ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን @tnshuabetechrstian Channel on Telegram

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

@tnshuabetechrstian


እኛስ በትዳር ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን።
ትንሿ ቤተክርስቲያንን እናይ፣እናውቅ እና እንወድ ዘንድ እንማማራለን። @LovableFamily

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን (Amharic)

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን የሚባለው የአምላክ እናት የቃልም ጊዜ ነው። እኛ ስለሚጠቀምበት እናቶች ላይ ያየነው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ለማምረትና ለታምራት እንዲያደርግ እንመለሳለን። ስለዚህም የትንሿ ቤተ-ክርስቲያንን ወደፕየሉ እና ወደላይቻና መረጃውን የሚረዳን፣ በአሁኑ ከፈለገው ቀላል ችግርን እንክበካለን።

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

06 Jan, 19:24


ኑ! እናመስግን። አምላካችን እግዚአብሔር ከሠማይ ወረደ ከንጽሕት ድንግል ተወለደ። ደግሞም እናድንቅ ፦ ቸሩ በበረት ሆኖ እያለቀሰ ከእናቱ ጡት ወተትን ለመነ። ለነፍሳችንም ፦ ንጉሥሽና አምላክሽ ዛሬ ተወልዷልና ደስ ይበልሽ እንበላት። መልካም የልደት በዓል ይሁንላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

22 Dec, 19:27


ልክ እንደዚህ

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

22 Dec, 04:53


ተወዳጆች።

ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር)
#በኢንቴክስ-ፉድ-ኤይድ-ፕላስ በሰላም ዘርፍ ዕጩ ሁነዋል።

ሁላችንም በመምረጥ እኛኑ ለምነው ተጨንቀው ለጉባኤ ቤት ከሚደክሙት ባሻገር በዚህም ተሳትፈን ለዓላማቸው መሳካት መንፈሳዊ ድርሻችንን መወጣት አለብን።

ካሸነፉ #10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ።

9355 ላይ BIW08 ን በመላክ መምረጥ ይቻላል።


🗓 ድምጽ መስጠቱ  እስከ ሐሙስ
ታህሳስ 17 ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

17 Dec, 09:49


ስለ አባ እንጦንስ እና አባ ሂላርዮን(አብላርዮስ) እንዲህ ተባለ፦
"አባ ሂላርዮን ከፍልስጤም ሶሪያ ወደ አባ እንጦንስ ደብር ሲመጣ አባ እንጦንስ እንዲህ አለው፦"ቀኑን የምታበራው ችቦ ሆይ እንኳን ደኸና መጣህ!" አባ ሂላርዮንም መልሶ እንዲህ አለው፦"ለዓለም ብርሃንን የምትሰጥ የብርሃን ዓምድ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን!"

_The Sayings of Desert Fathers, pp 111

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

23 Nov, 08:18


"ሰውን ወዳጅ አንተ ሰው አድርገህ ፈጠርከኝ አንተ የኔ አገልግሎት አያስፈልግህም እኔ ግን ያንተ ጌትነት ያስፈልገኛል" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ)
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

18 Nov, 07:04


"ሚስቶች ሆይ፦ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ። ባሎች ሆይ፦ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው። ልጆች ሆይ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። አባቶች ሆይ፦ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው።" ቆላስይስ ፫፥፲፰-፳፩
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

15 Nov, 03:59


ሳምራዊቷ ሴት ውሃ አጠጭኝ ሲላትም የተጠማው
ውሃን ሳይሆን የእርሷን ነፍስ ነበር እርሷ ግን የተጠማው ምን እንደሆነ ሳታውቅ ፣ስለዘር ልዩነት
ለመከራከር ተነሳች። መቼም የእግዚአብሔር ን ስጧታና ውሃ አጠጡኝ የሚላቸው ማን እንደሆነ የማያውቁ ሁሉ  ዘኞች ናቸው። ከመድኃኒዓለም
ክርስቶስ ፊት ቆመውም እንኳን ዘር መቁጠራቸውን
አያቆሙም። እግዚአብሔር ግን የሚፈልገው የሰዎችን ነፍሳቸውን እንጂ ወደላይ ቢቆጠር ሄዶሄዶ
አንዱ አዳም ላይ የሚያርፈውን የዘር ሀረጋቸውን አይደለም። "

