Hasen Injamo @haseniye Channel on Telegram

Hasen Injamo

@haseniye


Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye

Hasen Injamo (Amharic)

ሐሴን እንጃሞnn"ሐሴኒዬ"nnማህበራዊ ምርጫ ተከታታይ አሳች እና የሰውነታችንን ድንቅ አመራንነት በሚከፈል ያሳለፈ ፋይናንስ ነው:: ስለሆነ በተለያዩ መረጃዎችን መላክና አማካኝ እንዲሆን ለመመለስ እና ለስለስ የትኩረት ፋይናንስን እንዲያግድቡ ይፈልጋል:: በዚህ አምስት ሰላም ከተደረገ ማሕበረሰብ አይደንግግም ለለውጥ ለቴቶሎም በሌላ ሙሉ ስንቲላ እንቀርባለን::

https://telega.io/c/Haseniye

Hasen Injamo

11 Jan, 19:08


Stove የሚለው ቃል እንግሊዞች ከሞስኮቮች የተዋሱት ቃል ሲሆን ትርጉሙም ሚስት ማለት ነው::

Hasen Injamo

11 Jan, 17:56


የዛሬው መንቀጥቀጥ ትንሽ የጠና ነው::

Hasen Injamo

11 Jan, 17:41


በአሜሪካ ለምትኖሩ ብቻ መረጃ | የአሜሪካ፣ [የሃገር] የውስጥ ገቢ አገልግሎት (IRS) በ2021 የታክስ ዘመን Recovery Rebate Credit ላልጠየቁ 1 ሚሊዮን ግብር ከፋዮች በዚህ ወር ክፍያዎችን እንደሚከፍል አስታውቋል። ይህን ክፍያ ለማግኘት ምንም ማድረግ አይጠበቅባችሁም። ለዚህ ብቁ የሆናችሁትን ራሱ ለይቶ በዚህ ወር መጨረሻ አካባቢ በቼክ/በቀጥታ ወደ ባንካችሁ ክፍያ እንደሚፈጽም አስታውቋል።
[የሃገር] የውስጥ ገቢ አገልግሎት (IRS) "ብቁ ለሆኑት፣ የምፈጽማቸው ክፍያዎች 'እንደ ሰው ገቢ' ቢለያይም፣ ነገር ግን የሚከፈለው ከፍተኛው ስብስብ 1,400 ዶላር ነው' ማለቱን ዘ-ሐበሻ ያገኘው መረጃ ያስረዳል።

Hasen Injamo

11 Jan, 17:00


የግዴታ ፎርም ወይም ጽሑፍ ላይ ካልሆነ በስተቀር ማዕረጉን ከስሙ ፊት አድርጎ ከጻፈ ጽሑፉን መጨረስ አልችልም:: በአካዳሚ እንኳ ዶክትሬት የያዙ ሰዎች ማዕረጋቸውን ከስማቸው ሗላ PhD ብለው በቅንፍ ያሰፍራሉ እንጂ ዶክተር እያሉ አይዘባነኑም:: ዶክትሬቱ በግዢ ከመጣ ሊሆን ይችላል:: ፍግት ብለው የሠሩት ግን በኮንፊደንስ በነጠላ ስም ይጠቀማሉ:: አስፈላጊ ሰነድ ላይ ብቻ ለፎርማሊቲ ይጨምሩታል:: Well, ይህስ ዐለማዊ ነው:: የኃይማኖት ሰዎች እንዴት ብለው ነው ኡስታዝ ወይም ሸይኽ እያሉ ስማቸው ላይ ከፊት የሚጨምሩት? እንደው የተሸየኹትስ ይሁን መቸም ማልጎደኒ:: በእርግጥ ምንም ቂርአት የሌለው ሰው ኡስታዝ ቢል ችግር የለውም:: ይግገባዋል:: የዕውቀት ስብራቱን በማዕረግ ይደግፍ:: በደንብ የቀራ ሰው ግን እራሱን ኡስታዝ ማለት የለበትም:: ኡስታዝ ማለት PhD እንደሆነ ቢያውቅ ኖሮ አይልም ነበር:: የሚሉትን አያውቁምና ጌታ ሆይ ይቅር በላቸው እያልን እንጸልይላቸዋለን:: በኃይማኖት ሰፈር እራስህን ማስተናነስ ያስፈልጋል:: ዶክትሬት ብትደርስ እንኳ እራስህን ኡስታዝ ብለህ አትጥራ:: ሰዎች ይበሉህ:: እኛ ሀገርማ ዕጩ ዶክተር ብለው እራሳቸውን የሚክቡ, ወንድ ነርስ ሆነው "ሲስተር" የሚሉ ሁላ አሉ::

Hasen Injamo

11 Jan, 14:38


ሰሞኑ የጀማሪ ወሃb ገጾች ጋር
እየተዟዟርኩ ፈታ እያልኩ ነው::

አቡዘከር ሪያ አል-ወልቂጢይይይይይ መጥቶላችሗል ያ አህለል ወራቢይ::

እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አድርጎን አልወልቂጢይ ወጉንችሪይ ወል ቁርጭምጭሚትይ ብለን ስንቱን የጀሃነም ቦኖ እንደሰጠነው::

ወይኔ ክባድ ወይኔ ጉራ ወዮ ፉለላ
-> ሱፊያ የተባልክ ገሪባ ሁላ የቂያም ቀን የምትለቀቅ መስሎሃል:: አዎ አሁን እግርህን ዘርግተህ ቃም:: በእያንዳንዱ ብልዝ ጥርስህ አምስት አምስት ግመል ትጠየቃለህ:: ዳሩ ግን እዚያ ግመል የለህም:: መልካም ሥራህን በአምስት ግመል በ32 ጥርስ ተባዝቶ ጀሃነም በግንባርህ ትደፋታለህ:: አላህ አስውቦ የሰጠህን ጥርስ አንተ በጫት ጨርሰህ "የሰጠሁህን ጥርስ ምን አደረግኸው?" ሲልህ ምንድነው ምላሽህ? ወይ ምላሽ አዘጋጅ ወይ ለጀሃነም ተዘጋጅ:: ያንተ መግቢያ ጀሃነሞች ሳይቀሩ የሚሸሹት ሌላ ጀሃነም እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ከአፍህ ውስጥ ሲዋክ አይጠፋም ነበር:: (ያኔ ግን ዶክተር አሸብር የጥርስ ሕክምና ነበር እንዴ ስፖንሰራችን?)

ይህንን በመሰለ የሰለፊነት ዳዕዋ ድሮ ጫት ያስተውኩት ጋር አብረን እየቃምን ነው:: ማነህ እስቲ ቡናውን ቅዳው:: እነወልቂጢይ ሲዖል VVIP ላይ ይዘውልናል:: ሲዖል ከሞላ ፒዮንግያንግ መግባታችን ነውና በደንብ እንቃም::

Hasen Injamo

11 Jan, 13:32


እንግሊዝኛ መማርን ግዴታ አድርጎ ግብርናና ዕደ ጥበብ መማርን ምርጫ ያደረገ የትምህርት ሥርዓት እንግሊዝኛ የሚኮላተፍ ደሃና ማይምን ነው የፈጠረው:: እንግሊዝኛንም ሳንችል, ሀብትም ሳይኖረን የዓሳ ቀለብ ሆንን:: እንደው አፍሪካውያን እንግሊዝኛን ከሚማሩ ቢያንስ የሻርክን ቋንቋ ቢማሩ ባሕር ያሻግራቸው ነበር:: 24 ዓመታት ከተማረ አፍሪካዊ የአራት ዓመት የፈረንጅ ሕጻን የተሻለ እንግሊዝኛ ይችላል:: አንድ ፈረንጅ በአፍሪካኛ ቢማር ኖሮ በዚህ ሊጥ መልኩ ማን ይፈልገው ነበር? 30 ዓመታት በአማርኛ ከተማረ እንግሊዛዊ ይልቅ የሽሮሜዳ ወይም የሳሪስ የአራት ዐመት ሕጻን የበለጠ አማርኛ አቀላጥፎ ይናገር ነበር::
እንግሊዝኛም አልቻልን:: እንግሊዛዊም አልሆንን:: እንግሊዞቹም አልወደዱን:: ኑሮአችንም ቁልቁል::

Hasen Injamo

11 Jan, 11:13


አሜሪካ የምትኖሩና ድርጅት የምታቋቁሙ እንዲሁም ያቋቋማችሁ የሒሳብ ሥራና ሠራተኛ የተሸገራችሁ ወይም የተወደደባችህ ወዲህ ምጡ:: ከአማሪካ እጅግ ባነሰ ዋጋ ይሠራላችሗል:: የአካውንቲንግ የአሜሪካ ሲስተሙ ላይ ሠርተናል:: እየሠራንም ነው::
QB Intuit ጥርሳችንን የነቀልንበት ነው::

ስልክ
+251941 959595
ቴሌግራም, ዋትስአፕ

Hasen Injamo

11 Jan, 08:38


- ድሮ ሽልማት በሥራ ነበር:: አሁን በግዢ ሆኗል:: የሆነ ቦታ ተሸለምኩ ካልክ እንዳጭበረበርክ ይቆጠራል::
- ድሮ ሐኪሞች ምግብ በደንብ እንድንበላ ይመክሩን ነበር:: አሁን እንድንቀንስ ይመክሩናል::
- ድሮ ኡስታዞች በጣም ታማኝ ነበሩ:: አሁን ወመኔዎችና ዘራፊዎች ሆነውብናል::
- ድሮ የተማረ በጣም ይከበር ነበር:: አሁን ጎበዝ ተማሪነት እያሳፈረ ነው::
- ድሮ ካሽ መያዝ የሀብታምነት ምልክት ነበር:: አሁን የድህነት ምልክት ነው:: ሀብታም ንብረት እንጂ ካሽ አይዝም::
- ድሮ ብሎ ማውራት የማር-jet ምልክት ነበር:: አሁን የወጣትነት በመሆኑ ደስ ብሎኛል:: ማሻአላህ! አልሃምዱሊላህ::

Hasen Injamo

10 Jan, 18:47


በሬውም ታሟል ጊደሯም ታማለች
ኧረ ለመሆኑ ያችስላም እንዴት ነች

Hasen Injamo

10 Jan, 18:35


የባንክ ፖሊሲው የውጭ ባንኮች ሲገቡ የሠራተኞች ስብጥርን ረስቶት ነበር:: ትኩረት እንዲሰጠው በቴሌቪዥንም በመጽሐፍም ድምጽ ለማሰማት ሞክሬ ነበር:: አዋጁ ላይ ታርሟል::
(መ-ገንዘብ ገጽ 161)

Hasen Injamo

10 Jan, 18:01


የሰኪዩሪቲ ገበያው ከዓለም ለየት ብሎ መጥቷል ተብሏል:: ስጋቴ:-

1) ያልተሞከረ አካሄድ የት እንደሚያስኬደን የምናየው ይሆናል::
2) የባንክ ኦሊጎፖሊዎች ገበያውን በስፋት በመቆጣጠር የጥቂት ድርጅቶች ብቻ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል::

ባንኮች በአምቻ ጋብቻ በብሔርና በኃይምኖት በመደራጀት ብዙ ደሃና ጥቂት ሀብታም ፈጥረው የሀብት ክፍፍሉ ፒራሚዳዊ ይዘት ይዟል:: ይህ ሳይስተካከል የሰኪዩሪቲ ገበያው ባለአክሲዮኖች ጥቂት ድርጅቶች ናቸው የተደረጉት:: ይህንን ስጋት ቀድሜ ገልጫለሁ:: ይህንን የምለው ከሰፊው ሕዝብ ጥቅም እና ቀጣይ ሊገጥመን ከሚችል ችግር አኳያ ነው::

አዲሱ የባንክ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ብዙ ክፍተቶች ነበሩበት:: በተለይ የሠራተኛና የአስተዳደር ጉዳይ በETV ብቻ ሳይሆን በመ-ገንዘብ መጽሐፍ ላይ አንስቼው ነበር:: ይህኛው ክፍል በአዋጁ ተስተካክሎና ትኩረት ተሰጥቶበት ወጥቷል:: በተጨማሪም የብሔራዊ ባንክና የንግድ ባንኮች ዝምድና ካልተገደበ ለፖለቲካውም ስጋት እንደሆነ ስገልጥ ቆይቻለሁ:: በአዋጅ ደረጃ ምላሽ አግኝቷል:: አመሰግናለሁ::

ልክ እንደዚሁ የግል ንግድ ባንኮችና መሰል ተቋማት የሰኪዩሪቲ ገበያው ዋነኛ ባለአክሲዮን ናቸው:: ሰኪዩሪቲ ገበያውን ብቻ ሳይሆን የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን እጅ ጭምር ሊጠመዝዙ ይችላሉ::

የአሜሪካው Sarbanes–Oxley Act (SOX) አዋጅ የወጣበትን ምክንያት ማየትና ተመሳሳይ አዋጅ ማውጣት የግድ ነው:: Corporate and Auditing Accountability, Responsibility, and Transparency Act" ይሰኛል:: አማካሪና ኦዲተር, የንግድ ኮርፖሬሽንና የሒሳብ ሪፖርት ድርጅቶች ዝምድና ለመለየት የወጣ ነው::

ምሳሌ እኛ ጋር
ኮንታ ባንክ የጨበራ ሰኪዩሪቲ ገበያ ዋነኛ ባለአክሲዮን ነው:: ስለዚህ
- ሰኪዩሪቲ ገበያው የ Insider information ሰለባ ይሆናል::
- የሥልጣን ጥቅለላ ይፈጥራል::
- የጥቅም ግጭት ይመጣል::
- አዳጊና ታዳጊ ኩባንያዎች እንዳይቀላቀሉ ሊያግድ ይችላል::

-> ጥቅምም አለው:: ባንኮችና ትላልቅ ካምፓኒዎች ወትሮም የተረጋጉ ስለሆኑ ሰኪዩሪቲ ገበያውን ለማረጋጋት የተሻለ ላይኖር ይችላል:: ግን በሒደት ሥርዓቱን እያረሙ መሄዱ ይመከራል:: ሰኪዩሪቲ ገበያው ዘግይቷል:: ለጅማሮው congratulations 🎊🎈🎉.

Hasen Injamo

10 Jan, 15:19


ለጠቅ-ላላ ዕውቀት
የኢትዮጵያ ሰኪዩሪቲ ኤክስቼንጅ ገበያ በይፋ ተከፍቷል:: በአምስት ዐመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች ሰነዳቸውን ይሸጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል::

Hasen Injamo

10 Jan, 15:04


እንቅጥቃጤ እንዲችል ተብሎ የሚሠራው እንዲህ ነው አሉ ማንዲሶች:: ያው በሰበብ ባስባቡ እንዳይፈርስ ለማለት እንጂ መቸም ብርታት የሚሰጠው አላህ ነው::
(
ከደሳለኝ ከበደ የፌስቡክ ገጽ የተገኘ ምስል)

Hasen Injamo

10 Jan, 15:01


የዋጋ ማስተካከያ
==========
ቪስኮ ሪል ኢስቴት ቤቶች ግንባታቸው ወደ መጠናቀቅ እየደረሱ በመሆኑ በቀሪ ቤቶች ላይ የዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል::

የተስተካከለው ዋጋ ለተወሰኑ ቤቶች ብቻ
Fully finished per Sqm
-> 100% ETB 113,000
-> 75% ETB 118,000
-> 50% ETB 125,000

በመዋዋል ሒደት ላይ ያላችሁ ጭማሪው አይመለከታችሁም:: የተዋዋላችሁማ ተዋዋላችሁ እኮ::
ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ::

0941 959595 አቃጭሉ

Hasen Injamo

10 Jan, 12:13


ብዙ ዐይነት ሱሶች አሉ:: አንዳንድ ሰው "ይሰጣል" በሚባል ሱስ ተጠቂ ይሆናል:: ካልታየ አይሰጥም:: አንዳንድ ታጋይ "ታጋይ ነው" በሚባል ሱስ ይጠቃል:: ከታጋይነት ወደ በጥባጭነት ይዞራል:: አንዳንድ ሰው "የአቋም ሰው ነው" በሚባል ሱስ ይጠቃና ግትር ይሆናል:: ሐቅ ብታመጣለት እንኳ ለአቋሙ ሲል በተቃራኒ ይቆማል::

ሐቅ እና ምሉእነት ግን የአላህ ብቻ ነው::

Hasen Injamo

10 Jan, 10:41


የቀድሞ ተራራ ሕትመትና ማስታወቂያ በትጋት ተራራው ላይ ከወጣ በሗላ "ፍቅረ ሕትመትና ማስታወቂያ" ሆኗል:: ደንበኞቹን እያመሰገነ በፍቅር አብረን እንዝለቅ ብሏል::

ስም እንጂ አድራሻ አልቀየረም::
እዚያው 22 ውኃ ልማት አካባቢ PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

Hasen Injamo

10 Jan, 07:36


ብራንድ Logitech ጅራት አልባ አይጥ ለመሸመት ካዛንቺስ ብቅ በሉ:: ካዛንቺስን ካቀኑት ውስጥ አንዱ የሆነው ሉኮም ትሬድ የሚሰኘውን ረድኤት ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ታገኙታላችሁ:: ኮምፒውተራችሁን በዚህ ማውስ ክሊክ ስታደርጉት cut cut cut ብሎ ይስቃል:: ለማቆም Paste ትሉታላችሁ::
ስልክ:- 0982 926592

Hasen Injamo

09 Jan, 15:29


እስከ አለፈው 10 ዓመት ድረስ ወደሗላ የተፈራ ንብረት "ባለንብረቱ" የገቢ ምንጩ ካላረጋገጠ ይወረሳል ተብሏል:: አዋጁም ጸድቋል:: የሚወረሰውም የባለ ንብረቱ ገቢ እና ዕድገቱ ተሰልቶ ነው::

======

የእኔ ጓደኞችና የሶሻል ሚዲያ ፍሬንዶች ግዴላችሁም ከባንክ ተበደሩ:: በገዛ ገንዘባችሁ ስትሠሩ እንቅስቃሴ እየታየ የሚወርስ ኃይል ይመጣል ብያችሁ ነበር:: ገንዘብ እንኳ ባይቸግራችሁ ተበደሩ እያልኩ::: 2008 ላይ የመውረስና አካውንት የማገድ እንቅስቃሴዎች ነበሩ::

አሁንም ወደ full digital system ከመግባታችን በፊት ቀድሞ ንብረት መያዝ የግድ ይላል:: ከዚያ ግን ማን ምን እንደበላ ብቻ ሳይሆን የጓሮዋችሁ ተክል መች እና ስንት ሲሲ ውኃ እንደጠጣ ይታወቃል:: ሽንት ስትሸኑም ይሁን ስትጸዳዱ እዚያው ሽንት ቤቱ ስንት ግራም እንዳራችሁና ምን ምን በሽታ እንዳለባችሁ ወይም እንደሌለባችሁ ለማዕከላዊ ዳታ ይልካል::

Hasen Injamo

07 Jan, 19:11


በጣም ሙስሊም የምትሆነው አግራሪና አበሳሪ ስትሆን እንጂ በጣም አክራሪ ስትሆን አይደለም:: በሊቃውንት ዘንድ የዕውቀት 9/10ኛው ማቅለል ነው:: ምክንያቱም የምታቀለው ደግሞ ቅድሚያ ለራስህ ሲገባህ ነው:: ካልገባህማ እንጉልፋቶ ነው የምትሆነው:: ትንተፋተፋለህ::

እስልምና ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሎ "ላኢላሃ ኢለላህ" ውስጥ ይገባል:: የስንብት ቃልህ ላኢላሃ ኢለላህ ከሆነ የሕይወት ጌሙን ሁሉ ዘግተኸዋል:: የምንለፋው መዝጊያችን ይህንን ቃል ለማግኘት ነው:: ምላስህን የሚቆልፉብህ ነገሮች አሉ:: አንዱ የወላጅ ሐቅ ነው:: ልትሞት ስትል lock 🔐 ያደርጋል::

ላኢላሃ ኢለላህ የሚለው ቃል ከሰውነት ክፍላችን በአንዱ ማለትም በምላስ ብቻ ነው የሚወጣው:: ምላስ ይርገበገባል እንጂ ጥርስም ይሁን ጉሮሮ, ትናጋም ይሁን አፍንጫ ጣልቃ አይገቡም:: እግርና እጅ, ሆድና ማጅራት ሩቅ ናቸው:: ምላስ ላይ ብቻ:: ሞክሩት:: ሞት አጣድፎት ምላስ መርገብገብ ቢያቅተው እንኳ በትንፋሽ አላህ, አላህ ቢል አበቃ ጌሙ በአሸናፊነት ተዘግቷል::

የ113 የቁርአን ምዕራፍ መክፈቻዎች በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ የሚል ዐረፍተ ነገር ነው:: ልስልስ ያለ::

ሙሉ ቁርአን ተጠቃሎ በ7 አንቀጾች (ፋቲሃ) ውስጥ ይገባል:: ይህኛውም "አንተን ብቻ እናመልካለን:: አንተን ብቻ ዕርዳታ እንጠይቃለን" ወደሚል ሁለት ዐረፍተ ነገር ያበቃል:: ይህም ስታዞሩት የላኢላሃ ኢለላህ ትርጉም ነው::

እስልምና so simple ነው:: የነቢያችን صلى الله عليه وسلم አዋጅ:- አግራሩ, አታክርሩ, አበስሩ, አታባርሩ ነው::

Hasen Injamo

07 Jan, 16:13


ሰሞኑ ስግብግብ ነጋዴዎች በሚል የሚታሰሩት አሳዘኑኝ::

Hasen Injamo

07 Jan, 15:38


ያለፈው

Hasen Injamo

07 Jan, 15:22


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
************

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በዚሁ መሰረት እስከ አንድ ወር የሚቆየው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ:-

1. ቤንዚን -------------- 101.47 ብር በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ ---------- 98.98 ብር በሊትር

3. ኬሮሲን ------------- 98.98 ብር በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ------ 109.56 ብር በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ ------- 108.30 ብር በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ -------- 105.97 ብር በሊትር መሆኑ ተገልጿል።

Hasen Injamo

07 Jan, 09:44


የሙስሊሙን ወጣት ምን ያህል አግድም እንዳደገ የምትገነዘቡት ለዓለም ሰላም ያመጣል የምትሉት ትልቅዬ ሰውዬ "እስልምና ሰላምታ ይከለክላል" ብሎ ማመኑ ነው:: ዘወር ይልና "ኢስላም ሰላም, እስልምና የሰላም ኃይማኖት ነው" እያለ ይፎክራል:: በዚህ ዕድሜህ ይህንን አንቀጽ እናብራራልህ? ወይስ ሌላም እንጨምርልህ?
ማንም ይሁን ማን በሰላምታ ካከበረህ በተሻለ ሰላምታ አክብረው:: ቢያንስ እንኳ ያለህን አትንፈገው ነው:: ምናልባት ለስላቅ እንደሆነ እርግጠኛ ከሆነ እንኳ ወዓለይኩም በለው::

አሰላሙ ዓለይኩም ካለህ
ወዓለይኩሙሰላም ወራህመቱላህ ወበረካቱሁ በለው:: የአላህን ሰላም እዝነትና ሲሳዩን ተመኝለት:: ውስጡንም ውጪውንም የምቆጣጠረው እኔ ነኝ ይልሃል አላህ:: ግዴለህም ይህንን ተመኝ:: ምርጥ ሰላምታ ከሰጠህ አንተም እጅግ በጣም ምርጥ ሰላምታ መልስ:: ወንድሜ ጀሃነሙ እራሱ ይተፋሃል::

Hasen Injamo

07 Jan, 08:49


5.1

Hasen Injamo

07 Jan, 08:07


Logitech wireless 🛜 brand mouse ከሉኮም ትሬድ
ትሬድ
ካዛንቺስ መናኸሪያ ጋር ረድኤት ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0982 926592

Hasen Injamo

07 Jan, 08:05


የልጆቻችሁን የምሳ ዕቃ በዚህ መልክ አሳምሩ::
ከተራራ ሕትመት
22 ውኃ ልማት አካባቢ
ተራራ ከፍታውን ጨምሮ እየሠራ ነው::

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

https://t.me/Teraraprinting1

https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

Hasen Injamo

07 Jan, 07:41


እኛ ዶላርን ስናገኝ ሀብታም እንሆናለን:: አሜሪካ ግን ዶላርን ስታስወግድ ሀብታም ሆና ትቀጥላለች:: ዶላር ለአሜሪካ use and throw ነው:: በነጻ ያወጣችውና የሸመተችበት ዶላር ተመልሶ ንብረቷን የሚወስድ ከሆነ በራስ ድግስ መስከር ይሆናል:: ብሔራዊ ባንክ አንዴ ወርቅ የገዛበትን ብር አይፈልገውም: ከብሔራዊ ባንክ መልሶ ወርቅ መውሰድ የለበትም::

ይህንን ከገባን ብዙ ነገር ይበራልናል::

Hasen Injamo

06 Jan, 16:26


የሰው ልጆች ሆይ አንዳንድ ኃይማኖታዊያንም ይሁኑ ሰለጠንን የሚሉ ሰዎች denaturalize እንዲያደርጉዋችሁ አትፍቀዱ:: ከሰዋዊ ተፈጥሮ ውጭ ሲመሩህ that is denaturalize ማለት::
ሰው ሁኑ:: ሰውነት ከሁሉ ይቀድማል:: ሰውነት ተሟልቶ ነው የተፈጠረው:: ሰው ሁኑ::

Hasen Injamo

06 Jan, 15:53


ለጀነት ግንባታ አንድ ዛፍ እንዲሁም ለጀሃነም መጋጋም አንድ ፓኬት ክብሪት ያላዋጣ ሰው ፍርድ ባይሰጥ ጥሩ ነው::

Hasen Injamo

06 Jan, 15:37


ለክርስቲያን ፍሬንድ መልካም የገና እና ጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ:: በዕለቱ የዚህ ሰፈር "ይቻላል/አይቻልም" ንትርክ ውስጥ መግባት አልፈልግም:: መነታረክ የፈለጋችሁም ዛሬ በአዘቦቱ ይሻለናል::

Hasen Injamo

06 Jan, 15:31


ባለፉት 15 ሰዓታት የኢትዮጵያ መሬት ሰባቴ ብቻ ነው የተንቀጠቀጠው::

Hasen Injamo

06 Jan, 15:27


ለቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገና በዓልን አስምልቶ ለቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በበዓሉ ዕለት በመላው አገሪቱ በተመረጡ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ካርድ መሙላት እንዲችሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ በዚህ መሰረት በበዓሉ ዕለት

⚠️ ከሽረ ሪጅን፡- የዓደዋ፣ አክሱም፣ ሽረ አገልግሎት መስጫ ማዕከት ለግማሽ ቀን፣
⚠️ ከመቐለ ሪጅን፡- የመቐለ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና ቁጥር 4 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከጠዋት 2፡00 ጀምሮ ለግማሽ ቀን፣
⚠️ከሰሜን አዲስ አበባ ሪጀን ፡-ቁ:2 : አራት ኪሎ የሚገኘው ማዕከል ሙሉ ቀን
⚠️ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጀን ፡- በ7ቱም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን፡- ቁጥር 9 እና ቁጥር 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙ ቀን፣
⚠️ ከምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን፡- ቁ 1 ልደታ ሻርፕ ህንፃና ቁ 2 አየር ጤና ቴሌ አካባቢ የሚገኘው ማዕከል
⚠️ ከጎንደር ሪጅን ፡- የጎንደር ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ከደብረማርቆስ ሪጅን፡- የደብረ ማርቆስ ቁጥር 1 እና 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለግማሽ ቀን፣
⚠️ ከባህር ሪጅን፡- የባህር ዳር ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 አገልግሎት መስጫ መዕከላት ለግማሽ ቀን፣
⚠️ ከሻሸመኔ ሪጅን፡- ሻሸመኔ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 አገልግሎት መስጫ መዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከጅማ ሪጅን፡- የጅማ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከነቀምት ሪጅን፡- ነቀምት ቁጥር 1 እና 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በፈረቃ ጠዋትና ከሰዓት፣
⚠️ ከመቱ ሪጅን፡- የመቱ፣ የበደሌ እና የያዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለግማሽ ቀን፣
⚠️ ከአምቦ ሪጅን፡- የአምቦ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከአዳማ ሪጅን፡-ቁጥር 1 እና 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከሸገር ሪጅን፡- የቢሾፍቱ ቁጥር 1 እና 2፣ የለገጣፎ፣ የቡራዩ፣ የጫንጮ፣ የሆለታ፣ የሱልልታ፣ የታጠቅ (አሸዋ ሜዳ)፣የዱከም፣ የገላን፣ የጨፌ ዶንስ፣ የአዱላላ፣ የሰባታ፣ የአልም ገና፣ የፉሪ (ወለቴ)፣ የአንፎ ሜዳ እና የኦሮሚያ ኮንዶሚኒየም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከሐረሪ ሪጀን፡- የሐረሪ ቁጥር 1 እና 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ከድሬዳዋ ሪጀን፡-ቁጥር 1 (ኮኔል) እና ቁጥር (ቁጥር 2) ግማሽ ቀን፣
⚠️ ከሱማሌ ሪጀን፡- ጅግጅጋ ቁጥር 1 እና 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ከአፋር ሪጅን ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አገልግሎት ይሰጣሉ ፣
⚠️ከሆሳና ሪጅ፡- ቡታጅራ ወራቤ ሆሳና ቁጥር ቁጥር 2፣ ወልቂጤ፣ ዱራሜ፣ እምድብር አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ ከደቡብ ምዕራብ ሪጅን፡- ቦንጋ ፣ ቴፒ እና ሚዛን ማዕከላት ለሙሉ ቀን፣
⚠️ከወላይታ ሪጅን፡- የሶዶ ቁጥር 1 እና 2፣ የአለባእና ዲላ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሙሉ ቀን የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው አውቃችሁ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Hasen Injamo

06 Jan, 13:07


ብር ከፍላችሁ ቤቱም ካርታውም ለረጅም ዓመታት ያላገኛችሁ ብዙ ሰዎች ትኖራላችሁ:: የተመሰገኑም ይኖራሉ። ይባርክላቸው። እኔ ቪስኮ ሪል ኢስቴትን የማስተዋውቀው ካርታም ጭምር እያስረከበ ስለሆነ ነው:: እኔን አምነው ሄደው የክፍላቸውን ዲዛይን reshape አስደርገው ካርታቸውን ይዘው ሲገቡ ማየት እንዴት ደስ እንደሚል:: ካልሆነ አልነካካም ነበር:: 3D ብቻ እየለጠፉ ማማለልም ጥሩ አይደለም::

አላለቀም ወይ? ካላችሁኝ ቤቱ እየተገነባና ፊኒሺንግ ደረጃ ላይ ነው ያለው:: ውጪው ኒቃብ እንደለበሰ ነው:: ኒቃብና መወጣጫ ፖንቴው ሰሞኑ ይነሳል:: ሀገር ውስጥ ያላችሁ የራሳችሁን ኢንጂነርም ይሁን የሕግ ባለሙያ ይዛችሁ ሄዳችሁ ጎብኙና ክፍላችሁን አይታችሁ ብሪቷን ከፍላችሁ ተዋዋሉ:: ቪዲዮ የምትፈልጉ አላችሁ:: ሲያልቅ ምን እንደሚመስል ቪዲዮ እለቅላችሗለሁ::

በነገራችን ራስጌና ግርጌ በርካታ ሰዎች ሪል ኢስቴት ሊገዙ ሲመጡ አቅማቸውን እጠይቃለሁ:: የሚችሉትን ብቻ ነው ወደ ቪስኮ የምልካቸው:: ኮንዶሚኒየም እንዲገዙ የላክሗቸው ብዙ ናቸው:: ማማከርም ማኅበራውት ኃላፊነትም ጭምር ስለሆነ ነው::
_
ሄሎ
ሄሎ
ዲዲዲdddሪርርዝዝዝ

እሺ ስንት ብር ነው ያለሽ?
ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን

Well, ስለዚህ በዚህ ብር ቀድመሽ ዲጂታል ካርታ የያዘ ስቱዲዮ ግዢ:: ከዚያ እርሱን አስታከሽ ለራይድ የሚሆን መኪና በማይክሮፋይናንስ ሸምችና አግብተሽ ከባልሽ ጋር ተባብራችሁ ልጅ ውለዱ:: ገና የ15 ሚሊዮን ብር ሪል ኢስቴት ውስጥ ገብተሽ ጉልበትና ዕድሜሽን በበረሃ አታባክኝ ብዬ ስልኩን ዝግት:: በነገራችን ላይ ከየትኛው time zone በየትኛውም ስልክ ቢደወል ማነው ከየት ነው ሳልል አነሳለሁ:: አልሃምዱሊላህ::

Hasen Injamo

06 Jan, 10:19


በተለይ ለሙስሊሞች
ከሀራም ነገሮች በበለጠ "ሀራም ነው" ማለትን ተጠንቀቁ:: ፈቃጅም ከልካይም, ሰጪም ነሺም አላህ ብቻ ነው:: ሀራም ያልሆነን ነገር ሀራም ስታደርግ እራስህን በራስህ ሕግ አውጪ አድርገህ እየሾምክ ነው:: አልታወቀህም እንጂ ፊርዓውን እየሆንክ ነው:: የማንም የመንደር ፊርዓውን እየተሳ ሀራም ቢልህ እና ብትከተለው መድረሻህ የቀይባሕር ሸለቆ ነው:: የልብ ሚዛን ተሰጥቶሃል:: አላህ ለሰው ልጅ ውጉዝና ፍቁድ ይለይ ዘንድ ያለ ምንም ኃይማኖት ገደብ ሕገ-ልቦና ሰጥቶታል:: በኢልሃም ልቡ ውስጥ ቀብሮለታል:: ሀላል እና ሀራም ኃይማኖት የላቸውም:: የተፈጥሮ ሕጎች ናቸው:: ሥርዓተ አምልኮ ግን ነቢያት በነገሩን መልክ ይካሄዳል:: አኗኗራቸውም የጸዳና የተመጠነ, ከሰው ምንም የማይፈልጉና ምሳሌነታቸው የተሟላ ነው:: ሀላልና ሀራም ነብይ ባይላክ እንኳ ግልጽ ናቸው:: የሰው ፍላጎት ሲገባባቸው ግን ያወዛግባሉ::

Hasen Injamo

05 Jan, 13:25


ደብረሲናም ተጨምሯል:: ከደቂቃዎች በፊት 4.5 ሬክተር ተከስቶ ነበር ይላል ሪፖርቱ::

Hasen Injamo

05 Jan, 12:46


ደህና ውሎ አሁን 4.9 ሬክተር ንዝረት ተሰምቷል:: አርፎ አንዴ ሲጀምር ስለሚያከታትል ጥንቃቄ ይኑር::

Hasen Injamo

05 Jan, 12:32


የትኛውንም የጥንት የዋሻ ስዕሎች ላይ የሰላጣ ስዕል የለም:: የእንስሶቹን ምግብ እየበላችሁ አትሻሙዋቸው::

ስዕሎቹ የተሳሉት ግን ቅመው እንደሆነ ተደርሶበታል:: ዛሬ ዋሻ ውስጥ የበቀለ ነው እንዴ የቃምኩት?

