ESAT (ኢሳት🇪🇹)® @esat_tv1 Channel on Telegram

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

@esat_tv1


ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

ESAT (ኢሳት🇪🇹)® (Amharic)

ኢሳት (ESAT) ከኢትዮጵያ እና ጆሮ በታሪክና ማብራሪያ እናወራለሁ። ይህ ቡድን ተከታዮችን በነጻ የተወከሙትን እና የተቃወሙትን መረጃዎችን እናውራለን። ኢሳት በተለያዩ ቻናሎች እና ችግሮች ውስጥ በሚከተለው ወቅታዊ መረጃ እና አገልግሎት ለማሳወቅ በመቀየር ይፈልጋሉ። ከሚከተለው ዓለም አቀፍ ህዝብ በሆነ በአገልግሎቱ ላይ ባለው ምክንያት አፍሪካ አይነቱን ወደ ኢንተርናችን እንዲሁም ከአዳራሽ ከፊልሞን እንድትመፃ ውስጥ በተመለከተ ከተሰናበታቸው ያለውን መረጃዎች እና ንብረትና በማስረጃቸው ለአንዴ ቡድን አሉ። በቡድን ውስጥ እናንተን በሚከተለው ገጽ ያሳካል። የምንከተለውን አገልግሎት እና መረጃዎችን እናፈቅሻለን። ይህ ቡድን ከተለያዩ ኢትዮጵያዊ ወገን እና አዜብ ተማሪዎች ጋር አሁን በቀጣይ ምላሽ እንዳለው ስነ-ምግባረን ይናገራል።

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

21 Nov, 08:59


በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ‼️

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስራ፣ በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ማስገባት መጀመሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ተሀድሶ ማዕከላት ለመግባት በእጃቸው ያለውን ቀላል ትጥቅ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የነፍስ ወከፍ እና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ርክክብም የአፍሪካ ህብረት፣የመንግስታቱ ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።

በመቐሌ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው ማዕከላት መዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል።

የቀድሞ ተዋጊዎች በተዘጋጁ ማዕከላት ስልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የመቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል ተብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

20 Nov, 08:28


ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሚሳኤል ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች‼️

ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን በትናንትናው ዕለት ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ይበልጥ መባባሱ ነው የተነገረው፡፡

በዛሬው ዕለትም ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ለፈጸመችው ጥቃት ተመጣጣኝ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡

የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጥቃቱንም የምዕራባውያን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ስትል ሩሲያ መወንጀሏን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ድርጊቱ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጀመሩት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ተመጣጣኝ ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቃለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምስራቃዊ ዩክሬን እየጨመረ የመጣውን የሩሲያ ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል ጸረ-ሰው ፈንጂዎችን ለዩክሬን ለመስጠት መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ባይደን በዩክሬን ግዛት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ጸረ-ሰው ፈንጅ ለመስጠት ቢስማሙም በዩክሬን በኩል ፈንጂውን የመጠቀም ፍላጎት እንደሌለ ተጠቁሟል።

@Esat_t11
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

19 Nov, 08:01


ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ሊጀምር ነው‼️

የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ በሚል ማስተላለፍ የጀመርነው ተወዳጁ ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘው ተከታታይ ፊልም በብዙዎቻችሁ የተወደደ መሆኑን አይተናል።

ኮርፖሬሽኑ ይህንን ስራ የባለቤትነት መብቱን ጠብቆ ካቆየው ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ፊልም የመስራት መብቱን በሕጋዊ መንገድ በመግዛት የደራሲውን ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ሕልም ሊያሳካ በሚያስችል፣ ክብራቸውን እና የተመልካቹን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ ከፍተኛ ወጭ በመመደብ ፊልሙ እንዲሠራ አድርገናል።

ይህ እንደ ብሔራዊ ጣቢያ ታሪክ ሰንዶ የማቆየት፣ የማስተላለፍ እና የማሳደ ይህንን የሕግ፣ የሞራል እና ሀገራዊ ሓላፊነታችንን እየተወጣን ባለንበት ወቅት የክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ወራሽ ነኝ በሚሉ ሰዎች የፊልሙን መተላለፍ በፍርድ ቤት እንዲታገድ አድርገዋል።

ተቋሙ የደራሲውን ሥራ በወጋየሁ ንጋቱ ትረካ ከፍ ያደረገ እና በዚህም በይፋ ደራሲው ያመሰገኑት ተቋም ነው። አሁንም የደራሲውን ህልም የሚፈታ እና በህጋዊ እና እውቅና ባለው ይሁንታቸው የተላለፈውን መብት መነሻ በማድረግ ፊልሙን ለእይታ አብቅተናል።

ይሁንና አሁን የተከሰተው አይነት ጉዳይ ሲያጋጥም ችግሩን በሕግ አግባብ መፈታት አስፈላጊ በመሆኑ በፍርድ ቤት ስንከራከር ቆይተን እግድ የሰጠው ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ሲያይ ቆይቶ ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ክርክሩ በስር የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲታይ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰጠው እግድ እንዲነሳ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መነሻ በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የፍቅር እስከመቃብር ፊልም በኮርፖሬሽኑ የመዝናኛ ቻናላችን ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚጀምር መሆኑን አንገልፃለን።
©EBC

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

18 Nov, 11:49


ዛሬም የመርካቶ ሱቆች በአብዛኛው ዝግ ሆነዋል‼️

በዛሬው እለት በርካታ የመርካቶ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ዝግ እንዳደረጉ ታውቋል፣ ምክንያቱ ደግሞ ከሰሞኑ በመንግስት አካላት እና በነጋዴዎች መካከል ውዝግብ የፈጠረው የገቢዎች የደረሰኝ አጠቃቀም ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።

ነጋዴዎች እየተጠየቁ ያሉት የደረሰኝ ቅጣት እና የቅጣት አፈፃፀም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲናገሩ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ በመደረጉ ያነሱት ጉዳይ ነው ብሏል።

"በግምት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ ሱቆች ዛሬ ዝግ ናቸው" ያለው አንድ ነጋዴ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር የተሳተፉባቸው የኮንትሮባንድ ምርቶች ወደ ገበያ ያለደረሰኝ እየተበተኑ ነጋዴውን ደረሰኝ ቁረጥ ማለት አግባብ አይደለም ብሏል።

