SUNRISE BOOKS @sunrisebookss Channel on Telegram

SUNRISE BOOKS

@sunrisebookss


የፀሐይ መውጣት የአዲስ ቀን ጅማሬን ያመላክታል :: ብርሃንን ፣ ተስፋን እና ጉልበትን ያመጣል :: በተመሳሳይ መጽሐፍ ማንበብ አእምሮን ለአዳዲስ ዕውቀቶች ፣ ሐሳቦች እና አመለካከቶች መውጪያ መንገድ ይከፍታል :: ለስብዕና ብስለትና ለሚጨበጥ ዕውቀት መነሻም መዳረሻም ይሆናል :: የፀሓይ መውጣትም የመጽሐፍ ንባብም ራስን ለማደስ ዓለምን ለማላቅ እንደ የብርሃን ፍኖት ናቸው ::

SUNRISE BOOKS (Amharic)

የSUNRISE BOOKS ቦኪስ አለን ቢሊንንን፡፡ በዚህ ቦኪስ ላይ የፀሐይ መውጣት እና መጽሐፍዎች ምንቸባርን ለእኛ መጠቀም እንዴት ነው። ብርሃንን ፣ ተስፋንን እና ጉልበትን የሳምባት እንደሚመላለሱና ሐሳቦችን የመሰረቱ በድርጅቶች ድጋፍ እንዲሁም ውጊያ ዕድሲዎችን እንዴት ያጥሩን ለመጠቀም በመዋላቸው የሚሰጡትን እንዴት ያዳግም አለን። SUNRISE BOOKS ለየትኛውም ቦኪስ በዓለም እንከታተል፣ አድራጎት እና መዓዛ እንደሚያስከቨር ቢሆንም ከእኛ ጋር የምትለዋወጥ እንከባክና።

SUNRISE BOOKS

12 Feb, 15:06


እያንዳንዱን 450 ብር ብቻ ::

To Order 👉 @thesunmon

SUNRISE BOOKS

06 Feb, 10:37


#1 Pcs only

" Early Economic Thought "

Order @thesunmon

SUNRISE BOOKS

13 Jan, 04:54


አዲስ አድማስ ከተመሰረተ 25 ዓመት ሞላው ::

SUNRISE BOOKS

10 Jan, 12:20


የአብዛኞቻችን እውነታ !

SUNRISE BOOKS

16 Dec, 13:52


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገቢ ለማመንጨት ሲል እየተጨነቀ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት በ2017 የ1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል! ይህንን የገቢ  እቅድ ለማሳካት ሲባል በፌደራል እና በክልል ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢኮኖሚውን እያስጨነቁት ነው።

የሚወሰዱ እርምጃዎች እየፈጠሩ ያሉት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር "The Cobra Effect" እንዳያመጣ ያሰጋል!

በዝርዝር እንመልከተው https://youtu.be/UiaO3c58NtQ

SUNRISE BOOKS

15 Dec, 16:21


ሲፈለግ የነበረን መጽሀፍ ከ 50 አመታት በኋላ ወደ ቤተ መጽሃፍ የመለሰው ግለሰብ

በአሜሪካ በዴትሮይት ዳርቻ ያደገው ግለሰብ ከ 50 አመታት በኋላ የተዋሰውን መጽሀፍ በልጅነት ጊዜው ይጠቀምበት ለነበረው ቤተመጽሃፍ መልሷል።
https://bit.ly/4iNPoky

SUNRISE BOOKS

14 Dec, 14:45


የእያንዳንዱ ዋጋ 300 ብር ነው ::አንዳንድ ቅጂ ብቻ ነው ያላቸው ::

ለማዘዝ በቴሌግራም @thesunmon

በስልክ -0949006262

SUNRISE BOOKS

08 Dec, 11:40


Funny 😁

SUNRISE BOOKS

06 Dec, 15:36


የ 1953 ቱ መፈንቅለ መንግስት ትክክለኛ ገጽታ

በይላቅ ኃይለማርያም

ዋጋ - 300 ብር ብቻ

ለማዘዝ inbox 👉 @thesunmon

SUNRISE BOOKS

02 Dec, 10:38


መነሻህ ከአንድ ትንሽ ነጥብ ቢሆንም፣ ጅማሬህ ላይ ሁሉን ማወቅ ሁሉን መያዝ ትሻለህ። ያ ግን ምን ይጠቅማል?

ጅማሬህ ላይ ብዙ መያዝ ብትሻ ብዙ ብትለፋና ብትሰበስብም፣ ፍጻሜህ ግን ትንሽ የጠራ እና የነጠረ ሊሆን የተገባ ነው።

ወርቅ ሲወጣ ተመልከት። ብዙ አፈር ተቆፍሮ ይታፈሳል፣ ይታጠባል። መነሻው ብዙ ነው። አሰስ ገሰስ ይበዛዋል። መጨረሻው ግን አንዲት የተጣራች የወርቅ ቅንጣት ማግኘት ነው።

ህይወትም እንዲያ ናት!

መነሻህ ላይ የምትማረው፣ የምትሠራው፣ የምትወዳጀው፣ የምታገኘው ብዙ ነው። ከዚያ ሁሉ ውስጥ በስተመጨረሻ ነጥሮ አብሮህ የሚቀረው ጥቂት ነው። ይህንን አስተውል!

መነሻህ ላይ ከስህተት ይልቅ መሻሻሎች ላይ አተኩር!

ገና ከመነሻው ስህተት እና ጉድለት ላይ አታተኩር። መነሻህ ላይ መሻሻሎች ላይ አተኩር። መነሻህ ላይ ከትናንት መሻልህ ላይ አተኩር። መነሻህ ላይ የብዛት መሻሻል ላይ አተኩር። እንዲህ እያልህ ቀስ በቀስ ወደ ሙላት መጠጋት ትጀምራለህ። ያኔ ጥራት ላይ እያተኮርህ ስህተት እና ጉድለት የምትቀንስበት ጊዜ ይመጣል።

ወደ ሙላት ስትጠጋ ከመሻሻል ይልቅ ስህተትን መቀነስ አስፈላጊ ነው። ያኔ ወደ ፍጽምና ወደ ጥራት እየተጠጋህ ነው።

ወደ ሙላት ስትጠጋ ያገኘኸውን ሁሉ አትገዛም፣ የተጠራህበት ቦታ ሁሉ አትሄድም። በቂ ጊዜ የለህማ! የቀረበልህን ሁሉ አትበላም፣ የቀረበህን ሁሉ አትወዳጅም፣ ለጠየቀህ ሁሉ አትሸጥም። ያኔ ትመርጣለህ!

