ግጥም እና ሳቅ ™🤣 @teddy_yunki19 Channel on Telegram

ግጥም እና ሳቅ 🤣

@teddy_yunki19


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀

⚡️WELLCOM TO Poem AND LAUGH 😂

💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የሳቅ ምንጭ ነን!

● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏




👉any comments & Cross ➡️ @Tedo27 ያነጋግሩ::

ግጥም እና ሳቅ 🤣 (Amharic)

እንዴት ነው ይህ ቻናል? መጽሐፍና ሳቅ በእምነት ጀምር የሚያደርጋትን ያወጣል፡፡ ግጥሞች፣ ፍቅር ቃላቶች እና ሳቅ በአጭር ፍጥነት ይሁኑ፡፡ ይህ ቻናል በቻናሉ በአንድነት ሚስጥራዊ ጨርቅ በተለያዩ አቅቷል፡፡ ከአርቲስቱ ውስጥ የተወሰነ የፀሐፋ እና ስለመጻፊያ ከግጥም ሳቅ 🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀 እርዳታ የሆነውን ፡፡ በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ ግጥឝች፣ የሳቅ ምንጭ የተመረጡን እርዳታውን ማስተርጎት እና SHARE ለእርዳቶችም ጠቀመባቸዋል፡፡ የማፍቀር ስለሚጀምሩ ከቻናላችን ጋር ያጋሁጡ፡፡ ከቻናሌ ሳቅ 💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥም፣የሳቅ ምንጭ ናቸው፡፡ እናንተም ግንብ ላከ፡፡

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Jan, 18:48


ፋዘር:- ትሰማለህ ፈተና ከወደቅክ አታውቀኝም አላውቅህም

Me :-እሺ

ከፍተና በኋላ

ፋዘር:- እሺ ፈተና እንዴት ነበር?

Me :- ማነህ ደሞ አንተ
😅😂😂😂🤣



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Jan, 17:10


#ጥቁር ከሆንክ ልትነጣ ትችላለህ
.
ወፍራምም ከሆንክ ልትከሳ ትችላለህ
.
አጭር ከሆንክ ግን ቻው
👋😁


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Jan, 04:06


ተመስገን በሰላም አስውሎ በሰላም ላሳደረን ፈጣሪ🙏


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

10 Jan, 18:06


ብንቆይ ይሻላል

   ከመኖር አለመኖር ይሻላል እሚሉህን እንዳትሰማቸው። አለመኖር ተሽሎ አያውቅም…ሁሌም ፈጣሪን እንዲያቆይህ ለምነው…ለንሰሐ ሞት እንዲያበቃህ ፤ ቤተሰቦችህን ለመጦር እስኪያበቃህ ፤ አግብተህ ልጆች ወልደህ እስክትስም ድረስ እንዲያቆይህ ፀልይ።

   መረጋጋትን ከፈለግክ ደሞ ወደ ፈጣሪህ ቅረብ…የውስጥ ሰላምን ከፈለግክ ወደ ፈጣሪ አብዝተህ ቅረብ…ሁሉም ችግር ከሱ በታች ነው…እመነኝ ሁሉም ያልፋል…ከዚ በፊት እኮ ብዙ አልፈሀል…የሚያልፉ እማይመስሉ ቀናትንም ጨምሮ።



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

10 Jan, 17:00


ATM ተሰልፈን ከኋላዬ ለቆመችው ቆንጅዬ ተራዬን ስለቅላት "You're so gentle" ብላኝ ሳቅ... የዛሬን መዋያ 50 ብር ሳወጣ እንዳታየኝ መሆኑን አላወቀችም🤭



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Jan, 19:04


                ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Jan, 18:53


🍷cheers የኳስ ችሎታ እያለን
CLUB ላጣነው
😢


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Jan, 18:02


ምረጪ

አፍቅረሽ ከማታገኚው ወንድ ❤️
       
               እና

ከሚያፈቅርሽ አንቺ ከማትወጂው ወንድ💔


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Jan, 16:44


🚨 ሰበር ዜና!

የመብራት ሀይል አስተዳደር ስራአስኪያጅ የሶላር ነጋዴ መሆኑ ተደረሰበት!

#በሪያክት_እንዲቀጣ_ተወስኗል🤣😁

ግጥም እና ሳቅ 🤣

08 Jan, 18:26


አንድ ጀለስ Bank ቤት በየቀኑ 10 ብር 20 ብር እየተመላለሰ ያወጣል...
:
#ወንድሜ_እየቆጠብክ_ነው_እየቆነጠርክ ?

      
#react ማንን ገደለ😂😂😡
😁😁🤣🤣



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

08 Jan, 17:55


ሞት ሞት  ሸተተኝ ምትሉ ሰዎች ግን 🤩


ምን ምን ይላል
😂😂 እስኪ ንገሩኝ


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

07 Jan, 07:28


ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ

ክርስቶስ ከድንግል ማርያም

በቤተልሔም በግርግም ተወለደ🥰🙏 እንኳን ለ ገና በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ ፤ አደረሰን 😍😍
መልካም የገና በዓል 🥰


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Jan, 18:09


የዋዜማ ድባብ እንዴት ነው
የኔ
🤗
.
.
.
የእናንተስ?

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Jan, 17:27


💔ፍቅርሽ አስጨንቆኝ እንደዛ ስቸገር
አንቺ ዘና ብለሽ ትበያለሽ በርገር
🍔
       
      
#የሆንሽ_ጅብ_ነገር🐻
😁😁😁😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Jan, 15:00


እሷ ለገና ስጦታ አትሰጠኝም እንዴ
እኔ፡ልደቱ የክርስቶስ እንጂ ያንቺ አይለይም 🤗


እንካን አደረሳቹው
🎄

   @Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

05 Jan, 16:21


ተወሳሰበና ሲፀና ነገሩ
.
.
.
.
.
አራዳና ፋራ አንድ ቤት አደሩ
😁

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Jan, 18:50


Bro አንድ እረኛ ከአስር በላይ ላሞችን በአንድ ዱላ መቆጣጠር እንደሚችል ታውቃለህ ??

ይህ post ስለ ዱላ አይደለም?