      --- ሕማማት ----
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

11 Nov, 10:18


የጥሩ ኑሮ መነሻው መንፈሳዊነት ነው፡፡ መፍትሔው ራስን መርሳት ሳይሆን ራስን በወንጌል ማንሳት ነው!! ኦርቶዶክሳዊነት ወደ ከፍታ የምንወጣበት መሰላል ነው። ከእግዚአብሔር ለመኖር ቀጠሮ ማብዛት አያስፈልግም። እርሱ ሰላማችን ነው ያለእርሱ የተረጋጋ ሕይወት መኖር አንችልም። “ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን አሜን።” ሮሜ 11፥36
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

03 Nov, 03:43


እህት ወንድሞቻችሁን Add አድርጉ🙏

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

29 Oct, 12:20


#ሼር
#የካህኑን_ልጅ_እንድረስላት

በዓለም ዙርያ የምትኖሩ ልጅ የምትወዱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ በምስሉ የምናያት ህጻን ስርጉት ጥዑመ ልሳን ትባላለች።

ገና የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን ስትሆን ዕድሏ ሆኖ መናገርም መንቀሳቀስም በሰላም መተንፈስም መቦረቅም አልቻለችም ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ በህመም ላይ ነችና።

ወላጆቿ ምንም ገቢ ስለሌላቸው የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። ዛሬ ላይ #ወገን_ቢያግዘን_የተሻለ_ህክምና ብንሞክርላት ብለው ፊታችን ቆመዋልና ደጋግ ወገኖቻችን ከቻላችሁ በገንዘብ ካልቻላችሁ በሀሳብ፣ በጸሎትና ለሌሎች ረጂዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድታግዟቸው እንማጸናችኋለን።

ቄስ ጥዑመ ልሳን ገደፋው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000561662014

ለበለጠ መረጃ
ቄስ ጥዑመ ልሳን ➛ +251967438386

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

28 Oct, 16:52


https://vm.tiktok.com/ZMh9nDKxS/

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

28 Oct, 15:09


"ሚስቶች ሆይ፦ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ። ባሎች ሆይ፦ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው። ልጆች ሆይ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። አባቶች ሆይ፦ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው።" ቆላስይስ ፫፥፲፰-፳፩

#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
ቤተሰብ ላላቸው፣ ቤተሰብ መመስረት ለሚያስቡ ፣ለቤተክርስቲያን ለሚጨነቁ ሁሉ አጋሩ🙏

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

25 Oct, 19:12


"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው።" እንዲል ቅዱስ መጽሐፍ ልጆች የሚያደርጉት ያዩትን/ያሳዩዋቸውን/እንዲያደርጉ የመሯቸውን ነው፤ እነዚህ አዳጊዎችም ያደረጉት ያንን ነው።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን!
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

25 Oct, 06:32


#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

23 Oct, 04:22


የእናንተ ባል የትኛው ይነት ነው?

+++

10 ዓይነት ባሎች አሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ ወንዶች እኔ ምን ዓይነት ባል ነኝ ብላችሁ ታስባላችሁ? ሚስቶችስ የእናንተ ባል የትኛው ዓይነት ነው?

1. ላጤ ባል
ይህ አይነቱ ባል ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ሚስቱን ሳያማክር በራሱ ወስኖ ነው። ከሚስቱ ይልቅ ከጓደኞቹ ጋር ብዙ ጊዜ ያሳልፋል። ለትዳር ሕይወት ግዴለሽ ነው።

2. መርዛማ ባል
ሁል ጊዜ እንደ አሲድ የሚፈላ፥ ሁል ጊዜም ቁጡና ጠበኛ ነው። ለሚስቱ ስሜት የማይጨነቅ፣ ሁሌም የበላይ ነኝ የሚል እና በጣም አደገኛ ሰው ነው።

3. ጨቋኝ ባል
እንደ ንጉስ መታየት ይፈልጋል ነገር ግን ሚስቱን እንደ ባሪያ ያያታል። ሚስቱ ወግ፣ ባሕልና ስርዓቱን አክብራ ተገዝታ እንድትኖር ይፈልጋል፣ እርሱ ግን በዚያው ሕግ መገዛት አይፈልግም። ከሚስቱ አንቱታን እና ሁሌም ሙገሳን ብቻ የሚፈልግ ባል ነው።

4. የሁሉም ባል
ይህ ሰው የጋራ ባል ነው። ከሚስቱ ውጭ ላሉ ሴቶች ሁሉ የሚያስብ፣ ከሚስቱ ይልቅ የሴት ጓደኞችን የሚያበዛና የሚያስብላቸው አይነት ሰው ነው። ለሴት ጓደኞቹ ገንዘብም ሆነ ጊዜ መስጠት ይወዳል እና ከወንዶች ይልቅ ብዙ የሴት ጓደኞች ያሉት ነው።