መነሻህ ላይ ትኩረትህ ብዛት ቢሆን አያስደንቅም። መድረሻህ ላይ ግን ትኩረትህ ከብዛት ይልቅ ጥራት ላይ ይሁን። ችግሩ ቀድሞ የተጣመመን ልማድ ኋላ ላይ ወደ ጥራት ለማምጣት አድካሚ መሆኑ ነው። አድካሚ ቢሆንም ግን ወደ ጥራት ማምጣት ይቻላል። ዋናው ትዕግስት እና አካሄድን ማወቅ ነው።

እናም ስትጀምር አካሄድህ ላይ ለኋላ ሥራ ዋና ጉድለት የሚሆን እንቅፋት አለመኖሩን አረጋግጥ።

ሚዛን በቅድሚያ በብዛትና በፍጥነት ይሰፈራል፤ በመጨረሻ ግን ቀስ በቀስ በትንሹ በጥንቃቄ ይሞላል። ህይወት እንደዚያ ናት!

በቅድሚያ በፍጥነትና በብዛት የምትፈልገውን እውቀት ይሁን ወዳጅ ትሰበስባለህ። በኋላ ግን በጥራት፣ በጥልቀት እና በጥንቃቄ እያጠራህ ልትሄድ ግድ ነው።

በመጨረሻ የሚያስፈልግህ ትንሽ መሆኑን ትረዳለህ። ትኩረትህም ይሰበሰባል። መስፈሪያና መመዘኛህም ይቀየራል።

ብዙ ትሰማለህ? የሰማኸው ምን ጠቀመህ?

ብዙ ታነባለህ? ያነበብኸው ምን ጠቀመህ?

ብዙ ትሰበስባለህ? የሰበሰብከው ምን ጠቀመህ?

ዋናው ቁም-ነገር ያለው የሰበሰብከው ሀብት ሳይሆን ጥቅም ላይ ያዋልከው ነው። የገዛኸው ግዛት ሳይሆን ያለማኸው ነው። ያስገበርከው ህዝብ ሳይሆን ደስተኛ የሆነው ነው።

በመጨረሻ ከግብስብሱ ይልቅ ወርቁ ላይ አተኩር። ከገለባው ይልቅ ፍሬው ላይ አተኩር። ከአንጉላው ይልቅ ንጥሩ ላይ አተኩር።

በመጀመሪያ ግን አንጉላውም፣ ገለባውም፣ ግብስብሱም ከፍሬው ጋር እንደነበሩ አትርሳ።

የመጀመሪያህንና መጨረሻህን መስፈርት አንድ አታድርግ። ያንን መለየት አዋቂ መሆን ይጠይቃል። ያ ልዩ ጥበብ እና መገለጥ ይጠይቃል። ያኔ ብስለት መጣ ማለት ነው።

በመጨረሻ ንጥሩን ቅቤ ከነአንጉላው ወደ ማስቀመጫው አታስገባ። ያ ትልቅ ስህተት ነው!

በመጨረሻ ውሎህም ሥራህም፣ የነጠረ እና የተረጋጋ ሊሆን የተገባ ነው።

( በጌቱ ቱጌዘር የተጻፈ )

SUNRISE BOOKS

02 Dec, 09:32


" ከእውቀት ይልቅ ለቅንነት ዋጋ እሰጣለሁ :: ቅንነት የሌለበት እውቀት በዜሮ ይባዛብኛል ። ቅንነት የሞላበት አለማወቅ ይበልጥ ይገዛኛል። ... "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

በመደብሮቻችን ይገኛል ::

SUNRISE BOOKS

29 Nov, 13:17


https://www.ethioeyewitness.com/book-review-%E1%88%B8%E1%88%99%E1%8A%94-shemune/

SUNRISE BOOKS

27 Nov, 08:37


እነዚህ የውጪ መጽሐፎች የሚያስፈልጓችሁ ካላችሁ በደንብ ተመልከቷቸው ::

ዋጋቸው እያንዳንዱ የሚሸጠው 300 ብር ነው ::

ኦርደር ለማድረግ

Link - @thesunmon
Call - 0949006262

SUNRISE BOOKS

27 Nov, 06:54


Busy ስለሆንን ምርታማና ትርፋማ ነን ማለት አይደለም !

SUNRISE BOOKS

26 Nov, 16:15


" ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ መተው የለበትም ብዬ ያለፈውን ከኔ አርቄ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር። ምናልባት አይቻል ይሆናል። ዛሬ ከተከሰተው ክስተት ምኑ ከኔጋ እንደሚያያዝ አላውቅም። የሰው ልጅ ሁሉ ከትላንቱ ተጋብቶ ሳይሆን አይቀርም የሚኖረው። ዛሬው የትላንት ጭማቂ ነዋ!! የዛሬ ግቡ የትናንት ምክኒያቱ ነበራ! ከዓመታት በፊት እናቴ ወይ አባቴ ያነቡት እንባ ምክንያቱን እንኳን ሳይቀይር በልጃቸው  ጉንጭ ላይ ሊወርድ ይችላል። አባቶች በበሉት መራር ፍሬ የልጆች ጥርስ በለዘ አይነት ሆኖብኝ ትላንት ትዝታ ብቻ አለመሆኑ የገባኝ ዛሬ ነው፡፡ ትናንት ትውልድን እንኳን ጥሶ እንደሚያልፍ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ሀበሻ ሙዚቃው ውስጥ እንኳን ትዝታ ስልት መኖሩ ከትናንት መፋታት አለመፈለጉ ወይ አለመቻሉ ይሆናል። "


ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም


መጽሐፉን :-

በጃፈር መጻሕፍት በሁለም መቅርንጫፎች
( ለገሃር ፣ ሳሪስ ፣ ጥቁር አንበሳ ፣ አራት ኪሎ )

ጦቢያ መጻሕፍት
( ካዛንቺስ )

እነሆ መጻሕፍት
( ሜክሲኮ ተግባረዕድ ፊትለፊት )

ሀሁ መጻሕፍት
( አራት ኪሎ አብርሆት )

አዳነ መጽሐፍ መደብር
( ባህርዳር )

SUNRISE BOOKS

26 Nov, 13:03


Constitutional Law: A Contemporary Approach ( 2d Ed . 2011 )
Gregory E. Maggs & Peter J. Smith,

Abstract

The second edition of the textbook, which is suitable either for a one- or two-semester course, strives to make constitutional law easily teachable and readily accessible for students. The authors have selected the cases very carefully and provided fuller versions of the opinions so that students get a good sense of the Court's reasoning. Text boxes call the students' attention to important aspects of each opinion, and the book is filled with introductions, points for discussion, hypotheticals, and executive summaries. The authors present a diversity of views on every subject, and, reflecting some of their own disagreements, the authors have written point-counterpoint discussions on many disputed questions.

