የሀገሬ ወጎች @ye_hagere_wegoch Channel on Telegram

የሀገሬ ወጎች

@ye_hagere_wegoch


2017 ዓ.ም!

DM💼 @ermias_ks

የሀገሬ ወጎች (Amharic)

የሀገሬ ወጎች በ2017 ዓ.ም በተለያዩ ምሽት አዳዲስ ነገሮችን እና መረጃዎችን በአሜሪካውያን አለይለይ ስሜት ውስጥ እንደመለሰ የአሜሪካውያንን ባህል ስለ ሀገር አንድ ለእንግዳ ፔጅ ይሆንናል። የሀገሬ ወጎች ለሀገር የሚገኘው እሳት ለመስራት ነባር እና ውሰድ ለሳቋም የሚምላሽ ቀስት ነው። ለሀገር ለድምፅ ይገኛል ስለሚል ጥያቄ ለማስፈራረም ከባህል የተገኘ ፍላጎታ አለው። ይሁንና ለሀገር መግቢያ እስከሚመለሰው ሰዓት ያልተለመደ ሰው በሳንክ ስለምናናውን ጭዋን ዲናል እንቀናቀናለን።

የሀገሬ ወጎች

11 Jan, 06:17


እግር ኳስ እና ጦርነት! የሞሶሎኒ የልጅ ልጅ ሜዳ ወስጥ ያሳየው ተግባር እና የ አደንዛዥ እፁ ኤስኮባር እና ማራዶና ተግባር በዩቱብ ቻናላችን ይመልከቱ ያዳምጡ👇👇👇👇

https://youtube.com/watch?v=pyl5vj58yfs&si=udI1wOWQJLELD_xC

የሀገሬ ወጎች

09 Jan, 21:09


‹‹ሰባተኛ….በል    እኔም አሁን ወደዛ እየሄድኩ ነው፡፡ ሰባተኛ ያለውን ሰው ቶሎ መርካቶ ወደ ሱማሌ ተራ እንዲንቀሳቀስ አሁኑኑ ንገረው..ንግድ ባንክ ብር እያወጣች መሆኑን አውቀናል ..በነፍስ ነው የምትፈለገው ..በነፍስ…ይሄንን ለሁሉም ንገራቸው…እና አንተም ወደእዛው ተንቀሳቀስ መጣሁ››ስልኩን ዘጋው
‹‹ልሄድ ነው…››
‹‹ሂድ ፍጠኑ.. የደረስክበትን ነገር በየጊዜው አሳውቀኝ››አለው ፕሮፌሰሩ ስለእሷ አንድ ነገር በመስማቱ የተወሰነ ተስፋ በፊቱ ላይ እየታየ፡፡
‹‹እሺ በቃ ሄድኩ….››እየነጠረ በችኮላ ወጥቶ ሄደ፡፡
ሼኩ ‹‹አሁን ፈራሁ››አሉ..በቀሙበት ከዘራቸውን ተደግፈው እየተከዙ
‹‹ምነው ሼኪ እንደውም የሆነ ቦታ መታየቷ እኮ አሪፍ ነገር ነው››አቶ ሙሉ ነው ተናጋሪው
‹‹አይ አይደለም….5.5 ሚሊዬነ ብር ለምን በአንዴ ልታወጣ ቻለች..?ምን አስባ  ነው….?ከሀገር ልትወጣ…?እኛን የሚያስወግድ ነፍሰ ገዳይ ልትቀጥርበት..?በእኛ ላይ ምርምር ለሚከፍት የህግ ሰው ጉቦ ለመስጠት ?ብዙ ብዙ ነገር ያሳስባል፡፡››
ፕሮፌሰሩም ‹‹እሱስ እውነቶትን ነው ያሳስባል…››አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለ..
‹‹እሺ ጠበቃው ምን ላይ ደረስክ?››
‹‹ዳኛውን ለማሳመን እየሞከርኩ ነው››
‹‹ለመሞከር እኮ አይደለም ያንን ረብጣ ብር የተፃፈበትን ቼክ እስይዤ የላኩህ..አንተ ስትንቀረፈፍ እሷ አንተን መግዛት የሚችል ብር ከባንክ ደብተሯ ማውጣቷን አሁን ከባንክ ሪፖርት ደርሶናል…..ዛሬ እገዳውን ሳትጨርስ ወደመኝታህ እንዳትሄድ..በኤልያስ ግድያ ላይ ቀጥታ እጇ እንዳለበት የሰጠውህን መራጃ ተጠቀምበት…እና ጭንቅላትህንም አሰራው…ቸው››ጆሮው ላይ ዘጋበት፡፡
በሉ  ሁላችሁም ወደመቀመጫችሁ ተመለሱና ስለቀረው ነገር እንነጋገር››አለ ፕሮፌሰር ቀድሞ ወደለቀቀው ወንበር ሄዶ በመቀመጥ
ሁለቱም ወደለቀቁት መቀመጫቸው ተመለሱና ቁጭ አሉ..ሴኪው የመናገሩን ቅድሚያ ወሰዱ፡፡‹‹አሁን ስልክ ስታወራ ትዝ አለኝ የኤልያስን ጉዳይ እንዴት አደረጋችው፡፡
‹‹አልቋል..አስተካክዬዋለሁ››አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ፡፡
‹‹ሆስፒታል መግባቱን እንደሳማ  ለሊቱን 10 ሰዓት አካባቢ ነበር ሆስፒታል የሄደው..ሲደርስ ዶክተሮቹ ቀዶ ጥገናውን በስኬት አጠናቀው ውስጡ ተቀርቅሮ የቀረውን ሁለት ጥይት አውጥተውለት ጨርሰው ነበር…ልክ ሲደርስ የኤልያስ ሚስትም ሆነች ሁለት ልጆለት  እላዩ ላይ ተጠምጥመው እያለቀሱ …አባታቸውን እንዲያድንላቸውና ገዳዩንም እንዲያዝ እንዲያደርግ ተማፀኑት ..እሱም ጥልቅ ሀዘኑን በከፍተኛ የትወና ብቃት እያሳየቸው ቃል ገባላቸውና ገብቶ ሁኔታውን አየው…ከዛ ወደቢሮው ተመለሰና ከተሰካለት መድሀኒት ጋር የሚቃላቀል ገዳይ ግን ስውር መድሀኒት አዘጋጅቶ ተመለሰ…ቼክ እንደሚያደርገው ማንኛውም የሚመለከተው ዶክተር በቀላሉ ገባና ቀላቀለው….ከዛ ሚስቱን ሆነ ልጆቹን አረጋግቶና አፅናነቶ ..ችግር ካለ እንዲደውሉለት እሱ ግን እስከዛ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ስለገዳዩ ማንነት ከፖሊሶች ጋር መነጋር እንዳለበት አብራርቶላቸው  ሹልክ ብሎ የሆስፒታሉን ቅጥር ጊቢ ለቆ ዶክተር ሰጵራን ወደመከታተል ስራው ተመለሰ…
እንደነገራቸውም ከሁለት ሰዓት ቡኃላ ደወሉለት…‹‹ባለቤቴን ሰረቁኝ….ኤልያስ ሞተ..››ብላ ከታላቅ ሲቃ ጋር ደውላ መሞቱን ያረዳችው  ሚስቱ ነበረች፡፡
እንደሚሞት እርግጠኛ ቢሆንም መሞቱን በሰማበት ሰከንድ ግን ክፉኛ ደንግጦ ነበር፡፡ፕሮፌሰሩ የሰው ልጅ ነፍስ አቅዶና አስቦ ሲያጠፋ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኙ አይደለም…ግን ደግሞ በኤልያስ ልክ ቅርቡ የሆነን ጓደኛውን ገድሎ ግን አያውቅም..እና ልቡ ላይ ጨለማ ቋጥኝ ሲከመር ታውቆታል…በቀጣይ ደግሞ የገዛ እጮኛውን ሲጨምርበት ከዚህን ቡኃላ ህልሙ እንደሆረር ፊልም ስቃይ የተሞላ እንደሚሆን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆነ…..‹‹አዎ በቀሪ ህይወቴ  ሙሉ ዋጋ እከፍልበታለሁ..ቢሆንም ምርጫ አልነበረኝም››ብሎ ነበር  እራሱን ያፅናናው፡፡
‹‹ፕሮፌሰር››ሼኪው ናቸው ከሀሳቡ ያባነኑት፡፡
‹‹ከሞተ ታዲያ ይሄን ያህል ምን ሀሳብ ውስጥ ሰነቀረህ?››
‹‹አይ እንዲሁ ነው….ያው ምንም ቢሆን ጓደኛዬ አልበረ››
‹‹እንግዲህ ቻለው ..እኛም እንችለዋለን..ግን በእቤቱ ዙሪያ በጣም ንቁ ሰው መመደብ አለብህ?››
‹‹ለምን?››
‹‹እንዴ …እጃችን እስካልገባች ድረስ እኮ ምን እንደምታደርግ መገመት አይቻልም..ሄዳ አንዳቸውን አግኝታ የሆነ ነገር ብትላቸውስ ጥርጣሬ ላይ ወድቀው የሆነ ነገር ማዛባታቸው ይቀራል?››
‹‹አዎ ነገሮች በዙብኝ መሰለኝ ይህንን ፈፅሞ አላሰብኩበትም ነበር..አሁን መድባለሁ››
‹‹አቶ ሙሉ ቀጠለ….‹‹ቆይ በስልክ ደውላ ብትነግራቸውስ…?››
‹‹አይ እንደዛ የምትሞክር አይመስለኝም….እኛ ያለችበትን አካባቢ በስልኳ አማካይነት ለማግኘት እንደምንሞክር ስለምታውቅ ፈፅሞ አትከፍተውም..››ፕሮፌሰር ግምቱን ተናገረ፡፡
‹‹ለማንኛውም አዋጩ ዘዴ መከላከል የምንችለውን አደጋ ሁሉ በሙሉ አቅማችን እየተከላከልን..እሷን ደግሞ ብዙ ጉዳት ሳታደርስ አግኝቶ መጨፍለቅ ነው››ሼኪው ናቸው ተናጋሪው፡፡
‹‹ትክክል ብለዋል..አሁን እዚህ ላይ ይብቃን …መሰራት ያለባቸው ብዙ ጉዳዬች ስላሉ እንንቀሳቀስ››
‹‹እሺ››
ተስማሙና ተያይዘው ወጡ
..

ለአስተያየትዎ @Tsiyon_awit አድርሱን!

ይቀጥላል......

የሀገሬ ወጎች

09 Jan, 21:09


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ ስድስት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

የዳይመንድ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል ከፍተኛ  ባለአክሲዬኖች ሼክ ጠሀ ቤት  በሚገኝ ምድር ቤት ውስጥ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አራት ሰዎች ናቸው፡፡ፓሮፌሰር ይሳሀቅ፤አቶ ሙሉ እና ሼክ ጠሀ ሲሆኑ በተጨማሪ የጋንግስተሮች ዋና ሀላፊ ዶዬ የሚባለው ወጠምሻ ተገኝቶል፡፡
አራቱ ሰዎች ጠረጵዛውን ከበው ተቀምጠዋል፡፡ፕሮፌሰሩ ስብሰባውን አጠር ባለ ንግግር ከፈተ …..እንግዲህ ለምን እንደተገናኘን ከመካከላችን የማያውቅ ሰው አለ ብዬ አላስብም ፡፡ካለም ያው ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጧል ማለት ነው፡፡
አሁን ዶክተሯ ተገኝታ አፎን እንድትዘጋ እሰከልተደረገች ድረስ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነን….ሴትዬዋ ለሆነ ከእኛ ሰርክል ውጭ ላለ አንድ አካል የምታውቀውን ነገር ተናገረች ማለት የወንጀሉ አይነት ሆነ በወንጀሉ የተጨመላለቁት ሰዎች ብዛት ተግተልትሎ የሚያልቅ አይሆንም….እንደው እሷ ባትናገር እንኳን አሁን የተፈጠረውን ነገር ከእኛ ጋር የሚሰሩት ትላልቆቹ ባለስልጣን ጆሮ ቢደርስ ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ቅድመው ሊያጠፉን ይችላሉ…
‹‹እና ምን እንዳርግ?፡፡››ሼኪው በለዘብተኛ ንግግር ጠየቁ
‹‹አቶ ሙሉ በከፍተኛ ብስጭት እድል እስኪሰጠው እንኳን ሳይጠብቅ መናገር ጀመረ…‹‹ይህ ግልፅ ነው…ያለ የሌለ አቅማችንን አሞጠን እሷን አግኝቶ ማስወገድ ነው ከዚህ መአት መውጫ ብቻኛ መንገዳችን፡፡..ጠቅላላ አዲስ አበባን በርብረን መፈለግ አለብን ;;በየወሩ በመቶ ሺ ብሮች ወደካዝናቸው የሚከቱት እነ ዶዬ ይሄንን ማድረግ ካቃተቸው ጥቅማቸው ምንድነው….?ደግሞ ከሀገር እንዳትወጣ አየር መንገድ አካባቢም ክትትል ማድረግ አለብን…ዘመዶችም ክፍለ ሀገር ካሏት ከውስጥ አዋቂ ጠይቀን ልትሄድ ትችላለች በተባለ ከተማ ወይም መንደር ክትትል ማድረግ አለብን፡፡..ጨርሼያለው››
ፕሮፌሰሩ ተቀብሎት መናገር ጀመረ..‹‹አቶ ሙሉ  አሁን የተናገርከው ሁሉ እያደረግን ያለነው  ነገር ነው…..እና ደግሞ ስትናገር እንደወንድ በቀጥታ ብታደርገውና አሽሙር ባትቀላለቅልበት ጥሩ ነው….ውስጥ አዋቂ ማለት ምን ለማለት ነው? እኔን ለመንካት ነው?ደግሞ አሁን የተገናኘነው አዲስና  የተለየ ሀሳቦችን ለመስማት ነው…ለምሳሌ ሴትዬዋ ከእጃችን አምልጣ እሷን ማሳደድ ከጀመርን ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ እስከ አሁን ….አሁን ስንት ሰዓት ነው?እጁ ላይ ከሰረው ሰዓቱ ሰዓት  አየና ‹‹አምስት ሰዓት..እስከአሁን ቢያንስ ከሶስትና ከአራት ሰዎች ጋር ተገናኝታ ሚስጥራችንንም ተናግራ ሊሆን ይችላል እና የሚያበሳቸው ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ ባገኘናት ቦታ ደፍተናት ዞር ማለት አንችልም …››
‹‹ለምን?›› አሉ አዛውንቱ ሼክ ጠሀ ……ጭል ጭል በምትል አይናቸው በትዝብትና በጥርጣሬ አጨንቁረው እያዩ
‹‹አሁን የምንችለው እንዳገኘናት ከእነ ህይወቷ አፍነናት ወደሰዋራ ማቆያ ቦታ መውሰድ ነው፡፡ ከዛ ቡኃላ…ከማን ጋር እንደተገናኘች ..?ምን መረጃ  እጆ ላይ እንደለ ካጣራን ቡኃላ ነው እርምጃ መውሰድ ምንችለው››
‹‹እሺ ብላ ትነግረናለች?››
‹‹እሷ ትገኝ እንጂ እሱ የእነዶዬ  ስራ ነው..ከፈለጉ ገርፈው ከለበለዛም ሰውነቷን እየቆራረጡ በአእምሮዋ የሰወረችውንም ሆነ በሆዶ የቀበረችውን የምታውቀውን ሚስጥር ሁሉ እንድትናዘዝ ማድረግ አለባቸው ››
‹‹እሱ አያሳስባችሁ….እኔ እራሴ አናዝዛታለሁ….አስር ደቂቃም እትቋቋመኝም››በልበ መሉነት ማረጋገጫ ሰጠ፡፡
‹‹ግን በእውነት ልታገባት የወሰንካት ፍቅረኛህ ነበረች?›ገርሞቸው የጠየቁት ሼክ ጠሀ ናቸው
‹‹አዎ …አሁን እዚህ ጋር እያወራን ያለነው ግን ስለ ፍቅር ጉዳይ  አይደለንም..የህልውና ፊልሚያ ላይ ነን››አለ ኮስተር ብሎ፡፡
‹‹ይሁን…ሌላው እሷን ማሳደዱ እንዳለ ሆኖ ነገሮች መስመር ይዘው ወደቀድሞ ቦታቸው እስኪመለሱ ድረስ ከሆስፒታሉ ከሚሰጡ መደበኛ ህክምናዎች በስተቀር ሌሎች ሙሉ በሙሉ ይቁሙ…..ለተለዩ ተግባራት የሚንገለገልባቸውን መሳሪያዎችም ከሆስፒታሉ ልዩ ክፍሎች ዛሬውኑ ወጥተው በጣም አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ ሄደው ይቀመጡ…ፕሮፌሰር ከአንተ ጋር የሚሰሩትም ረዳቶች ከጥሩ ጉርሻ ጋር አረፍት ቢወጡ መልካምይመስለኛል፡፡››
‹‹ሼኪ በጣም ወሳኝ ነገር ተናግረዋል….ስለአሉት ነገር ቀድሜ ሳስብበት ነበር….ዛሬ ለሊት ሙሉ በሙሉ የሆስፒታሉ ሚስጥራዊ የህክምና ክፍል ንፅህ ይሆናል….ሶሰቱ ረዳቶቼም ቢሆኑ ለ15 ቀን እረፍት በሆስፒሉ ወጪ ድበይ ሄደው ተዝናንተው እንዲመጡ እንደተወሰነ ነግሬቸዋለሁ…የጉዞ ሰነዳቸው እንዲያመቻቹላቸው ለሚመለከታቸው የሆሰፒታል ሰዎች መመሪያ አስተላልፌያለሁ…እርግጠኛ ነኝ ከነገ ወዲያ ይሄንን ሀገር ለቀው ይበራሉ፡፡››
‹‹ጎበዝ ለዚህ እኮ ነው ካንተ ጋ መስራት ደስ የሚለኝ››ሼኪው ተደሰቱ
‹‹እሺ ዶዬ የምትለን የተለየ ነገር አለ፡፡?››ሲል ጠየቀው ፕሮፌሰሩ… የሚለውን ለመስማት ሁሉም አይናቸውን እሱ ላይ ተከሉ
‹‹ደረቱን ነፋ አድርጎ ልክ እንደሚደባደብ ሰው እጆቹን እንደክንፍ በመዘርጋት በጎረነነ ድምፅ መናገር ጀመረ…..‹‹እንግዲህ እንደምታውቁት ከለሊት ጀምሮ ከመካከላችን የተኛ ሰው የለም…ልጆቼ ሁሉም ከተማዋን እየበረበሩ ነው….እንደምታውቋት አዲስ አበባ ወደጎን መንቦርቀቋ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይም ተመንድጋለች….በዛ ላይ የሀገሪቱ ግማሹ ህዝብ በውስጧ ሚኖር ነው የሚመስለው… ጉንዳን በሉት…ዝም ብሎ ይርመሰመሳል….ይሄ ሁሉ ሰው ግን በልቶ ያድራል.....?››
ዶዬ …..በልቶ ስለማደሩ ራሱ ሰውዬው ካልሆነም መንግስት ይጨነቅበት..አሁን ወደ ነጥብህ ግባ ››ፕሮፌሰሩ በረዘመ ማብራሪው ተሰላቸና ጣልቃ ገባበት፡፡
‹‹….እና ለማለት የፈለኩት ፍለጋው እንዲህ እንደምታስቡት ቀላል እንዳይመስላችሁ…ይሁን አንጂ በተቻለን መጠን ተግተን እየሰራን ነው….አንዳንድ የእኛ የቅርብ የሆኑ በየፖሊስ ጣቢያው ያሉ ፖሊሶችም ቀጥታ በፍለጋው በመሰማራትም ሆነ መረጃ በማቀበል እያገዙን ነው….ከዚህ በላይ ተጨማሪ አዲስ ሰዎችን በፍለጋው ላይ ማሰማራት ብንፈልግም ከእናንተ በኩል ሚስጥር ይባክናል ስለተባለ ያንን ማድረግ አልቻልንም…ሌላው…››
ንግግሩን ሳይቋጭ ስልኩ ተንጫረረ…ንግግሩን ገታ አድርጎ ከኪሱ አወጣና ተመለከተው‹‹…ማንሳት አለብኝ…ከንግድ ባንክ ዋናው ቢሮ ያለ የእኛ ሰው ነው የደወለልኝ››
ሁሉም በህብረት የሆነ የምስራች ለመስማት በመቋመጥ ስሜት ‹‹አንሳው ..አንሳው›› አሉት …ከተቀመጠበት ተነሳና አነሳው..ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው እሱን እየተከተሉ መንጎራደድ ጀመሩ
‹‹እሺ እንዴት ነው ..?አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ….5.5 ሚሊዬን ብር ከደብተሯ ላይ ወጪ አድርጋለች፡፡
‹‹ምን አለ?..
‹‹ ምን አለ?››በጥያቄ አጣደፉት.
ስልኩን ከጆሮው  አላቀቀና…‹‹5.5 ሚሊዬን ብር ወጪ አድርጋለች ነው የሚለኝ››
‹‹ላውድ ላይ አድርገውና ከየትኛው  ቅርንጫፍ እንደሆነ ጠይቀው››
እንዳሉት ስልኩን ላውድ ላይ አድርጎ ‹‹ከየት ቅርንጫፍ ነው?››ሲል ጠየቀው
‹‹ከመርካቶ ሱማሌ ተራ ቅርንጫፍ››
‹‹መርካቶ››
‹‹አዎ››
‹‹መች ነው? ቆይታለች?››
‹‹አይ አስር ደቂቃ ቢሆነ  ነው..እርግጠኛ ነኝ አሁንም እዛው አካባቢ ነው የምትሆነው››
‹‹እሺ ለማንኛውም ቸው ..አመስግናለው..ቡኃላ ደውልልሀለው..››ስልኩን ዘጋውና ፤ሌላ ቦታ ደወለ
‹‹ስማኝ…መርካቶ አካባቢ ሰው አለን?››ጠየቀ

የሀገሬ ወጎች

09 Jan, 18:02


https://t.me/Yonny_Athan?livestream=f7c4a750dd73d84860

የሀገሬ ወጎች

08 Jan, 13:06


ውሃ ሆኜ ሳለሁ ከአፈር ሳልነሳ
እውነቴን ነው ምልሽ
ደስ ይለኝ ነበረ ስምሽን ሳነሳ
ምኑንም ሳላውቀው
ገና ሳልፈጠር ምድርን ሳላውቃት
እወድሽ ነበረ ያለምንም ምክንያት
እወድሽ ነበረ
እወድሽ ነበረ
እወድሽ ነበረ
ዳሩ ምን ያድርጋል
እኔን አቆይቶ ቀድሞ አንቺን ፈጠረ።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

08 Jan, 12:36


ጎዳና ለመውጣት ትንሽ ቀርቶት ነበር የህይወት ፈተናውን ይመልከቱ ያዳምጡ👇👇👇👇👇

https://youtu.be/6TLNl3yhP3E
https://youtu.be/6TLNl3yhP3E

የሀገሬ ወጎች

07 Jan, 05:04


ዝምታ ወርቅ ነው
ሚለውን አስቦ ዝም ቢል ምላሱ
ወርቅነቱን አይተው ሊሸጡት ተነሱ

እዮብ z ማርያም

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

06 Jan, 17:15


የሰበረችኝ ሴት....
ለምን ዘጋው ልቡን ድንገት ብትላችሁ
ዝምብላችሁ እለፏት #ከፍቶታል ብላችሁ።

እዮብ z ማርያም

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

06 Jan, 15:58


"አዎ በትክክል ...ካለንበት ጋር የማይዋሰን"
ቀጥታ መርካቶ ነው ይዞት የሄደው።እንደዛ ያደረገው አንድም ከእሱ መኖሪያ አካባቢ ስለሚራራቅ ሁለትም ግርግር ያለበትና በሰው የተሞላ በመሆኑ ድንገት ቢመጡባቸው እንኳን በሰው አጀብ ተከልለው ለማምለጥ የተሻለ እድል የሚሠጥ ቦታ በመሆኑ።ሲደርስ ከባንኩ 50 ሜትር ርቀት ላይ አቆመና...አሁን በግር እንሄድ ብሎ ጎን ለጎን መሄድ ጀመሩ ..በራፍ አካባቢ ሲደርሱ" እንቺ ይሄን ስልክ ያዢ ..እላዩ ላይ አንድ ቁጥር ብቻ ነው ያለው እሱም የእኔ ነው ..የሆነ ችግር ወይም አጠራጣሪ ነገር ካየሽ ወዲያው ደውይልኝ።"
"የሆነ የሞሳድ ወይም የኬጂቢ ሰላይ የሆንኩ ነው የመሠለኝ"
"ብትሆኚ ነው የሚሻልሽ"
"እሺ የባንክ ቁጥርህን ስጠኝ?"
"እርግጠኛ ነሽ...?"
"ባክህ ጊዜዬን አትብላው።"
ከኪሱ ወረቀትና እስኪሪብቶ አወጣና ጫር ጫር አደረገና አቀበላት"
አቢዬት እንደልብ
100002385....
አነበበችና ፈገግ አለች
"ምነው ?"
‹‹ምንም አይደል አቢዬት ››ብላው በፈገግታ እንደተሞላች ወደውሰጥ ገባች

ይቀጥላል......

የሀገሬ ወጎች

06 Jan, 15:58


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ አምስት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹ባክህ የመጣው ይምጣ…ፌዴራል ፖሊስ ሄጄ ከሳቸዋለሁ…››
‹‹አዎ ጥሩ ውሳኔ ነው…..ግን እዛ ድርስ ምን አለፋሽ ..ከዚህ ከእኔ ቤት ትንሽ ራቅ በይና ቀጥታ ለእጮኛሽ ደውይለት….››
‹‹ለምን?››
‹‹ለመሞት እዛ ፌዴራል ፖሊስ ድረስ ታክሲ ተሳፍረሽ ከምትሄጄ እነሱው ባለሽበት መጥተው ይግደሉሻል››
‹‹እና…አንተ ዝም ብለህ ታየኛለህ ?አትረዳኝም..?››
አፍጥጦ አያት….‹‹በሽተኛ ነሽ እንዴ? ለምን ብዬ እረዳሻለሁ….?አንቺን የመርዳት ምንም አይነት ቅንጣት ፍላጎት የለኝም››
‹‹በቃ?››
‹‹አዎ በቃ …ግን ደግሞ ያን እጮኛሽንና ግብረአበሮቹን እበቀላቸዋለሁ..እነሱን ከስራቸው ገንድሼ ሳልጥል እንቅልፍ አልተኛም››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩህ..እነሱን መበቀል የምትፈልግ ከሆነ እኔ በጣም እረዳሀለው….እኔ እንድረዳህ ደግሞ በህይወት መቆየት አለብኝ ..?ለዛ ነው የምታግዘኝ፡፡››
‹‹አንቺ ከእነሱ የማፊያ ስራ ውስጥ ፍጽም እጅሽ እንደሌለበት በምን እርግጠኛ እሆናለሁ..?አብራችሁ ስትገድሉ እና ስትዘርፉ ኖራችሁ በጥቅም ተጣልታችሁ አሁን ለመገዳደል ሰየፍ የተማዘዛችሁ ከሆነስ…?››
‹‹ቀላል ነው…ነገ ተነገወዲያ ስለሁላችንም ሆነ ስለሆስፒታላችን ታሪክ በዝርዝር ስታጠና እና ስታውቅ እውነቱን ትደርስበታለህ..ከዛ እኔም ለአንድ ቀን እንኳን በዚህ አሻጥር ካለሁበት በቃ ከእነሱ ቀድመህ ታጠፋኛለህ…››
‹‹እንግዲያው እቅድ እናውጣ››
ፊቷ ሁሉ በራ ..ለመጀመሪያ ጊዜ የመትረፍ ተስፋ በውስጧ ሲራወጥ ታወቃት‹‹ተስማማን ማለት ነው?››ጠየቀችው
‹‹ቢያንስ ለጊዜው አብረን እንድንሰራ የሚያስችል የጋራ ፍላጎት አለን…..አሁን ለመጀመሪያ ማድረግ ያለብን ባንክ ያለሽን ብር በፍጥነት ማውጣት ነው››
‹‹ምን ያህል?››
ፈገግ አለ‹‹እንደእኔ የተወሰኑ ሺ ብሮች ያለሽ መስሎኝ እኮ ነው..ባንክ ያለሽን ብር ሁሉ እንድታወጪ የጠየቅኩሽ..አንቺ ለካ ሚኒዬነር ነሽ››
‹‹እሱን ተውና ምን ያህል ብር ላውጣ…?››
‹‹እንግዲህ እኔ ይህን ያህል አልልሽም..ግን የሆስፒታሉን ደህንነት የሚፈታተን ወንጀል ሰርተሸ እንደተሰወርሽ ፍርድ ቤቱን በማሳመን በተገኘሽበት እንድታዳኚ እና እስከዛው ባንክ ያለሽን ሂሳብ ጨምሮ ጠቅላላ ንብረትሽ እንዲታገድ እንዲያደርግ ለጠበቃቸው ነግረውት እንቅስቃሴ ጀምሯል…ምን አልባት ይሄንን ለማድረግ አንድ ወይም ሁለት ቀን ብቻ ይሆናል የሚፈጅበት….ከዛ ቡኃላ አተላዬችሽን ማሸነፍ እስክትቺይ ቢሳ ቢስቲ አይኖርሽም…እና አሁን የነገርኩሽን ከግምት በማስገባት ይበቃኛል ያልሽውን ብር አውጪ…››
‹‹ምን.. አንድ አስር መሊዬን ላውጣ…››
‹‹እንዴ? ሰራዊት ነው እንዴ የምናቋቁመው….ደግሞ አስር ሚሊዬን አውጥተሸ በኩንታል አድርገሽ በመኪና ይዘሽ ልትዞሪ ነው? ወይስ የት ልትሄጂ፡፡››
‹‹የት ሄዳለሁ? እዚሁ አንተ ቤት ነዋ፡፡››
‹‹አንገትሽን ቀንጥሼ ብሩን የግሌ እንደማላደርገው በምን እርግጠኛ ሆንሽ?፡፡››
‹‹ከዛሬ ቡኃላ በህይወት ውስጥ ባለ በምንም ነገር እርግጠኛ አልሆንም..››
‹‹እና?››
‹‹እናማ ያልከሀውን ብታደርገው ያው አደረከው ማለት ነው፡፡››
‹‹እንግዲያው አሁን የለበሽውን የባለቤቴን ቀሚስ በክብር አውልቀሽ ያገኘሽበት ቦታ መልሺና ፔስታል ውስጥ ያመጣውትን አልባሳት ሞክሪያቸው….››
ከተቀመጠችበት የአልጋ ጠርዝ ለቃ ሲገባ በራፉ አካባቢ ጣል ወደአደረገው ፔስታል ሄደችና አነሳችው፡፡ ከፈተችው..ውስጡ ያለውን ነገር እዛው ወለሉ ላይ በርከክ ብላ ዘረገፈችው….
ረዘም ያለው ቀይ ቀለም የተቀባ በጭንቅላት ጥልቅ የሚደረግ አርቴ ፊሻላ ፀጉር….
የሚሰካ ቅንድብ..ጥቁር መነፅር፤ ሶስት የሚሆኑ ሊፒስተክ ብልቃጦች… ሁለት የተለያየ ቀለም ያላቸው ቀሚሶች..ሁለት የአንገት ልብሶች…››
‹‹ምነው ፓንትና ጡት ማስያዣ ረሳህ?››አለችው …ይህንን ያለችው የገዛላት ሁሉ ከግምቷ ውጭ በመሆኑ ተገርማና ተደስታ ጥቂት ለመቀለድ ነው
‹‹ያው ሁለቱንም ትናንት እላይሽ ላይ ስላላየዋቸው የመጠቀም ልመድ የለሽም ብዬ አስቤ ነው….››
‹‹አንተ..ትናንት ያላደረኩት እኮ ድንገት ተጣድፌ ከቤት ስለወጣሁ ነው እንጂ የመጠቀም ልምድ ስለሌለኝ አይደለም፡፡››
‹‹መጀመሪያውኑስ ለምን አውልቀሽ ነው ?››
ፈተኝ ጥያቄ ጠየቃት‹‹ውይ አንተ ለካ እንዲህ ነገረኛ ነህ?››
ፀጉሩን አነሳችን አስተካክ አጠለቀች…ቅንድቦቹን ሰካካች….
‹‹እስኪ ፊትህን ወደእዛ አዙር ..ቀሚሱን ልቀይር ››
‹‹ምነው ከማታው የተቀየረ ነገር አለ እንዴ?›;ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ በቀልድ መለሰላት
‹‹አረ አታሳፍረኝ..››አለችው እንደ18 አመት ታዳጊው ወጣት እየተሸኮረመመች፡፡
‹‹እሺ በረንዳ ላይ እሆናለው ቶሎ በይ ››ብሎ ክፍሉን ለቆ መወጣና በራፉን ዘጋላት
ከላይ የለበሰችውን ልብስ ተራ በተራ አወለቀችና ካመጣላት ቀሚስ አንድን አነሳችና ለበሰች……ሊፒስቲካን ተቀባች…ጥቁር መነፅሯን ሰካችና..መጨረሷን ስታረጋግጥ ‹‹ግባ ጨርሼለሁ›› አለችው..ቀስ አለና በራፉን ከፍቶ ገባ….ዝም ብሎ ተሰጥኦዋን ለመዳኘት እንደተሰየመ የፋሽን ሾ ዳኛ በትኩረት ከላይ እስከ ታች ተመለከታት
‹‹መስታወት የት ጋር ነው ያለህ?››ጠየቀችው
‹‹ፊት የሌለው ሰው መስታወት ምን ያደርግለታል?››አለት
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ገብቶሻል››አለና ወለላ ላይ ካሉት እስካርፕ አንድን በማንሳት በአንገቷ ዙሪያ ጠመጠመላትና ‹‹አሁን ማንም አይለሽም…ተከተይኝ››
‹‹አንተማ የት ታውቀኘና ትለየኛለህ….ከአመታት በላይ አብረውኝ የኖሩ ሰዎች እጠፋቸዋለው ብለህ ታስባለህ›.
‹‹ፕሮፈሰርሽም መንገድ ላይ ገጭቶሽ እንደሚያልፍ እርግጠኛ ሁኚ››ተከታትለው ወጡ፡፡
ቀድማ ወደ ውጩ በራፍ ሄደችና ልትወጣ ስትል
‹‹ወዴት ነው?›› አላት ግቢው መሀል ላይ ቆሞ
‹‹እንዴ እየሄድን ነዋ….ምነው ቆምክ?››
‹‹በመኪና አይሻልም..?››አላት ግቢው ውስጥ ወደቆመችውና እስካአሁን ልብ ያላለቻትን አይጣማ ቪታራ መኪና በእጁ እየጠቆማት፡፡
ፈገግ አለችና ወደኃላ ተመለሰችና መኪናዋ ውስጥ ቀድማው ገባች ..እሱ ደግሞ በተራው ወደፊት ሄደና የመኪናውን በር ሙሉ በሙሉ ከፈተው.. ወደመኪናው በመመለስ ሞተሩን አስነስቶ ወጣ…..መኪውን አቁሞ ተመልሷ የከፈተውን በራፍ ይዘጋዋል ብላ ብትጠብቅም እሱ ግን ትዝም ያለው አይመስልም፡
‹‹እንዴ የከፈትከውን በራፍ እኮ አልዘጋህም?››የረሳው መስሎት ማስታወሷ ነበር፡፡
‹‹አውቄያለሁ››
‹‹አከራዬችህ ዝም ይሉሀል?››
‹‹እንዴት?››
‹‹እንዳያስወጡህ ብዬ ነዋ››
"ሌባና ማጅራት መቺን ደፍሮ ከቤቱ የሚያስወጣ አከራይ እምብዛም የለም"አለት ኮስተር ብሎ
"እሱስ እውነትህን ነው ..መጀመሪያውን አለማከራየት እንጂ ካከራዩ ብኃላማ እንዳልከው ጣጣው ብዙ ነው።"
"አሁን ገብቶሻል...በይ ወደቁም ነገሩ እንመለስና የት ባንክ ነው የምውስድሽ .?"
"..መጀመሪያ ንግድ ባንክ"
"እሺ"
"ያው እንደውም ንግድ ባንክ...ቦታ ፈልግና አቁም አለችው" በሚሄድበት መንገድ ሀምሳ ሜትር ርቀት ላይ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አይታ ። እሱ ግን ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን ዝም ብሎ ነዳው።
"አልሰማሀኝም?"
"ሰምቼሻለሁ ግን በሀሳብሽ አልተስማማሁም...ሂሳብሽን ባንቀሳቀሽ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የትኛው ቅርንጫፍ እንደነበርሽ መረጃው ይደርሳቸዋል ..ከዛ አካባቢውን ማሰስ ይጀምራሉ።ይሄ አካባቢ ደግሞ ከእኔ ቤት ቅርብ ነው ።አንድ ወረዳ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ ቀበሌ ውስጥ ነው..."
"ስለዚህ ክፍለ ከተማ እንቀይር እያልክ ነው።››

የሀገሬ ወጎች

05 Jan, 04:09


"መገዳደል የአውሬዎች ተግባር ነው"
"አረ ባክሽ?..እኔ ግን በህይወት ልምዴ የማውቀው አደገኛው አውሬ ይሄ ሰው የምትይው ቀፋፊ ፍጡር እንደሆነ ነው።ቆይ ቆይ አሁን አንቺን እያሳደደ ያለው አንበሳ ነው ነብር?"አላገጠባት ፡፡ምትመልስለት መልስ አልነበራትም።
‹‹በይ ተመልሰሽ ተኚ…እኔ ወጥቼ ሁኔታዎችን አጣርቼ ልምጣ።ደግሞ ስልክሽን እንዳትከፍቺ ።እስከዛ ወዴየት እንደምትሄጂ …?ምን እንደምታደርጊ... ?እንዴት  ነፍስሽን እንደምታተርፊ ?እያሰላሰልሽ ጠብቂኝ ።››አለና ስለምትለብሰው ልብስ ምንም ነገር ሳይናገር  ከመቀመጫው ተነሳቶ  ወደበራፍ ተጓዘ  ።በራፉን ከፈተና መልሶ ዘግቶላት ሄደ…..፡፡
አልተኛችም ፡፡ከአልጋዋ ተነሳችና እርቃኗን ወለሉ ላይ ቆመች ፡፡ጠረጵዛው ላይ ያለውን ካፖርቷን አንሳችና ለበሰችው… ማሰብ ጀመረች…ምን አይነት ብሽቅ ነኝ ? ስትል እራሷን ወቀሰች…..አዎ ልብስ ገዝቶላት እንዲመጣ ብር ልትሰጠው ይገባ ነበር….የሆነ ሀሳብ መጣላት ወደ እሱ ቁምሳጥን ሄደችና ከፈተችው፡፡ቁምሳጥኑ ሙሉው በልብስ የተጠቀጠቀ ነው..ክፋቱ ግን መጣናቸው ከእሱ ጋር በጣም ስለሚራራቅ ለእሷ የሚሆን ልብስ ለማግኘት አልቻለችም..ድንገት የሆነ የማታውቀው ስሜት ገፋፋት እና የታችኛውን መሳቢያ ከፈተችው…በስነ-ስርአት ተጣጥፈው የተቀመጡ አንድ አምስት የሚሆኑ ቀሚሶች ፤የሴት ሱሪዎች፤ ፓንቶችና፤ ጡት መሳያዣዎች፤ ኮስሞቲኮች ጭምር አሉ‹‹….የሚስቱ ነው ?የት ሄዳ ይሆን …?ምን የት ሄዳ እላለሁ..እቤቱ እኮ ምኑም የባለ ትዳር  ቤት አይመስልም››አለች..ይሄንን ልትል የቻለችው የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ አንድ ክፍል ከመሆኑም በላይ ምንም አይነት የማብሰያ ዕቃዎች ባለመኖራቸው ነው፡፡››
ከመሀሉ ዓይኗን የሳባትን አንድን መካከለኛ ቁመት ያለው ቀሚስ መረጠችና ለበሰች…..ለራሷ ተለክቶ የተሰበፋ ይመስል እላዬ ላይ ልክክ አለ፡፡
ከዛ በላዩ ላይ ካፖርን ደረበችበትና ዝግጁ ሆና መምጣቱን ትጠባበቅ ጀመር..‹‹አዎ ፓንት ደግሞ ስወጣ ገዛና ወደ  ሆነ ሆቴል ሬስት ሩም ጎራ ብዬ አደርጋለሁ› በማለት በአዕምሮዋ እቅዷን አቅዳ ጨረሰች፡፡
ከ40 ደቂቃ ጥበቃ ቡኃላ በራፉ ገፋ ገፋ ተደረገና አልከፈት ሲል ተንኳኳ
እሱ መሆኑን ስላወቀች ተንደርድራ ሄዳ ከፈተች
‹‹በራፌን ምነው ቀረቀርሺው?››
" ምነው አጠፋው?"
"አይ እቤቴ መቆለፍም መቀርቀርም አለመደበትም›› ብሎ …ንግግሩን ሳይጨርስ አይኖቹን እሷ ላይ እንደተከለ ባለበት ፈዞ ቆመ..በእጁ አንጠልጥሎ ነበረው በቀይ ፔስታል የሞላ እቃ ወለሉ ላይ ጣል አደረገው፡፡
እሷን ሳይሆን በለበሰችው ቀሚስ ሌላ ሰው አሻግሮ እየተመለከተ እንደሆነ ተረዳች…እና መልበስ አልነበረብኝም ይሆን እንዴ? ስትል በውስጧ አሰበችን …ፍራች  ..
ከዛ ከደነዘዘበት እንደመባነን አለና ምንም ሳይናገር  ወደውስጥ በመዝለቅ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡
..ልክ ረጅም አመት እንደምታውቀው ፍቅረኛዋ ከጎኑ ሄዳ አልጋ ላይ ቁጭ አለችና ‹‹ ..ምን የሰማሀው አዲስ ነገር አለ?››ጠየቀችው
‹‹አዲስ  ነገር ትያለሽ እንዴ….?መፈንቅለ መንግስት እንኳን ቢደረግ ይሄን ያህል ከተማዋ አትተረማመስም…ከተማዋን መነቃቅረው እያሰሱስሽ ነው…እና ደግሞ ብቻቸውንም አይደሉም የመንግስት ሰዎች አብረዋቸው አሉ ያልሽው ትክክል ነሽ...እንዳንድ ፖሊሶችና ፤ ትራፊከ ፖሊሶች በየተመደቡበት ድንገት ካዩሽ እንዲያሳውቁ ተነግሮቸው ፎቶሽ ተሰጥቷቸዋል….››
በመላ ሰውነቷ ፍራቻ ለቀቀባት‹‹እየቀለድክ እንዳይሆን…?››
ያንን አስፈሪ ፊሉን ይበልጥ አጨመዶ ‹‹አሁን በዚህ ፊት ቀልድ የሚያምረኝ ሰው እመስልሻለሁ?››አላት
‹‹እና ምን ይሻለኛል….?››
‹‹እሱን አምላክሽን ጠይቂ እኔ ምን አውቃለሁ?››
///         

ይቀጥላል......

