FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) @fmaddis Channel on Telegram

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

@fmaddis


ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) (Amharic)

ከዚህም በላይ የቴሌግራም እና ሶል ዘግቧ 97.1 የቴሌአገቧ ቻናሎች ዓይነቴን አስመልክቶ የተመሠረተ በክረምቱ ላይ ይገኛል። ይህን ቻናል እሴት ኣዲስ ኣስራሓም ኣብታልና የሚቆጠሩትን ዘገባዎች አስተምሮአል፣ ኦርቶማና ጥቂት መረጃዎችን በመረጃዎቹ እንግዳዎች ያገኘል። fmaddis ቻናልን በምዝገባ ከግልፅ እና ከባለ ሥራ ጋር ይመልከቱ።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

06 Jan, 12:22


ገናን በኢቢሲ ዶትስትሪም
#etv #EBC #ebcdotstream #Ethiopia

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Jan, 21:19


በምእራባውያን ፕሮዲውሰሮች ከተሰሩ ሙዚቃዎች መካከል የአስቴር አወቀ እና እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) ስራዎች በምርጥ አርያነት የሚጠቀሱ ሲሆን ጃን ስዩም እና ሚኒሹ ክፍሌ ግን የብቃት ችግር ታቶባቸዋል


በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በየሳምንቱ ቅዳሜ ከቀኑ 6፡00-8፡00 በሙዚቃ ባለሙያዎቹ ምዕራፍ ተክሌ እና ሰርጸ ፍሬ ስብዓት የሚቀርበው የጣእም ልኬት ዝግጅት ለተከታታይ 2 ሳምንት በምራባውያን ፕሮዲውሰሮች የተሰሩ እና በኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች የተቀነቀኑ ሙዚቃዎችን ገምግሟል፡፡

ካነሷቸዋ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል

-ከኢትዮጵያ በወርልድ ሚውዚክ ዘውግ ለመጀመሪያ ጊዜ የዘፈነችው ድምፃዊት አስቴር አወቀ ናት "ካቡ" በሚለው አልበሟ::

-የአስቴር አወቀ ካቡ የታዋቂው ሙዚቃ ባለሙያ የፖል ሳይመን የወርልድ ሚውዚክ ፍልስፍና በደንብ ተንፀባርቆበታል፡፡

-የአስቴር የድምጽ ነጻነትና ብቃት እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አብረው መሳተፋቸው ካቡ አልበምን የተሳካ አድርጎታል

የአስቴር ሙዚቃዎች በሙሉ ተሰብስበው ቢደመሩ ካቡን አያክሉም፡፡ወይም ከካቡ አይበልጡም

-ሌላው በወርልድ ሚውዚክ የተሰራው የኢትዮጵየ አልበም በ1993 የወጣው የእጅጋየው ሽባባው ‘’ጉድ ፈላ’’አልበም ነው፡፡
-በዚህ አልበም ስራ ላይ ፕሮዲውሰሩ ቢል ላስዌልና ኸርቢ ሃንኩክ ጨምሮ ፣ ኢትዮጵያውያኑ አበጋዝ ክብረ ወርቅ፣ደረጄ መኮንን እና ለሎች መሳተፋቸው የሙዚቃውን ደረጃ ለመጠበቅ እድል ፈጥሯል

-ይህ የእጅጋየሁ አልበም በአርያነቱ የሚጠቀስ ከፍ ያለ ሙዚቃዊ አልበም ነው፡፡
-በየእጅጋየው ሙዚቃ ላይ የህንዶቹን ታብላ እንሰማዋለን፡፡ህንዶቹ ይህ ሙዚቃ ቢከፈትላቸው ያለምንም የባህል ገደብ የራሳቸው መስሏቸው ያዳምጡታል፡፡
-ይሄንኑ ሙዚቃ ማሊ ወስደን ብንከፍተው የራሷ የእጅጋየሁ ድምጽ የኦሞ ሳንጋሪን መምሰል ጋር ተያይዞ በቀጥታ የማዳመጥ ዕድል ይፈጠራል፡፡አንዳንድ ኢንስትሮመንቱ የማሊንም ይመስላል፡፡

-በወርልድ ሚውዚክ የሙዚቃ አልበሙን የሰራው ሌላው ኢትዮጵያዊ ጃን ስዩም ሄኖክ ነው፡፡ይህ አልበም በጣም ጥሩ ነው፡፡ ጥሩ ያደረገው የተሰራበት መንገድ ነው፡፡ግን እንከኖችም ደግሞ አሉት፡፡ እከኖቹ አሁንም ደረስ የመስተካከል ዕድል ያላቸው ናቸው፡፡

-በጃንስም አልበም የታየው ደካማ የድምጽ ወይም የቮካል ጉዳይ ነው፡፡

-ድምጻዊው የድምጻዊነት ልምድ ማነስ ፣መደበኛ ሰው ወጥቶ የሚዘፍን የመመስል ፣በተለይ ቀጭን ድምጾች ሲወጡ ጥንቃቄ የሌለበት ፣ለልህቀት ካለመጨነቅ የመጣ ወይም ዋናው ዜማ ነው በዚህም ያክል ከዘፈንኩት ይበቃል ከሚልም ነገር ሊመጣ ይችላል፡፡ ወይም በተፈጥሮ ያለኝ በቂ ነው ብሎም ሊሆን ይችላል፡፡

-የዣን ስዩም ሙሉ በሙሉ አይደለም የድምጽ ኪህሉ አነስተኛ ሆኖ የምናየው የናቹራል የድምጽ አወጣጡ መልካም ከሚባል የድምጽ ዓይነጽ የምንመድበው ነው፡፡የቴክኒክ እጥረት ግን በጣም አለበት ፡፡

-የምንሹ ክፍሌም በሚውዚክ አረጅመንት ፣በሳውንድ ቅጂ በፕሮዳክሽን በጣም ጥሩ ሆኖ ወደ ቮካል ጋር ስትመጣ ጃን ስዩም ላይ ያነሳነው እንደውም ከዚህም ከፋ ባለ ሁኔታ የድምጻዊቷ የብቃት ችግር ይታይበታል

ታህሳስ 19 /2017 የተላለፉትን ዝግጅቶች ከታች ያድምጡ

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Jan, 08:55


ክርስቲያል ፓላስ ከቸልሲ የሚያደርጉትን ጨዋታ በኢቲቪ መዝናኛ
****************

ቅዳሜ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በእንግሊዝ ፕሪሚየሪሊግ ክርስቲያል ፓላስ ከ ቸልሲ የሚያደርጉትን ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመዝናኛ ቻናል በቀጥታ ያቀርብላችኋል።