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Jan, 16:53


ቤብ 😍😂

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

03 Jan, 18:28


          ይኸውልሽ ስሚ

ይወደኛል የሚል - ወሬሽን አቁሚ
ወፍዘራሽ ስንደዶ
የማንም ልቅምቅም የማንም ቅራሪ
ማንአባሽ ስለሆንሽ
ይወደኛል ብለሽ የምትናገሪ?
በርግጥ አይሻለው ይህንን አልክድም
አይን ያየውን ሁሉ ልብ ግን አይወድም
አዎ አይቼሻለው
ስትቆለጳጰሽ    ስትቆሚ ስተኚ
ግን እንደሞኝ ሰው አይኔን እንዳታምኚ
አንቺን የሚያስንቁ እቆጥራለው መቶ
እንኳን አንቺን ጀዝባ ልለማመጥ ቀርቶ
አስቤሽ አላውቅም - ትመስክር ጨረቃ
ግን
ግን
ግን - አቦ ግን አበዛው
ወድሻለው በቃ.





@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

03 Jan, 17:53


ንግድ ፍቃድ ሊያወጣ ሄዶ የታደሰ መታወቂያ አለህ ሲባል ምን ቢል ጥሩ ነው
.
.
.
የታደሰ የለኝም ግን የራሴ አለኝ😂😂😂😂😂😂

        
#Er ተጫኑ😂😂😂😂🤪


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Jan, 16:43


ግጥም እና ሳቅ 🤣

ጓደኛዬ በጣም አጭር ከመሆኗ የተነሳ መንገድ ላይ ስትሄድ

እንቅፋት እሚመታት
#አገጯን ነው

😂😆


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Jan, 16:49


ለዚ ልጅ ፍቅረኛ የሰጠክ አምላክ አረ እኛንም አስበን😔


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

31 Dec, 18:30


ፈግግ ካልክ ጥሩ ጓደኞች ኮስተር ካልክ የተሸበሸበ ግንባር ይኖርሃል።

እስኪ_አንዴ_እንሳቅ_አይቆጥርም 😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

31 Dec, 17:34


#ታውቂያለሽ?

ፎቶሽ ላይ ጠረንሽን መፈለጌ
የእኔን ስም ከግርጌው ማድረጌ
.   .   . አታውቂም!

እኔ ውድቅ ሆኜ የአንቺን ክብር አግዝፌ
ስወድሽ ከልቤ እንዳይደለ ከአፌ
.   .   . አታውቂም!

ገብቶሻል?
እንደ ከሰልኩ እንደ ከሳኹ
በአዝማድ እንደተረሳኹ
.   .   . አልገባሽም!

ቢሆንም
እኔ እያለኹ መቼም አትወድቂም
ደግሞ'ኮ ይሄንንም አታውቂም
እንዲህም ስልሽ እንኳ በደስታ አትስቂም
.   .   . አታውቂም!

ደግሞ
ሳኮርፍሽ ወዲያው ስትናፍቂኝ
አፍቅሪኝና በናፍቆትሽ ይባስ አጨናንቂኝ
“አፈቅርሃለኹ!” በዪኝና ከልቤ አስታርቂኝ!



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

31 Dec, 15:54


ሮፍናን ቁንጅና ሰው ሆኖ ይሄዳል ቦሌ ያለው
.
.
እኔ ቦሌ ጎዳናዎች ላይ ወክ ስበላ አይቶኝ ሊሆንም ይችላል 🙄😁


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Dec, 17:10


ለ 10ኛ ግዜ ሰርቀህ ፍርድ ቤት ቀርበህ ዳኛው አንተ ልክስክስ ዛሬም ሰርቀህ
"
"
#ክቡር ፍረድ ቤት አይሳደቡ ደንበኛ ክቡር ነው 😂 😂 😂 🤣 😆

#like🙂‍↕️


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Dec, 18:35


አንድ አህያ 🐴 ነበር እንደኔ የከፋው 😞
የሆዴን ስነግረው የጉንጩን ሳር ተፋው 😁

       መልካም ምሽት ይሁንላቹ ቤተሰብ


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Dec, 18:12


የኔና ያንቺ ህይወት

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት

እውነት እውነት ስልሽ
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።

                       
                         
   
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Dec, 17:17


ፍቅርን አምኜ ብዙ ታግያለው
መውደድን አምኜ ብዙ ታግያለው
አንቺን ለማስደሰት የማይሆን ሆኛለው

🎶🎶



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Dec, 13:40


ለምንድነው ግን ምግብ ቤት ገብተን ዋጋ ተከራክረን ቀንስ አያዋጣም ብለን አስቀንሰን መብላት የማንችለው…?😂😁🤭


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

07 Dec, 16:30


1;በጠራራ ፀሀይ የተወለደችዉን ልጅ ስሟን ማን አሏት

ME👉 ፀሀይ ቦጋለ🤭😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Dec, 18:37


ኢትዮጵያ ህዝብ ግን ውብ እና ግሩም ነው Fam
'' Respect'' 🫡

150 like ግድ ነው



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Dec, 17:03


እማ.........!

ስለ እናቴ ልፅፍ ብዬ
ብዕሬን ያዝኩኝና

ቁሜም ቁጭ ብዬም
ትንሽ አሰብኩና

እማ ብዬ ተዉኩት
መላው ጠፋኝና

አሳምሮ ኸልቋት
ሁሉንም አሟልቶ

እንደት ትጠፋለች
እናት በስኪቢርቶ

እማ እንዲህ ናት ብዬ
ችዬ አልዘረዝርም ግን
እናት እናት ናት ሁሌ አትቀየርም

                    እማዬ



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

06 Dec, 16:32


አንዳንድ ሰዎች ግን ለምን ያለፈዉን ነገር ረስተዉ አዲስ ኑሮ አይኖሩም

በተለይ ያበደርከኝ ሰዉዬ🥹
🤣😂😁

      
#Like ማንን ገደለ😂😂😂?





@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

05 Dec, 17:37


ለሊት የምትሉ ሰዎች ግን🙄😁😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

05 Dec, 16:38


ቆይ ግን ከማታ እና ከቀን የቱ ይሻላል…?✌️


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Dec, 18:21


#ቺርስ🥂  እያፈቀርናቸው ፍቅራችንን ላልገለፅናላቸው😢🥂

♡ ㅤ     ❍ㅤ             
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Dec, 17:59


ልውደድሽ♥️ ደግሜ💗

ያኔ ትዝ ይልሻል በልጅነት እድሜ
እወድድሽ ነበረ እኔም በአቅሜ
በትንሿ ልቤ ማንነትሽ ሰርፆ
ብዙ አንገላቶኛል ፍቅር ተፀንሶ
መውደዴን ሳታቂ ችላ ብትይኝም
ያንቺ ችላ ማለት ፍቅሬን አልቀነሰም
       ወድዬ....................
ያለ አንቺ ፍቃድ    ልቤ ፍቅርን ቢሻ
ላንቺ ያለኝ መውደድ የለው መጨረሻ 
እያለ ነበረ ሲያፈቅርሽ የኖረው
የጊዜው እርዝማኔ ፍቅሬን ቢያስታግሰው
ያ ሁሉ አመታት ግን አልቻለም ሊሽረው
ውድዬ.................
በአፍቃሪው ልቤ ፀባይሽ ተዘርቶ
መፍትሄ አልባው ፍቅርሽ ዳግም አገርሽቶ
መድሀኒት የሌለው ሆነሻል ህመሜ
እባክሽ ፍቀጅልኝ ልውደድሽ ደግሜ
  ውድዬ💓💓



