Addis Ketema Education Office @akscedu Channel on Telegram

Addis Ketema Education Office

@akscedu


The offical Addis ketema education information is avilable.

Addis Ketema Education Office (English)

Welcome to the official Telegram channel of Addis Ketema Education Office, also known as @akscedu! For all the latest information and updates regarding education in the Addis Ketema region, this is the place to be. The Addis Ketema Education Office is dedicated to providing quality education to all residents, ensuring that students have access to the best learning opportunities. Whether you are a parent, teacher, or student, this channel is designed to keep you informed about important news, events, and programs related to education in Addis Ketema. Stay up-to-date with school schedules, exam results, and educational initiatives by joining our channel today. Be part of a community that values education and aims to empower the youth of Addis Ketema with the knowledge and skills they need to succeed. Join @akscedu now and be part of the education revolution in Addis Ketema!

Addis Ketema Education Office

02 Dec, 06:24


ብሔራዊ መታወቂያ

📌ከጥር 2017 አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ግዴታ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያስፈልጋል።

📌ከሰኔ ወር 2017 መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትልልቅ ከተሞች ባሉ ባንኮች አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ግዴታ ነው

📌በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያን ግዴታ ያደርጋሉ

📌በታሕሳስ 2019 ዓ.ም ነባር የባንክ ደንበኞችም ቢሆኑ ፋይዳ ካልያዙ አገልግሎት አያገኙም መባሉን ሰምተናል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

Addis Ketema Education Office

28 Nov, 15:38


የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተማሪ ወላጅ ማህበር የ1ኛ ሩብ አመት ጉባኤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት 18/03/2017 በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ ።

Addis Ketema Education Office

25 Nov, 13:40


የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በየሳምንቱ ሰኞ ሰኞ ጧት 2:00 ሰዓት ጀምሮ የሚያደርጋውን የእውቀት ሽግግር/Knowledge Transformation/ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ/ም ራስን የማብቃት ዕቅድ/Self Development Plan, SDP/ በሚለው ርዕስ ላይ በጥልቀት ተወያይቷል።የመክፈቻና የመዝግያ ንግግር ያደረጉ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም እንዳመላከቱት የዕለቱ የመድረክ አቅራቢ የሆኑ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመስገን ግዛው ያቀረቡት ጥሩና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሁል ጊዜም ስራዎችን በኃላፊነት ለመምራት መዘጋጀት እንዳለብን አስቀምጧል። የት/ጽ/ቤቱ የመ/ልማትና የሱፐርቪዥን ስራዎች ዘርፍ አስተባባር የሆኑት አቶ ብርሃኑ ቱጂ አሁን ባለንበት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ዘመን Kowledge Change እና Change Management የሚሉትን በአግባቡ ለመጠቅ ሁል ጊዜ ከ Self Ego በመውጣት ራስን ለለውጥና ለተሻለ አፈፃፀም ለማብቃት ለመማር ዝግጁ መሆንና አለም ያለበት የእውቀት ሽግግርን በአግባቡ መረዳት ወሳኝ መሆኑን አመላክቷል። የት/መረጃና የአጠቃላይ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቤኩማ ደበሎ በበኩላቸው የትምህርት ባለሙያዎች ዘርፉን ለመምራትና ውጤታማ ለመሆን ራስን የማብቃት ስራን በአግባቡ መወጣት አለባቸው ብሏል። በስተመጨረሻም የመዝግያ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ራስን ማብቃት ለተቋም መብቃት መሠረት መሆኑን አስምሮውበት የሳምንቱን የስራ አቅጣጫ በመስጠት የዕለት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

Addis Ketema Education Office

22 Nov, 12:13


እንዴት ዋላችሁ ?
የተማሪዎች የመንፈቀ ዓመቱ ግማሽ ፈተና ( Mid Exam) ህዳር 16 / 2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚሰጥ አውቃችሁ ተማሪዎቻችሁን በተጠቀሰው ቀን ጀምሮ መፍተን መቻል እንዳለባችሁ አሳውቃለሁኝ ።