ከጨዋታ በፊት ትንታኔዎችን ጨምሮ ጨዋታው በመዝናኛ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Jan, 08:05


አዳማ ላላችሁ

በአዲስ መልክ የሚጀምረውና እናንተ ወዳላችሁበት አዳማ ከተማ በመምጣት ችሎታችሁን እንድታሳዩ እድሉን ያመቻቸው የኢትዮጵያ አይዶል ምዝገባውን ለማጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ታድያ እርሶም የማሳየው የተለየ ችሎታ አለኝ፣ ተሰጥኦ ኖሮኝ መድረክ አላገኘሁም የምትሉ አዳማ ከበቀለ ሞላ ሆቴል አለፍ ብሎ ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ የአዳማ ኤፍኤም 100.7 ሬድዮ ድርጅት በሚገኝበት ግቢ ውስጥ በሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም ባሉበት ሆነው በቴሌግራም አድራሻችን መመዝገብ ይችላሉ።

ለመመዝገብ

https://t.me/EtvEthiopianidolbot

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Jan, 17:57


የዶክተሮች ወግ
የቤተሰብ አባላት የህክምና ባለሞያዎች የጋራ ቆይታ
የበአል ዕለት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና በኢቲቪ ዜና ቻናል ይጠብቁን
መልካም በአል

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

28 Dec, 20:28


የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች
*******************
• የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር - ኤላ ትሪክ
• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ
• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi
• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ
• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮንቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ
• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ /Miss Fendisha/
• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ - ጃዝሚን/jazmin_hope1/
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት - ኤላ Review
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ - Baes
• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ
• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ
• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu
• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ
• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ /Elatick/
• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ - I did it በዘነዘና
• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ - አቤል ብርሃኑ
• የዓመቱ ምርጥ ኢንፎርማቲቭ ኮንቴንት አዋርድ- ሙሴ ሰለሞን
• የዓመቱ ምርጥ ኢመርጂንግ ኮንቴንት አዋርድ-ስኬት ቤስት ሾርት ሙቪ ቪዲዮ አዋርድ
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በወንድ አሸናፊ- ከርተንኮል
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በሴት አሸናፊ - ማሂልት ኢብራለም

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

28 Dec, 18:05


የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ - በኢቢሲ በፎቶ

የሽልማት መርሐ-ግብሩን በኢቢሲ ዶትስትሪም የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጠቀም በቀጥታ ይከታተሉ፦

Instagram https://www.instagram.com/ebcnews1/

Tiktok https://www.tiktok.com/@ebc_tiktok?lang=en

Facebook https://web.facebook.com/EBCmezenagna

Telegram https://t.me/EBCNEWSNOW

YouTube https://www.youtube.com/@EBCworld

Website www.ebc.et

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 10:24


የኢትዮጵያ አይዶልን በነፃ!!!
***************

የኢትዮጵያ አይዶልን ካሉበት ቦታ ሆነው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የቴሌግራም ቦት በነፃ ይመዝገቡ።

የቴሌግራም ቦቱ ሊንክ ከዚህ በታች👇 የተጠቀመጠው ብቻ ነው።

https://t.me/EtvEthiopianidolbot

ከቴሌግራሙ በተጨማሪ ምዝገባ የሚካሄድባቸው 21 የክልል ከተሞች የሻሸመኔ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ደብረብርሀን፣ አርባምንጭ፣ ደሴ፣ ሰመራ፣ ነቀምት፣ ጎንደር፣ አዲግራት፣ አዳማ፣ መቐሌ፣ ባህርዳር፣ አሶሳ፣ ጅማ፣ ሐዋሳ፣ ሐረር እና ሆሳዕና ከተሞች የኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪዎች በኢቢሲ ቅርንጫፎች በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

#የኢትዮጵያአይዶል #ኢትዮጵያ #አይዶል #etv #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #musica #IDOL #ethiopianidol

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 07:24


የ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አዘጋጅ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆኗል
*******************

በቀጣይ ዓመት የሚከበረው የ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አዘጋጅ ክልል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሆኑ ታውቋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 07:23


የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ከሶማሌ ክልል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተላለፈ
*******************

የኢትዮጵያውያን የወል እውነት የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ በሱማሌ ክልል ላለፈው አንድ አመት ያደረገውን ቆይታ አጠናቅቆ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርክክብ ተደርጓል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫውን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የርክክብ ስነ-ስርአቱን አካሂደዋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 05:53


19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው
*************

19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እንዲሁም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 05:22


በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ወደሚገኘው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የክብር እንግዶች እየገቡ ነው
#ብሔርብሔረሰቦች #EBC #etv #ebcdotstream

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Dec, 04:56


19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአርባ ምንጭ እየተከበረ ነው
*********************
19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነው በድምቀት መከበር የጀመረው።
ፎቶ በEBC DOTSTREAM
#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Dec, 14:33


የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ካምፕ መግባት ጀመሩ
***

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሠራዊቱ አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባት ጀምረዋል።

ሕዝብን ለስቃይ ሲዳርግ የነበረውን የፖለቲካ ልዩነት በውይይት መፍታት ተገቢ መሆኑ ታምኖበት የሰላም ስምምነቱ ባሳለፍነው እሁድ መፈረሙ የሚታወስ ነው።

በስምምነቱ መሠረት በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ መሆኑ ተገልጿል።

የሠራዊቱ አባላት ወደ ካምፕ መግባታቸውም ስምምነቱ ወደ ተግባር መሸጋገሩን አመላካች ነው ብሏል በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Dec, 20:54


ባለዋሽንቱ እረኛ በግርማ ይፍራሽዋ | The Shepherd with the Flute
https://youtu.be/oEjzn3N12ZE?si=ISYidZA23BcjLi9T

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Dec, 20:49


ትሬሲ ቻኘማን በአይዶሏ ኮከብ ዳግማዊት Tracy Chapman "Give me one reason"
https://www.youtube.com/watch?v=w0jRY0vZ73g&ab_channel=EBC

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Dec, 16:03


የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ ሆኗል
**************

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ በመሆን ልዩ ዋንጫ፣ አንድ ሚሊዮን ብር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ነፃ የትምህርት እድል አሸናፊ ሆኗል።

2ኛ ሚኪያስ ጌቱ

3ኛ ማቲያስ አንበርብር

4ኛ ብዙአየሁ ሰለሞን

ውጤቱ የ2 ዙር የዳኞች ውጤት እና ተመልካቾች በ8600 በፅሁፍ መልእክት የሰጡት ድምፅ ተደምሮ ነው አሸናፊው የተለየው ።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Dec, 11:47


