🌍ተውሂድና ሱና ✍ @tewhidnasuna Channel on Telegram

🌍ተውሂድና ሱና

@tewhidnasuna


ቁርአንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተውሂድ፣ሲራ አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺ ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።ቻናሉን ይቀላቀሉ ኪታቦችን ይቅሩ

🌍ተውሂድና ሱና ✍ (Amharic)

ተውሂድና ሱና በሁሉም በማንኛውም በበለስ ወደ ሱናይት እንጂ በባጭ ያለው ለመቅረብ ጥፍ ይኖራል። ተውሂድ፣ ሱና ለየዕለተ ቆሞርዎች ሰጮች፣ ሕማም ሐዲስን መስማማት፣ አብቅር የሰለፋም ላይ የተላያዩ ባለጠግነት ሁለቱን ከፍችሞች ለመረዳት ያልተነሱ በአጭር የሀብት ስም ሲሆን፣ በሽታማ ነው። አፈንጋን ከፍተኛ እና ኢስራን በመከላከል ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ያገኙት ተውሂድና ሱና በእነዚህ ቆሞርዎች ላይ እንደሚገኖኛው ሀገር አሉት።

🌍ተውሂድና ሱና

11 Jan, 13:36


#በቁርአን ያለን እምነት ሙሉ ሊሆን የሚችለው አራት ነገሮችን ስናሟላ ነው እነሱ ተብራርቶበታል
#ቁርአን ከሌሎች መፅሀፍት በምንድነው የሚለየው መልሱን ከደርሱ

🌍ተውሂድና ሱና

11 Jan, 11:35


👉⭕️ምርጥ  ሷሊህ የሆነች ሚስት፦
ባለቤትዋ ሪዝቅን ፍለጋ ሲወጣ
" ውዴ ሆይ አላህን ፍራ እኛ ከረሀብ መታገስ
እንችላለን ከእሳት ግን መታገስ አንችልም
" የምትለዋ ናት🌹🌹

ለመ🀄️🀄️👇👇👇
[🌹ጆይን🌹] ተጫኑኑኑ🥰👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4982
https://t.me/Sobabilalmesjid/4982

🌍ተውሂድና ሱና

11 Jan, 10:25


አትንኩ ሒጃቤን!

ግጥም በሕፃን- ዚክራ እሸቱ

🌍ተውሂድና ሱና

11 Jan, 06:01


🔺አድስ ሙሀዶራ

🎙ርዕስ:የመልካም ነገሮች መክፈቻ

🕌 አልብኮ ሰላም መስጅድ አሏህ ይጠብቃት

🎤 ሸይኽ ጀማል አዘሀቢ[ ሀፊዘሁሏህ]


ሊንክ መቀየር አይቻልም
https://t.me/Sobabilalmesjid/4964
https://t.me/Sobabilalmesjid/4964

🌍ተውሂድና ሱና

11 Jan, 05:07


በቢሊዮን የዓለም ሰዎች በፍቅር የሚጠበቀው
ረመዳን 1 ወር ከ15 ቀን ቀረው::

ዝግጁ

The beauty of Islam.....

እዚህ ቦታ ላይ

* ሀብታሙ
* ድህው
* ሼኩ

ሁሉም በአንድ ላይ :-

* ነጭ ለብሰው
* ለፈጣሪያቸው ለአላህ ሰላት ይሰግዳሉ::

🌍ተውሂድና ሱና

10 Jan, 19:34


የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ከሰደድ እሳቱ በተጨማሪ አንድ ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሁለት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመታለች።



Earthquake M3.0 - 6 km NW of San Francisco Zoo, CA (Jan 10, 2025, 9:48:01 PM) https://earthquake.muradtadesse

🌍ተውሂድና ሱና

10 Jan, 14:24


♦️ የካሊፎርኒያ ሎስአንጀለሱ ቃጠሎ በምን ምክንያት እንደተነሳ አልታወቀም
♦️ ቃጠሎው የጀመረው ማክሰኞ ሌሊት ሲሆን በተቀራራቢ ሰዓታት በ7 የተለያዩ ቦታዎች ተነሳ
♦️ አሁን 5 ቦታዎች የእሳት ቃጠሎ ቀጥሏል
♦️ እስካሁን 10,000 ህንፃዎች ተቃጥለዋል
♦️ 14,000 ሄክታር መሬት ወድሟል
♦️ 180,000 ሰዎች ከአካባቢ እንዲለቁ ተደርጓል
♦️ 10 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል

👉 ቃጠሎው ለአላህ ቁጣ ትንሿ ማሳያ ብትሆንም ነገርግን ከጋዛ ውድመት ጋር ምንም የሚነፃፀር አይደለም። በጋዛ እስካሁን 170,000 ህንፃዎች ወድመዋል። ከ46,000 ሰዎች በላይ ደግሞ ተገድለዋል።

🌍ተውሂድና ሱና

10 Jan, 08:35


የጁሙዓህ ፈገግታ፦

በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

√ በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል።

√ በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

√ በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።



ንጹሐንን አላህ ይጠብቃቸው እንጂ በዳዮችንማ ያዳርሳቸው።

🌍ተውሂድና ሱና

02 Jan, 13:49


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት #የዑለማ ጉባኤ ሶላትንና #ሂጃብን አስመልክቶ የተሰጠ ፈተዋ!

🌍ተውሂድና ሱና

01 Jan, 14:47


🌹 ሶባ አሸብርቃለች🌹
💧💧💧💧💧💧💧

ጀግና ፣ልጆቿ አምራ ፣እየተጦረች
በከፍታ ፣ማማ፣ ደስታን ፣እየረጨች
ዛሬም ፣በልጆቿ  ፣ደምቃ ፣እንደታፈረች
በሀቅ ፣ተውባ ፣ጣፍጧት ፣ሳትሰለች
በሱና ፣ልጆቿ~ሶባ~አሽብርቃለች



ከወንድማችሁ አቡ ሹራ አህመድ ከደሴ

💫 ታህሳስ /08/04/2017 ተዘጋጅቶ


🎙 በድምፅ ለሶባ ሰለፍይ ጀመአወች የቀረበ

ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/Sobabilalmesjid/4929
https://t.me/Sobabilalmesjid/4929

🌍ተውሂድና ሱና

31 Dec, 12:23


ለአክሱም ሙስሊሞች ሒጃብ እንደተፈቀደው ሁሉ፤ የመስጅድና የመቃብር ቦታም ይፈቀድላቸው

🌍ተውሂድና ሱና

30 Dec, 13:35


የኢማን ማዕዘናቱ ስድስት ናቸው ። እነሱም ቡኻሪበዘገቡት ሐዲስ -
👉1. በአላህ ማመን
👉2. በመላእክቱ ማመን
👉3. በመጻሕፍቱ ማመን
👉4. በመልዕክተኞቹ ማመን
👉5. በመጨረሻው ቀን ማመንና
👉 6. በቀደር ክፍም ሆነ ደጉ ከአላህ መሆኑን ማመን ናቸው

©ማስታወሻ 5ቱ የእስልምና መሰረቶችና እና 6ቱ የኢማን መአዘናት ለይተን አናቃቸውም ልዩነታቸውን ማወቅ አለብን

🌍ተውሂድና ሱና

30 Dec, 03:33


🌷የጥዋት ዝክሮች🌷
ሁለት ንግግሮች ለምላስ የሚቀሉ ሚዛን ላይ የሚከብዱ አላህ ዘንድ  ግን የተወደዱ ቃላት ናቸዉ
👉ሱብሀነላሂ ወቢሀምዲሂ
👉ሱብሀነላሂል አዚም የሚሉት
ረሱል  ﷺ

🌍ተውሂድና ሱና

29 Dec, 08:40


#ረመዳን ሁለት ወር ብቻ ቀረው
አላህ በሰላም ያድርሰን።

🌍ተውሂድና ሱና

29 Dec, 07:19


«"ሒጃብ ከተፈቀደ፤ እኛም ነጠላ እናደርጋለን"

እምነትሽ ካዘዘሽ፤  ለምን ብርድልብስ አትደርቢም?»

🌍ተውሂድና ሱና

29 Dec, 06:55


የነጃሳ ትርጉምና አይነቶቹ
ነጃሳ ማለት ሸሪዓው እንድንርቀው ያዘዘን ማንኛው ፀያፍ አካል ሲሆን ነጃሳ ሁለት አይነት ነው::
1. ግኡዝ አካላዊ ነጃሳ፡- እንዲህ አይነቱን ነጃሳ ነገሩ ራሱ ነጃሳ በመሆኑ ማፅዳት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ ደም፣ ሽንትና የመሳሰሉት ማለት ነው::
2. አካል ላይ በማረፍ ሶላትን የሚከለክል ነጃሳ፦ እዚኛው ውስጥ በዉዱእ የሚወገድ ትንሹ ሀደስና በትጥበት የሚወገድ ትልቁ ሀደስ ይካተታል::
ነጃሳን የምናስወግድበት ዋናው አስወጋጅ ውሃ ነው፡፡ ውሃ እያለ በሌላ ነገር ማፅዳት አይቻልም፡፡
አላህ አንዲህ ይላል፡-
‹‹ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ… በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡›› (አል አንፋል 11)
ነጃሳ በሶስት ይከፈላል፦
ከባድ ነጃሳ፡- ይህ ውሻና የእሱ ተዋላጅ ነው፡፡
ቀላል ነጃሳ፡- ምግብ ያልጀመረ የወንድ ህፃን ልጅ ሽንት ነው፡፡
መካከለኛ ነጃሳ፡- የተቀሩ ነጃሳዎች በአጠቃላይ ለምሳሌ ሽንት፣ ሰገራና በክት እዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

🌍ተውሂድና ሱና

28 Dec, 16:31


#ኡሱሉል ኢማን ክፍል 61

🌍ተውሂድና ሱና

28 Dec, 12:04


👆👆👆
🔖 ሒጃብን ከመልበስ ምን ከለከለሽ ?

ዛሬ አብዛኛው ሙስሊም እህቶቻችን በሒጃብ ጉዳይ ፍጹም መዘናጋታቸው ጎልቶ ይታያል ለዚህም በተደጋጋሚ እንደምክንያት የሚያቀርቧቸው 10 ነጥቦችን ሸሪዓው የሚሰጣቸውን ምላሾችን በማስመልከት የቀረበ ትምህርት።

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

🌍ተውሂድና ሱና

27 Dec, 14:47


«እናንተ መራቆት መብታችን ነው ካላችሁ እኛ ደግሞ መሸፋፈን መብታችን ነው!»

🌍ተውሂድና ሱና

27 Dec, 12:42


#አላህ ረጅም እድሜህ ይስጥህ ሸይኹና ።ምርጥ መፅሀፍ ነው የበረከተልን ይህንን መፅሃፍ ገዝተው እየኮመከሙ ንግድዎን በሀላል ይስሩ ።
በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
➤ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
➤ አት-ተውባ መጽሐፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
➤ አት-ተቅዋ መጽሐፍት መደብር (ቤተል)
➤ ዛዱል መዓድ መጽሐፍት መደብር (ፋሪ)
ዋጋ= 400 ብር

🌍ተውሂድና ሱና

27 Dec, 04:43


صلوا على رسول اللهﷺ

#መልካም ጁመአ

🌍ተውሂድና ሱና

26 Dec, 19:05


#ተራቁቶ መሄድን መብት ያደረገች ሃገር፤ ተሸፍኖና ሒጃብ ለብሶ መሄድን ልትከለክል አይገባም
ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች

🌍ተውሂድና ሱና

26 Dec, 12:41


Merry Christmas ስላልካቸው አይወዱህም። የሚወዱህ ስትከፍር ብቻ ነው። ይወዱኛል ብለህ ብታሸረግድ እነሱም ሳይወዱህ አላህም ሳይወድህ መሃል መቅረት ነው።

🌍ተውሂድና ሱና

26 Dec, 08:41


ሴኩላሪዝም ማለት መንግስትን ከሃይማኖት መነጠል ማለት ነው። ኢትዮጵያ ሲደርስ ግን ትርጉሙን ይቀይራል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሴኩላሪዝም ማለት ሙስሊም ተማሪዎችን እምነታዊ አለባበሳቸውን ሰበብ እያደረጉ ከትምህርት ማእድ ማራቅ ነው። ሴኩላሪዝም ለሽፋንነት ይነሳል እንጂ አላማው በአፄው ዘመን የነበረውን ሙስሊሞችን ከትምህርት ማእድ የማራቅን ክፋት ማስቀጠል ነው። ሴኩላሪዝም ማመሀኛ ብቻ ነው። ከድሮው በተሻለ ወደ ትምህርት የዞረው የሙስሊም ቁጥር በአንፃራዊነት ጨምሯል። ይሄ ሐቅ እንቅልፍ የሚነሳቸው፣ የተማረውን ሙስሊም እንደ ስጋት የሚያዩ አካላት ታዲያ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሰበብ እየፈለጉ ሙስሊሙን ከትምህርት ለማራቅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።

ፈተናዎቹን ሁሉ እንደ ምንም ተቋቋመህ ተማር ወገኔ። ጠላት መማርህን እንደ ስጋት ቆጥሮ በዚህ ልክ ተግቶ ከትምህርት ሊያፈናቅልህ የሚተጋው ለምን እንደሆነ ይግባህ። ራስህንም ሆነ ልጆችህን ከትምህርት ገበታ በማራቅ ባላሰብከው አቅጣጫ የጠላት አጀንዳ እያሳካህ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።

IbnuMunewor

🌍ተውሂድና ሱና

25 Dec, 15:51


የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሰቆቃ
==========================

ሙስሊም በመሆን ብቻ ንጹሐን የሚጨቆኑባትና መብታቸው የሚረገጥባት የትግራይዋ አክሱም!