Hasen Injamo

05 Jan, 11:50


ዛሬ አንድ የቢዝነስ ሐሳብ መጣልኝ:-
የሆነ ጊዜ ዶክተር ዐብይ ሲናገር "የሕወሓት አመራሮችን ይዞ ያመጣ 10,000,000 ብር እሸልማለሁ" ብሎ ነበር:: ለምን ይዘን አምጥተን ቦነሱን አንቀበልም?

Hasen Injamo

05 Jan, 11:34


ዛሬ ሌሊት 8:00 ገደማ በተመሳሳይ ወቅት ከተንቀጠቀጡ ሁለት እንቅቃጤዎች ውጭ እስካሁን በኢትዮጵያ ምድር አልተመዘገበም:: አልሃምዱሊላህ:: በነገራችን ላይ ለእኛ አዲስ ሆኖብን እንጂ በዓለም ደረጃ በየቀኑ በመቶዎች እንቅቃጤዎች ይከሰታሉ:: መሬት ቢዚ ናት::

Hasen Injamo

05 Jan, 07:40


ብሄራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ግብይት መሠማራት ለሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ለጊዜው ፍቃድ መስጠት አቁሟል።

ባንኩ ለግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፍቃድ መስጠት ያቆመው፣ ካሁን ቀደም ፍቃድ የወሰዱ አምስት ቢሮዎችን የሥራ አፈጻጸም በቅድሚያ መገምገም ስለፈለገ መሆኑ ታውቋል።

Hasen Injamo

05 Jan, 05:37


አውስትራሊያ ላይ ተማሪዎች ሲያረፍዱ ለቅጣት ዳቦ ያለማባያ እንዲበሉ ይደረጋሉ:: ይህንን ቅጣት ላለመቀጣት ሁሉም ተማሪ በጊዜ ትምርት ቤት ይገኛል::
የአውስትራሊያን ተሞክሮ ወደ አፍሪካ ሲመጣ ግን አይደለም ተማሪዎች መምሕራንም ማርፈድ ጀመሩ::

(ከሌንጮ ገጽ ተገኝቶ የተቀመመ)

Hasen Injamo

04 Jan, 20:17


የዛሬ ሲሆኑ ከ10 ደቂቃ በፊት 5.2

Hasen Injamo

04 Jan, 18:31


አይ ሱስ

Hasen Injamo

04 Jan, 18:23


የሚሆነው አይታወቅምና ለጥንቃቄ ያህል:-
- ላፕቶፓችሁ ለማንሳት የሚመች ቦታ ብታደርጉ
- የትምህርትም ይሁን ሌሎች ወሳኝ ዶክመንቶችን ከቃጠሎም ይሁን መሰል አደጋ ለመቋቋም በሚያስችል ወይም ይዞ ለመውጣት በሚያመች ቦታ ቢሆኑ
- በተጨማሪም ስካን አድርጋችሁ cloud ላይ አድርጉዋቸው::
- የአፓርትመንት ነዋሪዎች ግሪል ስላሠራችሁ ለመስበሪያ የሚሆን እና ለመውረጃ የሚሆን ገመድ በአቅራቢያው ብታደርጉ ጥሩ ነው::

መንቀጥቀጥ በሚኖር ወቅት ከመንቀልቀል አንድ ቦታ በተለይ ቋሚ አካባቢ መሆን ይመከራል ተብሏል:: ፊልዴ ስላልሆነ የባለሙያዎችን ማድመጡ ጥሩ ነው:: የላይኞቹ ግን ተያያዥ ቃጠሎዎችና መታፈኖች ቢከሰቱ ለማለት ያህል ነው::

እኛ ሀገር የተለመደ ስላልሆነ ነው አዲስ የሆነብን:: እያሟረትኩ ወይም እያሸበርኩ አይደለም:: አደጋ ቢኖርም ባይኖርም የሚጠቅሙ ነገሮች ናቸው:: ዶክመንቶችን ስካን አድርጎ ጎግል ወይም አማራጭ ሰርቨር ላይ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው::

ድሮም ቢሆን ልጆቼን አሰለጥናለሁ:: አደጋ ከመጣ መስተዋቱን በዘነዘናም ይሁን ባገኛችሁት ነገር ስበሩት:: እንዳትራሩለት እላቸዋለሁ:: በሮችን ከቁልፍ ይልቅ መቀርቀሪያ እንጠቀማለን:: በደህና ጊዜ የሚያደናብር ቁልፍ በችግር ወቅት ሌላ ጉድ ነው::

Hasen Injamo

04 Jan, 15:53


እባብን ያየ በልጥ በረየ እንዲሉ የሲኖትራክ እንቅጥቃጤ በሬክተር ስንት ይሆን? ጂዖሎጂካል ሰርቬይ የሚባለው መሥሪያ ቤት ይህንን እንኳ አያውቅም ይሆን? ፕሮፌሰር አታላይን ጠይቁዋቸውማ:: የማግማ ይሁን የሲኖ መለየት እስክንችል የሲኖ ሰዓት እላፊ ቢታወጅ ባይ ነኝ:: ሲያቀብጠኝ የሞባይል app አውርጄ አሁን ከመሸ ሁለቴ ከአፋር ነው ብሎ አምባረቀብኝ:: 4.5 እና 4.8 ይላል:: Appፑን ዴሊት አድርጌ እተኛለሁ እንጅ ማን ሲባንን ያድራል?

Hasen Injamo

04 Jan, 14:52


ከውጭው ሀገርም ከውስጥም በስልክ በኢሜልና በመሴጅ "ይህ ነገር ሬክተር ስኬል ነው ወይ?" ብላችሁ በተደጋጋሚ ጠይቃችሁኛል:: በጣም እንዳሳሰባችሁ ተገንዝቤያለሁ:: ሆኖም ግን በምስሉ የሚታየው የሬክተር መለኪያ ሳይሆን የፕሮፌሰር አታላይ ስክሪፕቶ ነው::

በቅንፍ (ማንም ምንድነው ብሎ የደወለም የጠየቀም የለም:: ብዙ ሰው ፍርሃት ቢጤ ስለወጋው ለማስተንፈስ ነው:: ፕሮፌሰራችንም እንዳይቀየሙ:: ለጨዋታ ነው) ቅንፉ ተዘግቷል:: ስንጥቁ ግን ሰፍቷል::

Hasen Injamo

04 Jan, 14:09


ትናንትና ማታ ሲንቀጠቀጥ ያልሰማችሁ ዛሬ የመልስ እንቅጥቃጤ ሊኖር ስለሚችል በንቃት ጠብቁ:: እስካሁን በራሱ ሜዳ ነው:: ይሁን ተመችቶናል::

Hasen Injamo

04 Jan, 13:15


ኢትዮ ቴሌኮም ልዩ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን የሚልክበት መንገድ ቢያመቻች ጥሩ ነው:: መልዕክቱ ሲላክ ሁሉንም የስልክ ምልልሶችን አቋርጦ የሚገባ መሆን አለበት::

Hasen Injamo

04 Jan, 11:42


ሽሮም በእሳተ ገሞራ ሙድ መያዝ ጀመረ

Hasen Injamo

04 Jan, 11:29


የሆነ ሰው ባልተረዳኝ ጉዳይ በጣም ይከፋብኛል:: ምክንያቱም እኔ የተጣድኩበትን እሳት አያውቀውም:: ብነግረውም እሳቱ ምሥጢሬ ወይም የሌላ ሰው ምሥጢር ይሆናል:: አልያም መናገሩ ችግሩን ያወሳስበዋል በሚል ከውጪ የሚቀየምህ ከስር ደግሞ አጥብቀህ የተቀመጥክበት ነገር መሃል ሆነህ ሾልከህ ለማለፍ የምታደርገው ትግል አንተን ደነዝ ነገር ያስመስልሃል:: ገጀራነትህን ተቀብለህ እየተብሰለሰልክ ሕይወት ይነጉዳል:: አጃኢበቲ ዱንያ::
-----
ብዙዎቻችሁ ስለሚገጥማችሁ ብዬ ነው::

Hasen Injamo

04 Jan, 11:11


ቢጠቅም
- የውኃ መስመር ሊቋረጥ ስለሚችል የመጠጥ ውኃ,
- የእጅ ባትሪ
- ብድግ ሊደረግ የሚችል ልብስ
- አስፈላጊ ዶክመንትና መታወቂያ
- የኃይማኖት መለያ ቀለበት, ሙሰቢሃ ወይም መስቀል አንገት ወይም ጣት ላይ ማድረግ
- የአቧራ ማስክ ኪስ ውስጥ መያዝ
- ከፈን ወይም ጋቢ በአቅራቢያ ማድረግ አይከፋም::
- ንስሃ ለሁልጊዜ ይጠቅማል::

ምክንያቱም የኢትዮጵያው መንቀጥቀጥ ችግራችን አይቶ ከወር በላይ እያስጠነቀቀን ነው::
ለማሸበር ሳይሆን እንደው ቢሆንም ባይሆንም አይከፋም ለማለት ያህል ነው::

Hasen Injamo

04 Jan, 10:54


የእሳተ ገሞራ ከመከሰቱ በፊት መወሰድ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

በእሳተ ገሞራው ፍንዳታ መክንያት ከሚከሰቱ አደጎች ሰዎችን ለማዳን ከመኖሪያቸው ማስወጣት አስፈላጊ ሆኖ በሚግኝበት ሁኔታ ቤት መልቀቅ ሊኖር ስለሚችል ከመንግስት አካላት የሚሰጡ ትዕዛዞችን እና መልዕክቶችን በትጋት መከታተል።

ከቤት ልቀቁ ከተባለ የሚከተሉትን እቃዎች ቀድመው ያዘጋጁ፥-
• ደረቅ ምግቦችና የመጠጥ ውሃ
• ማስኮች
• አስፈላጊ መድሃኒቶች
• ፊት መሸፈኛ ሻርፖች
• ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍኑ ልብሶች
• ስልክ መረጃ ለመለዋወጥ
• የእጅ ባትሪዎች
• የመጀመሪያ እርዳታ መሳሪያ ኪቶች
• መነጽሮች
• ሬድዮ
• የጤና ባለሙያዎች ስልክ ቁጥር መያዝ
• እና የመሳሰሉት…

የእሳተ ገሞራ ከተከሰተ በኋላ መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የእሳተ ገሞራው ጭስ የሚደርስበት አካባቢ ከሆኑ ጭሱ የተለያዩ ጎጂ ጋዞችን የያዘ በመሆኑ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያደረጉ

በቤት ውስጥ ከሆኑ
👇👇👇
• ጭሱ እንዳይገባ መስኮቶችን እና በሮችን በመዝጋት ቤት ውስጥ መቀመጥ
• የመጠጥ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ውሃዎችን በደንብ መክደን
• እንስሳቶችም በጭሱ ምክንያት አደጋ ሊደርስባችው ስለሚችል በቤት ውስጥ በርና መስኮት ዘግቶ ማስቀመጥ
• በተለያዩ ተአማኒ ከሆኑ የመረጃ ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ መረጃዎችን በንቃት መከታተል
• የአየር ማቀዝቀዣ ፋኖችን ማጥፋት
• በቤት ውስጥ ከሰል አለማቀጣጠል
ከቤት ውጪ ከሆኑ
👇👇👇
• ወዳገኙት መጠለያ በመግባት መጠለል
• በጋዙ ምክንያት የአይን፣ የአፍንጫ፣ የጉሮሮ ማቃጠል ካጋጠሞት ጭሱ ካለበት ቦታ ወደ ቤት በመግባት እራስዎን ያርቁ።

ይህን አድርገው ማቃጠሉ ካላቆመ ለህክምና ባለሙያ ደውለው ማሳወቅ።
• የተቃጠለ አካል ካለ ወዲያውኑ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ
• ቅልጥ አለቱ ሊፈስ ወደሚችልበት ቁልቁለታማ ወደ ሆኑ ቦታዎች አለመሄድ
• ፊትን እና የተገለጠ የሰውነት ከፍሎችን መሸፈን፣ መነጽሮችንና የመተንፈሻ ማስኮችን ማድረግ
• የመኪና ሞተር ማጥፋት
• አቅመ ደካማ እና ህጻናትን መርዳት

Hasen Injamo

04 Jan, 10:29


ብዙ ሚስት ባለማግባቴ ተጸጽቻለሁ:: ጌታ ሆይ ጸጸቴን ተቀበል:: የሸይኽ ሲራጅን ሌጋሲ እናስቀጥላለን::
----
የጃዋር አልጸጸትም መጽሐፍ ሳነብ ብዙ ነገር እየበራልኝ ነው:: አያቱ 17 ሚስቶችን አግብተው ነበር::

Hasen Injamo

04 Jan, 09:52


ከሰም ስኳር ፋብሪካ 🥺 የመሬት መንቀትቀጡ ያደረሰው ጉዳት። አላህ በቃችሁ ይበለን::

Hasen Injamo

01 Jan, 11:53


ብሔራዊ ባንክ የባንኮችን የ14% የተጨማሪ ብድር ማርጅን ወደ 18% አሳድጎታል:: ከአምናው ጋር መጨመር የሚችሉት የብድር ከፍታ ማለት ነው:: እና 18% ሆኗል:: ዝም ብላችሁ መደፋፋት አትችሉም ዓይነት ነገር::

Hasen Injamo

01 Jan, 11:37


ኢትዮጵያ 132 ሚሊዮን ሕዝብ በመያዝ ከዓለም 10ኛ ሆናለች:: ኢትዮጵያውያን ሆይ ይቅር በሉኝ:: እንቅልፍ አበዛሁ መሰለኝ:: ለቀጣይ ዓመት 9ኛ ለመሆን በቀንም በማታም በሁለት ሺፍት በአራት አቅጣጫ ልጠምድ ነው::

Hasen Injamo

01 Jan, 11:28


ለጠቅ-ላላ ዕውቀት
ዶላር ብላክ ሰፈር በ140 እና 146 ብር መካከል እየተጫወተ ነው::

Hasen Injamo

01 Jan, 10:38


ወንድ ልጅ ከሴቶች ባልተናነሰ ዕድሜ ያሯሩጠዋል:: ዱንያ ሲያባርር ዘግይቶ ካገባ ልፋቱ ሁሉ ለሚስቱ ባል ነው የሚሆነው:: አንዳንድ ወንድ እኮ ከዘመዶቹ, ከጓድደኞቹና ከመንግሥት ጋር ተጣልቶ ብር የሚሰበስበው ለሚስቱ ባል ነው::

Hasen Injamo

01 Jan, 08:43


ሎጊቴክ ብራንድ ማውስ ከጥንቱ ከንጋቱ ከሉኮም ትሬዲንግ ግዙ:: በስሙ የተቀጠቀጡና የተጠፈጠፉ ብዙ ይኖራሉ::

ካዛንቺስ መናኸሪያ ጋር ሂዱ ወይም የሚከተለውን ስልክ ምቱ::
0982 926592

Hasen Injamo

01 Jan, 08:32


የምትፈልጋትን ዓይነት ሚስት ማግባት ከፈለግህ:-
ሴቶቹ ከመጣህበት ይልቅ ወደፊት የምትሄድበትን መንገድ ያያሉ:: መጻኢ ዕድልህን ይተነትናሉ:: ትናንትህን እርሳና ፊትለፊትህ ላይ አተኩር:: የምትፈልጋት ሚስት መንገድህ ላይ ታገኛታለህ::

><><><><><><

የምትፈልጊውን ዓይነት ባል ማግባት ከፈለግሽ:-
ያለፈው ታሪክሽ ያማረና የተጓዝሽው ኪሎሜትር ያጠረ ይሁን:: አሁንም ቢሆን funጅ ላይ አትቁሚ:: የሗላ ማየቻ ስፖኪዮሽን ተመልከቺ:: አንዳንዴም ዘወር ብለሽ እዪ:: እየጠራሽ ያለ አፍቃሪሽ ሊኖር ይችላል:: ጭቃ ነክቶሽም ከሆነ ወልውዪ:: ተወልወዪ:: (ያለፉ መሴጆቹን መርምሪ)

Hasen Injamo

01 Jan, 06:28


ከኦሎምፒያ ወደ ቡልጋሪያ
ሲኬድ አንድነት ስጋ ቤት ጀርባ
ቪስኮ ሪልኢስቴት

አፓርታማው የሚያካታቸው
🏠 2B+G+18 አፓርታማ
🏠 በወለል 3 ቤት
🏠 የግል የመኪና ማቆሚያ
🏠 2 አሳንሰር (ሊፍት)
🏠 ጀነሬተር
🏠 የከርሰምድር ውሃ ከበቂ የውሃ ታንከሮች ጋር
🏠 የደህንነት ካሜራ በየወለሉ
🏠 የቆሻሻ ማስወገጃ በየወለሉ ( Garbage shooter )
🏠 ለየቤቶቹ የግል ቴራስ
ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚውል የጋራ ቴራስ
🏠 የእንግዳ መቀበያ
🏠 ባለ3 መኝታ ከተጨማሪ የረዳት ክፍል ጋር
🏠 153 ካሬ እና 167 ካሬ
🏠 Semi-finished and Finished እንደ ፍላጎት
🏠 አከፋፈል ከ25% እስከ 100%
🏠 የግል ካርታ ስላለው በመሃል ላይ ወደ ሌላ ሰው ማዘዋወር የማይቸገሩበት (resale option) የተመቻቸለት
🏠 የአዲስ አበባ ሲቲ ሴንተር ውስጥ
🏠 ከኮሪደር ገባ ያለ
🏠 ዲጂታል የተናጠል ካርታ
🏠 ክሊራንስ የጨረሰ
🏠 ዛሬውኑ ስም ማዞር የሚችሉት
____
100% በ fully finished
በካሬ 105,000

Hasen Injamo

01 Jan, 06:26


ስለክሪፕቶከረንሲ እጅግ አሰልቺ እና የበዛ ጥያቄ ነው ያለው:: ፊያትን ያልገባው ክሪፕቶ አይገባውም:: የፊያት ምንነት የገባቸው የፒራሚዱ ጫፍ ላይ ነው የተቀመጠው:: የ1 ብር ፊያት ወደ ክሬዲት ሲቀየር ወደ 9 ብር ያድጋል:: አሁን ያለንበት ሥርዓት ይኸው ነው:: በክሬዲት ተቀፍድዶ መኖር:: ልታሰልመውም ልትጠምቀውም አይመችም:: አፈጣጠሩን ማወቅ የግድ ይላል::

ክሪፕቶከረንሲ የዚህ ተቀጥላ ነው:: የፊያት ሥርዓት የማይዳኛቸው ክፍሎችን የሚያዳርስና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ልሒቃን የተሠራ ነው:: ክሪፕቶከረንሲ ላይ የሚወሩ ነገሮች ብዙዎቹ ማታለያ ናቸው::

1) ክሪፕቶከረንሲ ለወንጀለኞች መሸሸጊያ ነው ተብሎ ብዙ ተወርቷል:: ይልቅስ ለወንጀለኛ ወጥመድ ነው:: ወንጀል ለመሥራት የብሔራዊ ባንክ ፊያት ኖት ምቹ ነው:: ምክንያቱም በእጅ ማዘዋወር ይመቻል:: ከሪከርድ ጀርባ ይዘዋወራል:: የንግድ ባንኮች ክሬዲት ንግድ ፈቃድና የቤት ካርታ ተይዞ የሚሠራ በመሆኑ ለወንጀል ብዙም አይመችም:: ክሪፕቶከረንሲ ግን የእያንዳንዱ ትራንዛክሽን ታሪክ በደንብ ለማወቅ ያስችላል:: ብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀም ማንም ሊያስወግደው አይችልም:: ከመጀመሪያው ኮይን ጀምሮ ያሉ ትራንዛክሽኖች trace back ማድረግ ይቻላል::

2) ኢንክሪፕትድ ማለትም ከዳር እስከ ዳር የተቆለፈ ነው ይባል ይሆናል:: አሁን ላይ የተሠሩ የኮምፒውተር ቺፖች እንኳንስ ክሪፕቶ ኢንክሪፕሽን ቀርቶ ሌላም የመፍታት ብቃት አላቸው::

3) የመሥራቹ አለመታወቅ:- በባንኮች ሲተዳደር የነበረ ማኅበረሰብ አስተዳዳሪ የሌለው የወርቅና የገንዘብ ቁፋሮ ተሳተፍ ተብሎ የደበቀውን ዶላር ወደ ባንኮች ይዞ መጣ:: ምናባዊ ወርቅ ለመግዛት የተደበቁ ዶላሮች ወጡ:: መሥራቹ ሳቶሺ ናካሞቶ ዐሳ ሲያጠምድ ሞቷል ተባለ:: ሆኖም ግን ሳቶሺ ናካሞቶ የአሜሪካ አስተዳደርና የባንከሮች ግሩፖች ናቸው::

4) የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘብ (Central Bank Digital Currencies- CBDC) ማለማመጃ ነው:: ሰዎችን ለ CBDC ባርነት ያዘጋጃል:: ትራዲሽናል የገንዘብ ዝውውርን ወደ ዲጂታል ዶላር መቀየር አስፈልጎ ነበር:: ስለዚህ በተለይ ወጣቱ ይህንን ሥርዓት በክሪፕቶከረንሲ በደንብ ተለማምዶታል:: ክሪፕቶከረንሲ በቀላሉ ወደ ምርትና አገልግሎት ስለማይቀየር የግድ የባንኮች ዲጂታል መገበባያዎች ይለውጡዋቸዋል::

5) ያልተማከለ በመሆኑ ማዕከላዊና ፒራሚዳዊ የባንክ አሠራሮችን ያስወግዳል ተብሎ ነበር:: ግን ትናንሽ ቆሮሶዎችና ሽሪምፖች በግዙፍ ዐሳነባሪዎች የሚዋጡበት የሀብት ፒራሚድ ሆነ:: የመደበኛው ባንክ ዐሳነባሪዎች የክሪፕቶውን እየዋጡ ያጠፉዋቸዋል:: ከሀብት ክፍፍል ይልቅ ሀብቶች ከድሆች ሀገራት የሚሸሹባቸው መንገዶች ነው:: 80% ቢትኮይን በ2% ዋሌቶች የተያዘ ነው:: ዶላሮች ከደሃ ሀገራት ይወጣሉ እንጂ የረባ ምንዛሪ ተመልሶ አይመጣም:: ይህንን በመ-ገንዘብ መጽሐፌ ለማብራራት ሞክሬያለሁ::

6) የሚጠቀመው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይልና ኮምፒዩተሮቹ የሚያመነጩት በካይ ጋዝ ለመደበኛ ባንኮች ማመሳከሪያነት እየዋለ ነው::

7) መንግሥት ሲፈልግ ብዙ ፊያቶችን ፓምፕ አድርጎ ወይም የብር ኖቶችን ቀይሮ የማይፈልገውን ክፍል እንደሚያከስረው የክሪፕቶ ውስጣዊ ሰዎችና መሥራቾች የ Pump and dump አካሄድ በስፋት ይጠቀማሉ:: ትናንሾችን እየገፈተሩ ያስወግዳሉ:: ሁሉም ክሪፕቶከረንሲ መሥራቾች አሉት:: እንዴት እንደሚመሠረት ጎግል አድርጉ:: መ-ገንዘብ ላይ ለመጠቆም ሞክሬያለሁ:: ከሰማይ ዱብ ያለ አይደለም:: በአክሲዮን ነው የሚቋቋመው:: ሆኖም ግን ኃላፊነት አይወስዱም:: ኃላፊነቱ በብሎክቼይኑ ላይ የተወሰነ የማቋመር ማኅበር ነው::

8.) የወሬው ያህል የክፍያ ሥርዓት ሊሆን አልቻለም:: በዓለም አቀፍ ግብይት ላይ ያለው ድርሻ ኢምንት ነው::

9) በወሬ የሚሞቅና የሚበርድ, የሚሰቀልና የሚወርድ እጅግ የሚላጋ ኢንቨስትመንት ነው::

10) ምንም ዓይነት ተጨባጭ ወርቅም ይሁን ወረቀት የሌለው ምናባዊ የቁጥር ድወራ ነው::

11) ምንም ዓይነት የሕግ ከለላ የለውም:: ፓስወርድ ቢጠፋ የሚጠየቅ አካል የለም::

12) የተሻለ ኮምፒውተር እና የተሻለ ሶፍትዌር የያዘ የተሻለ ስለሚያገኝ እንዲሁም ለተራው ሰው ብዙም ግልጽ ባለመሆኑ ከሚያተርፉት እየተመቱ የሚወጡት በእጅጉ ይገዝፋሉ::

13) ለመድበኛ ባንኮች ስጋት የሚሆኑ አይደሉም:: ምክንያቱም የባንኮቹ ኤሊቶች የሚዘውሩት ብቻ ሳይሆን ወደ ምርት እና አገልግሎት ለመለወጥ የግድ የባንኮችን መስኮት ይጠቀማል:: እንደ ባይናንስ ያሉት ለቀጥታ ክፍያ ይውላሉ ቢባልም ከባይናንስ ጀርባ ያሉት ደግሞ የካናዳ ንግድ ባንኮች ናቸው::

በመጨረሻም ክሪፕቶከረንሲም ይሁን ፊያት ከረንሲ ከመያዝ ተጨባጭ ሀብት መያዝ ይሻላል:: በያዛችሁት አንጡራ ገንዘብ ተጨባጭ ሀብት ያዙ:: ከዚያ ሀብቱን አስይዛችሁ በሞኞች ገንዘብ ነግዱ::

Hasen Injamo

01 Jan, 05:01


ለምንድነው ሴት አመራሮችን የሾማችሁት?

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምላሽ:- ሴት የላከችው ጎል አይፈራም

Hasen Injamo

01 Jan, 04:58


በ48 ሰዓታት ውስጥ 39 ጊዜ መሬት ተንቀጥቅጧል ተብሏል:: ምእመኑም ተላምዶ በዜናዎቹ ስር love ❤️ ሪአክት ያደርጋል:: ሞትንም እንዲህ ነው የለመድነው:: ሙሉ ክፍለሃገር ሕዝብ ቢያልቅ ምንም የማይመስለን ደረጃ ደርሰናል::

Hasen Injamo

31 Dec, 16:02


የኢትዮጵያ የኢስላሚክ ባንኮች እጣ ፈንታ
===============================

ባለፈው የሂጅራን ባንክ አመታዊ ሪፖርት ዳስሼው ነበር። በዚህ ሳምንት የወጣውን የዘምዘምን አመታዊ ሪፖርት አየሁት። ያው ነው። ሁኔታዎቸ‍ በዚህ ከቀጠሉ እነዚህ ባንኮች ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የካፒታል ጣሪያ በእርግጠኝነት በጊዜ ገደቡ ማሟላት አይችሉም።

ኢስላሚክ ባንክ ለምን ያስፈልጋል?
======================+
ፈረነንጆቹ ‘Debt is cheapest form of financing’ ይላሉ። በአለም አቀፉም ደረጃ ወለድ አልባ ተብሎ በሚጠራው ባንክ ሲስተም በብዙ ምክንያቶች የብድር ዋጋው ይጨምራል። ይሁን እንጂ ሙስሊሞች በእምነታቸው ምክንያት ጭማሪውን ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።

በአውሮፓ በተደረጉ ጥናቶች የሙስሊም የቤት ባለቤቶች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ይህን ክፍተት የተገነዘቡት ግዙፎቹ አለም አቀፍ ባንኮች ኢስላሚክ ዊንዶ ከፍተው “ሙስሊም ፕሪሚየም” ጨምረው Sharia-compliant ብለው ያበድራሉ

What is Muslim Premium?

በፋይናንሱ ቋንቋ ሙስሊሞች በዕምነታቸው ምክንያት ወለድን ሸሽተው ለመበደር የሚከፍሉት ተጨማሪ ክፍያ ነው።

ዋናው ጉዳይ በእምነታቸው ምክንያት ወለዱን የሚሸሹ ሰዎች ፋይናንሲንግን ካልተጠቀሙ ከቢዝነሱ እየተገለሉ ይሄዳሉ። ሌላ አማራጭ መንገድ እስኪበራልን ያሉትን ማጠናከር ግድ ነው። በአውሮፓ በተለይ በእንግሊዝ ሸሪአን መሰረት ያደረጉ አስደመሚ “ኢስላሚክ የፊንቴክ ካምፖኒዎች” እንደ አማራጭ እየመጡ ነው። እኛ ገና ነን

አሁን ዳዴ የሚሉት ኢስላሚክ ባንኮች ካልተዋሃዱ ምን ይፈጠራል?
================

በነገራችን ላይ ለብሄራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች አንድ ናቸው ምንም የተለየ የህግ ማዕቀፍ የላቸውም

1️⃣ ለኮንንቬንሽናል ባንክ ሸጠው ለመውጣት ይገደዳሉ።

2️⃣ የአንዱ መደበኛ ባንክ ኢስላሚክ ዊንዶ ይገዛቸዋል።

ይህ ሟርት አይደለም ። በመሀከለኛው ምስራቅ እና በኢሲያ ተደጋግሞ የተከሰተ ነው። ኮንቬንሽናል ባንክ ኢስላሚክ ባንክን ይገዛል። በተቃራኒውም ይከሰታል። በምኖርበት ሀገር ኮንቬንሽናል ባንክ ወደ ኢስላሚክ ሲቀየር አይቻለሁ፣ ኮንቬንሽናል ባንክ ከኢስላሚከ‍እ ባንክ ጋር ተዋህዶ ዘርፉን ሲቀይር አይቻለሁ፧ ተከፉል ካምፓኒ መደበኛውን የኢንሹራንስ ካምፓኒ ሲገዛ አይቻለሁ። Just it is operating model.

