ክፍል ፩
✍በቤዛዊት የሴት ልጅ ✍
የስልኩ ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ ተናደድኩ...... ያቋረጡኝ ምን ከመሰለ ህልም ነበር። የህይወቴ የመጨረሻዋ ስኬቴ ናት አምላኬ እሷን የሰጠኝ ዕለት እውነት በዓለም ላይ ሾሞኛል ማለት ነው። "ባሮክ ባሮክ" ጩኸቷማ እህቴ ነበረች ወደ ቆጡ መውጫ መሰላል ላይ ሆና የምትጠራኝ። "ተነስ ኧረ እንዳትበቅል" አለችኝ። ብበቅል ደስ ባለኝ እሷን እያሰብኩ ጥርሴ ቢረግፍ ጸጉሬ ቢሸብት አልኮነንም ነበር።
እንደ ምንም ተነስቼ ወረድኩኝ። ምሳ ቀርቧል የእህቴ ቆንጆ ሽሮ እንጀራው ላይ ራስ ሆኖ ይታያል ተጣጥቤ ከማዕዱ ተቋድሼ ወደ ጓደኛዬጋር ሄድኩኝ።
ባሮክ እባላለሁ በኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ከተመረኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል እንደማንኛውም ወጣት የመንግስት ስራ ባይኖርኝም ለራሴ ባመስነፍ ከአንድ ሞል ላይ አንዲት ልጅ ቀጥሬ ቡና ጠጡ እየሰራሁ ነው። አብሮ አደጌም ሳሚም የራሱ የስፖርት ቤት ከፍቶ እየሰራ የሚገኝ የቅባት ልጅ ነው። ከሁለተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ተምረን ያደግን ልጆች ነን። አሁንም ወደ እሱ ነው የምሄደው። ገና ስደርስ ሽሮ በልቶ የሚያድረው ህዝቤ ይሄን ብረት እየገፋ ነበር የተጨማደደ ፊቴን ፈገግ አድርጌ ወደ ሳሚ ቢሮ ገባሁ።
"እ ብሮ ቆየህ እኮ" ገና እንዳየኝ ሳሚ ተናገረ።
"ምን ከመሰለ ህልም ላይ እንደተነሳሁ ብታውቅ እንዲህ ባላልክ" አልኩት ሰላም ብዬው እየተቀመጥኩ።
"ቅዠታም ደግሞ አገረሸብህ" አለኝ ፋይሉን እየከተተ።
"የምሬን ሳም በአሁኑ እኮ ሳገባት ነው ያየኋት" አልኩት ውስጤ ያለውን ደስታ ከፊቴ እያስነበብኩት።
"ቆይ ለምን ሱባኤ አትይዝላትም እንዴ ተቆጣጠረችህ እኮ" አለኝ የባከንኩ የመሰለው አብሮ አደጌ።
"ሳምዬ ብትቆጣጠረኝማ እየበተነ ያለው በረከቴ በሰበሰብኩት የተዘጋው በሬ በተከፈተልኝ እውነት እንዴት ውብ ሆና ስታየኝ እንደነበር በተለይ የምወደው ጥርሷ ብልጭ አድርጋ ስታሳየኝ እኮ....." አቋረጠኝ።
"ተነስ ባክህ እንሂድ" አለኝ። ተናደድኩ ተኮሳትሬ ቀድሜው ወጣሁኝ። መኪና ውስጥ እየሄድን ዝም አልኩኝ ዕቃቃውን እንደተቀማ ህፃን እጄን አጣምሬ በመስኮቱ ወደ ውጪ እያየሁ ነበር እንደማላወራው የተረዳው ሳሚ ሙዚቃውን ከፈተው።
🎧🎧🎧🎧🎧
ኤፍሬም እኔን የጠየቀኝ ይመስል ስለ ውበቷ የዘፈነልኝ የሚመስለኝን የምወደውን ሙዚቃ ነበር
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
ዞሬ አየሁት እና ፈገግታዬን ሰጠሁት። "ኧረ ወንድሜ ለአንተ ብዬ ነው አልነገርካት ነገር ልጅቷ በየት ትወቀው ሁሌ እየተያዩ መሳቅ በአይን መሸኛኘት ይጎዳሃል። በህልምህ አትቃዥ ንገራት" አለኝ አፍ ሆኖ የሚነግርልኝ ይመስል። እኔም ሌላ ክርክር ውስጥ ላለመግባት የወሬውን ርዕስ አስቀይሬ ስለ ምንሄድበት ስራ ማውራት ጀመርኩ። ከደቂቃዎች በኋላም የምንገባበት ህንጻ ጋር ደርሰን መኪናውን ፓርክ እያደረግን እኔም ሳሚም የደነገጥነው። ህልሜ ናት......
ክፍል ፪ይቀጥላል
❤️🩹🥹መድኃኒት አዲስ ተከታታይ ታሪክ ❤️🩹🥹
በማንበብ አስተያየት ስጡ ወዳጆቻችሁን ጋብዙ!
https://t.me/yebezigetmoch