5. ደረቅ ባል
በራሱ ስሜት ብቻ የሚመራ፣ ሁሉንም ነገር እንደስራ የሚቆጥር፥ ቀልድ የማያውቅ፥ የሚስቱን ስሜት የማይጠብቅ እና ግንኙነቱን አሰልቺ የሚያደርግ ባል ነው። እንዲህ አይነቱ ባል አንዳንድ ጊዜ ምሁራዊ በሆኑ ጉዳዮች ብቻ የተጠመደና ሚስቱ ጋር ልክ እንደስራ ባልደረባዎቹ እንድትሆንለት የሚፈልግ አይነት ይሆናል።

6. ፓናዶል ባል
ሚስቱን ችግር ሲገጥመው ብቻ እንደሕመም ማስታገሻ የሚፈልጋት፥ ለእርሷ ያለው መውደድ የሚገለጠው ከእሷ የሆነ ነገር ሲፈልግ ብቻ ነው። ይህ ባል ብልጣብልጥ በመሆኑ የሚስቱን ድክመቶች አሳምሮ ያውቃል፣ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ሰላም መሆን ሲፈልግ ብቻ ይህን ካርድ መዞ የሚጫወት ነው።

7. ጥገኛ ባል
ሰነፍ እና ለገንዘብ ሲል ብቻ ሚስቱን የሚወድ ነው። የሚስቱን ገንዘብ ግን የሚጠቀምበት መልሶ ሌሎች ሴቶችን ለማጥመድ ነው። ምንም ተነሳሽነት የሌለውና ሚስቱን ዘወር ብሎ የማያያት ነው። ቤቱ ውስጥም ቢሆን ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም።

8. ጨቅላ ባል
ልጅነቱን ገና ያልጨረሰ፣ ውሳኔ ለመወሰን የእናቱን ወይም የሌሎች ዘመዶቹን እገዛ የሚፈልግ፣ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ነው። ሚስቱ ጋር የሀሳብ ልዩነት ከተፈጠረ ሮጦ ዘመዶቹ ጋር የሚሄድና ሚስቱን ከዘመዶች ጋር እያወዳደረ መፍትሔ ለመፈለግ የሚሞክር ነው። ይህ አይነቱ ባል ፍቅር የሚሰጥ (Romantic)፣ መዝናናት የሚወድ (Adventurous) ወይም በጣም የተጋነነ ሕልም ያለውና የማይተገብር (Ambitious) ሊሆን ይችላል። ይህ ባል ገና ባለማደጉ በምንም ነገር ላይ ኃላፊነት የጎደለው እና ችግር ከተፈጠረ ደግሞ በመሸሽ ነው የሚያምነው።

9. እንግዳ ባል
ሁልጊዜ ቤት ውስጥ ስለማይገኝም ልክ እንደ እንግዳ ነው የሚመጣው። ለቤተሰብ ሁሉንም አይነት ቁሳዊ ነገሮች የሚያቀርብ ሲሆን ለእነርሱ የሚሰጠው ግን ምንም አይነት ጊዜ የለውም። ይህ ባል በሥራ ሱስ የተጠመደ (Workholic) በመሆኑ በአካልም ሆነ በስሜት ከቤቱ ከመራቁ የተነሳ ትዳሩን በሥራ የተካ ሰው ነው።

10. ትጉህ ባል
ተንከባካቢ እና አፍቃሪ ሲሆን ቁሳዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶችን አመጣጥኖ ማቅረብ የሚችል ነው። ይህ ባል ለቤተሰቡ በቂ ጊዜ የሚሰጥ፣ በነገሮች ላይ ኃላፊነት የሚወስድ፣ የሚስቱን ደስታ የሚያስቀድም፣ ቤቱን በመተማመን የሚመራና ሰላም እና የደስታ የሁሉም ነገር ቁልፍ መሆኑ የገባው ባል የሚወስን ነው።
ትጉ ባል ለመሆን ጣሩ ሁኑም🙏
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

21 Oct, 12:16


አብራችሁ የምትውሏቸው ሰዎች በእናተ ሕይወት ላይ በጎም ክፉም ተጽኖ አላቸው። ማንነታችሁ የሚወሰነው አብራችሁ በምትውሏቸው ሰዎች ነውና አብሯችሁ የሚውሉ ሰዎችን ምረጡ ። መልካም ነገር እንኳን ቢኖራችሁ “አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33 እና ተጠንቀቁ።
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