ማጠቃለያ
========
በተናጠል የምትሮጡ የሀገራችን ኢስላሚክ ባንኮች ሆይ! ለአደራጆቹ ጥቅም ሳይሆን ሙስሊሙ ከቢዝነስ እንዳይወጣ እና ጥሩ አማራጭ እንድሆኑ ታስፈልጋላችሁ።

አሁን ከፊታትሀ‍ኡ ያለው አማራጭ ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ሆኗል።

The deadline is June 2026

Hasen Injamo

31 Dec, 14:08


የባንኮቹን አክሲዮን እንግዛ ወይ ለምትሉ እስላሞችና ሙስሊሞች:-

ያለፈው አምስት ዐመት ያልኳችሁን ነው የምደግመው:: አክሲዮን ማለት ብርህን ለጀማዓው ሰጥተህ ይሠሩና ያተረፉ ወቅት ላይ ከጀማዓው ጋር ተዘርዝሮ የሆነ ቅንጣቢ ይሰጥሃል:: አክሲዮን በትርፍ ገንዘብ የምትደበርበት እንጂ እንደ ቋሚ ሥራ የምትይዘው አይደለም:: ገቢህ quadrant four የሚባለው ምድብ አራት ጋር ሲደርስ እንደ መደበኛ ሥራ ልትይዘው ትችላለህ::

ከአምስት ዐመት በፊት የአንድ አክሲዮን ዋጋ 50,000 ብር አድርገው ገድበውት ብዙ ሰዎች እንዳያመልጣቸው ተበድረው ሁላ ሲገዙ አስታውሳለሁ:: አምስት ዐመት ብትጠብቅ በ5,000 ብር ይለምኑሃል ብዬህ ነበር:: አስታውስ:: ተሯሩጦ የቀደመህ ጎረቤትህን ጠይቀው:: ስለዚህ አሁንም ቢሆን አትሩጥ:: ከገዛህም ትርፍና ኪሳራቸውን እንዲሁም ያለፉት ዓመታት ሒደታቸውን እይና ተደበር:: ቆጣቢ ከምትሆን ባንከር ብትሆን ይሻላል:: ተበዳሪ መሆን ግን ዐይነተኛ መላ ነው ስልህ:: ሳትበደር አትደር ያልኩህ ዓየሩን እያየህ ነው:: አየሩ ከተመታ ልትመታ ትችላለህ::

Hasen Injamo

30 Dec, 16:41


የአንድ ሀገር የመገበያያ ገንዘብ ዋነኛ መሠረቱ ብሔራዊ ባንክ ሳይሆን የኮሎኒያሊዝምን ድንበር ነው:: ድንበር ከሌለ የየሃገራቱ መገበያያ ክፍፍሎሽ አይኖርም:: አይ ኤም ኤፍ የራሱ መገበያያ የለውም:: የሚጠቀመው የኮሎኒያሊስቶቹን ቢል ነው:: ድንበር ተሻግረው የትኛውንም ምርትና አገልግሎት መውሰድ ይችላሉ:: ምርት ያለው ሰው (ባሪያ) ከማመጽ ይልቅ ፈንድቆ ይሰጣቸዋል:: ወርቅና ብር ግን ይህንን የኮሎኒያሊዝምን የድንበር ክፍፍሎሽ እንኳ አያግዳቸውም::
_______
ለሙስሊሞች:- ዘካም ይሁን ሌሎች ኢስላማዊ ገንዘብ ነክ ነገሮች በዘመንና በቦታ በማይገደቡ ቁሶች ላይ ነው የተደረጉት:: ሶላት በፀሓይ, ጾምና ሐጅ በጨረቃ ነው የሚለኩት:: የማንም መንግሥት ካላንደርና ሰዓት አይገድባቸውም:: ፋይናንሱን በኮሎኒያሊስቶች በተገደበ ድንበር ላይ በተገደቡና ማኒፑሌት በሚደያደርጉዋቸው መገበያያዎች ከገደብከው እራስህን በራስህ ነው እስር ቤት የምትከተው:: በእነርሱ የባርነት ቀንበር መደሰት መብትህ ነው:: የእስልምና መስመሩ ላይ የቆምነውን የተለየ ነገር ያመጣን እንዳይመስልህ:: አንተ ነህ መንገድ የሳትኸው:: ይህ ለክርስቲያኖችም ይሠራል:: በእርግጥ እነርሱ ብዙም አይጃጃሉም:: ከዘመናት መከራ ተምረዋል::

Hasen Injamo

30 Dec, 14:43


ስሄድ ይቆጭሃል ማለት የሚችለው ገንዘብ ብቻ ነው:: ሌሎቻችሁ ግን ውረዱ:: ሂዱ በቃ:: ጥርግ በሉ::

Hasen Injamo

30 Dec, 12:59


84% ገበሬ ባለበት ሀገር የመንግሥት ንግድ ባንክ 99.8% ብድር ያቀረበው ለከተሜዎች ነው:: በእርግጥ ንግድ ባንክ ተብሎ ተቋቁሞ ለግብርና ስጥ አይባልም:: ግብርናን የተመለከተና አሁን ያሉ ባንኮችን ልክ እንደ እቁብ የሚያደርግ የኢትዮጵያ ግብርና ባንክ ያስፈልጋል:: ምክንያቱም እሴት ተኮር ስለሆነ ግሽበትን ተቋቁሞ ነው የሚሠራው:: የምንዛሪ ምንጭም የግብርና ባንክ ይሆናል:: ሌሎች ባንኮች ይሰግዱለታል:: ABE.

Hasen Injamo

30 Dec, 12:45


ሎጊቴክ ብራንድ ማውስ
ካዛንቺስ
በጅምላና በችርቻሮ
ገዝታችሁ ኮምፒውተሩን አማስሉ:: ይወጠውጠዋል አይገልጸውም:: እዚህ ቁጭ ብለህ ማርስ ላይ ክሊክ ማድረግ ሁላ ትችላለህ:: የኤለን መስክ ማውስ በሉት:: (ትንሽዬ ግነት አለው)::

ስልክ: 0982 928592

Hasen Injamo

30 Dec, 12:42


ልቀቀኝ እኔን ብሎ ጥንቁቅ
ልቀ ቀ ኝኝኝኝኝ

Hasen Injamo

30 Dec, 12:29


ጫት የማትቅሙም የምትቅሙም ሰዎች በሆኑ ወራት አንዴም ቢሆን እንኳ የሞቲቬሽናል ቪዲዮዎችን ብታዩ እመክራለሁ:: የሞቲቬሽናል (አነቃቂ) ምክሮችና ተሞክሮዎችን መናቅ ተገቢ አይደለም:: ጥቅስ ብዙዎቻችን ላንወድ እንችላለን:: ጥቅሶችን እንድንጠላ የተደረግነውም በሌላ ጥቅስ ሲሆን አነቃቂ ምክሮችን እንድንንቅ የተደረግነውም በሌላ አነቃቂ ንግግር ነው:: ሁሉም መንቃት ይፈልጋል:: በተቃራኒው ማደንዘዝ መቻል እኮ ትልቅ ማደንዘዣ መርፌ ይፈልጋል::
(ዛሬ ልቃም እንዴ?)

Hasen Injamo

29 Dec, 16:58


ምናልባት ባንታገስ ኖሮ እጅግ በጣም ያማረ ሕይወት ልንኖር እንችል ነበር:: መታገስና መደንዘዝ አቀላቅለን ሊሆን ይችላል::

(ከሲራጅ ተኮርጆ የተሻሻለ)

Hasen Injamo

29 Dec, 11:06


በዚያኛው ፌስቡክ አካውንት ድሮ ከጻፍኳቸው ውስጥ:-
የወለድ ነጻ ባንክ ለመክፈት ምንም ትግል አይፈልግም:: ሙስሊም ያልሆኑት ጥቅሙን ያወቁ ቀን ሙስሊሙ wrongly እንዲገባበት ያስገድዳሉ:: ምክንያቱም ለሙስሊሙ ጉዳት የሆነን ነገር ላይ ይጣደፋሉ:: ይጠቅማል ብለው ያሰቡትን ለማደናቀፍ ግን በተባበሩት መንግሥት ጭምር አጀንዳ ያስይዛሉ:: ሙስሊሙ የፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ ለመንቃት ከ50 ዓመታት በላይ ይፈልጋል:: ይህኛው ትውልድ ሞቶ ካላለቀ የመንቃት አዝማሚያ የለውም:: እንደውም ምን ምን የቅርንጫፍ ስም እንደሚሰይሙ ሁላ ተንብዬ ነበር:: ያልኩት የቀረ አለ?

ምርጥ የሆነ የኢስላማዊ የፋይናንስ ሥርዓት እኮ አለን:: በአራቱም መዝሃብ ምዕራፍ ተሰጥቶት ሁሉም ደረሳ ይማረዋል:: እንዴት ያለ ፍትሓዊ መሰላችሁ:: ወላሂ:: ሸሪዓን አምርሮ ከሚጠላ ወገን ሸሪዓዊ የፋይናንስ ሥርዓት መጠበቅ የዋህነትም ጅልነትም ነው:: የወለድ ነጻ ባንክ ተብሎ በየቦታው በመስኮትም በሉት በግል የሚቋቋመው ትክክለኛውን የሸሪዓ የግብይት እና የፋይናንስ ሥርዓትን ለማጠልሸት ነው:: ሪባ መሠረታዊ ክልከላው "በደልን" ለማስወገድ ነው:: የወለድ ነጻው ግን ከመደበኛው በባሰ ሙሉ ሪስክ ለሙስሊሙ ያሸክማል:: በደል በጣም ሲጨምር እንዴት ብሎ ነው ከሪባ ነጻ የሚሆነው?

አጭር ግንዛቤ:- በሸሪዓ ሪባ እና ታክስ የለም:: በተቃራኒው የዚህኛው (ካፒታሊዝም) የፋይናንስ ሥርዓት መቆሚያ ደግሞ ሁለቱ ናቸው:: አንዱን ካንዱ ነጥለህ ማየት አትችልም:: ታክስን አልከፍልም ማለት አትችልም:: በሲስተም ታክስ ላለመክፈል ከፈለግህ ወለዱን አብዝተህ ስትጠቀም ሁለቱም ይጣፋሉ:: ብዙ ወለድ ማለት አነስተኛ ታክስ ማለት ነው:: ፒራሚዱን እያጠበብክ ስትወጣ የምትከፍለው ታክስ ዜሮ ይሆናል:: ወለድና ታክስ ይበላላሉ:: ይህንን ለማወቅ ግን እኔ ጋር ለወራት መሰልጠን ይጠበቅባችሗል::

Hasen Injamo

27 Dec, 16:16


የአሜሪካን 1 ዶላር በኢትዮጵያ 1 ብር የማይቀየርበት ምክንያት ያልገባችሁ ሰዎች ይህኛው ይበልጥ ያስረዳችሗል

Hasen Injamo

27 Dec, 13:16


ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ 5ኛ ናት ይባላል:: 215 ሚሊዮን ይሆናሉ:: ቀንድ እና ጅራት በሌላቸውም ብንቆጥር ደረጃችን እንደዚያ ይመስለኛል:: ምክንያቱም ይህኛው ፎቶ ብር (Silver) ወይም የብር ምትክ ነው ብሎ ያምናል:: ወንድሜ ከጋዜጣ ያልተሻለ ኩፖን ነው:: 1944 ላይ አሜሪካና እንግሊዝ ምእመኑን ወግተው አሳምነውት ነው:: ብልጦች ግን በ90 ሚሊዮን ቀንድና ጅራት በሌላቸው "በሃኢሞች" ቁጠባ ዞረው ንብረታቸውን ይገዙና መልሰው ይሸጡላቸዋል:: ቀንድና ጅራት ከሌለህ ፖስቱ ይገባሃል::

Hasen Injamo

27 Dec, 09:23


የዚህን ነሺዳ ትርጉም የሚያውቅ:: ዛሬ በዚህ ልቅም አስቤ ነበር::

Hasen Injamo

27 Dec, 09:04


ይህ ማውስ 🐁 በምንም ዓይነት መርዝ አይሞትም:: አትድከሙ:: ገዝታችሁ ተጠቀሙ:: በባለሙያ የተመሰከረለት:: Logitech ይሰኛል::

Addራሻ:- ካዛንቺስ መናኸሪያ ጋር ረድኤት ሕንጣ 1ኛ ፎቅ
ቢልቢሌ:- 0982 926592

Hasen Injamo

27 Dec, 08:55


"የባንክ አማራጭ የተመቻቸላቸው" የሚባሉ ሪል ኢስቴቶች ጋር ከመክፈላችሁ በፊት የተመቻቸበትን ባንክ እና ከባንኩ ጋር ያካሄዱትን ውል ተመልከቱ:: ምክንያቱም የሚገነባ ቤት ቀርቶ ተገንብቶ የሚከራየውም ለባንኮች ምናቸውም አይደለም:: በአሁን ወቅት ዶላር እንኳ እያመጣህላቸው ካዝናቸው ላይ የኢትዮጵያ ብር የለም:: ገና የሚገነባ ቤት ላይ የባንኮች ጥቅም ምንድነው? ምንም! ገንቢው ባለው የሌላ ሥራ ግንኙነት ካርታውን አስይዞ ሊበደርና ቤት ፈላጊዎች ያንን ብር ሊከፍሉለት በማስታወቂያ ሊያግባባ ይችላል:: ባንኮችም ቅድመ ክፍያውን ይፈልጉታል:: ምክንያቱም ከወለድ ነጻ ቁጠባ ስለሆነ ባንኩም ሽፋን ሊሰጥ ይችላል:: ልክ ቀሪ ክፍያ ጋር ስትመጡ ነው ጉዶችና ባዶች የሚወጡት:: Even ስም ሊዞር ወደ ሰነዶች ማረጋገጫ (ውልና ማረጋገጫ) ሲኬድ መአት ጉዳይ ይታወቃል:: በግሌ ዕቃ ሽጬ እና ቼክ ተጽፎልኝ እንኳ የባንክ “Your account is credited by … የሚል መሴጅ ካልመጣ እንደ ሽያጭ አላየውም:: ክሊራንስ አልቆ ካርታው በስማችሁ ታትሞ እስካልወጣ ድረስ ማማጥ ነው:: ከፊል ክፍያ ከፍላችሁ ስለሆነ ብሩም ያሳዝናችሗል:: መልስልኝ ብትሉት ቢመልስ እንኳ የውል ማፍረሻ ቆርጦ ነው:: ሳይቆርጥ ቢከፍላችሁም ግሽበት በልቶታል:: ርካሽ ስለሆነ ብቻ አትንገብገቡ:: ዝርዝሩን አንብቡ:: The devils are in the details ይባላል:: ሸይጧኑ ያለው ዝርዝሩ ውስጥ ነው እንደማለት::

Hasen Injamo

27 Dec, 08:00


ኢትዮጵያ የምታድገው በንግድ ባንኮች አይደለም:: ንግድ ባንኮች ሥራቸው ንግድ በመሆኑ ለግብርናም ይሁን ለኢንደስትሪው ባለማበደራቸው መወቀስ የለባቸውም:: ከዚህ በፊት እንዳልኳችሁ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጠቅልሎ ኢንደስትሪ ባንክ ቢሆን የሚል ነበር:: አሁን ትድድሩ ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሄዷል:: ጥሩ ነው:: ስለዚህ እራሱን የቻለ የግብርና ባንክ (ABE) መቋቋም የግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን::

Hasen Injamo

27 Dec, 07:51


ይህንን ስሜት ሳላይ በመማሬ አዝናለሁ

Hasen Injamo

26 Dec, 11:25


በአዲስ አበባ በመኪና ሽያጭ ላይ ከፍተኛ ግብር ተጥሏል፣ ነጋዴዎች የባንክ ሂሳባቸው እየታገደ ነው

ዋዜማ- የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ በመኪና ሻጮች ላይ ከፍተኛ የገቢ ግብር መጣሉን እና ነጋዴዎች መክፈል ባለመቻላቸው የብዙዎችን የባንክ አካውንታቸውን ማሳገዱን ዋዜማ ሰምታለች።

ነጋዴዎቹ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ዓመታዊ የገቢ መጠናቸውን ለማሳወቅ ወደ ወደ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሲያመሩ፣ ቢሮው ለኹሉም የተሽከርካሪ ዓይነቶች የራሱን መሸጫ ዋጋ እንዳስቀመጠ እና በዚያ መሰረት ግብር መክፈል እንዳለባቸው እንዳሳወቃቸው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት አሁን 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚሸጥን አውቶሞቢል ቢሮው 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የተመነው ሲሆን፣ ገበያ ላይ በስፋት ያለችውን እና በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር አማካኝ ዋጋ እየተሸጠች ያለች BYD የተሰኘች መኪና ቢሮው 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ተመን አውጥቶላታል።

11 ሚሊዮን ብር የሚሸጠው ቶዮታ አውቶሞቢልም በገቢዎች የተቆረጠለት ዋጋ 16 ሚሊዮን ሆኗል።

ስለሆነም ነጋዴዎች 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በደረሰኝ ለሸጡት መኪና ግብር የሚታሰብባቸው 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር እንደሸጡት ተደርጎ ነው።

ይህ መመሪያ በነጋዴዎች ውይይት ያልተደረገበት፣ ለሕዝብም ይፋ ያልተደረገ ከመሆኑ በላይ፣ ነጋዴዎች ስለመመሪያው የሰሙት ግብር ለመክፈል ወደ ገቢዎች ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ነው።

መመሪያው የአዲስ አበባ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን የመኪና ሻጮች ብቻ የሚመለከት ሲሆን፣ ከክልሎች ፈቃድ አውጥተው አዲስ አበባ ውስጥ መኪና የሚሸጡትን እና በፌደራል የተመዘገቡ ሻጮችን አይመለከትም።

100 ሚሊዮን ብር ግብር የተጠየቁ ነጋዴዎች አሉ ያሉን አንድ የመኪና ሻጭ፣ ከዚህ ቀደም ግብር የምንከፍለው ከአንድ መኪና ትርፍ ከ12 እስከ 15 በመቶ ነበር ሲሉ ገልጸው፣ አሁን የተጣለው ግብር ሶስት እጥፍ ገደማ ጨምሮ ወደ 35 በመቶ ማደጉን ነግረውናል።

ሌላ ነጋዴ ደግሞ፣ አሁን የተጣለብን ግብር ከአጠቃላዩ የመኪናው ሽያጭ 45 በመቶ የሚሆን ነው ሲሉ ጠቅሰው፣ ለምሳሌ አንድ መኪና 10 ሚሊዮን ብር ብሸጥ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለገቢዎች እከፍላለሁ ብለዋል።

ነጋዴዎች እንደሚሉት ይህ መመሪያ የመኪና ገዥዎች ላይም ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር መኪና የገዛ አንድ ግለሰብ ስም ለማዛወር ወደ መንገድ ትራንስፖርት ሲያቀና፣ የሚጠበቅበትን 2 በመቶ ክፍያ የሚከፍለው መኪናውን 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር እንደገዛው ተቆጥሮ ነው። መንገድ ትራንስፖርት ከገቢዎች ቢሮ ነው ትዕዛዝ የደረሰኝ የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን፣ ገዥዎች ደግሞ መኪናውን ወደ ሸጠላቸው ነጋዴ ተመልሰው ብር መልሱልን እንደሚሉ ነጋዴዎች ነግረውናል። ሆኖም ደረሰኝ የተቆረጠ በመሆኑ ገንዘባቸውን ማስመለስ አይችሉም።

ያናገርናቸው ሶስተኛው ነጋዴ፣ የቢሮውን ኃላፊዎች ስንጠይቃቸው “መንግስት ገቢውን ለማሳደግ ነው ያወጣው እቅድ ነው” ይሉናል ሲሉ አንስተው መመሪያው የተዘጋጀውም፣ ነጋዴዎች በጥቁር ገበያ ሽያጭ ያከናውናሉ በማለት እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲሁም የወቅቱን የዋጋ ግሽበት ከግምት ያስገባ ዋጋ ገቢዎች ማዘጋጀቱን ለነጋዴዎች እንደተነገራቸው ነግረውናል።

ነጋዴዎች የተጣለብንን ከፍተኛ ግብር መክፈል አንችልም በማለታችን የባንክ አካውንታችን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ታግዷል ሲሉ ገልጸው፣ በዚህ የተነሳ ወደብ ላይ ያሉ መኪኖችን ማስገባት አልቻልንም፣ የሰራተኛ ደሞዝ መክፈል፣ ጉምሩክ ላይ የተያዙ ዕቃዎቻችን መረክብ እና መሰል ስራዎችን መከወን አልቻልንም ብለዋል።

ነጋዴዎቹ መመሪያው በፍትህ ሚንስቴር ያልጸደቀ በመሆኑ በፍርድ ቤት እንዲታገድ ብናደርግም፣ የገቢዎች ቢሮው “ዕግዱን አልቀበልም” ብሏል ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

ነጋዴዎቹ ለተጣለባቸው የተጋነነ ግብር መንግስት እልባት እንዲሰጣቸው ጠይቀው፣ መመሪያው የአዲስ አበባ ንግድ ፈቃድ ባላቸው ላይ ብቻ መተግበሩ የበለጠ ግራ አጋብቶናል ይላሉ።

ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ ያወጡ የመኪና ሻጮችን በሙሉ ኦዲት ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡንም ዋዜማ ተረድታለች። አሁን ላይ ተግባራዊ መደረግ የተጀመረው መመሪያው ሚያዚያ 2015 ዓ.ም የወጣ ነው።

ዋዜማ የተመለከተችው ይሄው መመሪያ፣ በከተማዋ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው የአዳዲስ ተሽከርካሪ ሞዴሎች ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በግብር ከፋዮች ዘንድ የሚቀርበው ደረሰኝ ከወቅታዊ ትክክለኛ ዋጋው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ መንግሥት ከዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ እያጣ መሆኑን በጥናት እንደተረጋገጠ ይገልጻል።

በዚህም መመሪያው የመዲናዋን የመኪና ሽያጭ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ለመወሰን የሚያስችል የቢሮውን ስሌት/አሰራር የያዘ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል።

Hasen Injamo

26 Dec, 09:36


እዚያ ሰፈር ለእኔ መልስ ከመስጠታችሁ በፊት ጮርሳቹ አንብቡ ወይም ለጎረቤትም ቢሆን አስነብቡ:: የመጀመሪያውን ሦስት መስመር ወስደው ብቻ ሲተቹ አይቼ ነው:: ከገጠማችሁ ለጠቅላላ ዕውቀት ለማስታወስ ያህል ነው::

Hasen Injamo

26 Dec, 08:25


የወለድ ነጻ የተባለውን ጨምሮ አሁን ያለንበት የገንዘብና የባንክ ሥርዓት ትክክል ናቸው ብለህ ከወሰድክ ክርክርህ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከሥርዓቱ ጋር ነው:: በተለይ ባንኮች ዘንድ በተግባር ያለው የወለድ ነጻ አሠራር እና ሲጋራ ሻጭ የሚጋሩዋቸው ነገሮች አሏቸው:: ሁለቱም ለደንበኞቻቸው አያዝኑም:: ደንበኞቻቸውን አማቅቀው ይገ^ድላሉ:: መሞት መብታችሁ ቢሆንም ቅሉ አሟሟቱ ግን ለአላህ ተብሎ ሳይሆን ከዕውቀት ማነስ ነው::

Hasen Injamo

26 Dec, 08:09


✍️ የባንክ አሠራር እየጠፋና በሌላ ሥርዓት እየተተካ ሲሆን ከባንክ አሠራሮች ውስጥ ቶሎ የሚከስመው የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ነው:: ምክንያቱም ከእስልምና የግብይት ሕጎች ማፈንገጡ ብቻ ሳይሆን ከበደል አኳያ ሲመዘን ከመደበኛው ስለሚከፋ, የአገልግሎት አሠጣጡ ይበልጥ የተወሳሰበና 100% ሪስክ ሕዝቡ ላይ ስለሚጫን ነው::

✍️ በማበደርም ይሆን በቁጠባ ወቅት ባንኮች እራሳቸውን ከስጋት ነጻ ያደርጋሉ:: በምንም ዓይነት ሁኔታ ስጋትን (risk)ን አይጋሩም:: ይህ ከሸሪዓው በተቃራኒ ነው:: ሕዝቡ ሲቆጥብም 100% ግሽበት ይሸከማል, ሲበደርም ቀድሞ የመክፈል ጥቅም ይነፈጋል:: ቀድሞ ቢከፍል የወደፊቱንም የብድር ወቅት ወለድ ይከፍላል::

✍️ የእንግሊዝኛውን interest ወደ እንግሊዘኛው markups መቀየሩ የተለየ አያደርገውም::

✍️ ብር ፈልጎ ባንክ የሄደን ሰው እቃ ሻጭ ፈልግና ለእርሱ ከፍዬልህ እቃውን ሽጠህ ብሩን ውሰድ ስትለው ተበዳሪው ብዙ ጥልፍልፎሽ ውስጥ ይወድቃል:: እቃውን ሲገዛ ወይም ፕሮፎርማ ሲያመጣ ደግሞ ቫት እና የንግድ ትርፍ ጭምር ያካተተ በመሆኑ ከወለድ ነጻ ተበዳሪ ቫትና የንግድ ትርፍ ተጨምሮበት ይበደራል:: ከተበዳሪነት ወደ consumerነት ይቀየራል::

✍️ በሀገራችን የወለድ ነጻ ቆጣቢዎች የብሔራዊ ባንክ ከለላ የላቸውም:: ቁጠባ ያመጣሉ እንጂ የግሽበት ማካካሻ ተነፍገዋል:: እኛ ሀገር ላይ የባንክ አካውንታቸው በማንኛውም ወቅት ባንኩ ወዳመቸው የባንክ ሥርዓት ይቀየርባቸዋል:: ብሔራዊ ባንክ ይህንን ተከታትሎ የሚይዝበት ሥርዓት አላዳበረም:: ኦዲት ሳይደረጉ ሁለት "የይርጋ" ዘመናት አልፈዋል:: አሁን ኦዲት ቢያደርግ እንኳ ይርጋ ሊያግደው ይችላል:: የብዙዎች አካውንት ያለፈቃድ ተቀይሯል::

✍️ ስለዚህ የዚህ ፕሮዳክት ተጠቃሚ ልክ እንደ ሲጋራ አጫሽ ነው:: በተጠቀመው ቁጥር እየገደለው ይሄዳል:: ከተጠቃሚዎች ጋር ምንም ዓይነት ሙግት አያስፈልግም:: ሥርዓቱ አኝኮ ይጨርሰዋል:: አንተ ሁሌ ብር አምጣና እኔ ብቻ ልክበር ካለው ሁሌ ብር የሚያመጣ አይገኝም:: ቢገኝም ሲስተሙ ይበላዋል::

የእስልምና የሸሪዓ ሕግጋት ላይ:-
- አንድ በአደራ ገንዘብ አስቀማጭ ገንዘቡ በምንም ዓይነት ሁኔታ ሊሠራበትና የይዘት ለውጥ ሊደረግበት አይፈቀድም:: አደራ ሁሌ አደራ ነው::
- ገንዘቡ ሥራ ላይ እንዲውል ሲስማማ ወይም አስተዳደሩ ሲያዝ ግን ቆጣቢው ከባንኩ ጋር ትርፍ የመካፈል ሙሉ መብት አለው::
- 100 ብር ስትቆጥብ ሰባት ብር እሰጥሃለሁ ሳይሆን በመቶ ብርህ ላይ ካተረፍኩት ውስጥ በሚከተለውና በተጠቀሰው XY ፐርሰንት እንካፈላለን ይባባላሉ:: የሙዷረባ አሠራር ዓይነት ሲሆን ባንኮች ግን ይገለብጡታል:: ስለዚህ 7% ኢንተረስትን እንደ minimum የትርፍ ክፍፍል ወስዳችሁት የተረፈውን ወደ ድርድር መግባት ነው:: ባንኮች "ሂባ" ብለው ቅንጥብጣቢ ጥቅም ጣል የሚያደርጉት ነገር ላግጣ ነው:: ሸሪዓው የሚለው በብርህ ከሠራበት ትርፍ ተካፈል:: አላካፍል ካለህ አማራጮችን ተጠቀም እንጂ በቁም ተገፈፍ የሚል ሸሪዓ, ሸሪዓ ሳይሆን የኢስላሚስት ቡድኖች በኢስላም ስም ሙስሊሙን የሚያጠቁበትና ጥቂት lords of poverty የሚተውኑበት ነው::

ይህንን የፊያት ሥርዓት ትክክል ነው ብሎ ያሰበ ሰው እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም::

Hasen Injamo

25 Dec, 07:34


ሰክረህ ደመወዝና ወጪ ለማጣጣም ስትሞክር

(ብትሰክርም ባትሰክርም ያው ነው)

Hasen Injamo

25 Dec, 06:49


ካዛንቺስ መናኸሪያ አጠገብ ረድኤት ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
የተጨበጨበለት ዋየርለስ ማውስ:: ኮምፒውተር ላይ ማውስ ማለት እንደ እጅ ነው:: እጃችሁ አሪፍ ይሁን

0982 926592 ስልክ ውጉና እዘዙ

Hasen Injamo

23 Dec, 11:44


በቻይንኛ:- ሹሮ ( 鼠肉) ማለት የአይጥ ስጋ ማለት ነው:: እና ያው ሐበሾች ናቸው 鼠肉 የአይጥ ስጋ የሚበሉት:: ካላመናችሁኝ ቻይንኛውን ጎግል ላይ ተርጉሙት::

ቹንጎችዬ አውፍ በሉኝ:: 道歉

Hasen Injamo

23 Dec, 09:17


ዛሬውኑ ስም ማዘዋወር የምትችሉትን ሪል-ኢስቴት ልጠቁማችሁ:: ቪስኮ ሪል ኢስቴት መስቀል ፍላወር አካባቢ

- በራሱ ገንዘብ, በራሱ ይዞታ, ካርታውን በባንክ ሳያስይዘው ሠርቶ ወደ ማጠናቀቅ ደርሷል:: ካርታ መበተን ብቻ ሳይሆን ክሊራንስ ጭምር ስላዞረ ስም ማዞር ቀላል ነው:: ወዲያው ነው ጋሼ: የግንባታ ጥራትና ፋሲሊቲዎችን ሄዳችሁ መስክሩና ካርታ ውሰዱ:: ሰባት ዓመቴ ነው ግን ካርታ አልሰጡኝም አትበል:: ካርታህን ያዝና collateral አድርገው ስልህ::

- ስፋት 153 እና 167 ካሬ
- ባለሦስት መኝታ
- ወደ ፊኒሺንግ የተዛወረ
- የ fully finished ዋጋ

ስልክ: 0941 959595

Hasen Injamo

23 Dec, 07:43


ኢስላማዊ አሳማውን እናሳድገውና በሗላ በሬ ይሆናል:: ላምም መሆን ይችላል::

አሳማ አሳማ ነው:: ዶሩራ እንኳ ሀላል አያደርገውም::

Hasen Injamo

23 Dec, 06:48


የባንክ ወለድ ሪባ ነው ወይ?

-> በስሚ ስማ የሚያወራ ጥራዝ ነጠቅ እና ሪዝቁ በሰዎች እጅ የሆነበት ሰው ሪባ ነው ሊልህ ይችላል:: የባንክ ወለዱ ብቻ ሳይሆን ዶላሩም ብሩም እልል ያሉ ሪባዎች ናቸው:: የባንክን ብድር እና ወለድ ከተውክላቸውማ በቁም ነው የሚገፍፉህ::

አይ ተሳስተሃል ካልከኝ 100 ሺህ ብር ቆጥብና ሞክረው:: እዚያው ገጅርና እየው:: የምታመሰግነኝ ቀን ሩቅ አይደለም::

Hasen Injamo

07 Dec, 17:41


አመስግን 24
ጠዋት ሲነሱ እሳት ለማቀጣጠል እንዳይቸገሩ ገና ማታ ላይ ፍም እሳት አመድ ውስጥ ቀብረው የሚያሳድሩ አሉ:: በሆነ አጋጣሚ ከጠፋ እሳት ፍለጋ ጎረቤት ልመና የሚሄዱ:: ሳይጠፋ እየሮጡ መጥተው ምድጃ ጋር አድርገው ዳግም እንዳይጠፋ ተንከባክበው ያቀጣጥላሉ:: ከዚያ በጭስ እየተጨናበሱ ቁርስ ያዘጋጃሉ:: እሳቱ እስኪያያዝ ውኃ ለመቅዳት ረጅም ርቀት ይኼዳሉ:: ይሄኔ በሪሞት የሚበራ መብራት በሪሞት የሚከፈት ቧንቧ ኖሮህም ታማርር ይሆናል:: ጠዋት ተነስተን ቋ አድርገን መብራት የምናበራ ሰዎች ትልቅ ምስጋና ይጠበቅብናል:: ከተወሰነ ሳንቲሜትር በላይ ጭላንጭል የማያሳይ እሳት የሚያቀጣጥሉ ሰዎች ንጋታቸውን ረጅም ምስጋና ያቀርባሉ:: ነገሮች ሲቀሉልን ምስጋና አይክበደን::

Hasen Injamo

07 Dec, 17:37


ብዙ ሰው ካልተጨናነቀና ካልተከለከለ ያመነ አይመስለውም:: ያንተ መቸገርን የአምላክ የድሎት ምንጭ, ያንተ መራብ የአምላክ የጥጋብ በጀቱ አድርገህ ማየትህን ካልተውክ ኃይማኖትህ ቀርቶ ተራ ኑሮህ እራሱ የጤነኛ አይሆንም:: ኃይማኖት ማለት መልካም ኑሮ የመኖሪያ መስመር እንጂ የሆነ መንገድ ላይ " danger ⚠️” ገመድ አስረህ ዘለልኩ/አልዘለልኩ obsession አይደለም:: የጾም ዓላማ አምላክን ለማጥገብ ሳይሆን ስሜትህን ለመግራት እንዲሁም የሶላት ዓላማ አምላክን ለማስታወስ, መልካምነትን ለመላበስና disciplined የፕሮግራም ሰው ለመሆን ነው:: እየሰገድክ ዲሲፕሊን ከሌለህ እርሳው::

Hasen Injamo

07 Dec, 16:01


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
*******

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

Hasen Injamo

07 Dec, 06:32


ዛሬ የሰማሁት የጉራጌ ጥበባዊ አኗኗር

ጉራንስ ጥርሱን የሌለ አሞት ሊያስነቅል ሐኪም ቤት ሄዶ በማደንዘዣ 5,000 ብር ያለማደንዘዣ በ1,000 ብር ተብሎ ያለማደንዘዣ ለመነቀል ተስማምቶ ብር ሊያመጣ ወጣ:: ያለውን ለቃ-ቅሞ ይዞ መጥቶ ሐኪሙ ግን ተው ያምሃል:: አትችለውም ቢለውም ግዴለም ከሕመሜ አይብስም:: ነቅለህ ጣልልኝ አለው:: ሐኪሙም እየደበረው ሲነቅልለት ጉራንስ ግን ሊጮኽ ቀርቶ ይስቃል:: አንዳንድ ክፍያ ከሕመሙ በላይ ያም የለ:: የአምስት ሺውን በአንድ ሺህ እየተነቀለ መሳቅ ሲያንሰው ነው:: ሐኪሙ ተገርሞ ሊያስከፍለው ቀርቶ ጭራሽ በአድናቆት ብር ጨመረለትና ሸኘው:: ማታ ሐኪሞች የሆነ መዝናኛ ቦታ ተሰብስበው ስለውሎአቸው ሲያወሩ አንዱ ሐኪም ... ዛሬ ደብሮኝ ነው የዋልኩት:: አንዱን ታካሚ ጥርሱን ልነቅለው ማደንዘዣ ወግቼው ሳይነቀል ለሽንቴ ብሎ ወጥቶ እስካሁን አልተመለሰም:: የማደንዘዣ ግን 500 ብር አስቀምጧል ሲል ያ በአንድ ሺህ ብር የነቀለው ሐኪም "እኔ ነኝ የተነቀልኩት, የእኔ ኪስ ነው የተነቀለው" እያለ ውሎውን መተረክ ጀመረ::

Hasen Injamo

07 Dec, 05:13


ወንድሜ ለብር ብለህ ሕሊናህን አትሽጥ

ትውልዱ is saying:- የት ነው የሚሸጠው? ብዙ አለኝ:: እንደውም ላንተ እቀንስልሃለሁ:: ጎረቤቶቼም የሚሸጥ ብዙ ሕሊና አላቸው::

Hasen Injamo

06 Dec, 19:13


ይህ ትውልድ የአላህ መሻኢኾችን ከአላህ ቤት ሲያሳድድ ጊዜ ከቤቱና ከሱቁ የሚያሳድድ በላእ ተላከለት::

ቆም ብለን እንሰብ::

Hasen Injamo

06 Dec, 19:00


ድሮ አንዱ ሀጅ ዘይኑ ሙቀናን ሲያሰግዱ ድምጻቸው አያምርም ብሎ ሲናገራቸው

-> ታዲያ ጥላሁን ገሰሰ ወይም ማኅሙድ አሕመድ መጥቶ ያሰግድህ ወይ አሉት::

እና መሻኢኾቻችንን ያሳደዱና እያሳደዱ ያሉ ሰዎች የዛሬ ሁለት ዐመት ማለትም አቡበክር እራሱ "እኔ ደናሽና ተወዛዋዥ ነበርኩ:: አሁንም የ 2Packን ካንተ በተሻለ እዘፍንልሃለሁ" ብሎ በአደባባይ ኢንተርቪው የሰጠውን ሼር ሲደረግ የምታፈሉ ሰዎች ጂኒፈር ሎቤዝ ከሪያድ ትምጣላችሁ እንዴ? ወይስ 2Pack ይምጣ?