ጸጉራችሁን ገልጣችሁ ካልተማራችሁ መማር አይቻልም ከተባሉት የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ  የማትሪክ ፈተና ፎርም መሙላት አልቻሉም። ፎርም መሙላት የሚቻለው ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 16 ድረስ ነበር።

ስለዚህ ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ በግልፅ ከትምህርት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ይህን የፈጸሙት አካላት የሙስሊሞችን ጸጉር ማየት አምሯቸው አይደለም፤ ይልቁንም ሙስሊም መሆናቸው አስጠልቷቸው ነው። ጸጉራቸውን ገልጠው ቢገቡ እንኳ አሁንም ሌላ ከትምህርት ማስቆሚያ ዘዴ ከመፈለግ ወደ ኋላ አይሉም። ለዛም ነው ሙስሊሞች ከናካቴው በማይደራደሩበት የሒጃብ ጉዳይ የመጡት። እያወራን ያለነው ስለ ኒቃብ ወይም ጂልባብ ሳይሆን ስለ ትንሿ ሒጃብ ነው።

የመቃብርና የመስጅድ ቦታ መነፈጋቸው ሲገርመን፤ ጭራሽ ጸጉር ሸፍነው መሄድ ተከለከሉ። ኡማውና ተቋሙ ግን እስካሁን ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ነው። እስከዛሬ «ተቋም ቢኖረን!» እያልን ነበር መሰል ነገሮችን ስንመለከት። ግና አሁን ተቋምም አለን ብለን ከጭቆና ሊታደገን አልቻለም።


ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች
ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች
ሙስሊምነት ወንጀል አይደለም
#Justice_For_Axum_Female_Students

MuradTadesse

🌍ተውሂድና ሱና

25 Dec, 11:32


“አንድ ባሪያ ሶላት ለመስገድ በሚቆምበት ጊዜ ወንጀሉ በሙሉ ይመጣና ራሱና ትከሻዎቹ ላይ ይቀመጣል፤ሩኩዕና ሱጁድ ባደረገ ቁጥር ከእሱ እየተንጠባጠበ ይረግፋል።”

ረሱል (ﷺ)

🌍ተውሂድና ሱና

25 Dec, 07:10


የትግራይ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ የህዝቡና የክልሉ ጉዳይ ያገባል የምትሉ ሁሉ! በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ማግለል ሲፈፀም ለምንድነው ዝም የምትሉት? ሰብአዊነት የለም? እነዚህ ልጆች የክልሉ ተወላጆች አይደሉም? በሙስሊሞች ልጆች ሻሽ መልበስ ማን ስለሚጎዳ ነው እንዲህ አይነት በደል የሚፈፀመው?

እብኑ ምነወር

🌍ተውሂድና ሱና

24 Dec, 19:00


ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች

ሙስሊም መሆን ክብር እንጂ ወንጀል አይደለም

🌍ተውሂድና ሱና

07 Dec, 17:49


የበሻር ፀሐይ እየጠለቀች ነው። ከ50 ዓመት በላይ የዘለቀው የኑሶይሪያ ስርአት ህልም በሚመስል ፍጥነት እየተናደ ነው። ጦርነቱ ዋና ከተማዋ ደማስቆ ዳርቻ ደርሷል። ለሶሪያውያን መጪውን ጊዜ አላህ የኸይር ያድርግላቸው። የተሻለውን እንጂ የባሰውን ያርቅላቸው።
IbnuMunewor

🌍ተውሂድና ሱና

07 Dec, 12:27


በእንግሊዝ ሙሐመድ የሚለው ስም ከፍተኛው መጠሪያ ሁኗል።

"..መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል.."
[ ሱረቱ አል - ኢሻራሕ - 4 ]
#150 ሚሊዮን ሰዎች በአለም ላይ ሙሀመድ የሚል መጠሪያ ስም አላቸው።

🌍ተውሂድና ሱና

07 Dec, 03:53


ነብያችን ﷺ የመጨረሻው ቀን ሲቃረብ ያለዉን ሁኔታ ሲገልፁ እንዲህ አሉ፦
«ጊዜ ይቀራረባል ፣ እውቀት ይነሳል ፣ ፈተና ግልፅ ይወጣል ፣ ስግብግብነት (ስስት) ይስፋፋል ፣ "ሀርጅ"ም ይበዛል አሉ:: "ሀርጅ" ደግሞ ምንድን ነው ሲባሉ? ነብያችን ﷺ "ግድያ ነው" አሉ፡፡»
[ ቡኻሪ 92/14ዘግበውታል]
@tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

06 Dec, 19:08


➡️ሦስት ሰዎች ይገርሙኛል!⬅️
================
👉®አላህ ያዘዘውን በጎ ስራ ለትእዛዙ ሳይሆን ለሰዎች ይዩልኝ ብሎ የሚሠራ፣
👉®አላህ የሰጠውን ገንዘብ አላህ መልሶ ሲጠይቀው(ለድሆች እንዲሰጥ ሲያዘው)የሚሰስት፣
👉®አላህ ወደ እሱ ውዴታ ሲጠራው አላህን በሚያስከፋ መልኩ ከሰዎች ጋር የሚወዳጅ።

🌍ተውሂድና ሱና

06 Dec, 15:58


🍃ለማመስገን ኑር/ሪ

🔹በክፉውም በደጉ - الحمدلله
"አልሐምዱ ሊላህ" ለማለት በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ዕድል ነው።
ለምን/ እንዴት? ከተባለ አልሐምዱ ሊላህ ማለት አላህን የሚያስደስት፣ ለአምስጋኙ ምንዳ የሚያሰጥ፣ ልብን የሚያረጋጋና ሸይጣንን ተስፋ የሚያስቆርጥ ወዘተ. ቃል ስለሆነ።
ነቢዩ ﷺ አልሐምዱ ሊላህ ሚዛን ትሞላለች" ብለዋል።
አንድ ጊዜ ብቻ ከልብ الحمد لله በማለት አላህን ማመስገን የምልካም ስራ ሚዛንን እንደሚሞላ፤ የአልሐምዱ ሊላህ ምንዳ ቁስ ሆኖ ቢለካና ቢመዘን ሰማይና ምድሩን እንደሚሞላም ተናግረዋል።
🔹" የሙእሚን ነገር ይገርማል! መልካም ነገር ሲገጥመው ያመሰግናል ይህ ለርሱ መልካም ነው። ችግርም ሲገጥመው ይታገሳል ይህም ለሱ መልካም ነው። ይህ ለሙእሚን እንጂ ለማንም ያልተሰጠ ዕድል ነው"ም ብለዋል።

ሁሌም፣ ስለሁሉም አልሐምዱ ሊላህ!
الحمد لله حمدا كثيرا طيبا مباركا فيه كما يُحب ربنا ويرضى.

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
    🔹🔸🔹🔸🔹🔸
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

🌍ተውሂድና ሱና

06 Dec, 03:08


🌴 #سورة_الحجرات
👉ሱረቱል ሁጁራት

👤 القارئ : #يوسف_الصقير
👉ቃሪእ ዩሱፍ ሳቂር



.

🌍ተውሂድና ሱና

05 Dec, 14:50


🌱ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌱

🔘ጁማዓ ቀን ሱና የሆነው የቱ ነው

⚠️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌹Add የሚለውን በመንካት  ውሰዱ🤌

⚡️ 🚿 ሻወር መውሰድ 🧼

⚡️ 👕ጥሩ ልስ መልበስ👟

⚡️🧴ሽቶ መቀባት ለወንዶች

⚡️ ጥፍርን መቁረጥ

⚡️ ሲዋክ መጠቀም🪥

⚡️🕋በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ🕌

⚡️ሱረቱል ካህፍን መቅራት

⚡️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ

⚡️ሁሉም መልስ ናቸው


🔘🩵መልካም እድል🩵😀

🌍ተውሂድና ሱና

05 Dec, 14:24


የምሽት ስንቅዎ ለቀልብዎ

🌍ተውሂድና ሱና

05 Dec, 04:54


ቁርኣን_የአላህ_ቃል_ነው
ከእለታት አንድ ቀን ጠዋት # ሙዕተሲም የሚባለው ንጉስ
ወደ #ኢማሙ_አሕመድ የታሰሩበት ቦታ ሄደና እንዴት አደርክ
አላቸው
እሳቸውም አልሐምዱ ሊላህ ደህና ነኝ ነገር ግን እጅግ
አስደንጋጭ ክስተት አይቻለሁ እንጂ እሱም ቁርኣን ሞቶ
አገኘሁትና ከዚያም አጠብኩትና ከፈን አለበስኩት አሉት
# ንጉሱም ወዮልህ አሕመድ ቁርኣን ይሞታል እንዴ ወይስ
እያላገጥክብኝ ነው አላቸው
# እሳቸውም እናንተ ፍጡር ነው ስላላችሁ እኮ ነው ፍጡር
ደግሞ ሳይሞት አይቀርም አሉት
#ንጉሱም ለፊትናው ቀንደኛና መሪ ወደ ሆነው # አቡ_ዱኣድ ዞር
ብሎ ተመለከተ
▼የዛኔ #አቡዱኣድ "ንጉስ ሆይ እኔ እሚለው እንዲገረፍ ነው
ምክንያቱም ከግርፋት ሌላ ስርኣት የሚያስይዘው ነገር የለምና"
አለ
# ንጉሱ ደግሞ # አሕመድ ሆይ! ቁርኣን ፍጡር ነው በለኝ
እራስህን አትግደል አላቸው
#እሳቸውም ለሚትለው ነገር ከቁርኣንና ከሐዲሥ ማስረጃ
አምጣልኝ አሉት
#ንጉሱም ለገራፊው ጠንክረህ አሳምመው አለውና ገራፊው
የመጀመሪያ ሲገርፋቸው # ቢስሚሏህ አሉ ሁለተኛ ሲገርፋቸው
# ላሐውለ_ወላ_ቁወተ_ኢላ_ቢላህ አሉ ሶስተኛ ሲገርፋቸው
# አል_ቁርኣኑ_ከላሙ_ሏህ_ፍጡር_አይደለም አሉ ለአራተኛ
ሲገርፋቸው # አላህ_ለኛ_ከቀደረው_ሌላ_አይነካንም አሉ
▼ከዚያም በኃላ # አቢ_ዱኣድ ጠጋ በልና ጆሮዬ ላይ ከንጉሱ
ቅጣት ነፃ የሚታወጣህ አንዲት ቃል ተናገር አላቸው
#እሳቸውም ይልቁንስ አንተ እኔጋ ጠጋ በልና ጆሮዬ ላይ ከአላህ
ቅጣት ነፃ የሚታወጣህ አንዲት ቃል ተናገር አሉት
ያን ጊዜ አረመኔው #አቡ_ዱኣድ ለገራፊው አሳምማቸው ብሎ
አማላከተለት
ገራፊውም ልክ አቅላቸው ተሸፍኖ እስኪወድቁ ድረስ ገረፋቸው

▼☞ ይሄንን ፊትና # አል_ሙተወኪል በሚባለው ንጉስ ጊዜ አላህ
አስቆመላቸው እስከዛ ድረስ ተቆጥረው የማይዘለቁ ዑለማዎች
በስቃይ ላይ ሲሞቱ አላህ (ሱ.ወ) # ኢማሙ_አሕመድን ብቻ
አቆያቸው በእርሳቸውም ሰበብ ዲኑን ጠበቀው ።
■ አላህ ሰፊ እዝነትን ይዘንላቸው ■
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ :
◇ ﺳﻴﺮ ﺃﻋﻼﻡ ﺍﻟﻨﺒﻼﺀ ﻟﻠﺬﻫﺒﻲ " ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ ﺑﻦ ﺣﻨﺒﻞ "◇
* ﻟﻠﻪ ﺩﺭﻙ ﻳﺎ ﺇﻣﺎﻡ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻭﺍﻟﺠﻤﺎﻋﺔ 

🌍ተውሂድና ሱና

04 Dec, 14:39


ማንኛውም በህይወት የሚደርስ ፈተና ልንተገስ ይገባል።
ሸህ አህመድ አደም

🌍ተውሂድና ሱና

04 Dec, 06:18


ከታሪክ ማህደር🍀
* የኢማም አህመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁላህ ዐንሁ) የህይወት ታሪክ🍀
👉ሙሉ ስማቸው ኢማም አቡ አብዱላህ አህመድ ቢን መሐመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁ አሏህ ተዓላ)  በራቢኡል አወል 20ኛው ቀን 164 ሂጅራ ተወለዱ። በባስራ ኢራቅ ይኖሩ ነበር።
ኢማም አህመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁላህ ዐንሁ) በጣም አስተዋይ ልጅ ነበሩ፣ ኢስላማዊ ትምህርቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው።
በ16 ዓመታቸው የሐዲስ ሥነ-ጽሑፍን ማጥናት ጀመሩ። አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሀዲስ በልባቸው ተማረዋል ይባላል። ታዋቂ የሕግ ባለሙያም ሆኑ።