We have only 1 Copy

To Order - @thesunmon
0949006262

SUNRISE BOOKS

26 Nov, 10:49


Heroic Leadership
Leading with Integrity and Honor

Price - 350

To Order - @thesunmon

SUNRISE BOOKS

26 Nov, 08:28


ያገለገሉ መጽሐፎችን እንገዛለን ::

SUNRISE BOOKS

25 Nov, 13:30


ከታተመ የቆየ መጽሐፍ

" ስም የለሽ "
( የእናት ፍቅር )

ትርጉም :- ባህሩ ዘርጋው ግዛው

ዋጋው - 200 ብር

ኦርደር ለማድረግ
👇

link - @thesunmon
Call - 0949006262

SUNRISE BOOKS

25 Nov, 10:13


The Theories Of Human Nature
Classical and contemporary reading

By :- Donald C . Abel

Only 1# Copy

For Order -

link 👉 @thesumon

Call 👉 0949006262

SUNRISE BOOKS

08 Nov, 14:49


No Privacy
No Problem

SUNRISE BOOKS

08 Nov, 07:48


📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ  ጓድ ፋሲካ ሲደልል፣ እና ኮሎኔል መርሻ ወዳጆ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የታኅሣሥ ግርግር(1953 ዓ.ም) እና የግንቦቱ መፈንቅለ መንግስት(1981 ዓ.ም) " ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

SUNRISE BOOKS

04 Nov, 08:55


" የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የማይታወቅ ክስተት እንኳን ቢሆን ቀጣይ አለው ። ከመጀመሪያ ወይ ካለፈው የሚያይዘው ግምድ የድር ያህል የቀጠነ ቢሆንም ... ሁሌም ከመሃል ቆመህ ራስህን ስታገኘው መጀመሪያውን የምትጠይቀው ለዛ ነው ። "

ከገጽ 101
ርዕስ - ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ

አምስተኛው ልዩ ዕትም ወደማለቁ ነው :: በሁሉም መጻሕፍት መደብር ያገኙታል ::

መልካም ንባብ !

SUNRISE BOOKS

04 Nov, 07:54


ይህን የተመሰከረለት መጽሐፍ አነበባችሁት ?
አምስተኛው ልዩ ዕትም ወደማለቁ ነው :: ካልገዛችሁት ግዙ እና አንብቡት ::
ትወዱታላችሁ
ትማሩበታላችሁ
ራሳችሁን ታገኙበታላችሁ ::


አዲስ አበባ ጃፋር መጽሐፍ መደብርን ጨምሮ በሁሉም መጽሐፍ መሸጫ ያገኙታል ::

እንዲሁም :-

ባህር ዳር
ናዝሬት
ሐዋሳ ያሉ መጽሐፍ መደብሮች ውስጥ ታገኙታላችሁ ::

SUNRISE BOOKS

03 Nov, 11:40


5 BOOKS TO READ IN A LIFETIME

1. Atomic Habits by James Clear
Why: This book offers a practical approach to building good habits and breaking bad ones. Clear’s concept of small changes leading to significant results teaches readers how to harness the power of consistency and growth over time. It’s a must-read for anyone looking to make meaningful, lasting changes.

2. Start with Why by Simon Sinek
Why: Sinek explores the power of purpose and how understanding your "why" can transform leadership, motivation, and personal fulfillment. This book encourages readers to focus on their deeper reasons for actions, sparking passion, and commitment in life and work.

3. Rich Dad Poor Dad by Robert Kiyosaki
Why: Using his own story, Kiyosaki reveals key lessons about wealth and financial independence. This book emphasizes financial literacy, asset-building, and the mindset shifts needed to build wealth, making it an essential read for anyone aiming to master personal finance.

4. The Power of Habit by Charles Duhigg
Why: Duhigg delves into the science of habit formation and how habits shape our lives. By understanding and altering our routines, readers can gain control over their choices and environments, leading to a more productive and intentional life.

5. Think and Grow Rich by Napoleon Hill
Why: This classic book is based on interviews with some of the world’s most successful people, unveiling principles for achieving success. It emphasizes the power of desire, persistence, and mental discipline, making it invaluable for anyone aspiring to reach their fullest potential.

SUNRISE BOOKS

02 Nov, 12:11


52 Books That Will Change Your Life

SUNRISE BOOKS

02 Nov, 09:00


" ቀይ አንበሳ "
ደራሲ - ኮሎኔል አልኸንድሮ ዴል ባዬ
ተርጓሚ - ተስፋዬ መኮንን
ይዞት - አዲስ
ለማዘዝ - በቴሌግራም @thesunmon በስልክ 0949006262

SUNRISE BOOKS

02 Nov, 08:53


" አልቦ ዘመድ እና ቄሳርና አብዮት "
( በአንድ መጽሐፍ ሁለት ርዕስ )

ደራሲ - ብርሃኑ ድንቄ
ይዞታ - ያገለገለ
ለማዘዝ - በቴሌግራም @thesunmon በስልክ 0949006262

SUNRISE BOOKS

02 Nov, 06:22


አዲስ አድማስ ጋዜጣ ገበያ ላይ ነው ::

SUNRISE BOOKS

01 Nov, 20:15


" ማደግ የሚናፍቀኝ እንደነ ‘እገሊት‘ እንደነ ‘እገሌ‘ ለመሆን ሆነ ። እንደ‘ራሴ‘ መሆን መኖሩን የማውቅበት ስንዝር የሀሳብ ክፍተት አልነበረኝም ። እገሊትና እገሌን ለመሆን ስኳትን ብዙ ስብርባሪ እገሌዎችን ሆንኩ ።   ሁሉንም የምሞክር ፣ ልክና ስህተትን ልክ ሆኜና ተሳስቼ የምፈትን ፣ ቀናና ወልጋዳውን ቀንቼና ተወላግጄ የማረጋግጥ ሆንኩ ። ምክንያቱም ትክክለኛ መንገድ የሚሉትን በዱላና በስድብ ሊያሳምኑኝ ሲሞክሩ እንጂ ሲኖሩት አይቼ የማላውቅ ነኛ ! .. "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

SUNRISE BOOKS

01 Nov, 11:58


#አስተያየት

በሁሉም መጻሕፍት መደብር ይገኛል !

SUNRISE BOOKS

01 Nov, 11:48


ሰላም ወዳጆች ስለ መጽሃፍት ማስታወሻዎች/ አበርክቶዎች/dedications ይቺን ሶስት ጥያቄ የያዘች ቅጽ በመሙላት ተባበሩን። https://docs.google.com/forms/d/1fDw86HvJP3CBfW7WWCWfZ0N-vt71ROs5-qZ4eb79GeI/edit

SUNRISE BOOKS

01 Nov, 10:13


1. ‹‹የዘጠኝ ወር እርጉዝ በማግባት በአንድ ወር የራስህን ልጅ ልትወልድ አትችልም››

2. ‹‹ዛሬ ዛፍ ጥላ ስር የምንቀመጠው የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ ሰው ዛፉን ስለተከለው ነው፡፡››

3. ‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››

4. ‹‹ባልገባህ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት አታድርግ››

5. ‹‹ስጋት ወይም ፈተና የሚመጣው የምትሰራውን ባለማወቅ ነው፡፡››

6. ‹‹በአንድ ገቢ ብቻ ጥገኛ አትሁን፡፡ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ ፍጠር››