ሌላ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያለ የመርካቶ ነጋዴ የሱቅ መዝጋት አድማው "እስከ ስድት ቀን ሊቆይ ይችላል፣ እየተነጋገርን ነው" በማለት ለመሠረት ሚድያ ተናግሯል።

መንግስት ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም የተገኘ ነጋዴ ንብረቶቹ ይወረሳሉ በሚል 'ሀሰተኛ መረጃ' አንዳንድ ባለንብረቶችና ነጋዴዎች ሱቃቸውን የመዝጋትና እቃዎችን የማሽሽ ሁኔታዎች አሉ ቢልም ነጋዴዎቹ የዛሬ ሳምንት ገደማ ይርጋ ሀይሌ የገበያ ማዕከል ደረሰኝ አልተቆረጠም በሚል ምክንያት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ደንብ አስከባሪዎች እንሰወሰዱባቸው ተናግረዋል።
©መሠረት-ሚዲያ

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

18 Nov, 08:13


ዩክሬን የሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ በአሜሪካ ሚሳኤሎች እንድትመታ ባይደን ፈቃድ ሰጡ‼️

ዩክሬን አሜሪካ የሰጠቻትን የረዥም ርቀት ሚሳዔሎች ተጠቅማ ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቃ መምታት እንደምትችል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈቃድ ሰጡ።እርምጃው አሜሪካ በፖሊሲዋ ላይ ያደረገችው ትልቅ ለውጥ መሆኑን አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ አረጋግጠዋል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አገራቸው ከድንበራቸው አልፈው ለመምታት እንዲችሉ ኤቲኤሲኤምኤስ በመባል የሚታወቁት ሚሳኤሎች ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ለወራት ሲወተውቱ ቆይተዋል።

ዕሁድ በሰጡት አስተያየት "እንዲህ ያሉ ነገሮች አይነገሩም፤ ሚሳዔሎች በራሳቸው ይናገራሉ" ብለዋል።የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል የምዕራባውያን አገራት ከእንዲህ ዓይነት እርምጃ እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ካልሆነ ግን ኔቶ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ "በቀጥታ መሳተፉን" እንደሚያሳይ ተናግረዋል።ፕሬዝዳንቱ እስካሁን በውሳኔው ላይ አስተያየት ባይሰጡም ከፍተኛ የክሬምሊን ፖለቲከኞች ግን ውሳኔውን ጦርነቱን እንደማባባስ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

የዋሽንግተን በኤቲኤሲኤምኤስ ዙሪያ ያሳለፈችው ውሳኔ ኪዬቭ በነሐሴ ወር ድንገተኛ ወረራ ባደረገችበት በሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ያሉ የዩክሬን ሃይሎች ጥበቃ ብቻ እንዲውል ተወስኗል።በዚህም ዩክሬን የያዘችውን አነስተኛ የሩሲያ መሬት በመያዝ ወደፊት ለሚደረገው ማንኛውም ድርድር እንደትልቅ መደራደሪያ ልትጠቀመው እንደምትችል የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን አስታውቋል።

በኪዬቭ የሚገኘው የዩክሬን የጸጥታ እና የትብብር ማዕከል ሊቀመንበር ሰርሂ ኩዛን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጆ ባይደን ውሳኔ ለአገሪቱ “በጣም ጠቃሚ” ነው።“ጦርነቱን የሚቀይር ውሳኔ ባይሆንም ግን ኃይላችንን የበለጠ እኩል የሚያደርግ ይመስለኛል” ብለዋል።

ኤቲኤሲኤምኤስ እስከ 300 ኪሜ መምዘግዘግ ይችላል። ስማቸው ያልተጠቀሰው የአሜሪካ ባለስልጣናት ለኒውዮርክ ታይምስ እና ለዋሽንግተን ፖስት እንደተናገሩት የክሬንን ኤቲኤሲኤምኤስ እንድትጠቀም በባይደን የተፈቀደው የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ጎን ሆነው በዩክሬን እንዲዋጉ ለፈቀደችበት ውሳኔ ምላሽ እንዲሆን ነው።ኩዛን በበኩላቸው የእሑዱ ውሳኔ የዩክሬን ሃይሎችን ከሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ለማስወጣት ታስቦ በሩስያ እና በኮሪያ ወታደሮች ሊከፈት ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው ጥቃት አስቀድሞ የመጣ ነው ብለዋል። ጥቃቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚፈጸም ይጠበቃል።

እንደዩክሬን ከሆነ በኩርስክ 11 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እንዳሉ ግምቷን አስቀምጣለች።የፕሬዚዳንት ባይደን ውሳኔ ብሪታንያ እና ፈረንሣይ ስቶርም ሻዶው የተባሉ የረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን ዩክሬን እንድትጠቀም ፈቃድ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።ዩናይትድ ኪንግደምም ሆነች ፈረንሳይ ከባይደን ውሳኔ ጋር በተያያዘ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

18 Nov, 08:13


Platinum Mass Gainer

ጤናማ የሆነ ክብደት መጨመር ይፈልጋሉ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን እና የካርቦሃይድሬት ዉቅር ሲሆን  በአንድ  ማንኪያ:-

👉1,250 ካሎሪ
👉 60  ግራም ፕሮቲን
👉 6 G ግራም ግሉታሚን
👉 9 G ግራም ክሬቲን
👉 2 G ግራም ቢሲኤኤ
👉ቪታሚኖችን

👩🏽‍⚕️ የያዘው ይህ የከፍተኛ የፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት ድብልቅ የጡንቻን ብዛት በፍጥነት እና በብቃት ለማጎልበት የሚረዳዎትን በቂ የፕሮቲን ፍጆታ በማረጋገጥ የሰውነትዎን ጂኤች እና ቴስቶስትሮን ደረጃን ለማሳደግ የሚያስፈልግዎት ውህድ ነው።

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

17 Nov, 11:52


በመርካቶ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዛሬ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ሰዓት ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ሳይዛመትና የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

17 Nov, 09:42


በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ‼️

በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።

ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አጋርቶ ነበር ።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

17 Nov, 09:39


ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ‼️

ከአዲስ አበባ እና ከሀገራችን ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን በሚገባ ተወጥቷል ፡፡

የበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ለሀገራችን መልካም ገፅታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃትና በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የላቀ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

16 Nov, 08:47


ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች‼️

ለ24ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች የሚታደሙበት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ ገልፆ  የወድድሩ ተሳታፊዎች  በሚያልፉት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን እያስተላለፈ  ውድድሩ የከተማችንን ዋና ዋና መንገዶች የሚያካልል በመሆኑ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት  አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው  ስራ መጀመራቸውን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለባቸው እያሳሰበውድድሩ  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-