    
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Dec, 16:11


Like እማታረጉ ሰዎች

ምቀኛ መሆናቹህን ደርሼበታለው😒🤍👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Dec, 12:43


ታናሽ ወንድሜ ማታ ቀምቅሞ🍺 መጥቶ እንዴት አልኮል ትጠጣለህ ስለው

100% ገብስ ስለሚል በሶ መስሎኝ እኮ ነው!😂😁😂




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

03 Dec, 17:45


ኑሮ ስለመረረኝ የአሜሪካው ገዳም መሄጃውን መንገድ ንገሩኝ። አለም በቅቶኛል 🤔🙄😁


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

03 Dec, 16:45


#የባልታሳር_ችሎት

👩‍⚖ ዳኛዋ፦ ሚስትህ ላይ ሴቶችን በተደጋጋሚ ትደርባለህ በሚል የቀረበብህ ክስ እውነት ነው?

🧑‍🦲 ባልታሳር ፦ ውሸት ነው ውዴ

👩‍⚖ ፍርድ ቤቱ በእኔ ቤት ውስጥ ለ ሁለት ዓመት በቁም እስር እንዲቆይ ወስኗል🙈🙈

#የገባው 😁😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Dec, 17:15


🔥እውነት ግን ....!?🔥
ሁሌም ሁሌም ሳያት ከቦታ እማጠፋው
ከሰው እማትገኝ እውነት ናት አውቃለሁ
አይቀድማትም ቢሮጥ ውሸት ከፊት ቢፃፍ
እውነት አለኝ ብሎ እውነታዋን ቢያከሽፍ
ግን .......
በትናንት አይቀርም የነገውም ታሪክ
ሁሉን ይቀይራል የሰማዩ አምላክ
እንጂ ግን ......
በጊዜ ጊዜ ላይ ውሸት ስትበረታ
እውነት ግን እውነት ናት ትታያለች ነግታ🔥🔥🔥🔥💚💚💚💚

𝗝𝗼𝗻𝗶😘😘

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Dec, 18:45


እስኪ ለ ባይስ #👏 ይገበዋ ምትሉ



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Dec, 18:02


#⃣በ አምላክ ቦታ ሆኜ
ነፍሴን ብመለከት፤
    
        አቃተኝ!
        ከበደኝ!

ራሴን ይቅር ማለት።



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Dec, 16:27


ለኢትዮጲያ እግር ኳስ VAR ሳይሆን ሳር ነው ሚያስፈልገው 😕😂😂

ለዚህ ቻናልም እይታ ሳይሆ
#Reaction👍 ነው ሚያስፈልገ😊😂😂




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Nov, 17:55


ሴት ልጅ ስጦታ ናት !
  

ህፃን ስትሆን አጫዋች ልጅና እህት ትሆናለች።

ከፍ ስትልም እናቷን አጋዥ እና ታናናሾቿን ተንከባካቢ የቤቱ ሁለተኛ ናት።

ይበልጥ ስትበስልም ለወላጆቿ ወግ መአረግ አሳይታ ተድራ፤
ትዳሯን ተንከባካቢ፣ የቤቱ አድማቂ እና
ውድ ልጆችን የምትሰጥ ውድ ሚስት ትሆናለች።

ከዛም አልፎ ለልጆቿ አሳቢ፣
እራሷን ጥላ ለቤተሰቧ የምትኖር አዛኟ እናት ትሆናለች



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Nov, 17:30


#አረብ_ሀገር_ያሉ_የሀበሻ_ቺኮች_የtg_ስም....

ሀኒ ነኝ የማዳሟ ቅመም
ሳምሪ ነኝ የኩበቱ ሽታ ናፋቂ
ቤቲ ነኝ የአስታጥቄ ምርኮኛ አሌክስን ናፋቂ በተለይ ቴዲን 😁
..
..
..
#አስተውላችሁታል_ግን_ሪያክት_እኮ_ቀንሷል😞


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Nov, 16:59


ልጅ እያለን እዚጋ ሻንጣ ሙሉ ብር ብናገኝስ
.
.
.
የምንላት ነገር ❤️🥹🤌🏿

❤️ትዝታው ያለበት



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Nov, 18:51


🥂ቺርስ  ቤተሰባች ውስጥ
አንድ ነገረኛ አክስት ላለችን  😭😤😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Nov, 18:34


ታክሲ ላይ 1 ብር ለጣለች ቺክ Flashlight
.
.
.
.
.አብርቶ ከሚፈልግ ወንድ በላይ
#አሽቃባጭ የለም🤷‍♂️




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Nov, 17:21


#ዘመድ ቤት ሄጄ ምግብ እየበላን ውሀ ጠምቶኝ ልጠጣ ብድግ ስል "ብላ እንጂ ብላ እንጂ" ሲሉኝ
.
,
,
በቃኝ ብዬ በዛው እጄን ታጠብኩ😢

እንደኔ ያጋጠመዉ😒
🫢



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Nov, 17:00


ሀሳብ አስተያየት ካሎት በ ኮሜንት ያድርሱን😘


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

27 Nov, 18:12


ሰላም እደሩልኝ ውዶቼ ጭንቀት ሀዘናችሁን በእንቅልፍ የምትረሱበት ለሊት ይሁንላችሁ

love you all🔥❤️👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Nov, 18:22


🥷🏽 :- ebet nesh
      :-  እራስህ ነህ እሺ እበት ቆሻሻ
🥷🏽 :-አረ እኔ እቤት ነሽ ነው ያልኩሽ
      :- 🥲
🥷🏽 :- BLOKED


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Nov, 17:35


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
#ካወራሽው_ላውራው 

ሌላ ወደድኩኝ ብል ፥ በአፌ ደጋግሜ፣
ለቃል ፍጆታ ነው ፥አትመኚ አለሜ።
ስምሽን አረሳም፥ፍቅርሽን አላወጣም፣
በንግግር መሃል፥ያንቺን ስም አላጣም።

ያቺን የዛሬ ሴት፥ገላ አረማመዷን፣
ድንቅ አለባበሷን፥ቀሚስና ጉርዷን፣
ገፅታ ስሜቷን፥ማኩረፍና ሳቋን፣
የጉንጯን ስርጉዳት፣ ከንፈርና ጥርሷን፣
በማየት መካከል፣አንቺን መስላኝ እንጅ፣
ካንቺ የበለጠ፥ማን አለኝ ወዳጅ።

እኔም እንዳቺው ነኝ፥ስምሽ ያመልጠኛል፣
ማሬ ፍቅሬ ማለት፥ሁሌም ይቀናኛል።
እናም ሳንጨርሰው፥የፈታነው ፍቅር፣
ዛሬ ናፍቀነዋል፥ልመለስ ጥል ይቅር።
ያምቺንም ሰማሁት፥የኔውም ይሄው ነው፥
ተራርቆ ፍቅር ፥ቢቀርብን ምነው?
     