10 Oct, 11:25


የመልካም ሚስት ዋነኛ ባህሪያት ታማኝነት  ረዳትነት ትጉህ በህይወትዋ ከ እግዚኣብሄር ቀጥላ ለቤተሰቧ ቅድሚያ የምትሰጥ ናት።                              
ለራሷ ተክክለኛውን ግምት የምትሰጥ ናት።                       ከባሏ ጋር ባለው ጉዳይ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ የማታስገባ  ናት።       በባሏ ላይ በቃልም ሆነ በድርጊት ከስነምግባር ውጪ የሆነ ነገር የማታደርግ ናት።(ጭቅጭቅ፣ ስድብ፣ማማት፣ለግጭት መጋበዝ)።                           
ለባሏ የሚገባውን ፍቅር እና አንክብካቤ የምትለግስ ናት።     

#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

10 Oct, 11:19


💕ባል ከሚስቱ ምን ይፈልጋል? 💕 1.#ፍቅር፦ባል ሚስቱ እንድትወደው ይፈልጋል ቲቶ(2;4)                                                                      2.#ልጆችዋን የምትወድ ሚስት   3.#ባሏንአክባሪ፦ባል ሚስቱ በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር አንድታከብረው ይፈልጋል (1ኛ ጴጥ 3፡6)       4.#ቤቷን በመልካም የምታስተዳድር 5.#አድናቂ(አመስጋኝ) ፦ ባል በሚስቱ በመደነቁ በራስ መተማመኑ ከፍ ይላል።                                           6.#የማትነዘንዝ፦ባል ሚስቱ እንድትተቸው ኣይፈልግም ።ይህን የምታደርግ ከሆነ እራሱን አይገልጥላትም። 7.#ሚስጥር የምትጥጠብቅ ፦ ሚስጥር መጠባበቅ በሁለታቸው ያለውን መተማመን ያጠነክረዋል።  8.#ታማኝየሆነች፦ታማኝ ሚስት በባሏ የተወደደች ናት።                                                                             9.#ሰላማዊት፦ባል ሚስቱ ሰላምና መረጋጋት ያላት አንድትሆን ይፈልጋል (ምሳ 19፡13)                                         10.#ውበቷን ጠባቂ፦ባልበሚስቱ፣ ሰውነት፣ ኣካሄድ፣ኣለባበስ፣ኣነጋገር፣መኩራት ይፈልጋል።                   
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

10 Oct, 05:16


1 ቆሮንቶስ 13 (1 Corinthians)
2፤ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር #ግን #ከሌለኝ #ከንቱ #ነኝ።
3፤ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን #ከሌለኝ #ምንም #አይጠቅመኝም።
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@tnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

09 Oct, 13:40


🌺🌺ለልጆችህ ማድረግ የምትችለው ትልቁ ነገር ቢኖር እናታቸውን መውደድ ነው።🌺🌺
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

08 Oct, 20:41


An Orthodox father's birthday wishes to his 2 year old son:

"My deepest prayer is that, as you grow, you come to know the depth of God's love and live a life filled with faith, compassion, and kindness."
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

08 Oct, 11:19


ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አትስጥ መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው፤ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው፡፡ እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲዖል ሰው ለመሆን ዋጋ እንዳለው እወቅ፡፡
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

07 Oct, 13:42


🌺🌺«ጥሩ ባል ለማግኘት ጥሩ ሚስት ሁኚ»🌺🌺
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

04 Oct, 12:47


ኦርቶዶክሳዊ ልጆችን ማስተማር

በቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክሳውያን ልጆችን ማስተማር የተለመደ ነው። በተለይ በውጭው ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ልጆችን ስለ ሃይማኖታቸው ስለ ሀገራቸው ለማስተማር የወላጅ ትልቁ ፍላጎትና ስቃይ ነው። ይኹን እንጂ ኹለት ትልልቅ ፈተናዎች እንዳሉ እገነዘባለሁ።

አንደኛው ምእመኑም ካህናቱም ለልጆች የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ ከመኾኑ ባሻገር ከእቅድና ወሬ ያለፈ አለመሆኑ ነው። እኔም ለመረጃ ስጠይቅ “ከተወራ ይበቃል” አይነት መልስም ሰምቻለሁ። ከልባቸው በትክክል እያስተማሩ ያሉ ጥቂት አጥቢያዎች ይኖራሉ። 