👉√ ኡስታዞቻቸው፡- ከመምህራኖቻቸው መካከል ኢማም ሻፋኢ፣  ቢሻር ቢን አል ሙፈዳል፣ ኢስማዒል ቢን ኡለይያህ፣ ጃሪር ቢን አብዱል ሀሚድ እና ያህያ ቢን ሰይድ (ረሂመሁላህ አንሁሙል አጀማዒን) ነበሩ።
ታላላቅ የሀዲስ አዘጋጆች ኢማም ቡኻሪ እና ኢማሙ ሙስሊም (ረሂመሁላህ አንሁማ) ኡስታዛቸውን ኢማም ሻፋኢይ (ረሂመሁላህ ዐንሁ) ጨምሮ ከሳቸው ሀዲስ ዘግበዋል። ኢማሙ ሻፋኢ (ረሂመሁላህ ዐንሁ) በዘመናቸው እጅግ የተማሩ ቢሆኑም ኢማም አህመድ ቢን ሀንበልን ( ረሂመሁላህ ዐንሁ) ስለ አንዳንድ ሀዲስ ይጠቅሱ ነበር። ተማሪዎቹ፡ ከተማሪዎቻቸው መካከል በጣም ታዋቂዎቹ  አቡበከር አል አልሀረም፣ ሀምባል ቢን ኢሻቅ እና  ቃሲም አል ባግዊ (ረሂመሁላህ አንሁሙል አጃማኢን) ነበሩ።

👉√* ምእመናኑ፡
ኢማም አህመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁላህ ዐንሁ) ዘመናቸውን ሁሉ በሀዲስ እና በፊቅህ ሳይንስ ያሳለፉ እጅግ አላህን የሚፈሩ አሊም ነበሩ። የመንግሥት ሹመት እያለቸው በማንም ሰው ቤት ለመብላት ፈቃደኛ አልሆኑም። አንዳንድ ጊዜ የሚበሉትን አጥተው እጅግ በጣም ድሃ ሆኖው አሁንም በሃያሉ አላህ ላይ ሙሉ እምነት አለኝ በማለት ምፅዋትን ለመቀበል እምቢተኛ ነበሩ።

👉√* ሥራዎቻቸው፡-
ከመጽሃፋቸው ውስጥ በጣም ዝነኛ የሆኑት፡ ኪታቡል አእማል፣ ኪታቡል ተፍሲር፣ ኪታቡል ናሲህ ዋል ማንሱክ፣ ኪታቡል ዛሂድ፣ ኪታቡል ማሳኢል፣ ኪታቡል ፈዳኢል እና ኪታቡል ማንሲቅ ናቸው።
በጣም ዝነኛ የሆነው መጽሃፉ "MUSNAD"ሙስነድ

👉√* እስራት፡
ኢማም አህመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁላህ ዐንሁ) በኋለኛው የህይወት ዘመናቸው ከእስልምና እምነት ውጪ በሆነው እምነትና ተግባር ምክንያት በእርሳቸው ላይ በተነሱት ጨካኞች ገዥዎች ታስረው አሰቃይተዋቸዋል።
ኸሊፋ ሙተሲም ቢላህ ኢማሙን “ሙእተዚላ” (የተበላሹ አንጃዎች) እምነት እንዲቀበል አስገድደዋቸው ነበር ነገር ግን እምቢ በማለታቸው  ተደብድበው እስከ መገጣጠሚያቸው ድረስ ተነቅሏል።
በባግዳድ እስር ቤት ለ30 ወራት ያህል በከባድ ሰንሰለት ታስሯል። አሁንም የተበላሹ የሙእተዛሊ ሴክት እምነትን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እራሳቸውን ስቶው እስኪወድቁ ድረስ በድጋሚ ተደብድበዋል።

👉√* ኸሊፋ ሙተሲም የሰራውን ሀጢያት በመፍራት በረመዷን 25ኛው ቀን 221 ሂጅራ ኢማሙን ነፃ አወጣቸው።
ኢማሙ አህመድ ቢን ሀንበል (ረሂመሁላህ ዐንሁ) ከሙታዛል በስተቀር ለሰዎች ሁሉ ይቅር ብለዋል።

👉ኢማሙ አህመድ በተወለዱ በ75 አመታቸው በጁመአ ቀን ረቢአል አወል 241ሂ /ነሃሴ 2 855   ኢራቅ ውስጥ  በባግዳድ ከተማ ህይወታቸው አለፈ የታሪክ ሙህራን 800,000 ወንዶች 60,000 ሴቶች 20,000 ክርስትያኖችና ጀዊሾች እስልምናን ተቀብለዋል ይላሉ ያን ቀን።
@tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

04 Dec, 05:06


لا تنس ذكر الله
የጥዋት ዝክር እንዳትረሱ
√ሱበሃነላህ
√ወልሀምዱሊላህ
√ለኢላህኢለሏህ
√አላሁአክበር

🌍ተውሂድና ሱና

03 Dec, 15:48


☑️ይህንን ዱአ በማድርግ ለህመማችን ፈውስ እናግኝ⬅️

= عن عثمان بن أبي العاصي رضي الله عنه
 👉 እስልምናን ከተቀበለ ጀምሮ በሰውነታቸው ላይ ስላጋጠመው ህመም ቅሬታቸውን አቀረቡ። ። رسول الله  ﷺ  እንዲህ አሉት፡- “እጅህን በሚጎዳ የሰውነትህ ክፍል ላይ አድርግና 

بسم اللهሶስት ጊዜ ።
👉ሰባት ጊዜ ደግሞ

أعوذ بالله وقدرته من شر ما أجد  وأحاذر   
በል
👉 ካገኘው መጥፎ ነገር በአላህ እና በኃይሉ እጠበቃለሁ።”
√ሰሀቢዩም ይህንን ዝክር አደረኩ ከዛም  አላህም በውስጤ ያለውን በሽታ ፈወሰልኝ፡ እኔም ቀጠልኩ። ቤተሰቤን እና ሌሎች እንዲያደርጉ ማዘዝ ጀመርኩ”)

ቡኻሪና ነሳኢ ዘግበውታል።

🌍ተውሂድና ሱና

03 Dec, 04:39


ሸይኽ ሰዕዲይ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ:-

"የወጣትነቱን ግዜ የተጠቀመና (የስራው) መዝገብ ከመጠቅለሉ በፊት   በተውበትና (ወደጌታው) በመመለስ የተቻኩለን ባሪያ አላህ ይዘንለት"

【አል ፈዋኪሁ ሸሂያህ 217】


ወንድሜ ወጣትነትም ያልፋል

ሀይልም ይደክማል

ገንዘብም ያልቃል

ስለዚህ ኋላ ከመፀፀትና ከመለደም በፊት ወደጌታችን እንመለስ
t.me/tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

02 Dec, 15:10


ተፍሲር አማ ጁዝ
➡️ኡስታዝ ያሲን ሙሌ(አቡ አማር)

🌍ተውሂድና ሱና

02 Dec, 15:10


ዳእዋን በየገጠሩ ማድረስ ትልቅ መታደል ነው አላህ ላገራለት። በተለይ

ሽርክን በማውገዛ
ማህበረሰባችንን ከባጢል ለመምዘዝ

ተውሂድና ሱናን ለማስያዝ

በጢልን መዋጋት
ወጣቶችን ማፍራት

የሁላችንም ግዴታ ነውና ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉ👇👇👇👇👇
https://t.me/+Ix19CLmB79g4MjRk
https://t.me/+Ix19CLmB79g4MjRk

ይህ ሊንክ የሶባ ወንድሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ነው። ግቡ የድርሻችንን እንወጣ

🌍ተውሂድና ሱና

02 Dec, 07:34


يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۖ وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِاللَّهِ الْغَرُورُ

እናንተ ሰዎች ሆይ! የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታታላችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) አያታላችሁ፡፡

🌍ተውሂድና ሱና

02 Dec, 03:08


⭐️ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!!⭐️
ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!!
ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡
5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚባል ዋጋው የገዘፈ አንድ ትልቅ
ዚክር!!
[ ﺳﺒْﺤﺎﻧَﻚ ﺍﻟﻠَّﻬُﻢّ ﻭﺑﺤَﻤْﺪﻙَ ﺃﺷْﻬﺪُ ﺃﻥْ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺃﻧْﺖ
ﺃﺳْﺘﻐْﻔِﺮﻙَ ﻭَﺃﺗَﻮﺏُ ﺇﻟﻴْﻚَ ]
[ሱብሓነከልሏሁመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢላ አንተ
አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ]
1. ከዚክር ቆይታ በኋላ ይህንን ያለ ልክ እንደ ማሸጊያ፣ ጥሩ
መቋጫ ይሆነዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 81]
2. ከዛዛታና ቀልድ በኋላ ይህንን ያለ ከቦታው የተፈፀሙ
ወንጀሎቸን አላህ ያብስለታል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 2651]
3. ከውዱእ በኋላ ይህንን ዚክር ያለ እስከ እለተ ቂያማ ምንዳው
ባስተማማኝ መቀመጫ ታሽጎ ይቀመጥለታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ፡
225]
4. ይህንኑ ዚክር ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሶላት በኋላም
ይሉት ነበር፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3164]
5. ቁርኣን ከቀሩ በኋላም ይሉት ነበር ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
[ነሳኢይ]
እንዲህ አይነት ትልቅ ሀብት ይዘው ዝም አይበሉ፡፡ ለወዳጅ
ዘመዶችዎ ያድርሱ፡፡

🌍ተውሂድና ሱና

01 Dec, 15:01


🌹ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌷

🍁የቀብር ዓለም መጠሪያው ____ይባላል

🍃ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🍃

add በማለት ውሰዱ

🌐መልካም እድል🌐🌐

🌍ተውሂድና ሱና

21 Nov, 19:21


የተከበረው የረመዿን ወር 99 ቀናት ገደማ ይቀሩታል! አላህ በሰላም አድርሶን ለመፆም ያብቃን። ቀዿ ያለባችሁ ከወዲሁ አጠናቁ!

🌍ተውሂድና ሱና

21 Nov, 15:34


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

አባታችን አደም 『عليه السلام』 የተፈጠሩት በየትኛው ቀን ነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  እሁድ 『الأحد 』

ለ}  ሐሙስ 『الخميس 』

ሐ}  ጁሙዓህ 『 الجمعة 』

መ}   ሰኞ  『الاثنين 』

⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላቹም ማለት ነው⚠️

🔘🩵መልካም እድል🩵🔘

🌍ተውሂድና ሱና

21 Nov, 04:24


🕯መርከቧ ከመስመጧ በፊት🕯

በዳዒ ሐዊ ሙሐመድ (ረሒመሁላህ)
ወላሂ በምርጥ አንደበቱ ብዙ ነገሮችን የደሰሰበት እጅግ ጣፋጭ ደእዋ
ከአመታት በፊት ለሞተው ወንድማችን ሐዊ ሙሐመድ (ረሒመሁላህ) አጅሩ እንዲበዛለት ሼር በማድረግ ለአድማጮች እናድር

t.me/tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

21 Nov, 04:10


➡️4 ጀነት የሚያስገቡ ነገሮች ከሰሓቢዩ ኢብኑ ዑመር رضي الله عنهما አንደተነገረው አራት ነገሮችን የታደለ ሰው ጀነትን ያገኛል⬅️
👉1- ላ ኢላሀ'ኢለላህ ያለ/ ያበዛ لا إله إلا الله.
👉2- ተሳስቶ ወንጀል ከፈጸመ "ኢስትግፋር የሚያበዛ" استغفر الله.
👉3- መልካምን ነገር/ ጸጋን ሲያገኝ ጌታውን የሚያመሰግን الحمد لله. 4- አደጋ ሲገጥመው፤ ኢና ሊላህ ወ'ኢና ኢለይሂ ራጂዑን إنا الله وإنا إليه راجعون የሚል- እነዚህ
👉 4 ነገሮችን መታደል ሙስሊምን ጀነት ያስገባሉ። ኢብኑ ዐብዲል-በር بهجة المجالس عة زاد المعاد التمـ العلم أول داد المكان
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

🌍ተውሂድና ሱና

20 Nov, 11:22


⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
☑️ዱኒያ እኛ እንደፈለግናት አትሆንም
☑️እንዳሰብናትም አትሳካም
☑️እንዳሻናትም አትሄድልንም
☑️ዱኒያን እንዳመጣጡዋ ግን ተቀብለን ማስተናገድ ግድ ይላል➡️ያለነው ዱኒያ ውስጥ ስለሆነ

🌍ተውሂድና ሱና

19 Nov, 12:11


➡️ወላሂ አፊያ ከነጠቀህ የፈለገ ነገር ቢሰጥህ አትደሰትበትም፣ስትበላ ሊጣፍጥህ፣ ስትለብስ ሊያምርብህ ሰዎች ሊወዱህና ሊያቀርቡህ የሚችሉት አፊያ ሲኖርህ ነው።አላህ አፊያ ይስጠን።⬅️

🌍ተውሂድና ሱና

19 Nov, 06:25


ሁሌም ይህቺን የቁርኣን አንቀፅ አስታውሱ።


{ أَلَيْسَ اللَّهُ بِكَافٍ عَبْدَهُ } 

«አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን?»

እንደታ! ቀላል በቂ ነው!

