ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY @prosperity_news Channel on Telegram

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

@prosperity_news


We provide Latest news and information about prosperity party and Ethiopian politics;We will ensure unity,peace and prosperity of the motherland Ethiopia!!!

ስለ ብልጽግና ፓርቲ እና ኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃዎችን እናቀርባለን፤ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ብልጽግናና ሰላም እናረጋግጣለን!!!!

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY (Amharic)

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY ተቆማሚ ብልጽግና እና ኢትዮጵያን መረጃዎች እና መረጃዎች እንዲለዋወጡ፣ እናቀርባለን። ብልጽግና ፓርቲን ለአንድነትና ለሰላም እና ብልጽግናን ላይ ማህበረሰብ ሊቆም ያልቻለውን ምንም እንደሚፈጽም እናረጋግጣለን፣ እናረጋግጣለን።

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

15 Feb, 19:54


አዲሱን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበርን በክብር ተቀብለናል። ተሰናባቹ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ ባለፉት ዓመታት ላሳዩት አመራር እና ወዳጅነት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት የምታደንቅ ሲሆን በወደፊት ጉዞዎም መልካሙን ትመኛለች።

Dura ta'aa Komiishinii Gamtaa Afrikaa isa haaraa wayita kabajaan simannu Dura taa'aa Komiishinichaa gaggeeffaman, Muusaa Faakii Mahaammatiin hooggansaafi michummaa waggoota darbanitti agarsiisaniif nan galateeffadha.

Itoophiyaan of kennuudhaan Afrikaa waan tajaajiltaniif isin galateeffatti. Imala keessan fuulduraafis waan gaarii isiniif hawwina.

As we welcome the new Chairperson of the African Union, I thank Moussa Faki Mahamat, outgoing Chairperson of the African Union, for his leadership and friendship over the past years.

Ethiopia thanks you for your dedicated service to Africa. We heartily wish you the best in your endeavors.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

15 Feb, 16:59


የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጠናዊ፣ አኅጉራዊ እና የልማት ቀዳሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር። ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል። ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶቻችንን ለማጠናከር ተወያይተናል።

ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ ተወያይተናል። ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል። ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና ውይይት አድርገናል።

በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን።

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

14 Feb, 18:53


ከሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት አድርገናል። በሚገጥሙን ፈተናዎች ውስጥም ሆነን በጠንካራ አመራር እስከተመራች አህጉራችን አፍሪካ ሰፋፊ እድሎች ያሏት መሆኗን አውስተናል። ለሁለቱ ሀገሮቻችን የጋራ ጥቅም እንዲሁም ለአህጉራችን ፋይዳ ስንል እነዚህን እድሎች በጋራ ለመጠቀም አብሮ ለመሥራት ተስማምተናል።

Pirezdaantii Senegaal, Baasiiruu Diyomaye Faayee waliin walittidhufeenya biyyoota keenya lachanii haala cimsuu dandeenyurratti marii gaarii taasifneerra. Qormaatilee numudatan keessa taanees ardiin keenya Afrikaan hooggansa cimaafi mul'ata qabuun hoogganamnaan carraawwan babal'aa akka qabdu kaafnee dubbanneerra. Faayidaa waloo biyyoota keenya lachaniif jecha carraawwan kanneen waliin ittifayyadamuuf waliin hojjechuuf waliigalleerra.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

11 Feb, 20:39


ኢትዮጵያ ለ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ እንኳን በደህና መጣችሁ ብላ ስትቀበል ሁሉም ተሳታፊዎች ኢትዮጵያን በእውነትም ምድረ ቀደምት ያደረጓትን የታሪክ ሀብቷን፣ ብዝኃነት የሞላውን ባሕሏን እና አስደማሚ መልክዓ ምድሯን ለመመልከት ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ አበረታታለሁ። ከጉባኤው ባሻገር ከጥንታዊ የቅርስ ስፍራዎች እስከ ደማቅ ባሕሎች፤ አቻ የለሽ የተፈጥሮ ውበቶችን ጨምሮ ልታውቋቸው የሚገቡ ብዙ መዳረሻዎች አሉ።

ወደቤታችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ!

Itoophiyaan wayita Yaa'ii Gamtaa Afrikaa 38ffaaf anaadhufu jettee keessummootashee simattu hirmaattonni hundi waantoota Itoophiyaa dhugumaan biyya duree taasisan: qabeenyaa seenaashee, aadaawwanshee daneessa ta'aniifi teessuma lafashee ajaa'ibsiisaa ta'e daawwachuuf turtii isaanii akka dheereffattanin isaan jajjabeessa. Yaa'ichaan cinatti iddoowwan hambaa duriirraa kaasee hamma aadaawwan babbareedaa, miidhaginaa uumamaa gita hinqabne dabalatee hawwattota beekuu qabdan hedduutu jira.

Gara mana keessaaniitti anaadhufu!

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

09 Feb, 01:37


የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮዽያ ለሚያደርጉት ጉብኝት እንኳን ደህና መጡ!