-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
-  ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
-   ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
-  ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
  ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
-  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
-  ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
-  ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
-  ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
-  ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
-  ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት  (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
-  ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
-  ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
-   ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
-  ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
-  ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት  አደባባይ)
-  ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
-  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
-  ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
-  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)
-  ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
-  ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

15 Nov, 18:32


ቤተመንግስት ተገኘ የተባለው ወርቅ ከተሸጠ የመንግስት አካላት ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው እናት ፓርቲ ገለፀ‼️

ፓርቲው ባወጣው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” በሚል ያቀረቡት ገለፃ ላይ ለህዝብ ማብራርያ እንዲሰጡ ጠይቋል።

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም" ያለው ፓርቲው "ከእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አስቀድሞ ለ44 ዓመታት ደርግ እና ኢህአዴግ ሲመሩ ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" የሚለው ምላሽ እንደሚፈልግ ገልጿል።

እናት ፓርቲ በመግለጫው በጠ/ሚኒስትሩ የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም ብሏል።

ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡ እናት ፓርቲ በጽኑ ያሳስባል በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

15 Nov, 16:01


በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች 'በመንግስት የተመቻቹ ናቸው መባሉን' የክልሉ መንግስት አስተባበለ‼️

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ትናንት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ/ም የተካሄዱት የሰላም ጥሪ ሰልፎች “በመንግስት የተመቻቹ ናቸው” መባሉን የክልሉ መንግስት “ከእውነት የራቀ” ሲል አስተባበለ።የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ “ህዝቡ ሰላምን ከመጠማቱ የተነሳ የወጣውን ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት አስተባባሪነት እንደተካሄደ ለማሳየት መሞከር ከእውነታ የራቀና የህዝቡን ቁስል በእንጨት መንካት እንደሆነ የሚታሰብ ነው” ብሏል።

መግለጫው የወጣው በክልሉ የተካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ ከመንግስት ጋር ለአመታት የትጥቅ ግጭት በማካሄድ ላይ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እንደ ጀዋር መሐመድ ያሉ ፖለቲከኞች በመንግስት ላይ ትችት መሰንዘራቸውን ነው።

ፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ በፌስቡት ትስስር ገጻቸው “መንግስት በአንድ በኩል ጉዳዩን የያዙ ሀገሮች ለሶስተኛ ዙር የሰላም ንግግር የሚያደርጉትን ውትወታ ባለመቀበል፤ በሌላ በኩል ምስኪኑን ህዝብ ወደ ፀኃይ በማውጣት ማስወትወት ትክክል አይደለም” ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

15 Nov, 07:21


ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ከተማ ገቡ‼️

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ገብተዋል።

ፊልድ ማርሻሉ ባሕር ዳር ሲገቡ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ ሌሎችም የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች እና ነዋሪዎችም ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕር ዳር ቆይታቸው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም የክልሉን ሕዝብ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውይይቶችን ያደርጋሉ።

ከዚህ በተጨማሪም በባሕር ዳር ከተማ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

15 Nov, 07:21


ታላቅ የምስራች ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ
👉 በካሬ  78,246 ብር ጀምሮ

👉 በ432,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ ከፍለው ይመዘገቡ

👉#እስከ 30% ቅናሽ ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ

👉#50% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

  🏠ቢኖሩባቸው ምቹ ፣ ቢያከራዩዋቸው በዶላር ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙባቸው እንዲሁም መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ በብዙ የሚያተርፉባቸው ውብና ማራኪ መንደር በለቡ መብራት ኃይል...

👉#እስቱዲዮ 56.6 ካሬ

👉#በለ 1 መኝታ
        ከ 69 ካሬ -85 ካሬ ድረስ

👉#ባለ 2 መኝታ
        ከ 99 ካሬ - እስከ 155 ካሬ

👉#ባለ 3 መኝታ
       ከ 139 ካሬ እና 181 ካሬ

ለበለጠ ☎️ +251940464607
                      0901022738
           

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

14 Nov, 12:40


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ‼️

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለሙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ሕዝባዊ ስልፉ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች እየተደረገ ሲሆን፤ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች 'ሰላምን ለማጽናት የበኩላችንን እንወጣለን'፣ 'በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል'፣ 'ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

13 Nov, 05:08


አቶ ጃዋር መሀመድ ስለ አፈሳው የተናገሩት‼️

ካለፈው አመት ጀምሮ በኢትዮጵያ በታጣቂ ሃይሎች የሚፈጸመው የአፈናና የአፈና ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ ወንጀሎች ብዙውን ጊዜ መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ ቢሆንም፣ የመንግሥት ኃይሎች ከተለያዩ ታጣቂዎች ጋር በመሰባጠር ትርፉን በመካፈል ላይ መሆናቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ይባስ ብሎ ደግሞ አሳሳቢ አዝማሚያ ታይቷል፡ የመንግስት አካላቶች አሁን ለብር ተብሎ የሚፈጸመውን አፈና በግልፅ እያረጋገጡ ነው። እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት፣ መንግሥት ወታደራዊ ግዳጁን ለመሙላት እየታመነ ነው። መጀመሪያ ላይ ቀዳሚ ኢላማው ያልደረሰው ወጣት፣ በተለይም ከቀያቸው ርቀው የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች ነበሩ። ይሁን እንጂ ትኩረቱ በቅርቡ ከሀብታም ቤተሰቦች ወደ ወጣቶች ተዘዋውሯል.