ጭንቀትህን የሚያስወግድልህ፣ ጭንቅ ጥብብ ካለ ቀዳዳ የሚያወጣህ፣ እንቅልፍ የነሳህን ጉዳይ ባላስብከውና ባልጠበቅከው መልኩ የሚፈርጅህ፤ አላህ እንጂ ሌላ ማን ነው

ትክክለኛ ስኬት አላህን በመያዝ ትገኛለችና ወደርሱ እንመለስ።

🌍ተውሂድና ሱና

19 Nov, 05:11


#የጥዋት ስንቅ ለቀልብዎ

🌍ተውሂድና ሱና

18 Nov, 17:20


👉ይታሰብበት እጅግ ያስቸገረ ነገር የህፃናት ሽንትና ረብሻ በየመስጅዱ⬅️
ብዙውን ጊዜ ወላጆች ለሶላት ያልደረሱ ልጆችን ወደ መስጂድ ይዘው ይመጣሉ። ሶላቱ ሲጀመር ታዲያ ለቅሶና ጩኸታቸው መከራ ነው። እና ኢማማችን በዚህ ተበሳጩና «ለሶላት የደረሱ ልጆቻችሁ በየሜዳው ጎፈሬያቸውን እያበጠሩ እናንተ ህፃን ልጆችን እያመጣችሁ ሰው አዛ ታደርጋላችሁ።» አሉ።

ሃቅ ነው። እርግጥ ረሱል ﷺ ልጆች ወደ መስጂድ መምጣት ከፈለጉ አትከልክሏቸው ብለዋል። ነገርግን ሶላት የዋጀበባቸውን ትቶ ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉትን ማምጣት ስህተት ነው። ጎርምሰው እንቢ ካሉም እየመከሩም እየተቆጡም እየገረፉም ማለማመድ ያስፈልጋል። አለማምዱ የተባለውም ከ7 ዓመት በኋላ ነው። ሽንቱን እንኳን መቆጣጠር የማይችልን ህፃን ልጅ መስጂድ ማምጣት ግን ለመነጀስ ካልሆነ በቀር ማለማመድ አይባልም። እና በጣም ህፃናቱን ተውና ጎረምሶቹ ላይ ብትበረቱ ለማለት ነው።

🌍ተውሂድና ሱና

18 Nov, 14:50


 ۞ يَٰٓأَيُّهَا
#ቃሪእ አፊፍ ታጅٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱبْتَغُوٓاْ إِلَيْهِ ٱلْوَسِيلَةَ وَجَٰهِدُواْ فِى سَبِيلِهِۦ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ(35)...
የምሽት ስንቅ
ቃሪእ አፊፍ ታጅ

🌍ተውሂድና ሱና

18 Nov, 03:03


☑️”“ኢማን ከ 73 እስከ 79 ወይም ከ 63 እስከ 69 የሚደርሱ ቅርንጫፎች አሉት። ከፍተኛውና በላጩ «ላኢላሀ ኢልለላህ»ን ማለት (ከአላህ ሌላ የሚመለክ ኃይል እንደሌለ መመስከር) ሲሆን፣ የመጨረሻውና ዝቅተኛው ከመንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ ነው። «ሐያእ» የኢማን አንዱ ዘርፍ ነው።” ነብዩ (ﷺ ) (ቡኻሪ ዘግበውታል)⬅️

🌍ተውሂድና ሱና

17 Nov, 15:31


💜ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ💜

የነቢዩ 『 ﷺ』 አጎት እና የጥቢ ወንድም ማነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

መልሱን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ〗ሐምዛ 『رضي الله عنه 』

ለ〗ዐባስ 『رضي الله عنه 』

ሐ〗ዑመር 『رضي الله عنه 』


🔘⭐️መልካም እድል⭐️🔘

🌍ተውሂድና ሱና

17 Nov, 09:08


ተፍሲር አማ ጁዝ
#ኡስታዝ ያሲን ሙሌ(አቡአማር)
ክፍል 8

🌍ተውሂድና ሱና

17 Nov, 03:21


እነዚህ ዚክሮች ወንጀሎችን ያራግፋሉ👇
🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻🗻
🥀ረሱል ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም
       እንዲህ ብለዋል። 👇

"ሱብሃንአላህ
"ወልሐምዱሊላህ
"ወላኢላሃ ኢለሏህ
"ወላሁ አክበር
√የሚሉ ንግግሮች ወንጀሎችን ያረግፋሉ ቅጠል ከዛፍ ላይ እንደሚረግፈው።"
📚ሲልሲለቱ አሶሂሃ 3168
=
🥀ይህን መልዕክት እኛ ጋር እንዳይቀር ለተለያዩ ወዳጆቻችን በማስተላለፍ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን  @tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

16 Nov, 17:03


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

🌍ተውሂድና ሱና

16 Nov, 16:55


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

🌍ተውሂድና ሱና

16 Nov, 15:22


#ርእስ የመላኢካዎች የስራ ድርሻ ምንድነው?እጅግ አንገብጋቢና ሊቀራ የሚገባው ኪታብ፣

🌍ተውሂድና ሱና

16 Nov, 10:53


#ከ8 ቢሊዮን ህዝብ አንተን መርጦ ሙስሊም ለደረገ ጌታ አልሀምዱሊላህ በል።

🌍ተውሂድና ሱና

16 Nov, 10:39


ዚክር የነፍስ ምግብ
~
በቅርቡ በግምት የስምንት ሰዐት መንገድ ከአንድ ሾፌር ጋር ተጓዝኩ፡፡ ጉዞው ለኔ በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ጉዞዎች እጅግ ልዩ ሆኖብኛል፡፡ ሾፌሩ ከኔ ጋር ከተለዋወጣቸው ጥቂት ቃላት ውጭ ይሄን ሁሉ ሰዐት ስንጓዝ ዚክር ላይ ነበር፡፡ ወላሂ እጅግ በጣም ነው የገረመኝ፡፡ እሱን አይቼ እኔም ዚክር እጀምርና ብዙም ሳልቆይ እራሴን ከሆነ የሀሳብ ባህር ውስጥ ስንቦጫረቅ አገኘዋለሁ፡፡ እመለሳለሁ፡፡ ዳግም እራሴን ከሌላ ቦታ አገኘዋለሁ፡፡ ሱብሃነላህ! እራሴን ታዘብኩት አልላችሁም፡፡ ነገሩ ከዚያም በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ እራሴን ተጠየፍኩት፡፡ በወንድሜ በጣም ቀናሁኝ፡፡ አላህ በተውሂድና በሱና ላይ ያፅናው ብያለሁ፡፡
ግን ወንድሞችና እህቶች ስራችን ብለን ቁጭ ብለን ዚክር ላለማረጋችን አዋጣም አላዋጣም ምክንያት ይኖረን ይሆናል፡፡ አሰልቺ ረጃጂም ጉዞዎችን ስናደርግ አሁንም አሁንም ከማዛጋት፣ አስቀያሚ ማስታወቂዎች ላይ ከማፍጠጥ፣ … ዚክር ብናረግ ምን ነበረበት? ሱብሓነላህ! አንዴ ሱብሓነላህ ሳንል ስንት መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠናል?! ስንት ረጃጅም ሰአቶችን በከንቱ አሳልፈናል? አራት መቶ አምስት መቶ ኪሎ ሜትሩ ይቅር፣ የአራትና አምስት ሰዐት መንገዱም ይቅር፤ ኧረ ሌላው ቀርቶ የፒያሳ መገናኛ፣ የመርካቶ አየር ጤና መንገድም ይቅር እሩቅ ነው እንበል። በአንዲት አጭር ፌርማታ ስንትና ስንት ዚክር ማድረግ፣ ስንት አጅር ማፈስ አይቻልም? እውነት በዚክሩ የሚገኘው አጅር በገንዘብ ቢቀየር እንዲህ እንዘናጋ ነበር? አቤት የኛ ነገር!
እስኪ አንድ ደቂቃ በማይፈጁ ዚክሮች የሚገኘውን አጅር ያስቡ

- “ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል ዐዚም”
በሐዲስ እንደተነገረው እነኚህ ለምላስ የሚቀሉ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አረሕማን ዘንድ የተወደዱ ቃላት ናቸው፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል? ሰላሳና አምሳ ኪሎሜትሮችን ስንጓዝስ?
- “ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ” ከጀነት ድልብ ሀብቶች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- የነብዩ (ﷺ) ባለቤት ጁወይሪያ ከፈጅር ሶላት እስከ ረፋድ ዚክር ስታደርግ ቆይታ “እኔ ካንቺ በኋላ አራት ከሊማዎችን ሶስት ጊዜ ደጋግሜ ብያለሁ፡፡ ብትመዘን እስካሁን አንቺ ካልሺው ትበልጣለች አሏት፡፡(ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ፣ ወሚዳደ ከሊማቲሂ)
- አንዴ በነብዩ (ﷺ) ላይ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድበታል፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማድረግ ይቻላል? … እነኚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ውድ የኢስላም ወንድሞችና እህቶች! ኢስላም እኮ ሂወት ነው፡፡ ጁሙዐ ወይም ረመዳን ብቻ ተጠብቆ ሽር ጉድ የሚባልበት ድግስ አይደለም፡፡ “የኢስላም ድንጋጌዎች በዙቡኝ” ያላቸውን ሰው “ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ” ብለው አይደል ያመላከቱት ነብዩ (ﷺ)? ጌታችን እንዲህ ይላል፡
(ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَتَطۡمَىِٕنُّ قُلُوبُهُم بِذِكۡرِ ٱللَّهِۗ أَلَا بِذِكۡرِ ٱللَّهِ تَطۡمَىِٕنُّ ٱلۡقُلُوبُ)
(እነዚያ ያመኑት ልቦቻቸውም አላህን በማስታወስ የሚረኩ ናቸው፡፡ አዋጅ! አላህን በማስታወስ (የአማኞች) ልቦች ይረካሉ።) (አረዕድ፡ 28)

ነብያችን (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡ "ጌታውን የሚያስታውስና የማያስታውስ ምሳሌ የህያውና የሙት ምሳሌ ነው።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
አሁን እኛ ህያዋን ነን ወይስ የቁም ሙት? በጊዜ እናሳችንን እናስተካክል።
የአላህ ሰዎች ሀይላቸውም፣ ምግባቸውም፣ እስትንፋሳቸውም፣… ዚክር ነው፡፡ ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ  እንዲህ ይላሉ፦ እንደ ኢብኑ ተይሚያ ዚክር የሚያበዛ አላየሁም፡፡ በአንድ ወቅት ፈጅር ከሰገዱ ጀምሮ ዚክር ያደረጋሉ፡፡ ባሉበት ሁኔታ ላይ እያለ ሰዐቱ በጣም ሄደ፣ ረፈደ፡፡ በሁኔታቸው ተገርሜ እያየኋቸው ነው፡፡ እንደተገረምኩ ገብቷቸዋል፡፡ ዘወር ብለው እንዲህ አሉኝ፡- ይሄ ምግቤ ነው፡፡ እሱን ካላገኘሁ ብርታት አይኖረኝም። (ቃል በቃል አይደለም ያሰፈርኩት።)
“ጌታችን ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን፡፡”

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 21/2005

🌍ተውሂድና ሱና

15 Nov, 18:55


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

🌍ተውሂድና ሱና

15 Nov, 11:04


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

🌍ተውሂድና ሱና

15 Nov, 08:03


ሶላት ዐለ'ነቢይ
~
{ إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا }
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" [አልአሕዛብ፡ 56]

Ibnumunewor

🌍ተውሂድና ሱና

15 Nov, 06:51


♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
_
🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል።
____
©ተውሂድና ሱና

🌍ተውሂድና ሱና

15 Nov, 04:07


#የጁመአ ግብዣ
#ሱረቱል ኻህፍ
ቃሪእ ሸይኽ ፋሪስ አባድ

🌍ተውሂድና ሱና

14 Nov, 16:05


በቴሌግራም ምርጥ ምርጥ የሱና ቻናሎችን
ይፈልጋሉ
⁉️

⚡️🤎ስልኩን በመጫን ይቀላቀሉን🤎⚡️

💐🌹ለመ🀄️🀄️🌹💐
       ≼👇👇👇
┌───────────┐╯
‌│⫸╭─━━━━━━╮⫷│╯
│⫸│  ╰─ ━ ─╯    │⫷│╯
│⫸│▅▅▅▅▅▅▅│⫷│╯
‌│⫸│╰╮ • ★•╭╯   │⫷│╯
│⫸┃┊  ŝùñãĥ ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊ channal     │⫷│╯
│⫸┃┊  ŵãvê  ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊  ▓🌹▓  ┊    ┃⫷│╯
│⫸┃╰─◦◇◦╯    ┃⫷│╯
‌│⫸┃██████    ┃⫷│╯
│⫸│→         ━        ←┃⫷│╯
│⫸╰━━━━━━━╯⫷│╯
╰━━━━━━━━━━━╯╯
𝐀𝐝𝐝 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
        👇👇👇👇
🔘WAVE :- @ibnurahmeto🔘

🌍ተውሂድና ሱና

14 Nov, 10:51


ለነፍስህ 3 ደቂቃ ቦታ ስጥ
ምርጥ ደእዋ
ኡስታዝ አ/ካፊ

🌍ተውሂድና ሱና

14 Nov, 03:52


#አልሃምዱሊላህ #አልሃምዱሊላህ !
ይህን አከባቢ ማንም ያልተመለከተው ዞር ብሎ እንኳ የሚያየው የሌለው አከባቢ ነው። ወረደው ውስጥ ግን ብዙ መሻኢኮች እንዳሉ እሙን ነው። ወላኪን ይህችን አከባቢ የዘየራት የለም፤ደዕዋ የጠማው አከባቢ ነው። በተለይ በንፅፅር ዙሪያ የሚሰሩ ኡስታዞችን ጁሁድ ይፈልጋል። አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ።
#ሼር በማድረግ እንተበበር የአክፍሮት ሀይላት ያንዣበቡበት አከባቢ ነው።
https://www.facebook.com/@tewhidnasuna/

🌍ተውሂድና ሱና

13 Nov, 14:56


#የመላኢካዎች የስራ ድርሻ።ነፍስ፣በማውጣት ወህይ በማምጣት፣ዝናብ በማዝነብ የተወከሉት እነማን ናቸው?