Addis Ketema Education Office

14 Nov, 13:38


የእንግሊዝኛ እና የሂሳብ መምህራን መረጃ የላካችሁ ት/ቤቶችንን እያመሠገንን፤ አሁንም ያላደረሱ ት/ቤቶች፦ ድላችን፣ ዕድገት፣ ፈ/ብርሀን፣ ብርሀን በር፣ ፊሊጶስ፣ ጉለሌ ፋና፣ ሚኪሊላንድ፣ ዳ/ብርሀን ቁ.2 እናአስኮ 2ኛ፣ ሲሆኑ ለተጠያቂነቱ ሀላፊነቱን የምትወስዱ መሆኑን አስቀድመን እናሳውቃለን።

Addis Ketema Education Office

08 Nov, 13:15


በአሰላ እና በደብረ ብርሃን ኮሌጆች በቅዳሜ እና እሁድ መ/ግብር ለመሠልጠን የመጨረሻ የመመዝገቢያ ዕድል ተሠጥቷችሁ እስከ አርብ 29/2/17 መስፈርቱን በማሟላት በክ/ከተማችን የተመዘገባችሁ ሰልጣኞች፦ ቅዳሜ 30/02/2017 ብቻ የአማርኛ በደ/ብርሃን መ/ኮሌጅ (ፀሐይ ጮራ ት/ቤት)፤ የአፋን ኦሮሞ በአሰላ መ/ኮሌጅ (ሃና ማርያም ት/ቤት) ሔዳችሁ በመመዝገብ በዚያው ት/ት እንድትጀምሩ አሳስባለሁ፡፡

Addis Ketema Education Office

07 Nov, 18:29


ስልጠና፦ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስር ባለፈው  ቅዳሜ በ23/2/17ዓ.ም የሠለጠናችሁ (አማርኛ እና አፋን ኦሮሞን እንደ 2ኛ ቋንቋ ለምታስተምሩ መ/ራን በሙሉ)፦ 2ኛው ዙር ስልጠናችሁ ቅዳሜ በ30/2/17 በበኮተቤ ት/ት ዩኒቨርሲቲ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ  ስለሚቀጥል በሠአቱ እንድትገኙ እናሳስባለን።

Addis Ketema Education Office

06 Nov, 08:34


አስቸኳይ፦ ለክፍለ ከተማችን በመንግስት እና በግል ት/ቤቶች በሞግዚትነት እያገለገላችሁ በአሠላ እና በደ/ብርሃን ት/ኮሌጅ በKG መምህርነት በ2017ዓ.ም ለመማር ጠይቃችሁ ጊዜው በማለፉ ያመለጣችሁ፦
A. ለመንግስቶች፦
1ኛ. በ12ኛ ክፍል 120 እና በላይ፣
2ኛ. በ10ኛ ክፍል 1.5 እና በላይ
B. ለግሎች፦
1ኛ. በ12ኛ ክፍል 220 እና በላይ፣
2ኛ. በ10ኛ ክፍል 2.41 እና በላይ
ውጤት ያላችሁ ብቻ እስከ 29/02/17ዓ.ም 10:00 ድረስ ብቻ ኦርጅናልና ኮፒ የት/ት ማስረጃችሁን እና በሞግዚት ስራ ላይ በቋሚነት እየሠራችሁ (6ወር የሞላችሁ) መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ከት/ቤታችሁ በመያዝ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

Addis Ketema Education Office

05 Nov, 11:15


በሁለቱም ክፍለ ከተማ የምትገኙ ፖርትፎልዮ ያልተመዘናችሁ መምህራን በ 28/02/2017 የመጨረሻ የምዘና ጊዜ በመሆኑ በዕለቱ መቅረት የማይፈቀድ መሆኑን እናሳስባለን

Addis Ketema Education Office

04 Nov, 08:17


በአዲስ ክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር ላላችሁ የመንግስት 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ር/መ/ራን፦ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት ከትምህርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ለሙዚቃና ስዕል መምህራን ስልጠና ለመስጠት አቅዷል። በመሆኑም በአቢሲንያ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ረቡዕ እና ሐሙስ ከ27- 28/02/17 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ለ2 ተከታታይ ቀናት፣ ሠልጥኖ ሲመለስ የት/ቤቱን መምህራንን ማሠልጠን የሚችል ከሙዚቃና ስዕል መምህራን መካከል አንድ (1 ሠው ብቻ) መርጣችሁ እንድትልኩን እናሳስባለን።