ኹለተኛው ደግሞ የምናስተምርበት መንገድ ነው። በጥቂት አብያተ ክርስቲያናት  ራሱን ችሎ በተመደቡ በብዛት ግን ወላጅ አልያ ፈቃደኛ በኾኑ ምእመናን የሚሰጥ የልጆች ትምህርት ነው። እኔ በጥቂቱ ለመታዘብ በሞከርኩት እንኳን ለማስተማር ቀርቶ የሚናገሩን ምን እንደኾነ እንካ የማያውቁ ብሎም ስህተት መረጃ ለልጆች የሚሰጡ “የልጆች አስተማሪዎች” እንዳሉ ታዝቤያለሁ። 

ሌላው ልጆቹን የሚያስተምሩት ወላጅ እያስቀደሰ ልጆች እንዳይረብሹ አንድ ክፍል ውስጥ ዘግቶ ማንጫጫት ወይም ማስተማር ነው። ፊደል አልያ ዓረፍተ ነገር ማሰራት። ይኽ ትምህርት ሳይሆን  ልጆቹ እንዳይረብሹ ማድረግ ነው ዓላማው። 

በተጨማሪም ኦርቶዶክሳዊ የልጆች ትምህርት ምንድነው የሚለው በደንብ መለየት አለበት። በውጭው ዓለም  እንዳየሁት ልጆች የሚማሩት በቅዳሴ ሰዓት ሲሆን ለቁርባን ተሰልፈው ይመጣሉ። ይኽ በብዙ ምክንያት እንደሆነ ብረዳም በጣም ጎጂ ከመሆኑ በላይ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስ ትምህርት ከክርስቶስ ጋር የምንኖረው የሱታፌ ሕይወት እንጂ እውቀት ብቻ አይደለም። ስለሆነም የምንማረው በተሳትፎ በተግባር ነው። ልጆች ቢረብሹም ከወላጆች ስር ሆነው ማስቀደስ አለባቸው። 

በቅዳሴ ወቅት በር ዘግተን ከምንማረው ትምህርት ይልቅ በቅዳሴ ተሳትፈው ሲያልቅ አንድ ሰዓት በትክክል ልጆችን ማስተማር የበለጠ ትክክለኛ ይሆናል። 

መ/ር ንዋይ ካሳሁን
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

03 Oct, 23:41


በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የተዘጋጀው ነገረ ማርያምን የተመለከተና 'አሐቲ ድንግል' የተሰኘ ባለ 626 ገጽ ግዙፍ መጽሐፍ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት ጥቅም ፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ይመረቃል።
____
ከምርቃቱ በኋላም በባኮስ እና ሰርዲኖን መጻሕፍት መደብሮች ይከፋፈላል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

03 Oct, 06:32


በአንድ ወቅት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ባሉበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕጻናት ይጮሁ ነበር። ወላጆችም "ቅዳሴ እንዳይበጠብጡ" ብለው ልጆቹን ወደ አንድ ክፍል ወስደው አስቀመጧቸው። በእነርሱ ቤት ትልልቆቹ ለማስቀደስ ፈልገው ልጆቹ እንዳያስቀድሱ ማድረጋቸው ነው። ምዕመናኑም ወደ ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ ቀርበው "አባታችን ሕጻናቱ እየበጠበጡ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ቅዳሴ እንዳይመጡ ብለው ይናገሩ" አሏቸው። አቡነ ሽኖዳ ደግሞ እንዲህ ብለው መለሱ "እኔ የሚሰማኝ የብጥበጣቸው ድምጽ ሳይሆን የነገይቱ ቤተክርስቲያን የተስፋ ድምጽ ነው።"
"ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው።" ሉቃ 18፡16
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

02 Oct, 06:02


ጠያቂ፦ "አባ! የባለቤቴ ቁጣ በጣም ያስቸግረኛል። ይህን እንዴት መቋቋም እችላለሁ?

አባ፦ " በትዕግሥት!"

ጠያቂ፦ "ትዕግሥት ከሌለኝስ?"

አባ፦ "ግዛ! ከየትና እንዴት እንደሚገዛ አታውቅም?"

