በሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮች እና ጁባላንድ ኃይሎች መካከል ትናንት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ የጁባላንድ ኃይሎች ራስካምቦኒ ከተማን ተቆጣጠሩ። ውጊያው በሁለቱ አካላት መካከል ትናንት ታህሳስ 2 ቀን ጠዋት የተጀመረ ሲሆን የጁባላንድ የፌዴራል ኃይሎች ግጭት አስጀምረዋል ሲል ከሷል።የሟቾች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም የመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት እንደተከሰተ ሪፖርት ተደርጓል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የጁባላንድ መሪ የሆኑትን አህመድ ኢስላም ሞሀመድ ማዶቤ ከአልሸባብ ጋር ተባብረዋል ሲል በመክሰስ በተሳታፊዎች ላይ "ህጋዊ እርምጃ" ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቋል ሲል ሶና ዘግቧል።የጁባላንድ ባለስልጣናት ኃይላቸው ስትራቴጂካዊ አየርማረፊያን ጨምሮ በራስካምቦኒ ቁልፍ ቦታዎችን መቆጣጠሩን ገልጸዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከ300 በላይ የፌደራል ወታደሮች ወደ ኬንያ ተሻግረው በኬንያ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርገዋል። በተጨማሪም 240 የፌደራል ወታደሮች በጁባላንድ ወታደሮች እጅ መግባታቸው ተነግሯል።
@Addis_Mereja