ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA @felegeqidusan Channel on Telegram

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

@felegeqidusan


የወልቂጤ መንበረ ጵጵስና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ፈለገ ቅዱሳን ሰንበት ት/ቤት የቴሌግራም ቻናል ነው።

የ tiktok ገፅ
https://www.tiktok.com/@felegeqidusan1221?_t=8il96OIiSSD&_r=1

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA (Amharic)

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ በትምህርት እና ታሪኩ አዘጋጅቶ በአማርኛ በአንደኛው ውጤት በተለያዩ ምርጫዎች በአንድ ተከታታይ ስልኩን ይደረጋል። የህዝብ እና የህዝቦች ታሪኮችን ለመማር የፈለገችው እና ቀላል ችግር ይሰማል። በስፖርትን፣ ሳይሆንም ብሔራችንን ስለሚይዘው የትኛውን ፕሮግራም እንደሚከብር በአንድ ተከታታይ ስልኩ እንቀላቀል። በእኛ የሚዳመጥበት በርካታ እና ምንም እንኳን በጣም ምን እንደሆነ ማሻሻል። የቴሌግራም ከነማ አገልግሎት በመጠቀም ወደቴምያም እንዳትረክሱ መደብ ማስተማር ከቻሉ የሚሆነውን እና ለጊዜ የተለያዩ ዜናዎችን በቴሌግራም እንማማን።

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

08 Feb, 08:01


ጾም ለምሕረት አውደርዕይ

ከየካቲት 3-5

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

06 Feb, 09:41


ጾም ለምሕረት አውደርዕይ

ከየካቲት 3-5

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

03 Feb, 15:00


http://t.me/QuizBot?start=zMtQYBVx

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

01 Feb, 09:58


"ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም"  ማር 10:8
+++++++++++++++++++++++++++++

ነገ ቅዱስ ጋብቻችሁን በሥርዓተ ተክሊል የምትፈጽመው የደብራችን አገልጋይ ዲያቆን ቦጋለ ወርቁ እና ወ/ት ምህረት ፍቃዱ የምትፈጽሙትን ጋብቻ የአብርሃም እና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፤ ይቀድስላችሁ።
አባታችሁ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በሕይወታችኹ ሞገስ እንዲሆናችሁ፤ እንዲሁም በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ በፈለገ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ስም መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

      መልካም ጋብቻ!

“ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል።”
   ምሳሌ 18፥22

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

01 Feb, 08:51


ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት
+++++++++++++++++++++++++++


ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና  ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሥርዐተ ቤተክርስቲያን ጋብቻችሁን የምትፈጽሙ የሰንበት ት/ቤትታችን አገልጋይ ዲያቆን ካሳሁን ግዛው ( ገብረ ዮሐንስ ) ከእህታችን ፀጋነሽ ውድማ ( ፍቅርተ ማርያም ) ጋር የምትፈጽሙት  ጋብቻ የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ሚካኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡

መልካም ጋብቻ!!

" ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "
                          መጽሐፈ ዲድስቅልያ

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

31 Jan, 04:41


መንፈሳዊ ፊልም
ዛሬ 11:00 ሰዓት
23/05/2017ዓ/ም

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

29 Jan, 18:16


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍት በዓል (አስተርዕዮ ማርያም ) በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ።
++++++++++++++++++++++++++

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍት በዓል የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ፣ የሃገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣ ከመንበረ ፖትርያርክ ተጋብዘው የመጡ መምህራን  ፣ እንዲሁም በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ተከበረ።

የማኅሌቱ አገልግሎት ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ  በሊቃውንት አባቶቻችን  እየተመራ እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ከቀጠለ በኃላ ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በግንባታ ላይ ወዳለው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን አምርተዋል ።

በመጨረሻም በሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ያሬዳዊ ዝማሬ (ወረብ) ፣ አዲስ ስለሚገነባው ህንጻ ቤተክርስቲያን አመታዊ ሪፖርት በህንጻ ኮሚቴ በኩል ሰፊ ማብራሪያ ፣ በብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ እለቱን የሚያብራራ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቶ ታቦታቱ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