7. ‹‹በአሜሪካ ቢዝነስ ቁጭ ብሎ ማሰብ ያልተለመደ ነው፡፡ እኔ ግን ብዙ ጊዚዬን የማጠፋው ቁጭ ብዬ በማሰብ ነው፡፡

8. ‹‹በጣም አስፈላጊው ኢንቨስትመንት በራስህ ላይ የምታደርገው ነው፡፡››

9. ‹‹የማትፈልገውን የምትገዛ ከሆነ የምትፈልገውን ወዲያው ትሸጣለህ፡፡››

10. ‹‹ከመጥፎ ሰው ጋር ጥሩ ውል ማሰር አትችልም፡፡

11. ‹‹ደስተኛ ሰዎች የሚደሰቱት ምርጥ ነገር ስላላቸው አይደለም፡፡ እነሱ የሚደሰቱት ያላቸውን ነገር አክብረውና ወደው ስለያዙ ነው፡፡

12. ‹‹በመኝታህ ሰዓት ገንዘብ ለማግኘት አስበህ አዲስ መላ ካልፈጠርክ እስክትሞት ትሰራለህ፡፡

13. ‹‹አጥፍተህ የቀረህን አትቆጥብ፡፡ ከቁጠባ በኋላ የተረፈህን አጥፋ፡፡››

14. ‹‹ብዝሃነት ወይም ሁለገብ ዕውቀት ከመሐይምነት ይከላከላል፡፡

15. ‹‹ታማኝነት በጣም ውዱ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ስጦታ ከርካሽ ሰዎች አትጠብቅ፡፡››

16. ‹‹ያልተለመደ ከሆነ ሰዎች ብዙ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ከመስራት ሊያስቆሙህ ይሞክራሉ፡፡

17. ‹‹በዓለም ላይ ሐይል ያለው ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ነው፡፡

18. ‹‹ሁልጊዜም ሐብት ማግኛ ምርጡ መንገድ ለራስህ ዋጋ መስጠት ነው፡፡

19. ‹‹አነባለሁ፣ አነባለሁ፣ አነባለሁ! በቀን ውስጥ ከአምስት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ አነባለሁ፡፡››

20. ‹‹ብዙ በተማርክ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ። ››

SUNRISE BOOKS

31 Oct, 15:04


ተመልከቱልኝ ይህን መረጃ
===================
ከትናንትና ከትናንት በፊት ከታዘብኩት የአሊባባ ኩባንያ ወደኛ ሃገር ገበያ የመቀላቀል ጉዳይ ተነስቼ የተወሰነ የኢኮመርስ ግብይት መረጃዎችን እየቃኘሁ ነበር። ለትምህርት ስለሚሆኗችሁ የተወሰኑ ቁጥሮችን ላጋራችሁ ወደድኩ።

የኢ-ኮሜርስ አሠራር በባህላዊ ንግድ ላይ ያመጣውን ለውጥና ጫና እንመልከት። (ቁጥሮች በሙሉ በጎርጎረሳውያኑ አቆጣጠር ናቸው!)

①) የስራ እድል ለውጦች (2010-2024)፦

- በባህላዊ ንግድ የጠፉ ሥራዎች (ከገበያው የወጡ ባህላዊ ንግዶች):
  √ በአሜሪካ ከ2014-2021 90,000 ገደማ የሚጠጉ መደብሮች ተዘግተዋል።

  √ ከ70 አመታት በላይ በአሜሪካ ገበያ ናኝቶ የቆየው ቶይስ "አር" ዩኤስ (Toys "R" Us) አማዞንንና ወልማርትን መቋቋም ተስኖት በ2018 ሲዘጋ 33,000 ሰራተኞቹ ስራ አጥ ሆነዋል።

  √ Sears: ከ2007-2017 175,000 ሰራተኞቹ ስራ አጥ ሆነዋል።

  √ ጄሲፔኒ (JCPenney): ከ2010-2020 27,000 ሰራተኞቹን ለመቀነስ ተገዷል።

ቴክኖሎጂው ሥራ አጥ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ደግሞ ሥራ ይፈጥራል።

በኢ-ኮሜርስ የተፈጠሩ አዳዲስ ስራዎች:

  √ አማዞን: ከ2010 ጀምሮ 1.6 ሚሊዮን ስራዎችን ፈጥሯል።
  √ በ2020 ብቻ 427,300 አዳዲስ ስራዎችን ፈጥሯል።
  √ በሎጂስቲክስና ዴሊቨሪ 500,000 ተጨማሪ ስራዎችን ፈጥሯል።
  √ አሊባባ: በቻይና 36 ሚሊዮን ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ስራዎችን ፈጥሯል።

②) የገበያ እሴት ለውጦች:

- የአማዞን እድገት:

  √ የገበያ ዋጋው 2010 ላይ 17.5 ቢሊዮን ዶላር ከነበረበት ተነስቶ 2024 ላይወደ 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ጨምሯል።

  √ እስከ 2022 49.1% የአሜሪካን የኢ-ኮሜርስ ገበያ ድርሻ ይዟል።

  √ በ2023 በቀን 683 ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ አስመዝግቧል።

- የባህላዊ ንግድ ውድቀት:

  √ ከ2000-2020 ባህላዊ መደብሮች 40% የገበያ ድርሻ አጥተዋል።

  √ ከ2019-2022 የሾፒንግ ሞል ጎብኝዎች ቁጥር በ22% ቀንሷል።

  √ ከ2015-2020 ባለው 60 ትላልቅ የንግድ ተቋማት ከንግድ ውጪ ሆነዋል።

3. በአነስተኛ ንግዶች ላይ የታየ ለውጥ:

- ባህላዊ እና ዲጂታል:
  √ 65% የባህላዊ አነስተኛ ነጋዴዎች የገቢያቸውን መቀነስ ሪፖርት አድርገዋል።

  √ የድጅታል ላይ አነስተኛ ንግዶች በ2020-2022 በ45% አድገዋል።

  √ 72% የአነስተኛ ንግዶች አሁን ላይ አሠራራቸውን አዘምነው የኦንላይን ገፅ አላቸው።

4. የስራ ዝውውርን በተመለከተ:

- የክህሎት ሽግግር:
  √ 200,000 የቀድሞ የሱቅ ሰራተኞች ወደ ኢ-ኮሜርስ ማሟያ ማዕከል ሰራተኝነት ተቀይረዋል። አስቡት! በዛኛው ከገበያ ሲወጡ በሌላኛው ወደ ገበያ ገብተዋል።

  √ 150,000 የሚሆኑት የዴሊቨሪ ሾፌሮች ሆነዋል።
  √ 85,000 የሚሆኑት ወደ ዲጂታል ማርኬቲንግ ተሸጋግረዋል። አየሩ ወደነፈሰበት መንፈስ ነው ወገን።

⑤) የኢ-ኮሜርስ ስኬታማ ሽግግር:

- ባህላዊ ወደ ዲጂታል:
 
