🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 @wektawi1mereja Channel on Telegram

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

@wektawi1mereja


This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 (Amharic)

ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 is a national and international news and advertising channel that aims to provide timely and reliable information to the people of Ethiopia. With a focus on keeping the audience informed about the latest developments in the country and around the world, this channel serves as a valuable resource for those looking to stay updated on current affairs. ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 features a variety of news and announcements, ensuring that subscribers are always well-informed and up-to-date. Whether it's political news, social issues, or cultural events, this channel covers a wide range of topics to cater to diverse interests. Stay connected and informed with ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 for all your news needs.

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

19 Mar, 21:29


ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

18 Feb, 17:32


ያሳዝናል ገላን ኮንዶሚኒየም ተገድለው ተገኙ።

<<አቶ ከበደ በለው  የታርጋ ቁጥር 3 ኦሮ 60716 ነጭ ሀይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ትላንት የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ/ም  ከቀኑ 9:00 ሰዓት ከአሰላ መናኸሪያ ጭኖ አዲስ አበባ ቃሊቲ መናኸሪያ 11:40 ሰዓት  ደረሰ።መደረሻቸው ሳሪስ ዶሮ ተራ 12:10 ሰዓት የነበረ ሲሆን የጫኑት አረግፈው ከወጡ በኋላ የስልክ ግንኙነታቸው ተቋርጧል።>>ሲሉ ቤተሰቦቻቸው አፋልጉኝ ሲያስነግሩ ነበር።

በሚያሳዝን ሁኔታ እኝህ አባት አቶ ከበደ በለው ገላን ኮንዶሚኒየም ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።ቤተሰቦቻቸው ከምንሊክ ሆስፒታል አስክሬን ተቀብለን ነገ 6 ሰአት ሳሪስ ዮሴፍ ስርዓተ ቀብራቸው ይፈፀማል በማለት መናገራቸውን የሾፌሮች አንደበት አስነብቧል።

መኪናውም እንደጠፋ ነው።ኢትዮጵያ ሰዎች በጠራራ ፀሐይ የሚታፈኑባትና የሚገደሉባት እየሆነች ነው።ፍትህ ብሎ መጠየቅ ፌዝ ይሆንብናል። መንግስት አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስን መታፈንና ግድያ እንዲቆም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።ለአቶ ከበደ በለው ቤተሰቦች መፅናናቱን ይስጥልን።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

18 Feb, 16:49


ሰሞኑን በቋሪት ወረዳ በተደረገው ውጊያ
እስከ መቼ…?

"…እንዴት ነው የሰዉ ሞት እንደዚህ የረከሰው…? እርስ በራስ እየተበላላን፣ እየበጣጠሰው ደሙን እያፈሰሰ፣  የሚኖረውስ እስከመቼ ድረስ ነው?   ይሄ ሁላ ግፍ ሲፈጸም እንዲህ ዝም፣ ጭጭ ብለው የሚቀመጡት ዝምታቸው እስከመቼ ነው…?

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

26 Jan, 18:36


ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

26 Jan, 11:40


አቶ ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳትነት ለቀቁ‼️

አቶ ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳትነት መልቀቃቸውን ፓርቲው አስታወቀ።የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አቶ ደመቀ መኮንን መሸኘቱን አስታውቋል።

በምትካቸውም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስጌን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

16 Jan, 08:19


https://vm.tiktok.com/ZM6Quh8cV/

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

03 Jan, 18:09


#Update

ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች።

ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች።

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር።

ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦

- ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024 በአዲስ አበባ የተፈርመውን የመግባቢያ ስምምነት በሙሉ ድጋፍ አፅድቆ እንደተቀበለውና እንደሚያደንቅ ገልጿል።

- ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሉዓላዊነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያ ሀገር በመሆኗ ምስጋናውን አቅርቧል።

NB. (የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ ስምምነቱ በሂደት ሶማሌላንድ ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት በጥልቀት አጢኖ አቋም እንደሚወስድበት መግለፁ ይታወቃል)

- ምክር ቤቱ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ  ሶማሌላንድ ምድሯን፣ አየሯን እና ባህሯን ሙሉ በሙሉ የምትቆጣጠር ነፃ ሀገር ናት ብሏል። በተጨማሪም " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሕገ መንግሥት መሠረት " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ከማንኛውም ብሔራዊ ጥቅሟን ከሚያስጠብቅና ከሚጣጣም አካል ጋር ስምምነት የማድረግ ሥልጣን አላት ብሏል።

- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ የሶማሊያ መንግስት የሰጠውን መግለጫ እና ድርጊት በጽኑ አውግዟል። የሶማሊያ መንግስት በመሰል ጉዳዮች ከመሳተፍ እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል።