የኢትዮጵያ አይዶል ተጋባዥ እንግዶች እየገቡ ነው
**************

የኢትዮጵያ አይዶል ተጋባዥ እንግዶች የተወዳዳሪዎች ቤተሰቦች እና ደጋፊዎች ውድድሩ በሚካሄድበት የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አሸናፊ ከበደ የጥበባት ማዕከል በአደይ አበባ ምንጣፍ ወደ አዳራሽ እየገቡ ነው።

የዓመቱን ኮከብ ውድድር ለማሸነፍ አራት ተወዳዳሪዎች በፍፃሜው መድረክ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

አንደኛ የሚወጣው ተወዳዳሪ 1 ሚሊዮን ብር ይሸለማል።

አጓጊው ጥያቄ "ማን ያሸንፋል?" የሚለው ነው።

ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሁሉም የኢቢሲ ቻናሎች፣ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና በኢቢሲ ዶትስትሪም በቀጥታ ይተላለፋል።

#የኢትዮጵያአይዶል #ኢትዮጵያ #አይዶል #etv #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #musica

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

27 Nov, 08:06


"አዳር ሌላ ስራ ሰርቼ ሳልተኛ ነዉ ለውድድር የምመጣው" ማቲያስ አንበርብር

ለረጅም ጊዜ ከሙዚቃ ጎን ለጎን ሌላ ስራ እሰራላሁ፡፡

የኢትዮጵያ አይዶልን መወዳዳር ከጀመርኩ በኃላ ግን የበለጠ ጊዜዬን ለሙዚቃ ነው የምሰጠው፡፡

ሙዚቃን በመስራት ነው የተማርኩት ቢሆንም ትልቁ ትምህርቴ የተገኘዉ በኢትዮጵያ አይዶል የውድድር መድረክ ላይ ነው፡፡

"በዚህ ውድድር ላይ የከበደኝ ነገር ለሊቱን ሙሉ ሌላ ስራ ስሰራ አድሬ ያለ እንቅልፍ ለውድድር መቅረቤ ነው።

በኢትዮጵያ አይዶል የመጀመሪያ ምዕራፍ ሁለተኛ ነበር የወጣሁት። አሁን የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ተወዳዳሪ ነኝ። ከውድድሩ ጥሩ ውጤት እጠብቃለሁ።"

ማቲያስ አንበርብር እሁድ ህዳር 22 በዓመቱ ምርጥ የፍፃሜ ውድድር ላይ ይቀርባል።

ማቲያስ አንበርብር ስራዎች ከዚህ በታች ባሉት ሊንኮች ይመልከቱ።

https://www.youtube.com/watch?v=j-tnSLIEhnI...

https://www.youtube.com/watch?v=wHXhEiYMmKE...

https://www.youtube.com/watch?v=QdHsXwv4pLc...

1 ሚሊየን ብሩን ያሸንፍ ይሆን?
የዓመቱን ኮከብ - ኅዳር 22 ይጠብቁን!
#የኢትዮጵያአይዶል #ኢትዮጵያ #አይዶል #etv #EBC #ebcdotstream

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

26 Nov, 17:06


ሊገናኙ ነው

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ አይዶል ዝነኞች ከአዳዲሶቹ ምርጦች ጋር እሁድ በዓመቱ ኮከብ ልዩ ኘሮግራም ላይ ሊገናኙ ነው።

ዳግማዊት ፀሀዬ፣ ዳዊት አለማየሁ፣ ተመስገን ታፈሰ፣ አዝመራው ሙሉሠውና ሌሎች የአይዶል ፈርጦች አዳዲሶቹን ኮከቦች ያገኟቸዋል።

እሁድ ህዳር 22 በሚካሄደው የኢትዮጵያ አይዶል የአሸናፊዎች አሸናፊ ኘሮግራም ላይ አርቲስቶቹ ልዩ ቆይታ ይኖራቸዋል።

1 ሚሊየን ብር በሚያሸልመው የዓመቱ የፍፃሜ ውድድር በሙዚቃ ድግስ ደምቆ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁሉም ቻናሎች በመላው ዓለም በቀጥታ ይተላለፋል።

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ማን ያሸንፋል? #ኢትዮጵያአይዶል #Ethiopia #ETV #EBC #Ethiopia #EBCDOTSTREAM

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

26 Nov, 14:12


ለውጡና የለውጡ ፍሬዎች

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02eu6oQMbPmgCGm8qbKPcX7XuyzF3xgirQDv7CggmC5rP3YiZTYGhs7mfrbLme4gpzl

#የኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ #etv #EBC #ebcdotstream #PMO #AbiyAhmed #Ethiopia #Ethiopian #news

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Nov, 14:05


ተመዝገቡ፣ ተወዳደሩ፣ ሚልዮኖችን አሸንፉ!!
የነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር የምእራፍ 4 ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
ነጋድራስ በየምእራፉ 1.8 ሚሊዮን ብር ለአሸናፊዎች አሸናፊ ደግሞ 5 ሚሊዮን ብር ይሽልማል።
በተጨማሪም ምርጥ አምስት ውስጥ ለሚካተቱ ተወዳዳሪዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማስያዣ የብድር እድል ይመቻችላቸዋል።
በነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ በመሳተፍ ከሽልማት ባሻገር የስራ ሀሳብዎን ያስተዋውቁ፣ የቢዝነስ እድልዎንም ያስፉ።
👇 ለመመዝገብ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ አለያም ኪው አር ኮዱን ይጠቀሙ።
https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx
#etv #EBC #cbe #የኢትዮጵያንግድባንክ #ነጋድራስ #CBE #Ethiopian #Commercial_bank_of_Ethiopia #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ስራፈጠራ #ነጋድራስ_የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_የሥራ_ፈጠራ_ውድድር #negadras

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Nov, 13:03


በደጃች ውቤ ሰፈር የተከሰተውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል ርብርብ እየተደረገ ነው
*************

በአራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ውቤ ሰፈር በሚገኘው በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ስራ ድርጅት ላይ ያጋጠመዉን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

#ኢቲቪ #ኢቢሲ #እሳት_አደጋ #Ethiopia #etv #EBC

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

24 Nov, 11:55


ለጥንቃቄ ‼️
"ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ" ፦ የእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን
#ለጥንቃቄ #etv #EBC #Ethiopia
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid07dzegR6zjThbC5tJtFbCSAqfCcULuNcroKaoKpDmGB93LG3x8vxnrdWL5oxor4PXl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