#react❤️👍


        
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Nov, 16:58


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
#ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።





@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Nov, 16:13


ሄደ ወዳምላኩ ሄደ😢🥺😁😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

17 Nov, 17:15


ከዛሬ ነገ ታፈስን እያልን ለምንጨነቀው ወንዶች 🍻


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

17 Nov, 14:33


Ʀᴇᴀʟ💠



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

16 Nov, 18:18


ኪሎ ተመዝነህ 35ት ስትሆን..

መዛኙ፦
የእድራቹህ ድክመት ነው እንጂ ሞተሀል😂😂




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

16 Nov, 15:47


የግጥሜ እርስ ዳቦ
አይንሽ ዳቦ ቆሎ
ከንፈርሽ ጨጨብሳ
እኔስ ማበዴ ነው
ባንቺ የተነሳ

#ከተመቻችሁ_like_share




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

15 Nov, 16:25


👧  ዛሬ አንገናኝም? 

                                  👨 እሁድ ብንገናኝ ይሻላል እሁድ
                         ቀኑምረዥም  ስለሆነ አብረን እንውላለን።

👧 ቀኑ አልመሽ ሲልህ ለመደበርያ
ነው እንዴ የምትፈልገኝ?

                              👨 እሺ በቃ ዛሬ እንገናኛለን 8:00 ላይ
                                   ደውይልኝ
👧 አሃ እሁድ ሌላ ሰው ልትቀጥር
አስበሀል ማለት ነው?

                           👨 እሺ በቃ ዛሬም እሁድም እንገናኛለን

👧 ከዛ ተጣበቀችብኝ ነፃነት ነሳችኝ ልትለኝ ነው?


ምን ላርግ?  😢😢




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

15 Nov, 12:46


ማፍቀር አምሮኛል መፈቀር ምትፈልጉ
inbox😑😑🫣😂😂




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

14 Nov, 16:47


የሌለ 🤪ጦዤ ቤት ስገባ      👴ፋዘር"ለምንድነው የአቶ ይልማ ቀብር ላይ ያልሄድከው?" ሲለኝ
.
.
.
🤪እኔ መች ጠራኝ

👴ፋዘር ምን አልከኝ🤯🤬

👴ፋዘር በዱላ እያበረረኝ ነው የፖሰትኩላቹ ይሄን 🥸😂🤣




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

13 Nov, 16:42


ሁሉም ቆንጆ ነገሮች በ“M” ነው የሚጀምሩት Mom, Money, Music, Me 😜😂😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

12 Nov, 16:46


እኔ እንቅልፍ እወዳለው እንቅልፍም ይወደኛል ግን ቤተሰቦቼ በኛ ግንኙነት ደስተኞች አይደሉም😔😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

12 Nov, 16:13


አለምህ እናትህ ብቻ ናት ተንከባከባት❤️💐



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

12 Nov, 14:19


🗣ሲፋቀሩ፦

👱‍♂እሱ

አለምን በሙሉ ለብቻዬ ዞርኩኝ
ያንቺን አይነት ቆንጆ ፈልጌ አጣሁኝ😇

👱‍♀እሷ

ወንድ ነኝ እያለ ከሚያወራው ሙሉ
አንተ ትለያለህ ካየኋቸው ሁሉ🤤

🗣ሲጣሉ

👱‍♂እሱ

እንደው በምድር ላይ ብቻሽን ብትቀሪ
ዞሬም አላይሽም ብቻሽን ብታድሪ 😎

👱‍♀እሷ

ለምዶብኝ ነው እንጂ እንዲያው ስግደረደር
ከአንተ የሚበልጡ ስንት አይቼ ነበር 😩

  ስቆ
#ላሽ ይደብራል😁🙏 like ቤተሰብ



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Nov, 18:16


ነገ የሚፈጠረው አይታወቅም! 

ተሰጣጡ !

✌️😁


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

10 Nov, 17:30


#እውነትን ከውሸት
ትወጂኝ እንደሆን እያልኩ ሳሰላስል
ሆኖብኝ ተቸገርኩ ፍቅርሽ የጅብ ችኩል
የጅብማ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉኝ
ፍቅር ጣቴን ብሰጥ ነክሰሽ አቆሰልሽኝ
ትቀበዪኝ ብዬ ፍቅር ልቤን ብሰጥ
አልቀበል ብለሽ አንቺን ስለማመጥ
ሰከሬ ወደኩኝ በጭካኔሽ መጠጥ
አደነጋገርሽኝ ግራም አጋባሽኝ
ምን ልበል ጨነቀኝ የማወራው ጠፋኝ
እንደስደተኛ መሄጃ አጣሁኝ
ሀገሬ ውስጥ ሆኜ ሰው ሀገር መሰለኝ
በአይኔስ አያለሁ አሳወርሽው ልቤን
አካሌስ እዚሁ ነው ገደል ከተትኩ ፍቅሬን
ለምን?አትበዪኝ ልቤ ከታወረ በምኔ አያለሁ
ሁሉ ጨልሞብኝ ሰው ያለህ እላለሁ
ሰውም ጨካኝ አይደል ሚደርስልኝ አጣሁ
መስጠት እየቻልሽ ድምቅ ያለ ብርሀን
ጭካኔን ጨክነሽ አጨለምሽው ልቤን
ያንቺስ አጃኢብ ነው እንዲያው ትገርሚያለሽ
እውነተኛ ፍቅሬን ውሸታም ትያለሽ መልሰሽ
እየደባለቅሽ እውነትን ከውሸት ውሸትን ከእውነት
አመቱን ወር አልሽው ወሩን ደግሞ አመት
አሁን ግን ከበደኝ መለመን አልችልም
ሂጂ ሸኝሻለሁ ፍቅር በልመና ፈፅሞ አይሆንም



@Teddy_yunki19
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

10 Nov, 16:15


ሰንበት እንዴት አለፈ ቤተሰብ?


