የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 14:7-17
የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል ማንም ለሰርግ ቢጠራህ በከበሬታ ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ተጠርቶ ይሆናልና፡ አንተን እርሱንም የጠራ መጥቶ ለዚህ ስፍራ ተውለት ይልሃል፥ በዚያን ጊዜም እያፈርህ በዝቅተኛው ስፍራ ልትሆን ትጀምራለህ። ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ ወዳጄ ሆይ፥ ወደ ላይ ውጣ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል።
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።
የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ። ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና። ከተቀመጡትም አንዱ ይህን ሰምቶ በእግዚአብሔር መንግሥት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው። እርሱ ግን እንዲህ አለው አንድ ሰው ታላቅ እራት አድርጎ ብዙዎችን ጠራ....
👉2 ቆሮንጦስ 9:5-ፍጻሜ
👉1 ጴጥሮስ 5:2-12
👉ሐዋ.ሥራ 14:23-ፍጻሜ
👉ቅዳሴ ዘቄርሎስ
ምስባክ
መዝሙር 20:1-2
👉
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