√ 125,000 ንግዶች በስኬት ወደ ድጅታሉ ዓለም ንግድ ተሸጋግረዋል።

  √  አማካይ የገቢ ጭማሪ: 31% ጨምሯል
  √ የደንበኞች መብዛት: 47% ጨምሯል።
  √ የስራ ማስኬጃ ወጪ መቀነስ: 18% ቀንሶላቸዋል።

6. የወደፊት እይታ (2024-2028):
- አዋቂው አላህ ነው፤ ግን በዚህ አካሄድ ፀወደፊት የሚጠበቁ ግምታዊ ለውጦች:

  √ 100,000 ተጨማሪ ባህላዊ የንግድ ስራዎች በአደጋ ላይ ናቸው። ሊዘጉም ይችላሉ።

  √ 150,000 አዲስ የኢ-ኮሜርስ ስራዎች እንደሚፈጠሩ ይጠበቃል።

  √ 50,000 አዲስ የሎጂስቲክስ/ዴሊቨሪ ቦታዎች ይኖራሉ።

  √ በዲጂታል ንግድ 100,000 የተጣራ ስራ ጭማሪ ይኖራል።

⑦) የሸማቾች (የተጠቃሚው) ባህሪ ለውጥ:
- የግዢ ልማዶች:
  √ ህዝቤ ሱቅ ሂዶ የመግዛት ሞራሉ በ36% ቀንሷል። (2019-2023)

  √ በኦንላይን ላይ መግዛቱ በ43% ጨምሯል።
  √ የሞባይል ንግድ በ56% አድጓል።

ከዚህ መረጃ የምንረዳው:
1. አጠቃላይ የስራ እድሎች በአብዛኛው ጨምረዋል
2. የስራ አይነቶች ከመጥፋት ይልቅ ተለውጠዋል።
3. በዲጂታል ንግድ አዳዲስ እድሎች ተፈጥረዋል።
4. ተስማሚ ለውጦችን በመቀበል እንደየአየሩ ጸባይ እያጠኑ በመዞር ስኬታማ መሆን ይቻላል።



እናንተስ ምን አሰባችሁ? በቴክኖሎጂው ከሚፈናቀሉት ብትሆኑ እንኳ ወደሚያፈናቅለው ዘርፍ ለመዞር አታስቡም? ከወዲሁ ቦታ ያዝ ብያለሁ።


||
© t.me/STEMwithMurad

SUNRISE BOOKS

31 Oct, 09:15


" ሁሉም ሰው በልቡ  ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ ….. ብቻ አንዱ ይኖርበታል፡፡ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎን ካልተገለጠ በስተቀር ንፁህ፣ ቅን እና ፍፁም እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

SUNRISE BOOKS

29 Oct, 18:56


" ... አባቱ ሲገደሉ በዓይኑ አይቷቸዋል ። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት ። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ  ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ ። ቤታቸው መግቢያ ጋር ሲደርሱ የተቃቀፉ መሰለው ። ብዙም ሳይቆይ ግን አባቱ ወደቁ ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት  ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ ። ዳግማዊ እየሮጠ አባቱ ጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውን እና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው ። የቅድስት አስራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር ። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት ። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ ። በደመ—ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የወንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩኸት ተጣራ። ... "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

በመደብሮቻችን ይገኛል !

SUNRISE BOOKS

27 Oct, 16:28


" ጥንቅቅ ያለ ስርዓታም መሆኑ ልብ የሚሰቅዝ ነገር አለው። ሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስለው ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኝም። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል።  ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም ። ራስን ለመሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንምጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ ።  " 


ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

SUNRISE BOOKS

26 Oct, 07:52


" ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት::

“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ᎙_ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ….. አንዱ በነነ ይኖርበታል፡፡

ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባሕሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በስተቀር ንጹሕ፣ ቅን እና ሁኔታ  እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡

የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው ሕይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል። አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም። "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል !

TelegramFacebook ● Instagram ● Tiktok ● Website

SUNRISE BOOKS

25 Oct, 18:23


አዲስ አድማስ ጋዜጣ ነገ በማለዳ ጠብቁን !

SUNRISE BOOKS

25 Oct, 13:37


ርዕስ - በይነ - ዲሲፕሊናዊ የሥነ ጽሑፍ ንባብ
አዘጋጅ - ቴዎድሮስ ገብሬ
አታሚ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
ይዞታት - ያልተነበበ አዲስ

ዋጋ ለማወቅና ኦርደር ለማድረግ - @thesunmon

SUNRISE BOOKS

25 Oct, 08:37


ርዕስ - የቢሆን ዓለም
ደራሲ ደጉ ቁምቢ
ይዞታ - ያገለገለ
ዋጋ - 200

Order - @thesunmon

SUNRISE BOOKS

25 Oct, 08:14


መሸጥ የምትፈልጓቸው ያገለገሉ መጻሕፍት ካላችሁ ደውሉልን እንገዛለን ::

0949006262

SUNRISE BOOKS

24 Oct, 05:40


የመጽሐፍ ምርቃት ::

SUNRISE BOOKS

23 Oct, 07:36


Reality !

SUNRISE BOOKS

22 Oct, 14:45


የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ ረቡዕ ይመረቃል።

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ  ርዕስ የተሰጠው አዲስ  የግጥም መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ከ11:00 ጀምሮ  አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

SUNRISE BOOKS

20 Oct, 15:32


ኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ለ6ኛ ዙር በተመረጡ መጻሕፍት ድልድል ማሳወቂያ ፕሮግራም በክለብሀውስ ከምሽት 2:00 ሰዓት ጀምሮ ያደርጋል።

የውይይቱ ሊንክ:

https://www.clubhouse.com/invite/Yv3UKZeEbgG7N98ER217QQqL9B5rhKAaYe6:XGZVSMuGnOFYY4sJv72X71OHyesbKGbLSQbVlCe7d84

SUNRISE BOOKS

19 Oct, 11:22


፮ኛው የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም

ከጥቅምት 17 እስከ የካቲት 30፣ 2017 ዓ.ም ለንባብ የተመረጡ የመጻሕፍት ዝርዝር


ዘወትር እሑድ ፣ ምሽት 2፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት በክለብ ሀውስ መተግበሪያ ላይ

የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም

SUNRISE BOOKS

18 Oct, 18:55


«የኢትዬ ቴሌኮም ሼር ልግዛ ወይንስ አልግዛ?