29 Jan, 04:52


" እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፣ አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፣ ንዌድሰኪ ድንግል  ምክሐ ዘመድነ፣ ዮም በፍስሓ ለማርያም እምነ፣ አስተርእዮ በሰማይ  ኮነ
       👇ትርጉም
"የትንቢት አበባ እግዚአብሔር የእኛ ሥጋ የሆነውን የአንቺን ሥጋ ለብሶ በምድር እንደ ተገለጠ ለእኛም እንደ ታወቀ፤ ድንግል ሆይ የወገናችን መመኪያ ዛሬ ለእናታችን ለማርያም በሰማይ ፍጹም በደስታ መገለጥ ሆነ እያልን እናመሰግንሻለን" ብሏል። ስለዚህ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት አስተርእዮ ማርያም እየተባለ ይከበራል።
በሰማይ ለቅዱሳን ሁሉ የተገለጠችበት ነውና።

፪ኛ, ዘመነ አስተርእዮ ተብሎ በሚታወቀው የጌታችን መገለጥ በሚነገርበት ወር ውስጥ በዓለ ዕረፍቷ ስለሚከበር ነው።
"ወአስተርአየ ወልደ እግዚአብሔር ከመ ይስአር ግብሮ ለጋኔን = የዲያብሎስን/የጋኔንን ሥራ ያፈርስ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" እንዲል (፩ዮሐ፫፥፱/3፥9)

             
🤲የእመቤታችን ምልጃና ጸሎቷ አይለየን!

ምንጭ 👉መምህር ዳንኤል አለባቸው
https://t.me/FELEGEQIDUSAN

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

29 Jan, 04:52


#ሞትና_እመቤታችን

#አስተርእዮ_ማርያም

🤲ያንብቡ ያስነብቡ

፩ኛ. የሕሊና ሞት፦
     "ወይቤሎ ካልእ እምአርዳኢሁ እግዚኦ አብሐኒ እቅድም ሐዊረ ወእቅብሮ ለአቡየ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ አንተሰ ትልወኒ ወሕድጎሙ ለሙታን ይቅብሩ ምውታኒሆሙ "ትርጉም" ከደቀመዛሙርቱ አንዱ አቤቱ አስቀድሜ ሂጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ/አሰናብተኝ" ባለው ጊዜ "ጌታችንም መልሶ ሙታንን ሙታን ይቀብሯቸው ዘንድ ተዋቸው አንተ ግን ተከተለኝ" ብሎታል።" ሙታንን ሙታን ይቀብሯቸው ዘንድ" ማለት " ሙታነ ሥጋ ዘመዶችህን ተዋቸው ሙታነ ሕሊና ዘመዶቻቸው ይቅበሯቸው" ማለት ነው።(ማቴ፰፥፳፩/8፥21)

፪ኛ. የሥጋ ሞት፦
    የሥጋ ሞት የምንለው የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው ማንኛውም ሰው ጻድቅም ይሁን ኃጥእ ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ ሞተ ይባላል። ይህ በቅዱስ መጽሐፍም ሆነ በሰው ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ጥቅስ አያስፈልገውም።
“ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።” እንዲል (ዘፍጥ፵፱፥፴፫/49፥33)

፫ኛ. የነፍስ ሞት ነው
  የነፍስ ሞት  የሚባለው ቀድሞ በሕይወተ ሥጋ ሳለ ሕሊናው ሞቶበት በክርስቶስ ሳያምን ሳይጠመቅ በጥቅሉ ትእዛዛተ እግዚአብሔርን ሳይፈጽም ኑሮ በሥጋ ሲሞት የነፍስ ሞትም ይሞታል። " ብፁዕ ወቅዱስ ውእቱ ዘረከበ ክፍለ በትንሣኤ እንተ ትቀድም መጺአ እስመ አልቦ እንከ ዳግመ ሥልጣነ ሞት ላዕሌሁ= መጀመሪያ በምትሆነው ትንሣኤ እድል ፈንታ ያገኘ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፤ የሁለተኛው ሞት ሥልጣን በእርሱ ላይ የለበትምና"(ራዕ፳፥፮/ 20፥6)እንዲል።
✔️የመጀመሪያው ትንሣኤ የተባለው ትንሣኤ ልቡና /ትንሣኤ ሕሊና ነው። ሕሊናው ተነሥቶለት በእግዚአብሔር አንድነት ሦስትነት አምኖ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአስተማረችው ትምህርት ጸንቶ ከኖረ  ሁለተኛው ሞት የተባለው የነፍስ ሞት አያገኘውም ማለት ነው።

