#እስራት ሰዎችን ውስን ያደርጋል እንዳትበዙ ፣ እንዳትወጡ ፣ እንዳትሰፉ ለብዙ ትውልድና ሀገር እንዳትሆኑ ነው እስራት የሚያደርገው ።
#ያቺ የአህያ ውርንጭላ ሰፈር ሊያስቀሯት ነው የፈለጓት ከቻሉ የራሳቸው ባሪያ ። እስራት ባሪያ ነው ሚያደርገው ። ፍቃድ የሌለን ፣ ምርጫ ፣ ሀሳብ የሌለን ፣ ራእይ የሌለን ነው ሚያደርገው ።
#እስራት ያለንን ህልም እና ራእይ እንዳንፈፅም paralized ነው ሚያደርገው ። ሳምሶንን የሚያክል ሰው አይኑን አውጥተው አስረውት ነበር ። #ኢየሱስ ያስነሳው አላዛር ተነስቷል ትንሳኤ መንፈስ ውስጡ አለ ግን አይራመድም ለምን ታስሯል #አያችሁ ከአጋንንት ቀጥሎ ወደ ብዙ አቅጣጫ እንዳትዘረጉ የሚያደርጉ ሰዎች አሉ እነዚህን ሰዎች እንድንለይ እግዚአብሔር አይናችንን ይክፈት አሜን
#ደግሞ አሉ በህይወታችን ጓደኛ ፣ ባል ፣ ሚስት ፣ ፓስተር ሆነው የተቀመጡ ለእግዚአብሔር ነገር ውስጣችን ላለው አቅም መንገድ ዘግተው እንዳንገለጥ አስረው ያስቀመጡ :- አንዳዶች ደግሞ ከእኔ ውጭ ምንም ማድረግ አትችይም አትችልም ብለው ያሰሩ ይሄ ክፉ እስራት ነው እግዚአብሔር ሲፈጥረን ብዙ አቅም አስቀምጧል ለሃገር ለትውልድ ሚሆን ሊገለጥ የተገባው ዛሬ ንቁ እስራቱን ፍቱ ውጡ ከወጥመድ ውስጥ
#አስባችሁት ታውቃላችሁ አንዳንድ የቅርብ የምትሏቸውን ሰዎች ውስጣችሁ ያለውን የስራ ፍላጎት ልታደርጉ ያሰባችሁትን ስታማክሯቸው እንዳትሰሩ ደግማችሁ እንዳታስቡ አድርገው ላትነሱ አድርገው ሚገድሏችሁ በቁም ሚያስሯችሁ በአሳብ ከማገዝ በርቺ በርታ ከማለት ይልቅ በቃ ድንዝዝ አድርገው እስር ሚያደርጉ ይሄ እስራት ነው አምልጡ ሽሹ ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ለምን ካላችሁ ውስጣችሁ ያለው አቅም ሊገለጥ ይገባል
#እያንዳዳችን ውስጥ የሆነ ሊገለጥ የሚገባው አቅም አለ ። ያቺ የአህያ ውርንጭላ ሰፈር አስረዋት ነበር ጌታ ደቀመዛሙርቱን ሲልካቸው የታሰረች የአህያ ውርንጫ አለች ፈታችሁ አምጡልኝ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ አላቸው
#ዛሬ የሆነ አጥር ውስጥ ያላችሁ ምንም እንደማትጠቅሙ የተነገራችሁ አቅማችሁን የቀበሩባችሁ ተነሱ ውጡ ከወጥመዳችሁ አምልጡ እስራታችሁን ፍቱ የዛሬ መልእክቴ ነው
ቻናላችንን ይቀላቀሉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ ✓👇
https://t.me/focusinternationalministry