ሼር ለመግዛት ስናሰብ የድርጅቱን አሰተዳደራዊና የፋይናንስ ጤንነት ማረጋገጥ አለብን። የአንድ ድርጅት የፋይናንሰ ጤንነት ለማወቅ መጠናዊ (quantitative)እና አይነታዊ (qualitative) መለኪያዎች አሉ።

✍🏽 ቀዳሚው የድርጅት ፋይናንሰ መጠናዊ መለኪያ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ (Market Capitakization) ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ለአክሲዮን ሸያጭ ያወጣው የሸያጭና የድርጅት ቁመና መግለጫ ሪፖርት (prospectus) እንደሚያሳየው የእያንዳንዱ ዋጋ 300 ብር የሆነ አጠቃላይ 1 ቢሊየን ሼሮች አሉት። ይህም ማለት አጠቃላይ የገበያ ዋጋዬ ነው ብሎ ያሰቀመጠው 300 ቢሊየን ብር ነው። ከዚህ ውሰጥ ለሽያጭ የቀረበው እያንዳንዳቸው 300 ብር የገጽ ዋጋ ያላቸው 1 ሚሊየን ሼሮችን ነው። የድርጅቱ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ 300 ቢሊየን ነው ስለተባለ ነው ማለት አይደለም። ይሄ የሚያመለክተን የሼሮቹን ዋጋ ወይም በስቶክ ማርኬት ውስጥ የሚኖረውን ዋጋ ነው። የሚጠቅመንም ኢንደስትሪው ውስጥ ካሉ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር ለማነጻጸር ነው። የድርጅቱን ትክክለኛ ዋጋ የምናውቀው Enterprise value በማሰላት ነው። ይህ በቀላሉ የድርጅቱን የገበያ ዋጋ ላይ ድርጅቱ ያለበትን ብድር በመደመርና ያለውን ጥሬ ገንዘብ በመቀነስ ማስላት ይቻላል። በተጨማሪ አይነታዊ የሆኑ መለኪያዎችን በመጨመር ድርጅቱ ያለውን ሀብት፥ የዘረጋውን መሰረተ ልማት፥ የሰበሰባቸውን ደንበኞች፥ ማፍለቅ የሚችለውን ገቢ፥ የገነባውን ብራንድ፥ በገበያው ውስጥ ያለውን ድርሻ እንዲሁም ያለበትን እዳ ግምት ውስጥ አሰገብተን ማሰላት እንችላለን።

✍🏽 የገቢና የትርፍ (Revenue& Earning)ልኬት ነው። ቢያንሰ ባለፉት አምስት አመታት የድርጅቱ ገቢ ምን ያክል ነበር? በምን ያህል እያደገ ነው? የትርፉ ምጣኔስ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ማስላትና ሂደቱን መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ የኢትዬ ቴሌኮምን የገቢና ትርፍ እድገት ስንመለከት በ 2020 ገቢው 56 ቢሊየን ብር አካባቢ የነበረ ሲሆን በሰኔ 2024 ደግሞ 93•7 ቢሊየን ብር ደርሷል። ይህ በአማካይ የገቢው እድገት 21% አካባቢ እንደሆነ ያሳያል።

✍🏽ሌላው የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያ የሼር ገቢ (Earning per share)ነው። በዚ ቀመር የድርጅቱ አንድ ሼር በአመቱ ምን ያክል የትርፍ ምጣኔ አገኘ የሚለው ይሰላል።
ለምሳሌ: ኢትዬ ቴሌ ኮም ባለፈው የሂሳብ አመት የተጣራ ትርፉ  21•79 ቢሊየን ብር እንደሆነ ተገልጽዋል። ይህ ትርፍ ድርጅቱ ላለው አጠቃላይ የሼር ብዛት (1 ቢሊየን) ሲካፈል 21•79 ብር የሼር ገቢ ምጣኔ ይኖረዋል። ይህም ማለት አንድ ሼር 21•79 ብር ትርፍ ይኖረዋል። አሁን ባለው የሼር ዋጋ አንዱ ሼር 300 ብር የሚሸጥ በመሆኑ የ 300 ብር ኢንቨሰትመንት በአመት 22 ብር አካባቢ ትርፍ ያሰገኛል። ይህ ትርፍ ያለፉት አመታት እድገቱን ከተከተለ በየአመቱ በአማካይ 21 ፐርሰንት እያደገ ይሄዳል።

✍🏽ሌላኛውና ወሳኝ የሚባለው የፋይናንሰ መለኪያ PEG ratio ይባላል። የአንድ ሼርን ትርፍ እድገትን ግምት ውስጥ አሰገብተን የምናሰላበትና የሼሩ ዋጋ ተገቢ ነው? በዝቶበታል? ወይንስ ርካሸ ነው የሚል የሚያመላክተን ነው።

የቴሌን ምሳሌ ቀጠለን ብንመለከተው የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ እንደሆነ አይተናል። ይህን የአንድ ሼር ትርፍ ለአመታዊ እድገቱ ማለትም 21 ፐርሰንት (በሙሉ ቁጥር) ሰናካፍለው 1•04 አካባቢ ይመጣል። የአንድ ሼር PEG ratio ከ1 በላይ ከሆነ የሼር መሸጫ ዋጋው ውድ መሆኑን ያመላክታል።

✍🏽ከነዚህ በተጨማሪ ለውሳኔ የሚያግዙን ንፅፅራዊ የሆኑ የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያዎች አሉ። ከነዚህ ቀዳሚው የሼር ትርፍ ንጻሬን(EPS ratio) ከሌሎች ትርፎች ጋር ማነጻጸር ነው። ከላይ እንዳየነው የኢትዬ ቴሌኮም የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ ነበር። ይህን ትርፍ በአንድ ሼር መሽጫ ዋጋ ስናካፍለው (22/300)= 7 ፐርሰንት አካባቢ ነው። ሰለዚህም ባለፈው የሂሳብ አመት የቴሌ ሼር የትርፍ ምጣኔ 7 % ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ከባንክ የቁጠባ ወለድ በታች ከመሆኑ በተጨማሪም ከሌሎች ኢንቨሰትመንቶች የትርፍ ምጣኔ ያነስ ነው።

✍🏽 ግምት ውስጥ መግባት ካለበት የአይነታዊ መለኪያ አንዱ የድርጅቱ የቢዝነሰ ሞዴል የእድገት ተስፋ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌኮም ሰርቪስ በተጨማሪ ግዙፉ የዲጂታል ፋይናንሰ(Fin-Tech) ተቋም እየሆነ መጥቷል። ይህም የድርጅቱን እድገት ብሩህ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዬ ቴሌኮም ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ያፈሰሰ በመሆኑ ባለፉት አመታት ትርፉ ያነስ የመሆን እድሉና ወደፊት የማደግ ተሰፋ እንዳለው አመላካች ነው።

✍️የአንድ ድርጅትን ሼር ለመግዛት እነዚህ መለኪያዎች በቂ አይደሉም። ወሳኙ መለኪያ መግዛት የፈለግንበት ምክኒያት ነው።  ከትርፍ ባሻገር ባለቤት የመሆን፥ ተጽዕኖ የመፍጠር፥ ውርስ የመሳሰሉ ምክኒያቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ሌላው እጃችን ላይ ያለው የገንዘብ መጠንና ያሉን አማራጭ ኢንቨሰትመንቶች ውሳኔያችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።»