#react አርጉ እስቲ

የኔ👍😊😁😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

10 Nov, 15:55


የ united ደጋፊ የሆናችሁ አላችሁ?
.
.
.
#react አርጉ እስቲ🤗



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Nov, 16:45


ኪስ ውስጥ የተረሳ ብር ስታገኙ የሚሰማችሁ ስሜት 😊🤌🏽🫀

😎😎


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Nov, 15:57


ድስት ቢኖረን ኖሮ ዱቄት የለንም እንጂ ቂቤ ተበድረን ገንፎ እንሰራ ነበር።...  አለች. ...


ቀጥሉበት  😁😂😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Nov, 12:47


ሳላስብ ነው post ያረኩት ሳታስቡ like አርጉልኝ🤔🤣ool



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

08 Nov, 18:21


Single በመሆኑ የሚያዝን ሰው አለ ከናንተ ውስጥ ?😁🤩


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

08 Nov, 18:03


​​👉 ሚስጥር የነገርከው ሰው

ሰክሮ እንደማየት ምን ሚያስደነግጥ ነገር አለ😂


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

07 Nov, 17:23


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ አባ አንተ ማለት

የውበት አክሊሌ ክብርና ኩራቴ
የመኖሬ ትርጉም የምድር ገነቴ
ስምህ ስሜን ሲከተል ሆኖ ወደኋላ
ልጁናት ተብዬ በስምህ ስጠራ
እንኳንስ አቀበት እንኳንስ  ተራራ
ድቅድቅ ያለ ጽልመት ጨለማም አልፈራ

ጀግና ማነው ብለው ሰወች ቢጠይቁኝ
ጎበዝ እነ ደፋር ብለው  ቢጠይቁኝ
ካንተ ውጪ ሌላ ማነው እላለሁኝ

ጓደኛየ ሆነህ ሚስጥር ምትጋራ
አባቴም እየሆንክ መንገድ የምትመራ
ያንተ ልጅ እኮነኝ አባ እንዴት አልኮራ
የፍቅህን ዋጋ አምላክ ይክፈልልኝ
የበደልኩህ ካለም እሱ ይካስልኝ

እንጂማ በእኔ አቅም ካለው የምችለው
ነፍሴንም አልሳሳ ስላንተ ብከፍለው😍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

07 Nov, 17:05


አሁን ደግሞ ሁላችንም ❤️እቺን reaction እንነካለን



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

05 Nov, 12:23


አብይ ዝናብ አዝንበናል ሲል...

#People:- እስቲ በነካ እጅህ የፀሀይዋን Brightness ቀንስልን
😁😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Nov, 18:28


👨 የኔ ውድ ለምን ጠዋት ጠዋት አንሮጥም

                                     👩‍🦱  ወፍራም ነሽ እያልከኝ ነው?

👨 ኧረ አይደለም በቃ ተይው! 

                               👩‍🦱 ለምን ሰነፍ ነሽ እያልከኝ ነው?

👨 አምላኬ ሆይ እርዳኝ
      መጀመርያ ተረጋጊ እስቲ

                              👩‍🦱  እብድ ነሽ እያልከኝ ነው?

👨 ኧረ እኔ እንደሱ አላልኩም

                             👩‍🦱  ውሸታም ነሽ እያልከኝ ነው...

👨 አዎ!!  የመላጣ ልጅ

#የሪያክት❤️👍


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Nov, 17:52


Reaction ማታደርጉ ከሆነ post መልቀቄን ላቆም ነው😐😒

አይከፈልበትም እኮ🎧😳


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Nov, 17:18


😘♥️ልብሽን ለማግኘት📝
ልብሽን በፍቅር መማረክ ፈልጌ
ከጉብታው መሀል ከጡትሽ መሽጌ
ባልመው ባልመው ላገኘው ብለፋ
ላገኘው አልቻልኩም
ጡትሽን ስነካው ልብሽ እየጠፋ።



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Nov, 15:17


#ስልኬን እና ብሬን የሰጠሁት የተቸገረን መርዳት ስለምወድ እንጂ ያወጣብኝን #ጩቤ🔪 ፈርቼ አደለም...

ስጡ ይሰጣቹኋል ስለሚል ነው ቃሉ 😆😂🤣




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

04 Nov, 05:03


አስባችሁታል🤔 ትምህርት ሚባል ነገር ባይኖር 😮



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

03 Nov, 19:07


ሳምንቱን በemoji...
የኔ😢
.
.
የእናንተስ?



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Nov, 17:50


ጀለስ ማብርያ እና ማጥፍያ ሊገዛ ጠይቆ 6 birr ሲባል ምን ቢል ጥሩ ነው



ማብርያውን ብቻ 3 birr ሽጥልኝ
😂😂😂😂😂😂😂😂

  

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Nov, 17:10


ፎቶዬን ልፖስት እልና "ለምን ሴት ልጅ በኔ ምክንያት ከፍቅረኛዋ ጋር ትጣላለች ብዬ ተወዋለው...
:
 እውነት ነው እሺ????👇comente


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Nov, 16:39


ልቅር🥹🥹

@Teddy_yunki19



ሼር🙏

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Nov, 15:52


♥️😁ላንቺ ስል•••

<<እንጀራ እወዳለሁ  >> ፥  ስትዪኝ ሰምቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ ፥  አብሲቱን ጠጥቼ
ሞቼልሽ ነበረ  ፥ ኩፍታ አብዝቼ😂
ደግሞ እንደገና…
<<ማፍቀር መታደል ነው>> ፥ ስትይ ሰማሁና
አንቺን እረስቼ  ፤ ሌላ አፈቀርኩልሽ
ምን ማልሆነው አለ ፥ አንቺን ደስ እንዲልሽ?!😂


#ሼር



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

02 Nov, 11:29


የፍቅረኛዬ ልደት ቀን #be_like

Me: Happy birthday የኔ ፍቅር ! እንኳን ተወለድሽ 😍😍

እሷ : አመሰግናለሁ ውዴ፤ ስጦታ ምን ገዛህልኝ?