- ምክር ቤቱ  ከሶማሊያ የወጡት መግለጫዎች " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በሶማሊያ መንግስት መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶችን የሚጻረር መሆኑን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይወቅልኝ ብሏል።

- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍ ወይም ለመቃወም ለሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

- ምክር ቤቱ የሶማሌላንድ ህዝብ  ለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላደረገው ደማቅ አቀባበል እና ድጋፍ ያለውን አድናቆት ገልጿል።

- ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክን አርአያነት በመከተል በዓለም ዙሪያ ያሉ መንግስታት " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እውቅና ለመስጠት ድፍረት እና ጥበብ እንዲያሳዩ አሳስቧል። ይህን መሰሉ ዕውቅና ለአህጉራዊ መረጋጋት፣ ለደህንነት እና ለአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ መርሆች መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥቷል።

ሶማሊላንድ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እራሷን እንደ አንድ ነፃ ሀገር የምትቆጥር ሲሆን የራሷ ህገመንግስት፣ የመገበያያ ገንዘብ፣ የፀጥታ ኃይል፣ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ስርዓት አላት። እስከዛሬ ግን ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት አልቻለም። ሶማሊያ እንደ አንድ የራሷ ግዛት ነው የምታያት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

02 Jan, 09:48


ሰበር
ሶማሊያ በኢትዮጵያ የሾመችውን  አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ ጠራች።

ማንም ሀይል የሶማሊያን ሉአላዊነት መድፈር የለበትም የሚል ውሳኔ የሚንስትሮች ምክርቤት ወስኗል።

የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግኑኝነት ወዳልተፈለገ መቋሰል የሚያመራ ይመስላል።

ሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ ግዛቴ ናት ብላ ነው የምታምነው። ልክ ቻይና በታይዋን ላይ እንዳላት አይነት።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት ውስጥ እንደ ሀገር "እውቅና" መስጠቷ ብስጭት ፈጥሯል።

2024

አዲስ ውዝግብ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ሊከሰት ይመስላል።

ያሳዝናል 😢

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

01 Jan, 14:35


ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች‼️

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

26 Sep, 06:04


አዲስ አበባ


ከመጪው የመስቀል በዓል ጋር ተያይዞ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቲሸርት ታስትማላችሁ፣ግጭት ቀስቃሽ ፅሁፎች ታዘጋጃላችሁ በሚል ህትመት ቤቶች ከፍተኛ ቁጥጥር እየደረገባቸው መሆኑን ከህትመት ቤት ሃላፊዎች የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። ሽሮሜዳ አካባቢ አንድ በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ የህትመት ባለሙያ እንደገለፁልኝ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያለው ቲሸርት በህትመት ቤቴ በመገኘቱ  አሽግተውታል ብሏል(አዩዘሀበሻ)።
👉መረጃ ለሚፈልጉ ብቻ ከስር ባለው ሊንክ ለሌሎች በመጋበዝ መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ ያድርጉ(ከአክብሮት ጋር)"መረጃ ህይወት ነው"
በርካታ ሀሰተኛ አካውንቶች ስላሉ ትክክለኛው ሊንክ👇👇

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

25 Sep, 00:47


ኢሰመጉ ፤ በአዲስ አበባ በህገወጥ የሚታሰሩ ሰዎችን የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በማቆያነት ያገለግላሉ መባሉን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን አካላት ብጠይቅም ምላሽ አልሰጡኝም አለ

👉🏼 በአዲስአበባ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ የጅምላ እስሮች አሁንም ቀጥለዋል ብሏል

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአዲስ አበባ ከተማ እና በአማራ ክልል በንጹሀን ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰዋል ሲል በትናንትናዉ እለት ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።

ኢሰመጉ በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ እና አንዳንዶቹም አስገድዶ የመሰወር ባህርይ ያላቸው የጅምላ እስሮች መፈፀም መቀጠላቸውንም ተናግሯል። የሚታሰሩ ሰዎችም በተገቢው ጊዜ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ ፣ የታሰሩ ሰዎች የት እንዳሉ በቤተሰቦቻቸው እንደማይታወቅ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ለእነዚህ እስሮች በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንደማቆያነት እንደሚያገለግሉ የደረሳቸውን መረጃ ለማረጋገጥም አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ፣ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በደብዳቤ ቢጠይቅም ሪፖርቱን እስካወጣበት መስከረም 12/ 2016 ዓ.ም. ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።

በተጨማሪም አንዳንድ የእስረኞች ማቆያዎች ለዚህ ተግባር ያልተቋቋሙ እና በንጽሕና ያልተያዙ በመሆናቸው ታሳሪዎች ለከፍተኛ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውንም ኢሰመጉ በሪፖርቱ ገልጿል።

በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላም ጋዜጠኞችንና ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የምክር ቤት አባላት ጨምሮ መጠነ ሰፊ የጅምላ እስሮች መፈፀማቸውን አስታውሶ፣ የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈፀሙ እስሮች ለማስቆም እርምጃ ባለመውሰዳቸው አሁንም የጅምላ እስሮች ቀጥለዋል ሲል በመግለጫው ጠቅሷል። ከታሳሪ ቤተሰቦች አገኘኋቸው ባላቸው መረጃዎች በመዲናዋ በርካታ ሰዎች ያለአግባብ እንደታሰሩም አሳዉቋል።

https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

04 Sep, 19:04


‹‹ በቅፅል ስሙ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› - ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘላለም በቅፅል ስሙ ደግሞ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ግለሰብ ላይ የማድረገውን ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡ከሰሞኑ ‹‹ ልጅ ያሬድ ›› በሚል ቅፅል ስም የሚጠራዉ የቀድሞ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም  በተረጋገጥ የፌስቡክ ገፁ ‹‹ የአንድ ትልቅ የእምነት ተቋምን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ ባስተላለፈዉ ጸያፍና ማንንም ብሄር በማይወክል መልዕክት ምክንያት የፌደራል ፖሊስ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ›› የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ ተሰውሯራል፣ጠፍቷል እያሉ ያልተጣራና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሚነዙና ኅብረተሰቡ ላይ ዉዥንብር የሚነዙ ›› ያሏቸው ‹‹ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም ›› አሳስበዋል፡፡

ጄይላን ሲቀጥሉ ‹‹ ይህን ከኢትጵያዊነት ያፈነገጠ ተግባር የፈጸመዉ ልጅ ያሬድ( ያሬድ ዘላለም) የተባለ ግለሰብ ከ3ቀናት በፊት የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥሩ ስር አውሎት እንደሚገኝ ›› ጠቅሰው ‹‹ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እንወዳለን ›› ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ወጥቶ የአንድ ብሄር ተወካይ በሚመስል መልኩ ያስተላለፈው ግብረገብነት የጎደለው፣ የተወደደና የተከበረ የእምነት ተቋም ላይ ያስተላለፈው ጸያፍ ቃላቶች ታላቁን የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደልም ›› ሲሉም ነቅፈዋል፡፡

‹‹ ማንም ደግሞ ለዚህ ግለሰብ የሠጠዉ የእምነትም ሆነ የብሔር ውክልና የለም ›› በማለት  ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቁዋል፡፡

‹‹ ሌሎችም ከእንዲህ ዓይነት ከኢትጵያዊነት ከወረደና የእምነት ተቋማትን በመሳደብ ህዝብን ለቁጣ የምታነሳሱና፣ አንድን ብሄረሰብ ከሌላዉ ለማጋጨት በተለያየ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምትቀሳቀሱ ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ›› አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ›› ጠይቃለች፡፡

‹‹ በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት  ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና  ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለሁ ›› ብላለች።

ቤተ ክርስቲያኗ አክላም ‹‹ የተከሳሹ ድርጊት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን መልካም ስም የሚያጎድፍ ድርጊት፤ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ሰዎችን ለአመጽ እና ብጥብጥ የሚያነሳሳ፤ የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ያራከሰ ፤ የምዕመናኑን ስሜት የሚነካ በመሆኑ ፣ በሚያዋርድ እና ቤተክርስቲያንን በሚያናንቅ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑ በግለሰቡ እና  በተባባሪዎቹም ላይ ጭምር ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሠርት ለአቃቤ ሕግም እንዲልክ ›› ጠይቃለች።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

29 Aug, 18:07


የአቡሽ ዘለቀ አልበም በአዲስ አበባ እንደይሸጥ መከልከሉን አርቲስቱ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አሳወቀ።

የሚከተለው የአቡሽ ዘለቀ መልዕክት ነው 👇

"ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ! በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ።"

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

14 Aug, 03:51


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል። ከእረፍት የተጠራው ምክር ቤት በዚኹ ስብሰባው፣ መንግሥት በግጭት ሲታመስ በሰነበተው አማራ ክልል ለስድስት ወራት ባወጀውና "እንዳስፈላጊነቱ" በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ይተገበራል በተባለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል። ኢሰመኮ ቅዳሜ'ለት ባወጣው መግለጫ፣ ምክር ቤቱ አዋጁን ካጸደቀው የጊዜ ቆይታውን በአንድ ወር ብቻ እንዲወስነውና ከአማራ ክልል ውጭ ተግባራዊ እንዳይኾን መጠየቁ ይታወሳል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja