አንድ ተሳቢ መኪና ነጠላ ክብደቱ እስከ 220 ኩንታል ወይንም 22,000 ኪሎ ይደርሳል በሊቭሬ ላይ የሀገሪቱ መንግስት መጫን ይችላል ብሎ የፈቀደው እና ሊቭሬ ላይ ያሰፈረው 387 ኩንታል ወይም 38,700 ማለት ነው ነጠላ ክብደቱን ሊብሬ ላይ ከተፃፈው ጋር ደምረን ጠቅላላ ክብደቱን ብንደምር 60,700 ኩንታል ይሆናል የሚዛን ህግ ብለው ባወጡት ግን መጫን የሚፈቅደው 56,000 ሽህ ኪሎ ይላል ይህ 4,700 ኪሎ ልዩነት አለው ለምን ??
ህግ የጣሰ አይቀጣ ባንልም ሊብሬ ላይ የተቀመጠው የመኪናው የመጫን አቅም እና የመኪናው ነጠላ ክብደት ሲደመር እኩል ባልሆነበት የ47 ኩንታል ልዩነት ባለበት ሂደት ማነው
ህገወጡ ??
እናንተ ጠቅላላ ክብደት 560 ነው መጫን የሚቻል ካላችሁ እንኳን አንድ ተሳቢ 340 ኩንታል ብቻ ነው መጫን አለበት የምትሉን :: ሊቭሬው ደግሞ 387 የመጫን አቅም አለው ይላል መንግስት ራሱ ፅፎ በሰጠው ሊቭሬ ላይ ያለን ክብደት በምን ህግ ነው የሻረው ?? 47 ኩንታል የቀነሳችሁ በየትኛው አዋጂ በተቀመጠ ስልጣናችሁ ነው ??
የትራንስፖርት ማህበራት የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በጥምረት ይህንን ጉዳይ ይዛችሁ ቀርባችሁ ሊቭሬ ራሱ ሰጦ ራሱ ሊብሬ ላይ ያሰፈረውን ክብደት የቀነሰበትን ሂደት ልትጠይቁ ይገባል ::
የትራንስፖርት ሎጂስቲክ ሚንስቴር ይህንን ጉዳይ ሊመረምር ይገባል :: ነው ተሽከርካሪዎችን ከጂቡቲ ኮሪደር በማስወጣት በባቡር ብቻ ስራውን የመስራት አንዱ ዕቅድ ይሆን ??
የኢትዮጽያ መንገድ ትራንስፖርትስ ሊብሬ ላይ የመጫን አቅም 387 ኩንታል ብሎ አፍሮ የራሱ የክብደት መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ 340 ነው መጫን አለባችሁ ማለቱ ስህተት ነው