🌍ተውሂድና ሱና

12 Nov, 18:03


⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️
የአረበኛ"ፊደላት በአማርኛ አረብኛ ለመፃፍ ሆነ ለማንበብ የምፈልጉ"እነዚህ በጣም ይጠቅማሉ::!!ተጠቀሙባቸው

🌍ተውሂድና ሱና

12 Nov, 18:01


👉ሸሪዓዊ አለባበስ!!

ሸሪዓው ወንዶች ልብሳቸውን ሱሪያቸውን፣ጀለብያቸውን፣ሽርጣቸውን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ ታዘዋል።

ሴቶች ደግሞ መላ ሰውነታቸውን በሒጃብ እንዲሸፍኑ፣ ስስ ያልሆነ የሰውነታቸውን ቅርፅ የማያሳይ፣ የሆነና ከቁርጭምጭሚት በታች አንድ ስንዝር ለቀቅ አድርገው እንዲለብሱ ታዘዋል።

የሚገርመው በአሁን ሰዓት አንዳንዶች ዘንድ ነገሩ በተቃራኒ ሆኗል።

ወንዶች ልብሳቸውን አሳጥረው ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው እንዲለብሱ ታዘው ሳለ እንደ ሴቶች ካለበስን መሬት እየጎተትን መሬት ካልጠረግን አሉ።

ሴቶች ደግሞ በተቃራኒው ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት እነሱ ይመስል ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው ያውም ስስ የሆነ ያውም በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ካለበስን አሉ።

በጣም የሚገርመው ከወንዶችም ከሴቶች ወደ ሰላት ሲገቡ ወንዱም ሱሪውን ወደ ላይ ያጥፈዋል።ሴቷም የለበሰችውን ቀሚሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።

ስለዚህ ሸሪዓው ያዘዘውን አለባበስ ምን አይነት አለባበስ እንደሆነ ያውቃሉ ማለት ነው። ሸሪዓው ወንዶችን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት በሰላት ብቻ አይደለም። በየትኛውም ሁኔታ ነው። ሴቷም እንዲሁ በሰላት ብቻ አይደለም መላ ሰውነቷን እንድትሸፍን የታዘዘችው። ይህን ያልኩት ከላይ እንዳልኳችሁ ወንዱም ልክ ወደ ሰላት ሊገባ ሲል ሱሪውን ወደ ላይ ለማጠፍ ሲሞክር ታየዋለህ። ሴቷም ልብሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።


ወንድሜ ሆይ! ሱሪህን፣ጀለብያህን፣ሽርጥህን ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገህ አሳጥረህ ልበስ። አርኣያዎችህ እነ አቡበክር፣እነ ዑመር፣እነ ዑስማን፣እነ ዐሊይና የመሳሰሉት ናቸው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሊዘይሩት ከመጡ ሰዎች መካከል አንድ ወጣት ሱሪውን ሲጎትት ተመለከተው አስጠርቶ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ምንድነው ያለው አንተ ልጅ ሆይ ልብስህን ከፍ አድርገህ ልበስ። ይህ ለልብስህ ንፅህና የተሻለ ነው። ጌታህንም ለመፍራት የቀረበ ነው ብሎ ነው የመከረው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይህን ማለቱ ጉዳዩ በጣም ከባድ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

እህቴ ሆይ! አንቺም አርኣያዎችሽ እነ ዓኢሻ፣እነ ኸዲጃ፣እነ ሱመያ፣እነ ሐፍሳና የመሳሰሉት ናቸው። እነሱን ተከተይ።
በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ያቺ አዙሮ የምጥል በሽታ የነበረባትን ሴት ተመልከቺ። በሽታው በጣም ያሰቃያት ነበርና በሽታው አዙሮ ሲጥላት ሰውነቷ ይገላለጣል።ይህቺ ሴት ለነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምንድነው ያለችው እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝ። በምወድቅበት ሰዓት ሰውነቴ ይገለጣል። ምን ላድርግ ብላ ስትጠይቃቸው የአላህ መልዕክተኛ ምንድነው ያሏት ከፈለግሽ አላህ ይህን በሽታ እንዲያነሳልሽ ዱዓ አደርግልሻለሁ። ከፈለግሽ ሰብር አድርጊ ጀነት አለልሽ አሏት። የሷ ምላሽ ምን ነበር ሰብር አደርጋለሁ። በሽታው በሚጥለኝ ሰዓት ሰውነቴ እንዳይገላለጥ ዱዓ አድርጉልኝ ነበር። ታዲያ አንቺና ይህቺ በበሽታ ምክንያት ራሷን ስታ በምትወድቅበት ሰውነቷ ለሚገላለጠው የሚትጨነቅ ሴት የትና የት ናችሁ?


🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈

🌍ተውሂድና ሱና

12 Nov, 15:13


የማታ ዝክሮች

🌍ተውሂድና ሱና

11 Nov, 18:28


©السلام عليكم ورحمة الله وبركاته©
➡️የቻናሉ ተከታታዮች ⬅️
በዚህ ቻናል እየተሰጡ ያሉ ትምህርቶች
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
☑️የኪታብ ቅርአት በሸይኽ ኸድር ሰኢድ ኡሱሉል ኢማንና ፊቅህል ሙየሰራ ቅዳሜና እሁድ ከመግሪብ እስከ ኢሻ እና ከኢሻ በሗላ
☑️የቁርአን ተፍሲር በኡስታዝ ያሲን ሙሌ
☑️የጥዋትና የማታ አዝካሮች
☑️የነቢዩ ( ﷺ)የህይወት ታሪክ
☑️የነቢዩ( ﷺ)ሚስቶች የህይወት ታሪክ
☑️ጥያቄና መልስ
☑️የሰሃባዎች የህይወት ታሪክ
☑️ፈትዋዎች
☑️እስልምና ነክ ዜናዎችን
☑️የተለያዩ ኡስታዞች ፁሁፎችና ደርሶች፣የእብኑ ምነወር፣የሸይክ ኢሊያስ አህመድ፣የኡስታዝ ሳዳት ከማል፣የኡስታዝ አህመድ አደም

ሀሳብ አስተየየት ካላቹ በቀጣዩ ቦት አድርሱን t.me/tewhidnasunabot

🌍ተውሂድና ሱና

11 Nov, 05:12


👉ተፍሲር አማ ጁዝ
በኡስታዝ ያሲን (አቡ አማር)
ክፍል 7

🌍ተውሂድና ሱና

10 Nov, 16:14


የአላህ ፀጋ
ኡስታዝ ጅብሪል አክመል

🌍ተውሂድና ሱና

10 Nov, 15:00


🔘🔠🔤🔠🔤🔤🔠

🔠🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔠ባለቤቶች🔘

🌹የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት🌷

💚የሱና ቻናል ባለቤቶች፡ ቻናላችሁን ማሳደግ የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላችሁ💚

Ʀᴏʏᴀʟ ᴡᴀᴠᴇ

⭐️1k+ subscribers 
⭐️5k+ subscribers 
⭐️10k+ subscribers 
⭐️15k+ subscribers 
⭐️20k+ subscribers 

🔈የሱና ቻናል ያላቹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ!

ከ 1k በታች ያላችሁ በስምምነት

🔘ለመመዝገብ ➪ @ibnurahmeto🔘

🌍ተውሂድና ሱና

10 Nov, 08:53


🌹ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌷

🍁ሴት ልጅ ሐይድ ላይ ከሆነች___የለባትም⁉️

🌐ከምርጫው በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና መልሱን በመንካት  ውሰዱ

🌍ተውሂድና ሱና

10 Nov, 03:41


#እጅግ አንገብጋቢ ልቀራና ሊደመጥ የሚገባው ምርጥ የአቂዳ ኪታብ
#ኡሱሉል ኢማን ክፍል 50
#ርእስ የመላኢካዎች የስራ ድርሻ ምንድነው?

🌍ተውሂድና ሱና

09 Nov, 14:51


💜ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ💜

ጣኦታትን በመሰባበሩ ምክነያት ጣኦት አምላኪዎች ወደ እሳት የጣሉት ነቢይ ማን ይባላል⁉️

⭐️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⭐️

🌸መልሱን በመንካት  ውሰዱ🌹

ሀ❳ ሙሀመድ [ﷺ]

ለ❳ ሙሳ [عليه السلام]

ሐ❳ኢብራሒም [عليه السلام]

መ❳ ዒሳ [عليه السلام]

መልካም እድል

🌍ተውሂድና ሱና

09 Nov, 11:38


የነቢዩ ﷺሚስቶች ክፍል 2
👉2.ሰውደህ ቢንት ዘምዐህ
ሰውደህ ቢንት ዘምዐህ ቢን ቀይስ
👉እናቷ: አሹሙስ ቢንት ቀይስ እህቶቿ እና ወንድሞቿ: ዐብድ ቢን ዘምዐህ፡ማሊክ ቢን ዘምዐህ እና ዐብደረህማን፡በሱ ዘር ሰዎች ተከራክረው ነበር ነብዩ/ዐ.ሠ.ወ/ ግን የዘምዐህ ልጅ ነው ብለው ፈርደዋል 👉የስነ-ምግባሯ ባሕሪ: ራሷን ከዱንያ ቆጣቢ አማኝ ነበረች ነሻጣም ነበረች አንዳንዴም በአንዳንድ ነገር ነብዩን/ ﷺ ታስቃቸው ነበር ጥሩ እና ቸር የሆነች ሴት ናት ዓኢሻ/ረዲያላሁ አንሁ/ ስለ እሷ እንዲህ ትል ነበር "እስካሁን ድረስ ከሴቶች ሁሉ በቁጥብነቷ፡በጥሩነቷ እንደ ሰውዳ መሆንን የወደድኩ ነገር የለኝም" (ሙስሊም)
🍀መሕሯ: 400 ዲርሀም ስለ እሷ ተጨማሪ: ከኸዲጀህ ቀጥሎ ነብዩን/ ﷺያገባችው እሷ ናት

ከባለቤቷ ሰክራን ቢን ዐምር አል አንሷሪይ ጋር ለዲኗ ስትል ወደ ሀበሻ ሸሽታለች ከስደትም ስትመለስ ባሏ ሞተባት የእሷ ቤተሰብም ጨካኝ እና ብርቱ የሆኑ የአላህ እና የመልእክተኛው ጠላት ነበሩ ነብዩም/ ﷺ/ እሷን ከቤተሰቦቿ ጭካኔ ለመጠበቅ ሲሉ አገቧት የዛኔ እድሜዋ 55 ነበር
👉 ህልፈቷ: በ መጨረሻው የዑመር ቢን ኸጣብ የ አስተዳደር ዘመን በ54ኛው አመተ ሂጅራ በመዲና ውስጥ ሞተች ያስተላለፈችው ሀዲስ: ከነብዩ / ﷺ/ አምስት ሀዲስ ብቻ ነው ያስተላለፈችው

🌍ተውሂድና ሱና

08 Nov, 13:56


👉ከታሪክ ማህደሮችችን ክፍል2
በነብይነት ጥላ ሥር 🍀
በሒራእ ዋሻ ውስጥ
እድሜያቸው አርባ አመት ሲቃረብ፣ የረዥም ጊዜ ማስተንተናቸው ከወገኖቻቸው ጋር የነበራቸውን የአስተሳሰብ ሸለቆ ይበልጥ አሰፋው። እናም ተገልለው በጥልቀት ማሰብን በመምረጥ ሂራእ ወደ ተባለው ዋሻ ይሄዱ ጀመር። ዋሻው የሚገኘው ከመካ ሁለት ማይሎች ያህል ርቀት ላይ «ጀበለኑር» (የብርሃን ተራራ) በተባለው ጋራ ውስጥ ነው። መጠኑም ትንሽ ነው። ርዝመቱ አራት ክንድ፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ከሦስት አራተኛ ክንድ። በዚህ ዋሻ ውስጥ የረመዳንን ወር ድሆችን በመመገብ፣ በአምልኮና ፍጥረተ ዓለሙንና ከበስተጀርባው ያለውን እጅግ ጥበበኛ ሐይል በማስተንተን ያሳልፋሉ። የወገኖቻቸው የጣኦት አምልኮ ደካማ ባህል እና የተልፈሰፈሰ አመለካከት ያውካቸዋል። ግና የሚረኩበትና የሚረጉበት ግልጽና ጉልህ ጎዳና አልነበራቸውም። ይህን ብቸኝነትና መገለል መምረጣቸው ከምድራዊ ሃሳብ፣ ሕይወትን ከሚጠምዱ ጥቃቅን ጣጣዎች ርቀው ወደፊት የሚጠብቃቸውን ታላቁን አደራ የመሽከም፣ ምድርን የመቀየር እና የታሪክን ሂደት የማስተካከል ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ አላህ ያመቻቸላቸው እቅድና ፈቃድ ነበር። በነብይነት ከመላካቸው ከሦስት ዓመታት በፊት ጀምሮ ይህን የመገለል ልምድ አላህ አመቻቸላቸው። በዚሀ መገለል ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ከነጻው የፍጥረተ ዓለሙ መንፈስ ጋር ይመጥቃሉ። ከፍጡራን ጀርባ ያለውን ሩቅ ሚስጥር ያስተነትናሉ። የአላህ ፈቃድ ሆኖ ከዚህ ሩቅ ሚስጥር ጋር የሚገናኙበት ወቅት እስኪመጣ ድረስ ይህን ያደርጋሉ፡፡ይቀጥላል………

https://www.facebook.com/@tewhidnasuna/

🌍ተውሂድና ሱና

08 Nov, 04:27


صلى الله عليه وسلم ረሱል እንዲህ ብለዋል
"የጁመአ ቀን"
አስራ ሁለት ሰአት ነው። ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰዓት አስች: ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰዓት አሳህን ከጠየቀ አሳህ የጠየቀውን ይሰጠዋስ፣ (ያቺ ሰዓት) በመጨረሻ አካባቢ ከአስር በኋላ ፈልጓት።” ११ [ነሳዒ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ (1389)]

🌍ተውሂድና ሱና

07 Nov, 04:30


የጥዋት የቀልብዎ ስንቅ
ሱረቱል ካፍ
#ቃሪእ ሸይኽ አብዱረህማን ሱደይስ

🌍ተውሂድና ሱና

06 Nov, 11:19


እኔ በሁለቱ መሃል ነኝ
አንድ በዕድሜ ከፍ ያሉ አባት በሁለት ወጣቶች መሃል
ቁጭ ብለው ሳለ ወጣቶቹ ሊሳለቁባቸው ፈለጉና
ከሁለቱ አንዱ ለአዛውንቱ "አንተ ጅል ነህ ወይስ ጃሂል (መሃይም)?" _ ብሎ ጠየቃቸው። እሳቸውም “እኔ በሁለቱ መሃል ነው ያለሁት" በማለት ጅልነቱም ጃሂልነቱም ያለው በትልቅ ሰው ላይ የሚሳለቁና ታላቅን የማያከብሩ ሰዎች ዘንድ እንደሆነ ገለጹላቸው!

ከኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም መፅሀፍ የተወሰደ

🌍ተውሂድና ሱና

06 Nov, 06:39


የመሀላ አይነቶች
~
1. የዛዛታ መሀላ፡- ታስቦበት ሳይሆን በወሬ መሀል ሳይሰተዋል የሚወጣ መሀላ ነው፡፡ ይሄ የመሀላ አይነት እንደመሀላ አይቆጠርም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ
“አላህ በመሀላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]
2. በውል የተቋጠረ መሀላ፡- ታስቦበት የሚወጣ የመሀላ አይነት ነው፡፡ “ወላሂ! ይህን ላደርግ፣ ወይም ላላደርግ” በሚል መልኩ፣ ባለፈ ሳይሆን ወደ ፊት ባለ ነገር ላይ፣ በማይታሰብ ሳይሆን መሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ታስቦ የወጣ መሀላ ሲሆን ሰውየው መሀላውን ካልጠበቀ ማካካሻ (ከፋራ) ይጠብቀዋል፡፡
3. የሀሰት መሀላ፡- የሰዎችን ሐቅ ለመብላት ወይም ለማታለልና ለማጭበርበር ወይም ለሌላም አላማ ቢሆን ሆን ተብሎ በውሸት ላይ የሚፈፀም መሀላ ነው፡፡ ይሄ ዛሬ በንግዱ እና በሌሎችም ማህበራዊ ህይወቶች ውስጥ የተንሰራፋ ጥፋት ነው፡፡ ሆን ብሎ በሀሰት እየማለ የሚሸጥ የሚለውጠው ዛሬ ቀላል አይደለም፡፡ ጌታችን አላህ በዚህ ላይ ምን አይነት ከባድ መልእክት እንዳስተላለፈ እንመልከት፡-
إِنَّ الَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَأَيْمَانِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَئِكَ لَا خَلَاقَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
“እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን እና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ጥቅምን የሚለውጡ በመጨረሻይቱ አለም ምንም እጣ የላቸውም፡፡ በቂያማ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፤ ወደነሱም አይመለከትም፤ አያጠራቸውም፡፡ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡” [አሊ ዒምራን፡ 77]
ጥፋቱ ከከባኢር ማለትም ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ የሚመደብ እንደሆነ ሲገልፁ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “በአላህ ማጋራት፣ ወላጆችን ሐቃቸውን መጣስ፣ ነፍስን ማጥፋት እና የቅጥፈት መሀላ ታላላቅ ወንጀሎች ናቸው፡፡” [ቡኻሪ]

የሀሰት መሀላ ከባድ ወንጀል ከመሆኑ የተነሳ ማካካሻ አልተደረገለትም፡፡ ይሄ የብዙሃን ዑለማእ እይታ ነው፡፡ ይህን የፈፀመ ሰው ያለው ምርጫ የወሰደው ሐቅ ካለ መልሶ፣ የፈፀመው በደል ካለ አስተካክሎ ትክክለኛ ተውበት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አምስት ጥፋቶች ማካካሻ የላቸውም፡፡ በአላህ ማጋራት፤ ያለ አግባብ ነፍስን ማጥፋት ሙእሚንን መዝረፍ፣ በጂሃድ ላይ በፍጥጫ ሰዓት መሸሽ እና ያለ አግባብ ገንዘብ የሚበላበት ሀሰተኛ መሀላ!!” [አልኢርዋእ፡ 2564] ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ “ሆን ተብሎ የሚፈፀም የሀሰት መሀላ ማካካሻ ቅጣቶች ከሚያብሱት በላይ ነው” ብለዋል፡፡ [አልሙደወናህ፡ 1/577]

የመሀላ ማካካሻ /ከፋራህ/
-
አንድ ሰው የሆነን ጉዳይ ሊፈፅም ከማለ በኋላ ቃሉን ቢያፈርስ ወንጀለኛ እንዳይሆን የሚያመልጥበትን ቀዳዳ አላህ አመቻችቶለታል፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከማለበት ጉዳይ የተሻለ ነገር ከታየው ይፈፅመው፡፡ ከዚያም መሀላውን ያካክስ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] ማካካሻውን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡-
فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ذَلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ
“ማበሻውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው (ምግብ) አስር ምስኪኖችን ማብላት ወይም እነሱነ ማልበስ ወይም ጫንቃን (ባሪያን) ነፃ ማውጣት ነው፡፡ (እነዚህን) ያላገኘም ሰው ሶስት ቀናትን መፆም ነው፡፡ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሀላችሁ ማካካሻ ነው፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]

ስለዚህ ማካካሻዎቹ፡-

1ኛ፡- አስር ምስኪኖችን ቤተሰቡን ከሚመግበው መካከለኛ የምግብ አይነት የአንድ ወቅት ምግብ ማብላት፣
2ኛ፡- አስር ምስኪኖችን ሶላት የሚያሰግድ ልብስ ማልበስ፣
3ኛ፡- ሙእሚን ባሪያ ነፃ ማውጣት
ከነዚህ ማካካሻዎች ውስጥ ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ የቀለለውን መርጦ መፈፀም ይችላል፡፡ እነዚህን ካልቻለ ግን፡-
4ኛ፡- ሶስት ቀን መፆም አለበት፡፡ ከ 1 – 3 ካሉት ውስጥ መፈፀም የሚችል ሰው ዘሎ ወደ ፆም መግባት አይችልም፡፡

ማሳሰቢያ 1፡- የመጀመሪያዎቹን ምርጫዎች ባለመቻሉ ፆም የመረጠ ሰው አከታትሎ የመፆም ግዴታ የለበትም፡፡

ማሳሰቢያ 2፡- ከፋራ ወይም ማካካሻ የሚመለከተው መሀላ፡-
1. ወደ ፊት ባለና ሊሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ከተማለ ነው፡፡ ባለፈ ወይም ፈፅሞ ሊሆን በማይታሰብ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከፋራ አይመለከተውም፡፡
2. መሀላው በአላህ ወይም በስሞቹ ወይም በሲፋዎቹ ከሆነ ነው፡፡ በፍጡር የተማለ መሀላ ወንጀል ስለሆነ ማካካሻ ሳይሆን ተውበት ነው የሚያስፈልገው፡፡
3. ተገዶ ሳይሆን በምርጫው የማለው መሀላ ከሆነ ነው፡፡
4. በቃሉ ሳይገኝ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡

ማሳሰቢያ 3፡- አንድ ሰው በሚምል ሰዓት “ኢንሻአላህ” የሚል ቃል አብሮ ካወጣ መሀላውን ቢያፈርስም ማካካሻ መፈፀም አይጠበቅበትም፡፡ [ሶሒሑ ቲርሚዚ፡ 1237]

ማሳሰቢያ 4፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ” ብሎ ቢምልና ያኛው ሰውየ ሳያደርግ ከቀረ የማለውን ሰው ከፋራ ይመለከተዋል፡፡ ነገር ግን ሰውየውን ለማስገደድ ሳይሆን ለማክበር ብሎ ከሆነ ያደረገው ከፋራ ግዴታ አይሆንበትም፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ እንግዶች መጥተው ምግብ ሲያቀርቡላቸው “አንተም ብላ” አሉ ለአቡበክር፡፡ “ወላሂ እኔ አልበላም” አሉ እሳቸው፡፡ እንግዶቹም “ወላሂ እኛም አንበላም” አሉ፡፡ ሁሉም ሲምሉ ጊዜ አቡበክር “ይሄ ከሸይጧን ነው” በማለት በሉ፡፡ እንግዶቹም በሉ፡፡ ነብዩ ﷺ ሲነገራቸው አቡበክርን “አንተ ከሁሉም መልካም የሰራና በላጭ ነህ” በማለት ከማሞገስ ውጭ ከፋራ እንደሚመለከታቸው አልነገሯቸውም፡፡ [ሙስሊም፡ 2057]

ማሳሰቢያ 5፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ ወይም ላታደርግ” ብሎ ቢምል ከሰውየው ጋር እልህ ከመጋባት ይልቅ በመሀላው እንዳይጠየቅ ብንተባበር መልካም ነው፡፡

ማሳሰቢያ 6፡- መሀላን ማፍረስ የተለያየ ብይን አለው፡፡
1. ዋጂብ የሆነ ማፍረስ፡- ወንጀል ሊፈፅም የማለ ሰው መሀላውን ማፍረሱ ግዴታው ነው፡፡
2. ሐራም የሆነ ማፍረስ፡- የማለው ያለበትን ግዴታ ለመፈፀም ወይም ከሐራም ለመራቅ ከሆነ ቃሉን ማፍረሱ ሐራም ነው፡፡
3. ምርጫ ያለው ማፍረስ፡- በሸሪዐው የተፈቀደን ወይም ግዴታ ያልሆነን ነገር ለመስራት ወይም ለመተው ቢምል ፍላጎቱ ከሆነ መሀላውን የማፍረስ ምርጫ አለው፡፡

በሶስቱም ሁኔታዎች መሀላውን ያፈረሰ ሰው ማካካሻ ወይም ከፋራ መፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ ይህ የሚሆነው ግን እያወቀ፣ በምርጫው እና እያስታወሰ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡ እንጂ ባለማወቅ ወይም ተገዶ ወይም ረስቶ መሀላውን የሚፃረር ነገር ቢፈፅም ማካካሻ የመፈፀም ግዴታ የለበትም፡፡

ማሳሰቢያ 7፡- አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ለምሳሌ “ወላሂ ይህን ላልሰራ” እያለ ደጋግሞ ቢምል የሚመለከተው ከፋራ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 01/2010)

🌍ተውሂድና ሱና

05 Nov, 13:46


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
IbnuMunewor

🌍ተውሂድና ሱና

05 Nov, 10:33


«የታሰሩ ሙስሊም ተማሪዎች ዜና!
እለተ ማክሰኞ ጥቅምት 2017 E.C.

   በኒቃብ ጉዳይ ከታሰሩት የአዲስ ከተማ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ተማሪ አሚር አ/ከሪም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ ተማሪ አሚር በት/ቤት ውስጥ ት/ቱን በአግባቡ በመከታተል እና ተማሪዎች በአካዳሚም ይሁን በዲናዊ ህይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በመምከር የሚታወቅ አርአያ ተማሪ ሲሆን፤ ከት/ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር አብሮ እህቶቻችን ለምን ኒቃብ መልበስ ይከለከላሉ ብሎ በሰላማዊ መንገድ በመጠየቁ ብቻ ት/ቤቱ በከፈተው የውሸት ክስ እለተ አርብ በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ ስም ዝርዝራቸው ለፖሊስ ተሰጥቶ በየክፍላቸው እየተዞረ ከተለቅሙት ሙስሊምች ተማሪዎች አንዱ ነበር።

  በዛሬው እለት በዋለው ችሎት አቃቢህጉ ት/ቤቱን በማስረበሽ እና የት/ቤት ንብረትን በማውደም የሚል የውሸት ክስ በተማሪ አሚር አ/ከሪም ላይ ያቀረበ ሲሆን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ተወክሎ የቆመለት ጠበቃ ሁሴንም በችሎቱ ላይ ባቀረበው ብርቱ ክርክር የዋስ መብቱ ተጠብቆ በመጨረሻም በ5ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወስኗል፤ በቅድሚያ አላህን እናመሰግናለን በመቀጠል ለአዲስ አበባ መጅሊስ እና ለጠበቃ ሁሴን ምስጋናችን ይድረስ።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪ ነቢል እና ተማሪ ሰሚር በመጪው ሀሙስ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የክስ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሮ ያልተያዙ ሙስሊም ተማሪዎች አሁንም ድረስ በፖሊስ እየተፈለጉ በመሆኑ ሁሉም የት/ቤታችን ሙስሊም ተማሪዎች በነፃነት የመማር መብታቸው ተከብሮ ወደ ቀድሞው የትምህርት ገበታቸው እስኪመለሱ ድረስ ሁሉም ሙስሊም የሚችለውን አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርግልን በአላህ ስም እንጠይቃለን።

ኒቃቧንም ትለብሳለች‼️
ትምህርቷንም ትማራለች‼️»

©: የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ

🌍ተውሂድና ሱና

05 Nov, 07:36


ሁሉንም ልጆች እንደዚህ አላህ ያስተካክላቸው

🌍ተውሂድና ሱና

05 Nov, 04:03


🍀የጥዋት አዝካር
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلَّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ.