23 Nov, 14:27


ከ11 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት
በእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ አርሰናል ከኖቲንግሀም ፎረስት የሚያደርጉትን ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመዝናኛ ቻናል በቀጥታ ያቀርብላችኋል።
ከጨዋታ በፊት ትንታኔዎችን ጨምሮ ጨዋታው በመዝናኛ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።
ከቴሌቪዥን በተጨማሪ በኢቢሲ ዌብሳይት እና የቴሌግራም ገፅ ጨዋታውን በቀጥታ መመልከት ይችላሉ።
https://t.me/etventertainment1
https://ebc.et/videolink.aspx?id=6

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

22 Nov, 13:30


የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ውድድር ህዳር 22 በደማቅ ሥነ-ስርዓት ይጠናቀቃል
**************

ለአንድ ዓመት፣ በአራት ምዕራፎች ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ውድድር ህዳር 22 በደማቅ ሥነ-ስርዓት ይጠናቀቃል።

በየምዕራፉ አሸናፊ የነበሩ ተወዳዳሪዎች የዓመቱ ኮከብ ዋንጫን ለማሸነፍ በአሸናፊዎች አሸናፊ መድረክ ይወዳደራሉ።

የዓመቱ ኮከብ በመሆን ውድድሩን የሚፈፅም አንድ ተወዳዳሪ ብቻ አንድ ሚሊዮን ብር ይሸለማል።

በዝግጅቱ ላይ ደማቅ ሙዚቃዊ ትርኢቶች ይቀርባሉ። ታላላቅ የጥበቡ ዓለም ሰዎችም ይታደሙበታል።

በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ህዳር 22 በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሁሉም ቻናሎች እና በኢቢሲ ማህበራዊ ድረ-ገፃች በቀጥታ ይተላለፋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

22 Nov, 05:43


የከተማ አስተዳደሩ መርካቶ ሸማ ተራ በእሳት አደጋ ሱቅ ለተቃጠለለባቸው ነጋዴዎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
******************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እስኪገነባ ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል።

በአካባቢው ያለውን ጥግጊትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ጨምረው ገልጸዋል።

ከከንቲባ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ድጋፉን የተቀበሉት የአካባቢው ነጋዴዎች ተወካዮች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው ድጋፉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid032Tmn78cvG6WvxCpX49HG8Tu8WSs7Jchu2emtFw1vHftYSZw7woFDJ6PTuRavezzDl

#etv #አዲስአበባ #ኢቢሲ #EBC #Ethiopia

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

21 Nov, 11:46


ህዳር 22
የዓመቱ ኮከብ
#Ethiopia #ኢትዮጵያ #አይዶል #ETV #EBC

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

20 Nov, 14:14


ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች
**********

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዋ በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዋ በእጇ ላይ የተገኘውን የውጭ አገራት ገንዘብ ከየት ያመጣችው እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለEBC DOTSTREAM ገልፀዋል።

የቤት ሰራተኛዋ በተለያየ ወቅት በተለያዩ የመኖሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ወንጀል ስትፈፅም የቆየች እንደሆነች እና በእጇ ላይ የተያዙት የውጭ አገራት ገንዘብ እና ሌሎች ንብረቶችን ከየት የተገኙ እንደሆነ የሚደረገው የማጣራት ስራ የሚቀጥል መሆኑን ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ጠቁመዋል።

ሙሉ ዜናውን ከተከታዩ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02FSLfcU7qQdnBSZJ9FYGRLVUt6sTRkoXMTmRmY42VYZrKa593tU2sRKeWs7TEWouwl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

19 Nov, 12:04


ፍቅር እስከ መቃብር በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳግም ሊመጣ ነው|
https://www.youtube.com/watch?v=Un3DU3Y2Hy0

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

18 Nov, 09:36


ዜና ኢትዮጵያ ከመላ ኢትዮጵያ ጀምሯል

https://www.youtube.com/watch?v=X1Ej63ECQEE

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

18 Nov, 09:02


ዜና ኢትዮጵያ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል!
#Ethiopia #EBC #ETV #news #Ethiopian #EthiopianNews

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

13 Nov, 12:02


የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር በቅርብ ቀን...
በቴሌግራም፦ https://t.me/etventertainment1
በዌብሳይታችን ፦ https://www.ebc.et/videolink.aspx?id=6
#አይዶል #ኢቲቪ #ኢቢሲ #የኢትዮጵያ #የኢትዮጵያአይዶል #Ethiopian #idol #ethiopianidol

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

12 Nov, 13:21


ለነጋድራስ ተመዝግበዋል?

የነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር የምእራፍ አራት ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

ነጋድራስ በየምእራፉ 1.8 ሚሊየን ብር ይሸልማል።

ለአሸናፊዎች አሸናፊ ደግሞ 5 ሚሊዬን ብር ተዘጋጅቷል።

በተጨማሪም ምርጥ አምስት ውስጥ ለሚካተቱ ተወዳዳሪዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማስያዣ የብድር እድል ይመቻችላቸዋል።

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx

ተመዝገቡ፣ ተወዳደሩ፣ አሸንፉ

#etv #EBC #cbe #የኢትዮጵያንግድባንክ #ነጋድራስ #CBE #Ethiopian #Commercial_bank_of_Ethiopia #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ስራፈጠራ #ነጋድራስ_የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_የሥራ_ፈጠራ_ውድድር #negadras

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

10 Nov, 08:38


በኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ውድድር ዛሬ ማን ይሰናበት ይሆን?
**********************

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ውድድር ዛሬም በድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል፤ ላለፉት 11 ሳምንታት 12 ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ ሲካሄድም ቆይቷል።

በየምእራፉ 8 ተወዳዳሪዎችን በማሰናበት ዛሬ ላይ 5 ተወዳዳሪዎች ማለትም ድምፃዊ ዮሐንስ አምደወርቅ፣ ድምፃዊ ብዙአየሁ ሰለሞን፣ ድምፃዊ ሚኪያስ ጌቱ፣ ድምፃዊት መብራት ንጉሴ እና ድምፃዊ ማቲያስ አምበርብር በአዶል መድረኩ ላይ ከተሰየሙት ዳኞች ፊት ይፋለማሉ።

በዛሬው ፍልሚያ አንድ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ይሰናበት እና ቀሪዎቹ 4 ተወዳዳሪዎች ለፍፃሜው የሚቀርቡ ይሆናል።