የሀገሬ ወጎች

05 Jan, 04:09


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ አራት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ

ከእንቅልፎ ባና እጇን እዚህና እዛ ወጣጥራ ተንጠራራችና አይኖቾን ገለጠች።ልክ እቤቷ ከመኝታ ክፍሏና ከገዛ አልጋዋ የምትነሳ ነበር የመሰላት። አይኖቾን በልጥጣ ከፍታ  የቤቱን መለየትና ከፊቷ ተቀምጧ በመገረም ያፈጠጠባትን ጎልማሳም ስታይ በርግጋ ተነሳችና ቁጭ አለች።እርቃን መሆኗን ስታይ ቶሎ ብላ ብርድልብሱን ወደላይ ጎተተችና ከጡቶቾ በታች ያለውን የሰውነቷን ክፍል ሸፈነች፡፡
ከዛ ሁሉ ስቃይና የመደፈር ሙከራ ቡኃላ እንደዚህ አይነት እንቅልፍ መተኛት መቻሏ ለራሷም በጣም አስገረማት፡፡
"የቤቱ እማወራ እንኳን እንዲህ ዘና ብላ ስተኛ አይቻት አላውቅም"
"ይቅርታ ሳላስበው ነው እንቅልፍ የወሰደኝ...ግን ሚስት ከለችህ እንዴት?"
"ማለት?ሚስት እያለችህ እንዴት ልትደፍረኝ ሞከርክ ለማለት ነው …?ጠጥቼ ስለነበር ከእሷ ጋር ተምታተሸብኝ ነው…..?"አላት፡፡
"አረ እንደዛ ማለቴ አይደለም...ችግር እንዳልፈጥርብህ ፈርቼ ነው?።"
"ትቀልጂያለሽ አይደል...?አሁን በዚህን ሰዓት ከሚስቴ ጋር ባንቺ የተነሳ የሚገጥመኝ ችግር ነው ያሳሰበሽ?"ምን ለማለት እንደፈለገ አልገባትም"
‹‹ሌላ ደግሞ ምን አለ?"
"እዚህ ቤቴ ሸሽጌ እንዳሳደርኩሽ አሳዳጆችሽ ቢደርሱበት መጥተው አንቺን ብቻ ደፍተውሽ የሚሄድ ይመስልሻል...የወንበዴዎቹ ህግ እንደዛ አይደለም የሚሰራው። በመንገዳቸው እንቅፍት የሚሆንባቸውንም ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆን አብረው ደፍተውት ነው የሚሄድት"
"ወይኔ በፈጣሪ...በቃ አሁን ወጥቼ ልሂድልህ… " አለችና ልትነሳ ካለች ቡኃላ እርቃኗን እንደሆነች ለሁለተኛ ጊዜ ስታስታውስ ግራ በመጋባት መልሳ ባለችበት ቀረች ፡፡
‹‹ምነው ዝም አለሽ….?››
‹‹ሱሪዬን  እኮ ብትንትን አድረገኸዋል››አለች በአይኗ ወለሉ ላይ ተቀዳዶ የተጣለውን ሱሪዋን እየተመለከተች፡፡
‹‹እና እየወቀሺኝ ነው?››
‹‹አረ በፍፅም..አንተ በጣም ጥሩ ሰው ባትሆን እኮ እደዛ በቀላሉ ወደህሊናህ ተመልሰህ አትተወኝም ነበር…››ከአንጀቷ የተሰማትን ነው የተናገረችው፡፡
‹‹ጥሩ ሰው?››የለበጣ ሳቅ ሳቀ፡፡
‹‹ኣዎ ከአንጀቴ ነው..በመከራ ላይ ሌላ መከራ ስላልጨመርክብኝ አመሰግናለሁ››
‹‹በይ አሁን በዛ ድቅድቅ ለሊት እዚህ ሰፈር ለምን እንደተገኘሽና? አሳዳጆችሽ ለምን እንደሚያሳድዱሽ ንገሪኝ፡፡››
‹‹መነሻው የስራ አለመግባባት ነው››
‹‹የስራ አለመግባባት ለግድያ?››
‹‹ማለቴ ቀላል አለመግባባት አይደለም... ብዙ መቶ ሚሊዬን ብሮችን የማግኘትና ያማጣት ጉዳይ ነው ….ከአሳዳጆቼ ጋር በጋራ በመሰረትነው ድርጅት የሚሰራ    አፀያፊ ወንጀልን ለመከላከል ስለሞከርኩ ነው፡፡አሳዳጆቼ የሚፈልጉት ብር  የሚገኘው በሰው ደም እጅን በመታጠብ ነው…..በተጨመላለቀ ወንጀል››
‹‹እስኪ ትንሽ አብራሪልኝ።››
‹‹  የማወራህ ስለዳይመንድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ነው››
‹‹እና አንቺ የዛ ግዙፍ ሆስፒታል ባለቤት ነኝ እያልሽ ነው››
‹‹አይ አላልኩም ፡፡22 ፐርሰንት ሼር አለኝ፡፡በአጠቃላይ ሆስፒታሉ አርባ  የሰዎች ንብረት ሲሆን 35 ሰዎች ግን በጣም ጥቂት ድርሻ ነው  ያላቸው..በአጠቃላይ 11 ፐርሰንት ብቻ፡፡ቀሪው 89 ፐርሰንት የአምስት ሰዎች ነው…››
‹‹እሺ እጮኛዬ ያልሺውስ እሱ ነው አይደል ትልቅ ድርሻ ያለው?…››
‹‹.አይ እሱ 16 ፐርሰንት ነው ያለው፡፡  ሼክ ጠሀ የሚባሉት ባለሀብት ናቸው 45 ፐርሰንት ድርሻ ይዘው ትልቁ  ስልጣን የያዙት ፡፡አሁን ይሙት ይትረፍ ያላወቅኩት ለሊት ደውሎ አስጠነቀቀኝ ያልኩህ ኤልያስ 10 ፐርሰንት ድርሻ ሲኖረው የተቀረውን አቶ ሙሉ የተባሉ ግለሰብ ይይዙታል፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነው ያ ስሙ ከየቴሌቪዥን ማስተወቂያና ጋዜጦች ላይ የማይጠፋው ግዙፍ የህክምና ተቆም ከወንጀል ጋር ተገናኘ የምትይኝ?››
‹‹በሰዎች ኦርጋን ህግ ወጥ ንግድ ላይ እስከአንገታቸው ተዘፍቀዋል፡፡በአረመኒያዊ መንገድ  ከአንዱ የሆነ ነገር እየነቀሉ ለሌላው መትከል ብቻ ሳይሆን ውጭ ሀገር ድረስ እየወሰዱ መሸጥንም  ያጠቃልላል፡፡››
‹‹አልገባኝም››
‹‹አንድ ልብ እንዲቀየርለት የሚፈልግ ሚሊዬን ብሮችን መክፈል የሚችል ባለሀብት በቀጥታ ለእሱ ልብ የሚለግሰው ሰው ባይኖር እንኳን በእኛ ሆስፒታል ዋና ሰዎች ይቀርብለታል ማለት ነው፡፡››
‹‹እንዴት ተደርጎ..አርቴፌሻል ማለት ነው…?››
‹‹አይ በትክክል…ከሰው››
‹‹እንዴት አድርገው?››የምትናገረው ቶሎ ሊገባው ስላልቻለ ተበሳጨ፡፡
‹‹እንግዲህ ያጣላን ይሄ ጉዳይ ነው፣ባደረግነው መጠነኛ ክትትል የተለያየ መንገድ ነው የሚጠቀሙት…. ከእነሱ ጋር የሚሰራ በጣም ብዛትም ጥልቅነትም ያለው ብድን አለ..ደላሎችን ..ገዳዬችን ..ፖሊሶችን እና ባለስልጣኖችን ያካተተ ነው፡፡
‹‹ይሄ ሁሉ?››
‹‹አዎ እንደውም ይሄ እኛ የደረስንበት ነው..ከዚህም በላይ ውስብስብ ይሆናል ብዬ ገምታለሁ?››
‹‹አሺ እንዴት ነው የሚያደርጉት?››
‹‹ከተቻለ ለምሳሌ እንደኩላሊት አይነቱን ከጎዳና ተዳዳሪዎች ፤ከቸገራቸው የተለያዩ ሰዎቸ ጋር በገንዘብ በመደራደር..አንዳንዴ በመጠጥና በሀሺስ አደንዝዞ በመስረቅ…ከዛም ከፍ ሲል በተለያ መንገድ በመኪና በመግጨት ማጅራት በመምታት ፤ ቤተሰብ የሌላቸውና አድራሻቸው በቀላሉ መገኘት የማይችል ከቤተሰብ ተነጥለው በከተማዋ የሚገዋለሉ ባይተዋሮችን በማፈን፤በመግደል ወዘተ
‹‹በምታወሪው ግን እርግጠኛ ነሽ..እኔ እኮ ሌባና ማጅራት መቺ ነኝ…የምውለውም ከብዙ መሰሎቼ ጋር ነው..በዚህ ከተማ የተደረገች የተወራችና የተፈሳች ሁሉ አያመልጠኝም ብዬ የማሲዝ ሰው ነኝ››
‹‹እንግዲያው ተሸውደሀል…ለነገሩ ይሄ በከፍተኛ ሚስጥር የሚሰራ ስራና በዚህ የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ ያለበት ሰው ስለአንድ ነጠላ ክስተት እንኳን ለገዛ ሚስቱ መንገሩ ከተረጋገጠ ያለምንም ማቅማማት እሱንም መላ ቤተሰቡንም በማግስቱ እንደሚገደሉ አውቆና ምሎ ነው ወደ ብድኑ የሚገባው፡፡››
‹‹እኚማ ደንበኛ አሸባሪ  ናቸው በይኛ?
‹‹ትክክል….እኔ እንደውም  ያልገባኝ በፍቃደኝት አካላቸውን ስለሚቸበችቡት ሰዎች ነው ..ሰው እንዴት አካሉን አውጥቶ በብር ይቀይራል?››እስከዛሬ በአእምሮዋ ሚመላለሰውን ጥያቄ ነው አሁንም ደግማ ለእሱ ያነሳችው፡፡
‹‹ሰው ሲቸገር ምንም ነገር  ለመሞከር ይደፍራል..አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ  የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል.. የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል… የትኛውንም የሚወደውን ነገር አሳልፎ ይሰጣል፤አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል፡፡ለነገር አንቺ ችግር ባለፈበት አልፈሽ የምታውቂ አትመስይም..ስለዚህም እንዲህ አይነት ነገር ሊገባሽ አይችልም..እሱን ተይውና አሁን ምን ለማድረግ አሰብሽ?››
"ምን አስባለሁ ...መች የማሰቢያ ጊዜ አገኘሁና ላስብ?"
"ሊገሉሽ የተቀጠሩትን ሰዎች ግን አውቃቸዎለሁ..ማለት በተለያየ አጋጣሚም አብሬያቸው ሰርቼም አውቃለሁ...በጣም አደገኞችና ለመስራት ተስማምተው የወሰድትን ስራ ሳይፈፅሙ ወደኃላ የማይሉ..ለስራቸው ትልቅ ክብር ያላቸው ቆራጦች ናቸው።››
ገላመጠችው...ምንም እንኳ ነፍሷ በእሱ እጅ እንዳለች ብታውቅም ንግግሩን ልትቆጣጠረው የማትችል አብሻቂ ሆኖ ነው ያገኘው፡፡
"ምነው?"አላት ያንን የተቦጫጨቀ ፊቱን አጨማዶ
"ለስራቸው ክብር አላቸው የምትለው መግደል ስራ ነው እንዴ?"
ፈገግ አለ..."አልገባሽም እንዴ? ይህቺ አለም እኮ የተመሠረተችው በመግደልና በመሞት ነው።ለጊዜው ትገያለሽ ጊዜ ሲጥልሽ ደግሞ በሌላ ገዳይ እጅ ትወድቂና ትገደያለሽ።እንስሳ ሆንሽ ተክል ሆንሽ የሠው ልጅ  ህጉ ተመሳሳይ ነው።"

የሀገሬ ወጎች

04 Jan, 12:01


አጋቾ በራፍን ዘግቶ ከዛው አካባቢ ሳይንቀሳቀስ ግድግዳውን ተደግፎ ቆሟል…..ሲጋራውን እና ላይተሩን ከቀኝ ኪሱ አወጣ… ለኮሰ…ጪሱን በጥልቀት ወደውስጡ እየሳበ ለሰከንዶች አቆይቶ ይለቀዋል..እየተትጎለጎለና ክብ እየሰራ አየሩን ይሞላዋል… በዛ ክብ ውስጥ አሻግሮ እሷን ይመለከታታል… ያለብዥታ..ያለምንም የአይን እርግብግብታ….፡፡‹.ይህቺ ሴት ከእሱ ሴት ጋር በጣም ትመሳሰላለች….››ሲል አሰበ በውስጡ፡፡ከከዳችውና እያፈቀራት ጥላው ከተሰደደችው ፍቅረኛው ጋር..የገዛ ጓደኛውን ተከትላ ከሄደችው ፍቅሩ ጋር.. ከውስጡ ሊቆጣጠረው የማይችለው ቁጣ ሲቀጣጠል ይታወቀዋል‹‹….አብዬት  እቺ እሷ አደለችም..እራስህን  ተቆጣጠር…እንዳትጎዳት፡፡››እራሱን ለመገሰፅ የሚቻለውን መጣር ጀመረ….እጁን ወደግራ ኪሱ ሰደደና  የአረቄ ብልቃጥ ይዞ ወጣ.. አንደቀደቀው፡፡
ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ዶክተር በጣም ፈራችው..እያየችው ስሜቱ እየተቀያየረ ነው….ዛሬ በቃ  ሙቺ ተብሎ ከእግዚያብሄር ትዕዛዝ ተላልፎብኛል  እያለች በማሰላሰል ላይ ሳለች…በእጁ የቀረችውን የሲጋራ ትርኮሽ የጣውላ ወለል ላይ ጥሎ በእግሩ ጭፍልቅልቅ አደረጋትና ከአረቄው አንዴ ተጎንጭቶ ብልቃጦን በግራ እጁ እንዳንጠለጠለ ወደ እሷ ተጠጋ …፡፡በተቀመጠችበት መነሳት ባትችልም እራሷን ወደኃላ ለጥጣ ከፕላስቲክ ወንበሩ ጋር  በመለጠፍ ለመሸሽ የማይሆን ሙከራ ሞከረች ፡፡ ጨምድዶ ያዛትና ወደ ላይ ጎትቶ አስነሳት….አረቄ የያዘ እጁ በወጋቧ አዙሮ ያዛትና ወደ እሱ ስቦ ከሰፊ ደረቱ ጋር አጣበቃት…፡፡ጡቶቹ ከጠናካራ ደረቱ ጋር ሲጋጩ የመጨፍለቅና የህመም ስሜት ተሰማት….ከእሱ ትንፋሽ ወደእሷ የሚደርሰው ሽታ ከቅድሙ በላይ አስጠሊታ ሆነባት…
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹ምነው ትንፋሼ አንገሸገሸሽ..እንቺ ይሄን ስትጠጪ ይተውሻል›› ብሎ በግድ ህጻን ልጅ ጡጦ እደሚግት  አፏን ፈልቅቆ አረቄውን በጉሮሮዋ አንደቀደቀው….፡፡
እንዳዛ ያደረገው ሳትዘጋጅ ስለሆነ ሁለቴ ወደውስጥ እንዳስገባች ትን አላት..ከአፎ አላቀቀውና ብልቃጡን ወረወረው….ከዛ ነፃ በሆኑ ሁለት እጆቹ ሙሉ በሙሉ ተሸከማትና አልጋው ላይ ወረወራት…
‹‹ምን እያደረክ ነው..?እጮሀለው….ተወኝ›››
‹‹አምቦርቂው…..ግን ልንገርሽ ጉሮሮሽ ይሰነጠቃል እንጂ ማንም ደፍሮ ወደእዚህ አይመጣልሽም..ምን አልባት አሳዳጆችሽ ሰምተው ሊመጡ ይችሉ ይሆናል ››
‹‹በፈጠረህ….በምትወደው››
‹‹ምንም የምወደው የለም›› አለና….ከላይ ለብሳው ነበረውን ካፖርት ጫፍን ያዘና ሞሽልቆ ከላዬ ላይ አወለቀው…፡፡እጇ የተገነጠለባት መሳለትና ድምፅ አውጥታ ጮኸች፡፡ አፎን በአስፈሪ መዳፉ አፈናት በቀኝ እጁ የለበሰችውን የጨርቅ ሱሪ ከላይ ይዞ ወደላይ ጎተተው….እግሮቾን አንድ ላይ አጣምራ                 ያሰበውን እዳያደርግ ለመከላከል ሞከረች…አፎ ላይ የከደነውን እጁን አነሳና በሁለት እጆቹ የሱሪዋን ጠርዝ ግራና ቀኝ ይዞ ወደታች ሸረከተው……በግራ በኩል ተመሳሳዩን አደረገ..ከዛ ሞሽልቆ ከላዬ  ላይ ሙሉ በሙሉ አንሰቶ ጣለው..፡፡
በዚህ ጊዜ ወሰነች….ተስፋ ከመቁረጥ ተመዘዘ ውሳኔ.. በቃ ከዚህ በላይ መታገል ይበልጥ ለመጎዳትና በራስ ላይ ስቃይን መጨመር ነው እንጂ ሌላ የምታተርፈው ነገር እንደሌለ አሰበች..ይኅን የህክምና ሰው ስለሆነች በልምድ ታውቀዋለች….ቡዙ ግዚ ሴቶች በመደፈር ታሪክ ውስጥ በጣም ጉዳት የሚደርስባቸው ከግንኙነቱ በላይ በትግልና እራሳቸውን ለማትረፍ በሚያደርጉት መፋተግ ነው..እርግጥ ለራሳቸው ክብር ሲሉ እስከመጨረሻው ህቅታ ለሚፋለሙ ሴቷች ክብር አላት…አሁን ግን እሷ ያንን ማድረግ  አትችልም…አራሷን ከትግል ሙሉ በሙሉ አላቀቀች…፡፡ከላይ የለበሰችውን ልብስ ወደ ላይ ሞሽልቆ ሲያወጣ በፍቃደኝነት ተባበረችው……ጡት ማስያዣዋን ሳይቀር አወለቀ…እሷ እየለዘበች ስትመጣ የእሱም የንዴትና የእልህ ስሜቱ እየረገበ መጣ፡፡
እንዳጋጣሚ ከቤት ስትወጣ ፓንት አላደረገችም ነበርና፡፡እንዳጋጣሚ ማታ ስትተኛ ፓንት አውልቆ ቢጃማ ብቻ አድርጎ የመተኛት ልምድ ነበራት …እና ለሊት ኤልያስ ሲደውልላት ከመደናገጧ የተነሳ   ቢጃማዋን አውልቃ ሱሪዋን ከመልበስ ውጭ ስለፓንት አስፈላጊነት  በወቅቱ አልተገለፀላትም ነበር…እና አሁን ሱሪዋን ቀዳዶ ሲጥለው..ቀጥታ እርቃኖን ነበር ቀረችው...እርቃኖን ካስቀራት ቡኃላ  ወለሉ ላይ በሁለተ እግሮች ቆሞ ቁልቁል ያያት ጀመር..እሷ አይኖቾን ጨፍና በቀጣይ የሚሆነውን እየጠበቀች ነው….አዎ አሁን ልብሱን አውልቆ መጥቶ ሊጫወተብኝ ነው……ግን ምን ምርጫ አለኝ…አምላኬ ሆይ አንተ ካልክ ይሁን ››ብላ ስታሰላስል
.እሱ ጎንበስ ብሎ አንደ እጅን እግሯን በሌላ እጁ አንገቷ አካባቢ በመያዝ ሰቅስቆ እንደህፃን ልጅ  ወደላይ አቀፈት…..
‹‹‹አረ..እሺ በስርአቱ አድርገው..በፈጠረህ››መልሳ መወራጨት ጀመረች ፡፡እሷ ያሰበችው ወዳ ላይ ሲያቅፋትና ሰያነሳት በፊልም የወሲብ ፊልም ሚሰሩ ፈረንጆች  እንደሚፈፅሙት አይነት እሷም     ያለመደችውን አይነት ወሲብ ሊፈፅምና ሊያበለሻሻት መስሎት ነበር፡፡ እሱ ግን እንዳቀፋት ጎንበስ አለና አልጋ ልብሱንና ብርደልብሱን ገፎ ከውስጥ አንሶላው ላይ አስተኛት..ከዛ እንሶላውንና ብርድ ልብሱን አልብሶት አልጋ ልብሱን ከላይ ገፈፈና ወደፊት ለፊት ተራመደ …ከዛ አይኖቾን በስሱ ገልጣ  እያየችው በራፉን ከፍቶ ወጣና መልሶ ዘጋው..፡፡ባዶ ከፍል ብቻዋን ስትቀር ቅድም ከፈራችው በላይ አሁን ይበልጥ ፈራች…..፡፡
ሊያደርግ የፈለገውን ሳያደርግ ሀሳቡን ቀይሮ መልሶ መውጣቱን አሁንም አላመነችም..አሁንም መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..አረ ውስጧም ጭምር እየተንዘፈዘፈ ነው..፡፡‹‹ገና የእውነት ሀሳቡን ቀይሮ ነው ወይስ የቡድን ወሲብ እንደሚሉት ጎደኞቹን ጠርቶ ሊመጣ ይሆን?›› የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ተፈበረከ፡፡ ብድግ ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃኖን ወለሉ ላይ ቆመች.. ካፖርቷን ከመሬት አነሳችና ለበሰች….ቅስ ብላ     ወደ በራፉ ሄደችና ቆለፈችው…. ከዛ ደግሞ ሀሳቧን ቀይራ ከፈተችው..እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ከፈተችው ..እንገቷን አስግጋ ወደ ውጭ ስትመለከት እዛው በራፍ ስር በረንዳ ላይ እልጋ ልብሱን ተከናንቦ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ አይቹን ሰማይ ላይ የተሰቀለችው ጨረቃ ላይ ተክሎ ሲጋራውን እያቧነነ ነበር፡፡መልሳ ወደ ውስጥ  ገባች..፡፡
‹‹አሁን ዝም ብዬ ሳልቀረቅረው ልተኛ.?...ለሊት ላይ የወንድነት ስሜቱ ዳግም አገርሽቶበት መጥቶ ቢከመርብኝስ?አይ መቆለፍ አለብኝ..››አለችና ቆለፈችው፡፡ ሁለት እርምጃ ከሄደች  ቡኃላ ደግሞ ሌላ ተቀያሪ ሀሳብ መጣባት..‹‹እንዴ የሰው ሰው በገዛ ቤቱ ውጭ አሳድርሬ እንዴት ይሆናል…ምን አልባት ለሊት ላይ ብርዱን መቋቋም አቅቶት ወደ ውስጥ  መግባት ቢፈልግስ….?የራሱ ጉዳይ›› አለችና ተመልሳ የቆለፈችውን ቁልፍ  ከፋታ ወደመኝታዋ ሄዳ ተኛች…እንቅልፍ የወሰዳት ግን ምን አልባት ከሳዕታት መገለባበጥ ቡኃላ ነው… ለዛውም በቅዠትና የተሞላ አስጠሊታ እንቅልፍ፡፡

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን @ermias_ks አድርሱኝ

የሀገሬ ወጎች

04 Jan, 12:00


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ ሶስት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

////
ሰዓቱ ዘጠኝ ሰኣት ከ20 ሆኗል..ፕሮፌሰሩ ሳሎን ውስጥ ከወዲህ-ወዲያ እየተወራጨ  ይሽከረከራል….ግማሽ መላጣው ፊቱን ጨምሮ በላብ ተዝፍቋል…በዚህ ቀዝቃና ነፋሻማ ለሊት እንዲህ አይነት ላብ ከከፍተኝ ንዳድ ካለበት በሽታ እንጂ  ከጭንቀትና ንዴት የተነሳ ሆነ ቢባል ማን ያምናል፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ
‹‹እ..እስከአሁን አላገኛችሆትም….?››በቁጣ ድምፅ ጠየቀ
‹‹አላገኘሁትም….በሶስት የተለያየ መኪና በከተማዋ መንገዶች እያሰስናት ነው፡፡››
‹‹ግን ምን አይነት ዝርክርኮች ናችሁ በፈጣሪ….ፕሮፌሽናል ነን ..ምንጥቅርሴ እያላችሁ ያንን ሁሉ ብር ስትጠይቁ እኮ እንኳን አንድ እራሷን በቅጡ መከላከል የማትችል ሴት ይቅርና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን እኮ ከቤተመንግስት ገብታችሁ መግደል የምትችሉ ነው ምታስመስሉት››
ወቀሳውን መከላከል በሚያስችል ጠንከር ያለ ንግግር፡፡‹‹ፕሮፌሰር …ችሎታችንን በተመለከተ  እስከምን ጥግ እደሚሄድ በዚህ ከተማ ከአንተ በላይ ምስክር ያለ አይመስለኝም…እንግዲህ በማንኛውም ስራ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ስሀትት ይፈጠራል››ሲል መለሰለት
‹‹ስለትናንት ጀብዶችሁ ማውራት ምን ይረባል…?ትሰማኛለህ..አንዳንድ ስራዎች ፍፅምናን ይጠይቃሉ….እንደእዚህ አይነት ስራዎች ለስህተት ሙሉ በሙሉ  ዝግ መሆን አለባቸው….ከስህተታቸው ጀርባ እኮ ታላቅ ውድቀትነው የሚያስከትሉት…ድምጥማጥን የሚያጠፋ ውርድት….ወለል ብሎ የተከፈተ እስርቤት…አሁን ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ አመልክታስ ከሆነ ማን አወቀ?››
‹‹አይ እሱን በአካባቢውና በቅርብ ርቀት ባሉ ፖሊስ ጣያዎች ሁሉ ዝር እንዳላለች በየጣቢያው ባሉ የእኛ ሰዎች አማካይነት አረጋግጠናል››
‹‹እሺ እሱም አንድ ነገር ነው….ለመሆኑ ያንን ኤሌያስ ተብዬውንስ   ሄዳችሁ አረጋገጣችሁ?››
‹‹‹አዎ መልሰን ሰው ልከን ነበር….እንደውም ሰለእሱ ጉዳይ ልደውልልህ ስል ነው ቀድመህ የደወልክልኝ..››
‹‹ምን አዲስ ነገር አለ እንዴ?›› በስጋትና ጥርጣሬ ጠየቀ
‹‹እራሱን ስቶ ቤተሰቦቹ አግኝተውት ወደ ሆስፒታል ወስደውታል››
ጭንቅላቱን ያዘ‹‹ወደሆስፒታል? ያንተ ያለህ..አልቆልናል በለኛ››
‹‹አይ አላለቀልንም..ቤተሰቦቹም ይመስለኛል ምንም የጠረጠሩት ነገር ስለሌለ ወደእናንተው ሆስፒታል ነው የወሰድት››
‹እሱም አንድ ነገር ነው….ግን እስከአሁን ለሆነ ሰው የሆነ ነገር ብሎ ከሆነስ?››
‹‹አይመስለኝም….አሁን ሆሰፒታል ደውዬ ማጣራት እንደቻልኩት   ሰውዬው እራሱን ስቷል፡፡ አሁን ቀዶ ጥገና ሊያደርጉለት ማደንዘዣ ሰጥተውታል…..እንደሰማሁት ከሆነ ቀዶ ጥገናው ቢያንስ ሶስት ሰአት ይፈጃል..ስለዚህ አስበን የሆነ ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ ያለን ይመስለኛ፡፡››
‹‹በቃ እሺ ..ደግሞ በየደረሳችሁበት  አሻራ ምናምን እንዳታዝረከርኩ…ምን ላድርግ ይሄንንን ልንገራችሁ እንጂ..በል አሁን ከፈለክ ሳማይ ውጣ..ከልሆነም መቀመቅ ግባ..ይቺ  ለሊት ከመንጋቷ በፊት ያቺን ሴት አግኝተህ አጥፋልኝ…፡፡ይህንን ካሳካችሁ ከተነጋገረንው እጥፍ ክፍያ ይጠብቃችሆል..ካልተሳካላችሁ ግን አብረን እንጠፋታለን፡፡የኤልያስን ጉዳይ ምን ማድረግ እንደምችል አስብበት እና ደውልላችሆለው››
‹‹እሺ ጌታዬ››
ስልኩን ዘጋውና ወደጠረጳዛው ሄደ፡፡ ውስኪ ያያዘውን ጠርሙስ አነሳ ፡፡አፉ ላይ ደቅኖ ገርገጭ ገርገጭ አድርጎ ጠጣለት….፡፡አዎ ስሜቱን ቢያስተካክልለት …አይኖቹን ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ገዝፎ ከሚታየው ከእጮኛው ፎቶ ላይ ሰካ…..ዶ/ር ሰጲራ…በጣም ነው የማፈቅርሽ..በጣም..››አለና በእጁ ይዞ የነበረው ጠርሙስ ልክ እንደ ዲስከስ ፉር አድርጎ ወረወረው ….ተምዘግዝጎ ከፎቶ በታች ካለ ግድግዳ ጋር ተላተመና ፍርክስስ ብሎ  ተበተነ…በአቅራቢያው ያለ የሳሎን ወለል በጠርሙስ ስብርባሪ እና በውስኪ ፈሳሽ ፍንጥቅጣቂ ተሞላ
ድጋሚ ስልኩን ካስቀመጠበት ጠረጳዛ አነሳና ደወለ….ጥሪው ሰልችቶት ሊዘጋ ሲል ተነሳለት
‹‹ሄሎ ….ሼኪ ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል…››ጎርናና...ያልተሞሸ የለሊት ድምጽ
‹‹ጭራሽ ማን ልበል?››እሱ ለሊቱን ሙሉ ነፍስ ግቢ ነፍስውጪ መከራውን ያያል የሆስፒታሉ ትልቁ ባለድርሻ ሀገር ሰላም ብለው እንቅልፋቸውን መለጠጣቸው አበሳጭቶታል፡፡
‹‹እ..ፕሮፌሰር..ምነው በለሊት?
‹‹በለሊት…አስር ሰዓት እየተቃረበ እኮ  ነው››
‹‹ለ85 ዓመት ሽማግሌ 10 ሰዓት ለሊት አይመስልህም?››
‹‹አይመስለኝም ..ለ85 ዓመት ሽማጊሌ ቢያንስ ሌላው ይቅር ለፀሎት በዚህን ሰዓት ንቁ መሆን የለበትም…?››
‹‹ፕሮፌሰር ምነው እንደምታስተምራቸው ተማሪዎች ወረድክብኝ..በሰላም ነው?››
‹‹ምን ሰላም አለ…ነገሮች ምስቅልቅላቸው ወጥቷል…››
‹‹ተረጋጋ የነገሮች መመሰቃቀል ሳይሆን አደገኛው የገዛ አይምሮህ መመሰቃቀል መሆኑን መቼም ለአንተ አልነግህም…መጀመሪያ የተመሰቃቀለውን አዕምሮህን አረጋጋው …ከዛ ሌላውን ለማስተካከል መንገዱ ይገለጽልሀል››
‹‹ወይ እርሶ …ነገሩ እንዲህ ቀላል አደረጉት እንዴ?››
‹‹ቀላል እዳልሆነማ በዚህ ሰዓት  ደውለህ መአት ስታወራ መገመት ችያለሁ››
ያንን በቀደም ያማከርኮትን ነገር ዛሬ ማታ ለማድረግ ተንቀሳቅሰን ነበር.. አንደኛውን ማድረግ ብንሞክርም ሁለተኛው ግን እስከአሁን ማሳካት አልቻልንም….፡፡››
‹‹እስኪ ልገምት..ያንተዋን ነው አይደል ያለተሳካላችሁ?››
‹‹አዎ በምን አወቁ ?ኤልያስ ልክ እንደተመታ እራሱን ከመሳቱ  በፊት ደውሎ አስጠንቅቋት ስለነበረ በለሊት ከቤቷ ወጥታ ተሰውራለች.እስከአሁን ልጆቹ  እያሰሶት ቢሆንም እልተሳካላቸውም፡፡››
‹‹አይ.. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ…መጀመሪያ በዲፕሎማሲ እስከመጨረሻ ሞክር ብዬህ ነበር እኮ››
‹‹ያልሞከርኩ ይመስሎታል ..እምቢ አለች …ደጋሜ ሞከርኩ ለመንኳት አስፈራራዋት እምቢ አለች››
‹‹ምነው ወደፊት ይህችን ሀገር መምራት ፈልጋለሁ  ትል የለ እንዴ? ታዲያ የገዛ ፍቅረኛህን ማሳማን ሳትችል ይሄንን ውስብስብና ሙልጭልጭ ህዝብ እንዴት አድርገህ ልታሳምን ነው?››
‹‹እርሶ ደግሞ…አሁን ለዚህ አይነት ተራባ አሁን ጊዜው ነው››
‹‹አይደለም አፉ በለኝ..ለመሆኑ ያኛውስ በትክክል ተጠናቋል..ማለት የኤልያስ?››
‹‹ያበሳጨኝ እሱ አይደል…እሱም ክፍኛ ቆስሎ እራሱን ቢስትም እስከአሁን አልሞተም›››
‹‹እና››
‹‹እናማ..ቤተሰቦቹ ወደ ሆስፒታል አምጥተውት ዶክተሮች ቀዶ ጥገና እያደረጉለት ነው››
‹‹አይ ፕሮፌሰር..ዛሬ ሁሉን ነገር አጨመላልቀኸዋል››
‹‹አውቃለው..እሱን እራሴ እንደምንም አስተካክለዋለሁ…..አሁን የደወልኩሎት አንድ ሰዓት ቢሮ እንድንገናኝ ነው….ለአቶ ንገሩት››
‹‹አንድ ሰዓት ቢሮ..ትቀልዳለህ….?ከባለደረባችን አንዱ በቤቱ ተተኩሶበት ለህይወቱ እያጣጣረ ሌላዋ  ያለችበት ሳይታወቅ እኛ በግልጽ ሰው እያየን ቢሮ ለዛውም ባልተመደ ሰዓት…?››
‹‹እና የተለየ ሀሳብ አሎት?፡፡››
‹‹መልሼ እደውልልሀለው…እከዛው እራስህን አረጋጋ››
ስልኩን ዘጋና የኤልያስን ጉዳይ ከኮማው ከመንቃቱ በፊት እንዴት አድርጎ እልባት እንዲሚያበጅለት ማሰላሰል ጀመረ….
//////
ዶክተር ሰጵራ የገባችበትን ክፍል ዙሪያ ገባ በደንብ ካተመለከተች ቡኃላ አጠገቧ ያገኘችው የፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀመጠች….

የሀገሬ ወጎች

03 Jan, 10:19


መቼም ሊሰበሩ የማይመስሉ ሪከርዶች! አራት አመት ያለ ሽንፈት ክስተት ይሄን እና ሌሎች ያልተጠበቁ ክስተቶች በዩቱብ ገፃችን ጋበዝኳችሁ👇👇👇👇

https://youtu.be/jwYJgoSnPBo https://youtu.be/jwYJgoSnPBo

የሀገሬ ወጎች

01 Jan, 17:33


በለሰለሰ አንደበቷ ለምና አንጀቱን አራራለሁ ብላ ጭራሽ  የሚያበሳጨውን ነገር ተናግራው አስቆጣችው….ምርጫ አልነበራትም፡፡ የሚንቀጠቀጡ እግሮቾን እንደምንም አበርትታ ቆመች….ጩቤ የያዘ እጆችን እንደቀሰረ ቦርሳ በያዘ ሌላ እጁ ትከሻዋን ደርቦ ጨመደደና እየጎተተ ጨለማ ውስጥ ሁለት ሰው በመከራ በምታሳልፍ ቀጭን መንገድ ውስጥ ይዞት ገባ….ተስፋ በመቁርጥ ያለምንም መወራጨትና ትግል እንዳላት ሆና ተከተለችው…ደግነቱ ቡዙም ሳይጓዙ አንድ የቆርቆሮ በራፍ ጋር ስደርሱ ገፋ አድርጎ ከፈተና እሷን ቀድሞ ገፍትሮ አስገባት፡፡ ከኃላ ተከትሏት ገባ፡፡
የቆርቆሮውን በራ መልሶ ዘጋውና እየጎተተ  በመዳዳ ወዳሉት ሶስት ክፍል ሰርቢስ ቤቶች ይዞት ሄደ፡፡ በቀኝ በኩል ጥግ ላይ ያለውን ክፍል ደረሱ.. ቁልፍ ከኪሱ አውጥቶ ይከፍታል ብላ ስትጠብቅ ዝም ብሎ  በራፉን ሲገፋው ወለል ብሎ ተከፈተ..ገፍትሮ  ወደውስጥ አስገባትና ተከትሎት ገብቶ መልሶ ዘጋው…..በዳበሳ መብራቱን ሲያበራው ጨለማው ተገፈፈና በክፍሉ ደማቅ ብርሀን ሞላ…ዝም ብሎ ገፍቶ ሲከፍተው ውስጥ ሰው ያለ መስሏት ነበር…ከገቡ ቡኃላ ዙሪያ ገባዋን ስታይ ግን ጠባብ እና በጣም ንጽህ አራት በአምስት ስፋት ያለት ክፍል ባዶ ነች፡፡ከአንድ ጥግ ያልተተኛበት ሮዝ ቀለም ያለው ባለዘርፍ አልጋ ልብስ የለበሰ  ባለሜትር ከሀያ አልጋ ይታያል……ከአልጋው ጎን ባለ ኮመዲኖ ግዙፍ ጂፓስ አለ….ትንሽ እራቅ ብሎ ግድግዳ ላይ ተለጥፈ የተሰቀለ አርባ ምናምን ኢንች ቴሊቪዝን ይታያል…ከስር ሌሎች መጠናቸው አነስ የሚሉ  ሁለት ቴሌቪዥኖች አሉ… መሀከል ላይ ባለ ጠረጵዛ ቁጥራቸው ቢያንስ  10 የሚሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ስልኮች እና ታብሌቶች ተዘርግፈው ይታያሉ….
                                                                                                                                                     ይቀጥላል......

የሀገሬ ወጎች

01 Jan, 17:33


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ- ሁለት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

///
"በፈጣሪ ሊያጠቁኝ ማለት ?››
‹‹ምን አልባት ሊገድሉኝ…››
"እንዴ ምን ለማለት ነው? እነማን ናቸው...?
"ለጊዜው ማንነታቸውን እርግጠኛ ሆኜ  መናገር አልችልም..ግን ደግሞ የእኛው ሰዎች ይመስሉኛል"
"ታዲያ እንዴት አመለጥሻቸው።"
"እድሜ ለኤልያስ ቀድመው እሱ ጋር ነበር የሄድት… ደውሎ ወደእኔ እየመጡ እንደሆነ አስጠነቀቀኝ።››
"እንዴት ?አልሞተም ማለት ነው?"
"እኔ እንጃ ….ውስጤ በጣም እየፈራ ነው… አምልጪ እያለኝ ነው ስልኩ የተቋረጠው ፡፡ምን አልባት እራሱን ስቶ መሠለኝ"
"እሺ አሁን የት ነሽ ?መጥቼ ልውሰድሽ"
ያለችበትን ስፍራ ነገረችው፡፡
‹‹በ10 ደቂቃ ውስጥ መጣሁ›› ብሎ ስልኩን ዘጋው።እሷም ነገሮችን መልሶ ወደማመንዠግ ተመለሰች።የሆነ የማታውቀው ስሜት ይረብሻት ጀመር፡፡ ስሜቷ ድፍርስርስ ከማለቱም በላይ ትከሻዎን እየከበዳት ነው።
ከተቀመጠችበት ቦታ ድንገት ተነሳች።መንገድን ተሻገረችና ተቃራኒውን አቅጣጫ ያዘች፡፡ በጨርቆስ አቅጣጫ ወደውስጥ የምትታጠፍ ቀጭን መንገድ ታጠፈችና  የሆነች የዘበኛ ቤት ጀርባ ካለች ጠፍጣፋ ድንጋይ ጋር ዝርፍጥ ብላ ቁጭ አለች።
እሷ ከተቀመጠችበት ሀያ ሜትር በማይበልጥ ርቀት ላይ አንድ ሰፊ በረንዳ ባለው ቤት ከአስር በላይ የጎዳና ልጆች   በተተረማመሰ አቅጣጫ የተተረማመሠ አለባበስ ለብሰው ተኝተዎል።በግራ በኩል ሁለት ከፊት ለፊት አንድ በአጠቃላይ ሶስት  ውሾች ልጆቹ እግር ስር ተወትፈው ተኝተዋል። ከእነዚህ ህጻናት ጓደኞች የነበሩ ስንቶች እሷ ባለቤት በሆነችበት ሆስፒታል ባለቤቶች ትዕዛዝ ተፍነው  ልክ ሱማሌ ተራ ገብቶ ታርዶ ለመለዋወጫ እንደሚበታተን መኪና የእነሱም ሆድ እቃ ተቀዶ ለሞላላቸውና ለደላቸው ሀብታሞች አካል መለዋወጫ ሆኖ ይሆን? .ዝግንን አላት……ከምድር ሌላ ጥግ የተሠራ ፊልም የመሠለ ትዕይንት በምናቦ እያመላለሰች ከፊት ለፊቷ እያየች ካለቻቸው ልጆች የነገ እጣ ፋንታ ጋር በማገናኘት እያሰላሰለች ተመስጣ ሳለ ስልኳ ጠራ…  አነሳችው ፡፡ድምፅን በውስጧ ውጣ በሰለለ ድምፅ"ሄሎ"አለች፡፡
"ሄሎ እየደረስኩ ነው…. እዛው ነሽ?"
"አዎ የነገርኩህ ቦታ ነኝ ...ከሰላም ፋርማሲ  ጎን ካለው የባስ ፌርማታ ቁጭ ብያለሁ...ቶሎ በል…. ብርድ ሊገድለኝ ነው።"
"ከዛ እንዳትንቀሳቀሺ ሁለት ደቂቃ ብቻ ስጪኝ"ስልኩ ተዘጋ፡፡
የሠጠችው ቅድም ተቀምጣ የነበረበትን ከአለችበት ተሻግሮ የሚገኘውን  ስፍራ ነው።የዘበኛ ቤቱን ከለላ ለቃ ሳትወጣ እንገቷን አስግጋ አይኖቾን ከማዶ ተከለች።ለምን እንደዛ ማድረግ እንደፈለገች ለእሷም አልገባትም።ግን ድንገት ሀገር ሰላም ብላ ፤መንግስት አለ ብላ፤ አምላኳን አመስግና በተኛችበት ውድቅት ለሊት የህይወት ፍፃሜዎ ሊሆን  ከጫፍ ደርሷ ነበር ፡፡ስለዚህ አይደለም ሌላ ሰው የራሷንም ጥላ ብትጠራጠር ማን ይፈርድባታል?"
"እንዴ..እንዴ...""እያየች ያለውን ነገር ከመደንገጧ የተነሳ በእጇ ይዛው የነበረ ቦርሳ ተንሸራቶ መሬት ላይ ወደቀባት...ቅድም ነፍሷን ሊነጥቋት እቤቷ መጥተው የነበሩ ወጠምሾቾ ከነጥቁር መኪናቸው ከመንገድ ወዲያ ማዶ እሷን ፍለጋ ከወዲህ ወዲያ እየተወነጨፍ ይሹለከለካሉ። ባለችበት እራሷን ኩርምትምት አደረገችና ተቀመጠች።እንደምንም አቅሟን አጠንክራ የወደቀባትን ቦርሳ እጇን ሰደደችና አነሳው፡፡ ውስጡ ያለውን ሞባይሎን አወጣችና ሙሉ በሙሉ አጠፋችው፡፡  መልሳ ወደቦርሳው ከተተች።
እንደምንም እራሷን አደፋፍራ አንገቷን አሰገገችና ማዶ የሚካሄደውን ትእይንት ማየቷን ቀጠለች …አንድ ሚኒባሷን እየተሽከረከረ በመወራጨት ስልክ ያወራል...ሌሎቹ በፍለጋቸው ተስፍ ቆርጠው ወደ ሚኒባስ ተመልሰው ገብተዋል..ብዙም ሳይቆይ ያኛውም የሚያወራውን ስልክ በማጠናቀቅ  ከሹፌሩ በተቃራኒ ገቢናውን ከፍቶ ገባና መኪናወ ትንቀሳቀሰች…በአንድ ለሊት ሁለተኛ ጊዜ ነፍሷን በተአምር አተረፈች ፡፡
የመኪናዋን መሄድ ከተመለከተች ብኃላ በተሸጎጠችበት ቦታ ሆና ደቂቃዎችን አሳለፈች...ያጋጠማት ድብእዳ የማሰብ ብቃቷን የሚፈታተን ሆኖ ነው ያገኘችው...አሁን ማን ጋር ደውላ እርዳታ ለመጠየቅ እንደምትችል ወይንም ማን ቤት  ሄዳ መጠለል እንደምትችል መወሰን አልቻለችም። የምትሄድባቸው ሰዎች   ከአሳዳጆቾ ጋር  ግንኙነት ይኑራቸው ወይም  እዛ ስትሄድ አድፍጠው ጠብቀው ይድፋት  መተማመን አልቻለችም።ድንገት አንድ ሰው ትዝ አላት  ...ተመላላሽ ሰራተኛዋ ጥሩነሽ...የእሷን ቤት ታውቀዋለች ::አሁን ካለችበት 20 ደቂቃ አይርቅም ..በእርግጠኝነት አንደኛ እሷ ጋር ትሄዳለች ብሎ ማንም አያስብም፤ቢያስብ እንኳን እንዲህ በቀላሉ  የቤቷን አድራሻ ማግኘት አይችሉም ስትል አሰበች።ወሰነች።
ከተቀመጠችበት ልትነሳ ስትመቻች ጎኗ ላይ የሆነ ጠጣር ነገር ቆረቆራት ::ዞር ስትል  ፊቱን በከፊል የሸፈነ  ከሲኦል ድንገት ወደታች የተወረወረ የሚመስል ወጠምሻ ሰው ጎኗ ተንበርክኮ አብረቅራቂ ጩቤ ጎኖ ላይ ሰድሮ ሊከመርባት በሚመሰል ሁኔታ ተጠግቷታል።ትንፋሹ ፊቷ ላይ ሲበተን የሚያቅለሸልሽ ስሜት ተሰማት..የሲጋራ፤የጫትና የኦልኮል ድብልቅ ሽታ ነው በአፍና በአፍንጫዋ ያለ ፍቃዶ ወደውስጦ የገባው፡፡
"በፈጣሪ...ምንድነው እሱ..?."ተናገረች፡፡
"ዝም በይ.."የሰከረ መሆኑ የሚያስታውቅ ሻካራ ድምፅ፡፡
"እሺ"እሷ ሳትፈቅድ አንደበቷ ቃላት ያወጣ ይመስል እጇን አፎ ላይ ከደነች
‹‹በዚህ ውድቅት ለሊት በዚህ ቦታ ምን አባሽ ነው ምትሰሪው?››
‹‹ከገዳዬቼ  እየሸሸው››መለሰችለት
‹‹ከባለሚኒባሾቹ ነው?››
<‹አዎ››
የከተማዋ ቁጥር አንድ ቅጥር ነፍሰ ገዳዬች እንዲህ የሚያሳድዱሽ የትኛውን  ፈርጣማ ባለሀብትን ወይም ባለስልጣንን ብታበሳጪ ነው…..?››ሰውዬ ስለገዳይና አስገዳዬች ብዙ የሚያውቅ ይመስላል፡፡
‹‹እኔ አስቤ ያባሳጨሁት ሰው የለም..ባክህ የምትፈልገው ቦረሳዬ ውስጥ አለ..እኔን ልቀቀኝ ልሂድበት››ለመጀመሪያ ጊዜ እንባዋ በጉንጮቾ ዝርግፍ ብሎ ወረደ… እያሳለፈችው ያለውን ከዚህ በላይ ልትቋቋመው የምትችለው መስሎ አልተሰማትም…..ነፍሷንም ለማተርፍ መንፈራገጡ ብዙም ውጤት ያለው መስሎ አልተሰማትም…ከአንዱ ሞት አምልጣ ሌላው የሞት መዳፍ ላይ እየወደቀች እራሷን እያገኘችው ነው …
‹‹.ሂዱ ሁላችሁም በከተማው ተሰማሩ ተሳክቶለት እሷን ያመጣ ሽልማት አለው›› ተብለው መላአከ ሞቶች ጠቅላላ እሷን ለማደን በከተማው ውስጥ  በሁሉም አቅጣጫ የተሰማሩ መስሎ ነው የተሰማት..ከአንዱ ሾልካ ስታመልጥ ሌላው ከፊት ለፊቷ ይጠብቃታል፡፡
‹‹እኔ ብለቅሽ እኮ እነሱ ያገኙሻል››
‹‹የእድሌን እሞክራለሁ››
‹‹አይ እኔ የእድሌን ብሞክር አይሻልም ..?ስልካቸው አለኝ….ደውዬላቸው ስንት እንደምትወጪ  እጠይቃቸዋለሁ?››
እስከአሁን ከደነገጠችው በላይ ደነገጠች….‹‹አረ በፈጣሪ ……የሠው ነፍስ ከየትኛውም ገንዘብ በላይ እኮ ነው?››
‹‹አረ ባክሽ….አሁን እዛ ፊትለፊትሽ የተረፈረፉት የጎዳና ልጆች ነፍስ ከገንዘብ በላይ ነው..?በእውነት እንደእዛ ነው የምታስቢው ..?ነው ወይስ አንዳንድ እንደአንቺ ለየት ያለ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ና በእንቁ ያጌጠ ነፍስ ሲሆን  ነው በገንዘብ ሊትተመን የማይችለው…?በይ አሁን ባዶ ዲስኩርሽን ለራስሽ አቆይውና ይሄን ጩቤ እዚህ ለስላሳ አንጀትሽ ውስጥ ሳልሽጠው ቀስ ብለሽ ተነሺ..››