«የኢትዬ ቴሌኮም የሼር ሽያጭን በተመለከተ ለውሳኔ የሚያግዙ የፋያናንሰ ጤንነት መለኪያዎችን በተመለከተ አንድ ልጥፍ አቅርቤ ነበር። ሆኖም የተወሰኑ ግልፅ አልሆነልንም የሚል ጥያቄዎች ደርሰውኛል። በቀላል ነጥብ ለማሰረዳት ልሞክር።

ለሽያጭ የቀረበው ሼር የአንዱ መግዢያ ዋጋ 300 ብር ነው። በተጨማሪ 1•5 ፐርሰንት ሰርቪስ ቻርጅና ከሰርቪሰ ቻርጁ ላይ የሚሰላ ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ አለው። አንድ ስው 1000 ሼር መግዛት ቢፈልግ
👉 የሼር ክፍያ 300 ሺ ብር
👉 ሰርቪሰ ቻርጅ 4500 ብር
👉 የተጨማሪ እሴት ታክሰ 675 ብር

በድምሩ 305,175 ብር ይከፍላል።

ይህን ሼር የሚገዛው ለትርፍ ከሆነ፥ በዚህ ብር ምን ያክል አተርፋለሁ የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ይሆናል። መልሱን ለማግኘት መጀመሪያ ኢትዬ ቴሌኮም ባለፈው አመት ሰንት አተረፈ እና የትርፍ እድገቱስ ስንት ፐርሰንት ነው የሚለውን ማወቅ ያሰፈልጋል።

በዚህ መሰረት የኢትዬ ቴሌኮም ያለፈው አመት

👉 የአንድ ሼር ትርፍ  22 ብር አካባቢ ነበር።
👉ያለፉት አመታት አማካይ የትርፍ እድገት 21 ፐርሰንት አካባቢ የነበረ ሲሆን እድገቱ በዚሁ ከቀጠለ የዚህ አመት የአንድ ሼር ትርፍ 27 ብር አካባቢ ይሆናል።

👉 ይህም አንድ በ300 ብር የተገዛ ሼር 27 ብር አካባቢ ያተርፋል ማለት ነው። 1 ሺ ሼሮችን 305 ሺ ብር አካባቢ አውጥቶ የገዛው ሰው ትርፉ 27 ሺ ብር ይሆናል።

ይሄን መግዛት ያዋጣኛል አያዋጣኝም ግላዊ ውሳኔ ነው።»

©: Ibrahim Abdu

SUNRISE BOOKS

18 Oct, 14:05


አዲስ አድማስ ጋዜጣ ነገ ጠዋት ይጠብቁ !

SUNRISE BOOKS

18 Oct, 10:48


ስለ Ethio Telcom ሼር ሽያጭ


አለች.....

"ሣይኖርህ በትእግሥት ሥታገኝ በጥበብ ኑር፣በትእግሥት ወቅት...
ለሚያልፉ ግዜአዊ ችግሮች ተብሎ ኑሮህን እንደማታፈርሠው ሁሉ....ደሃ እናትህን ለትርፍ እንደማትሸጥ ሁሉ....ያለችህን ጥገት ለእለት እንደማታርድ ሁሉ....ለሚያልፍ ክረምት ዘርህን ለእለት እንደማታሥፈጨው ሁሉ...." እማሆይ እርጎዬ የነተበውን ብቸኛ ቡኒ ካባዋን እያሥተካከለች።

ብዙ ወጣቶች ሥቶክ ማርኬት ላይ መሣተፍ አለባችሁ።
ሥቶክ ግዙ፣ሽጡ፣አትርፉ....
~~~~~
ይህ ጽሁፍ ለሁለት ለማከብራቸው ሠዎች የተጻፈ ሢሆን...የሚያሥተምር ከሆነ እዚህ ላቅርበው።
ለ Get Toughe Zer እና ለ Ethio Telecom CEO ለ ፍሬህይወት ነው።
ጌቱ ወዳጄ የሠፈሬ ልጅ እና ሞዴሌ ነ፣ነነነነነፍ ቢዝነሦችን የመራ 'ጀን ዋይ' ነው። ፍሬ ደግሞ ወጣት ሤት ሢኢኦ፣ያራዳ ልጅ፣ዘመናዊነት የገባት፣ሃሣብ ለመተግበር ወደኋላ የማትል 'ጀን ዚ' ነች።ሁለቱም በአመራር ብቃታቸው ይመቹኛል።
~~~~~~
እሺ ወደቀደዳ .....

ኢንጂኒር ጌቱ በልጥፉ ለምን ኢትዮ ቴሌኮም ሥቶክን ትገዛለህ?ለሚል ጥያቂ በመጠየቁ ነው።

የኢትዮጵያ ቴሌን፣አየር መንገድን፣መብራት ሃይልን፣ንግድ ባንክን ሼር የምገዛው...ለናሽናሊሥት እሣቤዬ ድጋፍ እንዲሆነኝ እንጂ ለትርፍ አልገዛውም።ሥቶክ ሢገዛ ሥቴትመንት ማየት ግድ ነው እዚህ ሁሉም ጂያንት እጅግ ደሥ የሚል ገቢ አላቸው። ነገር ግን ሁሉም በሚባል ደረጃ ወጪያቸው እጅግ ያበጠ በመሆኑ በአትራፊነት ላይ ተመርኩዘህ በምትገዛው ሥቶክ ላይ ድርሻህን ያቀጭጩታል።

በርግጥ ወደፊት ብዙ ኢንተርናሽናል የሥቶክ ግብይቶች ሢጀመሩ፤የኛዎቹ ራሣቸውን ከዝርክርክ ወጪ ካልቆጠቡ ገበያው ላይ ሊቸገሩ ይችላሉ ማለት ነው።

ለምሣሌ የቴሌ CEO (ፍሬህይወት ታምሩን) የቀጣይ የሥቶኳ አቅርቦት አጓጊ እንዲሆን ምን ማድረግ አለባት?ብዬ ላሥብና....