የአካባቢው የጸጥታ ባለስልጣናት ወጣቶችን ከትምህርት ቤት ወይም ከማህበራዊ ስፍራዎች ሲመለሱ እያሰሩ ወደ ጊዜያዊ እስር ቤቶች በግዳጅ እያጓጉዟቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተያዙት ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች መጓጓዝን በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ደላሎች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመቅረብ ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ልጆቻቸውን ለማስፈታት ያቀርባሉ። እነዚህ ክፍያዎች እንደ ቤተሰቡ ሀብት ከ100,000 እስከ 500,000 ብር ይደርሳል። ባለሥልጣኖች እና ደላሎች የቤተሰብ ገቢ መረጃን ከባንክ እና ከግብር መዝገቦች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ፣ ይህም የታለመውን የመክፈል አቅም ለመገምገም እና ምን ያህል እንደሚፈልጉ ለመወሰን ያስችላቸዋል። በእጃቸው ያሉት ገንዘብ የሌላቸው ከጓደኞቻቸው ለመበደር ተገድደዋል. ቀጣዩ ተጎጂ ከመሆን በመፍራት ብዙ ወጣቶች ትምህርታቸውን እና ስራቸውን ትተው ተደብቀዋል።

ይህ አፈሳ በሩቅ የገጠር መንደሮች ብቻ የተገደበ አይደለም። በዋና ዋና ከተሞች ያሉ ቤተሰቦች አሁን ዋና ኢላማዎች ሆነዋል። ይህ ከመላው ሀገሪቱ በወጡ ዘገባዎች ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም - እኔ በግሌ የማውቀው ቤተሰብ ከጥቂት ቀናት በፊት ልጃቸውን ለማስፈታት 300,000 ብር መክፈል ነበረባቸው። የኑሮ ውድነቱ ሊቋቋመው በማይችልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ ምዝበራ ጨካኝነት ነው።

የግዳጅ ግዳጅ መግባቱ ራሱ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አሳዛኝ ነው!

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

13 Nov, 04:51


በአዲስ አበባ እና አዳማ የጀመረው አፈሳ እና የገንዘብ ድርድር ወደ ሻሸመኔ እና ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቷል‼️

ሻሸመኔ 010 ቀበሌ ስታድየም ዋናው በር ፊት ለፊት ባለው መጋዘን ውስጥ እና 02 ቀበሌ ምክር ቤት ጀርባ (ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጎን ባለው አዳራሽ) በርካታ ወጣቶች ታጭቀው እንደሚገኙ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።

"ዙሪያ ገባው በሚሊሻ ተከቧል፣ ቤተሰብ አይደለም መጠጋት ለራስም ያሰጋል። ግን ምን እየሆነ ነው ያለው?" ብለው የሚጠይቁት ነዋሪዎች ከመሸ መንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸው እና የሚሊሻው አፈሳ ተባብሶ እንደቀጠለ ተናግረዋል።

"ስልክህን ይፈተሻል ብለው መንገድ ላይ ይቀበሉህና ጠዋት ሚሊሻ ቢሮ ና ይላሉ። ስትሔድ ለማነው የሰጠኸው ተብለህ ወንጀለኛው አንተው። መሮናል። እኔም አንድ የኦሮሞ ወጣት ነኝ የታገልኩት ግን ለዚህ አልነበረም" በማለት መልዕክቱን ያደረሰኝ ደግሞ አንድ የከተማው ወጣት ነው።
©Elias Meseret

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

13 Nov, 04:51


Platinum Mass Gainer

ጤናማ የሆነ ክብደት መጨመር ይፈልጋሉ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን እና የካርቦሃይድሬት ዉቅር ሲሆን  በአንድ  ማንኪያ:-

👉1,250 ካሎሪ
👉 60  ግራም ፕሮቲን
👉 6 G ግራም ግሉታሚን
👉 9 G ግራም ክሬቲን
👉 2 G ግራም ቢሲኤኤ
👉ቪታሚኖችን

👩🏽‍⚕️ የያዘው ይህ የከፍተኛ የፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት ድብልቅ የጡንቻን ብዛት በፍጥነት እና በብቃት ለማጎልበት የሚረዳዎትን በቂ የፕሮቲን ፍጆታ በማረጋገጥ የሰውነትዎን ጂኤች እና ቴስቶስትሮን ደረጃን ለማሳደግ የሚያስፈልግዎት ውህድ ነው።

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

11 Nov, 17:39


በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው‼️

🗣አስተዳደሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል ሲል አስታወቀ።ውዥንብሩ የመጣው “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ” ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ጠቁሟል።

“በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን” ያወሳው አስተዳደሩ “ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው” ብሏል።በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ያሳሰበው አስተዳደሩ “እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል” ብሏል።

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጠይቋል።ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የአስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

11 Nov, 12:10


በአዲስ አበባ ከተማ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ የሚያሰራ ምግብ ቤት እና ሆቴል የ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ የደንብ ረቂቅ ፀደቀ‼️

ከጉልበት በላይ የሆነ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ያሰራ ሆቴል እና መሰል ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ የወጣዉ የደንብ ረቂቅ ፀድቋል።በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉ የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት እንዲፀድቅ ተደርጓል።

በረቂቅ ደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚለብሷቸው አልባሳት እና የሚያደርጓቸው ጌጣጌጦች የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡እንደዚሁም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ገንዘብ ቅጣትና ከባድ የሚባል እርምጃ ድረስ በረቂቅ ደንቡ ተጠቅሷል ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዉ  እንደ ጥፋት ደረጃዉ የገንዘብ መቀጮዉ ተወስኗል።

በተደነገገዉ ክልከላ መሰረት በደረጃ ሀ፣ አምሳ ሺህ ብር፣በደረጃ ለ ፣ 30 ሺህ ብር፣በደረጃ ሐ ደግሞ  5 ሺህ ብር  ያስቀጣል።በዚህም መሰረት አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ሲያሰራ የተገኘ የሆቴል ተቋም ሆነ መሰል አገልግሎት ሰጪ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያቀጣ ወ/ሮ ገነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴለተቪዥን ተናግረዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ከአንድ በላይ ጥፋቶችን ያጠፋ ተቋም ለእያንዳንዱ ጥፋት አምሳ ሺህ ብር ተደምሮ ይቀጣል ሲሉ ዳይሬክተሯ  ጨምረዉ ተናግረዋል።

የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ እንደዚሁም ከጆሮ ጌጥ ዉጪ በሚታዮ የሰዉነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጦችን አድርጎ መገኘት  የፀደቀዉ ረቂቅ ደንብ ይከለክላል ሲሉ ወ/ሮ ገነት አስረድተዋል፡፡ይህ ደንብ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴልና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲሰፍን ከማገዙም በላይ ባህልና ወጉን ያልጠበቀ የአለባበስ ስነ-ስርዓትን በመቆጣጠር ኢትዮጵያዊ አለባበስና መስተንግዶ ስርዓትን ለማስከበር እና ባለሙያዎች ከሚደርስባቸዉ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ለማስቀረት አጋዥ ነዉ ተብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

10 Nov, 10:39


ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም‼️

የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው?

እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ:

- "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው። ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።"

- "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።"

- "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።"

- "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው"

- "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት"

ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን።
©Elias Meseret

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

09 Nov, 11:00


ኤፍቢአይ በመላው አሜሪካ ለጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ ጀመረ‼️

በመላው አሜሪካ ለሚገኙ ጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ መክፈቱን የአሜሪካው የፌደራል የምርመራ ቢሮ አስታወቀ።

የተላኩት የጽሑፍ መልዕክቶች በባርነት ዘመን እንደነበረው “ወደ ማሳ ሄደው ጥጥ ለቅመው ለጌቶቻቸው ሪፖርት” እንዲያደርጉ የሚጠቅስ ነው።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዩኒቨርስቲ ጥቁር ተማሪዎችን ጨምሮ በአላባማ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ቨርጂኒያ፣ ኒውዮርክ እና ፔንስልቬንያ ግዛቶች ነዋሪ የሆኑ ጥቁሮች እነዚህ የጽሑፍ መልዕክቶች ደርሷቸዋል ተብሏል።

“ኤፍቢአይ ለነዋሪዎች የተላኩትን አጸያፊ እና ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶችን ያውቃል እናም በጉዳዩ ላይ ከፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች የፌደራል ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነው” ብሏል የፌደራል ምርመራ ቢሮው
የጽሑፍ መልዕክቶቹ መላክ የጀመሩት አሜሪካ ካደረገችው ብሄራዊ ምርጫ ማግስት እንደሆነ ይታመናል።

አንዳንድ መልዕክቶች የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ቡድንን ቢጠቅስም ቡድኑ በበኩሉ ንክኪ የለኝም ሲል ውድቅ አድርጓል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

08 Nov, 16:36


በሆላንድ እስራዔላውያንን ኢላማ ባደረገው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ‼️

እንዲሁም በድርጊቱ የተጠረጠሩ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአምስተርዳም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የእስራዔሉ ማካቢ እግር ኳስ ቡድን ከሆላንዱ አያክስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ለድጋፍ የሄዱ እስራዔላውያን በአምስተርዳም ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

የእስራዔል መንግስት ዜጎቹን ለማምጣት ሁለት የጭነት (cargo) አውሮፕላን ወደሆላንድ መላኩ ተዘግቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

08 Nov, 14:09


የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የትምህርት ተቋት በትብብር ለመስራት ተስማሙ‼️

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር እና የሩሲያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

እኩልነት፣ የጋራ ተጠቃሚነትና ውጤታማነት መርህ ላይ የተመሰረተ ነው የተባለው ይህ ስምምነት፤ ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ወቅት፤ ሩሲያ የሰው ሃይል በማብቃት ዙርያ ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት፤ በሁለቱም ሀገራት በኩል የቴክኒክ ቡድን እንደሚቋቋም፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

07 Nov, 15:39


በአዳማ ስጋ በሚቆርጥበት ቢላ የሬስቶራንቱን ስራ አስኪያጅ በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

በአዳማ ከተማ ደምበላ ክፍለከተማ የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ በስለት ተወግታ መገደሏን ተከትሎ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ፖሊስ በተከራየበት ሆቴል ውስጥ በወለጪቲ ከተማ መያዙን አስታውቋል።

በአዳማ ከተማ አስተዳደር ደምበላ ክፍለከተማ ወንጂ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆነችውን የ24 ዓመት ወጣት ተጠርጣሪዉ በስለት ወግቶ መሰወሩን እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን መያዙን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው የእቴቴ ባርና ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆነችውን ሃሴት ደርቤ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በሬስቶራንት ውስጥ የስጋ ቆራጭ ሆኖ እየሰራ ባለበት በስራ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስጋ በሚቆርጥበት ቢላዋ ወደ የግል ተበዳይን ወግቶ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል።

ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብ እና ተጎጂዋ በስራ ምክንያት በተደጋጋሚ ይጋጩ እንደነበር ተጠቁሟል።ፖሊስ ድርጊቱን ከፈጸመ እለት ጀምሮ ክትትል እና ምርምር እያደረገ እንደነበረ እና በሂደቱ እገዛ ላደረጉ አካላት በሙሉ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ምስጋና ማቅረባቸውን ብስራት ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

06 Nov, 17:46


በአዳማ ከተማ የተፈፀመ አሰቃቂ ወንጀል‼️

በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ማናጀርነት ተቀጥራ ምትኖር ሴት ተናግራኛለች በሚል ምክንያት በምግብ ቤቱ ፍየል የሚያርደው ልጅ የልጅቱ ቢሮ ገብቶ 4ጊዜ ልቧን ወግቶ አንገቷን አርዶ ቢሮዋን እራሷ ላይ ቆልፎ ተሰወረ።

በአዳማ ከተማ  ወንጂ ማዞሪያ  እቴቴ ሬስቶራንት በተባለ ጊቢ ውስጥ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው ከቀኑ  7:33 በጠራራ ፀሐይ ሲሆን እድሜዋ 20 መጨረሻዎች የምትገኝ ወጣት ናት።

በሆቴሉም ገንዘብ ያዢነትና  የሂሳብ  ሰራተኞችን  የመቆጣጠር ሃላፊነት ነበራት። ጥቃት  የፈፀመባት ከትላንት በስቲያ  አብሯት በሚሰራ ሰራተኛ ነው። ግለሰቡ ለሬስቶራንቱ ፍየል አራጅ  ሲሆን "ቀን አብረው ገበያ ውለው መተዋል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ታዲያ  በሩን ሰብሮ  እርዳታ  ለመስጠት የፖሊስ የአንቡላንስ አገልግሎት ማግኘት  የተቻለው  ከአንድ ሰዓት በኃላ ህይወቷ ካለፈ በኃላ ነበር።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

06 Nov, 08:53


ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላለፉ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በእርስዎ የስልጣን ዘመን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን” ሲሉ አስፍረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

06 Nov, 07:57


ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ተረጋገጠ‼️

መልዕክታቸውንም ለደጋፊዎቻቸው እያቀረቡ ነው። "የአሜሪካ ህዝብ ላሳደረብኝ እምነት አመሰግናለሁ ።ሀገራችንን እንጠብቃለን፣ ለናንተ ጥቅምና ፍላጎት እታገላለሁ።