          #የእመቤታችን_ሞት
     👉 ታዲያ የሞት አይነት እኒህ ከሆኑ እመቤታችን የሞተችው ሞት የትኛውን ሞት ነው? ቢባል መልሱ የሥጋ ሞት ነው።
እመቤታችን በሕሊናዋም/በሐሳቧም በሥጋዋም ንጽሕት ቅድስት ድንግል ናት።
ሰሎሞን በመሐልይ መጽሐፉ "ኵለንታኪ ሠናይት እንተ ኃቤየ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ-  ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው አደፍ ጉድፍ ፣ ነውር ነቀፋ ምንም ምን የለብሽም"(መሐ፬፥፯/ 4፥7) እንዳለ ከኃጢአት ማለትም የነፍስ ሞትን ከሚያመጣው ከጥንተ አብሶ ጀምሮ ማንኛውም ኃጢአት ስለሌለባት ፣በውስጥ በአፍኣ ፣ በነፍስ በሥጋ ሁለንተናዋ ንጹሕ ስለሆነ አንድያ ልጇ በለበሰው ሥጋ ሞትን እንደቀመሰ እሷም ሞትን ቀምሳለች።
"እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኵሉ አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ"      
         ትርጉም👇
"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈራጅነቱ እንደማያዳላ ይህንን ዕወቁ፤ ምክንያቱም የእርሱ እና የዓለሙ ሁሉ እናት እመቤታችን ሞትን ትቀምስ ዘንድ በእውነተኛ ቃሉ አዘዘ" እንዲል (ቅዱስ ያሬድ) 
እመቤታችን ምንም አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችና ኃሊበ ድንግልናን እያጠባች ያሳደገች ብትሆንም ሞትን እንድትቀምስ ጌታችን አዝዟል ።
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዓፅብ ለኵሉ= ሞትስ ለሟች ሰው ይገባል፤ (ሞት የኃጢአት ውጤት ነውና)። የእመቤታችን ሞት ግን ለሁሉ ያስደንቃል"(ምክንያቱም ኃጢአት የለባትምና)እንዳለ ደራሲ። ጌታችንም  ያደላ ዘንድ ሰው አይደለምና ቅድስት እናቱ ሞትን እንድትቀምስ አዘዘ።

👉ደግሞም ስንኳን የእመቤታችን ሞት የሌሎችም ጻድቃን ሞታቸው ሕይወታቸው ነው ምክንያቱም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም መሸጋገሪያ ድልድይ ነው ሞት።
የጻድቃን ሞት ሕይወት እንደሆነ ሲገልጥ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ብሏል።
"ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ - የጻድቃን ሞታቸው ሕይወታቸው ነው" (ድጓ)ብሏል። ✔️በመዋስዕት መጽሐፉም እንዲህ ብሏል።
"ጻድቃንሰ ኢሞቱ ኀበ እግዚኦሙ ነገዱ በመንግሥተ ሰማያት ይሁቦሙ ዘፈቀዱ - ወደ ጌታቸው ሄዱ እንጂ ጻድቃንስ አልሞቱም በመንግሥተ ሰማያትም የወደዱትን ይሰጣቸዋል"ይላል።
✔️ተወዳጁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም "ልሄድ ከክርስቶስም  ጋር ልኖር እናፍቃለሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና" እንዲል (ፊልጵ፩፥፳፫/1፥23)ስንኳን እመቤታችን ሞት።

👉ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ጥር ፳፩ ቀን በዓለ ዕረፍቷን በማኅሌት ፣ በቅዳሴና ወንጌልን ለምእመናን በመንገር የዕረፍቷን ነገር ከነገረ ማርያም አምጥቶ ከወንጌል ጋር አዋሕዶ በመስበክ ታቦት በማውጣት በደመቀ መልኩ ታከብራለች እናከብራለን!

          #አስተርእዮ_ማርያም
👉የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት ለምን "አስተርእዮ ማርያም = የማርያም መገለጥ" እየተባለ ይጠራል ቢባል
  👇ሁለት ምክንያቶች ማየት እንችላለን።
፩ኛ, ሰው ከሞተ መቀበር ልማድ ነውና ሐዋርያት የእመቤታችንን አስከሬን እንቀብራለን ብለው በአጎበር (በአልጋ)  አድርገው ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና " ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ያውኩናል ደግሞ እሷን ተነሣች ዐረገች ሊሉን አይደለም ብለው ኑ በእሳት እናቃጥላት ብለው ሄዱ።

(((እመቤታችን ግን እነርሱ እንዳትነሳ ፈልገው እናቅጥላት ቢሉም  እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሥታለች " ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ =አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ( ፻፴፩ ፥ ፰/132፥8) እንዲል። "የመቅደስህ ታቦት"የተባለች እመቤታችን ናት። አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም " ወምስሌሆሙ ታቦት ዘዶር እንተ ይእቲ እግዝእትነ ማርያም = ከእነሱም ጋር ታቦት ዘዶር ካለችበት ያግባችሁ ይህችውም እመቤታችን ማርያም ናት" ብሎ እንደነገረን)))

✔️ታውፋንያ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ተራምዶ የአልጋውን ሸንኮር እይዛለሁ ሲል መልአኩ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው።
እጆቹም ተንጠልጥለው ቀሩ እርሱም ተቅለበለበ እመቤቴ ይቅር በይኝ እያለ ያለቅስ ይለምን ጀመር። በዚህ ጊዜ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ርኅራኄ ልማዷ የሆነች እመቤታችን አፈፍ ብላ ተነሥታ ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲፈውሰው ነግራው ተመልሳ አረፈች።
ቅዱስ ጴጥሮስም የተቆረጡት እጆቹን አስጠግቶ ቢጸልይለት እንደቀድሞው ሁኖለታል ከዚህ በኋላ ያ ታውፋንያ የተባለ አይሁዳዊ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የእመቤታችንንም አማላጅነት ሲመሰክር ኖሯል።
  (ነገረ ማርያምና ተአምረ ማርያም ይመልከቱ)
✔️ያን ጊዜ መልአኩ  እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯታል። ዮሐንስም በተመሥጦ እየሄደ ሥጋዋን ያጥን ነበር።

ያን ጊዜ በገነት ላሉ 
#አበው ለእነ አብርሃም ፣ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ለሌሎችም አበው፣ 
ለነቢያት ለሐዋርያት፣
ለጻድቃን ለሰማዕታት ፣
ለደናግል ለመነኮሳት ፣
ለካህናት ለሊቃነ ካህናት
ለምዕመናን ሁሉ
እንዲሁም
ለመላእክት
በሰማይና በምድር የተሰጣት ጸጋና ክብር የተገለጠበትና ክብሯ ልዕልናዋ ስለተገለጠላቸው በገነት ተሰብስበው ያመሰገኑበት ዕለት በመሆኑ
"አስተርእዮ ማርያም - የማርያም መገለጥ " ተባለ።

✔️ይህንንም ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/ አባ ጽጌ ብርሃን በማኅሌተ ጽጌ መጽሐፉ እንዲህ ብሎ ገልጦታል።

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

28 Jan, 15:44


መንፈሳዊ ፊልም
አርብ 11:00 ሰዓት
23/05/2017ዓ/ም

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

28 Jan, 07:29


🎯 ጉባኤ አዳም

ሐሙስ 11:30 ጀምሮ

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

27 Jan, 19:35


“ኑ ለነገው ትውልድ መጽሐፍ እናበርክት”
የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ መርሀግብር

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከጥር 20 ጀምሮ  የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ መርሀግብር አዘጋጅቶ መጽሐፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

የአስተርእዮ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከዋዜማው ጀምሮ  ታላቅ ጉባኤ ተዘጋጅቶ እና የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ  ተዘጋጅቶ እናንተን ይጠብቃል በዕለቱም ተገኝተው መንፈሳዊ በረከትን ይሸምቱ እያልን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱም ስትመጡ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ይጠቅማል ምትሉትን መጽሐፍ እድታበረክቱ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን  ።

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

26 Jan, 14:29


''ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ''

ታላቅ በዓለ ንግስ

በወልቂጤ መንበረ ጵጵስና ደብረ ጽዮን ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ቤ/ን

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

24 Jan, 17:39


<<አስተርዕዮ እና የወልቂጤዋ ማርያም >>

በጉራጌ ሀገረስብከት ስር ከሚገኙ ጥንታዊ እና አንጋፋ ደብራት መሀከል የምትመደበው ይህች ባለ ታሪክ ደብር ስሟ ከአስተርዕዮ ጋር ተሳስሮ መቶ አመታትን ተሻግሯል ።

በደብሩ ከሚነግሱ አበይት በዓላት መካከል ጥር 21 የሚታሰበው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም መታሰብያ ዋነኛው ሲሆን ከቃና ዘገሊላ ጀምሮ ዝግጅት ከደብሩ አልፎ በመንደሩ ይጀመራል ።