ከ 16,000 በላይ ቋሚ ሠራተኛ ወጪን መቀነሥ አለባት።ተቀናሾች ሥራ እንዲፈጥሩ እና የተሻለ ገቢ ኑሯቸውን ማገዝ እንዲችሉ በማሥቻል ።ምክንያቱም የሠራተኛ ብቻ ኮንትራቶቹን ጨምሮ ወጪ ከ አንድ ቢሊዮን በላይ ያየሁ መሠለኝ። የኛ ሃገር ትልልቅ ድርጅቶች ወጪን ማሥተዳደር የተሣናቸው ይመሥላል።
ብዙ ጥቅም ላይ የማይውሉ ሥክራፕና ቁሣቁሦች አሏት ወደ ሃብት ልትቀይራቸው ይገባል።ብዙ ሪሢቬብልና ideal inventory አላቸው በቶሎ ማሥተካከልን ይጠይቃል።የተሽከርካሪዎች ጥገና ወጪ..... ወዘተ የተቆጠቡ አይደሉም።

ለአሥረጅ ያህል ለወጪ የሚዳርጉ አገልግሎቶች ያሉ ይመሥለኛል ለምሣሌ 1500 ብር የምትከፍልበት ዋይፋይ 'ሞደም' አገልግሎት ሢበላሽ ደውለህ የሚመጣው ቴክኒሺያን ወጪው ተመጣጣኝ የሚሆን አይመሥለኝም።2k ለጥገና ወጪ ሊኖረው ይችላል።አውት ሦርሥ መደረግ ያለበት ብዙ አገልግሎቶች አላቸው።የጥገና፣የእቃ፣ያገልግሎት ጥራት መጓደል ለዚህ እና ለተለያዩ ወጪዎች የሚዳርግ ይመሥለኛል።

ሌላው በቴሌ ብር አገልግሎቱ አሪፍ ነው። ሎን npl ን እንዴት ታሥከፍላለህ? ተገልጋይህን ማንቃ፤መረጃን መያዝ ወጪን ይቀንሠዋል ነው።

አየር መንገድሥ፣ንግድ ባንክሥ፣መብራት ሃይልሥ ወጪያቸውን ካልተቆጣጠሩት የአለም አቀፍ ሥቶክ ላይ እንደሚቸገሩ እሙን አይደለም?
እነዚህ ችግሮች በቶሎ የሚሥተካከሉም ይመሥለኛል....

ግን የቴሌን ሼር የምገዛው በናሽናሊሥት ፍላጎቴ ነው ።

ለምሣሌ.....

ቴሌ 10 billion dollars ሽያጭ ኖሮት 70% ወጪ ቢኖረውና፤ ሣፋሪ ኮም 5 billion dollars ሽያጭ ኖሮት ወጪው 30% ቢሆን የየቱን ሥቶክ ትገዛለህ?...

በሥቶክ ማርኬት እይታ ለማትረፍ ሣፋሪን ትገዛለህ ክፍፍሉ ያተርፍሃላ።ነገር ግን እኔ የኢትዮጵያ ቴሌ ኩራቴ በመሆኑ በሆደ ሠፊነት፣በያድጋል ባይነት ተሥፋ እና በናሽናል እሣቤ ተወሥውሼ በክፍፍል የሚቀንሠውን ቴሌን ሼር እገዛዋለሁ ማለት ነው።ወደፊት ሢገባቸው ወጪአቸውን ያሥተካክላሉ ብዬ ሥለማምን።

ኢንጁ....

ሥቶክ ለመግዛት የአንድን ድርጅት ገቢውን ብቻ ሣይሆን ወጪውንም በጥልቀት ማየት የጠበቅብናል ።

መንግሥት ልምምዱ እንዲመጣ ና ማሥጀመሪያ እንዲሆነው ባንክ መሠሉን፣የሎተሪ ድርጅት መሠሉን፣የቴሌኮም መሠሉን ...የኛን ቴሌ ፈር ቀዳጅ አድርጎታል። ምክንያት የሚመሥለኝ በፍጥነት በመተግበር CEO ዋን ይተማመንባታል።እኔም እጅግ አድናቂዋ ነኝ።viva ፍሬ👌

ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ቢገፉ ቢገፉ ቆፍጠን ብለው ባለመግባታቸውና በመፋዘዛቸው ይመሥለኛል....ቴሌ ደግሞ የቀደመ ዲጂታል ፕላትፎርም ሥላለው ሥራውን ያሣልጠዋል።

ለምሣሌ ...መብራት ሃይል ከሃርድ ኮፒ አልተላቀቀም።አየር መንገዱ popular crowd ፕላትፎርም ላይ አልተዘጋጀም። ባንኮቻችን የሥቶክ ማርኬት ግራ እያጋባቸው ይመሥላል..የመጀመር. ውሥንነት ይታይባቸዋል።ሌሎች ድርጅቶች ደሞ ለሽ ብለዋል።ለካፒታል ማርኬቱ ከነጉድለቶቹ የተዘጋጀው ቴሌ ብቻ ነው።ለዛም ነው ቴሌዎችን የምንደግፋቸው....ወደፊት ኢንተርናሽናል ጠንካራ አለማቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ።

ምንግዜም የኢትዮጵያ ቴሌ፣ባንክ፣አየር መንገድ፣መብራት ሃይል...ልማት ባንክ ውሥጤ ናቸው። እዚህ ግን የ 1 ቢሊዮን ካምፓኒ አለን?

በርቱ🙏

በ Bejai Nerash Naiker የተጻፈ

SUNRISE BOOKS

18 Oct, 06:58


ደብረዘይት ያላችሁ ደምበኞቼ " ጠበኛ እውነቶችን " አምስተኛውን ዕትም ከፈለጋችሁ በ 0949006262 ደውሉልኝ :: ወይንም በ telegram link @thesunmon ጻፉልኝ ::

SUNRISE BOOKS

18 Oct, 06:42


እኔ የምላችሁ?? ከ21,396 ሰብስክራይበር ስንት ሰው በጣም ይወደኛል?? በጣም ለምትወዱኝ ብቻ ይሄን የጠበኛ እውነቶች አምስተኛ እትም ምስል ስቶሪያችሁ አድርጉልኝማ!!❤️❤️


የሚገኙባቸው መጻሕፍት መደብሮች

¶ ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር -
- ለገሃር ኖክ ተወልደ ሕንጻ ስር
- አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ፊት ለፊት
- አብርሆት ቤተመጻሕፍት ጊቢ ውስጥ
- ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፍት ለፊት

ስልክ ( 0911125324 / 0928936426 / 0911932088 /

¶ እነሆ መጻሕፍት - አራት ኪሎ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ፊትለፊት
ስልክ ( 0912735000
¶ ጦቢያ መጻሕፍት - ካዛንቺስ መብራት ኃይል አካባቢ
ስልክ ( 0913108312 )

¶ ኮሜርስ መጻሕፍት - ኮሜርስ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ወይንም የቀድሞ ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ አካባቢ

ስልክ ( 0942408292 )

ከብዙ ፍቅር ጋር ❤️❤️❤️

SUNRISE BOOKS

17 Oct, 10:53


ባህርዳር ያላችሁ አንባቢዎች የሜሪ ፈለቀ " ጠበኛ እውነቶች " አምስተኛውን ዕትም መጽሐፍ " ዮቶር መጽሐፍ መደብር " ታገኙታላችሁ ::

አዲስ አበባ በሁሉም መጻሕፍት መደብር እና መጽሐፍ አዟሪዎች እጅ ታገኙታላችሁ ::

SUNRISE BOOKS

17 Oct, 09:16


ውስን ቅጂዎች ናቸው ያሉን :: ኦርጅናልና ተፈላጊ መጽሐፎች ናቸው ::

ለማዘዝ - By Telegram 👉 @thesunmon
Call 0949006262