በሁሉ ነገር አሜሪካ ከፊት ሆና እንድትመራ እናደርጋለን እኔ የዴሞክራቱም የሪፐብሊካኑም ፕሬዝዳንት ሆኜ ወደ ነጩ ቤት እመለሳለሁ ይህ የሆነው በፈጣሪ ፍቃድ ነው ሀገራችን ስለተጎዳች እና መዳን ስላለባት ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

06 Nov, 07:48


ትራምፕ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ነው‼️

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ይገኛሉ፡፡

270 ድምጽ ለማግኘት የ3 መቀመጫ ድምጽ ብቻ የቀራቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ በፍሎሪዳ ተገኝተው ለደጋፊዋቻቸው ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

06 Nov, 06:46


በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ነው‼️

በአሜሪካ እየተካሄደ የሚገኘውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ዓለም በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል።

እስካሁን ባለው ውጤትም ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ዴሞክራቷን ካማላ ሃሪስ እየመሩ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ የምርጫውን አሸናፊ ለመለየት ወሳኝ ናቸው የተባሉ ሰባት ግዛቶችን ድምጽ ውጤት መጠበቅ ግድ ይላል፡፡

አሁን ላይ ተፎካካሪዎቹ የመጨረሻ ትንቅንቅ ውሰጥ የሚገኙ ሲሆን ፥ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛት ማሸነፋቸው ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

05 Nov, 09:06


ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች‼️

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

04 Nov, 19:52


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል‼️

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የፌዴራል የፍትህ እና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ሌላኛው የስብስባ አጀንዳ መሆኑም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

04 Nov, 12:51


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ‼️

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

02 Nov, 13:38


በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ‼️

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።
©Elias Meseret

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

02 Nov, 09:02


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ‼️

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል በዚህም መሰረት መገናኛ ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ከመገናኛ - ቃሊቲ ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች ወደ መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በጊዜያዊነት ተዛውሯል፡፡

ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች ደግሞ አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ - ገርጂ ፣ ከመገናኛ-ጎሮ ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው በመረጃው አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

02 Nov, 09:02


Platinum Mass Gainer

ጤናማ የሆነ ክብደት መጨመር ይፈልጋሉ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን እና የካርቦሃይድሬት ዉቅር ሲሆን  በአንድ  ማንኪያ:-

👉1,250 ካሎሪ
👉 60  ግራም ፕሮቲን
👉 6 G ግራም ግሉታሚን
👉 9 G ግራም ክሬቲን
👉 2 G ግራም ቢሲኤኤ
👉ቪታሚኖችን

👩🏽‍⚕️ የያዘው ይህ የከፍተኛ የፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት ድብልቅ የጡንቻን ብዛት በፍጥነት እና በብቃት ለማጎልበት የሚረዳዎትን በቂ የፕሮቲን ፍጆታ በማረጋገጥ የሰውነትዎን ጂኤች እና ቴስቶስትሮን ደረጃን ለማሳደግ የሚያስፈልግዎት ውህድ ነው።

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

01 Nov, 14:57


በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዉሏል‼️

በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ35 ላይ በመኖሪያ ቤቶች ላይ አጋጥሞ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

በአደጋዉ ቆሮቆር በቆርቆሮ ሆነዉ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችና ሁለት የውሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተው ነበር።

የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት እንደዚሁም በአቅራቢያዉ ባለ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የአደጋዉ መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተጣራ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ጉዳት አለመድረሱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። አሁን ያለንበት የጥቅምት ወር ደረቅና ነፋሻማ አየር ያለዉ በመሆኑ ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ ስለሚያደርግ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

01 Nov, 11:50


በኮንታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ገለጸ‼️

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ አስረድተዋል፡፡

በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋም ሁለት ቤት መውደሙን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ እስከ አሁን 1 አስከሬን ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በአካባቢው አሁንም መሬቱ እየተናደ መሆኑ እና የውኃ ሙላት (ጎርፍ) መኖሩ የነፍስ አድን ሥራውን በሚፈለገው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል ነው ያሉት፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

31 Oct, 07:14


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

እንደ ሀገር በተለያዩ ተቋማት እና ዘርፎች ሪፎርም ሥንሠራ ቆይተናል፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንደ ሀገር የምናንሠራራበት ጊዜ ነው፡፡ በርካታ ውጤቶችም ይጠበቃሉ፡፡ ቀጣዩ የማጽናት ጊዜ ይሆናል፡፡

አንዳንዶች ትፈርሳላችሁ ቢሉም፤ እንደማንፈርስ እንደ ሀገር በተግባር እያሳየን ነው፡፡ ይህ ጥንካሬ በይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግበናል፤ ይህም እጅግ አበረታች እና ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሁሉ አስደማሚ ሆኗል፡፡

በያዝነው ዓመት ደግሞ 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ በቅንጅት ርብርብ እያደረግን ነው፡፡

የግብርናው ዘርፍ ብቻ በዚህ ዓመት 6 ነጥበ1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ብለን እንጠብቃለን፤ ለዚህም አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን ነው፡፡

30 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

31 Oct, 06:18


ኤርትራ የአየር ክልሏን ዘጋች‼️

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሏን የኤርትራ እና የሶማሊያ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር  መንገድ የተጓዦችን ሻንጣ ጥሎብናል በሚል ክስ መስርቻለሁ ማለቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ማቆሙ ይታወሳል።

አየር መንገዱ በኤርትራ የሚገኘውን ገንዘቡን ማንቀሳቀስ እንዳይችል መደረጉንም መግለፁ ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

30 Oct, 17:19


" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ

ካለፋት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መኖሩን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አሳውቋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ይህን ያሳወቀ ለከተማው ትምህርት ቢሮ በላከው ደብዳቤ ነው።

" ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳና ክ/ከተማ የመጅሊስ መዋቅሮቻችን አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል " ብሏል።

" በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን እድርገው እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ሲል ምክር ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች እነማን እንደሆኑ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

በጉዳዩ ላይ ሰሞኑን ከከተማው ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደነበርም አስታውሷል።

ምክር ቤቱ " የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት ተማምነናል " ብሏል።

" ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል " ሲል አክሏል።

" ስለሆነም በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት እንዲካካስላቸው " ሲል አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል።

ሰሞኑን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ምክንያት ችግሮች መከሰታቸው ፤ በዚህም ተማሪዎቹ ለ3 ሳምንታት ያህል ከትምህርት ገበታቸው እንደተስተጓጎሉ ተገልጿል።

እነዚህን ተማሪዎችን የሚወክሉ ከአዲስ ከተማ ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳተፉበት በዛሬው ውይይት ፦

° ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

° በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችንና አለባበሳቸውን መነሻ በማድረግ እየተስተዋለ ያለው አግላይነትና ከትምህርት የማራቅ ተግባር ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

° ዛሬ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ነገ ወደ ሌላ የእምነቱ የስርዓተ አምልኮ ላይ ተሸጋግሮ ችግር ይፈጥራል የሚል ስጋት ገብቶናል ያሉ ተማሪዎቹ የተነሳውን ችግር ከወዲሁ እንዲፈታ አሳስበዋል።

የምክር ቤት አመራሮቹ ምን አሉ ?