አንድ ሚሊዮን ብር እና የክብር ዋንጫ ተሽላሚ የሚያደርገውን በቅርብ ወደሚደረገው የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር የሚያልፉት 4 ተወዳዳሪወች በዛሬው እለት የሚለዩ ይሆናል።

በኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ውድድር ሲጠናቀቅ 1 ሰው ብቻ አንድ ሚሊዮን ብር እና የክብር ዋንጫ ተሽላሚ ተሸላሚ ይሆናል።

ውድድሩን በቀጥታ ለመከታተል ቀጣዮቹን ሊንኮች መጠቀም ይችላሉ፦

በኢቲቪ መዝናኛ ፦ https://web.facebook.com/EBCmezenagna/videos/1783352265769532/

በቴሌግራም፦ https://t.me/etventertainment1

በዌብሳይታችን ፦ https://www.ebc.et/videolink.aspx?id=6

#አይዶል #ኢቲቪ #ኢቢሲ #የኢትዮጵያ #የኢትዮጵያአይዶል #Ethiopian #idol #ethiopianidol

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

10 Nov, 04:37


ዛሬ የበሰቃን ሐይቅ ድብቅ ውበት ገልጠናል፤ የተገለጠው ምሥጢርም 'ቤኑና መንደር' ይሰኛል
**

ከመተሃራ ከተማ አቅራቢያ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቤኑና መንደር' ከእሳተ ገሞራ ቅሪት መልክዓ ምድር ገጽታው ወደ ሰላምን የሚያጎናፅፍ የመዝናኛ መዳረሻ እና አረንጓዴ የእርሻ ምድርነት በአስደናቂ አኳኋን ተለውጧል ሲል የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

#PMOEthiopia

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

09 Nov, 03:57


ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር።

ሃሳብ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ባደረገው ነጋድራስ የስራ ፈጠራ ውድድር ከምዕራፍ ሶስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የታይትል ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ከይዘት ስራዎች አንዱ የሆነው ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ከህዳር 1 ጀምሮ ይቀርባል፡፡

አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች ወደ ፊት እንዲመጡና በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ኢቢሲ ሁልጊዜም ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡

ከሀገር ልማት ጀርባ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዚህ ፕሮግራም የታይትል ስፖንሰርሽፕ ስምምነትን ከኢትዮጰያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ከማድረግ ባለፈ ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ቁርጠኝነቱን በተግባር አሳይቷል።

በስምምነቱ መሠረት የውድድሩ ሽልማት ወደ ላቀ ደረጃ የተሸጋገረ ሲሆን አሸናፊዎች ከሚያገኙት የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ብድር ያለማስያዣ የሚያገኙ ይሆናል፡፡

ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር ከእሁድ ህዳር 1 ቀን 2017 ጀምሮ ከቀኑ 8 ሰዓት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና ቻናል በየሳምንቱ ይቀርባል፡፡

#etv #EBC #cbe #የኢትዮጵያንግድባንክ #ነጋድራስ #CBE #Ethiopian #Commercial_bank_of_Ethiopia #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ስራፈጠራ #ነጋድራስ_የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_የሥራ_ፈጠራ_ውድድር #negadras

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

07 Nov, 06:31


ከነጋ ቡና ቀምሰዋል?

ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ ሀገር ናት።

ለቡና ተስማሚ የሆነ 5.47 ሚሊዮን ሄክታር መሬት፣ ምቹ ስነ-ምህዳር፣ በቂ የሰው ጉልበት ያላት፣ በልዩ ንጥረ-ነገር ይዘታቸውና ጣዕማቸው በዓለም እጅግ ተወዳጅ የሆኑ የቡና ዝርያዎች ባለቤት የሆነች ናት- ሀገራችን።

ባለፉት ስድስት ዓመት ቡናን ከ #አረንጋዴዓሻራ ጋር አስተሳስረን በመትከላችን ምርታችን በየአመቱ በአማካይ በ100 ሺህ ቶን ቡና እየጨመረ መጥቷል፡፡

በባለፈው የበጀት አመት በቡና የውጪ ንግድ 1.43 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አግኝታለች።

የኢትዮጵያን ብሩህ መንፈስ በእያንዳንዱ የቡና ስኒ ከቡናችን ጋር ይቀዳል። ፉት ይበሉት።

ምንጭ ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

06 Nov, 04:58


ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን እየመሩ ነው
******************

የአለም ፖለቲካ ዘዋሪዋ ሀገር አሜሪካ 47ተኛውን ፕሬዝዳንቷን በመምረጥ ላይ ትገኛለች።

ፉክክሩ የጋለው እና እጩዎቹ አንገት ለአንገት የተያያዙበት ምርጫ ውጤት በዚህ ሰዐት የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ይገኛሉ።

የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሀሪስም ሆኑ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ለሀገራቸው ይበጃል ብለው የያዟቸው ፖሊሲዎች አሜሪካውያንና የቀረውን አለም ቀልብ ስቦ የምርጫውን ውጤት አለም በጉጉት እንዲከታተል አድርጎታል።

እስከመጨረሻ ውጤቱን ለመገመት አስቸጋረ የሚሆነው 47ተኛው የአሜሪካ ምርጫ ፉክክር ማንን ፕሬዝዳንት ያደርግ ይሆን?
አሁንም የሁለቱን ፉክክር እና ውጤት ለማወቅ "ስዊንግ ስቴት" የሚባሉትን 7 ግዛቶች የምርጫ ውጤት መጠበቅ አስገዳጅ ነው።

ካማላ ሀሪስ እስካሁን በብዙ ሴቶች በመመረጥ ቅድሚያውን ቢይዙም በአጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ በሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እየተመሩ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ባለው መረጃ ትራምፕ ምርጫውን የማሸነፍ ዕድላቸው ወደ 89% ከፋ ማለቱ እየተዘገበ ነው::

በናርዶስ አዳነ
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0KCyGkjCneLH2FSW7h6aXeDNFwHm7QowbrpUpHpdEwvETxZVeREkDa2XDxp9Vnxfql

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

06 Nov, 04:16


የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ አዲስ አበባ ገቡ
**********************

የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው "የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ" ብለዋል።

#etv #ኢቲቪ #ኢቢሲ #ዐቢይአሕመድ #Guinea #TheRepublicofGuinea
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02xA7Jsts1NpT1sB3yWUU3WYHBV6JnzRFSXLF5kBcWC3N6eMuCgBzTkW5XYaF56zrrl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Nov, 06:49