Hasen Injamo

06 Dec, 18:29


መቶ ለሰባት ተላልፈናል ወንድሜ

እኔ 100 ብር እራሱ ሪባ ነው እላለሁ

አንተ ግን በመቶ ብር ላይ የሚጨመረው 7 ብር ሪባ ነው ትለኛለህ::

ቢያንስ በ93% እቀድምሃለሁ::

Hasen Injamo

06 Dec, 18:10


ይህንን ፈተና ተወጡት
==============
የወረቀት መገበያያ የወርቅ ገንዘብን ተክቷል ካላችሁ

ባለ አንድ ቅጠል የኢትዮጵያ መቶ ብር በአስር ቅጠል ብሮች መመንዘር ሪባ ነው:: አንዱን ተቀብሎ ሌላውን መጣልና ዚግዛግ መሥራት ለቀጥተኛው የእስልምና መንገድ አይሆንም::

ወርቅ ለወርቅ ወይም ብር ለብር እኩል በእኩል እጅ በጅ ይለወጣል:: ማበላለጥ ሪባ ነው:: ነጭ ወርቅ በቀይ ወርቅ እኩል በእኩል ካልሆነ ሪባ እንደሆነው ሁሉ አንድ ግራም ቅጠል መቶ ብር በ10 ግራም አስር ብሮች መለወጥ ሪባ ነው::

ይህንን ካልመለሳችሁ ሌላውን እርሱት:: ሸሪዓ ያሟላ እያላችሁ አታገጫጩ:: ሸሪዓውን ከተቀበልን ሙሉውን እንቀበል::

Hasen Injamo

06 Dec, 16:51


ዛሬ እራሱ የ2packን ካንተ የተሻ እዘፍነዋለሁ

Hasen Injamo

06 Dec, 16:49


ለስፖርት ቢሮ ተመርጣ የምትሳለቁ ምእመናን ተወዛዋዥና ደናሾችን ለኃይማኖት መሪነት ለያውም ቢሮ ገንጥላችሁ ገብታችሁ የለ?

Hasen Injamo

06 Dec, 16:47


የአንድ ወረዳ ሙሉ አመራሮች ተገደሉ
በአማራ ክልል ከወደ ደጋዳሞት የተሰማው መረጃ አሳዛኝ ነው
የአነደድ ወረዳ ኮሙኒኬሽን የደጋዳሞት ወረዳ አመራር የነበሩ 35 ሰዎች መገደላቸውን ከእነ ስም ዝርዝራቸው እንደሚከተለው አስቀምጧል።
1,ዋለ አለማየሁ...የወረዳው ዋ/አስተዳዳሪ
2,ቄ/እንዳለ ገበየሁ...ኮሚኒኬሽ ጽ/ቤት ኃላፊ
3,ዘመኑ ይባቤ...እንስሳት ሀብት ጽ/ቤት ኃላፊ
4,አይናለም ስንሻው...ውሃ ጽ/ቤት ኃላፊ
5,አንቢዛው ጠቅላይ...ትም/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
6,ወንድይፍራው ጌታነህ...አስ/ጽ/ቤት ኃላፊ
7,ጌታሰው ውቤ...ሲቭልሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ
8,ተመስገን መኮነን...ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ
9,ሞላ አንተነህ..ስፖርት ጽ/ቤት
10,ይፍረድ ወንድሜነህ...መንገድ ጽ/ቤት ኃላፊ
11,አስፋው ስንሻው...ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ
12,ጌታቸው የሽዋስ...ጤና ጽ/ቤት
13,  ተከታይ  ውድነህ   ገቢዎች ሀላፊ
14, ምግባሩ  አእምሮ መዘጋጃ  ምክትል
15,አይናለም ስንሻው   ውሀ  ጽ/ቤት ሀላፊ
16,ማስተዋል አሻግሬ አፈጉባኤ
17,ጎሹ  ወርቄ     መሬት ሀላፊ
18,ብናየው  ምስጋናው -ንግድ ሀላፊ
19, ከፋለ  ንብረት  መስኖና  ቆላማ ጽ/ቤት      
20, አበበ ይስማው  ማህበራት   ሀላፊ
21,ዘመኑ ሙሉነህ  ፖሊስ
22,አሰሜ  መኮነን  ምሊሻ
23,ምስጋናው   ምሊሻ
24,ይላቸው   ፈንታ  ምሊሻ 
25,አንሙት  አየነው  ምሊሻ ባለሙያ
26,የኔሰው  ምሊሻ 
27,ሽብሬ  አፈንጉስ  ግብርና ባለሙያ 
28,ማተቤ  ተመስገን  ገቢ ባለሙያ
29,በላይ ዋለ-ገቢዎች ቡድን መሪሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ 6 አሉ ብሏል።
አሳዛኝ ነው

Hasen Injamo

06 Dec, 14:37


በውስጣዚኛ

https://vt.tiktok.com/ZSjcQcvxy/

Hasen Injamo

06 Dec, 05:07


የወለድ ነጻ መስኮት 100% ሪስክ የባንክ ዕውቀት ወደሌለው ሕዝብ ማዞሪያ መንገድ ነው::

-> ባንኮች ቢሠሩም ባይሠሩም ለቆጣቢ 7% መክፈል አለባቸው:: ይህ deposit risk ይባላል:: ይህንን የሚሸሹበት ብቸኛ መንገድ የወለድ ነጻ ሲሉ እና ሞኝ ሲያገኙ ነው:: ባንኮች ይህንን በማድረጋቸው እጥፍ ማለትም 14% ያተርፉበታል:: እንዴት? ካላችሁ በብሔራዊ ባንክ ሕግ ለቆጣቢ መክፈል የነበረባቸውን ወደ ገቢነት ያዞሩታል::

ሲያበድሩ ከውል በፊት ብድር መዝጋት ሪስክ አለባቸው:: የአምስት ዓመታት ብድር በአንድ ዓመት ብትዘጋባቸው የአራት ዓመታት ትርፍ ታሳጣቸዋለህ:: ይህንን የሚሸሹበት ብቸኛው መንገድ አሁንም የወለድ ነጻ ነው:: በወለድ ነጻ ተበድረህ በ2ኛው ቀን ብድሩን ብትዘጋም የአምስቱንም ዓመት ትከፍላለህ::

በመደበኛው ስትበደር ብሩን ላንተ ይሰጡሃል:: ምክንያቱም ቤት አስይዘሃል:: በወለድ ነጻው ግን ቤት አስይዘህም ላንተ አይሰጡህም:: ለሞኝ ብር አይሰጠውም:: አላህን ለማታለልና ብድር ሳይሆን ሽያጭ ለማስመሰል "ፕሮፎርማ አምጣና እንክፈልልህ" ይሉሃል:: ብርህ ቤት ወደአላስያዘ ሰው አካውንት ይገባል:: የሙራባሃ አሠራር ሸሪዓው አልተቀበለውም:: የወለድ ነጻ አሠራር ጀማሪዎችም አስጠንቅቀው ጽፈዋል::

በአንድ ግብይት ሁለት ግብይት ክልክል እንደሆነ የሚገልጹ "ሙተዋቲር" ሀዲሦች አሉ:: አንተ ካሹን ክፈልና ለእኔ በዱቤ ሽጥልኝ ማለት ሀራም ነው::
عن عمرو بن شعيب عن أبيه عن جده رضي الله عنهم قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: لا يحل سلف وبيع، ولا شرطان في بيع ولا ربح ما لم يضمن، ولا بيع ما ليس عندك؛ رواه الخمسة وصحه الترمذي وابن خزيمة والحاكم، وأخرجه في علوم الحديث من رواية أبي حنيفة عن عمرو المذكور بلفظ
ዐምር ኢብን ሹዓይብ ከአባቱና ከአያቱ ይዞ ነቢያችን ﷺ ብድርና ሽያጭ ማጣመርን፣ በአንድ ሽያጭ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥና በእጅ የሌለን ነገር መሸጥን ከልክለዋል። ( ሶሂህ አቡዳውድ 3504፣ አንነሳኢይ 4611፣ ቲርሚዚይ 1234፣ ኢብንማጃህ 2188 ፣ አህመድ 174 እና ሀኪም 17/2

ኡስታዞቹ ለምን ዝም አሉ? ትላላችሁ:: ታስቁኛላችሁ:: ጄኒፈር ሎፔዝ ራቁቷን ብትደንስም የከደኑባችሁን ደበሎ መግለጥ አትችሉም:: እናንተ ዝም ብላችሁ የለ? እናንተን ለእነርሱ ቆጥሮ የሰጣቸው አለ እንዴ? አቄሉዋችሁ:: ታዘዛችሁ:: ምን ያድርጉ? ዶክተርና ኢንጂነር ሚኒስትሪ ባላለፈና ፋቲሃ በትክክል በማይቀራ ይነዳል:: ባይሆን የወለድ ነፃ ቡካችሁን ውሰዱላቸው:: ዑምራ ሲያስጎበኙ ይጸልዩበት::

Hasen Injamo

05 Dec, 14:57


ንብ ባንክ በዘንድሮ ዓመት ሊከፋፈል የሚገባው የትርፍ ክፍያ ገንዘብ እንደማይኖር አሳወቀ

ንብ ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከግብር በፊት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ማትረፉን እና ከግብር በኋላ ደግሞ 957 ነጥብ 97 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አሳውቋል። ነገር ግን ለባለአክሲዮኖች ሊከፈል የሚገባው የትርፍ ድርሻ ቀደም ባሉ ዓመታት ለተሠሩ ስህተቶች የሒሳብ ማስተካከያ ሥራዎች እንዲውል ተወስኗል፡፡

ንብ ባንክ የT24 ሲስተም ለውጥ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ ችግር በተለይም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ይምጣ እንጂ መነሻው ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ዕዳ 56 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሆኑ ታውቋል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 45 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ነው። ይህም ካለፈው ዓመት አንፃር የ14.3 ቢሊዮን ብር ወይም የ24 ነጥብ 1 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 10 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው ዓመት የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወይም የ16 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

የተከፈለ ካፒታሉም በ26 ነጥብ 3 በመቶ አድጎ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ የንብ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 67.0 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ባንኩ የሰጠው ብድር ክምችት መጠንም ከአጠቃላይ ሀብቱ 72 ነጥብ 3 በመቶ ነው፡፡

ባንኩ በ2016 የሰጠው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያዎች 49 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

Hasen Injamo

05 Dec, 04:26


እነዚህ ወረቀቶች "ገንዘብ ናቸው እንዲሁም የተለያዩ ናቸው" ብለህ የምታምን ከሆነ የሸሪዓ ቦርድ ቀርቶ የምንም ቦርድ መሆን የሚያስችል ነገር አለህ ተብሎ አይታመንም:: ሀዲሶቹን ወደዚህ መጠምዘዝ አግባብ አይደለም:: ሸሪዓው:- ጂንሲያው (gene) አንድ የሆነ ከፊል ዓይነት እህል ወይም ከፊል ዓይነት ማእድናት በእኩል ይለዋወጣሉ ይላል:: በተቃራኒው:- የቤንጃሚን ፍራንክሊን ፎቶ የተሳለበት አንድ ግራም ወረቀት የጋንዲ ፎቶ ከተሳለበት አንድ ግራም ወረቀት በምንም ሊበልጥ አይችልም:: ተፈጥሯዊ ይዘታቸው ወረቀት ነው:: በሚዛን ነው የምንመዝናቸው:: "ሰዎች በጉልበት ነው ያበላለጡት ምን እናድርግ?" የምትል ከሆነ ሀዲሱን ወደ ጉልበተኞች አትጠምዝዘው:: እስልምና ጭቁኖችን ነጻ ያወጣል እንጂ ጭራሽ ከድሃዎች በማታለል እየቀሙ ለሃብታሞች ስጡ ይላል ብለህ እንዴት ታስባለህ? እንዴት ለበዳይ አባሪ ተባባሪ ትሆናለህ? ወይ ጺማችሁን ላጩትና ስማችሁን ቢል, ትራምፕ አድርጋችሁ ባንክ ሥሩ:: ግን ለምን? ሱና ክብር ነው:: ምልክት ነው:: ሕዝቡ እናንተን እያየ ነው እየታጨደ ያለው:: Elementary አቢሹጃእ የቀራ ሰው እንኳ እንዲህ አይደናቆርም::

Hasen Injamo

04 Dec, 11:14


"ከሰው ምንም አትፈልግ" ይልሃል::
እና ከቢምቢ ነው የምንፈልገው ወይስ ከገበሎ?

ከሰውማ ብዙ ነገር እንጠብቃለን:: አንድን ሰው በጠበቅነው ቦታ ካላገኘነው ቦታ ተሳስተን ነው የሚሆነው::

እና ይታረም::

Hasen Injamo

04 Dec, 07:44


ፌክ እና ዕውነተኛ ገንዘብ
መደበኛና ትክክለኛ ትምህርት

https://vt.tiktok.com/ZSjWBqJhn/

Hasen Injamo

27 Nov, 17:11


https://vt.tiktok.com/ZSjVPne5X/
ኡስታዝ ሀሰን

Hasen Injamo

25 Nov, 15:46


ሀኪሞች << ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ እራሳችንን ወደ ማጥፋት እንሄዳለን >> የሚል ዜና አሁን አንብቤ ደክሞኝም ደንግጬም ነው የመጣሁት:: ገዋናቸውን አስቀምጠውና ሰፈር ለውጠው ሊስትሮ ለመሥራት እያኮበኮበ ያሉ ሀኪሞች አሉ:: ከኬጂ ጀምረህ እስከ ዶክትሬት "ጎበዝ" እየተባልክና እየተሸለምክ አድገህ ልጆች "ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?" ሲባሉ ቅድሚያ የሚመርጡት ሙያ ዋጋውን አጥቶ ዘንባባ የተሻለ እንክብካቤ ሲያገኝ ግራ ያጋባል:: የከተማም የገጠርም ማማርን የሚጠላ በፍጹም የለም:: ግን መማር እየተጠላ ነው:: ሀኪም አንገቱን በትምህርት ቀብሮ ነው ያደገው:: የተግባር ውሎ ላይ አላተኮረም:: ተጓዳኝ ሥራ እንድፈልግላቸው የሚፈልጉ አሉ:: ትልቁ ሲስተም ማስተናገድ ያልቻለ እኔ ምን ውስጥ ልክተታቸው? ይጨንቀኛል:: ወላሂ አዝናለሁ:: ዱዓ አደርጋለሁ:: እዚህ ስጽፍ እንኳ እየከፋኝ ነው:: "ዶክተር" እያልከው ካልተማሩት ጋር ተቀላቅሎ ማሠራት አንጀቴ እንዴት ይቻል?

<<ራሳቸውን ማጥ^ፋት>> የሚለው ዜና እኮ ሕሊና ስላላቸው ነው:: ምክንያቱም the ground ሕሊናህን ሽጠህ ነው የምትንቀሳቀሰው:: ሕሊና ያጣማ በገፍ አግቶ ይገፋል:: አይደለም ዶክተር ሆነህ ለመደበኛ ሰው እንኳ ለመልመድ ብዙ ማመንታትና ከችግርህ ጋር ኮሌታ ለኮሌታ መያያዝን ይጠይቃል:: ሀኪሞቻችንን አላህ ይጠብቅልን:: ልፋታቸውን የሚክስ ሲስተም ያብጅልን::

ለሀኪሞች ነጻ የንግድ ስልጠና መስጠት ለእኔ ቀላል ነው:: ቢሮዬ ላይ አስር አስር እያደረግሁ ሁሉንም ማዳረስ አያቅተኝም:: ግን ሀኪም ነጋዴ መሆን አለበት ወይ? ላለፉት ስልጠናዎች ሲመዘገቡ የከለከልኳቸው አሉ:: የተቆጣሗቸውም ጭምር:: ለሰዓታት በስልክ ነው ያዋራሗቸው:: ሀኪሞችን ብቻ የሚደጉም side income መፍጠር እንችላለን:: የሆነ ዘርፍ እንመርጥና exclusive እናደርገዋለን:: ማኔጅመንቱን እንይዘውና በደንብ ሲቋቋም እናስተላልፍላቸዋለን:: ሕክምናቸው ላይ እንዳሉ side income ይኖራቸዋል:: ለዚያ የሚገቡት እና እስካሁንም የገቡት dedications አሉ:: ያንን Dedicationsን እንደ token ይያዝና ወደ አክሲዮን ይቀየራል::

በነገራችን ላይ ለሀኪምና ለመምህር የሚከፈል ደመወዝ ከሀገር አይወጣም:: ምንዛሪ አያሸሽም:: የሚፈልገው የመንግሥት ልዩ ትኩረት ብቻ ነው::

Hasen Injamo

25 Nov, 10:35


ዲቫሉዌሽን, መንግሥትና ነጋዴው
====================
የፋይናንስ አለቃችንና አስገባሪያችን የሆነው IMF መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መበደሩን አቁሞ ከሕዝብ ግብር እየሰበሰበ ይተዳደር ብሏል:: በዚህም እያደናነቀ ነው:: መንግሥትም ይህንን አሚን ብሎ ተቀብሎ ሕግ በሕግ, መመሪያ በመመሪያ አድርጎታል:: IMF እንደ ጥቅም ከሚያሰላቸው ነገሮች በኢትዮጵያ ወረዳ የሚገኘው መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ካገኘ ዶላርን በቀላሉ መሥራት (ማጫወት) ስለሚያመቸውና ከቁጥጥሩ ውጭ እንዳይወጣበት ነው:: ለዚህም በራሱ ላይ ገዳቢ የሆነ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ እያሻሻለ ነው:: ሌላው የ IMF ጥቅም በብሔርና በኃይማኖት የተከፋፈለን ሕዝብ በግሽበትና በኑሮ ውድነት አንድ ይሆንለታል:: መንግሥት የማይችለው አንድነት ስለሚመጣ ፈርቶ ይታዘዛል የሚል ነው:: ጉዳቱ የመንግሥትም የሕዝብም ነው::

ዘንድሮ ገቢዎች ላይ የታየው ትርምስና ውርክብ የዚህ ውጤት ይመስላል:: አሁን ላይ ኑሮውን የሚያንሩት የመንግሥት ተቋማት ናቸው:: እብደቱን በዋናነት የሚመሩትም ትላልቅ ተቋማት እንጂ ሕዝቡ አይደለም:: መንግሥት መሠረታዊ ነገሮችን በነጻ ጭምር የማቅረብ ግዴታ አለበት:: ሥራው ይኸው ነው:: የሕዝቡን ሀብት ለሕዝቡ የማዳረስ ኃላፊነት እንጂ አዲስና የሌለ ነገር ከሌላ ፕላኔት እንዲያመጣ አልተጠየቀም:: ከብሔራዊ ባንክ, ከጉምሩክና ከፓስፖርት ጀምሮ ብዙ ነገሮች ድንገት ጦዘዋል:: በተቃራኒው የሚታፈሱትና የሚታሰሩት ደሃ ቸርቻሪዎች ናቸው::

የሰሞኑ የመኪና ጉዳይን ብንመለከት መኪኖቹ አዳዲስ ስለሆኑ ያን ያህል ለውዝግብ ክፍት አይደሉም:: ከቻይና በ$16 ሺህ እስከ ዶላር የሚገዛ መኪና ጉምሩክ ዋጋው $28 ሺህ ዶላር ነው ብሎ ይቀርጣል:: Ok ተቀረጠ:: መኪናው በጉምሩክ ዋጋ ተሰልቶ 3 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ቢፈጅ .. ነጋዴው ከነቫቱ አራት ሚሊዮን ቢሸጠው እና በትክክል ደረሰኝ ቆርጦ አወጣው እንበል:: ገዢው ሊብሬ ሊያሠራ መንገድ ትራንስፖርት ሲሄድ "የግሽበት" ተብሎ በዲክለሬሽን ዋጋ ላይ 85% ተጨምሮ ይሰላል:: መኪና የገዛው ሰውዬ ያለ ሊብሬ መንቀሳቀስ ስለማይችል የግዱን አዲሱን ዋጋ ተቀብሎ ለመንገዶች 2% ከፍሎ ይሄዳል::

Well, ገቢዎች ደግሞ የመንገድ ትራንስፖርትን ስሌት እንደ ግብዓት ወስዶ ነጋዴውን ቫት እና የትርፍ ግብር እየጠየቀ ነው:: Actually ከነቫቱ 4 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ ዜሮ ዜሮ መኪና መንግሥት አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር አድርሶታል:: ነጋዴው ያልሰበሰበውን 700 ሺህ ብር ቫት ወዲህ በል:: አልያም ፈቃድህ አይታደስም ብሎ ቁም ስቅሉን እያሳየው ነው:: ገና የንግድ ትርፍ ይጠብቀዋል::

የመኪናውን ዋጋ ጉምሩክ መንገድ ትራንስፖርትና ገቢዎች ከ$16 ሺህ ዶላር ወደ $46 ሺህ ዶላር አድርሰውታል:: እንደገና በቴሌቪዥን መጥተው "ስግብግብ ነጋዴ" ይላሉ:: ነገሮች እንዲህ ሲመሰቃቀሉ ለአስፈጻሚው ግን ሰርግና ምላሽ ነው:: Harvesting time ይሆንለታል:: የዓመቱን ጥቅምት ላይ ዘግቶ ይወጣል:: ሆኖም ግን ነጋዴውን ማስጨነቅ ነዋሪውን ማስጨነቅ ነው:: ነጋዴው ጉቦ እንኳ ሲከፍል ከሕዝብ እንደሚቀበል ታሳቢ አድርጎ ነው:: ኑሮ በጉቦ በዪው ዘመዶችም ጭምር ነው የሚወደደው:: መንግሥት ማረጋጋት ሲገባው አጉል ማጦዙ እና ምሬት መፍጠሩ ጦሱ ለራሱ ነው:: በተለያዩ ነገሮች የተከፋፈሉለት ሕዝቦች በኑሮና በግሽበት አንድ ይሆኑበታል::

ከተመቸው ይግፋበት::

Hasen Injamo

24 Nov, 12:47


ጂኒ ፈር ሎቤዝ በቡታንቲ የምትደንስበት መድረክ ላይ 🕋 ካእባ በቪዲዮ ተቀናብሮ ከመድረኩ እየሰመጠ ይወድቃል:: እርሷና አጃቢዎቿ ጥቁር ካፖርት ነገር ለብሰው ያወልቃሉ:: ይህ ነገር ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ ዐለም ተቀውጦ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ይሞቱ ነበር:: ይልቅስ በሚሊዮኖች ሙስሊሞች ልባቸው ሞተ:: ደነዘዙ::

Hasen Injamo

24 Nov, 12:38


በቁርጭምጭሚትና በሱሪ ሲነታረኩ ሲካካዱ ሙስሊሙን ለማክ^ፈር ፈንድ ሲረጩ, እነሆ ራቁቷን ካእባ አናት ላይ የምትደንስ አመጡ:: ስለእርሱ ጉዳይ ግን እዚህ በቁርጭምጭሚት የሚንጫጫ ብኩንና ቡከን ትንፍሽ እንኳ አይልም:: ምክንያቱም ልባቸው በጥቃቅን አጀንዳ ታፍኗል::

ሸይኽ ጢሱ (ጢምና ሱሪ) ጭንቁ ከዚህ ቤት ውጡ:: ይህንን ቻነል አታቆሽሹ::

Hasen Injamo

24 Nov, 10:01


የሱሪህ የጫፉ የጫፍ የጫፍ ቁርጭምጭሚትህን ስለነካ god ይቆጣል ብለው የሚቆጣ-ጠሩን ኡስታዞች አሉን:: የ god ዐርሽ (ዙፋን) ቁርጭምጭሚት ላይ ሁላ ይመስለን ነበር:: ጀሃነም የሚበዙት ሴቶችና ሱሪያቸው ቁርጭምጭሚታቸውን ያስነኩ ወንዶች እንደሆኑ እንድናስብ ተገደን ነበር:: ኃይማኖት ማለት እከክ እና የ X mark ብቻ የሆነ ነገር ሆኖ መኖር በዕውነቱ ይቀፋል:: God እንደዚህ ከሆነ መቀየር ነው ያለበት:: የሰው አስተሳሰብ ከእንዲህ ያለ ግብስብስ (ሽርክ) ማጥራት የግድ ይላል::

M.N. Kibret አትነካካኝ

Hasen Injamo

24 Nov, 08:57


ለብዙ ዐመታት ያእጁጅ እና ማእጁጅ (ጎግ ማጎግ) የሚባሉት ቻይኖች ይመስሉን ነበር:: ይህም የሆነው በተንሻፈፈ የኃይማኖት አስተምህሮ ምክንያት ነው:: ቻይና ሄጄ ተዟዙሬ 1350 ዓመታት ያላቸው መስጂዶችን ሁላ አይቼ ኢማሙ ሳይቀር የያእጁጅ ሙአዚኑ ደግሞ የማእጁጅ የአክስቱ ልጅ ይመስሉኝ ነበር:: ማዖማ በአባቱም በእናቱም ችሏል:: ምን የመሰሉ ድንቅ ሕዝቦችን ጎግ እና ማጎግ አድርጎ የሳለ የትምህርት ሥርዓት ብዙ ጥበቦቻችንን ነጥቆናል:: በተለይ በልጅነት የሚተከልብህ ነገር ይመርዝሃል:: ዙልቀርነይን (Alexander the Great) ከአውሮፓ ተነስቶ ቻይኖች ላይ ተራራዎችን አጋጥሞ እንዳሸገባቸው ነው የተማርነው:: ሆኖም ግን ዙልቀርነይን ቻይኖች ላይ ሳይሆን ከምድር ገጽ ውጪ ማለትም ከሌላ ምድር ወይም ፕላኔቶች የሚነሱ ጦርነቶች ላይ መሬትን እንዳጠራት የሚተነትን መረጃ ሳነብ ነው ቆ^ሻሻው ትምህርት የተወገደልኝ:: በማያያዝ:- አላህንም ፎቅ ላይ የሰቀሉት ከገጠር መጥተው በፎቅ የተደነቁ ሰዎች ናቸው:: ተራራና ሰማይ የተጋጠሙ የሚመስለው የዶሮ ጭቅጭቅ ከዚህ የዘለለ ሊያስብ አይችልም:: ጭራሽ ፈርዖን ፒራሚድ የገነባው አምላክ ጋር ለመድረስና ለመጋጠም ብሎ ስለሆነ አምላክ ከፍተኛ ቦታ ላይ ተቀምጧል ማለት ነው ብለው በማመናቸው ነው:: የዓለም አቀፍ የሕዋ ጣቢያ እኮ ከፒራሚድ በጣም ከፍ ብሎ በሺዎች ኪሎሜትሮች ነው የተገነባው:: ለዚያውም ኢ-አማንያን ናቸው የገነቡት:: እናላችሁ ዙልቀርነይነይን የገነባው ግድግዳ ምንነት የምትረዱት የመሬት ከባቢ ላይ ያሉ ነገሮችን ስታጠኑ ነው:: ከምድር ገጽ መውጣት ለሰውም ለጂንም ቀላል ነበር:: ጂኖች አሁንም ይሞክራሉ:: የሜቲዎር ሚሳኤሎች (ሺሃብ) የሚወረወሩት እነርሱን ለመምታት እንደሆነ በቁርአን በርካታ ቦታ ተጠቅሷል:: የሕዋ ላይ የማያቋርጡ ጦርነቶች አሁን በዚህ ሰዓት አሉ:: ያእጁጅ ወማእጁጅም የመሬትን ከባቢ ለመሸንቆር ይምሳሉ::
-> ቻይኖችን ብቻ ሳይሆን ድንቁርናህንም ፍታው:: ወንድሜ የእስልምና እውቀት ከማይሞች, ከንባብና ምርምር ጋር ከተጣሉ, ማንበብን ከድንቁርና ጋር ከሚያገናኙት ላይ አትቅሰም:: ያጃጅሉሃል::

Hasen Injamo

23 Nov, 16:53


ሰፊውን ሕዝብ ለማሳመን የሚደክሙ or ሁሉም ሰው ሐሳባቸውን እንዲገዛው የሚታትሩ ሰዎች ያሳዝናሉ:: ነውርም ይመስለኛል:: የአላህ ነቢያት እንኳ ሁሉንም ሰው ለማሳመን ቢላኩ እንኳ ሁሉም አልገባላቸውም::

ከሰሞኑ ስልጠናችን ላይ የነበረው መግቢያ ሲስተሙን ማወቅ የሚል ነበር:: ግብን ማስቀመጥ ብቻው ጥቅም የለውም:: ሲስተማቲክ መሆንም ወደ ግብ አያደርስህም:: የቅርጫት ኳስ ግብ አስቀምጠህ እግር ኳስ ብታጣጥፍ ዋጋ የለውም:: አንድ ቢሮ ሄደህ ሲስተም down ካለ በቃ ማንም አያናግርህም:: ሲስተሙ ነው::

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ላይ እናምጣው::

የኢትዮጵያ
አማካይ ግሽበት .......... 30%
ቫት ........................... 15%
የባንክ ቻርጆች ............ 5%

ድምር ......................... 50%

አምና በወር የተጣራ 10,000 ብር የምታገኝ ከሆነ ዘንድሮ ቢያንስ እንደ አምና ለመኖር በወር 15,000 ብር ያስፈልግሃል:: ሲስተሙ ነው:: ይህንን ብቻህን ምንም ልታደርገው አትችልም:: ቀላል እንዳይመስልህ:: ከዚሁ ከቀበሌ ተነስቶ እስከ አሜሪካ ፌደራል ሪዘርቭና IMF ድረስ የተዘረጋ ሲስተም ነው:: ከወለድ ነጻ ተጃጅለህ ተቀፍድደህ ቀርቶ በመደበኛውም ብትሮጥ እንኳ አትደርሰውም:: ለእስልምና ብዬ ነው እንዳትል:: እስልምና የዐዋቂዎች እንጂ የመንጋ ኃይማኖት አይደለም:: ከገጠር የተላከ ነብይ የለም:: የመጨረሻው ነብይ صلى الله عليه وسلم ከከተሞች እናት ከዑመልቁራ ናቸው:: እና ሲስተሙ በልቶ ካደከመህ በሗላ በረሮ ላይ እንደሚረጭ ፍሊት funጅ በድሮን ይርከፈከፍብሃል:: ዐረቦች የት ናቸው? ሙስሊሞች የት ናቸው? ትላለህ:: ከ hellwood ጂኒፈር low-base የምትባል ሴት ካእባ 🕋 አናት ላይ ስትደንስ ማን ትንፍሽ ይበል:: ጸጥ ረጭ::

Hasen Injamo

22 Nov, 07:36


መልካም ጁምዓ

በፈጣሪና በፍጡር መሃል ጣልቃ መግባት ያስቆሙኝ ምክንያቶች:-
1) የነቢ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم አጎት አቡለሃብ ጉዳይ ነው:: ስንት ገድል የሠሩ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ውስጥ ከዘይድ رضي الله عنه ውጭ የአንድዳቸውም ስም በቁርአን በቀጥታ አልተጠቀሰም:: ሆኖም በጣም ያስቸገራቸው አጎታቸው አቡለሃብ ስም ጭራሽ በምዕራፍ ደረጃ አለ:: ይህንን ሳትቀራው ቁርአንን ማኽተም አትችልም:: ስትቀራ ስሙን መጥራትህ አይቀርም:: ያው "አቢለሃብ" ስትል ቢያንስ 50 ነጥብ ታገኛለህ:: ቁርአኑ በቀጥተኛ ስሙ ሳይሆን በቅጽሉ ነው የጠራው:: ቀጥተኛ ስሙ "ዐብዱል ዑዝዛ" ነው:: ዑዝዛ የሚባለው ጣዖት "ገብረ" እንደማለት ነው:: ቅጽሉን ያገኘው ቁንጅናውና ቅላቱ ልዩ ስለነበር የሚንበለበል እሳት ይመስል ነበር:: "የአብረቅራቂዎች አባት" ማለት ነው:: ቁርአን በቅጽሉ ነው የጠራው::

ነቢዩን صلى الله عليه وسلم ካስቸገሩ ሰዎች ይኸው አጎታቸውና ባለቤቱ ዑሙጀሚል ናቸው:: እርሷ የአቡሱፍያን እህት ስትሆን ዞራ የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ዘመድ ነች:: አቡለሃብና ዑሙጀሚል በሥራቸው እንደሚቀጡ ቁርአን ገልጿን:: እናምናለን:: ግን ስንት ታሪክ የሠሩት ሳይጠቀሱ እንዴት ተጠቀሱ? አቡለሃብ በቸርነቱ ወደር አልነበረውም:: ፊርዓውንም ተደጋግሞ የተጠቀሰው በቸርነቱ ነው ይባላል:: የአቡለሃብ ሌላ መታወሻ ነቢ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم የተወለዱ ወቅት ውድ በሚባል ግመል ትልቅ ድግስ ደግሷል:: ባሪያ ነጻ አውጥቷል:: የሆነ የማናውቀው ጉድ ስለሚኖር ዝም ማለትና በራስ ሥራ መጠመድ ይሻላል::

2) ኢብሊስ:- ምላሽ ያጣሁለት ነገር ቢኖር ከአላህ ጋር ያደረገውን ቀጥታ ውይይት በቁርአን ሳነብ ነው:: ደግሞ እኮ እያጠፋና ለጥፋት እያቀደ እንኳ አላህን "ወቢ ዒዘቲከ ... በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ" እያለ የሚፎክረውና የሚለምነው ነገር ሳነብ ... በቃ በአላህና በፍጡራኑ መካከል ጣልቃ መግባት አዋጪ እንዳልሆነ ገባኝ::

Hasen Injamo

21 Nov, 18:01


ትናንትና የሥራ ማስታወቂያ ከእነ CV መጻፊያ ፎርማት ለጠፍኩኝ:: ፎርማቱ ከአንድ ገጽ አይበልጥም:: ከሰነድ ደግሞ ዲግሪ ብቻ እንዲልኩ በአማርኛም ጭምር አስጠነቀቅሁ:: Almost all አመልካቾች የራሳቸውን ፎርም እና አንድ ሀገር ሰነድና ረጅም CV ነው የላኩት:: ሁሉም ቦታ እንደዚያ ነው ማለት ነው? ሥራው ላይ እንዴት ልትሠሩ ነበር?