ጠያቂ፦ "አላውቅም"

አባ፦ "ይኸውልህ! አንድ ሰው በጣም በቁጣ ከነደደ፥ ምንም ብትናገር ለውጥ አታመጣም። ነገር ግን ቃል ሳታወጣ በዝምታና በውስጥህ እየደጋገምክ 'እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ... እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ... እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ...' ብትል የተቆጣው ሰው መቀዝቀዝ ይጀምራል። አንተም እንደሚገባ ማውራት የምትችለው ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው። ዓሣ የሚያጠምዱ ሰዎች እንኳን ማዕበሉ ጸጥ ካላለ በቀር ዓሣን ማጥመድ አይችሉም።"
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
#👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

01 Oct, 07:05


ለወላጆች
+++

አባት ለልጁ እንዲህ አለው
"ልጄ ስትሄድ ተጠንቀቅ።"
ልጅም መለሰ
"አባቴ አንተ ይበልጥ ተጠንቀቅ፤
እኔ ያንተን እርምጃ ነው የምከተለው።"

+++
ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲያጸና እንዲህ ይላል፦
"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።" ምሳሌ ፳፪፥፮
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

30 Sep, 12:44


https://vm.tiktok.com/ZMhrYMHrp/

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

29 Sep, 07:06


ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዞ ማለት የመዳን ጉዞ ስለ ኾነ፡-
💍 ከመጽናናት በላይ ማጽናናትን፣
💍 ሌላው እንዲረዳን ከመሻት በላይ ሌላውን ለመረዳት መጣርን፣
💍 ለመፈቀር ከመሻት በላይ ለማፍቀር መሞከርን፣
💍 ይቅርታ እንዲጠይቁን ከመጠበቅ በላይ ይቅርታ ማድረግን እየተለማመዱ የሚጓዙበት ነው፡፡
💍 መጽሐፍ፡- “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” ያለው ይህንንም ነውና፡፡
(መምህር ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

28 Sep, 05:22


+ ጸሎትና የትዳር ጉዞ +

ጸሎታችን ግዳጅ እንዲፈጽም ከፈለግን፣ ጸሎታችን ከደመና በታች እንዳይቀር የምንሻ ከኾነ፣ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደ መኾኑ ከእርሱ ጋር የምንነጋገራት ንግግር እንዳትደናቀፍ ከሻትን፥ ይህን የትዳር አጋራችንን ከማክበር ጋር በቀጥታ የተሰናሰለ እንደ ኾነ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ "ጸሎታችሁ እንዳትሰናከል ሚስቶቻችሁን አክብሩ" ሲል ይነግረናል (1ኛ ጴጥ.3:7)።

ህምም... ጸሎታችን አልሰማ ያለው፥ ምናልባት ይህን የምስክር ጉባኤ ቤት ዘንግተነው እንደ ኾነስ? እግዚአብሔርን ለማክበራችን ከትዳር አጋር በላይ ማን ሊቀርብ ይችላልና? የማናከብረው አካል አክብሮ ይሰማናልን? ሰውን ያውም የትዳር አጋርን አቃልለንስ፥ እግዚአብሔር ሆይ አከብርሃለሁ ማለት ልግጫ አይደለምን?

ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዟችን ጥራት ሲኖረው የጸሎት ሕይወታችንም ጥራት ይኖረዋል

ወዳጄ ሆይ! ሚስትህን ታከብራለህ? በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለህ ጠባይ በሚለው ሲሞላልህ A, A+ ተሞልቶልህ ይኾናል። አሁን ሚስትህ ብትሞላውስ? አሁን ባልሽ ይህን ቢሞላው ምን የሚል ይመስልሻል?
(GebreEgziabher Kide)
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

27 Sep, 12:47


ሚስትነት በቃል ከመነገር በላይ ነው ፡፡ ሚስትነት ከአንድ ሴትነት በላይ የኾነ ማንነት ነው፡፡ ሚስት የባልዋን ብቸኝነትና ነጠላነት አስወግዳ ሙሉ ሰው ታደርገዋለች፡፡ ሚስትነት አስተማሪነት ነው፡፡ ሚስትነት መልካም መካሪነት ነው፡፡ ሚስትነት ለባል ዘውድነት ነው፡፡ ሚስት ለባልዋ ስትል ቤተሰቦችዋን፡ ሀገሯን ትታ ትሄዳለች፡፡ አብርሃምን ለመታደግ ሣራ ሁለት ጊዜ ራስዋን ለትልቅ ፈተና አሳልፋ ሰጥታለች፡፡ ባልዋን አብርሃምን ጌታዬ እያለችው በትዳር ዘመኗ ሁሉ ታዝዛዋለች፡፡ አብርሃም ባለ ማቋረጥ በየቀኑ የሚያመጣቸውን እንግዶች ፊቷ ሳይቀየር ተቀብላ አስተናግዳለች፡፡  ወ/ሮ ሚስት ሆይ ሣራን ለመኾን የሚያስችል ሰብእና አለሽ? እንደወንጌሉ ቃል ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትታዘዘው ሕሊናሽን አንዳች ሳይጎረብጠው ለባልሽ ለመታዘዝ የሚያስችልሽ ማንነት አለሽ?