👉አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ዐላ ነቢይና ሙሃመድ

👉አላህ ሆይ! በነብዩ ላይ ሰላምታ አውርድ፡፡ ሰላም አስፍንም፡፡(አሥር ጊዜ)

🌍ተውሂድና ሱና

04 Nov, 15:06


#ፂም ማሰደግ ወንጀል የሆነበት ሀገር#
ሰለምቴው መምህር ፂሙን በማሳደጉ ለዲሲፕሊን ቅጣት መዳረጉ ተገለፀ።

▣ ጺሙን ካልተቆረጠ በስራው ላይ መቀጠል እንደማይችል ተነግሮታል።

- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ሰቱዲዮ ጥቅምት 25/2017

ሰለምቴው መምህር አሸናፊ ትርፋ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ገዋታ ወረዳ የገዋታ ትምህርት ቤት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት መምህር ሲሆን መደበኛ ስራውን እየከወነ ቢሆንም ከጺሙ ጋር በተያያዘ የዲስፒሊን ቅጣት ተጥሎበታል። ጺሙን ካልተቆረጠ ወደ ማስተማር እንደማይመለስም ተገልጾለታል።

ለጺም ማሳደጉ ምክንያት ተደርገው የቀረቡ ክሶችም፦

1/ የተማሪዎችን ስነ-ልቦና የሚሰርቅ መሆኑ

2/ ትም/ት ከፖለቲካና ሃይማኖት ነፃ ነዉ የሚለዉን መርህ መጣሱ

3/ በየደረጃ ካሉ አመራሮች ወይም በህግ ስልጣን ከተሰጣቸዉ አካላት ለሚሰጡ ህጋዊ ትዕዛዞቸ አፋጣኝ ምላሽ ያለመስጠትና አለመፈፀም

4/ በማኅበራዊ ምድያ የዉሸት መረጃ በማሰራጨት በትም/ቤቱ ር/መ/ራን ላይ ሌሎችን መቀስቀስና ማነሳሳት ጥፋት የሚሉ ሲሆን በእነዚህ አራት ክሶች ምክንያት የ3 ወር ደመወዝ ቅጣት እና ፂሙን እንዲያስቆርጥ መወሰኑን ከውሳኔ ደብዳቤው መረዳት ችለናል።

- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ የወረዳውን ትምህርት ጽ/ቤት አመራሮችን ለማግኘት ጥረት እያደረግን ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚዲያ

🌍ተውሂድና ሱና

04 Nov, 14:24


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።
* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።
- "አዎ" አለ ሰውየው።
* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።
- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ
Ibnumunewor

🌍ተውሂድና ሱና

04 Nov, 06:15


#ተፍሲር አማ ጁዝ
#ኡስታዝ አቡ አማር ያሲን ሙሌ
ክፍል 6

🌍ተውሂድና ሱና

03 Nov, 09:12


የቁርአኑን ቀጣይ ክፍል አሟሉ
نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ نَبَأَهُمْ بِالْحَقِّ إِنَّهُمْ فِتْيَةٌ آمَنُوا بِرَبِّهِمْ وَزِدْنَاهُمْ.........؟

سورة الكهف

🌍ተውሂድና ሱና

03 Nov, 04:33


ለፈጅር ሶላት ስነሳ እነሱም ወደ ቸርች የሚሄዱ ጎረቤቶች አሉኝ። ታዲያ እስቲንጃም አያደርጉ። ፊታቸውንም አይታጠቡም። ለምንድነው ብዬ ስጠይቅ በእምነቱ ጠዋት ለፀሎት ሲሄዱ መተጣጠብ ይከለከላል አሉ።

አላህ ንፁህ ነው። ንፁህንም ይወዳል። ሸይጧን ቆሻሻ ነው። ቆሻሻንም ይወዳል። ንፁህ ሆናችሁ አትምጡ የሚል «አምላክ» ካለ እሱ ሸይጧን ነው።

ጠንቋዮችም እንዲሁ ናቸው። እስቲንጃም አያደርጉም። ጀናባቸውንም አያወርዱም። ምክንያቱም ንፁህ ከሆኑ ሸይጧኑ ሊቀርባቸው አይችልም።

አላህ የጠላውን ሰው እንዲህ ያደርገዋል። በዱንያ ሲኖር ቆሻሻ ያሸክመዋል። በአኼራ ደግሞ የቁስል መግላሊት ይግተዋል።

አላህ ከእንዲህ አይነቱ ኪሳራ ይጠብቀን
ከሰልማን የተወሰደ

🌍ተውሂድና ሱና

02 Nov, 11:57


ለወላጆች ሁነኛ ሶደቃ
~
ለሞቱ ወላጆችዎ ሶደቃ መፈፀም ይፈልጋሉ? አቅሙ ላለው ሰው የውሃ ችግር ባለበት አካባቢ ውሃ ማውጣት ትልቅ ሶደቃ ነው። አገልግሎቱ እስካለ ድረስ አጅሩ አይቋረጥም።
* ሰዕድ ብኑ ዑባደህ ረዲየሏሁ ዐንሁ - "እናቴ ሞተች። ሶደቃ ልፈፅምላት?" ብለው ነብዩን ﷺ ጠየቁ።
- እሳቸውም "አዎ" አሉ።
* "የትኛው ሶደቃ ነው በላጩ?" አሉ ሰዕድ።
"ውሃ ማጠጣት" አሉ ነብዩ ﷺ።

[ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 3668]
bnuMunewor

🌍ተውሂድና ሱና

02 Nov, 06:35


በመላኢካዎች ማመን ክፍል #49

🌍ተውሂድና ሱና

01 Nov, 17:03


የጎዳና ላይ ደእዋ
#አላህ ይጨምርላቹ በዚህ ሰበብ ስንቱ ይሰልማል

🌍ተውሂድና ሱና

01 Nov, 05:19


♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
_
🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል።
____
©ተውሂድና ሱና

🌍ተውሂድና ሱና

31 Oct, 18:15


صلوا على رسول اللهﷺ
#ሰሉ አለ ረሱልአላህ

🌍ተውሂድና ሱና

30 Oct, 17:37


ርእስ፣በመላኢካዎች ማመን ሊቀራ የሚገባው ምርጥና አንገብጋቢ የአቂዳ ኪታብ

🌍ተውሂድና ሱና

29 Oct, 16:59


ኒቃቧንም ትለብሳለች
ትምህርቷንም ትማራለች

🌍ተውሂድና ሱና

29 Oct, 10:22


#ተፍሲር አማ ጁዝ
#ኡስታዝ አቡ አማር ያሲን ሙሌ
ክፍል 5

🌍ተውሂድና ሱና

28 Oct, 10:33


ኒቃቧንም ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች !!

🌍ተውሂድና ሱና

28 Oct, 06:49


#ለሁሉም ነገር አልሀምዱሊላህ
ምንኛ ያማረ ቃል ነው።

🌍ተውሂድና ሱና

27 Oct, 12:32


ኒቃብ መልበስ ወንጀል አይደለም።

🌍ተውሂድና ሱና

27 Oct, 05:48


#የጅብሪል ሀዲስ ኡሱል ክፍል 47
ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት፡- አንድ ቀን ከአላህ መልእክተኛ ( ﷺ) ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ እና በጣም ጥቁር ፀጉር ያለው አንድ ሰው ከፊታችን ታየ። በእርሱ ላይ ምንም ዓይነት የጉዞ ምልክት አይታይበትም, እና ማናችንም ብንሆን አናውቀውም. ከነብዩ ( ﷺ) አጠገብ ተቀምጦ ጉልበቱን ከጭኑ ላይ አርፎ "ሙሐመድ ሆይ! ስለ እስልምና ንገረኝ" አለ።ﷺ
# ‹ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሰላት መስገድ፣ ዘካን መስጠት፣ የረመዳንን ጾም መጾም እና ወደ ቤቱም ሐጅ ማድረግ ነው። ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለው።
#እርሱን በመጠየቁ በጣም ተገርመን ነበር።
#የአላህ መልእክተኛ ( ﷺ) “ስለ ኢማን አሳውቀኝ” አሉ። (የአላህ መልእክተኛም) እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “በአላህና በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቶቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን በቀደርም (በዕጣ ፈንታው) በመልካምም ሆነ በመጥፎው ነገር ማመን ነው። እውነት ተናገርክ አለ።
#ከዚያም (ሰውየው) ኢህሳንን አሳውቀኝ አለ። እሳቸውም ነቢዩ ( ﷺ)፡- ‹‹አላህን እንደምታዩት አድርጋችሁ ተገዙት፤ ምንም እንኳን ገና ማየት ባትችሉም እርሱ ያያችኋልና።
#ስለ ሰዓቲቱም ስለ ቂያማ አሳውቀኝ አለ። እሳቸውም (የአላህ መልእክተኛ) ‹‹ስለዚህ ተጠያቂው ከጠያቂው በላይ አያውቅም። እርሱም፡- «ታምራቶቹን ንገረኝ» አለ። ባርያይቱ እመቤቷን ትወልደለች፣ ባዶ እግራቸውን፣ ራቁታቸውን፣ ድሆችን፣ የበግ እረኞች (እርስ በርስ ሲፎካከሩ) ከፍ ያሉ ሕንፃዎችን ሲያሳድጉ ታያለህ አለ። ከዚያም ሰውየው ሄደ. ትንሽ ቆይቼ ከዛ (የአላህ መልእክተኛ ) "ዑመር ሆይ ያ ጠያቂ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?" እኔም “አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ አልኩዋቸው፣

🌍ተውሂድና ሱና

26 Oct, 15:40


#ቁርአን የልብ እርጋታ
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ

🌍ተውሂድና ሱና

26 Oct, 13:17


አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፍት ሶስት አመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪወች ወይ አውልቁ ወይ ትምህርት ቤት አትምጡ ተብለዋል ። ከትምህርት ከታገዱም ሳምንት አለፍቸው መጅሊሱም መረጃ ቢደርሰውም እየተባበረ አይደለም እዛ አከባቢ ያላቹህ የተማሪወች ወላጆች ወጣቶች ይህንን ችግር በኔነት ስሜት ተከታትላቹህ እህቶቻችን ዳግም ትምህርት እንዲመለሱ እንቅስቃሴ አድርጉ ።

🌍ተውሂድና ሱና

26 Oct, 03:06


ከሶላት በኋላ የተስቢሕ አፈፃፀም
~
1- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ። 100ኛ "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለት። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
2- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 34 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [ሙስሊም]
3- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ ማለት። ድምሩ 99 ይሆናል። [ሙስሊም]
4. ሱብሓነላህ 10 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 10 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 10 ጊዜ ማለት። ድምሩ 30 ይሆናል። [ቡኻሪይ]
5. ሱብሓነላህ 11 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 11 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 11 ጊዜ ማለት። ድምሩ 33 ይሆናል። [ሙስሊም]
6. ሱብሓነላህ 25 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 25 ጊዜ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ 25 ጊዜ እና አሏሁ አክበር 25 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]

🌍ተውሂድና ሱና

25 Oct, 13:42


#ኡሱሉል ኢማን ክፍል 46
#የመላኢካዎች ባህሪ

🌍ተውሂድና ሱና

25 Oct, 05:47


በጁሙዐ ቀን ከሚወደዱ ተግባሮች ውስጥ አንዱ በነብዩ ﷺ ላይ ሰላት ማውረድ ነው።

🌍ተውሂድና ሱና

24 Oct, 08:44


#ተፍሲር አማ ጁዝ
#ኡስታዝ አቡ አማር ያሲን ሙሌ
ክፍል 4

🌍ተውሂድና ሱና

24 Oct, 03:35


👉የጥዋት ዚክር
الَّذِي لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيءٌ في الأرْضِ وَلَا في السَّمَاءِ وَهـوَ السَّمِيعُ العَلِيمُ [ثَلاثَ مَرَّاتٍ]

👉"ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ ማዐስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዲ ወላ ፊሰማእ ወሁወ ሰሚዑል ዐሊም።"

#በአላህ ስም፣ እርሱ አላህ ከስሙ
ጋር በስሙ የተጠበቁትን በሰማይም በምድርም ምንም ነገር አይጎዳቸውም፡፡ እርሱ ሰሚም አዋቂም ነው፡፡ ይህን ዚክር ቀንና ማታ 3 ጊዜ ያለ ሰው ምንም ጉዳት አይደርስበትም ድንገተኛ በላዕ አያገኘውም።

🌍ተውሂድና ሱና

23 Oct, 14:38


لا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لا شَريكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ ولهُ الحَمْـد، وهُوَ على كُلِّ شَيْءٍ قَدِير

ላኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለህ
ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሃምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር

#ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር
የለውም፡፡ ንግሥና ለርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢው ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡››- (1ዐ ጊዜ ወይም ካልቻለ 1 ጊዜ)

🌍ተውሂድና ሱና

22 Oct, 19:05


መርካቶ ላይ ንብረታቹ የወደመባቹ እህትና ወንድሞች አብሽሩ ሶብር ማድረግ አሁን ነው።አላህ በተሻለው ይተካላቹሃል፣አጅራቹም እጥፍ ድርብ ነው።

🌍ተውሂድና ሱና

22 Oct, 16:13


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

الحمد لله
የሶባው ፕሮግራም በሰላም እና ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።