➡️  ምክር ቤቱ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ሙስሊሙ በሚታወቅበት ሰላም ፈላጊነቱ ምክንያት እስካሁን የነበሩ ጉዳዮችን በሕግ አግባብ ማሳለፍ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ችግር በተለመደው የሕግ አግባብ እልባት ለማስገኘት እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

➡️ ሰሞኑንም ሆነ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ ያገኙ ዘንድ መላው ሙስሊም፣ ተማሪዎችና መሪው ተቋም መጅሊስ የተለመደ ሕጋዊ አካሄዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

ከተማሪዎቹ ጋር በነበረው ውይይት የም/ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ፤ የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ዳይሬክተር ኡስታዝ ሀሰን አሕመድ እና የመምሪያው ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ በድር ተገኝተው ነበር።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

30 Oct, 09:11


በወላይታ ዞን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት የሰባት ሰዎች  ሕይወት አለፈ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጫቴ ኮምሻ ቀበሌ እና ኮይሻ ላሾ 01 ቀበሌ በዛሬው እለት  ከጠዋቱ አንድ ሰአት ላይ የጣለ  ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሰዎች ህይወት አልፏል።

በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ  የሰባት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት  እና በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው አንድ ህፃን እና አንድ አዛውንት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል ።

አደጋ በደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ምን ያህል ሰዎች እንደነበሩ በውል የማይታወቅ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በመቆፈር ላይ መሆናቸውን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በአካባቢዎቹ  ቀደም ሲል በከባድ ዝናብ ምክንያት የመሬት መሸንራተት አደጋ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

27 Oct, 07:32


በአዋሽ ፈንታሌ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ቀበሌ ጎምዲሊ በተባለ ሥፍራ እስከ 4 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከማለዳው 11 ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9 ሠዓት 21 ላይ ቢከሰትም ጉዳት አለመድረሱን በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምድር ጥናት መምህር ኖራ የኒሞኖ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ትናንት በተለያየ ሠዓት ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀን ቀን 9 ሠዓ 21 ላይ የተከሰተው ከፍ ያለ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የአካባቢዎች ነዋሪዎች በበኩላቸው ትናንት የተከሰተው ቀደም ሲል ከነበሩት ከፍተኛ መንቀጥቀጥ ነበረው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመሬት መንቀጥ ቀጥ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና ሌሎችተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

27 Oct, 07:32


🌻50% ቅናሽለ10 እድለኞች
አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ
#ከ DMC Real estate.
በመሀል ከተማ ለቡ 
  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  B4  ለሽያጭ አቅርበናል::

ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው

8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም 
    
💝💝💝አንድ መኝታ
        69ካሬ  =431,918ብር
        77.6ካሬ=485,751
💝💝💝ሁለት መኝታ👇👇
            99ካሬ=>619,708ብር
             104ካሬ=651,000ብር
💝💝💝ሶስት መኝታ👇👇
    👉139ካሬ=870,000ብር
      👉147.6ካሬ=923,928ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ለሱቅ ፈላጊወች  ከ20 ከካሬ
ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251918642895
@Gashawkefie

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

26 Oct, 06:10


እስራኤል ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች‼️

ኢራንም በበኩሏ በዋና ከተማዋ ቴህራን፣ ኹዜስታን እና ኢላም በተባሉ ግዛቶቿ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮች የእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቃለች።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው ኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አጋሮቿ የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ለፈጸሙት “ለወራት የዘለቀ ጥቃት" ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።

ጥቃቱን የፈጸመው “በተመረጡ ወታደራዊ ዒላማዎች” ላይ መሆኑን ያስታወቀው የእስራኤል መከላከያ ኃይል ኢራን ካለፈው ዓመት መስከረም 23/2016 ዓ.ም. ጀምሮ “ያለማቋረጥ እስራኤል ላይ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች” ሲል ወንጅሏታል።

ይህ የእስራኤል ጥቃት የተፈጸመው ቴህራን ውስጥ በሐምሌ ወር የሐማስ ፖለቲካ መሪ በመገደላቸው ኢራን ከ200 በላይ ባሌስቲክ ሚሳዔሎችን መስከረም 21/2017 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከተኮሰች በኋላ ነው።

የእስራኤል አየር ኃይል ሌሊቱን የፈጸመው ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የተኮሰቻቸውን ሚሳኤሎች የሚያመርቱ ተቋማትን፣ የአየር ጥቃት መከላከያ እና የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ሥርዓቶችን ዒላማ መደረጋቸው መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢራን በወታደራዊ ይዞታዎቿ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመባት አረጋግጣ፤ ነገር ግን “ጥቃቱ ውስን ጉዳት” ቢያደርስም በተሳካ ሁኔታ ማክሸፏን አስታውቃለች።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

26 Oct, 06:10


[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

በፆም ወቅት የሚወሰድ!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
👨🏾‍⚕️የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!🏃‍♂️

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን
☎️9369 ☎️

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

Join https://t.me/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

26 Oct, 06:10


🌻50% ቅናሽለ10 እድለኞች
አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ
#ከ DMC Real estate.
በመሀል ከተማ ለቡ 
  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  B4  ለሽያጭ አቅርበናል::

ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው

8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም 
    
💝💝💝አንድ መኝታ
        69ካሬ  =431,918ብር
        77.6ካሬ=485,751
💝💝💝ሁለት መኝታ👇👇
            99ካሬ=>619,708ብር
             104ካሬ=651,000ብር
💝💝💝ሶስት መኝታ👇👇
    👉139ካሬ=870,000ብር
      👉147.6ካሬ=923,928ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ለሱቅ ፈላጊወች  ከ20 ከካሬ
ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251918642895
@Gashawkefie