የሀገሬ ወጎች

30 Dec, 07:25


‹‹አዎ ኤሊያስን ያጠቁትም እሷን ለማስወገድ  እቤቷ ድረስ የሚገድላት ሰው የላኩት ሌሎች የኮሚቴ አባላት ናቸው ፡፡በተለይ ሼክ ጠሀ እና  አቶ ከፍያለው?አዎ እነሱ ናቸው ወንጀላቸውን ለማዳፈን ከፕሮፌሰሩ ጀርባ ገዳይ እስኮድ ያሰማሩት"ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች።
"ግን  የቤቴን መክፈቻ ቁልፍ ፕሮፌሰሩ ብቻ ነው ያለው እሱ ካልሰጣቸው ማን ሊሰጣቸው ይችላል?››አስጠሊታ ስሜት የሚያጭር  ጥያቄ በምናቧ ተሠነቀበረ..ነው ወይስ ትናንት አባቴ ሞቶል ብሎ ድንገት ስራውን ጥሎ ወደክፍለሀገር የሄደው የቤቷ ዘበኛ ስራ ይሆን
."አዎ ወይ ዘበኛውን በብር ኃይል አታለውት እንዲተባበራቸው አድርገዋል…ወይ ደግሞ ከፕሮፈሰሩ ቁልፉን ሰርቀውት ይሆናል...አዎ እንደዛ ነው የሚሆነው"እርግጠኛ ሆነች።
ስልኳን አነሳችና ደወለችለት ፡፡ዘጠኝ  ሰዓት እየተቃረበ ነው፡፡በሁለት ጥሪ ተነሳ፡፡
"ፕሮፌሰር እንዴት ነህ?"
"ደህና ነኝ …ምነው ደህና አይደለሽም እንዴ?"
‹‹ሰላም ነኝ››
‹‹የት ነሽ?"
"እንዴት የት ነሽ እቤቴ ነኛ"ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እቤት የት..ማለቴ እንዴት...?"የሚርገበገብ የተሰባሀረ እና ድንብርብሩ የወጣ ድምፅ
"እንዴት ማለት..?."
"ማለቴ በዚህ ሰአት በሰላም ልትደውይልኝ አትችይም ብዬ ነው ፡፡ሰዓቱን አይተሽዋል...?ምነው አመመሽ እንዴ?"
ልንገረው አልንገረው ...አለበት ?የለበትም ? ከፍተኛ ሙግት ከራሷ ጋር ገጠመች፡፡
"አረ አናግሪኝ...ካልሆነ ልምጣ እንዴ?"
"የት"
"እንዴት የት? እቤቴ ነኝ አላልሺኝም እንዴ?"
"አይ እቤት አይደለሁም..."
"አረ ግራ አታጋቢኝ ?የሆንሺውን ነገር ነገሪኝ"
‹‹መቼስ ያን የሚያህል ሰውዬ በዚህ መጠን አያስመስልም››አለችና እውነቱን መናገር ጀመረ…
‹‹የሆኑ ሰዎች ሊያጠቁኝ እቤቴ ድረስ መጥተው ነበር...››
"በፈጣሪ ሊያጠቁኝ ማለት ?››                                                                                             ይቀጥላል......

የሀገሬ ወጎች

30 Dec, 07:25


‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ አንድ

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከለሊቱ 8.15 ሞባይሏ ተንጣረረ… በግማሽ መንቃት ተንጠራርታ አጠፋችውና ወደእንቅልፏ ተመለሠች።ከ3 ደቂቃ ብኃላ  የቤቷን መደበኛ ስልክ አንቃጨለ...ድምፁ እየሠመጠችበት ካለ የእንቅልፍ ማዕበል  ዳግመኛ መንጭቆ አወጣት :: እያጎረመረመች  ተነሳችና በዳበሳ መብራቱን አበራችው።እና  መቆም በተሳናቸው እግሮቾ እየተንገዳገደች ስልኩ ወዳለበት ቦታ  ሄደችና እጀታውን አንስታ ጆሮዋ ላይ ለጠፈች።
‹‹ሄሎ...ማን  ል...በል?"
"ዶ/ር አምልጪ...ሊ...ገድ..ሉሽ ...እየ...መጡ  ..ነው" ጭል ጭል እያለች ልጥፋ አልጥፋ በማለት ከንፋስ ጋር ትግል  እንደገጠመች ቁራጭ ሻማ  ለህይወቱ የሚታገል የተቆራረጠ እና  እጅጉን የተዳከመ የወንድ ድምፅ..ማንነቱን ወዲያው አወቀችው፡፡
"ኤልያስ..?"
"እባ...ክሽ ፍጠ..ኚ"
‹‹ኤልያስ አንተ ደህና ነህ..?ጎድተውሀል እንዴ?"መልስ ሳይሆን የእቃ መንጓጓትና  ድምፅ ነው የተሠማት ..ያንን ተከትሎ ከውጭ ተንጋግቶ የሚገባ ሚመስል የእግር ኮቴ፤ ጩኸትና ጫጫታ ጆሮዋ ላይ ለጥፋ በያዘችው ስልክ ውስጥ እየተሰማት ነው፡፡ 
‹‹አባዬ ..ምንድነው…?….ቶሎ በሉ አንብላንስ ጋር ደውሉ…››ብዙ ብዙ ድምፅ እየተደራረበ ወደ ጆሮዋ ይገባል፡፡
‹‹ሄሎ ኤልያስ...ሄሎ አናግረኝ…ሌላ ሰው አለ..ባካችሁ አነጋግሩኝ"
ስልኩ አልተዘጋም…ረዘም ላለ ደቂቃ ብትታገስም የሚያናግራት ሰውም አላገኘችም፡፡ ተስፋ ቆርጣ ስልኩን ዘጋችው..የእንቅልፍ ስሜት ተሟጦ ከውስጧ በኖ ስለጠፋ ፍፅም ንቁ ሆናለች።ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው።
"ምንድነው የተፈጠረው?"….ቢጃማዋን አውልቃ ሌላ ልብስ እየለበሰች መልስ የማታገኝላቸውን ጥያቄዎችን እየጠየቀች ነው።
"ግድያን ምን አመጣው? "
የሆነ የመንጎጎት ድምፅ ከውጭ የሠማች መሠላት "ቀስ ብላ ወደመስኮት ተጠጋችና መጋረጃውን በጥቂቱ ገለጥ አድርጋ አይኖቾን ወደውጭ አጨነቆረች።ምንም የሚታያት የተለየ ነገር የለም።
"ውይ ከፍራቻዬ የተነሳ በሀሳቤ የፈጠርኩት  ነገር ነው"አለችና ዝግጅቷን ቀጠለች..በለበሰችው ልብስ ላይ ረዘም ያለ ብኒ ቀለም ያለው ባለኮፍያ ኮፓርት ደረበች...ኮመዲኖዎን ከፈተችና ውስጡ የነበረውን ብር  በማውጣት ወደ ቦርሳዎ ከተተች።መታወቂያ እና ፓስፓርቷን፤ ኤት.ኤም ካርዶን  መረጃ የምታከማችበትን 64 ጂቢ ፍላሽ ያዘችና እቤቷን ወደኃላም ሳታይ  ግቢዎንም ለቃ ወጣች።
የተረገመ አጋጣሚ መኪናዋ  ግቢዋ ውስጥ የለችም፡፡ የተወሰነ ያልተለመደ ድምጽ ስላሰማቻት ማታ ወደቤት ስትገባ ነበር ደንበኞቾ የሆኑ ጋራዥ ጋር ጎራ ብላ ለጥዋት  እንዲያደርሱላት ጥላላቸው በኮንትራት ታኪሲ ወደቤቷ የገባችው…..ስለዚህ አሁን ያላት ምርጫ በእግር ማምለጥ ነው፡፡
ከቤቷ የውጨኛው በር 20 ሜትር ሳትርቅ ከሩቅ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ሰማች፡፡ በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነች...፡፡ዘላ ከመንገድ ወጣችና  በጨለማ የተጋረደ መሸሸጊያ በመፈለግ እራሷን አጣጥፍ በመወሸቅ  የሚሆነውን ለማየት እይታዋን ወደመንገድ አስተካከለች ።አልተሳሳተችም አንድ የቀብር አስፈፃሚዎች ድርጅት ንብረት የምትመስል ጥቁር ጨለማ ሚኒባስ እየተክለፈለፈች  መጣችና ከእሷ ቤት በራፍ ጋር ስትደርስ ቀጥ ብላ ቆመች። ወዲያው የኃላው በራፍ ተንሸራቶ ተከፈተና ሶስት የሆሊውድ አክሽን ፊልም ላይ የሚተውኑ ሚመስሉ  የተወጣጠሩ ወጠምሻ ሰዎች ድብ ድብ እያሉ ወረድ።.
"እኚ ሁሉ ለአንድ ሴት ?"ስትል በውስጧ ጠየቀች
"አሁን በዚህ ሰውነታቸው ይሄን በአደገኛ ሽቦ የታጠረ ግዙፍ ግንብ አጥር እንዴት አድርገው ዘለው ሊገቡ ነው?›› እያለች ስታሰላስል ይግረምሽ ብለው ቀጥታ እንደቤቱ አባወራ ወደበራፍ ተጉዘው በተዝናና ሁኔታ  ቁልፍ ከኪሳቸው አውጥተው በመክፈት ወደውስጥ ሲገብ ባለማመን ተመለከተች።ይሄ እንዴት ሆነ የቤቷ ቁልፍ እሷና ፕሮፌሰሩ ጋር ነበር ያለው፡፡ከዛን በላይ በዛ አካባቢ መቆየት እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ነው ብላ ስላመነች ሚኒባሱ ውስጥ የቀረው ሹፌር  እንዳያያት ተጠንቅቃ ከተወሸቀችበት ወጥታ ጥግ ጥጉን እየታከከች ከሰፈሯ ርቃ ወጣች።
አሁን ካለችበት መኖሪያ ቤቷ ከሚገኝበት ወሎ ሰፈር ወደብዙ አቅጣጫ ሚወስዱ መንገዶች አሉ..ወደቦሌ መሄድ ትችላለች….በአቋራጭ ወደላንቻ መሄድ ትችላለች..እሷ ግን የያዘችው ወደጎተራ የሚመራውን  መስመር ነው….…ጎተራ ማሳለጫው ጋር ስትደርስ  ለተወሰነ ደቂቃ ቆመችና ለሰከንድ አሰላሰለች …ከፊት ለፊቷ ሌላ ሶስት ምርጫ አጋጠማት ፡፡ወደግራዋ ታጥፋ ወደ ሳሪስ መሄድ ወደ ቀኞ ታጥፋ  ወደ ላንቻና ስቴዲዬም መጎዝ ወይም የፊት ለፊቱን አስፓልት  ይዛ ወደቄራ መሸምጠጥ….
ያለምንም ደጋፊ ምክንያት የፊት ለፊቱን መርጣ ጉዞዋን ቀጠለች…...አስር ደቂቃ ከተጓዘች ቡኃላ ከሰፈሯ በጣም መራቋንና አዳኞቾም በቀላሉ  ሊያገኞት በሚችሉባት አቅጣጫና ስፍራ ላይ አለመሆኗን ስትረዳ እራሷን ገታ  ተረጋግታ ማሰብ ጀመረች ፡፡
‹‹ከኃላ ከሚያሳድደኝ ሞት ሳመልጥ  ፊት ለፊቴ ያልታሰበበት ሞት እንዳይገጥመኝ"አለችና ዙሪያዎን አማተረች….…ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣ ድምፅ እንኳን አይሰማትም ወይም ከመሸታ ቤት ወጥቶ ወደቤቱ እየተወለጋገደ      ሚሄድ  ሰካራም  በስፍራው አይታይም……ብቻ የተወሰኑ መቶ ሜትሮች ወደፊት ጠጋ ብሎ የቄራው አጥር አካባቢ የሚልከሰከሱ የተወሰኑ ውሾች ይታዬታል..በተረፈ  አካባቢው ፍፅም ጭር ብሏል... መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው… ከፊት ለፊቷ በአንድ ሜትር ርቀት የትራፊክ መብራት አለ……ትንሽ ሳብ ብሎ ወደሚታየው የባስ ፌርማታ አመራችና ጥጎን ይዛ ቁጭ አለች።
‹‹ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ ላመልክት?›› የሚል ሀሳብ መጣላት፡፡ግን ነገሩ ፖሊስ ጆሮ አንዴ ከገባ ወደኃላ የሚመለስ ነገር አይኖርም…ሄዶ ሄዶ  ወንጀሉ በግለሰቦች ደረጃ ታጥሮ አይቀርም ወደ ሆስፒታላቸውም  መዛመቱ አይቀርም…ያ ሆስፒታል ደግሞ የእሷም ሀብት ነው……ጠቅላላ ልፋቷንና ህልሞን ያዘለ ተቋም ነው….የእሱ መውደም እሷንም ቀጥታ ያወድማታል….ይሄንን ሁሉ በታትና አሰበችና ‹‹የነገሩን ጭራ በደንብ ሳልይዝ ለጊዜውም ቢሆን ፖሊስ ጋ አልሄድም ››ብላ ሀሳቧን ሰረዘችው፡፡
‹‹እሺ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ..?››በቀጣይ እራሷን  የጠየቀችው ጥያቄ ነው፡፡አሁን ምን ላድርግ..?ማን ጋር ልደውል?ስትል ፕሮፌሰሩ ወደ አእምሮዋ መጣ፡፡
…እዚህ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩ አለበት?"ስትል ህሊናን አዙሮ የሚደፋ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች።
ኘሮፌሰር ማለት የስራ ባለደረባዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የረጅም ጊዜ የቅርብ ጓደኛዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የሶስት አመት ፍቅረኛዋ ነው...ኘሮፌሰር ማለት ከአራት ወራት ብኃላ ልታገባው  ሽር ጉድ ያለችለት ያለ የወደፊት ባሏ እና የልጇቾ አባት ለመሆን ጫፍ ላይ ያለ ሰው ነው....
ፕሮፌሰር ብዙ የውጭና የሀገር ውስጥ ዪኒቨርሲቲዎች ለሁለት አስር አመታት ያስተማረ በአለም አቀፍ የምርምር ጆርናሎች አያሌ የጥናት ስራዎቹን ያሳተመ    የአደባባይ ምሁር ነው.....በዚህ ላይ ሀገሪቱ ከለቻቸው ከአንድ እጣት ከማይበልጡ የልብ ቀዶ ህክምና  ሀኪሞች አንዱ ነው፡፡ታዲያ እንዴት ነው ይሄ ሰው የእሷን የትሙት በቃ ውሳኔ ከሌሎች ገዳይና ማጅራት መቺዎቾ ጋር በማበር ሊፈርም የሚችለው?እሷ ስለሆነች አይደለም ሌላ ማንስ ቢሆን እንዴት እንዲህ ያደርጋል? ይሄ ሰው እኮ ለእንስሳት ነፍስ ሁሉ  አንጀቱ ከመንሰፍሰፍ የተነሳ ቬጂቴሪያል የሆነ ሰው ነው?..ምንም ሊዋጥላት አልቻለም፡፡

የሀገሬ ወጎች

29 Dec, 19:08


#ስኳር_መች_ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ።

‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ….
‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ…
ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይና አታላይ አምልጣ፣ እሷም እንደማንም ግጣሟን አገኘችና ጎጆ ወጣች። ተሰበሰበች። አገባች….ተነካች።

በቃል እና በእምነቷ መሰረት፣ ክብር እና ንፅህንናዋን ጠብቃ ኖረ ተዳረች። ከባሏ ተኛች።

በዚህ ዘመን ቀረ ብለን የምንገረምበት ወግ አጥባቂነቷ የአስናቀች ወርቁን ዘፈን ያስታውሰኝ ነበር። አስናቀች ቀኑን ሙሉ ከምታፈቅረው ልጅ ውላ ልክ ሲመሽ ሌላ እንዳያስብ ‹‹ልሂድ›› ስለምትል ወዳጄን የምትመስል ሴት ዘፍናልን ነበር።

‹‹ፍቅርዬ- ፍቅርዬ ደህና ሁን
ሊመሽ ስለሆነ መሄዴ ነው አሁን…..
…እኔ እንደምወድህ – ፍቅሬ ሆይ ውደደኝ
በህጋዊ ስርአት ማልድና ውሰደኝ…
አፍቅረኝ ላፍቅርህ ኑሯችን ባንድ ይሁን
እስከዚያው ድረስ ግን- ፍቅርዬ ደህና ሁን›› እያለች ዘፍናልን ነበር።

እናም…የ34 አመቷ ወዳጄም በህጋዊ ስርአት፣ በአማላጅና በምልጃ የፈለገችውና የፈለገችውን አገኘችና፣ ወሰዳትና አገባች። ተነካች።

ሰርጉ ተከናውኖ…
ጫጉላው አብቦ…
ከስንት ያመለጠው ብር አምባር ተሰብሮ ጥቂት ቀናት ካለፉ በኋላ አሁንስ ይበቃታል ብዬ ደወልኩላት። እንዴት ሆንሽ….አጥሚትና ገንፎ የት ይዘን እንምጣ ልል እና ላጫውታት ደወልኩላት።

ብዙ ሳይጠራ አነሳች።

(በቅቷታል ማለት ነው…)

ሰላምታችን ሲያልቅ ወደ አንገብጋቢውጉዳይ ገባሁና..
‹‹እህስ…ነገሩስ? እንደጠበቅሸው አገኘሽው ወይስ ቅር አለሽ?›› አልኳት።
‹‹ቅር አለሽ ወይ? ወይ ጉድ…አንቺ….ስኳር መች ይጣፍጣል?!›› ብላ መለሰችልኝ።

ከአንጀቴ ሳቅሁ።

እንዲህ ትላለች ብዬ ስላልጠበቅኩም፣ ያ ከአመታት በፊት የሰማሁት ታሪክ ላይ ያለችው ልጅንም አስታወሰችኝና ሳቅሁ።

(ታሪኩ እንዲህ ነው። ልጅቱ ለስኳር ያላት ፍቅር የትዬሌሌ ነው። ‹‹ከስኳር የሚጥም፣ ከስኳር የሚጣፍጥ ነገር በአለም ላይ…አንዳችም ነገር የለም›› የምትል አይነት። እጮኛዋ ‹‹ተይ ተጋብተን ፍቅር ስንሰራ ኋላ ሃሳብሽን ትለውጫለሽ›› ቢላትም እሷ ግን ወይ ፍንክች! በኋላ ጋብቻው ተከናውኖ ባልና ሚስት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እየሰሩ ወደ ማገባደዱ ሲደርሱ የሚስቱን ሁኔታ ያየው ባል በእጁ የጨበጠውን ስኳር በተከፈተ አፏ ውስጥ ሙጅር ያደርጋል። ይሄን ጊዜ የስኳር ነገር የማይሆንላት ሚስቱ ምን አለች? ‹‹ውይ ውዴ…! የምን አፈር ነው አፌ ውስጥ የጨመርከው?!››)

‹‹ወይ አንቺ…እና ታዲያ ይሄን ያህል ጊዜ በመቆየትሽ ትንሽ አልተቆጨሽም ታዲያ?›› አልኳት
ለመመለስ ሰከንድ አልፈጀባትም።
‹‹በጭራሽ! መቆየቴ መቼም አይቆጨኝም….ግን እንዲህ መሆኑን ግን ነገራችሁኝ አታውቁም….››
‹‹ ብንነግርሽስ ኖሮ?››
‹‹እሱስ ምንም ለውጥ አያመጣም ነበር…ያው ምናልባት ትንሽ…ይበልጥ ልጓጓ ግን እችል ነበር……..››

ወሬያችን አልቆ ስልኩን ስዘጋ በዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም ሰው ለመምሰል በሚሮጥበት ጊዜ፣ ለግል አቋምና እምነቷ ባላት ታማኝነት እንዳዲስ ተደነቅኩባት። ቀናሁባት።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን (በእኔ እና በአለም ስሌት) ዘግይታም ቢሆን አዳሜ የአለምን ምሬት የሚያጣፍጠው ፍቅርን በመስራት ስኳር መሆኑን በማወቋ ተደሰትኩላት።

         🔘በሕይወት እምሻው🔘

የሀገሬ ወጎች

28 Dec, 18:31


https://t.me/Tizitawolde_poems?livestream

የሀገሬ ወጎች

26 Dec, 16:36


ምንም ፃድቅ ባልሆን
ይፃፍ ተዓምሬ
ማትወጂኝን ወደድኩ
ከጌታ ተምሬ

ገጣሚ እንደልቡ


Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

23 Dec, 17:47


የዚች አለም ችግር
ሁሌም ወደኋላ
የተራበው ቀርቶ
የጠገበው በላ
እንዲህ ነው ምሳሌው
ሲተነተን ፍቺው
አንቺም የሌላ ሰው
እኔም ደግሞ ያንቺው

አወይ የኔ ህይወት
አወይ የኔ ተድላ
የማፈቅርሽ እኔ
የሚበላሽ ሌላ

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

22 Dec, 06:15


ህይወት ሞልታ አትሞላም
ወይ ጎላ አትጎድል
ቁልፉ ስኬት ሲሆን
ውድቀት ዋነኛው ድል

ስቃይ እና ደስታ...ድሎት እና ችግር
ምን ቢሆን ጣዕሙ
ሁሉም እርግፍ ይላል
ባንቺ ከተሳሙ
"ደስታ ምንም ነው
ስቃይ አይታሰብም
ለእንደኔ እና እንዳንቺ
ብቻ ሳሚኝ አንቺ"

ብዬ ነበር ብዬ ነበር

ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እያየሁት ዛሬ ባይኔ
አትረሳህም እለዋለው
ለተጎዳው ባንቺ ጎኔ
የቀን ሳቄን ከሳቅሽ ጋር
እንዳልሳቅነው ተያይዘን
ሲመሽ ሲጠልቅ ሁሉም ነገር
ስንቱ ቀናት ደበዘዘን
አይኔ ይበቃል ለመረዳት
ባላወጣው የፍቅሬን ቃል
እንደወደድኩሽ ነው...
ድፍን ሐገር ያውቃል

ውድቀት ቢሆን ሲመሽ ጊዜው
ይበቃኛል ለቀኑ ዕድል
ህይወት እንደዚህ ነች
ወይ ሞልታ አትሞላም
ወይ ጎላ አትጎድል።

አሳየሽኝ ስቃይ ድሉን
ከዚም ከዛም እያጣቀሽ
ተኮሳትረሽ ያው ወርቅ ነሽ
ትገያለሽ ደግሞ ስቀሽ

አስረዳሁሽ በአይን ወሬ
ልብሽ ከቶ ምኑን ነቃ
አንቺም ሂጂ ይለይልኝ
እኔም ደግሞ ልርሳሽ በቃ።


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

20 Dec, 15:04


የሚወዳት ፍቅረኛውን ያጣው ሰው! የኦዴጋርድ የህይወት ፈተናው በዩቱብ ገፃችን ይመልከቱ ያዳምጡ👇👇👇

https://youtube.com/watch?v=x9bzIflt6fM&si=qfnzpDM-Bbwet9J1

የሀገሬ ወጎች

11 Dec, 09:02


Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

03 Dec, 21:03


ታሪኩ እንዲህ ነው
ልጁ ከዋሻው ስር እባብ እንዳለ አላወቀም፤ሴቷ ደግሞ ልጁ ላይ የተጫነው ከባድ ድንጋይ እንዳለ አታውቅም😳😳😳😳
ሴቷ እንዲህ አሰበች See more

wave ለመመዝገብ

የሀገሬ ወጎች

02 Dec, 17:05


የፍቅር ማእበል



   (  የመጨረሻ ክፍል )

ጠበቅን ጠበቅን ጠበቅን በስተመጨረሻም ቀዶ ህክምናው ተጠናቀቀ።

ከምሽቱ 5 ሰአት አካባቢ ዶክተሩ ወጣ ተከተልኩት እኔን አትከተይኝ እስኪነቃ ጠብቁ አለኝ ።

ከምንድነው ሚነቃው ከሞት ነው ???

ቀልድ ነው ወይስ ምንድነው እረፍት ላደርግ ነው አሁን ብሎ ጥሎኝ ገባ ።

አንዴ ወደ ሰማይ አንዴ ወደ ምድር አይዘለል ነገር ሆኖብን እንዳፈጠጥን የጠዋቷ ወጋገን ወገግ አለች።

ማየት  ትችላላችሁ ግን አልነቃም ተባልን እኔ በዛ ሰአት አቅም እያጣሁ ነበር።

አንጀቴ እጥፍ እጥፍ እያለ ነበር ድካሙ ህመሙ ጭንቀቱ ተደራረበብኝ ። ለመቆም አቅም አጣሁ  ከዛ ቡሀላ ምን እንደተፈጠረ አላቅም እራሴን የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ነበር ያገኘሁት ።

እንደነቃሁ ልዑሌ ደና ነው ልዑሌ ደና ነው አልኩኝ ።

አንዲት ነርስ መጣችና አንቺ ግን ፅንሱን አትፈልጊውም እንዴ የመግደል ሙከራኮ ነው እያደረግሽበት ያለሽው እባክሽ ቢያንስ ለልጁ ስትይ እራስሽን ጠብቂ።

ባለቤትሽ ደና ነው አይዞሽ ይድናል ግን አንዳችሁ እንድትድኑ ሌላኛችሁ መሞት የለባችሁም አለችኝ ።


ልዑሌ ከ2 ቀን ቡሀላ ነቃ።
ከህመሙ ዳነ በፊት ከነበረው ግርማ ሞገስ ትህትና ደግነት የበለጠ ተላብሶ ነበር ።

እንደገና ህይወት ሀ ብሎ ተጀመረ ከኔና ከልጆቼጋ የሞከ ቤተሰብ የሞቀ ኑሮ ተጀመረ ።

ልዑሌ አሁን እንደበፊቱ ዝምታን አያበዛም የሚስቅበት ምክንያት እራሱ ያስቀኛል ፈገግታ ከፊቱ አይጠፋም።

ልዑሌ ከዳነ ቡሀላ እናቴ የደስ ደስ ትንሽዬ ፕሮግራም ነገር አዘጋጀጅታ ለቤተሰብ ብቻ ምትሆን
ወደናቴ ቤት ሄድን። ሆዴ እያስታወቀ ነበር መኪናችንን አቁመን ወረድን ማክቤል ከፊት ለፊታችን መኪና እየነዳ የሞቀ ሰላምታ አቅርቦልን አለፈ ።

ልዑሌ በምላሹ የሞቀ ሰላምታ ሰጠው እኔ ደርቄ ቀረሁ ሰላሜ ምነው ትዝታሽ ተቀሰቀሰ እንዴ ንቂ እንጂ አለኝ።

አረ ወደዛ ሂድ የምን ትዝታ ነው መኪና ይዞ ሳየው ገርሞኝ ነው እንጂ አልኩት ለማንኛውም ተይው ተንቀሳቀሽ አለኝ ።

ወደናቴ ቤት ገባን ፕሮግራማችንን እኛው እራሳችን አደማመቅናት ።

ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ text ገባልኝ ከማክቤል ነበር  እንዲህ ይላል...

አየሽ እግዚአብሔር ሲባርክ እንደዚህ ነው እኔና አንቺ 6 አመት ሙሉ ስንቆይ ፍቅራችን ከልባችን አልነበረም እኔ በግልፅ ነግሬሽ መፍታት እየቻልን እንደህፃን አይንሽ ላፈር አልኩሽ አንቺ ከኔ እንዳረገዝሽ ስታውቂ በልጁ አይጨክንም ብለሽ ለኔ እንደመንገር ልዑልን አገባሽ ።

የኛ እህል ውሀ አልተፃፈም ነበር ከኔ ወሰደና በፍቅር በልጅ በትዳር ባረከሽ ያውም ሁሉንም ሰው የሚያስቀና ትዳር።

እኔም አንቺን ባጣሁባቸው ሰአታት ብዙ ነገርን ተማርኩኝ እየኖርኩ እንዳልነበር ገባኝ እስከመቼ ያባቴ ጥገኛ ሆኜ እንደምኖር ፈጣሪ ነበር ሚያቀው በኔና አንቺ መለያየት ውስጥ ግን እራሴን አገኘሁት ።

የዛብሎን አባት እኔ አደለሁም ልዑል ነው የዛኔ አስወርደሽው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ዛብሎን አይኖርም ነበር ።
ይቺን ምድር እንዲቀላቀል በምቾት እንዲያድግ ያደረገው የሚያደርገውም ልዑል ነው  ።

ፈጣሪ ይመስገን እኔም አባቴ እንደሚፈልገው አይነት ልጅ ሆኛለሁ እንደዚህ ሆነሽ ስላየሽም ደስ ብሎኛል ይላል።

አመሰግናለሁ አንተንም እንደዛ በማየቴ ደስ ብሎኛል ጥሩ ነገር ይግጠምህ ከዚህ የበለጠ አባትህን ደስ አሰኛቸው ባይይይ......

.
.
.
.
.
አሁን የ3 ጎረምሳ ልጆች እናት ነኝ ሴት ልጅ ፍልጋ ገና ስንት ልጅ እንደምንወልድ አላውቅም😂  ደርዘንም ቢሆን አናቆምም ሴት ልጅ ካልወለድን ብሎኛል ልዑሌ። 


ለልዑሌ ደግነቱ  መልሶ ከፈለው ።

እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው በህይወታችን ውስጥ ፣ትልቁ  ቁም ነገር ገንዘብ አደለም።

በህይወታችን ውስጥ ፍቅር ላይ ስንሆን መተማመን ግልፅነት ከሌለ ያ እውነተኛ ፍቅር አደለም።

ፈጣሪ ሊያነሳን ሲፈልግ በየት በኩል እንደሆነ አናቅምና እሱን እንጠብቀው።

ልባችሁን እንጂ ገንዘብን አትከተሉ።

የናንተ ያልሆነን ሰው ፈጣሪ ካጠገባችሁ ሲያርቅላችሁ አሜን ከመጀመሪያውም ያ ሰው የኔ አልነበረም ብላችሁ ተቀበሉ እንጂ ልባችሁን በማይሆን ተስፋ አትሙሉት።


አመሰግናለሁ ።

ተፈፀመ!!!!!!!

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

01 Dec, 16:23


የሀገሬ ወጎች pinned «ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የፍቅር ማዕበል የተሰኘው ተከታታይ ልብወለድ 1የመጨረሻ ክፍል ይቀረዋል እስካሁን በነበረን ቆይታ ደስተኛ ናችሁ?ሀሳባችሁን አካፍሉን ከወደዳችሁት 🥰 ምንም አይልም👍 ካልወደዳችሁ😕 react በማድረግ አሳውቁን የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ 2 ሰዓት ይለቀቃል።»

የሀገሬ ወጎች

01 Dec, 16:23


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የፍቅር ማዕበል የተሰኘው ተከታታይ ልብወለድ 1የመጨረሻ ክፍል ይቀረዋል እስካሁን በነበረን ቆይታ ደስተኛ ናችሁ?ሀሳባችሁን አካፍሉን ከወደዳችሁት 🥰 ምንም አይልም👍 ካልወደዳችሁ😕 react በማድረግ አሳውቁን የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ 2 ሰዓት ይለቀቃል።

የሀገሬ ወጎች

28 Nov, 18:48


የፍቅር ማእበል




    ክፍል 65

ሲጨንቀኝ እናቴጋ ደወልኩ የምላት ሲጠፋኝ ሰላም መሆኗን ብቻ ጠይቂያት ዘጋሁት ።


ልዑሌ ትንሽ ቆየና ተመልሶ መጣ ተረጋጋሽ አለኝ ለመሳቅ እየሞከረ ሳየው እንዳዲስ አሳዘነኝ እንባዬ መጣ ላለማልቀስ ታገልኩኝና አቃተኝ ።  ወዲያው ሊሞት ይመስል ጥብቅቅቅቅ አድርጌ አቀፍኩትና ቆይ አንተ ብትሞት ቀብርህ ላይ ሰው ሆኜ ምቆም ይመስልሀል አሁን ላወራኸው እራሱ እየሰቀጠጠኝ ነው ገና መኖር ስትጀምር መሞት የለብህም እስከዛሬ የለፋህበትን የደከምክበትን ፈጣሪ ሚከፍልህ ገና ካሁን ቡሀላ የምር ስለምትሞት ሳይሆን ፈጣሪ ልጅ የሰጠኽ እንድትነቃ ምልክት ሊሰጥህ ፈልጎ ነው እሺ የኔ ባል አልኩት ።

እሱም ሲያዬኝ ሆድ ይብሰዋል እኔም ሳየው ሆድ ይብሰኛል ሳልፈልግ ካይኔ እንባ ግልብጥ ይላል ።
ቢያንስ ከሰራሁት ስተት መማር አለብኝ ብዬ አሰብኩና ቆንጆ እራት ተዘጋጅቶ በልተን በሱ ምርጫ ፊልም አዘጋጀሁ ከዛን በፊት ግን አሁን የህክምናው ሂደት እንዴት እንደሆነ ከዶክተሩጋ ምን እንዳወሩ ጠየኩት ።

የህክምና ሂደቱ በጣም ከፍተኛ ነው በመጀመሪያ ወደ ውጪ ሄጄ የምታከምበትን ያህል ብዙ ገንዘብ ነው የጠየቀኝ ሁለተኛ ደሞ ህክምናውን ሳደርግ ከመዳን ይልቅ የመሞት እድሌ በጣም ሰፊ ነው ያንን ሀላፊነት መውሰድ አለብኝ ካልሆነ ህክምናው አይደረግም ደሞ ገንዘቡም ከምልሽ በላይ ብዙ ነው ከሌሎች ሰዎችም እንዳስቀድምህ ከፈለክ የጠየኩህን ገንዘብ ክፈል አለኝ እሱን መክፈል ካልቻልኩ ደሞ ህክምናውን ለማግኘት በጣም መቆየት ይኖርብኛል አለ።

እና አንተ ገንዘብ ቸገረህ እንዴ ብትፈልግኮ ከወንድሞችህጋ ያለህን ድርሻ መሸጥ ትችላለህ አልኩት ወደኔ ዞሮ ፍጥጥ አለና ሁለቱንም እጆቹን ጉንጮቼ ላይ አድርጎ ጥብቅ አርጎ ያዘኝና ልክ ነሽኮ እኔን የጨነቀኝኮ ባንክ ያስቀመጥኩትን ብር እንዳለ ለህክምና አውዬ ድንገት ባልተርፍ እንኳን ላንቺና ለልጆቼ ገንዘብ ሳላስቀምጥ ያለኝ ሀብት እስኪወሰንላችሁ ትንከራተቱብኛላችሁ እያልኩኮ ነው ልክ ነሽ እነሱ እንደሆነ ምንም ባደርግላቸው እኔን ቼክ አያደርጉኝም ድርሻዬን መሸጥ እችላለሁ አለኝና ግንባሬን ሳምም እያደረገ ስማርትኮ ነሽ አለኝ ።

እየተሳሳቅን ፊልማችንን ማየት ጀመርን  ትንሽ ከገባንበት ድባብ እንድንወጣ ፈልጌ ነበር ፊልሙን ስንጨርስ በእኩለ ለሊት ዘፈን ከፈትን እኔ መደነስ አልችል ቁጭ ብዬ እቅፎቹ ውስጥ እየተምነሸነሽኩ ዘፈናችንን መኮምኮም ጀመርን።

ልዑሌ በዛ አስረቅራቂ ድምፁ
ተስለሻል እንዴ ካይኔ ከመሀሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ ........
እያለ አዜመልኝ ።

በትንሹም ቢሆን ከሀዘን ድባብ ለመውጣት ሞከርን ውስጣችን እያለቀሰ በጥርሳችን ፈገግ አልን።

እኔ ከ3 ቀን ቡሀላ ወደ ሀኪም ቤት ሄጄ ቼክ ተደረኩ በጣም ጥንቃቄ እያደረኩ ግን መንቀሳቀስ እንደምችል ልጁም ቆንጆ ሁኔታ ላይ እንዳለ ነገሩኝ ደስ አለኝ።

ልዑሌን ዶክተሩጋ አብረን እንድንሄድ ለመንኩትና እሺ አለኝ ከቀን 6 ሰአት ጀምሮ አስከምሽቱ 5,50 ድረስ አስጠበቀንና ወደ ቢሮ ገብተን አገኘነው በቃ ለመክፈል ዝግጁ እንደሆንን እኔ ባለቤቱ እንደሆንኩ ሁሉንም አስረዳነው እሺ ቀኑን አሳውቃችኋለሁ አለን በዛ በሌሊት ተነስተን ወደቤታችን ሄድን ።

ልዑሌ በነጋታው ከወንድሞቹጋ ያለውን ድርሻ ለመሸጥ መሯሯጥ ጀመረ ተሳካለት ከምንፈልገው ብር 3 እጥፍ ሸጠው ።

ዶክተሩ ግን ቀጠሮውን ደውሎ አላሳውቅ ሲለን ተመልሰን ሄድንና እዛው ቀጠሮ እንዲሰጠን ለመንኩት ለ15 ቀን ቀጠረንና ተመለስን ልዑሌን 7ቱን ቀን ቤተክርስቲያን ውስጥ እየፀለየ እንዲያሳልፍ አደረኩኝ።

ከዛ ቡሀላ መዘጋጀት ጀመርን ልዑሌ ከሞትና ከህይወትጋ ፊት ለፊት ሊጋፈጥ ቀናቶች ቀሩት የፈሩት ቀን ደሞ ለመድረስ በጣም ይፈጥናልና ቀኑ ደረስ ቢያንስ 11 ሰአት ይፈጅበታል ህክምናው የተጀመረው ከረፋዱ 4 ሰአት አካባቢ ነበር።


ልዑሌ ወደ ህክምናው ሲገባ ለመሞት እንደሚገባ ሰው ለሁላችንም ፍቅሩን ተናዞ ተሰናብቶን ነው የገባው።
ወንድሞቹ ከመግባቱ በፊት መጡና ስራ አለን ስትጨርሱ ውጤቱን አሳውቁን ብለው ሄዱ ገረመኝ እንዴት ካንድ አባት ተወልደው በዚህ ልክ ይጨክኑበታል አልኩኝ ።

ምስኪኗ እናቴ እኔ መሲ እህቴ ብቻ ነበርን እዛ የተገኘነው የስራ ባልደረቦቹ ለስራ ጉዳይ ከሀገር እንደወጣ ነው ሚያውቁት።

ልዑሌ ውስጥ ከገባባት ሰአት አንስቶ ምን እየተፈጠረ እንዳለ እንኳን በትክክል ማወቅ አልቻልኩም ነበር እያየኋቸው ብዥዥ ይሉብኛል እያወሩኝ እንኳን ምን እንደሚሉኝ አልሰማቸውም ።

ምግብ ሚባል ስላልቀመስኩ ጭንቀቱም ይሄ ነው የሚባል ስላልነበር ወደ 9 ሰአት አካባቢ እራሴን ስቼ ወደኩ ስነቃ ገና 9.30 ነው ፈጣሪ ሆይ ዛሬ ደሞ ሰአቱ ወደ ኋላ ነው እንዴ ሚቆጥረው

