......................................................................
HDMI ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው ዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለማገናኘት የምንጠቀምበት ባለ19 ፒን ማገናኛ ሲሆን ዲዛይን የተደረገው በኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድምጽ እና ምስል በአንድ ጊዜ በአንድ ገመድ ለማስተላለፍ ተደርጎ ነው፡፡
ኤችዲኤም አይ በቐሚነት በቴሌቪዥኖች፣ የቲቪ ሪሲቨሮች ሳጥን፣ የብሉ ሬይ ማጫዎቻዎች፣ በጌም ካውንሱሎች፣ በቪዲ መቅጃ ካሜራዎች እንዲሁም በዲጂታል ካሜራዎች ላይ እና በኮምፒውተሮች ላይ እናገኘዋለን፡፡
ኤችዲኤምአይ/ HDMI በጣም ጥሩ ትልቅ ነገር እነዚህን ሁሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በጋራ ለማስጠቀም የሚያስችል ሲሆን ንጹህና የጠራ ያልተወሳሰበ የዲጂታል ምልከታ ድምጽ ለማስተላለፍ የተሻለው አማራጭ ነው፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ኤችዲኤምአይ 1.0 ተሰርቶ ለገበያ የቀረበው ታህሳስ 2002 እ.ኤ.አ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እቃዎች እየተሰሩ ሲመጡ እና ሲሻሻሉ በነሱ ላይ እንዲሰራ ራሱን ላይ መጠነኛ ለውጦች እያሳደገ መቱዋል
ጥር 2017 ጀምሮ ኤችዲኤምአይ 2.1ን አቅርባል ይሄም ቨርዥን የቅርብ ግዜ ከፍተኛ የምስል ጥራት፣ ከፍተኛ ብርሃን፣ ኮንትራስት፣ብዙ ቀለማት ያለው፣ 3ዲ ግራፊክስ እቃዎች ላይ የሚሰራ ሲሆን ከቀድሞዎቹ ስሪቶች ጋር ወደ ኋላ ይሰራል፡፡
ኤችዲኤምአይ በሶስት አይነት ይከፈላል ።
የኤችዲኤምአይ መሳሪያዎች በሚገዙበት ጊዜ የትኞቹን ባህሪያት ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ለማስተዋል ሁኔታዎች ዙሪያ ይህ ጽሑፍ ይረዳዎታል፡፡
ምንጭ፡-ኢንፎቶፒያዝ ቴክኖሎጂ
https://t.me/Tadte