Me : ሰርፕራይዝ ለማድረግ አስቤ ነበር። ያቺ ባለፈው ያየናት
ፒንክ መርሰዲስ መኪና ትዝ አለችሽ?...❤️

እሷ : ወይኔ ደስ ሲል ፍቅሬ! አንተ እኮ አታደርገውም አይባልም!...😄

Me : አዎ ስሜትሽን እኮ እረዳለሁ። እሱን የሚመስል የጥርስ
ብሩሽ ገዝቼልሻለሁ...🙄

ሼር ብታደርጉ አሪፍ ነው!! ግን
#react ❤️👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Nov, 16:07


አቤና ሚስቱ😁

ለሊት ላይ ትቀሰቅሰዋለች

ሚስት: አቤ ተነስ ጅቦች አህያውን ሊበሉት ነው

አቤ: አንቺ ለምን አቶጪም እኔ እፈራለሁ🙄

ሚስት: ቱ  አሁን አንተ ወንድ ነህ ለስሙ ነው ያንጠለጠልከው 😏

አቤ:  ባንጠለጠለ ቢሆንማ  አህያው አይበልጠኝም ብለሽ ነው 🙂😁

  ስቆ
#ላሽ ይደብራል😁🙏 like ቤተሰብ




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

01 Nov, 14:56


 ቆሻሻ አውጡ እያሉ ሲጨው
ማዘር ወደኔ ትዞርና

#እራስህን ችለህ ውጣ☹️😂

Like ማንን ገደለ😂🤭


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Oct, 19:16


አላቹ ወይ👍


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Oct, 17:25


👥ብዙዎች ለክብራቸው ሲሉ ፍቅራቸውን መስዋት ያደረጋሉ።

እናንተስ ከፍቅራችሁና ከክብራችሁ የቱን ትመርጣላችሁ?
ፍቅር❤️
ክብር👍


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

30 Oct, 16:20


ተቀበል

እዛ ጋራ ማዶ ተተክሏል ፓፓዬ
*
*
*
* ብላው 😏😏



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Oct, 16:35


የራስታ 👩 ፍቅር  ሲገባልክ
.
.
.
.
.
.
የጋንጃ ገበሬ ትሆናለክ🍁

ከንቱ ዓለም😭



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

29 Oct, 16:01


የድሮ ባሎች be_like : የማን ኮቴ ነው የሚሠማኝ የጅብ ነው
እንዴ ቆመጤን ስጪኝና ወገብ አገዱን
ብዬ ልጣለው 😎😎😎😡😡

የአሁን ባሎች : ውዴ አብሲቱን ጥዬ ጎመኑንም ቀቅያለሁ
በኋላ ደግሞ እጋግረዋለሁ...... 😢😢

#React አልፈልግም ❤️👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Oct, 17:53


አንዱ ጀለስ ነው አሉ…. ከስራ ተባሮ  በተጨናነቀ ሐይገር ተሳፍሮ ወደቤቱ ሲገባ አከራዩ የቤት ኪራይ ብር እንደጨመሩ ነገሩት።

ቀና አለና ወደ ፈጣሪ....
“ይሄንማ መጥቼ ነው ምነግርህ”🥲😅

Like ማንን ገደለ😳😂👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Oct, 17:33


ጠብቄሽ ነበረ

ከቀጠርሸኝ ቦታ ፡ ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ከትልቋ ዛፍ ስር ፡ ጥላ ተከልዬ
"ና" ካልሽኝ ቦታ ላይ ፡ ሰዐተን አክብሬ
ጠብቄሽ ነበረ ባንቺ ፡ ተቀጥሬ
ፀሀይዋን ሳልሰለች ፡ በፀሀይ መጥቼ
ጉዳይ እያለብኝ ፡ ጉዳዬንም ትቼ
እስክትመጪ ድረስ ፡ ናፍቆቴ እየናረ
ፍቅሬ ለብቻዬ ፡ ጠብቄሽ ነበረ
 
ታዲያ ምን ያደርጋል
እኔ ስጠብቅሽ ፡ አንቺ አልመጣሽም
ቀጥራኝ ቀረች ብዬ ፡ ለሰው አላማሽም



       ,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
            •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  

 
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

28 Oct, 14:23


መልካም ዜና☑️

ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን አሰናብቷል ባይ ባይ😁😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

27 Oct, 17:43


ስሙኝም🤲
ከፍቅረኛቹ ጋር ተጣልታቹ💔 ይመጡና ነገ ሌላ ቀን ነው ሌላ ትወዳለችሁ ❤️ቀናቹ ይፈካል አታስቡ ምናምን ይሏችኋል..

እውነታችሁን ነው 😏😏😏
ፀሀይ በሌለችበት ንጋት የለም
እሷ ወይ እሱ ከጎንሽወይ ከጎንክ ከሌሉ ሁሌም ጭለማ ሁሌም አንድ አይነት ቀን ነዉ😔🖤

ኑሪልኝ የኔ🥺🖤

አይምሮዬን አስጨንቄ ያለኝን እውቀት አንጠፍጥፌ ነው የፃፍኩት😁LIKE ውዶችዬ❤️🥰




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

27 Oct, 16:25


ገንዘብ የሚፈልግ ያናግረኝ አብረን እንፈልጋለን🍸😢


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

27 Oct, 12:19


ጋዜጠኛ : አውስትራሊያ ላረፈደ ተማሪ ደረቅ ዳቦ በማብላት    
             ይቀጣሉ ለምን እዚህ አይሞከርም?
ብሬ :     እዚህ ሞክረነው ነበር ግን እዚህ ስንሞክረው  
             አስተማሪዎቹም ማርፈድ ጀመሩ 🤷🏾‍♂

ዛሬ ማንም ሪያክት እንዳያደርግ  ይቅር!! 👍❤️



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

26 Oct, 17:53


🤭ይሄ ነው ቀመሩ ለሴት😂😂

~ቆንጆ ፊት =no ቂጥ
🍑

~አስቀያሚ face =ግብዳ ቂጥ
🍑

~ቆንጆ ፊት +ግብዳ ቂጥ =ባዶ ጭንቅላት
😶‍🌫️

dislike ማንን ገደለ🫣😂




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

26 Oct, 12:01


የ Sigma ነገር ግን ቀዘቀዘ እኮ ጎበዝ እንደ በፊቱ አይወራለትም እኮ
.
.
.
ወንድ ሁን🤧😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

24 Oct, 16:28


         ✈️ ለዉጥ የለም አትበሉ ✈️

ሆደ ጩቤ ይሉት~ አፈ ቅቤ ነግሶ
በየቀኑ ሰበር~ በየቀኑ ለቅሶ
መልካም ዜና ናፍቆት~ ጆሮ ግንባር ላይ ነው
'ምንሰማው ይቀድማል~ ባ'ይናችን ካየነው