ዐመታዊ ሪፖርት በአገር ውስጥ ገቢ FIRA ፎርም ሙሉ ብትባሉ በጆግ ነበር የምትሞሉት?

Hasen Injamo

21 Nov, 11:31


ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

ማስታወቂያ እና ሕትመት ሥራ


ልብስ ላይ ህትመት :-

=ቲሸርት
=አንፀባራቂ
=ሁዲ
=ባንዲራ (ለድርጅት እና መሰል )
=ጃኬቶች
=የስራ ልብሶች
=የስፖርት ማልያዎች እና ትጥቆች

ወረቀቶች

=በራሪ ወረቀት
=የሰርግ ካርድ
=ቢዝነስ ካርድ
=ፖስት ካርድ
=ደረሰኝ
=የሃኪም ቤት እና መሰል ካርዶች
=መፅሄት
=መፅሐፍ
=ተለጣፊ ወረቀቶች
=ትኬቶች
=የሃዘን ካርዶች
=ለድርጅትዎ ፖስታዎች ወዘተ

ሌሎች

=ባነር
=ማግ
=ሾፒንግ ባግ
=ሕጋዊ ማህተሞች
=ላይት ቦክስ
=ማይካ
=ድጅታል መታወቂያ እናትምልዎታለን
=እስክርቢቶዎች
=ለኮምፕዩተርዎ ማዉዝ ፓድ
=የድርጅትዎ የቁልፍ መያዣዎች
= የድርጅትዎን አርማ የያዙ ማስታወሻዎች (note book)
= ወዘተ

ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

👇
https://t.me/Teraraprinting1

https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

ሎኬሽን 👇
https://maps.app.goo.gl/heRTnskHQDUj2jgQ9

Hasen Injamo

20 Nov, 14:38


የቻይናና የውጭ ሀገራት ድርጅቶች የደረሰኝ ቁጥጥር ምን ያህል ያስኬደናል?

ይህ ጉዳይ ከምንዛሪ ሽሽት ጋር በተያያዘ በትላልቅ ሚዲያዎች አቅርቤው ነበር:: እኛ በኢኮኖሚ ገና ነን:: የውጭ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች እኛ ጋር ሲመጡ አትርፈው ለመውጣት ነው:: አንድ መቶ ሺህ ብር ሀገር ውስጥ ካጭበረበረ ማለትም ደረሰኝ ካልቆረጠ ኢትዮጵያዊ ይልቅ የውጭ ሰው ያላግባብ ድንበር ያሻገረው አንድ ዶላር ይጎዳናል:: ቢሆንም ቢሆንም ዐለም አንድ መንደር በሆነበት ወቅት ከውጭ ሰው ጋር አልሠራም ማለት የማይታሰብ ነው::

ቻይኖቹ የገጠማቸው ችግር አንድ:-
ሀበሻ ጭንቅላቱ መፍጠር ቀርቶ መኮረጅ እንኳ ብዙም አልቻለም:: አንድ የሀበሻ ባለሙያ አግኝተህ overtime ብታዘው እንኳ ሊያለምጥ ይችላል:: በእርግጥ ሲስተማችንም አልምጥ ስለሆነ:: ስለዚህ ሀበሻው ከቻይናው ጋር በሼር ሥራ ይዋዋላል:: ምሳሌ የሀበሻው የፋብሪካ አወቃቀር በቀን ተጋኖ ሁላ 2,000 ፍሬ ያመርታል እንበል:: ቻይኖቹ በጋራ ለመሥራት በ2,000ው ይዋዋላሉ:: ምክንያቱም የእነርሱ ቴስታታ በቀን 5,000 ፍሬ ወደ ማምረት ማሳደግ ይችላል:: ኢንጂነር, ኬሚስትና የፋይናንስ ባለሙያ አምጥተው ይቀይሩታል:: ይህንን ጋፕ እንደራሳቸው ድርሻ ይወስዱታል:: ከዚያ እንዴት ይሸጥ? የሚባለው ጋር ሲመጣ ነው ያለደረሰኝ የሚል ነገር የሚመጣው:: የእኛ ቴስታታ ወይ ሥራ አልፈጠረ, የመንግሥት አሠራርም አላፈናፈነ:: በድሕነት ከሗላ 2ኛ ሆነን አናስነካ ብለን እየተጋተትን ነው:: የገንዘብ ዘረፋ ሊኖር ይችላል:: ግን በቁም ከምንገፈፍና ከምንዘረፍ እየሠራን ቢሆን ይሻላል:: ሁሌ እንደምለው, በአጉል ሕግ ከቆመ ሲኖ ትራክ ተንቀሳቅሶ የተጋጨው የበለጠ ኢኮኖሚውን ያንቀሳቅሳል:: ሲኖው ቆሞ ሾፌርና ረዳቱ ከሚቅሙና ሺሻ ከሚያፈነዱ ወጥተው ቢሠሩ ቀርቶ ቢጋጩና ረዳቱ ቢሞት ከእድር ጀምሮ እስከ ተዝካር, ከመቃብር ቆፋሪ እስከ ፕላን አንሺ, ከነዳጅ ማደያ እስከ ትራፊክ ማኔጅመንት ሥራ ይፈጠራል:: አጉል ቁጥጥር ትርፉ ሙስና ነው:: ከመንግሥት የሚጠበቀው ተቀዳሚ ሚና ማመቻቸት እና በስሱ መቆጣጠር:: ሰውን በሥራ ወጥሮ መንግሥትን እንዲረሳ ማድረግ::

ቻይኖቹ የገጠማቸስ ችግር ሁለት:-

Hasen Injamo

20 Nov, 06:05


መርካቶ እና ደረሰኝ
============
መርካቶ አሁንም ቢሆን ዋጋ መወሰኛ ቦታ ነው:: በግሌ ሁሉም ድርጅት ደረሰኝ ይቁረጥ የሚለው ላይ ከሀገር ጥቅም አኳያ አከራካሪ ነገር ነው:: ብዙ ታክስ መሰብሰብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል:: ታክስ ዋነኛ ዓላማው ፍጆታን መገደብና የኢንፍራስትራክቸር ኪራይ ማስከፈል ነው:: አንዳንዴም ፍጆታ (consumption) ለመጨመርም ጥቅም ላይ ይውላል:: ፍጆታ መገደብ ሲባል ገበያ ይዤው የምወጣው ካሽ ላይ የተወሰነውን withheld ይደረግብኛል:: ከእኔ የተቆረጠው ወይም የተቀነሰው "የመግዛት ኃይል" ወደ መንግሥት አካውንት ቢገባ ለመንግሥት ምንም አያደርግለትም:: Just number chat 💬 ነው:: ባይሆን እኔ ከማጥፋት አቅቦኛል::

በተቃራኒው ፍጆታ ለመጨመር ሲባል ታክስ በጣም ሊቀነስ ይችላል:: ምርት ከተትረፈረፈ ካልተበላ ፋብሪካዎች ይከስራሉ:: ሠራተኛ ይበትናሉ:: ስለዚህ የተመረተው መነሳት አለበት:: የላይኛው ተቃራኒ ማለት ነው:: ሀገራችን የምታመርተው ትንሽ ነው:: ፍጆታን በለቀቅነው ቁጥር ብዙ ኢምፖርት ይጠይቀናል:: ብዙ ኢምፖርት ደግሞ ብዙ ዶላር ይፈልጋል:: ሀገሪቷ ውስጥ ረብሻ መኖር አንዱ ጥቅሙ እንቅስቃሴን በመገደብ ፍጆታን መቀነሱ ነው:: ፋብሪካዎችን ባላስፋፋንበት ሁኔታ ሰላም ቢሆን ኖሮ ግሽበታችን የቬንዝዌላ ወይም የዚምባብዌ ይሆን ነበር:: በእርግጥ ሰላም ሆኖ ግሽበት ቢበዛ የተሻለ ነው::

መርካቶ ሱቆችን የመዘጋጋት ነገር ነበር:: ወንድሜ 3/4ኛ ኢትዮጵያ ተዘግቶም ሥርዓቱ ቀጥሏል:: ሱቃችሁን ከፍታችሁ ሥሩ:: ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ሥርዓት ሲለወጥ መንግሥት እራሱ አያውቅም:: አጼ ኃይለሥላሴ እስኪታፈኑ, መንጌ ዚምባብዌ እስኪደርስ, ወያ^ኔ ተንቤን እስኪገባ አላወቁም:: ከሕዝቡ በሗላ ነው የሰሙት:: እራሳቸውን የሆነ ጥግ ላይ ሲያገኙት ነው የድንብር ጸብ ውስጥ የገቡት:: የዚህኛው ሥርዓትስ ካላችሁኝ እናቴ ዝም በል ብላኛለች::

Well, መንግሥት ይህንን የደረሰኝ ኦፕሬሽን ሲጀምር የራሱ ምክንያት ይኖረዋል:: ብዙ የውጭ ሀገራት ፋብሪካዎች ገንዘብ እያሸሹ ናቸው:: ምሳሌ ቻይኖች የ10 ሚሊዮን ብር ዕቃ ለጅምላ ሻጭ ሲሸጡ 8 ሚሊዮኑን በሐዋላ ሀገራቸው ላይ አስገብተህላቸው ለቀሪው ለ2 ሚሊዮኑ ነው ደረሰኝ የሚቆርጡልህ:: ጅምላ ሻጩም በተራው ያለ ደረሰኝ የገዛውን በደረሰኝ ቢሸጠው ትርፉ በጣም ይጋነንበታል:: ስለዚህ አየር ላይ ይመታዋል:: መንግሥትን በጣም የሚያሳስበው ድንበር ዘሎ በሐዋላ የወጣውን $1 ዶላር እንጂ የችርቻሮ ደረሰኝ መቁረጥ አለመቁረጥ አይደለም:: እዚቹ በዚቹ ነው:: እራሳቸው ቻይኖቹን ብቻ እየተከታተለ ለምን አይዝም? ከተባለ የቻይና $14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ አለብን:: BRICS ላይ ሁላ የሚያገናኙን ለፌስቡክ የማይመቹ እከክልኝ/ልከክልህ-ኦች አሉ:: ለነገሩ እኛ ነን እከካሞቹ:: ባይሆን እኛም ሀገራቸው የምንሄደው ሸቀጥ ለማምጣት ሳይሆን ሲስተማቸውን በልተን ለመጫወት መሆን አለበት:: መንግሥት ወደ ቻይና የሚልካቸው አምባሳደሮች እና ሠራተኞች በሙሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ስልጠና የወሰዱና እምጷ አድርገው የጠጡት መሆን አለባቸው:: በየኤምባሲው እየተመደቡ ፐርዳይም የሚጠብቁና ዶላር የሚያዘዋውሩ አይጠቅሙም:: ዶሮ ብታልም ጥሬውን እንዲሉ ሳይቀየሩ ቶሎ ለቤትና ለመኪና ልሸቅል የሚሉት መሆን የለባቸውም::

ሌላው የ under invoice ጉዳይ ነው:: $50 ሺህ ዶላር የፈጀ ዕቃ በ$100 ዶላር እንደተገዛ ተደርጎ ይገባል:: የሒሳብ ልዩነቱ በጉምሩክ ተመን ተይዞ እንኳ አሁንም ክፍተት ይኖራል:: ያ ዕቃ ያለደረሰኝ ካልተመታ አሁንም የተጋነነ ትርፍ ያመጣል:: ስለዚህ ነጋዴው ያለደረሰኝ ያጫውተዋል:: ነጋዴው ይህንን የሚያደርገው ወዶ ሳይሆን ሀገሪቷ ማለትም ባንኮች በቂ ምንዛሪ ማቅረብ ስለማይችሉ ነው:: ኢምፖርተሩ በከፍተኛ ሪስክ የሚሠራው ሥራ ነው::

መንግሥት ትላልቅ ነጋዴዎች ብቻ ነው የምፈልገው ዐይነት ነገር የያዘ ይመስላል:: ምክንያቱም ትላልቆቹ ለመንግሥት ባይሉ እንኳ ለራሳቸው ሲሉ ደረሰኝ ይቆርጣሉ ብሎ አስቦ ነው:: ዋናው ስጋታችን የምንዛሪ መሸሽ ነው ብለን ካመንን የሚሸሸው በትናንሽ ነጋዴ ነው ወይስ በትላልቆቹ? ብዙዎቹ ትላልቆች በሁለት ዜግነት ነው የሚጫወቱት:: ደሃው ቢያሸሸውን አትርፎ ይዞት ይመጣል እንጂ ኑሮውን ውጭ አያደርግም:: ሌባና ፖሊስ መጫወት ብዙም ይቀይረዋል የሚል ግምት የለኝም:: ብዙ ምንዛሪ የሚወጣብን ሀገር ሄደን ቁጭ ብለን እናጥናው:: የሀገር ውስጡን በተለይ ቫት እና ቲኦቲ ከነጋዴው ላይ እናውጣውና ለባንኮች ሲስተም እንስጠው:: እኔ ዕቃ ስሸጥ የምሰበስበው አብዛኛውን ክፍያ በባንክ ስለሚሆን ለምሳሌ የ10,000 ብር ዕቃ ስሸጥ ወደኔ አካውንት መግባት ያለበት ቫት ተቀንሶ 8,695.65 ብር ብቻ መሆን አለበት:: ቫቱ ወደ ገቢዎች ሚኒስቴር አካውንት ቀጥታ ይሄዳል:: የተለየ ካለኝ ወር መጨረሻ ላይ ታክስ ፋይል እጠይቃለሁ::

Hasen Injamo

19 Nov, 13:58


የወለድ ነጻ መሠረታዊ ችግር ሸሪዓው በነቀፈው ሙራባሃ አሠራር መዘፈቅ ብቻ አይደለም:: ከችግሮቹ ሁሉ የከፋው ችግር የፈንዱ ምንጭ በባዶ የሚያመጣው ደሃው መሆኑ ነው:: ልብ በሉ! መላ ካጡ ደሃዎች በነጻ የተሰበሰበውን ባንኮቹ ለሃብታም አትርፈው ያከራዩታል:: አይ^ሁዶች እና ኢምፔሪያሊስቶች እንኳ በሙስሊሞች ላይ ይህንን ያህል አልጨከኑም:: ደሃ ሆነህ ለባንኩ በነጻ ትሰጠውና ባንኩ አትርፎ ያከራየዋል:: ለደሃው ሲሆን ወለድ ነው ያሉትን ለባንኩ ሲሆን ሀላል ነው:: ይህንን ለማሳመን ሆ^ዳም ኡስታዞች ጢም ያከራያሉ:: የትርፉን ፐርሰንት እያሳየ <<ሙዷረባም እኮ አለ>> ይልሃል:: ሙዷረባማ ጭራሽ የባንኩን ኪሳራ ወደ ቆጣቢው የሚያዞር ሌላ ግፍ ነው:: በሙዷረባ ሙሉ ኪሳራ የቆጣቢ ነው:: እስቲ ባንኮቹ በሙዷረባ ለሕዝቡ አበድሩ:: እስቲ ወንድ::

Hasen Injamo

19 Nov, 10:13


የአዳራሹን ጨርሰን
በግል ምክክር ጀምረናል
===============
በሁለት ዙር የተዘጋጀው የኢንተርናሽናል ንግድ እና የእሴት ተኮር ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ትናንትና ጨርሰናል:: አዳራሽ ላይ አውርቶ መለያየት ሳይሆን የሁለቱ ዙሮች ሰልጣኞች የንጥል ምክክር ይቀጥላል:: ምክንያቱም ከተለያየ ባክግራውንድ የመጡ ስላሉ እያንዳንዱን በግል አግኝቶ አቅጣጫ ማመላከት የግድ ነው:: በተቻለ መጠን እኔ እንኳ ባልኖር (ብሞት) በየመንገዱ ላይ ሊረዷቸው የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ሰዎችን ለማስተዋወቅ ሞክሬያለሁ:: እስካለሁ ድረስ ግን ክትትሉ ይቀጥላል:: ሶፍትዌር የሚጫንላቸው ይኖራሉ, የባንክ ብድር ሒደት ላይ በሙያ የሚታገዙም እንዲሁ:: ዋናው ጥረት የአዳራሽ ስብከት ሳይሆን መስመር የማስያዝ ነው:: ይህንን team ካገባደድኩ በሗላ ወደ ሦስተኛው ዙር ልንሻገር እንችላለን::

Cooperative Bank Of Oromia ለሰልጣኞቹ ላቀረበልን ምርጥ ፕረዘንቴሽን በጣም አመሰግናለሁ:: ባለፈው የነበረው ጽሑፌ ላይ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ያለማስያዣ ያበደረው 8 ቢሊዮን ብር እንደነበረና የቅርቡ ሪፖርት ሲካተት ግን 10 ቢሊዮን ብር አበድሯል:: ከ264 ሺህ ሰው በላይ ተጠቃሚ አድርገዋል:: ሻይና ቡና ለሚያዞሩት ወገኖቻችን ጭምር ነው ያበደሩት:: ድሮ አክሲዮን ሲሸጡ የአክሲዮን ዋጋ 100 ብር ያደረጉ ሲሆን 400 ብር ለያዘ ሁላ አክሲዮን ሽጠዋል:: ከውስጡ 4 ባንኮች ተገንጥለው ሲወጡ እንኳ አልወደቀም:: እኔ የራሴን ግምቶችን ወስጄ ነበር ለድርጅቴ ለዲናር የመረጥኳቸው:: ምርጫዬ ትክክል እንደነበረ የአቶ ባይሳና የአቶ አበራ መግለጫ አስረድቶኛል:: አመሰግናለሁ::

ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክም ይሁን ለሌሎች ባንኮች የማስተላልፈው መልዕክት ቀጣዩ የባንክ አሠራር የአበዳሪ/ተበዳሪ ግንኙነት ሳይሆን <<የባንክ - ለ - አጋር >> በአገልግሎት መወዳደር ነው:: Say “ከዚህ ሰው ወይም ድርጅት ስንት አተርፋለሁ?” ዓይነት ሳይሆን አብረን ስንት እናትርፍ ለሕዝቡስ ምን የተሻለ እናቅርብ በሚል corporate social responsibility (CSR) ጭምር ነው የሚሆነው:: ትልልቅ የዓለም ባንኮችን background ብታጠኑ ለተበዳሪዎቻቸው የምክር እገዛ ይሰጣሉ:: ለማኅበረሰቡ ደግሞ CSR ወይም ድርጅታዊ የማኅበረሰብ ኃላፊነት ይወጣሉ::

ተገልጋይህን በአገልግሎት ክበበው::
በአገልግሎት አክብረው::
Honor your client with service.

እኔም ሰልጣኞቼን የምችለውን ያህል ለማገዝና ለመተጋገዝ እጥራለሁ:: ዋናው በዱዓ ነው::

Hasen Injamo

18 Nov, 03:21


ጎል ማስቀመጥም ይሁን ሲስተማቲክ መሆን ጥሩ ቢሆንም ግን ቋሚ ሲስተሙን ማወቅ መቅደም አለበት::

https://vm.tiktok.com/ZMhtqLa1C/

Hasen Injamo

17 Nov, 11:30


መርካቶ

#Ethiopia | በመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ በተባለ ቦታ የእሳት ቃጠሎ ከቀኑ 6:30 ሰዓት መከሰቱ ተሰምቷል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች በቦታው ተገኝተው እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያረጉ እንደሚገኙ ታውቋል።

Hasen Injamo

17 Nov, 09:28


የስዑዲ እስልምና ማለት በሜክአፕ እና በስፖርት አምራና ተሸንቅጣ በውድ ሰርግ አግብተሃት ልጃችሁ የዝንጅል እና የሀብሃብ ድቅል የመሰለ ሲሆን ማለት ነው::

ስዑዲ አከረረችና ተበጠሰች:: በጺም ያበጠ ጭንቅላት, በኒቃብና በጀለቢያ የተጀቦነ ገላ ተራቆተ::

"ለብሳለች ሲባል ግን የተራቆተች, ተራቁታለች ሲባል ግን የለበሰች የመሰለች ትመጣለች" የተባለችው ኒቃብ ለብሳም ውስጥዋ የተራቆተንም ይጨምራል:: ጺም አሳድጎ አዕምሮው ከቀጨጨ ምን ዋጋ አለው:: የልብስ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሰውነት መሪው ልብ ነው:: ገጽታ ላይ አተኮሩና ልብን ዘነጉ:: የልቦና ሐኪሞችን "በኩ^ፍር" እና "ቢድዓ" ቃላት ከየመስጂዱ አባረሩዋቸው:: ፍሬውን በወንጭፍ ሲያረግፉት ሾህና ቆንጥሩ ፈጦ ወጣ::
_
ፌክ ባእባ 🕋 ሠርተው በራቁት ይጠወፋክ:: የኢማም ዐሊ رضي الله عنه ዙልፊቃር ሰይፍ በቀበቶ መልክ ሠርተውት በ-ራቁት ገላ ላይ ይታጠቁታል::

Hasen Injamo

11 Nov, 17:07


Hasen Injamo pinned «ለማስታወስ ያህል በፌስቡክ በራስህ wall መጥቶ የሚሳ^ደብ ሰው ማለት ለምንም ኃላፊነት መታጨት የማይችል ሰው ነው ተብሎ ይታሰባል:: ይህ ዐይነት ሰው ልትሰጠው የምትችለው ብቸኛ ሥራ funጅ ማምከን ነው የሚሆነው:: ሐሳብን መግለጽ እና መሳደብ የተለያዩ ናቸው:: በግሌ በሰው wall ስኮምት እጅግ በጣም ቃላት እመርጣለሁ:: እኔም ጋር ማንም እንዲናፈጥብኝም አልፈልግም:: ምክንያቱም ከተሳ^ዳቢ ምንም የሚቀር…»

Hasen Injamo

11 Nov, 17:07


ለማስታወስ ያህል
በፌስቡክ በራስህ wall መጥቶ የሚሳ^ደብ ሰው ማለት ለምንም ኃላፊነት መታጨት የማይችል ሰው ነው ተብሎ ይታሰባል:: ይህ ዐይነት ሰው ልትሰጠው የምትችለው ብቸኛ ሥራ funጅ ማምከን ነው የሚሆነው:: ሐሳብን መግለጽ እና መሳደብ የተለያዩ ናቸው:: በግሌ በሰው wall ስኮምት እጅግ በጣም ቃላት እመርጣለሁ:: እኔም ጋር ማንም እንዲናፈጥብኝም አልፈልግም:: ምክንያቱም ከተሳ^ዳቢ ምንም የሚቀር ጥቅም አይኖርም:: ልጆች ቤተሰቦች አሉኝ:: የአንባቢንም ክብር ለመጠበቅ ስል እቦልካለሁ:: በዚያኛው አካውንት ከ4,000 በላይ ተቦላኪ አለ:: አንዳንዴ ደብለቅ አድርጌ የምጽፈውን የእያንዳንዱን ነገር ዓላማ ለልጆቼ እነግራችዋለሁ:: እነዚያ የምቀላቅላቸው አንዳንድ ቃላት ለዓላማዬ ስኬት ጠቅመውኛል:: ስቀልድ የምቀልድ እንዳይመስልህ:: ቀላት ስቀላቅልም የተቀላቀለብኝ እንዳይመስልህ:: ቆሻ^ሻ የምትጥልለት scavenger አለ:: ያ ለቃቃሚ Completely mislead ይሆናል:: ተስፋ የሌለህ ይመስለዋል:: አንተ ግን ሥራህን ትሠራለህ::

Hasen Injamo

11 Nov, 13:57


ስልኮቼ ብዙ ሆነው በየትኛው ለማን እንደምደውል የቱ መች እንደሞላሁ አላውቅም:: አልቋል ሲለኝ መሙላት ነው:: ለጥንቃቄ ብዬ የካርድ ያደረግሗቸው አሉ:: አንድ ብዙም የማልጠቀምበት VIP ስልኬ ላይ የአየር ሰዓት ሞልቼ "ያሎት ቀሪ እድሜ ማለቴ ቀሪ ሐሳብ ..." ሲለኝ ደገምኩት:: አሁንም እንደዚያው ነው:: ቅዳሜለት ዘጭ አድርጌ ሞላሁና ቅድም ስደውል አሁንም ያሎት ቀሪ ሚስት ... ይቅርታ ቀሪ ሒሳብ ምናምን እያለ ሲያዝገኝ ደግሜ ዘጭ አድርጌ ሞልቼ ደውዬ አሁን ስደግመው ደገመኝ:: ችግር ካለ ብዬ ኢትዮ ቴሌኮም ደውዬ ይህንን ወፍጮ አስቁሙልኝ:: ካርዱን ሁላ ጨርሶ ወደኔ ሊዞር ነው ስለው ኧረ የሞሉዋቸው ሁሉ በመደዳ አሉ:: አልተነኩም:: ምናልባት ወደ ሳፋሪ እየሞከሩ ከሆነ አለኝ:: ከሳፋሪ የማውቀው አንድ ቁጥር ብቻ ነው:: እሱኛው ሰውዬ ጋር ሞክሬ አላውቅም አልኩት:: በቃ መኪናዎትን ማለቴ ሞባይሎትን restart አድርገው ይሞክሩት አለኝና ስሞክር ያው ነው:: መሴጅም በተደጋጋሚ failed እያለ አዛ አደረገኝ:: በሗላ ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር country code (+251) የሌላቸው ስልኮችን በሙሉ by default ወደ ኬንያ እየቀየረ ነው የሚሞክረው:: SMS መላክ ሁላ ተውኩኝ::

ወገን ከቀፎዬ ነው ወይስ ከኢትዮ ቴሌኮም ሲስተም? 994 ደውዬ ጥያቄው እንደተደጋገመ ዓይነት ነገር ነግሮኝ ግን restart እንዳደርግ ነው የመከረኝ:: ከገጠማችሁ ትክክለኛ ችግሩና መፍትሔው ከመደወላችሁና መሴጅ ከመሞከራችሁ በፊት +254 (ኬንያ) አለመሆኑን አረጋግጡ:: ኢትዮ ቴሌኮሞችም መሰል ጥያቄ ከመጣላችሁ ይህንን እንደ መረጃ ውሰዱት::

የእኔ ጊዜያዊ ችግር እዚሁ ቀርፌዋለሁ:: ምናልባት ከቀፎ ከሆነ iOS 18.1 የገጠማችሁ ካላችሁ ብታካፍሉኝ:: መቼለት iOS 18.0 እንዲሁ ሊያጨልለኝ ደርሶ ነበር::

Hasen Injamo

11 Nov, 10:09


ኃጢአትን የመሰወር ጥቅሞች
===================
አላህ ከማይምራቸው ኃጢአቶች አንዱ ይፋ የሆነውን ነው:: አንድ ሰው በድብቅ የሠራውን ወንጀልም ይሁን ኃጢአት አላህ ሰውሮለት እያለ ለጉራም ይሁን ለበቀል ኃጢአቱን ይፋ ካደረገው የማይማር ምድብ ውስጥ ይካተታል:: በድብቅ የሠራነውን ለመፍትሔ ሰጭ ካልሆነ በስተቀር በምንም (ቱስ) ሊያመልጥ አይገባም:: የሚካስ ከሆነ እዚያው በድብቅ መካስ ነው:: ይፋ ማድረጉ ጥቅም ካለው ብቻ ሊደረግ ይችል ይሆናል::

አንድ ሰው የሆነ የዝሙት ድርጊት አይቶ ለኸሊፋው መጥቶ ሲናገር "ተጨማሪ ሦስት ምስክር አለህን" ቢሉት 'እኔ ብቻ ነኝ ያየሁት' አላቸው:: "በል ወሬውን እንዳትደግመው:: ካልሆነም በቁርአን ሕግ መሠረት 80 ጂራፍ ነው የምገርፍህ" አሉት:: የዝሙት ቅጣቱ ላላገቡት 100 ጂራፍ ሲሆን በጋብቻ ሆነው ለዘለሉት ደግሞ ከወገብ በታች በጉድጓድ ተከተው በድ^ንጋይ ነው የሚ^ወገሩት:: የምጽአት ቀን ዝሙተኞች ከብልታቸው እዥ እና መግል እየወጣ ይመጣሉ:: ጀሃነምም ውስጥ ክርፋቱ ከእሳቱ ይብሳል ተብሏል:: የመረረ ንስሃ መግባትና ወደ ሀላሉ መሄድ ነው:: የተጠበቀም ጌታውን ይጠብቅ::

የሰሞኑ ቅሌት በአንድ ቤተሰብ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን የሀገሩ ሕዝብ ሳይወድ በግድ ሚስቴ አለችበት ወይስ የለችበትም እያለ ቪዲዮ ሊያይና የብልግናው አካል ሊሆን ነው:: ጉዳዩ ይፋ ስለሆነ ፈጻሚዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቦና አረጋግጦ መ^ውገር ነበር የሚቀርፈው:: እኛ ሀገርስ ቢሆን? እንዲህ ያሉ ወስላቶች ይኖራሉ:: የማውቃቸው ስሞታዎችም አሉ:: ከገጠር ዐረብ ሀገር የሚሄዱ እህቶች ላይ የሚፈጸሙ:: እንዲሁም ታዋቂ ሴቶችን እያጠመዱ ቪዲዮ ይቀርጹዋቸውና የዕድሜ ልክ ባሪያ ያደርጉዋቸዋል:: ገንዘባቸውን ይገብራሉ:: ኑ ባሉዋቸው ወቅት ይመጣሉ:: ደግመው ይቀርጹዋቸዋል:: የራሳቸውን ፊት ሸፍነውት የሴቶቹን ግልጽ አድርገውት የሚጫወቱባቸው አሉ:: ራሳቸውን ሊያጠፉ የደረሱና ለመምከር የሞከርናቸውም ጭምር:: ይፋ ቢወጡ ኖሮ ብዙ ትርምስ ይፈጥሩ ነበር::

ሴቶች አደራችሁን:: የሥራ ግንኙነት ወዴት እንደሚያመራ አይታወቅም:: ብዙ ጉዳትች ከሥራ ጋር የተያያዙ ናቸው:: እንደው ፈጣሪን የሚያስረሳ ድህነትም ይሁን ወይም ፊልሞች የፈጠሩዋቸው ስሜቶ ቢይዙዋችሁ እንኳ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ፍሩት:: ባሉና በሞቱ ሰዎች መካከል የሆነ ሕይወት ውስጥ ትገባላችሁ:: The real beast (ጭራቆች) መካከላችን አሉ:: ማንንም እንዳታምኑ:: ወላ ኃይማኖተኛ ወላ ዘመድ ወላ ፍቅረኛ ቢሆን ጥንቃቄ የግድ ነው:: ጥንቃቄዎቻችሁን ያዙ:: አስባችሁበት ሳይሆን ለሥራ በሄዳችሁበት የሚሆነውን አትገምቱትም:: የመሥሪያ ቤት አለቃ ሲያስመሻችሁ ወይም ፊልድ ሲልካችሁ ጥርጣሬ ይኑራችሁ:: ሌላው ስልክ ስትገዙም እራሳችሁ ብቻ ግዙ:: በምንም ተዓምር የሞባይል ቀፎን ከእጮኛ እንዳትቀበሉ:: ብሩን ተቀብላችሁ ግዙ:: ከተቀበላችሁም በባለሙያ ፎርማት አስደርጉ:: የስለላ app ተጭኖ ተሰጥቷቸው ኑሮአቸው መቃብር የሆኑባቸውን አውቃለሁ:: እኔ ጋር የማይመጣ የችግር ዓይነት የለም:: የማኅበራዊና ቤተሰባዊ ጉዳይ ላይ መጻፍ የተውኩት የሚሰሙ ነገሮች ልቤን እንዳያደነድኑት ነው::

በድብቅም ይሁን በይፋ ሁሉንም ነገራችንን የሚያየን አምላካችንን እንፍራ::

የጽሑፉ ዓላማ:- ለቀልድም ይሁን ቅሌቱን ባናሰራጭ

Hasen Injamo

11 Nov, 07:00


የመጀመሪያው ዙር የእሴት ተኮር ፋይናንስ እና የዓለም አቀፍ ስልጠናችን ምን ይመስል ነበር?