ቆይ ከሞተ ለምን ሞቷል አይሉንም አውቀው ነዋ ውስጥ ሚያቆዩት አረ ምን ማልው አለ ሰላሳውን ስዘላብድ መሸልኝ።

አስቡት እስቲ ከብዙ ነገር ያዳናችሁ ከዛ ሁላ ችግር ያወጣችሁ የምትወዱት የምታፈቅሩት ሰው ሞቶ ይሁን በህይወት የሚወጣው ሳታውቁ ስትቀሩ...
ልባችሁ ጭንቅላታችሁ ስራ አቁሟል በሚባል ደረጃ ስታክ ነው ምታደርጉት አንዳንድ ስሜቶች ለማብራራት አይመቹም።
ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

27 Nov, 16:38


የፍቅር ማእበል



        ክፍል 64

የዛኔ ምንም መልስ አጣሁ ዝም ብዬ አይኑን አየሁት ቆይ ግን  ልዑሌ ምን እያልክ እንደሆነ ታውቆሀል እእ እሞታለሁ ማለት ምን ማለት ነው ወይስ እየቀለደክ ነው ብዬ አፈጠጥኩበት ።

አረ ሰላም ላልሞትምኮ እችላለሁ ግን

ግን ምን ቆይ አንተ ደደብ ነህ እንዴ ታክመህ በተረፈህ ነው እንጂ ሀብታም መሆን ያለብህ ከሞትክኮ ሁሉም ነገር ተራ ነው አልኩት እያለቀስኩ ።

አቀፈኝና አይዞሽ አሁን እኮ ተስፋ አለኝ ዶክተሩን እንደምንም ብዬ ካሳመንኩት እድናለሁ ሰላም አሁን መፀለይ ነው።

ደሞ የልጄ አምላክ ያድነኛል ብሎ ወደራሱ አቅፎኝ አለቀሰ እኔም አለቀስኩ ለምን አረፈድክ ፍቅር ሲይዘው የሰው ልጅ ለምን እውር እንደሚሆን አላቅም ቅድሚያ ለራስህ አትሰጥም እንዴ ቆይ ጮኩበት

ሰላም ለምንድነው ይበልጥ ፀፀት እንዲሰማኝ ምታደሪጊኝ ነገርኩሽኮ በሰአቱ ለኔ ልክ ነው ብዬ ያሰብኩትን አደረኩኝ በቃ  አሁን ጊዜውን ወደ ኋላ መመለስ አልችልም ሆኗል አንዴ እኔን አይዞህ ትድናለህ እፀልይልሀለሁ ብለሽ በማፅናናት ፈንታ ጭራሽ ትጮሂብኛለሽ ብሎ ተነስቶ ገባ።

ተነስቼ ተከተልኩት በቃ ልዑሌ ይቅርታ አድርግልኝ እኔኮ እንዳላጣህ ፈርቼ ነው እንዲህ ምቀባጥረው እንባዬ ዝምብሎ ይፈሳል ።
ማንኛችን ማናችንን እናባብል ልክ እንደለቅሶ ቤት ሁለታችንም ማልቀስ ሆነ።

መሬት ላይ ተቃቅፈን ቁጭ እንዳልን ነጋልን  ቀጥታ ከእንቅልፌ እንደነቃሁ ልዑሌ ዶክተሩ የት ነው ያለው ውሰደኝ እኔ እለምነዋለሁ አልኩት ።

ሰላም ይሄ በእንደዚህ አይነት ነገር አይሆንምኮ ሄዶ በለመነ ቢሆን ያ ሁላ ሰው ወረፋ አይጠብቅም ነበር።

እሺ ቆይ ምን ላድርግ ልዑል እ ዛብሎኔም አዲስ የሚወለደው ህፃንም ካላባት ይቅሩ እእ ንገረኝ እኔን ባትወደኝ እንኳን ለልጅህ ስትል አትኖርም እንዴ በድጋሜ እሱን መቆጣት ጀመርኩ ።

ሰላም ምንምኮ አልተረዳሽኝም እኔምኮ ለመኖር በህይወት ለመቆየት ለመታከም ለመዳን እየሞከርኩ ነው  አለኝ።

መሞከር ሳይሆን አድርገው ወይስ አሁንም  መቅዲ ያንተ ስላልሆነች መኖር አትፈልግም አልኩት ።

የዛኔ ብስጭት ብሎ ሰላም ለመዳን ለመታከም ስሞክር እንደዛ እንደዛ ሆንሽብኝ ጥለሽኝ እስከመሄድ ድረስ ደረስሽ ዛሬ ደሞ መቅዲ ምናምን ትያለሽ በቃኝ አሁንስ ህይወቴን ቁጭ አድርጌ እንደፊልም ስተርክልሽ ቆይቼ መልሰሽ ከዜሮ ትጀምሪያለሽ እንዴ ብሎ ጥሎኝ ከቤት ወጣ እየሮጥኩ ለመከተል እንኳን አቅም አጣሁ ።

ጉልበቴን አቅፌ ተደፍቼ ማልቀስ ጀመርኩ።

ምንድነው ማደርገው እንዴት ይሄን እንኳን እስከዛሬ ማወቅ ይከብደኛል እንዴት ባሌ ብዬ አብሬው እየኖሩክ ችግሩን ውስጡን ያስጨነቀውን ነገር ጠጋ ብዬ አልጠይቀውም ምኗ ደደብ ነኝ ድምፅ እያወጣሁ ማልቀስ ጀመርኩ መሲ መጥታ እንድረጋጋ ቢያንስ ለልጄ ጤንነት ስል እንድረጋጋ ነገረችኝ ።

ስለ ጨነቀኝ ከቤት መውጣት ፈለኩ ግን አልችልም በቅጡ መንቀሳቀስ እንኳን አይፈቀድልኝም ።

እንዳልደውልለት ስልኩን ቤት ትቶ ነው የወጣው

ይቀጥላል

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

27 Nov, 13:09


"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

የተነፋው የታች ቦርጩ
በደሃ ኪስ የጠገበ
የሱን ጎጆ ልስን ሲያበጅ
የኛን ድንኳን አረገበ
ሽፍን ጭንብል ለፊቱ መልክ
ቢፈለስፍ ጥሩ መስሎ
ባዶ እንደሆን ያው ባዶ ነው
እንጨት አይሆን ክሰል ከስሎ
ዲግሪ ዲስኩር ተጫጭኖ
ምሁር ነኝ ቢል የተማረ
የኛን ህይወት ጣል አድርጎ
የሱን ህይወት አሳመረ

"እናት አልባ"....አልኩት
በጭካኔ መንፈስ
አይኑ ካይኔ ፈጦ
ተኮሰብኝ እሳት ጥይት
ካፎቱ ላይ ሹል አውጥቶ
ደም ይረጫል ከደረቴ
ወለል ክፍሉን አበስብሶ
የተበደልኩ እኔ ሳለሁ
ይገለኛል ከሱም ብሶ

ዙፋን አርጎት ወንበር ስልጣን
ለተመካ በሰዓቱ
ጊዜ እንደሆን ሰው አይደለም
ያሳየዋል ሁሉን ፊቱ
ከዕለታት መሐል አንዲት ዕለት ቆጥሮ
ክፍያ አለው ሁሉም ምላሽ
አይዘገይም ጊዜ ቀጥሮ

"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

ተኮሰብኝ አካሌ ላይ
ገድል ፃፈ...ሰብሮ ገድል
በጊዜ ላይ ለነገሰ
አያነሳም የፅዋ ድል

ለፍቶ መና...ለፍቶ ከንቱ
በሆነባት በዚች አለም
የጊዜ ነው እንጂ
የሰው ጀግና የለም


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

26 Nov, 10:26


ለሊት 7፡00 ግቢያችን ሌባ ገባ። ሌባው ከሄደ በኃላ የቤቴ አከራይ ጋሽ በላቸው ባደረጉት የቴክኒክና የታክቲክ ጥናት መሰረት መጀመሪያ ሌባው የግቢውን በር ለመውጫ እንዲያመቸው አድርጎ አዘጋጀ።...በመቀጠል የእያንዳንዱን የግቢ ተከራይ የቤት በር ከውጪ ቀረቀረ(ለምን? ቢጮህበት እንኳን ሰው ወዲያው ከቤቱ ወጥቶ እንዳይዘው በሚል)።...በመጨረሻ የእኔን የደሀውን በር ሰርስሮ ከፍቶ ገባ። ሰርስሮ ማለቴ እንኳን ለደንቡ ነው፤ የኔ በር ባይሰረስሩትም ከ 45ኪሎ በላይ የሆነ አንድ ሰው በአመልካች ጣቱ ገፋ ቢያደርገው እራሱ ብርግድ የሚል በር ነው። ብቻ ሌባው ቤቴ ገባ....

ኮሽታ ሰምቼ ብንን ስል ቤቴ በመጣበቡና የሚያነሳው ነገር በማጣቱ ምክንያት ሌባው እንደ ምድር በራሱ ዛቢያ ይሽከረከራል። ሳስበው ከቤቴ ምንም የሚዘርፈው ነገር እንደሌለኝ ገባኝ። በቃ ሲወጣ እጮሀለው ብዬ አይኔን ገርበብ አድርጌ አየው ጀመር። ጥቂት አማተረ አማተረ ፈታተሸና ጭንቅላቱን እየወዘወዘ "አይ ድህነት..." ብሎ ጠዋት ጠዋት ለቁርስ በዳቦ የምቀባትን የለውዝ ቅቤ ብልቃጥ ብድግ አድርጓት እግሩ ወጣ እንዳለ "ኡኡኡኡ...."ብዬ ያለ አንዳች ወንዳወንዳዊ እፍረት ጩኸቴን አቀለጥኩት።

ሌባው መለስ ብሎ "ኧረ ሳይኖርህ አታንባርቅ ..." ብሎ ተፈተለከ።

ከቆይታ በኃላ ከውጭ የቀረቀረባቸውን የጎረቤቶቼን በር እየከፈትኩ ሁሉም ዱላና ፍልጡን ይዞ ተሰበሰበልኝ። ጎረቤቶቼ "ወይ አብርሃም ም'ፅፅ! ዋናው ብቻ ነፍስህ መትረፉ ...ገለው እኮ ይሄዳሉ...ባለፈው እዚህ እታች መንደር አይደል እንዴ..." እያሉ ትንሽ የሌባ ታሪክ ዘገባዎችን እየመዘዙ ካወሩ በኃላ አከራዬ አቶ በላቸው አንሶላቸውን እንደተከናነቡ በሀል ላይ ቆመው "ግን ምን ወሰደብህ...?" ብለው ጠየቁኝ። ያኔ ነው ጥሩ ሰይጣናዊ ሀሳብ ብልጭ ያለልኝ

ዓይኔን እንባ እንዲጎበኘው ጭምቅ እያደረኩት..."ጠዋት እሰጦታለሁ ብዬ ያስቀመጥኩትን የቤት ኪራይ 5000 ብር ነው ይዞት የሄደው ጋሼ...ኧረ በያዘው ጩቤ ሊወጋኝ ሲል ሽል ባላልኩት... ኧረ ገሎኝ በሄደ ምነው....ምነው በያዘው ቆንጨራ በከተከተኝ ...ኧረ አሁንስ እኔ ይሄ አመት አልሆነልኝም። ብሄድ ይሻላል....ኧረ ዕድሌ...." እያልኩ ብክንክን አልኩ።

የአከራዬ ሚስት እማማ ዝናሽ "ተው እንደሱ አይደለም የኔ ልጅ ብር እኮ ይተካል...ዋናው ነፍስህ መትረፉ " ብለው ከተቀመጡበት ተነስተው ፀጉሬን እያሻሹ ባልተቤታቸው አቶ በላቸውን መመልከት ጀመሩ። ተከራዩ በሙሉ እሳቸው ላይ አፈጠጠ።

አከራዬ ጥቂት ዝም ካሉ በኃላ "ምን እንደው!....በቃ የዚህን ወር የቤት ኪራይ ምሬሀለው....ኪራይህን ማታ መስጠት ስትችል ልጅ አብርሃም አየኸው የተፈጠረውን? ...ሁሌ ሳምንታትን ካላዘገየህ መች ሰጥተኸኝ ታውቃለህ?....ከቀጣይ ወር ጀምሮ ይሄን ነገር አስተካክል..." ብለው ገሰፁ።

"እሺ ጋሼ ባይሞላልኝ ነው አስተካክላለሁ..." ብዬ የሌለኝን እንባ ጠረግኩ። ሁሉም "በል በርህን አጥብቅና ዝጋ" እያለ ቀስበቀስ ከቤቴ ተበትኖ እቤቱ ገባ።

በሬን ዘጋሁና 'አልያሼ ሹንቡራ' እያልኩ ድንስ 🕺...ከዛ ለጥጥጥጥ.....

"አሃሃ....ሌቦ ነይ" 😊🕺

Abrham F. Yekedas

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

25 Nov, 15:58


የፍቅር ማእበል

    
      ክፍል 63


በ4ኛው አመት ላይ የራሴን ኤጀንት ከፈትኩኝና የራሴን ሰራተኞች ቀጠርኩ ሴልስ ሆኜ ከማገኘው 3 እጥፍ ማግኘት ጀመርኩ ከዛ ቡሀላ የባንክ እዳዬን እየከፈልኩ ገንዘብ እንደልቤ ማግኘት ማጥፋት ጀመርኩ።
ገንዘብ አንዴ እስኪመጣ ነው እንጂ ከዛ ቡሀላ በራሱ  ሰአት ወደ አንቺ ይጎርፋል ።

በየቀኑ የኔ ማርኬት ስሙ እየሰፋ እየታወቀ መጣ ።
የኔም ተራ ሰው መሆን ቀረና  አለቃ ሆንኩኝ።
ገንዘብ ሲኖርሽና አለቃ ስትሆኚ በራሱ የምትላበሽው ገፀ ባህሪ አለ ።

የራሴን መኪና ገዛሁ አትክልት ቤቶችን በሙሉ ተዘጉ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው የራሱ መኪና ያለው ደሞዝ ከፋይ ሆንኩኝ።

ከዛስ አትይም ገንዘቡ ሲመጣ ሰው መፈለግ ጀመርኩ እናት አባት ዘመድ ጓደኛ  አጣሁ በአል ሲመጣ ቤቴ ውስጥ ድግስ ተደግሶ አያቅም ለማን ይደገሳል ።

ለኔ በአልም ሆነ ሌላ ቀን ልዩነቱ አልታይ አለኝ።
  በአልም ሲሆን ውጭ ነው ምበላው ኖርማል ቀን ላይም ውጭ ነው ምበላው።

በኔ ስር ብዙ ሰራቶኞች አሉኝ እነሱ በአል ሲደርስ ያስፈቅዱኛል ዘመድጋ ሄደን ነው ሲሉኝ እኔ በነሱ መቅናት ጀመርኩ።

ከዛ ልሙት ልኑር ወደ ማያቁት ወንድሞቼ ሄድኩና አሁን ሀብታም ነኝ ከናንተ ምንም አልፈልግም ወንድምነታችሁን ብቻ ነው ምፈልገው አልኳቸው ።

ሁሉቱም አሪፍ ሚባል ኑሮ ላይ ነበሩ ግን አሁንም ያን ያህል ትኩረት አልሰጥ ሲሉኝ አብረን እንድንሰራ ሀሳብ አቀረብኩላቸው ምናልባት በስራ ምክንያት ከተቀራረብንና ወንድማማቾች ከሆንን ብዬ።

ከዛ የጋራ ድርጅት ከፈትን ካሰብነው በላይ ስኬታማ ሆንን ውስጣችን የእውነተኛ ወንድማማችነት ስሜት ባይኖርም ቢያንስ ወንድሞቼ እያልኩ ለማውራት በቃሁ።

ከዛ ቡሀላ ታክሜ ሰው መሆን እንዳለብኝ ወሰንኩና ዶክተሩጋ ሄድኩ እረፍዷል አለኝ።

ትናት ታክመህ መዳን ስትችል ገንዘብን አሳደድክ አየህ ከታከምክ ቡሀላም ገንዘብን ማሳደድ ትችል ነበር ።

ለሷ ስትል ሀብታም የሆንክላት ሴት ዛሬ አብራህ የለችም ልታድንህ አትችልም ።

እስቲ አሁን ያገኘኸው ገንዘብ ጤነኛ ሲያደርግህ ከልብህ ስትደሰትበት ታያለህ አለኝ ።

ዝም ብዬው ተነስቼ ወጣሁ በስራ ምክንያትም ይሁን በሆነ ነገር ትንሽ ስበሳጭ ባፌም ባፍንጫዬም ደም ይፈሰኛል። ካልተናደድኩ ፀሀይ ላይ እረጅም ሰአት ካላሳለፍኩ - ካልተበሳጨሁ ግን ነስርም ይሁን ህመም የለብኝም ።

ከሆነ ሰአት ቡሀላ ለመታከም የነበረኝ ሀሳብ ሁላ ጠፋ እንደዛ የለፋሁለት የደከምኩበት ሀብት ደስታን አይሰጥሽም። ለካ የውስጥሽን ሰላም ደስታ ሙሉ ሚያደርገው ሰው ነው።

መንገድ ላይ መኪና እየነዳሁ ስሄድ ብዙ ሴቶች ሊያስቆሙኝ ሊፍት ሊጠይቁኝ ይሞክራል እኔ ግን በጣም እናደዳለሁ  ትናት ጎዳና ላይ እያለሁ ቢሆንኮ በእግራቸው ክፍ ብለውኝ ነበር የሚያልፉት እኔ ያ የትናቱ ልጅ ነኝ እላለሁ።

ከዛ ቡሀላ የመታከም ሞራሌ ጠፋ ብኖርስ ለማነው ብሞትስ ለማነው በቃ ከሞትኩም ልሙት ፈጣሪ ካቆየኝም ልቆይ ብዬ ዝም ብዬ መኖር ጀመርኩ።
ለመኖር የሚያጓጓኝ አንዳች ነገር የለም ማታ ስተኛ ጠዋት ስለመነሳቴ እርግጠኛ አደለሁም ግን እተኛለሁ ።

የሆነ ቀን እራሴን ጠየኩኝ ምንም ቢሆንኮ ከመሞት መኖር ይሻላል ብዬ በድጋሜ ለመመርመር በሄድኩበት ሰአት ነበር ካንቺጋ ተጋጭተን የተዋወኩሽ ።

ካንቺጋ ከተዋወቅን ቡሀላ መጀመሪያ ሰሞን ለምን እንደማገኝሽ አላውቅም ግን አገኝሻለሁ ።

ከማክቤል አረገዝኩ ያልሽኝ ቀን ሌሊቱን ሙሉ ከራሴጋ ስማከር አደርኩኝ ቢያንስ እኔ ስሞት የልጁን ስም ልዑል ብትለውኮ ለኔ መጠሪያ ይሆነኛል ።

እኔ ብሞት ትናት ሲርበኝ ሲጠማኝ ዞረው ያላዩኝ ወንድሞቼ ናቸው ቀድመው ከፊት የሚሰለፉት ገንዘቤን ለመውሰድ።

ስለዚህ ቢያንስ አንቺንና ምስኪን እናትሽን ልጅሽን በሰላም እንድትኖሩ ማድረግ ከቻልኩ ልፋቴ መና አይቀርም ብዬ ነበር።

እኔ ተጋብተን እየኖርን ሁላ ላንቺ ስሜት አልነበረኝም እንዲሁ ደስ ትይኛለሽ ባየሁሽ ቁጥር መቅዲን ታስታውሽኛለሽ።
ቀስ በቀስ ግን አንቺ ከመቅዲጋ ምትወዳደሪ ሴት አልነበርሽም የራስሽ ፀባይ የራስሽ መልክ የራስሽ አቋም አለሽ ግን የሁል ጊዜ ስጋቴ እኔ መቅዲን በቀላሉ ልረሳት እንዳልቻልኩት አንቺም ማክቤልን መርሳት ባትችይስ ብዬ አስባለሁ ። እኔን አቅፈሽ በተኛሽ ቁጥር ስለሱ ብታስቢስ ፍቅሩ በቀላሉ ባይወጣልሽስ ብዬ አልጋ ለይቼ ለብቻዬ መተኛት ጀመርኩ ግን
አንችን ቀርቦ ተግባብቶ አለመውደድ ቀላል አደለም።

በየቀኑ ልክ እንደሱስ ስራ ቦታ ደርሼ እስክመለስ ትናፍቂኝ ጀመር ። ያለመደብኝን ቤቴን እንድናፍቅ እንድወደው እያደረግሽኝ መጣሽ ዛብሎኔ ከተወለደ ቡሀላ ደሞ ይበልጥ ባሰብኝ መኖር ምን ያህል እንደሚያጓጓ ተረዳሁ ለካ ከመቅዲ ቡሀላ አግብቼ መውለድ እችላለሁ የሚለውን ስረዳ እራሴን ለማዳን መሯሯጥ ጀመርኩ ።
ልጄን በሆድሽ እንደያሽ ስትነግሪኝ ደሞ እዚህ ምድር ላይ መቆየት ምርጫዬ ሳይሆን ግዴታዬ እንደሆነ አመንኩኝ።
ስራ ከምገባበት ይልቅ ለበሽታዬ የሚሆን ዶክተር ምፈልገበት ሰአት በዛ።

ከተማዋ ውስጥ አለ የተባለ ስፔሻሊስት ዶክተርጋ ሄድኩኝ የመዳን ትንሽ ተስፋ እንዳለኝ ግን ከኔ በፊት በጣም ብዙ ሰዎች ለመታከም ወረፋ እንደያዙ ነገረኝ።

የኔ ተራ እስኪደርስ ብሞትስ  ብዬ ፈራሁ ዶክተሩ ቀዶ ህክምና አድርጎ ጨርሶ እስኪያርፍ ድረስ እጠብቅና ባለችው  ትንሽ ሰአት  ገና በደንብ ለተጠናከረ ምርመራ ብቻ ከመጠን በላይ የሆነ ብር እየከፈልኩት መታየት ጀመርኩ ።

ላንቺ ያልነገርኩሽ እንዳትጨነቂ እንዳትረበሺ ብዬ ነው ምናልባትም ስሞት እንደሞትኩ ማወቅሽ አይቀርም ከተረፍኩ ደሞ እንደዚህ ሆኜ ነበርኮ አሁን ግን ተረፍኩልሽ ብዬ አብረን እናወጋዋለን ብዬ ነበር ግን አንቺ ልትታገሺኝ አልቻልሽም ጭራሽ እራሴን አድናለሁ ብዬ ልጄን ላጣው ነበር ። በሱ ድንጋጤና ጭንቀት እንዳዲስ ነስሩ ተነሳብኝ መጠጣት በፍፁም አይፈቀድልኝም ግን ስጠጣ የተፈጠረውን አየሽ አደለ

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

24 Nov, 18:50


የፍቅር ማእበል

      ክፍል 62

ምሽቱን ሙሉ ዶክተሩ ስላለኝ ነገር ሳስብ አመሸሁ ።
ወደቤት ከተመለስኩ ቡሀላ አዲሱ ፕሮግራማችን ቤት መግዛት እንደሆነ ሌላም ተጨማሪ ሱቆች እንደምንከፍት ነገርኳት።

እንዳልኳትም የመጀመሪዋን ሱቅ ሌላ ሰው አስገብተንባት እሷ እኔ ምሰራበትጋ ገባች እኔ ደሞ አዲስ የከፈትኩትን ማጧጧፍ ጀመርኩ።

እንደዛ እንደዛ እያልን  ስራችንን ወጥረን እየሰራን ለዶክተሩ አሪፍ ብር እንደያዝን ነገርኩት ።
ብድር ያለባቸው ቤቶች አሉ አናንተ ለሰዎቹ የእጅ የተወሰነ ትከፍሉና ብድሩ ስንት ሚሊየን ብር ቢሆንም ወደናንተ ይዞራል ከዛ እናንተ እየሰራችሁ ትከፍላላችሁ ሰዎች ለእጅ ትንሽ ነው ሚፈልጉት አለኝ በደስታ ተስማማሁ እንዳለውም እሱ ከሚያቀቸው ሰዎች ላይ ይሄ ቤት ተገዛ ። አከራየሁትና ለባንክ ምከፍለውን እዳ ከሱቆቹ ከማገኘው በላይ የዚህ ቤት ኪራይ ይሸፍንልኝ ጀመር

ይሄ ሁላ ነገር እየተፈጠረ እያለ ለካ እሷ ከኔ ፍቅር ይዟታል እኔ ግን አንድም ቀን አስተውያት አላውቅም  ብድራችንን በአሪፍ ሁኔታ እየከፈልን አሪፍ ገቢ እያገኘን እያለ እሷ ከዛ በላይ መታገስ እንደማትችልና በጣም እንደተጎዳች ስለመቅዲ ባወራሁላት ቁጥር ውስጧ እየተሰበረ እንደሆነ ወደ ቤተሰቦቿ ተመልሳ ያደረጓትን ቢያደርጓት እንደሚሻል ፅፋልኝ ጥላኝ ጠፋች።

አሪፍ ተነሳሁ ሄድኩ ትልቅ ደረጃ ልደርስ ነው ብዬ ሳስብ እንደገና ወደ ኋላ እመለሳለሁ ።

ታማኝ ሰው ለማግኘት መከራ ሆነብኝ በሂሳብ መጨቃጨቅ አስጠላኝ።
ሌላ ተጨማሪ ሰራተኛ ባስገባም ትርፉ ከበፊቱ እየቀነሰብኝ መጣ ።

የባንክ እዳዬን ለመክፈል ደሞ ከበፊቱ የበለጠ ገቢ እንጂ ያነሰ መሆን የለበትም ተመልሼ ወደ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ ።

እዛው ደንበኛዬ የነበረ አንድ ሰውዬጋ በቅርበት እያወራን ስላጋጠመኝ ነገር ነገርኩት ።

አሪፍ አቋም እንዳለኝ ንግግር ላይም ቆንጆ እንደሆንኩ ነገረኝና ለምን እኛ ድርጅች አትገባም አለኝ ።

ምን እንደሚሰራ ቀረብ ብዬ ጠየኩት ነገ ቢሮ ናና እናወራለን ጠዋት መጥቼ እወስድሀለሁ ብሎኝ ሄደ ።

በነጋታው 3 ሰአት አካባቢ ሱቅ መጣና ሊያወራኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ ።
እዛው ሱቅ ሆኜ እንዲያወራኝ ዘግቼ መሄድ እንደማልችል ነገርኩት ።

እሺ ስራው cells  መሆን ነው እንደዛ ስልህ እንዴት መሰለህ ሙሉ ፕሮቶኮልህን ጠብቀህ ሱፍ ለብሰህ መንገድ ላይ ፋርማሲይ  ሱፐር ማርኬት ስጋ ቤት ብቻ ማንኛውም ሰው ሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ እየተገኘህ ሰዎች ሪል እስቴት እንዲገዙ ታደርጋለህ ቢያንስ 2 ቤት ብትሸጥ በጣም ብዙ ብር ታገኛለህ እዚህ ወር ተመላልሰህ ማታገኘውን ብር እዛ ባንድ ቀን ታገኘዋለህ ሳይህ አሪፍ እድሜ ላይ ነህ መልከ መልካምም ስለሆንክ ከሰዎችጋ መግባባት ከቻልክ ቀላል ነው አለኝ።

በደስታ ተስማማሁ ግን እኔ ሱፍ ሚባል ለብሼ አላቅም ደሞም አልወድም አልኩት።

ሱፉ ብር ነው ብለህ አስበው ለገንዘብ ስትል ማትወዳቸው ነገሮች ቢኖሩ እንኳን መውደድ አለብህ አለኝ።

ከዛ በስራው ተስማማሁና ሶስቱም ሱቄ ውስጥ ሌሎች ሰዎችን ቀጥሬ እኔ ወደዛኛው ስራ ሄድኩኝ  መጀመሪያ አካባቢ የገዛሁት ሱፍ በራሱ ምቾት አልሰጠኝም ነበር ስራውም እኔ እንዳሰብኩት አልነበረም።
ቀን ሙሉ ፀሀይ ላይ ነው የምትውይው ድካም አለው ።

ከዛ በተቃራኒው ደሞ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው ለደንበኞች ስልክ በመደወል ብቻ ሚውሉም አሉ።

ጠንክረሽ ከሰራሽ ሁሉም ስራ እዳ ከፋይ ነውና በዛን አመት የአመቱ ምርጥ ሴልስ ተብዬ ተሸለምኩ አንዳንዶቹ አሪፍ ሰርተው አነስ ያለች መኪና ምናምን ሲገዙ እኔ ቀጥታ የባንክ እድዬን ነው ምከፍለው ።

ያንን ስራ እየሰራሁ አትክልት ቤቱም ቆንጆ ደንበኛ ስለነበረን ገበያውም ቆንጆ ስለሆነ የብር ችግሬ እየተቀረፈ መጣ ።
እሁድ ነበር ቀኑ መቼስ መቅዲ በእሁድ ቀን ከእናትና አባቷ ቤት አትቀርም ብዬ ሰፈሯ ሄድኩኝና በሆነች ልጅ  ብስኩት ግዥልኝ ብለሽ አስወጫት ብዬ አስጠራኋት ።

ወደኔ ስትመጣ ስታየኝ ደነገጠች ሁለት ደቂቃ ብቻ ስጭኝ ብዬ ለመንኳትና ምን የመሰለ ቪላ ቤት እንደገዛሁ 3 ሱቅ እንደከፈትኩ ነገርኳት ። ከት ብላ እየሳቀችብኝ አስጠንቁለህ ነው ሰርተህ አለችኝ።

እንደፈለግሽ አድርገሽ አስቢው ግን አሁን ባልሽን ፈተሽ ከኔጋ መሆን ትችያለሽ ። አሁን አሪፍ ገቢ አሪፍ ስራ አለኝ ቤተሰቦችሽም ይቀበሉኛል አልኳት።

እሷ ያወራሁትን ከምንም ሳትቆጥረው አንደኛ ያኔ ስለተውኩህ ልትበቀለኝ እንጂ አሁንም ድረሰ ወደኸኝ አደለም ሁለተኛ ደሞ አሁን ላይ ባሌን አፈቅረዋለሁ የሚቀናው የሚናደድብኝ ስለሚያፈቅረኝ ትቼው እንዳልሄድ ስለሚፈራ ነው አሁን ሁሉንም ተረድቼዋለሁ አለችኝና ሁለተኛ አጠገቧ እንዳልደርስ አስጠንቀቃኝ ትታኝ ሄደች እኔም እዛው በቆምኩበት በፈጣሪ ስም ማልኩኝ ከዛሬ ጀምሮ መቅዲ ለኔ ሞታለች ከዚህ በላይ ሀብታም ሆኜ ካላሳየኋት እኔ ልዑል አደለሁም አልኩኝ።

ለተከታታይ 3 አመት ሴልስነቱን  ሰራሁኝና የቤት እዳዬን 75% ከፈልኩ በየአመቱ የአመቱ ምርጥ ሰራተኛ ምርጥ ሰራተኛ ተብዬ እየተሸለምኩ ነበር ።

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

23 Nov, 17:56


የፍቅር ማእበል


  
         ክፍል 61


እሺ ነይ በቃ ብያት ወደቤቴ ይዣት ሄድኩ ቤት ከገባን ቡሀላ ጥጓን ይዛ ተቀመጠች።

እዛ 2 ሱቅ አለኝ ምናምን ስትልኮ ቤትህን እንደዚህ አልጠበኩም አለችኝ።

ቁጭ አድርጌ ሌሊቱን ሙሉ  ታሪኬን ነገርኳት ታሪኳን ነገረችኝ ።

ታቂያለሽ ነጭ ወረቀት ማለት ናት ነገሮችን በቀጥታ ብቻ ነው ምታየው ወደ ግራ ወደቀኝ አጣማ አታስብም እራሷን በሆነው ባልሆነው አታስጨንቅም ሀይማኖቷ ላይ በጣም ጠንካራ ናት ።

በነጋታው እኔ ሌሊት ፒያሳ ደርሼ ምሸከመውን ጨርሼ ለራሴ ሚያስፈልገኝን እቃ ጭኜ  ተመለስኩ።

ሱቅ ከመክፈታችን በፊት ልብስ ቤት ይዣት ሄድኩና ሙሉ ቀሚስና ክፍት ጫማ ገዛሁላት ከዛ መልስ ፀጉሯን አሰራኋት።

ከዛ በየቀኑ ልብስ መቀየር አይጠበቅብሽም ግን ያለችሽን ነገር ፀዳ አደርገሽ መልበስ አለብሽ የሰው ልጅ በምን እንደሚለካሽ አታቂውም አንዳንዱ በለብሽው ልብስ ይለካሻል አንዳንዱ ባነጋገርሽ አንዳንዱ ደሞ በመልክሽ ብቻ በምን ሁኔታ ውስጥ ብትሆኚ ሰዎች አውርደው እንዲያዩሽ እንዳታደርጊ ደንበኛን በክብር አስተናግጂ ሊገዙሽ ሲመጡ አሳስቂያቸው በፈገግታ ተቀብለሽ በፈገግታ ሸኛቸው ከዛ እኔም አሪፍ እሰራለሁ አንቺም አሪፍ ትሰሪያለሽ ከዛ በቃ አብረን እንቀየራለን አልኳት ።

ከዛ በቃ እሷም እዛ በደንብ መስራት ጀመረች እኔም መስራት ጀመርኩ ሌላ የኔን ፍራሽ ምታክል ፍራሽ ገዛንና ቀን ቀን አደራርበን አንጥፈናት እንወጣለን ማታ ማታ ደሞ ለየብቻ አንጥፈን እንተኛለን።

ማታ እኔ ሱቅ ዘግቼ እስክመለስ ድረስ እሷ ሱቅ አትዘጋም እኔ ስደርስ ነው አብረን ዘግተን ወደ ቤት ምንገባው ።

ሰፈሩ ላይ እንዳለ ሚስቴ እንደሆነች ነው የሚያቁት እኔን መንገድ ላይ ሲያገኙኝ አንተም ቆንጆ እሷም ቆንጆ ፈጣሪ ይባርካችሁ ይሉኛል እኔም አሜን ብዬ አልፋለሁ።
ስራችንን አጧጧፍነው  እሷም እኔም ወጥረን ነው ምንሰራው ሰዎችን እንዴት ትሪት ማድረግ እንዳለባት ከኔ በላይ የገባት ናት ደንበኞቿ አቆላምጠው ነው ሚጠሯት ።
ብዙ ወንዶች ከሱጋ በድህነት ከምትኖሪ እኔ አንቀባርሬ ላኑርሽ ይሄንን መልክ ይዘሽ ምን በወጣሽ ይሏታል ።

እኔ በየቀኑ በገባን በወጣን ቁጥር ስለመቅዲ ነው ማወራት በፊት አዳማጭ ስላልነበረኝ ብዙም አላወራም ነበር እሷ ቤቴ ከገባች ቀን ጀምሮ ግን አዳማጭ አገኘሁ በወጣሁ በገባሁ ቁጥር መቅዲ መቅዲ እላታለሁ እሷም ሳትሰለች ትሰማኛለች አሁን ሳስበው ታሳዝነኛለች ።

እሷም ገንዘብ አያያዝ ላይ ቆንጆ ስለነበረች እኔም ገንዘብ ስለማላጠፋ በየቀኑ ገቢዬ እያደገ እያደገ ሄደ ለዶክተሩ ሄድኩኝና ያገኘሁትን ገንዘብ ምን ላይ ባውለው ነው ሚሻለኝ ገንዘብን የሆነ ነገር ላይ invest  ካላደረከው ዋጋው እያነሰ ነው ሚሄደው አልኩት ።

እራስህ ላይ invest አድርገው እራስህን ስራው ታከምበት አሁን ነገ ተባብሶ ሌላ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ታከምበት በቀላሉ ብር መዳን እየቻልክ ነገ መዳን ማትችልበት እድሜ ላይ ስትደርስ እንዳይቆጭህ አለኝ ።

ችግር የለም መጀመሪያ ገንዘብ ላግኝ የገፉኝ የናቁኝን ሰዎች አፋቸውን ላሲዝ የማፈቅራትን ልጅ የኔ ላድርጋት እሷ አብራኝ ካለች እኔ ጤነኛ ባልሆንም ጤነኛ ነኝ አልኩት ።

ጥሩ እንደዛ ከሆነ ካሁኑ በተሻለ የተወሰነ ስራና ቤት ትገዛለህ አለኝ።

ከት ብዬ ሳኩበት እኔኮ ቤት መግዛት የሚያስችል ገንዘብ አደለም አጠራቀምኩ ያልኩህ እንዲያው በፊት በባዶ እጄ ስለነበርኩ አሁን ያለችኝ ብዙ ሆና ታይታኝ ነው እንጂ አልኩት። 

ችግር የለም እንዴት እንደምታደርግ እኔ ነግርሀለሁ ጎበዝ ነህ ማንም ሰው ባንተ እድሜ አንተ ሰርተህ ያገኘኸውን ያህል ሰርቶ ማግኘት አይችልም ጥንካሬህን እወድልሀለሁ አደንቅልሀለሁ ።

ግን አሁንም በድጋሜ ምነግርህ ነገር ነገ ሚቆጭህን ነገር እንዳታደርግ ገንዘብ ስታገኝ እራስህን ካጣኸው ዋጋ ቢስ ነህ ፍቅረኛህም ብትሆን ገንዘብ ሳይኖርህ ትታህ ሲኖርህ ወዳንተ ከመጣች ይቺ ሴት የገንዘብህ እንጂ ያንተ ሚስት አደለችም መጀመሪያ እራስህን አድንና ጤነኛ ሁን ከዛ ትደርስበታለህ አለኝ።

አይ ዶክተር ተሳስተሀል  መቅዲ ተገዳ እንጂ ፈልጋ አደለም የተወችኝ ።

በቃ እሺ እንደተመቸህ መልካም ቀን መሄድ ትችላለህ አለኝ በእጁ ወደ በሩ እየጠቆመ ።

እሺ ብዬ ተነስቼ ወጣሁ ቤት ካለኝማ ሌላ ምን እፈልጋለሁ ቤት ካለኝኮ ባንዴ መቅዲን የኔ አደርጋታለሁ ቤተሰቦቿም ይቀበሉኛል ከዛ እታከማለሁ ወይ ደሞ ፈጣሪ ያለፍኩበትን ችግር አይቶ ይምረኝ ይሆናል እያልኩ ወደ ሱቄ ተመለስኩ።

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

22 Nov, 17:13


የፍቅር ማእበል



        ክፍል 60

ከዛ ትንሽ እራቅ ያለ አስፋልት ዳር የሆነ ከመጀመሪያው ሰፋ ያለ አትክልት ቤት  ተከራየሁ ።

ከዛ ግን የመጀመሪያው ቤት ሰው አስፈለገኝ እዛው ሰፈራችን የነበረ አንድ ልጅ ቀጠርኩኝና እኔ አዲስ የከፈትኩትን ሰዎችን በፈገግታ እየተቀበልኩ እየተግባባሁ አላመድኩት በጣም ብዙዙ ሰዎችን ደንበኞቼ አደረኩኝ ።

ነጋዴ ስትሆኚ መረቅረቅ ማድረግና ቆንጆ እቃ ከያዝሽ የደንበኛ ችግር አይኖርብሽም ትርፉን ደሞ ከብዛት ታገኝዋለሽ ።
ብዙ ሰዎች የሚሸወዱት የደንበኛው ፍላጎት ላይ ሳይሆን የሚያገኙት ገንዘብ ላይ ትኩረት ስለሚያደርጉ ነው።

ሁለቱም ሱቄ ውስጥ አሪፍ ለመስራት እየሞከርኩ ነበር ግን  ትንሿ ሱቄ ውስጥ የቀጠርኩት ልጅ ምንም ሊታመንልኝ አልቻለም ገንዘብ ያጭበረብረኛል ከትርፉ ኪሳራው ሲበልጥብኝ አስወጣሁትና ሱቁን ለመዝጋት አሰብኩ እንዲህ አይነት ስራ ላይ ታማኝ ቤተሰብ ሲኖርሽ ነው ቆንጆው ።
ዝም ብዬ ትንሹን ሱቅ ዘግቼ አዲስ የከፈትኩት ሱቅ ቁጭ ብዬ በሀሳብ ተመስጫለሁ ምን እያሰብኩ እንደነበረ ግን አላውቅም ።

አንዲት ገና አስራዎቹ መጨረሻ አካባቢ ያለች ልጅ መጣችና እባክህ እርቦኝ ለምሳ ሚሆን ብር ስጠኝ አለችኝ ።

ታቂያለሽ ልቅምም ያለች ቆንጆ ናት እዚጋ ጎሏታል አትባልም ከመቆሸሿ ውጭ ።

አየኋትና ወደ ውስጥ እንድትገባና ምሳ አብረን እንደምንበላ ነገርኳት እሺ ብላ ገባች።

ከዛ የሆነችው በሙሉ ጠየኳት የክፍለ ሀገር ልጅ እንደሆነች በትምህርቷ በጣም ጎበዝ ተማሪ እንደነበረችና ለትምህርቷ ካላት ፍቅር የተነሳ ብዙ ባሎች ሲመጡላት ቤተሰቦቿን እንቢ እያለች እንደቆየች ከዛ ግን ቤተሰቦቿ አንድ ባለሀብት ከዚህ በፊት አግብቶ የፈታ ሰውዬ ለትዳር እንደጠየቃት ቤተሰቦቿም እንደተስማሙ እሱን ከማገባ ብላ ጠፍታ ወደከተማ እንደመጣችና ምንም ምታቀው ሰው ስለሌ ዝም ብላ በየመንገዱ እየለመነች እንዳለች ነገረችኝ።

ባለፈው የመሲን ታሪክ ስትነግሪኝ ቀጥታ ትዝ ያለኝ የሷ ታሪክ ነው መሲን ሳያት እሷን ያየሁ ነው ሚመስለኝ ውስጤ እንደዛ የተረበሸውም ለዛ ነው።

ከዛ በጣም ስላሳዘነችኝ የገጠር ሰውም ታማኝ እንደሆነ ስለምሰማ ለምን እኔጋ አትሰሪም አልኳት አነጋገሯ አስተያየተቷ ተግባሯ በዛ ሁላ ችግር ውስጥ ጎልቶ ሚታየው መልኳ ሁሉ ነገሯ አሳዝኖኝ ነበር።

አላመነችም በጣም ደስ አላት ምንድነው ግን ምሰራው አለችኝ ።

እንደዚህ አይነት ሌላ ሱቅ አለ እና አንቺ ስለተማርሽ ሂሳብ ያን ያህል አይከብድሽም ስለዚህ እኔ በምነግርሽ ዋጋ መሸጥ ነው።
ካንቺ ሚጠበቀው ደንበኞችን በፀባይ መያዝ ጎበዝ መሆንና ከምንም በላይ ደሞ ታማኝ መሆን አለብሽ ። አንድ ቀን የሆነ ማጭበርበር ባይብሽ ሁሌ እንደዛ ምታደርጊ ስለሚመስለኝ አንቺን ማመን ይከብደኛል ።

አረ በአርሴማ እኔ በምላሴ ማር አይሟሟብኝም ለቃሌ ሟች ነኝ አለችኝና የዛን ከኔጋ አመሸን እንዴት እንደምመዝን ሰዎችን እንዴት እንደማወራ ሂሳብ አሰራሬን ሁሉን ነገር ቁጭ ብላ ስታይ አመሸች።

ማታ ላይ በቃ እኔ ልዘጋ ነው ወዴት ነሽ ስላት እዚሁ አካባቢ አድራለሁ ችግር የለውም ነገ በሰአቴ እዚህ እገኝና ስራውን በደንብ ታሳየኛለህ አለችኝ ።

የችግርን ምንነት ከኔ በላይ የሚያውቀው የለምና አሳዘነችኝ ካልፈራሽና ምታምኚኝ ከሆነ ከኔጋ ማደር ትችያለሽ ቤቴ በጣም ጠበባ ናት ግን አንችና እኔን መቻል አያቅታትም።

የዛኔ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች እዚህ ጎዳና ላይ ስታድር ህመሙ ህመም እንዳይመስልህ ሌሊት እንቅልፍ ሚባል የለህም በመንገድ ለማለፍ የመጣው ወንድ ሁሉ ሊደፍረኝ ሊያስፈራራኝ እየመሰለኝ ሰውነቴ በሰቀቀን ያልቃል ።

አንዱ ሰካራም ይመጣና ይዤሽ ካላደርኩ ይለኛል ከሱ አምልጬ ደሞ ሌላምጋ ስሄድ ያዩኝ ወንዶች ይዤሽ ካላደርኩ ይላሉ ጎዳና ላይ ምታድር ሴት ለነሱ ስሜት ማብረጃ የተፈጠረች አድረገው ነው ሚያሰቡት ለሴት ልጅ ደሞ ክብሯን ጠብቃ መኖሯ ነው ትልቁ ማንነቷ  ።

እዛጋ ቆሽሸህ ታመህ ጠውልገህ ቢያዩህ ግድ አይሰጣቸውም የመጣው ወንድ ሁሉ ካልሰፈርኩብሽ ይላል። ከነሱ አመለጥኩ ስትል ደሞ ብርዱ አጥንት ድረስ ሰርስሮ ይገባል።  ታዲያ ከዚህ ስቃይ አንተን ማመኑ አይሻለኝም እእ ደሞኮ ገና ልጅ ነህ ፊትህም ሲታይ የገራገር ነው እሺ ካልከኝማ አብሬህ እሄዳለሁ አለችኝ።

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

20 Nov, 22:04


የፍቅር ማእበል.