ጥቅምት 24 መቼም የትም አይደገምም!!
ክብር ለአገር ሉዓላዊነት ለተሰዉ ጀግኖች!!
#ኢቢሲ #ኢቲቪ #መከላከያሠራዊት #etv #EBC #DefenseForce #Ethiopian #Ethiopia #ጥቅምት24

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

03 Nov, 04:00


«የማይደገም ስህተት!!»
************
ሀገር በጋራ እንደትቆም፤ የፈተናዋን ቀን እንድትሻገር፤ አልፎም ነገ ላይ ያልተደፈረ ክብር ይዛ እንድትቀጥል የመከላከያ ሠራዊቷን ያህል ዋጋ የሚከፍል የቁርጥ ቀን ልጅ የለም።

ሕዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና የሰላም አየር እንዲተነፍስ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ፤ የአገር ዘብ ሆኖ በዱር በገደሉ ኑሮውን እያደረገ፤ ታሪክን ያስጠበቀ፤ ልዑላዊነትን ያላስደፈረ ጀግና የሚሉ የክብር ስሞች የተቸሩት፤ ምግባሩም ይህንን የሚገልፀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነው።

ይህ ሠራዊት የህዝቡን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ለገበሬው ልጅ ነውና የደረሰ ሰብል ይሰበስባል፣ ያጭዳል፣ አይዞን ይላል፤ ይህ የዘውትር ተግባሩ ሆኖ የኖረ አሁንም ያለ ነው።

በዚህ ለወገን ክብር፤ ለሀገር ዳር ድንበር ራሱን በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ቀብሮ የኖረ የኢትዮጵያ አለኝታ በሆነው በሰሜን እዝ ሠራዊት ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የደረሰው እጅግ አሳዛኝ ክህደት፤ ጀግኖች በገዛ ወገናቸው ከኋላ የተጠቁበት፤ በደገፉት የተገፉበት ቀን ነው።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ሠራዊት ላይ የተፈፀመው ክህደት ሀገርን ጦርነት ውስጥ ከትቶ፣ ለመከራም ዳርጎ ቢያልፍም ዛሬም ኢትዮጵያውያን "ያ ቀን የትም፣ መቼም፣ በምንም እንዳይደገም" በእንባ ያስቡታል፣ ያስታውሱታል።

ያ ቀን … ሲያምናቸው ከዱት … የተዋደቀላቸውን ወጉት፤ ከፊት የቀደመላቸውን በጀርባ አጠቁት...

ያ ቀን የኢትዮጵያን ህዝብ እኩል ያሳዘነ፤ እንባ ያራጨ፤ የማይሆን መጥፎ ታሪክ የተፃፈበት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም።

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02MrQfpYng4AMBVX14NwbNcmCHqa6L5r8KLfpfgL8PZiWXo9FgznBBf3dmTdSMdhetl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

02 Nov, 19:11


የትላንት ጉጉታችን፣ የዛሬ ሥራችን የነገ ትዕምርታችን የ60 ዓመት አዲስ መልክ
********************

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለፉትን ስድሳ አመታት የኢትዮጵያውያንን ደስታ፣ ፍቅር፣ ችግር፣ ጥበብ፣ ሃሳብ ያለ ተቀናቃኝ የሰነደና ያስተላለፈ ታሪካዊ መስኮት።

ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ አገዛዝ ሂደት እስከ ደርግ አመጣጥ፣ ከኢህአዴግ መባቻ እስከ ማብቂያ እንዲሁም የለውጥ ሃይል እንቅስቃሴን ከአፈጣጠሩ እስከ ብልፅግና ፓርቲ ውልደት እና የለውጥ ሂደት ለህዝቡ ያደረሰ።

ለአፍሪካውያን ስለአንድነትና ስለህብረት የሰበከ….ኢትዮጵያ የሚል ብሄራዊ አርማና ስም ከፊቱ አስቀድሞ ከሁሉም ቤት የሚዘልቅ ሀገሩን ይዞ ተንቀሳቃሽ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን።

ከሮሙ የአበበ ቢቂላ ድል ከሀይሌ ገብረሥላሴ የአትላንታ ጀብዱ፣ ከደራርቱ የባርሴሎና ስኬት፣ ከቀነኒሳና ከጥሩነሽ የቤጅንግ ተጋድሎ እስከ ፓሪሱ የታምራት ቶላ የሀገር ፍቅር ማሳያ ድል ድረስ የጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ወኔና አልሸነፍ ባይነት ለህዝቡ በቀጥታ ያደረሰ የሀገርን ደስታን አብሮ የተቋደሰ።

የጥላሁን ገሰሰን ኢትዮጵያ፤ ሜሪ አርምዴን አራዳ በምስል የከሰተ በጥበብ የተዋጀ የሀገሪቱ የመረጃ እና የጥበብ ቋት።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ydqag32kPEEqRQYBkwzS5jdD68f936avNEJTKU6StwPBQZ7tdUkrPkGPSf4SPzWBl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

02 Nov, 16:31


"ሰላማዊ ነኝ" በሚል የህጻናት የስዕል አውደ ርዕይ እየተካሄደ ነው
***************

በዓለም የስነ ጥበብ ትምህርት ቤት የስእል ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ከጥቅምት 23 እስከ 25 የሚቆይ የስዕል አውደ ርዕይ ገርጂ በሚገኘው የዓለም ጋላሪ በማሳየት ላይ ናቸው።

"ሰላማዊ ነኝ" በሚል የተከፈተው ይህ አውደ ርዕይ ህፃናት ዓለም ላይ እየሆነ ያለውን ከማየት ይልቅ ውስጣቸው ያለውን ተስፋና ምኞት በራሳቸው መንገድ እንዲገልጹ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ሰዓሊ አለም ጌታቸው ገልጻለች።

አውደ ርዕዩን የጎበኘው ሰዓሊ ወንደሰን በበኩሉ፤ በጉበኝቱ ህጻናት ስለሰላም የሚያስቡበት ሁሉንተናዊ እይታ መመልከት መቻሉን ተናግሯል፡፡

ህጻናቱ ስለሀገራቸው ያላቸውን ራዕይና መረዳት፤ ጥያቄዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ስዕሎች መመልከቱንም ጠቁሟል።

ወላጆችና ሌሌች ታዳሚዎችም፤ ህጻናቱ ስለሰላም ያላቸው ተስፋና ግንዛቤ ለታላላቆቻቸው መልእክት መሆን የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

01 Nov, 17:48


በBRICS+ ማሕቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና
https://www.youtube.com/live/EpOX6O9_bq0?si=MijVCJStZbnWfrZ8