ሙሉ የሰፈሩም ሰው እንደየ አቅሙ ቤት ባፈራው ከተለያዩ ቦታዎች ለሚመጡ እንግዶቹ ጸበል ጻድቅ አዘጋጅቶ በሩን ከፍቶ ይጠብቃል።

እንደ ጥምቀት በዓል አረጋውያን እናቶች <ማርያም ኤቦ> <ኤቦ ንገሽ > እያሉ ከ ዋዜማው መጠናቀቅ በኃላ እስከ ማኅሌቱ ጅማሮ ድረስ ሲዘምሩ ይቆያሉ

ይህ የበዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቶ አሁን ያለውም ትውልድ (ሰበካ-ጉባኤ፣ ቀሳውስት ፣ዲያቆናት ፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ) ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ነው ።


እናንተም በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንድትሳተፉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን !

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

18 Jan, 16:52


የከተራ እና ጥምቀት በዓላት ወልቂጤ

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

18 Jan, 07:21


የጥምቀት በዓል ስናከብር ፍቅር ፣ አብሮነትና መቻቻልን በማጎልበት ሊሆን እንደሚገባ የጉራጌ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ አቡነ መልከጼዴቅ ገለጹ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ከፊታችን የሚከበሩ የከተራና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ በድምቀት ከምታከብራቸው በዓላት ውስጥ በየዓመቱ ጥር 11 ቀን የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት አንዱ ነው።

መላው የሰው ልጅ በሙሉ የእዳ ደብዳቤው ተቀዶለት ነጻ የወጣበትና ሚስጢር የተገለጸበት እለት መሆኑን ተናግረዋል።

የጥምቀት በዓል አምላካችን ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳየበት ሲሆን እኛም ከክርስቶስ በተማርነው መሰረት በፍቅር በሰላም እና በአብሮነት ልንኖር ይገባል።

ብጹእ አቡነ መልከ ጼዲቅ አክለውም ምእመናኑም ተንኮል፣ቂም በቀል፣ዘረኝነት ጸብንና ክፉ ስራዎችን በመተው ለጽድቅ ስራ የበለጠ መትጋት እንዳለባቸው መክረዋል።

በዓሉን ስናከብር የተጣላውን በማስታረቅ የተለያየው አንድ በማድረግ፣አብሮ በመጸለይ፣ በመዘመር ፣አብሮ በመብላትና በመጠጣት ፣ድሆችን በመመገብ ሌሎች ወደ ጽድቅ መንገድ ሊወስዱ የሚችሉ ስራዎች በመስራት ፈጣሪያችንን ልናስደስት ያስፈልጋል።

በዓሉን ስናከብር እግዚአብሔር በመፍራትና መልካም እሴቶቻችን በማጎልበት መሆን አለበት ብለዋል።

ይህ በዓል ያለ እምነት ልዩነት ክርስቲያኑና ሙስሊሙ ተባብረው በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በማድረግ አብሮነታቸው የሚያሳዩበት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ አንድነታቸውን የሚያስመሰክሩበት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ለአብነትም ለበዓሉ ድምቀት በሰላምና ጸጥታ፣በጽዳት እና ሌሎች በርካታ ስራዎች በጋራ እንደሚያከናውኑ አስታውሰው ይህንን የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሀይማኖቱ የማይፈቀድው እና ስርዓቱን ከሚያበላሹ አላስፈላጊ ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባ ብጹእ አቡነ መልከ ጼዲቅ ገልጸዋል።

በዓሉ ሀይማኖታዊም ብሄራዊ ከመሆኑ በተጨማሪ አለም አቀፋዊ ቅርስ በመሆኑ ይህንን ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አባታዊ መልእክታቸው አስተላልፏል።

በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የደስታ ፣የመቻቻል እንዲሆንም ተመኝተዋል።

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

17 Jan, 20:55


የከተራ እና ጥምቀት በዓላት ወልቂጤ 2016 ዓ.ም ትዝታዎች ከፎቶ ማህደራችን

ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ/FELEGE KIDUSAN MEDIA

17 Jan, 20:55


የከተራ እና ጥምቀት በዓላት ወልቂጤ 2016 ዓ.ም ትዝታዎች ከፎቶ ማህደራችን

1,034

subscribers

3,230

photos

26

videos