    
      ክፍል 59

እሷ ግን የቤተሰቦቼን ደስታ ከምነፍጋቸው እኔ እንዲህ ብሆን እመርጣለሁ ካሁን ቡሀላ ለኔ ስሜት ባይኖርህ ነው ሚሻለው ብላኝ ጥላኝ ሄደች።

ከዛ ቡሀላ ይበልጥ ሀብታም መሆን እንዳለብኝ ገባኝ ለሷ ስል ቶሎ ቶሎ ሰርቼ ተቀይሬ መቅዲን የኔ አደርጋታለሁ ብዬ አሰብኩ ።

ይሄኔ እንዳለው ደም በደም ሆነ ከገባሁበት ተመስጦ አወጣኝ።

ደነገጥኩኝ ልዑሌ ልዑሌ እያልኩ እየጠራሁት ወደ መሲጋ እሮጥኩ  እሷ ባንዴ ታድነው ይመስል።

ባባን አቅፋ እያጫወተች ነበር ወደ አልጋው አስተኝታው እየሮጠች መጣችና ሶፍት ሰጠችው እኔ እየተናነቀኝ ስለነበር ወደ ሽንት ቤት እሮጥኩኝ የበላሁት እንዳለ ዝርግፍ ብሎ ወጣ ልዑሌ ደሙን እያንጠባጠበ እኔጋ  መጣና ይቅርታ ሰላሜ አሳመምኩሻ አለኝ።

ቀና ብዬ ሳየው አንጀቴን በላው ሰው እንዴት በዚህ ልክ ጠንካራ ይሆናል ብዬ አሰብኩ  አረ አንተ ምንም አላደረክም ታጠብ እና እረፍት አድርግ በቃ አልኩት።

እውነት ለመናገር ታሪኩን ለመስማት ጓጉቻለሁ እንዴት በዚህ ልክ ሀብታም ሆነ ታዲያ ግራ ገባኝ ።
አሁን ያለበት ሁኔታስ ምንድነው የጭንቅላት ህመሙ ብሶበት ይሆን ጭንቅላቴ ያለማቋረጥ ጥያቄ ያነሳብኛል።

ደሞ ስለ መቅዲ ሲያወራ የደበዘዘው ፊቱ ሁላ ይበራል ደሞስ ሰው እንዴት አንዲት ሴት ከድታው ሌላ አግብታ ድጋሜ ይቅር ብሏት አብሯት እስከመሆን የሚያደርስ ትግስት ይኖረዋል ምን ያህል ቢወዳት ነው ።

አሁንም ድረስ ያፈቅራት ይሆን እንዴ ለዛ ይሆናልኮ ዝም ሚለው ስለሷ ሲያወራም ደም በደም ሆነ ቆይ እኔን አሳዝኜው ይሆን እንዴ አብሯኝ የሆነው  ውስጤ ነዴትና ጉጉት አደረብኝ።

ልዑሌ ተጣጥቦ መጣና ሰላሜ አንቺስ ተረጋጋሽ ደነገጠሽ እንዴ እእ አለኝ።

አዎ ግን ታሪክህን ለመስማት በጣም ስለጓጓሁ ታሪኩን ጨርስልኝ አሁን አልኩት።

አይ ሰላሜ  ማታ እጨርስልሻለሁ ትንሽ ልረጋጋ  አንቺም እረፍት አድርጊ  አለኝ።

እኔማ ተረጌግቻለሁ አንተ ስትረጋጋ ትነግረኛለህ አልኩትና በጀርባዬ ተዘርሬ ተኛሀ እንዲሀ ተኛሁ ልበል እንጂ እንቅልፍ አልወሰደኝም ውስጤ ብክንክን አለ ንዴት ይሁን ምን አላውቅም ግን ታሪኩን ሲነግረኝ የመቅዲን ስም ባነሳ ቁጥር ውስጤ ብስል እያለ ነበር ።

እድለኛ ናት የልዑሌ የመጀመሪያ ፍቅር መሆኗ ቆይ ለሷ ሲል ነው እንደዚህ ሀብታም የሆነው ለሷ በተሰራ ቤት ውስጥ ነው ነገባሁት ።
ቆይ ከተዋወቅን ቀን ጀምሮ ሲነስረው አይቼ አላቅም አሁን ምን ተገኝቶ ነው ድንገት ነስር በነስር እየሆነ ያለው ልዑሌን የምር ላጣው ነው እንዴ ጭንቅላቴ በጭንቀት ሊፈነዳ ደረሰ ።

ባባ እንቅልፍ እንደወሰደው እኔጋ አምጥታው ስለነበር  መሲን ጠራኋትና ባባ እንቅልፍ እንደወሰደው ሳይነሳ በፊት በረንዳ ላይ ቆንጆ ቡና እንድታቀራርብና ትንሸን ፍራሽ አውጥታ እዛው እንድታነጣጥፈው ነገርኳት ።

ልዑሌ ስራ ቦታ ደውሎ ዛሬ የተፈጠረ አዲስ ነገር ካለ ሚፈራረም ነገር ካለው እየጠያየቀ ነበር ።

ልክ እንደመጣ ባባ እንደተኛ አቅፎት ወደ በረንዳው ወጣ እኔም ጋቢዬን ደርቤ ተከተልኩት መሲ ጠጅ የሆነ ቡና አፈላችልንና ጠጣን በዛው እየመሸ ስለነበር እዛው እራታችንን በላን ።

ቡናውን ስትጨርስ አነሳሳችና ባባን ይዛው ወደ ውስጥ ገባች ።።

እኛ የሰፈሩን ቆንጆ እይታ ከላይ በረንዳችን ላይ ቁጭ ብለን አንድ ጋቢ ለሁለት ለብሰን መኮምኮም ጀመርን።

ልዑሌ ታሪክህን ስትነግረኝ ፊልም እያየሁ እንጂ አግብቼው የምኖረው በቅርቡ የልጄ አባት ለመሆን  እያሰበ ያለው በዝምታው በውበቱ በፀባዩ የተማረኩለት ልዑሌ አልመስልሽ ብሎኛል ።

ቶሎ ቶሎ ንገረኝና ገላግለኝ ልቤ በእንጥልጥል ላይ ነው ሌላው ቀርቶ አሁን ላይ እንዴት ከወድሞችህጋ ልትግባባ ቻልክ አይንህ ላፈር ብለውህ ከነበር በየት በኩል መጠያየቅ ጀመራችሁ ካቆምክበት ቀጥልና ንገረኝ አልኩት ።
እሺ ይሄን ያህል ካጓጓሽ ልቀጥልልሽ

አንድ የማልሰራው ስራ አልነበረም ያገኘሁትን በሙሉ እሰራለሀ  ከቤቴ የሆነ ቦታ ለመሄድ ፈልጌ እየወጣሀ ከነበረ እንኳን መንገድ ላይ የሚሸከም እቃ ካገኘሀ ተሸክሜ ብሬን ተቀብዬ ነው ምሄደው ።

ሀሳቤም ምኔም ምኔም ገንዘብ ማግኘት የሚለው ላይ ብቻ ነው ።

ሳልፈልግ ቋጣሪ ሆንኩኝ ሳላስበው የሆነ ነገር አስፈልጎኝ ወይ ዝም ብሎ አምሮኝ 5 ብር ለሆነ ነገር ካጠፋሁኝ በቃ  ካለፈ ቡሀላ የሌለ እናደዳለሀ ምነው ባላጠፋሁት ካለኝ ብር ላይ 5 ብር ቢጨመርኮ  ይሄን ያህል ብር ይሆነኛል እላለሁ  በየቀኑ እኔን ባንክ ቤት ፈልገሽ አታጭኝም እጄ ላይ ብር ከያዝኩ አጠፋለሁ ብዬ ስለማስብ በየቀኑ አስገባለሁ።
አንድም ቀን እንደ እኩዮቼ ልብስ ጫማ መዝናናት አያምረኝም ።

ባንክ ቤት ያስገባሁትን ብር ተአምር ቢፈጠር  አላወጣም ።  እንደዛ እንደዛ እያለ ያለኝ ብር በጣም ቆንጆ ሆነ ።

በዛው ሌላ ቤት ተከራይቼ ለመሸጥ ወሰንኩኝ...

ይቀጥላል

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

20 Nov, 18:22


  የፍቅር ማእበል


      ክፍል 58


አባባም ስለሞቱ ቀን ስራውንም ስላቆምኩ በፊት 3 ስራ ምሰራውን አሁን ሁለት ብቻ ሆነ እንደዛ ከሆነ ደግሞ የምፈልገውን ያህል ገቢ የማግኘት እድሌ ይቀንሳል ሌሊት ለመሸከም የሚመቸኝነት አይነት ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ ግን ላገኝ አልቻልኩም ።
ስለዚህ ሌሊት 10 ሰአት ፒያሳ ሄጄ ከተሸከምኩና ለራሴ ምፈልገውን እቃ ካመጣሁ ቡሀላ ሱቄን ዘግቼ እስከ 11 ሰአት ቀን ስራ መስራት ከዛ ቡሀላ ሰውም በብዛት ከስራ ሲመለስ ስለሚገዛኝ ከ11 ሰአት ቡሀላ ሱቁን ለመክፈት አሰብኩና ቀን ስራውንም ጀመርኩ ግን እንዳሰብኩት ሳይሆን ቀረ ምክንያቱም በጣም ይነስረኝ ጀመር ።
ሽያጩም በፊት ከምሸጠው ቀነሰብኝ ከዛ ቀን ስራውን  ሙሉ በሙሉ አቆምኩኝና ሙሉ ትኩረቴን ሽያጬ ላይ አደረኩ በፊት  ከምሸጣቸው እየሰፋ እየሰፋ መጣ። ሁሉንን ሰው በፈገግታና በትትና ስለማስተናግድ ብዙ ደንበኞች ኖሩኝ ከሰፈሩ ሰውጋ በሙሉ ተግባባሁና ከኔ መግዛት ጀመሩ።

ከጠበኩት በላይ አሪፍ  ገቢ ማግኘት ጀመርኩ እዛ ብዙ ደንበኞች  ስላሉኝ የተበላሸ እቃ በፍፁም አላመጣምጎን ለጎን ደሞ ማታ 3 ሰአት ገብተሽ ሌሊት 8 ሰአት ላይ የሚዘጋ ክለብ ላይ መስተንግዶ ጀመርኩ ሌሊት 8 ሰአት ቤት እገባና ለ2 ሰአት እተኛለሁ 10,30 ወደ ፒያሳ ሄዳለሁ ።
ክለብ ላይ በጣም ቆንጆ ብር ነበር ማገኘው ብዙ ሰዎች ጠጥተው ሰክረው የሚሰጡሽን ብር እንኳን አያቁትም ።

ከዛ ለዶክተሩ ስነግረው ከለከለኝ እረጅም ሰአት በስራ ካሳለፍክ በቂ እረፍት አታገኝም እረፍት ደሞ ያስፈልግሀል አልገባህም እንጂኮ ታመሀል አለኝ።

እሺ ብዬ የክለቡን ስራ አቆምኩኝ ለህሂናዬን ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አልነበረም ።

በዛ መሀል ግን መቅዲን የሆነ ቀን taxi ውስጥ አገኘኋት ፊቷ ተበላሽቶ ሰውነቷ ከስቶ ነበር ሳያት እንዳዲስ ፍቅሯ አገረሸብኝ  ውስጤ ተላወሰ አሳዘነችኝ ከዛ ቁጭ ብለሽ ካላወራሽኝ ሞቼ እገኛለሁ ብዬ እንድታወራኝ አደረኳት ምን እንዳለችኝ ታውቂያለሽእያለቀሰች የኔ ግፍ እንደደረሰባት ባሏ ገንዘብ እንጂ ጭንቅላት እንደሌለው ነገረችኝ ።
ቤተሰቦቼ  ፊት መልአክ ይሆንና ቤት ስንገባ ሴጣን ይሆናል ቤተሰቦቼ እኔ እንደምፈልገው አይነት ኑሮ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል እኔ ግን ተጎዳሁ መንገድ ላይ ወንድ ካየኝ ምን ብለሽው ነው ብሎ ይናገረኛል ከቤት ከወጣሁ ማንን ልታገኚ ነው የሄድሽው ከማንጋ ተኝተሽ መጣሽ ይለኛል ።

ቤተሰቦቼ ቤት እንኳን ብቻዬን ከሄድኩ በዛው ወንድ ልታገኚ ነው እንጂ ለምን ብቻሽን ሄድሽ ብሎ ጥርግርጌን አውጥቶ ይሰድበኛል ።
ያገኘውን አጋጣሚ በሙሉ እየተጠቀመ እከክሽን አራገፍኩልሽ በኔ ሀብት  ነው ምትኖሪው ቤተሰቦችሽም በኔ እርዳታ ነው ያሉትእያለ ሰላሜን ነሳኝ።
ስራ ልስራ ስለው ምን ጎሎሽ ነው ስሪ ምትሰሪው ይለኛል እሺ ልማር ስለው የት ለመድረስ ነው ለመንዘላዘል ካልሆነ ብሎ ዱላ ቀረሽ ንግግር ይናገረኛል ።

በፊትም የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር ይባስ  ደሞ እሱን ካገባሁ ቡሀላ 24 ሰአት እራሴን በፀፀት መቅጣት ጀመርኩ።
በጣም ብዙ ጊዜ ልደውልልህ እና ይቅር እንድትለኝ ልጠይቅህ ነበር ግን ስልክህ አይሰራም አሁንም ቢሆን ይቅር እንዳልከኝ ብቻ ንገረኝ ሌላ ምንም አልግም አለችኝ።

መቅዲን እንደዛ ሆና ማየት በራሱ ያማል አሁንም ቢሆን ለኔ ስሜት ካለሽ አብረን መሆን እንችላለን።
እኔ ይቅር ብዬሻለሁ አልኳት


ይቀጥላል.....

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

19 Nov, 18:13


የሀገሬ ወጎች pinned « የፍቅር ማእበል        ክፍል 57 አንድና አንድ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ነው አማራጭሽ። ከዶክተሩጋ በጣም ቆንጆ ግንኙነት ፈጠርን ሴቷ ዶክተርም ብትሆን እንደናትም እንደ እህትም ሆነችልኝ ። እኔ ብር ማግኘት ስጀምር አስተሳሰቤም ተቀየረ በቃ ሞት ሚባለው ሀሳብ ከጭንቅላቴ ጠፋ አልፎ አልፎ መቅዲ ትዝ ስትለኝ ግን ሄደህ ጠጣበት ጠጣበት ይለኛል ግን አንድም ቀን ጠጥቼ አላውቅም። ብር ማግኘት…»

የሀገሬ ወጎች

19 Nov, 18:06


የፍቅር ማእበል


       ክፍል 57

አንድና አንድ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ነው አማራጭሽ።
ከዶክተሩጋ በጣም ቆንጆ ግንኙነት ፈጠርን ሴቷ ዶክተርም ብትሆን እንደናትም እንደ እህትም ሆነችልኝ ።

እኔ ብር ማግኘት ስጀምር አስተሳሰቤም ተቀየረ በቃ ሞት ሚባለው ሀሳብ ከጭንቅላቴ ጠፋ አልፎ አልፎ መቅዲ ትዝ ስትለኝ ግን ሄደህ ጠጣበት ጠጣበት ይለኛል ግን አንድም ቀን ጠጥቼ አላውቅም።

ብር ማግኘት ስጀምር ብር እራሱ ማስቀምጥበት ቡክ አልነበረኝም ።
ከዛ ዶክተሩ እንደምንም ተሟሙቶ መታወቂያ አወጣልኝና ቡክ ከፈትኩኝ።

ቀን ስራ ስሰራ አልፎ አልፎ ድንገት ባፌም ባፍጫዬም ደም ይፈሰኛል ከዛ ደሙ እስኪቆም መከራዬን እበላለሁ ።
ዶክተሩ በተደጋጋሚ ምርመራ እንዳደርግ ነገረኝና በድጋሜ ምርመራ ለማድረግ ወደሌላ ሆስፒታል ሄድኩኝ።

ከዛ ግን ምርመራ ካደረኩ ቡሀላ ዶክተሩ ምን እንደሆነ የማይታወቅ ጭንቅላቴ ውስጥ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ ነገረኝ በዛ ሰአት ብዙም ማገናዘብ አይችልም ብሎ መሰለኝ ትክክለኛውን ነገር ያልነገረኝ።

መፍትሄው ምንድነው አልኩት ??

ፀሀይ ላይ እረጅም ሰአት ከማሳለፍና ጭንቅላትህን ከማጨናነቅ ተቆጠብ በቂ እረፍት አድርግበት እነዚህን ነገሮች ካደረክ  ወደ ጤንነትህ መመለስ ትችላለህ ካልሆነ ግን ግዜው በሄደ ቁጥር ህመሙ እየከፋብህ ይሄዳል አለኝ።

እሺ ብዬው ዝም ብዬ ወጣሁ
በዛ ሰአት ገንዘብ ማግኘት የጀመርኩበት ሰአት ስለነበር ድጋሜ ወደኋላ መመለስ ለኔ አይታሰብም ነበር ምክንያቱም ምንም ገንዘብ ባልነበረኝ ሰአት ለመሞት ፈጣሪን ስለምን ነበር ስለዚህ ብሰራም እሞታለሁ ባልሰራም እሞታለሁ።

በዋናነት ደሞ ከምንምና ከማንም በላይ ስራ እንድስራ  ከሚያደርጉኝ ነገሮች ውስጥ በምን እርግጠኛ ነበርኩ መሰለሽ ሀብታም ከሆንኩ ብር ካለኝ መቅዲን ማግባት እችላለሁ ።
ባሏን ሳትወደው ስላገባችው እኔም ሀብታም ሆኜ አገባታለሁ ብዬ አስብ ነበር ትንሽ ልጅነትም ጅልነትም ነበረብኝ መሰለኝ ።

እና በቃ በየቀኑ የሰራኋትን እየያዝኩ ወደ ባንክ ነው ምሮጠው እንደሰው ልብስ ጫማ ምግብ ወይ ደሞ የተደላቀቀ መኖሪያ አያምረኝም አንድናአንድ ሀብታም መሆን ብቻ ነው ሀሳቤ ።

ህይወት ቆንጆ እየሆነች እራሴን እየጎዳህ ግን የምፈልገውን  ያህል ገንዘብ እየሰራሁ እያለ አባባ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሱና ሞቱ የዛን ቀን ከልጆቻቸው በላይ ሳለቅስ የነበርኩት እኔ ነበርኩ።

እሳቸው ሲሞቱ ከምንም በላይ አሪፍ ገቢ የማገኝበት ስራ ቆመ ከዛ ግን ፈጣሪ ጥሎ አይጥለኝምና የአባባ ልጆች ከስራ ከመሰናበታችሁ በፊት እስከዛሬ አባታችንን ሳትፀየፉ ስለተንከባከባችሁ ብለው ጠቀም ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጡን።

እሱን ወደ ባንኬ አስገባሁና የፒያሳውን ስራዬን ለመስራት ሞከርኩ ግን እኔ ምኖርበት ቤትና አስፋልቱ ምንም ሊመጣጠን አልቻለም እኔ ተነስቼ taxi ምይዝበትጋ እስክደርስ እየረፈደብኝ ተቸገርኩ መንገዱም በጣም ምቾት እየነሳኝ መጣ ያለችኝን ልብስና ለምግብ መስሪያነት ሚያስፈልጉኝን እቃዎች ብቻ ይዤ ከዛ ቤት እስከዘላለሙ ወጣሁ።
ቤት ተከራየሁ በጣም ጠበባ ግን ለኔ በቂ ነበረች።

እሷ ውስጥ እየኖርኩ ቀን ስራና አትክልት ተራውን እየሰራሁ አንድ ሀሳብ መጣልኝ።
አኔ ከተከራየሁበት ቤት ቀጥሎ አንድ ትንሽዬ ሱቅ ነገር አለች በጣም ብዙ ሰው በዛ ይተላለፋል አስፋልት ዳር ስለሆነ የብዙዎቹ taxi  መያዣና መውረጃ እሱጋ ነው ።
እሷን ቤት ተከራይቼ ለምን አትክልት አልሰራባትም ቀን ስራውም በጣም እየጎዳኝ ነው ቀን በቀን ከነስርጋ ከምታገል ይሄን ብከፍት ቢያንስ ከፀሀይ እንደምድን አሰብኩና ለዶክተሩ ነገርኩት በጣምምም ደስ አለው።
ከዛ ሌሊት ፒያሳ ሄጄ ለደንበኞቼ ሸክሙን ካደረስኩ ቡሀላ ለራሴም 1 ኩንታል ሽንኩርት ብቻ ጫንኩኝ ።  ከዛ እንደተመለስኩ ከባንክ ብር አውጥቼ ሚዛን ገዛሁኝና ማታ 11 ሰአት አካባቢ አሀዱ ብዬ ጀመርኳት።

የመጀመሪያ ቀን ገና ሰው እያየው ስለነበር ብዙም ገበያ አልነበረም እንዲሁ አንዳንድ ሰዎች ብቻ ውይ ተከፈተ እንዴ እስቲ እንመርቅልህ እያሉ ይገዙኛል ።

ብርቅ ሆነብኝ ልክ የትልቅ ሱቅ ባለቤት የሆንኩ ያህል ተሰማኝ በነጋታውም ሄድኩኝና ሌላ 1 ኩንታል አመጣሁ ከመጀመሪያው ቀን ሁለተኛው ቀን ላይ የተሻለ ሰው ገዛኝ ።
ጠዋት በሄድኩ ቁጥር  ሌላ ሌላ እቃ እያመጣሁ ሱቅ ውስጥ ማስቀመጫ እስኪጠበኝ ድረስ ሁሉንም አትክልት ደረደርኩላቸወሰ ሰዎች እግረ መንገዳቸውን እየገዙ ወደቤት መግባት ጀመሩ ገበያው ደራልኝ
ከዛ ቀን ስራውን ሳቆም እንደዛ ቀን በቀን የሚነስረኝ ነገር ቆመልኝ።

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

18 Nov, 15:48


የፍቅር ማእበል

አንድ ሰውዬ መጣ ሁሉም ብድግግ ብለው ከበቡት እሱ ግን ከመሀላቸው 5 ሰው ብቻ መርጦ ሄደ።
እንዴት እንደሚያሳዝኑ ብታይ ሁሉም ትጥቃቸውን አሟልተው ምሳቸውን ይዘው ሰው እስኪመጣ አይን አይኑን ማየት ከዛ ደሞ ገና ከተመረጥሽ ነው ምሰሪው ካልሆነም ምሳሽን ይዘሽ ወደቤትሽ ትመለሻለሽ።

እኔ ትንሽ እዛ ቆምኩኝ ፀሀዩ ግን አናት አናቴን ሲለኝ ደም በደም ሆንኩኝ ሁሉም ደንግጠው ከበቡኝና ሶፍት ምናምን ሰጡኝ ከዛ ተመልሼ ወደቤት ሄድኩኝ ።

ቀኑን ሙሉ ባዶ ቤት ተኝቼ ሳለቅስ አመሸሁና ወደ ማታ አካባቢ የዶክተሩን ልብስ አጣጥፌ ፌስታል ውስጥ ከተትኩትና የራሴን አያቴ በነበረችበት ጊዜ ምለብሰውን ቆንጆ ልብስ ለብሼ ሄድኩኝ።

ጤና ጣቢያ ሄጄ ለዶክተሩ ስለሰጠኝ ልብስ አመስግኜ መለስኩለትና ዶክተሯ እስክትመጣ መጠበቅ ጀመረን ።

እንዲሁ አይቶኝ እራት በልተሀል እንዴ አለኝ።

አዎ አልኩት።
አልበላህም አለኝ ??

በምን አወክ እንዳልበላሁ አልኩት ።

እኔ ዶክተር ነኝ ሰዎችን በመሳሪያ መርምሮ ከማወቅ በተጨማሪ ፊታቸውን አይቼ ውስጣቸውንም ማንበብ እችላለሁ አሁን ያለህበት ሁኔታ እራሱ ይገባኛል።

በጣም እርቦህ እርቦህ እረሀብህ ይወጣልህና ለመሄድ ለመሳቅ ስትሞክር አንጀትህ እጥፍ እጥፍ እያለ ነው አደለ???

እንዴ ዶክተር ቆይ በዚህ ልክ ያስታውቅብኛል እንዴ አልኩት

አይ እኔ በዚህ ልክ የሰውን ስሜት ስለማውቅ ነው ለማንኛውም አሁን ዶክተሯ ትምጣና እራት በልታችሁ ትሄዳላችሁ እኔኮ ትናት ኪስህ የነበረውን 75 ብር የወሰድኩት እዛ ሄደህ እንዳትጠጣ ነው ።

እራስህን ለመቀየር ዝግጁ ከሆንክ ግን በሁሉም ነገር አብሬህ ነኝ እንካ ብርህን ብሎ 75 ብሬን ሰጠኝ ።

አመሰግናለሁ ዶክተር ይሄ ብር እኔጋ ሆኖ ቢሆን እጠጣበት ነበር አልኩት ከዛ ዶክተሯ መጣችና እንሂድ በቃ አለችኝ።
ተከተልኳት እራት እንድንበላ ነግሯት ስለነበር እራት ለመብላት ወደ አንድ አነስ ያለች ቤት ገባንና አዘዘች።

ምግቡ እስኪደርስ ማውራት ጀመርን ይቅርታ የመጀመሪያ ቀን እንደዛ ስላመናጨኩህ ግን   እኔ ሰው እራሱን ሲጥል ለችግር እጁን ሲሰጥ አልወድም በቃ ምንም ነገር ካልተጋፈጥከው ማለፍ አትችልም። እኔን ተመልከት እንቅልፍ የምተኛው ቀን ከ6 ሰአት እስከ 8 ሰአት ብቻ ነው ።

ጠዋት 2 ሰአት ወደ ጤና ጣቢያ ሄዳለሁ ከዛ ከ6_8 እተኛለሁ እስከ ማታ 2 ሰአት እሰራና አባባጋ እሄዳለሁ እዛ ደሞ አባባን ጥበቃ ቁጭጭ ብዬ አድራለሁ ጠዋት 2 ሰአት ከነሱጋ እወጣለሁ ተመልሼ ወደ ስራ ገባለሁ ።
እንደዚህ ምሆነው ነገን አስቤ ነው ዳይፐር ስቀይር በጣም ብዙ ጊዜ አጠገባቸው ስለሚያስታውከኝ ለነሱ ሞራል ተጨንቄ እንጂ ለቅንጦት አደለም አብረኸኝ እንድትሰራ የፈለኩት።

ስራህ አለቃህ ነው ታዘዘው ከዛ ከበቂ በላይ ይከፍልሀል ስራ አትናቅ የትኛውንም አጋጣሚ እየተጠቀምክ ስራ ገንዘብ ያዝ save ማድረግን ልመድ በህይወትህ ትልቁ ስልጣኔ ገንዘብ የቱጋ ማጥፋት የቱጋ መቆጠብ እንዳለብህ ስታውቅ ነው።

በቃ ከሰራህ ታገኛለህ ካገኘህ ትከበራለህ ትንሹም ትልቁም ወዳጅህ ነው ገንዘብ ካለህ የሰው ሁሉ አይን አንተ ላይ ነው አለችኝ።
ከጠበኳት በላይ ምርጥ ሰው ሆና አገኘኋት እራታችንን በልተን እንደጨረስን ሄድን።




ከዛ ቡሀላ በቃ ህይወቴ ስራና ስራ ብቻ ሆነ ።
ማታ አባባጋ እሄዳለሁ ሌሊት 10 ሰአት ፒያሳ ሄድና ቢያንስ ለ4_5 ሰው ኩንታል እሸከማለሁ ጠዋት 3 ሰአት ተመልሼ እመጣና ቀን ስራ ሚሰሩትጋ እቀመጣለሁ ካገኘሁ እሰራለሁ ካጣሁ ቤት ተኝቼ እውላለሁ ።

በቃ ገንዘብ በደንብ ማግኘት ጀመርኩ አባባም በጣም ስለማሳዝናቸው ከልጆቻቸው ብር እየተቀበሉ ሸጎጥ ያደርጉልኛል።

ብታምኚም ባታምኚም በስህተት የምትጠፋብኝ አንድ ብር አትኖርም ገንዘብ አንዴ ማግኘት ስትጀምሪ በቃ ምን ልበልሽ እንቅልፍ ሁላ ለመተኛት ጊዜ አይኖርሽም በተለይ ደሞ እንደኔ ማጣትን ለገንዘብ ተብሎ መከዳትን ካየሽ ቡሀላ በቃ ..........

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

17 Nov, 12:48


የፍቅር ማእበል


         ክፍል 55
እሺ ብያት ልወጣ ስል ለካ እንደሚሰቀል  ሰው ባዶ እራቁቴን ነኝ ።
እሷን ለመጠየቅ ፈራሁ እንዳልቀር ደሞ ስራውን መስራት አለብኝ ።
እንደምንም ደፍሬ ፒያሳ ድረስ የሚያደርሰኝን የtaxi ብር ትሰጭኛለሽ ማለቴ ማታ ምመልስልሽ አልኳት ።

እሺ ችግር የለም ብላ ከቦርሳዋ አውጥታ ሰጠችኝ እሷን ተቀብዬ እየተቻኮልኩ ከዛ ቤት ወጣሁ ።
እንዳለችኝ አስፋልት ተሻግሬ ቆምኩኝ እውነት ለመናገር እኔ ጨለማ እፈራ ነበር ችግር ውስጥ ስትሆኚ ግን ምትፈሪው ነገር በራሱ ኖርማል ይሆናል ።

ትንሽ ጠበኩኝና taxi አግቼ ወደ አትክልት ተራ ሄድኩኝ  እዛ ስደርሰሰ ግን ትናት ሴትዮዋ ያስተዋወቀችኝ ሰዎች ጠፉብኝ።
ሰውም ወከባ ስለሆነ በዛ ላይ ተሸካሚዎቹ መሯሯጥ ስለሆነ መግቢያውም የተለያየ ስለነበረ ጠፋብኝ እዛ አንዱጋ እየገባሁ አንዱጋ እየወጣሁ ቆየሁና መጨረሻ ላይ አገኘኋቸው ።

ስደርስ ውይ አረፈድኮ ብዙ ሰዎች እቃ ጭነው ጨርሰዋል ማለት ይቻላል አለኝ።

የት እንዳሉ ጠፍቶብኝ እንደቆየሁ ነገሩት ምናልባት ያረፈዱ ሰዎች ካሉ እድሌን እንድሞክር ነገረኝ ።
ከነሱ አጠገብ ጥጌን ይዤ ቆምኩኝ ትንሽ ቆይታ አንድ ሴትዮ መጣችና ውይ የተመረጠ እቃ ነው ያላችሁ አደል ዛሬ አረፈድኩኝ አለቻቸው እነሱ ግን አደለም ምናምን ብለው በት በት ብለው አሳመኗት እና 1 ኩንታል ገዛች ከዛ እኔ ተሸከምኩላት 25 ብር ብቻ ሰርቼ ወደቤቴ ተመለስኩ ትልቅ የተሸወድኩት ነገር ደሞ ለካ ማታ የለበስኩትን ልብስ መቀየር ነበረብኝ ካልሆነ ማታ ድጋሜ ለብሼው ሰውዬውጋ መሄድ አልችልም።

ያቆሸሽኩትን ለማጠብ ደሞ ቤት መሄድ አለብኝ ወደዛ ቤት መመለስ ደሞ አልፈለኩም ነበር ግን ግዴታ ስለሆነ ከዛ እንደተመለስኩ ወደቤት ሄድኩኝ ከላይ የለበስኩት ብቻ ስለሆነ የቆሸሸው እሱን አጣጥቤ አሰጣሁ።
ከዛ ተኛሁኝ ምግብ ስላልበላሁ እራበኝ ጠዋት የሰራሁትን ብር እንዳልበላበት ለዶክተሯ ያበደረችኝን መመለስ ነበረብኝ።

በእንቅልፍ ካለፈልኝ ብዬ ተኛሁኝ ግን መተኛት አልቻልኩም ብዙ ነገር በጆሮዬ አቃጨለብኝ ከዛ ተነስቼ ከቤት ወጣሁኝና ዝም ብዬ እጄን ኪሴ ከትቼ መጓዝ ጀመርኩ ።

የት እንደምሄድ አላውቅም ግን ዝምም ብዬ ወደፊት እየተጓዝኩ አንድ ቦታ ላይ በጣምም ብዙ ሰዎች ስብስብ ብለው ቁጭ ቁጭ ብለው አየሁኝ አንዱን ቀስ ብዬ ጠጋ አልኩኝና ለምንድነው እዚህ ሰው የተሰበሰበው አልኩት ።
ቀን ስራ ሰራተኞች ነን አሰሪ ይመጣና የፈለገውን ይዞ ይሄዳል አለኝ ።
እኔም ጠጋ ብዬ ተቀላቅዬ ቁጭ አልኩኝ።

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

14 Nov, 18:27


የፍቅር ማእበል



    ክፍል 54

ስታስበው ልብስ በሻንጣ ይዤ ምዞር ነው ሚመስልህ ወይስ የለበስኩትን አውልቄ እንድሰጥህ ነው ሲጀመር ለስራው ትንሽ እንኳን ፍላጎት ቢኖርህ ቀደም ብለህ ትመጣ ነበር አለኝ።

እኔ ግን በስንት ታቦት እየማልኩኝ ነገርኩት በቃ ስራው ህይወቴን ለማቆየት ያስፈልገኛል   በፈጣሪ ስም የዛሬን ብቻ ብዬ ለመንኩት ዶክተሯጋ ደወለና አሁንም ሰው ያስፈልግሻል አደል አላት ።

አዎ በናትህ እየታመምኩ ነውኮ ምን ይሻለኛል እንደምንም ብለህ ሰው ፈልግልኝ እንጂ  አለችው ።

በቃ ልጁ እኔጋ መቷል እኔ እራሴ ይዤው እመጣለሁ ግን ትንሽ እንቆይብሻለን አላት።
አረ ችግር የለውም ብቻ እናንተ ኑ እንጂ አለችውና ስልኩ ተቋረጠ ዶክተሩ እስከ ሁለት ሰአት እንድጠብቀው ነገረኝና ቁጭ ብዬ ጠበኩት  ከዛ ወደቤቱ ወሰደኝና ከራሱ ልብሶች ሚሆነኝን እንድመርጥ ነገረኝ ጅንስ ሱሪና ቡኒ ቲሸርት  ሰጠኝ ከዛ ሌሊት እዛ ሊበርድህ ስለሚችል ጃኬት ብትወስድ ጥሩ ነው ብሎ ጃኬትም ጨመረልኝ ።
ወደ ዶክተሯጋ እየሄድን አሁን የሰጠሁህ ልብሶች እንዳለ ልክ አበድሬህ እንደገዛኸው ቁጠረው ሰርተህ ትከፍለኛለህ ብሬን አለኝ ።

እሺ እከፍላለሁ አልኩት ።
ዶክተሯ ያለችን ሰፈር ላይ ስንደርስ መጥታ ተቀበለችን በደንብ አየችንና በነካ እጅህ ጫማ አትቀይርም ነበር ለማንኛውም ተከተለኝ ብላኝ ዶክተሩን ተሰናብታው ሄድን ።

ሰውዬውጋ ከመግባታችን በፊት ሰውዬው በጣም ጥሩ ልብ ያላቸው ምስኪን እንደሆኑና ዳይፐር እንደሚጠቀሙ ልጆቻቸው እንደማያውቁ እሳቸው ዳይፐር ስለሚያደርጉ ይሳቀቃሉ ስለዚህ አንተ ሁልጊዜም ኖርማል እንደሆነና ምንም እንዳይጨነቁ ጭንቅላታቸው ላይ መስራት አለብህ።

ትልቁና ዋነኛው ነገር ደሞ እራስህን መጠበቅ አለብህ በፍፁም ወደ ሰውዬውጋ ስትጠጋ ጠረንህ መጥፎ መሆን የለብህም ልጆቻቸውም ሲያዩህ ንፁህ ሆነህ ነው ሊያዩህ የሚፈልጉት እዚህ ቤተ መንግስት የመሰለ ቤት ውስጥ ስትገባ ተንቋሸህ የጎዳና ልጅ መስለህ አደለም አለችኝ ።
እኔ እሺ እሺ ብቻ ነው ምላት በጣም ትልቅ ቪላ ነው ቤቱ ስፋቱ ያስደነግጥሻል ።
ሰውዬው ለብቻቸው የራሳቸው ሰፊ ክፍል አላቸው ክፍሉ መታጠቢያም ሽንት ቤትም አለው ከዛ አይወጡም ።

በመጀመሪያ ስተዋወቃቸው አይተውኝ ፈገግ አሉ እኔም ፈገግ አልኩላቸው።

ከዛ በፊት ዳይፐርን እራሱ በቅጡ ስለማላቀው ለዶክተሯ ለአሁን ብቻ እሷ ስትቀይርላቸው እንድታሳየኝ ጠየኳት አሳየችኝ።
እኔ ደሞ ነገሮችን የማየት ችግር ስሌለብኝ በቃ ከዛ የድጋሜ ሌሊቱን ቀየርኩላቸው ልጆቻቸው ማታ ከስራ ሲመጡ ሰላም ሏቸዋል ከዛ ውጪ አይመጡም።

ሌሊቱን እንቅልፌ በጣም አስቸገረኝ በዛ ላይ ቀን እንደበላሁ ስለነበር በጣም እራበኝ ቁጭ ብዬ እንቅልፌ ሲያዳፋኝ አየችኝና እዛው ክፍሉ  ውስጥ ከአልጋው አጠገብ ያለው ሶፋ ላይ እንድተኛ ነገረችኝ።

ተኛሁኝ
የሆነ ሰአት ብንን ስል ዶክተሯ ቁጭ ብላ ስልኳን ትነካካለች ሰውዬው ተኝተዋል እኔም እንደዛው ግን ግዴታ እሳቸውን መጠበቅ ስላለባት ሌሊቱን ሙሉ አትተኛም ።
ሌሊት 10 ሰአት ሲሆን እንድትቀሰቅሰኝ አደራ ሰጥቻት ተመልሼ ተኛሁ።

10 ሰአት ላይ ቀሰቀሰችኝ አጋጣሚ ሆኖ ሰውዬው ከ10  ሰአት በፊት ይነቃሉ ከዛ አይተኙም ።
ስለዚህ ለኔ ተመቻቸልኝ ማለት አደል እኔ ለሳቸው ዳይፐራቸውን ቀያይሬ ምናምን ስጨርስ 10,30 ሆነ ከዛ ዶክተሯን አትክልት ተራ መሄድ ፈልጌ ነበር እዚህ ሰፈር taxi አገኛለው እንዴ አልኳት።

ብዙ አትክልት ቦታ አለኮ የትኛውጋ ነው ምቴደው ምን ትሰራለህ ደሞ በዚህ ሰአት አለችኝ።

ከዛ ትናት ከሴትዮዋጋ ስኔድ እረዳቱ ፒያሳ ነሽ ሲላት እየሰማሁ ነበር ።
ፒያሳ ያለውጋ ነው ምሄደው ለምን እንደምሄድ እነግርሻለሁ ንገሪኝ taxi አለ አልኳት ።

አዎ አለ በር ላይ እንደወጣህ አስፈልት ተሻግረህ መቆምኮ ነው እራሳቸው ፒያሳ ነህ ብለው ይጠይቁሀል አለችኝ .......
ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

13 Nov, 18:29


❤️❤️የፍቅር ማእበል


       ክፍል 53



ቅርብ የነበረው ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነበር።
ቀጥታ ሄድኩኝና ድፍት ብዬ አለቀሰኩ ቀን ስለነበረ ግቢው ጭር ብሏል ጥጌን ያስኩኝና በድጋሜ ተረጋግቼ ቁጭ ለማለት ሞከርኩ ግን አቃተኝ ሳላስበው ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩ ።
እንዴት አንድ ምፅናናበት ነገር በዙሪያዬ አይኖርም እንዴት አንድ አይዞህ እኔ አለሁልህ ከጎንህ ነኝ ቢከፋህ አፅናናሀለሁ ደስ ሲልህ አብሬህ እደሰታለሁ ብትራብም አብረን እንራባለን የሚለኝ አንድ ሰው ለኔ ታጣለህ::
እንደሰው ፈጥረኸኝ እንደዚህ አይነት ህይወት እንድኖር ትፈርድብኛለህ አረ ፈጣሪ ሆይ ወይ ግደለኝ በቃ ምርር ብዬ እያለቀስኩ እያለ አንድ የግቢው መነኩሴ ይመስሉኛል መጡና አጠገቤ ቁጭ አሉ የዛኔ ለቅሶዬን ዋጥጥ አደረኩኝና ዝም አልኩኝ ።

ምነው አልቅስ እንጂ ልጄ ፈጣሪን እንዲህ ስታማርር አላፈርክ እኔን እንዴት ታፍረኛለህ እእእ ....
እያየኋቸው ዝም አልኩኝኝ።

እየውልህ የኔ ልጅ አንዳንዴ ፈጣሪ የሰውን ልጅ ሊያነሳ ሲፈልግ  ከጥልቁ ይጥለውና በትልቁ ያነሳዋል እኛ ሰዎች ግን እሱን ለመጠበቅ ጊዜ የለንም።
የኔ ልጅ ፈጣሪ በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሚያሳልፍህ ለበጎ ነው ።
በቃ ሊያከብርህ ትልቅ ቦታ ሊሾምህ ስለፈለገ ነው አሁን በፈተናዎች ውስጥ የሚያሳልፍህ ።
ግን አንድ ነገር አትርሳ ፈጣሪ አንተ የጠየከውን በሙሉ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ አንተስ ፈጣሪ ከጠየቀው ውስጥ ምን ያህሉን አድርገሀል እእእ እስኪ ንገረኝ  ???