በቅርቡ ይፋ በተደረገ አንድ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ ከተጋቡት ጥንዶች መካከል በትዳራቸውና በቃል ኪዳናቸው ጸንተው ያሉት እጅግ ጥቂቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ለምን? ተዋድደው ከተጋቡ ለምን ትዳራቸውን ለማፍረስ ወሰኑ? የአብዛኞቹ ትዳር ለመፍረስ የሚዳረገው ራስን (ድካምና ብርታትን) ማወቅ በመጉደሉ ነው፡፡ በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ለሽምግልና እጅግ በርካታ ዓመታት ተቀምጫለሁ፡፡ ነፃ ሆኜ ባልና ሚስት የሚያቀርቧቸውን ወቀሳዎችና ክሶችን አድምጫቸዋለሁ፡፡ ባል ሚስቱ ስላጎደለችበት ሚስትም ባሏ ስላጎደለባት ነገር ነው የሚያወሩት፡፡ አንዳቸውም ጥሩ ሚስት/ባል መለያ ጠባያቸውና ተግባራቸው ምንድን ነው? በዚህ መሠረት እኔ ጥሩ ሚስት/ባል መሆን ችያለሁን? ለባሌ/ለሚስቴ ለቤተሰቤ መሆንና ማድረግ የሚገባኝን ሆኛለሁን? አድርጌያለሁን? መሆንና ማድረግስ እችላለሁን? ብለው ሲጠይቁ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም እነዚህን ለመጠየቅም ሆነ ለመመለስ አስቀድሞ ባልተሸራረፈ መልኩ ራስን ማወቅን ስለሚጠይቅ ነውና፡፡

ክቡር ባል ሆይ ጥሩ ሥራ ሠርተህ ጥሩ ገንዘብ ልታመጣና የሚያስፈልጋችሁን ቁስ ሁሉ ልታሟላ ትችላለህ፡፡ ክብርት ሚስት ሆይ ከባልሽ እኩል እየሠራሽ በገንዘብ ባልሺን እየረዳሽ ወዲህ ደግሞ ልጆች ወልደሽ እያሳደግሽ እንደገና ደግሞ ምግብ እየሠራሽ ቤተሰብሽን ትመግቢያለሽ፡፡ መልካምና ብርቱ ድካም ያለበት ትጋት ነው፡፡ ግን ግን ይኽንን ሁሉ ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ውጪ ያሉ ባልና ሚስትም እነዚህን ሁሉ እንዲያውም በተሻለ ሁኔታ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አንተ ግን እንዲህ የምትደክምልህን እናትና አባትዋን ስለ አንተ ትታ ከአንተ ጋር በክብርም ሆነ በሐሳር ለመኖር የወሰነችውንና የተከተለችህን ሚስትህን ለመውደድ ለማክበር ለመንከባከብ የሚያስችል ማንነትህ ምን ያኽል ነው? ራስህን እወቅ፡፡ ሚስት ሆይ በዙርያሽ ትዳራቸውን ያፈረሱ፡ ልጆቻቸውን የበተኑ፡ ለብቻ ልጆች ማሳደግንና መኖርን (Single Mom) እያሞካሹ የሚያወሩ ጓደኞች ሊኖሩሽ ይችላል፡፡ እነዚህ ሴቶች ስለባሎች ጉድለትና መጥፎነት የሚያወሩትን እውነተኛም ሆነ ክፉ ወሬ፡ በሌላ በኩል ደግሞ እኩልነትን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ለባል መታዘዝን እንደጭቆና እያብጠለጠሉ የብዙዎችን ትዳር እያናጉ ካሉት ስሑታን ክፉ ምክር ሊጠብቅሽና በእግዚአብሔር ፈቃድ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቅዱሳን አሠረ ፍኖት ሊያጸናሽ የሚችል ማንነት አለሽ ወይ?