አይኤምኤፍ ለኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራማችን የሚያደርገውን የቀጠለ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ የእርስዎንም የግል ጥረት እና አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጠዋለን።

በአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ታላላቅ የድጋፍ መርሃግብሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም በሀገር በቀል ርዕይ እና የለውጥ አጀንዳ ላይ የተመሠረተ የእድገት እና የልማት ህልሞቻችንን በሚገባ ቀርፆ የያዘ ነው። ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማክሮኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመሻገር የለውጥ ሥራዎቻችንን በጠንካራ ትኩረት እና ባለቤትነት በመያዝ ቆራጥ፣ ሁሉን አቀፍ እና ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስደናል።

በፕሮግራሙ እስካሁን የታዩ ውጤቶችም ቀና እና አበረታች ናቸው። እየተካሄዱ ያሉ የትግበራችን ሥራዎችም የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት፣ እድገትን ማፍጠን፣ የዜጎች ኑሮ ደረጃን ማሻሻል ሲሆኑ በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል ናቸው።

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

05 Feb, 20:10


የዘንድሮ የ #አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካል የሆነ የሻይ ተክል ችግኝ ዝግጅት
The preparation of tea seedlings is well underway as part of this year’s #GreenLegacy planting program

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

03 Feb, 15:25


ለበዋ ንህዝቢ ትግራይ ብፍላይ ድማ ንልሂቃን ትግራይ !

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

02 Feb, 12:39


ዛሬ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ አካሂደናል። ይኽም ወደዲጂታል ሽግግር የምናደርገው የሀገራዊ ጉዞ አካል ነው።

በምርጫው ውጤት በእኔና በምክትል ፕሬዝዳንቶች የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው።

Today, we conducted Prosperity Party’s election, embracing technology as part of our national journey toward digital transformation.

The trust and responsibility entrusted to me and the deputy presidents through this reelection inspires us to move forward with renewed commitment.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

01 Feb, 10:39


ብልጽግና ፓርቲ በሀገር በቀል እሳቤ ሀገርን ወደ አዲስ የለውጥ ባህል ያሸጋገረ ነው Paartiin Badhaadhinaa yaadama biyyaa maddeen, biyya aadaa jijjiiramaa haaraatti kan ceesisedha.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

01 Feb, 00:31


“ከቃል እስከ ባህል”

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ጀምረናል፤ የኢትዮጵያም ብልጽግና ጉዞ አይቀሬ ነው!

“From Pledge to Practice”

As we commence the 2nd Congress of the Prosperity Party, Ethiopia’s path to prosperity is inevitable!

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

12 Jan, 14:28


በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለሁ።

This afternoon, I bid farewell to President Hassan Sheikh Mohamud following productive discussions on deepening cooperation and strengthening bilateral ties during his working visit to Ethiopia.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

30 Nov, 06:52


ዛሬ ጠዋት ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ጋር በኢትዮጵያ እና ባንኩ መካከል ሊኖር ስለሚችለው የአረንጓዴ ኢነርጂ፣ አቪዬሽን እና መሠረተ ልማት ትብብር ዙርያ ተወያይተናል።

I met this morning with President of the Asia Infrastructure Investment Bank, Jin Liqun for discussions on partnership between Ethiopia and the Bank on green energy, aviation and infrastructure.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

27 Oct, 06:29


የአዝርዕት እርሻ፣ የአበባ ልማት እና የከብት ማደለብ ሥራ የተቀናጀበት የጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ የቅይጥ ግብርና ስፍራ።

Mixed farmland in Gamo Zone’s Daramalo Woreda incorporating productive crop cultivation, horticulture, and animal fattening.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

18 Oct, 16:28


አሁን ያለው ትውልድ በትብብር መወሰን ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ልጆቻችን ላይ አብዝተን በመስራት የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል እንዳለብን ነው።

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

13 Oct, 10:32


ትልቅ ተስፋ ያለው የሩዝ ምርታማነት በአማራ ክልል።
Naannoo Amaaraatti homishtummaa ruuzii abdii guddaa qabu.
Promising rice productivity in the Amhara region.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

11 Oct, 10:40


ዛሬ የእንግሊዙን የአፍሪካ ሚኒስትር የሀይበሪውን ሎርድ ኮሊንስን አግኝቼ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል።

I met earlier today with Lord Collins of Highbury, the Minister for Africa, for a rich discussion on bilateral and regional matters of mutual concern.

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

11 Oct, 07:14


የኢትዮጵያን ብልጽግና የምናረጋግጠው በውጭ እርዳታ ሳይሆን በኢትዮጵያዊያን የጋራ ስራና አቅም ብቻ ነው!

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

10 Oct, 18:10


በዓለም ላይ የኮፊ አረቢካ መገኛ ብቻ ሳንሆን ትልቁ አምራች ለመሆን በሕብረት መትጋት ይኖርብናል።

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

08 Oct, 12:08


በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል። 34.5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬ እና 7.6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል። ይኽን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘት እና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።

As is the case for many parts of the country, the South Region is immensely rich in natural resources. This season, fruit and vegetable production has been exceptionally fruitful, with abundant harvests yielding 34.5 million quintals of fruits and 7.6 million quintals of vegetable crops. To build on this success, we must intensify our efforts across other regions, working towards a unified progress that strengthens our food security ambitions and ensures sustainable growth for the entire nation.