እኔ ምን ልመልስ አልፆም -: አልፀልይ : ህግጋቱን አላከብር ታዲያ ፈጣሪ ከሰው ልጅ ከሚጠብቃቸው ነገሮች ውስጥ አንዱንም ሳላደረግ እንዴት እኔ የጠየኩትን እንዲሰጠኝ እጠብቃለሁ 🤔
እራሴን ጠየኩኝ።
ከዛ እኚያ አባት የእዮብን ታሪክ ነገሩኝ እኔ እዮብ ከሰው ስም የዘለለ ታሪክ እንዳለው አላውቅም ነበር።

ልክ የሱን ታሪክ ስሰማ ለካ እኔ ቆሜ መሄዴ ጤነኛ መሆን በራሱ ትልቅ ስጦታ ነበር ያው ሁሉም ሰው ያለውን ሳይሆን የሌለውን ነው የሚያየው አደል ።
ቀጥታ ብድግ ብዬ  አባቴ በፀሎቶት አስቡኝ ብዬ ጉልበታቸውን ስሜ ከቤተክርስቲያኑ ወጣሁ ።

ለምንና እንዴት እንደሄድኩኝ አላቅም ግን እራሴን እነመቅዲ ሰፈር ቁጭ ብዬ አገኘሁት አይኔ የቤታቸው በር ላይ ተተክሎ ነበር ።

መቅዲን ካየኋት በጣም ስለቆየሁ ናፈቀችኝ ታቂያለሽ እሷ ስትናፍቀኝ የበለጠ ውስጤን ባዶነት ይሰማዋል እንባ ተናነቀኝ ። ያቺን አረቄ ብጠጣ እንደምረጋጋ አሰብኩኝ ግን ብር ከየት ላምጣ።
ከዛ ለምን እዚህ መጣሁ አንድ እርምጃ ወደፊት ስራመድ ሁለት ወደኋላ እመለሳለሁ በስራየ አፈርኩኝና ተመልሼ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩ ቁጭ ብዬ በእጄ ጭንቅላቴን ደግፌ መሬቱ ላይ አይኔን እንደተከልኩ መሸልኝ 1,30 አካባቢ ዶክተሩጋ ሄድኩኝና የመጨረሻ እድል እንዲሰጠኝና ቤተክርስቲያን ሄጄ እራሴን ለማስተካከል ቃል እንደገባሁ አስረግጬ ነገረኩት።
ዶክተሩ ግን አይሆንም ደደብ ብቻ ነው ከስተቱ ማይማረው አሁንም ብሰጥህ ሄደህ ትጠጣበታለህ አበቃ።

እሺ ብሩን ለመስጠት ካላመንከኝ ለዛሬ ብቻ ለብሼው ዶክተሯጋ ምሄደውን ልብስ አበድረኝ ዛሬም ስታየኝ ደብሯት እንቢ እንዳትለኝ አልኩት .............

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

12 Nov, 19:18


የፍቅር ማእበል


         ክፍል 52

እሺ ችግር የለም ብቻ ብር ላግኝበት እንጂ ምንም ቢሆን አሰራለሁ አልኳት ።

እሺ ና በቃ ዛሬ የኔን አንተ ታደርስልኛለህ አንዴ ደንበኞች እስኪኖርህ ማንም አምኖህ እቃውን አያሸክምህም ግን ደሞ አንዴ በሰዎች ዘንድ ታማኝነትን ካገኘህ በቃ ያንተ ጉብዝና ብቻ ነው እንጂ ሚፈለገው በቃ ጥሩ ገንዘብ ትሰራለህ አለችኝ taxi ውስጥ እየሄድን ።

ከዛ እዛ ደረስንና ወረድን ግር ግሩ ሌሊት አይመስልሽም ገና በሌሊቱ ገበያው ደርቶ ነበር እኔም ሴትዮዋ የገዛችውን  እቃ እሷ እየመራችኝ ቦታው ድረስ አደረስኩላት ሰላም ልነግርሽ አልችልም ግን እቃውን እዛ እስካደረስ ለመሞት እያጣጣርኩ ያህል ነበር የደከመኝ ።
አንድ ኩንታል ስትሸከም 25 ብር ነው ሚከፈልህ በዛ ያለ ከሆነ ደሞ 30 ብር እኔ ደንበኞቼጋ ወስጄ አስተዋውቅሀለሁ ከዛ አዳዲስ ሰዎች ሊገዙ ሲመጡ አንተ ትሸከምላቸዋለህ አለችኝና ተመልስን ወደገበያው ገባን ከሰዎቹጋ አስተዋወቀችኝ የሰፈሬ ልጅ ነው በጣም ጎበዝ ነው ሲሰራ እና አብሯችሁ ይስራ ብላ እቃ ከሸጡላት ሰዎችጋ አስተዋወቀችኝ ።

እስኪነጋ ሶስት ሰአት ድረስ ግርግሩ እንደሞቀ ነበር ከዛ ቡሀላ ግን ይቀዘቅዛል 3 ኩንታል ተሸክሜ  75 ብሬን ይዤ  ወደ አረቄ ቤት ሄድኩኝ በባዶ ሆዴ ምንም ሳልበላ ያንን አረቄ መጠጣት ተያያዝኩት ግን ብዙም አልቆየሁም ደም ባፌም ባፍጫዬም መፍሰስ ጀመረ ሰዎቹ ደንግጠው ያው የፈረደበት ዶክተርጋ ወሰዱኝ ጤና ጣቢያው እኔ ከምጠጣበት ቤት ቅርብ ስለሆነ ብዙም አይቸገሩም በቃ ለኔ ተውት ስንት ያለበት ሂሳብ አላት አብራኝ የመጣችውን ሴትዮ ነገራውን ሂሳቡን ከኪሱ ከፍሎ አሰናበታቸውና ለኔ አስፈላጊውን ነገር አደረገልኝ ደሙ ሲቆም እኔም ወደራሴ ተመለስኩ ።

ምሳ ሰአት እስኪሆን ቁጭ ብዬ እንድጠብቀው ነገረኝ ቁጭጭጭ አልኩኝ ምሳ ሰአት ላይ እሱ ከላይ ደርቦት የነበረው ጃኬት ሰጠኝና እንድለብሰው ነገረኝ (ልብሴ በደም ተጨማልቆ ስለነበር ለዛ ነው)  ።

ከዛ ቀጥታ ወደሱ መኪና ውስጥ ገባንና  ወደፊት ነዳው አንድ ቦታ ላይ ስንደርስ አቆመና ከመኪናው ወረድን ።
አንድ ትልቅ ምግብ ቤትጋ እራቅ ብሎ መኪናውን አቆመው እስቲ ከዚህ መኪና ውረድና እዚህ ቤት ባትበላ እንኳን ገብተህ ለመቀመጥ ሞክር አለኝ ።
እንዳዘዘኝ ሄድኩኝ ሁሉም standardun የጠበቀ ልብስ ለብሷል ሁሉም ሰዎች ከተቀመጡበት ጠረጴዛ ላይ የመኪና ቁልፍ አለ  ።
ገና ወደመግቢያውጋ ስጠጋ አንድ ሱፍ የለበሰ ሰውዬ ፈጠን ብሎ መጣና እግዘብሔር ይስጥልን እዚህ መለመን አይቻልም አትገባ አለኝ ።
እሺ ብዬ ተመለስኩና ለዶክተሩ ያለኝን ነገርኩት አየህ ደና ልብስ ለብሰህ ብር ኖሮህ ቢሆን ግን እዚህ የመጣኸው ገና ሳትገባ ከበር ጀምሮ እንኳን ደህና መጡ እያለ ወንበር አመቻችቶ ያስቀምጥህ ነበር።
ቀጣይ እዛው አቅራቢያ ወዳለ በሸራ የተወጠረች ትንሽዬ ቤት ወሰደኝና ሂድና ሴትዮዋን ብር ስላልያስኩ ነው ምሳ ስጭኝና ሌላ ጊዜ አመጣልሻለሁ በላት አለኝ ።
እሺ እንደምንም እየፈራሁ ጠየኳት እኔምኮ 5እና 10 ብር ለማግኘት ነው እዚህ ምማቅቀው ላንድ አንተ ምሳ ስሰጥህ የቀን ሙሉ ትርፌን አጣሁ ማለት ነው አለችኝ።
ተመልሼ ሄድኩኝና ያለችኝን ነገርኩት ጥሩ ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ቦታ ልውሰድህ አለኝና
ሸራ ተጠቅልለው  ለብሰው ፀጉራቸው ጥጥ የመሰለ አባት መንገድ ላይ ተኝተው አሳየኝና እነዛ አባት አያሳዝኑም በዚህ እድሜያቸው እንደዚህ መንገድ ዳር ተኝተው የሰው አይን ሲገርፋቸው ይሄኔኮ እርቧቸው ይሆናል ሂድ እስቲ ምሳ ግዛላቸው አለኝ ።
ኪሴ ስገባ ጠዋት የሰራኋት 75 ብር የለችም ኪሴ ውስጥ ብር ነበር ጠፍቷል በምኔ እገዛላቸዋለሁ አልኩት ማታ የሰጠሁክስ አየህ አንተ ጠጥተህ ሸናህበት ለሷቸው ግን አንተ የጣህበትን ገንዘብ ብትሰጣቸው የዛሬን እህል ቀምሰው ነፍሳቸውን ማቆያ ይሆናቸው ነበር ።
እንዚህ አባት ቢያሳዝኑህ ምን ቢሉህ ምንም መርዳት አትችልም ምክንያቱም አንተ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ማሰቢያ ጭንቅላትህንም ነው ያጣኸው አለኝ።
እነዛ  አባትን እንባ እየተናነቀኝ ምንም ሳላደርግላቸው ትተናቸው ሄድን እኔ ውስጤ ስፍስፍ አለ ግን በቃ ምንም ማድረግ ስላልቻልኩ ትተናቸው ሄድን።

ምሳ በጣም እንደራበኝ ነገርኩት እና ለመብላት የሆነ ቤት ወሰደኝ ምሳ ጋበዘኝና ወደስራ መመለስ እንዳለበት ነግሮኝ ተመለስን የሆስፒታሉ በርጋ የሆነች ልጅ ቆማ አየና እስቲ ሂድና እንደመልከፍ በላት ከዛ ምን እንደምትልህ ትነግረኛለህ ብሎ መኪናውን ተደግፎ ቆመ ።
አጠገቧ ሄጄ ቆምኩና እ እናት ወዴት ነሽ ልሸኝሽ አልኳት ።
የንቀት ፈገግታ ፈገግ ብላ መጀመሪያ እኔን ስለመሸኘት ከማሰብህ በፊት እላይህ ላይ የነተበውን ልብስህን እጠበው ባንተ ቤት ለመላከፍ መሞከርህ ነው ጅል ብላ ሰድባኝ ሄደች።

ከዳር ቆሞ ሚሆነውን እያየ ስለነበር እኔ ወደስራዬ ልገባ ነው እንግዲህ አረቄ ዱቤ ከሰጡህ ሂድና ጠይቃቸው ስራውን መስራት አትፈልግም መልካም ቀን ብሎ ጥሎኝ ገባ ።

ቀጥታ ወደ አረቄ ቤት ሄድኩኛ ነገ ብሩን እንደምሰጣትና ዛሬ በዱቤ እንድጠጣ ጠየኳት  ።
ቀልደኛ ነህ ያደለው ልጅ ተምሮ እናት አባቱን ይጠቅማል ያንተ አይነቱ ገልቱ አረቄ ዱቤ ይጠይቃል ቅድሚያ ካልከፈልክ አትጠጣም አለችኝ ።
መልስ ሳልሰጣት ፊቴን አዙሬ ቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩ.......

ይቀጥላል ....
✍️ማኔ
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

11 Nov, 08:05


የፍቅር ማእበል

   
          ክፍል 51

ምን እንደወሰደኝ አላውቅም ግን እራሴን የነመቅዲ ሰፈር አገኘሁት።

ትንሽ ቆምኩኝና ተመልሼ አስፋልት ዳር ቁጭ ብዬ ማልቀሱን ተያያዝኩት አንድ በእድሜ ገፋ ያሉ ሴትዮ መጡና የኔ ልጅ ምን ሆነህ ነው ምታለቅሰው አሉኝ።

አፌ ላይ እንዴት እንደመጣልኝ ባላውቅም እርቦኝ ነው አልኳቸው።
ውይ የኔ ልጅ እኔ አፈር ልብላልህ ና ተነስ በለው እዛው አካባቢ ወደነበረ ምግብ ቤት ይዘውኝ ገቡና አብረውኝ ምሳ በላን የኔ ልጅ ወደቤት እንዳልወስድህ እኔም ከልጄጋ ተጠግቼ ነው ምኖረው የልጄ ሚስት ደሞ ጥሩ አደለችም ። ያለችኝ ይችው ናት አብቃቅተህ ተጠቀማት ብለው 300 ብር ከቦርሳቸው አውጥተው ሰጡኝ በዛ ሰአት 300 ብር ማለት በጣም ብዙዙዙ ነበር ። ብርቅ ሆነብኝ አመስግኛቸው ተለያየን እኔ ቀጥታ ያቺ የለመድኳት አረቄ ቤት ሄድኩኝና ስጠጣ አመሸሁ ።
ማታ 1 ሰአት ምናምን ላይ ጤና ጣቢያ ሄድኩኝና ዛሬ ነው አደል ስራ ምጀምረው አልኩት አዎ እየጠበቀችሁ አብራችሁ እንድትሄዱ ብሎ አብራው ተቀምጣ ወደነበረችው ዶክር ጠቆመኝ ። ዶክተሯ አየችኝና ፅይፍ ነገር አለች ።
አይታይህም እንዴ እንደዚህ ጨርቅ ሆኖ በሸተኛ ፊት ይዤው ልቀርብ ነው እንዴ ሰዎቹ ከምንም በላይ የሚንከባከበውን ሰው ንፅህና ይፈልጋሉ እንደዚህ ሆኖ ይዤው አሌድም አለች እየተበሳጨች ቻው ብላው ዶክተሩን ወጣች።

የዛኔ በጣም ባዘነ ፊት እያየኝ አሁን ወደቤትህ ሂድ ነገ ልብስህን ቀያይረህ ሻወር ወስደህ ና አዲስ ልብስ መግዛት ካስፈለገህ ከኔ ብር ውሰድ ግን አስታውስ ሰርተህ ትከፍለኛለህ ብድር ነው አለኝ።

እሺ አልኩት እየተፍለቀለኩ ከኪሱ አውጥቶ ቆጥሮ ሰጠኝ ተቀብዬ በፍጥነት ከሆስፒታሉ ወጣሁና እዛው  ስጠጣበት የነበረው  አረቄ ቤት ገባሁኝና ካቆምኩበት ቀጠልኩ ከሌሊቱ 5 ሰአት አካባቢ ላይ ልንዘጋ ነው በቃ ውጡ አሉን።

እኔ ሲያወሩ ሁላ ምን እንደሚሉ በትክክል አይሰማኝም ብቻ የመቅዲን ስም በተደጋጋሚ እየጠራሁ እንደነበር ነው ማቀው ።

እዛው ከአረቄ ቤቱ አጠገብ መሬት ላይ ዝም ብዬ ተኛሁኝ ስካሬ ትንሽ በእንቅልፍ  ካለፈልኝ ቡሀላ ነቃሁኝ ከመኪና ውጭ ምንም ሚንቀሳቀስ ነገር የለም አልፎ አልፎ አንድ መኪና ውልብ ሲል ታያለሽ ከዛ ውጭ ፀጥ ያለ ነው ይጨንቃል ።

እራሴን ብቻዬን በሌሊት መንገድ ዳር ቁጭ  ብዬ  ሳገኘው ታቂያለሽ ተሰማኝ ፈጣሪ የትኛውን ደስታ ሊሰጠኝ አስቦ እንዲህ እንደሚፈትነኝ ግራ ገባኝ ።

ማልቀስ ጀመርኩኝ ዶክተሩ የሰጠኝን ብር ጠጥቼበታለሁ ስለዚህ ከሱጋም ስራ መጀመር አልችልም  ።

ወደ አያቴ ቤት ደሞ መመለስ አልፈልግም ገና ወደዛ ሰፈር ስረግጥ ያመኛል ሁሉ ነገር ትዝ ይለኛል።

ቁጭ ብዬ እራሴን  ጠየኩኝ እሺ ወደቤት መሄድ አልፈልግም በዚህ ሁኔታ ስራ መስራት አልችልም ሳላስበው ደሞ ወደመጠጥ ሱስ እየገባሁ ነው ስለዚህ ነገ ምንድነው ሚጠብቀኝ ምንድነው ተስፋ ማደርገው ብዬ እራሴን ጠየኩ ግን ምንም መልሰ የለም ልክ በየመንገድ ዳሩ እየተኙ እንደምታያቸው ሰዎች ትሆናለህ ከዛ ትሞታለህ በቃ ከዛ የዘለለ ምንም የለም አልኩኝ ።

እንዲሁ አይኔ እስኪያብጥ አለቀስኩ።

እዛው ቁጭ ብዬ የሆነች ሴትዮ በእጇ መዳበሪያ ይዛ taxi ስትጠብቅ አየኋትና ጠጋ ብዬ እናት ስንት ሰአት ሆኗል አልኳት።
10,30 ሆኗል አለችኝ::

ታዲያ በዚህ ሰአት ወዴት እየሄድሽነው ???
አትክልት ተራ እየሄድኩ ነው ሲነጋ ምሸጠውን እቃ በዚህ ሰአት ነው ሄጄ ማመጣው ።
አረ ሁሌ በዚህ በሌሊት ስትወጪ ግን አትፈሪም እንዴ አልኳት።
ፈጣሪ ከቀኝም ከግራም ይጠብቀኛል አለችኝ  ።

በዛው ቀስ ብዬ እኔ አሁን ካንቺጋ ልስራ ብል እችላለሁ እንዴ ???

እኔማ ምን አቅም አለኝ ብለህ ነው ከኔጋ ምትሰራው ስራ የለም ግን እዛ አትክልት ተራ ምንፈልገውን እቃ ከገዛን ቡሀላ ወደዚህ ሚያመጣልን መኪና ድረስ ተሸክመው ሚወስዱ ልጆች አሉ እንደዛ መስራት ትችላለህ ???

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

10 Nov, 08:59


በብዙዎች መነጋገሪያ የሆነው ሰው ቪዲዮ ወጣ 400 ሴቶችን ሲማግጥ የሚያሳይ ቪድዮ ባታዩት ይመረጣል👇👇👇
t.me/seed_coin_bot/app?startapp=851939899

የሀገሬ ወጎች

09 Nov, 18:45


የፍቅር ማእበል

      
       ክፍል 50(🥺)

ከምንጠጣበት ቤት ፊት ለፊት የነበረው ጤና ጣቢያ አፋፍሰው ወሰዱኝ እዛ ስደርስ ደሙ ከቆመልኝ ቡሀላ ዶክተሩ ሊያናግረኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ እሺ አልኩት።

ወደ ትልቅ ሀኪም ቤት መሄድ እንዳለብኝና ሰፋ ያለ ምርመራ ባደርግ ጥሩ እንደሆነ ነገረኝ ።
ለዶክተሩ እንኳን የምታከምበት እራት የምበላበት እራሱ ቸግሮኛል አልኩት የት ነው ምትኖረው ብሎ ጠየቀኝ ነገርኩት ።

ነገ ተመልሼ ጤና ጣቢያ እንድመጣና  እሱ ወደሚያቀው ዶክተርጋ በነፃ እንድመረመር እንደሚወስደኝ ነገረኝ የታክሲ ሰጥቶ ሸኘኝ ።

እንዳለኝም በነጋታው ተመልሼ ጤና ጣቢያ ሄድኩኝ እስከምሳ ሰአት እንድጠብቅ ነገረኝ ጠበኩትና ምሳ ሰአት ላይ ወደሌላ ሆስፒታል ይዞኝ ሄዶ ምርመራ ተደረገልኝ ።

ዶክተሩ ጭንቅላቴ ላይ በጣም  ልጠነቀቅ እንደሚገባ ከፀሀይ እና እረጅም ሰአት ከመጨነቅ እንዳቆም በአደራ ጭምር ነገረኝ።

እሺ ብዬ ተነስቼ ወጣሁ።
ጤና ጣቢያ ካገኘሁት ዶክተርጋ አብረን እየተመለስን ምሳ እንብላ ብሎ የሆነ ቤት ይዞኝ ገባ ።
ምሳ እየበላን የህይወት ታሪኬን በሙሉ ነገርኩት ።
በጣም አሳዘንኩት ።
በተለይ ትምህርቴን በማቋረጤ በጣም ተናደደ ።
ከዛ እኔ አንድ ማቀው ስራ ነበረኝ ግን ይከብድሀል ።
ዋናው ገንዘብ ማግኜቴ ነው ምንም ቢሆን እሰራለሁ የምትል ከሆነ ግን ችግር የለም ጎን ለግንም ሌላ ስራ እየሰራህ መስራት ምትችለው ነው አለኝ።

እኔ አረ ምንም ይሁን እሰራለሁ ብቻ ብር ላግኝበት አልኩት ።
እሺ ብሎ ስለስራው አስረዳኝ ።

ስራው ምን መሰለሽ ከሱጋ ጤና ጣቢያ አብራው ምትሰራ ዶክተር አለች እና እሷ ደሞ Homecare (ታመው ሆስፒታል አልጋ ሳይዙ ህክምናቸውን ቤት ውስጥ የሚያደርጉ ትላልቅ ሰዎች እንደማለት ነው )

እና እሷ አሁን ክትትል ምታደርግላቸው ሰውዬ የቀድሞ ባለስልጣንና ባለሀብት ነበሩ ግን እርጅናም ሲመጣ በዛ ላይ ህመም ተጨምሮ ታመው ቤት ውስጥ ክትትል ይደረግላቸዋል ።

እኚህ ሰውዬ  ደሞ ዳይፐር ይጠቀማሉ እራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም ዶክተሯ ደሞ የሳቸውን ዳይፐር ለመቀየር እየተፀየፈች ስለሆነ እሷ በምታዘኝ መልኩ እኔ ዳይፐራቸውን መቀየር ነበር ስራዬ።

መጀመሪያ ብዙም ባልስማም እሷ ብዙ ብር ስለሚከፈላት ለኔም ቆንጆ ብር እንደምታስብልኝ በዛ ላይ ቀን ቀን ሌላ ሰው ስለሚንከባከባቸው እኔና ዶክተሯ ማታ ማታ ብቻ እንደምንገባ ነገረኝ እሺ አልኩት ።
ከነገ ጀምሮ ስራ መጀመር እንደምችል ነገረኝ ተነስቼ ወደ ቤት ሄድኩ ተኛሁኝ ከዛ ቡሀላ ሌሊት አካባቢ በሀይል አልቦኝ እየተፈራገጥኩ ነበር ብንን ስል ጨልሟል እኩለ ሌሊት አካባቢ ይሆናል በግምት ከዛ ተመልሼ ለመተኛት ሞከርኩ እራሴን ስላመመኝ አቃተኝ ።

ጠዋት ተነስቼ ወዴት ልሂድ ቤት እንዳልቀመጥ እራበኝ ቤት ውስጥ ስሆን ደሞ ከመቅዲ ውጪ ማሰብ አልችልም ለአያቴ ቡና ስታፈላላት የተቀመጠችበት ላይ እሄድና ቁጭ እላለሁ ከዛ ያሳለፍነውን በሙሉ አስታውሳለሁ

ለዛ ስል ነው ቤት ማልውለው...


@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

09 Nov, 15:50


ግጥም መፃፍ ምንም ነው
በፈጠርኩት አንዳች አለም
ለደረሰብኝ ግን ግጥም ሚባል የለም

ይገርመኛል አንዳንድ ግዜ
ግጥም ግጠም ስትይ ላንቺ
ጠንቋይ ለሱ አያውቅም ነው
አንቺም ለኔ አትመቺ
ይገርመኛል አንዳንድ ግዜ
እኔን ፃፈኝ ስትይ በቃል
ቃል ይከዳል
ቃል ይርቃል ለሚወዱት ይታወቃል
አንዱን ሃሳብ ለመጨበጥ
ሃሳብ የትም ባክኖ ይቀራል
ለሚወዱት ለልብ ወዳጅ
ግጥም መግጠም ያስቸግራል

የመውደዴን ትርጉም
በቃላት ሳልነግራት
ታውቀዋለች ካይኔ
ግጥም ምንም ነው
ቃላት ምንም ነው
ለእንደሷና እንደኔ

አስር ብንዋደድ ብንከንፍ በፍቅር
ቃል የለኝም ላንቺ ግጥሙም ተይው ይቅር
ዝም ብዬ ልውደድ
ዝም ብዬ ላፍቅር

ገጣሚ ብባልም በሃሳብ በመስጠም
ላንቺ ሲሆን ጊዜ
ሲከብድ ግጣም መግጠም


ዮኒ
ኣታን @yonatoz


Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

08 Nov, 17:18


የፍቅር ማእበል


              ክፍል     49

ግን አደለም የምርም ከጎኔ አልነበረችም ቃል ሳልተነፍስ  ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩኝ አንዳንዳንድ ህመሞች ቃላት አይገኝላቸውም የእውነት አሞኝ ነበር ሰላም ህመሙ ግን ምኔ ላይ እንደነበር አላቅም ።

ቤት ሄጄ ዝም ብዬ ጉልበቴን አቅፌ ቁጭ አልኩ ልክ የሆነ ሰው ከፊት ለፊቴ ተቀምጦ እየሆነ ያለውን ያብራራልኝ ይመስል።

የሆነ ሰአት ላይ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ነገር ብንን አልኩኝና ፈጣሪን መጠየቅ ጀመርኩ በመጀመሪያ እናትና አባቴን በአንድ ቀን ነጠከኝ ከዛም አለችኝ ብዬ ላወራ ምችለውን አያቴን ወሰድካት የመጨረሻዋና ልፅናናባት የምችለውን መቅዲንም አጣኋት እንደምታየው ምንም ገንዘብ የለኝም ዘመድ የለኝም ጓደኛውም እንደዛው ጠዋት ከእንቅልፌ ሳልነሳ ብቆይ ምነው ምን ሆንክ ብሎ ሚጠይቀኝ ጎረቤትም የለኝም ስለዚህ እኔን አሁን ምን እንዳደርግልህ ነው እዚህ ምድር ላይ ያስቀመጥከኝ ።

ሰዎች እኔን እያዩ እንኳንም እንደሱ አላደረከን ብለው እንዲያመሰግኑህ ነው። ወይስ ደሞ ለምንድነው ሲጀመር ለምን ፈጠርከኝ ።

አላቅም በዛ ሰአት ምን እያወራሁ እንደነበር ።
እራሴን ላጥፋ እንዴ ብዬ አስብና ከተቀመጥኩበት እነሳለሁ ከዛ ደሞ መቅዲ አውቃ ቢሆንስ እንደዛ ያለችኝ እኔ እራሴን ባጠፋኮ በፀፀት ትሞትብኛለች በቃ እሁድ የምር ሰርጓ ከሆነ ከዛ ቡሀላ እራሴን አጠፋለሁ አልኩኝ።

በነጋታው እንደምንም ብዬ ተሟሙቼ ወንድሞቼጋ ሄድኩኝ አክስታቸው ነበረች በሩን የከፈተችው አሁን አያቴ ስለሞተች ምናልባት ለትንሽ ጊዜ እነሱጋ መቆየት ከቻልኩ ብዬ ጠየኳት ።

እዚህ ችጋር አትጥራብን ድጋሜ እንዳላይህ ብላ አባረረችኝ ከነሱጋ ከተመለስኩ ቡሀላ ወደቤት መሄድ አልፈለኩም እዛ ቤት ውስጥ ስገባ የማስባቸው ብዙ ሀሳቦች አሉ ዝም ብሎ ጭልም ይልብኛል።

እስከ 11 መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ሳይ አመሸሁና ለመቅዲ ደወልኩኝ ለካ ስልኬን ብሎክ አድርጋዋለች ስላላስቻለኝ ሰፈራቸው ሄድኩ እሷን ከየት ላምጣት የሆነ ህፃን ልጅ ሳገኝ ሂድና ጥራልኝ ብዬ ላኩት ።
በጣም በስራ ተወጥራ እንደነበ ያስታውቃል ስታየኝ ብስጭት አለች ።

ድጋሜ እዚህ ሰፈር መጥቼ እሷን የማስጠራት ከሆነ ጮሀ በፖሊስ እንደምታሲዘኝ ነገረችኝ።

አይኗን  ማየት ብቻ ስለነበር የፈለኩት ስላየኋት ደስ እያለኝ ወደቤት ተመለስኩ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳልበላ ስለዋልኩ በጣም እሮብኝ ከንፈሬ ሁላ እየደረቀ ነበር።

መንገድ ላይ ስልክ ቤት አየሁ በርሀብ ከምሞት ስልኬን ብሸጠውስ ከማንጋ አወራበታለሁ ከመቅዲ ውጪ አልኩኛ በጣም በርካሽ ዋጋ ሸጥኩለት ለሆነ ልጅ ከዛ እራቴን በላሁ የቀረችኝ ብር ይዤ ወደቤት ሄድኩ።

ምሽቱ ምሽት እንዳይመስልሽ ልክ ቤት ውስጥ ስገባ ነው በሽታው ሚነሳብኝ ።

በነጋታው በጠዋት ተነሳሁና ከቤት ወጣሁ ምሄድበት ወይ ምውልበትኮ የለኝም ግን ቤት ምውል ከሆነ ብዙ ነገሮችን አስባለሁ ምናልባትም እናትና አባቴ ባይሞቱ ከማንኛውም ልጅ በላይ ተንደላቅቄ እየኖርኩ ነበር እላለሁ ።
ምናልባትም አያቴ ባትሞት ባለቻት የጡረታ ገንዘብ ያሰናዳችውን ብትበቃንም ባትበቃንም ቀምሰን እናድር ነበር ።
ምናልባትም ከመቅዲጋ ባንጣላ ኖሮ ቢያንስ እሷን ለማስደሰት ስል ስራዬን አላቆምም ነበር።

ከምንም በላይ ከባዱ ህመም ያፈቀርሽው ሰው ሲከዳሽ ነው ሰላም ልብሽ ላይ ይሁን ምንሽ ላይ አታቂውም ግን ውስጥሽን ቅጥልልል የሚያደርግ ነገር አለው ።

በቃ እሱን ሰው የሌላ ሆኖ ማየት በዛ ላይ በዙሪያሽ ችግር ብቻ ሲወርሽ እራስሽን የማጥፋት ድፍረቱን ደሞ ስታጪ በቃ የትኛውም አጋጣሚ አንቺን እንዲገልሽ ትማፀኛለሽ ።

እኔ ከቤት ስወጣ ፈጣሪ እራሴን አጥፍቼ ግፍ ከምሰራ በቃ የሆነ ሰበብ ፍጠርና ግደለኝ ወይ አስፋልት ስሻገር ዝም ብለህ በሆነ መኪና እንድገጭ አድርገኝ እላለሁ።

እና ከቤት ወጥቼ ዝም ብዬ መንገድ ዳር ቁጭ እንዳልኩ ይመሽልኛል 11 ሰአት ቡሀላ መቅዲ ሰፈር እሄዳለሁ።

እንዳለችው ለካ እሁድ ቀን  ሰርጓ ነበር።
በጠዋት ተነስቼ ሰፈራቸው ሄድኩኝና ቆምኩ የነሱ ግቢ ድባቡ ጦፏል አንዷን ሴትዮ ቀስ ብዬ ጠጋ አልኩኝና እዚህ ግቢ ምንድነው ያለው አልኳት??  ውይ መቅዲዬ ምን የመሰለውን ሀብታም ባል ልታገባ ነው ብላ አልፋኝ ሄደች ።

ከዛ በቃ አመንኩ ተመልሼ አሰፋልት ሄጄ ቁጭ አልኩኝ። የሆኑ ሴትዮ እቃ ለመሸከም ከብዷቸው ተሸካሚፍለጋ አይናቸው  ሲንከራተት አየሁና እኔ ላድርስሎት ማዘር አልኳቸው እሺ ልጄ ብለው አሸከሙኝ ።
ሁኔታዬን አይተው በጣም ስላሳዘንኳቸው 50 ብር ሰጡኝ እሷን ይዤ እየተጣደፍኩ አረቄ ቤት ሄድኩኝ እስኪመሽ ድረስ ከሽማግሌዎች መሀል ቁጭ ብዬ ስጠጣ አመሸሁ  ድንገት ባፌና ባፍንጫዬ ደም መጣ  ከዛ እዛው ባፍጢሜ ተደፋሁ....

ይቀጥላል ...
✍️ማኔ
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

07 Nov, 19:19


የፍቅር ማእበል


             ክፍል48

በዛ መሀል ከጎኔ የነበረችው 1 ሰው መቅዲ ብቻ ነበረች እስከሰልስቱ ድረስ እኛ ቤት ነበር ያደረችው።

ከዛ ቀስ በቀስ የአያቴ ሀዘንም እየተረሳ ጎረቤትም ከኛ ቤት እየጠፋ መጣ ብቻዬን ማደር ጀመርኩ።
እዛ ቤት ውስጥ ብቻዬን ሳድር በጣም እታመም ጀመር የማይሆን ነገር ያሳስበኛል አንዳንዴ ተኝቼ ለመናስት ስሞክር ሁላ ያቅተኛል አያቴ ከሞተች ቡሀላ እሷ ትኖርበት ከነበረው የቀቤሌ ቤት ውጪ ምንም አልነበረኝም ።
የጡረታ ገንዘብ ሚባል ነገር ቀረ ምግብ ቤት ውስጥ መዘጋጀት አቆመ።

ትምህርት ከተጀመረ ቡሀላ  ጠዋት በባዶ ሆዴ ከቤት እወጣለሁ  ቀን መቅዲ ያመጣችውን ምሳ አብረን እንበላለን ከዛ ደሞ በሚቀጥለው ቀን እሷ ያመጣችውን ምሳ ነው ለሁለት ምንበላው ።

አንዳንዴ ቤት ውስጥ ዳቦ ወይ የተለየ ነገር ሲኖር ታመጣልኝና ይሄንን ማታ ቤት ብላው ትለኛለች ቤተሰቦቿ በብር ጉዳይ ሲሬስ ስለነበሩ እጇ ላይ ብር የማግኘት እድሏ ጠባባብ ነው እሷ ግን ከጓደኞቿ ከሰው እየተበደረች ብር ትሰጠኛለች እንደበፊቱ አየር ባየር ስራ መስራትም አልቻልኩም ምክንያቱም እኔ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ገብቼ ስለነበር ከሰዎችጋ አውርቼ ለመግባባት እራሱ ይከብደኝ  ነበር።

ያንን አመት እንደምንም ጨርሰን ክረምት ላይ ስራ ጀመርኩ ።
ከስራ እንደወጣሁ ቀጥታ እነመቅዲ ሰፈር እሄዳለሁ አብረን አምሽተን ወደቤት እመለሳለሁ ።

አስታውሳለሁ በተከታታይ ለ3 ቀን አልተገናኘንም ነበር::

ከዛ ደውላ በጣም ልታገኘኝ  እንደምትፈልግ ነገረችኝ በጣም ናፍቃኝ ስለነበር ለማግኘት ጓጉቼ  ከስራ ቀድሜ ወጥቼ ሰፈሯ ሄድኩ ሀሙስ ቀን ነበር።

ለ1 ሰአት ምናምን ያህል መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ ጠበኳት ከዛ መጣች ና ካፌ ቁጭ ብለን እናውራ አለችኝ።
እንደሌላ ጊዜው በስርአቱ እንኳን ሰላም አላለችኝም ነበር ።
ተነስተን ወደካፌ ገባንና ቁጭ አልን በጣም እንደናፈቀችኝ ይሄ 3 ቀን ሶስት አመት እንደሆነብኝ ነገርኳት ።

እሷ ግን ልጥጥ እያለች ካሁን ቡሀላ አለመገናኘታችንን መልመድ አለብህ አለችኝ ።

በጣም ደነገጥኩና ማለት አልኳት ።
ላገባ ነው አለችኝ ከዛ ከት ብዬ ሳኩባትና ባክሽ  አትጃጃይ እኔ ከልቤ ነው የናፈቅሽኝ ምናባሽ ነው ግን እንደዚህ ያጠፋሽ አልኳት ።

ኮስተር ብላ ቀልዴና ምሬን እንኳን ለይ እንጂ አባቴ ይሙት ላገባ ነው አለችኝ ።
የዛን ሰአት የተሰማኝን ስሜት አሁን ለማብራራት አልችልም ።
ግን እንደምንም ብዬ እንዴት አልኳት።

በቃ ላገባ ነው ተምሬ እንደሆነ አያልፍልኝ አሁን ያገኘሁትን እድል ተጠቅሜ የኔንም የቤተሰቤንም ህይወት መቀየር አለብኝ አለችኝ ።
ደግሜ ለምን አትወጅኝም እንዴ አልኳት የዛኔ እያየኋት እራሱ ብዥዥ እያለብኝ ነበር።

እወድሀለሁ ግን ፍቅር ገንዘብ አይሆንም አለችኝ ።
አንድም ቀን ስለድህነትህ አስቤ አላቅም ነበር አሁን ግን እየበሰልኩ ስመጣ እዚህ ምድር ከምንም በላይ አስፈላጊው ገንዘብ ነው ገንዘብ ካለህ ብትታመም ታክመህ ትድናለህ ሰው የሚያከብርህ የሚወድህ ገንዘብ ሲኖርህ ነው። ገንዘብ ካለህ ቤተሰብህ እራሱ ያከብሩሀላ ሁሉም ሰው ወዳጅህ ይሆናል : ገንዘብ ካለህ ፈልገህ የምታጣት ሴት አትኖርም ብቻ አንተ ገንዘብ ይኑርህ እንጂ ምድሪቷ ገነት ናት አለችኝ ።

እያወራች ያለችውን ለማመን ከብዶኝ ነበር ድጋሜ አትወጅኝም አልኳት።
እወድሀለሁ ግን ካንተጋ ብንጋባ ገና ሀብታም ለመሆን ስንት አመት ይፈጅብኛል ።እኔና አንተ ሀብታም እስክኖን አባቴ በህክምና እጦት ይሞታል
እኔና አንተ ብዙ ገንዘብ እስኪኖረን እናቴ ለኔና ለእህቶቼ ስትል መልፋቷን አታቆምም እንደጎረቤቶቻችን የቤት እመቤት መሆን አትችልም አንተን ትቼ አዲሱን ሰውዬ ካገባሁ ግን ሀብቱ ለኔ ብቻ አደለም ቤተሰቦቼንም ይቀይራል በኔ ምክንያት ቤተሰቦቼ ከማየት ውጪ ደሞ ምንም ደስታ የለም ግን አሁንም ቢሆን እወድሀለሁ ላንተ ስሜት አለኝ የማገባውን ሰው ደሞ ገንዘቡን እወድለታለሁ ለዛም ነው እንደጓደኞቼ ቦርቄ ሳልጨርስ የማገባው ።

ሰርጉ የአሁኑ እሁድ ነው ሰሞኑን ልነግርህ ፈልጌ ግን እንዴት እንደምነግርህ ፈርቼ ነው በቃ ጨርሰናል ብላ ጉንጬን ስማኝ ተነስታ ሄደች እኔ የተቀመጥኩበት ወንበር ላይ እንዳለሁ ያወራችው የእውነት ስላልመሰለኝ ጠረጼዛው ላይ ድፍት ብዬ አይኔን ጨፈንኩኝ.....

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

06 Nov, 19:56


የፍቅር ማእበል


     ክፍል 47

እሺ ግን በቃ በየመሀሉ እየገባሽ ለምን እንዲህ ሆነ ለምን እንዲህ አደረክ እንዳትይኝ በቃ አንቺ እዚጋ ማዳመጥ ብቻ ነው ስራሽ በመሀል እያወራሁ ቢነስረኝ እንኳን እንዳትደነግጪ አለኝ።

የዛኔ ይበልጥ ለመስማት እየጓጓሁ እሺ ችግር የለም ቀጥል አልኩት አይን አይኑን እያየሁ።

ልዑል እባላለሁ የተወለድኩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው።

እናቴ እና አባቴ ሲተዋወቁ አባቴ ከሌላ ሴት የወለዳቸው ሁለት ወንድሞች ነበሩኝ።

እናቴ ሲበዛ ቆንጆ የዋህ ነበረች አባቴም ያለ ቤተሰብ ስላደገ የቤተሰብ ማጣት ለልጆች ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ስለሚያቅ ለልጆቹ በጣም የተለየ ፍቅር ነበረው ሁላችንንም አብዝቶ ይወደናል ይንከባከበናል ። በጣም ቆንጆ ሚባል የሚኖሩ ቤተሰቦች ነበርን ።

አንድ ቀን እናቴና አባቴ የናቴን እናት(አያቴን ) ለመጠየቅ እንደሄዱ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ሁለቱም ሞቱ የናትነትንም ያባትነትን ፍቅር በአንድ ቀን ተነጠቅን ። ህይወት ስትሰጥሽም ስትነሳሽም አትሳሳም ።

ከዛ በዛ ሁላ ሀዘን ውስጥ በገባንበት ሰአት  የወንድሞቼ  እናት ሞታ እንደነበረና ከዛ ቡሀላ አባቴ የኔን እናት እንዳገባ ነግሬሻለሁ አደል እና የሷ እህት ማለትም የወንድሞቼ አክስት ሙሉ የማሳደግ መብቱን ወሰደችና እኛ ቤት ገባች።

ከዛ ግን ብዙም ሳይቆይ እኔን ከቤት አስወጣችኝ ምን እዳ አለብኝ የሰው ሰው ማሳድገው ብላ ከናትና አባቴ ቤት አባረረችኝ ከዛ ወደ ደካማዋ አያቴ ቤት ሄድኩኝ ።

እሷ ከጡረታ ገንዘብ ውጪ ገቢ የሌላት ምስኪን ብትሆንም እኔም ጎዳና ከምወድቅ መጠጊያዬ እጇን ዘርግታ የተቀበለችኝ እሷ ስለነበረች እሷጋ ትምህርቴን እየተማርኩ መኖር ጀመርኩኝ።  ልክ 7ኛ ክፍል ስደርስ ከአንድ የትምህርት ቤታችን ልጅጋ ፍቅር ያዘኝ።

በሰአቱ እኔ ሰፈር ውስጥ አየር ባየር የተወሰኑ ስራዎችን እሰራ ስለነበር  ቆንጆ ቆንጆ ጫማዎችን እገዛለሁ ብታምኝም ባታምኚም 1 ሱሪ ብቻ እያለኝ እኔ ግን ብር ባገኘሁ ቁጥር ጫማ ብቻ ነበር ምገዛው ምክንያቱም ትምህርት ቤት ካሉ ጓደኞቼጋ በዩኒፎርም እኩል ስለሆንን አሮጌ ጫማ እያደረኩኝ እራሴን አላስፎግርም እያልኩ ነበር።

በሰአቱ የነበሩን ጓደኞቼ አይን ውስጥ ትገባለህ ቆንጆ ነህ አቋምህ ያምራል ለምን ሴቶችን አታተራምስም ይሉኝ ነበር።
አንድም ቀን ግን ሰምቻቸው አላቅም በትምህርቴም ቢሆን በጣም ጎበዝ ነበርኩ ።

እና እንዳልኩሽ ፍቅር ያስያዘችኝ ልጅ መቅደላዊት ትባላለች ።

እንዲሁ በመተያየት ብቻ ወደድኳት ወደድችኝ ትምህርት ቤት ውስጥ አሉ ከሚባሉ ቆንጆዎች ውስጥ አንዷ እሷ ናት።

እና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቅር ተነደፍኩ አሁን እንደማወራልሽ እንዳይመስልሽ ነፍሴን ሰጥቼ ነበር ምወዳት።

ስለኔ ሁሉንም ታውቃለች ድህነቴን አትፀየፈውም ሚስጥረኛዬ ነች አያቴን አስተዋውቂያታለሁ በሄድኩበት ሁላ እሷ አለች ።
ምሳ እንኳን ለሁለታችንም የሚበቃንን ቋጥራ ትመጣለች አንዳንዴ በሁለት ምሳቃ ትቋጥርና ይሄንን ቤት ስትገባ ከአያትህጋ ብሉት ብላ ቦርሳ ውስጥ ትከትልኛለች ።

እንደሌሎቹ ሴቶች ከኔ ምንም ስጦታ አጠብቅም ግብዣ ምናምን እሷ ጭራሽ ትዝ አይላትም በቃ እኔና እኔን ብቻ ነው ምታስቀድመው።
አስታውሳለሁ የሆነ ጊዜ ልደቷ ደርሶ ነበር እኔ እንደምንም ተሯሩጬ ብር አገኘሁኝና ስጦታ ገዝቼ ሰጠኋት ብታምኚም ባታምኚም 3 ቀን አኮረፈችኝ ለኔ ስጦታ ምትገዛበትን ለአያትህ ብትሰጣቸውኮ ይመርቁን ነበር አለችኝ ።

ትምህርት ቤት ውስጥ እኔ ነኝ ያለ couple ሆንን በሀላችን የመርፌ ቀዳዳ ታክል ክፍተት አልነበረም ከ7ወደ 8 አልፈን 8ኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን ለኔ ስኮላር ሺፕ መጣልኝና ከዛ እራቅ ወዳለ የሀብታም ትምህርት ቤት እንድገባ ሀሳብ ቀረበልኝ። ግን ከመቅዲጋ መለያየት ስለማንችል ሀሳቡን ውድቅ አድርጌ ወደ 9 እዛው አብረን ገባን ።

9 ክፍል ላይ ስንደርስ አያቴ በጠና ታመመችብኝ አብዛኛውን ጊዜ መቅዲ ክላስ እያለች እየወጣች እኛ ቤት ለአያቴ ምግብ ስትሰራ ቡና ስታፈላ ትውላለች ልክ ተማሪዎች ሲበተኑ ወደ ቤቷ ትሄዳለች።

በህይወቴ ከሷ ውጭ ላላይ እሷም ከኔ ውጭ ላታይ ቃል ተገባባን ።አንድም ቀን ለደቂቃ ከሷ ስለመለየት አስቤ አላቅም ነበር ። ቶሎ ተመርቄ ቆንጆ ስራ ይዤ እሷን ሚስቴ ስለማድረግ እንጂ ከሷጋ ተለያይቼ ሌላ ሴት ለምጄ አፍቅሬ እኖራለሁ የሚል ሀሳብ በህልሜ ሁላ አላይም ነበር።
ለምን ካልሽኝ በቃ እሷ ፈጣሪ ሁሉን አሟልቶ ነው የሰጣት ስላገኘሁም ስላጣሁም አትቀየርም።

እና 9 የመጀመሪያውን ሴሚስተር ጨርሰን እረፍት ላይ ነበርን በየቀኑ ከመቅዲጋ እንገናኛለን ።

እና በዛ መሀል አንድ አለችኝ የምላትን አያቴን በሞት አጣኋት  ሳላስበው ቤተሴቤ ብዬ ልጠራት ላስተዋውቃት ምችለውን አንድ ሰው ልክ እንደናትና አባቴ ሞት ነጠቀኝ .......