በአጭሩ አንድ ሰው አንድን ሥራ ለማጠናቀቅ በመንገዱ ላይ ያሉ ተቋማትና የሚያስፈልጉ ፕሮፌሽናሎችን ማቀናጀት ነው:: እኔ በሕይወት ብኖርም ብሞትም ሰልጣኙ በእነዚያ በኩል ይስተናገዳል:: ሁላቸውም የየራሳቸው የሥራ ፈቃድ ያላቸው ናቸው:: Independently or jointly አለን:: የስልጠናው ፍሰት እንደሚከተለው ነበር::
=========

ከጠቅላላ ዕውቀት:-

እሴት ተኮር ሲባል:- አንድ ሰው ግብ (Goal) ማስቀመጡ ጥሩ ነው:: ግን አንግልና አግዳሚ እንዲሁም መረብ ያለው የሕይወት ግብ ማስቀመጡ ብቻው ግብ አይደለም:: Well, ወደ ግቡ የሚወስድ ጥበብ (skill) እና ጥበበኛ (systematic) መሆን ይፈልጋል:: ይህም ብቻው በቂ አይደለም:: ሲስተሙ እንዴት እንደተዋቀረ ማወቅ የግድ ይላል:: አዎ! የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሲስተሙ 30% ግሽበት, 15% ቫት እና በየትራንዛክሽኑ የባንክ ቻርጅ ከንጹሕ ገንዘባችን (net pay) ላይ እንክት አድርጎ ይወስዳል:: ግብ ቢኖረንም ባይኖረን እና ቀልጣፋ ብንሆን ባንሆን ፐርሰንቱ ይኸው ነው:: ብድሩ ደግሞ ኮላተራል ቤዝድ ማለትም ማስያዣ እና ትርፋማ ንግድ ይጠይቃል:: ይህንን ሲስተም ካልተረዳን በሥራም ይሁን በትምህርት ጎበዝ መሆናችን ብቻው አይጠቅመንም:: እንዴት ነው የምንሾልከው? የግድ ማወቅ አለብን::

መውጫው ምንድነው? ስንል ከራሱ ከባንኩ ጀመርን:: የሲስተሙ አካሄድ ላይ ስልጠና መውሰድ እና ከሲስተሙ ባለቤቶች ጋር መገናኘት ነበረው:: የባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ ከ18 ዓመታት በላይ የቆየው አቶ መላኩ የዕለቱ ርዕስ የነበረው የኢንተርናሽናል ንግድ ላይ ብቻ ገለጻ አድርጓል:: የመላኩ ትልቁ ድርሻ ገለጻ ብቻ አይደለም:: በቀጣይ ለሰልጣኞቹ ቢዝነሶች ባንኮች አካባቢ እርጥበት (Liquidity) ማሰስ እና አቅጣጫ መምከር ነው:: ዶክመንታችሁን ሥርዓት በማስያዝ ጭምር ያግዛችሗል:: ሰሞኑ በቴሌግራም ግሩፖቻችን ስለፍራንኮቫሉታ መቆምና ቀጣይ ሒደት ትምህርት ይኖረናል:: መሌ ትገባለች::

ይህ ብቻው በቂ ስላልሆነ የእኔ ድርጅት ዲናር ማማከርና ንግድ ከፋይናንስ ተቋማት የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክን መርጧል:: ሲመርጥም የባንኩ የተለያዩ ጠንካራ ጎኖችን አስልቶ ነው:: ምሳሌ:- ባንኩ ከውስጡ አራት ባንኮች ተገንጥለው ወጥተው ችሎ ቆሟል:: ይህ የአገልግሎትና የማኔጅመንት ምንነትን ያሳያል:: ከታች ከገበሬ በመነሳቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ስሙም የመተባበር ባሕል ስላለው ነው:: ማንም ከማይደፍረው ከገበሬዎች ጋር የሚሠራ ባንክ ከከተሜው ጋር አያቅተውም:: Relatively የአበዳሪ ተበዳሪ ግንኙነት ሳይሆን የኢንቨስተር ፓርትነር ግንኙነት ነው ያለው:: በእኔ የግል ዕይታ ነው:: ብዙ ነገር ላይ test አድርጌያቸዋለሁ:: ምሳሌ ባንኮች ከምእመኑ ላይ በወለድ ነጻ ስም ብር ሰብስበው ጭጭ ሲሉ ወይም ከ3% ያልበለጠ ሲያበድሩ COOPBANK ግን ከ80% በላይ ለሥራ አውሎት ነበር:: የሆነ ወቅት ሁሉም ባንኮች በሚባል መልኩ ሁጃጆች ላይ ምንዛሪ ሲያድሙ COOPBANK ግን ያለውን ሁሉ ነው የሰጠው:: ሥራ ካልሆነ በስተቀር ፖለቲካው ብዙም የሚገርመው አይመስለኝም:: እንዳሰብኳችሁ ያድርጋችሁ::

ሌሎች ብዙ ጠንካራ ጎኖች ጋር የአብሮ ለመሥራት መርጬ ለባንኩ ኃላዎች ጥሪ ሳደርግ በሰዓቱ መጥተው ስለባንክ እና ስለባንካቸው ዝርዝር አሠራር ብሎም ሰልጣኙን እንዴት ሊያግዙና በቀጣይም አብረው ሊሠሩ እንደሚችሉ በቂ ግንዛቤ ሰጥተዋል:: የአቶ ባይሳን አጃኢበኛ ፕረዘንቴሽን አመሰግናለሁ::

በቀጣይ የትራንዚተር የአቶ ሙባረክ ናስር ትምህርት ግን ሰቃይ ነበር:: ኢምፖርተርም ይሁን ኤክስፖርተር ምን ምን ማድረግ እንዳለበትና ምን ሲያደርግ ምን እንደሚገጥመው ፍንትው ባለ አገላለጽ አስረድቷል:: እዚህም ጋር ሰልጣኞች እኔን አይፈልጉም:: ሙባረክ ጋር ነው የሚሄዱት:: ስልክ ወስዳችሗል:: ወደኔ እንዳትመጡ:: ዋ!

ሒሳቦች ከ Lazy-man አሠራር ጀምሮ እስከ ውስብስብ አሠራሮች የሚሠራ ሶፍትዌር በአቶ አልታየ በኩል ተሠርቷል:: እኔ የምሠራው በ MS XL ነበር:: ይህንን በቀናት ውስጥ ወደ ሶፍትዌር ቀይሮታል:: አንድ ሰነፍ ነጋዴ ወይም ብዙም ፊደል ያልዘለቀው ሰው ከሚይዘው 4 መስመር ሒሳብ እስከ ብዙ ቅርንጫፍ ላሉት ሒሳቦች ድረስ የሚሠራ ነው:: አንድ ኢምፖርተር/ኤክስፖርተር በሦስት ሀገራት ገንዘብና ሕግ ነው የሚተዳደረው:: ሶፍትዌሩ ሦስት ወይም ብዙ መገበያያዎችን ብቻ ሳይሆን በባንክ እና በትይዩ ገበያ የተገኙ ጥምር ምንዛሪዎችን ብሎም ውጭ ሀገራት ወጭ ተደርገው ግን የእዚህ ሀገር የጉምሩክና የታክስ ሥርዓት የማይቀበላቸው ወጭዎችን ጭምር ያሰላል:: ኮንቴይነሩ ስንት ሜትር ኪዩብ ዕቃ ወይም ኪሎግራም ዕቃ እንደጎደለው ከበጀታችን ጋር ያሰላል:: ሲያልፍ warning ‼️ ያበራል:: በዚያው ቅጽበት cost ምን ያህል እንደፈጀብን, ጉምሩክ ላይ ስንት እንደምንቀረጥ እና ስንት እንደምናተርፍ ያሰላልናል:: ስቶክ ጭምር ማኔጅ ያደርግልናል::

ከሕግ አኳያ ረ/ኮሚሽነር እጥር ምጥን ያለ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል:: የሕግ ድርጅታቸው ከሰልጣኞቹ ጋር አብሮ ይሠራል:: አንድ ነጋዴ ሥራ ከመጀመሩ በፊት, በሥራ ላይ እያለ የሚዋዋላቸው ውሎች ምንነትና counter effects ከዚያም ችግር ቢፈጠር እንዴት እንደሚያስተካክሉ ያሉ አካሄዶችን ለማየት ተሞክሯል:: የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ በየእርከኑ ምን ይፈለግብናል:: እዚያ ጋር ማን አለ? የሚል ነበር/ነው:: የእሳቸው ድርጅት ጋር ትገናኛላችሁ::

እንዲሁም ውጭ ለመጫን ስትሄዱ ማን አለ? ምንስ ይጠበቅባችሗል? የሚሉትን A to Z ለመጠቋቆም ነበር:: በተለይ ቻይና ላይ we are there. ምንም አታስቡ:: እያንዳንዱ ርዕስ ለየብቻው አንድ ስልጠና እንደሚፈልግ እናውቃለን:: የሕጉ ብቻው እራሱን የቻለ ነው:: On job training ይበልጥ ያስተካክለዋል:: ውኃ ዋና እየጠጣኸውም እያሸናህም እያናፈጠህም ከለመድክ በሗላ ልስመጥ ብትል አትችልም:: እናንተ ማራቶን ሯጮች ብትሆኑ እኛ መንገድና መተጣጠፊያውን አመላካቾች ነን::

ለ2ኛ የተመዘገባችሁ የፊታችን ቅዳሜ ጠዋት ነው:: ወደ ቴሌግራም ግሩፕ እሰበስባለሁ::

Hasen Injamo

10 Nov, 09:00


የጥንቃቄ መልዕክት ለአየር መንገድ እና ለሕንጻ ባለቤቶች:-

በእሳትና መሰል አደጋ ወቅቶች ሰውዉ ከአደጋው ከመራቅና ከመታዘዝ ይልቅ ቀርጾ ወደ መፖሰት ላይ ያተኩራል:: ስለዚህ "በአደጋ ወቅት መቅረጽ አይቻልም:: እኛው ቀርጸን እንፖስተዋለን" የሚል መልዕክት ቢለጥፉ ጥሩ ነው::

Hasen Injamo

09 Nov, 17:24


የ1ኛ ዙር ስልጠና ዛሬ ጨርሰናል:: ዝርዝሩ እንደተጠናቀረ እፖስታለሁ:: የ2ኛውን ዙር የተመዘገባችሁ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ነው የሚሰጠው:: ተዘጋጁ:: ሰኞ ለመረጃ መለዋወጫ የቴሌግራም ሊንክ እልክላችሗለሁ::

Hasen Injamo

09 Nov, 16:50


አዎ ባሕላችን ክብራችን አይፈቅድም
=======================
ሶሻሊዝምና ካፒታሊዝም ሲመጡ ካጠፉዋቸው ነገሮች አንዱ የባሕል ዘፈኖችን ነው:: የኃይማኖት አክራሪነቶች ደግሞ ሁለቱን ተከትለው መጥተው ሁሉንም ነገር "ክልክል ነው" ብለው ለማቀብ ቢሞክሩም መንገዱ እራሱ መምህራኑን (ኡስታዞችና ፓስተሮችን) እንክት አድርጎ በላ:: ኃይማኖት ሳንቲም ከመልቀሚያነት የዘለለ ፋይዳ የሌለው መሰለ:: ጥሩ ኡስታዞችና ጥሩ ፓስተሮች አቅም እስኪያጡና ድምጻቸው የውቅያኖስ ውስጥ ጩኸት እስኪመስል ታፈነ:: ጥበብ ማለት ትርጉሙ አስረሽ ምችውና ፍትወት ሆነ:: የተፈቀደን ነገር ካቀብን corrupt የሆነ ትውልድ ይበቅላል:: መረንም ሳይለቅ አጉልም ሳይጠብቅ ማኅበረሰቡ በታላላቆቹ ስር መሆኑ አማራጭ የለውም:: ጥበብን ለጥበበኞች ሰጥተን, ጥሩ ሲሠራ እያወደስን, ብል^ግናን እያኮሰስን ከሄድን ለልጆቻችን ጥሩ environment እንፈጥራለን::

በዚህ ሁሉም ነገር በብል^ግና በሚገለጽበት ወቅት ሙሐመድ አደም የሚባል ወጣት ከጉጂ አካባቢ ከወላጅ ፈቃድ ውጭ መሳሳምን ጠይቆ በሴቷ በኩል ግን "ባሕሌ አይፈቅድም, ክብሬ ይጎድፋል, ከማኅበረሰቤ ያስወጣኛል, ያዋርዳል, የቤተሰብን ክብር ይነካል" የሚል ጥበብ ይዞ መጣ::

በአሁን ወቅት የሚገርማችሁ ብዙ እህቶች በድንግልና ቶሎ ያገባሉ:: ገጠር እንዳይመስላችሁ:: እዚሁ አዲስ አበባ:: ምክንያቱም ትምህርት ፋይዳው እምብዛም ሆነ:: ቢቀጠሩም ለወር አያደርስ, ዲግሪ ቢጭኑም ልጅ ከማስጠኛ አላልፍ እያለ አስቸገረ:: በትምህርቱ በጣም ከገፉ የመውለጃ ጊዚ አላፊ ሆነና በአስራዎቹ መጨረሻ ከእነክብራቸው ማግባትን ወደ መምረጥ ሄዱ:: ይህ ጥሩ አብዮት ነው:: ወንዶችም ክብራችሁን ጠብቃችሁ ክብሯን የጠበቀችውን በክብር አግቡ:: ባሕላችንን እንጠብቅ::
_
ሸኾቹ ዘፈን ሀራም አይደለምን? የሚል አይጠፋም:: የዘፈን ቀርቶ የንግግርም የምግብም ሀራም አለው:: የሀላልና ሀራም መሠረቱ ጥሩ እና ቆ^ሻሻ ሲሆን naturally የቆሻ^ሻነት መሠረት ሸይጧን ነው:: ወደ ሸይጧን መንገድ የሚወስድ ሀራም ሲሆን ወደ መልካም መንገድ የሚመራ ግን ሀራም ሊሆን አይችልም::

ዝሙት በድብቅ ሲሆን ጋብቻ ግን በይፋ ነው:: በጋብቻ ወቅት ቢያንስ በከበሮ ይፋ ማድረግ የተወደደ ሲሆን እንዲህ ያሉ ጥበቦች ለሰርጎች ቢደረጉ ፋይዳቸው ብዙ ነው::

Hasen Injamo

08 Nov, 16:52


የጉራጌ ፈላስፋ እንደሚለው:- ጠዋት በባዶ ሆዳችሁ ቁርስ አትብሉ:: ቀድማችሁ ውኃ ጠጡ::

Hasen Injamo

08 Nov, 15:44


ገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ምርቶች ላይ ክልከላ ጣለ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዘይትን ጨምሮ ያለውጭ ምንዛሬ ፍቃድ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች ላይ ሚኒስቴሩ ክልከላ እንዳደረገ ነው የገለጸው፡፡

በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያ ዘላቂ በሆነ መንገድ ውጤታማ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ይህን ውሳኔ መወሰን የግድ ሆኖ መገኘቱም ነው የተገለጸው፡፡

በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈጸመባቸው እቃዎችም ከዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ጀምሮ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን የጉምሩክ መስፈርት በማሟላት እቃቸውን ማውጣት እንደሚገባቸው የገለጸው ገንዘብ ሚኒስቴር ይህን እንዲያስፈጽሙም ለጉምሩክ ኮሚሽንና ለብሄራዊ ባንክ ደብዳቤን ልኳል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤው በቀጣይ ዘይትን ጨምሮ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በምን አግባብ በአዲስ አሰራር ይቃኛሉ የሚለው ላይ ግን ግልጽ የሆነ ማብራሪያን አላስቀመጠም፡፡

Hasen Injamo

08 Nov, 07:51


አደንቋሪ ወሬ የምትጋትበትና ምንም ማድረግ የማትችልበት environment

Hasen Injamo

08 Nov, 04:52


ሰሞኑ ፌስቡክም ይሁን ቲክቶክ ባትገቡ ይመረጣል:: ሰው በግሉ ፈልጎ ሄዶ ሊወሳለት ይችላል:: ግን ሲስተሙ እራሱ ፈልጎ ሲያመጣልህ የተሻለው መንገድ አንተ አለመገኘት ነው:: አትገኝ ማለት ተገኝ የሚመስለው በሽ ነው::

Hasen Injamo

08 Nov, 03:49


ሰሞኑ ፌስቡክ ወሬው ስለተጨመላለቀ አለመግባት ይመከራል:: እኔም እየገባሁ አይደለም:: ለቀናት ላልገባ እችላለሁ:: በድብቅ ከተሠሩ እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎችና ኃጢአቶች ይልቅ ትንሽ ሆኖ ይፋ የወጣው ጎጂ ነው:: ገዘፍ ያለ ሆኖ ይፋ የወጣውማ ይመርዛል:: ይፋ ለወጣ ዝሙት መድኃኒት ... ፈጻሚዎችን በድንጋይ መው^ገር ነው:: ዝሙት በደረጃ 2ኛ ካልሆነ 3ኛ ነው::

1ኛ) በአላህ ላይ ማጋራት
2ኛ) ነፍስ ግ^ድያ
3ኛ) ዝሙት ነው::

ዝሙት ከገንዘብ ስርቆት የከፋው የማያዛባው የሕይወት ዘርፍ የለም:: ወላጅና ልጅ, ውርስ, ጋብቻ, የቤተሰብ መዋቅር, ሀገር ምሥረታ ወዘተ በዝሙት ይፈርሳሉ:: በቀላል አማርኛ በአባት ስም መጠራራት ቢቀር የጠቀስኳቸው ሁሉ ይወዛገባሉ:: ጋብቻ ክቡር የሚሆነው ለእነዚህ ሁላ መሠረት ስለሆነ ነው:: ለመጀመሪያው የሰው ልጅ .. ወላጅም ይሁን ልጅ ሳይፈጠርለት ሚስት ነው የተፈጠረለት:: የልጅነትም ይሁን የወላጅነት መሠረታቸው ባልና ሚስት ነው::

Hasen Injamo

06 Nov, 13:08


በቅርብ ወራት እዚሁ የአሜካኖችን ጸባይ ስፖስት ያልተመቻቸው ፍሬንዶች ነበሩ:: አሜሪካውያን ሴትን ፕሬዝዳንት አድርገው አያውቁም:: ከዚህ በፊት ከነጭ ሴት ይልቅ ጥቁር ኬንያዊን መርጠዋል: ዘንድሮም በዝረራ ጥለዋታል:: አሜሪካውያን ያስፈርማሉ እንጂ አይፈርሙም:: የሕጻናት, የሰብዓዊ መብት, የጸረ ሰው funጅ ምናም አይፈርሙም:: በአካውንቲንግኛ ብንሄድ እንኳ Generally Accepted Accounting Principles (GAAP)ን ነው የሚጠቀሙት:: እኛን ጨምሮ ዓለም ግን ወደ IFRS እየገባ ነው:: በኦዲት ከሄድን የዶላር አታሚ ቡድኖች ሒሳብ ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት አይመረመሬ ሆኖ ቆይቷል:: ቢመረመርም ውጤቱ ግልጽ አይደረግም:: "ዶላር ሊወድቅ ስለሆነ ክሪፕቶ ግዙ" የሚሉ እንሰማ ነበር:: ምን ላይ ቆመሽ ምን ላይ ትወድቂያለሽ ነው ነገሩ:: የዶላሩ ሲስተም እራሷ አሜሪካ ብትፈልግና ብትተባበር እንኳ በቀላሉ አይወድቅም::

Hasen Injamo

06 Nov, 08:32


መቼለት ቢሮ ለቢሮ እየተንከራተትኩ ነበር:: ካሉ ቢሮዎች ውስጥ አንዱ ጋር ገባሁ:: አስፈጻሚዋ ባንኮኒውን እንደ ጋሻ አድርጋ ኮምፒውተርዋ ላይ አፈጠጠች:: እኔም ስመጣ እኔው ላይ አፈጠጠች:: ተፋጠጥን:: ብዙም ሳትሰማኝ መለሰችኝ:: በጣም ተናድጄ ወጥቼ ከመኪና ውስጥ ምዥርጥ አድርጌ ጣቶቼን ቃታው ላይ አቀባብዬ ተመልሼ በባንኮኒው ሳይሆን ወደ ውስጥ ገባሁ:: ፊቴን ትታ እግሬን አየችው:: አውራ ጣቴ የኤርገንዶው የጣት ማስገቢያ ላይ ተቀባብሏል:: ያቀባበልኩት ያልኳችሁ የእግር አውራ ጣቴና ከጎኑ ያለው ጣት በairገንዶ ክፍት ጫማ በአንድ ቀዳዳ ደርቤ ከተትኳቸው ለማለት ነው:: ምስኪኖች ምን ይቀባበላል ብለህ ነው? ከላይ አዲስ ሸሚዝ በአዲስ ሱሪ ለብሻለሁ:: ከታች ግን ኤርገንዶ:: መጀመሪያ የለበስኩት ስኒከር ነበር:: አላየችውም:: ያለኝ አማራጭ ሙዷን መስረቅ ነበርና ከመኪና ውስጥ የነበረውን ጥቁር የነተበ ኤርገንዶ አድርጌ ስገባ የሆነ ቦታ አየር የተጋጨብኝ መስሏት በደንብ አስተናገደችኝ:: ትክክለኛ መረጃ ሰጥታኝ ወደ ሌላ ቦታ ጠቆመችኝ:: "እገሊት ነች የላከችኝ" በል ሁላ አለችኝ:: ወደ ተባለው ቦታ አድሬ ስለሄድኩ ስሟም ጠፋኝ:: ግን አለቀልኝ:: In case በ Airገንዶ ካያችሁኝ እኔው ነኝ:: የሆነ ሌላ ሀጃ ይዞኝ ነው የሚሆነው::

Hasen Injamo

05 Nov, 10:31


አሜሪካ ከዓለም ከ40 ትሪሊዮን በላይ ተበድራለች ይባላል:: ከእኛው የተበደረችውን አትርፋ ታበድረናለች:: ኢትዮጵያም ከአይ ኤም ኤፍ ተበ-ድራ አበደረች:: ብልጠት እንዲህ ነው:: ቻይና መንገድ የምትሠራልን ብዙውን ከራሷ አምጥታ ሳይሆን ለአፍሪካ የሚመጡ የሆኑ ፈንዶች አሉ:: ባለፈንዶቹ ውጤቱን ይፈልጋሉ:: ብድሩ በእኛ ስም ቢመጣም ዓለም አቀፍ ተቋራጭና ተቃራጭ ሆነው ይመጣሉ:: ፈንዱን አየር ላይ አቅጣጫ አስቀይሰው ይጠልዙታል:: ኢትዮጵያ ማበደርን በደቡብ ሱዳን እየተለማመደች ነው:: አትርፈን ማበደራችን ሳይሆን ለማበደር መው-ጣታችን እራሱ ትርፍ ነው:: ለደቡብ ሱዳን ፊያት ሰጥተን በወርቅ መቀበል እንዳይዘነጋ:: አደራ:: ሌላም እንደዚህ ጠቆር ጠቆር ያሉትን እየፈለግን አበድረን ተለማምደን ከዚያ ወደ ጠይሞቹ ከዚያ ወደ ብጫዎቹ እንሄድና በመጨረሻም ለራሰ በራዎች እናበድራለን::

Hasen Injamo

05 Nov, 10:11


ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች (ካፒታል)

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው ሲል ካፒታል አስነብቧል።

Hasen Injamo

05 Nov, 09:10


ቢዝነስ ካርድ ሕትመት

ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

https://t.me/Teraraprinting1

https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

Hasen Injamo

05 Nov, 08:00


ያልሰረዝኩት የባንክ አካውንት አለ እንዴ? 2ኛው ዙር ስልጠናው እኮ የዚያኑ ዕለት ሞልቷል። ፎርማታችን ሰው እንዲበዛ አልፈግንም። ከሰለጠነው ወደ ሥራ የሚቀጥለውን ፊልተር ማድረግ ስለሚያስፈልግ ሰው እንዲበዛ አልተፈለገም። ብር ባታስገቡ ይመከራል። በሀብትም በጤናም ክበሩ። (ዲናር ማ.ን.)

Hasen Injamo

04 Nov, 16:19


መካሪና ተመካሪ

Hasen Injamo

04 Nov, 14:06


በሁሉም አካውንቶቼ ፖስት ማድረግ በጣም የቀነስኩት አንድ ነገር ከተደጋገመ የመሬት መንቀጥቀጥም ቢሆን ይናቃል:: የመጀመሪያው ቀን መንቀጥቀጥ ወቅት ባይፖስት እንኳ ያልኮመተ አልነበረም:: የጀሞና የኮዬ ምእመናን ሌሊቱን ውጪ ነው ያሳለፉት:: ሲደግመውና ሲሰልሰው ተናቀ:: እንደውም "ማግማው" ወደ መሬት ተረጋግቷል የሚል ትንበያ ከዶክተሩ ሲሰማ ከፋው:: ሰው እንዴት እንደተረጋጋ ለማወቅ ጓጓ:: ለነደደው ኑሮ ከማግማው መፍትሔ ይኖር ዘንድ ሻ::

ሴትና ፖስት አታብዛ:: ትናቃለህ::

ምናለ ይዞልን በሄደ የሚል ኮሜንት ያስቦልካል::

Hasen Injamo

03 Nov, 11:17


የጥንቃቄ መልዕክት | ቦታ እና መሬት በረቀቀ ዘዴ ወስደው በስማቸው ካርታ ያወጡ አንዳንድ "ባለስልጣናት" ቤታቸውን እና መሬታቸውን መሸጥ ጀምረዋል እና እንዳትታለሉ።

ጓደኛችን ህጋዊ ካርታ ያለው መሬት ወይ ቦታ የሚሸጥ ሰው እያፈላለ፥ ከብዙ ደላሎች ጋር ሲያመራርጥ ከቆዬ በኋላ በጥሩ ዋጋ የሚሸጥ መሬት ያገኛል።

ከመሬቱ ባለቤት ጋር በዋጋ ተደራድረው፣ ህጋዊነቱን ለማረጋገጥ ወደ ክፍለከተማው ሲያቀኑ፤ እዚያ የነበሩት ሰዎች ፡ንፁህ ነው፣ ካርታም ያለው ህጋዊ ነው" በማለት ያረጋግጡላቸዋል ።

ይህንን ቦታ ካርታ እያለው ህጋዊ የሆነ መሬት ካርታ ግን አሻራ የለውም። ማዘጋጃም አይቀበለውም ። በአዲሱ ህግ መሰረት: አሻራ የሌለው ቦታ ያለውም ሆነ አሻራ የሌለው ይዞታ ገዝቶ የተገኘ ሰው ቤቱም ሆን ይዞታው ይወረሳል ።

ባለስልጣናቱ ለራሳቸው የወሰዱትን መሬት በአሻራቸው ካረጋገጡ የሚጠብቃቸው እስር ስለሆነ (ተራ ግለሰቦችም በማጭበርበር ያገኙት በመሆኑ) ለሌላ ሰው እየሸጡ መላቀቅ ፈልገዋል።

ይህንን መሬት ሊገዛ የነበረው ጓደኛችንም የመሬቱ ሻጭ የካቢኔ አባል መሆኑን ይሰማል። ካርታውን በአሻራ የተረጋገጠ አለመሆኑን እና ሰውዬው ይህንን ካርታ በአሻራ ማስመዝገብ ያልቻለው ስልጣኑን በመጠቀም ያገኘው በመሆኑ እንደሆነ ይደርስበትና : የግዢው ስምምነት ይቋረጣል።

ባለስልጣናት ከአንድ ህጋዊ ቤታቸው በቀር ሌላ እንዳይኖራቸው የሚቆጣጠረው ይሄ አሰራር መጀመሩ፣ ያለአግባብ ቦታ እና መሬት በራሳቸው ስም የሰበሰቡትን ሰዎች በእጅጉ በማስጨነ፥ በስማቸው ያሉትን ቤት እና መሬቶች መሸጥ በመጀመራቸው፣ ህብረተሰቡ ይህንን ተረድቶ: አሻራ የሌለው መሬትና ቦታ በመግዛት ለኪሳራ እንዳይደረግ፣ እንደዚህ አይነት ስምምነቶችን እንዳይፈፅም እባካችሁ ዘ-ሐበሻዎች መልዕክታችንን አድርሱልን።

ኢፋ ነኝ ከሰፈረ ጎፋ፣ አዲስ አበባ።

Hasen Injamo

03 Nov, 07:01


ሁለተኛ ሚስት የሚመኙት
- የባንክ አካውንት ባላንስ መሴጅ የሚደርሳቸው የብር መጠን የ FM 📻 ራዲዮ ጣቢያ ጋር ይመስላል::

ቢያንስ ስልክ ቁጥር አስመስለውና ተመኝ ብትለው የአምቡላንስ ወይስ የእሳት አደጋ ሊልህ ይችላል::

Hasen Injamo

02 Nov, 20:12


በመምሕራን እና ሐኪሞች ደመወዝ ጉዳይ እጅግ በጣም ከሚያዝኑት ነኝ:: The most essential the most ignored ዘርፍ ነው:: ሐኪም እና ፕሮፌሰር የሚሆነው በጣም ጎበዙ ተማሪ ነው:: ዘርፉ ከግብረገብነት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ መሽሎክሎክ አይመችም:: የመማርም ይሁን ልጆችን አጎብዞ የማስተርን ሞራል በእጅጉ እየጎዳ ነው:: ልጅህን ጎብዝ ማለት አስፈሪ ወይም አጠራጣሪ አድርጎታል:: ጎበዝ ተማሪ አሳቃቂ ኑሮ የሚኖር ከሆነ የትምሕርት ካሪኩለሙ መቀየር ነው ያለበት::

Hasen Injamo

02 Nov, 19:58


2ኛው ዙር ስልጠናም በግማሽ ቀን almost ስለሞላ አንስቼዋለሁ:: እጅግ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ:: የተመዘገባችሁ ሊንክ እልክላችሁና ወደ ግሩፕ ቴሌግራም ትገባላችሁ::

Hasen Injamo

02 Nov, 18:05


የመምህራን የምግብ (Canteen )ፕሮግራም ዓይነት ቢቻል በየመሥሪያ ቤቱ መኖር ያለበት ነገር ነው:: እሠራበት የነበረው ኢንተርናሽናል ድርጅት ደመወዛችን ጥሩ እና በውጭ ምንዛሪ ሆኖ እንኳ ምግብ እዚያው ነበር የምንበላው:: ከድርጅቱ የሚመደብና ከደመወዛችን የሚቆረጠውን ደምረን ለኮሚቴ ይሠጣል:: Operation Support Department ነበር የሚቆጣጠረው:: ምሳ ሰዓት ሰብሰብ ብለን እየተሳሳቅን እንበላለን:: እዚያው ቡና እናስፈላለን ወዘተ:: የሚወጣ ሠራተኛ የለም:: ጠዋት እንገባለን:: ሳንወጣ ውለን ነው በሰዓታችን የምንወጣው:: Even ቡናና ሻይም እዚያው ስላለ የሚወጣ የለም:: አዲስ ሠራተኛ የመጀመሪያ ሰሞን ብዙ ሊጠቀም ይችላል:: ከዚያ ግን ትዝም አይለው::
Canteenኑን አንዳንዶች ስታወግዙት ጥሩ አልመሰለኝም::

ምናልባት ያንተው ድርጅት በቂ ደመወዝ ስለሚሰጥ ምንም ላይመስላችሁ ይችላል ትሉኝ ይሆናል:: እንደውም የመምሕራኑን በጤናማ ይዘነው መቀጠል አለበት:: ለምሳሌ ከመምሕራኑ ትንሽ መዋጮ ቢጨመር ከፍለው እንደሚበሉ ይሰማቸዋል:: ማዕድ እኮ ይሰበስባል:: ማዕድ ያስታርቃል:: የአንድ መሥሪያ ቤት ሰው አንድ ማዕድ ላይ ሲቀርብ ኩርፊያ ቢኖር እንኳ ይጠፋል:: ማዕዱም ይቀጥል:: ደመወዝም ይጨመር::

Hasen Injamo

02 Nov, 12:57


ሊንክ አስቸገረኝ ያላችሁ ፎርሙን ተውትና ብሩን በሚከተለው አስገቡት:: የቴሌግራም ስልክ እንዳትረሱ:: የምታወራርዱም TIN ላኩ:: ስክሪንሹት መላኪያ ቴሌግራም

https://t.me/AbdulkadirN

ETB 7,800

DINAR CONSULTANCY AND TRADE

Cooperative Bank of Oromia

1000096088888

Abdulkadir Nureddin
CBE:- 1000617162001

Telebirr
923115500

Hasen Injamo

02 Nov, 12:29


በግማሽ ቀን almost እየሞላ ነው:: አመሰግናለሁ::
አሰልጥኖ መልቀቅ አይደለም::
ሰልጣኙ ሥራው እስኪገባው couch ማድረግ, ቻይና ከሆነ ከማጋዛት ጀምሮ መጫን ወዘተ ነው::

ትልቁ ነገር ታማኝነት እና ምሥጢርን መጠበቅ ቁልፍ ነገሮች ናቸው:: ብሮችህ ሄደው በትክክል supplier ጋር መድረስ አለባቸው:: የምትጭነው ዕቃ ለ3ኛ ሰው መተላለፍ የለባቸውም:: ለእናንተ ብለን ሳይሆን ለራሳችን ቢዝነስ ስንል ነው::

(2ኛው እየሞላ ስለሆነ በጣም ከተንቦረቀቀ ከሦስት ዙር አያልፍም)::

ፎርሙ

https://docs.google.com/forms/d/1QMHyShnpN38SAZzQzuqDwf34aFBMfsVFPXGYWVTXJ_s/edit

Hasen Injamo

02 Nov, 11:42


ከፊት 2ኛ ተይዘሃል:: በርትተህ ተማር::

Hasen Injamo

02 Nov, 10:31


ስልጠናው ላይ
- የባንክ ጉዳይ የባንክ ሠራተኞች
- የትራንዚት እራሳቸው ትራንዚተሮች
- የቻይና እና ውጭ ሀገር በዚያው ሥራው ላይ ባሉ ሠራተኞች
- ወዘተ ነው የሚሠጠው:: ስትመጡ ጥያቄ አጭቃችሁ ምጡ::

ከእናንተ የሚጠበቀው የምትሠማሩበትን ዘርፍ መወሰን, የተወሰኑ በጀቶችን ማመቻቸት, እንደ ጸባያችሁ ዱቤም አይጠፋም::

እስክትችሉ ድረስ couch እናደርጋችሗለን:: አንድ cycle 🔄 ማለት አንድ ዲግሪ በሉት::

መመዝገቢያ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe_DB4J7S8BekfXoMpkjEarGAJM1N6SQOENYtfe_OQikv38vA/viewform?usp=sf_link

Hasen Injamo

02 Nov, 10:21


መጠነኛ ለውጥ
2ኛው ስልጠና ቅዳሜ እና ሰኞ ሆኗል:: November 16 & 18/2024.