ለ.ው.ጥ.ማ... አለ!
መፈናቀል አለ
መገዳደል አለ
ሴራ ማሴር አለ
መንገድ መዝጋት አለ
ቤት ማቃጠል አለ
ዘረኝነት አለ~ ዱለኝነት አለ
ይህ ሁሉ ተደርጎም~ ማስተባበል አለ።
ለዚህ ስራ ስኬት~ ለትግላችን ሲባል
ዓለም አጨብጭቦ~ ኖቤል ሸልሞናል
ስለዚህ...
እንለወጣለን~ ገና ከመሃሉ
ይሄ ሁሉ እያለ~ ለውጥ አታጣጥሉ
ከዚህ በላይ የለም~ ለውጥ የለም አትበሉ
የኋሊትም ቢሆን~ ብዙ ለውጦች አሉ።



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

24 Oct, 14:53


👍Likeም ጠረረ እኛም ቅር አለን እስቲ ደስ ይበለን አንዴ ጠቅ አድርጉልን🗿😇

ገጣሚ ግደላቸው
😎



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

23 Oct, 16:42


​​••●◉ንፋልኝ አለችኝ🙊🙉🙈
    ----------------------------------
ከመሸ ቡሃላ ስልክ 📲 ደውላልኝ
እቤት ማንም የለም ቶሎ ድረስልኝ
         ብላ ነገረችኝ...
በማራኪ ድምጿ እያማለለችኝ
           ታክሲ ተሳፍሬ 🚗
           እንደ ጀት በርሬ 🚀
ከቤቷ ደርሼ ቀና ብዬ ሳያት
በጣም ተኳኩላ እጅጉን አምሮባት
           ፀጉሯን ተተኩሳ
ጭኗን የሚያሳይ አጭር ልብስ ለብሳ
ከንፈሯን በቀለም ቀብታ አለስልሳ
     እጄን ይዛ ገብታ ከመኝታ ቤቷ
     እፍረት ሳይሰማት አርጋኝ ከደረቷ
አጠገቧ አስቀምጣ እየዳበሰችኝ
እባክህን አንዴ ንፋልኝ አለችኝ....
.
.
   በጇ ወደ ዋሽንት እየጠቆመችኝ።
🤣🤣

dirty mind 🙈🙈🤣




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

23 Oct, 15:35


Ethiopian drill music ምትሰሙ ሴቶች ትገርሙኛላችሁ🤩😂

አንጠልጥላቹሀል እንዴ ቆይ😳?



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

22 Oct, 16:30


#የአያቴ_ተረባ🥹 
እኔ ትልልቅ አይን ያላትን ፍቅረኛዬን ላስተዋውቃት ስሄድ
#be_like

Me፦አያቴ ይቺ ፍቅረኛዬ ናት ተዋወቂያት:
አያቴ፦አንተም ደርሰህ ፍቅረኛ አመጣህ? ነይ እስቲ ደግሞ        
        ምንድነው አይኗ? በዚህ አይነትማ የድሮ ታሪኬን  
        ባልነግራትም ታየዋለች ልጄ በናትሽ የምሞትበትን ቀን  
         መቼስ አይተሽዋል ንገሪኝ?💔 
*
*
*
*  ይኸው እኔ ውሀ ሆኛለሁ 😢😢



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

22 Oct, 16:06


ስለሆነው ብቻ ሳይሆን ስላልሆነውም ገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን🙏




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

21 Oct, 18:54


ወንዶች በዳሌ ሴቶችም በመኪና አይጨክኑም😜




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

21 Oct, 17:35


ያበደ LOGO ነው እንዴት አያቹውት ቤተሰብ✌️🎭


የተመቸውም ያልተመቸውም ሪያክት😁👍

@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

21 Oct, 17:11


😊 የኔ ነሽ ❤️‍🔥

የምጠረጥረው ፣ የማልጠረጥረው
ቄስና መነኩሴ፣ ወታደር ደብተራው☹️
ጥራዝ ነጠቅ ሊቁ ፣ ጀዝባውና ፋራው😏
ያም የኔ ነሽ ሲላት ፣
ያም የኔ ነሽ ሲላት ፣😡
ለበለበኝ ፍቅር ፣ አቃጠለኝ ቅናት😤

ወይ ጠንካራ ክንዴ ፣ ጉልበቴ አያስቀራት
እንዴት የብቻዬ ፣ የግሌ ላድርጋት?☹️
ሰው በጠራት ቁጥር ፣ ባልነቴ ሟሟ🥺
የሰማኒያ ሚስቴ ፣ የኔ ነሽ ነው ስሟ።🙄

😁😅
ሼር አደራ🙌 😊የኔ ነሽ❤️‍🔥

​​​​               ᴊᴏɪɴ ᴀɴᴅ sʜᴀʀᴇ
   



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

20 Oct, 17:28


ሳምንቱን በ Emoji
የኔ



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

20 Oct, 16:41


በሔድሽበት ሁሉ ጅብ ይብላሽ አለ አህያ
      ቺኩ ጥላው ስትሄድ😜😁😂

#👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

19 Oct, 17:54


- ወደ ፊት እንዳትጓዝ ወደኋላ የሚጎትቱህን ነገሮች ቆርጠህ ጣላቸው።. ..... እግርህንም ቢሆን💪
*
*
*
*
ወንድ ሁን!!

ሪያክት እንዳይረሳ ይሄ ማሟሟቂያ ነው!!!❤️😁👍




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

19 Oct, 15:58


ዋ ጋዋን Manchester united ✌️✌️🔥💪



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Oct, 17:24


እማ ዋሽተሺኛል😔

የኑሮ ሁኔታ ካቅምሽ በላይ ሆኖ
ህመሙ ጭንቀቱ ሲጽናብሽ ገኖ
በተሰበረ ልብ ካይንሽ ዕንባ ሲፈስ
ማይጠገብ ፊትሽ ባዘን ሲደፈርስ
     
                ምን ሆነሽ ነው ብዬ ያኔ ስጠይቅሽ
                 ጽጕሬን እየዳበሽ እንዲ ነበር መልስሽ
                 ፊቴን ታጥቤ ነው ለምን አለቅሳለው
                 አንተ ካለህልኝ ሁል ጊዜ ስቃለው
 
    ብለሽ ዋሽተሺኛል እኔ እንዳልከፋ እንደዛ በለቅሶ አይንሽ እየጠፋ

ውስጥሽ የተጎዳ ክፉኛ እያመመሽ
ደናነኝ አታስብ እርሳው ትዪኛለሽ
ግን ልጅነት ሆኖ አምንሻለው ቶሎ
ከቅፍሽ ስገባ እጅሽ እንኳን ዝሎ

                 ደግሞም አይቻለው ከሆድሽ አጉድለሽ   
                ጥራጊ ስትበዪ  እኔን ጥግብ አርገሽ
                 ለምንስ ዋሸሺኝ ለምንስ ደበቅሺኝ
                 እንደዛ እየክፋሽ ደስተኛ ነኝ አልሺኝ