በዚህ ፕሮግራም በቻላችሁት ሁሉ ለተሳተፋችሁ ወንድም እህቶች ጀዛኩሙላህ ኸይረን ጀዛ

👉ሶባ ላይ በነበረው የዳእዋና የዚያራ ፕሮግራም ብዙ ጥቅሞች እንዲሁም መስለሀወች ተገኝተዋል። ከነዚህም ውስጥ👇

- የሀሪማ ደረሳወች እና ሸሆችም ጭምር በቂ የሆነ ነሲሀ አግኝተዋል

- የአሽአሪያ መዝሀብና አቂዳ ተብራርቷል

- ተውሂድ በስርአቱና በደንብ ተነግሯል

-ሱና በደንብ ተተርኳል

-ቢድአ እና የቢድአ ባልተቤቶች በደንብ ተዘርዝረዋል

- ከአርባ ጫማ ሄደው ሰወች እያመጡ የሚያስፈራሩበትና የሚፋረዱበት ``አንካሴ`` ምንም እንደማይፈጥር የሽርክ ተግባር እንደሆነ ተነግሯል

-ላይ ሶባ እና በሌሎች ሀገሮች የሚሰራ [የጎበደን`አምልኮ ባጢል መሆኑና አላህ ከማይምረው የሽርክ ተግባር እንደሆነ በገሀድ ተጠቅሷል

- ``ቦረናም`` በሰሱ ተነክቷል

-ከአላህ ውጭ ማመልና መፋረድ ሽርክ መሆኑ ተነግሯል

-የአህባሽና የሱፍያ አመለካከት ያላቸውን አከላቶች አስደንግጧል

-ከኢስላም ውጭ ሌላን እምነት ለመስበክ የሚሯሯጡ የሱናና የሱንዬች ጠላት የቢድአና የቢድአ ባልተቤቶች ወዳጆች ኩርቤያቸው ተስብሯል

- በተውሂድና በሱና ላይ ቡሎም በሱንዬች ላይ ፊጥ ፊጥ የሚሉ እና ካለ አቅማቸው የሚንጠራሩ አካላት አቅማቸውንና ደረጃቸውን ብሎም ቦታቸውን ሊያውቁ ችለዋል

-ብዙ አባት እና እናቶች ፣ወጣቶች ተመክረዋል ተገስፀዋል


الحمد لله
ብዙ ጥቅሞችንን እና ብዙ ነገሮችን አጊተንበታላል ጠቃሚ እውቀትም ከመሻኢኾቻችን ጨብጠንበታል።

ወንድም አቡ ሹራ አህመድ ሶባ

ቻናላችንን ተቀላቀሉ👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4598
https://t.me/Sobabilalmesjid/4598

🌍ተውሂድና ሱና

22 Oct, 08:03


አይ የመርካቶ ነገር፣በጣም ያሳዝናል አንዱ ንብረቱ ይወድማል ከፊሉ ለመሰረቅ ይራራጣል አላህ ይድረስላቸው

🌍ተውሂድና ሱና

20 Oct, 18:58


ኡስታዝ የሲን ሙሌ
ተፍሲር ክፍል 3

🌍ተውሂድና ሱና

20 Oct, 06:43


👆🏻👆🏻👆🏻
📚የቴሌ እና ሌሎች አክሲዮኖችን ይቻላል ወይስ አይቻልም?
በደንብ ይደመጥ በደንብ የተብራራ


🔗 ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/tewhidnasuna

https://www.facebook.com/tewhidnasuna

🌍ተውሂድና ሱና

19 Oct, 03:30


#ኡሱሉል ኢማን ክፍል 45
ስለ ጂብሪል ባህሪ እስከ 600 ክንፎች እንዳሉትና በሌሎችም ባህሪያቱ ዙሪያ የሚያጠነጥን።ስራውስ ምንድነው?

🌍ተውሂድና ሱና

18 Oct, 08:41


💫ብስራት  💫ብስራት  💫ብስራት

🫧[[ ታላቅ የደዕዋእና የኢጅቲማእ ፕሮግራም ]]🫧

🌃 በዉቢቱ'ና የሙስሊሙች መናገሻ በሆነቺው "በደቡብ ወሎ ዞን" አልብኮ ወረዳ ሶባና ጀብል በ013 ቀበሌ ሶባ ቢላል መስጅድ ታላቅ የደዕዋ እና የኮንፈረንስ ፕሮግራም ✈️

📢 ለመላው ደዕዋ ናፋቂ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ ጥቅምት -10/02/2017- በአይነቱ ለየት ያለ የደዕዋ ፣የኢጅቲማእ ፣የዚያራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እየጠበቃቹህ ይገኛል።

🔄የእለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ፦

❶ ሸይኽ ሙሀመድ መኪን -ሐፊዞሁሏህ - [ከደሴ]

     ❷ ኡስታዝ ሀሰን ኢድሪስ(አቡ ሙአዝ) -ሐፊዞሁሏህ -[ከሀርቡ]

          ❸ ሸይኽ ሙሀመድ ሰኢድ- ሐፊዘሁሏህ [ከደሴ]

❹ ሸይኽ ጀማል አዘ ሀቢ -ሐፊዞሁሏህ -[ከደሴ]

      ❺ ሸይኽ ኢማም ፔፕሲ -ሐፊዞሁሏህ -[ከደሴ]

           ❻ ሸይኽ አህመድ አወቀ -ሐፊዞሁሏህ - [ከደሴ]

❼ ሸይኽ ሀሰን ቃዲ -ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

❽. ሸይኽ ሙሀመድ አሚን-ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ) (ከደሴ) (ከደሴ)

❾. አቡ ሶላሁዲን ሸይኽ ሁሴን- ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

❿ ወንድም አቡ ሀሳን አሊይ -ሐፊዘሁሏህ (ከኮ/ቻ)

❶❶ ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሴን- ሐፊዘሁሏህ(ከደሴ)

❶❷ ወንድም አቡ ዑበይዳህ ሰኢድ-ሐፊዘሁሏህ(ከኬሚሴ)

❶❸ ወንድም አብደል መሊክ-ሐፊዘሁሏህ (ከኬሚሴ)

❶❹ ሸይኽ ኢስማኢል-ሀፊዘሁሏህ(ከኮ/ቻ)

❶❺ ሸይኽ ሙሀመድ ኡመር ''ጀሜ''-ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

እና በሌሎችም ተናፋቂና ብርቅየ መሻኢኾች እና ኡስታዞች 'ሶባ'' ደምቃ እና ተውባ ትውላለች-ኢንሻ አሏህ- ስለሆነም የሶባ(የአሸዋው) እና   እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ብሎም ተወላጆችም ጭምር በየትም የምትገኙ የደዕዋ ናፋቂዎች  በሙሉ በክብር ተጋብዛችኋል።

🕌 አድራሻ ፦ አልብኮ ወረዳ ጦሳ ፈላናን ተሻግሮ በተለምዶ "አሸዋው " በመባል የሚጠራው ሰፈር "ቢላል መስጅድ" ወንዙን ተሻግሮ ከጁኒየር ትምርት ቤቱ አጠገብ።

አዘጋጅ = የሶባ ቢላል መስጅድ ጀመአ

በአካል መገኘት የማትችሉ ኔት ካለ -ኢንሻ አሏህ- በዚህ ቻናል ለማስተላለፍ እንሞክራለን!
ወይንም እሪከርድ ይለቀቃል
👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4305
https://t.me/Sobabilalmesjid/4305

የፕሮግራሙ ሰዓት፦ ጠዋት 3:00-4:00 ባለው ሰአት ይጀመራል

🚙እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል

መልዕክቱን ሸር እና ኮፒ አድርጉልን
ሸር ሸር ሸር

ይህ ቻናል ዳእዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል 013 የቴሌግራም ቻናል ነው። ይቀላቀሉ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid

🌍ተውሂድና ሱና

18 Oct, 03:06


#ቃሪእ ሸይኽ አብደላህ መጥሩድ #ሱረቱል ከህፍ ከጁመአ ሱናዎች አንዱ ሱራ ካፍ ማዳመጥ ወይም መቅራት

🌍ተውሂድና ሱና

18 Oct, 03:03


♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
_
🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል።
____
©ተውሂድና ሱና

🌍ተውሂድና ሱና

17 Oct, 09:34


የጎዳና ላይ ደእዋ

🌍ተውሂድና ሱና

17 Oct, 04:59


#እነ ሊላሂ ወኢነ ኢለይሂ ራጂኡን!መውተል ፉጀአ ከባድ ነው።ማታ ምንም ሳይታም ሰርቶ የገባ ሰው ለሱቢ ሞቶ ስታገኘው ያስደነግጣል አላህ ይዘንለት።እኛንም አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን!

🌍ተውሂድና ሱና

16 Oct, 07:35


🍀እንዳስለቀስካቸው አስቃቸው!

🎙ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ
……………………………………………

☑️Telegram
t.me/tewhidnasuna

☑️Facebook:
fb.com/tewhidnasuna
👉tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMhfQPKor/

🌍ተውሂድና ሱና

15 Oct, 08:08


ቁርአንን እናዳምጥ

🌍ተውሂድና ሱና

14 Oct, 17:54


🎤 አድስ ሙሀዶራ ቁጥር ❺

🗳 ርዕስ:-«በአላህ ድን ላይ በነፍስያም በገንዘብም መታገል»

📌  መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሀዶራ።

🎙 በኡስታዝ :-አቡ ሙአዝ ሀሰን ኢድሪስ {ሀፊዘሁላህ}

🕌 በአልብኮ ወረዳ ሰላም መስጅድ አለህ ይጠብቃት

📆 በዕለተ እሁድ በቀን 03/02/2017 E.C
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
❇️======🟢=∞=====🟢

📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል
ሚዲያ ለመከታተል:

🟢"የዳእዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባና ጀብል ቀበሌ የቴሌግራም ቻናልን ይጎብኙ"‼️

🗞️ በ Telegram~Channel 👇
🌐
https://t.me/Sobabilalmesjid
🎙ሌሎች ተጨማሪ ድምፆችን ለማግኘት
👇https://t.me/Sobabilalmesjid

🌍ተውሂድና ሱና

14 Oct, 17:13


#ቁርአን ተፍሲር
በአቡ አማር ኡስታዝ ያሲን ሙሌ ክፍል 2
ሙአዊዘተይን

🌍ተውሂድና ሱና

14 Oct, 06:32


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
ከወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሶደቃ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
IbnuMunewor

🌍ተውሂድና ሱና

13 Oct, 09:14


ኡሱሉል ኢማን ክፍል 44
ሊቀራ የሚገባው ምርጥና አንገብጋቢ የአቂዳ  ኪታብ# ስለ ሽርክ፣ስለ አቂዳ  ስለ ተወሱል የሚያብራራ,።

🌍ተውሂድና ሱና

13 Oct, 06:51


እጅግ አስደናቂ ታሪክ!
ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ የግብረ ገብ ኪታብ ውስጥ መፃፍ አለበት!"
አቡ ዐብደላህ ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሙሳ አል– ቃዲ "- በአር-ረይ - ከተማ በሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት አ/ሂ ምክር ቤት ተገኘሁ።" ይላሉ። የሰሙት እና ያዩት አሰደናቂ ክስተት እንዲህ ሲሉ ያጫውቱናል።

"አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ለክስ ቀረበች፣ ቅርብ ሀላፊዋ (ወሊዯ) ባሏ ላይ አምስት መቶ ዲናር መህር እዳ እንዳለበት ክስ መሰረተ፣ ባልየው ግን የተባለው ብር እዳ የለብኝም በማለት ክሱን አልተቀበለም።

ዳኛውም፦ “ምስክሮችህ የት አሉ?” ሲል ጥያቄ አቀረበ።
ባልም፦ “ሁሉም እዚህ ተገኝተዋል” በማለት መለሰ።
ዳኛውም፦ ከምስክሮች መካከል አንዱን ጠርቶ፤ " "ሴትየዋ እሷ መሆኗን እንዲመለከትና ምስክርነቱ እንዲሰጥ አዘዘ።
ምስክሩም ተነስቶ፣ ሴቲቱን፦ “ተነሺ” አላት።

ባልየውም(በቅናት መንፈስ)፦ "ምን እየሰራህ ነው?" ምን ልታደርጋት ነው?! ሲል ጥያቄ አቀረበ።

የሴቲቱ ወኪል፡- "ሚስትህን በትክክል ለይቶ ያውቃት ዘንድ ኒቃቧን ከፍታ ሊመለከታት ነዋ።"

ባልየውም ለዳኛዋ ፦ " ፊቷን በፍፁም እንዳትገልጥለት! የምትለውን ጥሎሽ የማግኘት መብት እንዳላት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለ።

ሴቲቷም ክሷን ወዲያውኑ ሰርዛ፡- "ጥሎሽን አውፍ ብየዋለሁ! በዱንያም ሆነ በአኼራ ነፃ እንዳደረግኩት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለች።

ዳኛውም፡- "ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ በመልካም ሥነ ምግባር ኪታብ ውስጥ ይስፈር!" ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ።

📚ኸጢብ አልበግዳዲይ "ታሪኽ አልበግዳድ" በተሰኘው ኪታባቸው (13/55) ላይ ኢብኑል ጀውዚይ ደግሞ " አልሙንተዘም ፊ ታሪኽ አል ኡመም ወል ሙሉክ (12/403) ላይ አስፍረውታል።

🌍ተውሂድና ሱና

13 Oct, 03:25


🎙አድስ ሙሀዶራ

   🏟 ወደ ሽርክ የሚያዳርሱ ነገሮቾ
        
🎙በአቡ ሹራ አህመድ ኢብኑ ካሳየ «ሐፊዘሁሏህ»

🎥📲 በቀጥታ የስርጭት ሊንክ የተደረገ
✈️

ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid

10,368

subscribers

350

photos

245

videos