ሠራተኞች አንድ ቀን መስዋዕት ታደርጋላችሁ:: ድሮ ዱባይ ስጀምር ዓርብ ማታ እሄድና ሰኞ ጠዋት መጥቼ በዚያው ቢሮ እገባለሁ ወይም አብዝቼ ሳዛጋ "ዘበኝነት አድረህ ነው እንዴ?" ብለው ይፈቅዱልኝ ነበር::

Hasen Injamo

02 Nov, 08:52


አዲስ ነጋዴ ከአሮጌ ሻጭ ነው መግዛት ያለበት። ምክንያቱም ሁለት ዕውሮች 9 ሺህ ኪሎሜትር ላይ ዕቃ ሊቀባበሉ አይችሉም። በቀላል ምሳሌ አዲሱ ነጋዴ Standard packing list ነው የሚያውቀው። ጉምሩክ ግን ጭማሪ ኮድ ይጠይቃል። ይህንን ስተህ ብታመጣ የምትበላው መከራ አንተና ኮንቴይነሩ ናችሁ የምራውቁት። አሮጌ ጫኞች የኢትዮጵያ ጉምሩኮችን ጸባይ ያውቃል። ስልጠናው ተግባር ላይ የተፈተሸ እንጂ ቲዎሪ አይደለም።

Hasen Injamo

02 Nov, 08:13


የስልጠና ፎርም ፖስቻለሁ:: ፌስቡክ ማስታወቂያ ከመሰለው እይታውን ይቀንሰዋል::

ምሳሌ ችርቻሮ ወይም ጨረታ እየሠራችሁ ይሆናል:: ሆኖም ግን የኢምፖርት ፈቃድ ማውጣት እና ጣጣውን ትፈሩና ትተውታላችሁ:: ይህም መፍትሔ አለው:: ፎርሙ ቅድም ተለቋል::

(በደቂቃዎች ውስጥ ደህና ሄዷል)

Hasen Injamo

02 Nov, 07:29


(እንደሞላ ፖስቱ ይነሳል)
ሁለተኛ ዙር ስልጠና
ለኢንተርናሽና ንግድ
A to Z
Plus Value Based
==============
በተለይ ኢምፖርት ላይ እናተኩራለን:: ከገበያ ጀምረን የባንኮች አይቀረን, የጭነት, የአገዛዝ, የአሻሻጥ ወዘተ::

አንድ ጭነት 8 ሚሊዮን ብር ሆኖ በጀታችሁ ግን 2 ሚሊዮን ብር ቢሆን ምርጥ መፍትሔ አለው:: ለጀማሪ ይህኛው አሪፍ ነው:: ሙሉ ሳይክሉን ያውቅበታል::

በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ውጭ መሄድ አስፈላጊ ቢሆንም ግን መሄድ ላይጠበቅባችሁ ይችላል:: ቻይና ከሆነ በራሳችን ድርጅቶች ይከናወናል::

የምንዛሪ መዋዠቅን በተመለከተ ከባንኮች ጋር ተነጋግረናል:: የትኞቹ እንደሆኑ እንነግራችሗለን::

ቀን:- November 16 & 18/2024 አንድ ግማሽ እና ሙሉ ቀን (ቅዳሜ እና ሰኞ)

ምሳ እና የመሳሰሉትን በድርጅቱ ተካቷል::

ዝርዝሩን ከፎርሙ ውሰዱ::
የክፍያ ሰነዱን ስክሪንሹት አድርጉና አያይዙት:: የምታወራርዱ ሰዎች TIN ስክሪንሹቱ ላይ ጻፉልን::

Hasen Injamo

02 Nov, 05:29


በርካታ ጊዜ የሚገጥመኝ ችግር አለ:: መቸም የእኔ ብቻ አይሆንም:: ከሆነ ጓደኛ or ዘመድ ጋር እየተኗኗርክ በመሃል የማይመችህ ነገር ይኖራል:: ያንን ችግር እንዲቀርፈው ብትጠቁመው ከችግሩ የባሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ወይም ቀልቡን እሰብረዋለሁ ብለህ ዝም ትላለህ or ትርቀዋለህ ወዘተ. ፖለቲካ ላይ ችግር አለ, ችግሩን ለመናገርም ችግር አለ እንዳሉት ሰውዬ ማለት ነው:: እና በቃ ወይ ክፉ ወይ ዝጋታም ወይ ዱርዬ ትመስልላቸዋለህ:: የተሻለው አማራጭ ያ ይሆናል:: አንዳንዴም ችግሩ የራስህ ይሆናል:: ጠፍተህበት ወይም የተሰጠህ ነገር ሳትፈጽም ቀርተህ ተቀይሞሃል:: አንተ የግል በቂ ምክንያት አለህ:: ግን ካንተ እንዲያልፍ አትፈልግም:: ያንን ሰው ለማሳመን የምትከፍተው ሳጥን ሌላ ብዙ ነገር ያበለሻሻል:: ያልሆነ ነገር መስዋዕት ታደርጋለህ:: ስለዚህ አሳማኝ ምክንያት እያለህ ጥፋተኛነትን ተሸክመህ ትኖራለህ:: ምን የከበደ ሸክም!!!

ሰው ምክንያት አለው ብለን እንውሰድ:: የሆነ ሰው በመጠጥ የሚሰክርበት ምክንያት አለው:: ሴተኛ አዳሪ የሆነችበት የባሰ ምክንያት አላት:: ሽፍታ የሆነበት ምክንያት አለው:: ስለዚህ እኛ ሌሎች ባልተፈተኑበት አለመፈተናችንን እያመሰገንን ከጀርባ የማላውቀው ምክንያት አለ ብለን በሰላም እንኑር::

Hasen Injamo

01 Nov, 12:49


ሀገራችን ውስጥ ኒቃብ ለባሽ የሆኑ በርካታ እህቶች አሉ:: ለመማር ጭምር ወጥተዋል:: ማባረር ወይም አውልቃችሁ ግቡ ማለት ብቻው መፍትሔ አያመጣም:: ልክ እንደዚሁ "ትምህርት ቤቱ ሴት ፈታሽ ይቅጠር ሰኪዩሪቲ ያጠናክርኣ" ብሎ መተውም አይፈይድም:: ትምህርት እንዴት ይድረሳቸው? የሚለው ላይ መሠራት አለበት:: ቴክኖሎጂዎች ለዚህ ምቹ ናቸው:: የሁሉም ፎከስ ወይም አጀንዳው ጨርቁን ኒቃብ ነው እንጂ ... ከደህንነት አኳያ ከታየ በአሁን ወቅት የኒቃብ ዐይነቱ ብዙ ነው:: በሜክአፕ የአንድን ሰው ማንነት ሙሉ ለሙሉ መቀየር ይቻላል:: ጾታ ጭምር በተምታታበት አውድ ኒቃቡ ላይ ብቻ ማተኮሩ አግባብ አይደለም:: ጉዳዩ ለሙስሊሙ ብቻ የሚተው አይደለም:: የዓይን እና የጣት እንዲሁም የድምጽ አሻራዎች ቢደረጉ ብዙ ለውጥ ይመጣል:: ፈታሽ ዘበኛውን በአንድ ቀላል ባዮ-ማሽን የሚፈታ ነው:: ትምህርት ቤቶች በር ላይ ይህ ቢቀመጥ ማን እንደገባ ብቻ ሳይሆን ማን እንደቀረም ጭምር ሪፖርት ያደርጋል:: በተለይ ከቴክኖሎጂ ጋር ቅርበት ያላችሁ ሙስሊሞች ብታስቡበት ጥሩ ነው:: ዘንድሮ ባይሳካ በአምስትና አስር ዓመታት ይሳካል:: የኒቃቡ ኺላፍና የፉቀሓእ አቋም ምንም ይሁን ምን ከትምህርት የሚቀሩት የኛው ቤተሰብ ናቸው::

Hasen Injamo

01 Nov, 12:27


አብሮ ፈራሚ (Co-signer)ን ማወቅ ተቀዳሚ ተግባር ነው:: ንግድ ከመጀመራችሁ በፊት የጋብቻችሁን ጉዳይ ቆም ብላችሁ ማሰብ ያስፈልጋል:: ወላጅና ልጅ በሕግ ፊት የተለያዩ ሰዎች ሲሆኑ የትዳር አጋር ግን ዕዳም ምንዳም በጋራ ይመለከታቸዋል:: አጭር ቪዲዮ ከቲክቶክ! ቤቱን መርቁ::
ሊንክ 👇🏼

https://vm.tiktok.com/ZMhCF1EuV/

Hasen Injamo

01 Nov, 03:38


ለሚስት ሳይነግሩ 2ኛ ሚስት
ማግባት almost ፋሽን ሆኗል:: Why?
========================
ኃይማኖት ተፈጥሯዊ ስብእናህን ሸርሽሮ denaturalize ካደረገህ መንገዱን ፈትሸው:: ኃይማኖት የጎደለ ስብእና ካለ ይሞላል እንጂ ያለውን አይንድም:: "እኔ እኮ የተላክሁት መልካም ስብእናን ላሟላ ነው" አሉ ነቢ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم :: ሁለተኛ ሚስት ለማግባት ሊሆን የሚችልባቸው መንገዶች ይኖራሉ:: ግን ስብእናህን በሚቃረኑ አካሄዶች አይደሉም:: ወንድሜ ሚስትህ ሮቦት ወይም እየመጣህ የምትጋልባትና ልጅ የምትጭናት ሴት አሕያ ከሆነች አትንገራት:: ሄደህ ሌላ አሕያ ጫን:: ማንኛይቱም ብትሆን ጠይቀሃት እሺ የሚለት ፍላጎቷ less likely ነው:: ይታወቃል:: መፍትሔው ግን መወሳለት አይደለም::

ሚስት ግን እንደኔው ሰው ነች, ሥጋ, ጅማት, ደም, ቅስም, አቅል, ቀልብ አላት, ይሰማታል, አካሌ ነች ካልክ ሁለተኛ ሚስት አታስብም:: What if የማያስኬዱ እና የማያኗኑሩ major ነገሮች ከተፈጠሩ ተፈጥሮ ላንተ የሰጠችህ upper hand 🤚 አለ:: በተለይ ልጆች ካሉ ቅያሪ ቡታንታ እንኳ እንዳትነካ:: ውልቅ በል:: ከዜሮ ወይም ከኔጌቲቭ ጀምር:: ወላሂ ትደርሳለህ:: ሚስትህ ለነበረችዋ መልካም ዋል:: አላህ መልካም ያሳድርሃል:: የተሻለችዋን ይተካሃል::

የማትበላውን እዚህም እዚያም የምትነካካ ከሆነ ይህ የአይጥ ባሕሪይ ነው:: አንበሳ የሚወደድባቸው ምክንያቶች አሉት:: በተለይ ወንዱ ዝም ብሎ እየወጣ አያድንም:: ለአንደን የሚያበቁ ምክንያቶች መሟላት አለባቸው:: በደንብ ሊርበው ይገባል:: አንድ አድኖ ታዳኙን ቶሎ ማንቁርቱን ገልብጦ እስትንፋሱን ዘግቶ ሩሁ ሲወጣ አንበሳ እርፍ ይላል:: በልቶ አብልቶ ሲጠግብ ፈታ ለማለት ዎክ ይሚመስል ነገር ያደርጋል:: እኛ ደግሞ ከአንበሳም እጅግ የተላቀና የመጠቀ አቅል አለን:: ሕገ-ልቦና ተሰጥቶናል:: ምንም አንወዳደርም::

እና እንደ ሰው ስናስብ:-
- የልጆቻችንን እናት አስተኝተን በድብቅ ስንወሳለት ሕገ-ልቦና ምን ይላል?
- ውስልትናውን ጨርሰን ወደ ቤት ስንሄድ ሕገ-ልቦና ምን ይላል? ዝሙት እንዳይመስልህ:: በድብቅ ማግባት ውስልትና እንደሆነ ስለማምን ነው:: በዚህ የሚበሳጭ "ኡስታዝ" ይኖራል እኮ::
- ዞረን ቤት ከደረስን በሗላ ሕገ-ልቦና ምን ይላል?
- አብረናት ስንተኛ ሕገ-ልቦና ምን ይላል?
- ያወቀች ወቅት ሕገ-ልቦና የሕሊና ሚዛን ምን ይላል?
- የልጆቻችንን ዐይን ስናይ ሕገ-ልቦና ምን ይላል?

በቃ ሰው ሁን! ሰውነት ይቀድማል:: ሴት የተከበረች የአላህ ፍጡር ነች:: አላህ ወንዶች ላይ የጠበቀ ቃልኪዳን ይዟል:: ይጠይቀናል:: ወላሂ!

Hasen Injamo

31 Oct, 15:46


The Chinese never cease to amaze us with their crazy inventions. We find the strangest things from AliExpress for pennies, and you still haven't subscribed !?

👉 View products

👉 View products

👉 View products
https://t.me/+DiVOW7jOH505NTNi
https://t.me/+DiVOW7jOH505NTNi
https://t.me/+DiVOW7jOH505NTNi

Hasen Injamo

31 Oct, 15:40


ቀጣይ የሚመጣው ማስታወቂያ በቴሌግራም በኩል የመጣ ነው። ችግር ያለበት አይመስለኝም። የሚከፍሉኝ በዶላር ስለሆነ ነው የማስተዋውቀው። አዳጊ ቻናል ነው:: ለሞራሌም ለሞራላቸውም እዩላቸው።

Hasen Injamo

30 Oct, 18:16


ቡናና ሻይ አካባቢ ጀርባን ግቢ የሚባል መስጂድ አለ:: ብዙ ጊዜ የጎረምሳ ወፈፌ አይጠፋውም:: ያው የከተማ ለያውም የጨርቆስ ልጅ ወሃb ሊሆን አይችልም:: ሴንተር ስለሆነ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ሰገጦች ነበሩ:: እኔም ገጠር የቆየሁባቸው ጊዜያት ስቦኝ መሰል "ወሃb ገባ ወጣ" ሆንኩ:: ወስላና ጥብስ ደረጃ ሳልደርስ አይቼው ወጥቻለሁ:: አንድ ሰሞን (ቆይቷል) "መማር ሀራም ነው" በሚሉ ወጠጤዎች ተሞልቶ እኛ ኮሜርስ ስንማር የሌባ ትምህርት እንደምንማር ሁላ ሊያሸማቅቁ ይሞክሩ ነበር:: እኔ እንኳ ሰፈሬ ስለነበር አይዳፈሩም:: እና በጣኣኣኣም ያከረሩ ልጆች ኢማሙን ካልደበደብን ብለው ረብሻ አስነስተው ታሰሩ:: ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኛ ወደ ችሎት ሲገባ ሰው ሁሉ ሲነሳ እነርሱ "በካ^ፊ ር ሕግ አንዳኝም" በሚል ቁጭ አሉ:: ያው የፍርድ ቤት ስነሥርዓት ባለማክበር በሚል የሆኑ ወራት ማረሚያ ታዘዘላቸውና እስሩን ጠጥተው በቀጠሮ ቀን አመጧቸው:: እንደው ጠላታችሁ ይታረምና ጠበቆች ገዋን ለብሰው ሲገቡ ሁላ መነሳት ጀመሩ:: እንደውም መዝገብ ቤቷ ለቅሶ ላይ ሆና ጥቁር ለብሳ ነበርና እሷም ስትገባ ተነሱ ይባላል:: ዳኞቹ ቆይተው ሲገቡ ሱጁድ መውረድ ነበር የቀራቸው::

በቅርቡ እንዳያችሁት ሸይኾቻችንን ሲ^ሰድቡ "ቄስ" ሲሉ የነበሩ, ድፍን ሙስሊሙን ዓለም ሁላ ነጻ እናወጣለን ሲሉ የነበሩ ሁላ ዛሬ በሙስሊሙ ፈተና ወቅት, መስጂዶች በሚፈራርሱበት ቦታ ሁላ አካፋና ዶማ አቀባይ ሆነው ቁጭ አሉ:: በምልክት ቋንቋ እንኳ አያወሩም:: ምን ቢካሄድ ትንፍሽ የለም:: ድቤ በሰው እጅ ያምር:: ሲይዙት ያደናብር ነው:: የመጅሊሱን በር አስበርግደው ሲገቡ ውስጡ ምንም የማይሉዋቸው መሻኢኾች ስለነበሩ ነው:: ፖሊስ ሲሆንማ ጀለቢያ ሰብስቦ ሩጫ ነበር:: "አላሁ አክበር" ለሩጫ እንደነበር ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር የታየው:: አቅምህን እናውቀዋለን:: ትሟሙ ዘንድ ወደ ወረዳዎች እንድትገቡ ምኞታችን ነው:: አፉፋ እንኳ እንዲህ መች ይተነፍሳል::

Hasen Injamo

30 Oct, 17:01


ሴቶች በሂጃብ እንዳይማሩ ተከለከሉ

መፍትሔ አፈላላጊ ኡስጣዝ:-
እህቶቻችን ሰብሰብ ብለው መካ ሀረም ላይ ዱዓ ቢያደርጉ አስቸኳይ መፍትሔ ያገኙ ነበር:: በዚያ ላይ በቡድን ከመጡ ከፍተኛ ቅናሽ አድርገናል::

Hasen Injamo

30 Oct, 07:51


አምና እዚሁ መካከለኛውና ምዕራብ የአፍሪቃ ሀገራት አካባቢ ካለ የአንዱ ሀገር የፕሬዝዳነንቱ ዋና አማካሪ ጋር ድንገተኛ የዘመድ ትውውቅ ገጥሞን ረጅም ደቂቃዎች አውርተን ነበር:: (እንግሊዝኛዬ ከየት እንደተሰባሰበ ሁላ ገረመኝ😄):: ሲለኝ "ከ470 ዓይነት በላይ ማዕድናት አሉን:: ሀገራችን ለእርሻ ምቹ ነው:: የውጭ ምንዛሪ መንገዶችን አያሳስብህ:: የብዙዎች ትልቁ ስጋት ደሕንነት ነበር:: የራሽያ ወታደሮችን አስገብተናል:: ደሕንነቱንም እንዳያሰጋችሁ:: ኑልን" ብሎኝ የራሴን የቤት ሥራ ለመሥራት ቆየሁ::

Well, ሀገሬስ? እርሱ የሚላቸው ነገሮች እኛም አሉን:: ግን እኛ እርስበእርስ እየተዋጋን, በጥቃቅን መመሪያዎች እየተንገላታን, በምቀኝነት እየተጠላለፍን ለውጭ አልጋ ለቤት ቀጋ ነን:: እኔ እዚያ ብሄድ በአጀብ በእንግሊዝኛው ከፕሬዚደንትነቱ ተነስቼ ወደ ታች ልወርድ ነው:: በተቃራኒው ግን የሀገሪቱ ዜጎች በሀገራቸው ቋንቋ ሆኖ እንኳ እየተጠላ-ለፉ ዳገት ነው የሚወጡት:: በዚህ የሕሊና ግጭት እና በሀገሬም ምስቅልቅ እያዘንኩ ከረምኩ:: እኔ ሀገሬ ላይ የግብርና ባንክ ባሳካና ለውጥ ባመጣ እመርጣለሁ:: ሰውየው ሀገር ጋር ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ምንነትና ይዘት ጠይቄው ነበር:: ያሳዝናሉ:: የፋይናንስ ተቋሞቻቸው ደካማ ናቸው:: ወደኛ ስንመጣ የተሻሉ ነገሮች አሉን:: በተጨማሪም የአፍሪቃ ሕብረት እዚሁ ስላለን ፈረንጆች የሚበሉትና ተዝቆ አላልቅ ያለው የአፍሪቃውያን ማዕድናት ካዝና እዚሁ ማድረግ ይቻላል:: የእኛ ባንኮች እየወጡ መሥራት ሲገባቸው አካውንት ለመክፈት መንደር ለመንደር ይልከሰከሳሉ:: ጭራሽ የውጭ ነጻ አውጭ ባንክ እየፈለግን ነው:: የተባለው ሀገር ላይ ራሽያውያን ሲገቡ ለመቦጥቦጥ እንጂ የተለየ ነገር አያደርጉም:: እኛም ሀገር ቻይኖች የሚያደርጉትን ነው የሚያደርጉ::

*********
ወንድሜ በጃይ ናይከር ከኢትዮጵያ እዚያ መሄዱ እንደ ቀላል አትዩት:: ትልቅና ፈጣን ጭንቅላት ያለው ወንድማችን ነው:: እንደ ኢንቨስተር ብቻ ሳይሆን እንደ አምባሰደርም እንየው:: አምባሳደሮቻችን ሁሉ የኢንቨስትመንት ዕውቀት ያላቸው መሆን አለባቸው:: ቻይና የሚላክ አምባሳደር የጨሰ ነጋዴ መሆን አለበት:: ቻይና በቆየሁባቸው ጊዜያት የአሜሪካና የቻይና ጉዳይ እያየሁ ነበር:: አሜሪካ ታይዋን ላይ የነበረው የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን ስትዘጋ ትታው አልወጣችም:: ቢሮውን ወደ ንግድ LLC ነው የቀየረችው:: እንደውም ከቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ በላይ ነው የሚሠራው:: ቱርክ ላይ የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ ጎበዝ ነበሩ:: አምባሳደር/ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመም ትልቅ ሥራ ሠርተዋል::

በእርግጥ በጃይ purely የንግድ ሰው ነው:: ለሥራው ትተነው ግን ከሗላው የመንግሥት ደጀን ይፈልጋል ይመስለኛል:: ምክንያቱም እዚያ ሰፈር ተዝቆ አላልቅ ያለ ሀብት አለ:: የዓለም ዐይኖች አፍሪቃ ላይ ነውና እንፈርክ::

Hasen Injamo

29 Oct, 17:13


"ሁሌ ጠዋት ጠዋት የምትደውልልህ Alarm ግን ማነች? ደግሞ እንደደወለችልህ ፍንጥር ብለህ ተነስተህ ቻዎ እንኳ ሳትለኝ ትወጣለህ" በሚል የተነሳ ግጭት አስተካክዬ እየገባሁ ነው:: ይህችማ ፌስቡክ ጀምራ ለባሏ ላይክ ያደረጉለትን እየቆጠረች ውላ ውኃ አፍልታ ልትደፋበት ትችላለች::

Hasen Injamo

29 Oct, 16:28


ፍላጎት ላላችሁ ሰዎች መጫረት ትችላላችሁ:: ሂጅራና ዝምዘም በሀራጅ የሚሸጡ ማስያዣዎችን አውጥተዋል:: ጨረታው ከፉክክር ነጻ ነው ወይ እንዳትሉ:: በነጻ ቁጠባ የተገኘ ገንዘብ በማስያዣ ነው የሚከራየው:: መክፈል ካቃተህ ንብረትህ ይሸጣል:: ይኸው ነው:: መረጃውን ያጋራኸን D.T.ን አመሰግናለሁ::

Hasen Injamo

29 Oct, 15:18


ችግሩ የኢስላሚክ ኢኮኖሚክ ሲስተም ሳይሆን "ኢስላሚክ" ነን የሚሉት የባንኮቹ ነው።
=====================================

ኢስላሚክ ፋይናንስ ሲስተም ከመደበኛው ወለድ መር ኢኮኖሚ በተፃራሪ "ኢቲካል" የሆነ፤ የኢኮኖሚ ፍትሃዊነትን የሚያበረታታ፤ ማህበራዊ ፍትህን ፕሮሞት የሚያደርግ ነው። ባንኮቹ ግን ይህን ስም በመጠቀም ብር ለቀማ ነው የተያያዙት። በዓለም አቀፍ ደረጃም ይሁን በሀገራችንም።

በአገራችን ባሉ ኢስላሚክ ባንኮችም ይሁን የመደበኛ ባንኮች ኢስላሚክ ዊንዶዎች በዌብሳይትም ይሁን በማስታወቂያቸው በአረብኛ ቃላቶች ያሸበረቁ ናቸው። ሁሉንም አገልግሎት እንደሚሰጡ ያስታውቃሉ። ሁሉም የሚያቀርቡት "ሙራበሃ" ብቻ ነው።

የኢስላሚክ ባንኪግ "ኮር ቫሊዩ" ከሚባሉት መሃከል ወለድ ካለመክፈል ባሻገር

➡️ Profit and loss sharing ከደንበኞቻቸው ጋራ አደጋን በመጋራት ፍትሃዊ የትርፍ እና ኪሳራ መጋራት

➡️ Financial Inclusiveness መደበኛው ባንክ ያላገለገላቸውን ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉ ጋር በፍትሃዊነት ማገልገል። የመሳሰሉት ናቸው።

ሙዳረባ እና ሙሻረካ ይህን ሲያሳኩ ሙራበሃ ግን በአጠገቡም አያልፍም። ለአንባቢው ቃላቶቹ ተመሳሳይ ቢመስሉም ጭብጣቸው የሰማይ እና መሬት ያህል ነው።

ሙራበሃ ባጭሩ Asset based, cost+ profit ሞዴል ነው። ባንኩ ንብረቱን ይገዛል ከወለድ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ትርፍ ጨምሮ በብድር መልክ ለተጠቃሚው ያስተላልፋል። ሙራበሃ ፋይናንሲግ ከመደበኛው ፋይናንሲግ ጋር ሲወዳደር ብዙ ጉዳቶች ያለው እና በሸሪዐ ኮምፕሊያንትነቱ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ ያለበት ሞዴል ነው።

የፋይናንሻል ስቴትመንት ዳሰሳ
============================
➡️የንግድ ባንኩ CBE Noor ባለፈው አመት 2002/23 በኢስላሚክ ዊንዶው 9 ቢሊዬን ፋይናንስ ያደረገ ሲሆን 100% ሙራባሃ ነው። ሙሻረካ፤ሙዳረባ...ከማስታወቂያ። ፍጆታ እና ማደናገሪያ አላለፉም።

➡️ አዋሽ ባንክ እንዲሁ በ2022/23, 6.3 ቢሊየን ኢስላሚክ ፋይናንስ ሲያደርግ 100% ሙራባሃ እንደሆነ ዘግቧል።

➡️ሂጅራ ባንክ በ2022/23 አመታዊ ሪፖርቱ 2.9 ቢሊዬን ፋይናንሲንጉ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ለሙራባሃ ነው።

➡️የዘምዘም ባንክም ፋይናንሲንግ እንዲሁ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ለሙራባሃ
ሁሉም አመታዊ ሪፖርታቸውን ድረገፃቸው ላይ ስለጫኑ ገብቶ መጎብኘት ይቻላል።

እና ምን ይሁን? ከወቀሳ ባሻገር።
=====================
የፍራክሽናል ሪዘርቩ እና የፊያት ገንዘቡ ጉዳይ ኮንቬንሽናል ይሁን የኢስላሚክ ባንኮች ላይ ያለ ችግር ስለሆነ ወደ ጎን እንተወውና ቢያንስ የሀገራችን ኢስላሚክ ባንኮች ምን ያድርጉ?

1️⃣ ከማስታወቂያ ፍጆታ ያላለፉት "ሙዳረባ"እና "ሙሻረካ" ን ተግባር ላይ አውሉት።

Mudarabah (Profit Sharing):
ባንኩ ካፒታል አቅርቦ ደንበኛው ሃሳቡን ይዞ በሽርክና የሚሰሩበት አሰራር ነው። ትርፉ በተስማሙበት ሬሾ የሚከፋፈል ሲሆን ኪሳራ ካለ ባንኩ ብቻውን ይወጣዋል። ይህ የባንኩን የፕሮጀክት አዋጪነት ግምገማ ችሎታ ይጠይቃል።

Musharakah (Joint Venture)
ባንኩ እና ደንበኛው በጋራ ፕሮጀክት ወይም ንግድ ላይ ኢንቨስት አድርገው። ትርፉን እና ኪሳራውን እንደ ሼራቸው የሚከፋፈሉበት ነው።

2️⃣ ፍትሃዊ ክፍፍል ላይ ስሩ። በብላሽ ያለ ወለድ የሰበሰባችሁትን ብር ከኮንቬንሽናል ባንክ በበለጠ ወለድ ከምታከራዩት። ቢያንስ ባንኩ ላይ ለቆጠቡ ሰዎች በአነስተኛ ማርክ አፕ አቅርቡላቸው።

3️⃣ Unique Islamic Identity ይኑራችሁ።አሁን ባለው ሁኔታ የሀገራችን መደበኛ ባንኮች በኢስላሚክ ዊንዶው ከሚያቀርቡት በተለየ ኢስላሚክ ባንኮች ከሚያቀርቡት ፕሮዳክት የላቸውም።

4️⃣ Outreach The diaspora። በተለይ በመሃከለኛው ምስራቅ እምቅ ፖቴንሻል አላችሁ። Design suitable product and outreach Them.

