በናሳ ማርስ ኦርቢተር ካሜራ የተቀረፀው ምስል ‘ቀይዋ ፕላኔት’ በመባል በምትታወቀው ማርስ ላይ ህይወት ሰለመኖሩ አመላካች ነው እየተባለ ነው።
በማርስ ላይ የተገኘው 235 ካሬ ሜትር የሚሆን ስፋት ያለው ምንነቱ ያልታወቀው አካል ባለ አራት ማዕዘን ቅርጽ እንዳለው ከተነሳው ፎቶ ለማዬት ተችሏል።
ሆኖም ምስሉ በባለሙያዎች ሳይንሳዊ ማብራሪያን ባይሰጥበትም ብዙዎች የአልታወቁ በራሪ አካላት (ዩኤፍኦ) ስለመኖራቸው አመላካች ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
ምስሉ በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ሲሆን የብዙ ሰዎችን ቀልብ ስቧል። ታዋቂው የፖድካስት አዘጋጅ እና ኮሜዲያን ጆው ሮውገን በኤክስ ገጹ ምስሉን ‘እንግዳ ነገር’ ከሚል ጽሁፍ ጋር አጋርቶት የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል።
አሜሪካዊው ባለሃብት ኤለን መስክ ጉዳዩን የሚመረምሩ ጠፈርተኞች መላክ ይገባናል ሲል ለጆው በኤክስ ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል በማርስ ላይ እንዲህ አይነት ቅርስ መገኘቱ ምንም አዲስ ነገር አይደለም፣ ምናልባትም በንፋስ እና በአፈር መሸርሸር የተፈጠረ ሊሆን ይችላል የሚሉ ወገኖችም መኖራቸውን ሜይል ኦንላይን አስነብቧል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!