፅዳት ሰራተኛው የእድሜ ልክ ህልም ጂፕ ራንግለር መኪና ባለቤት መሆንና መኪናውን ለመግዛት እጅ እንደሚያጥረው በመገንዘባቸው የእርዳታ ዘመቻ ከፍተው መኪናው የሚያወጣውን 20,000 ሺህ ዶላር 💰 በማሰባሰብ የዓመታት ህልሙን ዕውን ማድረግ ችለዋል።

እነዚህ ተማሪዎች የፅዳት ሰራተኛውን የልደት ቀን ጠብቀው የመኪናውን ቁልፍ በእጁ በማስረከብ ሲያስገርሙት በዙሪያው እየተከናወነ ያለውን ነገር ባለማመን በደስታ ስሜት ተውጦ እንደ ህጻን መሬት ላይ ተንከባለለ። በሀሴት ብዛት እንባው በጉንጮቹ ላይ ተንኳለለ።

🚩 እኛ ደግሞ በነጭ ዱቄት እና በዘይት ስጦታ ብቻ ዓለምን የወረሱ ያህል ደስታ የሚሰማቸው ሚሊዮኖች ድሆችን ያቀፈች አገር ውስጥ ስላለን ዙሪያችንን እየቃየኘን የቤት አስቤዛ ማሟላት ተስኗቸው ልቦቻቸው የተሰበሩ ወገኖቻችንን ልብ እንጠግን !!!

http://t.me/abuafnanmoh