ይቀጥላል

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

06 Nov, 03:35


ደህና ነኝ በሚለዉ..
የቃላት ጨዋታ የልቤን ስብራት
እንደሸፋፈንኩት......... እንዳድበሰበስኩት
የዉስጥ ስሜቷን ያልታዬዉን የእሷን ህመም
በልማድ መልስ ለይስሙላ በደና ነች አልዘጋዉም
ስለዚህ.....
እሷ መጥታ ደና እስክትል
አላዉቅም ነዉ እኔ የምል።

@JahOnyx

የሀገሬ ወጎች

05 Nov, 20:02


የፍቅር ማእበል

    
          ክፍል 46

ምን ማለትህ ነው ልዑል ንገረኝ ላብድ ነው ቆይ እኔን ተወኝ ሆዴ ውስጥ ያለው ልጅ ሰላም እንዲሆን ከፈለክ ምን ለማለት እየሞከርክ እንዳለህ አስረዳኝ ።

አይዞሽ እስከነገ ጠዋት መቆዬቴ አይቀርም ጠዋት በተረጋጋ መንፈስ አወራሻላሁ  ብሎ ተነስቶ ጥሎኝ ገባ ።

ከነ ደሙ በደረቱ ድፍት ብሎ ተኛ ተነስቼ ሶፍት አምጥቼ ሰጠሁት ቢያንስ አፍንጫህ ላይ አድርገው አልኩት ።

ሳሎን ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ የማደርገው የማወራው ግራ ገባኝ  እጄ እየተንቀጠቀጠ ነበር ምን እየተፈጠረ እንዳለ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ ለደቂቃ ልዑሌን በዚህ መልኩ አየዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ከመደንገጤ የተነሳ አስሬ እየተነሳሁ ትንፋሹን ቼክ እያደረኩኩ እቀመጣለሁ ።

አንዳንዴ ጭንቅላታችሁ በጣም ቢዚ ሆኖ በጣም ብዙ ሀሳብ ሲደራረብባችሁ ምን ማሰብ እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችሁ ድንዝዝ ብላችሁ አታቁም እኔ እንደዛ ነው የሆነኩት።።

ሌሊቱን እንደ እብድ ሲያደርገኝ የሆነ ሰአት የማየው ነገር ሁላ ጭልም እያለብኝ መጣ ህመሙ ይሄ ነው የምለው አደለም ከእስከዛሬው በተለየ እያመመኝ ነበር እረፍት ካላደርኩ እራሴን ካልጠበኩ ልጄን ላጣው እንደምችል ስለገባኝ ተነስቼ ገብቼ ተኛሁ ፊቴን ወደ ልዑሌ አዙሬ ነበር የተኛሁት ግን አቅለሸለሸኝ ደሙን ማየት አልቻልኩም ነበር ድጋሜ ፊቴን አዙሬ ተኛሁ።

ሳላስበው እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር ጠዋት ስነቃ ልዑሌ ተነስቶ ሻወር ወሳስዶ ልብስ ቀያይሯል እኔ እንደተነሳሁ አይኔን ለማየት ሁላ እያፈረ ነበር ይቅርታ ሰላም ማታ ማይሆን ነገር ተናግሬሻለሁ እንዴ አለ ።

ቁርስ በላህ አልኩት አይ በቃ እንብላ ከዛ እናወራለን ብዬው ቁርሳችንን በላን ።

እንደጨረስን በቃ ልዑሌ እኔና አንተ ሰፋ ያለ ሰአት ስለሚያስፈልገን እዚህ እንሁን አልኩት ወይም ወደ ውስጥ እንግባ ባባ ከመሲጋ ይሆናል አልኩት እሺ አለኝ።

ስራ ሚረፍድብህ ከሆነ ግን አሳውቃቸው ዛሬ እንደማትገባ እኔንም ሀኪም ቤት መውሰድ  አለብህ በዛ ላይ አሁን ብዙ እናወራለን ዛሬ ጊዜህን ለኔ ስጠኝ አልኩት።

እሺ ሰላም ስልክ ደውዬ መጣሁ ብሎኝ ወጣ ብዙም ሳይቆይ ተመለሰ  ።

በመጀመሪያ በግልፅ እንደባልና ሚስት ሁሉንም እንደምናወራ ማልልኝ አልኩት ማለልኝ።

በመጀመሪያ ትናት ምን ሆነህ ነው እንደዛ የሰከርከው አልኩት ??

ይቅርታ ሰላም እንደዛ ማድረግ አልነበረብኝም ግን ካንቺጋ ከወጣሁበት ሰአት ጀምሮ ስጠጣ ነበር በዛ ላይ በባዶ ሆዴ ስለነበር የጠጣሁት ለዛ ነው እንደዛ ደም በደም የሆንኩት ማታ ይቅርታ አለኝ ::

ችግር የለውም አሁን ከመጀመሪያው ጀምርና እኔ ማወቅ ያለብኝን እያንዳንዱን ነገር ንገረኝ አላቋርጥህም ከመጀመሪያው ጀምርና አሁን እስካለንበት ድረስ በቃ በግልፅ ምንም መደባበቅ ሳይኖረው ንገረኝ ።

ጀምር እየሰማሁህ ነው አልኩት..

ይቀጥላል....

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

05 Nov, 19:12


ድኩም ስጋ ይዘን
አንዲት ሀረግ መዘን
ላንችለው መግፋቱን
ላናውቀው ወረቱን
እንድያው ብክንክኑን ስንዋልል ውለን
ዛሬም እንደ ትላንት እንዳለነው አለን

አለን እንደ ትላንት ስንል ደፋ ቀና
ጥርስን እያሰቅነ እንላለን ደህና
ደህና መሰንበት ነው ዋናው ከመክረሙ
እያታለላችሁ ጥርሳቹን አትሙ
እንዲም እንዲያም አልን
ዉልፍት ላንል ችለን ከግዜር ትዛዝ ወጉ
ሆዴ ነው ጠላቴ ብላችሁ አታውጉ

ይልቁንስ ትተህ ማማረሩን ክቦ
የዚች አለም ዕጣ ላያልቀው ተነቦ
እንደ ሀረጊቱ ላይጨርሰው ስቦ
ተመስገን በል አቦ!


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

04 Nov, 14:46


💊🔮 ከፍቶሀል? ወንድሜ 🙍‍♂
           ከፍቶሻል? እህቴ 🙍‍♀

🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ቶሎ በሉ ከ10 ደቂቃ ቡሀላ ይጠፋል👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የሀገሬ ወጎች

03 Nov, 19:47


የፍቅር ማእበል



          ክፍል45

ምን ማለት ነው ህይወቴን ለማትረፍ ማለት እእ ምንድነው ምትቀባጥረው አልኩት ።

በቃ እንደውም ሁሉንም ትቼዋለሁ ያኔ ስታጭኝ ይቆጭሻል አንድም ቀን ቁጭ አድርገሽ እንደትልቅ ሰው ምን አጋጥሞህ ነው ምንድነው ከኔ የደበከኝ በህይወትህ ውስጥ ምን አሳልፈሀል ብለሽኝ አታቂም።

የመጀመሪያ ቀን አመሸሁ ተቆጥተሽ ከመናገር ውጭ ምንም ነገር በእርጋታ ሳጠይቂኝ ቀረሽ በድጋሜ ሳመሽ 2 ቀን ሙሉ ፊት ነሳሽኝ ለምኜሽ ታረቅን ለሶስተኛ ጊዜ ሳመሽ እንደ ሚስት እንደጓደኛ  ቁጭ አድርገሽ ምን ገጥሞህ ነው እንዲህ እስካሁን ያመሸኸው ሳትዋሽ የገጠመህን ንገረኝ በማለት ፈንታ እኔ ስገባ እንደህፃን ልጅ ከክፍል ወጣሽ ።
ይኸው ያ ሁላ ነገር ተፈጠረ እሱም አልበቃ ብሎሽ ተመልሼ ወደቤት አልመጣም ብለሽ እናትሽ ቤት መጣሽ  እሺ  ቆይ በዚህ ህይወት ውስጥ ጥፋተኛ እኔ ብቻ ነኝ እእእ

ሌላ ምንም አደለም ሚቆጨኝ በህይወቴ ምኖርለት ሰው አገኘሁ ብዬ እንደ አዲስ ለመኖር ህይወቴን ሀ ብዬ ለመጀመር በህይወት ለመቆየት ስጣጣር አንድ ከጎኔ ሚሆን ሰው ማጣቴ ብቻ ነው ሚቆጨኝ።

ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲያለቅስ ማየት ያስጠላል ለዛውም ያ ባለ ግርማ ሞገሱ ልዑሌ ።

ምላሼን አልጠበቀም ቀጥታ ከቤት ወጣ ልዑሌ ልዑሌ እያልኩ እየጠራሁት ዞሮ እንኳን አላየኝም ተነስቼ መሮጥ አልችል ነገር መሲን ጠርኋትና ልዑልን ተከተይው አልኳት ፈጠን ብላ ከቤት ወጣች  ብዙም ሳትቆይ ተመልሳ መጣች እንዳትከተይኝ ብሎ ጮኸብኝ ምን ሆኖ ነው እንደዚህ  ሲሆን አይቼው አላቅም አለችኝ።

የዛኔ ይበልጥ ጨነቀኝ ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ዘጋብኝ ደግሜ ደወልኩኝ ከነጭራሹ ስልኩን አጥፍቶታል ።

እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩኝ እዛው ሶፋ ላይ በጀርባዬ እንደተኛሁ ግን ምን ለማለት እየሞከረ እንደነበረ ተደበላለቀብኝ እኔ ያንጰያህል ሰውን ማልረዳ ግድ የለሽ ሚስት ነኝ ልዑሌ ለማውራት የሞከረው ስለምንድነው ግራ ገባኝ ።

መሲ ምሳ ልስጥሽ አለችኝ እኔ በፍፁም ምንም አልበላም አልኳት ።

ወደ ማታ አካባቢ እህቴ ከመጣች ቡሀላ እኔና መሲ ባባን ይዘነው የፅንስ ማጠናከሪያውን ልወጋ ወደ ሆስፒታል ሄድን ። 

ከዛ ስንመለስ ልዑሌጋ ደወልኩለት ስልኩ እንደተዘጋ ነው ወደ ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር ግን ቁልፍ አልያዝኩም አልኳት ለመሲ ።
አረ እኔጋ አለኮ የዛኔ ከቤት ቀጥታ ወደ ሆስፒታል ስንመጣኮ ቆልፈን ያንቺን ቁልፍ ይዘነው ነው የመጣነው አለችኝ እሺ በቃ እንደዛ ከሆነ ወደ ቤት እንሂድ አልኳትና ሄድን ።

ቤት ስንሄድም ልዑል የለም ደጋግሜ ብደውልም አይሰራም ስልኩ የምር መጨነቅ ጀመርኩ ብዙ ጊዜ በጎን በጎን እያደረገ ሊነግረኝ የሚፈልገው ነገር አለ ግን አንድም ቀን ጆሮ ሰጥቼው ሰምቼው አላቅም ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም ።

አልጋዬ ላይ እንደተኛሁ መብሰልሰል ጀመርኩ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደረሰ አምላኬ ሆይ አረ እባክህ ገንዘብ ምን ይሰራል ሰላም መሆንን የመሰለ ጤና እያለ  አልኩኝ ለራሴ ።

ባባ ከመሲጋ ነበር የተኛው ቢያለቅስም እኔ ተነስቼ ላባብለው ስለማልችል  እሷጋ ነው የሆነው ።

እነሱ እንቅልፋቸውን እየለጠጡ ነው እኔ እዚህ በሀሳብ  እብሰለሰላለሁ።

አየመሸ ነው ግን አይመጣም ልዑል ምን አስቦ ነው ቆይ የት ሊሄድ ይችላል ግራ ገባኝ ሰአቱን አላስታውስም ግን በጣም መሽቶ ነበር ልዑል መጣ ሲያየኝ ደነገጠ።

በጣም ጠጥቶ ሰክሮ ነበር
የለበሰው ሸሚዝ ደም በደም ሆኗል ሳየው ደነገጥኩኝ ምን ሆነህ ነው ምን ሆነህ ነው አልኩት እየተርበተበትኩ ምንም አልሆንኩም ነስሮኝ ነው አይታይሽም እንዴ አለኝ ።

አረ ልዑሌ ተቀመጥ ምንድነው የሆንከው በፈጣሪ ንገረኝ አልኩት ምንም እንደምታይው ባፌም ባፍጫዬም ደም እየፈሰሰ ነው በቃ ልሞት ነው እስካሁን መቆየቴ ሁላ ታምር ነው ይገርምሻል አለኝ።


ይቀጥላል...
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

02 Nov, 18:09


የፍቅር  ማእበል


      ክፍል 44

የዛኔ እናቴ የሆነ ነገር እንዳለ ገባትና ዝም አለችኝ ።
ልዑልም ዝም ብሎ ወደናቴ ቤት ነዳው ቤት ከደረስን ቡሀላ እናቴና እህቴ ቤቱን ፏፏ ለማድረግ መሯሯጥ ጀመሩ ።

እኔ ሶፋ ላይ ተስተካክዬ ተኛሁ መሲም ባባን እያባበለች ለማስተኛት እየሞከረች ነበር ።

ልዑሌ ጥጉን ይዞ አንገቱን ድፍት አድርጎ  ቁጭ አለ ባባ ሲተኛ እኔጋ አምጥታ አስተኛችውና እነማዬን ለማገዝ ወደ ጓዳ ገባች መሲ የዛኔ ቆይ ሰላም ለምንድነው እንዲህ ምትሆኚው አለኝ።

ዝም አልኩት  እሺ ልታይኝም ልታናግሪኝም አትፈልጊም ቆይ ምን አደረኩሽ አለ ።
ከዚህ በላይ ምን እስክታደርገኝ መጠበቅ ነበረብኝ እእእ ባንተ ምክንያት ልጄን አጥቼ ነበር እኔም ልሞት ነበር ።

ያንተን ነገር ሳብሰለስል ነው የወደኩት ድንገት ተነስቶ  እስከ እኩለ ለሊት እያመሹ መምጣት ጀብድ መሰለህ እንዴ  አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም ከቻልክ  በቃ ከዚህ ብትሄድ ጥሩ ነው መሲንም ይዘሀት ሂድ ምግብ ትሰራልሀለች ለኔ እናቴ አለች አልኩት ።

አይ መሲ ካንቺጋ ትሁን እናትሽና እህትሽን አታስቸግሪ እህትሽም ተማሪ ናት በቃ ቻው ብሎኝ  ወጣ።

እናቴ እንድናወራ ብላ ወደ ጓዳ እንደገባች ገብቶኛል ልክ እሱ ሲወጣ እየሮጠች ተከተለችውና ቡና ሳትጠጣ አትሄድም አለችው እሱ አይ አመሰግናለሁ ሰው ቆሞ እየጠበቀኝ ነው ብሎ ዋሽቷት ሄደ።

እሱ ከሄደ ቡሀላ ቡናችንን ጠጥተን ምሳችንን በላልተን ስንጨርስ እናቴ ባባን ያዙትና እስኪ ውጪ ተጫወቱ አለቻቸው  መሲንና እህቴን እሺ ብለው ወደ ውጪ ወጡ ።

እናቴ ቁጭ አደረገችኝና ልጄ ምንድነው የተፈጠረው ከልዑልጋ ሳትዋሽ እውነቱን ንገሪኝ ??አለችኝ ።

አረ እማዬ ምንም አልተፈጠረም አልኳት ።

ልጄ እኔ እናትሽ ነኝ እንኳን ይሄንን ከዚህ በላይም ብዙ እረዳለሁ ።

ልጄ ልዑል እኔ እስከማቀው በጣም ጥሩ ልጅ ነው ግን የሰው ልጅ ፀባዩ አይታወቅም አሁን እየቆየሽ ስትመጪ ደሀ ስለሆንሽ እየናቀሽ መጣ እንዴ ንገሪኝ እውነቱን ወይስ ምንድነው አለችኝ።

አይ እማዬ ልዑል የገንዘብ ነገር ችግር የለበትም ግን እንዲሁ ስላናደደኝ ነው እማዬ አምሽቶ እየመጣ ስላናደደኝ ትንሽ ልቅጣው ብዬ እንጂ ተናንቀን ምናምን አደለም ግን እማዬ ካሁኑ ካልቀጣሁት ነገ ኖርማል እያደረገው ስለሚመጣ ነው እንጂ አንቺ እንዳሰብሽው አደለም አልኳት።

እርግጠኛ ነሽ አለችኝ ።
አዎ እማዬ አታስቢ አሁን እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ ትንሽ ልተኛ አልኳት ።

ግን የሰው ልጅ  መተኛቱ አደለም ዋናው ነገር ጭንቅላቱ እረፍት ማግኘቱ እንጂ ጭንቅላታችን ሰላም ከሌለው እረፍት ካጣን መተኛታችን ትርጉም አልባ ነው።

የዛን ቀን መሽቶ ከነጋ ቡሀላ በነጋታው እናቴንም ስራ ካልሄድሽ ብያት ወደ ስራዋ ሄደች እህቴም ወደ ትምህርቷ እኔና መሲ ቤት ውስጥ ቀረን ወደ 5 አካባቢ ልዑል መጣ  እኔ መንቀሳቀስ ስለማልችል ልዑል ሲመጣ መሲ ልጁን ለልዑል ሰጠችና ምሳ መስራት ጀመረች።

ባባ እንቅልፉን ሲተኛ አምጥቶ አስተኛውና ማውራት እንችላለን አለኝ?

ምን እናወራለን አልኩት ??

ሰላም ማታ ቤት ሄጄ እንቅልፍ ሚባል ባይኔ አልዞረም ሰላም እኔ ወደ ኋላ መመለስ አልፈልግም ቤት ስገባ ሰው እንዲጠብቀኝ እፈልጋለሁ ጠዋት ስራ ወጥቼ እስክመለስ ምናፍቀው ሰው ያስፈልገኛል ሰላም በፈጣሪ ቆይ ምን እየሆንሽ ነው ቆይ እኔ አንቺን ቤቴን ልጄን ጠልቼ ነው ሚመስልሽ እእ....

እሱን ማሰብ የነበረብህ  አሁን አደለም ስልክህን እያጠፋህ እያመሸህ ስትመጣ ባንተ ምክንያት መጨነቅ የለብኝም ባንተ ሀሳብ ምን እንደምረግጥ እንኳን ማስተዋል አቅቶኝ ልጄን አጥቼ ነበር በቃ አሁንም ላይህ አልፈልግም አታስጨንቀኝ ደና እስክሆን መነሳት እስክችል እንኳን ተወኝ አልኩት....

የዛኔ ብስጭት ብሎ ብድግ አለ ሰላም ቆይ እኔ የት ማመሽ ነው ሚመስልሽ በየመጠጥ ቤቱ ስዝናና ስጨፍር አደለምኮ ህይወቴን ለማትረፍ ነው በኩለ ሌሊት ምገባው .......


ይቀጥላል ....

Maneget
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

02 Nov, 15:41


ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

እፈራለሁ እንዳልነገርሽ የውስጤን ውስጥ ጉዳጉዱን
እንዳትርቅህ የሚል ሃሳብ አሳሰበኝ እግዞ ስንቱን
ይበላኛል ንዴት ስሬን
አይታከክ እንዳላከው
ምን ስትይኝ ፈዛዛ ሆንኩ
ንፁህ ልቤን የባረከው
እቀናለሁ ሳይሽ ደግሞ
ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እህትህ ናት ይላል ልቤ
አካል ስጋ ሆኖ ባዳ
ጉደኛ ነኝ ኧረ እኔማ
ጉዴ ገና ያላለቀ
ጓደኛ ነን በሚል ሰበብ
እሳት ፍቅሬ ያልተወቀ
አልታጠኩም የድፍረት ሻሽ
ለመናገር የፍቅሬን ቃል
ይነደዋል የዋህ ሆዴ
ጥርሴ ደግሞ ስንቴ ይስቃል
ሲያወሩሽ ባያቸው እንደው የድንገቱን
አሳሰበኝ እግዚኦ ስንቱን።

ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

01 Nov, 16:29


የፍቅር ማእበል.

          ክፍል 43

እና የሆነ ቀን ልዑሌ በጠዋት ተነስቶ ቁርስ ሳይበላ ሳይነግረኝ ከቤት ወጣ።

አድርጎት ስለማያቅ ልክ እንደተነሳሁ ደወልኩለት አነሳውና በጣም አስቸኳይ ነገር ገጥሞት እንደሆነ ነገረኝ ።

እሺ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት ቀን ሙሉ ደግሞ ሳይደውልልኝ ምሳ ሰአትም እመጣለሁ ሳይለኝ መሸ  ማታ አካባቢ ደግሜ ደወልኩለት ድምፁን ቀንሶ ሰላሜ እንደባለፈው አመሻለሁ ስመጣ እደውልልሻለሁ ተኚ እስከዛ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው።

በጣም ተበሳጨሁ መሲን ባባም ስለተኛ እሷም እንድትተኛ ነገርኳት እሷ ግን እንቢ ትቼሽ አልተኛም እናውራ ዝም ብለን አለችኝ እሺ አልኳት ።
ስትፈልግ እደር አትምጣ እንደውም አሁንስ አበዛኸው ብዬ text ላኩለት አልመለሰልኝም::

መሲ ያው ሁሌ አውርታ ስለማትጠግበው ስለ በፊት ባሏ ትነግረኛለች ብታይ የመጀመሪያ ያየሁት ቀን ምን እንደተሰማኝ ከሰው መሀል ልቤን ትርትር አደረገው። እንዴት እንደሚወደኝኮ ገበያ ሄዶ ማበጠሪያ ገዝቶልኝ ይመጣል ።
ይሄኔኮ እኔና እሱም ወልደን ዛብሎኔን የሚያክል ጎረምሳ ይኖረን ነበር አለችኝ ካይኗ እንባ እየቀደማት።

አይ በቃ መሲ ሂጂ ተኚ እኔም ልተኛ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እያወራሽ ወደ ኋላ አትመለሽ ነገሽ የተስተካከለ እንዲሆን ፈጣሪሽን ለምኝው አልኳትና ተነስታ ገባች።

እሷ ከተኛች ቡሀላ ባባ ተነሳ ድጋሜ እሱን አባብዬ ልብስ ቀያይሬ አስተኛሁት ።

ለረጅም ሰአት ስንጎራደድ ስለነበር በጣም እራበኝና ወደ ኪችን ገብቼ ለመብላት ሞከርኩኝ ግን ምንም መብላት አልቻልኩም።
ቤቱ ሊበላኝ መሰለኝ አንዴ እታች እወርዳለሁ ድጋሜ ተመልሼ ባባጋ እወጣና አየዋለሁ ።

ትንሽ አብሬው ስቀመጥ ጭንቅ ይለኝና እነሳለሁ ።
ጭንቅላቴ በሀሳብ ሊፈነዳ ደረሰ ዝም ብለሽ ጩሂ ጩሂ አለኝ ።

አስሬ ሰአት አያለሁ ስልኬን አነሳና አስቀምጣለሁ ።
እንዲሁ እንደተጨነኩ ምንም ሳያፍር ሰአቱን ጠብቆ መጣ ።

በሩን ከፍቼለት ምንም ቃል ሳልተነፍስ ወደ ውስጥ ገባሁ እሱም ምንም ሊለኝ አልፈለገም ፊቱን ቋጥሮ ዝም ብሎ ተከትሎኝ ገባ ።
ወጥቼ ባባን አየሁትና እያየኸው እንዳይታፈን ካለቀሰ ጡጦ ስጠው ብዬ ከክፍሉ ወጣሁ ።

አንቺ የት ልትሄጂ ነው ???

አንተን ወደማላይበት ብዬው ዝም ብዬው ሄድኩ በነገር ጦፌ ምን እንደምረግጥ ምን እንደማይ ምን እንደማስብ ሁላ አላውቅም ነበር ::

ከክፍሉ ወጥቼ ገና ደረጃውን ሳልወርድ ምን እንዳንሸራተተኝ ሳላውቅ በቂጤ ወርጄ እንዘጭ አልኩ ።

ሳላስበው በሀይል ጮኩኝ እውነት ለመናገር የሞትኩኝ ያህል ነበር የተሰማኝ

ልዑሌ ከመቼው ከአልጋ ወርዶ አጠገቤ እንደደረሰ ሳላውቅ ሰላም ደና ነሽ ደና ነሽ እያለ አፋፍሶ አነሳኝ ።
እኔ ግን ህመም ይሄ ነው የምለው ስላልነበር መጮሄን አላቆም አልኩኝ የወለድኩኝ ሰአት እንኳን በዛ ልክ አልሆንኩም መሲም ደንግጣ ተነሳች ።

ልዑሌ በፍጥነት ወደ መኪናው ወሰደኝና ባባን አደራ መሲ በምታምኚው አምላክ ብሏት ክትትል ወደ ማደርግበት ሆስፒታል ወሰደኝ እንዴት እንደነዳው አላውቅም ቅርብም ስለሆንን ጭምር መሰለኝ ቶሎ ደረስን።

ውስጥ ገብቼ ካዩኝ ቡሀላ ፅንሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል በሀይል ነው የወደቅሽው አለችኝ ዶክተሯ ።

ስንት አይነት መርፌ ከተወጋሁ ቡሀላ ትንሽ ህመሙ በረድ አለልኝ ።

ልዑሌ በጣም ደንግጦ  ስለነበር ዶክተሯ እንዲረጋጋ  አስሬ እየነገረችው ነበር ።

እዛው አድረን ጠዋት ላይ እናቴና እህቴ ሳይነጋባቸው ሆስፒታል መጡ ።
እናቴ በጣም ደንግጣ ነበር ።
ድንጋጤዋ ፊቷ ላይ ይታያል ።

ዶክተሯ ቢያንስ ዛሬና ነገን እዚህ ሆና በደንብ ልንከታተላት ይገባል ለፅንሱ ብቻ ሳይሆን ለሷም ህይወት ያሰጋናል አለች ።

ልዑሌ ወደ ቤት ተመልሶ ሄደና መሲና ባባን ይዟቸው መጣ ።

እዛው ውለው ማታ እናቴ እህቴና መሲ ባባን ይዘው ተመልሰው ሄዱ ።

ልጄ ካጠገቤ ሲርቅ የምሞት የምሞት መሰለኝ ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ።(ልክ ወላጅ ስትሆኑ የሚገባችሁ ትልቁ ነገር መኖር ምን ያህል ውድ እንደሆነ ነው )

የዛን ቀን እዛ ካደርኩ ቡሀላ ዛሬም ሳይነጋባቸው ተመልሰው መጡ ልዑሌ እዛው አብሮኝ እያደረ እየዋለ አንድ ቃል ካፉ አልወጣም እኔም አንድም ቃል አልተናገርኩትም ወደኔ ሲመጣ ፊቴን አዞራለሁ ።

የዛን ቀን መዋል እንዳለብኝ ዶክተሯ ብትነግረኝም እኔ ግን ሙሉ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ ወደ ቤት ካልሄድኩኝ አልኩ።
የማጠባው ህፃን ስላለም የፅንስ ማጠናከሪያ መርፌ ተወጋሁኝ::

እኔና ልዑሌን ቢሮ ጠራችንና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳላደርግ እቃ ሚባል እንዳለነሳ ከዛ በተረፈ ግን በጣም እያዘነች ፅንሱ ላይ ብዙም ተስፋ አታድርጉ እናንተ ገና ወጣቶች ናችሁ ከዚህ ቡሀላ ስንትና ስንት ልጅ ትወልዳላችሁ ከኛ ይልቅ ደሞ ፈጣሪን ለምኑት አለችን ።

እኔ የዛኔ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ልዑሌ ምድሩ የተደበላለቀበት መሰለው ዶክተር በድጋሜ እንዲህ አይነት ቃል ካፍሽ እንዳይወጣ አላት ።

ጥሩ ተገቢውን ጥንቃቄ በሙሉ አድርጉ አሁን መሄድ ትችላላችሁ አለችን ።

ወጣንና እናቴ ደግፋኝ ወደ መኪናው ገባን የዛኔ ባባን አቀፍኩት ጠረኑ ሁላ ናፍቆኝ ነበር ልዑሌ ገና መኪናውን መንዳት ሲጀምር ወደናቴ ቤት ነው ምንሄደው አልኩት ።

ሁሉም ደነገጡ እንዴ ልጄ ለምን አለችኝ  በቃ እማዬ መሄድ ፈለኩኛ  ምነው ሸክም እሆንብሻለሁ እንዴ አልኳት ።

አረ ልጄ በፈጠረሽ እንዴት ነው ሸክም ምትሆኝብኝ እኔ ለምን ብዬ ጠየኩሽ እንጂ ያው እኔጋ ሽንት ቤቱም ምኑም አይመችሽም ብዬኮ ነው ልጄ መሄድ ከፈለግሽ ግን እሺ አለችኝ ።

የዛኔ ልዑሌ ቀበል አለና አንዳንዴ እንደ ልጅ ያደርጋታል እዛ አኔድም ወደቤታችን ነው ምንሄደው  አለ።
እኔ እማዬ ትሙት ወደናቴ ቤት ነው ምሄደው በቃ ማድረስ ካልፈለክ አውርደን taxi እንይዛለን አልኩት .......

ይቀጥላል
Maneget
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

31 Oct, 17:54


የፍቅር ማእበል

      
           ክፍል 42

እንዲሁ ሳስብ አንዱን ሀሳብ ስጥል አንዱን ሳነሳ ሌሊቱ ሊነጋ ሲል እንቅልፍ ወሰደኝ ።

ጠዋት ልዑሌ ቀድሞኝ ተነስቶ ከመሲጋ ባባን አጣጥበው ልብስ ቀያይረውለት እኔንም ለቁርስ ቀሰቀሱኝ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እንዲሁ ምግቡጋ ቀረብኩ እንጂ ።

ልዑሌ ስራ አልገባም ዛሬ ግን በጣም ትልቅ ቀጠሮ አለኝ ላመሽም ቶሎ ልመለስም እችላለሁ አለኝ ::

እንዴት የት ነው ቀጠሮህ ቆይ አምሽተህ ማታቀው ሰውዬ ምታመሸው አልኩት ።

ትልቅ ጉዳይ አለብኝ ሰላሜ በቃ ቻው አለኝና ሁላችንንም ተሰናብቶን   ወጣ ።

ሁኔታው ትንሽ ግራ አጋብቶኛል ግን ነዝናዛ የት ገባህ የት ወጣህ አይነት ሴትን መሆን አልፈልግም ለዛ ብዬ ዝም አልኩት
ቀኑን ሙሉ ውስጤን ሰላም እየተሰማኝ ስላልነበር ተኝቼ ዋልኩኝ ልዑሌ አድርጎት ማያቀውን ቀኑን ሙሉ ሳይደውልልኝ ዋለ ።

ሰአቱ ቀስ እያለ ቀስ እያለ መሸ እንዳልደውልለት ስብሰባ ነኝ ቀጠሮ አለኝ ስላለ እንዳልረብሸው ፈራሁ ማታ 3 ሰአት አካባቢ ሲል ግን የመጨረሻ ስላላስቻለኝ ደወልኩለት ስልኩ ዝግ ነው ደጋግሜ ደወለኩ text ላኩኝ ግን ምንም መልስ የለም ።

ጨነቀኝ ማንጋ ልደውል ማንን አይታችኋል ወይ ልበል ሰአቱ ያለከልካይ ይሮጣል ።

ለ5 ምናምን ጉዳይ ሲል መጣ ።
ሳየው ይበልጥ ንዴቴ ጨመረ ምን ሆነህ ነው በሰላም ነው ቢያንስ ስልክህን ከፍተህ ማደር ከፈለክ ማምሸትስ ከሆነ አትናገርም እንዴ ቆይ ሰው ያስባል አትልም እንዴ ምንድነው ተምረህ እንዳልተማረ ምቶነው ግን ጭንቅላትህን ለማሰብም ተጠቀምበት እንጂ አልኩት ።

የዛኔ እሱም ብስጭት ብሎ ስላልደወልኩልሽ ይቅርታ ግን ጠዋት ላመሽ እንደምችል ነግሬሽ ነበር አደል እንዴ የሰውን ችግር ሳትረጂ ዝም ብለሽ ለመናገር ትቸኩያለሽ ብሎ አልፎኝ ገባ ።

በጣም ብበሳጭም ቻል ለማድረግ ሞክሬ እኔም ዝም ብዬው ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ትንሽ ቆይቶ መጣና ከአልጋው ስር በርከክ ብሎ ሰላም አለኝ የለበስኩትን ብርድ ልብስ እየገለጠኝ አትንካኝ በቃ መተኛት ነው ምፈልገው ብዬ መልሼ ተሸፈንኩ እልህ ይሁን ምን ይሁን እንባ እየተናነቀኝ ነበር::
በድጋሜ ገለጠኝና ሰላም በፈጣሪ ይቅርታ  በቃ እንዴ ይሄን ያህል ምን አጠፋሁ ስላመሸሁ ይቅርታ በቃ አለኝ እየተቅለሰለሰ ።
ምን ማለት ነው አንድ ስልክ ደውለህ ዛሬ አመሻለሁ ማለት ከብዶህ ነው እኔ እዚህ በጭንቀት ስንቱን ነገር አሰብኩት ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ ስናደድ ወይ እልህ ሲይዘኝ እንባ ነው ሚቀድመኝ ።

አረ ሰላሜ ተረጋጊ በቃ እኔኮ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አደለም ካቅም በላይ ሆኖብኝ ነው እንጂ ቆይ እኔ የት ገባህ የት ወጣህ ዛሬ የት አመሸህ በሰላም ነወይ ወይስ ችግር ገጥሞህ ነወይ መባሉን ጠልቼው አደለምኮ እንደውም ይሄ ለኔ ብርቄ ነው ቢያንስ ሰው አለኝ የሚጨነቅልኝ እንድል ያደርገኛል ሰላም በፈጠረሽ በቃ ይቅርታ ሁለተኛ አይደገምም አለኝና ሳመኝ የዛኔ አላስቻለኝም እኔም እቅፍ አድርጌ ስሜው ተቃቅፈን ተኛን .......

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

30 Oct, 07:18


በአንድ ቀን ውስጥ 1 ሚሊየን ተከታዎችን ማፍራት የቻለው አዲሱ ኤርድሮፕ PAWS በብዙዎች ተጠባቂ አድርጎታል !

ዶግስ በትዊተር ገፃቸው repost አርገውታል !

ካለፈ በኃላ ከምትቆጩ አሁኑኑ ጀምሩ👇👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=UVQFW6ss

የሀገሬ ወጎች

29 Oct, 16:38


የሀገሬ ወጎች pinned «የፍቅር ማእበል            ክፍል 41 እሺ በቃ ልክ ነህ አሁን ና ወደክፍላችን እንግባ ባባ ብቻውን ነው የተኛው ብዬ ይዤው ገባሁ በነጋታውም ወደቢሮ ሳይገባ ቤት ዋለ ከራሱጋ አልነበረም ማለት ይቻላል ከደስታው በላይ ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው ። ብቻ ልዑሌ እርግዝናዬን ከነገርኩት ቀን ጀምሮ ቶሎ ሆድ ሚብሰው ነገር አለ ። የትኛውም ነገር ላይ ስለ ልጅ ስናወራ እንባ ይቀድመዋል…»

የሀገሬ ወጎች

29 Oct, 16:38


የፍቅር ማእበል


           ክፍል 41

እሺ በቃ ልክ ነህ አሁን ና ወደክፍላችን እንግባ ባባ ብቻውን ነው የተኛው ብዬ ይዤው ገባሁ በነጋታውም ወደቢሮ ሳይገባ ቤት ዋለ ከራሱጋ አልነበረም ማለት ይቻላል ከደስታው በላይ ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው ።

ብቻ ልዑሌ እርግዝናዬን ከነገርኩት ቀን ጀምሮ ቶሎ ሆድ ሚብሰው ነገር አለ ።
የትኛውም ነገር ላይ ስለ ልጅ ስናወራ እንባ ይቀድመዋል አንዳንዴ በእጁ የያዘውን እቃ እንደ አዲስ ይፈልጋል::

ይኼኛው እርግዝናዬ እንደመጀመሪያው አደለም  በጣም ከባድ ነው የበላሁት ነገር ሆዴ ውስጥ አይቀመጥም እንደዛ ምወደው ቡና ገና ሲሸተኝ ያቅለሸልሸኛል በፍቅር እወዳቸው የነበሩትን ምግቦች አንዳቸውንም አልጠቀምም  ::
በቃ ሰውነቴ በየቀኑ ቅይይር ይላል ::

እናቴጋ ከሄድን ስለቆየን እሁድ ቀን  እናቴም ጠፋችሁ እያለችኝ ስለነበር ሄድን እንደተለመደው እዛ ስንጫወት ቤቱን ስናደምቀው ዋልን  በየመሀሉ እያመመኝ ወደውጪ እየወጣሁ ነበር ማታ አካባቢ ወደቤታችን ለመሄድ ተነሳን እናቴ በሩን አስወጥታን ተመልሳ ገባች።
መሲ ባባን አቅፋ እኔና ልዑሌ ደሞ እጅ ለእጅ ተያይዘን እያወራን እየተሳሳቅን መኪናውጋ ደረስን ልዑሌ እኔንም መሲንም በሩን ከፍቶ  ካስገባን ቡሀላ እኔ ስልኬን እረስቼው ስለወጣሁ ተመልሶ ሄደ ::

መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን ከመሲጋ ስለሰፈራችን እየነገርኳት ማክቤል በፍጥነት እየተራመደ ከፊት ለፊታችን ትንሽ እራቅ ብሎ አስፋልት ሲሻገር አየሁት አስፋልቱን ተሻግሮ ቆሞ ሚጠብቀው መኪና ነበር አይኔን ማመን አስኪያቅተኝ ድረስ እሱ አልመስልሽ አለኝ።

ማክቤል በህይወቱ የጨርቅ ሱሪ  እና ሱፍ ሚባል ነገር አይወድም ነበር ።
ዛሬ ግን አለባበሱ ቢሮ የሚውል በጣም ትልቅ ድርጅት አስተዳዳሪ ነገር ነው ሚመስለው ፂሙን ፀጉሩን ተስተካክሎ አማላይ ሆኗል አረማመዱ ሁላ ልክ ቢዚ እንደሆነ የስራ ሰው ነበር ሳየው ወሬዬን አቋርጬ አፈን ከፍቼ እያስተዋልኩት ወደመኪናው ውስጥ ገብቶ በፍጥነት መኪናው ከዛ አካባቢ ተሰወረ ።

እውነት ለመናገር ገረመኝ እንዲ በዚህ ፍጥነት መቀየሩ ጥያቄ ሆነብኝ ።
ልዑሌ አትዝረክረኪ እሺ እቃሽን የትም እያጋደምሽ እኔን አታልፊኝ ብሎ እየሳቀ ስልኬን ሰጠኝ ተቀበልኩትና ወዲያው ለማክቤል አምሮብሀል እንዲህ ተለውጠህ በማዬቴ ደስ ብሎኛል ኩል ሆነሀል አልኩት ።
ምንም አልመለሰልኝም ከልዑሌጋ እያወራን እየሄድን አስሬ ስልኬን አያለሁ መልስ የለም ።

ወደቤታችን ከደረስን ቡሀላ ልብሳችንን ቀያይረን ባባም ቀን ሙሉ አንዴ እናቴ አንዴ እህት ሲቀባበሉት ደክሞት ስለነበር እንቅልፍ ተኝቶልን ስለነበር እኛም አረፍ አልን::

ማታ 2 ሰአት አካባቢ text ገባልኝ ማክቤል ነበረ አመሰግናለሁ🙏 ብቻ ነበር ያለኝ ።
እውነት ለመናገር ልጁን ካሳየሁት ቡሀላ ከበፊቱ የበለጠ እኔን ማስቸገር ልጄን ልየው እያለ መጨቅጨቅ እንጂ እንዲህ ድራሽ አባቱ መጥፋት ነበረበት እንዴ ቆይ ምን አስቦ ነው  ከረሴጋ እያወራሁ እንቅልፍ ጣለኝ ::

ሌሊት ላይ ባባ ተነስቶ እያለቀሰ ነበር አባብዬ አስተኛሁት እኔ ግን ተመልሶ መተኛት ከበደኝ ።

ይቀጥላል....
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

25 Oct, 14:49


የፍቅር ማእበል

         ክፍል 40

ቀስ ብሎ አየውና እኔን ቀና ብሎ አየኝ  ምንድነው ምንድነው ይሄ አለኝ አይኑ እንባ እያቀረረ እርጉዝ ነኝ የልጅ አባት ልትሆን ነው አልኩት::
እናቴ እንዴት እንደተነሳች ባላውቅም ብድግ አለችና የያዘውን ተቀበለችው ።
ልዑሌ እኔን እያየ አላምንሽም ሰላም አውቀሽ ፕራንክ አደረኩህ ልትይኝ ነው አደለ ሰላም ማይልኝ እውነትሽን ነው አለኝ??

