የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመገኘት ከአቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ከተጋለጡ ነዋሪዎቻችን ጋር ማዕድ ተጋርተናል::
በዓልን ከአቅመ ደካሞች ጋር አብሮ ማክበር ፤ የተቸገሩትን ዝቅ ብሎ መመልከት ነባር ኢትዮጵያዊ ባህላችን እና የብልፅግናችን መለያ በመሆኑ በከተማዋ በሚገኙ 22 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በአሉን ከአቅመ ደካማ እና የሀገር ባለዉለታ ወገኖቻችን ጋር የማክበር መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛል::
መላው የከተማችን ነዋሪዎች በዓሉን ስናከብር በፍቅር፣ በመተሳሰብና በአብሮነት መንፈስ ለሌላቸው በማጋራት እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ::
መልካም በዓል
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
#aa_prosperity
#ከቃል_እስከ_ባህል