5️⃣ ከሁሉም ከሁሉም ዘርፉ "በዳኢ" ብቻ ሳይሆን በብቁ ባለሙያ ይመራ።

ያለበለዚያ "ሚሽን እስቴትመንታችሁ" ላይ ሸሪአ ምናምን የሚለውን አውጡና በግልፅ "Only maximizing share holders profit" ብላችሁ አውጁ። በጀነት አታስፈራሩን።
via Aminu Nuru የፋይናንስ ባለሙያ

Hasen Injamo

29 Oct, 03:01


ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

ልብስ ላይ ህትመት :-


=ቲሸርት
=አንፀባራቂ
=ሁዲ
=ባንዲራ (ለድርጅት እና መሰል )
=ጃኬቶች
=የስራ ልብሶች
=የስፖርት ማልያዎች እና ትጥቆች

ወረቀቶች

=በራሪ ወረቀት
=የሰርግ ካርድ
=ቢዝነስ ካርድ
=ፖስት ካርድ
=ደረሰኝ
=የሃኪም ቤት እና መሰል ካርዶች
=መፅሄት
=መፅሐፍ
=ተለጣፊ ወረቀቶች
=ትኬቶች
=የሃዘን ካርዶች
=ለድርጅትዎ ፖስታዎች ወዘተ

ሌሎች

=ባነር
=ማግ
=ሾፒንግ ባግ
=ሕጋዊ ማህተሞች
=ላይት ቦክስ
=ማይካ
=ድጅታል መታወቂያ እናትምልዎታለን
=እስክርቢቶዎች
=ለኮምፕዩተርዎ ማዉዝ ፓድ
=የድርጅትዎ የቁልፍ መያዣዎች
= የድርጅትዎን አርማ የያዙ ማስታወሻዎች (note book)
= ወዘተ

ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

👇
https://t.me/Teraraprinting1

https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

ሎኬሽን 👇
https://maps.app.goo.gl/heRTnskHQDUj2jgQ9

Hasen Injamo

28 Oct, 02:51


ከፈለግህ በ500 እንሂድ

Hasen Injamo

28 Oct, 02:48


https://vm.tiktok.com/ZMh95JGo9/

Hasen Injamo

27 Oct, 16:52


ስለገንዘብ እና ዘዋሪዎቹ በጥልቀት አጠናሁ:: ልክ የዓባይን ምንጭ እንዳጠናው ሰውዬ ምንጩን እና መፍሰሻ ቦዩን ካወቅሁ በሗላ ገንዘብን የማሳደድ ሩጫ ትቼ ቤቴ ገባሁ:: ገንዘብ የሚያልቅ ይመስለን ነበር:: ለካ የማያልቅ infinite number ሆኗል:: እናልቅ ይሆን እንደሆን እንጂ አንጨርሰውም:: በጥበብ ካልሆነ በልፋት አይደረስበትም:: ስለዚህ ከአባታችን አደም አንስቶ እስከ ዘመናችን ድረስ ምን እንደሚመስልና ምን ላይ ማተኮር እንዳለብን መ-ገንዘብ የሚል መጽሐፍ ጻፍኩ:: በታተመ በአምስት ቀኑ አለቀ:: አልደገምኩትም::

ዐለም በጥቂት 1% አልአሙዲኖች እና 99% አጣሙዲኖች ተከፍሏል:: ሚድሮክ ስትሠራ ደመወዝህ ዳሸን -> ዳሸን ለኤልፎራ -> ኤልፎራ ለኩዊንስ ሱፐርማርኬት -> አንተ ከኩዊንስ ገዝተህ ትመገባለህ:: አዋሽ ወይም አቢሲኒያ ወይም ሕብረት ወይም ወጋገን ወይም ሂጅራ ባንክ ብትሄድም አሰላለፉ ይኸው ነው:: በብሔርና በቤተሰብ ተደራጅተው ነው የያዙት:: ስለዚህ ካዝናው ጠርቀም ሲል በሗላ በር ለድርጅታቸው ይስቡታል:: አንተ አኗኗሪ ነህ:: የማይደርስህን እቁብ ትጥላለህ:: ከጎደለባቸው ከእያንዳንዱ ትራንዛክሽን ላይ ያስከፍሉሃል:: ሞባይልህ ላይ ጭነውልህ ከፍለሃቸው ነው የምታገለግላቸው:: ማን ምን እንደበላ ያውቃሉ:: ይህ ፒራሚድ እየሾለ ሄዶ አሜሪካ 12 ወንድማማቾች ጋር ይደርሳል:: በአንድ ዓይን 👁️ ያዩሃል::

Hasen Injamo

27 Oct, 15:33


ቡታጅራ
ነቢ ሙሐመድ ﷺ ዓለምን የመሩበት ቤታቸው ከእነግቢው 70 ካሬ አይሞላም:: ግማሹ እሳቸውን ﷺ ጨምሮ ሦስት ሰዎች ሲቀበሩበት ቀሪው 30 ካሬ ባለቤታቸው ለ40 ዓመታት ኖረውበት ሙስሊሙን መርተውበታል:: የዱንያ ግሳንግስና ኮተት አላስፈለገም:: ቡታጅራ በኢጅቲማዕ ታሪክ ሪከርድ የሰበረ እና የሀጅ ስብስብ ጋር የሚዳረስ ሰው ሲካሄድ የሚዲያ ጥሪ የለም:: ቴሌቪዥንም ይሁን መጅሊስ አላስፈለጉም:: በጀት የለውም:: ቀድሞ የተሠራ አዳራሽ የለም:: Use and dismantle ጨርቅ ነው የተጋረደው:: የተሰበሰበው ሰው ደግሞ ከየዓለማቱ ነው::

የዚህ የዳዕዋ ሲስተም ምሥጢሩ ከልብ ውስጥ የፍጡራንን ታላቅነት አውጥቶ የአላህን ታላቅነት መክተት ነው:: ገንዘብ ያጋጫል:: ከመካከላችን ካስወገድነው እንስማማለን በሚል ነው የተዋቀረው:: ሀብታምም ደሃም ለግላቸው እኩል ነው የሚያዋጡት:: አንድ ሰው ጋር ይሰበሰብና ሀጃቸውን ሲጨርሱ የተረፈውን እኩል ይመልሱታል::

የሚሰማህ ሰው ይኑርም አይኑር ሳምንታዊ የዳዕዋ ቦታህ ላይ ትቀመጣለህ:: የታመመ ኖረም አልኖረ ዚያራ ትወጣለህ:: የደሕንነት ስጋት ኖረም አልኖረ ሒራሳ (ምድብ ጥበቃህ) ላይ ትቆማለህ:: ቢገባህም ባይገባህም ትማራለህ:: የሚያገራው አላህ ነው:: ዘንዶ እና ዱርዬ ያለበት ሰፈር ገብተህ ወደ መስጂድ ታመጣለህ:: ድህትህና ከፈንህን ይዘህ ትዞራለህ:: ምግብ የምትበላው "ብሉ አታባክኑ" የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ለመፈጸም ሲሆን ዓላማውም ወገብህ ለትእዛዙ ብቻ እንዲቆም ለአመጽ እሺ እንዳይል ነው::

መመሪያው 5,000 ገጽ እንዳይመስልህ:: ግማሽ ገጽ አይሞላም:: 6 ባሕሪያት እና 20 ስነሥርዓት ናቸው:: አለቀ:: መሥራቹ ሸይኽ ሙሐመድ ኢሊያስ ሲሆኑ ከአቡበክር አስሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ዝርያ ናቸው)::

(በፎቶው የምናያቸው የአሁኑ አሚር ናቸው:: ከቡታጅራ)

Hasen Injamo

27 Oct, 14:58


የዚህ ትውልድ ትልቁ ስኬቱ እንደ አባቶቹ ትላልቅ History መሥራት ሳይሆን ኢንተርኔት ላይ የተወሳለተበትን Watching and searching history አጥፍቶ መውጣቱ ነው::

(አጎቴ አብራር ከጨርቆስ)

Hasen Injamo

27 Oct, 08:14


አዲስ ቲክታክ ነው
በተለያዩ ሀጃዎች ተዋክቤ ትቼው ነበር:: በአሮጌ መንፈስ በአዲስ አካውንት እንጨዋወታለን::

https://www.tiktok.com/@abdulkadir.hajj.n?_t=8qsxoTQbbVY

Hasen Injamo

26 Oct, 15:52


ባንኮች ለግብርናው ዘርፍ የሚያቀርቡት ብድር ከአጠቃላይ 1% ሲሆን ለሠራተኞቻቸው 3% ገደማ ይመድቡ ነበር:: መብታቸው ነው:: ምክንያቱም "ንግድ ባንክ" ተብሎ አሁን ባለው collateral based banking ሪስኩ ከፍተኛ ለሆነ ለግብርና አበድር ማለት የማይሆን ነው:: ሌላ ባንክ የግድ ያስፈልጋል:: ለሠራተኛ የሚመደበው ብድር ለቤትና ለመኪና ሲሆን ሠራተኞች እንዳይለቁ በዚህ ይያዙ ነበር:: ይህም ብዙ ነው ማለት አይቻልም:: ያልተበደሩ ሠራተኞች እንዳይለቁባቸው ደመወዛቸውን ቀድመው ተበድረው በ time deposit የሚያስቀምጡም ነበሩ:: ቤት ለሚገዙት ባንኩ ሲያበድራቸው እጅግ አነስተኛ በሚባል በ7.5% ወለድ ነበር:: አሁን ላይ ታክስ ሊጣልበት መመሪያ ተዘጋጅቷል::

ሌላ ተጨማሪ ችግር አለ:: ባንኮች ብዙ ሥራዎቻቸው በ online እየሆነ ስለሆነና በተመሳሳይ ዓይነት ሥራ በባንኮች መሃል ውድድሩ በመክፋቱ ባንከሮች ደንበኛ ለቀማ መንደር ለመንደር መዞር, ከቀብር ሐውልት ላይ ፎቶና ስም በሞባይል በመውሰድ ብዙ ደንበኛ እንዳላቸው በማሳየትና ሙስሊሙን ደግሞ ጺም የሚያከራዩ ሆዳም ኡስታዞችን በመቅጠር ትርፋቸውን ያጋንኑ ነበር::

ከሠራተኞቹ ጉዳይ መቅደም ያለበት ነገር አለ:: ሙስሊሙን በጺም ማጭበርበር ከባንክ ኢንደስትሪ የማይጠበቅ ነው:: ለዛሬ እንለፈው:: ሙስሊም ነው ብለው የገመቱትን ድሮ የከፈተው አካውንቱን ያለፈቃድ በመቀየር በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወደ "ወለድ ነጻ" አዘዋውረዋል:: ልዩ ኦዲት ቢደረጉ በቀላሉ መያዝና ታክስ መሰብሰብ ይቻላል:: የታክስ ይርጋ ሳይገባ ይታይ ብዬ ቀድሜ አሳስቤያለሁ:: ብሔራዊ ባንክም ገቢዎችም ቸል ብለዋቸው 10 ዓመታት ያለፋቸው አሉ:: የእኔን አካውንት ያለፈቃዴ በአንድ ዓመት አራቴ የቀየረብኝ top 5 ውስጥ ያለ ባንክ አለ:: ቢቸግረኝ ስሙን ጠቅሼ ስፖስት ከባንኩ ደውለው እንዳነሳላቸው ሲጠይቁኝ ፖስቱን አጠፋሁት:: ከዚያ በሗላ ከዚያ ባንክ ለ ATM እንኳ አልጠቀመውም::

Well, የባንክ ሠራተኞች የሚያገኙት ጥቅማጥቅም ድጋሚ በልዩ ቢታይ ጥሩ ነው:: ለማዕድን ቆፋሪዎች እና የአበባ እርሻ ላይ ላሉ ሠራተኞች የሚሰጥ የምግብ አበል ገንዘብ ሚኒስቴር በልዩ አይቶት ከታክስ ነጻ አድርጎት እንደነበር አንብቤያለሁ:: ባንኮችም ልዩ ተቋማት ስለሆኑ በልዩነት የመታየት እድል ሊኖረው ይችላል:: በእርግጥ የማዕድኖቹና ከኬሚካል ጋር በንክኪ የሚሠሩ ድርጅቶች ሠራተኞች ምግብና ወተት ነው የሚቀርብላቸው:: ምግቡ ታክስ ይደረግ አይደረግ በሚል ተጠንቶ ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አዘጋጅቶ ነጻ አድርጎት ነበር:: የባንክ ሠራተኞችም ቢታይ መልካም ነው:: ሆኖም ግን በቅድሚያ የወለድ ነጻ መስኮቱን እዩት:: ያለፈቃድ የተቀየሩ ሒሳቦችን አጣሩ:: የቢሊዮኖች ብሮች interest ወይ ለቆጣቢው ይመልሱ:: ወይ ታክስ ይክፈሉበት::

Hasen Injamo

26 Oct, 12:46


Well እንግዲህ
✔️3.9 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ (ለተወሰኑ ቤቶች)
✔️ ቀሪ ክፍያ 18 ወራት በብር
✔️ ሰፈር መስቀል ፍላወር
✔️ ዲጂታል ካርታ ክፍያ በጨረሳችሁ በጥቂት ሰዓታት:: አሁኑኑ ለሚከፍል ወዲያው ውልና ማስረጃ
✔️ ቤታችሁን ገብታችሁ ክፍል መምረጥና በመሃንዲስ ማስፈተሽ ትችላላችሁ
✔️ መስጂድ በቅርብ አዒሻ
✔️ ቤተክርስቲያን በቅርበት መስቀል ፍላወር ጋር
✔️ ሲናጎግ ለደሕንነታችሁ ሲባል ይለፈን:: ግን ባቅራቢያው ባለስድስት ቀንድ ኮከብ ሆቴል አለ
✔️ ምግብ አንድነት ስጋ ቤት, ሰንዓ አሉላችሁ

✔️ የግንባታ ደረጃ 18ኛና የመጨረሻው ፎቅ እየተዘጋ ነው:: ፓርቲሽን 14ኛ ደርሷል:: ፓርቲሽኑ ሳያልቅ ተዋውላችሁ በምትፈልጉት መሠረት አከፋፍሉ::
✔️የውጭ ከለሩ ላይ ማሻሻያ አለ:: ቡኒው ወደ እርሳስማ ይቀየራል::

ዋጋው ርካሽ ክመሆኑም ጋር ውድ ነው ካላችሁ በጣም የሚቀንስ እና ቀስ ብላችሁ የማትከፍሉት ኮሜንት ላይ አለ::

Hasen Injamo

26 Oct, 05:13


🟩 ከ Work ይልቅ network ላይ ብታተኩሩ
🟩 ከ መደበኛ ትምህርት ባሻገር ትክክለኛ ትምህርት ላይ ብታተኩሩ:: ትክክለኛ ትምህርት መሬት ላይ ነው ያለው::
🟩 ወደ ሥራ ከመሄድ ይልቅ ሥራው ወደናንተ እንዲመጣ ዘዴ ብትፈጥሩ

ሪስክን በመዳፈር የሚሠሩ እንዳሉ ሁሉ ሪስክን መዳፈርም ስግጥና ወይም የዕውቀት ማነስ ነው የሚሉም አሉ:: ኤለን መስክ ሲዳፈር ዋረን ቡፌት ግን በጥናት ላይ ተመስርቶ ይንቀሳቀሳል::

መደበኛ ትምህርት ያላችሁ ሰዎች ትንሽ ድፍረት ጨምሩ:: ያኛው የሌለው ነገር ይዛችሗል:: ትምህርት የሌላችሁ ሰዎች ልጆቻችሁ ጋር intimate ሁኑ:: ያግዙዋችሁ:: ቴክኖሎጂ ጎበዝ ናቸው:: ሶሻል ሚዲያ የሚቀጠቅጡበትን ሰዓት ቴክኖሎጂ ይሰልጥኑ::

አንድን ነገር ከመተግበር በላይ በሐሳብ መሸከም በጣኣኣኣም ያደክማል:: ምሳሌ ልስጣችሁ:: በፍቅር ያበዳችሁላት, መርዝ ልትጠጡ ያደረሰቻችሁ ፍቅረኛ ጋር ተጋብታችሁ ያለልብስ ከተያያችሁ በሗላ "አንቺ ነሽ እንዴ? አንተ ነህ እንዴ?" መባባል የሚመጣው እኮ ብዙ ጊዜ በሐሳብ የምንስለውና actually what it is የተለያዩ ስለሆኑ ነው:: በይሆናል ያልሆነ ስእል ሰጥተን እራሳችንን እናደክማለን::

በመጨረሻም በኪሳራ እዬዬና ቂም የለም:: በቃ ተምረሃል:: መቀጠል ነው:: ኪሳራ ከትርፍ ያልተናነሰ ያነቃል:: ብዙ ሰዎች በቅስም ሰባሪ ንግግሮች ተለውጠዋል::

*****
የትም ዓለም ብትዞሩ የትም ሀገር ብትሄዱ የሰማዩንም የምድሩንም ብታካትቱ ... ድርጅቶች 4 ዓይነት ናቸው:: ጠቅላይ ሚኒስትር ብትሆኑ የአራቱን ገመድ ጫፍ ነው የምትይዙት:: ከየት መነሳት እንዳለብህ (pre-requisite), ድንበራቸው (scope and boundaries) እና end goals ማወቅ የግድ ይላል:: በስልጠና ተካቷል::

Hasen Injamo

25 Oct, 17:52


መቼለት ክትፎ አዝዤ ደህና ተመችቶኝ እየበላሁ የጥፍር ቁራጭ ቅርጽ ያለው ሽንኩርት አገኘሁ:: ጥፍር ቢሆን እኮ እገላገል ነበር:: ሽንኩርት ነው ወይስ ጥፍር በሚል ለማረጋገጥ ደቂቃዎች ፈጀብኝ:: በጥርስም በቅምሻም ሽንኩርትነቱን ካረጋገጥኩ በሗላ ... በዚህ ዓይነትማ ጥፍርም ሳይኖር አይቀርም በሚል ክትፎውን ትሪው ላይ ደፍቼ ፍለጋ ገባሁ:: ሰው ማዕድን ይቆፍራል እኔ ግን ከክትፎ ውስጥ ነገር እየቆፈርኩ ነው:: ከአድካሚ ቁፋሮ በሗላ ጥፍር ላገኝ አልቻልኩም:: በእርግጥ በሞባይል ፍላሽ መብራት እንዳልፈልግ ሁለቱ እጆቼ በቅባት ወዝተዋል:: ትንሽ እረፍት ከወሰድኩ በሗላ ሽንኩርት ከጥብስ ሰፈር ተፈናጥሮ ክትፎ ውስጥ የሚገባ ከሆነ ተዝለግላጊ ነገሮችም ከከታፊዎቹ መንጭቶ ሊደባለቅበት ይችላል የሚል ወስዋስ ቱስ ብሎኝ ቀኔንም ምሽቴን ከንቶብኝ ከክትፎም ከዱፎም ሳልሆን አለፈ:: አይ ያንዳንድ ቀን ጥጋብ! አይ ወስዋስ!

Hasen Injamo

25 Oct, 16:58


ጣጣ ያለቀለት ሪልኢስቴት በምትጠራጠሩት ዋጋ በገራሚ ሰፈር በአዲስ አበባ ማዕከል ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር ወደ ቪስኮ ምጡ:: ታመሰግኑኛላችሁ::

መክፈል:- ካርታ ወዲያው በስም ማዞር
_
ቡኒው ዳለቻ ይቀባል::

Hasen Injamo

25 Oct, 15:53


ሰሞኑ ከሱቄ ጎን ጂም ልከፍት አስቤያለሁ::

ክፍያ:- ቀጥናችሁ በዚህ በር ማለፍ ስትችሉ ብቻ ነው::

መግቢያ በር:- በዚህኛው በኩል ነው ያለው:: ሰፊ ነው:: ግን ያው በአሻራ ነው የሚሠራው:: ያው ግን መክፈት ስትፈልጉ በምታዩት በር ነው የምትወጡት::

Hasen Injamo

25 Oct, 13:55


በዚህ ሄዳችሁ ኮንታ በርገር ከበላችሁ ቀጥታ ጨበራ ትገባላችሁ

እድሉ ነው:: እናፐምሰው:: በርገር ሊያስተዋውቅ አምጥተውት ነው::

Hasen Injamo

25 Oct, 03:30


ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

https://t.me/Teraraprinting1

https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

Hasen Injamo

24 Oct, 14:34


ዲናር ማማከርና ንግድ DINAR CT
እሴት ተኮር ፋይናንስ በተግባር
-> ኤክስፖርተር የሆናችሁ ኢምፖርት ብታውቁ ዙሩን ጨረሳችሁት:: IMPEX
-> ኢምፖርተር ስትሆኑ ለውጭ ምንዛሪ ኤክስፖርት የግድ ይላል::
-> ተቀጥረው የውጭ ምንዛሪ የሚያገኙ አሉ:: ዝም ብሎ ይጋ-ሽባ-ል::

Well, ትግበራ እንዴት እንደሚጠቅም ምሳሌ ልስጣችሁ:: አንድ ፍሬንድ $22,352.22 ጭነት አስፈቅዶ የ $22,250 ዶላር ጭኖ አመጣ:: ከዚያ ዕቃ አምጥቶ ሽጦ ምናምን የተወሰነ ቆይቶ ሊጭን ሲያስፈቅድ የብሔራዊ ባንክ ሲስተም $2.22 ዶላር ልዩነት ያሳያል:: ለጭነት የወጣ እያንዳንዱ ሽራፊ ሳንቲም በዕቃ ዞሮ መምጣት አለበት:: ከቁብ ያልቆጠረው ሽራፊ ዶላር ገትሮ ያዘው:: ከኪሴ ልሙላ ቢል የማይሆን ነው:: በሕጋዊ መንገድ የወጣ ዶላር በሕጋዊ መንገድ መመለስ አለበት:: ውጪ ደውሎ በሰው በሰው የመላኪያ ከፍሎ አስገባ:: ከሰፕላየሩ ነው የምንፈልገው ቢሉ እኮ ጉድ ነበር:: በምንም በምንም ብሎ ብዙ ቀናት ፈጅቶ clear አደረገ::

Commercial Invoice ስታሠሩ exact መግጠም አለበት:: ይህንን የሚነግራችሁ ኮሌጅ ሳይሆን ያለፈበት ብቻ ነው:: እኔ ባላለፍኩባቸው ቅያሶች ያሉ ነገሮችን ምንነት አላውቅም:: በስልጠናዎቻችን ወቅት እንወጋጋቸዋለን::

ከዲናር ጋር ወደ ዕሴት ተኮር!

Hasen Injamo

24 Oct, 11:40


ራይዶች አሳዘናችሁኝ
እዚህ ሀገር ሠራተኛ ቀርቶ የሚሠራ ሰውም ጋር ከተመሳሰልክ ችግር ነው:: አሪፍ ንግድ እየነገድክ እንደሆነ ከታወቀ የማይመጣ የደንብና የመዋጮ የችግርና የእንቅፋት ዐይነት የለም:: ዛሬ ዙህር ሜክሲኮ ሰግጄ ቤተሰብ ኢሚግሬሽን ወረፋ ይዛ ሶላት ስለረፈደባት ላነሳ በጥቁር አንበሳ ቁልቁለት እየወረድኩ ከውስጥ የምትወጣዋጣዋን ስልክ ለማውራት ገና ዳር እየያዝኩ ነው:: ከማዶ ትራፊኳ ዳገቱን እየወጣች ነው:: ችግሩ የያዝኩት መኪና 3 ቁጥር ቪትዝ ነበር:: ራይድ መስሏት ይሁን አይሁን እንጃእ:: ራይዶች በትራፊክ ፖሊሶች ስቃይ እየበሉ እንደሆነ ብዙዎቹ ሲያማርሩ እሰማለሁ:: ምክንያቱም ይሰራሉዋ! ሁለት ቁጥር ከያዝክ በተለይ አዲስ መኪና ከሆነ ለወራት ቀርቶ ለዓመታትም ትራፊክ ፖሊሶች አያስቆሙህም:: ካስቆሙህም በአግባቡ ሰላም ይሉሃል:: አሮጌ መኪና ከያዝኩኝ ብሞት በስተቀኝ በዳር አልሄድም:: በቀን 13 ጊዜም ሊያስቅሙኝ ይችላሉ:: አዲስ ስይዝ ግን በአፍንጫቸው ስር ነው የማልፈው::

በግሌ በስህተትም ይሁን ደንብ ከተላለፍኩ ስቀጣ ደስስስስ ይለኛል:: የንስሃ ቅጣት ሁላ ይመስለኛል:: ግን ድሮ "መሽናት ክልክል ነው" የሚል ይለጥፉና ሽንት የወጠረው ሰው ሽንቱን እስኪጀምር ከርቀት ይጠብቁታል:: ሲጨርስ ቅጣት ይሰጡታል:: ጥቁር አንበሳ ቁልቁለቱ ጋር ምልክቱ ከፍ ብሎ ነው ያለው:: በባሕሪዬ አቁሜ የምሄድ ከሆነ ምልክ ሳላይ አልፌ ሊሆን ስለሚችል ተመልሼ ወርጄ አያለሁ:: በአቅራቢያው የትራፊክ ፖሊስ ካለ እጠይቃለሁ:: ሒሳብም ስሠራ ያውቃል የተባለ ሰው ጋር እደውላለሁ::

ከልምድ ትራፊክ ፖሊሶች የከተማ ልጆች ከሆኑ ታስረዳቸዋለህ:: ትግባባለህ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም የገጠር ልጅ ከገጠመህ እና በትህትና ካናገርከው በተለይ "ጌታዬ" ካልከው አለቅልህ:: " ለካ ነኝ እንዴ?" ይላል:: ዛሬ ገና ዳር እየያዝኩ እንደሆነ አይታኛለች:: የመሰላት የራይድ ሥራ ልሠራ ዐይነት ነገር ነው:: "ልትጭን እየቆምክ ነው" አለችኝ:: እያየሽኝ አይደል እንዴ? እያልኩ ትህትና ነገር ሳሳያት ባሰባትና መጻፍ ጀመረች:: መጀመሪያ "ቴሌብር እያለችኝ" ነበር:: የሚያውቁዋትም በፌስቡክ የሚያውቁዋት ፍሬንዶች በዚያ ሲያልፉ ሁለታችንም ሰላም ብለውን ተጫጩኸው ስላለፉ ለእነርሱም ለመለዮውም ክብር በትህትና ስላናገርኳት መሰለኝ ጽፋ ሳታስፈርመኝ ሁላ ቦጭቃ ሰጥታኝ በቴሌብር እንደመቅጣት ወረቀቱን ጋቢና አድርጋ ነካችው:: ወይኔ act! አሃሃሃሃ. አይ ሳጅን ቡርቴ ይመችሽ::

ራይዶችም አላህ ይድረስላችሁ:: በአጋጣሚው ልተንፍስላችሁ ብዬ ነው::

(ለቅሶ ለመድረስ ስጣደፍ አጉል ሆንኩ)

Hasen Injamo

24 Oct, 07:50


በክድሬነት ከተጠረጠርኩ
አይቀር ዜና ሼር ላድርግ
==========

የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ
*****

በዚህም መሰረት፦
1. ኮ/ር ኡማን ኡጋላ ኡቸንግ- ገጠር መንገድ ዋና ዳይሬክተር
2. አቶ ኡገቱ አዲንግ_ የክልሉ ኤች አይ ቪ መከ/መቆ/ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር
3. አቶ ኡቦንግ ኜል_የጤና ቢሮ የጤና/ዘ/ም/ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ኡቦንግ ኡጁሉ_የበጀት ፋይ/ጉ/ኦዲት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
5. ዶ/ር ኝግዎ ጋላ_ አካ/ጥበቃ ቢሮ የአካ/አ/ን/ለ/ዘርፍ ም/ሃላፊ
6. ረ/ፕ ኡቦንግ ኡቻላ_ሥራና ክህ/ ቢሮ/የክህሎት/ዘርፍ ም/ ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ ኤልያስ ገዳሙ_የማዕድን/ኤጄ/ም/ዳይሬክተር
8. አቶ ኡጁሉ ሉዋል_ተፈጥሮ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ
9. ኢ/ር ጓነር ጆክ_ገጠር መንገድ ም/ዳ/ር
10. አቶ ጋትሉዋክ ጋች_የሰው/ሀብትና ማህ/ጉ/ቋሚ /ኮ/ሰብሳቢ
11. አቶ ፒተር ሆዉ_የኢኖቬሽንና ቴክ/ዘ/ም/ኮሚሽነር
12. አቶ ቱት ቶት_ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ
13. አቶ ጃክ ጆሴፍ_አደጋ ስጋትና መከላከል ዋና ዳይሬክተር
14. አቶ ኡማን ኡኬሎ_ዉሃ ስራዎች ኮ/ድ ዋና ስራ አስኪያጅ
15. ጀሙስ ኞች_ዉሃ ቢሮ ኢነርጅ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ
16. ፓራኖክ ዋዋይ_ህ/ስ/ማ/ማደ/ዋና ዳይሬክተር
17. ፖል ቤል ተርጃት_የጤና መሰ/ል/አገ/ስር/ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ ጀምስ ዶማች_ዉሃና ኢ/ሀብት/ዉሃ/ዘ/ም/ቢሮ ሃላፊ
19. ዶ/ር ቾል ኬት_የከተሞች ፕላን ዋና ዳይሬክተር
20. ወ/ሮ አኳታ ቻም_መን/ትራ/ም/ቢሮ ሃላፊ
21. ወ/ሮ ሳራ ኛዮንግ_አካ/ጥበ/አየ/ንብ/ለ/ም/ቢሮ ሃላፊ
22. ወ/ሮ ታቢታ ኡሪያሚ_የከተ/መሰ/ል/ም/ቢሮ ሃላፊ
23. አቶ ቢየል ዳክ _የግብርና ምርምር ዋና ዳ/ር
24. አቶ ሳይመን ቱት ፓል_የመስ/ም/ቤት/የኢኮ/ፋይ/ታ/ጉ/አማካሪ
25. አቶ ኡቦንግ ኡቶዉ_በመ/ም/የዲያስፖራ ጽ/ቤት ኃላፊ
26. አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ_ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ዋና ዳ/ር
27. አቶ ኦኬሎ ቾል_መስ/ር/ም/ቤት ማህ/ጉ/አማካሪ
28. አቶ ፒተር አማን_መስ/ር/ም/መሠ/ል/አማካሪ
29. አቶ ሲሳይ ተስፋዬ_በአዲስ አበባ የጋም/ጉዳይ አስፈፃሚ
30. አቶ ሙድ ቶክ_መስ/ም/ቤት የህግ ጉዳዮች አማካሪ
31. አቶ ኮንግ ጆክ ጋች_ክ/ም/ቤት የማህ/ጉ/አማካሪ
32. አቶ ቡዎም ኩዎት ፓኖም_ክ/ም/ቤት የኢኮ/ጉ/አማካሪ
33. ወ/ሮ አሮሞቻን ኡጁሉ ኡቶንግ_የአንድ ማዕከል አገ/ት ዋና ዳ/ር
34. አቶ ካን ጋትሉዋክ_ጤናና ጤና ነክ ዳዮች ዋና ዳ/ር
35. አቶ ኡፓራ አጉዋ_ክ/ም/ቤት የሕ/ጉዳ/ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ
36. አቶ ሰናይ አኩዎር_የፍት/አካ/ማሠ/ኢንስ/ዋና ዳ/ር
37. አቶ ኡጁሉ ጊሎ_የማዕድን ሀብት ልማት ዋና ዳ/ር
38. አቶ ኡጁሉ ኝግዎ_የስራ አመራር ኢንስ/ዋና ዳ/ር
39. ኮ/ር ቱት ንጉት_ፀረ ሙስናና ስነ-ምግባር ዋና ኮሚሽነር
40. አቶ ባኳች ማሞ_ፀረ ሙስናና ስነ-ምግባር ምክትል ኮሚሽነር
41. አቶ ኡልየክ ኡሞድ_ገቢዎች ምክትል ቢሮ ኃላፊ
42. አቶ ቦት ጋች_መስኖና ቆላማ መስኖ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
43. አቶ ቱት ጆክ _ብዙሃን መገናኛ ዋና ዳ/ር
44. አቶ ጆን ቾል ጋትሉዋክ_የውሃ ስ/ኮን/ድ/ም/ስራ አስኪያጅ
45. አቶ ጃኮፕ ኒያል_ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር
46. አቶ ልዌል ዱዎት_የጋም/ት/ት/ጤና/ሳይ/ዋና ዲን
47. አቶ ኒያል ቱት_ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምክትል /ዳ/ር
48. አቶ ኡቦንግ ኡጉታ_ከተሞች ፕላን ምክትል ዳ/ር
49. አቶ ሪያክ ኡቺክ_አካ/ጥበ/አየ/ንብ/ለ/ም/ቢሮ ሃላፊ
50. አቶ ኡንጎም ኡማን_የት/ት/ጤና ሳይ/አካ/ጉ/ምክትል ዲን
51. አቶ ኡቻላ ኡዲየል_ዲማ ቴክ/ኮሌጅ ዋና ዲን
52. ኮማንደር ኡማን ኡጋላ_ኦፔኖ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ም/ዲን ሆነው ተሾመዋል።