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 10:04


አፍርሶ መገንባት፣
በዕድልና በጊዜ መቀለድ
ካለፈ በኋላ መቆዘም
በብዙ የጎዱን ሾተላዮች ናቸው!!!
#etv #EBC #Ethiopia #abiye #AbiyAhmed #Abiy #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia #ፓርላማ

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 09:15


ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡
ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡
ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#etv #EBC #Ethiopia #abiye #AbiyAhmed #Abiy #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia #ፓርላማ

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 09:01


“ብልፅግና ደሀን ይወዳል፣ ለደሀ ይራራል፤ ድህነትን ግን በጣም ይጠላል።
ድህነት እና ደሃን ለይተን ማየት አለብን።
ደሀ የሆኑ ሰዎች ድህነትን አብዝተን ጠልተን ከተበቀልነው ባለጸጋ መሆን ይችላሉ!!”
#etv #EBC #Ethiopia #abiye #AbiyAhmed #Abiy #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia #ፓርላማ

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 08:06


ባለፉት ሦሥት ወራት ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተናል፡፡ በዚህ ሦሥት ወራት ያገኘነው ገቢ በ2010 ዓ.ም ዓመቱን ሙሉ ካገኘነው ይልቃል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#etv #EBC #Ethiopia #abiye #AbiyAhmed #Abiy

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 08:06


ከኢንዱስትሪው ዘርፍ የ12.8 በመቶ ዕድገት ይጠበቃል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*************************

በተያዘው በጀት ዓመት ከኢንዱስትሪው ዘርፍ የ12.8 በመቶ ዕድገት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት 3 ዓመታት በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የተሰሩ ሥራዎች ለዘርፉ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ በአምራች ዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ እና መጠጥ፣ በኮንስትራክሽን፣ በኬሚካል እና በሌሎች ዘርፎች 72 ትላልቅ ፕሮጀክቶች ገበያውን እንደሚቀላቀሉም አመላክተዋል፡፡

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 08:06


በበጀት ዓመቱ 8.4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ታቅዷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

*****************

በ2017 በጀት ዓመት የ8.4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩብ ዓመቱ የታየው የኢኮኖሚ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ ከፍ ያለ ዕድገት ሊኖር እንደሚችል አመላካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የ8.1 በመቶ ዕድገት መመዝገቡንም አስታውሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 08:06


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው
*****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ የሚሰጡትን የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 04:09


Live stream started

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

31 Oct, 04:09


Live stream finished (11 days)

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

27 Oct, 16:54


ቅኝት ስፖርት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1
አርሰናል ከ ሊቨርፑል

ቅኝት ስፖርት ሙሉ ጨዋታን ቀጣዩን ሊንክ በመጫን በዩቱዮብ ገፃችን ይከታተሉ::

@FMADDIS97.1-qw6tj

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Oct, 10:00


"በፈተናዎች ውስጥ እየተገነባ የመጣ ሠራዊት"

#etv #EBC #Ethiopia #dfenceforce

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Oct, 08:02


"በፈተናዎች ውስጥ እየተገነባ የመጣ ሠራዊት"

#etv #EBC #Ethiopia #dfenceforce

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Oct, 07:08


የመከላከያ ሠራዊት ቀንን ስናከብር በፈተናዎች ሁሉ በድል እየተሻገረ ሀገርንን ያፀና ጀግና ሠራዊትን እያመሰገንን ነው:- ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

117ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

"በፈተናዎች ውስጥ እየተገነባ የመጣ ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል ነው ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው ።

ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር በዝግጅቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግራቸው
የመከላከያ ሠራዊት ቀን ስናከብር ሀገርን በፈተናዎች ውስጥ ያፀና ለመከላከያ ሠራዊት ምስጋና የምናቀርብበትና ለቀጣይ ለሀገራችን አለኝታነት ያለንን ዝግጁነት የምንገልጽበት ነው ብለዋል።

ሀገርን መጠበቅ ቀጣይነት ያለው ዕረፍት የሌለው እና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ተግባር ነው ያሉት ሚኒስትር አይሻ መሀመድ ሠራዊታችን ራሱን አሳልፎ በመስጠት ይሄንን ኃላፊነት እየተወጣ ነውና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ለሀገር ዘብ ቆመው ለተሠማሩ ለጀግና ሠራዊትም ሀገርን መጠበቅ ክብር ነውና ሀገርም በፅናታቸው ትቀጥላለች ምስጋናም ታቀርባቿዋለች ብለዋል።

117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀንም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል ።

በዝግጅቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀስላሴ ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን እና ሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ ሚኒስቴር ማዕረግተኞች እየተሳተፉ ይገኛል ።
በትዕግስቱ ቡቼ

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

25 Oct, 04:59


በብሪክስ ጉባኤ የነበራቸውን ቆይታ ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ለይፋዊ ጉብኝት ማሌዢያ ኳላላምፑር ገብተዋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

23 Oct, 11:49


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር ተወያዩ
**************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል።

በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን መግለጻቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

23 Oct, 06:22


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ መብረር ሊጀምር ነው
***********

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 3 ቀናት የላይቤሪያ ዋና ከተማ ወደሆነችው ሞንሮቪያ ለመብረር መዘጋጀቱን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ከሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀናት ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የሚያደርገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

21 Oct, 15:47


370 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
***************

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 370 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 329 ወንዶች፣ 39 ሴቶች 2 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 16 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0rkEQ2iDn3ZpAQHx9b8BLsDuFjvbEeGBZiqrJf78AkNSvcnEagBYjQS3JwaCWsp33l

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

19 Oct, 08:45


Live stream started

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

19 Oct, 08:45


Live stream finished (24 days)

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

18 Oct, 19:26


የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል ምረቃ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በያዘው ተቋማዊ ሪፎርም ሰፋፊ የይዘት እና የአቀራረብ ማሻሻያ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል። ከእነዚህ የሪፎርም ስራዎች መካከል ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የ''ፍቅር እስከ መቃብር'' ፊልምን ለኢትዮጵያ ህዝብ በስጦታነት አበርክቷል፡፡

ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚል መርህ የጀመረው የይዘት ለውጥ ተጠናክሮ ቀጥሎም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ''የዛሬይቱ ኢትዮጵያ - ነገን ዛሬ'' እና ‘’ሀ ሶስታ’’ በሚል ርዕስ የተዘጋጁ በሀገራዊ ትርክት ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን ለተመልካቹ ማድረስ ጀምሯል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የይዘት ሪፎርሙን አጠናክሮ በመቀጠል በኢቲቪ ቋንቋዎች ቻናል ያለውን የተጣበበ የስርጭት ሰዓት በጥናት በመለየት ወደ ሕብረተሰቡ በስፋት ተደራሽ የሚያደርጉትን ቋንቋዎች ወደ ቻናል ለማሳደግ ሰፊ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም ኮርፖሬሽኑ የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናልን ቅድሚያ ሰጥቶ ስርጭት እንዲጀምር በማድረግ በሙከራ ስርጭት ላይ ቆይቷል፡፡

የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል ለቋንቋው ተናጋሪ ህዝብ ስለኢትዮጵያ የሚናገር ብዝሃነትን ያከበረች፣ ጠንካራ እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትገነባ የሚሰራ ቻናል ነው። ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያሉትን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የክልሉን እምቅ አቅም እና የቱሪስት መስህቦች ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለዓለም ለማድረስ የሚሰራ ህዝብ የሚናገርበት ቻናል ይሆናል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0pffMg2SBmWBPaXiHw3EVc2kxRWugesxL5YpeZuW6u6mQFvxjk2Tun3vrUbZ7f1Rtl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

13 Oct, 06:20


በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ዳግም ተሰማ
*************************

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

ሰሞኑን በተደጋጋሚ በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው እንዳልቆመ የተናገሩት ዶክተር ኤሊያስ ለከፋ ችግር የሚያጋልጥ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ መሆኑ የተናገሩት ዶክተር ኤሊያስ ይሄው እንቅስቃሴ ወደላይ አለመወጣቱን ነው የተናገሩት።

ላለፉት 19 ተከታታይ ቀናት ያህል ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን እና አሁንም ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል ዶክተር ኤሊያስ።

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid024cFVuw1pYFKiay9NWL7138SDrGuG45Znpuf8UZZAX9CJU5xKTkTGECAccAgtAefLl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

13 Oct, 06:10


በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ዳግም ተሰማ
********************************
በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።
ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሊ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

13 Oct, 05:22


የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ወደ ተፈጻሚነት ገባ
*****

የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በአፍሪካ ሕብረት ማለፍ ያለበትን ሂደት አልፎ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ የናይል የትበብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈጻሚነት ማብሰሪያን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን አስታውቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የዛሬው ቀኑ በናይል ተፋሰስ ታሪክ ልዩ መሆኑን አንስተው÷ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታትና ሕዝቦች ለዚህ ታሪካዊ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ለዚህ ስምምነት ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በተለያየ መንገድ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ኢትዮጵያውያንም ሚኒስትሩ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን መመስረት እንደሚስችል ጠቅሰው÷ ኮሚሽኑ ለሁሉም ተጠቃሚነት የናይል ወንዝን የማስተዳደርና የመጠበቅ ኃላፊነት ይወስዳል፤ የትብብሩም የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ የሕግ ማዕቀፍ፣ የናይልን ወንዝ ለሁላችንም ጥቅም ለማዋል የጋራ ቁርጠኝነታችን ምስክር እንዲሁም የውኃ ሀብቱን በእኩልነትና ፍትሐዊነት የመጠቀም መብት ማረጋገጫ የሚሆን ስምምነት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

https://www.facebook.com/share/p/mqDjJVQHTD3S2fvL/

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

09 Oct, 16:28


"የግራ ቀኝ" ተከታታይ የቲቪ ድራማ የምእራፍ መዝጊያ ስነ-ስርአት እየተከናወነ ይገኛል
***

"የግራ ቀኝ" ተከታታይ የቲቪ ድራማ የምእራፍ መዝጊያ ስነ-ስርአት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፕሮዲዩሰርነት ሲቀርብ የቆየው ድራማ በሁለት ምዕራፎች፤ በ24 ክፍሎች ሲቀርብ የነበረ እጅግ ተወዳጅ ድራማ ነው።

የምዕራፍ መዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ''ኢቲቪ ወደ ይዘት'' በሚለው ታላቅ ለውጥ ውስጥ 'ግራ ቀኝ' ድራማ የለውጡ አካል ሆኖ ለተደራሲያን በስኬት በመቅረቡ ደስታ እንደሚሰማው ተናግረዋል።

ጨምረውም በኢትዮጵያ ራዲዮ ወደ 90 አመታት የተጠጋ ጉዞ፣ በኢትዮዽያ ቴሌቪዥን የ60 አመታት ጉዞ፣ እንዲሁም በቀዳሚው ኤፍ ኤም አዲስ ዘጠና ሰባት ነጥብ አንድ ሂደት ኢቢሲ የጥበብ ቤት በመሆን የኢትዮጵያን ጥበብ ማሳደጉን አውስተዋል።

አሁንም በአዲስ የይዘት ለውጥ ሂደት አዳዲስ የጥበብ ስራዎችን በጣቢያው ለማስተናገድ ዝግጅት እና ፍላጎት እንዳለ በመናገር ለዚህም ግብዣ እና ጥሪ አቅርበዋል።

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ አጠቃላይ ውይይት በተዋናዮቹ እና ፀሀፊዎቹ አቅራቢነት እየተደረገ ይገኛል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የጥበብ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Oct, 15:11


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ይቀርባል
***************************
ጉዳዩ፦ ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይመለከታል፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተስተካከለ ሥራ ላይ እንዲውል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት በአለም ገበያ የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0tKk2RYpCkMARQ8hoJbchfpr81ywM54gi7zxow9Pf4pe73X6c1Dsb4EVBDmSakK6Hl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

08 Oct, 07:19


በሊባኖስ የነበሩ 51 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
**********
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 51ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ወደ ሀገር የተመለሱት ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ሚኒስቴሩ ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ሥራዎች ቀዳሚ ትኩረቱን በሊባኖስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ዛሬ የተመለሱት ዜጎችም አንዱ የተግባር የእንቅስቃሴው መገለጫ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02TSCh3Tq28AKyRTRCgnaD2yWBKDuN6N6dxid1W8t4dKfYg5qkeWpgeVMZk2aLaiNnl

FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)

07 Oct, 13:02


“አሰናካይ ሐሳቦችን በማረቅ ወደ ፊት መራመድ አስፈላጊ ነው፡፡ ማስተዋል፣ ማሰላሰል፣ አርቆ ማሰብ እና ትዕግስት የኢትዮጵያ የጽናት ዋልታዎች ናቸው”፡፡ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0gcZhKvUhNkyS5Bhp6rao9oxxQzgjMhfsRGLasa67WNEHAizVCEcuTT3Gmbj8CJugl

7,482

subscribers

895

photos

22

videos