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

25 Oct, 17:56


አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ‼️

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በአሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተሰምቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

25 Oct, 08:16


የመከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው‼️

የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በመስዋዕትነት ያስከበረው መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊ ወታደራዊ መዋቅር እና የጦር ሠራዊት ሆኖ ከተዋቀረ ዛሬ 117ኛ ዓመቱን መያዙም በአከባበሩ ላየ ተገልጿል፡፡

ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስከበርና ማስጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የአፍሪካና የእስያ ሀገራት ሰላም በማስከበርና መስዋዕትነት በመክፈል ለሀገራት ሰላም መሆን የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱም ተነስቷል፡፡

ለአብነትም በኮሪያ፣ ኮንጎ፣ ላይቤሪያ፣ ርዋንዳ ፣ ቡሩንዲ፣ ሱዳን ዳርፉር እና በደቡብ ሱዳን አብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ሂደት ከፍተኛ ሚና መጫወቱ ተብራርቷል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የተረጋጋ እንዲሆንና እንደ አልሸባብ ያሉ የሽብር ቡድኖችን በመደምሰስ አኩሪ ገድሎችን መፈጸሙም ነው የተገለጸው፡፡

ሠራዊቱ አሁን ላይ ዘመኑ የደረሰበትን የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ከመታጠቅ ባለፈ ራሱን በስልጠናና በወትሮ ዝግጁነት ብቁ እያደረገ ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝም በአጽንኦት ተገልጿል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

25 Oct, 08:16


🌻50% ቅናሽለ10 እድለኞች
አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ
#ከ DMC Real estate.
በመሀል ከተማ ለቡ 
  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  B4  ለሽያጭ አቅርበናል::

ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው

8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም 
    
💝💝💝አንድ መኝታ
        69ካሬ  =431,918ብር
        77.6ካሬ=485,751
💝💝💝ሁለት መኝታ👇👇
            99ካሬ=>619,708ብር
             104ካሬ=651,000ብር
💝💝💝ሶስት መኝታ👇👇
    👉139ካሬ=870,000ብር
      👉147.6ካሬ=923,928ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ለሱቅ ፈላጊወች  ከ20 ከካሬ
ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251918642895
@Gashawkefie

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

25 Oct, 08:16


[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

በፆም ወቅት የሚወሰድ!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
👨🏾‍⚕️የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!🏃‍♂️

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን
☎️9369 ☎️

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

Join https://t.me/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

24 Oct, 17:32


መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል‼️

🗣Via Elias Meseret

በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።

"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።

መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።

ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።

ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።

ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

24 Oct, 12:53


የ2017 ዓ. ም የዪኒቨርሲቲ ምደባ ተለቀቀ‼️

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች👇

lWEBSITE:
https://placement.ethernet.edu.et

TELEGRAM
https://t.me/moestudentbot
Via_atc


@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

24 Oct, 08:07


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል‼️

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

23 Oct, 11:23


ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ። በውይይታችን ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ‼️

🗣ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

23 Oct, 08:16


እስራኤል አዲሱን የሂዝቦላህ መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን መግደሏን አረጋገጠች‼️

የእስራኤል መከላከያ ሃይል እንዳስታወቀው÷ የቀድሞው የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ የአጎት ልጅ የሆነው ሀሽም ሳፊይዲን ከሶስት ሳምንት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በወሰደችው የአየር ጥቃት ተገድሏል።

ከሀሽም ሳፊይዲን በተጨማሪ የሂዝቦላህ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ አሊ ሁሴን ሃዚማ እና የቡድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በጥቃቱ ተገድለዋል ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሂዝቦላህ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል።
ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ቀን 2024 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የእስራኤል መከላከያ ሀይል ሀሰን ሳፊይዲንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ መሪዎችና ታጣቂዎች መገደላቸውን ተናግረው ነበር።

በወቅቱም ሀሰን ነስራላህን በመተካት ወደ ሂዝቦላህ መሪነት የመጣው ሀሽም ሳፊይዲን ሳይገደል እንዳልቀረ እየተነገረ ነበር።

ይሁን እንጂ በእስራኤል ጥቃት የመሪውን መገደል የእስራኤል መከላከያ ሃይል አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

23 Oct, 07:53


የሞሪንጋ (ሽፈራው) ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ‼️

በኢትዮጵያ 'ሽፈራው' እየተባለ የሚጠራው የሞሪንጋ ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡ጥናት እና ምርምሩ ተግባራዊ እንዲሆን የጣሊያን መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዲስትሪ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በጋራ የሰሩትን ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በምግብ ቴክኖሎጂና ባዮቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር አዲሱ ፍቃዱ፤ የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር ጨምሮ ብዙ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በጥናት እና ምርምር መረጋገጡን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተክሉ ውስጥ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የሚገኝበት በመሆኑ ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል በመጠቀም እንደሚቻል አንስተው፤ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፍ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችንም ማስቀረት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በዋናነት ተግባራዊ የተደረገው ተክሉ በስፋት የሚበቅልበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ዘይሴ ቀበሌ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከተክሉ የተለያዩ ምርቶች እንደሚገኝበት እና ዘርፍ ብዙ ጠቀሜዎች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡

በተገኘው ጥናት እና ምርምር መሰረት፤ ተክሉ በብዙ መልኩ የሚቀነባበርበት የፋብሪካ ግንባታ ተጠቀናቆ የተለያዩ ማሽኖችም መግባታቻውን አሐዱ ማረጋገጥ ችሏል፡፡የተጀመረው ፕሮጀክት ተግባራዊ እንዲሆን ያሉትን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል አሐዱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ላነሳው ጥያቄም፤ የመንገድ እና የኤሌትሪክ አገልግሎት ችግሮች እንደሚፈቱም ተናግረዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የፕሮጀክቱ ቴክኒካል አማካሪ ዶክተር ለምለም ሲሳይ በበኩላቸው፤ በገጠር ላሉ ሴቶች የኑሮ ማሻሻያ ያስፈልጋል በሚል ከመንግሥት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረጉን አንስተው ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ እንደተሰራም አስረድተዋል፡፡የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክልን አብዛኛው የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን እና ደምግፊትን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚጠቀሙበት የሚታወቅ ነው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

22 Oct, 13:44


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ‼️

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

22 Oct, 09:16


በአዲስ አበባ እየተካሔደ የሚገኘው 46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ‼️

@Esat_tv1
@Esat_tv1