አዎ እማዬ ትሙት የምሬን ነው እርጉዝ ነኝ አልኩት የዛኔ በቁሙ መሬት ላይ  ውድቅ ብሎ ተንበረከከ እናቴ እልልታውን አቀለጠችው ።

ሄጄ ልዑሌን አቀፍኩትና ደስ አለህ አልኩት በእጁ ፊቱ ላይ ያለውን እንባ እየጠረገ ሰላም በህልሜ እየመሰለኝ ነው ደግመሽ ማይልኝ አለ።
ማልኩለት የዛኔ እንደለቅሶ ቤት ድምፅ እያወጣ መሬት ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ ከጠበኩት በላይ ሆነብኝ ልዑል በፈጣሪ ተረጋጋ እንጂ እንዴ አልኩት ።

እናቴም ልጄ ተው ደስታ ላይ እንዲህ አይኮንም ጥሩ አደለም ደስታውን በልኩ አድርገው አለችው።

የሱ እንባ ወይ ፍንክች አለ ዝም ብሎ ይፈሳል ።
አንስቶ አሽከረከረኝ ሰላም እውነት እኔም እንደሰው አባት ልሆን ነው እእእ ሰላም እውነት ፈጣሪ እያየኝ ኖሯል አረሳኝም አለ።

የዛኔ እናቴ ግራ ተጋብታ እንደዚህ ስትሆኑ ለሚያያችሁ ሰውኮ የመጀመሪያ ልጃችሁን ገና ልትወልዱ ነው ሚመስለው አለች ።

የዛኔ እኔ ደነገጥኩኝና ልዑሌን አየት አደረኩት ።
ያው እናቴ እሱ ወንድ ነው ቀጣዩ ደሞ ሴት ልትሆን ትችላለች ብሎኮ ነው እንዲህ ደስ ያለው ለሴት ልጅ ያለው ፍቅርኮ ይለያል አልኳት በሉ ተረጋጉና ቁጭ በሉ ልጆቼ ይህን ክብር ይሄን ደስታ ያሳየን አምላካችን ክብሩ አይጓደልበት።

እኔንም ከአንድም ሁለት የል ልጅ እንዳይ የፈቀደልኝ አምላክ ይመስገን የኔ ልጅ አሁንም እንዲሁ ከነፍቅራችሁ ጤናን ሰጥቶ በሰላም ያኑራችሁና ቤታችሁ በልጅ እንዲሞላ ያድርጋችሁ ።
በሉ እኛን ሸኙንና እናንተ ደሞ ደስታችሁን ከዚህ በበለጠ አክብሩ።
የኔ ልጅ እንዲህ በየጊዜው ደስታን እንዳይ እንድሰማ ስላደረግሽኝ አመሰግናለሁ
ፈጣሪ ያላሰብሽውን ፍቅር በረከት መትረፍረፍ ይስጥሽ ላንተም እንደዛው የኔ ልጅ በቃ ተረጋጋ አለችው ተነስታ በነጠላዋ እንባውን እየጠረገችለት::

በቃ ልዑሌ ተነስ እነማዬን እንሸኛቸው መሽቶባቸዋል አንተ እንደሆንክ በዚህ ሁኔታ መኪና መንዳት አትችልም አልኩት ሰውነቱን እራሱ በስርአት ችሎ መቆም አይችልም ነበር::

እነማዬን ሸኝተናቸው ወደ ቤት ተመለስን መሲ እንደታቀፈችው ባባ ተኝቶ ጠበቀን ተቀበልኳትና ቀስ ብዬ አስገብቼ አስተኛሁት ።

ከዛ ልዑሌን እንዲረጋጋ ወደ ማድረጉ ገባሁ እቅፍ አደረኩትና በቃ ተረጋጋ አባት ሆነሀል አባት ደግሞ ቆፍጣና ነው መሆን ያለበት አልኩት።

ሰላም እኔኮ ከዛ ሁላ ነገር ቡሀላ እንደዚህ አይነት ደስታ አለም እንዳለ አላውቅም ነበር አንድም ቀን አባት ስለመሆን ልጅ ስለመውለድ አስቤ አላቅም ::

ሰላም ይሄኮ ለኔ ምን ማለት እንደሆነ ስላልገባሽ ስሜቴን ሚገልፅልኝ ምንም ቃል ስላጣሁ ምንም ልልሽ አልችልም ግን ሰላም አስቢው እስቲ አባት ልሆን ነውኮ አባት አለኝ ፊቴን በሁለት እጆች ጥብቅ አድርጎ ይዞ እያፈጠጠብኝ

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

24 Oct, 17:09


@Yonny_Athan
@Yonny_Athan
@Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

24 Oct, 16:42


የፍቅር ማእበል


         ክፍል 39


ቤት ከደረስን ቡሀላ ቆንጆ እራት ከመሲጋ አዘገጃጅተን ልዑሌን ቤቱን ፏፏ አድርገን ጠበቅነው::
ቤት ሲገባ ልዑሌ እንደለመደው በደስታ ተሞልቶ ነበር የገባው ።

እራታችንን በላልተን ወደመኝታችን ሄድን ዛሬ እኔ ድክምክም ብሎኝ ስለነበር ባባን የማስተኛት ተራው የልዑሌ ነበር ።
እኔ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው አይኔን ጨፍኜ ተሸፈንኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ጭንቅላቴ ስለማክቤል ከማሰብ ማቆም አልቻለም ነገረ ስራው ሁሉ አሳዘነኝ ።
ቀን ፊቱ ላይ ያነበብኩት የመጎዳት የእውነት ልቡ እንዴት እንደተሰበረ ፊቱ ላይ ይታያል ድርጊቱ ከፊት ከፊቴ እየቀደመ አላስተኛ አለኝ ።

በፍቅር አለም የሆነን ሰው ማፍቀር መውደድ ያለ ነው መፈቀርም እንደዛው ግን በሁለት ሰው መሀል መሆን በጣም ከባድ ነው ካንዱጋ ሆኖ ስለሌኛው ማሰብ ህመም ነው አንድ ልብ ኖሮን ለሁለት ሰው እንደመስጠት ማለት ነው በጣም ያስጠላል ስሜቱ ከማክቤልጋ ስሆን ልዑሌ ያሳዝነኛል ይናፍቀኛል ከልዑልጋ ስሆን ደሞ ማክቤል ያሳዝነኛል🥺

ብቻ ማክቤል ከዛ ቀን ጀምሮ ሳይደውል text ሳይልክ ቆዬ አንዳንዴ ለመደወል ስልኬን አነሳና እራሴ ተወኝ ብዬ ለምኜው እንዴት እደውላለሁ ብዬ እተወዋለሁ ።

በ15 ቀን አንዴ እናቴጋ እንሄዳለን አሁንም መሲንም ጨምሮ ሰብሰብ ብለን ሄደን እሷጋ ዋልን እንደለመድኩት ሰፈር ላይ ማክቤልን አየዋለሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ላየው አልቻልኩም።

እህቴን ቀስ ብዬ ጠራዃትና ማክቤልን አይተሽው ታውቂያለሽ እንዴ አልኳት??

በፊት በፊት ሁሌ ከኛ በር ፊት ለፊት ይቀመጥ ነበር ሰሞኑን ግን አይቼው አላውቅም አለችኝ ።

በውስጤ በሰላም እንዲሆን እየፀለይኩ ሲመሽ ወደቤታችን ተመለስን ማታ ላይ ሁሉም ሲተኙ ስልኬን አንስቼ text ላኩለት 

ሰላም ነህ ይቅርታ ከረበሽኩህ ድምፅህ ሲጠፋ እንዴት እንደሆንክ ልጠይቅህ ብዬ ነው አልኩት ።

ደና ነኝ ብቻ አለኝ
ከዛ እኔም ዝም አልኩት በቃ ከዛ ቡሀላ ለ1 ወር ከምናምን ምንም አይነት text ተላልከን አናውቅም በስልክም አናወራም ዝም አለኝ ዝም አልኩት።

ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ነገሮች እየተቀየሩብኝ ሲመጡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ እንደገመትኩት እርጉዝ ነበርኩ ።

የመጀመሪያው እርግዝናዬ ላይ እንዳረገዝኩ ስሰማ ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ስፀልይ ነበር።

ባሁኑ ግን የደስታ ጥግ ላይ ነበርኩ ከሀኪም ቤት እንደተመለስኩ ለናቴ ደወልኩላት እና በጊዜ ወጥታ እኔጋ እህቴንም ይዛት እንድትመጣ ነገርኳት  እሺ አለችኝ።

እኔና መሲ ቤቱን በአል አስመሰልነው መሲ አስሬ ምን አለ ዛሬ ምን ዛሬ ትለኛለች ማታ ለሁሉም የተዘጋጀ ሰርፕራይዝ እንዳለ ነገርኳት ።

ልዑሌንም ደውዬ ስንት ሰአት እንደሚመጣ ስላረጋገጥኩ ሰርፕራይዙ እንዳሰብኩት ሄደልኝ ።

ማታ ሁላችንም ቤት ተሰባሰብን ሁሉም አስሬ ምንድነው ዛሬ ምንድነው ይሉኛል ምን የረሳነው በአል አለ አንዴ ይጠያየቃሉ እናቴና ልዑሌ  እኔ ከእራት ቡሀላ ነው ምነግራችሁ በቃ ተረጋጉ ብያቸው እራታችንን በላን ።

ሁሉም ልባቸው ተሰቅሎ እንዴት እንደበሉ ብታዩት እያሳቁኝ ነበር ከእራት ቡሀላ ቡናችንን እየጠጣን አሁን ሁላችሁም ተረጋጉና ሰርፕራይዙን ለማየት ተዘጋጁ አልኳቸው መጀመሪያ ግን ባባን ይዞት የነበረው ልዑል ስለነበር ለእህቴ ስጣት እሷ ትያዘው አልኩት ድንገት ስሜታዊ ሆኖ ቢጮህ እንኳን ባባ እንዳይደነግጥ ብዬ ነው እንደዛ ያልኩት ::
የዛኔ የምር ግራ እየተጋባ ባባን ሰጣት እኔ ተነስቼ ወደመኝታ ክፍላችን ገባሁና ቼክ ያደረኩበትን የእርግዝና ማስረጃዬን ይዤ መጣሁና  መጀመሪያ ለልዑሌ ሰጠሁት


ይቀጥላል ......
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

23 Oct, 09:01


የፍቅር ማእበል

  

       ክፍል 38

ልዑሌ ለምሳ እቤት መጥቶ ልክ እንደወጣ ማክቤልጋ ደወልኩለት ልመጣ ነው።
አልኩት እሺ ቤት እየጠበኩሽ ነው የት ነው ምንገናኘው አለኝ ።
ከሰፈር ትንሽ እራቅ ይበል ሰው የማያየን ቦታ አልኩት እሺ ለምን ቦታችንጋ አንገናኝም አለኝ። የዛኔ በጣም ተናደድኩ ህፃን ልጅ ጫካ ለጫካ ልዙር ለምንድነው ድንጋይ ምቶነው አልኩት።
ይቅርታ እሺ በቃ መቼስ መጠጥ ቤት አልቀጥርሽ ግራ ገብቶኝኮ ነው አለኝ ።
በቃ እናቴ ቤት እንገናኝ ስደርስ እደውልልሀለሁ አልኩና ልጄን አጣጥቤ ቆንጆ ልብስ አለበስኩት እኔም ልብሴን ቀያይሬ ፏ ብዬ ወደናቴ ቤት ሄድኩኝ እናቴ ቤት ስደርስ እህቴ ከትምህርት ቤት ተመልሳለች እናቴ የለችም ስራ ናት ።
ለእህቴ ይሄንን ነገር ለማንም እንዳትናገር ግን ማክቤልን ቤት ልጠራው እንደሆነ አስጠንቅቄ ነገርኳት እሺ አለችኝ።

ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ቶሎ ና እቸኩላለሁ ልዑሌ ቤት መጥቶ ካጣኝ ይናደድብኛል አልኩት እሺ አለኝ ::
ከ 10 ደቂቃ ቡሀላ ቤት መጣ ለእህቴ ባባን አቅፋው ወደ ክፍሏ እንድትገባ ነገርኳት እሱ ቤት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ልክ እንደገባ ብቻሽን የመጣሽው ልጄስ አለኝ??

በምልክት ድምፁን እንዲቀንስ ነገርኩትና ቁጭ በል በመጀመሪያ ትልቅ ላወራህ ምፈልገው ነገር አለኝ በሱ ከተስማማን ብቻ ነው ዛብሎንን ማየት ምትችለው አልኩት ።
ዛብሎን ነው ስሙ አለኝ ፈገግ እያለ
አዎ
በመጀመሪያ ደረጃ  በዚህ እድሜህ ይሄ በየመጠጥ ቤቱ ምታመሸው ምትሰክረውን ነገር ታቆማለህ : ማፈር አለብህ ጠጥተህ ለምትሸናው ነገር አባትህ ደም ተፍቶ ያመጣውን ገንዘብ ስታጠፋ።

በመቀጠል ይሄ ጎዳና ተዳዳሪ ያስመሰለህን ፂምህንና ፀጉርህን ተቆረጥና የአባትህን ፈገግታ መልስልት በየሰፈሩ ሰው ፊት አታስንቀው ተከብረህ አስከብረው እንጂ ።

ሶስተኛው ደሞ ወጥረህ ስራ ጓደኞችህን ምረጥ ሁሌ እንጠጣ ሚሉህን ተውና ሰርተን እንቀየር የሚሉህን ያዝ  በዚህ እድሜህ ያባትል ጡረተኛ መሆን የለብህም ግርሰሪውንም ቢሆን አንተ ሸፍንላቸው እሳቸውን አሳርፋቸው ።

የመጨረሻው ንግግሬ ደሞ እራስህን ቀይረህ ለውጠህ በተግባር አሳየኝ እንጂ በመሸ ቁጥር እየጠጣህ እየደወልክ አትለፋደድብኝ ትዳር አለኝ የባለቤቴንም የኔንም ክብር መጠበቅ አለብኝ።
ልጄን ዛሬ አሳይሀለሁ ከዛ ቡሀላ ግን አሳይኝ አገናኝኝ ማለት አይቻልም እኔ ስፈልግና ሲመቸኝ ሁኔታህን አይቼ ነው ድጋሜ እሱን ማየት ምትችለው ከዛ ውጭ እንደዚህ ሆነህ ሁለተኛ ልጅ አለኝ ብለህ እራሱ እንዳታስብ ምክንያቱም እራሱን መጠበቅ ማይችል ሰው  ሌላው ሰው መጠበቅ አይችልም ጨርሻለሁ አልኩት ።

በጥሞና ሲያዳምጠኝ ከቆየ ቡሀላ እንዴት እንደምቀየር አሳይሻለሁ እኔ ማክቤል ነኝ ለቃሌ እንዴት ሟች እንደሆንኩ ታቂያለሽ አለኝ።

ጥሩ መጣሁ ብዬው ወደ እህቴጋ ሄድኩ ባባን ተቀበልኳትና እሷ እዚሁ ሆና እንድትጠብቀኝ ነገርኳት ።

ማክቤል ልክ ባባን እንዳየው እጁ ተንቀጠቀጠ ካይኑ እንደሴት ልጅ እንባ ፈሰሰ አሳዘነኝ ።
መጀመሪያ ለመረጋጋት ሞክር ከዛ ቀስ ብለህ ታቅፈዋለህ አልኩት ።

እሺ አለኝ ጭንቅላቱን እያወዛወዘ ካይኑ ሚፈሰውን እንባ ጠረገና እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረ እጁን ዘረጋልኝ ባባን ሰጠሁት አቀፈው አየው ምን አይነት እድል ኖሮኝ ነው ግን በራሴ ስተት አብረኸኝ እንዳታድግ ያደረኩት አለ ቀና ብሎ አየኝና ሰላም እውነት ይሄ የኔ ልጅ ነው እውነት እኔ አባት ሆኜ ነው እእ ሰላም አስበሽዋል አባቴምኮ የልጅ ልጅ አየ ማለት ነው ቆይ ከዚህ በላይ ደስታ ምን አለ አለኝ እያለቀሰ አንዴ ባባን አንዴ እኔን እያየ እኔ ዝም ብዬ ቆምኩ ።

ልሳመው እንዴ እእ ችግር የለውም አለኝ??
አዎ ትችላለህ ሳመው አልኩት ።

ልክ ሲስመው ባባ እሪ ብሎ አለቀሰ የማክቤል ፂም በጣም ስላጎፈረ ኮስኩሶት መሰለኝ ደነገጠና ሰላም ያዥው አለቀሰ አለኝ እሺ ብዬ ተቀበልኩትና አባባልኩት።

ይበቃል የቀረውን ደግሞ የምር ተቀይረህ አሳየኝ በኔ በኩል ጨርሻለሁ አልኩት።

እሺ ለመጨረሻ ጊዜ አንዴ ብቻ ልቀፈውና እወጣለሁ አለኝ ።
ሰጠሁት አቀፈው አየው መልሶ ሰጠኝና በሹራቡ እንባውን እየጠረገ ከቤት ወጣ እኔም እህቴን ቻው ብያት ለናቴ እንደመጣሁ እንዳትናገር አስጠንቂቂያት ወደቤቴ ከልጄጋ ተመልስኩ ።
 


@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

22 Oct, 13:01


Hilina desalegn🥰

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

20 Oct, 20:29


የፍቅር ማእበል

       
       ክፍል37

አሁን ግን በቃ እኔጃ ብቻ ላንቺ ቃል የለኝም ብሎ አቅፎ ሳመኝ ትንሽ ከቆየን ቡሀላ ወደውስጥ ገብተን አረፍ አልን ።
ያው ባባ ቀን ቀን ስለሚተኛ ሌሊት በጣም ያስቸግራል አንዴ እኔ አንዴ ልዑሌ እየሆንን እንይዘዋለን ።
ዛሬ ግን ልዑሌ እንቅልፍ ስለወሰደው ብቻዬን ባባን አቅፌ ማጫወት ጀመርኩ እንደለመደው ሌሊት አካባቢ ላይ ማክቤል ደወለ ዝም ብዬ አንስቼ ስልኩን ጆሮዬ ላይ አደረኩት እልም ያለ ጫጫታ ውስጥ ነበር።
ዝም ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ ።
አፉ ሁላ ተሳስሮ ነበር ።
ህይወቴን በሰላም እንድኖርና የድሮውን ማክቤልን ማግኘት ከፈለግሽ ላንዴ ብቻ ልጄን አሳይኝ ምን እንደሚመስል አንዴ ብቻ ነው ማየት ምፈልገው ከዛ ቡሀላ አጠገብሽ አልደርስም አለኝ ።
አላስቸግርሽም ካንቺ እርቄ አባቴንና እራሴን የሚጠቅም ስራ እሰራለሁ መጀመሪያ ግን አይኑን አሳይኝ አለ ።

ዝም ብዬ ስልኩን ዘጋሁትና text ፃፍኩለት አሁን ወደቤትህ ግባና ሲነጋ እናወራለን አልኩት ።

ጠዋት እኔ በተራዬ እንቅልፍ ጥሎኝ ባባን እያጫወተው የነበረው ልዑሌ ነበር ስነቃ ቁርስ ቀርቦ እኔን እየጠበቁ ስለነበር ተነስቼ ተጣጠብኩኝና አብረን ቁርስ በላን።

ልዑሌ ወደስራ ሄደ እኔ ቁጭጭ ብዬ tv እያየሁ ማክቤል ደወለ ማታ ያወራነውን ምን አሰብሽ ቃል እገባልሻለሁ ላንዴ ብቻ ነው አይኑን ማየት ምፈልገው ከዛ ድጋሜ አላስቸግርሽም ቃሌ ነው አለኝ።

እሺ አልኩት በቃ ዛሬ ከሰአት ቡሀላ እንገናኝ የት ነው የሚመችሽ አለኝ ።
እኔ ሰፈር እመጣለሁ እዛው እንገናኛለን እደውልልሀለሁ አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት እውነት ለመናገር ብዙ ሰአት ከራሴጋ ታግያለሁ ግን ቢያንስ እሱ ሚቀየር ከሆነ ላንዴ የልጁን አይን ባሳየው ችግር የለውም ብዬ አሰብኩ ።

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

19 Oct, 19:59


የፍቅር ማእበል

           ከፍል 36

ትንሽ ከተኛሁ ቡሀላ ተነስቼ ልጄን አጣጥቤ ልብሱን ቀያይሬለት አብሬው ለመተኛት ሞከርኩ ።
ለራሴ ምን ያህል የህፃን ስራ እንደሰራሁ በጣም ሞኝ እንደሆንኩ  እየነገርኩት ነበር።
ለማክቤል ልጁ የሱ እንደሆነ ከነገርኩት ቡሀላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ በራሱ ከበደኝ ቀጥታ sms ሲሆን ወይ መደለት አልችል ግራ ገባኝ

ፈጣሪዬ ሆይ ማታ ሰክሮ ስልኩን ጥሎት በገባ ብዬ ፀለይኩ ከእንቅልፉ ሲነቃ ደውሎ ምን ሊለኝ እንደሚችል ማሰብ በራሱ ከበደኝ ከዛ ሽሽት ስልኬን አጠፋሁ።

ምሳ ሰአት ላይ ልዑሌ መጥቶ ቆንጆ ምሳ በላን ያው እኔ እንኳን ጭንቀቱ ሊያፈነዳኝ ትንሽ ነበር የቀረኝ አንብቦት ይሆን ካነበበው ቡሀላስ ምን ይወስን ይሆን ሄዶ ለናቴ ቢነግራትስ ብቻ  ምን የማላስበው አለ  ስልኬን ልክፈተው አልክፈተው ግራ ገባኝ ልክ እንደከፈትኩት ቢደውልልኝስ አንስቼ ምን አወራለሁ ።

ማታ አካባቢ በቃ የፈለገው ይምጣ ብዬ ከፈትኩት እንደፈራሁት ልክ እንደከፈትኩት ማክቤል ደወለ ።
ከእንቅልፌ ከተነሳሁበት ሰአት ጀምሮ ስደውልልሽ ስልክሽ ዝግ ነው አለኝ ።
አዎ ዝግ ነበር ምነው ለምን ፈለከኝ አልኩት ልክ ምንም  እንዳልተፈጠረ ነገር
  
አሁን ካንቺ በላይ ልጄ ነው ሚያስፈልገኝ ደሞኮ ታውቆኝ ገበር ካስታወሽ ጠይቄሽ ገበር አንች ዋሸሽኝ እንጂ አለ

ማታ በችኮላ የሆነ ነገር እራስህ ላይ እነሰዳታደርግ ስለፈራሁ ነው ያን ሁላ ውሸት የቀባጠርኩት እንጂ የምሬን አደለም ልጁ የልዑል ነው የሌለ ነገር ስላወራሁ ይቅርታ አድርግልኝ ቻው ብዬ ዘጋሁበት።

መልሶ ደወለ
በቃ ውሸቴን ነው አልኩህ አደል እየደወልክ አትጨቅጭቀኝ አልኩት ።
እሱ ግን ምንም ሳያፍር ማታ ያንን text ስልክልሽ  ካንቺ የጠበኩት 1 ነገር ያንተ ልጅ ነው ለልጅህ ስትል ኑርለት እንድትይኝ ነበር ያልኩት አልቀረም  የጠቀኩትን text ላክሽልኝ አንቺ በዛ ፍጥነት ከልዑልጋ  አብረሽ አድረሽ ልታረግዢ አትችይም አቅሻለሁኮ አለኝ ።
የዛኔ በጣሞ ተናደድኩ ታዲያ ምን ይጠበስ ልጁ ያንተ  ቢሆንስ ምን አገባህ በቃ እኔም ልጄም እንደሞትን ቁጠረው ልዑሌ ነው አፍርሶ የሰራን ትናት ምክንያትህን እንኳን ንገረኝ እያልኩ  ስለምንህ ዞረህ እንኳን አላየኸኝምኮ ቢያንስ አባቴ እንዲህ እንዲህ አለኝ ለትንሽ ጊዜ እንለያይ አብረን መፍትሄ እንፈልግ መች አልከኝ  ።
የ6 አመት ፍቅሬን እንደቆሻሻ አውጥተህ ጣልከው መች ለኔ ስሜት ተጨነክ ያንን ሁላ ሴት አጠገቤ እያመጣህ ስትስም ስትለፋደድ አልነበር ዛሬ ደርሶ ምን አፍቃሪ አፍቃሪ ያጫውትሀል ልዑሌ እየመጣ ስለሆነ ስልኬ ላይ ደግመህ እንዳትደውል እንዲደብረው አልፈልግም እኔንም ልጄኝ አትበጥብጠን አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት።
ፈጣሪ  ያክብረው ደግሞ አልደወለም ።
ማታ ልዑሌ መጥቶ እራታችንን በላልተን ባባ ተኝቶ ስለነበር ፊልም ማየት ጀመርን ስንጨርስ በረንዳ ላይ ወጥተን አንድ ጋቢ ለሁለት ለብሰን ጨረቃዋን እያየን ማውራት ጀመርን ።

ልዑሌ ምናለ ከሁለትና ከሶስት አመት በፊት ባወኩሽ ኖሮ አለኝ ።
እንዴ ለምን አልኩት ??
በቃ የዛኔ አውቄሽ ቢሆን ህይወት ላይ ተስፋ አልቆርጥም ነበር አለኝ
እንዴ ቆርጠህ ነበር እንዴ ሆ ሰው እንዴት ህይወት ላይ ተስፋ ይቆርጣል ግን ለምን እንደዛ አልክ አልኩት።

በቃ ታቂያለሽ እኔ ብዙ ታሪክ አለኝ ያልነገርኩሽ ግን አንቺንና ልጄን ከመተዋወቄ በፊት በነበረው ህይወቴ ውስጥ ተስፋ ቆርጬ ነበር ማታ ስተኛ ጠዋት ከእንቅልፌ ስለመነሳት አላስብም ነበር በየትኛውም አጋጣሚ ብሞት አይጨንቀኝም አንድም ቀን ለህይወቴ ሰግቼ አላውቅም ነበር ።

ይቀጥላል
@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

18 Oct, 18:27


የሀገሬ ወጎች pinned «የፍቅር ማእበል         ክፍል 35 አረ እንደዚህ አታስብ አሁንም ድረስ ለኔም ላባትህም ታስፈልገናለህ ብዬ ላኩለት መልስ የለም። ደግሜ አሁኑኑ ደውልልኝ በጣም ፈልጌህ ነው ?? አይመልስም ። የዛኔ የምር የሆነ ነገር የሆነ መስሎኝ ነበር ከመደንገጤ ብዛት ምን እየፃፍኩ እንደነበር እራሱ ማሰቢያ ሰአት አላገኘሁም ። ብቻ ማክቤል ቢያንስ ለልጅህ ስትል መኖር አለብህ ዛብሎን ያንተ ልጅ ነው ካንተ…»

የሀገሬ ወጎች

18 Oct, 18:27


የፍቅር ማእበል

        ክፍል 35

አረ እንደዚህ አታስብ አሁንም ድረስ ለኔም ላባትህም ታስፈልገናለህ ብዬ ላኩለት መልስ የለም።
ደግሜ አሁኑኑ ደውልልኝ በጣም ፈልጌህ ነው ??
አይመልስም ።
የዛኔ የምር የሆነ ነገር የሆነ መስሎኝ ነበር ከመደንገጤ ብዛት ምን እየፃፍኩ እንደነበር እራሱ ማሰቢያ ሰአት አላገኘሁም ።
ብቻ ማክቤል ቢያንስ ለልጅህ ስትል መኖር አለብህ ዛብሎን ያንተ ልጅ ነው ካንተ ስላረገዝኩ ነው ልዑሌ እንደዛ በተፋጠነ ሰርግ ያገባኝ ቢያንስ ለሱ ስትል ኑርለት አልኩት።

መልስ አልሰጠኝም ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር 12 ሰአት ሆነ ።
ዝም ብዬ ተነስቼ ልብሴን ቀየርኩና ከክፍላችን ወጣሁ ።
ለማንም ሳልናገር ስልኬንና የትራንስፖርት ብርብቻ  ይዤ ወጣሁ ።

ቀጥታ ወደነ ማክቤል  ግሮሰሪ ሄድኩኝ ዝግ ነው
ወደቤታቸው አመራሁ ከየት የመጣ ድፍረት እንደሆነ ባላውቅም በሩን በሀይል ደበደብኩት አባቱ መተው ከፈቱልኝ ሲያዩኝ በጣም ደነገጡ የሞት መልአክ እንጂ ሰው ያዩ አይመስሉም ነበር ።

እየተንተባተብኩ ይቅርታ ፋዘር ማ ማ ማክቤልን ፈልጌው ነበር ቤት ነው እንዴ  አልኳቸው ።

አዎ የኔ ልጅ ምነው ይሄን ያህል አስቸኳይ ነው እንዴ ልቀስቅስልሽ ሌሊት ሰክሮ እየተዘላገደ ነው የገባው ነይ ግቢና አንቺ ቀስቅሽው በዛውም ትንሽ መክረሽው ትሄጃለሽ አሉኝ።
የዛኔ ልክ ትልቅ ሸክም ከትከሻዬ ላይ እንደተነሳልኝ ነገር እፎይ አልኩኝ ።

አይ አባባ አመሰግናለሁ ይተውት በቃ ይተኛ ቡሀላ እደውልለታለሁ ብዬ መልሳቸውን እንኳን ሳልጠብቅ ፊቴን አዙሬ በፍጥነት ከዛ አካባቢ ሄድኩኝ ።
ወደቤት እየተመለስኩ ልዑሌ ደወለ ።
ሰላሜ የት ሄደሽ ነው በዚህ በጠዋት አስደነገጥሽኝኮ ??
ይቅርታ ልዑሌ መጥፎ ህልም አይቼ ስለነበር ባባ ሳይነሳ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ልምጣ ብዬኮ ወጥቼ ነው መጣሁ አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት ::

ወደቤት ስደርስ ልዑሌ አይቶኝ በጣም ደነገጠ እንዴ ሰላም አብደሻል እንዴ እንደዚህ ሆነሽ ነው ቤተክርስቲያን ሄድኩ ምትይኝ ወይስ ምንድነው አለኝ ።
አረ ልዑሌ ከእንቅልፌ ስነቃ በጣም ደንግጬ ስለነበር ምን እንደለበስኩ እራሱ አላስተዋልኩትም ነበር  ልክ ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ደርሼ ከተሳለመኩ ቡሀላ ነው የታወቀኝ አልኩት።

አይንሽ እራሱ ቀልቷልኮ አሞሻል እንዴ ??
አይ እየቃዠሁ ስለነበር ለዛ ነው በቃ ትንሽ እንቅልፍ ልተኛ መሲን ባባን አጫውችው በላት ብዬው አልጋው ላይ ተዘረርኩ ።
ልዑሌ ያወራሁት ያደረኩት ምንም አልተዋጠለትም ግን ዝምምም አለኝና ባባን አቅፎ ከክፍል ወጣ ።
ሌሊቱን ያልመጣው እንቅልፌ የማክቤልን ደህና መሆን ከሰማ ቡሀላ  ባንዴ መጣብኝ .....


ይቀጥላል.......

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagete_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

17 Oct, 18:48


https://t.me/Yonny_Athan?livestream=ef390589f25098de51

የሀገሬ ወጎች

17 Oct, 16:56


የፍቅር ማእበል

             ክፍል 34

ቡናችንን ጠጣተን : ምሳችንን በላልተን ቀኑን ሙሉ ጨዋታው እንደደራ አመሸንና ወደ 11 ሰአት አካባቢ ወደቤታችን ለመሄድ ወጣን።

ባባን ልዑሌ ነበር ያቀፈው ወደመኪናችን ልንገባ ስንል ልጁን ለኔ ሰጠኝና በዛው ግንባሬን ሳምምም አደረገኝ ።


ወደመኪናችን ገብተን እየሄድን ድንገት ዞርስል ማክቤል በመብራት ፖል ተደብቆ እያየን ነበር::
አስተያየቱ እንደነፍሰ ገዳይ ነው ።
በጣም ያስፈራ ነበር ባላየ ፊቴን አዞርኩኝ።
ከባባጋ እየተጃጃልኩ ልዑሌ ደሞ ዝም ብሎ እኔን እያየ እየሳቀ መንገዳችንን ቀጠልን በነገራችን ላይ የባባ ስም ማን ይመስላችኋል(ዛብሎን ነው ልዑሌ ነው ስሙን ያወጣለት ከኔጋ ይኖራል ማለት ነው) ለምን እንደዛ እንዳለው ባላውቅም የልጄ ስም ግን ዛብሎን ነው እውነት ለመናገር ደስ የሚልና ለየት  ያለ ስለሆነ እኔም ወድጄዋለሁ።

ቤታችን ከደረስን ቡሀላ ሁላችንም ደክሞን ስለነበር ለመተኛት እየሞከርን ነበር ባባ ግን እንቢ አለኝ አንዴ እኔ አንዴ ልዑሌ እያጫወትነው ቆየን ከሌሊቱ 6ሰአት አካባቢ ስልኬ ተደጋጋሚ ጊዜ እየጠራ ነበር ከማክቤል እንደማይዘል ስለገባኝ ቼክ አላደረኩትም ነበር ።
ልዑሌ አይቶ እንዳላየ ዝም አለኝ ሳይለንት አደረኩት ።
ትኝሽ ቆይቶ ባባ ሲተኛ ልዑሌም አብሮት ተኛ የዛኔ ስልኬን አንስቼ ሳየው እውነትም ማክቤል ነበረ 26 ጊዜ ደውሏል ።
10 text ልኮልኝ ነበር ።
መጀመሪያ እንደለመደው እየተጃጃለ ስለመሰለኝ ያን ያህል ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር  textochun ማንበብ ጀመርኩ ።
ema
Enate
Selam
አፈቅርሻለሁ
ናፍቀሽኛል
.........
...........
..........
የመጨረሻው ላይ ተስፋዬ ይሙት(ተስፋዬ አባቱ ነው)
ከዛሬ ጀምሮ አይኔን አታይኝም ካባቴም ካንቺም ካልሆንኩ ማንአለኝ ብዬ እኖራለሁ እራሴን ነው ማጠፋው የዛኔ አንችም ሰላምሽን ታገኛለሽ አባቴም ልጅ አለኝ ብሎ ተስፋ ማድረጉን ያቆማል ለነገሩ አሁንም ተስፋ ቆርጦብኛል ::

አባቴን ባየሁት ቁጥር እንደዛ ሆኖ አሳድጎኝ ዛሬ ባንቺ ምክንያት እንደዚህ ክብሩን ሳሳጣው ያናድደኛል

አንቺን ሳይሽ ደሞ ምናለ የዛኔ አባቴን እንደምንም ብዬ ባሳመንኩት አንቺን ጨክኜ ብመርጥ ኖሮ አባቴ ደስተኛ መሆኔን ሲያይ ሀሳቡን ይቀይር ነበር እላለሁ።
በመሀል ቤት እኔ ባክኜ ቀረሁ ሰላም አንቺ ከኔጋ እንደተለያየሽ ድጋፍ እንዲሆንሽ እንዲያፅናናሽ ልዑልን ላከልሽ ቆይ ለኔስ እእእ ብቻዬን ወይ አልሞትኩ ወይ አልዳንኩ ።
በየቀኑ እየጠጣሁ  እየሰከርኩ አባቴን ከማሰድብ እሱ ከማሳዝን አንችም ባየሽ ቁጥር ከምትሳቀቂ በቃ ቻውውውው:::

textun እንዳነበብኩ እጄ ተንቀጠቀጠ ወደ መታጠቢያ ቤት ገብቼ ደወልኩለት አያነሳም ደግሜ 2/3 ጊዜ ደወልኩ አያነሳም ።
እንደምንም እራሴን አረጋጋሁን text ፃፍኩለት ።

ይቀጥላል
ማኔ

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

17 Oct, 14:14


https://t.me/yomin1_2

የሀገሬ ወጎች

17 Oct, 06:36


መርሳት ቀላል አይደለም። ግን መረሳቱ አይቀርም። በጊዜ ህደት ሁሉም ነገር ይረሳል : ነበር ይሆናል። ቀስ በቀስ ቁስሉ ይድናል ፡ ህመሙ ይሽራል : ጠባሳውም ይደበዝዛል።

እናም ጠባሳውን ስናይ እንደበፊቱ ህመማችን አያገረሽም : የሆነ አስተምሮን ያለፈ ነገር ብቻ ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ ደሞ አናስተውለውም። እንለምደውና እንደማንኛውም ተራ ነገር ልብ ሳንል እናልፈዋለን።

ልክ ከመጽሐፍ ላይ ተቀዶ እንደተጣለ አንድ ገጽ መጽሐፉ ላይ የቅዳጁ ቦታ ብቻ እንደሚቀረው እና እዛ ቅዳጅ ላይ የተፃፈ ታርክ እንደማይታወቀው።

ከህይወታችን ስንክሳር ላይ ቀደን እንጥለዋለን ከዛ የቅዳጁ ቦታ እንጂ በላዩ የሰፈረው ታሪክ ስለመኖሩ ልብ እንኳን አንልም። የተጣለው ገጽ ቢኖርም ባይኖርም የታሪኩን ፍሰት ስለማይቀይረው ቀደን የምንጥለው ራሱ ምንም ሳይመስለን ነው። የተረሳ ነገር ስሜት አልቦ መሆኑ ስለማይቀር ደንታቢስ እንሆናለን አንጨነቅለትም።

እንግዲህ. . .

እንዲህ ነው መርሳት ታሪክ አልባ የሚያደርገው። በዛ ሰው ህይወት ውስጥ እንደክረምት አግቢዎቹ እንኳን ብቅ ብላቹ እንደማታውቁ ሁሉ። ያ ሰውም ያን ሁሉ ገድል በእናንተ ላይ እንዳልፈፀመ ሁሉ። እንዲሁ እንደዘበት እንዳለፈ ውሃ ይረሳል።

ታዲያ እንዲህ ለትዝታ እንኳ እንዳንተርፍ ሆነን ልንረሳሳ የየዕለት ስንክሳራችን ላይ የበደል ታሪክ ለመጻፍ ሽር ጉድ ማለታችን ይገርመኛል።

የምንከዳዳው : የምንወሻሸው : ልብ የምንሰባበረው ፡ ህመም የምንዋዋሰው : ተካክደን : ተበዳድለን : ተጎዳድተን ፡ ተቆሳስለን ፡ በብላሽ ተገናኝተን ፡ በብላሽ የምንለያየው... ያው በስተመጨረሻ ለመርሳሳት መሆኑ ያሳዝናል። ምክንያቱም ህመምን ለዘላለም በልቡ ይዞ ለማኖር የሚፈልግ የለም።

ከዚህ ሁሉ በኃላ ክፉ ቀናችንን ከልባችን አውጥተን ስለመጣል ብቻ ነው 'ምናልመው።

በዳያችንንም በደላችንንም ለመርሳት እንታገላለን እንጂ መጥፎ ትውስታን በልባችን ይዘን ትዝታው ስመጣብን በህመም ለማሰብ መች እንመርጣለን? ፎቶ የምናቃጥለው : በደግ ቀናችን ላይ የተለዋወጥነውን ስጦታ የምንሰብረው : ስብርባሪዎች እንኳ እንዳይቀሩ አድርገን አርቀን የምንጥለው እኮ ለመርሳት ካለን ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ነው።

ሁልጊዜም ቢሆን ከርሞ የምንወደው ቀን በልባችን ደግ በኩል የኖርነውን መልካም ቀን ነው። ልባችን ላይ እንድኖር የምንፈቅደውም : መኖር የምገባውም ዕለት... ደግና : ንፁህ የነበርንበት ስናስታውሰው ስለመልካምነታቸውም ስለመልካምነታችንም ፈገግ የምንልበትን ያንን ምስጉንና ጻድቅ ዕለት ብቻ ነው ፥ ለትዝታም እንዲሆን ጠብቀን የምናቆየው።

ሰብለ ወንጌል

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

16 Oct, 19:29


https://t.me/Yonny_Athan?livestream=ecb424e5d99c0019f5

የሀገሬ ወጎች

16 Oct, 17:53


የፍቅር ማእበል

         ክፍል 33

ክርስትናችን በቆንጆ ሁኔታ አለፈ ።
ልዑሌ የደስታ ጥግ ላይ ደርሶ ነበር ደስታ እንደሚያሰክር  በሱ ነው ያየሁት።

እኔና መሲ ባባን አጣጥበን አስተኛነው
አንዴ ከተኛ ደግሞ አይነቃም ሌሊቱን ግን ቁጭ ብሎ ነው ሚያድረው ።

ከመሲጋ ቁጭ ብለን እያወራን ልዑሌ መጣ ።
ልጄ ተኝቶ ነው ብሎ ገብቶ አየውና አንዴ ላወራሽ እፈልጋለሁ የኔ መኝታ ቤት ነይ አለኝ ።
መሲን እያየሽው ጨርቅ ነገር እንዳያፍነው ብያት እኔ ወደውስጥ ገባሁ።

ምነው ልዑሌ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ አልኩት።

አይ የለም ግን ሰላም ልጅ እንድትወልጅልኝ እፈልጋለሁ ።
ሳቄ መጣ ይኸው ወለድኩልህ አደል አልኩት ።

ጉንጮቼን በእጁ እየዳበሰ ሰላም አልቀለድኩም ከምሬ ነው ውለጅልኝ ።
ባባን ልጄ አደለም እያልኩሽ አደለም ግን በቃ ውለጅለኝ እሱን ባየሽ ቁጥር እኔን ታስታውሽኛለሽ  አለኝ።
ቆይ ልዑል ምን ሆነሀል አንተ የት ትሄዳለህ አልኩት ።

የትም እኔ ስራ ስሄድ እንዳልናፍቅሽ እሱን ታያለሸ ለማለት ያህል ነው ብሎ ፈገግ አለ

ሁለተኛ እኔ በሌሌለሁ ጊዜ የሚባለውን ነገር ብታነሳ ልዑሌ ሙት ትጣላኛለህ እንዴ ቆይ  ከኔጋ የመቆየት የመኖር ሀሳብ የለህም እንዴ ትተኸኝ ስለመሄድ ታስባለህ   እንዴ ቆይ እኔና አንተ በምን ልንለያይ እንችላለን ሳላስበው እንባዬ ወረደ አቅፎ አባባለኝ   ሳመኝ ሁለታችንም ወደንና ፈቅደን ለመጀመሪያ ጊዜ ከልዑሌጋ አንሶላ ተጋፈፍን ።
ከዛ ቡሀላ ኖርማል ባልና ሚስትነታችንን አወጅን።

ቀኑ እሁድ ነበር እናቴን ለማየት  መሲንም ጨምሮ ሰብሰብ ብለን በነጭ ልብስ አጊጠን ወደናቴ ቤት ሄድን ።

ይቀጥላል

@Ye_Hagere_Wegoch
@Ye_Hagere_Wegoch

የሀገሬ ወጎች

16 Oct, 17:30


እስቲ ልመርቅሽ
        እስቲ ደሞ ልጣሽ
የልብሽን አይቶ እግዜር ከኔ ያውጣሽ
.


ዮኒ_ኣታን

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

14 Oct, 10:51


ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
ችግር ውስጧን ሚረዳላት
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
የአይኗን እንባ ሚያብስላት

ለጠየኳት ጥያቄዎች
ምንም ነበር መልሰ ቃሏ
ብዙ እንደሆነች ግን
ይናገራል ፊት አካሏ

ብቻ...ዝም ብላለች

ታስታውቃለች ሆድ ብሷታል
ታስታውቃለች እንደከፋት
ቆንጆ መልኳን ተመልክቶ
ማን ይሆን ሰው ደርሶ የገፋት
ደረቅ ብሏል ውብ ከንፈሯ
አላገኘም አንዳች እህል
ቀዝቀዝ ብሏል የእጇ መዳፍ
ምን ሁናለች እቺ ጉብል

ቀና ብላ እያየችኝ
ዘረገፈች የአይኗን እንባ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
ነጠላ እጇን ተከናንባ

እንዲህ ነው እያለች መናገር ባትችልም የውስጧን አውጥታ
ብዙ አውርታኛለች ከኔ ጋራ ሳለች ቃሏን በዝምታ
ይገርማል አንዳንዴ
ቃላት ሳይደረደር ምስክር ሳይጠራ ሀቀኛ ሳይለካ
ብዙ ሳንናገር በዝምታ ብቻ ቃል ይወጣል ለካ!


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

የሀገሬ ወጎች

11 Oct, 14:48


Share
@yonny_athan
@yonny_athan

Gfx by
@mikias_56