እርቦሽ ሳትበዬ አንጀትሽም ታጥፎ
እኔን አብልተሻል ከጥጋብም አልፍ
ከህመምሽ በላይ ሚያሳስብሽ ነገር
ስለኔ ደስታ ነው ሳልከፋ እንድኖር

                     ባይኖርሽ እንኩዋን ከሰው ተበድረሽ
                    አንሼ እንዳልታይ ሁሉን ታደርጊያለሽ
                       እስካለሽ እስካለሁ
                   እምዬ ሁል ጊዜ ደምቄ እታያለሁ
  
               አንቺ እኮነሽ ወዜ😚

ባንቺ ፈገግታ ውስጥ እኔ እንድበራ
ስንት ጊዜ ስቀሻል ሆነሽ በመከራ
ቢከፋሽ ለብቻሽ ደብቀሽ ሸሽገሽ
እማዋሽተሺኛል እያነባሽ ስቀሽ

    
#እናቱን የሚወድ ይሄንን ግጥም ያንብላት 👏
          😉 𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር 🙏
      



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

18 Oct, 14:23


10 ብር የገዛሁት ዳቦ ሻይ ውስጥ ገብቶ ጠፋብኝ 😂😂😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

16 Oct, 18:37


አንድ አንድ ሰዎችን የተከበሩ ስለሆኑ ታከብራቸዋለክ አንድ አንዶቹን ደሞ የተከበርክ ስለሆንክ ታከብራቸዋለክ 🤗


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

16 Oct, 15:51


ኮማች ለዘለዓለም ይኑር!!! ✌️

አሁን ራሱ እኔ እየሳኩ ነው ምልክላችሁ 🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣

የታለ ሪያክት 🤣👍


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

15 Oct, 17:23


ስሚ አንቺ 😎

በቀጠርኩሽ ቦታ በቀጠርኩሽ ሰዓት በይ ቶሎ ድረሺ
አንቺን ያገኘሁሽ እሷን እየጠበኩ መሆኑን አትርሺ

ቀጥሉበት!!!🙌🤣🤣



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

15 Oct, 16:55


​​            💗ፍቅሬን በምን ቋንቋ💗
   
    ለአይኔ እንኳን ለአፍታ እንዳላጣሽ፤
      እፈልግ ነበረ ፍቅሬ እንዲገባሽ።
   ግን እንዴት ልናገር እንዴት ስ ላውራ፤
  ወደ ሌላ እንዳትሄድ እያለ ልቤ ሲፈራ።
     ስሜቱ ከባድ ህመሙ አይቻልም፤
ፍቅርሽ ከብዶኛል ያዢልኝ አልቻልኩም።
   እንዴትስ ልናገር እንዴት ላውጣው፤
     እያሰቃየኝ ነው ፍቅርሽ በእጣው።
   ፍቅር ሠው ይገላል ሲሉ እሰማለሁ፤
  እኔ ግን ስላንቺ ስንቴ ሞቼ ተነስቻለሁ።
           ቃል ሲሰማ ከአንደበትሽ፤
      በውበት ፍክትክት ይላል ፊትሽ።
  በምንስ ልግለፀው ፍቅርሽን በቃላት፤
     እኔ ግን እፈራለሁ አይንሽን ለማየት።

        ሁሌም እወድሻለሁ!
      

@Teddy_yunki19


                
#ሼር አደራ🙏

ግጥም እና ሳቅ 🤣

15 Oct, 15:58


ቤተሰብ ቻናላችን ምንም እያደገ አደለም ምን ይሻላል🥹😭😔



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

14 Oct, 17:34


ፈረስ የሚያስጋልብ ግምባር ይዛ


ላንተ የሚሆን ቦታ የለኝም ስትለኝ በቃ አልቻልኩም🤭🤣



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

14 Oct, 15:01


#ደኛ :- ለምንድነው ፍቺ የፈለከው?


#ከሳሽ ከጫት ቤት ጫት ቤት ከመዞር ሌላ ስራ የላትም!


      
#ዳኛ ምን ልሁን ብላ...?


#ከሳሽ እኔን_ፍለጋ🙄😁😂🤣



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

13 Oct, 17:43


ጨብሰህ መሽናት 50 ብር ያስቀጣል የሚልበት ቦታ እየሸናህ ባለቤቱ መጥቶ 50 ብር ክፈል ሲልህ 100 ትሰጠውና መልስ ሲሰጥህ...! 🤭

ያዘው ላራ ነው  🤒🤧🥴😁



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

13 Oct, 15:41


         🌹 🌹


ለምን ጥለሺኝ እንደሄድሽ አውቃለሁ
ለምን እስካሁን እንደምጠብቅሽ ግን
አልገባኝም።


​​​​               ᴊᴏɪɴ ᴀɴᴅ sʜᴀʀᴇ
             🌹
@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

12 Oct, 18:10


አንዳንዴ ባንክ ውስጥ ያለው 49 ብር ይዤ


ብን ብዬ ከሀገር መጥፋት ያምረኛል🙄😁😂



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

12 Oct, 17:33


ከክላስ ውስጥ መምህር እያስተማረ እንደዚህ ብትስቁ 😂😂😂😂ምን የሚከሰት ይመስላችኋል?

comment ላይ👇👇 እንደዚህ ጮኬ ሪያክትማ አትንሱኝ 😂👍



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Oct, 18:03


እስቲ አንዴ ሳይማሩ ያስተማሩንን መምህሮቻችንን በሪያክት

በዛውም የምትወዱትን መምህር ስም ኮመንት ላይ

😄😁😂😒😘



@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Oct, 16:51


ዛሬ ራሴን ማዳመጥ ሳይሆን ማላመጥ ነው ምፈልገው🫥🫥




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

11 Oct, 16:13


5️⃣k እንግባ እስኪ ቤተሰብ እስቲ በ reaction ሞቅ ሞቅ😍❤️☄️


@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

09 Oct, 16:36


ተቀበይ

ቀድመሽ ከሰጠሽው ካየ ያንን ቦታ:
በቃ ሰርጉን እርሺው ገብቷል ወደ ኮንታ።

እስቲ በሪያክት አናውጡት 👍😁 የሪያክት ዱቤ አይነፋም




@Teddy_yunki19

ግጥም እና ሳቅ 🤣

08 Oct, 18:15


EBS የሚለውን እብስ ብለህ ያነበብከው ልጅ EMS የሚለውን ምን ብለህ እንደምታነበው ሳስብ🤣🤣

#like 👍


@Teddy_yunki19