ትዳር ጉድለትን መሙያ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሔዋንን ለመፍጠር ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ሲወስድ አዳም ሲፈጠር ከተሰጠው ማንነት ጎድሎ ነበር፡፡ ያንን በሔዋን መፈጠር ምክንያት የተፈጠረውን ጉድለት እግዚአብሔር ያጠፋለት በክብር የምትተካከለውን በባሕርይ የባሕርይው ተካፋይ የኾነችውን፡ በመልክ የምትመስለውን ሔዋንን በማጋባት ነው፡፡ ራሳችንን እንወቅ፡፡ የሚጎድለንን የትዳር አጋራችን ይሞላልናል/ትሞላልናለች፡፡ የጎደለን እንዲሞላልን፡ የጎበጠው እንዲቃናልን፡ የሌለን ነገር እንዲኖረን፡ ያስቸገረን ጠባይ እንዲገራልን ግን አስቀድሞ ራስን ማወቅ የግድ አስፈላጊ ነው ፡፡ ራስዎን ምን ያኽል ያውቃሉ? ብርታትዎን ብቻ ሳይሆን ድካምዎን ያውቃሉ? የሚያስጠላብዎን ያውቃሉ? ከሰው የሚያጣላዎን ያውቃሉ? በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ጉድለትዎ ምንድን ነው? ራስዎን ለራስዎ በሚያደላ ሚዛን ሳይሆን ሕሊናን በሚረምር ለግራና ለቀኝ በማያዳላ በመንፈስ ቅዱስ ሚዛን ይመዝኑ፡፡ ራስዎን ያውቃሉ? (ይቆየን)

#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

26 Sep, 05:09


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንኳን አደረሳችሁ
‹‹ቅዱስ መስቀል ››
‹‹…ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኀቸው …›› መዝ 59፣ 4
ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያቢሎስ እናመልጥ ዘንድ ድል እናደርገው ዘንድ የተሰጠን ነው ፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን ፣የሰላም አርማችን ነው፤፡፡‹‹..እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው፡፡ ›› ኤፌ 2፣14-16
ቅዱስ መስቀል በዘባነ ኪሩብ ላይ የሚቆም የጌታችን እግሮች ተቸንክረው የዋሉበት የመድኅን ዓለም ክርስቶስ ዙፋን ነው፤ቅዱስ መስቀል ዲያቢሎስ ያፈረበት ሞተ ነፍስ ድል የተደረገበት ፣የሕይወት መንገዳችን እንቅፋት የነበረው ጠላታችን ዲያቢሎስ ከመንገዳችን ተጠርቆ የተወገደበት ፣በእኛ ላይ የነበረው ኃይል የተነጠቀበት ነው ‹‹… በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዝት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወገደው….›› ቆላ 2፣14 ፤
ቅዱስ መስቀል የመድኃኒታችንን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የተፈተተበት  ፣የእናቱ እመቤታችንን እናትነት የምናስታውስበት ነው፤‹‹ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ የእናቱም እኅት የቀለዮጵያም ሚስት ማርያም መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ አላት፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን እናትህ እነኋት አለው›› ( ዮሐ 19፣27)
ቅዱስ መስቀል በበደላችን ከገነት በወጣን ጊዜ በእሳት ሰይፍ ታጥራ የነረችው ገነት በክርስቶስ ሞት እንደተከፈተችልን ዳግመኛ እንኖርባት ዘንድ እንደተሰጠችን ያስታውሰናል‹‹…ኢየሱስም እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው…›› ( ፤ሉቃ 23፣43)
ቅዱስ መስቀል ሥራችንን ሁሉ የምንባርክበት ትምክህታችን ነው ፤ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናንን በላከው መልእክቱ ‹‹..  ዓለም ለእኔ ተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልኩበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ ›› ገላ 6፣14 
‹‹…እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን ..›› መዝ 131፣7
የመድኅን ዓለም ክርስቶስ እግሮቹ በቅዱስ መስቀል ላይ በዕለተ ዐርብ ተቸንክረውበታል በክቡር ደሙ ተቀድሷልና የጸጋን ስግደት እንሰግድለታለን ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን በጸሎቷ ምስጋናን ስታቀርብ ‹‹..እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር…›› ‹‹ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት በክቡር ደሙ ለቀደሰው  መስቀል እሰግዳለው በማለት ምዕመናንን ለቅዱስ መስቀሉ የአክብሮት ጸጋ ስግደት እንዲሰግዱ ሥርዓትን ያበጀች፡፡
         መልካም በዓል !
በዲ/ን ተስፋዬ ቻይ( ሱላሜ)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

2,784

subscribers

170

photos

12

videos